topic
stringlengths
16
333
news
stringlengths
16
46.2k
የኬንያው የደኅንነት ሚኒስትር ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ጋር መከሩ
መጋቢት ይህንን ለማጋራት በ ዋትስአፕ በአገራቸውና በሶማሊያ ድንበር አካባቢ ያለውን ውጥረት በተመለከተ ከኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር አዲስ አበባ ላይ መወያየታቸውን የኬንያው የደኅንነት ሚኒስትር ተናገሩ። ከሶማሊያና ከኬንያ ጋር ድንበር የምትጋራው ኢትዮጵያ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሚደገፈውንና ከእስላማዊው ቡድን አል ሻባብ ጋር የሚፋለመውን የሶማሊያ ማዕከላዊ መንግሥት ለመደገፍ ተሰማርቶ ለሚገኘው የአፍሪካ ኅብርት ሠራዊት አዋጥታለች። የደኅንነት ሚኒስትሩ ፍሬድ ማትያንጊ በድንበር አካባቢ ያሉትን ችግሮች በመቅረፍ የቀጠናውን መረጋጋት ለማጠንከር በአገራቱ መካከል የትብብር መንገድ ለመፈለግ ያቀደ ውይይት መሆኑን በትዊተር ሰሌዳቸው ላይ አስፈረዋል። የአህያ ቁጥር መቀነስ ያሳሰባት ኬንያ የአህያ እርድን አገደች ሚኒስትሩ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ጋር ያደረጉት ውይይት የተካሄደው የሶማሊያ ኃይሎች ከፊል እራስ ገዝ ከሆነችው የሶማሊያዋ ጁባላንድ ግዛት ከመጡ ኃይሎች ጋር በኬንያ ግዛት ውስጥ ከማንዴራ አቅራቢያ ባለ ቦታ ላይ ከተጋጩ ከሳምንት በኋላ ነው። ባለፈው ሳምንት ማብቂያ ላይ የኬንያው የደኅንነት ሚኒስትር ፍሬድ ማትያጊ ወደ ሶማሊያ አቅንተው ከአገሪቱ ፕሬዝዳንት ሞሐመድ አብዱላሒ ፋርማጆ ሞሐመድ ጋር በመገናኘት የድንበር አካባቢ ጸጥታን ለማጠመናከር ዲፕሎማሲያዊ ጥረትን አድርገዋል። ቀደም ሲልም ሶማሊያ ኬንያን በውስጥ ጉዳዬ ጣልቃ እየገባች ነው በማለት የከሰሰች ሲሆን ጨምራም በድንበር አካባቢም ያለውን መስፋፋት እንድታቆም አስጠንቅቃ ነበር። በሁለቱ የምሥራቅ አፍሪካ አገራት መካከል ያለው ግንኙነት በሕንድ ውቅያኖስ አካባቢ ባላቸው የጋራ የውሃ ድንበር ይገባኛል ውዝግብ ምክንያት ከሻከረ ቆየት ብሏል። ይህም የባሕር ድንበር ይገባኛል ውዝግብ በዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት በመጪው ሰኔ ወር ላይ ይሰማል። ቢቢሲ ማስተባበያ
አፍሪቃውያን፤ አሜሪካ እና አውሮጳ ዚምባብዌ ላይ የጣሉትን ዕገዳ እንዲያነሱ እየወተወቱ ነው
ነሐሴ ዚምባብዌ ውስጥ አንድ አነስተኛ ዳቦ ዶላር ብር ገደማ ያወጣል የአፍሪቃ ሃገራት ዩናይትድ ስቴትስ እና አውሮጳ ሕብረት ዚምባብዌ ላይ የጣሉትን ዕግድ በአስቸኳይ እንዲያነሱ በመወትወት ላይ ናቸው። የሳድቅ የደቡባዊ አፍሪቃ ዕድገት ማሕረበሰብ የወቅቱ ሊቀ መንበር የሆኑት የታንዛኒያው ፕሬዝደንት ጆን ማጉፉሊ ዕገዳው ከዚምባብዌ አልፎ ቀጣናውን እየጎዳው ነው ብለዋል። ዕገዳው የተጣለው በጎርጎርሳውያኑ አቆጣጠር ላይ ሲሆን የወቅቱ የዚምባብዌ ፕሬዝደንት ሮበርት ሙጋቤ ነበሩ። የሙጋቤ ምትክ የሆኑት ፕሬዝደንት ኤመርሰን ምናጋግዋ የሃገሪቱን ዕድገት ያደቀቁ ፖሊሲዎች ሲሉ ዕገዳዎቹን ተችተዋል። ሮበርት ሙጋቤ ከ ሚሊየን ብር በላይ ተዘረፉ በዕገዳው ምክንያት የውጭ ሃገራት ድርጅቶች ወደ ዚምባብዌ ገብተው መሥራት አይችሉም። ዚምባብዌ በተቃራኒው በከፋ የኑሮ ወድነት እና በመሠረታዊ ፍላጎቶች እጥረት በመዳከር ላይ ትገኛለች። የአንድ ዳቦ ዋጋ ባለፈው ሚያዚያ ከነበረው በአምስት እጥፍ የጨመረ ሲሆን የተባበሩት መንግሥታት ሚሊዮን ገደማ ዚምባብዌያውያን የምግብ እርዳታ እንደሚሹ ይናገራል። መጋቢት ላይ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በሃገሪቱ ተጨባጭ የፖለቲካ ለውጥ እስካልመጣ ድረስ ዕገዳውን አናነሳም በማለት ዕገዳውን በአንድ ዓመት ማራዘማቸው አይዘነጋም። ገደማ ከፍተኛ ባለሥልጣናትና እና ድርጅቶች ወደ አሜሪካ መግባትም ሆነ መገበያያት እንደማይችሉ ሮይተርስ የተሰኘው የዜና ወኪል አሳውቋል። የቀድሞዎቹ መሪዎች ኃይለማርያም ደሳለኝና ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለማርያም ተገናኙ የገዢው ዛኑ ፒኤፍ ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ ሮበርት ሙጋቤ እና ባለቤታቸው ግሬስ ሙጋቤ ወደ አውሮጳም ሆነ አሜሪካ መጓዝ አይችሉም። አልፎም በመንግሥት እጅ ያሉ ድርጅቶች ምጣኔ ሃብታዊ ዕገዳ ተጥሎባቸዋል። በሙጋቤ እግር የተተኩት ምናንጋግዋ ሃገር ቤት ከፍተኛ ተቃውሞ እየገጠማቸው ይገኛል። ባለፈው ሳምንት አገዛዙን ተቃውመው የወጡ ሰልፈኞችን ፖሊስ በኃይል በትኗል። የምናንጋግዋ ተቃዋሚዎች ኑሮ ከሙጋቤ ዘመን በላይ ከፍቷል ሲሉ ይተቿቸዋል። ሳድቅን እየመሩ የሚገኙት ማጉፉሊ መዲናቸው ዳሬሳላም ላይ በተሰናዳ ስብሰባ ላይ ነው ዚምባብዌ አሁን አዲስ ምዕራፍ ላይ ስላለች ዕገዳው ሊነሳ ይገባል የሚል ሃሳብ የሰነዘሩት።
ሲዘዋወር የተያዘ የዝሆን ጥርስ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደረሰ
ኦክተውበር ማጋሪያ ምረጥ በአፍሪካ ይፈፀም የነበረው የዝሆኖች አደን በተከታታይ ለአምስት ዓመታት መቀነስ ቢያሳይም ባለፈው ዓመት በዓለም ዙሪያ ሲዘዋወር የተያዘው የዝሆን ጥርስ መጠን ከፍተኛ ደረጃ ላይ እንደደረሰ አንድ ሪፖርት አመለከተ። ለጥፋት የተጋለጡ ዝርያዎችን ደህንነትና ንግድ የሚከታተለው ዓለም አቀፍ ተቋም ባወጣው ሪፖርት እንዳመለከተው ሺህ ኪሎ የሚመዝን የዝሆን ጥርስ በህገወጥ መንገድ ሲዘዋወር ተይዟል። በበርካታ ቦታዎች የዝሆን አደን እየቀነሰ ቢሆንም ባለፉት አስር ዓመታት ሺህ የአፍሪካ ዝሆኖች ለጥርሳቸው ሲባል ተገድለዋል። ጥናቱ የተያዘውን የዝሆን ጥርስ በተመለከተ የቀረበውን ግኝት በመልካምነቱ ቢጠቅሰውም ማስጠንቀቂያም መያዙን አመልክቷል። በዓለም አቀፍ ደረጃ እየተደረገ ያለው ጥረት አውንታዊ ውጤት እያሳየ ቢሆንም የሚፈለገው ደረጃ ላይ ግን አልደረስንም ሲሉ የድርጅቱ ዋና ፀሃፊ ጆን ስካንለን ተናግረዋል። ሪፖርቱ እንዳመለከተው በቁጥጥር ስር የዋለው ከፍተኛ መጠን ያለው የዝሆን ጥርስ ጠንካራ የህግ ማስከበር ሥራ በመሰራቱና የተሻለ ግንዛቤ መፍጠር በመቻሉ ነው ይላል። ዋና ፀሃፊው እንዳሉት ባለፉት አስር ዓመታት በዝሆኖች አደን ክፉኛ ከተጠቃው የምሥፍቅ አፍሪካ አካባቢ መልካም ዜና አለ። ከ በኋላ በዝሆኖች ህገ ወጥ አደን ላይ ከፍ ያለ መቀነስ የታ ሲሆን በ በተደረገው ጥናት የዝሆኖች አጠቃላይ የአደን ሁኔታ ከ በፊት ወደ ነበረው ዝቅተኛ መጠን የመመለስ አዝማሚያን አሳይቷል ይላሉ። በቦትስዋና፣ በደቡብ አፍሪካ እና በናሚቢያ ያሉ ዝሆኖች መልካም ሁኔታ ላይ ቢገኙም በመካከለኛው አፍሪካ ግን ባለፉት አስር ዓመታት ህገ ወጥ አደን እየጨመረ በመቀጠሉ የዝሆኖች ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ ቀንሷል። ተያያዥ ርዕሶች
የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ሞክግዌትሲ ማሲሲ ባለፈው ዓመት ሰኔ ወር ላይ ነበር በቀድሞው ፕሬዝዳንት የተጣለውን እገዳ ለመመርመር ኮሚቴ ያዋቀሩት።
በዚህ ዓመት የካቲት ወር ላይም ኮሚቴው እገዳው እንዲነሳ የሚል ምክረ ሀሳብ ማቅረቡ ተሰምቶ ነበር። የዝሆኖቹ ቁጥር መጨመር፣ በዝሆኖቹና በሰው ልጆች መካከል የሚፈጠር ግጭት መበራከት፣ ዝሆኖቹ በሰውና በእንስሳት ላይ የሚያደርሱት ጥቃት መጨመር ወደ እዚህ ውሳኔ እንደገፋቸው በመግለጫቸው ላይ የገለፁት የአካባቢ፣ የተፈጥሮ ኃብት እንክብካቤ እንዲሁም የቱሪዝም ሚኒስትሩ ናቸው። አክለውም አደን ሲፈቀድ ሕግን በተከተለ እና ስርዓት ባለው መልኩ እንዲሆን እናደርጋለን ብለዋል። የክልከላው መነሳት እርምጃው ፖለቲካዊ ነው ብለው በማያምኑ የአካባቢ ጥበቃ ተሟጋቾች ዘንድ ብስጭትን ይፈጥራል። ሀገሪቱም በዓለም አቀፍ ደረጃ ያላትን የአካባቢ ጥበቃ ስም የሚያጠለሽ ሲሆን ለሀገሪቱ ከዳይመንድ ማዕድን ማውጣት ቀጥሎ ሁለተኛ የገቢ ምንጭ የሆነው የቱሪዝም ሀብቷንም ይጎዳል ተብሏል። ተያያዥ ርዕሶች
ለአባልነት ዲግሪ ሲጠይቅ የነበረው ፓርቲ ለምርጫው ምን እያደረገ ነው
መጋቢት ይህንን ለማጋራት በ ዋትስአፕ የኢትዮጵያ ተራማጅ ፓርቲ ዛሬ ላይ ባለው ቅርፅ ከመጣ የተቆጠሩት ገና ጥቂት ወራት ብቻ ቢሆኑም የፓርቲው አመራር ውስጥ በ ቱ ምርጫ ጎልተው የታዩ ፖለቲከኞች እንዲሁም ቀደም ሲል በኢትዮጵያ ብሔራዊ ንቅናቄ ኢብን ውስጥ ተሳትፎ የነበራቸው ወጣቶችም አሉበት። ከቀናት በፊት ፓርቲው በተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች ፊርማ ያሰባሰብኩበት ሰነድ በፀጥታ ኃይሎች ተነጠቀብኝ በማለቱና በሌሎች ፓርቲውን በሚመለከቱ ጉዳዮች ዙሪያ የፓርቲውን ምክትል ሰብሳቢ አቶ አንዱአለም በእውቀቱ ገዳን አነጋገረናል። ፊርማ ያሰባሰባችሁበት ሰነድ እንዴት ነው ሊወሰድባችሁ የቻለው አቶ አንዱአለም፡ አምቦ ላይ የሚሆን ፊርማ ያሰባሰብንበት ሰነድ የተወሰደው በፌደራል ፖሊስ አባል ነው። አዳማ ላይ ደግሞ ፊርማ እያሰባሰቡ የነበሩ ሴት አባሎቻችን ሰነዱን የተነጠቁት የመንግሥት ደጋፊ ነን በሚሉ ሰዎች ነው። በደቡብ ክልል ቡታጅራ የማዘጋጃ ቤት ኃላፊ ነኝ የሚል ሰው ሰው የፈረመበትን ሰነድ ነጥቆ ወሰደ። ጉዳዩን እንደሰማ የፓርቲያችን አስተባባሪ አቶ መሐመድ አሊ መሐመድ ለምርጫ ቦርድ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ክትትልና ድጋፍ ክፍል አመልክቷል። አቤቱታችንን በፅሁፍም አስገብተናል። በሌሎች አካባቢዎች ተመሳሳይ ችግር አላጋጠማችሁም አቶ አንዱአለም፡ ብዙ ፊርማ ያሰባሰብነው ወሎ ውስጥ ነው ምንም ያጋጠመን ችግር የለም። አሁን አስተባባሪዎቻችን በድብቅ ነው ፊርማ እያሰባሰቡ ያሉት። የኢትዮጵያ ተራማጅ ፓርቲ የሚባል አለ ወይ የሚሉ አሉ። ትታወቃላችሁ ማን ነው ደጋፊያችሁ አቶ አንዱአለም፡ የድጋፍ መሰረታችን የአንድነት አቀንቃኙ ሕዝብ ነው። በሌላ ፓርቲ ውስጥ እያለንም የምንታወቀው ኢትዮጵያዊ ብሔረተኝነትና ኢትዮጵያዊ አንድነት ላይ የተመሰረተ ፖለቲካ በማቀንቀን ነው። አሁን እኛ ውስጥ ያሉ ሰዎች ከዚህ ቀደም በ ቱ ምርጫ ተሳትፎ የነበራቸው፤ አሸንፈው ፓርላማ የገቡም አሉ። ፊርማ ያሰባሰብንበት ሰነድ ተነጠቀ የሚለው አቤቱታችሁ ትኩረት ማግኛ ስትራቴጂ ነው ብለው የሚጠረጥሩ ይኖራሉ አቶ አንዱአለም፡ ይህ ፓርቲያችን ትኩረት ለማግኘት ካዘጋጃቸው መንገዶች መካከል አደለም። በዚህ ሰዓት ፌደራል ፖሊስን በሐሰት መወንጀል ትልቅ ድፈረት ይጠይቃል፤ እኛም ላይ ኃላፊነትን ያስከትላል። ከዚህ በፊት የፈረምነው የተቃዋሚ ፓርቲዎች የመግባቢያ ሰነድ አለ፤ በምርጫ አዋጁም ይሄ ያስጠይቃል። እንደዚህ ዓይነት ያለፈበት አካሄድ የሚከተል ስብስብም አደለንም። የተማሩና ልምድ ያላቸው ሰዎች የተሰበሰቡበት ነው። እንዲህ ዓይነቱን ነገር አናስበውም፤ አንሞክረውምም። ለምን ቀድሞ ከነበራችሁበት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ንቅናቄ ኢብን መውጣት አስፈለጋችሁ አቶ አንዱአለም፡ ኢብንን የመሰረትነው በወቅቱ አደጋ ነው ያልነውን ነገር ከመከላከል አንፃር ነው። በጣም የተጠናከረ የኦሮሞም የአማራም ብሔረተኝነት ነበር። ይህን ለመከላከል ደግሞ ኢትዮጵያዊ አንድነትን በለዘብተኝነት ሳይሆን በተመጣጣኝ ኃይል የሚያቀነቅን ቡድን መፍጠር ያስፈልጋል ብለን ነበር የተነሳነው። የዛሬ ሁለት ዓመት እና ሁለት ዓመት ተኩል ገደማ በሚያስፈራ ሁኔታ ኢትዮጵያዊነት የወደቀበት ጊዜ ነበር። አሁን ግን ኢትዮጵያዊነት አፈር ልሶ እየተነሳ ነው። ስለዚህ ይህንን ለማስቀጠል ጥያቄ የሚያነሱ አካላትን ጥያቄ በዘላቂነት የሚመልስ፤ ቅራኔያቸውንም በዘላቂነት የሚፈታ አካሄድ ማምጣት ነው ያለብን ብለን ስላሰብን ነው። አማራነት፣ ኦሮሞነት የለም ብለን በኃይል የሄድንበት መንገድ ምናልባት ትክክለኛ ነው ብለን ብናምንም ጊዜው ግን አሁን አይደለም። ስለዚህ እንደ ሽግግር ተራማጅ የሆነ ሃሳብ ለማራመድ ወስነናል፤ ወደ ተነሳንበት እንመለሳለን አሁን ግን ጊዜው አይደለም። ኢትዮጵያዊ ብሔረተኝነታችንን ግን አንክድም። ሲደረግ የነበረው ከዚህ በፊት አንድ ነን ልዩነትም የለንም፤ ኢትዮጵያ አንድ ነች የሚል አካሄድ ነበረ። እሱ አያዋጣም የሚደረስበት ወደፊት ነው። የሙስሊሙን፣ የኦሮሞውን፣ የኦሮሚያ ቤተክህነት እናቋቁም የሚሉም ብዙ ጥያቄ የሚያቀነቅኑ ስብስቦችን ማዳመጥ ያስፈልጋል። እንደ ከዚህ ቀደሙ ፀብ የማብረድ ዓይነት ሳይሆን እነዚህ ስብስቦችን ለየት ባለ አረዳድ ከሰማናቸው በኋላ ነው አገር መመስረት የሚቻለው። ለየት ያለ ተራማጅ አሰማም እንዴት ያለ ነው አቶ አንዱአለም፡ ተራማጅ አሰማም ማለት ዘመኑን የዋጀ አሰማም ማለት ነው። አሁን ለጥያቄዎች በአንድ ዓይነት መንገድ ነው ምላሽ እየተሰጠ ያለው። መልስ የጠፋው ጥያቄዎቹን የምናይበት አግባብ ችግር ያለው ስለሆነ ይሆናል። ተራማጅነት ማለት እነዚህን ጥያቄዎች መቀበል ማለት አይደም። ጥያቄያቸውንም ለማድመጥ ፍቃደኛ መሆን እና ተቀራርቦ መስራት ነው። የተለያዩ ጥያቄዎችን የሚያነሱ ስብስቦችን ከጅምሩ አቀራርቦ ይዞ የሚሄድና መዳረሻውን ኢትዮጵያዊነት ያደረገ አካሄድ ነው። አካሄዱ ግን የሚያዋጣ ነው ብላችሁ ታስባላችሁ አቶ አንዱአለም፡ አይመስልም ግን የያዝነው ትግል ነው። ትግል ደግሞ የሚሆን የማይመስለውን ነገር ሁሉ ታግሎ ማስቻል ነው። ቀላሉን ብቻ ሳይሆን የማይቻለውንም ታግሎ ማስቻል ይቻላል። የእኛ ሃሳብ አብዛኛው ዝም ያለው ሕዝብ ጋር ነው ያለው ብለን እናስባለን። ፅንፈኛ ሃሳብ የሚያራምዱትን ትቶ ለእኩልነት የሚሆን በቂ ሃሳብ ማራመድ የሚችል ኦሮሞ፣ አማራም አለ። እንደ አንተ ያሉ በማህራዊ ሚዲያ የሚታወቁ ወጣቶች በፓርቲው እንዳሉ ገልፀህልኛል። አንተን ራሱ ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ባለህ ተሳትፎ ብትቀጥል ይሻላል የሚል ብዙ አስተያየት አለ። በዚሁ ምክንያት ፓርቲያችሁን በቁም ነገር መውሰድ የሚቸግራቸው ሰዎች አሉ አቶ አንዱአለም፡ እውነት ነው የእኔ የማኅበራዊ ሚዲያ ተሳትፎ የተወሰነ ተፅእኖ ማድረጉ አይቀርም። ሰዎች ከእኔ የሚጠብቁት ነገር አለ፤ እኔም ራሴ ከራሴ የምጠብቀው ነገር አለ። ለውስጤ ቅርብ የሆነው ሥነ ፅሁፍ ነው ፖለቲካው ከሞላ ጎደል ተገድጄ የገባሁበት ነው። እንደ አብንና ጃዋር ያሉ አካላት ያላቸውን ነገር ተጠቅመው አገርን እንደፈለጉ ለማድረግ በሚሰሩበት ሰዓት እኔ ቁጭ ብዬ በአሽሙርና በሥነ ፅሁፍ መንግሥትን መጎንተል ተገቢ ነው ብዬ አላመንኩም። ተራማጅ ፓርቲ ዛሬ ባለው ቅርፅ ወደ መሬት ከወረደ ገና አምስት ወሩ ነው። በምርጫው ምን ያህል ይራመዳል አቶ አንዱአለም፡ ስም መጥራት አንፈልግም እንጂ ከተመሰረቱ ብዙ የቆዩ ግን በሕዝቡ ዘንድ ተቀባይነት የሌላቸው ፓርቲዎች አሉ። ስለዚህ ዋናው ነገር የጊዜ ጉዳይ አይደለም፤ እኛ የምናሳትፋቸው እጩዎች ልምድ ያላቸው ፖለቲከኞች ናቸው። የምትወዳደሩት የት የት ነው አቶ አንዱአለም፡ በእርግጠኝነት አማራ፣ ሶማሌ፣ ኦሮሚያ፣ ደቡብ እና አዲስ አበባ ላይ እንወዳደራለን። የኢትዮጵያ ተራማጅ ፓርቲ የወጣቶች ፓርቲ ነው አቶ አንዱአለም፡ ወጣት ይበዛዋል ግን ልምድ ያላቸው ትልልቅ ሰዎችም አሉ። ስንጀምር ገና አደረጃጀት ስንሰራ ለየት እንበል በሚል ዲግሪ እና ከዚያ በላይ ያላቸውን ነው አባልት ያደረግነው። መመስረቻ ምርሃ ግብር ስናካሂድ ሰዎች ተገኝተው የነበረ ሲሆን የሚሆነው ወጣት ነበር። ከዚህ ውስጥ ው ማስትርስ ዲግሪና ከዚያ በላይ ያላቸው ነበሩ። ኮሌጅ ብታቋቁሙ ይሻላል ተብሎ ተቀልዶ ሁሉ ነበር። በዚያ መንገድ መቀጠል ስለማይቻል ግን አሁን ሁሉንም ሰው እያሳተፍን ነው። ከምርጫ በኋላ በዚህ መስፈርታችሁ ልትቀጥሉ ትችላላችሁ አቶ አንዱአለም፡ አዎ እኛ ልንፈጥር ያሰብነው የምርጫ ፓርቲ አይደለም። ቀስ ብለን የጥናት ቡድን አደራጅተን፤ ተጠንቶ መንግሥትን በፖሊሲ የሚሟገት ትልቅ ፓርቲ መፍጠር ነው የፈለግነው። በዚህ ምርጫ ለምን አስር ወንበር አናገኝም ችግር የለውም። ቢቢሲ ማስተባበያ
የቀድሞው የዚምባብዌ ፕሬዚዳንት ሮበርት ሙጋቤ አረፉ
መስከረም ሮበርት ሙጋቤ የቀድሞው የዚምባብዌ ፕሬዘዳንት ሮበርት ሙጋቤ በ ዓመታቸው ከዚህ ዓመት በሞት ተለዩ። ዚምባብዌ ነጻነቷን ከተቀዳጀች በኋላ የመጀመሪያው መሪ የሆኑት ሙጋቤ፤ ባደረባቸው ህመም ምክንያት ሕይወታቸው ማለፉን ቤተሰቦቻቸው ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። ሙጋቤ ካለፈው ሚያዝያ ወር ጀምሮ ሲንጋፖር በሚገኝ ሆስፒታል ውስጥ ህክምና እየተከታተሉ ነበር። እንደ ጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር ላይ የዚምባብዌ መከላከያ ኃይል፤ ሮበርት ሙጋቤ ለሦስት አሥርት ዓመታት ይዘውት ከነበረው መንበረ ሥልጣን ማስነሳቱ ይታወሳል። በ በዚምባብዌ የተካሄደውን የመጀመሪያ ምርጫ አሸንፈው ጠቅላይ ሚንስትር ሆነው የነበሩት ሙጋቤ፤ ላይ ፕሬዘዳንት ሆነዋል። የአገሪቱ የትምህርት ሚንስትር ጸኃፊ ፋዲዛይ ማሀሬ ነፍስዎትን በገነት ያኑራት ብለው በትዊተር ገጻቸው አስፍረዋል። ሙጋቤ የተወለዱት እንደ ጎርጎሮሳውያኑ በ ነበር። ከእንጨት ሠሪ ቤተሰብ የተገኙት ሙጋቤ፤ በካቶሊክ የሚሽነሪ ትምህርት ቤት ነበር ትምህርታቸውን የተከታተሉት። ቢቢሲ ማስተባበያ
ሩሲያ ውስጥ ያለ ግድብ ተደርምሶ ማዕድን አውጪዎች ሞቱ
ኦክተውበር አጭር የምስል መግለጫ አደጋው የደረሰበት አካባቢ በጎርፍ ተጥለቅልቆ ሩሲያ ውስጥ በምትገኘው ሳይቤሪያ በሚገኝ የወርቅ ማዕድን ማውጫ አካባቢ ያለ ግድብ ተደርምሶ ቢያንስ ሰዎች ሲሞቱ ሌሎች ሰዎች ደግሞ የደረሱበት አልታወቀም ተባለ። ክራስኖያርክ በተባለው ክልል ውስጥ በሴይባ ወንዝ ላይ የተገነባው ግድብ ዛሬ ቅዳሜ በአካባቢው የጣለን ከባድ ዝናብ ተከትሎ በመደርመሱ የማዕድን ማውጫው ሠራተኞች የሚኖሩባቸውን ቤቶች በማጥለቅለቁ ነው አደጋው የደረሰው። የሩሲያ ጤና ሚኒስቴር እንዳለው ከሞቱትና እየተፈለጉ ካሉት ሰዎች በተጨማሪ የማዕድን ማውጫው ሠራተኞች ለህክምና ወደ ሆስፒታል ተወስደዋል። ከመካከላቸውም ሦስቱ የከፋ ጉዳት እንደደረሰባቸው ተገልጿል። ግድቡ የግንባታ ደንቦችን አላከበረም በመባሉ የወንጀል ምርመራ እየተደረገ ነው። የአገሪቱ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን የአደጋውን ምክንያት ለማወቅ ለሚደረገው ምርመራ ባለስልጣኖቻቸው አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርጉ ትዕዛዝ ማስተላለፋቸውን የፕሬዝዳንቱ ቃል አቀባይ ተናግረዋል። ኢንትርፋክስ የተባለው የዜና ወኪል እንደዘገበው የማዕድን ማውጫው ሠራተኞች የሚኖሩባቸው በርካታ ትናንሽ ቤቶች በከባዱ የጎርፍ ውሃ ተጠርገው ተወስደዋል። የማዕድን ማውጫው የሚገኘው ከሩሲያ ዋና ከተማ ሞስኮ ከ ሺህ ኪሎ ሜትሮች በስተ ምሥራቅ ርቆ በሚገኝ ስፍራ መሆኑም ተነግሯል። አደጋው ከደረሰ በኋላ በርካታ ቁጥር ያላቸው የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች ጉዳት የደረሰባቸውን ሰዎች ለመርዳት የተሰማሩ ሲሆን በተጨማሪም ደብዛቸው የጠፋውን ሰዎችንም በመፈለግ ላይ ናቸው። የሴይባ ወንዝና በአካባቢው ያለው የጎርፍ ውሃ መጠን እየጨመረ በመምጣቱ ምክንያት ከማዕድን ማውጫ አቅራቢያ በሚገኝ መንደር ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች ከአካባቢው እንዲወጡ እየተደረገ መሆኑን የሩሲያ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። ተያያዥ ርዕሶች
መንግሥት በፖለቲካ ፓርቲዎችና መገናኛ ብዙሃን ላይ እርምጃ እወስዳለሁ አለ
ማርች ማጋሪያ ምረጥ መንግሥት የሕዝብን አንድነትና አብሮነት እንዲሸረሸር በሚያደርጉ የፖለቲካ ፓርቲዎችና የመገናኛ ብዙሃን ላይ እርምጃ እንደሚወስድ ማስታወቁን ፋና ዘገበ። የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪያት ኃላፊ የሆኑት አቶ ንጉሡ ጥላሁን በሕዝባዊ መድረኮችና በመገናኛ ብዙሃን በኩል የሚተላለፉ የጥላቻ ንግግሮች በአገር አንድነትና አብሮነት ላይ አደጋ ይደቅናሉ ማለታቸውን ፋና ገልጿል። ኃላፊው ጨምረውም በመሰል ድርጊት በሚሳተፉ የፖለቲካ ፓርቲዎችና የመገናኛ ብዙሃን ላይ ከኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣንና ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጋር በመሆን መንግሥት ተገቢና ተመጣጣኝ ዕርምጃ ለመውሰድ እንደሚገደድ መናገራቸውን ገልጿል። የምታገለው ለማንም ብሔር የበላይነት አይደለም አቶ በቀለ ገርባ በትናንትናው ዕለት ዓለም አቀፉን የሴቶች ቀን በተመለከተ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ኦፌኮ ያካሄደው ዝግጅት ላይ የተደረገውን ንግግር ኦሮሞ ሚዲያ ኔትወርክ ኦኤምኤን ማስተላለፉን በተመለከተም ኃላፊነቱ የሁለቱም ወገኖች መሆኑን ተናግረዋል። ሕገ መንግስታዊ ድንጋጌን የጣሰና ኢትዮጵያዊ ዕውነታን ያላገናዘበ የጥላቻ ንግግር ለዘመናት በአብሮነት ወደኖሩ ሕዝቦች መተላለፉን ተከትሎ ፓርቲውም ሆነ የመገናኛ ተቋሙ ተገቢውን ኃላፊነት መውሰድ አለባቸው ሲሉ አሳስበዋል። ትናንት አዳማ ላይ የነበረው ዝግጅት በኦኤምኤን በቀጥታ የተላለፈ ሲሆን አንዲት ተሳታፊ ያቀረበችው ሃሳብ በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ በስፋት መነጋገሪያ ሆኖ ቆይቷል፤ ቪዲዮውም ከአማርኛ ትርጉሙ ጋር በስፋት ሲዘዋወር ነበር። ጉዳዩ መነጋገሪያ ከመሆን አልፎ ውግዘትና ቁጣን በማኅበራዊ መገናኛ መድረኮች ላይ አስተናግዷል። ይህንንም ተከትሎ የኦሮሞ ሚዲያ ኔትወርክ ዋና ዳይሬክተር አቶ ግርማ ጉተማ በፌስቡክ ገጻቸው ላይ ክስተቱን በተመለከተ የይቅርታ መልዕክት አስፍረዋል። አቶ ግርማ በጽሁፋቸው ኦኤምኤን ዝግጅቱን በቀጥታ እያስተላለፈ እንደነበርና ንግግሩን ማቋረጥ እንደነበረባቸው አምነው ነገር ግን እንዳልቻሉ አመልክተዋል። ነገር ግን ንግግሩ ካበቃ በኋላ ወዲያው ከማኅበራዊ ሚዲያና ከሳተላይት ላይ እንዲወርድ መደረጉን ገልጸዋል።
የቀድሞው የደኅንነት መስሪያ ቤት ምክትል ይናገራሉ
ማርች ማጋሪያ ምረጥ አቶ ወልደሥላሴ ወልደሚካኤል በ ዓ ም ወደ ህወሓት የትጥቅ ትግል የተቀላቀሉ ሲሆን ከደርግ ውድቀት በኋላ ደግሞ በብሔራዊ መረጃና ደኅንነት ተቋም ውስጥ በተለያዩ ኃላፊነቶች ላይ አገልግለዋል። በሙስና ተጠርጠረው ከተቋሙ በ ዓ ም እስከወጡበት ጊዜ ድረስ የአገር ውስጥ መረጃና ደኅንነት ኃላፊ ሆነው ሠርተዋል። እነሆ ከቢቢሲ ጋር የነበራቸው ቆይታ እርስዎ በደኅንነት ተቋሙ ውስጥ በነበሩበት ወቅት መስሪያ ቤቱ በትግራይ ተወላጆችና በህወሓት አባላት የተያዘ ነው ይባል ነበር። ምን ይላሉ አቶ ወልደሥላሴ፡ የተቋሙ ግዙፍ ክፍል በሆነው የአገር ውስጥ መረጃና ደኅንነት ኃላፊ በመሆን ነው ረጅም ጊዜያት ያሳለፍኩት። ስለዚህም በብሔራዊ መረጃና ደኅንነት ውስጥ የነበረውን አጠቃላይ የሠራተኞችን ብዛት ያየን እንደሆነ አብዛኛውን ቁጥር የሚይዙት የአማራ ብሔር ተወላጆች ናቸው። ቀጥሎ ደግሞ የኦሮሞና የትግራይ ተወላጆች ቁጥር ተቀራራቢ ነው። ይህን መረጃ ከተቋሙ የሰራተኞች ፋይል በቀላሉ ማረጋገጥ የሚቻል ነው። በመሰረቱ ይህ አጀንዳ በተደጋጋሚ ይነሳ ስለነበር ጥናት አካሂደንበታል። መንግሥት በታጣቂዎች ላይ ዘመቻ በሚያካሂድበት ምዕራብ ኢትዮጵያ ህይወት ምን ይመስላል ታድያ ሐቁ ይህ ከነበረ ለምንድነው ተቋሙ በትግራይ ተወላጆች እንደተሞላ ጥያቄ ሲነሳበትና በጥርጣሬ ሲታይ የነበረው አቶ ወልደሥላሴ ወልደሚካኤል፡ በታሪክ አጋጣሚ ከትጥቅ ትግሉ ጀምሮ በዘርፉ የተሻለ ተሞክሮና ትምህርት የነበራቸው ከህወሓት ይበዙ ነበር። ከዚህ የተነሳ እስከ ዓ ም ድረስ በኃላፊነት ደረጃ ከነበሩት ሰዎች አብዛኞቹ የትግራይ ተወላጆች ነበሩ። ነገር ግን ከዚያ በኋላ በኃላፊነት ያሉትም ሰዎች መመጣጠን አለበት ተብሎ የማመጣጠን ሥራ ተከናውኗል። ከላይ ለማስመቀመጥ የሞከርኩት ግን ከተቋሙ አጠቃላይ ስታፍ የሰው ኃይል አንጻር ያለውን ብዛት ነው። በመሐል ሜዳ ሚስቱን ለመግደል የሞከረው ግለሰብ የሦስት ሰዎችን ህይወት አጠፋ ሌላኛው በጥራጣሬ ዓይን ይታይ ነበር የተባለውን ግን እኔ አልቀበለውም። ምክንያቱም በምንሰራቸው ሥራዎች በሙሉ የሕዝቡ ተሳትፎ የላቀ ስለነበረ ነው። አብዛኞቹ አገሪቱን የማተራመስ ህቡዕ እንቅስቃሴዎችን በተመለከተ ሕዝቡ ቀድሞ መረጃ በመስጠት ይተባበረን እንደነበር አስረግጬ ልነናገር እችላለሁ። ኢትዮጵያ ተጋርጠውባት የነበሩት የደኅንነት አደጋዎችና እነዚህን በማክሸፍ ረገድ የሕዝቡና መንግሥትን ሚና በመጽሐፌ በስፋት ገልጬዋለሁ። የደኅንነት መስርያ ቤቱ በደርግ ግዜ በጣም ተፈሪ ነበር። በኋላ ግን የሚያስመካ እምርታ አስመዝግቧል ባልልም እንኳ በደርግ ጊዜ ከነበረው እጅግ የተሻለና ሕዝብ ወዶ የሚተባበረው ተቋም ነበር ማለት ግን እችላለሁ። የደኅንነት ተቋሙ ሰፊ የሰብአዊ መብት ጥሰት ሲፈጽም እንደነበር በስፋት ሲነገር ቆይቷል። ከዚህ አንጻርስ ምን ይላሉ አቶ ወልደሥላሴ ወልደሚካኤል፡ በቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ጊዜ የኢህአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በተለያዩ ዘርፎች ጉልህ ጉድለቶች እንደነበሩና ለዚህ ደግሞ ዋናው ተጠያቂ ራሱ የኢህአዴግ ሥራ አስፈጻሚ እንደሆነ ገምግሟል። ስለዚህ ከዚህ በመነሳት የሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት እንደየተልዕኳቸው በሰብአዊ መብት ረገጣ የየራሳቸውን ድርሻ ይወስዳሉ ማለት ነው። እውነት ለመናገር የአገሪቷን ደኅንነት ለማረጋገጥ ተብሎ በሰብአዊ መብት አያያዝ በኩል ጉድለቶች ሊኖሩ ይችላሉ። እኔ እስከማውቀው ድረስ ግን የደኅንነት ተቋሙ የዜጎችን ህይወት እና ንብረት ለመጠበቅ በታታሪነት ይስራ የነበረ ተቋም ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ በመገናኛ ብዙሃን በወንድ ብልት ላይ ውሃ ማንጠልጠልና ጥፍር እስከመንቀል የደረሱ በደሎች ተፈጽሞብናል የሚሉ ሰዎች ቀርበው ታይተዋል። የደኅንነት ተቋሙ በዚህ ውስጥ እጁ የለበትም አቶ ወልደሥላሴ ወልደሚካኤል፡ የአገሪቱ የደኅንነት መስሪያ ቤት ሥራው መረጃ ማሰባሰብ ነው። መረጃ አሰባስቦ ለጠቅላይ ሚኒስትሩና ለሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት ያቀርባል። ከዚያ በኋላ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያገኘውን መረጃ ተንተርሶ ከሚመለከታቸው የመንግሥት ተቋማት ጋር ሆኖ እርምጃ በመወስድና ባለመውሰድ ላይ ይወስናል። ኢትዮጵያ ውስጥ መካኖች ወልደው እየሳሙ ነው እኔ በተቋሙ በኃላፊነት ደረጃ እስከነበርኩበት እስከ ዓ ም ድረስ መረጃ በምርመራ የማግኘት ኃላፊነት የተሰጠው የፌደራል ፖሊስና የክልል ፖሊስ ኮሚሽኖች ነው። ስለዚህ የመረጃና ደኅንነት ተቋሙ ሥራና ኃላፊነት የነበረው የሕዝቡን አቅም ተጠቅሞ መረጃ በማሰባሰብ ለሚመለከተው የመንግሥት አካል መስጠት ነው። ሥራው ራሱ በሕግ የተወሰነ ነው። የምርመራ ሥራ የእኛ ሥራ ስላልነበረ ከዚህ ጋር ተያይዘው የሚነሱ ጉዳዮች ለእኔ ግልጽ አይደሉም። ስለዚህ ተፈጸሙ የተባሉት የሰብአዊ መብት ጥሰቶች በየትኛው የመንግሥት አካል ነው የተፈጸሙት አቶ ወልደሥላሴ ወልደሚካኤል፡ መረጃው የለኝም። በሙስና ተጠርጥረው ታስረው እንደነበር ይታወሳል። የቀረበብዎን ክስ ተቀብለውታል አቶ ወልደሥላሴ ወልደሚካኤል፡ በእኔ የሙስና ክስ ጉዳይ እኔ ባለጉዳዩ ከምናገረው በላይ ከእራሱ ከፍርድ ቤቱ ብትጠይቅ ነው የሚሻለው። በእርስዎ በኩልስ ግን ተቀብለውት ነበር አቶ ወልደሥላሴ ወልደሚካኤል፡ ክሶቹ መሰረተ ቢስ ስለነበሩ አልተቀበልኳቸውም፤ ፍርድ ቤቱም ሁሉንም ውድቅ አድርጓቸዋል። በሁለት ክሶች ግን አልከላከልም ብዬ አልተከላከልኩም። አንደኛው ክስ ሽጉጥና ጠብመንጃ ተገኝቶብሃል የሚለው ነው፤ በነበረኝ የሥራ ኃላፊነት የተነሳ ለምን እንደያዝኩት የሚታወቅ ስለሆነ ለመከላከል ሞራሌ አልፈቀደልኝም። ሁለተኛው ደግሞ በሥራ ምክንያት እንደሆነ እየታወቀ ለአንዲት ሴት የትራስፖርት አገልግሎት ትሰጥ ነበር ተብሎ የቀረብኝን ክስም አልከላከልም ብያለሁ። ታዲያ የተቀጣሁትም በእነዚህ ሁለት ክሶች ነው። በተረፈ ሌሎቹን ማለትም መጽሐፍ አሳትሞ ሲሸጥ ስልጣኑን ይጠቀም ነበር የሚለውንና በአዲስ አበባ ምንጩ ባልታወቀ ገንዘብ ቤት ገንብቷል ተብለው ለቀረቡብኝ ክሶች አስፈላጊውን መረጃዎችን አቅርቤ ፍርድ ቤት ነጻ ብሎኛል። ተከሰው ሲታሰሩ እኮ ከደኅንነት መስርያ ቤቱ ለቀው ነበርና በሚታወቅ የሥራ ባህሪ ምክንያት ነው መከላከል ያልፈለግሁት ያሉት አይጋጭም አቶ ወልደሥላሴ ወልደሚካኤል፡ የጠብመንጃውና የሽጉጡ ጉዳይን ለማለት አዎ አቶ ወልደሥላሴ ወልደሚካኤል፡ ለምን ሽጉጥና ጠብመንጃ እንደያዝኩ፣ ለምን መኪና እንዳሰማራሁ ለማብራራት የሥራው ባህሪና ዲሲፕሊን አይፈቅድልኝም። ሲታሰሩ ግን የትግራይ ልማት ማኅበር የቦርድ ሊቀ መንበር ነበሩ አይደል አቶ ወልደሥላሴ ወልደሚካኤል፡ የትግራይ ልማት ማኅበርን ሥራ እሰራ የነበረው በተደራቢነት እንጂ በቋሚነት አልነበረም። ከመታሰሬ ከሁለት ወር ገደማ በፊት ከሥራ ኃላፊነቴ እንደተነሳሁና ሌላ ሥራ ምድባ እየተጠባበኩ ሳለሁ ነበር የታሰርኩት። የቀድሞው የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት ዋና ኃላፊ የነበሩትን አቶ ጌታቸው አሰፋን እንዴት ይገልጿቸዋል በመካከላችሁስ ምን አይነት ግንኙነት ነበረ አቶ ወልደሥላሴ ወልደሚካኤል፡ የነበረው ኃላፊነትና የሥራ ባህሪ ምን እንደነበር ይታወቃል። እንደዚህ አይነት የሥራ ባህሪ ያለውን ተቋም ይመራ የነበረን ሰው ሥራው በሚድያ ወጥቶ መገምገም ፍትሐዊ ነው ብዬ አላምንም። በተጨማሪ ደግሞ እኔ በምሰጠው አስተያየት ላይ ምላሽ በማይሰጥበት ሁኔታ፤ ለዚያውም በዚህ ጊዜ መናገሩ ደግሞ አስፈላጊ አይደለም ባይ ነኝ። በአሁኑ ወቅት የት ነው ያሉት ምንስ እየሰሩ ነው አቶ ወልደሥላሴ ወልደሚካኤል፡ የማስተማር ፍላጎት ስለነበረኝ ከዚህ በፊት ከሥራዬ ጎን ለጎን በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲና በሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርስቲ አስተምር ነበር። የአክሱም ዩኒቨርስቲ መምህራንን ለመቅጠር ባወጣው ማስታወቂያ መሰረት ተወዳድሬ በፖለቲካል ሳይንስ ትምህርት ክፍል እያስተማርኩኝ ነው። ከእስር ቤት እንደወጡ በቀጥታ ወደ ትግራይ ነበር የሄዱት፤ በዚህም የማዕከላዊው መንግሥት ሰላይ ሆነው እንደሄዱ ይወራ ነበር፤ በዚህ ላይ ምላሽዎ ምንድን ነው አቶ ወልደሥላሴ ወልደሚካኤል፡ ይህ እንኳን ድካም ነው። እንደተባለውም ወሬ ነው ሊሆን የሚችለው፤ ሆን ተብሎ የተወራም ሊሆን ይችላል። ከድንቁርና የሚመነጭ ወሬ ስለሆነ በዚህ ላይ ጊዜያችንን ባናጠፋ ጥሩ ነው። እንደቀድሞ የአገሪቱ የመረጃና ደኅንነት ሹም አሁን ያለውን ተቋም እንዴት ትገመግመዋለህ አቶ ወልደሥላሴ ወልደሚካኤል፡ እውነት ለመናገር መረጃው የለኝም። ምን ዓይነት ፈተናዎች እየገጠሟቸው ነው እነዚያን ፈተናዎች ቀድመው እየደረሱባቸው ነው ወይ እንዴት አድርገውስ በአነስተኛ ዋጋ እየመከቷቸው ነው የሚሉ መረጃዎች ስለሌሉኝ በርዕሰ ጉዳዩ ላይ ለማውራት ይከብደኛል። ወቅታዊው የአገሪቱ ፖለቲካዊ ሁኔታ የማይገመትና እጅግ የተወሳሰበ እንደሆነ ይነገራል፤ በዚህ ላይ አስተያየትዎ ምንድን ነው አቶ ወልደሥላሴ ወልደሚካኤል፡ በእኔ እምነት የኢትዮጵያ ፖለቲካ ተገማች ፕሪዲክተብል ነው ባይ ነኝ። ተሳስቼ ልሆን ይችላል፤ ግን በነበረኝ የሥራ አጋጣሚ አገሪቷን አውቃታለሁ የሚል እምነት አለኝ። የኢትዮጵያ ፖለቲካ ከ ዓ ም በኋላ ከስር መሰረቱ ተቀይሯል። የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ራሳቸውን በራሳቸው ማስተዳደር ጀምረዋል። የራሳቸውን ሀብት በራሳቸው ማስተዳደር ጀምረዋል። በራሳቸው ፖለቲካዊና ማኅበረ ኢኮኖሚ ጉዳይ መወሰን የጀመሩበት ሁኔታ ነው ያለው። አንዳንድ የፖለቲካ ሊሂቃን ካልሆኑ በስተቀር አብዛኛው ሕዝብ በራሱ ጉዳይ ላይ ብቻ የተጠመደ ነው። የተማሪዎቹ መታገት ከተሰማ ቀናት አለፉ በአሁኑ ወቅት አንዱን ብሔር በሌላኛው ብሔር ላይ ልታነሳሳው አትችልም። ሰለዚህ በዚህ ጉዳይ መሰረታዊ ለውጥ አለ ብዬ ነው እማምነው። ለምሳሌ የኦሮሞ ሕዝብን ጥያቄ የወሰድን እንደሆነ ታሪካዊ በደል ደርሶብናል፣ በብሔርተኛ ልጆቻችን ነው መተዳደር የምንፈልገው፣ ከተፈጥሮ ሀብታችን ተጠቃሚዎች አይደለንም፣ ቋንቋችን በሚፈለገው ደረጃ አላደገም የሚሉ ፍትሀዊ ጥያቄዎች ነው የሚያነሳው እንጂ የትግራይ እና አማራ ጉዳይ ጉዳዩ አይደለም። የአማራ ህዝብ ጥያቄም የልማት፣ የፍትህና የዴሞክራሲ ጥያቄዎች ናቸው። እንደ አጋጣሚ ከትግራይ ሕዝብ ቀጥሎ አውቀዋለሁኝ የምለው ሕዝብ የአማራን ሕዝብ ነው። የትግራይ ጥያቄም ተመሳሳይ ነው። ከዚህ በኋላ ሕገ መንግሥታዊ ፌደራላዊ ሥርዓቱ ልታጎለብተው ካልሆነ በስተቀር ልትቀይረው አትችልም። ስለዚህ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፕሪዲክተብል ነው ባይ ነኝ። በቅርቡ ከህወሓት እውቅና አግኝተዋል፤ ይህ ማለት አሁንም የፓርቲው አባል ነዎት ማለትት ነው አቶ ወልደሥላሴ ወልደሚካኤል፡ እውቅናው ለእኔ ብቻ ሳይሆን ለብዙ የቀድሞ ተጋዮች የተሰጠ ነበር። እኔ በህይወት እስካለሁኝ ህወሓት ነኝ። ህወሓት ዳይናሚክ እንዲሆን ነው እምፈልገው። ደግሞ ተራማጅ ድርጅት እንደሆነ ነው የማምነው። ተራማጅ እንዲሆን ያደረገው ግን የሕዝቡ ንቃተ ህሊና ነው። አንዳንድ ሰዎች ህወሓትና የትግራይ ሕዝብ አንድ አይደሉም ሲሉ እሰማለሁኝ እንደ እኔ ግን አንድ ናቸው ባይ ነኝ። በትግራይ ብዙ ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች ባሉበት ሁኔታ ሕዝቡና ህወሓት አንድ ናቸው ማለት ተገቢ ነው ይላሉ አቶ ወልደሥላሴ ወልደሚካኤል፡ በፖለቲካዊ መነጽር ብቻ ካየነው ህወሓት ህጋዊ የፖለቲካ ድርጅት ነው። ቢሆንም የትግራይ ሕዝብ የህወሓት ፖለቲካዊና ማኅበረ ኢኮኖሚያዊ ስትራቴጂዎችን የእራሱ አድርጓቸዋል። ይህ በጥናትም ሊረጋገጥ የሚቻል ነገር ነው። የትግራይ ሕዝብን ፖለቲካዊ እምነቱን ብትጠይቀው የህወሓትን ንድፈ ሀሳቦች በይበልጥ ነው የሚያብራራልህ። ታዲያ ይህንን ሀሳብ የሚቃወሙ ሰዎች የሉም ማለት ግን አይደለም። የትግራይ ሕዝብና ህወሓት አንድ ናቸው የሚለው ሀሳብ ከህወሓት የተሻለ አማራጭ ለትግራይ ህዝብ ይዘናል የሚሉ ድርጅቶችን ማፈን አይሆንም ሀሳቡስ ለሕዝቡ ጠቃሚ ነው አቶ ወልደሥላሴ ወልደሚካኤል፡ በትግራይ ሁሉም ዓይነት ሀሳብና ማኅበራት በነጻ መንቀሳቀስ እንዳለባቸው አምናለሁ። የተለይ የፖለቲካ አማራጭ ያላቸው ሰዎች በነጻነት መደረጃት አለባቸው። አንዳች ተጽዕኖ እና ገደብ ሊደረግባቸው አይገባም። እነዚህ መሰረታዊ የዴሞክራሲ ጭላንጭሎች ስለሆኑ ሊሰመረበት ይገባል። የእኔ ሀሳብ ግን ህወሓት የምትመራባቸው ሀሳቦች በአብዛኛው ሕዝብ ተቀባይነት አላቸው ብቻ ሳይሆን በሕዝቡ ዘንድ የሰረጹ ናቸው ብዬ ነው እማምነው። ለዚህም ነው ከድሮ ጀምሮ ህወሓት እንቅፋት ሲገጥማት ሕዝቡ ተረባርቦ የሚያድናት። ይህ ማለት ግን ሌሎች የፖለቲካ ድርጅቶችና ሀሳቦች መምጣት የለባቸውም ማለት አይደለም። እንደውም ህወሓት ተራማጅ ልትሆን የምትችለው ሌሎች አማራጭ ሀሳቦች ሲመጡ ነው ብዬ ነው የማምነው። በቀጣይነት በመምህርነቱ ይቀጥላሉ ወይስ ወደ ፖለቲካው ይመለሳሉ አቶ ወልደሥላሴ ወልደሚካኤል፡ አላውቅም፤ ግን ማስተማር በጣም ይመቸኛል። ከታች ያለውን ፖለቲካ ለመረዳት መንግሥታዊ ኃላፊነት ይዞ ሳይሆን በአካዳሚክ ተቋማት ውስጥ ጥናት እያካሄዱ ሲሆን ይበልጥ ጠቃሚ ነው። ለአሁኑ ትውልድ በአካዲሚክ ተቋማት ሆኜ የራሴን ተሞክሮ እያስተላለፍኩኝ አገሩ ራሱን እንዲያስተዳድር በማድረግ ረገድ የምሰራ ይመስለኛል። ተያያዥ ርዕሶች
መንግሥት ታግተው የደረሱበት ስላልተወቁት ተማሪዎች ጉዳይ መረጃ እንዲሰጥ ተጠየቀ
ማርች ማጋሪያ ምረጥ አጭር የምስል መግለጫ ተማሪዎቹ የታገቱት ከደምቢ ዶሎ ጋምቤላ በሚወስደው መንገድ ላይ ነው የኢትዮጵያ መንግሥት ከወራት በፊት ባልታወቁ ሰዎች ምዕራብ ኦሮሚያ ውስጥ ታግተው የደረሱበት ስላልታወቁት የደምቢ ዶሎ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን ለማስለቀቅ የወሰደውን እርምጃ እንዲያስታውቅ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ጠየቀ። የመብት ተቆርቋሪው ድርጅት ይህንን ጥያቄ ያቀረበው በመላዋ አገሪቱ ያሉ ዩኒቨርስቲዎች የኮሮናቫይረስ መስፋፋትን ለመግታት መዘጋታቸውን ተከትሎ ነው። ባለፈው ኅዳር ወር ላይ የታገቱት የተማሪዎች ወላጆች ሰቆቃን የበለጠ የከፋ ያደረገው በምዕራብ ኦሮሚያ የስልክና የኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጡ ስለልጆቻቸው መረጃ ለማግኘት የሚያደርጉትን ጥረት እንዳደናቀፈው አምነስቲ በመግለጫው ላይ አመልክቷል። ሞተዋል ወይም በሕይወት አሉ ይበሉን የታጋች ተማሪዎች ቤተሰብ በኮሮናቫይረስ ምክንያት በኢትዮጵያ ውስጥ የተፈጠረው ስጋት፤ ተጠልፈው ከተወሰዱ በኋላ የት እንዳሉ ስላልታወቁት ልጆቻቸው መረጃ በሚፈልጉት የተማሪዎቹ ቤተሰቦች ሰቆቃን አበርትቶታል ሲሉ የአምነስቲ ኢንትርናሽናል የምሥራቅ አፍሪካ ምክትል ዳይሬክተር የሆኑት ሰይፍ ማጋንጎ ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ባለስልጣናት የተማሪዎችን ህይወት ለመጠበቅ ዩኒቨርስቲዎችን ለመዝጋት የወሰዱት እርምጃ የሚደነቅ ቢሆንም፤ ነገር ግን በተመሳሳይ ቱ ተማሪዎች ያሉበትን ቦታ በማወቅ ነጻ እንዲወጡ አድርገው ከቤተሰባቸው ጋር እንዲቀላቀሉ የሚያስችል ተጨባጭ እርምጃ መውሰድ አለበት ብለዋል። ማን ይለቀቅ ፤ ማን አይለቀቅ እስካሁን አላወቅንም የታጋች ቤተሰቦች አምነስቲ ኢንትርናሽናል አናገርኳቸው ያላቸው በርካታ የታገቱት ተማሪዎች ቤተሰቦች እየከበደ የመጣ ተስፋ መቁረጥና ደጋፊ የማጣት ስሜት ውስጥ መሆናቸውን እንደገለጹ አመልክቷል። ወደ መጡበት ሲመለሱ ከታገቱት ተማሪዎች መካከል አንዷ የሆነችው የሦስትኛ ዓመት የባዮቴክኖሎጂ ተማሪ የነበረችው ግርማነሽ የኔነህ አባት አቶ የኔነህ አዱኛ ለአምነስቲ እንደተናገሩት ልጆቻችንን ወደ ዩኒቨርስቲ የላክናቸው የተሻለ ተስፋ ሊኖራቸው ይችላል ብለን ነበ፤ አሁን ግን የት እንዳሉና በህይወት መኖራቸውን አናውቅም ብለዋል። ስለታገቱት ተማሪዎች መንግሥት ዝምታውን የሰበረበት መግለጫ አባትየው ጨምረውም መጠለፋቸውን ከነገረችን ዕለት ጀምሮ በለቅሶ ላይ ነው ያለነው፤ እንድንጸልይላት ነግራን ነበር፤ ቄስ እንደመሆኔ ጸሎቴን ሳሰማ ቆይቻለሁ። እናቷ በጣሙን ተጎድታለች፤ አእምሮዋ እየተነካ ነው። ከመንግሥት መንም የሰማነው ነገር የለም። አጋቾቹ መጀመሪያ ላይ ተማሪዎቹ ለቤተሰቦቻቸው ደውለው እንዲያናግሯቸው ፈቅደው የነበረ ቢሆንም አሁን ወላጆች ስለልጆቻቸው ከሰሙ ሦስት ወራት ተቆጥረዋል ይላል አምነስቲ። በምዕራብ ኦሮሚያ የግንኙነት አገልግሎት መቋረጡ ተቀባይነት የሌለውና የሰዎችን መረጃ የማግኘትና ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብትን የመጣስ ድርጊት ነው ሲሉ ሰይፍ ማጋንጎ ተናግረዋል። የተማሪዎቹን መታገት ተከትሎ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ አቶ ደመቀ መኮንን ተማሪዎቹ ያሉበትን ቦታ የሚያፈላለግና በሰላም ወደ ቤተሰቦቻቸው እንዲመለሱ የሚያደርግ ከተለያዩ የመንግሥት አካላት የተወጣጡ አባላት ያሉት ግብረ ኃይል ተቋቁሙ እየሰራ መሆኑን ገልጸው እንደነበር ይታወሳል።
በ አፍሪካ ያጣቻቸው ታላላቆች
ሊገባደድ ጥቂት ቀናት በቀሩት የጎርጎሳውያኑ ፣ አፍሪካ የዚምባብዌው የቀድሞ መሪ ሮበርት ሙጋቤ፣ ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ሰዓረ መኮንን፣ የሰብአዊ መብት ተሟጋቿን ቦጋለች ገብሬ፣ የዚምባብዌው ሙዚቀኛ ኦሊቨር ምቱኩድዚ እንዲሁም ስመ ጥር ፀሃፊያን፣ ሙዚቀኞች፣ ምሁራንን አጥታለች። ቢቢሲ ወደኋላ መለስ ብሎ አህጉሪቷ ያጣቸቻቸውን ታላላቆች ዘክሯል።
ያለን አማራጭ ውይይት ብቻ ነው ጀዋር መሐመድ
ኦክተውበር ማጋሪያ ምረጥ በኦሮሚያ ተጽዕኖ ፈጣሪ የሆኑ የሃገር ሽማግሌዎች እና ፖለቲከኞች ዛሬ ከሰዓት በሰጡት የጋራ መግለጫ ወጣቶች ከሰሞኑ ከተከሰተው ግጭት እራሳቸውን እዲቆጥቡ ጥሪ አስተላልፈዋል። ከትናንት በስቲያ በጀዋር ሞሐመድ መኖሪያ ቤት ከተፈጠረው ክስተት በኋላ በተለያዩ የኦሮሚያ ከተሞች የተቃውሞ ሰልፎች ተካሂደው ነበር። ከዚህ ጋር ተያይዞ በተፈጠረ በግጭት ቢያንስ ሰዎች ሕይወታቸውን ማጣታቸው ታውቋል። ዛሬ ከሰዓት መግለጫ የሰጡት ፖለቲከኞች ወጣቶች እንዲረጋጉ እና ሠላማዊ ትግል እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል። በጀዋር ሞሐመድ መኖሪያ ቤት በተሰጠው መግለጫ ላይ፤ ጀዋር ሞሐመድን ጨምሮ የኦነግ ሊቀመንበር ዳውድ ኢብሳ፣ ሌንጮ ባቲ፣ ከማል ገልቹ እና ሌሎች የፖለቲካ ሰዎች ተካፋይ ነበሩ። ጀዋር መሐመድ በመኖሪያ ቤቱ የተፈጸመውን ክስተት ካወገዘ በኋላ ይህ ሸር የኦሮሞን ህዝብ በጣም አስከፍቷል ብሏል። ጀዋር እሱን በመደገፍ ወጣቶች ያሳዩትን ድጋፍ አድንቆ ከዚህ በላይ ኩራት ሊሰማኝ አይችልም ሲል ተደምጧል። ይህን ህዝብ ለመንካት ለሚያስብ ኃይል መልዕክት ደርሶታል ያለ ሲሆን፤ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝደንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ እና የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽነር የሰጡት መግለጫ ኃላፊነት የተሞላበት ስለሆነ ሊመሰገኑ ይገባል ብሏል። የኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዝድነት አቶ ሽመልስ አብዲሳ በጀዋር መሐመድ መኖሪያ ቤት ላይ የተፈጸመው ክስተት መሆን ያልነበረበት ትልቅ ስህተት ነው ማለታቸው ይታወሳል። በተመሳሳይ መልኩ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽነርም ከክልሉ ምክትል ፕሬዝደንት ጋር ተመሳሳይ ይዘት ያለው መግለጫ ሰጥተው ነበር። የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል እንደሻው ጣሰው በኩላቸው ጀዋር መሐመድ ለተከታዮቻቸውና ለደጋፊዎቻቸው ልታሰር ነው፣ ጥቃት ሊደርስብኝ ነው በማለት ያስተላለፉት መልዕክት ስህተት ነው ብለው ነበር። ጀዋር ዛሬ ከሌሎች ተጽዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ጋር በሰጠው መግለጫ ቄሮዎች ላሳዩት አንድነት እናመሰግናቸዋለን። ይህችን ሃገር የሚያስተዳድረው መንግሥት ሰው የሚገደልበት እና የሚሸበርበት ጊዜ ማለፉን ማወቅ አለበት ብሏል። እንደ አንድ ታጋይ እና እንደ አንድ ፖለቲከኛ ለዚህ መንግሥት ማሳወቅ የምፈልገው ህዝብ የማይፈልገው ነገር በፍፁም ተፈጻሚ ሊሆን አይችልም። ይህንም ህዝቡ አረጋግጧል ሲልም ተደምጧል። ያለን አማራጭ አንድ እና አንድ ብቻ ነው። ይህም ውይይት ብቻ ነው ብሏል። ትግላችንን ወደ የብሄር እና ኃይማኖት ግጭት ለመቀየር የሞከሩ ኃይሎች አሉ ያለው ጀዋር ይህንን ኃይል ወጣቶች መቆጣጠር በመቻላቸው አድናቆቱን አቅርቧል። በቀጣዮቹ ቀናት ለተከሰተው ችግር ከሚመለከተው የመንግሥት አካል ጋር ውይይት አድርገን መፍትሄ እንሰጣለን ያለው ጀዋር፤ ጉልበተኞች በጉልበታቸው ከቀጠሉ ግን ልክ እንደ ትላንቱ መፍትሄ ፈልግ እንልሃለን። አሁን ወደ ማረጋጋት ተመለሱ። ግን ሁል ጊዜም እንደምላችሁ ንቁ ሁኑ። አንድ ዓይናችሁን ብቻ ዘግታችሁ ተኙ ሲል መልዕክቱን አስተላልፏል። ብ ጄ ከማል ገልቹ ብርጋዴር ጄነራል ከማል ገልቹ በቅርቡ የክልሉ የጸጥታ ቢሮ ኃላፊ በመሆን አገልግለው ነበር። በአሁኑ ወቅት ደግሞ የኦሮሚያ ብሔራዊ ፓርቲን ይመራሉ። በአዳማ፣ በአምቦ እንዲሁም ሻሸመኔን በመጥቀስ በእነዚህ ስፍራዎች የሰዎች ህይወት እያለፈ መሆኑን እና ይህም በአስቸኳይ መቆም እንዳለበት አሳስበዋል። ጥያቄያችሁ ትክክል ነው። ለውጡ መንገዱን ስቷል። ይሁን እንጂ ትዕግስተኛ መሆን ሞኝነት አይደለም ያሉት ብ ጄ ከማል ገልቹ፤ ሁኔታዎች በዚህ የሚቀጥሉ ከሆነ የሚጎዳው ሃገር የሚመራው ፓርቲ ነው ብለዋል። ብ ጄ ከማል ወጣቶች የአከባቢያቸውን ሰላም እንዲያስከብሩ ጥሪ አቅርበዋል። ገላሳ ዲልቦ ገላሳ ዲልቦ ከኦነግ መስራቾች መካከል አንዱ ናቸው። አቶ ገላሳ በመካከላችን የተፈጠረው አለመግባባት እና ግጭት እንዲቆም ለማሳሰብ ነው የመጣነው ብለዋል። አቶ ገለሳ ያላችሁን ብስጭት ገልጻችኋል፤ የከፈላችሁት መስዋዕትነት ይበቃል። አሁን በሰላም ወደ ቀያችሁ መመለስ አለባችሁ ብለዋል። የክልሉ ምክትል ፕሬዝደንት የሰላም ተስፋ በውስጣችን ዘርቷል ያሉ ሲሆን፤ ሰላም በአስቸኳይ ወርዶ ህዝቡ ወደተለመደው የዕለተ ተዕለት እንቅስቃሴው እንዲመለስ መልዕክት አስተላልፈዋል። ዳውድ ኢብሳ የኦነግ ሊቀመንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ በበኩላቸው፤ ወጣቱ የሚያደርገው ትግል ሌሎች ብሄሮችን እና ሃይማኖትን የሚጋፋ መሆን እንደሌለበት አሳስበዋል። በእስር ላይ የሚገኙ ሰዎችን ከእስር መለቀቅ ለህዝብ ጥያቄ ምላሽ ይሆናል ብለዋል። ይህንን ዜና ያጋሩ ስለማጋራት
ዝምባብዌ ረሃብ የጎዳቸው ዝሆኖችን ለሌላ ሀገር ሸጠች
ጥቅምት ይህንን ለማጋራት በ ዋትስአፕ ዝምባብዌ ዝሆኖችን ለተለያዩ ሀገራት እየሸጠች መሆኑ የተነገረ ሲሆን ከነዚህም መካከል በቅርቡ ለቻይና መሸጧ በመብት ተሟጋቾች ዘንድ ቁጣን ቀስቅሷል። የእንስሳት መብት ተሟጋቾች ሽያጩን የተቹ ሲሆን እንስሳቱ እንግልት ሊደርስባቸው ይችላል ሲሉ ስጋታቸውን ተናግረዋል። የዝምባብዌ ብሔራዊ ፓርክ አገልግሎት ግን፤ በዚህ ዝሆኖችን በገደለው የድርቅ ወቅት ሌሎች የዱር እንስሳትን ለማዳን ገንዘብ እንደሚያስፈልገው ተነግሯል። የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የሦስት ቀናት ጸሎት እና ምሕላ አወጀ አሁን የተሸጡት ዝሆኖች ከወላጆቻቸው ከተለዩ ዓመት እንዳለፋቸውም ለማወቅ ተችሏል። የዝምባብዌ ብሔራዊ ፓርክ ቃል አቀባይ የሆኑት ቴናሺ ፋራዎ እንዳሉት ከሽያጩ የሚገኘው ገቢ በሑዋንጊ ብሔራዊ ፓርክ ያሉ የዱር እንስሳትን ለመታደግ የውሃ ጉድጓድ ለመቆፈር ይውላል። ቃል አቀባዩ አክለውም የመብት ተሟጋቾች የሕዝብ ቁጣን ለመቀስቀስ ሆን ብለው እየሰሩ ነው ሲሉ ይወቅሳሉ። ነገር ግን የ አድቮኬት ፎር አርዝ ዳይሬክተር የሆነው ሌኒን ቺያስራ ውሳኔውን ይቃወማል። ያለን አማራጭ ውይይት ብቻ ነው ጀዋር መሐመድ ዝሆኖቹ ተይዘው መሸጣቸውና ከባህላቸውና ከለመዱት አካባቢ ውጪ መወሰዳቸው አግባብ አለመሆኑን ስንናገር ነበር። ብዙ ጊዜ ወደ እንስሳት ማሳያ ነው የሚወሰዱት፤ ከዚያም የተለያየ ጭካኔ የተሞላበት ድርጊት ይፈፀምባቸዋል ብሏል። በብሔራዊ ፓርኩ ዙሪያ የተስፋፋው የማዕድን ፍለጋ የእንስሳቱን የግጦሽ ስፍራ እና የውሃ አቅርቦት በእጅጉ ጎድቶታል ሲል የሚናገረው ቺያስራ ይህም እንስሳቱ ፓርኩን ጥለው እንዲሸሹና ከሌሎች እንስሳት ጋርም ለውሃ እንዲፎካከሩ እያደረገ ነው ይላል። በነሐሴ ወር ላይ የዓለም አቀፉ ንግድ ስምምነት ደህንነታቸው ላይ አደጋ ከተጋረጠ እንስሳት መካከል በአፍሪካ የሚኖሩ ዝሆኖችን በመጥቀስ ከአህጉሪቱ ውጪ እንዳይሸጡ ያለ ቢሆንም እስካሁን ግን ስምምነቱ አልፀደቀም። ከዚህ ዜና በተጨማሪ
የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የሦስት ቀናት ጸሎት እና ምሕላ አወጀ
ኦክተውበር አጭር የምስል መግለጫ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ዓመታዊ መደበኛ ስብሰባውን በማካሄድ ላይ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ዛሬ ጥቅምት ቀን ዓ ም በወቅታዊ ጉዳይ ላይ በሰጠው መግለጫ የምሕላና የሰላም ጥሪ አስተላልፏል። በአገሪቷ እንኳንስ ሊደረግ ቀርቶ ሊታሰቡ የማይገባቸው ጎሳንና ሃይማኖትን መሠረት ያደረጉ መጠነ ሰፊ ግጭቶች በተለያዩ አካባቢዎች መስፋፋታቸው እንዳሳሰበው የገለፀው ቅዱስ ሲኖዶሱ፤ ከዛሬ ጀምሮ ለሦስት ቀናት የጸሎትና ምሕላ እንዲደረግ አውጇል። ከመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች ጀምሮ ሁሉም አካላትና ዜጎች በየድርሻው ለአገራዊ ሰላም፣ አንድነት እና ተግባቦት የድርሻቸውን እንዲወጡም ጥሪ አድርጓል። ቅዱስ ሲኖዶሱ በመግለጫው በተለያዩ አካባቢዎች የሚነሱ ግጭቶች ምክንያታዊ ባልሆኑ ጉዳዮች መነሻነት የተከሰቱ ናቸው ብሏል። ከእውነታ የራቁ፣ የሕዝቡን የአንድነት እና የአብሮነት ባህል የሚጎዱ፣ ታሪክን የሚያፋልሱ ሐሰተኛ ትርክቶች ለግጭቶች መንስዔ እንደሆኑም ገልጿል። አክሎም የፖለቲካ ኃይሎች፣ የብዙኃን መገናኛዎች፣ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች እንዲሁም ምሁራንና የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ ብሔርንና ኃይማኖትን መሠረት ካደረጉ የትንኮሳ ቃላት ተቆጥበው፤ ለአገራዊ አንድነትና ተግባቦት የድርሻቸውን እንዲወጡ ጥሪውን አቅርቧል። የጸጥታ እና የፍትሕ አካላት፣ ግጭቶች እና አለመግባባቶች ከመከሠታቸው በፊት ቀድሞ በመከላከል የሰው ሕይወት መጥፋትንና የንብረት ውድመትን በማስቀረት የተጣለባቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ ቅዱስ ሲኖዶሱ ጠይቋል። እስከ አሁን ድረስ በግጭቶች እየደረሱ ካሉት የሰው ሕይወት መጥፋትና የንብረት ውድመት ልንማር ባለመቻላችን ችግሩ ቀጥሎ በዚህ ሳምንትም በአዲስ አበባ፣ በኦሮሚያ ክልልና በሌሎችም ክልሎች እየተሠከተ ያለው ግጭት እጅግ አሳሳቢ ነው ሲል ገልጿል ሲኖዶሱ። ችግሩ ጊዜ የማይሰጥና ሁሉም ኢትዮጵያውያን በአንድነትና በሕብረት ችግሩን ካልቀረፍነው መጠነ ሰፊ ጉዳትን የሚያስከትል በመሆኑም ከሌሎች የመወያያ አጀንዳዎች በማስቀደም በጉዳዩ ላይ በስፋት መወያየቱን ገልጿል። ከውይይቱ በኋላም ባለ አስራ ሁለት ነጥብ የአቋም መግለጫ እና የሰላም ጥሪ አስተላልፏል። ቅዱስ ሲኖዶስ የኦሮሚያ ቤተ ክህነት አደራጅ ኮሚቴ ጥያቄን አወግዛለሁ አለ ሲኖዶሱ በመግለጫው ማንኛውም የተለየ ሃሳብ ያለው ወገን በሰለጠነ እና በሰከነ መንገድ በውይይት ችግሮችን እንዲፈታ፣ የወደፊት የአገር ተረካቢ የሆነው ትውልድ አገራቸውንን ከጥፋትና ካልተገባ ድርጊት እዲታደጉ ጥሪ አቅርቧል። ልዩ ልዩ ፅሁፎችንና ዘገባዎችን በመገናኛ ብዙኃን አሊያም በማህበራዊ ሚዲያ የሚያቀርቡ የፖለቲካ ተንታኞች እና አክቲቪስቶች ከስሜት፣ ከብሔር፣ ከቋንቋና ከኃይማኖት ልዩነት በጸዳ ሁኔታ ለሰላም የበኩላቸውን እንዲያደርጉ፣ የመንግሥትም ሆነ የግል መገናኛ ብዙሃን ከተቋቋሙበት ዓላማ አንጻር ግጭትን ከሚፈጥሩ ነገሮችና ትንኮሳዎች እንዲቆጠቡና ሚዛናዊ የሆኑ መረጃዎችን ለሕዝቡ በማድረስ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡም ጠይቋል። ምሁራን ለአገር እድገት ያላቸውን ሚና የሚጠቅሰው መግለጫው አሁን አሁን ግን አንዳንድ ምሁራን የሚያስተላልፏቸው የኢትዮጵያን ታሪክ መሠረት ያላደረጉ ትርክቶች ለግጭትና ላለመግባባት መንስዔ ሲሆኑ እንደሚስተዋሉ ጠቅሷል። በመሆኑም ምሁራን ለአገራዊ አንድነትና ሰላም ኃላፊነታቸውን እንዲወጡም ጥሪ አስተላልፏል። በየደረጃው ያሉ የመንግሥት ኃላፊዎችም ግጭቶች ከመከሰታቸው በፊት ከሕዝብ ጋር ውይይት በማድረግ እና ከውይይቱ የሚገኙ ግብዓቶችን የእቅዳቸው አካል አድርገው ለትግበራው በመሥራት ኃላፊነታቸውን እዲወጡ ጠይቀዋል። መላው የኢትዮጵያ ሕዝብም እስከ አሁን ድረስ የኢትዮጵያን ሰላም በማይወዱ አካላት የሚከሠቱ ልዩ ልዩ አፍራሽና ግጭት ቀስቃሽ አጀንዳዎችን ወደ ጎን በመተውና በአርቆ አሳቢነትና በአገር ባለቤትነት መጠነ ሰፊ ትዕግሥት የተሞላበት አገራዊ አንድነትና ኅብረት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ላበረከቱት የማይተካ ሚና የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በቤተ ክርስቲያኒቱ ስም ምስጋና አቅርቧል። በመሆኑም አሁንም ለሰላምና አንድነት በዘር፣ ብሔርና ሃይማኖት ሳይለያዩ የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ ሲኖዶሱ የአደራ መልዕክት አስተላፏል። መግለጫው አክሎም ሌሎች የሃይማኖት ተቋማትም ለአገራዊ አንድነትና ለእምነት ነጻነት በአንድነትና በሕብረት ለመላው ሕዝባችን የሰላም ጥሪ በማስተላለፍ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡም ጥሪ አድርገዋል። በመጨረሻም መላው ሕዝብ እንደየእምነቱና ሃይማኖቱ ሥርዓት ከዛሬ ጥቅምት ቀን ዓ ም ጀምሮ ለ ቀን ያህል በጾም፣ በጸሎትና በሐዘን ስለ ሀገር ሰላም በአንድነት ጥሪውን ለፈጣሪው ያቀርብ ዘንድ ጥሪውን አስተላልፏል። ተያያዥ ርዕሶች
ወደ ኦሮሚያ፣ ሐረርና ድሬዳዋ ከተሞች የመከላከያ ሠራዊት መሰማራቱ ተገለፀ
ኦክተውበር ማጋሪያ ምረጥ ረቡዕና ሐሙስ ዕለት የተቃውሞ ሠልፍ በተካሄደባቸው የኦሮሚያ፣ ሐረርና ድሬዳዋ ከተሞች በክልሎችና በአስተዳደሩ ጥያቄ መሰረት የመከላከያ ሠራዊት መሰማራቱን የመከላከያ ኢንዶክትሪኔሽንና የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተሩ ሜጄር ጄኔራል መሀመድ ተሰማ ለሃገር ውስጥ መገናኛ ብዙኀን በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል። መከላከያ ሠራዊት የተሰማራባቸው ከተሞች መካከል አምቦ፣ ቢሾፍቱ፣ ባሌ ሮቤ፣ አዳማ፣ ሞጆ እንዲሁም በድሬዳዋ እና ሐረር መሆናቸውን በመግለጫቸው ወቅት ተናግረዋል። መከላከያ ሠራዊት ወደ ስፍራው የገባው የፌደራል መንግሥቱ ከክልሉ በቀረበለት ጥያቄ መሰረት መሆኑን ሜጄር ጄኔራል መሀመድ ተሰማ ገልፀዋል። እስካሁን በተሰራው ሥራ ተጨማሪ የሰው ህይወት እና ንብረትን ከጥፋት ማትረፍ የተቻለ ቢሆንም፤ መከላከያ ሠራዊት በፍጥነት ባልደረሰባቸው አካባቢዎች ጉዳት ማጋጠሙን የመከላከያ ኢንዶክትሪኔሽንና የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል። የመከላከያ ሠራዊት በእነዚህ አካባቢዎች ከአባ ገዳዎች፣ ከሃይማኖት መሪዎች፣ ከወጣቶች እና ከህብረተሰቡ ጋር በመሆን የማረጋጋት ሥራ እያከናወነ መሆኑን የገለፁት ኃላፊው የተዘጉ መንገዶችንና የንግድ ተቋማትን ማስከፈት ሥራ እየተሰራ መሆኑን ተነግረዋል። የፀጥታ መደፍረስ ያጋጠማቸው አካባቢዎች ወደ ቀደመ ሰላማቸው እስከሚመለሱ ድረስ የሀገር መከላከያ ሠራዊት አካባቢዎቹን የማረጋጋቱን ሥራ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል። በአንዳንድ የኦሮሚያ ከተሞች የሆነው ምን ነበር በአክቲቪስት ጃዋር ሞሐመድ መኖሪያ ቤት አጋጠመ የተባለውን ክስተት ተከትሎ በተለያዩ የኦሮሚያ ክልል ከተሞችና በሌሎች ቦታዎች ረቡዕ እና ሐሙስ ሲካሄዱ ከቆዩት የተቃውሞ ሰልፎች ጋር በተያያዘ እስካሁን በተገኙ ይፋዊ መረጃዎች የሟቾች ቁጥር ቢያንስ ደርሷል። የተቃውሞ ሰልፍ ተደርጎባቸው ሰው ከሞተባቸው አከባቢዎች መካከል አምቦ፣ ድሬዳዋ እና ዶዶላ ይገኙበታል። አምቦ ረቡዕ በአምቦ ከተማ ከተገደሉት ሶስት ሰዎች በተጨማሪ ሐሙስ ሁለት ሰዎች ተገድለዋል። ዛሬ በጥይት ከተገደሉት መካከል የ ዓመቱ አዛውንት አቶ ሞሮዳ ሞሳ የሚባሉ ይገኙበታል በማለት ነዋሪዎች ተናግረዋል። አቶ ሞረዳ ልጃቸውን ፍለጋ በወጡበት ከጸጥታ አስከባሪ ኃይል በተተኮሰባቸው ጥይት መገደላቸውን የከተማው ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናግረዋል። በአምቦ ሐሙስ ከተገደሉት ሁለት ሰዎች በተጨማሪ ሌሎች በርካታ ሰዎቸ በጥይት ተመትተዋል። የአምቦ ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር አቶ ደበበ ፈጠነ፤ ሰዎች በጥይት ተመተው እኛ ጋር መጥተዋል። ሁለቱ ህይታቸው አልፏል። ሰዎች ደግሞ ተኝተው እየታከሙ ሲሆን የተቀሩት ቀላል ህክምና ተደርጎላቸው ወደየቤታቸው ተመልሰዋል በማለት ያስረዳሉ። አቶ ደበበ ወደ ሆስፒታላቸው የመጡት ሰዎች በሙሉ ወንዶች መሆናቸውን እና ዕድሜያቸውም ከ እንደሚገመት ተናግረዋል። በዚህም በአምቦ ረቡዕ ፤ ሐሙስ በድምሩ የሟቾች ቁጥር ደርሷል። ምስራቅ ሐረርጌ በሁለቱ ቀናት በምስራቅ ሃረርጌ በተካሄዱት ሰልፎች የሟቾች ቁጥር መድረሱን ሰምተናል። በዞኑ የኮሚኒኬሽን ባለሙያ የሆኑት አቶ አየለ ዴሬሳ በምስራቅ ሃረርጌ በሚገኙ ከተሞች ሙሉ በሙሉ ሊባል በሚችል መልኩ የተቃውሞ ሰልፎች ተካሂደው እንደነበረ ተናግረው፤ በሁለት ከተሞች በተፈጠረው ግጭት የ ሰዎች ህይወት ማለፉን እና በተቀሩት ከተሞች ግን የተካሄዱት የተቃውሞ ሰልፎች በሰላም መጠናቀቃቸውን ለቢቢሲ ተናግረዋል። የተፈጸመው መሆን ያልነበረበት ትልቅ ስህተት ነው አቶ አየለ፤ ትናንት ቱ ሰዎች የተገደሉት ጉሮ ጉቱ በምትባል ከተማ ወደ ብሄር በተቀየር ግጭት ስለመሆኑ ይናገራሉ። አንድ ባለሃብት የደህንነት ስጋት ተሰምቶት ሁለት ሰዎችን በጥይት መትቶ ገደለ። ከዚያም በቂም በቀል ግለሰቡ እና ሁለት የቤተሰብ አባላቱ ተገደሉ ሲሉ ሁኔታውን ያስረዳሉ። የአወዳይ ከተማ ነዋሪ የሆነ ወጣት ከመከላከያ ሠራዊት በተተኮሰ ጥይት ስለመገደሉ የአወዳይ ከተማ ከንቲባ ጃፋር ሙሐመድ ለቢቢሲ ተናግረው ነበር። ዶዶላ በምዕራብ አርሲ ዞን ዶዶላ ከተማ ረቡዕና ሐሙስ በነበሩ ግጭቶች በጠቅላላው ሰዎች መገደላቸውን ታውቋል። ሐሙስ በነበረ ግጭት ሰዎች ሞተው ወደ ዶዶላ አጠቃላይ ሆስፒታል መምጣታቸውን የሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክተር ዶክተር ቶላ ቢዮ ተናግረዋል። ረቡዕ ደግሞ ሁለት ሰዎች ተገድለው ነበር። በአካባቢው ከጠዋት ጀምሮ ሠልፍ እንደነበር የተናገሩት ሜዲካል ዳይሬክተሩ ከሰዓት በኋላ ግን ይህ ሠልፍ መልኩን መቀየሩን ይናገራሉ። ሁኔታው አስፈሪ ስለነበር ለሕይወታቸው የሰጉ ሰዎች በአካባቢው በምትገኘው ኪዳነ ምህረት ቤተ ክርስቲያን ተጠልለው አንደሚገኙ ተናግረዋል። ሐረር በሐረር ከተማ ረቡዕ ሰዎች መገደላቸውን ከነዋሪዎች ሰምተናል። ድሬዳዋ በድሬዳዋ ከተማም ረቡዕ ሰው የተገደለ ሲሆን ዛሬ ደግሞ ሰዎች ተገድለዋል። የድል ጮራ ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር የሆኑት ዶ ር አብዱራሃማን አቡበከር ሐሙስ ሰባት ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸው ወደ ሆስፒታላቸው እንደመጡ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ለህክምና ከመጡት ሰዎች መካከል ቱ ህይወታቸው ማለፉን ጠቅሰው፤ ዶ ር አብዱራሃማን ሰዎቹ በጥይት እና በሌሎች ነገሮች ጉዳት ደርሶባቸው ወደ ሆስፒታል እንደመጡ አመልክተዋል። አዳማ ረቡዕ በአዳማ ከተማ የተቃውሞ ሰልፎች ተካሂደው ነበር። ሰልፎቹ ባህርያቸውን በመቀየር በሁለት ጎራ በተከፈሉ ሰዎች መካከል ግጭት ተከስቶ በሰዎች ላይ ጉዳት ደርሷል። ለጃዋር መሐመድ ድጋፍ ለማሳየት በወጡ ወጣቶች እና እነሱን በሚቃወሙ መካከል ግጭት እንደተፈጠረ በሥፍራው የነበረው የቢቢሲ ሪፖርተር ዘግቧል። የአዳማ ከተማ ኮሚኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ራውዳ ሁሴን በበኩላቸው በከተማዋ ውስጥ የሚገኝ የአንድ ዱቄት ፋብሪካ የጥበቃ ሠራተኛ ጥይት ተኩሶ ሁለት ሰዎችን መግደሉን እና በዚህ የተበሳጩ ሰልፈኞ በፋብሪካው ቅጥር ግቢ ውስጥ የነበሩ መኪኖችን ማቃጠላቸውን ለቢቢሲ ተናግረዋል። በግጭቱ ሁለተኛ ቀን ሐሙስ ዕለትም እዚያው አዳማ ከተማ ውስጥ የሚገኙ ከ በላይ የንግድ ሱቆች በተቃዋሚዎቹ በተፈጸመባቸው ጥቃት በእሳት ተቃጥለው መውደማቸው ተነግሯል። ግጭቶች ባጋጠሙባቸው አካባቢ ያሉ ነዋሪዎችን፣ የሆስፒታል ምንጮችንና የመንግሥት አካላትን በማነጋገር ባገኘው የተረጋገጠ መረጃ መሰረት በሁለት ቀናቱ ግጭት ቢቢሲ ሰዎች መሞታቸውን ለማረጋገጥ የቻለ ይሁን እንጂ ቁጥሩ ከዚህ ሊበልጥ እንደሚችል አንዳንዶች ስጋታቸውን ገልጸዋል። ይህንን ዜና ያጋሩ ስለማጋራት
የዲያቆን ዳንኤል ክብረት የቦርድ አባልነት ውዝግብ አስነሳ
ማርች ማጋሪያ ምረጥ የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው ኛ ዓመት የሥራ ዘመን ኛ መደበኛ ስብሰባው የሚኒስትሮችን፣ የኮሚሽነርና የቦርድ አባላት ሹመትን አጽድቋል። በዕለቱ አንዳንድ የምክር ቤቱ አባላት ምክር ቤቱ ሹመት በመስጠትና በመንፈግ ላይ መጠመዱን በማንሳት ቅሬታ ያቀረቡ ሲሆን ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ቦርድ አባልነት የቀረቡት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ላይ ያላቸውን ተቃውሞ አሰምተዋል። ለኢትዮጵያ የፕሬስ ድርጅት የቦርድ አባል ሆነው ከቀረቡ ዘጠኝ ሰዎች መካከል አንዱ የሆኑት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ላይ ቅሬታ ያቀረቡ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት እንዳሉት ከሆነ ግለሰቡ የሀይማኖት እኩልነት ላይ የማያምኑ፣ በዜጎች መካከል ክፍፍል እንዲፈጠር የሚሰሩ፣ በማለት በሕዝብ የሚነሱባቸው ቅሬታ ወደ ጎን በመተው መቅረብ አልነበረባቸውም በሚል አባልነታቸውን ተቃውመዋል። የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት መላውን ኢትዮጵያ የሚያገለግል በመሆኑ በእርሳቸው የቦርድ አባልነት ተቃውሟቸውን አሰምተዋል። ሞተዋል ወይም በሕይወት አሉ ይበሉን የታጋች ተማሪዎች ቤተሰብ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የቦርድ አባል ሆነው ከቀረቡት አባላት መካከል ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ላይ ቅሬታ በመቅረቡ ለብቻው ጉዳያቸው ታይቶ ድምጽ እንዲሰጥ ከተደረገ በኋላ በ ድጋፍ በ ተቃውሞ እና ድምጸ ተአቅቦ በአብላጫ ድምጽ የዲያቆን ዳንኤል የቦርድ አባልነት ፀድቋል። ከዚህ በኋላ በቀሩት አባላት ላይ ድምጽ የተሰጠ ሲሆን በአብላጫ ድጋፍ ድምጽ በመመረጣቸው በሕዝብ ተወካዮቹ ፊት ቀርበው ቃለ መሃላ ፈጽመዋል። ቀደም ሲል የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የቦርድ አባል የነበሩትና አሁንም በአባልነት እንዲቀጥሉ የቀረቡት ዲያቆን ዳንኤል በአብላጫ ድምጽ ከተመረጡ በኋላ በምክር ቤቱ ቀርበው ቃለ መሀላ ከፈፀሙ የቦርድ አባላት መካከል አልተገኙም ነበር። ምክር ቤቱ ዛሬ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባው በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ አቅራቢነት የቀረበለትን የተለያዩ የሚኒስትሮች ሹመትንም ተቀብሎ አጽድቋል። በዚህም መሰረት ምክር ቤቱ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ፣ ዶክተር ሊያ ታደሰ የጤና ሚኒስትር፣ አቶ ላቀ አያሌው የገቢዎች ሚኒስትር፣ ወይዘሮ ፊልሰን አብዶላሂ የሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ሚኒስትር በማድረግ በአብላጫ ድምጽ አጽድቆታል። በዛሬው እለት የተሾሙት ሚኒስትሮችም ሆኑ የፕሬስ ድርጅት ቦርድ አባላት በምክር ቤቱ ቀርበው ቃለ መሃላ ፈፅመዋል። በተጨማሪም ምክር ቤቱ የፌደራል የሥነ ምግባር እና የፀረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ሹመት አጽድቋል። አቶ ፀጋ አራጌ የፌደራል የሥነ ምግባር እና የፀረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር በመሆን ተሾመዋል። በምክር ቤቱ ውሎ ከቀረቡት ሌሎች ቅሬታዎች መካከል የብልጽግና ፓርቲ ሕጋዊነት ጉዳይ ከአንዳንድ አባላት የተነሳ ሲሆን ሌሎች የሕዝብ እንደራሴዎች ደግሞ የምርጫ ቦርድ ሕግን በመጥቀስ የፓርቲውን ሕጋዊነት ተከራክረዋል። ተያያዥ ርዕሶች
ለተከታታይ ስምንት ዓመታት የህዳሴ ግድቡን ቦንድ የገዙት ኢትዮጵያዊ
ማርች አጭር የምስል መግለጫ የአባይ ውሃ ለኔ ፀበሌ ነው፤ የኢትዮጵያ ህዝብም ፀበል ነው ወላጆቹ ስድስት ልጆች ወልደዋል፤ ሁሉም ሊያድጉላቸው ግን አልቻሉም። አንድ በህይወት የተረፈላቸውን ልጃቸውን ግን፤ እንደ ሴት አንቺ ብለው እየጠሩ አሳደጉት። ሰባት ዓመት ሲሞላው ደግሞ ኪሮስ የሚል ስም አወጡለት። እናቱ ግን፤ ልጄ አንድ ብቻውን ስለሆነ ሁለት ሰባት ዓመት እስኪሞላው አንቺ ነው የምለው ብለው አንቺ ማለታቸውን ቀጠሉ። ልክ ዓመት ሲሞላኝ፤ እናቴ አንተ ብላ ጠራችኝ፤ በዛው ለትግል ወደ በረሃ ወጣሁ የሚሉት አቶ ኪሮስ አስፋው፤ በ ዓ ም ህወሓትን እንደተቀላቀሉ ያስታውሳሉ። ሱዳን በህዳሴው ግድብ ጉዳይ አቋሟን ትቀይር ይሆን ከሁለት አመት በኋላ ግን የሻእቢያ ሰራዊትን ለመደገፍ ሳሕል ላይ በተካሄደው ጦርነት ለመሳተፍ ከሄዱት ታጋዮች አንዱ ስለነበረ፤ ጭንቅላታቸው ላይ ከባድ ጉዳት ደረሰባቸው። በዚህ ጉዳት፤ ለስድስት ወራት ራሳቸውን ስተው ቆዩ ፤ አንድ አይናቸውም በዚሁ አደጋ ጠፋ። ከስድስት ወራት ህክምና በኋላ ያገገሙት አቶ ኪሮስ፤ ወደ ትግራይ ተመልሰው ፊደል ቆጥረው፣ ዳግም ወደ ኤርትራ በመሄድ የህክምና ትምህርት አጥንተው ተመለሱ ከ ዓ ም ጀምሮ በትግራይ ማእከላይ ዞን አብዪ አዲ ከተማ በሚገኘው የአብዪ አዲ ሆስፒታል ነርስ ሆነው ሲሰሩ ቆይተው አሁን በፊዚዮቴራፒ ማዕከል እያገለገሉ የሚገኙ አካል ጉዳተኛ ናቸው አቶ ኪሮስ። ኪሮስ አስፋው፤ ለተከታታይ አመታት ያለማቋረጥ ለታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ የሚውል ቦንድ በየወሩ በግማሽ ወርሃዊ ደመወዛቸው እየገዙ ይገኛሉ። ቢቢሲ፤ ዓብዪ ዓዲ ላይ ኪሮስ ቦንድ ብለው የሚጠሩዎት ሰዎች እንዳሉ ሰማሁ፤ ለምንድን ነው ኪሮስ አስፋው፤ የድሮ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ ህያው ከሚያደርጉት ስራዎቹ አንዱ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ላይ የወሰደው ቆራጥ ውሳኔ ነው። የግድቡ ግንባታ ሲያበስሩ ካላቸው ሦስት ነገሮች በገንዘብ፣ ጉልበትና ሞያ ራሳችን የምንገነባው ግድብ ነው ማለቱን መቼም አልረሳም። በዚህ ምክንያት ግድቡ ተሰርቶ እስኪያልቅ የወርሃዊ ደሞዜን ግማሹ እሰጣለሁ የሚል ቃል ገባሁ። ቃሌን በማክበር እነሆ ስምንት አመት ሙሉ ቦንድ እየገዛሁ ነው። ቢቢሲ፤ ምን ያክል ቦንድ አለዎ ማለት ነው ኪሮስ አስፋው፤ ባጠቃላይ ቦንድ ገዝቻለው፤ የመጨረሻዋ የካቲት የገዛኋት ናት። ቢቢሲ፤ ይሄን ያክል ለቃልዎ ተገዢ እንዲሆኑ ያስቻለዎት ምንድን ነው ኪሮስ አስፋው፤ ቃሌ ለአባይ ነው የሰጠሁት። የበረሃው ትግልም የገባሀው ቃል እንደማይታጠፍ አስተምሮናል። የኢትዮጵያ ህዝብ ግድቡ እንዲሰራ ይፈልጋል፤ ተሰርቶም ለህዝብ ጥቅም ይውላል ብዬ አምናለሁ። እኔ ይሄ ሁሉ ቦንድ ለመግዛት ገንዘብ ተርፎኝ ወይም የሚያግዘኝ ሰው ኖሮ ሳይሆን፤ አባይ ተገንብቶ ጥቅም ላይ ሲውል እኔም ተጠቃሚ እሆናለሁ የሚል እምነት ስላለኝ ነው። ቢቢሲ፤ ከግድቡ እንደ ግለሰብ ምን እጠቀማለሁ ይላሉ ኪሮስ አስፋው፤ በቀጥታ ተጠቃሚ ባልሆንም፤ የኢትዮጵያ ህዝብ ተጠቃሚ ሲሆን እኔም እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ ጥቅሙ ይደርሰኛል እላለሁ። ግድቡ ወደ ሚገነባበት ቦታ ሂጄ ምን ይዤ መጣሁ መሰለሽ፤ አንድ ድንጋይና ከወንዙ በላስቲክ ኮዳ የቀዳሁት ውሃ ይዤ መጥቻለሁ። ሦስቱ ሃገራት በዋሽንግተን ምን ተስማሙ ቢቢሲ፤ ለምን ኪሮስ አስፋው፤ ድንጋዩ ግድቡ የሚገነባበት ቦታ እጅግ አስቸጋሪና ጠንካራ መሆኑን፤ እኛም ይህን እውን ለማድረግ ያለን እምነት ጽኑ መሆኑን ለማሳየት ነው። ውሃው ግን የአባይ ጸበል ነው። አንድ ሰው የሚካኤል፣ የማርያም ወዘተ ብሎ የሚያምንበት ጸበል ይጠቀማል። እኔ ከአባይ ያመጣሁት ውሃ ደግሞ፤ የኢትዮጵያ ህዝብ መድሃኒት ነው ብዬ ስላመንኩ ነው። ቢቢሲ፤ እሺ ቅድም ወደ ጀመርነው ወሬ እንመለስ ኪሮስ አስፋው፤ መልካም፤ ስለዚህ እንደ ሰው አስፈላጊውን ገንዘብ ከህዝቡ ተሰብስቦ ግድቡ ይገነባል። ከተገደበ በኋላ ደግሞ የኢትዮጵያ ህዝብ ይጠግባል፤ ከምን ነገር በላይ ግን የመለስ አደራ መወጣት እፈልጋለሁ። የኢትዮጵያ ችግር ገንዘብ ሳይሆነ፤ ፖለቲካና ሰላም ማጣት ነው። እንደጀመርነው ብንቀጥል ኑሮ አሁን ሁለተኛ አባይ ጀምረን ነበር እላለሁ። በተያዘለት ጊዜ አልቆ፣ ተመርቆ ስራ ቢጀምር ብዙ ተጠቅመን ነበር። ግን ባለው የፖለቲካ አመራር ችግር እስከ አሁን ወደ ኋላ እየተጎተተ ሲደናቀፍ ቆይቷል። ችግሮች ቢገጥሙንም ግን ይገነባል። ቢቢሲ፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ ወደ ስልጣን እንደመጡ ግድቡ የፕሮፖጋንዳ ስራ ሲሰራበት እንጂ ሲገነባ እንዳለነበረ በመግለጽ፤ ገንዘቡም በሙስና መጥፋቱን ጠቁመዋል። በዚህ ምክንያት በ አመት እንኳ አያልቅም ብለው ነበር። ፕሮጀክቱን ሲመሩ የነበሩት ኢንጀነርም በመኪናቸው ውስጥ ሞተው ተገኝተዋል። በወቅቱ እነዚህን ነገሮች ሲሰሙ ተስፋ አልቆረጡም ኪሮስ አስፋው፤ ልክ ነው፤ ይህ ስሰማ አዝኛለሁ። ከዚህ ሁሉ ልብ የሚሰብር ንግግር በኋላ ቦንድ መግዛት ማቆም አላቃተኝም። ግን ይህ አመራር የአባይ ግንባታ የማያምንበት ከሆነ፤ በግድቡ አስፈላጊነት እምነት ያለበት አመራር መጥቶም ቢሆን ያልቃል የሚል እምነት ማስቀደም እንዳለብኝ አወቅኩ። ትራምፕ ህዳሴ ግድብ ሲያልቅ እመርቃለሁ ማለታቸው ተሰማ የኢንጅነሩና የመለስ ሞት ለእኔ አንድ አይነት ናቸው፤ በቃ የኢንጅነር ስመኘው በቀለ መሞት ግድቡ እንዳይሰራ ማድረግ ይሆን እንዴ የሚል ስሜት ፈጥሮብኛል። በዚህ ደንግጬ፣ አዝኜ፣ አልቅሻላሁ፤ ግን መልሶ እንጽናናለን። እኔ ታጋይ ነኝ። በትግል ወቅት ታላላቅ መሪዎቻችን ሲሞቱ አዝነን እናለቅስና፤ አሁንስ ማን ይመራናል እንል ነበር። ሆኖም ግን ሌሎች ጀግና መሪዎች ይተኩና ትግሉን መርተው፣ አሸንፈናል። ስለዚህ ግድቡን መርተው ማሳካት የሚችሉ ጀግና ለመኖራቸው ተስፋ አልቆርጥም። አባይም በህዝብ ተሳትፎ ያልቃል፤ እነሱ ወደ ኔጋቲቭ እኛ ደግሞ ወደ ፖዘቲቭ እየገባን መንገድ ላይ እንገናኛለን። ቢቢሲ፡ ከማን ጋር ኪሮስ አስፋው፤ የአባይ ግድብ እንዳይገነባ ሲያደርጉ ከነበሩና፣ ገንዘባቹ ተበልቷል በማለት ተስፋ እንድንቆርጥ ካደረጉን ጋር። ቢቢሲ፤ አሁን ግን በወሬ ብቻ አይደለም፤ ከግብጽ፣ አሜሪካና ሌሎች ትልልቅ አለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማት ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ላይ እየገነባችው ያለችውን ግድብ የመጠቀም መብቷን ወደ ምታጣበት መስመር እንድትገባ ጫና እየተደረገባት ነው ብለው ምሁራን እየገለጹ ነው፤ ይህ እርሶን ጨምሮ ህዝቡ ለአመታት የከፈለው ገንዘብ ሜዳ ላይ እንዳይቀር አያሰጋዎትም ኪሮስ አስፋው፤ ለእኔም በግሌ እኮ ብዙ ነገር ደርሶብኛል። ከህጻን ልጅ ጀምሮ ብዙ ሰዎች እየመጡ አባይ ተሽጧል፣ አባይ ተከልክሏል፣ አባይ ተወርሷል፣ ገንዘብህ ጠፍቷል ይሉኛል። መሪዎቻችን በግድቡ ዙርያ ቆራጥ የሆነ አመራርና አቋም ባለማሳየታቸው አሁን እነዚህ አገራት እየፈከሩ ነው፤ ግን ትርጉም ስለ ሌለው ይሄም ያልፋል። ኢትዮጵያ፤ የአሜሪካንን መግለጫ ተከትሎ ብሔራዊ ጥቅሜን አሳልፌ አልሰጥም አለች ቢቢሲ፤ እንዴት ትርጉም አይኖረው ሃያላን አገራት አይደሉም ኪሮስ አስፋው፤ ቢሆኑስ የእኔ የቃል እምነት መለስ ያልቃል ማለቱ ነው። አሜሪካም ትሁን ግብጽ እንዲሁም ከራሳችን የግድቡን ግንባታ ሊያደናቅፉን ይችላሉ፤ ግን እንሻገረዋለን የሚል ጠንካራ እምነትና ጽናት እንዲኖረን በማድረግ አበርትቶን አልፏል። እኔም ከዚህ ቃል ነው የምነሳው፤ በማንኛውም አጋጣሚ ያልቃል የሚለው እምነቴን ይዤ ነው የምጓዘው። ቢቢሲ፤ ኑሮ በተወደደበት በዚህ ወቅት ግማሽ ወርሃዊ ደመወዝ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ብሎ መክፈል አይከብድም ኪሮስ አስፋው፤ ሃብታም እንደሚበላለት፤ ድሃም እንደሆነለት ይላሉ ወላጆቻችን። ግድቡ ሲያልቅ በተዘዋዋሪ ገንዘቡ እኔ ጋር ይደርሳል። እግዜር ይመስገን ሳልበላ አልዋልኩም፣ አላደርኩም። ልጆቼም ይማራሉ፣ ቤትም አለኝ። ሁሌም የምልከው ገንዘብ ደግሞ፤ ልክ ወደ ልጄ የላኩት ያክል ነው የሚሰማኝ። ስለ ሆነም አካባቢዬ ያለው ባንክ ማረጋገጫ ቦንድ ቢሰጠኝም፤ ስልክ ደውዬ ግን ደርሷል ብየ ጠይቄ አረጋግጣለሁ። እርካታ ይሰጠኛል። ቢቢሲ፤ ግድቡ የሚጠይቀው ገንዘብ ግን በመቶዎች ሳይሆን በቢሊዮን ዶላር የሚገመት ነው ኪሮስ አስፋው፤ አውቃለሁ፤ ግን የኢትዮጵያ ህዝብም እኮ በመቶ ሚሊዮን የሚቆጠር ነው። ቦንድ መግዛት የቻለውን ከገዛ፣ ያልቻለውን ደግሞ በቀን አንድ ብር ከሰጠ በአመት ስንት ሚሊዮን ብር ይገኛል ይህ በየአመቱ ተደምሮ ግድቡን መገንባት የሚችል ገንዘብ ይፈጥራል። ቢቢሲ፤ ስለዚህ ኪሮስ አስፋው፤ ስለዚህማ ግድቡ የሚገነባው፤ ገንብተን መጨረስ እንችላለን የሚል እምነት በህጻን፣ አዋቂ፣ ወጣትና የአገር መሪ ልቦና ውስጥ መኖር አለበት። የተበላሸው ፖለቲካዊ አስተሳሰባችንም መለወጥ ይገባዋል። ለብሄርና ሃይማኖታዊ ግጭት፣ መከፋፈልና መራራቅ የዳረገንን ፖለቲካ መስበር አለብን። የኢትዮጵያ ህዝብ ከሰሞኑ ያሳየውን ወኔ አስደስቶኛል፤ መንግስትም ወደ ፊት ባናውቅም አሁን አሜሪካ ያቀረበችለት ሰነድ ባለመፈረሙ እፎይታ ሰጥቶኛል። በቀጣይም አንፈተንም ማለት ግን አይደለም፤ አሁን የምናያቸው ችግሮች በሙሉ ተደምረው ግን ተስፋ የምናደርግበት የህዳሴአችን ግድብ የሚጎዳ መሆን የለበትም፤ ያ ያሰጋኛል። የፈለገው ፖለቲካዊ ልዩነት ቢፈጠርም አባይ ግን አንድ ሊያደርገን ይገባል። ፈተናዎች አሸንፈን የግድቡ ፍጻሜ የምናይበት ቀንም በተስፋ እጠብቃለው። ተያያዥ ርዕሶች
የሩስያ መንግሥት ስራ ለቅቂያለሁ ብሏል። ምን ማለት ይሆን
ጃንዩወሪ ማጋሪያ ምረጥ የሩስያ መንግሥት ሥራ ለቅቋል። ይህ የሆነው ደግሞ ፕሬዝደንት ፑቲን ሕገ መንግሥታዊ ለውጥ ያሻል የሚል ሃሳብ ካቀረቡ በኋላ ነው። ለመሆኑ የዚህ ትርጉሙ ምንድነው ሕገ መንግሥታዊ ለውጡ በሕዝበ ውሳኔ አብላጫ ድምፅ ካገኘ ሩስያ ከፕሬዝደንታዊ የመንግሥት አስተዳደር ወደ ፓርላሜታሪያዊ ትቀየራለች ማለት ነው። ፕሬዝደንት ፑቲን በግሪጎሪያን አቆጣጠር ላይ ሥልጣን በቃኝ እንዲሉ ሕገ መንግሥቱ ያዝዛል። ነገር ግን ለአራት የስልጣን ዘመናት ሩሲያን ያስተዳደሩት ፑቲን አዲስ መላ ይፈልጋሉ እንጂ ሥልጣን በቃኝ ይላሉ ተብሎ አይታሰብም ይላሉ ተንታኞች። ፑቲን በዓመታዊው ሃተታቸው ላይ ነው አዲሱን ዕቅዳቸውን ይፋ ያደረጉት። ከንግግራቸው በኋላ ጠቅላይ ሚኒስትር ዲሚትሪ ሜድቬዴቭ ፑቲን ያቀረቡት ሃሳብ እንዲፀድቅ በማሰብ የሩስያ መንግሥት ሥልጣን ለቅቋል ሲሉ ተደመጡ። በጣም ያልጠበቅነው ነገር ነው የሆነው ሲሉ አንድ ምንጭ ለቢቢሲ ተናግረዋል። የፑቲን ሃሳብ ምንድነው በዓመታዊው የላዕላይና ታህታይ ሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት መክፈቻ ላይ ንግግር ያሰሙት ፕሬዝዳንት ፑቲን፤ ከፕሬዝደንታዊ ወደ ፓርላሜንታዊ ስርዓት በሚደረግበት ሽግግር ላይ ሕዝበ ውሳኔ እንደሚደረግ አሳውቀዋል። ፑቲን ለ ኛ ጊዜ ዛሬ ቃለ መሐላ ፈጸሙ ይህ ማለት ፑቲን፤ ሩስያ ከፕሬዝደንታዊ አስተዳደር ልክ እንደ ኢትዮጵያ በፓርቲ ወደ ሚመረጥ ጠቅላይ ሚኒስቴርነት አስተዳደር እንደትሸጋገር ይሻሉ ማለት ነው። አሁን ባለው የአስተዳደር ሥርዓት በፕሬዝደንቱ የሚመረጡት ጠቅላይ ሚኒስትር የረባ ሥልጣን የላቸውም። ሌላኛው የፑቲን ሃሳብ ስቴት ካውንስል የተሰኘው ምክር ቤት አቅም እንዲጎለብት ነው። ፑቲን የሚመሩት ይህ ምክር ቤት በክልል ኃላፊዎችን ያዋቀረ ነው። ፑቲን ካነሷቸው ሌሎች ሃሳቦች መካከል የዓለም አቀፍ ሕጎችን ጫና መቀነስ፣ የፕሬዝደንት ሥልጣን ላይ መቆያ ጊዜ እንዲራዘም ማድረግ፣ የሌላ ሃገር ዜግነት ወይም የሥራ ፈቃድ ያላቸው ፖለቲከኞች ጉዳይ ይገኙበታል። ጠቅላይ ሚኒስትር ሜድቬዴቭ የሩስያ መንግሥት ሥልጣን ለቅቋል ብለው ሲያውጁ ከአጠገባቸው ፕሬዝደንት ፑቲን ነበሩ። ማሻሻያው ያስፈለገው የሕግ አውጭውን፣ ተርጓሚውንና አስፈፃሚውን አሠራር ለመናጥ ነው ሲሉም ተደምጠዋል። ጠቅላይ ሚኒስትራቸውን ያመሰገኑት ፑቲን እሳቸው በሚመሩት የብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤት በምክትልነት እንዲያገለግሏቸው ጠይቀዋል። አክለውም የሩስያ ቀረጥ አግልግሎት መሥሪያ ቤት ኃላፊ ሚካይል ሚሹስቲን የሜድቬዴቭን ቦታ ተክተው እንዲሰሩ ሾመዋል። የሩስያ ሕገ መንግሥት አንድ ፕሬዝድንት በተከታታይ ከሁለት ጊዜ በላይ እንዲያገለግል አይፈቅድም። ፑቲን ሁለት ጊዜ ካገለገሉ በኋላ ታማኝ አገልጋያቸው እንደሆኑ የሚነገርላቸው ሜድቬዴቭ ለአራት ዓመታት ፕሬዝደንት ሆነው አገልግለዋል። በወቅቱ ፑቲን ጠቅላይ ሚኒስትር ነበሩ፤ ሥልጣኑ የነበረው በእሳቸው እጅ ነው የሚሉ በርካቶች ቢሆኑም። ተቃዋሚዎች ፑቲን ያሰቡት ሕገ መንግሥታዊ ማሻሻያ የሥልጣን ጊዜያቸው እያበቃ ስለሆነ ያዘጋጁት ድራማ እንጂ ለውጥ ታስቦ አይደለም ይላሉ። በፈረንጆቹ ላይ ፕሬዝደንት ቦሪስ የልቲስንን ተክተው ሥልጣን የያዙት ፑቲን በፕሬዝደንትነትና በጠቅላይ ሚኒስትርነት ሃገራቸው ለ ዓመታት አገልግለዋል። መንበራቸውን እንዲሁ በቀላሉ ይለቃሉ ብሎ ማሰብ ዘበት ነው የሚሉ በርካቶች ናቸው።
የቀድሞው የፀረ ሽብር አዋጅ ታሳሪዎች ያልተመለሱ ጥያቄዎች
በፀረ ሽብር አዋጅ ተከሰው እስር ቤት የነበሩና ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ ወደ ሥልጣን ከመጡ በኋላ ክሳቸው ተሽሮ ነጻ የወጡ የሚደርሱ ግለሰቦች ተሰባስበው የአዲስ አበባ የፖለቲካ እስረኞች ማኅበር መስርተዋል። የቀድሞ እስረኞቹ ጥያቄዎች ምንድን ናቸው ቢቢሲ የአዲስ አበባ የፖለቲካ እስረኞች አስተባባሪ ኮሚቴ ዋና ጸሐፊ ዳሰማ ሶሪን አነጋግሯል።
ቻይና የዝሆን ጥርስ ንግድን አገደች
ጃንዩወሪ ማጋሪያ ምረጥ ቻይና የዓለም ትልቁ የዝሆን ጥርስ ገበያ ሆና ቆይታ በአዲሱ የፈረንጆች ዓመት በሃገሯ የሚከናወን ማንኛውም የዝሆን ጥርስ ግብይት ሕገ ወጥ እንደሆነ አውጃለች። ይህ ውሳኔዋም የቀሩትን ዝሆኖች ለመጠበቅ ለሚደረገው ጥረት አንድ ትልቅ እርምጃ ነው ተብሎ ተወድሷል። ዝሆኖችን ለመታደግ የሚሰሩ ተቆርቋሪዎች እንደሚያምኑት ሺህ ያህል የአፍሪካ ዝሆኖች በየዓመቱ በአዳኞች ይገደላሉ። የቻይና መንግሥታዊ መገናኛ ብዙሃን እንደዘገቡት ባለፈው ዓመት የዝሆን ጥርስ ዋጋ በ በመቶ ቅናሽ አሳይቷል። በተጨማሪም ወደቻይና ሲገባ የሚያዘው የዝሆን ጥርስ መጠን በ በመቶ መቀነሱም ዥንዋ ዘግቧል። የዝሆን ጥርስ ንግድን የማገዱ ውሳኔ ይፋ የሆነው በተጠናቀቀው የፈረንጆች ዓመት ሲሆን ተግባራዊ የሆነውም በዓመቱ የመጨረሻ ዕለት ጀምሮ ነው። ባለፈው ዓመት መጋቢት ወር ላይ በዝሆን ጥርስ ምርትና ንግድ ላይ ተሰማርተው የነበሩ ተቋማት የተዘጉ ሲሆን የተቀሩት ቱ ደግሞ እሁድ ዕለት እንደተዘጉ ተነግሯል። የዱር እንሰሳ ደህንነት ተከራካሪ የሆነው ተቋም ዜናውን ተከትሎ የዓለም ትልቁ የዝሆን ጥርስ ገበያ በሮች ሲዘጉ ማየት እጅጉን ያስደስታል ብሏል። የዝሆን ጥርስ ዋነኛ የመገበያያ ስፍራ እንደሆነች የሚነገርላት ሆንግ ኮንግን ግን አዲሱ ሕግ የማይመለከታት መሆኑ አሳሳቢ ነው ተብሏል። ነገር ግን ግዛቲቱ የእራሷን የዝሆን ጥርስ ንግድን የሚያግድ ሕግ ለማውጣት በሂደት ላይ መሆኗም ተነግሯል። ተያያዥ ርዕሶች
የዝሆን ግልገሎች ለዓለም ንግድ እንዳይቀርቡ ታገደ
ኦገስት በስዊዘርላንድ ጀኔቫ በተካሄደው ጉባዔ ከአፍሪካ የዝሆን ግልገሎችን በማደን ለእንስሳት ማቆያ እንዳይሸጡ የሚከለክለው ሕግ ፀድቋል። አደጋ ላይ በሚገኙ የእንስሳት ዝርያዎች ዓለም አቀፍ ንግድ ላይ የሚያተኩረው ጉባዔ ተሳታፊዎች በጉዳዩ ላይ ለቀናት ከተከራከሩበት በኋላ ሕጉን ለማጥበቅ ስምምነት ላይ መድረሳቸው ታውቋል። የባቢሌ ዝሆኖች ህልውና አደጋ ላይ ነው እግዱ በ አብላጫ ድምፅ ድጋፍ እና በ ተቃውሞ ካገኘ በኋላ እንዲፀድቅ ተወስኗል። ይሁን እንጂ ዝሆኖችን ወደ ውጭ በመላክ የምትታወቀው አፍሪካዊት ሃገር ዚምባብዌ ልክ እንደ አሜሪካ ሁሉ እግዱን ተቃውማለች። ዚምባብዌ እንቅስቃሴውን አጥበቃ በዘመቻ ስትቃወም የነበረ ሲሆን የአውሮፓ ሕብረትም በዓለም ላይ ያለውን የእንስሳት ዝርያ ስብጥር እንዳይኖረው ያደርጋል ሲሉ መጀመሪያ አካባቢ ተቃውመውት ነበር። ከሌሎች የአፍሪካ ሃገራት ዝሆን በብዛት የሚገኝባቸው ዚምባብዌና ቦትስዋና ተቀባይነት ላላቸውና ትክክለኛ ለሆኑ ተቀባይ ሃገራት ዝሆኖችን ወደ ውጭ ለመላክ ይፈቅዱ ነበር። በዓለም ላይ ከፍተኛ ቁጥር ዝሆኖች የሚገኙባት ቦትስዋና በዚህ በያዝነው ዓመት ዝሆኖችን ማደን የሚከለክለው ሕግ፣ ገበሬዎችንና ከዚህ በፊት በማደን ገቢ ያገኙ የነበሩ ግለሰቦችን እየጎዳ ነው በሚል መፍቀዷ ይታወሳል። ዚምባብዌ ከጎርጎሳውያኑ አቆጣጠር ጀምሮ ከ በላይ የሚሆኑ የዝሆን ግልገሎችን በመያዝ ለቻይና የእንስሳት ማቆያ መላካቸውን ሁዩማን ሶሳይቲ ኢንተርናሽናል አስታውቋል። በመሆኑም ትናንት የተላለፈው ውሳኔ የዝሆን ንግድን ቁጥጥር እንዲጠብቅ ያደርጋል ተብሏል። በአዲሱ ሕግ መሠረት ዝሆኖች ከዱር ተይዘው በእንክብካቤ በሚቆዩበት በየትኛውም የዓለማችን አካባቢ መቆየት የሚችሉ ሲሆን ይህ ግን የሚቻለው በከተማዋ የኮሚቴ አባላት ሲፀድቅ ይሆናል። ከአዕዋፍ እስከ አንበሳ ያሉ እንስሳት በግለሰቦች እጅ ለስቃይና ለጉዳት እየተዳረጉ ነው። ይሁን እንጅ የአውሮፓ ህብረት በልዩ ሁኔታ መላክ እንደሚቻልና በእንስሳት ማቆያ ያሉ ዝሆኖችን ማዛወር እንደሚቻል ሕጉ የተወሰነ መሻሻል ከተደረገበት በኋላ ሃሳቡን ቀይሯል። ይህ ማለት አንድም ዝሆን ከዱር ተይዞ በውጭ አገር ለእንስሳት ምቹ በሆኑ ማቆያዎች አይገቡም ማለት አይደለም ሲሉ የቦርን ፍሪ ፋውንዴሽን ፕሬዚደንት ዊል ትሬቨርስ ተናግረዋል። አክለውም እግዱ በተለይ በወደ ሩቅ ምስራቅ በጅምላ ያለ አግባብ የሚላኩ ዝሆኖችን ለመቆጣጠር ሕጉን ማጥበቅ አስፈላጊ እንደሆነም ገልፀዋል። ተያያዥ ርዕሶች
የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ሞክግዌትሲ ማሲሲ ባለፈው ዓመት ሰኔ ወር ላይ ነበር በቀድሞው ፕሬዝዳንት የተጣለውን እገዳ ለመመርመር ኮሚቴ ያዋቀሩት።
በዚህ ዓመት የካቲት ወር ላይም ኮሚቴው እገዳው እንዲነሳ የሚል ምክረ ሀሳብ ማቅረቡ ተሰምቶ ነበር። የዝሆኖቹ ቁጥር መጨመር፣ በዝሆኖቹና በሰው ልጆች መካከል የሚፈጠር ግጭት መበራከት፣ ዝሆኖቹ በሰውና በእንስሳት ላይ የሚያደርሱት ጥቃት መጨመር ወደ እዚህ ውሳኔ እንደገፋቸው በመግለጫቸው ላይ የገለፁት የአካባቢ፣ የተፈጥሮ ኃብት እንክብካቤ እንዲሁም የቱሪዝም ሚኒስትሩ ናቸው። አክለውም አደን ሲፈቀድ ሕግን በተከተለ እና ስርዓት ባለው መልኩ እንዲሆን እናደርጋለን ብለዋል። የክልከላው መነሳት እርምጃው ፖለቲካዊ ነው ብለው በማያምኑ የአካባቢ ጥበቃ ተሟጋቾች ዘንድ ብስጭትን ይፈጥራል። ሀገሪቱም በዓለም አቀፍ ደረጃ ያላትን የአካባቢ ጥበቃ ስም የሚያጠለሽ ሲሆን ለሀገሪቱ ከዳይመንድ ማዕድን ማውጣት ቀጥሎ ሁለተኛ የገቢ ምንጭ የሆነው የቱሪዝም ሀብቷንም ይጎዳል ተብሏል። ቢቢሲ ማስተባበያ
የቦይንግ ማክስ አውሮፕላኖች ችግር ከ ዓመታት በፊት ተደርሶበት እንደነበር ይፋ ሆነ
ኦክተውበር ማጋሪያ ምረጥ ከወራት በፊት ኢትዮጵያ ውስጥ ወድቆ ለበርካታ ሰዎች ህይወት መጥፋት ምክንያት በሆነው የቦይንግ ማክስ አውሮፕላኖች ላይ ስላለው የበረራ ደህንነት መቆጣጠሪያ ሥርዓት ችግር በተመለከተ ሠራተኞች መልዕክት መለዋወጣቸው ይፋ ሆነ። ከሦስት ዓመት በፊት አውሮፕላኑ ለበረራ ብቁ ስለመሆኑ ማረጋገጫ በተሰጠበት ወቅት ነው የቦይንግ ሠራተኞች የአውሮፕላኑን የበረራ ደህንነት የሚቆጣጠረውን አውቶማቲክ ሥርዓትን በተመለከተ አጭር የጽሁፍ መልዕክት መለዋወጣቸው የተነገረው። ለአሜሪካ ሕግ አውጪዎች በቀረበ ሰነድ ላይ እንደተመለከተው፤ አንድ አብራሪ በሙከራ በረራ ወቅት ያልተጠበቀ ችግር ገጥሞት እንደነበረ በጽሁፍ አስፍሯል። አብራሪው ሳያውቀው የአውሮፕላኑን ደህንነት ለሚቆጣጠሩት ባለሙያዎች መዋሸቱን ገልጿል። ቦይንግ ለሟች ቤተሰቦች ካሳ ሊከፍል ነው ይህን አብራሪው አስተላልፎታል የተባለውን መልዕክት ተከትሎ ሌላ የቦይንግ ሠራተኛ በጽሁፍ ባሰፈረው ምላሽ ውሸት አልነበረም፤ ስለጉዳዩ ማንም አልነገረንም ነበር ብሏል። ትናንት አርብ ይህ ሪፖርት ይፋ መሆኑን ተከትሎ ቦይንግ በአክስዮን ገበያ ላይ ያለው ዋጋ ከአምስት በመቶ በላይ መውረዱ ተገልጿል። ይህ የአውሮፕላኑ የደህንነት መቆጣጠሪያ ሥርዓት ባጋጠመው ችግር ሳቢያ በኢትዮጵያ አየር መንገድና በኢንዶኔዢያ አውሮፕላኖች ላይ አደጋን አስከትሎ ለ ሰዎች ሞት ምክንያት ሆኗል። የአሜሪካ የአየር ትራንስፖርት አስተዳደር አሁን ይፋ ስለተደረገውና በሰራተኞች መካከል የተደረገው የመልዕክት ልውውጥ መረጃ እንዳሳሰበው ገልጿል። ጨምሮም ቦይንግ ስለምን ይህንን መረጃ የያዘውን ሰነድ ቀድሞ እንዳላቀረበ በአስቸኳይ ማብራሪያ እንዲሰጥ አዟል። ቦይንግ ይህንን ሰነድ ያቀረበው አደጋውን በተመለከተ ለህግ አውጪዎች በዚህ ወር ውስጥ ከሚሰጠው ማብራሪያ ቀደሞ ነው። የቦይንግ ዋና ሥራ አስፈጻሚ የሆኑት ዴኒስ ሙሊንበርግ ከህግ አውጪዎቹ ፊት ቀርበው ምስክርነት ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል። ሙሊንበርግ ምንም እንኳን በኃላፊነታቸው የሚቆዩ ቢሆንም በቅርቡ ከቦይንግ ኩባንያ ሊቀመንበርነታቸው ተነስተዋል። ቦይንግ እንደሚለው ሁለት አደጋዎች ካጋጠሙት በኋላ በዓለም ዙሪያ ከበረራ ውጪ እንዲሆን የተደረገውን ማክስ ላይ ለሚደረገው ምርመራ ትብብር እያደረገ ነው። ሙሉ ቤተሰቤን በኢትዮጵያው አውሮፕላን አደጋ አጥቻለሁ ኩባንያው በቅርቡ እንዳሳወቀው የሚያመርታቸውን አውሮፕላኖችና አገልግሎታቸውን በተመለከተ ምርትና ሥራቸውን በበላይነት የሚቆጣጠር ቋሚ ኮሚቴ ማቋቋሙን ገልጾ ነበር። በኢትዮጵያውን በኢንዶኔዢያ የአውሮፕላን አደጋዎች ላይ ምርመራ ያደረጉት ባለሙያዎች ለአደጋዎቹ ዋነኛ ምክንያት ሊሆን ይችላል በሚል ትኩረት ያደረጉት አውሮፕላኑ በቀላሉ እንዲበር ያደርገዋል ተብሎ የተሰራለት የበረራ ደህንት መቆጣጠሪያ ሥርዓት ኤምካስ ላይ ነው። ምርመራዎች እንዳመለከቱት ይህ የመቆጣጠሪያ ሥርዓት በአግባቡ ካለመስራቱ በተጨማሪ አውሮፕላኖቹን ከአብራሪዎቹ ቁጥጥር ውጪ እንዲሆኑ በማድረግ አደጋዎቹን አስከትለዋል። ቦይንግ በበኩሉ አደጋዎቹ ያጋጠሙት በመቆጣጣሪያ ሥርዓቱ በተጫነው የተሳሳተ መረጃ የተነሳ መሆኑን ጠቅሶ ይህንንም ለማስተካከል ክለሳ እያደረገ መሆኑን ገልጿል። ቦይንግ አገኘሁት ያለው ይህ አዲስ የመልዕክት ልውውጥ ከሦስት ዓመታት በፊት የተደረገ ሲሆን፤ መረጃውን ያሰፈረው አብራሪም በአሁኑ ጊዜ በኩባንያው ውስጥ እንደማይሰራ ተገልጿል። ተያያዥ ርዕሶች
ሩሲያ ውስጥ ያለ ግድብ ተደርምሶ ማዕድን አውጪዎች ሞቱ
ጥቅምት አደጋው የደረሰበት አካባቢ በጎርፍ ተጥለቅልቆ ሩሲያ ውስጥ በምትገኘው ሳይቤሪያ በሚገኝ የወርቅ ማዕድን ማውጫ አካባቢ ያለ ግድብ ተደርምሶ ቢያንስ ሰዎች ሲሞቱ ሌሎች ሰዎች ደግሞ የደረሱበት አልታወቀም ተባለ። ክራስኖያርክ በተባለው ክልል ውስጥ በሴይባ ወንዝ ላይ የተገነባው ግድብ ዛሬ ቅዳሜ በአካባቢው የጣለን ከባድ ዝናብ ተከትሎ በመደርመሱ የማዕድን ማውጫው ሠራተኞች የሚኖሩባቸውን ቤቶች በማጥለቅለቁ ነው አደጋው የደረሰው። የሩሲያ ጤና ሚኒስቴር እንዳለው ከሞቱትና እየተፈለጉ ካሉት ሰዎች በተጨማሪ የማዕድን ማውጫው ሠራተኞች ለህክምና ወደ ሆስፒታል ተወስደዋል። ከመካከላቸውም ሦስቱ የከፋ ጉዳት እንደደረሰባቸው ተገልጿል። ግድቡ የግንባታ ደንቦችን አላከበረም በመባሉ የወንጀል ምርመራ እየተደረገ ነው። የአገሪቱ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን የአደጋውን ምክንያት ለማወቅ ለሚደረገው ምርመራ ባለስልጣኖቻቸው አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርጉ ትዕዛዝ ማስተላለፋቸውን የፕሬዝዳንቱ ቃል አቀባይ ተናግረዋል። ኢንትርፋክስ የተባለው የዜና ወኪል እንደዘገበው የማዕድን ማውጫው ሠራተኞች የሚኖሩባቸው በርካታ ትናንሽ ቤቶች በከባዱ የጎርፍ ውሃ ተጠርገው ተወስደዋል። የማዕድን ማውጫው የሚገኘው ከሩሲያ ዋና ከተማ ሞስኮ ከ ሺህ ኪሎ ሜትሮች በስተ ምሥራቅ ርቆ በሚገኝ ስፍራ መሆኑም ተነግሯል። አደጋው ከደረሰ በኋላ በርካታ ቁጥር ያላቸው የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች ጉዳት የደረሰባቸውን ሰዎች ለመርዳት የተሰማሩ ሲሆን በተጨማሪም ደብዛቸው የጠፋውን ሰዎችንም በመፈለግ ላይ ናቸው። የሴይባ ወንዝና በአካባቢው ያለው የጎርፍ ውሃ መጠን እየጨመረ በመምጣቱ ምክንያት ከማዕድን ማውጫ አቅራቢያ በሚገኝ መንደር ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች ከአካባቢው እንዲወጡ እየተደረገ መሆኑን የሩሲያ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። ከዚህ ዜና በተጨማሪ
የቅማንት የማንነትና የራስ አስተዳደር ጥያቄ ከየት ወደ የት
ኦክተውበር ማጋሪያ ምረጥ የቅማንት የማንነት ጥያቄ በተነሳባቸው አካባቢዎች በተለያዩ ጊዜያት ግጭቶች እየተፈጠሩ የሰው ህይወት ጠፍቷል፤ ንብረት ወድሟል። በርካታ ቁጥር ያላቸው ሰዎችም ከመኖሪያ ቤታቸው ሲፈናቀሉ ቆይተዋል። ለመሆኑ የዚህ ሁሉ ምክንያት ምንድን ነው የቅማንት የማንነት ጥያቄስ በምን መልኩ ተጠይቆ ምን አይነት ምላሽ ተሰጠው የቅማንት የማንነት ጥያቄ ከውልደት አሁን እስካለበት ደረጃ ድረስ ጉዞው ምን ይመስላል ቢቢሲ ጉዳዩን በዝርዝር ተመልክቶታል። ቅድመ ቅማንት የማንነትና አስተዳደር ጥያቄ የቅማንት ህዝብ በቀድሞው የጎንደር ክፍለ ሃገር፤ በአሁኑ ማዕከላዊ ጎንደር ዞን በሚገኙ የተወሰኑ ወረዳዎች የሚኖር ህዝብ ነው። በተለይ በጎንደር ከተማ ዙሪያ በሚገኙ ላይ አርማጭሆ፣ ወገራና ጭልጋ ወረዳዎች ማህበረሰቡ በብዛት የሚኖርባቸው አካባቢዎች ናቸው። ከ ዓ ም በፊት በነበረው የመንግሥት አወቃቀርም የብሔር ማንነትን መሰረት ያደረገ ስላልነበር ብሔረሰቡ የጎንደር ክፍለ ሃገር አካል ሆኖ ከአማራው ህዝብ ጋር በብዛት ተቀላቅሎ ይኖር ነበር። የራሱ የተካለለ ልዩ አካባቢና አስተዳደርም እንዳልነበረውም መረጃዎች ያሳያሉ። የቅማንት የማንነት ጥያቄ መነሻ ኢህአዴግ ስልጣን ከተቆጣጠረ በኋላ በኢትዮጵያ ቋንቋን መሰረት ያደረገ የብሔር ፌደራሊዝምን መሰረት ያደረገና ስልጣን በፌደራልና በክልሎች የተከፋፈለ ሥርዓት ተመሰረተ። የቅማንት የማንነት ጥያቄ ይህ ሥርዓት ከሰፈነ በኋላ በ ዓ ም መነሳቱን በቅማንት ማንነት ዙሪያ ጥናት ያካሄዱት አቶ ቹቹ አለባቸው ያስረዳሉ። የቅማንት ብሔረሰብ ጥያቄ ከየት ወደየት ከማንነት ጥያቄ እስከ የራስ አስተዳደር ጥያቄና የፖለቲካ ፓርቲ ምስረታ በሚለው ፅሁፋቸው፤ ጥያቄው በቅማንት ህዝብም ተቀባይነት ያልነበረው ሲሆን ለግለሰቦቹ የተሰጣቸውም ምላሽ የያዛችሁት ሐሳብ ከአማራ ወንድሞቻችን ጋር የሚያጋጭ ነው፣ ስለሆነም አንቀበላችሁም የሚል እንደነበረ ጥናቱ ያሳያል። በጎንደር የተለያዩ ዞኖች በተከሰተ ግጭት ሺህ ሰዎች ተፈናቀሉ በሕዝቡ ተቀባይነት ካጣ በኋላም ጥያቄው ለአስራ አምስት ዓመታት ያህል ተዳፍኖ ሳይነሳ መቆየቱን ይኸው ጥናት ያመላክታል። የ ዓ ም የሕዝብና ቤት ቆጠራ ግን አዲስ ክስተት ይዞ መጣ። የማንነት ጥያቄ ባይነሳም በ ዓ ም በተካሄደው ሕዝብና ቤት ቆጠራ የቅማንት ሕዝብ በራሱ ተለይቶ ቅማንት በሚል መለያ ኮድ እንደተቆጠረ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዋና የህግ አማካሪ አቶ መርሃ ጽድቅ መኮንን ይናገራሉ። ነገር ግን ለብቻው ተለይቶ መቆጠሩ አልቀጠለም፤ በቀጣዩ በተካሄደው ሕዝብና ቤት ቆጠራ ግን ኮዱ ተሰርዞ አማራ ወይም ሌላ በሚል የቅማንት ሕዝብ እንዲቆጠር መደረጉን ያስረዳሉ። ይህ ሁኔታ ቅሬታን እንደፈጠረና ጥያቄዎችም መቅረብ መጀመራቸውን የሚናገሩት አቶ መርሃ ጽድቅ፣ በተለይም ከ ዓ ም ጀምሮ የተለያዩ ግለሰቦች ማመልከቻ ይዘው ወደ ክልሉ መንግሥት መምጣት መጀመራቸውን ያስታውሳሉ። የቅማንት የማንነት ጥያቄ ኮሚቴ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ይርሳው ቸኮልም በአቶ መርሃ ጽድቅ ሃሳብ ይስማማሉ። ቅማንት ሆነን ሳለ ለምን ሌላ ተባልን በሚል ተሰባስበን ጥያቄውን ጀመርን ይላሉ። የቅማንትን ሕዝብ አምስት በመቶ ድምጽ ማለትም ድምጽ ሰብስበው ማንነታቸው እንዲታወቅ ለክልሉ መንግሥት ጥያቄያቸውን ማቅረባቸውን አቶ ይርሳው ይጠቅሳሉ። የቅማንት የማንነት ጥያቄ በተደራጀ መልኩ መቅረብ የጀመረው በዚህ ወቅት ነው። የቅማንት የማንነትና የራስ አስተዳደር ማንነት ጥያቄ ምላሽ የቅማንት የማንነትና የራስ አስተዳደር ጥያቄንም ለመመለስ የክልሉ የርዕሰ መስተዳድር ምክር ቤት ጥናት እንዲጠና አድርጓል። የአቶ ቹቹ ጽሁፍ እንደሚያመለክተው በክልሉ መንግሥት አነሳሽነት በተቋቋሙ ኮሚቴዎች አማካኝነት ሁለት ጥናቶች በ እና ዓ ም ተደርገዋል። ጥናቱም ሞዴል አድርጎ የወሰደው የአርጎባ ልዩ ወረዳ የማንነት ጥያቄ የተመለሰበትን መንገድ እንደነበር አቶ መርሃ ጽድቅ ያወሳሉ። የአርጎባ ጥያቄ በ ዓ ም ልዩ ወረዳ መሆን ይችላሉ በሚል ምላሽ ተሰጥቶታል። የተጠናው ጥናትም በ ዓ ም ለክልሉ ምክር ቤት መቅረቡንም የሚናገሩት አቶ መርሃ ጽድቅ፤ ይህም በሰነድ ደረጃ የአማራ ክልል ምክር ቤት የቅማንት የማንነት ጥያቄን አስመልክቶ ውይይት ሲያደርግ ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑ ነው። የቅማንትን ሕዝብ እንወክላለን የሚሉ ፅንፈኞች ከሌሎች ጋር በቅንጅት እየሰሩ ነው ጄኔራል አሳምነው በሕገ መንግሥቱ መሰረት የማንነትና የራስ አስተዳደርን ጥያቄ ለመመለስ አምስት መስፈርቶች አሉ፤ እነዚህም የጋራ ባህል መኖር፣ የጋራ መግባቢያ ቋንቋ መኖር፣ የአካባቢው ኩታ ገጠም መሆን፣ በሥነ ልቦናና ማንነት ለጠየቀው ብሔረሰብ አባል ነኝ ብሎ ማመንና የተዛመደ ህልውና መኖር ሲሆን፤ የአርጎባ ጥያቄም ምላሽ የተሰጠው እነዚህ መስፈርቶች በማሟላቱ እንደሆነም አቶ መርሃ ጽድቅ ያስረዳሉ። ጥናቱንም መሰረት በማድረግ የቅማንት ጥያቄ ማህበረሰቡ እንደ ማህበረስብ መኖሩ ተረጋግጦ እውቅና ቢሰጠውም የራሱን የውስጥ አስተዳደርና ነጻነት ለመመስረት ግን ሕገ መንግሥታዊ መስፈርቶችን አያሟላም ተብሎ አደረጃጀቱ በክልሉ ምክር ቤት ውድቅ መደረጉን ይናገራሉ። የማንነት ጥያቄው እንዲመለስ ሞዴል ከተደረገው የአርጎባ ልዩ ወረዳ ጋር ተቀራራቢነት የሌለው፤ የጋራ መግባቢያ ቋንቋ የሌለው በመሆኑና ኩታ ገጠም አሰፋፈር ስላልነበረው ጥያቄውን ለመመለስ የሚያስችል ሕገ መንግሥታዊ አካሄድ እንዳልነበረ አቶ መርሃ ጽድቅ ያስረዳሉ። በምክር ቤቱ ሰፊ ውይይት የተደረገበት ይህ ውሳኔም የምክር ቤት አባላት የብሔረሰብ አስተዳደሩን መቋቋም ሲቃወሙ፣ ሰባት ደግፈውና የምክር ቤቱ አባላት ድምጻቸውን በማቀባቸው ነው ውድቅ የተደረገው ይላሉ። የአማራ ልዩ ኃይል ከማዕከላዊ ጎንደር አይወጣም የክልሉ የሰላምና ሕዝብ ደህንነት ቢሮ ኃላፊ ይህ አካባቢ ያንተ ነው ራስህን አስተዳድር ለማለት የሚያስችል ሁኔታ አልነበረም። የራስ አሰተዳደሩን ለመወሰን የሚያስችል ሕገ መንግሥታዊ መስፈርቶች አልተሟሉም በማለት የራስ አስተዳደር ጥያቄው በክልሉ ምክር ቤት ውድቅ ተደርጓል ይላሉ አቶ መርሃ ጽድቅ። ከአማርኛ ጋር እየተቀላቀለና በተወሰኑ አዛውንቶች ብቻ የሚነገረውን የቅማንት ቋንቋ እንዳይጠፋ ለማበልፀግም ጥረት መደረግ እንዳለበት ምክር ቤቱ የራስ አስተዳደር ጥያቄውን ውድ ባደረገበተወ ወቅት ሃሳብ አቅርቦ እንደነበር አቶ መርሃጽድቅ ያስረዳሉ። ጎንደር፡ የአስቸኳይ ጊዜ ወይስ የመሣሪያ እገዳ አቶ ይርሳው በበኩላቸው ሕገ መንግሥቱ የሚጠይቀውን መስፈርት ማሟላታቸውን ይገልፃሉ። መግባቢያቸው አማርኛ ቋንቋ ቢሆንም የቅማንትኛ ቋንቋ ያልሞተ መሆኑን፣ ወጥ የሆነ የሕዝብ አሰፋፈር፣ በሥነ ልቦና ቅማንት ነኝ ብሎ የሚያምን ህዝብ መኖሩንና ከአማራው ጋር የተቀላቀለ ቢሆንም የራሳቸው ባህል እንዳላቸውም ይገልጻሉ። በዚህም መሰረት ውሳኔው የማንነት ጥያቄ ያነሱትን የኮሚቴ አባላት ያስደሰተ አልነበረም። ውሳኔውን ባለመቀበልም ለፌደሬሽን ምክር ቤት አቤቱታ ማቅረባቸውን አቶ ይርሳው ይናገራሉ። የፌደሬሽን ምክር ቤት ደግሞ ጉዳዩን የክልሉ መንግሥት ድጋሚ እንዲያየው መልሶ የላከው ሲሆን ከሁለት ዓመታት በኋላ ግን በ ዓ ም የቅማንት የማንነትና የራስ አስተዳደር መፈቀዱን አቶ ይርሳው ለቢቢሲ ገልፀዋል። የቅማንት የማንነትና የራስ አስተዳደር ጥያቄ እንዴት ተመለሰ ክልሉ በ ባደረገው ጥናት የቅማንት ማህበረሰብ የማንነትና የራሱን አስተዳደር ለመመስረት ሕገ መንግሥታዊ መስፈርቶችን አላሟላም ከተባለ ከሁለት ዓመት በኋላ ጥያቄው እንዴት ተቀባይነት አገኘ በምን መስፈርት የራስ አስተዳደሩ ተመለሰ ለአቶ መርሃጽድቅ የቀረበ ጥያቄ ነው። እንደ አቶ መርሃ ጽድቅ ከሆነ በተለይ በአካባቢው ግጭቶች እየተበራከቱና ተቋማት እየተዘጉ በመምጣታቸው፤ በ ዓ ም የክልሉ የርዕሰ መስተዳድር ምክር ቤት ጉዳዩ እንደገና ይታይልኝ በማለቱ ጥናቱ ለሁለተኛ ጊዜ ለክልሉ ምክር ቤት መቅረቡን ያስታውሳሉ። ችግርን ከመፍታት ይልቅ ጩኸት ማፈን ነው የሚቀናቸው ምክር ቤቱ የቅማንትን የማንነት ጥያቄ ለሁለተኛ ጊዜ ለማየት እንደተገደደ የሚያስረዱት አቶ መርሃ ጽድቅ ይህም ፖለቲካዊ ጫና ነበረበት ይላሉ። አቶ መርሃ ጽድቅ ፖለቲካዊ ጫና የሚሉትም የ ቱ ዓ ም የምክር ቤት ውሳኔ በቅማንት የማንነት ኮሚቴ ቁጣን ከመቀስቀሱ ጋር የተያያዘ እንደሆነም ያስረዳሉ። ውሳኔው በኮሚቴው ዘንድ ቁጣን ስለቀሰቀሰ እና የሰው ህይወትም እየጠፋ ሲመጣ ፖለቲከኞቹ በተለይ በፌደራል ደረጃ የነበሩ የብአዴን ካድሬዎች ከፍተኛ ጫና በማሳደራቸው እጃቸውን አስረዝመው ቅማንት ይኖርባቸዋል የሚባሉትን አካባቢዎች አገናኝታችሁ ወስኑላቸው፤ ሕዝባችን እስከሆኑ ድረስ የትም አይሄዱም የሚል ትዕዛዝ እንደተሰጠ አቶ መርሃ ጽድቅ ይናገራሉ። በዚሁ መሰረትም ከላይ አርማጭሆ ወረዳ እና ከጭልጋ ወረዳ በድምሩ ቀበሌዎችን በቅማንት የራስ አስተዳደር፤ በልዩ ወረዳ እንዲዋቀሩ ተወስኗል። ይህም ከሕገ መንግሥቱ መስፈርት ውጪ ብዙ ርቀት ተሂዶ የተወሰነ መሆኑን አቶ መርሃ ጽድቅ ይናገራሉ። ነገር ግን ውሳኔው ግጭቱን አላስቆመውም። የቅማንት የማንነት ጥያቄና የአስተዳደር ቅሬታ ክልሉ የቅማንትን አስተዳደር አርባ ሁለት ቀበሌዎች በልዩ ወረዳ እንዲዋቀር መወሰኑ በማንነት ኮሚቴው ዘንድ ተቀባይነት እንዳላገኘ የሚናገሩት አቶ ይርሳው ናቸው። ሕዝቡን ባላሳተፈ መልኩ፤ ቀበሌዎችን ሰጥቻችኋለሁ ነው የተባልነው ይላሉ። አርባ ሁለት ቀበሌዎች ለቅማንት የራስ አስተዳደር መወሰኑንም በመቃወምና በቂ አይደለም በሚልም በጭልጋ በ ዓ ም ሰላማዊ ሰልፍ ተካሄደ። እነዚህ ቀበሌዎች በውይይትና በፖለቲካዊ ውሳኔ የተካለሉ እንጂ ሕዝበ ውሳኔ የተካሄደባቸው አልነበሩም ብለውም አቶ ይርሳው ያምናሉ። የአቶ ቹቹ ፅሁፍም እንደሚያስረዳው በወቅቱ በቅማንት ወረዳዎች የመንግሥት ሥራ ቆሞ ስለነበር፤ ሥራ ለማስጀመር፤ እንዲሁም ውሳኔውን ለማስፈጸም፤ የፀጥታ ኃይሎች ወደ ሮቢት በሚንቀሳቀሱበት ወቅት ማውራ ከተባለ አካባቢ ጥቅምት ዓ ም ላይ ከሕዝብ ጋር ግጭት ተደርጎ የሰው ህይወት አልፏል። ግጭቱም በህዳር ዓ ም በሽንፋ አካባቢ ቀጠለ። ህገወጥ የሰዎች ዝውውር ረቂቅ ህግ የሞት ቅጣት ተካቶበታል ውሳኔውንም ባለመቀበል የማንነት ጥያቄ አቅራቢዎቹ በድጋሜ ቅሬታቸውን ለፌደሬሽን ምክር ቤት ቢያቀርቡም መልሱ ተመሳሳይ ነበር። የክልሉ መንግሥት እንደጀመረው ይጨርሰው የሚል ምላሽ እንደተሰጠ ይነገራል። ለሦስት ዓመታት ጉዳዩ በውዝግብ ከቀጠለ በኋላ ዓ ም ላይ ጥያቄው እንዴት መፈታት አለበት በሚል ከክልሉ መንግሥት ጋር መስማማታቸውን አቶ ይርሳው ይናገራሉ። በዚህም መሰረት ከቅማንት የማንነት ጥያቄና ከአማራ ክልል መንግሥት የተውጣጣ ጥምር ኮሚቴ ተዋቅሮ ጥናት ካካሄደ በኋላ ተጨማሪ ቀበሌዎች ወደ ቅማንት ይካለሉ ተብለው ወደ ቅማንት የራስ አስተዳደር መካለላቸውንም አቶ ይርሳው ይጠቅሳሉ። በተመሳሳይም እነዚህ ቀበሌዎች ሲካለሉ ሕዝበ ውሳኔ አለመካሄዱንና እንዲሁ በውይይትና በፖለቲካ ውሳኔ የተካለሉ መሆናቸውንም አቶ መርሃ ጽድቅም ሆኑ አቶ ይርሳው ይስማማሉ። ቀበሌዎቹን ወደ ቅማንት ራስ አስተዳደር የማካለል ውሳኔ ጥምር ኮሚቴው በማዕከላዊና በምዕራብ ጎንደር በመዘዋወር የተለያዩ ቀበሌ ነዋሪዎችን አወያይቷል። ከቀደሙት ውሳኔዎችም በተለየ መልኩ በ ዓ ም ቀበሌዎች በሕዝበ ውሳኔ እንወስናለን የሚል ምላሽ መስጠታቸውንም አቶ ይርሳው ይናገራሉ። ምንም እንኳን ቀበሌዎቹ የራሳቸውን አስተዳደርን በራሳቸው ድምፅ ለመወሰን ቢያስቡም አራት የጭልጋ ቀበሌዎች ላይ ሁከት በመፈጠሩ ምርጫ ሳይካሄድ መቅረቱን አቶ ይርሳው ይገልጻሉ። ከአስራ ሁለቱ በስምንቱ ቀበሌዎች ሕዝበ ውሳኔ ተካሂዶ ሰባቱ ወደ ነባሩ አስተዳደር እንዲካለሉ ሲወስኑ፤ አንዷ ቀበሌ ወደ ቅማንት የራስ አስተዳደር ለመካለል መወሰኗን ይናገራሉ። በቅማንት የራስ አስተዳደር ጥያቄ ሂደት ይህች አንዲት ቀበሌ የራስ አስተዳደሩን በሕዝበ ውሳኔ የተቀላቀለች ብቸኛዋ ቀበሌ ነች። በተፈጠረ ሁከት ምክንያት ሕዝበ ውሳኔ ያልተካሄደባቸው አራቱ ቀበሌዎች በጥምር ኮሚቴው አማካኝነት ከቀበሌው ነዋሪዎች ጋር ከተወያዩ በኋላ ሁለት ወደ ቅማንት የራስ አስተዳደር ሁለቱ ደግሞ ወደ ነባሩ አስተዳደር እንዲካለሉ መደረጋቸውን አቶ ይርሳው ይገልጻሉ። በዚህ ሁኔታ በውይይት፤ በፖለቲካዊ ውሳኔና በሕዝበ ውሳኔ የተካተቱት የቅማንት የራስ አስተዳደር ቀበሌዎች ቁጥር ከ በላይ መሆኑን የሚናገሩት አቶ ይርሳው ቀጣዩ ሥራ የራስ አስተዳደሩን መመስረት ነበር። የቅማንት የራስ አስተዳደርና የሦስት ቀበሌዎች ጥያቄ ቀበሌዎቹ ከተካለሉ በኋላ የራስ አስተዳደሩን ለመመስረት የሚያስችል መነሻ መዋቅር ኮሚቴው እንዲያዘጋጅ በክልሉ መንግሥት በተጠየቁት መሰረት ሌሎች ሦስት የመተማ ቀበሌዎች ሙሉ በሙሉ ቅማንት ናቸው በሚል እሳቤ በማካተት ቀበሌዎች፤ በስድስት ወረዳ ለማድረግ ወስነው ለክልሉ መንግሥት ምክረ ሃሳብ እንዳቀረቡ አቶ ይርሳው ያስረዳሉ። የኮሚቴውን ምክረ ሃሳብ በ ዓ ም የተመለከተው የክልሉ ምክር ቤት በከፍተኛ ጫና ውስጥ ሆኖ የማንነት ጥያቄው በ ቀበሌዎች እንዲዋቀርና ከልዩ ወረዳነት ወደ ብሔረሰብ አስተዳደርነት እንዲያድግ መወሰኑን አቶ መርሃ ጽድቅ ይጠቅሳሉ። ይሁን እንጂ ኮሚቴው ጥያቄያቸው ሙሉ በሙሉ ምላሽ እንዳላገኘና በቅማንት አስተዳደር ስር መካተት የሚገባቸው ቀበሌዎች መቃ፣ ጉባኤ ጀጀቢትና ሌንጫ በቅማንት ራስ አስተዳደር ስላልተካተቱ ቀበሌዎቹ በቅማንት ራስ አስተዳደር ካልተካለሉ ውሳኔውን እንደማይቀበለው ይፋ ማድረጉን የአቶ ቹቹ ጽሑፍ ያስረዳል። አቶ ይርሳውም በበኩላቸው በአቶ ቹቹ ፅሁፍ ይስማማሉ አራቱን ወረዳ ብንቀበለውም ሦስቱ ቀበሌዎች ወደ እኛ መካተት አለባቸው ብለን ስላሰብን በህግ ሊፈቱ ይገባል ብለን ቅሬታችንን ለፌደሬሽን ምክር ቤት ላክን ይላሉ። የፌደሬሽን ምክር ቤት ምላሽ ቅሬታው የደረሰው የፌደሬሽን ምክር ቤትም ጥናት አድርጎ ምላሽ እንደሰጠ የፌደሬሽን ምክር ቤት የሕገ መንግሥት ትርጉምና የማንነት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ጸሃፊ አቶ ወርቁ አዳሙ ለቢቢሲ ገልፀዋል። እሳቸው እንደሚሉት ሦስት ባለሞያዎች ከፌደሬሽን ምክር ቤት ወደ ስፍራው ተልከው፤ የተነሳውን ቅሬታ በአካል ቦታው ድረስ በመጓዝ ጥናት ማካሄዳቸውን ያስረዳሉ። ሕገ መንግሥቱ ጋር ስለማይጣጣምና ቅሬታ የቀረበባቸው ቀበሌዎች ኩታ ገጠም ስላልሆኑ፤ የክልሉ መንግሥት የሰጠው ውሳኔ ትክክል ነው የሚል ምላሽም መስጠታቸውን ያስታውሳሉ። እንደ ፌደሬሽን ምክር ቤት አሰራር ደግሞ እንደዚህ አይነት ቅሬታዎች ሲፈጠሩ በተለይ ቀበሌን ከቀበሌ፤ ወረዳን ከወረዳና ዞንን ከዞን የማዋቀር ውሳኔ መስጠት ያለበት ቅሬታ የተነሳበት ክልል ራሱ መሆኑን የሚናገሩት አቶ ወርቁ፤ ቅሬታው አስተዳደራዊ ጉዳይ በመሆኑ መመለስ ያለበት አስተዳደራዊ በሆነ መልኩ ነው ይላሉ። ጃፓን ያለ መሬትና ያለ አርሶ አደሮች የፈጠረችው የግብርና አብዮት አክለውም ዋናው ነገር ማንነትን እውቅና መስጠት ነው፤ ይህም ምላሽ አግኝቷል ያሉት አቶ ወርቁ በክልሉ ውስጥ የሚፈጠርን የአስተዳደር ወሰን በተመለከተ ክልሉ ራሱ እንዲፈታ ነው ህጉ የሚያዘው ብለዋል። ኮሚቴው ግን የፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔን አለመቀበሉን የሚገልፁት አቶ ይርሳው ለዚህ የሚያቀርቡት ምክንያት ጥናቱን ለማከናውን የተላኩት ሰዎች ከተለያዩ ብሔር ብሔረሰቦች የተውጣጡ ስላልነበሩ፤ ገና ከመመለሳቸው በፊት ምን ይዘው እንደሚመለሱ ስለምናውቅ እነዚህ ሰዎች ይዘውት የሚመለሱት ውጤት ምንም ይሁን ምን አንቀበልም ብለን ለሚመለከታቸው አካላት ደብዳቤ ጽፈናል ይላሉ። ኮሜቴው ጥናቱን ለማከናወን የተላኩት ግለሰቦች ገለልተኛ አይደሉም የሚል ጥያቄ ቢያነሳም አቶ ወርቁ በበኩላቸው የሚዛናዊነት ጥርጣሬ ካለ ከብሔር ብሔረሰብ የተወጣጡ ቢሆኑ የተሻለ ሊሆን ይችላል፤ ካልሆነ ግን መታየት ያለባቸው ሰዎቹ ሳይሆኑ ይዘውት የሚመጡት መረጃ ነው፤ ከዚህም አንጻር የመጣው መረጃ መሬት ላይ ያለውን ነባራዊ ሁኔታ በትክክል የሚገልጽ ነው ይላሉ። የማንነት ጥያቄና የራስ አስተዳደር ለምን ተፈለገ የቅማንት የራስ አስተዳደር ጥያቄ በዋናነት ልማትን ለማፋጠን እንደሆነ የሚናገሩት አቶ ይርሳው ከሌሎች ብሔር ብሔረሰቦች ጋር እኩል ተጠቃሚነት፣ ባህልንና እሴትን ለማሳደግ እንዲሁም የራስን አካባቢ ህዝቡ ራሱ በሚመርጣቸው ሰዎች እንዲያስተዳደርና በዚህም ከፍተኛ ልማት ለማምጣት ነው ይላሉ። የቅማንት የራስ አስተዳደር ጥያቄና የክልሉ ውዝግብ መፍትሔ ሳያገኝ በዚህ ከቀጠለ በኋላ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድ ወደ ስልጣን በመጡ ማግስት፤ ኮሚቴውንና የክልሉን መንግሥት ተወካዮች ባካተተ መልኩ ውይይት ተደርጎ ጉዳዩ በሰላማዊ ሁኔታ እንዲፈታ ምክረ ሃሳብ አቅርበዋል። እንደ አቶ ይርሳው ገለጻ ከጠቅላይ ሚንስትሩ ምክረ ሃሳብ በኋላ ኮሚቴው ነሐሴ ወር ዓ ም ጎንደር ለስብሰባ ተቀምጧል። ስብሰባ ላይ እያለን በክልሉ የፀጥታ ኃይል የእገታ ሙከራ ተካሂዶብናል፤ ከዚያም በኋላ ከክልሉ መንግሥት ጋር ያለን ግንኙነት ተቋረጠ ይላሉ። ውዝግቡ እንዳይቋጭ ምክንያቱ ይህ መሆኑንም ያነሳሉ። አቶ መርሃ ጽድቅ ግን በዚህ አይስማሙም፤ እሳቸው እንደሚሉት በተለይ የጸጥታው መደፍረስና ነገሮች መበላሽት የጀመሩት ክልሉ በ ባጠናው መሰረት የመጀመሪያውና ትክክለኛው ውሳኔ በመቀልበሱ እንደሆነ አፅንኦት በመስጠት ይናገራሉ። ክልሉ ሰለባ ሆኗል፤ በተለይ ከ ዓ ም ውሳኔ በኋላ ክልሉ ከሚገባው በላይ ባልተገባ መንገድ ተጠልፏል። በማንም አይደለም የተጠለፈው፤ በራሱ ሰዎች ነው። በተለይ በፌደራል ደረጃ ላይ በነበሩት ትልልቅ የብአዴን ሰዎች የክልሉን ምክር ቤት ወደዚህ ችግር አስገብተውት አካባቢው እንዳይረጋጋ ተደርጓል የሚል ሃሳብ ያነሳሉ። ግጭትና መፈናቀል በማዕከላዊና ምዕራብ ጎንደር በአካባቢው በተለያዩ ጊዜያት ችግሮች እየተነሱ የሰው ህይወት መጥፋትና ንብረት መውደም በስፋት ተስተውሏል። በተለይ ባለፈው ዓመት የተነሳው ግጭት የክልሉን አጠቃላይ ተፈናቃይ አሃዝ ወደ ሺህ ያሳደገና በግጭቱም ቢያንስ ቤቶች መቃጠላቸውን በወቅቱ የክልሉ መንግሥት አስታውቋል። ለተወሰኑ ወራት አንጻራዊ ሰላም ሰፍኖ ቢቆይም ሰሞኑን በተቀሰቀሰ ግጭት ደግሞ ሰዎች ተገድለዋል፤ ንብረት ወድሟል። ንጹሃን ዜጎችን ከተሽከርካሪ አስወርደው ማንነታቸውን መሰረት በማድረግ ቢያንስ ስድስት ሰዎች እንደተገደሉና ይህም በጽንፈኛው ኮሚቴ የሚመራና የሦስተኛ ወገን ጣልቃ ገብነት ያለው መሆኑን የክልሉ መንግሥት አስታውቋል። ቤይሩት፡ ባለፉት ወራት ኢትዮጵያዊያን ህይወታቸውን አጥተዋል ለዚህ ክስ ምላሽ የሰጡት አቶ ይርሳው እኛ የማንም ተላላኪ አይደለንም፤ እንደዚያም ሆነን ከሆነ የክልሉ መንግሥት ምን ይሰራ ነበር በማለት ይጠይቃሉ። ከሰሞኑ የተቀሰቀሰውን ግጭት በተመለከተ ደግሞ የቅማንት ሕዝብ የትም አልሄደም፤ ሲመጡበት ግን ራሱን ተከላክሏል ያሉት አቶ ይርሳው መኪና ላይ ሰዎችን አስወርዶ በማንነታቸው ምክንያት መግደል ነውር ነው፤ ማን እንደፈጸመው ግን መረጃ የለኝም የሚል ምላሽ ሰጥተዋል። አሁን የክልሉ መንግሥትና ኮሚቴው አንዱ ሌላውን በመክሰስ ላይ ይገኛሉ። በአካባቢው ግጭቶች እየተፈጠሩ በየጊዜው የሰው ህይወት መጥፋትና የንብረት መውደም የአካባቢው መገለጫ እንደሆነ ብዙዎች አስተያየታቸውን ይሰጣሉ። መፍትሄው ምን ይሆን አቶ መርሃ ጽድቅ ለጉዳዩ ሁለት የመፍትሔ ሃሳቦች መኖራቸውን ይገልጻሉ። እንደ እርሳቸው ገለጻ የራስ አስተዳደሩ ሕገ መንግሥታዊ መስፈርቶችን ሳያሟላ የተወሰነ በመሆኑ ህጋዊ መሰረት የለውም በማለት ውሳኔውን ውድቅ ማድረግ ይቻላል የሚለው አንደኛው አማራጭ ነው፤ ነገር ግን ይህ አማራጭ ተግባራዊ ቢደረግ ሰላም ሊሰፍን ይችላል ወይ የሚለው አጠያያቂ መሆኑን ይገልጻሉ። ሕዝቡ በዚህ ደረጃ ከተነሳሳ በኋላና ብዙ ተስፋዎችን ካሳየነው በኋላ የራስ አስተዳደርህን አጥፌብሃለሁ ቢባል ውጤቱ መረጋጋትን የሚያሰፍን አይሆንም ባይ ናቸው። ሌላኛው ደግሞ እንደ አማራጭ የሚያቀርቡት የተፈቀደውን የራስ አስተዳደር መመስረትና ይህንን ህጋዊ አካሄድ በሚያስተጓጉሉት አካላት ላይ ደግሞ ህጋዊ ርምጃ መውሰድ እንደሆነ አቶ መርሃ ጽድቅ ይናገራሉ። ሂደቱ የራሱ ችግር እንዳለበት ሆኖ ቀበሌዎችን ያቀፈው የራስ አስተዳደር ይደራጃል ያሉት አቶ መርሃ ጽድቅ ይካተቱልኝ የሚባሉት ሦስት ቀበሌዎች አስፈላጊ ከሆነ ባሉበት በልዩ ቀበሌ ሊደራጁ ይችላሉ ብለዋል። አቶ ይርሳውም በበኩላቸው ሁለት የመፍትሄ አማራጮችን ያቀርባሉ። አንደኛው የብሔረሰብ አስተዳደሩ እንዲቋቋም ነገር ግን ባለፈው የፌዴሬሽን ሰዎች የሰጡት ውሳኔ ተሽሮ ሌላ አካል በተለይ ከደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች የተውጣጣ አካል የሦስቱን ቀበሌዎች ጉዳይ እንዲያጠና ጠይቀዋል። ሁለተኛው ደግሞ ብሔረሰብ አስተዳደሩ ሲመሰረት ምንም አይነት ጣልቃ ገብነት አያስፈልገንም፤ ምክንያቱም አሁን ባለው ሁኔታ ከኮሚቴው ጋር የነበሩ ነገር ግን አሁን አብረውን ያልሆኑ ሰዎች እንዲሳተፉ እየተደረገ ስለሆነ ነው ይላሉ። ተያያዥ ርዕሶች
ወረርሽኝ ምንድን ነው እስካሁን በዓለም የተከሰቱት ወረርሽኞችስ ምን ዓይነት ነበሩ
ወረርሽኝ ምንድን ነው ዓለም እስካሁን ያስተናገደቻቸው ወረርሽኞችስ ምን ዓይነት ነበሩ ወረርሽኝ ምንድን ነው ዓለም እስካሁን ያስተናገደቻቸው ወረርሽኞችስ ምን ዓይነት ነበሩ ወረርሽኝ ምንድን ነው ዓለም እስካሁን ያስተናገደቻቸው ወረርሽኞችስ ምን ዓይነት ነበሩ
አሜሪካ ከህዳሴ ግድብ አደራዳሪነት እንድትወጣ የሚጠይቀው የዋሽንግተን ዲሲ ሰልፍ
ፌብሩወሪ አጭር የምስል መግለጫ በዋሽንግተን ዲሲ እየተካሄደ ያለው ሰላማዊ ሰልፍ ኢትዮጵያ፣ ግብፅና ሱዳን በታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ዙርያ የሚያደርጉትን ድርድር የአሜሪካ መንግሥት ቀደሞ በታዛቢነት አሁን ደግሞ በአደራዳሪነት መግባቱን በመቃወም በአሜሪካ፣ ዋሽንግተን ዲሲ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ሰላማዊ ሰልፍ እያካሄዱ ነው። የሰልፉ አስተባባሪ እና የዲሲ ግብረ ኃይል ተወካይ አቶ ጣሰው መላከሕይወት ለቢቢሲ እንደተናገሩት፤ ዋነኛ ጥያቄያቸው አሜሪካ ከአደራዳሪነት እንድትወጣ ነው። አሜሪካ እንዲሁም የዓለም ባንክ ከአደራዳሪነት ወደ ታዛቢነት እንዲመለሱ እንደሚፈልጉም አክለዋል። ሰልፉን የጠራነው የአሜሪካ መንግሥት ቀደም ሲል በታዛቢነት አሁን ደግሞ በአደራዳሪነት ለመግባት ኢትዮጵያ ላይ ያልተገባ ተጽዕኖ እየፈጠረ ስለሆነ፤ ያንን ተጽዕኖ ከኢትዮጵያ እንዲያነሳ ለመጠየቅ ነው ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ኢትዮጵያ በዋሽንግተኑ የህዳሴ ግድብ ድርድር ላይ እንደማትሳተፍ አሳወቀች በተጽዕኖ የሚመጣ ስምምነትን እንደማይቀበሉ ለማሳወቅና የኢትዮጵያ መንግሥትም የበርካቶች ህልውና የሆነው የታላቁ ህዳሴ ግድብ ጉዳይን በተመለከተ በተጽዕኖ ስምምነት እንዳይፈርም ለመጠየቅ ሰልፉ እንዳስፈለገም አብራርተዋል። አቶ ጣሰውን ያነጋገርናቸው ሰልፉ መካሄድ በጀመረበት ሰዓት ሲሆን፤ ወደ አንድ መቶ ሰዎች ገደማ እንደተገኙ ለቢቢሲ ገልጸው እየጨመረም ይመጣል ብለዋል። አጭር የምስል መግለጫ ሰልፈኞቹ ዋነኛ ጥያቄያቸው አሜሪካ ከአደራዳሪነት እንድትወጣ መሆኑን ገልጸዋል አገር ውስጥ ባለው ፖለቲካ የተለያየ አቋም ቢኖረንም በአገር ህልውና ላይ በተመሰረተው በአባይ ጉዳይ በጋራ እንደምንቆም፣ በጋራ ድምጻችንን እንደምናሰማ የሚገልጹ መፈክሮች አሉን ሲሉ አስተባባሪው ተናግረዋል። መንግሥት በግድቡ ጉዳይ ከማህበረሰቡ ጋር እንዲወያይና ያሚካሄደውን ነገር ለሕዝብ እንዲያሳውቅ የሚያሳስቡ መፈክሮች የሰላማዊ ሰልፉ አካል እንደሆኑም አቶ ጣሰው አክለዋል። አሜሪካንም ትሁን ዓለም ባንክ በኢትዮጵያ ላይ ጫና እንዳያሳድሩ ለመጠየቅ ከሰልፍ ባሻገር በየአካባቢያቸው ያሉ የሕዝብ ተወካዮችንና የመንግሥት ተቋሞችን የመድረስ እቅድ እንዳላቸውም ተናግረዋል። ሰልፉን ያስተባበሩት ዲሲ ግብረ ኃይል፣ መደመር በተግባር፣ ኢትዮጵያን አሜሪካን ሲቪል ካውንስል የተባሉ ስብስቦች እንዲሁም የመብት ተሟጋቾችም ጭምር ናቸው። አጭር የምስል መግለጫ በየአካባቢያቸው ያሉ የሕዝብ ተወካዮችንና የመንግሥት ተቋሞችን የመድረስ እቅድ እንዳላቸውም ተናግረዋል ኢትዮጵያ በዋሽንግተን የመጨረሻ ቀጠሮ ተይዞለት በነበረው የታላቁ ህዳሴ ግድብ ቀጣይ ድርድር ላይ እንደማትሳተፍ ለአሜሪካ ማሳወቋ ይታወሳል። ተያያዥ ርዕሶች
በዓመት ከ ሺህ በላይ ለሚሆኑ ፈረሶች ነጻ ህክምና የሚሰጠው የፈረሶች ክሊኒክ
በዓመት ከ ሺህ በላይ ለሚሆኑ ፈረሶች ነጻ ሕክምና የሚሰጠው የፈረሶች ክሊኒክ።በዓመት ከ ሺህ በላይ ለሚሆኑ ፈረሶች ነጻ ሕክምና የሚሰጠው የፈረሶች ክሊኒክ።
ሦስቱ ሃገራት በዋሽንግተን ምን ተስማሙ
ኖቬምበር ማጋሪያ ምረጥ የታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታንና የውሃ አሞላል ሂደትን በተመለከተ ለዓመታት ሲካሄድ የነበረው የሦስትዮሽ ውይይቶች ውጤት አልባ መሆኑ ሲነገር ቆይቷል። በዚህም ከግደቡ ጋር በተያያዘ በኢትዮጵያና በግብጽ መካከል ያለው አለመጋባባት እየጎላ መጥቷል። ትናንት የኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ግብጽ የውጪ ጉዳይ ሚንስትሮች የልዑክ ቡድናቸውን ይዘው አሜሪካ ከደረሱ በኋላ በጠረቤዛ ዙሪያ ውይይት አድርገው የጋራ መግለጫ አውጥተዋል። የጋራ መግለጫው ምን ይላል በውይይቱ ላይ ከሶስቱ ሃገራት የውጪ ጉዳይ ሚንስትሮች ባሻገር የአሜሪካ የገንዘብ ሚንስትር እና የዓለም ባንክ ፕሬዝደንት ተሳታፊ ነበሩ። የሶስቱ ሃገራት ሚንስትሮች በግድቡ አሞላል እና ኦፕሬሽን ላይ የሁሉንም ፍላጎት በሚያረካ መልኩ በትብብር እና በተቀናጀ መልኩ ለመስራት ጽኑ አቋማቸውን ገልጸዋል ይላል ትናንት ምሽት በዋሸንግተን የወጣው መግለጫ። የውጪ ጉዳይ ሚንስትሮቹ በየውሃ ሚንስትሮች ደረጃ የሚደረግ አራት መንግሥታዊ የቴክኒክ ስብሰባዎችን ለማካሄድ የተስማሙ ሲሆን፤ የዓለም ባንክ እና አሜሪካ ድጋፍ እንዲሰጡ እና በውይይቶቹ በታዛቢነት እንዲሳተፉ ከስምምነት ላይ መድረሳቸውን መግለጫው ያትታል። በተጨማሪም ሚንስትሮቹ ጥር ዓ ም ድረስ ከስምምነት ለመድረስ እንደሚሰሩ እና ኅዳር እና ጥር ዳግም በዋሽንግተን ለመገናኘት እና ሂደቱን ለመገምገም ቀጠሮ ይዘዋል። እስከ ጥር ዓ ም ስምምነት ላይ የማይደረስ ከሆነ በ ተፈርሞ የነበረው የጋራ አቋም መግለጫ አንቀጽ ተግባራዊ እንዲሆን ሚኒስትሮቹ ተስማምተዋል። የ ቱ ጋራ አቋም መግለጫ አንቀጽ ምን ይላል ስምምነቱ የተፈረመው በሱዳን ካርቱም ሲሆን፤ የመርሆ መግለጫ አንቀጽ ሶስቱ ሃገራት በአተረጓጓመ ወይም አተገባባር ወቅት ሊፈጠሩ የሚችሉ አለመግባባቶችን በመልካም መንፈስ ላይ ተመስረተው በውይይት ወይም በድርድር ይፈታሉ። ሶስቱ አካላት አለመግባባቶችን በውይይት እና በድርድር መፍታት ቢሳናቸው፤ አደራዳሪ ሊጠይቁ ወይም ጉዳዩ ለየ ሃገራትቱ መሪዎች ወይም ለርዕሳነ ብሔሮቻቸው ሊያሳውቁ ይችላሉ ይላል። የውሃ ሚንስትሩ ሲሌሺ በቀለ ዶ ር የሶስቱ ሃገራት የቴክኒክ ኮሚቴዎች ውይይት እንዲያደርጉ ከመግባባት መደረሱ እንዳስደሰታቸው በትዊተር ገጻቸው ላይ ገልጸዋል። የዋሽንግተኑ ውይይት፡ ድርድር ወይም ውይይት በትናንት ውይይት አሜሪካ እና የዓልም ባንክ ተሳትፎ ማድረግ እና በቀጣይ ውይይቶች ላይም በድጋፍ ሰጪነት እና በታዛቢነት በሚኖራቸው ተሳትፎ ላይ ብዙ ጥያቄዎችን የሚያነሱ አልጠፉም። የኢትዮጵያ መንግሥት በተደጋጋሚ ኢትዮጵያ ወደ ዋሽንግተን የምታቀናው ለውይይት እንጂ ለድርድር እንዳልሆነ ገልጿል። የተርባይኖች መቀነስ በሚመነጨው ኃይል ላይ የሚያመጣው ለውጥ የለም የህዳሴ ግድብ ዋና ሥራ አስኪያጅ የውጪ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ አቶ ነብያት ጌታቸው የአሜሪካ ግምዣ ቤት ሚንስትር ስቲቭ ማቺን ባደረጉት ግብዣ የሶስቱ ሃገራት የውጪ ጉዳይ ሚንስትሮች ወደ ዋሽንግተን ማቅናታቸውን ይጠቁማሉ። አሜሪካ ይህን ጥሪ ያቀረበችው የኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ግብጽ ወዳጅ ሃገር ስለሆነች ነው ያሉ ሲሆን አሜሪካም የአደራዳሪ ሚና እንደሌላት ተናግረዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ አንዳንድ የመካከለኛው ምስራቅ እና የግብጽ መገናኛ ብዙሃን የሶስቱ ሃገራት የውጪ ጉዳይ ሚንስትሮች በዋሽንግተን የከትሙት ለድርድር እንደሆነ በዘገባዎቻቸው ላይ አመላክተው ነበር። ኢጂፕት ቱደይ የተባለው በእንግሊዘኛ የሚታተመው ጋዜጣ እንዲሁም የተባበሩት አረብ ኤሜሬቶች ጋዜጣ የሆነው ገልፍ ኒውስ ወደ ድርድር የሚወስደው ወይይት በአሜሪካው ግምዣ ቤት ሚንስትር ቢሮ ይካሄዳል ሲሉ ዘግበው ነበር። የኢትዮጵያ፣ የግብፅና የሱዳን የውኃ ጉዳይ ሚኒስትሮች፤ መስከረም እና በህዳሴ ግድብ የውሃ አሞላልና አለቃቀቅ ላይ የተደረገውን የሦስትዮሽ ምክክር ተከትሎ ግብፅ ዓለም አቀፍ አደራዳሪዎች ጣልቃ እንዲገቡ ጥሪ ማቅረቧ ይታወሳል። የግብፁ ፕሬዚዳንት አብደል ፋታህ አልሲሲ፤ አሜሪካ በህዳሴ ግድብ ላይ ያላት ሚና ከፍ ያለ እንዲሆን ጥሪ አቅርበው ነበር። ኢትዮጵያ በበኩሏ የሶስተኛ ወገን ጣልቃ ገብነት፤ በሦስቱ አገራት መካከል የተደረሱ አበረታች ስምምነቶችን የሚያፈርስ ከመሆኑ በተጨማሪ ሦስቱ አገራት እንደ አውሮፓውያኑ በመጋቢት የፈረሟቸውን የመግለጫ ስምምነቶችም ይጥሳል በማለት የሦስተኛ ወገን ጣልቃ ገብነት እንደማትቀበል መግለጿ የሚታወስ ነው። ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ በታላቁ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ በዋሽንግተን የተካሄደው ውይይት ውጤታማ እንደሆነ በትዊተር ገጻቸው ላይ ጠቅሰው ነበር። ለምን ወደ አሜሪካ በናይል ጉዳይ በርካታ ምርምሮችን ያደረጉት ዶ ር ያእቆብ አርሳኖ ግብፅና ኢትዮጵያ በአሜሪካ ለመገናኘታቸው ምክንያት ሊሆን የሚችለውን ያስቀምጣሉ። እንደ እሳቸው እምነት የአሜሪካ ላወያያችሁ ግብዣ በሶስቱ አገራት በተለይም በኢትዮጵያና በግብፅ መካከል አለመግባባት እንዳይፈጠር ተቀራርበው እንዲነጋገሩ ለማድረግ ነው። ምክንያቱም ግብፆች ብዙ ነገሮችን ጮክ አድርገው ቀውስ እንዳለ አድርገው ስለሚያወሩና ስለሚያስወሩ ወዳጅ አገሮች ይህ ያሳስባቸዋል። የአሜሪካም ላወያያችሁ ማለት ለዚህ ይመስለኛል ይላሉ። በሉንድ ዩኒቨርሲቲ የናይል ተመራማሪ የሆኑት አቶ ወንደሰን ሚቻጎ ኢትዮጵያ ዛሬም በህዳሴው ግድብ ጉዳይ የአቋም ለውጥ እንዳላደረገች ያስረዳሉ። ኢትዮጵያ በህዳሴው ግድብ ለመምከር ወደ አሜሪካ ማቅናቷ የግድቡን ጉዳይ በሰላምና በትብብር ለመፍታት ካላት ፍላጎት የመነጨ እንጂ ትልቅ የአቋም ለውጥ አድርጋ እንደማይሆን አስተያየታቸውን ያስቀምጣሉ። ለምን ወደ አሜሪካ ለሚለውም አሜሪካ የኢትዮጵያም የግብፅም ወዳጅ ሃገር መሆኗን ነው አቶ ወንደሰን የሚጠቅሱት። አሜሪካ በዚህ መልኩ መንቀሳቀሷ ጉዳዩ ምን ያህል ቦታ እንደተሰጠው የሚያሳይ እንደሆነ፤ ይህም አዎንታዊ እንደሆነም ያክላሉ። ዞሮ ዞሮ ነገሩ መፈታት ያለበት ግድቡ እንዴት ይሞላ እና ግድቡ እንዴት ይስራ የሚሉ ነገሮችን ከቴክኒክ አኳያ በመመለስ ነው። የሚሉት አቶ ወንደሰን ኢትዮጵያ ግብፅና ሱዳን ከዚህ ቀደምም በዚህ መልኩ አምስት ጊዜ መደራደራቸውን ያስታውሳሉ። ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሄ በሚለው የሁልጊዜ አቋማ ላይ ትልቅ ለውጥ ያለ አይመስለኝም በማለት የዋሽንግተኑ ውይይት የኢትዮጵያ አቋምን የሚቀይር እንዳልሆነ እምነታቸውን ይገልፃሉ። በሌላ በኩል አሜሪካ ወዳጅነቷ ለግብፅ ያመዝናል፤ ስለዚህም ነገሮች እንደ ግብፅ ፍላጎት ይሄዳሉ የሚል ስጋቶች ስለመኖራቸው የተጠየቁት ዶ ር ያእቆብ ለአሜሪካ ወሳኙ ብሄራዊ ጥቅሟ እንጂ ሌላ ነገር እንዳልሆነ ይገልፃሉ። በኢትዮጵያ በኩል የህዳሴው ግድብ ግንባር ቀደም ተደራዳሪ የነበሩትና አሁን የምስራቅ ናይል የቴክኒክ አህጉራዊ ጽሕፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ ፈቅአህመድ ነጋሽም በኢትዮጵያ በኩል ምንም የአቋም ለውጥ እንደሌለ ያረጋግጣሉ። እሳቸው እንደሚሉት የኢትዮጵያና የግብፅ መሪዎች የቴክኒካል ስብሰባው እንዲቀጥል ተስማምተዋል። የኢትዮጵያ አቋም አሁንም የድርድር ነገር ገና ነው የሚል ነው። ሁለቱ መሪዎች የቴክኒካል ቲሙ ሥራውን ይቀጥል ልዩነት ካለ እኛ እየተገናኘን እንፈታለን ነው ያሉት ሲሉም ያክላሉ። አቶ ፈቅአህመድ እንደሚሉት ወደ ድርድር ለመሄድ፤ መጀመሪያ አገራቱ አደራዳሪ ያስፈልገናል ወይ ድርድሩ በምን ጉዳይ ላይ ነው የሚያተኩረው በሚሉ ነገሮች ላይ መስማማት አለባቸው። ቀጥሎም የአደራዳሪው ኃላፊነት ምንድን ነው የሚለውን በጋራ ወስነው አደራዳሪውን በጋራ መምረጥ ይኖርባቸዋል። እነዚህ ቅድመ ሁኔታዎች ሳይሟሉ ወደ ድርድር ሊኬድ አይቻልም። ወደ ድርድር መሄድ ራሱ ቀላል እንዳልሆነና የራሱ አካሄድ እንዳለውም ያስረዳሉ። ከዲፕሎማሲ አንፃር የአሜሪካን ላወያያችሁ ጥያቄ አለመቀበል ከባድ ስለሚሆን ኢትዮጵያ ከዚህ አንፃር ነገሮችን እንደምታስኬድ ያመለክታሉ አቶ ፈቅአህመድ። የግብፅና የአሜሪካ የቀደመ ንግግር ትናንት ከተካሄደው መርሃ ግብር ቀደም ብሎ የግብጽ የውጪ ጉዳይ ሚንስትር ሳሚህ ሽኩሪ ከፕሬዝደንት ትራምፕ ከፍተኛ አማካሪ ጃሬድ ኩሽነር ጋር ውይይት ማድረጋቸውን የግብጽ የውጪ ጉዳይ ሚንስትር ቢሮ አስታውቋል። በውይይታቸው ወቅት ሳሚህ ሽኩሪ አሜሪካ እና ግብጽ ለበርካታ ዓመታት የዘለቀውን ወዳጅነት አውስተዋል። የውጪ ጉዳይ ሚንስትሩ ግብጽ ባለፉት አምስት ዓመታት የሶስቱንም ሃገራት ፍላጎት ከሚያረካ ስምምነት ላይ ለመድረስ ጥረት ስታድርግ መቆየቷን እና በኢትዮጵያ በኩል ምላሽ ማግኘት ባለመቻሉ ምክንያት ውጤት አልባ እንደሆነ ተናግረዋል። ከዚህ በተጨማሪም ሳሚ ሽኩሪ እና ጃሬድ ኩሽነር የመካከለኛውን ምስራቅ እና የፍልስጤም ጉዳይን በማንሳት ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ መነጋገራቸውን የግብጽ የውጪ ጉዳይ ሚንስትር ድረ ገጽ አስነብቧል። ተያያዥ ርዕሶች
ትራምፕ ህዳሴ ግድብ ሲያልቅ እመርቃለሁ ማለታቸው ተሰማ
ኖቬምበር ማጋሪያ ምረጥ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለኢትዮጵያ፣ ግብፅና ሱዳን ሚኒስትሮች የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ሲጠናቀቅ ምርቃቱ ላይ በመገኘት ቀዩን ሪባን እቆርጣለሁ ማለታቸውን የኢትዮጵያ የውሃ፣ መስኖና ኃይል ሚኒስትር ኢንጅነር ስለሺ በቀለ ተናግረዋል። ሚኒስትሩ እንደገለፁት ትራምፕ ይህንን የተናገሩት በትናንትናው ዕለት አሜሪካ የሦስቱን አገራት ሚኒስትሮች በህዳሴ ግድብ አሞላል እና ኦፕሬሽን ውይይት ከተሳተፉ በኋላ ነው። በውይይቱ ላይ ከሦስቱ ሃገራት ሚንስትሮች ባሻገር የአሜሪካ የገንዘብ ሚንስትር እና የዓለም ባንክ ፕሬዝደንት ተሳታፊ ነበሩ። ኢንጅነር ስለሺ በቀለ አክለው እንደገለፁትም ፕሬዚዳንት ትራምፕ ከሦስቱ ሃገራት ከተውጣጡ ስድስት ልዑካን ጋር ተገናኝተው ጉዳዩንም ለመረዳት ሙከራ አድርገዋል ብለዋል። ውይይቱም ካለቀ በኋላ፤ ግድቡ ከተጠናቀቀ በኋላ በምርቃቱ ላይ ሪባን መቁረጥ እንደሚፈልጉ እንደነገሯቸው ገልፀዋል። ፕሬዚዳንቱ ጨምረውም ልዩነቶቻቸውን አስወግደው ተባብረው እንዲሠሩ መልዕክታቸውንም አስተላልፈዋል ብለዋል ሚኒስትሩ። ከዚህም በተጨማሪ ለገንዘብ ሚኒስትራቸውም የህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት በተሳለጠ ሁኔታ እስኪጠናቀቅ ድረስ የሚደረጉ ውይይቶች በተላሰለሰና ፈጣን ሁኔታ እንዲካሄዱ እንዲመሩ አቅጣጫ መስጠታቸውም ተገልጿል። አሜሪካ የአባይ ወንዝ አጠቃቀምን በተመለከተ መግለጫ አወጣች ውይይቱ ከተጠናቀቀ በኋላ ሦስቱን ሃገራት በመወከል የአሜሪካ ገንዘብ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ፤ ፕሬዚዳንቱ ግድቡን መመረቅ መፈለጋቸውን ምንም የጠቀሰው ጉዳይ የለም። የውጪ ጉዳይ ሚንስትሮቹ በየውሃ ሚንስትሮች ደረጃ የሚደረግ አራት መንግሥታዊ የቴክኒክ ስብሰባዎችን ለማካሄድ የተስማሙ ሲሆን፤ የዓለም ባንክ እና አሜሪካ ድጋፍ እንዲሰጡ እና በውይይቶቹ በታዛቢነት እንዲሳተፉ ከስምምነት ላይ መድረሳቸውን መግለጫው ያትታል። በተጨማሪም ሚንስትሮቹ ጥር ፣ ዓ ም ድረስ ከስምምነት ለመድረስ እንደሚሰሩ እና ኅዳር እና ጥር ዳግም በዋሽንግተን ለመገናኘት እና ሂደቱን ለመገምገም ቀጠሮ ይዘዋል። እስከ ጥር ፣ ዓ ም ስምምነት ላይ የማይደረስ ከሆነ በ ተፈርሞ የነበረው የጋራ አቋም መግለጫ አንቀጽ ተግባራዊ እንዲሆን ሚኒስትሮቹ ተስማምተዋል። ተያያዥ ርዕሶች
ሱዳን በህዳሴው ግድብ ጉዳይ አቋሟን ትቀይር ይሆን
ኤፕረል ማጋሪያ ምረጥ ሱዳን በህዳሴው ግድብ ግንባታ ጉዳይ ከጅማሮ አንስቶ በነበራት አቋም የኢትዮጵያ አጋር ነች። በአጠቃላይ የተፋሰሱ ሃገራት እንዲሁም በኢትዮጵያ፣ ግብፅና ሱዳን የሶስትዮሽ ድርድር ሱዳን የቆመችው ከኢትዮጵያ ጋር ነው። በአንፃሩ ግብፅ የግድቡ ሃሳብን በመቃወም ገና ከጠዋቱ ይሆናል ያለችውን ዕድል ሁሉ ስትሞክር ነበር። በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ዛሬም ያን ጥረቷን አላቋረጠችም። ከቀናት በፊት አንቀጥቅጠው የገዟትን ኦማር ሃሰን አል ባሽርን በቃኝ ብላ ከሥልጣን ያስወገደችው ሱዳን ያልለየለት የፖለቲካ ሁኔታ ውስጥ ነች። ይህን የመንግሥት ለውጥ ተከትሎ ሱዳን በህዳሴው ግድብ ጉዳይ የአቋም ለውጥ ልታደርግ ትችላለች ወይ በኢትዮጵያ በኩል የህዳሴው ግድብ ግንባር ቀደም ተደራዳሪ የነበሩትና በአሁኑ ወቅት የምስራቅ ናይል የቴክኒክ አህጉራዊ ጽሕፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ ፈቅአህመድ ነጋሽ ሱዳን የህዳሴው ግድብን በሚመለከት በአቋሟ ትቀጥላለች ብለው ያምናሉ። ግብፅ ግን ዳር ላይ ቆማ እንዲሁ ነገሮችን ልትመለከት አትችልም። በቀዳሚነት የሚያነሱት ነጥብ የግድቡን ግንባታ መደገፍ ለሱዳን የፖለቲካ ውሳኔ ሳይሆን የብሔራዊ ጥቅም ጉዳይ መሆኑን ነው። ትልቅ ጥቅም ነው የሚያገኙት ያለምንም ኢንቨስትመንት ይላሉ። ለአል ባሽር ከሥልጣን መውረድ ምክንያት የሆነው ተቃውሞ በዳቦ ውድነት ፤ በኑሮ ውድነት የተቀሰቀሰ ነው። ግድቡ ደግሞ ለዚህ ጥያቄ በአጠቃላይ ለሃገሪቱ የልማት ጥያቄ መልስ እንደሚሆን አቶ ፈቅአህመድ ያስረዳሉ። አቶ ፈቅአህመድ እንደሚያስረዱት ግድቡ ለሱዳን ኢኮኖሚያዊ ጥቅም አለው፣ ያለ ምንም ወጪ እስከ ሶስት ሺህ ጊጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል የሚያገኙ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪ ከኢትዮጵያ በርካሽ ሊገዙ ይችላሉ። በዚህ ደግሞ ኢንዱስትሪዎቻቸውን ሊያነቃቁ፣ ግብርናና ዓሣ እርባታቸውን ሊያስፋፉ ይችላሉ። ለህዳሴ ግድብ ግንባታ መዘግየት ምን አይነት መፍትሔዎች እየተሰጡ ነው ይህ ደግሞ ደቡብ ሱዳን ትልቁን የነዳጅ ሃብቷን ይዛ በመገንጠሏ አግኝቶ ማጣት እንደሚሉት ለሆነችው ሱዳን ከሰማይ እንደሚወርድ መና ሊቆጠር ይችላል። ግድቡ ሱዳንን የማትወደው እንግዳ ከሆነባትና በየዓመቱ ከሚጎበኛት ጎርፍም ይታደጋታል። ጎርፉ የሚያመጣውን ደለል ከግድቦችና ቦዮች ለመጥረግ በየዓመቱ እስከ ሰባ ሚሊየን ዶላር ከመክሰርም ያድናታል። ስለዚህም ምንም ዓይነት መንግሥት ቢመጣ ከዚህ ከፍተኛ ጥቅም የሚበልጥበትና ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ ይኖራል ብለው እንደማያምኑ አቶ ፈቅአህመድ ያስረግጣሉ። በተመሳሳይ በአባይ ጉዳይ በርካታ ጥናቶችን ያደረጉት ዶ ር ያዕቆብ አርሳኖም ግድቡን መደገፍ የብሔራዊ ጥቅም እንጂ የፖለቲካ ውሳኔ ባለመሆኑ ሱዳን በአቋሟ ፀንታ ከኢትዮጵያ ጎን መሰለፏን እንደምትቀጥል ያምናሉ። ነገር ግን ለመጭው የሱዳን መንግሥት የህዳሴው ግድብ ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ ይሆናል አይሆንም የሚለው በሂደት የሚታይ እንደሆነ ይገልፃሉ ዶ ር ያዕቆብ። ግብፅ በህዳሴው ግድብ ዙሪያ አዲስ ሃሳብ አቀረበች ለዚህ ብሔራዊ ጥቅም ሲሉ ነው አቋማቸውን የማይቀይሩት ሲሉም ያስረግጣሉ። ነገር ግን በአሁኑ ወቅት በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ላይ ያለችው ሱዳን ገና መንግሥት እስክታቋቁም የሚወስደው ጊዜ በተለይም በሂደት ላይ ያለው የሦስትዮሽ ድርድር ላይ የተወሰነ የማዘግየት ተፅዕኖ ሊኖረው እንደሚችል ይናገራሉ። እርሳቸው በጠቀሷቸው ምክንያቶች ሱዳን ለእራሷ ስትል የአቋም ለውጥ አታደርግም ተብሎ ቢታመንም ግብፅ የአሁኑን የሱዳን ፖለቲካዊ ለውጥ እንደሚያመቻት ለመጠቀም የምታደርገው ጥረት ምን ድረስ ሊሄድ ይችላል የሚለው ወሳኝ ጥያቄ ነው። ግድቡ ከተጀመረ ጀምሮ ግብፅ ሱዳን ላይ በተለያየ መንገድ ከፍተኛ ጫና ስታሳድር እንደነበር የሚናገሩት አቶ ፈቅአህመድ የግብፅ ጫና ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ይናገራሉ። ግብፆች አሁን ተጠናክረው ነው የሚንቀሳቀሱት። ጫናቸውም ሱዳን ላይ ይበረታል ይላሉ። ነገር ግን እስከ ዛሬም ሱዳን ለህዳሴው ግድብ ድጋፏን ስትሰጥ የቆየችው የግብፅን ጫና ተቋቁማ ስለሆነ ከአሁን በኋላም በዚሁ ትቀጥላለች ብለው እንደሚያምኑ ይናገራሉ። ግብፅ ከጅምሩ ሱዳንም ኢትዮጵያም ላይ ጫና ለመፍጠር ከመሞከር ወደ ኋላ ብላ እንደማታውቅ የሚያነሱት ዶ ር ያዕቆብ በቀጣይ የግብፅ ተፅዕኖ ስኬት የሚወሰነው ከምንም በላይ በኢትዮጵያ ጥንካሬ እንደሆነ ያስረዳሉ። በዚህ ረገድም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ዶ ር ቁርጠኝነታቸውን ማሳየታቸውን ይጠቅሳሉ። ዋናው ነገር ኢትዮጵያ ግድቡን ለመሥራት ያላት አቅምና ቁርጠኝነት ነው የሚሉት ዶ ር ያዕቆብ ግብፅ በሱዳንም በኩል ሆነ በቀጥታ ኢትዮጵያ ላይ የምታደርገው ተፅዕኖ እንደ ከዚህ በፊቱ እንደሚቀጥል ያመለክታሉ። ሌሎቹስ የተፋሰሱ ሃገራት በአቋማቸው እንደፀኑ ናቸው ለአቶ ፈቅአህመድ ያነሳነው ጥያቄ ነበር። እርሳቸው በግልፅ የአቋም ለውጥ ያሳየ ሃገር እንደሌለ ይገልፃሉ። ነገር ግን እንደ አውሮፓውያኑ በ ኡጋንዳ ላይ የተፈረመውን የአባይ ተፋሰስ የትብብር ማዕቀፍ ከአስራ አንዱ የተፋሰሱ ሃገራት የተወሰኑት በሦስት ወራት ውስጥ በፓርላማቸው ሲያፀድቁት ቀሪዎቹ እስከ አሁንም ሳያፀድቁት ዘጠኝ ዓመታት ተቆጥረዋል። ይህ መዘግየት ደግሞ እንዴት ነው ነገሩ የሚያስብል ነገር ነው። አቶ ፈቅአህመድ ደግሞ ይህን ስምምነት ብቻ በመመልከት የማፅደቁ ሂደት ዘግይቷል ሊባል ቢችልም በዓለም አቀፍ ደረጃ ግን ተመሳሳይ ስምምነቶች እንዲህ ያለ ጊዜ እንደሚወስዱ ይናገራሉ። የዚህ ዓይነቱ ድርድር እስከ እና ዓመት የፈጀባቸው ሃገራት መኖራቸውንም ይናገራሉ። ኬንያ ስምምነቱን ለማፀደቅ ሶስት ጊዜ ፓርላማ አድርሳ መመለሷ በደቡብ ሱዳንም በሃገሪቱ የፖለቲካ በተመሳሳይ ሰነዱ ፓርላማ ደርሶ በተደጋጋሚ መመለሱ የሚታወስ ነው። ስለአዲሱ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ሥራ አስኪያጅ ጥቂት እንንገርዎ የተፋሰሱ ሃገራት የውሃ ሚኒስትሮች በየዓመቱ እየተገናኙ የሚወያዩ ሲሆን ያለፈው ስብሰባ እንደ አውሮፓውያኑ በ አስረኛው ወር በቡጁምቡራ ነበር የተካሄደው። የትብብር ማዕቀፉን ሱዳን ፣ ግብፅና ኮንጎ ጨርሶ አልፈረሙም። ከፈረሙት ሃገራት መካከል ደግሞ ሦስቱ ማለትም ኢትዮጵያ፣ታንዛኒያና ኡጋንዳ በፓርላማቸው ያፀደቁት ሲሆን ተጨማሪ ሦስት ሃገራት ቢያፀድቁት ለአፍሪካ ሕብረት በማቅረብ ከፍተኛ ትብብር ማድረግ የሚረዳቸውን ኮሚሽኑን ማቋቋም ይችላሉ። የትብብር ማዕቀፉን ፈርመው እስካሁን ያላፀደቁ ሃገራት ኬንያ ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ብሩንዲና ሩዋንዳ ናቸው። ተያያዥ ርዕሶች
የግዙፉ ግድብ ግንባታ፡ የኢትዮጵያና ግብፅ ቅራኔ ወደየት ያመራ ይሆን
ጃንዩወሪ ማጋሪያ ምረጥ ኢትዮጵያና ግብፅ በታላቁ የሕዳሴ ግድብ ግንባት ዙሪያ ሊግባቡ የቻሉ አይመስልም። የኢትዮጵያ፣ ግብጽ እና ሱዳን የውጪ ጉዳይ ሚንስትሮች ከትናንት ጀምሮ በዋሽንግተን ዲሲ ተገናኝተው እየመከሩ ይገኛሉ። አራት የቴክኒክ ውይይቶችን አድርገው ከመግባባት ላይ ሊደርሱ ያልቻሉት ኢትዮጵያና ግብፅ ዛሬ የመጨረሻውን ውይይት አድርገው ከስምምነት መድረስ የማይቻል ከሆነ ከዚህ ቀደም ሶስቱ ሃገራት የተፈራረሙት ዲክላሬሽን ኦፍ ፕሪንስፕልስ አንቀጽ ተግባራዊ ይደረጋል። የሕዳሴው ግድብ ሲጠናቀቅ በአፍሪቃ ግዙፉ ከውሃ የኤሌክትሪክ ኃይል የሚያመነጭ ግድብ ይሆናል ተብሎ ይጠቃል። ግንባታው ላይ የተጀመረው ይህ ግድብ፤ በመቶ ውሃ ለናይል ወንዝ የሚያበርከትው አባይ ወንዝን መሠረት አድርጎ ነው የሚታነፀው። ሱዳን በህዳሴው ግድብ ጉዳይ አቋሟን ትቀይር ይሆን ነገር ግን የግድቡ ግንባታ ለግብፅ ሰላም የሰጣት አይመስልም። ከግድቡ ግንባታ መጀመር አንስቶ ኢትዮጵያ እና ግብጽ አንድ ጊዜ ሲኮራረፉ በሌላኛው ሲታረቁ ዓመታት ተቆጥረዋል። በዚህ ቅራኔ ሳቢያ ሳዑዲ አራቢያ ሁለቱን ሃገራት ለማግባባት በሚል ደፋ ቀና ስትል ጉዳዩ ወደ ጦርነት ሊያመራ ይችላል ተብሎ ተሰግቶ ነበር። አሁን ደግሞ አሜሪካ ሁለቱን ሃገራት ላስታርቅ እያለች ነው። ምንም እንኳ የትራምፕ መንግሥት ለግብፅ ይወግናል ሲሉ የአሜሪካንን ጣልቃ ገብነት ያልስደሰታቸው ቢኖሩም። የግብጽ ስጋት የግብፅ ፍራቻ ኢትዮጵያ ግድቡን መሙላት ስትጀምር ከአባይ ወንዝ ወደ ናይል የሚወርደው የውሃ መጠን ይቀንሳል ነው። ይህ ደግሞ በተዘዋዋሪ ለኢትዮጵያ ኃያልነት ያድላታል። ምንም እንኳ በውሃ የሚሠሩ ኃይል አመንጭ ግድቦች ውሃ ባያባክኑም ኢትዮጵያ በምን ያህል ነው ግድቡን የምትሞላው የሚለው ግብፅን ከሚያሳስቡ ጉዳዮች አንዱ ነው። ግድቡ ሲጠናቀቅ ግሬተር ሎንዶን ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ውሃ በላይ ቦታ ይይዛል የሚባልለት የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ለመሙላት የሚወስድባት ጊዜ ረዘም ያለ ከሆነ ግብፅ ይህን ያህል ጭንቀት ይኖርባታል ተብሎ አይታሰብም። ሶስቱ ሃገራት ከዚህ ቀደም በነበራቸው ስምምነት መሠረት ኢትዮጵያ ግድቡን በሰባት ዓመታት ሞልታ ማጠናቀቅ ትፈልጋለች። ግብጻዊቷ ዘፋኝ አባይ ላይ ቀልደሻል ተብላ እስር ተፈረደባት ዕቅዳችን በሚመጣው ክረምት ሙሙላት መጀመር ነው። በሁለት ማመንጫዎች ተርባይን በመታገዝ ታኅሣሥ ላይ ኃይል ማመንጨት እንጀምራለን ሲሉ የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ስለሺ በቀለ ዶ ር ኢንጅነር መናገራቸው አይዘነጋም። ግብጽ ግን ሰባት ዓመት የሚለው የተዋጣላት አይመስልም። ለዚህ ደግሞ እንደ ምክንያት የጠቀሰችው ውሃው በአንድ ጊዜ መጠኑ እንዳይቀንስ የሚል ነው። አጭር የምስል መግለጫ የውሃ፣ መስኖና ኤነርጂ ሚኒስትር ስለሺ በቀለ ዶ ር ኢንጅነር ባፈለው ሳምንት አዲስ አበባ ላይ ሶስቱ ሃገራት ተገናኝተው ያደረጉት ውይይት ፍሬያማ አልሆነም። የውሃ፣ መስኖና ኤነርጂ ሚኒስትሩ ግብፅ ስምምነት ላይ የመድረስ ሃሳብ የላትም ሲሉ ይወቅሳሉ። ስምምነት ላይ ለመድረስ ዝግጁ ሆነው የመጡ አልመሰለኝም። በዚያ ላይ አዲስ የሙሊት መርሃ ግብር ይዘው መጥተዋል። ይህ መርሃ ግብር ከ ዓመታት የሚል ነው። ይህ ደግሞ በፍፁም ተቀባይነት የለውም። የግብፁ ውሃ ሚኒስትር ሞሐመድ አብደል አቲ በበኩላቸው ሶስቱ ወገኖች በግድቡ አሞላል ዙሪያ አሁን የተሻለ መግባባት ላይ ናቸው ሲሉ ተደምጠዋል። አምሳለ ዋካንዳ በጢስ አባይ ይገነባ ይሆን የግብፅ አቋም ግብፅ በመቶ የውሃ ፍላጎቷን የምታሟላው ከናይል ወንዝ ነው። ሃገሪቱ ሁልጊዜም ስትል እንደምትደመጠው የናይል ወንዝ ሕልውና ማለት የግብፅ ሕልውና ማለት ነው። የግብፁ ፕሬዝደንት አብድል ፋታህ አል ሲሲ ባለፈው መስከረም ግብፅ የራሷ ችግር ላይ የአረቡ ዓለም አብዮት ባትሆን ኖሮ ኢትዮጵያ ግድቡን መገንባት ስትጀምርም ነበር ማለታቸው ይታወሳል። ከአባይ ወንዝ የሚመጣው የውሃ ኃይል ቀነሰ ማለት የናስር ሐይቅ አቅም ተዳከመ ማለት ነው። ናስር ኃይቅ ደግሞ ግብፅ አብዛኛውን የኤሌክትሪክ ኃይሏን የምታገኝበት የአስዋን ግድብ ደጀን ነው። ግብፅ እንደ ቅድመ መስማሚያ ካስቀመጠቻቸው ሃሰቦች አንዱ የአስዋን ግድብና የሕዳሴ ግድብ ይገናኙ የሚል ነው። ይህ ተግባራዊ ሊሆን አይችልም ብለው ለግብጽ ተደራዳሪዎች እንደ ነገሯቸው ሚኒስትር ስለሺ ይናገራሉ። ኢትዮጵያ ግዙፍ ግድብ መገንባት ለምን አስፈለጋት በብዙ ቢሊዮን ብር ወጪ የሚገነባው የሕዳሴ ግድብ የኢትዮጵያ ዕድገት ልብ ምት ተደርጎ ይቆጠራል። ግድቡ ሲጠናቀቅ ሺህ ዋት የኤልክትሪክ ኃይል የማመንጨት አቅም ይኖረዋል። በርካታ ሕዝብ የኤሌክትሪክ ኃይል እንደልብ ለማያገኝባት ኢትዮጵያ የግድቡ አስፈላጊነት የማያጠያይቅ ነው። ከዚህ ባለፈም እያደገ ለመጣው የማኒዩፋከቸሪንግ ዘርፍ ትልቅ እፎይታን የሚሰጥ ነው። ኢትዮጵያ ግድቡ ሙሉ በሙለ ኃይል ማመንጨት ሲጀምርላት ለጎቤት ሃገራትም ኮረንቲ መሸጥ ትችላለች። ሱዳን፣ ደቡብ ሱዳን፣ ኤርትራና ጂቡቲ ከሕዳሴው ግድብ ጥቅም ሊያገኙ ይችላሉ። ሌላኛው ኢትዮጵያ ከግድቡ የምታገኘው ጥቅም በገንዘብ የማይለካ ነው ይላሉ ባለሙያዎች ሉዓላዊነት። ትራምፕ ህዳሴ ግድብ ሲያልቅ እመርቃለሁ ማለታቸው ተሰማ ሁኔታዎች ወደ ጦርነት ያመሩ ይሆን ሁለቱ ሃገራት ካልተስማሙ ወደ ግጭት ሊያመሩ ይችላሉ የሚል ፍራቻ ነበር። ላይ የተለቀቀ አንድ ተንቀሳቃሸ ምስል የግብፅ ፖለቲከኞች ኢትዮጵያ ላይ ሊሰነዘሩ የሚችሉ ጥቃቶች ላይ ሲመክሩ አሳይቷል። ፕሬዝደንት አብዱል ፈታህ አል ሲሲም ግብፅ የትኛውንም ዓይነት እርምጃ ትወስዳለች ሲሉ ተሰምተዋል። የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር አበይ አሕመድም ለሕዝብ እንደራሴዎች ባደረጉት ንግግር የትኛውም ዓይነት ኃይል ኢትዮጵያን አያቆማትም ሲሉ ተናግረዋል። አሜሪካ በሁለቱ ሃገራት መካከል ጣልቃ መግባቷ የጉዳዩን አሳሳቢነት ያሳያል። ግብጽ የአሜሪካን አደራዳሪነት ቀድም ጠይቃ ነበር። ኢትዮጵያ በበኩሏ የአሜሪካን ጣልቃ ገብነት አልፈቀደችም ነበር። በአሁኑ ወቅት የሶስቱ ሃገራት የቴክኒክ ኮሚቴዎች ባደረጓቸው ውይይቶች ላይ አሜሪካ እና የዓለም ባንክ የታዛቢነት ድርሻ ኖሯቸው በውይይቶቹ ላይ ተካፋይ ሆነው ቆይተዋል። በቀጣይስ የሶስቱ ሃገራት የውጪ ጉዳይ ሚንስትሮች ከትናነት ጀምሮ አሜሪካ ላይ ተገናኝተው በመምከር ላይ ናቸው። ሃገራቱ በቀጠሯቸው መሠረት ጥር መስማማት ላይ ካልደረሱ ጉዳዩ ወደየ ሃገራት መሪዎች ወይም ወደ ሶስተኛ አደራዳሪ አካል ሊመራ ይችላል። የመጀመሪያው አማራጭ ከአወያይ አካል ቁጭ ብሎ ለመስማማት መሞከር ነው። ሶስቱም ሃገራት መስማማት አለባቸው። አንቀፅ በአንድ ሃገር ይሁንታ ላይ ብቻ ተመሥርቶ ሃሳብ ይፅደቅ አይልም ይላል የኢትዮጵያ ውሃ ሚኒስትር ስለሺ በቀለ። ተያያዥ ርዕሶች
በሰዎች ይዞታ ሥር የቆዩ የዱር እንስሳት ታሪክ
ኦክተውበር ማጋሪያ ምረጥ በርካታ የዱር አራዊትና አዕዋፍ ከተፈጥሯዊው የመኖሪያ ሥፍራቸው ተለይተው እየተወሰዱ ለጉዳት በሚያጋልጣቸው ሁኔታ እንዲቀመጡ ማድረግ የወንጀል ድርጊት ነው። ከዚህ ሲከፋ ደግሞ በህገ ወጥ መንገድ ከሃገር እንዲወጡ ይደረጋል። በተለይ ደግሞ በድብቅ ከሃገር ለማስወጣት በሚደረገው ጥረት እንስሳቱ ለሞት ይዳረጋሉ። የሃገሪቱን ህግ በተጻረረ መልኩ ከአዕዋፍ እስከ አንበሳ ድረስ በግለሰቦች እጅ ተይዘው ለስቃይና ለጉዳት ይዳረጋሉ። አንበሳ ደግሞ ከፍተኛ ስቃይ ከሚደርስባቸው እንስሳት መካከል አንዱ ነው። በረከት ግርማ ሆለታ ከተማ የሚገኘው፤ የቦርን ፍሪ በጎ አድራጎት ድርጅት የሚያስተዳድረው እንስሳ ኮቴ ተብሎ የሚጠራው ማዕከል ሥራ አስኪያጅ ነው። ይህ ማዕከል በከፋ አያያዝ ለተጎሳቆሉና ለተጎዱ የዱር እንስሳት ክብካቤ ያደርጋል። በረከት ማዕከሉን ባስጎበኘን ወቅት ከግለሰቦች እጅና ከህገ ወጥ የእንስሳት አዘዋዋሪዎች የታደጓቸውን በርካታ የዱር አራዊትና አዕዋፍ አሳይቶናል። በጣቢያው ውስጥ የሚገኙት ሁሉም እንስሳት የራሳቸው የሆነ አስደናቂ ታሪክ አላቸው። ዶሎ ወደ ማዕከሉ ሲያመሩ በመጀመሪያ ሊመለከቷቸው ከሚችሏቸው እንስሳት መካከል አንበሳው ዶሎ አንዱ ነው። ዶሎ በሱማሌ ክልል ዶሎ አዶ በሚባል ስፍራ በአንድ ሜትር ሰንሰለት ታስሮ በጨለማ ክፍል ውስጥ ዓመታትን አሳልፏል። ለረጅም ዓመታት በጨለማ ክፍል ውስጥ ታስሮ መቀመጡ ዶሎን ለዓይነ ስውርነት ዳርጎታል። በረከት እንደነገረን ግለሰቦቹ ዶሎን ያገኙት በደቦልነቱ ነበር። ከዚያ ጊዜ አንስቶ በአንገቱ ዙሪያ የታሰረው ሰንሰለትም ዶሎ እያደገ ሲሄድ አንገቱን ከመከርከሩ በላይ ቆዳውን አልፎ ገብቶ ከፍተኛ ጉዳት አድርሶበታል። አጭር የምስል መግለጫ ዶሎ በግለሰብ እጅ እያለ ከዚህም በተጨማሪ ይዘውት የነበሩት ሰዎች ተገቢውን የምግብ ዓይነትና መጠን ከመስጠት ይልቅ ይመግቡት የነበረው ከሆቴል የሚገኝን የምግብ ትርፈራፊ ነበር። ይህም የሰውነቱ መጠኑን በእጅግ እንዲቀንስና ጎፈሩ እንዲራገፍ አድርጎት ነበር። ወደ ማዕከሉ ከተወሰደ በኋላ ግን በተደረገለት ክብካቤ ከፍተኛ ለውጥ አሳይቷል። አጭር የምስል መግለጫ ዶሎ አሁን በማዕከሉ ውስጥ ተፈጥሯዊና ሰላማዊ በሆነ በተከለለ ቦታ ላይ ይገኛል ሳፊያ ከጥቂት ዓመታት በፊት ሁደታ በተባለ በደቡብ ኢትዮጵያ ባለ ቦታ የአንበሳ ደቦል በሰንሰለት ታስራ በግለሰቦች እጅ ትገኛለች የሚል መረጃ ለቦርን ፍሪ ማዕከል ይደርሳል። የማዕከሉ ሰራተኞች ወደ ተባለው አካባቢ ሲደርሱም ሳፊያ በአነስተኛ ጎጆ ውስጥ በስንሰለት ታስራ በልጆች በተወረወረ ድንጋይ የፊት እግሯ ተሰብሮ አገኟት። ሳፊያ በወቅቱ ኪ ግ ብቻ ነበር የምትመዝነው። በቦርን ፍሪ አማካኘነት በተደረገላት ክብካቤ ዛሬ ላይ ከዶሎ ጋር በእንስሳ ኮቴ ማዕከል ውስጥ በተከለለላቸው ተፍጥሯዊ ቦታ እየኖሩ ይገኛሉ። አንድሪያ እና ጃኖ አንድሪያ እና ጃኖ የተባሉት ወንድማማች አንበሶች ከብሔራዊ ቤተ መንግሥት በቀድሞ ፕሬዝዳንት ግርማ ወ ጊዮርጊስ መልካም ፍቃድ ወደ ጣቢያው የመጡ ናቸው። በረከት እንደነገረን አንዲሪያ እና ጃኖን ጨምሮ አብዛኛዎቹ በእንስሳ ኮቴ የሚገኙት አንበሶች በሰዎች ቁጥጥር ሥር ለበርካታ ዓመታት ስለቆዩ ወደ ዱር ተመልስው ለመኖር ይከብዳቸዋል። ስለዚህ በተቻለ መጠን ከስው ጋር ቀጥተኛ ግንኘነት እንዳይኖራቸው በማድረግ ተፈጥሯዊ በሚመስል የተከለለ የመኖሪያ አካባቢ ላይ እንዲኖሩ ይደረጋል ብሏል። አቦ ሸማኔዎች አዕዋፍና የዱር አራዊት ተፈጥሮ በሰጠቻቸው የመኖሪያ ቦታቸው ላይ ሳይረበሹ የመኖር መብታቸውን ማንም ሊጋፋቸው አይገባም የሚለው በረከት በእንስሳኮቴ ማዕከል ውስት የሚገኙትንም አቦ ሸማኔዎች አስጎብኘቶናል። ከበረከት እንደሰማነው አቦ ሸማኔዎች ከሌሎች የዱር እንስሳት በተለየ መልኩ እንደ የቤት እንስሳት ሊላመዱ ይችላሉ። ይህ ተፍጥሯዊ ባህሪያቸው በአረብ ሃገራት በሚገኙ ከበርቴዎች ዘንድ ከፍተኛ ተፈላጊነት እንዲኖራቸው አድርጓል። ስለዚህም እንስሳቱ የህገ ወጥ የእንስሳት አዘዋዋሪዎች ኢላማ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል። በአሁኑ ወቅት በእንስሳ ኮቴ ማዕከል ውስጥ አቦሸማኔዎች ይገኛሉ። ከእነዚህም መካከል ህገ ወጥ የእንስሳት አዘዋዋሪዎች ወደ መካከለኛው ምሥራቅ ሲያጓጉዟቸው ድንበር ላይ የተያዙ ይገኙበታል። ከዚህ በተጨማሪም በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ወደ ሶማሌላንድ በሚጓዙ ተሸከርካሪዎች ላይ በሚደረጉ ፍተሻዎች የተገኙ አቦሸማኔዎችም አሉ። አጭር የምስል መግለጫ በረከት ግርማ በየጊዜው በህጋዊና ህገወጥ በሆነ አደን ምክንያት በሰዎች የሚገደሉት የዱር አራዊትና አዕዋፍ ስፍር ቁጥር የላቸውም፤ የሚለው በረከት እንስሳትን የመጠበቅና የመንከባከብ ሃላፊነት የሁሉም መሆን አለበት ይላል። የቦርን ፍሪ የእንስሳት መንከባከቢያ ማዕከል የሆነው እንስሳ ኮቴ ለጉዳት ለተጋለጡ የዱር አራዊትና አዕዋፍ መጠለያና ማገገሚያ በመሆን እጁ የገቡትን እንስሳት እየታደገ ይገኛል። ተያያዥ ርዕሶች
ግብፅ በህዳሴው ግድብ ዙሪያ አዲስ ሃሳብ አቀረበች
ዲሴምበር ማጋሪያ ምረጥ አጭር የምስል መግለጫ የግብፅ እና የኢትዮጵያ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሮች የግብፁ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳሚ ሹክሪ ከኢትዮጵያው አቻቸው ከዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ ጋር ባደረጉት ውይይት የሁለትዮሽ ግንኙነትን በማጠናከር ላይ የተነጋገሩ ሲሆን፤ ሹክሪ ቀላልና ተግባራዊ መሆን የሚችል ያሉትን ምክረ ሃሳብ ኢትዮጵያ እንደምትመለከተው ዶክተር ወርቅነህ ገልፀዋል። የሁለቱ ሃገራት መሪዎች ለጉዳዩ ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት እየሰሩ መሆናቸውን ያስታወሱት ሳሚ ሹክሪ፤ ሉአላዊነትን፣ የጋራ መተማመንን መሰረት ያደረጉና ዓለም አቀፍ ሕግን የተከተሉ ሥራዎች ተከናውነዋል ብለዋል። ሆኖም ግን ላለፉት አስር ወራት ሲካሄዱ የቆዩት ውይይቶች በቂ ውጤት ማስገኘት አለመቻላቸውንም ገልፀዋል። የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳዮች ሚንስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ በበኩላቸው፤ የህዳሴው ግድብ ግንባታ የሚፈጥረው ስጋት እንደማይኖር በመግለፅ አለመግባባቶች ሲኖሩም ሕጋዊ አሰራሮችን በመከተል መፍታት ይቻላል። በሁለቱም ሃገራት የሚቆጣ ህዝብ አይኖርም። ኢትዮጵያም ግብፅን ለመጉዳት የምትሰራው ሥራም አይኖርም ብለዋል። በመቶ ህዝባቸው በረሃማ በሆነ አካባቢ እንደሚኖርና ህይወቱም በአባይ ወንዝ ላይ የተመሰረተ መሆኑን ያስታወሱት የግብፁ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር የግብፅ ህዝብ ተቆጥቷል ባልልም ስጋት ላይ መውደቁን ግን መናገር እችላለሁ ሲሉ ተናግረዋል። ቢሆንም ግን የኢትዮጵያን የመልማት እንቅስቃሴ እንደሚቀበሉ አስታውቀዋል። ጉዳዩ የሁለቱ ሃገራት ብቻ ሳይሆን ሱዳንንም እንደሚመለከት የገለፁት ሁለቱም ሚንስትሮች፤ በውይይትና በጋራ በመስራት መፍትሄ ለማምጣት እንደሚጥሩ ገልፀዋል። ፖለቲካዊ ሳይሆን ሳይንሳዊ ጥናቶችን መሰረት ያደረገ መፍትሄ እንደሚበጅና ተቀባይነት እንደሚኖረውም ሳሚ ሹክሪ ተናግረዋል። አዲሱ ምክረ ሃሳብ የእስካሁኑን መጓተት ለማካካስና ቶሎ ወደ መፍትሄ ለመግባት የሚረዳ ቀላል፣ ከፖለቲካዊ እሳቤ የራቀና ተግባራዊ ሊሆን የሚችል መሆኑን ሹክሪ አስረድተዋል። ጉዳዩን ለፖለቲካና ለመሪዎች ብቻ የሚተው አለመሆኑን በማስረዳት ጥናቱን እንዲያካሂድ የሦስታችንንም ሃገራት ፍቃድና ተቀባይነትን ያገኘው ዓለም አቀፉ ተቋም፤ የሚደርስበትን ማንኛውንም ውጤት ግብፅ ትቀበላለች ሲሉም አረጋግጠዋል። ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ በበኩላቸው በህዳሴው ግድብ ዙርያ ግልፅ ለመሆን እየጣርን ነው። አሁን የቀረበውን ምክረ ሃሳብንም እናየዋለን። የሦስት ሃገራት ጉዳይ ስለሆነ በጥንቃቄ መያዝና መታየት አለበት ብለዋል። ሃገራቱ በሌሎች የሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ በተጠናከረ መንገድ የመስራት ፍላጎት እንዳላቸው ሚንስትሮቹ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ አሳውቀዋል። ተያያዥ ርዕሶች
አሜሪካ የአባይ ወንዝ አጠቃቀምን በተመለከተ መግለጫ አወጣች
ኦክተውበር ማጋሪያ ምረጥ በኢትዮጵያ፣ በግብጽና በሱዳን መካከል የታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ውሃ የመሙላት ሂደትንና አጠቃቀም ላይ ትብብር፣ ዘላቂነትና የጋራ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥን በተመለከተ እየተደረገ ያለውን ድርድር እንደምትደግፈው አሜሪካ አስታወቀች። ይህ የተገለጸው ከኋይት የፕሬስ ጽህፈት ቤት ሐውስ በወጣና ዝርዝር ጉዳዮችን በማይጠቅሰው አጭር መግለጫ ላይ ሲሆን፤ መግለጫው የወጣበት ምክንያትም አልተገለጸም። በዚህ አጭር መግለጫ ላይ ሁሉም የአባይ ተፋሰስ አገራት በምጣኔ ሃብት የመልማትና የመበልጸግ መብት አላቸው ይልና ሲቀጥል አስተዳደሩ የአሜሪካ ሁሉም አገራት እነዚህን መብቶች ሊያስከብር የሚችልና የእያንዳንዳቸውን የውሃ ፍትሃዊ ተጠቃሚነትን የሚያስከብር በጎ ፈቃደኝነትን የተላበሰ ስምምነት ላይ እንዲደርሱ ጥሪ ያቀርባል ይላል። የሚፈርስ የግድቡ አካል የለም የግድቡ ዋና ሥራ አስኪያጅ የፕሬዝዳንቱ ጽህፈት ቤት የፕሬስ ክፍል ይህንን መግለጫ ከምን ተነስቶ እንዳወጣ የገለጸው ነገር የሌለ ሲሆን ተጨማሪ የሰጠው ማብራሪያም የለም። ይህ መግለጫ ምናልባትም ዛሬና ነገ ካርቱም ውስጥ የሦስቱ አገራት ከፍተኛ ባለስልጣናት ያደርጉታል ተብሎ ከሚጠበቀው ቀጣይ የሦስትዮሽ ውይይት ጋር የተያያዘ እንደሚሆን ይገመታል። ባለፈው ሳምንት ረቡዕ ኒውዮርክ ላይ በተካሄደው የተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የግብጹ ፕሬዝዳንት አብዱል ፋታህ አልሲሲ ባደረጉት ንግግር ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ላይ እየገነባች ያለችውን ግድብን በተመለከተ የሚደረገው ድርድር ውጤት ላይ አለመድረሱ በአካባቢው ላይ አለመረጋጋትን ሊያስከትል እንደሚችል መናገራቸው ይታወሳል። ይህንንም ተከትሎ የኢትዮጵያዋ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በዚያው መድረክ ላይ ለግብጹ ፕሬዝዳንት ንግግር ምላሽ በሚመስል ሁኔታ የአባይ ወንዝ ለተፋሰሱ ሀገራት የጋራ ሃብት እንጂ የጥርጣሬና የውድድር ምንጭ ሊሆን አይገባም በማለት ሃገራቱ የወንዙን ውሃ በጋራ መጠቀም እንዳለባቸው አመልክተዋል። ፕሬዝዳንቷ አክለውም የተፋሰሱ ሃገራት የአባይን ወንዝ የጋራ ተጠቃሚነትን ባረጋገጠ መልኩ ለመጠቀምም በትብብርና በቅንጅት ሊሰሩ እንደሚገባ በንግግራቸው ላይ አንስተዋል። ባለፈው መስከረም እና ዓ ም የኢትዮጵያ፣ የግብጽና የሱዳን ባለስልጣናት ካይሮ ላይ የግድቡን ውሃ አሞላል በተመለከተ በተከታታይ እያደረጉት ያለው የሦስትዮሽ ውይይት መካከል አንዱ የሆነው ካይሮ ላይ የተካሄደ ቢሆንም ያለስምምነት መጠናቀቁ ተነግሯል። የኢትዮጵያ የውሃ፣ መስኖና ኢነርጅ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ ከካይሮው ድርድር በኋላ አዲስ አበባ ላይ በሰጡት መግለጫ ግብጽ በግድቡ ውሃ አሞላል ላይ አዲስ ሃሳብ እንዳቀረበችና ኢትዮጵያ ሃሳቡን ውድቅ እንዳደረገች ተናግረዋል። እንደ ሚኒስትሩ ማብራሪያ ግብጽ ያቀረበችው ሃሰብ፤ የግድቡ የውሃ የሚሞላው በሰባት ዓመት እንዲሆን፣ ኢትዮጵያ በዓመት ቢሊየን ሜትር ኪዮብ ውሃ እንድትለቅና የአስዋን ግድብ የውሃ መጠኑ ከምድር ወለል በላይ ሜትር ላይ ሲደርስ ግድቡ በዋናነት ውሃ እንዲለቅ የሚጠይቅ ነው። ኢትዮጵያም ይህ የግብጽ ሃሳብ ቀደም ሲል በሦስቱ ዋነኛ የተፋሰሱ አገራት መካከል የተፈረመውን የአባይ ወንዝ ውሃን አጠቃቀም የተመለከተውን የመርህ ስምምነት የጣሰና ጎጂ ግዴታን የሚያስቀምጥ ነው በማለት እንደማትቀበለው አሳውቃለች። ለህዳሴ ግድብ ግንባታ መዘግየት ምን አይነት መፍትሔዎች እየተሰጡ ነው ሚኒስትሩ በተጨማሪም ይህ የቀረበው ሃሳብ ግብጽ የወንዙ ዓመታዊ የውሃ ፍሰት ቢልየን ሜትር ኪዩብ እንዲሆን ያቀረበችው ጥያቄ፤ በተዘዋዋሪ ኢትዮጵያ የአባይ ውሃን እንዳትጠቀም የሚከለክል በመሆኑ አልተቀበለችውም ብለዋል። በግድቡ የውሃ አሞላልና የመልቀቅ ሂደት ዙሪያ ያሉትን ሁኔታዎች እንዲያጠና የተቋቋመው የኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብጽ የሦስትዮሽ ብሔራዊ ገለልተኛ የሳይንሳዊ ጥናት ቡድን ኛ ስብስባውን ካርቱም ሱዳን ውስጥ ሰኞ እለት አካሂዶ የነበረ ሲሆን፤ ቡድኑ ዛሬ መስከረም እና ዓ ም እዚያው ካርቱም በሚካሄደው የሦስቱ አገራት የውሃ ሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ ሪፖርት እንደሚያቀርብ ይጠበቃል። ተያያዥ ርዕሶች
ከኢንጅነር ስመኘው ሞት በኋላ ታላቁ ህዳሴ ግድብ ምን ላይ ደረሰ
ጁላይ ማጋሪያ ምረጥ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ከጅማሮው በዋና ሥራ አስፈጻሚነት ሲመሩት የነበሩት ኢንጅነር ስመኘው በቀለ ከዚህ ዓለም በሞት ከተለዩ አንድ ዓመት አስቆጠሩ። ኢንጂነር ስመኘው በቀለ በመስቀል አደባባይ መኪናቸው ውስጥ ህይወታቸው በድንገት አልፎ ከተገኘ በኋላ፤ በወቅቱ የፌደራል ፖሊስ በሰጠው መግለጫ ኢንጅነሩ ራሳቸውን እንዳጠፉ በምርመራው እንደደረሰበት ማሳወቁ ይታወሳል። መኪናቸው ውስጥ የተገኘውም ሽጉጥ የኢንጂነሩ እንደነበር በምርመራው አረጋግጫለሁ ብሏል። ስለአዲሱ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ሥራ አስኪያጅ ጥቂት እንንገርዎ የግድቡ ምልክት ተደርገው የሚወሰዱት ኢንጅነር ስመኘው ሞት፣ በርካቶችን ያስደነገጠ እና ኃገሪቱ በቢሊዮን ዶላር የሚቆጠር ገንዘብ የፈሰሰበት የህዳሴ ግድብ ከየት ይደርሳል የሚል ስጋትን የፈጠረም ነበር። በኢንጅነር ስመኘው ቦታ የተተኩት የህዳሴ ግድብ ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢንጅነር ክፍሌ ሆሮ፤ አንድ ሰው በግሉ የሚቻለውን ያክል ነው አስተዋጽኦ ማበርከት የሚችለው እንጂ የጀመረውን ሁሉ ይጨርሳል ማለት አይደለም በማለት የቀድሞውን የፕሮጀክቱን መሪ ያስታውሳሉ። አክለውም ህዳሴ ግድብ የህዝብ ነው። እኔም አሻራዬን ትቼ ላልፍ እችላለሁ የኢንጅነር ስመኘውን አስተዋጽኦንም እንዲሁ ነው የምመለከተው ይላሉ። የቀድሞው የሕዳሴ ግድብ ፕሮጀክት መሪ ከሞቱ በኋላ ባለፉት አስራ ሁለት ወራት የህዳሴ ግድብ አፈጻጸም እንዴት ነው ምን ተለወጠ ምን ችግር አጋጠመው ከኢንጅነር ክፍሌ ጋር ቆይታ አድርገናል። የሚፈርስ የግድቡ አካል የለም የግድቡ ዋና ሥራ አስኪያጅ ፕሮጀክቱ ለምን ዘገየ ኢንጅነር ክፍሌ ፕሮጀክቱ በታቀደለት የጊዜ ገደብ ባይሄድም በአሁኑም ወቅት ህዝብ እና መንግሥት ለአባይ ግድብ የሚያደርጉትን ድጋፍ እንዳላቋረጡ ይናገራሉ። በዋናነት ከፕሮጀክቱ ጋር በተያያዘ ያጋጠሙ ሁለት ፈተናዎች አሉ የሚሉት ኢንጅነር ክፍሌ የመጀመሪያው ከስነ ምድር ጋር የተያያዘ እንደሆነ ይገልጻሉ። የአባይ ወንዝ የሚሄድበት መሬት ሥሩ ጠንካራ ነው ተብሎ ወደ ስራ መገባቱን ገልፀው፤ ወደ ስራ ከተገባ በኋላ ግን መሬቱ እንደተጠበቀው ሳይሆን እንደቀረና መሬቱን ቆፍሮ በኮንክሪት የመሙላቱ ሥራ ብዙ ጊዜ መውሰዱን ኢንጅነር ክፍሌ ያስረዳሉ። ለህዳሴ ግድብ መዘግየት እንደ ሁለተኛ ምክንያትነት የሚጠቅሱት ደግሞ ከብረታብረት እና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ሜቴክ ጋር የተያያዘ ነው። እንደ ኢንጅነር ክፍሌ ከሆነ መንግሥት የህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ተቀርፆ ወደ ግንባታው ሲገባ በተቻለ መጠን በግድቡ ላይ ሃገር በቀል ተቋማት አስተዋጽኦዋቸውን እንዲያበረክቱ ቅድሚያ ተሰጥቷቸው ነበር። በዚሁ መንፈስ ብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ሜቴክ ሥራውን እንዲያከናውን በንዑስ ተቋራጭነት እንዲሰራ መወሰኑን ያስረዳሉ። ተቋሙ የኤክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብን የመገንባት አቅምም ሆነ ልምድ ስለሌለው የግንባታ ስራውን ወደፊት ማስኬድ አልቻለም ብለዋል። ፕሮጀክቱ ላይ ብዙ ቢሊየን ብር ቢፈስም፤ መልክ አልያዘም ይላሉ። በአሁኑ ሰዓት የሲቪል ሥራው ወደ በመቶ በላይ ቢጠናቀቅም፤ የኤሌክትሮ መካኒካል ስራው በመቶ የደረሰ ሲሆን በአጠቃላይ ፕሮጀክቱ ወደ ስልሳ ስምንት በመቶ መድረሱን ተናግረዋል። መጋቢት ፣ ዓ ም በነበረው የታላቁ ህዳሴ ግድብ ሕዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ምክርቤት ጽሕፈት ቤት፣ ከሚዲያ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ጋር በነበረው የውይይት መድረክ የግድቡ የግንባታ ቡድን ተወካይ አቶ ኤርሚያስ ውብሸት የግድቡ የሲቪል ሥራ በመቶ፣ የኤሌክትሮ ሜካኒካል ስራ በመቶ እና የብረታ ብረት ስራ መድረሱንና በአጠቃላይ ፕሮጀክቱ በመቶ ደርሷል ብለዋል። መንግሥት ለሜቴክ ተሰጥቶ የነበረውን ውል ካቋረጠ በኋላ በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና እና ልምድ ላላቸው ለአዳዲስ ተቋራጮች በመስጠት ወደ ስራ እንዲገቡ የማድረግ ተግባርም ተከናውኗል ። በግንባታ ስራው ተሰማርተው የሚገኙት ስድስትተቋራጮች እንደሆነ የሚናገሩት ኢንጅነር ክፍሌ፤ ከእነዚህም መካከል የፈረንሳይ፣ ጀርመን እና ቻይና ኩባንያዎች ይገኙበታል ይላሉ። በውይይት መድረኩ ላይም እንደተጠቀሰው ከተቋራጮቹም መካከል ሲጂጂሲ፣ ሳይኖ ሃይድሮ፣ ቮይት፣ ጂኦ ሃይድሮ ፍራንስና ኤክሲዲ ይገኙበታል በማለት በስም ይዘረዝራሉ። እንደ ተርባይን ያሉ ከውሃ ጋር ግንኙነት ያላቸው ግንባታዎች ከፍተኛ ልምድ የሚጠይቁ ሥራዎች መሆናቸውን ኢንጅነር ክፍሌ ገልፀው አዳዲሶቹ ተቋራጮች የግንባታ ሥራውን በተቀላጠፈ ሁኔታ እየሠሩ እንደሚገኙ ለቢቢሲ ተናግረዋል። የሳሊኒ ቅሬታ እና የፕሮጀክቱ ክንውን የሲቪል ሥራውን ለማከናወን ኮንትራት ወስዶ ሲሰራ የቆየው የጣሊያኑ ሳሊኒ ከግንባታ ክፍያ መዘግየት ጋር ተያይዞ ቅሬታዎችን ሲያሰማ ነበር። ኢንጅነር ክፍሌ እንደሚሉት ሳሊኒ ያነሳቸው ቅሬታዎች አግባብነት ከተጠና በኋላ መንግሥት እና ሳሊኒ ከመግባባት ላይ ደርሰዋል ይላሉ። ሳሊኒ ሲያነሳው የነበረው ቅሬታ ፕሮጀክቱ የዘገየው እኔ በፈጠርኩት ችግር አይደለም። ሜቴክ የሚጠበቅበትን የተርባይን እና ሌሎች ለፕሮጀክቱ የሚያስፈልጉ ብረቶችን በወቅቱ ማቅረብ ቢችል ኖሮ ሥራውን በሰዓቱ ማጠናቀቅ እችል ነበር። ፕሮጀክቱ በመዘግየቱ ለኪሳራ ተጋልጫለሁ የሚል ነበር በማለት ኢንጅነር ክፍሌ ያስረዳሉ። ሳሊኒ በዚህ ምክንያት ለደረሰበት ኪሳራ መንግሥት ካሳ እንዲከፍለው ጥያቄ አቅርቦ ነበር። ኢንጂነር ስመኘው በቀለ ሕይወታቸው ያለፈው በጥይት ተመተው ነው፡ ፌደራል ፖሊስ ከሳሊኒ ጋር ያለው ጉዳይ አልተፈታም። በመንግሥት የተወሰደው እርምጃ በዚህ የመዘግየት ምክንያት ኪሳራ ደርሶበት አስጊ የሆነ የገንዘብ ደረጃ ላይ በመድረሱ፤ ሳሊኒ ይገባኛል የሚለው ጥያቄ እልባት እስኪያገኝ ድረስ በታሳቢነት ሚሊዮን ብር እንዲከፈለው ተወስኗል። ይህ የተወሰነው ስራውን ከማስቀጠል አንፃር ነው። የሳሊኒ ያቀረበው የኪሳራ ይገባኛል ካሳ ሙሉ በሙሉ መቀበል ማለት አይደለም። እየታየ እንዲሁም እየተጠና ነው። እውነት ይህ ሁሉ ኪሳራ ይደርስበታል ለሚለውም በዝርዝር እየታየ ነው ይላሉ ኢንጅነር ክፍሌ። ፕሮጀክቱ በመዘግየቱ ሳሊኒ ብቻ ሳይሆን ጉዳቱ የኢትዮጵያ ህዝብ ጭምር ነው የሚሉት ኢንጅነር ክፍሌ፤ እውነት ለመናገር ህዝቡ በግንባታው ሞራሉ ተነክቷል። ግንባታው የደረሰበትን ደረጃ በማስመልከት ለህዝብ የሚሰጠው መረጃ የተሳሳተ ነበር። እውነቱ ተደብቆ ቆይቶ በአንዴ እውነቱ ሲገለጥ ህዝቡ ማዘኑ አልቀረም ይላሉ። መቼ ይጠናቀቃል ፕሮጀክቱ በተጀመረበት ወቅት በአራት ዓመት ውስጥ በሁለት ተርባይኖች አማካኝነት ኃይል ማመንጨት ይጀምራል መባሉን እና በሰባት ዓመታት ውስጥ ደግሞ ሙሉ በሙሉ ይጠናቀቃል ተብሎ እንደነበረ ኢንጅነር ክፍሌ ያስታውሳሉ። ይህን መሰል ግዙፍ ፕሮጀክት በሰባት ዓመታት ውሰጥ መጨረስ ይቻላል ተብሎ መጀመሩ በራሱ ስህተት ነው የሚሉት ኢንጅነር ክፍሌ፤ ሜቴክ የሚጠበቅበትን በወቅቱ ማድረግ ቢችል ኖሮ ቢያንስ በ ላይ ኃይል ማመንጨት መጀመር ይቻል ነበር ይላሉ። ከሁለት አመታት በኋላ ኃይል የማመንጨት ጅማሮ እቅድ እንዳለ የሚናገሩት ኢንጅነር ክፍሌ በአራት ዓመታት ውስጥ ደግሞ ግንባታው ሙሉ በሙሉ የማጠናቀቅ እቅድም እንደተያዘ ይናገራሉ። ነገር ግን ተግዳሮቶች ሊያጋጥሙ እንደሚችሉም አልደበቁም። በተጠቀሱት ዓመታት ውስጥ ሁሉም ተርባይኖች ኃይል ማመንጨት ይጀምራሉ ማለት ሳይሆን በመጀመሪያ ግድቡ ውሃ የሚሞላበት ሁኔታ ላይ የታችኛው የተፋሰስ ሃገራትን ማወያየት ዋናው ስራ እንደሆነ ይናገራሉ። ተርባይኖቹ በሙሉ አቅም ኃይል የሚያመነጩት በግድቡ ውሃ መሙላት ላይ ተሞርኩዞ ነው። የተርባይኖቹ ስራ ግን ሙሉ በሙሉ ለመጨረስ ታቅዷል ይላሉ። የፕሮጀክቱ ተጨማሪ ወጪ ሃሳብ ሆኗል የዚህ ፕሮጀክት ወጪ ከህዝብ ከሚሰበሰበው እና መንግሥት ከሚመድበው በጀት ሲሆን፤ መንግሥት ተጨማሪ በጀት እየመደበ የግንባታ ሥራው እንዲቀጥል እያደረገ መሆኑንም ይናገራሉ። ህዝቡም ከ ቢሊዮን ብር በላይ በማዋጣት ለፕሮጀክቱ ግንባታ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከቱንም ጠቅሰዋል። የውጪ ምንዛሬ እጥረት እና ከግንባታው መጓተት ጋር በተያያዘ ተጨማሪ ወጪ ፕሮጀክቱን እንደጎዳው የሚናገሩት ኢንጅነር ክፍሌ ህዝብ እና መንግሥት አሁንም ፕሮጀክቱን ከግብ ማድረስ ያለስለሰ ጥረት እያደረጉ እንደሆነ ተናግረዋል። ተያያዥ ርዕሶች
በዶዶላ ቤተክርስቲያናት ተጠልለው የሚገኙ ምዕመናን ስጋት ላይ መሆናቸውን ገለፁ
ኦክተውበር ስለ ማጋራት ተጨማሪ ያጋሩ ማጋሪያ ምረጥ ባሳለፍነው ረቡዕ በተለያዩ ቦታዎች የተቀሰቀሰውን ግጭት ተከትሎ በምዕራብ አርሲ፤ ዶዶላ ከተማ በተፈጠረ ግጭት ለከፍተኛ ህክምና ወደ ሀዋሳ ሪፈራል ሆስፒታል የተላኩ ሁለት ግለሰቦችን ጨምሮ የ ሰዎች ሕይወት ማለፉን ከነዋሪዎችና ከሆስፒታል ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። የዶዶላ ወረዳ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ልሳናት ቀሲስ እየበሩ ዓለሙ ላለፉት አራት ቀናትም በሺዎች የሚቆጠሩ ምዕመናን በከተማዋ በሚገኙ ቤተክርስቲያናት ተጠልለው እንደሚገኙ ለቢቢሲ ገልፀዋል። በዚህም ጨቅላ ሕፃናት፣ እናቶች፣ ነፍሰጡር ሴቶች፣ አረጋዊያን እና ሕሙማን የከፋ ችግር ላይ መውደቃቸውን ይናገራሉ። የቤተ ክህነቱ ፀሐፊ ዲያቆን ደለለኝ ማሞ በበኩላቸው ባነጋገርናቸው ወቅት በሚገኙበት ኪዳነ ምህረት ቤተክርስቲያን ውስጥ ሁለት እናቶች ያለ ህክምና እርዳታ መውለዳቸውን ነግረውናል። ጭንቀት ውስጥ ነን ያለነው በዶዶላ ከተማ ኪዳነ ምህረት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ተጠልለው ከሚገኙት መካከል ስሟ እንዳይጠቀስ የጠየቀችን የሦስት ቀን አራስ ትገኛለች። ይህች እናት ረቡዕ ዕለት ወጣቶች ከፊት ለፊታቸው የነበሩ ቤቶችን ሲያቃጥሉ አይተው እግሬ አውጭኝ ብለው እንደሸሹና ሕይወታቸውንም ለማቆየት ቤተክርስቲያኗ ውስጥ እንደተጠለሉ ታስረዳለች። ወደኛ በኩል ድንጋይ ሲወረውሩ፤ በጓሮ በኩል አጥር ቀደን ወጣን፤ ምንም ሳንይዝ እያለቀስን ነው የወጣነው፤ በሰው ግቢ በኩል እየተረማመድን ወደ ቤተክርስቲያኗ መጣን ትላለች። የነበረው ሁኔታ በጣም አስፈሪ ነበር የምትለው አራሷ የተገላገለችውም ቤተክርስቲያኗ ውስጥ ነው። በልምድ የሚያዋልዱ ሰዎች ረድተውኝ በሰላም ተገላግያለሁ፤ ጡቴ ወተት እምቢ ብሎ፤ ውሃ በጡጦ እያጠባሁ ነው ያለሁት ትላለች። እርሷ እንደምትለው ከፍተኛ የሆነ የውሃ ችግር በመኖሩም ችግሩን አባብሶታል። ከሐዋሳ እናቷ ጋር ለመታረስ ብትመጣም በነበረው ብጥብጥ እናቷን ጨምሮ የሰባት ወር ህፃን የያዘች የአክስቷ ልጅ፤ በአጠቃላይ ሦስት ህፃናትና አራት አዋቂዎች ሆነው እንዳመለጡ ታስረዳለች። በቤተክርስቲያኗ ውስጥ በከፍተኛ የምግብ እጥረት እየተሰቃዩ እንደሆነ የምትናገረው እናት ቢቢሲ ከቀኑ ፡ አካባቢ ባናገራት ወቅት ምግብ እንዳልቀመሰችና ሻይ ብቻ እንደጠጣች ተናግራለች። ወደቤት ሄደውም ሆነ ውጭ ወጥተው ለመመገብ ለደህንነታቸው ስለሰጉ ችግር ላይ መሆናቸውን ታስረዳለች። ረቡዕና ሐሙስ ዕለት የተቃውሞ ሠልፍ በተካሄደባቸው የኦሮሚያ፣ ሐረርና ድሬዳዋ ከተሞች በክልሎችና በአስተዳደሩ ጥያቄ መሠረት የመከላከያ ሠራዊት መሰማራቱንና ሁኔታዎች እንደተረጋጉ ቢገለፅም አራሷ በዚህ ሃሳብ አትስማማም። ተረጋግቷል የሚባለው መንቀሳቀስ ሲቻል ነው። ያሉት ወታደሮች ቤተ ክርስቲያኗን በመጠበቅ ላይ ናቸው ትላለች። አክላም ያለነው በመከራ፣ በስቃይ ነው፤ ከፍተኛ ብርድ አለ፤ አራስ ሆነን ውጭ እያደርን ነው፤ የታመሙ ህፃናት አሉ፤ አንዲት የአምስት አመት ልጅ ቶንሲል ታማ ስታለቅስ ነበር ግን ምን ማድረግ ትችላለች ስትል መንግሥት እንዲደርስላቸው ተማፅናለች። ዲያቆን ደለለኝም በኪዳነ ምህረት ቤተ ክርስቲያን ከሁለት መቶ በላይ አባወራዎችም ልጆቻቸውንና ቤተሰባቸውን ይዘው በመቃብር ቤቶች እንዲሁም ድንኳን ውስጥ እንደሚገኙ ገልፀዋል። የሦስት ቀጠና ማህበረሰብ፤ ቀጠና ፣ እና በዚችው ቤተክርስቲያን ተጠልለው እንደሚገኙና ሌሎች ደግሞ በቅዱስ ገብረ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ይገኛሉ ብለዋል። በዛሬው ዕለት በአንፃሩ ከተማው እንደተረጋጋና ከቤተክርስቲያኗም በቅርብ ርቀት የሚገኙ ሰዎች ከቃጠሎ የተረፈ ንብረትም በመሰብሰብ ላይ የሚገኙ እንዳሉም ገልፀዋል። በቤተክርስቲያኗ ዙሪያ አንድ ፓትሮል፣ አስራ አምስት የማይሞሉ የመከላከያ ኃይል በአካባቢው እንዳለ ጠቅሰዋል። ይሁን እንጅ ተጠልለው የሚገኙት ምዕመናንም በምግብና ውሃ እጥረት እየተሰቃዩም እንደሆነ ለቢቢሲ ገልፀዋል። አንዳንድ ግለሰቦች ከውጭ ምግብ እያመጡ በሚረዱት ነው እየተዳደርን ያለነው። በጣም የተቸገርነው ደግሞ ውሃ መቅዳት ባለመቻሉ ነው። ይላሉ። ወደ ቤተ ክርስቲያኗ የሚመጣው የውሃ መስመር በመቋረጡ እንዲሁም ወንዝ ሄደው እንዳይቀዱ ለደህንነታቸው በመስጋታቸው በውሃ ጥም እንዲሰቃዩ ምክንያት መሆኑን ይናገራሉ። ቤተክርስቲያኗን ለቀው ቢወጡ አካባቢውን የሚጠብቀው ኃይል ለደህንነታቸው ዋስትና ስላልሰጣቸው አሁንም ስጋት እንዳደረባቸውና በጭንቀትም ላይ እንደሚገኙ ገልፀዋል። ሃይማኖትን መሠረት ያደረገ ጥቃት ነው የሚሉት ዲያቆን ደለለኝ ከሰባት ቤት በላይ ተቃጥሏል፣ የተዘረፈና የወደመ ንብረት አለ ይላሉ። ረቡዕ ዕለት በቤተክርስቲያኗ አባቶች ላይ ድብደባ እንደደረሰም ይናገራሉ። እስካሁን ባለው ስድስት ሰዎች እንደተቀበሩና በዛሬው ዕለትም ከሃዋሳ የመጣች የአንዲት ሴት ሥርዓተ ቀብር መፈፀሙን ይገልፃሉ። በሞትና በሕይወት ስላለው ሰው በቁጥር ልናገር አልችልም፤ ሦስት ሰዎች በሞትና በሕይወት መካከል ሆነው አሁንም በቤተክርስቲያኗ ውስጥ ነው ያሉት ሲሉም ጉዳት ያጋጠማቸው በርካታ ሰዎች መኖራቸውን ያስረዳሉ። በከተማዋ ገብረ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን እንደሚገኙ የገለፁልን የዶዶላ ወረዳ ቤተክህነት ኃላፊ ሊቀ ልሳናት ቀሲስ እየበሩም በበኩላቸው እንደ ኃይማኖት መሪ በግምት ለመናገር ቢቸገሩም በዚች ቤተክርስቲያን ብቻ ሺህ የሚሆኑ ሰዎች ተጠልለው እንደሚገኙ ገልፀውልናል። ከረቡዕ ዕለት አንስቶ በቤተክርስቲያኑ ውስጥ ህፃናት ፣ ሴቶች፣ አረጋዊያን ተጠልለው እንደሚገኙ ገልፀው፤ የተጎዳ ሰው ለመጠየቅ ትናንት ወደ ሆስፒታል በማምራት ላይ ሳለች ድብደባ የተፈፀመባት አንዲት ሴትም ሕይወቷ በማለፉ ዛሬ የቀብር ሥነ ሥርዓቷ እንደተፈፀመ ነግረውናል። በርካታ ሰዎች ላይ ዘግናኝ ጥቃት እንደተፈፀመ የተናገሩት ቀሲስ እየበሩ፤ የ ሰዎች ሕይወት ማለፉን፣ ቤቶች መቃጠላቸውን ፣ ንብረቶች መውደማቸውን ያክላሉ። ዛሬ ጠዋት ላይ መንገድ ተከፍቷል በሚል ከተለያየ ቦታ ለለቅሶና ለሌላ ጉዳይ የመጡ ነበሩ፤ እነርሱም ላይ የማዋከብና የማሰር ድርጊት እየተፈፀመ ነው ብለዋል። እስካሁን ድረስ በሥፍራው ተገኝተቶ የጎበኛቸው የመንግሥት ባለሥልጣናትም እንደሌሉ ይናገራሉ። በጣም የሚያሳዝን ነገር ነው የተፈፀመው፤ ሰው መረጋጋት አልቻለም። እናቶችና ሕፃናት እየተራቡ ናቸው፤ ውሃ ወጥቶ መቅዳት አልቻልንም። ወደ ፈጣሪ ከመጮህ ውጭ ሌላ የምናደርገው ነገር የለም ይላሉ። በቤተክርስቲያኗ ውስጥ አንድ መፀዳጃ ቤት ነው ያለው፤ ውሃ የለም ፤ ምግብ የለም ሲሉም በዚሁ ከቀጠለ ለበሽታ ሊዳረጉ እንደሚችሉ ስጋት አላቸው። ግጭቱም ከብሔር ጋር የተገናኘ ቢሆንም መልኩን ቀይሮ ወደ ሃይማኖት እንደዞረ በማስረዳትም በቤተክርስቲያኗ ውስጥ ተጠልለው የሚገኙት የተለያዩ ብሔር ብሔረሰቦች ስብጥር ያለውና በአብዛኛው የኦርቶዶክስ አማኞች መሆናቸውን ያስረግጣሉ። ዛሬ ቢቢሲ ያነጋገራቸው የዶዶላ አጠቃላይ ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር ዶክተር ቶላ ቢዮ ለከፍተኛ ህክምና ወደ ሀዋሳ ሆስፒታል ተልከው የነበሩትን ሁለት ሰዎች ጨምሮ የሟቾች ቁጥር መድረሱን ነግረውናል። የተጎዱትን ለማስታመም ወደ ሆስፒታል ያመሩ ሰዎች ላይ ጥቃት ተፈፅሟል ስለመባሉ ያነሳንላቸው ዶክተር ቶላ፤ ዝርዝር መረጃ ባይኖራቸውም ሀሙስ እለት ግን ሆስፒታሉ ግቢ ውስጥም ግጭቶች እንደነበሩ ገልፀውልናል። ከዚሁ ጋር በተገናኘ በአዲስ አበባ የሚገኙ የዶዶላ ተወላጆች፣ የሟቾች ቤተሰቦች በመሰባሰብ ለሚዲያዎች ፣ ለሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት አቤት ለማለት እንቅስቃሴ እያደረጉ እንደሆነ የዶዶላ ተወላጅ እና በአዲስ አበባ በሥራ ላይ የሚገኘው አስተባባሪ አቶ አለማየሁ ደምሴ ገልፆልናል። ዜጎች ደህንነታቸው ተጠብቆ ወደ ሰላማዊ እንቅስቃሴያቸው እንዲገቡም መንግሥት አፋጣኝ መፍትሔ እንዲሰጣቸው ጠይቋል። ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ተጠልለው የሚገኙት በርሃብ ሊያልቁ ነው፤ ሕፃናት፣ የሚያጠቡ እናቶች አሉ፤ ትናንትና እና ከትናንት ወዲያ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ንፍሮ ቀቅለው ነው የበሉት ይላል። ግጭት በተፈፀመባቸው አካባቢዎች መከላከያ እንደተሠማራ መንግሥት ቢገልፅም አሁንም ድረስ በከተማዋ ጥቃት እየተፈፀመ እንደሆነም ለቢቢሲ ገልጿል። በጉዳዩ ላይ የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ከፍያለው ተፈራን ለማነጋገር በተደጋጋሚ ብንደውልም ጥረታችን ሳይሳካ ቀርቷል። የተቃውሞ ሠልፍ በተካሄደባቸው የኦሮሚያ፣ ሐረርና ድሬዳዋ ከተሞች በክልሎችና በአስተዳደሩ ጥያቄ መሠረት በአምቦ፣ ቢሾፍቱ፣ ባሌ ሮቤ፣ አዳማ፣ ሞጆ እንዲሁም በድሬዳዋ እና ሐረር የመከላከያ ሠራዊት እንደተሠማራ መገለፁ ይታወሳል። ተያያዥ ርዕሶች
ወደ አውስትራሊያ ሲያቀኑ ለነበሩ ስደተኞች ሞት ምክንያት ነው የተባለው ኢራቃዊ ተከሰሰ
ኦክተውበር አጭር የምስል መግለጫ በጎርጎሮሳዊያኑ በተፈጠረው አደጋ ክስ ሲቀርብ የ ዓመቱ ኢራቃዊ ሦስተኛው ግለሰብ ነው። የአውስትራሊያ ፖሊስ ከ በላይ ስደተኞች ሞት ምክንያት ለሆነው የሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር እጁ ነበረበት ያለው ኢራቃዊ ግለሰብ ላይ ክስ መሠረተ። በጎርጎሮሳዊያኑ ፤ ጥገኝነት ፈላጊ ስደተኞች ከኢንዶኔዥያ ወደ አውስትራሊያ ለመሄድ የተሳፈሩባት ጀልባ የመስጠም አደጋ አጋጥሟታል። ፖሊስ እንዳለው የ ዓመቱ ኢራቃዊ የስደተኞቹን ጉዞ በማቀነባበር እና ከስደተኞቹ ገንዘብ በመቀበል የዝውውሩ አካል ነበር። ኢራቃዊው በኢንዶኔዥያ ባህር ዳርቻ ለተፈፀመው የጀልባ መስጠም አደጋ ክስ የቀረበበት ሦስተኛው ግለሰብ ነው። ይህ ግለሰብ ከኒውዚላንድ ተላልፎ በመሰጠት በቢርስቤን አየር ማረፊያ በቁጥጥር ሥር መዋሉን ፖሊስ አስታውቋል። ጥፋተኛ ሆኖ ከተገኘም እስከ ዓመታት እስር ይጠብቀዋል ተብሏል። ከ ቀናት በኋላም በብሪስቤን ፍርድ ቤት እንደሚቀርብ ተገልጿል። ምንም እንኳን ባለሥልጣናት የግለሰቡን ስም ባይጠቅሱም የሲይድኒ ሞርኒንግ ሄራልድ ጋዜጣ ግለሰቡ ሜይዜም ራዲሂ እንደሚባል ገልጿል። በጎርጎሮሳዊያኑ ከአገሩ በአስገዳጅ ሁኔታ መሰደዱን፣ የስደተኛ ሁኔታ ተመዝግቦ ከባለቤቱና ከልጆቹ ጋር በኦክላንድ ይኖር ነበር። ራዲሂ የቀረበበትን ክስ የተቃወመው ሲሆን ላለፉት አስርት ዓመታትም ተላልፎ እንዳይሰጥ ሲሟገት ቆይቷል። የአገሪቷ ፖሊስ ኮሚሽነር ሬሲ ኬርሻው በበኩላቸው ከ በላይ ስደተኞች የሞቱበትን አሳዛኝ አጋጣሚ እውነታ መማየት አለብን ሲሉ በመግለጫቸው አስረድተዋል። ኮሚሽነሩ አክለውም ፍትህ ማግኘት አለባቸው፤ በዚህ ንግድ በመሰማራት በሰው ሕይወት የሚነግዱ ሰዎችን ለማዳከምም እንሰራለን ብለዋል። ወደ ክሪስማሷ ደሴት እያመራች በነበረችው ጀልባ የደረሰውን ይህንኑ አደጋ አስመልክቶ ምርመራውን መቀጠሉን የአውስትራሊያ ፖሊስ አስታውቋል። ከዚሁ አጋጣሚ ጋር በተገናኘ በጎርጎሮሳዊያኑ ከስዊድን ለአውስትራሊያ ተላልፎ የተሰጠው ኢራቃዊው ካሊድ ዳኦድ ለፈፀመው የሕገ ወጥ ዝውውር ዓመታትን በእስር እንዲያሳልፍ ተወስኖበታል። ሌላኛው የጉዞው አቀናባሪ ግብፃዊው የሰዎች አዘዋዋሪ አቡ ቋሰይ በትውልድ አገሩ በጎርጎሮሳዊያኑ የሰባት ዓመታት እስር ተበይኖበታል። በሺህዎች የሚቆጠሩ ጥገኝነት ፈላጊዎች በየዓመቱ ወደ አውስትራሊያ ለመግባት የሚሞክሩ ሲሆን እንዲያሻግሯቸውም ለሕገ ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች በርካታ ገንዘብ ይከፍላሉ። ስደተኞቹ በአካባቢው ለቁጥጥር አስቸጋሪ የሆነውን የኢንዶኔዥያ ድንበር እንደመሻገሪያ ይጠቀሙበታል። ጉዞው በጣም አደገኛ በመሆኑም በባህር ላይ የሚቀሩ ስደተኞችን ለመታደግ የአውስትራሊያ መንግሥት የነፍስ አድን ሥራዎችን በተደጋጋሚ ለማድረግ ይገደዳል። ይሁን እንጂ አሁንም ስደቱ እንደቀጠለ ሲሆን በአውስትራሊያ ፖለቲካም አከራካሪ ጉዳይ ሆኗል። አውስትራሊያ ያለ ቪዛ ወደ አገሪቷ የሚገቡ ስደተኞችን እንዲታሰሩ በሚያዘው ሕጓም ትተቻለች። ተያያዥ ርዕሶች
የሠርጋቸው ቀን ምሽት ለትዳራቸው መፍረስ ምክንያት የሆነባቸው ሴቶች
ኦክተውበር ማጋሪያ ምረጥ ሠርግ በየትኛውም የዓለም ክፍል አስደሳች አጋጣሚ ቢሆንም የሠርግ ሥነ ሥርዓቶች ከባድ የሥነ ልቦና ስብራት የሚያስከትሉ የሚሆኑባቸው የዓለም ክፍሎችም አይታጡም። በበርካታ የአረቡ አገራት ሴቶች ሲያገቡ ክብረ ንጽህናቸውን እንደጠበቁ እንዲሆኑ ይጠበቃል። የሠርጋቸው ዕለት ቀሪ ህይወታቸውን ሲኦል ያደረገባቸው ሴቶች የህይወት ልምዳቸውን ለቢቢሲ አጋርተዋል። የ ዓመቷ ሶማያ ትወደው የነበረው ፍቅረኛዋን እንድታገባ ስላልፈቀዱላት ከቤተሰቦቿ ጋር ትልቅ ግጭት ውስጥ ገብታ ነበር። ሶሪያዊቷ ሶማያ በደማስቆ ዩኒቨርሲቲ በሥነ ጽሁፍ ዲግሪዋን ለማግኘት ትምህርቷን ወደ ማጠናቀቁ ነበረች። ምንም እንኳ ቤተሰቦቿ ፍቅረኛዋ ኢብራሂምን እንዳታገባው ቢከለክሏትም ልታገባው ወሰነች። ሰውነቴ ወሲብ እንድፈጽም አይፈቅድልኝም የብዙ ሴቶች የጤና እክል የሠርጋቸው ዕለት ምሽት ግን ፍቅር የሚባል ነገር በመካከላቸው እንደነበር እስክትጠራጠር ድረስ ነገሮች ወደ መጥፎ ተቀየሩ። የሠርጋቸው ዕለት ምሽት ወደ መኝታቸው ሲሄዱ ፍቅረኛዋ እና ባሏ ኢብራሂም እሷ ምን እየተሰማት እንደሆነ ለማወቅ ግድም ሳይሰጠው ወሲብ እንዲፈፅሙ አደረገ። ሶማያ በዝምታ የሚፈልገውን እንዲያደረግ ከመፍቀድ ባለፈ ልትታገለው አልሞከረችም። አንሶላ ላይ ምንም ዓይነት ደም ባለማየቱ ኢብራሂም በጥርጣሬ ተመለከታት። ጥርጣሬው ገብቷት ነገሩን ለማብራራት ሞከረች። ብዙ ሴቶች ድንግልናቸው ሲገሰስ የሚደሙ ቢሆንም የማይደሙ እንዳሉም የህክምና ባለሙያዎች ያረጋግጣሉ። ሃኪሞች እንደሚሉት ነገሩ ከሴት ሴት ሊለያይም ይችላል። ድንግልናቸው የግድ በቀዶ ህክምና እንዲሄድ የሚደረጉም ሲኖሩ ያለ ድንግልና የሚወለዱ ሴቶች እንዳሉ እንዲሁም ልጅ ሳሉ በሚደርስ ድንገተኛ ጉዳት ድንግልናቸውን የሚያጡም አሉ። እንግሊዛውያን የወሲብ ሕይወታቸው ደካማ ነው ተባለ የሶማያ ማብራሪያ ለውጥ አላመጣም። እንደ ጦር በሚወጉ አይኖቹ ተመለከተኝ። በዚህ አስተያየቱ ሳያውቀው እንደገደለኝ ነው የተሰማኝ በማለት ያን አስደንጋጭ አጋጣሚ ትገልጻዋለች። ሊያናግራት አልፈለገም ችሎት የቀረበ ተጠርጣሪ የመሆን ስሜት ተሰማት። አንዳቸው ስለ ሌላኛቸው ብዙ እንደሚያውቁ ያስቡ የነበረ ቢሆንም የድንግልና ምልክት ባለመታየቱ ሁሉም ነገር እንዳልነበር ሆነ። ደም የነካ አንሶላ ለወንዶች ምናቸው ነው አያት ቅድመ አያቶቿ በዚህ ቢያልፉም ፍቅረኛዋ የተማረ ሰው በመሆኑ ራሷን እዚህ ቦታ ላይ አገኘዋለሁ ብላ አላሰበችም። የተገሰሰ ድንግልናን በቀዶ ህክምና መመለስ እንደሚቻል የሚያሳዩ ማስረጃዎች አሉ። ባሏ ኢብራሂም በሠርጋቸው ማግስት ድንግል እንደነበች ለማረጋገጥ ወደ ዶክተር እንዲሄዱ ጠየቃት። ኢንተርኔትን የሚሾፍረው የወሲብ ፊልም ይሆን ምርመራ ያደረገላት የማህፀን ሃኪም ድንግልናዋ ወፍራም በመሆኑ ሙሉ በሙሉ ሊገሰስ የሚችለው ስትወልድ ብቻ እንደሆነ ገለጸላቸው። ባሏ በእፎይታ ተንፍሶ በፈገግታ ተመለከታት። ግን ሶማያ ልትፈታው ወስናለችና ዘግይቶ ነበር። የተሰማኝን በቃላት መግለጽ አልችልም። የኔነቴን ዋጋ ወደ አንድ ድንግልና የሚባል ተራ ነገር ከቀነሰ ሰው ጋር ቀሪ ህይወቴን ልኖር አልችልም። እኔ ሰው እንጂ ቁራጭ ሥጋ አደለሁም ትላለች። አጋጣሚው ሶማያ ላይ ከባድ የሥነ ልቦና ጉዳት አድርሷል። ድንግል ነን ካሏቸው ፍቅረኞች ጋር ወሲብ በፈጸሙ በመጀመሪያ ቀን ደም ባያዩ ምን እንደሚሰማቸው እድሜያቸው ከ የሚሆኑ ወንዶችን ቢቢሲ አስተያየት ጠይቋል። ከእነዚህ ውስጥ ምሁራን፣ ዶክተሮችና መምህራን ይገኙበታል። በጥቅሉ ሰፊ ምልከታ አላቸው የሚባሉ ወንዶች ናቸው አስተያየት ሰጪዎቹ። በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ የብዙዎቹ መልስ ደም ማየታቸው ለቀጣዩ ፍቅርና የትዳር ህይወታቸው አስፈላጊ ምልክት ነው የሚል ነበር። የ ዓመቷ ጁማናህ በሶሪያዋ አሌፖ የኖረችው ጁማናህ ወደ ቤልጀም የሄደችው እንደ አውሮፓውያኑ በ ነበር። የ ዓመት ወጣት ሳለች ነው አባቷ ለቅርብ ዘመዳቸው የዳሯት። እንደ ብዙ ወግ አጥባቂ ማህበረሰብ ሁሉ በአካባቢያቸው በሠርግ ምሽት በሙሽሮች መኝታ ቤት ዙሪያ ሆኖ ድንግልና እስኪገሰስ መጠበቅ ባህል ነበር። ዛሬም ድረስ በደማቅ ትውስታ የሚታያት ያ ምሽት ለጁማናህ የስቃይ ነበር። ባሌ ነገሩን ቶሎ ፈጽሞ ውጭ ለሚጠብቁት ዘመዶቻችን የምስራቹን ለማድረስ ተጣደፈ። ምንም ሊያናግረኝ አልፈለገም። ለወሲብ ትክክለኛው ዕድሜ የቱ ነው እንደዚያ ያለ አካላዊና ሥነ ልቦናዊ ስብራት ውስጥ ሆኜ የባሌ ብቸኛ ጭንቀት ደም የነካው ጨርቅ የማየት ነበር ስትል ታስታውሳለች። በዚያች ምሽት እኔ አልደማሁም ስለዚህ ባሌ ደምጹን አጥፍቶ ተቀመጠ። ዓይኑ ግን እንደ እሳት ገረፈኝ የምትለው ጁማናህ ለአንድ ሰዓት ያህል በድንጋጤና በፍርሃት መናወጧን ትናገራለች። እስኪነጋ ለመጠበቅ ትዕግስት ያጡት ቤተሰቦቿ በዚያው የሠርጓ ዕለት ሌሊት ወደ ማህፀን ሃኪም ወሰዷት። አስታውሳለሁ ሃኪሙ እንደ አባት ነበር ያጽናናኝ ሳትፈልግ በቤተሰብ ተገዳ በአደባባይ ካዋረዳት ባሏ ጋር ለ ዓመታት ለመኖር ተደደች። በነዚህ ጊዜያት አራት ልጆችንም ወልዳለች። ድንግልናን በቀዶ ህክምና መመለስ ሮዛና ከዓምስት ዓመት እጮኛዋ ጋር ተለያይታለች። ምንም እንኳ ከጋብቻ በፊት ወሲብ አልፈፅምም ብላ ብትቆይም ዞሮ ዞሮ መጋባታችን አይቀርም ለሚለው የእጮኛዋ ውትወታ በመጨረሻ እጅ ትሰጣለች። ቅርብ ግንኙነት ያላቸው የሁለቱ ቤተሰቦች ተቀያይመው ይራራቃሉ። ከዚያም ሮዛናና እጮኛዋ ይለያያሉ። በአካባቢው ድንግል ሆኖ አለመገኘት የሞትና የሽረት ጉዳይ በመሆኑ ሮዛና ከባድ ችግር ውስጥ ወደቀች። በመጨረሻ በጓደኛዋ ምክር በቀዶ ህክምና ሰው ሰራሽ ድንግልና እንዲኖራት ለማድረግ ወሰነች። በዚያ ቀላል ቀዶ ህክምና ባይሆን ዛሬ በህይወት አልኖርም ነበር ትላለች ሮዛና። ተያያዥ ርዕሶች
ተማሪዎች የካርቶን ሳጥን አጥልቀው ፈተና እንዲፈተኑ ያደረገ የህንድ ትምህርት ቤት ይቅርታ ጠየቀ
ኦክተውበር ተማሪዎች ጭንቅላታቸው ላይ የካርቶን ሳጥን አጥልቀው ፈተና እንዲፈተኑ ያደረገው የህንድ ትምህርት ቤት ባለሥልጣን ይቅርታ ጠየቀ። ትምህርት ቤቱ ይቅርታ የጠየቀው ያልተለመደውና ተማሪዎች የካርቶን ሳጥን አጥልቀው የሚያሳየው ፎቶ በርካታ ሰዎችን ካነጋገረ በኋላ ነው። ፎቶው የተነሳው በካርናታካ ግዛት በባጋት ቅድመ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ የኬሚስትሪ ፈተና ሲፈተኑ ነበር። በፎቶግራፎቹ ላይ እንደሚታየው ተማሪዎቹ በአንድ በኩል የተሰነጠቀ የካርቶን ሳጥኖች አጥልቀው የነበረ ሲሆን እንዳይኮራረጁ ለማድረግ ታስቦ የተደረገ ነው። ይህንን ተከትሎ የትምህርት ቤቱ አስተዳዳሪ በተፈጸመው ድርጊት የግዛቷ ባለሥልጣናትን በይፋ ይቅርታ ጠይቀዋል። የትምህርት ቤቱ አስተዳዳሪ ሳቲሽ፤ ኩረጃን ለመከላከል ያልተለመደ መንገድ በመጠቀማቸው ይቅርታ መጠየቃቸውን ለቢቢሲ ተናግረዋል። እርሳቸው እንዳሉት ተማሪዎችን እንዳይኮራረጁ ለማስቻል ይህንን ዘዴ የተጠቀሙት የሆነ ቦታ ስለ ጠቀሜታው በመስማታቸው ለመሞከር በማሰባቸው ነው። ተማሪዎቹ ፈቃደኛ በመሆናቸው የራሳቸውን የካርቶን ሳጥን ይዘው በመምጣት ውሳኔውን ተግባራዊ እንዳደረጉም አስተዳዳሪው አክለዋል። በምንም ዓይነት መልኩ አልተገደደዱም፤ በፎቶግራፉ ላይ ጥቂት ተማሪዎች ካርቶኑን ሳያጠልቁ ይታያሉ። ካርቶኑንም ከ ደቂቃ በኋላ፤ አንዳንዶች ደግሞ ከ ዲቂቃ በኋላ አውልቀውታል፤ እኛ ራሳችን ከአንድ ሰዓት በኋላ እንዲያወልቁት ጠይቀናቸዋል። ብለዋል። የግዛቷ ባለሥልጣናት ፎቶግራፉን እንዳዩ በፍጥነት ወደ ትምህርት ቤቱ በመሄድ ቅሬታቸውን አሰምተዋል። ህንዳዊቷ ተማሪ ራሷን በማጥፋቷ ተማሪዎች ዩኒቨርስቲውን አቃጠሉ የቅድመ ዩኒቨርሲቲ ትምህርት የቦርድ ምክትል ዳይሬክተር የሆኑት ፒርጃደ፤ ድርጊቱን ሰብዓዊነት የጎደለው ነው ሲሉ አውግዘውታል። በዚህ ጉዳይ ላይ መልዕክት ሲደርሰኝ፤ ወዲያውኑ ነበር ወደ ኮሌጁ ስከንፍ የደረስኩት። ከዚያም የኮሌጁ አስተዳደር ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ ነግሬያቸዋለሁ ብለዋል። ለኮሌጁ አስተዳደር አሳውቄያለሁ፤ በተማሪዎቹ ላይ ይህንን ድርጊት በመፈፀማቸውም ሥነ ምግባር በመጣስ እንዲቀጡ እናደርጋለን ማለታቸውን ታይምስ ኦፍ ኢንዲያ እርሳቸውን ጠቅሶ ዘግቧል። የትምህርት ቤቱ ባለሥልጣን በበኩላቸው ድርጊቱን እንዳቆሙ ገልጸው፤ በትምህርት ቤቱ ቦርድ መርህ በመከተል በትብብር እየሠሩ እንደሆኑ ገልጸዋል። ተያያዥ ርዕሶች
ኢትዮጵያ በዋሽንግተኑ የህዳሴ ግድብ ድርድር ላይ እንደማትሳተፍ አሳወቀች
አሜሪካና የዓለም ባንክ የሚሳተፉበትና ኢትዮጵያ፣ ግብጽና ሱዳን በዋሽንግተን ዲሲ ነገ እና ከነገ በስቲያ ሊያካሂዱት ቀጠሮ ተይዞለት በነበረው የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ድርድር ላይ ኢትዮጵያ እንደማትሳተፍ ተገለጸ። ቢቢሲ እየተካሄደ ለነበረው ድርድር ቅርበት ካላቸው ባለሙያዎች እንዳረጋገጠው እስካሁን በነበረው ሂደት ግብጽ ማግኘት በሚገባት የውሃ ድርሻ ላይ ትኩረት ማድረጓ ውይይቱን አስቸጋሪ አድርጎታል።
በህዳሴ ግድብ ላይ የአሜሪካ እና የዓለም ባንክ ሚና እልባት ሊያገኝ እንደሚገባ መንግሥት አስታወቀ
የህዳሴው ግድብ የውሃ አሞላልና አለቃቀቅ ድርድር ስምምነት እንዲፈረም በከፍተኛ ሁኔታ ጫና እያደረገች ያለችው አሜሪካም ሆነ የዓለም ባንክ ሚና ሊፈታ የሚገባው ጉዳይ መሆኑን መንግሥት አስታውቋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የአሜሪካና የዓለም ባንክ ሚና ከታዛቢነት ያለፈ መሆኑን ገልጸው እነዚህ ወገኖች ከታዛቢነት አልፎ ሕግ አርቅቆ የማቅረብ ፍላጎት አላቸው ብለዋል።
ዛፍ መትከል የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል ይረዳል ዛፍ መትከል የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል ይረዳል
ዛፍ መትከል የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል ይረዳል
የታላቁ ህዳሴ ግድብ ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ስመኘው በቀለ በጥይት ተመተው መኪናቸው ውስጥ ሞተው ተገኙ
ጁላይ ማጋሪያ ምረጥ ኢንጂነር ስመኘው በቀለ ህይወታቸው ያለፈው በጥይት ተመተው ነው ሲሉ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጄነራል ዘይኑ ጀማል አስታወቁ። ኮሚሽነሩ ጨመረውም እንደተናገሩት ከኢንጂነሩ አስክሬን ጎን ኮልት ሽጉጥ መገኘቱን ገልጸዋል። ዝርዝር የአሟሟታቸውን ሁኔታ በተመለከተ ፖሊስ ምርመራውን እያካሄደ እንደሆነ እና በአካባቢው የነበሩ የዓይን እማኞችን እና ምስክሮች ላይ ምረመራ እየተደረገ መሆኑን አመልክተዋል። የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢንጂኒየር ስመኘው በቀለ አዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ላይ መኪናቸው ውስጥ ባልታወቀ ምክንያት ህይወታቸው አልፎ መገኘቱ ይታወሳል። ሐሙስ ሐምሌ ዓ ም ጠዋት አዲስ አበባ ውስጥ በሚገኘው ትልቁ አደባባይ የሰሌዳ ቁጥሯ ኢቲ ኤ ፣ ላንድክሩዘር ቪ መኪናቸው ውስጥ ተገኘ የተባለው አስከሬን ወደ ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል የስነ ምረዛ እና አስክሬን ምርመራ ክፍል ተወስዶ መምርመራ እየተደረገለት ነው። በአካባቢውም ፖሊስ ተሰማርቶ ምርመራ እያደረገ ሲሆን፤ ለሞታቸው ምክንያት ምን እንደሆነ እስካሁን የታወቀ ነገር የለም። በሰልፉ ላይ የታየው ክፍተት ምን ነበር በአካባቢው የሚገኙት የህዳሴ ግድብ አስተባባሪ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ኃይሉ አብርሃም መኪናቸው በፖሊስ ምርመራ እየተደረገለት መሆኑና ብዙ ሰዎችም ተሰብስበው እንዳሉ ገልጸዋል። በትናንትናው ዕለት ቢቢሲ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታን አስመልክቶ ኢንጅነር ስመኘውን ባነጋገረበት ወቅት ፕሮጀክቱ በጥሩ ሁኔታ ላይ እንዳለ ገልጸው ነበር። ኢንጅነር ስመኘው ግድቡ የደረሰበትን ደረጃ በአካል ተገኘተን መመልከት እንደምንችል እና ከእሳቸውም ግድቡን በተመለከተ ማብራሪያ ለማግኘት በመንግሥት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽ ቤት በኩል እንድናቀርብላቸው ጠይቀውን ነበር። የእርሶ መሳሪያ ሚዲያ ፕሌይ ባክን ማጫወት ኣልተቻለም። ኢንጂነር ስመኘው በቀለ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ በኢንጂነር ስመኘው ሞት የተሰማቸውን ከፍ ያለ ድንጋጤና ሐዘን በልዩ ረዳታቸው በኩል ገልጸዋል። የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፍጹም አረጋ ከሰዓታት በፊት በትዊተር ገጻቸው እንደጻፉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዜናውን የሰሙት አሜሪካ ከደረሱ በኋላ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ለሟች ቤተሰቦችና ወደጃች መጽናናትን ተመኝተዋል። የኢንጅነር ስመኘው ሞት ከተሰማ በኋላ በርካቶች ሃዘናቸውን እየገለጹ ነው። የኢህአዴግ ምክር ቤትም ባወጣው የሃዘን መግለጫ ኢንጂነር ስመኘው በቀለ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ዕውን እንዲሆን ከኢትዮጵያ ህዝብና መንግሥት የተሰጣቸውን ኃላፊነትንና አደራ ለመወጣት በከፍተኛ ቁርጠኝነት አገልግለዋል። ከታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ በተጨማሪ በሌሎች የኃይል ማመንጫ ግድቦችም አሻራቸውን አሳርፈዋል፡፡ ያለ ሲሆን ምክርቤቱ ጨምሮም፤ ኢንጅነር ስመኘው በቀለ ከዚህ ዓለም በሞት ቢለዩም ትጋታቸውና ጽናታቸው በእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ልብ ውስጥ ታትሞ የሚኖር ነው፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብና መንግሥትም ታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ከዳር ለማድረስ የሚያደርጉትን ርብርብ በማጠናከር የኢንጂነር ስመኘው በቀለን ህልምና ራዕይ ዕውን ያደርጋሉ ብሏል በመግለጫው። የኢንጂነሩን ሞት ተከትሎም የተቆጡ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ጣቢያ ፊት ለፊት በመገኘት ተቃውሟቸውን አሰምተዋል። የተቃውሞ ሰልፈኞቹ ኢትዮጵያ ነጻ ትውጣ፣ ፍትህ ለኢንጂነር ስመኘ የሚሉ መፈክሮችን ሲያሰሙ ነበር። ኢንጂነር ስመኘው በቀለ ማናቸው ኢንጂነር ስመኘው በቀለ በጎንደር ማክሰኚት በ ዓም ተወልዱ። ኢንጂነሩ በ ዎቹ መጨረሻ እና ዎቹ መጀመሪያ አካባቢ በቀድሞው ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን የቴክኒክ ስልጠና ማዕከል ውስጥ ተማሪ ሆነው መጡ። ከዚያም ከፍተኛ ውጤት በማምጣት ከተመረቁ በኋላ እዚያው ማስተማር ጀመሩ። መምህር ሆነው የተወሰነ ጊዜ ከቆዩ በኋላ በተፈጠረ አለመግባባት መሥሪያ ቤቱን ለቅቀው የወጡ ሲሆን፤ ሲቪል ኢንጂነሪንግ አጥንተው ዳግመኛ በድርጅቱ ውስጥ ተቀጠሩ። ከዚያም በኋላ የጊቤ አንድ ምክትል ፕሮጀክት ኃላፊ በመሆን በተጨማሪም የጊቤ ሁለት ደግሞ የፕሮጀክቱ ኃላፊ በመሆን ሰርተዋል። ኢንጂነር ስመኘው የሦስት ልጆች አባት ሲሆኑ፤ ባለቤታቸው ከሃገር ውጪ ካናዳ ውስጥ እንደሚገኙ ለቤተሰባቸው ቅርብ የሆኑ ምንጮች ለቢቢሲ ተናግረዋል። ኢንጂነር ስመኘው በቀለ በ ዓ ም የበጎ ሰው ለተባለው ሽልማት መንግሥታዊ ኃላፊነትን በብቃት በመወጣት ዘርፍ ከቀረቡት ዕጩዎች መካከል አንዱ የነበሩ ሲሆን እስከ ህልፈተ ህይወታቸው ድረስም የታላቁ ህዳሴ ግድብ የፕሮጀክት ኃላፊ በመሆን ለሰባት ዓመታት ያህል ሲሰሩ ቆይተዋል። ይህንን ዜና ያጋሩ ስለማጋራት
በፊሊፒንስ በከባድ አውሎ ንፋስ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ደረሰ
ዲሴምበር ማጋሪያ ምረጥ ፊሊፒናዊያን የገና በአልን በማክበር ላይ እያሉ በጣለ ንፋስ የቀላቀለ ከባድ ዝናብ የሞቱ ሰዎች ቁጥር መድረሱ ተገለጸ። ታይፉን ፋንፎን ወይንም በአካባቢው ሰዎች አጠራር አርስላ በመባል የሚታወቀው አውሎንፋስ በሰዓት ኪሎሜትር የሚምዘገዘግ ንፋስና ከባድ ዝናብን ይዞ ነበር ፊሊፒንስ የደረሰው። ወዲያውም ከፍተኛ ጎርፍንና የመሬት መንሸራተት አስከትሏል። እንደ ሀገሪቱ ብሔራዊ አደጋ መከላከልና መቀነስ ካውንስል ከሆነ አሁንም ሰዎች እምጥ ይግቡ ስምጥ አልታወቀም። በታይፋን ፋንፎን አውሎ ንፋስ ምክንያት ሺህ ሰዎች ቤት ንብረታቸውን ለቅቀው ሲሄዱ፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ደግሞ መንቀሳቀሻ አጥተው ታግተው ይገኛሉ። እንደባለስልጣናት ገለፃ የሞቱት ሰዎች አንዳንዶቹ ዛፍ ሌሎቹ ደግሞ የኤሌትሪክ መስመር ወድቆባቸው ነው። ፋንፎን በዚህ ዓመት ፊሊፒንስን ከመቷት ሰባት አውሎ ነፋሳት አንዱ ነው። ይሄው ተመሳሳይ የተፈጥሮ ክስተት በአውሮፓውያኑ በፊሊፒንስ ተከስቶ ከስድስት ሺ በላይ ሰዎች ህይወታቸውን ያጡ ሲሆን በሀገሪቱ ታሪክ እጅግ አስከፊው አደጋ ተብሎ ነበር። የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙኀን እንደዘገቡት አብዛኛዎቹ ሰዎች የሞቱት ኢሊሎ እና ካፒዝ በሚባሉት ግዛቶች ነው። ራፕለር የተሰኘ መገናኛ ብዙኀን እንደዘገበው ከሆነ ወደ ቤተሰቦቻቸው ለቀብር የሄዱ ስድስት የቤተሰብ አባላት በአውሎ ንፋሱ ምክንያት ሞተዋል። የቱሪስት መናኸሪያ የሆነችው ቦራኬይ በአውሎንፋሱ የወደመች ሲሆን የስልክ መስመርም ሆነ የኤሌትሪክ ኃይል ሙሉ በሙሉ ተቋርጧል ሲል የፈረንሳዩ ዜና ወኪል የአቅራቢያዋን ግዛት ፖሊስ ኃላፊ ጠቅሶ ዘግቧል። የሀገሪቱ የአየር ጸባይ ቅድመ ትንበያ መስሪያ ቤት ደግሞ ታይፉን ፋንፎን ከረቡዕ ምሽት ጀምሮ በፊሊፒንስ ሰማይ ላይ ሲያንዣብብ መቆየቱን ጠቅሶ አሁን ወደ ደቡብ ቻይና ባህር ማቅናቱን አስረድቷል። ተያያዥ ርዕሶች
የታላቁ ህዳሴ ግድብ ሥራ አስኪያጅ ስለኢንጂነር ስመኘው በቀለ አሟሟት እስካሁን ምን እናውቃለን
ጁላይ ማጋሪያ ምረጥ ዛሬ ጠዋት የታላቁ የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ስመኘው በቀለ አዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ላይ መኪናቸው ውስጥ ህይወታቸው አልፎ ከተገኘ በኋላ እሰካሁን ያገኘናቸው አስር የተረጋገጡ መረጃዎች። ኢንጂነር ስመኘው በቀለ ህይወታቸው ያለፈው በጥይት ተመተው ነው፡ ፌደራል ፖሊስ የህዳሴው ግድብ ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ስመኘው በቀለ በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ መኪናቸው ውስጥ እንዳሉ ሞተው ተገኙ። ኢንጅነር ስመኘው ሞተው የተገኙት በሹፌር መቀመጫ ላይ እንዳሉ ነበር። ኢንጅነር ስመኘው ቀይ ጃኬት ለብሰው፤ ኮፍያ አድርገው የነበረ ሲሆን ጭንቅላታቸው ወደ ቀኝ ዘንበል ብሎ ነበር። ኢንጅነር ስመኘው ሞተው የተገኙባት መኪና ላንድ ክሩዘር ቪ ስትሆን የሰሌዳ ቁጥሯም ኮድ ኢቲ ኤ ነው። በቦታው የነበረው የቢቢሲ ጋዜጠኛ እንደተመለከተው አስክሬናቸ የተገኘበት መኪና ፊቷን ወደ ኢስጢፋኖስ ቤተ ክርስቲያን አዙራ በአግባቡ ነበር የቆመችው። የዓይን እማኞች ጨምረው እንደተናገሩት የመኪናው ሞተር ለረጅም ሰዓት አልጠፋም ነበር። በስተቀኝ በኩል ያለው የመኪናዋ የኋላ መቀመጫ ትንሿ መስኮት ተሰብሮ ይታያል። ነገር ግን መኪናው ተቆልፎ ስለነበር ለመክፈት በፖሊሶች እንደተሰበረ ታውቋል። ከረፋዱ ፡ ላይ አስክሬናቸው ለምርመራ ወደ ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል የሥነ ምረዛና የአስክሬን ምርመራ ክፍል ተወስዷል። የፖሊስ አባላት ኢንጅነር ስመኘው የነበሩበትን መኪና እያሽከረከሩ ይዘዋት ሄደዋል። አስክሬኑም ሆነ መኪናዋ ከቦታው ላይ እንዲነሱ ከተደረገ በኋላ የቢቢሲ ጋዜጠኛ በቦታው ላይ የደም ጠብታዎችን እና ፖሊስ በምርመራው ወቅት የተጠቀመበትን የእጅ ጓንቶች ተመልክቷል። የኢንጅነሩን ሞት ተከትሎ የተቆጡ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ህንጻ ፊት ለፊት በመገኘት ተቃውሟቸውን አሰምተዋል። የፌደራል ፖሊስ ጄነራል ዳይሬክተር ዘይኑ ጀማል ከኢንጂነሩ አስከሬን ጎን ሽጉጥ መገኘቱንና በጥይት መሞታቸውን ተናግረዋል። የኢንጅነር ስመኘው በቀለ ስርዓተ ቀብር ትናንት ሐምሌ ቀን ዓ ም በቅድስት ስላሴ ካቴድራል ቤተክርስትያን ተፈጸመ።
የአውሮፓ ሕብረት ኮሚሽን ለመጀመሪያ ጊዜ ሴት ፕሬዝዳንት መረጠ
ጁላይ ጀርመናዊቷ ኡርሱላ ቮን ዴር ሌይን በጠባብ የድምጽ ልዩነት ተመርጠው የአውሮፓ ሕብረት ኮሚሽን ፕሬዝዳንት ሆነዋል። አዲሷ ተመራጭ ፕሬዝዳንት ከግማሽ በላይ የአውሮፓ ፓርላማ አባላትን ድጋፍ ማግኘት ችለዋል። ኮሚሽኑ የአውሮፓ ሕብረት ሕጎችን ያረቅቃል፤ ያስፈፅማል፤ አስፈላጊ ከሆነ አባል አገራት ላይ ቅጣት ይጥላል። የምርጫው ውጤት እንደታወቀ የጣላችሁብኝ እምነት በአውሮፓ ላይ ያላችሁ መተማመን ውጤት ነው በማለት ንግግር ያደረጉት ተመራጯ ፕሬዝዳንት፤ ቮን ዴር ሌይን ለአውሮፓ ኮሚሽን የመጀመሪያዋ ሴት ፕሬዝዳንት ናቸው። ትራምፕን ከቁብ አትቁጠሩት አራቱ የኮንግረስ አባላት ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ፣ ከደቡብ እስከ ሰሜን በአንድነት በቆመችው አውሮፓ ያላችሁ መተማመን ያሳያል ያሉት ተመራጯ ትልቅ ኃላፊነት ነው፤ ሥራዬም አሁን ይጀምራል ካሉ በኋላ ለተሻለ ውጤት አብረን እንሥራ ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል። ብራስልስ ውስጥ የተወለዱት ቮን ዴር ሌይን፤ የሰባት ልጆች እናት ሲሆኑ ወደ ፖለቲካ ከመግባታቸው በፊት የማህፀንና ፅንስ ዶክተር ነበሩ። ለዚህ ቦታ ከመወዳደራቸው በፊት የጀርመን መከላከያ ሚኒስትር የነበሩ ሲሆን፤ በአስተዳደር ዘመናቸው የጀርመን ጦር ተከታታይ የሆነ የመሣሪያ እጥረት ገጥሞታል በሚል የሰላ ትችት ይቀርብባቸው ነበር። አዲሷ ፕሬዝዳንት የአውሮፓ ሕብረት ለማህበራዊ ደህንነት እንደሚታገል ቃል የገቡ ሲሆን፣ ድህነትን ለመቅረፍ እንዲሁም ለሴቶች መብት መከበር ጠንክረው እንደሚሰሩም ቃል ገብተዋል። በንግግራቸው ላይ ዩናይትድ ኪንግደም ከአውሮፓ ሕብረት ለመውጣት በቂ ጊዜ ሊሰጣት እንደሚገባ ጠቅሰዋል። በፕሬዝዳንቷ መመረጥ የተለያዩ ወገኖች ደስታቸውን የገለጹ ሲሆን፤ ተሰናባቹ ኮሚሽነር በትዊተር ገፃቸው ይህ ኃላፊነት ትልቅና ተግዳሮት ያለበት ነው። እጅግ በጣም የተሻለች ፕሬዝዳንት እንደምትሆኚ እርግጠኛ ነኝ ብለዋል። የጀርመኗ ቻንስለር አንግላ መርኬል በበኩላቸው የቀድሞዋ መከላከያ ሚኒስትራቸውን ለሥራዋ የተሰጠችና አውሮፓውያን እምነት የሚጥሉባት ሲሉ አሞካሽተዋቸዋል። ምንም እንኳ ዛሬ ለረዥም ጊዜ በሚኒስትርነት ያገለገሉትን ሴት ከአጠገቤ ባጣም በብራስልስ ግን አዲስ ወዳጅ አግኝቻለሁ በማለት ለወደፊትም በሥራቸው እንደሚጣመሩ ገልጸዋል። ተያያዥ ርዕሶች
አሜሪካ የአባይ ወንዝ አጠቃቀምን በተመለከተ መግለጫ አወጣች
ጥቅምት ይህንን ለማጋራት በ ዋትስአፕ በኢትዮጵያ፣ በግብጽና በሱዳን መካከል የታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ውሃ የመሙላት ሂደትንና አጠቃቀም ላይ ትብብር፣ ዘላቂነትና የጋራ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥን በተመለከተ እየተደረገ ያለውን ድርድር እንደምትደግፈው አሜሪካ አስታወቀች። ይህ የተገለጸው ከኋይት የፕሬስ ጽህፈት ቤት ሐውስ በወጣና ዝርዝር ጉዳዮችን በማይጠቅሰው አጭር መግለጫ ላይ ሲሆን፤ መግለጫው የወጣበት ምክንያትም አልተገለጸም። በዚህ አጭር መግለጫ ላይ ሁሉም የአባይ ተፋሰስ አገራት በምጣኔ ሃብት የመልማትና የመበልጸግ መብት አላቸው ይልና ሲቀጥል አስተዳደሩ የአሜሪካ ሁሉም አገራት እነዚህን መብቶች ሊያስከብር የሚችልና የእያንዳንዳቸውን የውሃ ፍትሃዊ ተጠቃሚነትን የሚያስከብር በጎ ፈቃደኝነትን የተላበሰ ስምምነት ላይ እንዲደርሱ ጥሪ ያቀርባል ይላል። የሚፈርስ የግድቡ አካል የለም የግድቡ ዋና ሥራ አስኪያጅ የፕሬዝዳንቱ ጽህፈት ቤት የፕሬስ ክፍል ይህንን መግለጫ ከምን ተነስቶ እንዳወጣ የገለጸው ነገር የሌለ ሲሆን ተጨማሪ የሰጠው ማብራሪያም የለም። ይህ መግለጫ ምናልባትም ዛሬና ነገ ካርቱም ውስጥ የሦስቱ አገራት ከፍተኛ ባለስልጣናት ያደርጉታል ተብሎ ከሚጠበቀው ቀጣይ የሦስትዮሽ ውይይት ጋር የተያያዘ እንደሚሆን ይገመታል። ባለፈው ሳምንት ረቡዕ ኒውዮርክ ላይ በተካሄደው የተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የግብጹ ፕሬዝዳንት አብዱል ፋታህ አልሲሲ ባደረጉት ንግግር ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ላይ እየገነባች ያለችውን ግድብን በተመለከተ የሚደረገው ድርድር ውጤት ላይ አለመድረሱ በአካባቢው ላይ አለመረጋጋትን ሊያስከትል እንደሚችል መናገራቸው ይታወሳል። ይህንንም ተከትሎ የኢትዮጵያዋ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በዚያው መድረክ ላይ ለግብጹ ፕሬዝዳንት ንግግር ምላሽ በሚመስል ሁኔታ የአባይ ወንዝ ለተፋሰሱ ሀገራት የጋራ ሃብት እንጂ የጥርጣሬና የውድድር ምንጭ ሊሆን አይገባም በማለት ሃገራቱ የወንዙን ውሃ በጋራ መጠቀም እንዳለባቸው አመልክተዋል። ፕሬዝዳንቷ አክለውም የተፋሰሱ ሃገራት የአባይን ወንዝ የጋራ ተጠቃሚነትን ባረጋገጠ መልኩ ለመጠቀምም በትብብርና በቅንጅት ሊሰሩ እንደሚገባ በንግግራቸው ላይ አንስተዋል። ባለፈው መስከረም እና ዓ ም የኢትዮጵያ፣ የግብጽና የሱዳን ባለስልጣናት ካይሮ ላይ የግድቡን ውሃ አሞላል በተመለከተ በተከታታይ እያደረጉት ያለው የሦስትዮሽ ውይይት መካከል አንዱ የሆነው ካይሮ ላይ የተካሄደ ቢሆንም ያለስምምነት መጠናቀቁ ተነግሯል። የኢትዮጵያ የውሃ፣ መስኖና ኢነርጅ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ ከካይሮው ድርድር በኋላ አዲስ አበባ ላይ በሰጡት መግለጫ ግብጽ በግድቡ ውሃ አሞላል ላይ አዲስ ሃሳብ እንዳቀረበችና ኢትዮጵያ ሃሳቡን ውድቅ እንዳደረገች ተናግረዋል። እንደ ሚኒስትሩ ማብራሪያ ግብጽ ያቀረበችው ሃሰብ፤ የግድቡ የውሃ የሚሞላው በሰባት ዓመት እንዲሆን፣ ኢትዮጵያ በዓመት ቢሊየን ሜትር ኪዮብ ውሃ እንድትለቅና የአስዋን ግድብ የውሃ መጠኑ ከምድር ወለል በላይ ሜትር ላይ ሲደርስ ግድቡ በዋናነት ውሃ እንዲለቅ የሚጠይቅ ነው። ኢትዮጵያም ይህ የግብጽ ሃሳብ ቀደም ሲል በሦስቱ ዋነኛ የተፋሰሱ አገራት መካከል የተፈረመውን የአባይ ወንዝ ውሃን አጠቃቀም የተመለከተውን የመርህ ስምምነት የጣሰና ጎጂ ግዴታን የሚያስቀምጥ ነው በማለት እንደማትቀበለው አሳውቃለች። ለህዳሴ ግድብ ግንባታ መዘግየት ምን አይነት መፍትሔዎች እየተሰጡ ነው ሚኒስትሩ በተጨማሪም ይህ የቀረበው ሃሳብ ግብጽ የወንዙ ዓመታዊ የውሃ ፍሰት ቢልየን ሜትር ኪዩብ እንዲሆን ያቀረበችው ጥያቄ፤ በተዘዋዋሪ ኢትዮጵያ የአባይ ውሃን እንዳትጠቀም የሚከለክል በመሆኑ አልተቀበለችውም ብለዋል። በግድቡ የውሃ አሞላልና የመልቀቅ ሂደት ዙሪያ ያሉትን ሁኔታዎች እንዲያጠና የተቋቋመው የኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብጽ የሦስትዮሽ ብሔራዊ ገለልተኛ የሳይንሳዊ ጥናት ቡድን ኛ ስብስባውን ካርቱም ሱዳን ውስጥ ሰኞ እለት አካሂዶ የነበረ ሲሆን፤ ቡድኑ ዛሬ መስከረም እና ዓ ም እዚያው ካርቱም በሚካሄደው የሦስቱ አገራት የውሃ ሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ ሪፖርት እንደሚያቀርብ ይጠበቃል። ቢቢሲ ማስተባበያ
አሜሪካ፡ አዛውንቱ በቀለጠ አለት የተሞላ ጉድጓድ ውስጥ ገብተው ሞቱ
ኖቬምበር ማጋሪያ ምረጥ የ ዓመት አዛውንት፤ በቅጥር ግቢያቸው ዛፍ እየቆረጡ ሳለ፤ በእሳተ ገሞራ ሳቢያ የተፈጠረ የቀለጠ አለት ውስጥ ወድቀው ሕይወታቸው አለፈ። አሜሪካ ሀዋይ ግዛት ውስጥ ይኖሩ የነበሩት አዛውንት፤ ሜትር በሚረዝመው የቀለጠ አለት የተሞላ ጉድጓድ ውስጥ መውደቃቸውን ፖሊስ ይፋ አድርጓል። በእሳተ ገሞራ አማካይነት የተፈጠረው በቀለጠ አለት የተሞላ ጉድጓድ፤ በስስ አለት ተሸፍኖ ስለነበር አዛውንቱ አላዩትም ነበር። አለቱን ሲረግጡት ወደ ጉድጓዱ ወድቀው ሕይወታቸው አልፏል። የእሳተ ገሞራ ቱሪዝም ፡ አፍቃሬ እሳተ ገሞራዎች አዛውንቱን ለቀናት ያላዩ ጓደኞቻቸው ለፖሊስ ጥቆማ ካደረሱ በኋላ፤ አስክሬናቸው ተገኝቷል። ናሽናል ጂኦግራፊክ እንደሚለው፤ የቀለጠ አለት በቀናት ወይም በሳምንታት ጊዜ ሊፈጠር ይችላል። የቀለጠው አለት ወደ ማይል የሚደርስ ትቦ ሊፈጥርም ይችላል። የሀዋይ ፖሊስ ክፍል ሻለቃ ሮበርት ዋግነር ቢግ አይላንድ ናው ለተባለው ሚድያ እንደተናገሩት፤ አዛውንቱ የወደቁት ወደ ሁለት ጫማ ወይም ሴንቲ ሜትር የሚሰፋው የቀለጠ አለት ያለው ጉድጓድ ውስጥ ነው። የእሳት አደጋ ተከላካዮች የአዛውንቱን አስክሬን ማውጣታቸውንም አክለዋል። ተያያዥ ርዕሶች
በፊሊፒንስ የተፈጥሮ አደጋ ቢያንስ ሰዎች ሞቱ
ዲሴምበር ማጋሪያ ምረጥ ፊሊፒንሳውያን የገና በአልን በማክበር ላይ እያሉ በጣለ ንፋስ የቀላቀለ ከባድ ዝናብ ሰዎች መሞታቸው ሲረጋገጥ የሟቾች ቁጥሩ ከዚህም በላይ ከፍ ሊል እንደሚችል ተሰግቷል። ታይፉን ፋንፎን ወይንም አርስላ በመባል የተጠራው ክስተት በሰዓት ኪሎሜትር የሚምዘገዘግ ንፋስና ከባድ ዝናብን ይዞ ነበር ፊሊፒንስ ደረሰው። ወዲያውም ከፍተኛ ጎርፍንና የመሬት መንሸራተት አስከትሏል። የገና በአልን ተሰብስበው ሲያከብሩ የነበሩ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችም ወደቤታቸው መመለስ ሳይችሉ ቀርተዋል። የዓለማችን ውቅያኖሶች ኦክስጂን እያጠራቸው ነው ይሄው ተመሳሳይ የተፈጥሮ ክስተት በአውሮፓውያኑ በፊሊፒንስ ተከስቶ ከስድስት ሺ በላይ ሰዎች ህይወታቸውን ያጡ ሲሆን በሀገሪቱ ታሪክ እጅግ አስከፊው አደጋ ተብሎ ነበር። የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙኀን እንደዘገቡት ቢያንስ ሰዎች በትናንቱ አደጋ ህይወታቸው ሲያልፍ ከሟቾች መካከል አንድ የሶስት ዓመት ህጻን ይገኝበታል። አብዛኛዎቹ ሰዎች የሞቱት ኢሊሎ እና ካፒዝ በሚባሉት ግዛቶች እንደሆነም ተዘግቧል። የፈረንሳዩ የዜና አውታር አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ግን የሟቾች ቁጥር በትንሹ እንደሆነ ዘግቧል። ዛፎችና የአእምሮ ጤና ምን ያገናኛቸዋል የፊሊፒንሱ ኤቢኤስ ሲቢኤን የተባለው የዜና ወኪል በበኩሉ የአንድ ቤተሰብ አባላት ወደከፍታ ቦታ ለመሄድ ጥረት በማድረግ ላይ ሳሉ በጎርፍ ተወስደዋል ሲል ዘግቧል። ቢያንስ የሚሆኑ ሰዎች ደግሞ በህይወት ይኑሩ አይኑሩ የታወቀ ነገር የለም ሲል አክሏል። የሀገሪቱ የአየር ጸባይ ቅድመ ትንበያ መስሪያ ቤት ደግሞ ታይፉን ፋንፎን ከረቡዕ ምሽት ጀምሮ በፊሊፒንስ ሰማይ ላይ ሲያንዣብብ መቆየቱን ጠቅሶ አሁን ወደ ደቡብ ቻይና ባህር ማቅናቱን አስረድቷል። ተያያዥ ርዕሶች
ካዛክስታን ውስጥ የመንገደኞች አውሮፕላን ተከሰከሰ
ዲሴምበር ማጋሪያ ምረጥ ዘጠና ስምንት ሰዎችን አሳፍሮ ይጓዝ የነበረ የካዛክስታን አውሮፕላን ወድቆ በመከስከሱን ቢያንስ ሰዎች መሞታቸውን የአገሪቱ አየር ማረፊያ ባለስልጣናት ተናገሩ። በአደጋው ቢያንስ ሰዎች የመቁደሰል ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን ከእነሱም መካከል ስምንቱ ህጻናት መሆናቸውን የአካባቢው የሆስፒታል ምንጮች ገልጸዋል። ባለስልጣናቱ እንዳሉት ቤክ ኤር የተባለ አየር መንገድ ንብረት የሆነው አውሮፕላን ከአልማቲ አየር ማረፊያ ዛሬ ጠዋት ከተነሳ ከአጭር ጊዜ በኋላ ነበር የወደቀው። በመጀመሪያ ላይ በአስቸኳይ ወደ ስፍራው የደረሱት የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች ሰባት ሰዎች መሞታቸውን አረጋግጠው ነበር፤ ነገር ግን የሟቾቹ ቁጥር ወደ ከፍ ብሏል። አደጋው ከደረሰበት ስፍራ አቅራቢያ የነበረ ቨየሮይተርስ ዘጋቢ እንዳለው በአካባቢው ከባድ ጭጋግ እንደነበረ ያመለከተ ቢሆንም የአደጋው መንስኤ ምን እንደሆነ እስካሁን አልታወቀም። አውሮፕላኑ ከካዛክስታኗ ትልቅ ከተማ አልማቲ ተነስቶ ወደ ዋና ከተማዋ ኑር ሱልጣን ለመጓዝ ነበር መንገደኞችን ይዞ የተነሳው። የአውሮፕላን ማረፊያው ባለስልጣናት እንዳሉት በአውሮፕላኑ ውስጥ የነበሩት መንገደኞች ሲሆኑ ቱ ደግሞ የአውሮፕላኑ ሰራተኞች ነበሩ። አክለውም አውሮፕላኑ እንደተነሳ ከቁጥጥር ውጪ መሆኑንና መጀመሪያ ላይ የመከለያ ግንብ ገጭቶ ከባለ ሁለት ፎቅ ህንጻ ጋር ተጋጭቶ ነው የወደቀው።
በሰኔ ቅዳሜ ሰልፍ ላይ የታየው ክፍተት ምን ነበር
ጁን ማጋሪያ ምረጥ ቅዳሜ ሰኔ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይን ለመደገፍ በተጠራው ሰልፍ ሚሊየኖች ተገኙ። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በተገኙበት በዚህ ሰልፍ ላይም የቦንብ ፍንዳታ ደረሰ። ትናንት የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀኔራል ዘይኑ ጀማል በቅዳሜው ሰልፍ ላይ የታየው የደህንነት ክፍተት ሆን ተብሎ በፖሊስ ቸልተኝነት የተፈጠረ መሆን አለመሆኑም ይጣራል፤ በእለቱ በመድረኩና በህዝቡ መካከል ያለው ርቀት መስፋት ሲገባው መቀራረቡም እንደ ክፍተት ተወስዶ ተገምግሟል ብለዋል።። ኮሚሽነሩ በመግለጫቸው ከፍተኛ ዝግጅት ተደርጎ የተፈጸመውን ጥቃት ማክሸፍ አለመቻሉ በእለቱ የተስተዋለ ክፍተት ነው ብለዋል። የአሜሪካው ኤፍ ቢ አይ በቦምብ ፍንዳታው ምርምራ ላይ መሰማራቱ ተገለፀ የሆነው ምን ነበር ኢቲቪ እያስተላለፈ በነበረው የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ድጋፍ ቀጥታ ስርጭቱ ላይ እንደታየው ጠቅላይ ሚንስትሩ ንግግራቸውን ካጠናቀቁ በኋላ ነው የፍንዳታ ድምጽ የተሰማው። ቀጥሎም መድረኩ አካባቢ የነበሩ ግለሰቦች ሲሯሯጡ ተስተውሏል። ጠቅላይ ሚንስትሩ ከአደጋው በኋላ ኢትዮጵያውያን በፍቅር ተደምረው ፍቅር እንዲዘንብ ያደረጉበት ዕለት ቢሆንም የአገራችንን ሰላም የማይፈልጉ አካላት በተጠና እና በታቀደ መልኩ ሙያቸውን ታግዘው ይህን ደማቅ ስነ ስርዓት ለማደፍረስ የሰው ህይወት ለመቅጠፍ እና ደም ለማፍሰስ ከፍተኛ ጥረት አድርገዋል ብለዋል። የድጋፍ ሰልፉ አስተባባሪ ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ጉደታ ገላልቻ በበኩላቸው ከፌደራል ፖሊስ፣ ከአዲስ አበባ እና ኦሮሚያ ፖሊስ ጋር በመሆን በቅንጅት ስንሰራ ነበር አሁን የተፈጠረው ግን ከደህንነት አካላት በኩል ክፍተት መኖሩን አሳይቶናል ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። አደጋው ከደረሰ ከጥቂት ሰአት በኋላ የአዲስ አበባ ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር ግርማ ካሳ ለኢቲቪ በሰጡት መግለጫ የጸጥታ ሃይሎች ብዙ ተግባር አከናውነናል ይሁን እንጂ ጥቃት አድራሾቹ ከፍተኛ ዝግጅት አድርገው ስለነበር ጥቃቱ ሊፈፀም ችሏል ብለዋል። ከዚህ ቃለምልልስ በኋላ ግን እርሳቸውን ጨምሮ ሌሎች ዘጠኝ የፌደራልና የአዲስ አበባ ፌደራል ፖሊስ አባላት ከስራቸው መባረራቸውን እንዲሁም በስራቸው ላይ ክፍተት በማሳየታቸው ምርመራ እየተካሄደባቸው መሆኑ ተዘግቧል። በዛኑ ዕለትም ፖሊስ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያደረገ መሆኑን ገልፆ ነበር፡፡ ከትናንት ጀምሮ የምረመራው ሂደት በውጭ አገር መርማሪዎች ሊደገፍ እንደሆነ ታውቋል። የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነሩ ዘይኑ ጀማል ለቢቢሲ እንዳስታወቁትም ፖሊስ ከአደጋው ጀርባ ያሉ ግለሰቦችን ለመለየት የሚያደረገው ክትትል ቀጥሏል። ከኤፍቢአይ ጋርም በጥምረት መስራት ጀምሯል፤ በቁጥጥር ስር የዋሉ ተጠርጣሪዎች ቁጥርም ደረሷል ብለዋል፡፡ አቶ ቢተው በላይ የቀድሞ ታጋይና የኢህአዴግ ምክር ቤት አባል ናቸው። በደቡብ ክልልም ከፀጥታና ደህንነት ጋር በተያያዘ ሲሰሩ ነበር። እርሳቸው ቅዳሜ እለት ስለተደረገው የድጋፍ ሰልፍ ዝግጅት ከአንዳንድ ሰዎች ጠይቀዋል። ከንግግራቸው እንደተረዱትም አዘጋጆቹ ከፀጥታ አካላት ጋር በሚጠበቀው መንገድ ተቀናጅተው የገቡበት አይመስልም። አቶ ቢተው ስለዝግጅቱ ከመንግስት አካላት ጠይቆ መረዳት አስፈላጊ እንደሆነ ተናግረው አንዳንድ ቦታዎች የፍተሻ መላላት እንደነበር ቀድመው በስፍራው ገብተው ያደሩም እንደነበሩ መነገሩ ሌላው የፀጥታው ጉዳይ መላላቱን ማሳያ ነው። ይህንን ሃሳባቸውን ሲያጠናክሩም ከውጭ ሆኖ ለሚመለከተው ግለሰብ የተቀናጀ ነገር እንዳልነበር ያሳያል ይላሉ። እንዲህ አይነት ትልቅ ህዝባዊ ስብሰባዎች ሲዘጋጁ በየደረጃው ካሉ የፀጥታ አካላት ጋር ከመነሻው ጀምሮ በጋራ በመሆን ማቀድ ያስፈልግ እንደነበር ያስታውሳሉ። እንዲህ አይነት በራስ ተነሳሽነት የሚደረግ ህዝባዊ ሰልፍ ሲደረግ ፍላጎት የሌላቸው ደግሞ በዓሉን ለማደናቀፍ የሚያደርጉትን ነገር ለመከላከል ዝግጅት ወሳኝ ነው ይላሉ። ምንም እንኳ ከመንግስት ውጭ የተዘጋጀ ሰልፍ ቢሆንም ከመንግስት አካል ጋር ተቀናጅቶ በመስራት ችግር ቢከሰት እንኳ እንዴት መፍታት እንደሚቻል መታቀድ ነበረበት ይላሉ አቶ ቢተው። በአቶ ቢተው ሃሳብ እነዚህ አካላት ከመነሻው ጀምሮ አለመገናኘታቸው ክፍተቱን ፈጥሮ ሊሆን እንደሚችል ይችላል። ለአቶ ቢተው ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚደረገው ጥበቃ ምን ይመስል እንደነበር ለመናገር በስፍራው የነበረ ሰው የሚታዘበው እና አስተያየት ቢሰጥበት የተሻለ እንደሚሆን ገልፀው ነገር ግን ጥበቃው በስፍራው ላይ ቀድሞ በመገኘት መጠናከር ይኖርበት እንደነበር ይገባኛል በማለት አስተያየታቸውን ያጠናቅቃሉ። በመስቀል አደባባይ በተፈጸመው የቦምብ ጥቃት ላይ የሚካሄደው ምርመራ ተጀምሯል በማለት ለቢቢሲ የተናገሩት።የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀኔራል ዘይኑ ጀማል የምርመራውን ሂደት አስመልክቶ ለሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል። በመግለጫቸውም በምርመራ ሂደቱ ከፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን፣ ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን፣ ከብሄራዊ የመረጃና ደህንነት አገልግሎት እንዲሁም ከፌደራል ጠቅላይ አቃቢ ህግ የተውጣጡና በዘርፉ ከፍተኛ ልምድ ያላቸው ባለሙያዎች እየተሳተፉ መሆኑን አስረድተዋል። ምርመራው የድርጊቱን ፈጻሚ የድርጊቱን ኢላማ በድርጊቱ ውስጥ የፖሊስ ተሳትፎ መኖር አለመኖሩን በተመለከተ የሚነሱ ጥያቄዎችን ለመመለስ ያለመ መሆኑንም ነው የተናገሩት። ከዚህ በተጨማሪ ኮሚሽነሩ በጥቃቱ ላይ የፖሊስ ተሳትፎ ስለመኖሩ የሚጣራ ነው የሚሆነው ብለዋል። ድርጊቱ ከመድረኩ ባልራቀ ቦታ ላይ መፈጸሙም በእለቱ እንደ ክፍተት የታየ ጉዳይ መሆኑንም ጠቁመዋል። በተጨማሪም ቦምብን ያክል መሳሪያ ብዙ ህዝብ በተሳተፈበት ሁኔታ መገኘቱ በፌደራል ፖሊስ ታሪክ ታይቶ የማይታወቅ መሆኑን ገልጸዋል።
ትራምፕን ከቁብ አትቁጠሩት አራቱ የኮንግረስ አባላት
ጁላይ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በዘረኛ የትዊተር መልዕክት ጥቃት ያደረሱባቸው አራቱ የኮንግረስ አባላት የፕሬዘዳንቱን ንግግር አጣጥለዋል። አራቱ ሴት የኮንግረስ አባላት የትራምፕ ንግግር የሰዎችን ትኩረት ከጠቃሚ ነገር ለማሸሽ ያለመ ነው ብለዋል። ራሺዳ ቲላብ፣ አያና ፕረስሊ፣ ኤልሀን ኦማር እና አሌክሳንድያ ኦስካዝዮ ኮርቴዝ ትላንት በሰጡት መግለጫ፤ አሜሪካውያን የትራምፕን ንግግር ከቁብ እንዳይቆጥሩት አሳስበዋል። ትራምፕ አራቱ ሴት የኮንግረስ አባላት አሜሪካውያን ቢሆኑም አገሪቱን ለቀው መሄድ ይችላሉ ማለታቸው ይታወሳል። በርካቶች ፕሬዘዳንቱን በንግግራቸው ቢያብጠለጥሏቸውም፤ ትራምፕ ንግግሬ ዘረኛ አይደለም ሲሉም አስተባብለዋል። ዘ ስኳድ በሚል ቅጽል ስም የሚጠሩት አራቱ ሴቶች፤ የአሜሪካውያን ትኩረት ፖሊሲ ላይ እንጂ የፕሬዘዳንቱ ንግግር ላይ እንዳይሆን አሳስበዋል። ርህራሄ አልባና ሙሰኛ የሆነ አስተዳደሩ ላይ ሰዎችን ትኩረት እንዳያደርጉ ፈልጎ ነው ብለዋል አያና ፕረስሊ። ራሺዳ ቲላብ እና ኤልሀን ኦማር ትራምፕ በሕግ ተጠያቂ ይደረጉ የሚለውን ጥያቄ አስተጋብተዋል። ሦስቱ ሴቶች የተወለዱት አሜሪካ ውስጥ ሲሆን፤ ኤልሀን ኦማር ሶማሊያ ውስጥ የተወለዱ አሜሪካዊ ናቸው። ትራምፕ ያሳለፍነው እሁድ ወደ መጡበት ተመልሰው በወንጀል የተመሳቀለ አገራቸውን ያሻሽሉ ሲሉ ዘረኛ ትዊት ማድረጋቸው ይታወሳል። የመጀመሪያውን ድራማ አንተ፤ ሁለተኛውን እኔ እፅፈዋለሁ ኤርሚያስ አመልጋ አያና ፕረስሊ፤ የኮንግረስ አባላቱን ለማግለልና ድምጻቸውን ለማፈን የተቃጣ ንግግር እንደሆነ ገልጸው፤ እኛ ከአራት ሰዎች በላይ ነን፤ ቡድናችን ፍትህ የሰፈነበት አገር ለመገንባት የሚሹትን ሁሉ ያካትታል ብለዋል። የኮንግረስ አባላቱ፤ ሜክሲኮ ድንበር ላይ ስደተኞች እየደረሰባቸው ስላለው እንግልት እንዲሁም የመሣሪያ ቁጥጥርና የህክምና አገልግሎት ተደራሽነት ላይ ማተኮር የተሻለ ነው ብለዋል። ኤልሀን ኦማር በበኩላቸው ድንበር ላይ ሰብአዊ መብት ሲጣስ፣ ሰዎች ሲታጎሩም ታሪክ እየታዘበን ነው ብለዋል። አራቱ ሴቶች ላይ የተቃጣው ዘረኛ ጥቃት አገሪቱን ለመከፋፈል ያለመ፤ የነጭ የበላይነት ሻቾች አጀንዳ ብለውታል። ራሺዳ ቲላብ፤ ንግግሩን ከፕሬዘዳንቱ ዘረኛ አመለካከት የተቀዳ ብለውታል። የአገሪቱን ሕግ ተመርኩዘው ፕሬዘዳንቱን ተጠያያቂ ከማድረግ ወደ ኋላ እንዳማይሉም አክለዋል። አሌክሳንድያ ኦስካዝዮ ኮርቴዝ፤ ከተሞክሯቸው ተነስተው ታዳጊዎች ይህ ፕሬዝዳንት ምንም አለ ምን፣ ይህ አገር ያንተ ነው፤ ያንቺ ነው መባል አለባቸው ብለዋል። የምንወደውን ነገር ትተን የትም አንሄድም ያሉት የኮንግረስ አባሏ፤ አዕምሯቸው ያልበሰለ መሪዎች ፓሊሲ ላይ ማተኮር እንደሚሳናቸውም ገልጸዋል። ባለፈው ሳምንት ራሺዳ ቲላብ፣ አያና ፕረስሊ፣ ኤልሀን ኦማር እና አሌክሳንድያ ኦስካዝዮ ኮርቴዝ የስደተኞች ማቆያ ጎብኝተው ምስክርነታቸውን ሰጥተው ነበር። ዴሞክራቶች ድንበር ላይ የስደተኞች ሰብአዊ መብት እየተጣሰ ነው ሲሊ የትራምፕን አስተዳደር ይተቻሉ። ትራምፕ ግን ድንበር ላይ የሰብአዊ መብት እንዳልተጣሰ ተናገረው፤ የኮንግረስ አባላቱን ደስተኛ ካልሆናችሁና የምታማርሩ ከሆነ መሄድ ትችላላችሁ ብለዋል። አራቱ ሴቶች ትላንት ጋዜጣዊ መግለጫ እየሰጡ ሳለም ትራምፕ ተመሳሳይ ነገር ትዊት አድርገዋል። እዚህ ደስተኛ ካልሆናችሁ መሄድ ትችላለእሀ። ምርጫው የናንተ ነው ብለዋል። ከበለስ ኤሌክትሪክ ለማመንጨት የምትመራመረዋ ኢትዮጵያዊት ፕሬዘዳንቱን እያወገዙ ያሉት ዴሞክራቶች ብቻ ሳይሆኑ ሪፐብሊካኖችም ጭምር ናቸው። ሴናተር ሚት ሮምኒ የፕሬዘዳንቱን ከፋፋይና ጠቃሚ ሆነው ጉዳይ የሚያስገነግጥ ብለውታል። ሰዎች የተለያየ የፖለቲካ አመለካከት ቢኖራቸውም አሜሪካውያንን ወደመጣችሁበት ተመለሱ ማለት መስመር ያለፈ ነው ብለዋል። የአሜሪካ ወዳጅ አገራትም ፕሬዘዳንቱን እየተቹ ነው። የኒውዚላንድ ጠቅላይ ሚንስትር ጃሲንዳ አርደርን እንዲሁም የካናዳ ጠቅላይ ሚንስትር ጀስቲን ትሮዶ ንግግሩን ነቅፈዋል። ተያያዥ ርዕሶች
ሬፓን የሸርኮሌው ስደተኛ፡ የድንቅ ሥራዎች ፈጣሪ
ጁላይ አጭር የምስል መግለጫ ሬፓን ከገነባው ቤት ፊት ይህ ሬፓን ሳዲቅ ነው። ከጀርባው የሚታየው ደግሞ ለመገንባት ሰባት ወራት የፈጀበት፣ በሸርኮሌ የስደተኞች መጠለያ ውስጥ የሚገኘው ባለ ፎቅ መኖሪያ ቤቱ ነው። ለመጀመሪያ ጊዜ ሬፓን የኢትዮጵያን መሬት የረገጠው ገና በአንድ ዓመቱ ነበር። ሱዳን በጦርነት ስትታመስ ነው ቤተሰቡ የኢትዮጵያን ድንበር አቋርጦ ሸርኮሌ የስደተኞች መጠለያ የገባው። ያኔ ጨቅላ ነበር፥ ከሚነግሩት ውጪ ሁኔታዎች እንዴት እንደነበሩ አያስታውስም፤ ሁኔታዎች ተረጋግተዋል ተብሎ ወደ ትውልድ ስፈራው ከተመለሰ በኋላ ግን ያሰበው ሁሉ እንዳልነበር በመሆኑ ለሁለተኛ ጊዜ ስደተኛ ሆኖ ወደ ኢትዮጵያ መምጣት ግድ ሆኖበት ከዓመታት በኋላ ተመልሷል። የዛሬ ዓመት ወደ ኢትዮጵያ ባለቤቱንና ስድስት ልጆቹን ይዞ ሲመጣ የ ዓመት ወጣት ነበር። ሬፓን ዛሬም ኑሮውን በቤኒንሻንጉል ጉሙዝ በሸርኮሌ የስደተኞች መጠለያ ነው። ሬፓን ሱዳን እያለ የእንጨት ሥራ ባለሙያ ነበር። አባቱም የብረትና የእንጨት ሥራ ባለሙያ ነበሩ። ታዲያ ይህ የእጅ ሙያው በአካባቢው ታዋቂ አድርጎታል፤ ታዋቂነቱም ከሸርኮሌ መጠለያ አልፎ አዲስ አበባ ድረስ የናኘባቸው ጊዜያትም ነበሩ። በተለያዩ የስደተኛ መጠለያዎችም ሥራዎቹን ያቀርባል። ሬፓን በሸርኮሌ መጠለያ ውስጥ ከሚያገኛቸውና አልፎ አልፎ ደግሞ ጥቅም ላይ ውለው ከተወገዱ ዕቃዎች የተለያዩ ፈጠራዎችን ይሰራል። ቀን ቀን በካምፕ ውስጥ ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጋር የስደተኞች ልጆችን የእጅ ሙያ ያስተምራል። ማታ ማታ ደግሞ ልቡን የሚያስደስተውን ነገር በመሥራት በቂ እንቅልፍ በዓይኑ ሳይዞር እንደሚነጋ ይናገራል። አጭር የምስል መግለጫ የሱዳን ዜናን ለማዳመጥ የሠራት ራድዮ ኢትዮጵያ ከመጣ ሬፓን የሚታወቀው በቀን ለሦስት ሰዓታት ብቻ እንቅልፍ በመተኛቱ መሆኑን የሚናገረው ሬፓን፤ ለእራሱ መኖሪያቤት ገንብቷል። ለመኝታ ያን ያህል ጊዜም የለኝ የሚለው ሬፓን ቡና እጠጣና ሌሊቱን ስሠራ አድራለሁ። በመጀመሪያ ግን በጭንቅላቴ ሃሳቡን ካውጠነጠንኩ በኋላ እና እንዴት እንደምሠራው ከደረስኩበት በኋላ ብቻ ነው ወደ ዋናው ሥራ የማመራው ይላል። የቴክኖሎጂ ፈጣሪዎች ልጆቻቸው ሞባይል እንዳይጠቀሙ የሚያግዱት ለምን ይሆን የሚኖርበትን ቤት ገንብቶ ለመጨረስ ሰባት ወር እንደፈጀ የሚናገረው ሬፓን ከዚያ በኋላም እጆቹን አጣጥፎ አልተቀመጠም። ቀስ በቀስ የሚያስፈልጉትን የተለያዩ የቤት ቁሳቁሶችን ሰራ። በቤቱ የሚገኙት የውሃ ማሞቅያ፣ አየር ማቀስቀዣ እና ሌሎች የእጅ ስራው ውጤቶች ናቸው። በዚህ ዓመት በተከበረው ዓለም አቀፍ የስደተኞች ቀን ሬፓን በአቅራብያው ወዳለው የባምባሲ የስደተኞች ካምፕ ተጋብዞ ሄዶ ነበር። የሠራውን ለየት ያለ የሙዚቃ ማጫወቻ መሣሪያ ይዞ በመሄድም የተለያዩ ክልሎችን ሙዚቃዎች በማጫወት በክብረ በዓሉ ላይ ተሳትፏል። ለሙዚቃ ማጫወቻው ራሱን የቻለ ዘፈኖችን የሚይዝ ሜሞሪ ካርድ በአሉሚንየም ሠርቶለታል። ኢንተርኔትን የሚሾፍረው የወሲብ ፊልም ይሆን ሬፓን ሥራዎቹን ለመሥራት የሚጠቀምባቸው ዕቃዎች ከእንጨት፣ ከቀርከሃ፣ ከአሉሚንየም እና ከካርቶን አያልፍም። ሬፓን የፈጠራ ውጤቶቹን ሲሠራ እንደ ግብዓት የተጠቀመባቸው ዕቃዎች በቀላሉ በአካባቢው የሚገኙ ቢሆኑም፤ እስካሁን አስቸጋሪ የሆነበት መሣሪያዎቹ በባትሪ ድንጋይ መሥራታቸው ነው። ቀስ ብሎም በፀሐይ ኃይል እንዲሠሩ ለማድረግ እንደሚያስብ የነገረን ሬፓን ሁሉም ባይሆን ቢያንስ የውሃ ማሞቂያው በፀሐይ እንዲሠራ ማድረጉን አጫውቶናል። አጭር የምስል መግለጫ ሬፓን እና ቤተሰቡ ሬፓን አሁን በካምፑ ላሉት ስደተኞች በሙሉ ለእራሱ የሠራው ዓይነት ቤት መገንባት ፍላጎት እንዳለው ይናገራል። የሚገነባውን ፎቅ ቤት ከዋናው መንገድ በማይርቅ ቅርበት በማሳረፍ ጎብኚዎች እየመጡ እንዲያዩለት እንደሚያደርግ ነግሮናል። አንዳንዴ የሚያሰፈልጉኝን ነገሮች ለመግዛት ስወጣ ድንገት ሰዎች ገብተው ዕቃ ቢወስዱ፤ ስመለስ በመቆጣጠሪያ ክፍሌ ገብቼ የተፈጠረውን ነገር ማየት እችላለሁ የሚለው ሬፓን በእጁ የሠራው የመቆጣጠሪያ መሣሪያ በቤቱ የሚፈጠረውን በሙሉ ቀርፆ እንደሚጠብቀው ገልጾልናል።
ደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል፡ ከሕግ ውጪ የተዋሃዱት አምስቱ ክልሎች
ጁላይ ማጋሪያ ምረጥ ወታደራዊው መንግሥት ከስልጣን ከተወገደ በኋላ የኢትዮጵያ አስተዳደራዊ መዋቅር መሰረታዊ ለውጥ ተደርጎበት በዋናነት ቋንቋን መሰረት ባደረገ ሁኔታ የአስተዳደር ክልሎች ተመስርተዋል። ከሰማኒያ በላይ የተለያየ ሐይማኖት፣ ቋንቋና ባሕል ያላቸው ሕዝቦችን መብትና ጥቅም ያስከብራል በሚል ዋና ዋና በሚባሉትና በርካታ የሕዝብ ቁጥር ባላቸው ብሔሮች ዙሪያ ውስጣዊ የአስተዳደር ሥርዓቱን ማዋቀር በወቅቱ የሃገሪቱን የመሪነት ሚና የተረከቡት ኃይሎች ዋነኛ ሥራ ነበር። በዚህም ለዘመናት ኤርትራን ጨምሮ በ ክፍላተ ሃገራት የተዋቀረው የአስተዳደር ሥርዓት ከ ዓ ም ወዲህ በአዲሱ ቋንቋን መሰረት ባደረገ የፌደራል አስተዳደራዊ አወቃቀር አንዲተካ ተደርጓል። የደቡብ ክልል፡ ውስብስቡ የዐብይ ፈተና ይህም የሆነው ሃገሪቱ የምትተዳደርበት ሕገ መንግሥት ከመጽደቁ በፊት በተቋቋመው ጊዜያዊ የሽግግር መንግሥት አማካይነት ነበር። የወቅቱ አከላለል ክልሎች እንዲፈጠሩ ያደረገ ሲሆን አዲስ አበባም በክልል ደረጃ የተዋቀረች ከተማ ነበረች። በሽግግሩ ወቅት በአዋጅ ቁጥር መሰረት አዲስ የክልል አወቃቀር ሲታወጅ በሂደቱ ውስጥ ተሳታፊ እንደነበሩ የሚናገሩትና በወቅቱ የምክር ቤት አባል የነበሩት ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ከሁለት ዓመታት በኋላ አሁን በደቡብ ክልል ውስጥ የሚገኙ አምስት አካባቢዎች በሕገ ወጥ መንገድ ተዋህደው አንድ ክልል እንዲመሰርቱ መደረጉን ያስታውሳሉ። በሽግግሩ ጊዜ የተዋቀረው አዲሱ የአስተዳደር ሥርዓት በዋናነት በቁጥርና በአሰፋፈር ተለቅ ተለቅ የሚሉትን ማዕከል አድርጎ የተካለለ ቢሆንም የደቡብ ክልል ግን የሚደርሱ ብሔር፣ ብሔረሰቦችን በመያዝ ከሌሎቹ ክልሎች በተለየ የተዋቀረ ነው። በወቅቱ አዲስ አበባም ራሷን የቻለች ክልል በመሆን የፌደራል መንግሥቱ አካል የነበረች ሲሆን በኋላ ላይ ይህ ተቀይሮ በቻርተር የምትተዳደር የከተማ አስተዳደር እንድትሆን ተደርጓል፤ ድሬዳዋም በተመሳሳይ የአስተዳደር ሁኔታ ውስጥ ትገኛለች። ለሲዳማ ክልልነት ይሁንታ ተሰጠ በሚል በርካቶች ደስታቸውን እየገለጹ ነው በወቅቱ ክልሎቹ ሲዋቀሩ ቋንቋንና ማንነትን መሰረት አድርገው ሲሆን አሁን ከያዙት ስያሜ በተለየ በቁጥር ነበር የሚታወቁት። ቁጥሩ ከትግራይ ክልል አንድ ብሎ ይጀምርና ደቡብ ተብሎ በአንድ እንዲጠቃለል የሆነው ክልል ከሰባት እስከ የሚደርሱትን ክልሎች በውስጡ እንዲይዝ ተደርጎ አምስት ክልሎችን ነበሩት ይላሉ ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ። እንደእርሳቸው አባባል በአከላሉ ሂደት ወቅት አሁን የደቡብ ኢትዮጵያ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ተብሎ ወደ አንድ የተጠቃለለው በአምስት ዋና ዋና ክልሎች ተዋቅሮ የተለያዩ ሕዝቦች የሚኖሩባቸው ክልሎች እንዲሆኑ ተደርገው ነበር የተደራጁት። በዚህም መሰረት በጊዜያዊው የሽግግሩ መንግሥቱ ዘመን እነዚህ አምስት ክልሎች እንደ ክልል ለሁለት ዓመት ራሳቸውን የቻሉ ክልሎች በመሆን ሲተዳደሩ ቆይተዋል። ክልል ፡ ይባል የነበረው ክልል ጉራጌ፣ ከምባታ፣ ሃዲያ፣ የም፣ ሐላባና ስልጤን ጨምሮ በመያዝ ዋና ከተማውን ሆሣዕና ላይ ነበር። ክልል ፡ ይባል የነበረው ክልል ዋና ከተማውን ሐዋሳ ላይ በማድረግ ሲዳማን፣ ጌዲኦን፣ አማሮንና ቡርጂን በመያዝ የተዋቀረ ነበር። ክልል ፡ ይባል የነበረው ክልል ማዕከሉን አርባ ምንጭ ላይ አድርጎ ወላይታ፣ ጋሞ ጎፋ፣ ዳውሮና ሌሎችንም አካቶ የተመሰረተ ነበር። ክልል ፡ ይባል የነበረው ክልል ደግሞ መቀመጫውን ጂንካ ላይ በማድረግ ደቡብ ኦሞ ውስጥ ያሉ ሕዝቦችን አቅፎ የተካለለ ነበር። ክልል ፡ ተብሎ ተሰይሞ የነበረው ክልልም ሚዛን ተፈሪን ዋና ከተማው በማድረግ ከኦሞ ወንዝ ባሻገር ያሉትን ህዝቦች አካቶ የተመሰረተ ክልል ነበር። ብዙም ያልዘለቀው የእነዚህ ክልሎች እድሜ ማዕከላዊው የሽግግር መንግሥት ክልሎቹ የተዋቀሩበትን አዋጅ ን በመጣስ አምስቱን ክልሎች በአንድ ላይ እንዲዋሃዱ የሚያደርግ ትዕዛዝ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽህፈት ቤት እንደወጣና በዚህ መሰረትም ክልሎቹ ከሁለት ዓመት በላይ ህልውና እንዳይኖራቸው ተደርጎ በአንድ ክልል እንዲጠቃለሉ መደረጉን ፕሮፌሰር በየነ ይገልጻሉ። ለዚህ ምክንያቱ እነዚህ ክልሎችን በአንድ ክልል ስር የማካተቱ እርምጃ ለማዕከላዊው መንግሥት ጥቅምና ቁጥጥር አመቺነት ነው ይላሉ ፕሮፌሰሩ፤ አክለውም ድርጊቱን ተቃውመው ውዝግብ ውስጥ መግባታቸውንና ከሽግግሩ ምክር ቤት እስከመባረር እንደደረሱ ይናገራሉ። ያስከተለው ጽዕኖ አምስቱን ክልሎች በአንድ ያማከለው የመንግሥት እርምጃ የተለያዩ ቦታዎች የየራሳቸው የሆነ የልማት ማዕከላት እንዳይኖራቸው እንደደረገ ይገላጻሉ ፕሮፌሰር በየነ። ይህም በተለያዩ ስፍራዎች ለሚኖር የሥራ ፈጠራና ለኢኮኖሚያዊ እድገት መፋጠን አስተዋጽኦ ይኖረው እንደነበር ያምናሉ። ክልሎቹ በነበሩበት መተዳደር ቢችሉ ኖሮ አሁን ሐዋሳ ላይ የተከማቸው ሐብት በተለያዩ ቦታዎች ላይ ጥቅም ይሰጥ ነበር። በዚህም ደቡብ ውስጥ በእድገት ጎላ ብላ የምትታየው የሐዋሳ ከተማ ብቻ ሆናለች የሚሉት ፕሮፌሰር በየነ፤ ነገር ግን አምስቱ ክልሎች በነበሩበት ቢቀጥሉ ኖሮ በርካታ ሊያድጉ የሚችሉ አካባቢዎችን መፍጠር ይቻል እንደነበር ያምናሉ። ነገር ግን ኢህአዴግ ክልሎቹን ወደ አንድ ለማምጣት በወሰደው የዘፈቀደ እርምጃ በተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች የልማት ማዕከሎች እንዳይፈጠሩ እንቅፋት በመሆን ክልሉም ሕዝቡም ተጎድቷል። ያልተነገረለት የኮንሶ ጥያቄ ከሃብት አንጻር ለተቀሩት የክልሉ አካባቢዎች በፍትሐዊነት ሊከፋፈልና ሊዳረስ የሚገባው ሐብት በሐዋሳ ላይ ብቻ እንዲፈስና እንዲከማች በማድረግ ሌሎቹ አካባቢዎች በተመጣጣኝ ሁኔታ እንዳያድጉ እንቅፋት መሆኑን ይናገራሉ። በደቡብ ክልል ውስጥ የቦታ ይገባኛል እንዲሁም ክልል እና ዞን ለመሆን በርካታ ጥያቄዎች በተለያዩ የክልሉ ማኅበረሰብ አባላት ሲቀርቡና በዚህም ሽኩቻና ውዝግብ የነበረ መሆኑን የሚናገሩት ፕሮፌሰር በየነ፤ የእነዚህ ምክንያቶች ደግሞ የመልካም አስተዳደርና የሕግ የበላይነት መጥፋት ያመጣው እንደሆነ ያምናሉ። ነገር ግን ይህ ሁሉም ጋር ያለ መናቆር ነው ደቡብ ውስጥ እነዚህ አምስት ክልሎች በአንድ በመዋቀራቸው ከሌሎች ክልሎች ከታዩት ችግሮች የተለየ ነገር ገጥሞታል ብለው የሚጠቅሱት እንደሌለ ይናገራሉ። ለፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ የቀረቡት ክልል የመሆን ጥያቄዎች ምላሽ ቢያገኙ በሃገሪቱ አንድነት ላይ የሚፈጥሩት ውጤት የለም። እንደ እርሳቸው አተያይ ዋነኛው ተግዳሮት የሚሆነው በእነዚህ ቦታዎች ላይ ከሚያጋጥመው ኢኮኖሚያዊ ውስንነት ውጪ ክልልም ሆኑ ዞን፣ በኢትዮጵያ ማዕቀፍ ውስጥ እስካሉ ድረስ ከስም ለውጥ ባሻገር የሚኖር ጉልህ ለውጥ የለም። ከአሉታዊው ውጤት ባሻገር ከተጠቀሱት ክልሉ ውስጥ የሚታዩ ውስጣዊ መሻኮቶችና መገፋፋቶች ባሻገር ከኢትዮጵያዊነትና ከኢትዮጵያ ህልውና አንጻር ሲታይ ሰፊ ቁጥር ያላቸው ሕዝቦች በአንድ ክልል ውስጥ መተዳደር እንደሚችሉ ትልቅ ማሳያ ሊሆን ይችላል ይላሉ ደቡብ ክልልን። ለዚህም ነው ደቡብ ሲነሳ ዘወትር ትንሿ ኢትዮጵያ እስከመባል የተደረሰው ሲሉ ሀሳባቸውን ያጠናክራሉ። የክልሎቹ መዋሃድና ውጤቱ ከሁለት አስርት ዓመታት በፊት የተወሰነው ክልሎቹን ያለሕዝቡ ፈቃድ የመቀላቀል ውሳኔ በየጊዜው በተለያዩ ደረጃዎች ራስን የማስተዳደር ጥያቄዎች ደጋግመው እንዲከሰቱ አድርጓል። አሁንም አስር የሚደርሱ የክልሉ አካባቢዎች ክልል እንሁን የሚል ጥያቄን ይዘው ምላሽ እየጠበቁ ነው። ፕሮፌሰር በየነም ሕግን በመጣስ አምሰቱን ክልሎች ወደ አንድ ሲያጠቃልሏቸው ፖለቲካዊ ውሳኔ ነበር ። ይህም ለዛሬው ጥያቄና ችግር ዋነኛ ምክንያት ነው በማለት ያምናሉ። ሌሎችም አካባቢዎች ክልል የመሆን ጥያቄ አንስተዋል፤ ይህ ተግባራዊ ቢሆን ትናንሽ ክልሎች ከመመስረት ባሻገር በኢትዮጵያ ሃገራዊ ህልውና ላይ ተጽእኖ ይኖራቸዋል ብለው አያስቡም። በርካቶች ክልል የመሆን ጥያቄን ያቀረቡት አካባቢዎች ሁሉም አወንታዊ ምላሽ ቢያገኙ በሚጠበቅባቸው ደረጃ ኃላፊነታቸውን መወጣት ይችላሉ ወይ የሚል ጥያቄ ይነሳል። ፕሮፌሰር በየነም እነዚህ አዲስ ክልል የሚሆኑት አካባቢዎች ከውስጣቸው በቂ ሐብትና ገቢ ማመንጨት ይችላሉ ወይ በራሳቸውስ በቂ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ማድረግና መተዳደር ይችላሉ ወይ የሚሉና ሌሎች ጥያቄዎች በቅድሚያ መመለስ አለባቸው። ባይ ናቸው። ከሌሎች የሃገሪቱ ክልሎች በተለየ በርካታ የክልል እንሁን ጥያቄዎች የቀረቡለት የደቡብ ክልል ምላሽ ለመስጠት የተቸገረ ይመስላል። የክልሉ ገዢ ፓርቲም ከመቀመጫው ሐዋሳ ርቆ አዲስ አበባ ውስጥ በጥያቄዎቹ ዙሪያ ለቀናት ተወያይቶ ያወጣው መግለጫ ተጨባጭ ነገርን አላቀረበም። ያልጠገገው የሀዋሳ ቁስል ጥያቄዎቹ አዎንታዊ ምላሽን አግኝተው ቢያንስ አንድ ክልል መመስረቱ እንደማይቀር የበርካቶች እምነት ሲሆን ይህ ውጤትም በደቡብ ክልል ላይ በተለይ በዋና ከተማዋ ሐዋሳ ላይ የራሱ የሆነ ውጤት ሊኖረው እንደሚችል ይሰጋሉ። ከዚህ አንጻርም አዳዲስ የሚከሰቱ የቦታ ይገባኛልና የድንበር ጥያቄዎች በሚፈጠሩትና በነባር ክልሎች መካከል ሊከሰቱ እንደሚችሉ አንዳንዶች ቢሰጉም ፕሮፌሰር በየነ ግን የሚባሉት ውዝግቦችና ግጭቶች አሁንም ያሉ ናቸው ነገር ግን በሰከነና በተረጋጋ ሁኔታ በሕግ አግባብ መፍታት ብቻ ነው የሚያስፈልገው በማለት ከአዳዲስ ጥያቄዎች ባሻገርም የነበሩ ጥያቄዎች ወደ ፊት መምጣታቸው አይቀርም ይላሉ። ተያያዥ ርዕሶች
የእሳተ ገሞራ ቱሪዝም ፡ አፍቃሬ እሳተ ገሞራዎች
ዲሴምበር ማጋሪያ ምረጥ በአሁኑ ወቅት ዓለም ላይ እየፈነዳ ያለ እሳተ ገሞራን ቀረብ ብለው የመመልከት፣ የፍንዳታ ድምፆቹን የመስማት ከዚህም አልፎ አካባቢው ላይ ተገኝተው ሙቀቱ እንዲሰማቸው የሚፈልጉ አፍቃሬ እሳተ ገሞራ ጎብኚዎች እየበዙ መሆኑ እየተነገረ ነው። ቢያስደነግጥም እሳተ ገሞራ ያለባቸውን አካባቢዎች በማዘውተር የሚደሰቱት እነዚህ ቱሪስቶች ራሳቸውንም አደጋ ላይ እየጣሉ ፤ የድንገተኛ ህክምና እርዳታ አገልግሎት ላይም ችግር እያስከተሉ ነው እየተባለ ነው። የሚፈነዳ እሳተ ገሞራ ለማየት ጎብኚዎች የሚገሰግሱባት አይስላንድ በነገሩ በጣም ከተቸገሩ አገራት የምትጠቀስ ናት። በአገሪቱ በመፈንዳት ላይ ያሉ እሳተ ገሞራዎችን በቅርበት የመመልከት ፍላጎት በጎብኚዎች ዘንድ ከፍተኛ ነው። ጎብኚዎቹ በዚህ ምን ያህል ራሳቸውን ለአደጋ እያጋለጡ እንዳሉ እንደማይረዱም ተገልጿል። በካምብሪጅ የመልክአ ምድር ማህበረሰብ የታተመ አንድ ጥናት የዚህ አይነቱ ቱሪዝም የአገራት የነፍስ አድን ስራ ላይ ትልቅ ጫና እንደሚፈጥር ያሳያል። በጉዳዩ ላይ ጥናት ያደረጉት ዶ ር ዶኖቫን እንደሚሉት እንደዚያ ያለ አስጨናቂ ቦታ ላይ በመገኘት የሚደሰቱ ሰዎች በሌሎች መሰል ነገሮችም ይሳባሉ። ጋዙን መተንፈስና ምድር የምታወጣውን ድምፅ መስማት ያሻቸዋል፤ የመሬትን ድምፅ በደንብ ለመስማት መቅረብ ይፈልጋሉ ይላሉ። የዚህ ዓይነቱ ፍላጎታቸው አይሎ በተለያዩ የአለም ክፍሎች ፈንድተው ያልጨረሱ እሳተ ገሞራዎችን እያደኑ የሚጎበኙ አፍቃሬ እሳተ ጎመራዎችም ቮልካኖፋይል እንዳሉ ዶ ር ዶኖቫን ይናገራሉ። እነዚህ አፍቃሬ እሳተ ገሞራዎች ስሜታቸው አሸንፏቸው ሊያጋጥማቸው የሚችለውን ችግር የዘነጉ መሆናቸውን ዶክተሯ ያስረዳሉ። በፍንቃይ አለቶች ወይም በእሳት ውርዋሪ መመታት እንዲሁም መርዛማ ጋዞችም ሊኖሩ ይችላሉ። እሳቸው እንደሚሉት ጎብኚዎቹ ይበልጥ የማይረዱት የእሳተ ገሞራ ፍንዳታዎች በፍጥነት ተቀይረው እንደ ጎርፍ ያለ አደጋ ሊመጣም ይችላል። በእንዲህ ያለው አጋጣሚ ጎብኚዎችን መታደግ የድንገተኛ አደጋ ተቋማት ላይ ከባድ ጫና ሲፈጥር የጎብኚዎች ደህንነትም አደጋ ውስጥ ይወድቃል። በአይስላንድ በአንድ ወቅት የደህንነት ቁጥጥርን ለማምለጥ ቱሪስቶች በሄሊኮፕተር ምሽት ላይ እሳተ ገሞራ ሳይት ላይ አርፈዋል። እአአ ላይም የቮልካኖ ግግር አቋርጠው ወደ ፍንዳታው የሄዱ ሁለት ጎብኚዎች ሞተዋል። የእሳተ ገሞራ ቱሪዝም ለቱሪዝም ኢንዱስትሪ ትልቅ እርምጃ ቢሆንም አደገኛ ጎንም እንዳለው ተገጿል።
የሚንቀለቀል እሳተ ገሞራ ጉድጓድ ውስጥ የገባው አሜሪካዊ ወታደር ተረፈ
ሜይ አጭር የምስል መግለጫ ሀዋይ የሚገኘው የእሳተ ገሞራ አንድ አሜሪካዊ ወታደር ሜትር ጥልቀት ያለው የእሳተ ገሞራ ጉድጓድ ውስጥ ገብቶ ህይወቱ መትረፉ ተሰምቷል። የ ዓመቱ ወታደር ሀዋይ ውስጥ የሚገኘው እሳተ ገሞራ አቅራቢያ የሄደው ለስልጠና ነበር። እሳተ ገሞራው አናት ላይ ቆሞ ሳለ መሬቱ ከድቶት ጉድጓዱ ውስጥ ወድቋል ተብሏል። እሳተ ገሞራው የሚገኝበት ፓርክ ኃላፊዎች ግለሰቡ ከባድ ጉዳት እንደደረሰበት አሳውቀዋል። ነፍስ አድኖች በገመድ ታግዘው ጎትተውታል። የመከላከያ ሚኒስቴር ሄሊኮፕተርም ረድቶናል የሚል መግለጫ አውጥተዋል። ወታደሩ ወደ ጉድጓዱ ከወደቀ በኋላ አንድ የድንጋይ ጠርዝ ላይ አርፎ ባይቆም ኖሮ እሳተ ገሞራው መሀል ላይ ይገባ ነበር። እሳተ ገሞራው የፈነዳው ባለፈው ዓመት ሲሆን፤ ወደ ቤቶች አውድሟል። ኪላውያ የተባለው ይህ እሳተ ገሞራ ዓለም ላይ ሁሌም ህያው ከሆኑ እሳተ ገሞራዎች አንዱ ነው። ተያያዥ ርዕሶች
የእሱ አባት ኩራዝ የላቸውም፤ እሱ ግን ኢትዮጵያን ሊያበራ ነው የሞተው
ጁላይ ስለ ማጋራት ተጨማሪ ያጋሩ ማጋሪያ ምረጥ ትናንት ባልታወቀ ሁኔታ መኪናቸው ውስጥ ህይወታቸው አልፎ የተገኘው የኢንጂነር ስመኘው ቤተሰቦች መሪር ሃዘን ውስጥ ናቸው። የቢቢሲ ዘጋቢ ትናንት የአስክሬን ምርመራ በሚካሄድበት የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ተገኝታ በጥልቅ ሐዘን ላይ የሚገኙ የቅርብ ቤተሰቦቻቸውን አነጋግራለች። የኢንጂነር ስመኘው በቀለ ቤተሰብ አባላት ሐዘናቸውና ቅሬታቸውን በለቅሶ መሐል ሆነውም አጋርተዋታል። የቅርብ ዘመድ ቢኾኑም ስለ ግድያው በሚዲያ መስማታቸውን የገለጹት እኒህ የቤተሰብ አባላት አስክሬኑ መጉላላቱና የሚገባውን ክብር አለማግኘቱ ቅሬታ እንደፈጠረባቸው ተናግረዋል። ሌሎች የቤተሰቡ አባላት ደግሞ አንድም የመንግሥት አካል በአካባቢው አለመኖሩ የፈጠረባቸውን ቅሬታንም አልሸሸጉም። ስለኢንጂነር ስመኘው አሟሟት እስካሁን ምን እናውቃለን ቢሮ ተቀምጦ አይደለም መግለጫ መስጠት ሲሉ የመንግሥት አካላት ላይ ያነጣጠረ የሚመስል ቅሬታን አሰምተዋል። እሱ ቤቱን ትቶ በረሀ ላይ ነው የኖረው። ለስመኝ ይሄ አይገባውም። ምን አረጋቸው፣ የበደላቸውን ለምን አይነግሩንም ምን አደረጋቸው ይሄ ለሱ አይገባውም ስትል በመሪር ሐዘን ሆና ስሟን ያልገለፀች አንድ የቤተሰብ አባል ተናግራለች። ማነው ጀግና፣ ማነው ጎበዝ ማነው ለአገር አሳቢ። የሚመስል ወይስ የሆነ ሲል በምሬት ሐዘኑን የገለጸው ሌላ ወጣት የእሱ አባት ኩራዝ የላቸውም፤ እሱ ግን ኢትዯጵያን ሊያበራ ነው የሞተው ሲል ሳግ እየተናነቀው ምሬቱን ገልጿል። ከሐዘንተኞቹ መሐል በቅርብ ቀናት ሟችን በስልክም ይሁን በአካል አግኝተዋቸው ያውቁ እንደሆነ ተጠይቀው ኢንጂነሩ ሥራ ላይ ስለሚያተኩሩ እምብዛም ከቤተሰብ ጋር እንደማይገናኙ የሚያመላክት አስተያየቶችን ሰንዝረዋል። እሱ አገሬን ሥራዬን እያለ ሁሉም ሰው ረስቶታል። እሱ ሁሉ ነገሩ ሥራው ላይ ነው። ዘመድ አይልም ስትል ስሟን መግለጽ ያልፈለገች የቤተሰብ አባል። ከሰው ጋር አልኖረም፤ በረሃ ነው የኖረው ስትል ሟች ማኅበራዊ ሕይወት የሚባል ነገር እንኳ እንዳልነበራቸው ተናግራለች። የእርሶ መሳሪያ ሚዲያ ፕሌይ ባክን ማጫወት ኣልተቻለም። ኢንጂነር ስመኘው በቀለ
የተትረፈረፈ ቢመስልም የአሸዋ እጥረት ዓለም ላይ ተፈጥሯል
ኖቬምበር ማጋሪያ ምረጥ በተለይም በበረሃና በባህር ዳርቻዎች የሚገኘው አሸዋ የትም የሚገኝ ቢመስልም በዓለም ላይ ሰዎች እጅጉን እየተጠቀሟቸው ካሉ ነገሮች ሁለተኛው ነው። ባለፈው መስከረም ወር ብቻ ደቡብ አፍሪካዊ ሥራ ፈጣሪ፣ ሁለት ህንዳዊያን እንዲሁም ሜክሲኳዊ የአካባቢ ጥበቃ ተሟጋች ብዙ ዋጋ ባልተሰጠው ነገር ግን በጣም አስፈላጊ በሆነው አሸዋ ምክንያት ተገድለዋል። አሸዋ የሰረቁ ፈረንሳያውያን ጥንዶች ለእስር ተዳረጉ ብዙም ባይመስልም አሸዋ እጅጉን አስፈላጊ ነገር ነው። በጥቅሉ ለከተሞች ግንባታ ወሳኝ ግብአት ነው አሸዋ። የገበያ ማዕከሎች፣ የጋራ መኖሪያ ቤቶች፣ የአስፓልት መንገዶች ግንባታ ያለ አሸዋ የሚታሰብ አደለም። በየቦታው የሚታዩት የመስታወት መስኮቶች፤ የስማርት ስልኮች ስክሪን ጭምር ከቀለጠ አሸዋ የሚሰሩ ናቸው። በስልኮቻችን እንዲሁም በኮምፒውተሮቻችን ውስጥ ያሉ ሲልከን ቺፖችም ከቀለጠ አሸዋ የተሰሩ ናቸው። ይህም ብቻ አይደለም በመኖሪያ ቤቶቻችን ለሚገኙ የኤሌክትሪክ መገልገያ እቃዎች ስሪትም አሸዋ ግብአት ነው። ምንም እኳ ከሰሃራ እስከ አሪዞና ባሉ ሰፋፊ በርሃዎችና በባህር ዳርቻዎች ቢገኝም፤ በአቅራቢያ ከሚገኝ መደብር በቀላሉ ልንገዛው የምንችለው ነገር ቢሆንም በአሁኑ ወቅት ዓለም ላይ የአሸዋ እጥረት አጋጥሟል። ለመሆኑ በዓለም ላይ የትም ቦታ የሚገኝ ነገር እንዴት እጥረት ሊፈጠርበት ይችላል በዓመት ቢሊዮን ቶን አሸዋ በሰዎች ጥቅም ላይ ይውላል። ይህ የአሸዋ መጠን መላዋን እንግሊዝ ሊያለብስ የሚችል ነው። አጥኚዎቹ እንደሚሉት ችግሩ ያለው ጥቅም ላይ እየዋለ ባለው አሸዋ አይነት ምክንያት እንደሆነ እየተናገሩ ነው። ከላይ ለተጠቀሱት አገልግሎቶች ጥቅም ላይ እየዋለ ያለው ለስላሳውና በቀላሉ በንፋስ የሚበነው የበረሃ አሸዋ አይደለም። ይህ በጣም ደቃቅ የበረሃ አሸዋ ለኮንክሪት የሚሆን አይደለም። ይልቁንም ለሰዎች አስፈላጊ የሆነው ባለ ማእዘኑ እና በወንዞች እና በሃይቆች የሚገኘው ነው። ስለዚህም ይህኛውን አሸዋ ለማግኘት በወንዞች መድረሻ፣ በእርሻ ማሳዎ እንዲሁም በጫካዎች ውስጥ ሕገ ወጥ ፍለጋ ይካሄዳል። ጥቂት በማይባሉ አገራትም የወንጀለኛ ቡድኖች በዚህ የአሸዋ ንግድ ላይ ተሰማርተዋል፤ በዚህ ሳቢያ ደግሞ የአሸዋ ጥቁር ገበያም ተስፋፍቷል። የአሸዋ እጥረት ጉዳይ ብዙዎች እያስገረመ ነው ግን ሊያስገርም አይገባም። ያለ ምንም አካባቢያዊ ተፅዕኖ የአንድን ተፈጥሯዊ ሃብት ቢሊዮን ቶን የሚያክል ነገር ማውጣት የሚቻል ነገር አይደለም ይላሉ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአካባቢ ጥበቃ ፕሮግራም ተመራማሪው ፓስካል ፔዱዚ። ተያያዥ ርዕሶች
በኒውዚላንድ እሳተ ገሞራ ፍንዳታ የሟቾች ቁጥር ደረሰ
ዲሴምበር ማጋሪያ ምረጥ ባለፈው ሳምንት በኒውዚላንድ ባጋጠመው የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ የሟቾች ቁጥር ወደ ከፍ ማለቱ ተዘግቧል። ከአደጋው ከባድ ጉዳት ደርሶበት የነበረ አንድ ግለሰብ ሕይወቱ ማለፉን ፖሊስ አስታውቋል። ማንነቱ ያልተገለጸው ይህ ግለሰብ ለህክምና ወደ አውስትራሊያ ተወስዶ ነበር። እስካሁን የሚደርሱ ሰዎች ከፍተኛ ቃጠሎ ደርሶባቸው በሞትና በሕይወት መካከል ይገኛሉ። ሙሽሪት በሰርጓ ቀን ዋዜማ ጉድጓድ ውስጥ ገብታ ሞተች በተጨማሪም ዛሬ እሳተ ገሞራው ወደ ፈነዳበት ደሴት በመሄድ የሌሎች ሁለት ሰዎችን ሬሳ ለማግኘት የተደረገው ጥረት ሳይሳካ ቀርቷል። በአካባቢው ፍለጋ የሚያደርጉ ስምንት ፖሊሶች ለ ደቂቃዎች ያክል ቢሰማሩም ምንም ነገር ሊገኝ እንዳልቻለ ምክትል ፖሊስ ኮሚሽነሩ ማይክ ክለመንት ለጋዜጠኞች ገልጸዋል። ምንም እንኳን ፍለጋችንን አጠናክረን ብንቀጥልም ተጨማሪ የሟቾችን ሬሳ ማግኘት አልቻልንም ብለዋል። እስካሁን የተገኙ የሟቾች ሬሳ ላይ ምርመራ እየተደረገ ሲሆን ከሟቾች መካከል አንድ ኒውዚላንዳዊ የ ዓመት አስጎብኚ እንደሚገኝበት ተገልጿል። አንዲት ዓመት አውስትራሊያዊና የ ዓመት አባቷ እንዲሁም ሌላ የ ዓመት አውስትራሊያዊ ከሟቾች መካከል ናቸው። የሌሎቹን ሟቾች ማንነት ለመለየት ደግሞ ተጨማሪ ምርመራዎች እንደሚያስፈልጉ ተገልጿል። እሳተ ገሞራው በደሴቲቱ ድንገት ሲፈነዳ ሰዎች በጉብኝት ላይ የነበሩ ሲሆን ከእነሱም መካከል አውስትራሊያውያን፣ ዘጠኝ አሜሪካውያን፣ አምስት ኒውዚላንዳውያን፣ አራት ጀርመናውያን፣ ሁለት ቻይናውያን፣ ሁለት እንግሊዛውያን እና አንድ ከማሌዢያ ናቸው። ተያያዥ ርዕሶች
ቦትስዋና፡ የምርምሩን ዝሆን የገደሉት አዳኞች ፈቃዳቸውን ተነጠቁ
ዲሴምበር በቦትስዋና ሁለት አዳኞች የምርምር ዝሆን መግደላቸውን ተከትሎ ፈቃዳቸው ተነጥቋል። ሚሸል ሊ ፖተርና ኬቪን ሻርፕ የተባሉት አዳኞችም በሃገሪቱ መንግሥት ትዕዛዝ መሰረት የአደን ፈቃዳቸውን አስረክበዋል። ለረዥም ጊዜያት የዝሆን አደንን ከልክላ የነበረችው ቦትስዋና ከጥቂት ወራት በፊት ነበር እንደገና የፈቀደችው። ዝሆኖች በመንደሮች ውስጥ ባሉ እርሻዎች ውስጥ በመግባት እህሎችን በማበላሸት እንዲሁም ሰዎችን እየገደሉ ስላስቸገሩም ነው አደኑ እንደገና ፈቃድ ያገኘው። ነገር ግን አሁን የተገደለው ይህ ዝሆን የምርምር በሚል ጥበቃ እንዲደረግለት ተወስኖ ነበር። በቦትስዋና የሚገኙ ዝሆኖች ቁጥር ወደ ሺ ይጠጋል። ዝሆኑ መገደሉን ተከትሎ ቅዳሜ እለትም የቦትስዋና መንግሥት ባወጣው መግለጫ ሚሼል ሊ ፖተር እስከ መጨረሻው ድረስ የአደን ፈቃዱ የማይመለስለት ሲሆን የሌላኛው አዳኝ ኬቪን ሻርፕም ለሶስት አመት የሚወሰድበት ይሆናል ተብሏል። የአብዲሳ አጋ ጀብዱ በሥዕል መጽሐፍ የሁለቱ አዳኞች ዜግነት ያልተገለፀ ሲሆን፤ ግለሰቦቹም ለቢቢሲ አስተያየት ከመስጠት ተቆጥበዋል። ከዚህም በተጨማሪ ዝሆኑ አንገቱ ላይ አድርጎት የነበረውን ቀበቶ እንዲተኩ የተጠየቁ ሲሆን አንገቱ ላይ አጥልቆት የነበረው ቀበቶ እንዴት እንደተበላሸ የተገለፀ ነገር የለም። ከዚህ ቀደም መንግሥት ባወጣው መግለጫ ዝሆኑ ፊት ለፊት ቆሞ ስለነበር አጥልቆት የነበረውን ቀበቶ ማየት እንዳልቻሉ አዳኞቹ መናገራቸውን አትቷል። ዝሆኑ ከወደቀ በኋላ ግን ቀበቶውን ማየት እንደቻሉና የምርምርም መሆኑን መረዳታቸውንም መናገራቸው በመግለጫው ተካትቷል። ነገር ግን ይህ አሳማኝ እንዳልሆነ የካላሃሪ የጥበቃ ማህበር ለኤኤፍፒ የዜና ወኪል አሳውቋል፤ ለዚህም እንደምክንያትነት የሰጡትም የዝሆን ቀበቶ በጣም ትልቅና ከየትም አቅጣጫ እንደሚታይ በመግለፅ ነው። ሮይተርስ በበኩሉ እንደዘገበው ሁለቱ አዳኞች ቀበቶውን ያበላሹት ማስረጃ ለመደበቅ ሲሞክሩ እንደሆነ ነው። አብዛኛዎቹ ዝሆኖች በሃገሪቱ ሰሜናዊ ክፍል የሚገኙ ሲሆን በናሚቢያ፣ ዛምቢያና ዚምባብዌን በሚያዋስነው ድንበር በነፃነት ይንቀሳቀሳሉ። በአፍሪካ ውስጥ ሺ የሚገመቱ ዝሆኖች የሚገኙ ቢሆንም ባለው የህገወጥ አደን ምክንያት ቁጥራቸው እያሽቆለቆለ ነው ተብሏል። ተያያዥ ርዕሶች
ብራዚል ተዋናይ ሌዎናርዶ ዲካፓሪዮ አማዞን ጫካ እንዲቃጠል አድርጓል ስትል ከሳለች
ዲሴምበር ማጋሪያ ምረጥ የብራዚሉ ፕሬዝደንት ጃይር ቦልሶናሮ ተዋናይ ሌዎናርዶ ዲካፕሪዮ የአማዞን ጫካ እሣት እንዲለብስ የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል ሲሉ ወቀሱ። ፕሬዝደንቱ ተዋናይ ይህንን ስለማድረጉ ምንም ዓይነት ማስረጃ ባይሰጡም አማዞን ጫካ ላይ የሚሠሩ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን ሲወቅሱ የመጀመሪያቸው አይደለም። ሰደድ እሣቱን ያስነሱት የገንዘብ ድጋፍ ማግኘት የፈለጉ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን ናቸው ያለው የብራዚል መንግሥት የጠረጠራቸውን በርካታ ሰዎች አሥሯል። ለአማዞን ጫካ መልሶ መቋቋም ሚሊዮን ዶላር ለመስጠት ቃል የገባው ሌዎናርዶ የፕሬዝደንቱን ወቀሳ አስተባብሏል። ብራዚል የቬንዝዌላን ዲፕሎማት አባረረች አራት በጎ ፈቃደኛ የሰደድ እሣት ተከላካዮች በብራዚል መንግሥት መታሠራቸውን ተከትሎ በርካታ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የቦልሶናሮ መንግሥትን እየወረፉ ይገኛሉ። ኢ መንግሥታዊ ድርጅቶች እና የመብት ተሟጋቾች የብራዚል መንግሥት ድርጊት ፖለቲካዊና ተፈጥሮ ላይ የሚሠሩ ድርጅቶችን ለመፈታተን ያሰበ ነው ሲሉ ቅሬታቸውን ያሰማሉ። ባለፈው ነሐሴ የሰደድ እሣት ሰለባ የሆነው የብራዚሉ አማዞን ጫካ ጉዳይ ብዙዎችን ያስጨነቀ ሆኗል። ኔይማር ደፍሮኛል ያለችው ሴት ቲቪ ላይ ቀርባለች ፕሬዝደንቱ ባለፈው አርብ በመኖሪያ ቤታቸው ሳሉ ነው ወቀሳቸውን የሰነዘሩት። ሌዎናርዶ ዲካፕሪዮ የሚሉት ሰውዬ ጥሩ ይመስላል አይደል ገንዘብ ሰጥቶ አማዞንን የሚያነድ። እነዚህ ኤንጂኦ ተብየዎች ምንድነው የሚሠሩት ጫካውን ያቃጥላሉ ከዚያ ፎቶ ያነሳሉ፤ ቪድዮ ይቀርፃሉ። ዎርልድ ዋይልድላይፍ ፈንድ ለምሳሌ ከዲካፕሪዮ ጋር ነው የሚሠራው፤ እሱም ሸህ ዶላር እርዳታ አድርጓል። በተፈጥሮ ጥበቃ ለተሰማሩ ድርጅቶች ድጋፍ በማድረግ የሚታወቀው ዲካፕሪዮ፤ ምንም እንኳ አማዞን ጫካ ውስጥ የሚሠሩ ድርጅቶች እርዳታ ቢሹም እኔ እርዳታ አላደረግኩም ሲል ወቀሳውን አስተባብሏል።
የዓለማችን ውቅያኖሶች ኦክስጂን እያጠራቸው ነው
ዲሴምበር ማጋሪያ ምረጥ የአየር ጸባይ ለውጥና የውሀ አካላት በተለያዩ ነገሮች መበከል ምክንያት በውቅያኖሶች ውስጥ የሚገኘው ኦክስጂን መጠን መቀነስ በርካታ የአሳ ዝርያዎችን ሊያጠፋ እንደሚችል ተገለጸ። በዚሁ ዙሪያ ጥናቱ የሰሩ ተመራማሪዎች እንደሚሉት ከሚሆኑ የተለያዩ የውቅያኖስ ክፍሎች ላይ በተደረገ ጥናት ውቅያኖሶቹ በእጅጉ ኦክስጂን እያጠራቸው ሲሆን በአውሮፓውያኑ ከ ዎቹ ጀምሮ ከፍተኛ መቀነስ ታይቷል። የውሃ እጥረት ዋነኛው የዓለማችን ስጋት በዚህም ምክንያት እንደ ቱና፣ ማርሊን እና ሻርክ ያሉ የአሳ ዝርያዎች የመጥፋት አደጋ ተጋርጦባቸዋል። ወደ ውሃ አካላት የሚለቀቁ ኬሚካሎች ደግሞ ለኦክስጂን መጠን መቀነስ ዋነኛ ምክንያቶች ናቸው። በተለያዩ ፋብሪካዎችና ትላልቅ እርሻዎች የሚለቀቁት እንደ ናይትሮጂን እና ፎስፈረስ ያሉ ኬሚካሎች በተለይ ደግሞ በዳርቻዎች አካባቢ ለሚገኙ አሳዎች መሞት ምክንያት ናቸው። ከዚህ በተጨማሪ የአየር ጸባይ ለውጥም ከፍተኛ ተጽዕኖ እየፈጠረ ነው። ከምን ጊዜውም በበለጠ ከፍተኛ መጠን ያለው ካርቦን ዳይኦክሳይ ወደ ከባቢ አየር የሚለቀቅ ሲሆን ይህ ደግሞ ከፍተኛ ሙቀት እንዲፈጠር ያደርጋል። ውቅያኖሶችና ሌሎች ትልልቅ የውሀ አካላት ሙቀቱን ሰብስበው ይይዙታል። ሙቅ ውሀ ደግሞ በውስጡ ብዙ ኦክስጂን መያዝ አይችልም። ተመራማሪዎቹ እንደገመቱት አ አ አ ከ እስከ ባሉት ዓመታት በውቅያኖሶች የሚገኘው የኦክስጂን መጠን በአማካይ በመቶ ቀንሷል። ምናልባት ይህ ቁጥር ትንሽ ሊመስል ይችላል፤ ነገር ግን ቁጥሩ የዓለማችን አማካይ ስለሆነ ነው እንጂ በአንዳንድ ሞቃታማ አካባቢዎች እስከ በመቶ ድረስ ቀንሷል። እንደ ቱና፣ ማርሊን እና ሻርክ ያሉ የአሳ ዝርያዎች በተለየ ሁኔታ ከፍተኛ የኦክስጂን መጠን በውሃ ውስጥ ይፈልጋሉ። ይህ ሁኔታ ለነዚህ የዓለማችን ህዝብ በብዛት ለሚመገባቸው አሳዎች መጥፎ ዜና ነው። የ ኛው ክፍለ ዘመን ነዳጅ ውሃ ትልልቅ አሳዎች በውሀ ውስጥ ለመንቀሳቀስ ከፍተኛ ሃይል የሚያስፈልጋቸው ሲሆን ያለ ኦክስጂን ደግሞ ይህ የማይታሰብ ነው። ታዲያ እነዚህ አሳዎች ኦክስጂን ፍለጋ ትልቅ ወደሚባለው የውቂያኖስ ክፍል መሸሽን እየመረጡ ነው። ሀገራት በዚሁ ውቅያኖሶችን የመበከል ስራቸው የሚቀጥሉ ከሆነ እ አ አ በ የምንላቸውን አሳዎች አናገኛቸውም ማለት ነው። ይህ ደግሞ አንድ የምግብ ምንጭ ከሰው ልጆች ተነጠቀ ማለት ነው። የውቅያኖሶች አሰራር አሁንም የሰው ልጅ ሙሉ በሙሉ ተመራምሮ ያልደረሰበት እንደመሆኑ እንዲህ አይነት እክሎች ምን አይነት አደጋ ይዘው ሊመጡ እንደሚችሉ መገመት እጅግ ከባድ ነው። ተያያዥ ርዕሶች
በኮሮናቫይረስ ስጋት ምክንያት የ ምርጫ መራዘሙ ተገለፀ
የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ከተከሰተ ወዲህ አገራት የተለያየ እርምጃ እየወሰዱ ነው። የአየርም ሆነ የብስ ድንበሮቻቸው የዘጉ፣ ከተሞቻቸውን ከእንቅስቃሴ ያቀቡ እንዲሁም ሰዓት እላፊ የጣሉ አገራት በርካቶች ናቸው። ሁሉም ቢሆኑ በአንድ ድምጽ ስለ ወረርሽኙ መከላከያ ሲናገሩ የሚደመጠው አካላዊ ርቀትንና፣ የግል ንጽህናን መጠበቅ እንዲሁም የበሽታው ምልክት የሚታይባቸው ሰዎች ራሳቸውን ለይተው እንዲያቆዩ ነው። ዓለም በአሁኑ ሰዓት ሺህ ያህል ዜጎቿን በኮቪድ ምክንያት አጥታለች። ከዚህ ሰዓት ጀምሮ ከዓለም ዙሪያ የምናሰባስባቸውን ዘገባዎች በቀጥታ እናቀርብላችኋለን።
የብዙ ኢትዮጵያዊያንን ህይወት እየቀየረ ያለው የተፈጥሮ ጥበቃ ሥራ
ኖቬምበር ስለ ማጋራት ተጨማሪ ያጋሩ ማጋሪያ ምረጥ በሰሜናዊ ኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ባለፉት አስር ዓመታት በሰው ሰራሽና ተፈጥሯዊ ምክንያት ተጎድተው የነበሩ አካባቢዎች በእጽዋት እየተሸፈኑ ይገኛሉ። ይህ ደግሞ በቂ ውሃ እንዲኖር ከማድረግ ባለፈ የዱር እንስሳትም እንዲመለሱ አድርጓል፤ ንቦችንም ጨምሮ። የቢቢሲው ጀስቲን ሮውላት ወደ ትግራይ ክልል በተጓዘበት ወቅት ብዙ አስገራሚ ነገሮችን እንደተመለከተ ይናገራል። የማይረሳው ነገር ግን የነደፉትን ንቦች እንደሆነ ገልጿል። በወቅቱ ያልጠበቅኩትና አስደንጋጭ ነገር ነበር ብሏል ስለንቦቹ ሲያስረዳ። በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ መሪነት የሚሰራው በዓለማችን እጅግ የተራቆቱ ከሚባሉት አንዱ የሆነውን አካባቢ መልሶ በደን የመሸፈን ስራ ትልቅ ራዕይ አንግቦ የተጀመረ እንደሆነ ጀስቲን ይገልጻል። ሳናውቀው እያለቁብን ያሉ ስድስት ነገሮች መልሶ የማልማት ስራውን ከሚቆጣጠሩ የስነ ደን ባለሙያዎች መካከል አንዷ የሆነችው ሳራ ተወልደብርሀን፣ ጀስቲንን ይዘው ወደ ጥብቅ ደኑ ሄደች። ይህንን የመሰለ ትልቅ ፕሮጀክት በአግባቡ እንኳን በአጥር አለመከለሉ እያስገረመኝ ተከትለኳት ይላል ጀስቲን። በሳራ መሪነትም ወደ ተለያዩ አካባቢዎች የሚከፋፈሉ ችግኞች የሚዘጋጁበትን ቦታ ተመለከቱ። አካባቢው ደስ የሚልና ሰላማዊ ስሜትን ይፈጥራል። ወፎች ሲዘምሩ መስማት ደግሞ እጅግ ያስደስታል። በልጅነቴ ስለ ሰሜን ኢትዮጵያ እየሰማሁት ካደግኩት ታሪክ ጋር ሊጣጣምልኝ አልቻለም። እኤአ በ ዎቹ ውስጥ ተከስቶ የነበረው ረሃብ ስለዚህ አካባቢ የተለየ አስተሳሰብ እንዲኖረኝ ነበር ያደረገው። አጭር የምስል መግለጫ በድርቁ ወቅት ምግብ በመፈለግ ላይ የነበረ ህጻን በወቅቱ ለተከሰተው ድርቅ ብዙ ምክንያቶች ቢኖሩም መንግስት አካባቢዎቹን ችላ ማለቱ፣ ጦርነት እና የደን ጭፍጨፋ ተጠቃሽ ናቸው። በምድራችን እጅግ ከፍተኛ ከሚባሉ የደን ጭፍጨፋዎች ከተደረገባቸው ሀገራት መካከል ኢትዮጵያ ቀዳሚውን ስፍራ ትይዛለች። ያለዛፎች ደግሞ ለም የሆነውን የአፈር ክፍል መጠበቅ ከባድ ነው። ነገር ግን ሳራ እና ጓደኞቿ እያከናወኑት ባለው የተፈጥሮ ጥበቃና መልሶ የማልማት ስራ አካባቢው አረንጓዴና እጅግ ማራኪ ቦታ ሆኗል። የስራቸውን ውጤት በቀላሉ መመልከት ይቻላል። ተፈጥሮ ራሷን መልሳ ማዳን ትችላለች በማለት ሳራ እንደነገረችው ጀስቲን ያስታውሳል። የማዉ ጫካን ለማዳን ሺ ኬንያውያን ከመኖሪያቸው ተባረሩ ደኑን ወደነበረበት መመለስ ለአካባቢው አዲስ ነገር ነው። ነገር ግን አካባቢው ነዋሪዎች ፕሮጀክቱን ለመደገፍ ከፍተኛ ፍላጎት አሳይተዋል። ከብቶች ለግጦሽ እንዳይጠቀሙትና ዛፎች እንዳይቆረጡ በትብብር ይሰራሉ ስትል ስለአካባቢው ነዋሪዎች ሳራ ታስረዳለች። በማህበረሰቡ ጋር በትብብር የሚሰራው አካባቢውን መልሶ በደን የመሸፈን ስራ፣ ውጤታማ በመሆኑ ምክንያት በትግራይ ክልል ስኩዌር ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ቦታ ሙሉ በሙሉ በደን ተሸፍኗል። በአንዳንድ አካባቢዎች ደግሞ ለብዙ ዓመታት ደርቀው የነበሩ ምንጮች ጭምር ተመልሰው ውሃ ማፍለቅ ጀምረዋል። ወንዞችም ቢሆን ዓመቱን ሙሉ መፍሰስ ከጀመሩ ሰነባብተዋል። በቅርብ የሚገኙ ገበሬዎች ምርት በእጅጉ ጨምሯል። በደኑ ውስጥ ስንዘዋወር አንድ ነገር ቀልቤን ገዛው። አረንጓዴ ቀለም የተቀቡ የንብ ቀፎዎች በብዛት ይታያሉ፤ በቅርበት ለመመልከት ተጠጋን። ምንም እንኳን ሳራ በጥንቃቄ እንድንቀሳቀስ ብትነግረኝም ብዙም አላሳሰበኝም ነበር የሚለው ጀስቲን በድንገት ግን ያላሰበው ነገር አጋጥሞታል። ወዲያውኑ በእጄ አካባቢ በጣም የሚያቃጥል ስሜት ወረረኝ። ልብሴን ሰብስቤ ስመለከት ሁለት ንቦች ወደታች ሲወርዱ አየኋቸው። ሁለቱም ንቦች ከነደፉኝ አካባቢ አነስተኛ ደም ተቋጥሮ ይታይ ነበር። እርዱኝ ንቦቹ ነደፉኝ ብዬ ጮህኩኝ ሳራ ወደ ጀስቲን ስትሄድ እሷም በንቦች ተነደፈች።
የአሜሪካ ምርጫ፡ ቢሊየነሩ ማይክል ብሉምበርግ ለፕሬዝዳንትነት ሊወዳደሩ ነው
ኖቬምበር አጭር የምስል መግለጫ ማይክል ብሉምበርግ ቢሊየነሩ የንግድ ሰው ማይክል ብሉምበርግ የዴሞክራቲክ ፓርቲን በመወከል ለአሜሪካ ፕሬዝዳንትነት ለመቅረብ ራሳቸውን በእጩነት የማቅረብ ጠንካራ ፍላጎት እንዳላቸው ተገለጸ። የቀድሞው የኒው ዮርክ ከተማ ከንቲባ የነበሩት የማክል ብሉምበርግ ቃል አቀባይ እንደተናገሩት፤ አሁን ካሉት ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር በመፎካከር ዲሞክራቲክ ፓርቲን ወክለው ለመቅረብ እጩ የሆኑት ሰዎች አሸናፊ ሆነው ለመውጣት ባላቸው ብቃት ላይ ብሉምበርግ ስጋት እንዳላቸው አመልክተወል። የ ዓመቱ ብሉምበርግ አላባማ ውስጥ የሚካሄደው የዕጩዎች ፉክክር ላይ ለመቅረብ የሚያስችላቸውን ማመልከቻ በዚህ ሳምንት ያቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል። በቀጣይ ዓመት በሚደረገው የአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ላይ ከዶናልድ ትራምፕ ጋር ለመፎካከር በአጠቃላይ ዕጩዎች ቀርበዋል። የአየር ንብረት ለውጥ ሚሊዮን አፍሪካውያንን ለረሃብ አጋለጠ የቀድሞው ምክትል ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን፣ የማሳቹሴትስ ግዛት ምክር ቤት አባል ኤልዛቤት ዋረንና የቬርሞንት ግዛት ምክር ቤት አባሉ በርኒ ሳንድስ በምርጫ ፉክክሩ ላይ በቀዳሚነት ይጠቀሳሉ። በቅርቡ በተሰበሰቡ የተወሰኑ የሕዝብ አስተያየት መለኪያዎች በተገኘ ውጤቶች መሰረት ኤልዛቤት ዋረንና በርኒ ሳንደርስ የዴሞክራቲክ ፓርቲን ፕሬዝዳንታዊ ዕጩነት ካገኙና ከወቅቱ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጋር ከተፎካከሩ ትራምፕ አሸንፈው ለሁለተኛ ዙር ዋይት ሐውስ ውስጥ የመቆየት እድላቸው የሰፋ ይሆናል ተብሏል። የማይክል ብሉምበርግ ቃል አቀባይ ጨምረው እንዳሉት፤ ትራምፕ የሚሸነፉበትን መንገድ ለማመቻቸት ሥራችንን መጨረስ አለብን። ነገር ግን ብሉምበርግ የዴሞክራቲክ ፓርቲውን ወክለው ለመወዳደር የቀረቡት እጩዎች ብቃት አሳስቧቸዋል ብሏል። ተያያዥ ርዕሶች
ካዛክስታን ውስጥ የመንገደኞች አውሮፕላን ተከሰከሰ
ታህሳስ ይህንን ለማጋራት በ ዋትስአፕ ዘጠና ስምንት ሰዎችን አሳፍሮ ይጓዝ የነበረ የካዛክስታን አውሮፕላን ወድቆ በመከስከሱን ቢያንስ ሰዎች መሞታቸውን የአገሪቱ አየር ማረፊያ ባለስልጣናት ተናገሩ። በአደጋው ቢያንስ ሰዎች የመቁደሰል ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን ከእነሱም መካከል ስምንቱ ህጻናት መሆናቸውን የአካባቢው የሆስፒታል ምንጮች ገልጸዋል። ባለስልጣናቱ እንዳሉት ቤክ ኤር የተባለ አየር መንገድ ንብረት የሆነው አውሮፕላን ከአልማቲ አየር ማረፊያ ዛሬ ጠዋት ከተነሳ ከአጭር ጊዜ በኋላ ነበር የወደቀው። በመጀመሪያ ላይ በአስቸኳይ ወደ ስፍራው የደረሱት የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች ሰባት ሰዎች መሞታቸውን አረጋግጠው ነበር፤ ነገር ግን የሟቾቹ ቁጥር ወደ ከፍ ብሏል። አደጋው ከደረሰበት ስፍራ አቅራቢያ የነበረ ቨየሮይተርስ ዘጋቢ እንዳለው በአካባቢው ከባድ ጭጋግ እንደነበረ ያመለከተ ቢሆንም የአደጋው መንስኤ ምን እንደሆነ እስካሁን አልታወቀም። አውሮፕላኑ ከካዛክስታኗ ትልቅ ከተማ አልማቲ ተነስቶ ወደ ዋና ከተማዋ ኑር ሱልጣን ለመጓዝ ነበር መንገደኞችን ይዞ የተነሳው። የአውሮፕላን ማረፊያው ባለስልጣናት እንዳሉት በአውሮፕላኑ ውስጥ የነበሩት መንገደኞች ሲሆኑ ቱ ደግሞ የአውሮፕላኑ ሰራተኞች ነበሩ። አክለውም አውሮፕላኑ እንደተነሳ ከቁጥጥር ውጪ መሆኑንና መጀመሪያ ላይ የመከለያ ግንብ ገጭቶ ከባለ ሁለት ፎቅ ህንጻ ጋር ተጋጭቶ ነው የወደቀው።
ውክልናን በቪድዮ፡ የውክልና ሂደትን በ ደቂቃ
ፌብሩወሪ አጭር የምስል መግለጫ ኬብሮን ደጀኔ ከአምባሳደር ካሳ ተክለብርሃን ጋር ኬብሮን ነዋሪነቱ በአሜሪካ ካሊፎርኒያ ግዛት ሲሆን ኢትዮጵያ ለሚገኙ ወዳጅ ዘመዶቹ ውክልና ለመስጠት አስቦ ሂደቱን በአሜሪካን ሃገር ቢጀምርም ነገሮች እንዳሰባቸው ቀላል ሆነው አላገኛቸውም። በዚህ ምክንያት የተነሳም የውክልና አሰጣጥ ሥርዓቱን ለመቀየር ቆርጬ ተነሳሁ ይላል፤ ኬብሮን ። እንዳለውም አደረገው። የውክልና ሥርዓቱን በማዘመን የሚወስደውን ጊዜ ከወራት ወደ ደቂቃዎች ለማሳጠር ችሏል። እንዴት ኬብሮን ደጀኔ ሲሊከን ቫሊ በመባል የሚታወቀው የአሜሪካ ቴክኖሎጂ እምብርት ውስጥ ቪዲቸር የሚባል ድርጅት ካቋቋመ አምስት ዓመት ሊሆነው ነው። አሁን ደግሞ ከኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር በመሆን የውልና ማስረጃን አሠራር ለማፋጠን ትልቅ ሚና ለመጫወት በቅቷል። በዛሬው ዕለት በ ቪዲቸር የተደገፈው የውክልና አሠራር በዋሺንግተን ዲሲ ባለው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ተመርቋል። ለሕዝብ አገልግሎትም ሥራ ላይ እንዲውል ይፋ ተደርጓል። ሞባይል ለኢትዮጵያ እናቶችና ህፃናት ጤና የተጓተተ የውክልና ሂደት ከሁለት ዓመት በፊት ነበር ከውክልና አሠራር ጋር ኬብሮን ግብ ግብ የገጠመው። በኢትዮጵያ ያለን የንግድ ተቋም ዘመድ እንዲያንቀሳቅስለት በማሰብ የውክልና ሂደቱን ቢጀምርም በካሊፎርኒያና በአካባቢው ውክልና የሚጽፍለትም ሆነ የሚያረጋግጥለት ማግኘት ሳይችል ቀረ። ከስድሰት ሰዓታት የአየር ጉዞ በኋላ በዋሽንግተን ዲሲ ሂደቱን አስጀመረ። ውክልና የመስጠት ተግባሩ ግን ቀላል አልነበረም። የተለያዩ ነገሮችን ማሟላት ይጠይቅ እንደነበር እንዲሁም በሕግ ባለሙያ አረጋግጦ ቢያንስ ቀናት መጠበቅ ግድ እንሆነ ይናገራል። ከስንት ወጣ ውረድ በኋላ ኢትዮጵያ የደረሰው የውክልና ወረቀት ስህተት አለበት በመባሉ በድጋሚ ለማሠራት መገደዱንም ኬብሮን ይናገራል። እንደዚህ ዓይነት ችግሮች መኖራቸውን ከዚህ ቀደም ከብዙ ሰዎች ይሰማ የነበረ ቢሆንም በእርሱ ላይ ከደረሰበት በኋላ አሠራሩን ለመቀየር ቆርጦ እንደተነሳ ይናገራል። በውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር እና ቪዲቸር መካከል በተደረሰው ስምምነት መሰረት የውልና ማስረጃን አሠራር ለመቀየርና ዲጂታላይዝ ወይም አውቶሜት ለማድረግም ቪዲቸር ለተሰኘው የኬብሮን ተቋም ፈቃድ ተሰጠ። እነ ፌስቡክ ግላዊ መረጃዎትን ያለአግባብ እንደሚጠቀሙበት ያውቃሉ ለመሆኑ ቪዲቸር ምንድን ነው ቪዲቸር ማለት የእንግሊዘኛውን ቪድዮ እና ሲግኒቸር ፊርማ ቃላት በማጣመር የመጣ ቃል ሲሆን ስሙ እንደሚገልፀውም እራስን ቪድዮ በማንሳት መፈረም ማለት ነው። በብዕር ጫር ጫር የሚደረገው ፊርማ የሰውን ደህንነት ይጠብቃል ብዬ አላምንም የሚለው ኬብሮን፤ አንድ ሰው ውክልና ለሚሰጠው ሰው በሰነዱ መስማማቱን እየገለፀ እራሱን በቪድዮ ይቀርፃል። ቪድዮውም በሰነዱ ይካተታል ስለዚህም ለማረጋገጥ ቀላል ይሆናል ሲል ያስረዳል። ጥሩነቱ ማንኛውም ባለ ጉዳይ ካለበት ሆኖ መተግበሪያውን በስልክ በመጫን ቪድዮውን ቀርፆ መላክ መቻሉ ነው። ለጊዜው ግን በአሜሪካ ላሉ ኢትዮጵያውያን ብቻ ነው የጀመርነው በማለት ሂደቱን ያብራራል። በመጀመሪያ ንግግሬን ከአምባሳደር ግርማ ብሩ ጋር ነበር የጀመርኩት ከዚያ በኋላ ከአምባሳደር ካሳ ተክለብርሃን ጋር ወደ ስምምነት አደረስነው። አምባሳደር ካሳም የቴክኖሎጂውን ሃሳብ ወደ ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር በመላክ ወደ ውሳኔ አደረሰው በማለት ወደ ሥራ እንዴት እንደገባ ያስረዳል። ከውጪ ሃገር ወደ ኢትዮጵያ የሚላክ የውክልና ሂደት ምን ይመስል ነበር ወካይ በአቅራቢያው ባለ የኢትዮጵያ ኤምባሲ በማምራት የውክልና ሰነዱን ያጽፋል ኤምባሲው ውክልናውን ተረክቦ ከገመገመ በኋላ ፊርማና ማህተም አስፍሮ ለአመልካች ያስረክባል አመልካች ሰነዱን ከኤምባሲ ተረክቦ ወደ ፈጣን የፖስታ አገልግሎት ወይም ወደ ፖስታ ቤት በመሄድ ሰነዱን ለተወካይ ይልካል ተወካይ ከፖስታ ቤት የውክልናውን ሰነድ ይረከባል ተወካይ ሰነዱ በቆንሱላ ጽሕፈት እንዲረጋገጥ ለውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ይወስዳል በቆንሱላ ጽሕፈት ቤት ከተረጋገጠ በኋላ ወደ ውልና ማስረጃ በመውስድ በሰነዶች ማረጋገጫ እንዲረጋገጥ ያደርጋል ይህ ሁሉ ሂደት በትንሹ ከ እስከ የሥራ ቀናት ሊፈጅ ይችል እንደነበርና በ ቪዲቸር ግን ሙሉ ሂደቱ ወደ ደቂቃ እንዲያጥር መቻሉ ተነግሯል። እስራኤል ዮሐንስ በቆንሱል ጽሕፈት ቤት ቢሮ ካሉት ሠራተኞች መካከል አንደኛው ሲሆን መተግበሪያው ለተጠቃሚም ሆነ ለእኛ በጣም ቀላልና ፈጣን ነው በማለት የማረጋገጫውን ሂደት እንደሚያቃልል ይናገራል። በኢትዮጵያ የቪዲቸር አማካሪ የሆነችው ጺዮን ትርሲት አክሊሉ ከውጪ የሚመጡ ብዙ የውክልና ሰነዶች ወደ ኢትዮጵያ እንደሚላኩና ሂደቱን ለማፋጠን መሞከሩ ለሁሉም ጠቃሚ መሆኑን ትናገራለች።
የ ፈጠራዎች ባለቤት የሆነው የ ዓመቱ ታዳጊ ኢትዮጵያዊ፡ ኢዘዲን ካሚል
ጁን አጭር የምስል መግለጫ ኢዘዲን ካሚል ለፈጠራ ሥራዎቹ ከጠ ሚ ዐብይ አሕመድ ሰርቲፊኬት ሲቀበል በፀሐይ ኃይል ያለ ፔዳል እንደ ሞተር የሚንቀሳቀስ ብስክሌት በተራመዱ ቁጥር ስልክዎን ቻርጅ ለማድረግ የሚበቃ ኃይል ከፀሐይ የሚያመነጭ ጫማ፣ የዘይት ጄሪካን ላይ ስልክ ተገጥሞለት የእሳት አደጋ ሲከሰት ጥሪ የሚያደርግ መሣሪያ፣ ድንገት ቁርስ ሠርተው ከረፈደብዎ ምድጃ ማጥፋት ረስተው ወደ ሥራ ቢሄዱ ከስልክዎ የሚያጠፉት ማብሰያና ከሌሎች የፈጠራ ሥራዎች በስተጀርባ አንድ ታዳጊ አለ ኢዘዲን ካሚል። ኢዘዲን ካሚል የ ዓመት ኢትዮጵያዊ ወጣት ሲሆን እስካሁን በአጠቃላይ የተለያዩ አገልግሎቶችን የሚሰጡ የፈጠራ ሥራዎችን ከ ዓመቱ ጀምሮ ሲሠራ ቆይቷል። ሃሳቦቹን ከየት አመጣቸው ለፈጠራስ እንዴት ተገፋፋ ወደፊትስ ምን የማድረግ ሕልም አለው ኢዘዲን ካሚል ኢዘዲን የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ ሲሆን ያደገው የወልቂጤ ክፍለ ከተማ በሆነችው ጉብሬ ውስጥ ነው። ወደ ቴክኖሎጂ ፊቱን ሲያዞር ገና የ ዓመት ታዳጊ የነበረ ቢሆንም ለፈጠራዎቹ ከተለያዩ ተቋማት ከሥራዎቹ በቁጥር የማይተናነሱ ሰርቲፊኬቶች ተሰጥተውታል። ያደገበት ከተማ ለቴክኖሎጂ ያላት ቅርበት እንደ አዲስ አበባ ስላልሆነ ለፈጠራ ሥራው የሚያስፈልጉት እንደ ላፕቶፕ፣ ኢንተርኔትና ሌሎች ቁሳቁሶችን እንደልብ አለማግኘቱ ኢዘድንን ተስፋ አላስቆረጠውም። ለዚህም በአካባቢው ከሚያገኛቸውም ሆነ አንዳንድ ጊዜ አዲስ አበባ ድረስ በመሄድ አገልግለው የተወገዱ ወይም የወዳደቁ ዕቃዎችን ከመርካቶ በትንሽ ዋጋ በመግዛት ያሰባቸውን አዳዲስ ፈጠራዎች እውን እንደሚያደርግ ይናገራል። ከፀሐይ ኃይል ማመንጨትንና ባደጉ ሃገራት ውስጥ ጥቅም ላይ የሚውሉ አጠቃላይ የቤት ውስጥ መገልገያ ቴክኖሎጂዎችን አስቦና አስተውሎ መሥራት ያልተሳነው ይህ ወጣት ማንም ሰው ምንም ነገር ለመፍጠር ሲያስብ ከችግር ተነስቶ ነው ሊፈጥር የሚችለው በማለት የሥራዎቹን መነሻ ምክንያት ይናገራል። አጭር የምስል መግለጫ በጫማዎ ስልክዎን ቻርጅ ማድረግ አስበው ያውቃሉ የኢዘዲን የፈጠራ ሥራዎች ብዙውን ጊዜ በቀን ሩጫ የተጠመደ ሰው ማለዳ ስልኩን ሙሉ በሙሉ ቻርጅ አድርጎ ቢወጣም አንዳንድ ጊዜ በቀኑ መጨረሻ ግን የስልኩ ባትሪ ሊያልቅ የሚችልባቸው አጋጣሚዎች አይጠፉም። አንዳንዴ ለአካባቢ ብክለት ታስቦም ይሁን ብዙ ገንዘብ የማያስወጣና የማያደክም የትራንስፖርት አማራጮችን የሚፈልጉም ሰዎች ከመካከላችን ላይጠፉ ይችላሉ። አልፎ አልፎ በችኮላ መካከል ጠዋት ተጥዶ የነበረውን ሻይም ሆነ መጥበሻ እዚያው ከማብሰያው ላይ ተረስቶ የሚወጡባቸውም ቀናት ሊያጋጥሙ ይችላሉ ወይንም የተረሳ ሻማ ቃጠሎ የሚፈጥርበት ጊዜስ ብለን ብናስብ ለእንደዚህ ዓይነት የዕለት ተዕለት ችግሮችና ከባድም ሆነ ቀላል ጉዳትን ሊያስከትሉ ለሚችሉ አደጋዎች መፍትሄ የሚሆኑ ዘዴዎችን ኢዘዲን ሠርቷል። የፀሐይን ኃይል በመጠቀም የእጅ ስልክ ቻርጅ የሚያደርግ ጫማ፣ ተቀምጠው ብቻ የፀሐይን ብርሃን በመጠቀም እንደ ሞተርሳይክል ያለ ፔዳል በእራሱ የሚሄድ ብስክሌት፣ ያልጠፉ የቤት መገልገያ ዕቃዎችን የሚያጠፋ እና የእሳት አደጋን የሚጠቁም መሣሪዎች ከሚጠቀሱት መካከል ናቸው። የኢዘዲን የፈጠራ ሥራዎቹ በአጠቃላይ ሲሆኑ ከአስደናቂዎቹ ናሙናዎች ፕሮቶታይፖች መካከል የተወሰኑት ከዚህ በታች ባለው ምስል ይታያሉ። ሌባ ያደገበትን ቤት ሲያንኳኳ ሰው ችግሩን ለመቅረፍ በማሰብ ነው ወደ ፈጠራ የሚሰማራው የሚለው ኢዘዲን አንድ ቀን የእጅ ስልኩን ቻርጅ እንዲያደርግ ቤቱ ትቶት ወደ ሌላ ቦታ ሄዶ ሲመለስ የጠበቀው ክስተት በጄሪካን ለሠራው ፈጠራ ጅማሬ መሆኑን ያስታውሳል። ስመለስ የጎረቤታችን ቤት በእሳት ጋይቶ ጠበቀኝ። መጀመሪያ ላይ ድንጋጤው እንድነቃነቅ አላደረገኝም ነበር። ከዚያ ግን ሰው ሁሉ ሲሯሯጥ እኔም እሳቱን ለማጥፋት ለማገዝ ሞከርኩ የሚለው ኢዘዲን ቻርጀር ላይ ተሰክቶ የነበረው ስልኩን አስታውሶ ለእሳት አደጋው ደራሽ ቢሆን የሚል ሃሳብ እንደሆነው ይነግረናል። ሃሳቡን ወደ ተግባር በመለወጥ ቤት ውስጥ የሚፈጠርን ጭስ በመለየት የእሳት አደጋ ምልክትን በአቅራቢያ ላሉ ሰዎች በድምፅ ይሰጣል። በዚህም በቅርብ ያሉ ሰዎች እርምጃ ካልወሰዱ በመሣሪያው ላይ በተገጠመ ስልክ አማካይነት መዝግቦ ለያዛቸው ሁለት ቁጥሮች ለምሳሌ ለቤቱ ባለቤት እና ለእሳት አደጋ መከላከያ በመደወል የእሳት አደጋ ጥሪ ያስተላልፋል።
ስለ አልጋዎ ማወቅ ያለብዎት ነጥቦች
በሀገራችን ከሰሜን እስከ ደቡብ ከምዕራብ እስከ ምስራቅ ብንጓዝና የአልጋ ዓይነቶችን ብንቃኝ የጠፍር፣ የሽቦ፣ ከገመድ የተሰራ፣ ከእንጨትና ከብረት የተሰሩ አልጋዎችን እናገኛለን። በአልጋ ዙሪያ ክፉ መንፈስን ለመከላከል የምናስቀምጣቸውም ነገሮች ቢሆኑም አይጠፉም። ይህ ግን የእኛ ታሪክ ብቻ አይመስልም። ዓለም ሁሉ ዶሴው ሲገለጥ ተመሳሳይ ታሪክ አለው።
ባለስምት ክፍል ቤት መኪናው ላይ የሰራው ኢትዮጵያዊባለስምት ክፍል ቤት መኪናው ላይ የሰራው ኢትዮጵያዊ
ባለስምት ክፍል ቤት መኪናው ላይ የሰራው ኢትዮጵያዊ
ሮቦቷ ሶፊያ ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጋር ተገናኘች
ጁላይ አጭር የምስል መግለጫ ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ከሮቦት ሶፊያ ጋር ሮቦቷ ሶፊያ ከጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ጋር ዛሬ በቤተመንግሥት ተገናኘች። ለጠቅላይ ሚኒስትሩም ኢትዮጵያ በመምጣቴ በጣም ደስ ብሎኛል፤ እኔ ኢትዮጵያን የምወድ ሮቦት ነኝ ብላቸዋለች። ከመጣች አራተኛ ቀኗን ያስቆጠረችው ሶፊያ በቆይታዋ በሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የተሰናዳው ዓለም አቀፍ አይ ሲቲ ኤክስፖ ላይ ተገኝታ ከታዳሚያን ጋር ተዋውቃለች። ባለስልጣናት፣ የጃዝ ሙዚቃ አባት ሙላቱ አስታጥቄን ጨምሮ የኪነጥበብ ባለሙያዎች በተገኙበት በቶቶት የባህል አዳራሽ የዳንስ ትርዒትም አቅርባለች። ምንም እንኳን በጀርመን በርሊን ኤክስፖ ቆይታዋ የተወሰነ የአካል ክፍሏን የያዘ ሻንጣ መጥፋት አማርኛ መናገር እንዳትችል የተፈታተናት ቢሆንም በትንሹም ቢሆን ተናግራለች። ከዚህ የበለጠ አማርኛ ስለምድ እናወራለን ስትል ተናግራለች። ንግግሯ ጠቅላይ ሚንስትሩን ፈገግ ያሰኘ ነበር ። በዛሬው ዕለትም በብሔራዊ ሙዚየም ተገኝታ ድንቅነሽን እንደጎበኘች የ አይኮግ ላብስ ስራ አስኪያጅ አቶ ጌትነት አሰፋ ለቢቢሲ ገልጿል። ተያያዥ ርዕሶች
ሶፊያ ከዐብይ አሕመድ ጋር የራት ቀጠሮ ይዛለች
ጁን ማጋሪያ ምረጥ ቅንድቦቿ ሲንቀሳቀሱ፣ የዓይን ሽፋሽፍቷ ሲርገበገብ፣ በቀለም የተዋበው ከንፈሯ ለንግግር ሲንቀሳቀስ፣ ጥርሶቿ ገለጥ ሲሉ በእርግጥ ይህች ሴት ሰው ሠራሽ ናት ያስብላል። ሶፊያ እምነት ታሳጣለች፤ ከራስ ጋር ታጣላለች። ጋዜጠኞች በእንግድነት ጋብዘዋታል፤ ዝናዋ በዓለም ናኝቷል፤ እንደሶፊያ ትኩረት የሳበ ሮቦት ገና አልተወለደም። አሜሪካዊውን ተዋናይ፣ የፊልም አዘጋጅ፣ ራፐርና የሙዚቃ ጸሐፊ ዊል ስሚዝን ጨምሮ ታዋቂ የፊልም ባለሙያዎች ከዚህ ቀደም ግብዣ አድርገውላት ነበር። ታዲያ በአንድ ወቅት ሶፊያና ዊል ስሚዝ ለሻይ ቡና ተገናኙና ድንገት ጨዋታውን አደሩት። እኔ የምልሽ ሶፊያ፣ ሮቦቶች የሚወዱት ሙዚቃ ምን ዓይነት ነው ሲል ዊል ጥያቄውን ሰነዘረ። ሶፊያም ትንሽ እንደማሰብ ብላ ሰዎች ለማሰብ ፋታ በሚወስዱት ልክ የኤሌክትሮኒክስ ሙዚቃዎች ይመቹኛል፤ ሂፕ ፖፕ ግን ምንም ግድ አይሰጠኝም ስትል ለዊል ጥያቄ ምላሸ ሰጠች። ዊል ስሚዝ በመልሷ ተደንቆ ሊሞት አይኮግ ላብስ የቴክኖሎጂ ድርጅት ኢትዮጵያዊው አይኮግ ላብስ ካምፓኒ ተቀማጭነቱን በሆንግ ኮንግ ከሚገኘው ሐንሰን ሮቦቲክ ጋር የሶፊያን ውስጣዊ ስሪት ለመቀመር ለሦስት ዓመታት ተፈራርሟል። በስምምነቱ መሠረት ኢትዮጵያውያኑ የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች በሶፊያ ላይ አሻራቸውን አሳርፈው እውን እንዳደረጓት የአይኮግ ላብስ መሥራችና ሥራ አስኪያጅ አቶ ጌትነት አሰፋ ይናገራል፡፡ ይህም በመሆኑ ሶፊያ ኢትዮጵያዊ ናት ልንል እንችላለን። አይኮግ ላብስ በቴክኖሎጂ ዘርፍ አስተዋጽኦ ለማበርከት ሰው ሠራሽ አስተውሎትንና ሰው ሠራሽ የአዕምሮ ስሪትን ለዓለም ለማስተዋወቅ ዓላማ አድርጎ ከአምስት ዓመታት በፊት የተመሠረተ ድርጅት ነው። ኢትዮጵያ በቴክኖሎጂው ዘርፍ ያላትን ችሎታ ለዓለም በማስተዋወቅ ወደፊት ታላላቅ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን ሠርተው ማሳየትንም ያልማሉ። በአሁኑ ሰዓት ይህ የቴክኖሎጂ ኩባንያ ጥናት አድራጊዎችን፣ ምልክት ተርጓሚዎችን ፣ የፕሮግራም ባለሙያዎችና በተግባር ልምምድ ላይ የሚገኙ ተማሪዎችን ጨምሮ ከ በላይ ሠራተኞች ይዞ እየሠራ ይገኛል። ሶፊያ ከሌሎች ሮቦቶች በምን ትለያለች ሶፊያ ሴት ሮቦት ናት ሲል ይጀምራል አቶ ጌትነት። እኛም ለመሆኑ ሶፊያን ሴት የሚል የጾታ መለያ ያሰጣት ምኗ ነው ስንል ፍካሪያዊ ጥያቄ ያነሳንለት ሥራ አስኪያጁ፣ ያው መልኳና የፊቷ ቅርጽ የሴት ነው በማለት በሳቅ የታጀበ መልስ ሰጥቶናል። ጥሬ ዕቃውን በቀላሉ ባለማግኘታቸው ውጫዊ አካሏን በመገንባት ያላቸው ተሳትፎ አናሳ ቢሆንም፤ በአስተሳሰቧ፣ በአረዳዷ፣ በስሜት አገላለጿ፣ በቋንቋ አጠቃቀሟ ላይ ረቂቅ የሆነና ብዙዎችን ያስደመመ ማንነትን አጎናጽፏታል። ሶፊያ በስሜት አገላለጽ፣ አካባቢን በመረዳት፣ የሰዎችን ገጽታ በአንክሮ በማየትና የሚያንጸባርቁትን ስሜት በቅጽበት በመረዳት ተገቢ ምላሽ የሚያሰጥ ውስጣዊ ሥሪት ስላላት እስከዛሬ ከተሠሩት ሮቦቶች ለየት ያደርጋታል። ምናልባት ይህ የሶፊያ ውስጣዊ ውበት ተብሎ ሊገለጽ ይችላል። ደግሞም አስተዋይ ሴት ናት። በተለያዩ አገራት፤ በተለያየ ባህል ውስጥ የሚኖሩ ሰዎችን ስሜት በማጤን፤ የሰዎችን ውስጣዊ የስሜት ነጸብራቅ የጓደኛ ያክል የምትረዳ ናት። ሳቅን፣ ቁጣን፣ ኩርፊያን፣ ደስታን፣ ሐዘንን ወዘተ ከፊት ገጽታ ከመረዳት አልፎ በንግግር ውስጥ ያሉ ድምጸቶችን መለየት ትችላለች። ከሰዎች ጋር መነጋገር የሚያስችላትን የተለያዩ ቋንቋዎችን እንድትናገር ኾናም ነው የተሠራችው። ምናልባት ሶፊያ የትዳር አጋር ቢኖራት እንደ ሶፊ የምትረዳኝ ሴት የለችም ብሎ ሊመሰክርላት በቻለ። የሶፊን ውስጣዊ ባሕሪ ከማየት ወደፊት የሰመረ ትዳር እንደሚኖራት መጠርጠር አይችልም። የተለያዩ ቋንቋዎችን እንዲያናግራት የሚስችላትን ውስጣዊ ሥሪት በመሥራት ከታሳተፉ ኢትዮጵያውያን የቴክኖሎጅ ባለሙያዎች አንዱ የሆነውና በድርጅቱ ውስጥ የሙሉ ጊዜ ሠራተኛ ኾኖ የሚሠራው ደረጀ ታደሰ ሶፍያ በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ ስትመጣ በአማርኛ ቋንቋ ቃለመጠይቅ ይደረግላታል ብሏል። በርግጥ የተለያዩ ቋንቋዎችን እንድትናገር ማድረግ ይቻላል፤ በዚሁ መሠረት የአማርኛ ቋንቋ እንድትናገር የሚያስችላት ቴክኖሎጂ እየተዘጋጀላት ነው ሲል ይገልጻል። ከአፏ የሚወጣው የመጀመሪያ የአማርኛ ንግግሯም እንኳን ደህና ቆያችሁኝ ሊሆን እንደሚችል ይገምታል። ሶፊያ መቼ ትመጣለች አርብ ጠዋት ሰኔ ቀን ዓ ም አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ የአውሮፕላን ማረፊያ ደማቅ አቀባበል ይጠብቃታል። ከፍተኛ ባለሥልጣናትም ለክብሯ ሲሉ ይገኛሉ። ከነዚህ መካከልም የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚንስትር ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ፣ የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚንስትሯ ወ ሮ ሁባ መሐመድ እና የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ አንዷለም አድማሴ ይገኙበታል። ከዚያም ጉዞ ወደ ብሔራዊ ሙዚየም ይሆናል። ከሉሲ እስከ ሶፊያ በሚል ርዕስ እሷው በተገኘችበት ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣል። ጋዜጣዊ መግለጫው በኢትዮጵያ ብሔራዊ ሙዚየም ለመስጠት የታቀደበት ምክንያት ምንድን ነው ስንል የጠየቅነው የድርጅቱ መሥራችና ሥራ አስኪያጅ፤ ኢትዮጵያ የሰው ዘር መገኛ እንደመሆኗ የአስተውሎት ምንጭ እንደሆነች ለማሳየት ታስቦ እንደሆነ ገልጾልናል። ሰኔ ቀን ዓ ም ሳይንስና ቴክኖሎጂ በየዓመቱ በሚያዘጋጀውና በጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ በተገኙበት ይከፈታል በተባለው የዘንድሮው ዓለም አቀፍ ኤክስፖ ላይ ሶፊያ በክብር ትገኛለች። በዝግጅቱ ላይ ታዳሚ የሆኑና ከተለያዩ ክልሎች የተውጣጡ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ጋር እንደምትተዋወቅም ገልፆልናል። የዚያን ዕለት ምሽት ታዲያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ በሚያደርጉላት የራት ግብዣ ላይ ትገኛለች ተብሎ ይጠበቃል። የታቀደው ከተሳካ ከጠቅላይ ሚንስትሩ ጋር በምን ርዕሰ ጉዳይ ላይ ይነጋገሩ ይሆን የምታስፈታው ታሳሪስ ይኖር ይኾን በዕቅድ ደረጃ በተያዘው መርሐ ግብር መሠረት ሶፊያ በአዲስ አበባ የአራት ቀናት ቆይታ ይኖራታል። በየትኛው የእንግዳ ማረፊያ፣ በባለ ስንት ኮከብ ሆቴል ውስጥ፣ በምን ሁኔታ እንደምታርፍ ግን ለጊዜው ይፋ አልተደረገም። መሳፈሪያዋ ስንት ነው ከዚህ ቀደም ወደ ግብጽ ጎራ ብላ የነበረችው ሶፊያ ለቆይታዋ ሐምሳ ሺህ ዶላር እንደወጣባት የተናገረው አቶ ጌትነት በሶፊያ አፈጣጠር ላይ ኢትዮጵያውያኖቹ ጉልህ ተሳትፎ በማድረጋቸው በባለቤትነት ከያዛት ሀንሰን ሮቦቲክስ ለኢትዮጵያ ጉዞዋ ቅናሽ እንደሚደረግላቸው ተስፋ እንዳለው አጫውቶናል፡፡ በመሆኑም ከሐምሳ ሺህ የአሜሪካ ዶላር ያነሰ ይወጣባታል ተብሏል። ኾኖም እስካሁን ወጪዋን የሚሸፍነው አካል ማን እንደሆነ ይፋ አልተደረገም። ኢትዮጵያዊ ስም ለሶፊያ በሳዑዲ አረቢያው ጉብኝቷ ሶፊያ የሚል ስያሜ ያገኘችው ይህች ሮቦት የሳዑዲ አረቢያ ዜግነትም ተሰጥቷታል። የኢትዮጵያን አፈር ስትረግጥም ኢትዮጵያዊ ስም ይወጣላታል። ጣይቱ እና ሉሲ የሚሉ ስሞች ለጊዜው በዕጩነት የተዘጋጁላት ሲሆን የእቴጌ ጣይቱን ስም ትወርሳለች ተብሎ ተስፋ ተጥሏል። ሉሲ የሚለው መጠሪያ ድንቅነሽን ካገኙት ተመራማሪ ስም የተወረሰ በመሆኑ ኢትዮጵያዊ ቀለም የለውም ሲል የገለጸው ሥራ አስኪያጁ ድንቅነሽ የሚለውን ስም እንደ አማራጭ እንዳቀረቡትም ነግረውናል። ኢትዮጵያዊ የክብር ዜግነት እንድታገኝም ጥያቄ ለማቅረብ እንደታሰበ ሥራ አስኪያጁ ጨምሮ ገልጿል። ተያያዥ ርዕሶች
ናሳ፡ ከአውስትራሊያ ሰደድ እሣት የመነጨው ጭስ ዓለምን ይዞራል
ጃንዩወሪ ማጋሪያ ምረጥ የአሜሪካው የጠፈር ሳይንስ ተቋም ናሳ ከአውስትራሊያ ሰደድ እሣት የተነሳው ጭስ ዓለምን ዞሮ ወደ መጣበት ይመለሳል ሲል ተንብየዋል። የአውስትራሊያ ምስራቃዊ ክፍልን ለወራት ሲያቃጥል የነበረው ሰደድ እሣት ጭስ የፓሲፊክ ውቅያኖስ ጣሪያ ላይ ተንሳፎ ይገኛል። ናሳ እንደሚለው በአው ጳውያኑ አዲስ ዓመት መጀመሪያ ቀን ከአውስትራሊያ የተነሳው ጭስ የደቡብ አሜሪካ ሰማይ ላይ ታይቷል፤ በሳምንቱ ደግሞ የዓለምን ግማሽ ተንሸራሽሯል። ጭሱ ዓለምን ቢያንስ አንድ ጊዜ ሊዞራት እንደሚችል ናሳ አሳውቋል። የአውስትራሊያ ሰደድ እሣት ከ ሚሊዮን ሄክታር በላይ መሬት ያቃጠለ ሲሆን ሰዎችን ገድሏል፤ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የዱር እንሳስትም ሰለባ ሆነዋል። ሺህ ገደማ መኖሪያ ቤቶች ደግሞ ዶጋ አመድ ሆነዋል። የዘርፉ ባለሙያዎች የአውስትራሊያ ሰደድ እሣት የዓለም አየር ንብረት ለውጥ ማሳያ ነው ይላሉ። ናሳ የሰደድ እሣቱ ጭስ በጣም ከፍተኛ ከመሆኑ የተነሳ ከእሣት የሚፈጠር መብረቅ መሥራት ችሏል ይላል። ጭስ በጣም ኃያል ከመሆኑ የተነሳ ከመሬት ወደ ሰማይ ኪሎ ሜትር ርቀት ድረስ ተጉዞ ስትራቶስፌር የተሰኘው የሰማይ ክፍል ላይ መስፈር ችሏል። ተቋሙ፤ ጭሱ ወደ ሰማይ ከተመዝገዘገ በኋላ ሙቀት ወይስ ቅዝቃዜ ፈጠረ የሚለውን ለማወቅ ጥናት ላይ መሆኑንም አሳውቋል። እውን አውስትራሊያ እንዲህ እየተቃጠለች ነው የደቡብ አሜሪካ ሃገራትና የአህጉረ አውስትራሊያ አካል የሆነችው ኒው ዚላንድ በአውስትራሊያ ሰደድ እሣት ምክንያት ሰማያቸው ታፍኖ እንደነበር የሚያሳዩ ፎቶዎች እና ተንቀሳቃሽ ምስሎች የማሕበራዊ ድር አምባ ተጠቃሚያዎች አጋርተዋል። ኒው ዚላንድን ጨምሮ ሲድኒ፣ ሜልቦርን፣ ካንቤራ እና አደላይድን የመሳሰሉ ትላልቅ የአውስትራሊያ ከተሞች በሰደድ እሣቱ ምክንያት ንፁህ አየር መተንፈስ ተስኗቸው ሰንብተዋል። አውስትራሊያ አሁንም እየተቃጠለች ነው። ገደማ ጫካዎች አሁን እሣት ይዟቸዋል። ነገር ግን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየጣለ ያለው ዝናብ ሁኔታዎችን ቀዝቀዝ አድርጓቸዋል። ጭሱ ግን መጓዙን እንደሚቀጥል ናሳ አሳውቋል። አፍሪቃን ጨምሮ ሁሉንም የዓለማችን አህጉሮች ሊነካ ይችላልም ተብሏል። የአውስትራሊያን ጭስ በኢትዮጵያ ሰማይ ላይ እናየው ይሆን
የአውስትራሊያ እሳት፡ በሺዎች የሚቆጠሩት እሳት ሽሽት ወደ ውሃ ዳርቻዎች ተሰደዱ
ዲሴምበር በአውስትራሊያ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የተነሳውን የሰደድ እሳት ለማምለጥ ወደ ባህር ዳርቻዎች ተሰደዋል። እሳቱ ወደ የቪክቶሪያ ባህር ዳርቻ ከተማ ወደ ሆነችው ማላኮታ የተዛመተ ሲሆን ፤ ወደ መኖሪያ ቤቶችም እየገሰገሰ ነው። የአካባቢው ነዋሪዎች፤ ደም በለበሰው ሰማይ ሥር በውሃ ዳርቻዎች ላይ መጠለልና ጀልባዎች ላይ ተሳፍሮ መቆየት በጣም ፈታኝ ነው ሲሉ ያሉበትን ሁኔታ ገልፀውታል። በደቡብ ዌልስ ሌላ ሁለት ሰዎች መሞታቸውንም ባለሥልጣናት አረጋግጠዋል። እስካሁን በአገሪቷ ከተከሰተው ሰደድ እሳት ጋር ተያይዞ ሰዎች ሕይወታቸው አልፏል። በሲድኒና ሜልቦርን መካከል በርካታ በዓል ወደ ሚከበርባቸው ቦታዎች የሚወስዱ መንገዶች በእሳት አደጋው ምክንያት ተቋርጠዋል። በሁለት አውስትራሊያ ግዛቶች፤ ከደቡብ ዌልስ ባቴማስ ቤይ፤ ወደ ቪክቶሪያ ቤርንስዳሌ በ ኪሎ ሜትር በአደገኛ ሁኔታ እየተስፋፋ ነው። የአባት እና ልጅ እንደሆነ የተነገረ የሁለት ሰዎች አስክሬን በኒው ደቡባዊ ዌልስ ኮባርጎ ከተማም ተገኝቷል። የደቡብ ዌልስ ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር ጋሪይ ወርቦይስ በጣም አሳዛኝ አጋጣሚ ነው፤ እሳቱ ወደ እነርሱ ከመዛመቱ በፊት ግለሰቦቹ የሚቻላቸውን አድርገዋል ብለዋል። ባለሥልጣናት እንዳሉት በአካባቢው ሌሎች አምስት ሰዎች የደረሱበት አልታወቀም። ከእነዚህ መካከል አራቱ ከቪክቶሪያ፤ ሌላው ደግሞ ከኒው ደቡባዊ ዌልስ ነው። የቪክቶሪያ ግዛት አስተዳዳሪ ዳንኤል አንድሪውስ እንዳሉት በአካባቢው ዋና አውራ ጎዳና በመዘጋቱ፤ አገልግሎት ለተቋረጠባቸው አካባቢዎች ምግብ፣ ውሃ እና ኃይል ለማድረስ መርከብ ሊጠቀሙ እንደሚችሉ አስታውቀዋል። እነዚህ ተነጥለው ያሉ ማህበረሰቦች የባህር ኃይልን በመጠቀም መድረስ ይቻላል ሲሉም አክለዋል። ባለሥልጣናት በአብዛኛው ጎብኝዎች የሆኑና በአካባቢው ያሉ ሰዎች አሁን አካባቢውን ለቆ ለመውጣት ስለረፈደና አደገኛ ስለሚሆን ባሉበት እንዲቆዩ አሳስበዋል። እነዚህ ማህበረሰቦች በሚኖሩበት ሰሜናዊ ግዛት፤ እሳቱ በአካባቢው ባለው ሙቀት ፣ ንፋስና ደረቅ መብረቅ የአየር ጠባይ ሳቢያ እየተስፋፋ መሆኑም ተነግሯል። ተያያዥ ርዕሶች
የዓለማችን ዋነኛ ሃብታም ለአየር ንብረት ለውጥ ቢሊየን ዶላር እሰጣለሁ አለ
ፌብሩወሪ ማጋሪያ ምረጥ የአማዞን ባለቤትና የበላይ ኃላፊ ጄፍ ቤዞስ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቆጣጠር የሚደረገውን ትግል ለማገዝ ቢሊየን ዶላር ለመስጠት ቃል ገባ። እንደ ግለሰቡ አስተያየት ከሆነ ገንዘቡ የአየር ንብረት ለውጥን ለመግታት ምርምር የሚያደርጉ ሳይንቲስቶችን ስራ ለማገዝ፣ የመብት ተሟጋቾችን እንዲሁም ሌሎች ቡድኖችን ለመደገፍ ይውላል። አክለውም የአየር ንብረት ለውጥ አስከፊ ተጽዕኖ ለመዋጋት የሚታወቁ መንገዶችን ለማጠናከርና አዳዲስ መንገዶችን ለመፈለግ በትብብር መስራት እፈልጋለሁ ብሏል። ጄፍ በኢንስታግራም ገፁ ላይ እንዳሰፈረው፣ ገንዘቡ በመጪው የክረምት ወር መከፋፈል ይጀምራል። ሚስተር ቤዞስ አጠቃላይ ሀብቱ ቢሊየን ዶላር የሚገመት ሲሆን ቃል የገባው የሀብቱን በመቶ ብቻ መሆኑ ታውቋል። አንዳንድ የአማዞን ሠራተኞች አለቃቸው የአየር ንብረት ለውጥን ለመዋጋት የበለጠ እንዲሰጥ ሲወተውቱ ነበር። አንዳንዶቹም በይፋ አደባባይ ወጥተው ይህንን አቋማቸውን የተናገሩ ሲሆን፣ አንዳንዶች ደግሞ ድርጅቱን ጥለው ወጥተው ነበር። ከዚህ ቀደም ሚስተር ጄፍ ቤዞስ ብሉ ኦሪጅን የተባለ የጠፈር ምርምር ፕሮግራምን በገንዘብ ቢደግፍም ለአየር ንብረት ለውጥ ሲባል እጅ ያጥረዋል ተብሎ ይተች ነበር። ከሌሎች የናጠጡ ሃብታሞች አንጻር ሲታይ ጄፍ ቤዞስ፣ በበጎ አድራጎት ተግባራት ላይ እምብዛም የማይሳተፍ ሲሆን ከዚህ የድጋፍ ተግባሩ በፊት ትልቅ ለልግስና ያወጣው ገንዘብ በ ለቤት አልባዎችና ትምህርት ቤቶችን በሚል የሰጠው ቢሊየን ዶላር ብቻ ነው። ከዚህ በፊት ቢሊየነሮች በሕይወት ዘመናቸው ያካበቱትን ሀብት ግማሹን ለበጎ ተግባራት እንዲውል ለመስጠት ተስማምተው ሲፈርሙ፣ እርሱ ባለመፈረሙ ምክንያት ስሙ ሲብጠለጠል ነበር። መቀመጫውን ሲያትል ያደረገው አማዞን ከማይክሮሶፍት ጋር የሚጎራበት ሲሆን በ ከካርቦን የፀዳ ተቋም ለመሆን ያለውን እቅድም ይፋ አድርጓል። ተያያዥ ርዕሶች
ይህ የአፍሪካ ዋነኛው የፈጠራ አካባቢ ይሆን
ጁላይ አጭር የምስል መግለጫ በርናርድ ኪዊያ የታንዛንያው የፈጠራ ትምህርት ቤት ትዌንዴ መስራች ነው በርናንድ ኪዊያ ከብስክሌት እጅግ ብዙ ነገር መስራት ይችላል። መጀመሪያ የታወቀው በብስክሌት የሚሰራ የተንቀሳቃሽ ስልክ ባትሪ መሙያ ቻርጀር በመፍጠር ነው። በርናንድ ከብስክሌት መለዋወጫ እቃዎች በርካታ ተጨማሪ ነገሮችን መስራት እንደሚችል በኋላ ላይ ቢገነዘብም ሥራ የጀመረው የብስክሌት መካኒክ ሆኖ ነው። አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን የምፈጥረው ቤተሰቤን እና ማህበረሰቡን የሚጠቅም ነገር መሆኑን ስለምገነዘብ ነው ይላል በርናንድ፡፡ ነገር ግን ብስክሌቶች ብቻ አይደለም። የወባ መድሃኒት ጥቅም ላይ ሊውል ነው የእርሱ የፈጠራ ውጤት የሆነውና በንፋስ ኃይል የሚሰራው የልብስ ማጠቢያ ማሽን የቤተሰቡን አልባሳት ንፋስ በሚበረታበት ጊዜ በአንዴ ስለሚያጥብላቸው ልፋትና ጊዜያቸውን ቆጥቦላቸዋል። የበርናንድ ፈጠራ አሁን ከራሱ ቤትና ጓሮ አልፎ ለማህበረሰቡ ተዳርሷል። ትዌንዴ የተባለውን እና እርሱ የጀመረውን የፈጠራ ሰርቶ ማሳያ እና ከዚያ በላይ የሚሆኑ የአካባቢው የፈጠራ ሰዎች ተጠቅመውበታል። በታንዛንያ የገጠር የፈጠራ ውጤት አባት እየተባለም ይጠራል። ለሰዎች ማሳየት የፈለገነው ሁሉም ተመጣጣኝ በሆነ ዋጋ ራሳቸው ሊጠግኑት የሚችሉት እና የሚፈልጉትን መለዋወጫ ሊያገኙለት የሚችል የራሳቸውን ቴክኖሎጂ ለመፍጠር ክህሎቱ እንዳላቸው ነው ይላል ብርናንድ። የሀገሬው ሰዎች ሁሌም ገቢያቸው ትንሽ ሲሆን በየሱቆቹ የሚሸጡት መሳሪያዎች ደግሞ ውድ በመሆናቸው ለእነዚህ ሰዎች አይሆኑም። ለዚያም ነው በአካባቢዬ በማገኛቸው ነገሮች ላይ ያተኮርኩት። አጭር የምስል መግለጫ ፍራንክ ሞሌል ማዳበሪያ ከሚያሰራጭበት ጋሪ ጋር ማዳበሪያን በአግባቡ ለመጠቀም የሚያስችል ፈጠራ ፈራንክ ሞሌል ከአካባቢው የፈጠራ ሰዎች አንዱ ሲሆን ማዳበሪያ እና ከከብቶች የሚወጣን ፍግ በእጅ ለመበተን የሚወስደውን ጊዜ ለማሳጠር የሚረዳውን የተሻሻለ ጋሪ ፈርት ካርት ን ፈጥሯል። የፍራንክ የፈጠራ ሃሳብ ተሻሽሎ የተሰራውን ጋሪ ለመግዛት በቂ መሬት እና ገቢ ለሌላቸው አርሶ አደሮች ማከራየትን ይጨምራል። ትዌንዴ በሰርቶ ማሳያቸው ውስጥ ያሉ ሁሉ ጥሩ የንግድ ልምዶችን መቅሰማቸውን እና የንግድ እቅድ ማዘጋጀታቸውን ያረጋግጣል። ከደንበኛቹ መካከል አንዱ ይህን መሳሪያ መጠቀሙ ለልጆቹ የትምህርት ቤት የመክፈል አቅምን እንደፈጠረለት ይናገራል። ተሻሽሎ የተሰራው ጋሪ ፈርት ካርት በእርሻ ተግባራት የሚጠፋውን በቢሊዮን የሚቆጠር ሰዓት ቀንሶታል ይላል ፍራንክ። አፍሪካ በተለይ ደግሞ በታንዛኒያ አርሶ አደሮች ምርታማነታቸው እንዲጨምር እና አነስተኛ እርሻ ያላቸው ገበሬዎች ገቢያቸው እንዲያድግ የሚረዳቸውን ይህን ድንቅ ቴክኖሎጂ ትፈልገዋለች። አጭር የምስል መግለጫ የጄሲ ኦሊጃንጌ የአቮካዶ ዘይት መጭመቂያ በትዌንዴ ሰርቶ ማሳያ ለስድስተኛ ጊዜ እየተሰራ ነው አረንጓዴ ወርቅ የጄሲ ኦሊጃንጌ አቦካዶ መጭመቂያ የማበረሰቡን ህይወት እየቀየረው ነው። ትዌንዴ እራሱ ማህበራዊ የፈጠራ ግኝት ነው ይላል ጄሲ። በአንድ ክፍል ውስጥ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን የሚሰሩ ሰዎች አሉ። እናም ችግር ቢገጥምህ ከመካከላቸው አንዱን በመጠየቅ መፍትሄውን ታገኛለህ። አርሶ አደሮቹ በገበያው ላይ የተሻለ ዋጋ ስለማያገኙ ዘይቱ ከመጨመቁ በፊት አቦካዶዎች በረገፉበት ቦታ ይበሰብሱ ነበር። አሁን በአካባቢው ማህበረሰብ ውስጥ ያሉ ሴቶች አቦካዶውን የሚሸጡትን ዘይት ለማውጣት ይጠቀሙበታል፡፡ ጄሲ እንደሚለው ትዌንዴ ውስጥ መሳተፉ ሰርቶ ማሳያውን እንደ እናት ድርጅት በመጠቀም የገንዘብ ድጋፍ ለመጠየቅም አስችሎታል። የገንዘብ ድጋፍ እና የመንቀሳቀሻ ገንዘብ ማግኘት እንደ ጄሲ ላሉ የአካባቢው የፈጠራ ሰዎች ሁለቱ ተግዳሮቶች ናቸው። በአብዛኛዎቹ በርናርድን የመሳሰሉ የሚያግዟቸው አማካሪዎች አሏቸው። ችግር ካጋጠመህ ጭንቅላትህ ሊዞር አይገባም ለበርናርድ ትነግረዋለህ። ለሁለት ደቂቃዎች ያህል አስቦ በዚህ መንገድ ሥራው ይልሃል። እኛም ብዙ የምናማክረው አለን ይላል ጄሲ። አጭር የምስል መግለጫ የማግሬት ኦማሬ የሳሙና መቁረጫ ግኝት የብዙዎችን ሰዎች እጣ ፈንታ ቀይሮታል የሳሙና እገዛ የማገሬት ህይወት ትዌንዴ ሰርቶ ማሳያ ውስጥ በፈጠረችው የሳሙና መቁረጫ ማሽን ምክንያት ተቀይሯል። የእራሷን የሳሙና ንግድ እንድትጀመር ከማስቻሉም ባሻገር ማሽኗን በከተማው ውስጥ ላሉ ባሎቻቸው ለሞቱባቸው ሴቶች በማጋራት ገቢ እንዲያገኙ ታደርጋለች። ልጆቼ ከዚህ በኋላ በክፍያ እጦት ምክንያት ከትምህርት ቤት ስለማይባረሩ ደስተኛ ነኝ ትላለች። ቀላል የፈጠራ ውጤት የብዙዎችን ህይወት እንዴት ሊቀየር እንደሚችል አስረጂ ነው። አጭር የምስል መግለጫ በርናርድ ኪዊያ በአካባቢው የሚገኙ ትምህርትቤቶችን በማዳረስ አዲስ የፈጠራ ትውልድ ለማፍራት ተስፋ ያደርጋል ምን ትምህርት ተቀሰሙ የወደፊት ህልሜ ታንዛንያዊያን በዘወትር እንቅስቃሴዎቻችን የምንጠቀምባቸው የራሳችን ምርቶች ኖረውን ማየት ነው ይላል በርናርድ። ይህ እንዲሆንም በአካባቢው ከሚገኙ ትምህርትቤቶች ልጆችን ወደ ትዌንዴ በመጋበዝ ለምርጥ የፈጠራ ውጤቶች እንዲበረታቱ ያደርጋል። ሰርቶ ማሳያው ልጆቹ መስሪያ እቃዎችን ይዘውም ሆነ ለስልጠና ወደ ገጠራማ መንደሮች የሚሄዱበት አነስተኛ መኪና አለው። ትዌንዴ ውስጥ ለማህበረሰቡ የሚጠቅሙ የፈጠራ ሥራዎች እንሰራለን። በመሆኑም ማህበረሰቡን የሚፈታተኑ ተግዳሮቶችን በማየት እሱኑ ለመወጣት ጥረት በማድረግ ችግሩን እንፈታለን ይላል ተማሪው ላይትነስ ሲምኦን ኪኒሳ። ብየዳን ለመሳሰሉ ትምህርቶች እንደሚያደርገው የተግባር ልምምድ ሁሉ በትዌንዴ ትምህርት ቤት አነስተኛ ንግድን እንዴት ማስኬድ እንደሚቻል እና የበጀት ዝግጅትን የተመለከቱ ሰርቶ ማሳያዎችም አሉ። በርናርድ ኪዊያ በጣም የተለየ ሰው ነው ይላል ከታንዛኒያዊን የፈጠራ ሰዎች እና ቴክኖሎጂ አመንጪዎች ማህበር የመጣው ኢሳ ካንጉኒ። እሱ እንደሚለው በአፍሪካ ወይም በታንዛኒያ የፈጠራ ሰው መሆን በጣም ከባድ ነው። ምክንያቱም የፈጠራ ሀሳብ ያላቸው ሰዎች የሚተገብሩበት ሀብት የላቸውም። በርናንድ ኪዊያ በትዌንዴ ሀብትን በመጋራት ማህበረሰቡ ለራሱም ሆነ ከእነሱ ውጪ ላለው ዓለም መፍትሄ የሚሆን አዳዲስ የፈጠራ ሀሳብ ማመንጨቱን እንዲቀጥል ለማነቃቃት ተስፋ ያደርጋል። አንዳንድ ጊዜ ላይሳካልህ ይችላል፤ ስለዚህ እንደገና ትሰራዋለህ ይላል በርናርድ። አንዳንድ ጊዜ በድጋሚም ላይሳካልህ ይችላል፤ አሁንም እንደገና ትሰራዋለህ። ነገር ግን በመጨረሻ ጥሩ ነገር ላይ ትደርሳለህ። ተያያዥ ርዕሶች
ሥራ ፈጣሪው የጋናን የወደፊት የፈጠራ ሰዎች ትውልድ እየፈጠረ ነው
ሴፕቴምበር ማጋሪያ ምረጥ አጭር የምስል መግለጫ ለትንሻ ቦርሳ ምስጋና ይግባትና በመላው ጋና የሚገኙ ልጆች የሳይንስ ህልማቸውን መቀጠል ችለዋል እኔ እኔ እኔ ከ የሚበልጡ ልጆች በአረንጓዴ ሸለቆ ጥግ ከሚገኘው ክፍላቸው ትናንሽ የእንጨት ወንበሮቻቸው እየዘለሉ በደስታ ይጮሃሉ። ውድድሩ ከጋና ዋና ከተማ አክራ ወጣ ብሎ በሚገኘው በረኩሶ መካከለኛ ሁለተኛ ደረጃ ት ቤት ሲሆን ውድድሩም ሽቦዎችን እና ትራንዚስተሮችን በማገናኘት ማን ትንሽዬ የቃጭል ድምጽ የምታሰማ መሳሪያ እንደሚሰራ ማየት ነው፡፡ በሰከንዶች ውስጥ ክፍሉ በብዙ ባለከፍተኛ የቃጭል መሰል ድምጾች ተሞላ። ልጆቹ በደስታ አበዱ። ማን እንዳሸነፈ ለመናገር አልተቻለም። የዛሬ ዓመት እነዚህ ታዳጊዎች ኤሌክትሮኒክስን እየተማሩ የነበሩት በጥቁር ሰሌዳ፣ በጠመኔ እና በጥቂት መጽሃፍት ነበር። አሁን መንገዳቸውን ለማቃናት የሚፈልጓቸው ነገሮች ሁሉ ከፊት ለፊታቸው አሉላቸው። የመማሪያ መጽሃፍት ፈጠራ የ ዓመቱ ቻርለስ ኦፎሪ አንቲፐም ከዚህ ሁሉ ጀርባ አለ። የመማሪያ መጽሃፍ ዋጋ ዶላር እና መጠን ያላት በኤሌክትሪክ መሳሪያዎች የተሞላች ትንሽ ጥቁር ሳጥን እውን አደረገ። ቦርሳዎችን በተማሪዎች ወንበር ላይ በማስቀመጥ የመጀመሪያውን የኤሌክትሪክ መስመር ሲገነቡ በተማሪዎቹ አይን ላይ የሚፈነጥቀውን ብርሃን ማየት መቻል፤ ያ ነው እርምጃችንን እንድንቀጥል የሚረዳን ይላል። ቻርለስ፤ ዴክስት ቴክኖሎጂ የተሰኘውን ኩባንያውን የመሰረተው ከ ወራት በፊት ነው። አሁን ዘጠኝ ሰራተኞች አሉት እስካሁንም ከ ሺህ በላይ ቦርሳዎችን በመላው ጋና ለሚገኙ የመንግሥት እና የግል ት ቤቶች ሽጧል። ሀሳቡን የጠነሰሰው አንድ ቤት ከሚጋራው ሚካኤል አሳንቴ አፍሪፋ ጋር በዩኒቨርስቲ የመኝታ ክፍላቸው ውስጥ ነው። በቀጣዮቹ ሁለት ዓመታት ጋና ውስጥ ያለ እያንዳንዱ ልጅ አንድ ቦርሳ እንዲኖረው ይፈልጋሉ። አጭር የምስል መግለጫ ቻርለስ ኦፎሪ አንቲፐም የሳይንስ ቦርሳውን በመላው አፍሪካ ለሚገኙ ልጆች የማጋራት ህልም አለው መጽሃፍ ውስጥ ያለን እውቀት መቅሰም አንድ ነገር ነው፤ ነገር ግን ዋናው ጠቃሚ ነገር በሙከራ መለማመድ መቻል ነው ይላል። ከ ጀምሮ ያሉት አስርት ዓመታት ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ምህንድስናና ሒሳብ የመሳሰሉትን መስፈርቶች ወደሚጠይቁ ሥራዎች እንደገና የሚዋቀሩባቸው ዓመታት እንደሚሆኑ ይጠበቃል። ምን ያህሎቹ የዓለማችን ሥዎራች እነዚህን አዳዲስ ክህሎቶች ወደሚጠይቁ መስፈርቶች እንደሚሸጋገሩ በትክክል ማንም አያውቅም። ወደ በመቶው አካባቢ እንደሚሆኑ ግን ግምቶች ተቀምጠዋል። ነገር ግን ከሰሃራ በታች ባለው ክልል ያሉ የአፍሪካ ሀገራት በሳይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በምህንድስናና ሒሳብ ትምህርት እና ስልጠና ላይ የሚያፈሱት መዋዕለ ነዋይ በእጅጉ ወደኋላ የቀረ ነው። የተባበሩት መንግሥታት እንደሚገልጸው አንድ እራሱን የቻለ ክልል የንጹህ መጠጥ ውሃ ማዳረስ እና ንጽህና ማሻሻልን የተመለከተውን የዘላቂ ልማት ግብ ለማሳካት ብቻ በርካታ መሃንዲሶችን ይፈልጋል። የጋና ሳይንስ ማህበር አባል የሆኑት ዶክትር ቶማስ ታጎኢ እንደሚሉት ሀገሪቱ በቂ መሃንዲሶች እና የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ባለሙያዎች ስለሌሏት በልጆች ላይ የሳይንስ ፍቅር እንዲያድረባቸው ይህ ፈጠራ በራሱ ጠቃሚ ነው። ይህ የዲጅታል ዘመን ነው። እናም ይህንን አጋጣሚ ሊጠቀሙበት የሚችሉ ሰዎችን እንፈልጋለን ይላሉ። በዚህም ከታዳጊ ሃገሮች ወጥተን በሳይንስ ሙያተኞች የምንታወቅ ልንሆን እንችላለን። የሳይንስ መሪነት ቻርለስ ያደገው ሳይንስ ትልቅ ቦታን በያዘበት ቤት ውስጥ ነው። ከጥቂት ዓመታት በፊት ህይወታቸው ያለፈው አባቱ በአካባቢው በሚገኝ ት ቤት ሳይንስ ያስተምሩ ነበር። ሁሌጊዜም ማንኛውንም ያገኘነውን እውቀት እንድንቀስም ይፈልግ ነበር። በተለይ ከሳይንስ ጋር የተገናኙ ነገሮች። ነገር ግን ቻርለስ ት ቤት እያለ በይነ መረብም ሆነ መሰረታዊ የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ቁሳቁስ ማግኘት አይችልም ነበር። የገደቡኝ በእጄ ላይ የነበሩት መገልገያዎች ናቸው። ይላል ለዛሬዎቹ ተማሪ ልጆች ይህንን መቀየር እንደሚፈልግ በማከል። ሥራዬ በቻልኩት አቅም እኔ በአባቴም ከተደረገልኝ በላይ ቀጣዩን ትውልድ አቅም ማጠናከር መሆን እንዳለበት ይሰማኛል። ይህም ከፊት የሚጠብቋቸውን ፈተናዎች መወጣት እንዲችሉ ይረዳቸዋል። አጭር የምስል መግለጫ የሳይንስ ቦርሳው የሚጠይቀው ወጪ ዶላር ብቻ ነው፡፡ ከሰሜን ምዕራብ ቤሬኩሶ የስድስት ሠዓት መንገድ ርቀት ላይ በኩማሲ ከተማ በሚገኝ የቴክኖሎጂ ማዕከል ውስጥ ባለች ትንሽ ሰርቶ ማሳያ የቻርለስ ቡድን የሳይንስ ቦርሳዎችን በማሰናዳት ሥራ ተጠምዷል። በሺዎች የሚቆጠሩ ቀጫጭን የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ ሽቦዎችን በትናንሽ መቆጣጠሪያ ወይም ርዚስተሮች ላይ እየበየዱ ነው። እሺ ይሄ ነው አለ ቻርለስ በኩራት ትንሿን ጥቁር ሳጥን ይዞ። የአጠቃቀም መመሪያውን፣ የኤሌክትሮኒክ ክፍሎችን፣ የኤሌክትሮ ማግኔት የብረት ቁርጥራጮችን፣ የብርሃን ሳጥኑን፣ መስታውቶችን በመሃል ደግሞ ሁሉንም የሚያንቀሳቅሱትን ባትሪዎች አንድ በአንድ ያሳያል። ቻርለስ የሳይንስ ቦርሳዎችን ከጎረቤት አይቮሪኮስት ካካዋ አምራች ማህበረሰቦች ውስጥ ላሉ ት ቤቶች ሊያስተዋውቅለት ከሚችል ደንበኛ ጋር የስልክ ቀጠሮ አለው፡፡ ጥልቅ ሙያዊ ፍቅር ያለው የሽያጭ ሰራተኛ ነው፤ ሁሉንም ጥያቄዎች ዘና ብሎ ይመልሳል። ስልኩን እንደጨረሰ ፈገግታ ፊቱን ሞላው። ጥሩ ነበር አለ ለሙከራ የተወሰኑ ቦርሳዎችን ለመግዛት መስማማታቸውን በማብራራት። ይህ ተጨማሪ የሥራ ትዕዛዝ ወይም በሳይንስ ቦርሳው ላይ ተጨማሪ ገንዘብ እንዲገኝ ሊያደርግ ይችላል ይላል። ወደ ቤሬኩሶ ስንመለስ ከት ቤቱ ትንሽ ኪሎ ሜትሮች ርቀት ላይ ባለው አቧራማ መንገድ አቅራቢያ የ ዓመቷ ፕሪንሰስ ማካፉይ ከት ቤት ጓደኞቿ ጋር ተቀምጣ የቤት ሥራዋን ትሰራለች። ቤተሰቦቿ የሚኖሩት ጨርሶ ባላለቀ ቤት ውስጥ ነው። ኤሌክትሪክ ይቅርና አንድም ግድግዳ የለውም። ፀሐይ ስለጠለቀች ራሳቸው የፈጠሯትን አንዲት መብራት ከጠረጴዛው መሃል አስቀምጠው ነው የሚሰሩ። አጭር የምስል መግለጫ ፕሪንሰስ ማካፉይ እና የክፍሏ ልጆች የሳይንስ ቦርሳውን በመጠቀም ውድድር አሸንፈዋል አራት ማዕዘን መብራት ነው ትላለች ፐሪንሰስ በኩራት። ይህም ማለት ሁላችንም የቤት ሥራችንን ለማየት አንደኛውን ጎን መጠቀም እንችላለን ማለት ነው። ፕሪንሰስና ሴት ጓደኞቿ በዚህ ፈጠራቸው በአካባቢያቸው የተካሄደውን የሳይንስ ውድድር አሸንፈዋል። ለዚህም የሳይንስ ቦርሳውን ተጠቅመዋል። ከሳይንስ ቦርሳዎቹ በፊት የሳይንስ ክፍለ ጊዜያችን አሰልቺ ነበር። ሁሉም ነገር ንድፈ ሃሳብ ስለነበር እየተረዳነው አልነበረም ትላለች። ለቻርለስ አዲስ የፈጠራ ሰዎች ትውልድ እውን የማድረግ ሀሳብ ማለት ተስፋ ሊያደርገው የሚችለው ነገር በሙሉ ማለት ነው። የሳይንስ ቦርሳቸውን ተጠቅመው ተማሪዎች በአዳዲስ የፈጠራ ሥራዎች ብቅ ሲሉ ማየት በእርግጥም እውን ለማድረግ ስንሞክረው የቆየነው ጉዳይ ነው። ለተማሪዎች መገልገያዎቹን ስትሰጣቸው ያንን እውቀት በመጠቀም በአካባቢው ላሉ ችግሮች መፍትሄ መፈለግ ይጀምራሉ። የፈጠራ ሰው የፈጣራ ሰዎችን እያፈራ ጥሩ ይመስላል ይላል በፈገግታ። አባቴ ቢኖር ኖሮ በእርግጠኝነት ይኮራ ነበር። ይህ የቢቢሲ ተከታታይ ክፍል የተዘጋጀው ከቢል እና ሚሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ ነው። የእርሶ መሳሪያ ሚዲያ ፕሌይ ባክን ማጫወት ኣልተቻለም። ታዳጊዎች ፈጠራ ላይ እንዲያተኩሩ የሚያደርገው ቦርሳ ተያያዥ ርዕሶች
ዘመናዊውን የመፀዳጃ መቀመጫ የፈጠረው ሰዓት ሠሪ
ኖቬምበር ለዘመናዊው የመፀዳጃ መቀመጫ ፈጠራ ሊመሰገን የሚገባው በለንደን የነበረ ሰዓት ሠሪ ነው። በ ኛው ክፍለ ዘመን የተፈጠረው ይህ ቀላል የሆነ የታጠፈ ቱቦ ለዘመናዊ መፀዳጃ ቤቶች ችግር ምላሽ ያስገኘና አስፈላጊው ክፍል ነው። ከግኝቱ ከሁለት መቶ ዓመታት በኋላም እስካሁን መደበኛ የሆነው የዘመናዊ መፀዳጃ ቤቶች የሌሏቸው ሰዎች ቁጥር ከሁለት ቢልዮን በላይ ይሆናሉ። ሰዓት ሠሪው ቴክኖሎጂውን ቢያመጣውም ለሁሉም ማዳረስ ግን እስካሁን ችግር ሆኖ ቀጥሏል። እንዴት መጣ አሌክሳንደር ካሚንግ የመፀዳጃ ቤት መሃንዲስ ብቻ አልነበረም። ብዙ የፈጠራ ሥራዎቹ የተለዩ ነበሩ። የአየር ጫናን ሊመዘግብ የሚችል የተራቀቀ መሣሪያ ለመሥራት በእንግሊዙ ንጉስ ጆርጅ ኛ ተቀጥሮ ነበር። ጥናታዊ ምርምሮችን ለማካሄድ የሚጠቅመውን ማይክሮቶም የተሰኘ እንጨት በስሱ የሚቆርጥ መሣሪያ በመስራትም የመጀመሪያው ነበር። ዓለምን የቀየረው የአሌክሳንደር ፈጠራ ግን ከምህንድስና ሙያው ጋር አይገናኝም ነበር። ለውጡን ያመጣው እጥፋት የነበረበት ቱቦ ነው። እ አ አ በ አሌክሳንደር የ ን ቅርጽ ለያዘው ቧንቧ የፈጠራ ባለቤትነት ሆኖ ተመዘገበ። ይህም በዘመናዊ መንገድ ዉሃ የሚለቀውን የመፀዳጃ መቀመጫ ለመፍጠር መንገድ ከፈተ። ከዚህም ጋር አብሮ የሕዝብ ንጽህና ተከተለ። ቀላል ዘዴ ከዚህ ቀደም የዉሃ መልቀቂያው ዘዴ ሽታ ያስከትል ነበር። ጠበቅ ያለ የማፈኛ ዘዴ ካልተፈጠረለት በስተቀር ዉሃ ከተለቀቀ በኋላ በቧንቧው በኩል ወደ ጉድጓድ የዉሃ ሽንትና ሰገራ ቢያስወግድም የጉድጓዱን ሽታ ግን ወደ ላይ ይመልስ ነበር። የአሌክሳንደር መፍትሔ ደግሞ ቀላል ነበር እሱም ቧንቧውን ማጠፍ ነበር። ዉሃ እጥፋቱ ላይ ስለሚከማች ወደ ላይ የሚመለሰውን ሽታ ይገድብ ነበር። ዉሃው በተለቀቀ ቁጥር ደግሞ ይታደሳል። አሁን ያለው ቧንቧ እንደፈረንጆቹን ፊደል ቀድም ተከተል ቅርጹ ከ ወደ ቢዘዋወርም በመፀዳጃ ቤት ዉሃ የመልቀቅ ግንዛቤው ግን አልተቀየረም። ግኝቱ ቢኖርም በሥራ ላይ ለማዋል ግን ረዥም ዓመታትን ፈጅቷል። እ አ አ በ በለንደን ታላቅ ኤግዚብሽን ከዓለም አቀፍ ግኝቶች ጋር ለሕዝብ ቀረበ። በመፀዳጃ ቤት ዉሃ መልቀቅ በለንደን አዲስ ከመሆኑ የተነሳም ለሕዝቡ ታላቅ የደስታ ምንጭ ምክንያት ሆኖ ነበር ። በዚህ መልኩ የተሠሩ መፀዳጃ ቤቶችን ለመጠቀም በእንግሊዝ ሀገር አንድ ሳንቲም ያስከፍል ነበር። እስከ ዛሬ ለዉሃ ሽንት ወደ መፀዳጃ ቤት መሄድ ሲፈለግ አንድ ሳንቲም ልከፍል ነው ይባላል። ዘመናዊው የቧንቧ ሥራ ባሰገኘላቸው አዲስ ፈጠራ ለመደነቅና ለመተንፈስ ብለው በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ የለንደን ነዋሪዎች ተሰልፈው ነበር። ከዓለም የጤና ድርጅት በተገኘው መረጃ መሠረት እ አ አ በ አንድ አራተኛ የሚሆነው የዓለም ህዝብ ብቻ የዘመናዊ የመጸዳጃ ቤት ተጠቃሚ የነበረ ሲሆን ከ ዓመታት በኋላሁለት ሶስተኛ የሚሆነው ሕዝብ ተጠቃሚ መሆን ችሏል። ኢኮኖሚ ላይ የሚያስከትለው ወጪ ይህ ማለት ከሁለት ቢልዮን ሕዝብ በላይ የሚሆኑ ሰዎች የዘመናዊ መፀዳጃ ቤት አገልግሎት የላቸውም። ይህ ዘዴ ጤናማ በሆነ መልኩ የሰውን ቆሻሻ ከሰው ግንኙነት ያርቃል እንጂ የቧንቧውንና የቱቦውን ችግር አያስወግድም። እንደዚህ አይነት የቆሻሻ ማስወገጃ አገልግሎት ያላቸው የዓለም ሕዝቦች ግማሽ እንኳን አይሞሉም። ይህንን ዜና ያጋሩ ስለማጋራት
ቶጎዋዊያን ተመራማሪዎች የኤሌክትሮኒክስ ቆሻሻን ወደ ሮቦቶች ቀይረዋል
ኖቬምበር ማጋሪያ ምረጥ አጭር የምስል መግለጫ ከተጣለ ማተሚያ ማሽን በሸረሪት ቅርፅ የተሰራ ሮቦት ቶጎ በየዓመቱ ወደ ሀገሯ ከምታስመጣቸው ሺህ ሰልባጅ ኤልክትሮኒክሶች መካከል አንዳንዶቹ ለጤና ጠንቅ ቢሆኑም እንኳ የሀገሪቱን ወጣት ተመራማሪዎችን ግን ለአዳዲስ ፈጠራ አነሳስቷቸዋል። ያገለገሉ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች በመንግሥት ወይም በግለሰቦች ጥቅም ላይ ውለው ከተወገዱ በኋላ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ቆሻሻ ይሆናሉ። የ ዓመቱ ቶጓዊ ሀገሩ የምታስገባቸው የኤሌክትሮኒክስ ውድቅዳቂዎችን በመሸጥ ይጠቀማል። አነስተኛ የእግር ኳስ መጫወቻ ሜዳ የሚያክል ስፍራ ላይ ያገለገሉ ቴሌቪዥኖችና ሌሎች የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ተከምረው ይታያሉ። ከእነዚህ ውድቅዳቂና ያገለገሉ እቃዎች በቶጎ የመጀመሪያውን ስሪ ዲ ማተሚያ እንደሰራ የሚናገረው ጊንኮ አፋቴ ያገለገሉ እቃዎችን መልሶ ጥቅም ላይ ስለማዋል በርካታ ነገሮች እንደተማረ ይናገራል። የእርሱ ፈጠራ እውቅና አግኝቶ በ በባርሴሎና የቴክኖሎጂ ምርቶች ጉባኤ ላይ ቅድሚያ አግኝቷል። ከዚህ በፊት የተጣሉ እቃዎችን እየሰበሰቡ የተለያዩ ነገሮች ከሚሰሩ ወዳጆቹ ጋር በህብረት ይሰራ የነበረው የ ዓመቱ የፈጠራ ባለሙያ ዛሩሬ የራሱን መስሪያ ቦታ ከፍቷል። የቶጎ ጎዳናዎች ባገለገሉ እቃዎችና በበሰበሱ የኮምፒውተር አካላት ተሞልተው ነበር። ዛሬ ይህ ነገር አይታይም። አሁን የቆሻሻ ክምር ሳይሆን የወርቅ ጉድጓድ ነው የሚታየኝ ይላል ለፈጠራ የሚያነሳሳውን የኤሌክትሮኒክስ ቆሻሻ ሲያስታውስ። በዓለም ላይ የአውሮፓ ሀገራት ብቻ ናቸው ስለሚያስወግዷቸው የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች መረጃ የሚይዙት። የእርሶ መሳሪያ ሚዲያ ፕሌይ ባክን ማጫወት ኣልተቻለም። ከ ሰው ፈጠራ ረሃብ የቀሰቀሰው ፈጠራ ያገለገሉ የሞባይል ቀፎዎች፣ ላፕቶፖች፣ ቴሌቪዥኖች፣ ጄኔሬተሮች፣ በእቃ መጫኛ መኪናዎች ተጭነው ከሎሜ ወደብ ይመጣሉ። መኪኖቹ እቃዎቹን የሚያራግፉት ከወደቡ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኝ የገበያ ስፍራ ነው። ያኔ ሰልባጅ እቃዎችን ለመግዛት የሚረባረቡ ሰዎች ቁጥር አይን አይቶ አይሰፍረውም። ሸማቾች ለቴክኖሎጂ ያላቸው ፍላጎት እየጨመረ በመምጣቱ ሰልባጅ እቃዎችን በድርድር ዋጋ መግዛት ጀምረዋል። ያገለገሉ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ፍላጎት መኖር ብቻ ሳይሆን ባደጉ ሀገራት ያገለገሉ እቃዎችን መልሶ ጥቅም ላይ የማዋል ነገር በበቂ ሁኔታባለመኖሩ ቶጎን መጣያ አድርጓታል። እኤአ በ በዓለማችን ሚሊየን ቶን የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ቆሻሻ እንደተሰበሰበ ተገልጾ ነበር። ከዚህ ውስጥ በመቶው ብቻ ተመልሶ ጥቅም ላይ እንዲውል ይደረጋል።
በ ዎቹ አጋማሽ ዊሊያም ኖርዶስ በብርሃን ዙሪያ ቀለል ያሉ ተከታታይ ሙከራዎችን ያደርግ ነበር።
መጀመሪያ በቀድሞ ታሪኮች የተመዘገቡትን ቴክኖሎጂዎች ነበር የተጠቀመው በእንጨት እሳት ማቀጣጠል። ሆኖም ፕሮፌሰር ኖርዶስ የብርሃን መጠንን የሚለኩ ዘመናዊ መሳሪያዎችም ነበሩት። ኪሎግራም የሚመዝን እንጨት አንድዶ ለምን ያህል ጊዜ እንደነደደ ፣እንደጠፋና እሳቱ የፈጠረውን ብርሃን በጥንቃቄ መዘገበ ። በመቀጠልም የጥንቱን ከጥፍጣፋ ድንጋይ የሚሰራውን የሮማውያንን ኩራዝ አምጥቶ የጋዝ ክር ካሰረበት በኋላ በቀደዳው ውስጥ ደግሞ የሰሊዝ ዘይት ያደርግበታል። ኩራዙን ለኩሶ ዘይቱ ነዶ እስኪያልቅ የሰጠውን ብርሃንናን የክሩን ፍም መጠን መዘገበ። አጭር የምስል መግለጫ ኖሮዶስ የሮማውያን ኩራዝ ከክምር እንጨት የተሻለ ብርሃን መስጠቱን ተረዳ ኖሮዶስ ያቀጣጠለው ኪሎግራም እንጨት የነደደው ለሶስት ሰዓታት ብቻ ነበር። በትንሽ ጠርሙስ ላይ የነደደው ኩራዝ ግን ለሙሉ ቀን ሲነድ የተሻለ ብርሃን ስጥቷል። ይህንን ሁሉ ነገር ማድረግ የፈለገው ደግሞ በተለያዩ ዓመታት ብርሃኑን ለማግኘት የሚውሉ ቴክኖሎጂዎች የሚጠይቁትን ወጪ በማስላት ምጣኔ ሃብታዊ ጥቅማቸውን መለየት ነው። ብዙ ወጪ የሚያስወጡ ዘዴዎች ብርሃን የሚለካው በሰዎች ዓይን ላይ በሚፈጥረው ድመቀት ነው ሉመንስ ለምሳሌ ሻማ ሲለኮስ ሉመንስ ብርሃን ይሰጣል። የተለመዱት ዘመናዊ አምፖሎች ደግሞ ከዚህ እጥፍ የሚሆን ድምቀት ይሰጣሉ። እስኪ ለስድስት ተከታታይ ቀናት በቀን ለ ሰዓታት እንጨት ስትለቅሙና ስትፈልጡ መዋልን አስቡት። በዛ ላይ ከ ሰዓታት ልፋት በኋላም ሊገኝ የሚችለው ሉመን ብርሃን ነው። ዘመናዊ አምፖሎች ግን ይህንን ብርሃን በ ደቂቃዎች ውስጥ መስጠት ይችላሉ። በርግጥ እንጨት የሚነደው ለብርሃን ብቻ አይደለም፡ ለሙቀትም ፣ምግብ ለማብሰልም ፣የዱር አራዊትን ለማስፈራራትም ሊሆን ይችላል። ነገር ግን ብርሃን ቢያስፈልግና እንጨትማንደድ ብቸኛ አማራጭዎ ቢሆን ፀኃይ እስክትወጣ ለመጠበቅ ይወስኑ ይሆናል። ከሺህ ዓመታት በፊት ግን ግብፅና ግሪክ ሻማን ፣ ባቢሎን ደግሞ ኩራዝን ለዓለም አስተዋወቁ። የሚሰጡት ብርሃንም ዘላቂና ለመቆጣጠርም የሚመች ቢሆንም በጊዜው ዋጋቸው ውድ ነበር። በአውሮፓውያን የሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት የነበሩት ኤድዋርድ ሆሊያክ ባሰፈሩት በማስታወሻቸው እንዳሰፈሩት ቤተሰበቸው ከቀለጠ ስብ ኪሎግራም የሚመዝን ሻማ ለመስራት ሁለት ቀናት ፈጅቶበታል። ከስድስት የበጋ ወራት በኋላ ደግሞ ሻማዎቹ በሙሉ አልቀዋል ብለው ጻፉ። ታዲያ እነዚህ ሻማዎች እንደአሁኖቹ ከሰም በጥራት የሚዘጋጁ አልነበሩም። ባለጸጋዎቹ ከማር እንጀራ የሚሰራውን ሲያበሩ ብዙኃኑ ግን መጥፎ ጠረንና ጭስ ያላቸውን የስብ ሻማዎች ነበር የሚጠቀሙት። ይህ ደግሞ በቀለጠው ስብ ውስጥ የፈትል ክርን ልክ እንደጧፍ መልሶ መላልሶ መክተትን ይጠይቃል ፤ ስራው በጣም አድካሚና ጊዜ የሚወስድ ነበር። አጭር የምስል መግለጫ የስብ ሻማ ስራው በጣም አድካሚና ጊዜ የሚወስድ ነበር። በፕሮፌሰር ናርዶስ ጥናት መሰረት በአንድ ዓመት ውስጥ ለአንድ ሳምንት ወይም ለ ሰዓታት ለሻማ መስሪያ ወይም እነሱን ለመግዛት ለሚያስችል ስራ ቢውል ማግኘት የሚቻለው ለሁለት ሰዓታትና ደቂቃዎች ብቻ የሚበራ ሻማ ነው። በ ኛውና በ ኛው ክፍለ ዘመን ግን ሁኔታዎች ይበልጥ መሻሻል ጀመሩ። ከሞቱ አሳነባሪዎች ከሚገኝ ዘይት መሰል የሚያጣብቅ ወፈር ያለ ፈሳሽም ሻማ መሰራት ተጀመረ። ሻማው በሚሰጠው ጠንካራ ብርሃን ፣ በእጅ ለመያዝ ምቹ በመሆኑንና በሞቃት አየርም እንደጠነከረ በመቆየቱን ተወዳጅ ሆነ። ታላቁ እመርታ አዳዲሶቹ ሻማዎች አስደሳች ቢሆኑም ዋጋቸው ግን ለብዙኃን የማይቀመስ ነው። ጆርጅ ዋሽንግተን ይህንን ሻማ በአመት በየቀኑ ለአምስት ሰዓታት ለማብራት ዶላር እንደሚያስወጣው ተናግሯል ። ይህ ገንዘብ አሁን ዶላር ያወጣል ። ከጥቂት አስርት ዓመታት በኋላ ደግሞ የነጭ ጋዝና በሌሎች ጋዞች የሚሰሩ ፋኖሶች በአንጻራዊ አነስተኛ ዋጋ መቅረብ ጀመሩ። ነገር ግን እነሱም ቢሆኑ አዘገጃጀታቸው አድካሚ ነበር። ከዚህ ሁሉ በኋላ ግን ሁሉንም የሚለውጥ አዲሱ የአምፖል ግኝት መጣ። አጭር የምስል መግለጫ የኤዲሰን የአምፖል ግኝት ከሰው ሰራሽ ብርሃን ፈጠራዎች ሁሉ ታላቁ ተደርጎ ይወሰዳል በ የቶማስ ኤዲሰን አምፖሎች ከሻማ እጥፍ የሚሆን ብርሃን ያለማቋረጥ ለ ቀናት ይሰጡ ነበር። በ አምፖሎቹ ዋጋቸውም እየረከሰ አቅማቸውም እያደገ ለአምስት ተከታታይ ወራት ብርሃን መስጠት ጀመሩ። ከጥቂት ዓመታት በኋላ ደግሞ የፍሎረሰንት አምፖሎች ተፈጠሩና ቀድሞ ለ ደቂቃዎች ብርሃን የመስጠት አቅም የነበረው የኤሌክትሪክ ኃይል አሁን ለ ዓመታት ማቆየት ቻለ። የፈጠራ ተምሳሌቶች ዘመናዊዎቹ የኤልኢዲ መብራቶችም ከጊዜ ወደ ጊዜ ዋጋቸው እየቀነሰ መጣ። በእርግጥም ከፋኖሶችና ሻማዎች በተለየ እነዚህ መብራቶች ንጹህ፣ ለአደጋ የማያጋልጡና ለቁጥጥርም የሚመቹ ናቸው። እናም ግኝቱ የፈጠራዎች ተመሳሌት ተደርጎ መወሰድ ጀመረ። ዓለማቀፉ ማሀበረስብም የመሥራት ፣ የማነበብና የመጫወት ፍላጎቱ በፀሐይ መጥለቂያ ሰዓት መገደቡ ቀረ። ይህንን ዜና ያጋሩ ስለማጋራት
በኢትዮጵያ በአንድ ቀን የተተከሉት ከ ሚሊዮን በላይ ችግኞች እንዴት ተቆጠሩ
ጁላይ ስለ ማጋራት ተጨማሪ ያጋሩ ማጋሪያ ምረጥ ትናንት ሐምሌ ቀን ዓ ም አረንጓዴ አሻራ በሚል ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድን ጨምሮ ከፍተኛ ባለሥልጣናትና የተለያዩ አካባቢ ነዋሪዎች በአገር አቀፍ ደረጃ ችግኝ ተክለዋል። ይህንን ቀን በማስመልከት በአንዳንድ አገራት የሚገኙ የኢትዮጵያ ኤምባሲዎችም ባሉበት አሻራቸውን አሳርፈዋል። የአየር ንብረት ለውጥ፤ የት ደረስን የአረንጓዴ አሻራ ዘመቻው በአንድ ቀን ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል የዓለምን ክብረ ወሰን መስበር እንዲሁም በአጠቃላይ ቢሊየን ችግኞችን የመትከል ዓላማ ይዞ የተነሳ ነው። በዚህ የአረንጓዴ አሻራ ዘመቻ በአንድ ጀምበር ከ ሚሊዮን በላይ ችግኞችን በመትከል በሕንድ ተይዞ የነበረውን የዓለም ክብረ ወሰን ኢትዮጵያ መስበሯ ተዘግቧል። ለመሆኑ የተተከሉት ችግኞች እንዴት ተቆጠሩ ይህንን ሂደት ሲከታተል የነበረው የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጅ ሚኒስቴር ሲሆን በሥሩም አንድ ቡድን ተቋቁሟል። ቡድኑ የችግኝ ተከላዎችን አቆጣጠራቸውንና ምዝገባቸውን የሚከታተል ነው። ያነጋገርናቸው የዚህ ቡድን አስተባባሪ አቶ ኢምራን አቡበከር በትክክል መተከላቸውን ለመቆጣጠር ቀድሞ የተሠራ ሶፍት ዌር መኖሩን ይናገራሉ። እርሳቸውም ይህንን ሶፍት ዌር በመስራቱ ረገድ ሚና ነበራቸው። ሶፍት ዌሩ በዛፍ መትከያ ቦታዎች ላይ የተከላውን ሂደት ለመቆጣጠር የተመደቡ ሰዎች ስልክ ላይ ብቻ የሚሠራ ሲሆን በአካል በመገኘት የቆጠሩትን ችግኝ ብዛት የሚያስተላልፉበት ሥርዓት አለው። በዚህም መሠረት በተመደቡበት ቦታ ላይ ምን ያህል ችግኞች እንደተተከሉ ቁጥሩን ሲያስገቡ ሶፍት ዌሩ በተለያዩ ቦታዎች የሚደርሱትን አሃዞች በማጠቃለል እየደመረ ውጤቱን ይሰጣል። በመጨረሻ ላይም በአጠቃላይ በመላዋ ሃገሪቱ የተተከሉትን ችግኞች ቁጥር ምን ያህል እንደሆነ ያሳውቃል ሶፍት ዌሩ። ከዚህም ባሻገር ሌሎች የመቆጣጠሪያ መንገዶችን እንደተጠቀሙና ከ ሚሊዮን በላይ ችግኞች መተከላቸውን አቶ ኢክራም ገልፀውልናል። ምድር በአስፈሪ ሁኔታ እየሞቀች ነው ከዚህ ቀደምም የተለያዩ የችግኝ መትከል ዘመቻዎች መከናወናቸው ይታወቃል። ሆኖም ምን ያህሉ ፀደቁ የሚለው ላይ ባለሙያዎች ጥያቄ ያነሳሉ። የለም ኢትዮጵያ አካባቢ ልማት ማኅበር ሥራ አስኪያጅ አቶ ሞገስ ወርቁ ችግኝ ከመተከሉ በፊት ጥንቃቄ ያስፈልጋል ሲሉ ይጀምራሉ። መንግሥት ከዘመቻ ሥራ ወጥቶ የተጠና ሥራ መስራት አለበት የሚሉት አቶ ሞገስ ሰሞኑን ችግኞች በተተከሉባቸው ቦታዎች ላይ ሰዎች ግንዛቤው ሳይኖራቸው ቁጥር ላይ ብቻ ትኩረት ሲያደርጉ መታዘባቸውን ነግረውናል። አተካከላቸው ሳይንሱ የሚፈልገው ዓይነት አይደለም፤ አንዳንዱ ተከልኩ ለማለት ያህል ጣል አድርጎ የሚመጣ አለ ሲሉ በግድ የለሽነት ችግኝ እንደማይተከል ያስረዳሉ። ችግኝ ያልተተከሉባቸው ቦታዎች እያሉ የተተከሉባቸው ቦታዎች ላይ መልሶ መትከልም ጠቃሚ እንዳልሆነ አቶ ሞገስ ያነሳሉ። በአንድ ጊዜ አገሪቱን በደን መሸፈን ይቻላል ብሎ ማሰብ አስቸጋሪ ነው የሚሉት አቶ ሞገስ በደንብ በባለሙያዎች በተጠና መልኩ፣ እቅድ ተይዞ፣ ይህን ያህል እንተክላለን ተብሎ፣ ቦታው ተለይቶ፣ የችግኞቹ ዝርያ ታውቆ፣ ችግኙም በወቅቱ ተዘጋጅቶ ሊካሄድ ይገባል ሲሉም ይመክራሉ። እስካሁን በነበረው ልምድ ችግኞች ሲተከሉ ለአካባቢው ተስማሚ የሆኑ ናቸው አይደሉም ብሎ ለመወሰን የሚያስቸግር መሆኑን በመግለጽ የተገኘው ሁሉ ነው ሲተከል የቆየው ብለዋል። ይሁን እንጂ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን ችግኞች ለመትከል የተደረገውን ይህን እንቅስቃሴና ዘመቻ ሳያደንቁ አላለፉም። ተያያዥ ርዕሶች
የአሜሪካ ምርጫ፡ ቢሊየነሩ ማይክል ብሉምበርግ ለፕሬዝዳንትነት ሊወዳደሩ ነው
ኅዳር ማይክል ብሉምበርግ ቢሊየነሩ የንግድ ሰው ማይክል ብሉምበርግ የዴሞክራቲክ ፓርቲን በመወከል ለአሜሪካ ፕሬዝዳንትነት ለመቅረብ ራሳቸውን በእጩነት የማቅረብ ጠንካራ ፍላጎት እንዳላቸው ተገለጸ። የቀድሞው የኒው ዮርክ ከተማ ከንቲባ የነበሩት የማክል ብሉምበርግ ቃል አቀባይ እንደተናገሩት፤ አሁን ካሉት ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር በመፎካከር ዲሞክራቲክ ፓርቲን ወክለው ለመቅረብ እጩ የሆኑት ሰዎች አሸናፊ ሆነው ለመውጣት ባላቸው ብቃት ላይ ብሉምበርግ ስጋት እንዳላቸው አመልክተወል። የ ዓመቱ ብሉምበርግ አላባማ ውስጥ የሚካሄደው የዕጩዎች ፉክክር ላይ ለመቅረብ የሚያስችላቸውን ማመልከቻ በዚህ ሳምንት ያቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል። በቀጣይ ዓመት በሚደረገው የአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ላይ ከዶናልድ ትራምፕ ጋር ለመፎካከር በአጠቃላይ ዕጩዎች ቀርበዋል። የአየር ንብረት ለውጥ ሚሊዮን አፍሪካውያንን ለረሃብ አጋለጠ የቀድሞው ምክትል ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን፣ የማሳቹሴትስ ግዛት ምክር ቤት አባል ኤልዛቤት ዋረንና የቬርሞንት ግዛት ምክር ቤት አባሉ በርኒ ሳንድስ በምርጫ ፉክክሩ ላይ በቀዳሚነት ይጠቀሳሉ። በቅርቡ በተሰበሰቡ የተወሰኑ የሕዝብ አስተያየት መለኪያዎች በተገኘ ውጤቶች መሰረት ኤልዛቤት ዋረንና በርኒ ሳንደርስ የዴሞክራቲክ ፓርቲን ፕሬዝዳንታዊ ዕጩነት ካገኙና ከወቅቱ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጋር ከተፎካከሩ ትራምፕ አሸንፈው ለሁለተኛ ዙር ዋይት ሐውስ ውስጥ የመቆየት እድላቸው የሰፋ ይሆናል ተብሏል። የማይክል ብሉምበርግ ቃል አቀባይ ጨምረው እንዳሉት፤ ትራምፕ የሚሸነፉበትን መንገድ ለማመቻቸት ሥራችንን መጨረስ አለብን። ነገር ግን ብሉምበርግ የዴሞክራቲክ ፓርቲውን ወክለው ለመወዳደር የቀረቡት እጩዎች ብቃት አሳስቧቸዋል ብሏል። ቢቢሲ ማስተባበያ
ኢትዮጵያ፡ የዛፍ ችግኝ የመትከል ዘመቻ ታሪካዊ ዳራ ምን ያሳያል
ኦገስት ማጋሪያ ምረጥ ሐምሌ ቀን ዓ ም አረንጓዴ አሻራ በሚል ዘመቻ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድን ጨምሮ ከፍተኛ ባለሥልጣናትና የተለያዩ አካባቢ ነዋሪዎች በአገር አቀፍ ደረጃ ችግኝ ተክለዋል። በዚህ የአረንጓዴ አሻራ ዘመቻም በአንድ ጀምበር ከ ሚሊዮን በላይ ችግኞችን በመትከል በሕንድ ተይዞ የነበረውን የዓለም ክብረ ወሰን ኢትዮጵያ መስበሯ ተዘግቧል። ለመሆኑ ችግኝን በዘመቻ መትከል መቼ፣ እንዴት እና በማን ተጀመረ የተተከሉት ችግኞች እንዴት ተቆጠሩ ችግኝን በዘመቻ መትከል በሕዝቡ ነው የተጀመረው የሚሉት በአካባቢ ጥበቃ ላይ በርካታ ምርምሮችን ያደሩት ዶ ር ተወልደ ብርሃን ገ እግዚአብሔር ናቸው። እርሳቸው እንደሚሉት ከአንድ ሺህ ዓመታት በፊት ያለው የኢትዮጵያ ሕዝብ የዛፍ ችግኞችን የመትከል ልማድ ነበረው። የዛፍ ጠቃሚነትን ከማንም በላይ ሕዝቡ ይረዳ ነበር የሚሉት ዶ ር ተወልደ ብርሃን ከዚያ በኋላ የዛፎች መቆረጥ በመብዛቱ እነርሱን የመተካት ጥረት ተጀመረ ይላሉ። ያ ጥረትም እየተፋፋመ መጥቶ ዘንድሮ በስፋት የችግኝ ተከላ መካሄዱን ይገልጻሉ። ሕዝቡ አካባቢውን ያውቃል፤ ተነግሮት አይደለም አካባቢውን እንዲያውቅ የሚማረው፤ የአካባቢ እንክብካቤ ለዘመናዊው ትውልድ የተላለፈው ከሕዝቡ ነው። በመሆኑም ሕዝቡ ድሮም ቢሆን መትከል ባያስፈልገው ዛፎችን ይንከባከብ ነበር፤ አስፈላጊ ሆኖ ሲታየውም ችግኞችን ይተክል ነበር። መሬቱ እንዳይሸረሸርም እርከኖችን ይሰራ ነበር፤ ይህም አዲስ ነገር አይደለም ብለዋል። ይሁን እንጂ ባለፉት ጥቂት ዓመታት ይኸው ባህል በዘመናዊነት ምክንያት መዳከሙን ገልፀው ወደፊት ወደ ነበረው ባህል የመመለስ ጥረት መጀመሩን ይናገራሉ። በሺህዎች ለሚቆጠሩ ዓመታት የቆየን ባህል በዚህ ጊዜ ተጀመረ ማለት ባይቻልም በተለያየ ጊዜ እና ዘመናት ተመሳሳይ የችግኝ ተከላ ዘመቻዎች ይካሄዱ እንደነበር ግን ያስታውሳሉ ዶ ር ተወልደ ብርሃን። ባሕልና ተፈጥሮን ያጣመረው ዞማ ቤተ መዘክር ከሺህዎች ዓመታት በፊት ሕዝቡ በራሱ ተነሳሽነት ነበር የሚተክለው ዘመቻውም ከታች ወደ ላይ ነበር፤ ከዚያ በኋላ ግን ዘመቻው ከላይ ወደታች ሆኗል ይላሉ። በዘመነ መሳፍንት ከነበረው የሥልጣን ሽኩቻ በኋላ ማዕከላዊ መንግሥት የጥንቱ የዛፍ ችግኞችን የመትከል ባህል እየተዳከመ ሲመጣ ወደነበረበት ለመመለስ ከላይ ወደታች ትዕዛዝ ማስተላለፍ እንደተጀመረ ያወሳሉ። የተለያዩ ጥናታዊና ታሪካዊ ፅሁፎች ችግኝን በዘመቻ መትከል የተጀመረው በ ኛው ክፍለ ዘመን በንጉስ ዘረ ያዕቆብ ዘመን እንደሆነ ያስረዳሉ። ከሁለት ዓመታት በፊት በሚል በታተመ ጆርናል ላይ በንጉስ ዘረ ያዕቆብ ዘመን በዘመቻ ከተተከሉና ተጠብቀው ከቆዩ ደኖች ወፍ ዋሻ፣ ጅባት፣ መናገሻ እና የየረር ተራሮች ጥብቅ ደኖች ተጠቅሰዋል። ከዚያም በኋላ አፄ ምንሊክ ዘመናዊ እፅዋትን ለኢትዮጵያ እንዳስተዋወቁ ይነገራል። በአገሪቱ ያለውን የማገዶና የቤት መሥሪያ ቁሳቁስ እጥረት ለመቀነስ የባህር ዛፍ ተክልን ከአውስትራሊያ እንዳስመጡ ይነገራል። በወቅቱም የደን መጨፍጨፍን ለመከላከል ሁሉም በግለሰብ መሬት ላይ ያሉ ዛፎች የመንግሥት ንብረት ናቸው ሲሉ አውጀው እንደነበር በዚሁ ጆርናል ላይ ተጠቅሷል። ይህም ደኖች የህዝብ ሐብት እንደሆኑ በሕብረተሰቡ ዘንድ ግንዛቤ ለመፍጠር አስችሏል። ከዚያም በኋላ ኢትዮጵያን ያስተዳደሩ መሪዎች የተለያዩ ስልቶችን እየተጠቀሙ ችግኞችን በዘመቻ ያስተክሉ ነበር። ቤተክርስቲያንና መስጊዶች ምን ጊዜም ዛፎችን የመጠበቅና የመንከባከብ ልማድ አላቸው፤ በእርሻና በተለያየ መልኩ ቦታው ቢፈለግም ዛፎችን ጠብቆ ማቆየት የተለመደ ነው የሚሉት ደግሞ የኢትዮጵያ የአካባቢና ደን ምርምር ኢንስቲቲዩት ዳይሬክተር ዶ ር አብዮት ብርሃኑ ናቸው። በመንግሥት ደረጃ ችግኞችን አፍልቶ መትከል የተጀመረው ግን በአጼ ልብነ ድንግል ዘመን ነው ይላሉ ። በ ኛው ክፍለ ዘመን አጼ ልብነ ድንግል ከወፍ ዋሻ ዘርና ችግኞችን ወስደው ከአዲስ አበባ በስተምዕራብ በሚገኝ መናገሻ ሱባ የሚባል ሥፍራ የሃበሻ ጽድ መትከላቸውን ያነሳሉ። ከዚያ በኋላ አፄ ምንሊክ ባህርዛፍን ከአውስትራሊያ በማስመጣት ተክለዋል ሲሉ ያወሳሉ። ምን አልባት አጼ ሚንሊክ ባህር ዛፍን አዲስ አበባ ባያስመጡ ኖሮ አዲስ አበባ አሁን ያለችበት ቦታ ልትገኝ አትችልም ነበር የሚል እምነት አለኝ ይላሉ። በወቅቱ የአፄ ሚንሊክ ሠራዊትና በዙሪያቸው የነበሩት ሠራተኞች የማገዶና የቤት መሥሪያ ግብዓት እጥረት ይገጥማቸው ነበር። ይህንንም ለመፍታት ንጉሡ ባህርዛፍ አስመጥተው ባያስተክሉ አዲስ አበባ ባለችበት ላትቀጥል ትችል ነበር ሲሉ ምክንያታቸውን ያስረዳሉ በዘመኑ ነገሥታት በተለያዩ ምክንያቶች መናገሻቸውን ይለዋውጡ እንደነበር በማስታወስ። አፄ ምንሊክ በፍጥነት ማደግ የሚችልና ራሱን በፍጥነት የሚተካውን ባህርዛፍን በአማካሪያቸው አማካኝነት እንደመረጡትም ይነገራል። በዛፍ ችግኝ ተከላ ታሪካዊ ዳራ ላይ የተሰሩ ጥናቶችን የሚጠቅሱት ዶ ር አብዮት አፄ ኃይለ ሥላሴ ችግኝን ለመትከልና ለመንከባከብ የደን አዋጅን በማውጣት በርካታ ሥራዎች ማከናወናቸውን ያስረዳሉ። አጼ ኃይለ ሥላሴ ችግኝ መትከልን እንደ አንድ የመንግሥት ሥራ አድርገው ይወስዱት ነበር ይላሉ ዶ ር አብዮት። የአየር ንብረት ለውጥ፤ የት ደረስን እርሳቸው እንደሚሉት አጼ ኃይለ ሥላሴ ደን መጠበቅና ችግኝ መትከል ብቻ ሳይሆን ብሔራዊ ፓርኮች እንዲቋቋሙ ምክንያት ሆነዋል። አዋሽ ብሔራዊ ፓርክን በምሳሌነት ያጣቅሳሉ። በደርግ ዘመነ መንግሥትም የአካባቢ ጥበቃን የተመለከቱ ፖሊሲዎች ተቀርፀዋል። ዋነኛ ትኩረታቸው ግን የዱር እንስሳት ጥበቃ ላይ እንደነበር ጥናቶች ያትታሉ። በተለይ በጎርጎሳውያኑ አቆጣጠር ዓ ም በተለያዩ አካባቢዎች ላይ የተከሰተው ርሃብና ድርቅ፤ አካባቢ ጥበቃ ላይ ጠንክሮ ለመስራት ካነሳሱት ጉዳዮች መካከል ይጠቀሳሉ። በአጠቃላይ ደን ሥራ ላይ ከፍተኛና የተቀናጀ ስራ ለመስራት ዝግጅት ተደርጎ፣ ቦታዎች ተመርጠው፣ ችግኞች ተፈልተው፣ ለማህበረሰቡ አነስተኛ ድጎማ በማድረግ፤ በተራቆቱ ቦታዎች ችግኞች እንዲተከሉ በርካታ ሥራዎች መሰራታቸውን ዶ ር አብዮትም ያረጋግጣሉ። በተራሮች ላይ በብዛት የሚታዩት ደኖችም በዚያ ዘመን የተተከሉ ናቸው ይላሉ። እርሳቸው እንደሚሉት የችግኝ መትከል ዘመቻዎችን ለማካሄድም በዋነኛነት ለሰዎች ማበረታቻዎችን በመስጠት፤ ለምሳሌ እርዳታ በሚያስፈልጋቸው ቦታዎች የእርዳታ እህል ለመስጠት ችግኝ እንዲተክሉ ይደረግ ነበር። ለትምህርት ቤት ደብተር መግዣ ችግኝ ተክለን ገንዘብ ይከፈለን ነበር ሲሉ የራሳቸውን ተሞክሮ ያነሳሉ። በጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ ጊዜ በተለይ ዋናው የትኩረት አቅጣጫ የአየር ንብረት ለውጥ በመሆኑ ችግኝ መትከልና አካባቢን መንከባከብ እንደ አንድ ትልቅ ሥራ እንዲወሰድ በርካታ ሥራዎች ይከናወኑ ነበር። ይህ ወቅት የልማትና የአካባቢ ጥበቃ ተቋማት የተመሠረቱበትም ነው። በፖሊሲ ደረጃም ሥነ ምህዳርን፣ አካባቢን፣ የተፈጥሮ ሐብት ጥበቃን በሚመለከት ግብ ተቀምጦለት እንቅስቃሴ የተጀመረበት ነው። በአሁኑ ሰዓት ኢትዮጵያን እየመሩ ያሉት ዶክተር ዐብይ አሕመድም አረንጓዴ አሻራ በሚል የተደረገው አገር አቀፍ የችግኝ መትከል ዘመቻ እየተካሄደ ነው። ዘመቻው በፍላጎት ላይ የተመሠረተ እና በስፋት በርካታ ችግኞች መተከላቸው ቀደም ካሉት ዘመናት ልዩ ያደርገዋል ሲሉ ዶ ር አብዮት አስተያየታቸውን ይሰጣሉ። በጥንታዊው ዘመን በሕዝቡ ተነሳሽነት የሚደረገው ችግኝ የመትከል ዘመቻ አሁን ላይ በመንግሥት አነሳሽነት መካሄዱ ብዙዎችን ያነጋግራል። ሕዝቡ ራሱ አውቆ ነው መትከል ያለበት፤ ዘመቻ አያስፈልግም በሚል። ይህንኑ ያነሳንላቸው ዶ ር አብዮት ከከተሞች መስፋፋትና ሥልጣኔ ጋር ተያይዞ ችግሮቹ እየገነኑ ሲመጡ ማህበረሰቡ የባህርይ ለውጥ ማሳየቱ የሚፈረድበት አይደለም ሲሉ ይመልሳሉ። በመሆኑም ማህበረሰቡን ማነሳሳትና ወደ ቀደመው ባህሉ ማሻገር እንደሚያስፈልግ ይመክራሉ። ባሳለፍነው ሰኞ በአንድ ጀንበር የተተከሉት ከ ሚሊየን በላይ ችግኞች በእርሳቸው ሙያዊ ስሌት ሺህ ሄክታር መሬት የሚሸፍን ሲሆን በዚህ ዓመት ሊተከል የታቀደው አራት ቢሊየን ችግኝ ደግሞ አንድ ሚሊየን ሄክታር መሬት ሊሸፍን እንደሚችል ለቢቢሲ ገልፀዋል። ችግኙ ፀድቆ ደን መሆን ሲችል የኢትዮጵያ የደን ሽፋን በአንድ በመቶ ሊያድግ እንደሚችል ይገምታሉ አንድ በመቶ በደን ሽፋን ሂሳብ ከፍተኛ መሆኑን በመግለፅ። የደን ሽፋን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ መምጣቱን የሚናገሩት ዶ ር አብዮት የኢትዮጵያ የደን ሽፋን ባለፉት አምስት ዓመታት በመቶ እንደሆነ ያስረዳሉ። በሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ በአውሮፓውያኑ የደን ሽፋንን በመቶ ለማድረስ መታቀዱን አስታውሰዋል። ከ ዓመታት በፊት የኢትዮጵያ የደን ሽፋን በመቶ እንደነበር ጥናቶች እንደሚያሳዩ የሚናገሩት ዶ ር አብዮት ምን ያህል የደን ሽፋን እንደሚያስፈልግ ጣራ ሊሰራለት እንደማይገባ ይናገራሉ። በኢትዯጵያ በአጠቃላይ የእፅዋት ዝርያዎች እንደሚገኙም ዶ ር አብዮት ነግረውናል። ተያያዥ ርዕሶች
ባህርዳርን ፅዱ ለማድረግ የሚታትሩት
ታህሳስ ባህር ዳርን ፅዱ ለማድረግ የከተማዋ ወጣቶች ተሰባስበው በየሳምንቱ ቅዳሜ ከጠዋቱ ፡ ላይ በመገናኘት ለ ደቂቃ ያህል በተለያዩ ስፍራዎች ለፅዳት ይሰማራሉ።
የዓለማችን ዋነኛ ሃብታም ለአየር ንብረት ለውጥ ቢሊየን ዶላር እሰጣለሁ አለ
የካቲት ይህንን ለማጋራት በ ዋትስአፕ የአማዞን ባለቤትና የበላይ ኃላፊ ጄፍ ቤዞስ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቆጣጠር የሚደረገውን ትግል ለማገዝ ቢሊየን ዶላር ለመስጠት ቃል ገባ። እንደ ግለሰቡ አስተያየት ከሆነ ገንዘቡ የአየር ንብረት ለውጥን ለመግታት ምርምር የሚያደርጉ ሳይንቲስቶችን ስራ ለማገዝ፣ የመብት ተሟጋቾችን እንዲሁም ሌሎች ቡድኖችን ለመደገፍ ይውላል። አክለውም የአየር ንብረት ለውጥ አስከፊ ተጽዕኖ ለመዋጋት የሚታወቁ መንገዶችን ለማጠናከርና አዳዲስ መንገዶችን ለመፈለግ በትብብር መስራት እፈልጋለሁ ብሏል። ጄፍ በኢንስታግራም ገፁ ላይ እንዳሰፈረው፣ ገንዘቡ በመጪው የክረምት ወር መከፋፈል ይጀምራል። ሚስተር ቤዞስ አጠቃላይ ሀብቱ ቢሊየን ዶላር የሚገመት ሲሆን ቃል የገባው የሀብቱን በመቶ ብቻ መሆኑ ታውቋል። አንዳንድ የአማዞን ሠራተኞች አለቃቸው የአየር ንብረት ለውጥን ለመዋጋት የበለጠ እንዲሰጥ ሲወተውቱ ነበር። አንዳንዶቹም በይፋ አደባባይ ወጥተው ይህንን አቋማቸውን የተናገሩ ሲሆን፣ አንዳንዶች ደግሞ ድርጅቱን ጥለው ወጥተው ነበር። ከዚህ ቀደም ሚስተር ጄፍ ቤዞስ ብሉ ኦሪጅን የተባለ የጠፈር ምርምር ፕሮግራምን በገንዘብ ቢደግፍም ለአየር ንብረት ለውጥ ሲባል እጅ ያጥረዋል ተብሎ ይተች ነበር። ከሌሎች የናጠጡ ሃብታሞች አንጻር ሲታይ ጄፍ ቤዞስ፣ በበጎ አድራጎት ተግባራት ላይ እምብዛም የማይሳተፍ ሲሆን ከዚህ የድጋፍ ተግባሩ በፊት ትልቅ ለልግስና ያወጣው ገንዘብ በ ለቤት አልባዎችና ትምህርት ቤቶችን በሚል የሰጠው ቢሊየን ዶላር ብቻ ነው። ከዚህ በፊት ቢሊየነሮች በሕይወት ዘመናቸው ያካበቱትን ሀብት ግማሹን ለበጎ ተግባራት እንዲውል ለመስጠት ተስማምተው ሲፈርሙ፣ እርሱ ባለመፈረሙ ምክንያት ስሙ ሲብጠለጠል ነበር። መቀመጫውን ሲያትል ያደረገው አማዞን ከማይክሮሶፍት ጋር የሚጎራበት ሲሆን በ ከካርቦን የፀዳ ተቋም ለመሆን ያለውን እቅድም ይፋ አድርጓል። ከዚህ ዜና በተጨማሪ
ሮቦቷ ሶፊያ ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጋር ተገናኘች
ሐምሌ ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ከሮቦት ሶፊያ ጋር ሮቦቷ ሶፊያ ከጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ጋር ዛሬ በቤተመንግሥት ተገናኘች። ለጠቅላይ ሚኒስትሩም ኢትዮጵያ በመምጣቴ በጣም ደስ ብሎኛል፤ እኔ ኢትዮጵያን የምወድ ሮቦት ነኝ ብላቸዋለች። ከመጣች አራተኛ ቀኗን ያስቆጠረችው ሶፊያ በቆይታዋ በሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የተሰናዳው ዓለም አቀፍ አይ ሲቲ ኤክስፖ ላይ ተገኝታ ከታዳሚያን ጋር ተዋውቃለች። ባለስልጣናት፣ የጃዝ ሙዚቃ አባት ሙላቱ አስታጥቄን ጨምሮ የኪነጥበብ ባለሙያዎች በተገኙበት በቶቶት የባህል አዳራሽ የዳንስ ትርዒትም አቅርባለች። ምንም እንኳን በጀርመን በርሊን ኤክስፖ ቆይታዋ የተወሰነ የአካል ክፍሏን የያዘ ሻንጣ መጥፋት አማርኛ መናገር እንዳትችል የተፈታተናት ቢሆንም በትንሹም ቢሆን ተናግራለች። ከዚህ የበለጠ አማርኛ ስለምድ እናወራለን ስትል ተናግራለች። ንግግሯ ጠቅላይ ሚንስትሩን ፈገግ ያሰኘ ነበር ። በዛሬው ዕለትም በብሔራዊ ሙዚየም ተገኝታ ድንቅነሽን እንደጎበኘች የ አይኮግ ላብስ ስራ አስኪያጅ አቶ ጌትነት አሰፋ ለቢቢሲ ገልጿል። ቢቢሲ ማስተባበያ
የአውስትራሊያ እሳት፡ በሺዎች የሚቆጠሩት እሳት ሽሽት ወደ ውሃ ዳርቻዎች ተሰደዱ
ታህሳስ በአውስትራሊያ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የተነሳውን የሰደድ እሳት ለማምለጥ ወደ ባህር ዳርቻዎች ተሰደዋል። እሳቱ ወደ የቪክቶሪያ ባህር ዳርቻ ከተማ ወደ ሆነችው ማላኮታ የተዛመተ ሲሆን ፤ ወደ መኖሪያ ቤቶችም እየገሰገሰ ነው። የአካባቢው ነዋሪዎች፤ ደም በለበሰው ሰማይ ሥር በውሃ ዳርቻዎች ላይ መጠለልና ጀልባዎች ላይ ተሳፍሮ መቆየት በጣም ፈታኝ ነው ሲሉ ያሉበትን ሁኔታ ገልፀውታል። በደቡብ ዌልስ ሌላ ሁለት ሰዎች መሞታቸውንም ባለሥልጣናት አረጋግጠዋል። እስካሁን በአገሪቷ ከተከሰተው ሰደድ እሳት ጋር ተያይዞ ሰዎች ሕይወታቸው አልፏል። በሲድኒና ሜልቦርን መካከል በርካታ በዓል ወደ ሚከበርባቸው ቦታዎች የሚወስዱ መንገዶች በእሳት አደጋው ምክንያት ተቋርጠዋል። በሁለት አውስትራሊያ ግዛቶች፤ ከደቡብ ዌልስ ባቴማስ ቤይ፤ ወደ ቪክቶሪያ ቤርንስዳሌ በ ኪሎ ሜትር በአደገኛ ሁኔታ እየተስፋፋ ነው። የአባት እና ልጅ እንደሆነ የተነገረ የሁለት ሰዎች አስክሬን በኒው ደቡባዊ ዌልስ ኮባርጎ ከተማም ተገኝቷል። የደቡብ ዌልስ ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር ጋሪይ ወርቦይስ በጣም አሳዛኝ አጋጣሚ ነው፤ እሳቱ ወደ እነርሱ ከመዛመቱ በፊት ግለሰቦቹ የሚቻላቸውን አድርገዋል ብለዋል። ባለሥልጣናት እንዳሉት በአካባቢው ሌሎች አምስት ሰዎች የደረሱበት አልታወቀም። ከእነዚህ መካከል አራቱ ከቪክቶሪያ፤ ሌላው ደግሞ ከኒው ደቡባዊ ዌልስ ነው። የቪክቶሪያ ግዛት አስተዳዳሪ ዳንኤል አንድሪውስ እንዳሉት በአካባቢው ዋና አውራ ጎዳና በመዘጋቱ፤ አገልግሎት ለተቋረጠባቸው አካባቢዎች ምግብ፣ ውሃ እና ኃይል ለማድረስ መርከብ ሊጠቀሙ እንደሚችሉ አስታውቀዋል። እነዚህ ተነጥለው ያሉ ማህበረሰቦች የባህር ኃይልን በመጠቀም መድረስ ይቻላል ሲሉም አክለዋል። ባለሥልጣናት በአብዛኛው ጎብኝዎች የሆኑና በአካባቢው ያሉ ሰዎች አሁን አካባቢውን ለቆ ለመውጣት ስለረፈደና አደገኛ ስለሚሆን ባሉበት እንዲቆዩ አሳስበዋል። እነዚህ ማህበረሰቦች በሚኖሩበት ሰሜናዊ ግዛት፤ እሳቱ በአካባቢው ባለው ሙቀት ፣ ንፋስና ደረቅ መብረቅ የአየር ጠባይ ሳቢያ እየተስፋፋ መሆኑም ተነግሯል። ከዚህ ዜና በተጨማሪ
ናሳ፡ ከአውስትራሊያ ሰደድ እሣት የመነጨው ጭስ ዓለምን ይዞራል
ጥር ይህንን ለማጋራት በ ዋትስአፕ የአሜሪካው የጠፈር ሳይንስ ተቋም ናሳ ከአውስትራሊያ ሰደድ እሣት የተነሳው ጭስ ዓለምን ዞሮ ወደ መጣበት ይመለሳል ሲል ተንብየዋል። የአውስትራሊያ ምስራቃዊ ክፍልን ለወራት ሲያቃጥል የነበረው ሰደድ እሣት ጭስ የፓሲፊክ ውቅያኖስ ጣሪያ ላይ ተንሳፎ ይገኛል። ናሳ እንደሚለው በአው ጳውያኑ አዲስ ዓመት መጀመሪያ ቀን ከአውስትራሊያ የተነሳው ጭስ የደቡብ አሜሪካ ሰማይ ላይ ታይቷል፤ በሳምንቱ ደግሞ የዓለምን ግማሽ ተንሸራሽሯል። ጭሱ ዓለምን ቢያንስ አንድ ጊዜ ሊዞራት እንደሚችል ናሳ አሳውቋል። የአውስትራሊያ ሰደድ እሣት ከ ሚሊዮን ሄክታር በላይ መሬት ያቃጠለ ሲሆን ሰዎችን ገድሏል፤ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የዱር እንሳስትም ሰለባ ሆነዋል። ሺህ ገደማ መኖሪያ ቤቶች ደግሞ ዶጋ አመድ ሆነዋል። የዘርፉ ባለሙያዎች የአውስትራሊያ ሰደድ እሣት የዓለም አየር ንብረት ለውጥ ማሳያ ነው ይላሉ። ናሳ የሰደድ እሣቱ ጭስ በጣም ከፍተኛ ከመሆኑ የተነሳ ከእሣት የሚፈጠር መብረቅ መሥራት ችሏል ይላል። ጭስ በጣም ኃያል ከመሆኑ የተነሳ ከመሬት ወደ ሰማይ ኪሎ ሜትር ርቀት ድረስ ተጉዞ ስትራቶስፌር የተሰኘው የሰማይ ክፍል ላይ መስፈር ችሏል። ተቋሙ፤ ጭሱ ወደ ሰማይ ከተመዝገዘገ በኋላ ሙቀት ወይስ ቅዝቃዜ ፈጠረ የሚለውን ለማወቅ ጥናት ላይ መሆኑንም አሳውቋል። እውን አውስትራሊያ እንዲህ እየተቃጠለች ነው የደቡብ አሜሪካ ሃገራትና የአህጉረ አውስትራሊያ አካል የሆነችው ኒው ዚላንድ በአውስትራሊያ ሰደድ እሣት ምክንያት ሰማያቸው ታፍኖ እንደነበር የሚያሳዩ ፎቶዎች እና ተንቀሳቃሽ ምስሎች የማሕበራዊ ድር አምባ ተጠቃሚያዎች አጋርተዋል። ኒው ዚላንድን ጨምሮ ሲድኒ፣ ሜልቦርን፣ ካንቤራ እና አደላይድን የመሳሰሉ ትላልቅ የአውስትራሊያ ከተሞች በሰደድ እሣቱ ምክንያት ንፁህ አየር መተንፈስ ተስኗቸው ሰንብተዋል። አውስትራሊያ አሁንም እየተቃጠለች ነው። ገደማ ጫካዎች አሁን እሣት ይዟቸዋል። ነገር ግን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየጣለ ያለው ዝናብ ሁኔታዎችን ቀዝቀዝ አድርጓቸዋል። ጭሱ ግን መጓዙን እንደሚቀጥል ናሳ አሳውቋል። አፍሪቃን ጨምሮ ሁሉንም የዓለማችን አህጉሮች ሊነካ ይችላልም ተብሏል። የአውስትራሊያን ጭስ በኢትዮጵያ ሰማይ ላይ እናየው ይሆን
አማዞን ነፍሰ ጡር ሠራተኞቹን ከሥራ በማሰናበት ተከሰሰ
ሜይ ስለ ማጋራት ተጨማሪ ያጋሩ ማጋሪያ ምረጥ አሜሪካዊቷ ትሠራበት የነበረው አማዞን ነፍሰ ጡር ነሽ ብሎ በማባረሩ ፍርድ ቤት ልትገትረው መሆኑ ተሰማ። አማዞን ባለፉት ስምንት ዓመታት ብቻ ተመሳሳይ ክሶች ሲቀርቡበት ነበር። ባለፉት ስምንት ዓመታት ተመሳሳይ ክስ ሲያቀርቡ የነበሩ ሴቶች እንደሚሉት፤ ይሠሩበት የነበረው ድርጅት ፍላጎታቸውን ሊያሟሟላቸው ፈቃደኛ አልነበረም። አማዞን በበኩሉ ምን ሲደረግ ነፍሰ ጡር የሆኑ ሠራተኞቼን አባርራለሁ ሲል ክሱን አስተባብሏል። አማዞን ሠራተኞቹን በማርገዛቸው ብቻ አባረረ የሚለው ክስ ፍፁም ውሸት ነው ሲል ለቢቢሲ ምላሽ ሰጥቷል። አክሎም ድርጅታችን ሁሉንም በእኩል የሚያይ ነው ብለዋል። ሠራተኞቻችን የሚያስፈልጋቸውን የሕክምና እገዛ የምናደርግ ሲሆን፤ ይህ ደግሞ ነፍሰ ጡር ለሆኑ እናቶችም ይሠራል። በማለት ልጅ ለወለዱ እናቶችም ሆነ አባቶች የወሊድ ፈቃድ እንደሚሰጥም ያስረዳሉ። ባለፉት ዓመታት ለቀረቡባቸውና ከሕግ ውጪ ስለፈቷቸው ጉዳዮች ግን አስተያየታቸውን ከመስጠት ተቆጥበዋል። በቅርቡ የደረሰባትን በደል ወደ ፍርድ ቤት የወሰደችው ቤቨርሊ ሮዜልስ፤ በሰኔ ወር በካሊፎርኒያ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ጉዳይዋ ይታያል ተብሏል። አማዞን ከ ሺህ በላይ ሠራተኞች ያሉት ሲሆን በገና ሰሞን ብቻ እስከ ሺህ ጊዚያዊ ሠራተኞችን ይቀጥራል። የአማዞን ሠራተኞች ድርጅታቸው ላይ ተመሳሳይ ቅሬታ ሲያቀርቡ ነበር። ቢቢሲ ያነጋገራትና ስሟ እንዳይገለፅ የጠየቀች እናት እንደተናገረችው፤ ነፍሰ ጡር በነበረች ወቅት ለአለቃዋ እርጉዝ መሆኗን ተናግራ ወደ ሌላ ክፍል እንድትዘዋወር ብትጠይቅም ሳይፈቀድለት ቀርቷል። ሥራዋ ከባድ ጋሪ መግፋት፣ ከባድ እቃ ማንሳትና ጎንበስ ቀና ማለት ስለሚበዛው ጤናዋ ላይ ችግር ገጥሟት እንደነበር አትረሳም። አማዞን ግን ማንነታቸውን በግልፅ ስላልተናገሩ ሠራተኞቹ አስተያየት ከመስጠት እንደሚቆጠብ ገልጾ፤ ነፍሰ ጡር መሆናቸውን ካሳወቁ ሠራተኞቹ ጋር በቅርበት እንደሚሠራ ተናግሯል። በእንግሊዝ የሚገኘው ጂኤምቢ የሠራተኞች ማኅበር ቃል አቀባይ የሆኑት ግለሰብ እንደሚሉት በአማዞን የሚሠሩ ነፍሰ ጡር እናቶች የሚነግሩን ለ ሰዓት ያህል ቆመው እንደሚሰሩ ነው። እንደ አማዞን ያሉ ድርጅቶች ሠራተኞቻቸውን በአግባቡ መያዝ ይጠበቅባቸዋል፤ እንደ ሮቦት ሊያሠሯቸው አይገባም ብለዋል። ተያያዥ ርዕሶች
ዞማ ቤተ መዘክር ለአዲስ አበባ በዓይነቱ ልዩ የሆነ ስፍራ
ማርች ማጋሪያ ምረጥ ዞማ ቤተ መዘክር የዛሬ ሃያ አምስት ዓመት ገደማ የተጠነሰሰው በመስከረም አሰግድ አዕምሮ ውስጥ ነበር። አሁን ዞማ የብዙዎች መዋያ፣ ነፍስ ማደሻ፣ ባህል እና ጥበብን መጠበቂያ እና ማስተዋወቂያ የሆነውም በእርሷና በባልደረባዋ ኤሊያስ ስሜ ጥረት ነው። በዞማ ግቢ እግር ሲረግጥ ከመጀምሪያው እርምጃ አንስቶ ቦታው በዓይነቱ ለየት ያለ መሆኑን አለማስተዋል ይከብዳል። እምቦጭ የጣና ቂርቆስ መነኮሳትን ከገዳሙ እያስለቀቀ ነው ቤተ መዘክሩ የተገነባው በጭቃ መሆኑ ለየት ያደርገዋል። ጭድን ከጭቃ በመቀላቀል የእንጨት ማገሮቹ ላይ እየተወረወረ ግንብ በሚሰራበት ዘዴ መሆኑን የምታስረዳው መስከረም፤ ይህን የግንባታ ዘዴ በሃገሪቱ የተለያዩ ቦታዎች ለጉብኝት በሄደችባቸው ጊዜያት ማየቷን ትናገራለች። ከታሪካዊ ግንባታዎቹ በተጨማሪ የሰው መኖሪያ ቤቶች የግንባታ ጥበብ እጅግ ያስገርሟታል። በጉብኝቷ ወቅት ባለቤቶቹን ስታናግራቸው ከቅድመ አያት እስከ ቅም ቅም አያት ድረስ ወደ ኋላ የተገነቡ በመሆናቸው አብዛኛዎቹ ቤቶቹ እንዴትም ሆነ መቼ እንደተገነቡ አያስታውሱም ትላለች። አጭር የምስል መግለጫ ኤልያስና መስከረም ከሁሉም በላይ እንድትገረም ያደረጋት የባህላዊ ግንባታ ዘይቤዎቹ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ የሆነ ትውልድ ላይ መቅረታቸው ነው። የቤቶቹ ውበት ብቻ ሳይሆን ይህን ያህል ጊዜ የተለያየ የአየር ፀባይ ተቋቁመው መቆየታቸው በጣም ያስደንቀኝ ነበር። ለዚህም ነው የግንባታውን ዓይነት ለማወቅ እጓጓ የነበረው የምትለው መስከረም፤ በማከልም ይህ የሃገር ቅርስ እየጠፋ ወይም እየተረሳ መምጣቱ ያሳሰባት እንደነበር ታስረዳለች። መስከረም እነኚህን የጥንት የግንባታ ጥበቦች ከዘመናዊ የግንባታ ዘዴዎች ጋር በማዋሃድ እንዲቆዩ ማድረግ እንደሚቻል ያላትን እምነት ሳታመነታ አካፍላናለች። ጤፍን ሰዳ የምታሳድደው ኢትዮጵያ በጣም ይቆጨኝ ነበርና የቤቶቹን የግንባታ ዘዴ ለሕዝብ የምናስተዋውቅበት አንደኛው መንገድ የእራሴን ቤት በዚያ መንገድ መሥራት አልነበረም ምክንያቱም ከጓደኞቼ ውጪ ማንም ላያየው ስለሚችል የምትለው መስከርም የግንባታ ዘይቤዎቹ በቅርስ መልኩ እንዲቆዩና ለመጪ ትውልዶች ማሳያ ብቻ ሳይሆን መማሪያም እንዲሆኑ በማሰብ ከሁለት አሥርት ዓመታት ጥረት በኋላ በዞማ ቤተ መዘክር መልክ ለሕዝብ መቅረብ መቻላቸውን አጫውታናለች። የዞማ አፀድ ከጭቃ የተገነቡትን ግድግዳዎች ተከትሎ በአንድ ጊዜ ለዓይን መለየት እስኪያቅቱ ድረስ የዛፍና የአበቦች ዓይነቶች በብዛት ይታያሉ። የአባቷ እርሻ ላይ ያደገችው መስከረም፤ አስተዳደጓን መለስ ብላ ስታስታውስ ከእንሰሳትና ከተለያዩ ተክሎች ጋር እንደነበር ትናገራለች። የሥራ ባልደረባዋ ኤሊያስን በተመለከተም እርሱም ቢሆን ከልጅነቱ ጀምሮ ለዕፅዋት ልዩ ቦታ ነበረው። እስካሁን በሄደበት ሁሉ ባለው ቦታ ላይ ትንሽም ነገር ቢሆን ይተክላል ትላለች። ሁለቱም ለዕፅዋት ካላቸው ፍቅር ባሻገር ዞማን በተለያዩ ዕፀዋት መሸፈንና ለዕይታ የሚማርኩ ብቻ ሳይሆኑ ታይተው የማይታውቁ ለብዙ የጤና እክሎች ጠቃሚ ሊሆኑ ለሚችሉ ተክሎች ቦታ እንዲሰጡ የገፋፋቸው ሌላ ምክንያት እንዳለ ትናገራለች። ካናዳን በጥበብ ሥራው ያስዋበው ኢትዮጵያዊ ኢትዮጵያ ውስጥ ብዙ ቅመማ ቅመሞች፣ ዛፎች፣ ተክሎችና ለመድሃኒትነት የሚጠቅሙ ብዙ እፆች እየጠፉ ነው ስለዚህም በዋነኝነት የዞማ የተክል ስፍራ ለመጽሐፍትና ለሥዕል ብቻ ሳይሆን የእፅዋትም ቤተ መዘክር እንዲሆን ታስቦ መቋቋሙን አጫውታናለች። ከሃገሪቱ በመጥፋት ላይ ያሉ ዛፎችና ተክሎችን መጎብኘት የሚቻልበት ስፍራ በመሆን የኢትዮጵያን የዕፅዋት ሃብት ለመጪው ትውልድ ማስተላለፊያ መንገድ ነውም ትላለች። ግቢው ውስጥ ያሉት ዕፀዋት በተተከሉበት ወቅት እነሱን ከመጠበቅ በላይ በጥበብ እንዴት አሳምሮ መትከል ይቻላል የሚለው ላይ በማተኮር ለዓይን ማራኪ በሚሆን መልኩ የተተከሉ ናቸው። ይህን በማድረጋቸውም ብዙ አዕዋፋትና ቢራቢሮዎች በዓይነት በዓይነት ዞማን ማረፊያቸው፤ እንደውም ቤታቸው እንዳደረጉት በደስታ ትናገራለች። ኢትዮጵያዊ ታሪኮችን ወደ ዓለም አቀፍ የፊልም መድረክ ማምጣት ፈታኝ ነው ዘረሰናይ መሐሪ ምንም እንኳን ዞማ ያረፈበት ግቢ ሰፊ ቢሆንም ወንዝ ዳር መገኘቱ አትክልቶቹ በሙሉ በቂ ውሃ እንዲያገኙ እንደረዳቸው ነግራናለች። የወንዝ ተዳፋት ላይ የሚገኘው የዞማ ግቢ የሰፈሩን ቆሻሻ በሙሉ ይዞ ወደ በግቢው ወዳለው የፍሳሽ መውረጃ መቀላቀሉ ትንሽ አስቸግሯቸው እንደነበር ታስታውሳለች። ለዚህ መፍትሔ ሊሆን የሚችለው ደግሞ ወደ ዞማ ግቢ የሚገባውን ውሃ በማጣራትና በማፅዳት ወደ ወንዙ ሲቀላቀል ለመጠጣት እራሱ የሚሆን ውሃ ማቅረብ ነው። ቢያንስ ከእኛ ግቢ የሚወጣው ውሃ ንፁህ ከሆነ ለጎረቤቶቻችንና ለሌሎቹ ምሳሌ በመሆን ሁሉንም ሰው ማበረታታት ይችላል ትላለች። መዋለ ሕፃናት የሆነው ቤተ መዘክር በዕፀዋት ካጌተው አፀደ ወረድ ሲባል ወደ ወንዙ ሲጠጉ ደግሞ አነስ ያለ እርሻ፣ የዶሮ ማርቢያ፣ የፍየልና የላሞች ማደሪያም ይታያል። በቤተ መዘክሩ እነዚህ የግብርና ግብአቶች ለምን እንዳስፈለጉ መስከረም ስትናገር ዋናው ለልጆቹ ተብሎ ነው በማለት ታስረዳለች። በቤተ መዘክሩ ውስጥ በከፈቱት መዋለ ሕፃናት ለሚማሩት ተማሪዎች የሆነበትም ምክንያት ልጆቹ ዶሮም ሆነ እንቁላል መገኛቸው ከመደብር እንዳልሆነ እንዲያውቁ መሆኑን ትናገራለች። አዝማሪዎቻችን የሙዚቃ ሳይንቲስቶች ናቸው ዶሮዎቹን መጥተው ይንከባከባሉ፣ ጫጩት ሲወለድ ያያሉ፣ ጫጩት ይንከባከባሉ፣ እንቁላል ይለቅማሉ እንደውም ስም አውጥተውላቸው እያንዳንዳቸውን ይለይዋቸዋል። ይህ ደግሞ ዶሮና እንቁላል ከየት እንደሚመጡ ከማወቃቸውም በተጨማሪ ለዶሮዎቹ ፍቅር እንዲያዳብሩ ያደርጋል ትላለች። ልክ እንደ ዶሮዎቹ ላሞችና ፍየሎች በዞማ ግቢ ውስጥ ስላሉ ከተለያዩ እንስሳት ጋር ጥሩ ግንኙነት ከመፍጠሩም ባሻገር ተጨባጭና ተፈጥሯዊ መማሪያ እንደሚሆንላቸው ገልጻለች። የቀድሞዋ ሶቭየት ህብረት ትውስታዎች በኢትዮጵያውያን ዓይን በተጨማሪም ልጆቹ ምግብ ማብሰልም ጭምር ይማራሉ የምትለው መስከረም፤ ህጻናቱ እግረ መንገዳቸውን ደግሞ ሂሳብ በሚታዩ ነገሮች እንዲማሩ በማሰብ ለምሳሌ ድንች ተሰጥቷቸው ለሁለት ቢከፈል ስንት ይሆናል ሲባሉ በእራሳቸው እየቆጠሩ ሂሳብ ተማሩ ማለት ነው ትላለች። ዞማ ቤተ መዘክር፣ የሥነ ሥዕል ዓውደ ርዕይ ማሳያ፣ የተንቀሳቃሽ ምስል ማሳያ፣ መጽሕፍት ማንበቢያ፣ ሱቅ፣ ምግብ ቤት፣ የአፀደ ስፍራ፣ አፀደ ሕፃናት እና እርሻም ጭምር ነው። ተያያዥ ርዕሶች
በአማዞን ሥራ ቀጣሪና አባራሪ እየሆነ የመጣው ሮቦት
ሜይ አጭር የምስል መግለጫ ኮምፒውተር የቀን በቀን ሥራዎትን ሲከታተል ምን ይሰማዎታል ሮቦቶች የሰዎችን ሥራ ይነጥቃሉ ተብሎ መወራት ከጀመረ ከራረመ። አሁን ተራ ወዛደር ብቻ ሳእሆን የሰው ኃእል አስተዳደር ሆኖም መግቢኣ መውጫ ሰዓትን ይቆጣጠራል፤ በሥራ ላይ ያለዎትን አፈፃፀም ይከታተላል። ይሾማል ይሸልማል፤ ካልሆነ ያባርራል። ይህ ጉዳይ ተግባራዊ ጉዳዩ መገናኛ ብዙኃን ጆሮ የደረሰው ደግሞ አማዞን ውስጥ ነው። ግዙፉ የአማዞን ድርጅት ውስጥ ካሰቡት በተለየ ሁኔታ ሠራተኞችን በማባረር የሰው ሰራሽ ቴክኖሎጂ ስራ ላይ ውሏል ይላል ዘገባው። ዘ ቨርጅ የተሰኘው የቴክኖሎጂ ዘጋቢ እንዳስነበበው አማዞን ውስጥ ኮምፒውተሮች የሰራተኞችን ውጤታማነት እየመዘኑ እስከማባረር ደርሰዋል። አማዞን በዝቅተኛ ክፍያና ከባድ የስራ ጫና ምክንያት በተደጋጋሚ ከሠራተኞች ቅሬታ የቀረበበት ሲሆን አንድ ሠራተኛ ድርጅቱ የሚመለከተን እንደ ሮቦት ነው ሲል ምሬቱን ገልጿል። ዘ ቨርጅ እንደዘገበው ብዙ ሠራተኞች በየዓመቱ እቃዎችን በፍጥነት ማንቀሳቀስ ባለመቻላቸው ከሥራቸው ይባረራሉ። ይህ ሁኔታ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ የሰዎች አለቃ እየሆነ እንደመጣ ያሳያል የሚሉ የዘርፉ ባለሙያዎች አሉ። ቴክኖሎጂው የሰዎችን ውጤታማነት ተከታትሎና መዝኖ ማስጠንቀቂያ መስጠት እስከመቻል ደርሷል። በሂደቱም ሁለተኛ እድል መጠየቅ እንደሚቻል ዘ ቨርጅ በዘገባው ላይ አመልክቷል። አጭር የምስል መግለጫ ወደፊት ሰው ሰራሽ ቴክኖሎጂ ሠራተኞችን ያባርር ይሆን በሮቦቶች እንደ ሮቦት መታየት በንግድ ሥራዎች ላይ የህግ ባለሙያ የሆኑት ስታንሲ ሚቼል አማዞን ውስጥ የሚሠሩ ሰዎች በሮቦቶች እንደ ሮቦት ነው የሚታዩት ይላሉ። ሠራተኞቹ እንዲያሳኩ የሚጠበቅባቸው የሥራ መጠንም ሆነ የውጤታማነት መለኪያዎቹ በውል አይታወቅም ሲሉም ያክላሉ። አማዞን ለቢቢሲ በሰጠው መግለጫ ሠራተኞች በኮምፒውር ውሳኔ ይባረራሉ የሚባለው ወሬ ፍፁም ውሸት ነው። እንደማንኛውም ድርጅት ለሠራተኞቻችን የሥራ ውጤታማነት መመዘኛ መንገድ ያለን ሲሆን ማንንም ግን ራሳቸውን እንዲያሻሽሉ እገዛ ሳናደርግ አናባርርም። በፍጥነት የሚያድግ ድርጅት ስላለን በዘላቂ የሙያ ድጋፍ የሠራተኞቻችንን ብቃት ለማሻሻል እንተጋለን ብሏል። ድርጅቱ ምን ያህል በኮምፒውተር ቴክኖሎጂ እንደተደገፈና ሠራተኞችን ለማባረር እየተጠቀመ እንደሆነ በግልፅ አልገለፀም። አማዞን ከአንድ ሳምንት በፊት ለደንበኞቹ ዕቃዎችን ያሉበት ድረስ ለማድረስ የሚወስድበትን ጊዜ ለመቀነስ ቃል የገባ ሲሆን ለዚህ መስዋትነት የሚከፍሉት ሠራተኞቹ ይሆኑ ሮቦቶች ግልፅ ያለ ነገር የለም። አጭር የምስል መግለጫ በሰው ሰራሽ ቴክኖሎጂ መከታተልና ማባረር ሠራተኞች ላይ ጫና ይሆረው ይሆን የወደፊቱ የሥራ ሁኔታ አማዞን ሠራተኞችን በሰው ሰራሽ ቴክኖሎጂ ውሳኔ ለማባረር የመጀመሪያው አይደለም፤ የመጨረሻውም አይሆንም። ታዲያ ይህ ለወደፊቱ የሥራ ሂደት ምን ያስከትላል ድርጅቶች ሠራተኞቻቸውን ለመቆጣጠርና ውጤታማነታቸውን ለመመዘን የሰው ሰራሽ ቴክኖሎጂ ለዓመታት ሲጠቀሙ ቆይተዋል። ይህንም ተከትሎ ብዙ ጥያቄዎች ይነሳሉ። ሠራተኞችን በመመዘን ምን ያህል ውጤታማ ነው ሠራተኞች ለሚሰሩበት ድርጅት ያላቸውን አስተያየት እንዴት ይቀይራል ቴክኖሎጂው በውሳኔው የሰው ድጋፍ ያስፈልገው ይሆን የዓለማችን ቱጃር ቢሊየን ዶላር ለድሆች ሊለግሱ ነው ዘ ቨርጅ ባወጣው ዘገባ በአማዞን ሠራተኞች በየጊዜው በሚሻሻሉ የሥራ መስፈርት መለኪያዎች ይመዘናሉ። አንድ የውጤታማነት መመዘኛ ወጥቶ በመቶ የሚሆኑት ሠራተኞች ግቡን ከመቱ በኋላ መመዘኛው ይሻሻላል ይላል። ይህንም ተከትሎ የተሻሻለውን የሥራ መመዘኛ ማሟላት ያልቻሉ ሠራተኞች ሊባረሩ ይችላሉ። ስታንሲ ሥራህን ለማትረፍ ሁሌም ሩጫ ነው። አንዴ በጣም ውጤታማው ሠራተኛ ልትሆን ትችላለህ ግን እሱ ምንም ፋእዳ የለውም ይላል። አጭር የምስል መግለጫ የሰው ሰራሽ ቴክኖሎጂ ሰራተኖች ላይና ድርጅቶች ላይ ከፍተኛ ጥያቄ እያስነሳ ነው ሠራተኞች ላይ ምን ጫና ሊኖረው ይችላል ዴቪድ ዲቪዛ ድርጅቶች ሠራተኞችን እንደ መቅጠርና ማባረር የመሳሰሉ መሠረታዊ የሃላፊነት ቦታዎችን በሰው ሰራሽ ቴክኖሎጂዎች ከመተካታቸው በፊት በደንብ ጥናት እንዲያደርጉ ያሳስባል። አንዳንድ ሥራዎች በቴክኖሎጂ መሠራት መቻላቸው ብቻ እንዲቀየሩ አያደርጋቸውም። በቴክኖሎጂ ስለተሰሩም የተሻለ ውጤታማ ናቸው ለማለት ያስቸግራል። ሠራተኞች ሊከበሩ ይገባል፤ የሚገባቸውንም ክብር በኮድ በተደገፈ ቴክኖሎጂ ለመስጠት ያስቸግራል ይላል። እ ኤ አ ዲአሎ ከስራው በሃላፊው ሳይሆን በኮምፒውተር ትዕዛዝ ነበር የተባረረው። ለቢቢሲ እንደተናገረው ሃላፊው ስለመባረሩ ምንም ማድረግ አልቻለም ነበር። ዲአሎ የእርሱ አጋጣሚ ለሌሎች ተቋማት ምሳሌ እንዲሆን ተስፋ ያደርጋል አለበለዚያ ግን ሠራተኞች ላይ ከፍተኛ ጫና ያሳድራል ይላል። ተያያዥ ርዕሶች
የ ዓመቷ ግሬታ ተንበርግና ፕሬዝዳንት ትራምፕ እልህ ተጋብተዋል
ዲሴምበር ማጋሪያ ምረጥ የዓየር ንብረት ለውጥ ተሟጋቿ ግሬታ ተንበርግ እና የዓለም ሀገራት መሪዎች እልህ ሲጋቡ የመጀመሪያቸው አይደለም። ግሬታ ከብራዚሉ ፕሬዝዳንት እስከ አሜሪካው ትራምፕ ድረስ ያላናደደችው የለም። ፕሬዝዳንት ትራምፕ ግሬታ በታይም መጽሔት የ ዓ ም የዓመቱ ሰው የሚለውን ስያሜ በማግኘቷ ብስጭት ብለዋል። ብስጭታቸውን ለመግለጽም ወደ ትዊተር ገጻቸው አምርተው አሸሙረዋል። ፕሬዝዳንት ትራምፕ በትዊተር ገጻቸው ላይ ግሬታን ጠቅሰው ንዴቷን የመቆጣጠር ችግር አለባት ሲሉ መልዕክት ካስቀመጡ በኋላ ቀጥለውም እናም ልክ እንደ ቀድሞ ጊዜ ሁሉ ከጓደኛዋ ጋር ወደ ሲኒማ ቤት መሄድ አለባት ብለዋል። ከዚያም ግሬታ ዘና በይ ዘና ብለዋል። የተመረጥኩት በኖቤል ሽልማት ኮሚቴው ነው ቤቲ ጂ ደግሞ ለትዊተር ማን ይሰንፋል ይመስላል የግሬታ መልስ። ሞባይሏን አንስታ የትዊተር ገጿን በመክፈት ትራምፕን ተቀበል ብላለች። አንዲት ታዳጊ ንዴቷን ለመቆጣጠር እየሰራች ነው። በአሁኑ ሰዓት የቆየ ፊልም ከጓደኛዋ ጋር እያየች ትገኛለች ስትል የመልስ ምት አስፍራለች። የ ዓመቷ ስውዲናዊ የዓለም የአየር ጠባይ ለውጥን በመቃወም የሚካሄደውን ዘመቻ ከመራች በኋላ በታይም መጽሔት የዓመቱ ሰው የተባለችው ረቡዕ ዕለት ነበር። ግሬታ የፕሬዝዳንት ትራምፕንና የሌሎች ፕሬዝዳንቶች ትችት ለመመከት የትዊተር መልዕክቷን ስታሰፍር ይህ የመጀመሪያዋ አይደለም። ሐሙስ ዕለት ግሬታ ትዊተር ገጿ ላይ የሚል የፖርቹጋል ቃል አስፍራ ነበር። ይህ ቃል ወዙ በተመጠጠ ትርጉም ሁሉን ለኔ ባይ ማለት ነው፤ ወይንም በሰው ገንዘብ የሚያለቅስ ህፃን በሉት። ይህንን ቃል ያሰፈረችው ታዲያ ከብራዚሉ ፕሬዛዳንት ወስዳ ነው። የብራዚሉ ፕሬዝዳንት ቦልሶናሮ ግሬታ በብራዚላ ቀደምት ሕዝቦች ላይ አስተያየቷን ከሰጠች በኋላ ግሬታ ኢንዲያናዎች አማዞንን ጥቅጥቅ ደን ከእሳት ለማዳን ሲታገሉ ተሰውተዋል በማለቷ የመገናኛ ብዙኀን ለዚህች ትንሽ ሁሉን ለኔ ባይ ለሆነች ልጅ ትኩረት መስጠታቸው ይገርማል ብለዋል ነበር ለጋዜጠኞች። ግሬታ የትዊተር ጦርነቱ ላይ በጥቅምት ወርም ተገኝታ ደግ ግን በቂ መረጃ የሌላት ታዳጊ የሚል መልዕክት አስፍራ ነበር። ይህ ደግሞ የሞስኮው ፕሬዝዳንት ፑቲን በሀገራቸው በተካሄደው ጉባኤ ላይ እርሷን የገለፁበት ነበር። መስከረም ላይ ፕሬዝዳንት ትራምፕ በተባበሩት መንግሥታት ጉባዔ ላይ ተቆጥታ ስትናገር የሚያሳየውን ቪዲዮ ለጥፈው ወደፊት ብሩህ እና መልካም ጊዜን የምትጠብቅ ደስተኛ ታዳጊ ትመስላለች ብለው ተሳልቀዋል። እርሷም ማን ከማን ያንሳል በሚል ወደፊት ብሩህ ጊዜን የምትጠብቅ ደስተኛ ታዳጊ የሚል መልዕክትን በትዊተሯ ላይ አስፍራለች። ተያያዥ ርዕሶች
የሰዎችን ማንነት የሚለየው ቴክኖሎጂ እያከራከረ ነው
ሜይ ማጋሪያ ምረጥ በአንድ ምስል ወይም ቪድዮ ላይ ያሉ ሰዎችን ማንነት የሚለየው የ ፌስ ሪኮግኒሽን ቴክኖሎጂ አሁንም እያከራከረ ነው። አማዞን ሪኮግኒሽን በሚል ስያሜ የሠራው የ ፌስ ሪኮግኒሽን ቴክኖሎጂ ለአሜሪካ ፖሊሶች መሸጥ አለበት ወይስ የለበትም የሚለው ጉዳይ የአማዞን ባለድርሻዎች መካከል አለመግባባት ፈጥሯል። ባለድርሻዎቹ በአማዞን ዓመታዊው ጉባኤ ላይ ምርጫ በማድረግ ውሳኔ እንደሚያሳልፉም ይጠበቃል። ባለድርሻዎቹ፤ አማዞን ሪኮግኒሽን ን ለመንግሥት ተቋማት መሸጥ አለበት ቴክኖሎጂው የሰዎችን ሰብአዊ መብት ስላለመጋፋቱ በገለልተኛ ወገን ይጠና የሚሉ ሁለት ጉዳዮች ላይ ምርጫ ያደርጋሉ። አማዞን ምርጫው እንዳይካሄድ ለማድረግ ቢሞክርም የማስቆም መብት ስለሌለው አልተሳካለትም። ሜሪ ቤት ጋልጋር የተባሉ ባለሙያ ለቢቢሲ፤ ሪኮግኒሽን ለመንግሥት ተቋሞች መስጠት የሚያስከትለው ተጽዕኖ ሳይጠና እንዳይሸጥ እንፈልጋለን። ውሳኔውን ለማሳለፍም ባለሀብቶች እንደሚያግዙን እናምናለን ብለዋል። ቴክኖሎጂው መቶ በመቶ ትክክለኛ መረጃ እንደማይሰጥ ጠቅሰው፤ ጥቅም ላይ ሲውል የሰዎችን መብት ተጋፍቶ እንደሚሰልል ተናግረዋል። ሰዎች፣ ፖሊሶች እያንዳንዱን እንቅስቃሴያቸውን እየተመለከቱና እየተከታሏቸው እንደሆነ ከተሰማቸው በነጻነት አይንቀሳቀሱም ብለዋል። አማዞን በበኩሉ ሪኮግኒሽን ያለአግባብ ጥቅም ላይ ውሏል የሚል ሪፖርት ቀርቦ ስለማያውቅ ባለድርሻዎች እንዲደግፉት ጠይቋል። ድርጅቱ በመግለጫው እንዳሳወቀው፤ ቴክኖሎጂው ወንጀለኞች በቁጥጥር ሥር እንዲውሉ ያግዛል። የጠፉ ሰዎች እንዲገኙ ይረዳል። ወንጀል መከላከልም ይቻላል። ያለአግባብ ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል ብሎ አዲስ ቴክኖሎጂ ማጣጣል ተገቢ አይደለም ተብሏል። አፕል ቲቪ ጀመረ ወደ ሚሊየን የሚጠጉ ሰዎች መረጃ ያለው ቴክኖሎጂው፤ በምስልና ቪድዮ ላይ የታየ ሰውን ማንነት ለማወቅ ያስችላል። የሰዎችን ጾታ ይለያል። ምስል ላይ ያለ ጽሁፍ እንዲተነተንም መረጃ ያቀብላል። ሆኖም በኤም አይ ቲና ዩኒቨርስቲ ኦፍ ቶሮንቶ የተሠሩ ጥናቶች፤ ቴክኖሎጂው ሰዎችን በጾታቸውና በቆዳ ቀለማቸው የሚያገል መሆኑን ይጠቁማሉ። ቴክኖሎጂው የነጭ ወንዶችን ማንነት በቀላሉ ለማወቅ ቢረዳም ስለጥቁር ሴቶች ትክክለኛ መረጃ አይሰጥም። አማዞን እነዚህ ጥናቶች የተሠሩት ቀድሞ በነበረው ቴክኖሎጂ እንደሆነና አሁን መሻሻሉን ይገልጻል። ቢሆንም የሰብአዊ መብት ተሟጋቾችና የአማዞን ሠራተኞችም ቴክኖሎጂውን ይቃወማሉ። ተያያዥ ርዕሶች
የአማዞን ባለቤት፤ ጄፍ ቤዞስ ቢሊየኖች ከፍሎ ትዳሩን ለማፍረስ ተስማማ
ኤፕረል ማጋሪያ ምረጥ የአለማችን ቀንደኛ ሃብታም ጄፍ ቤዞስ እና ባለቤቱ ማክኬንዚ ትዳራቸውን ለማፍረስ ተስማሙ። ፍቺው ግን እንዲሁ በባዶ እጅ አጨብጭበው የሚወጡበት አልሆነም። ባለቤቱ የድርሻዋ ነው የተባለውን ቢሊየን ዶላር ታገኛለች። ቢሊዮን ዶላር ድርሻዋን የምትቀበለው ማክኬንዚን ከዓለማችን ሃብታም ሴቶች ዝርዝር ውስጥ ያካትታታል። ይህ ብቻ ሳይሆን ባለቤቷ ከዛሬ አመት በፊት ከመሰረትውና በአለማችን ቁጥር አንድ ከሆነው የኢንተርኔት የችርቻሮ ግብይት ድርጅት አማዞን የአራት በመቶ ድርሻ ይኖራታል። በምትኩ ዋሽንግተን ፖስት ላይ ያላትን እና የሕዋ ላይ ጎዞ ከሚያደርገው ኩባንያው ላይ ያላትን ድርሻ ትተዋለች። ከዚህ ቀደም ትዳሩን ለማፍረስ ለአጋሩ ውድ ክፍያ የፈፀመው የኪነጥበብ ስራዎችን በማሻሻጥ የሚታወቀው አሌክ ዋይልደንአንስታይን የነበረ ሲሆን እርሱም የ ቢሊየን ዶላር ክፍያ ፈፅሟል። ጄፍ ቤዞስ ፍቺውን ለህዝብ ይፋ ያደረገው በቲውተር ገፁ ላይ ሲሆን ጉዳዩም በመስማማት መከናወኑን ጠቅሷል።
እነመታገስ በአጋጣሚ በበጎ ፈቃድ የጀመሩት የጽዳት ዘመቻ አንድ ዓመት አልፎታል።
በባህር ዳር ከተማ አንድ የስዕል አውደ ርዕይ ይዘጋጃል። ዝግጅቱ በታሰበው መንገድ ተጀምሮ በስኬት ወደ መጠናቀቁ ይቃረባል። የመዝጊያ ሥነ ሥርዓቱ ግን በተለመደው መንገድ እንዲሆን አልተፈለገም። ሃሳቡ ከአንድ ዓመት በፊት የስዕል አውደ ርዕይ መጨረሻ ላይ ጣናን እናጽዳ ተብሎ ተጀመር ሲል በወቅቱ የነበረውን መታገስ ያስታውሳል። በዚህም ወደ ጣና ሐይቅ በማቅናት ያለውን ቆሻሻ አጽድተው የስዕል አውደ ርዕዩ ተጠናቋል። ጥቂት የነበሩት ተሳታፊዎች ጣናን በማጽዳት የተጀመረው ሥራ እንዲቋረጥ አልፈለጉም። በየሳምንቱ ቅዳሜ በመገናኘት በተለያዩ የባህር ዳር አካባቢዎች በመንቀሳቀስ ማጽዳት ጀመሩ። በዚህም ሳምንታዊው የበጎ ፈቃድ የጽዳት ሥራ ተጀመረ። ባህር ዳር ከተማ ውብ ነች፤ ጽዱ ነች። አሁን ግን እንደቀድሞው አይደለችም። ጣንን በጀልባ እየቀዘፍን እና እየዋኘን ብዙ ላስቲኮች እና ቆሻሻዎችን እያወጣን ነው። ቆሻሻዎች አንድ ላይ በመሰብሰብ በመኪና ጭነን እያስወገድን ነው። በገንዘብ ሊተመን የማይችል ብዙ ቆሻሻ በበጎ ፈቃደኞች አማካይነት እየተነሳ ነው። ቁጥራችንም እየጨመረ ነው። ስንጀምር አካባቢ ነበርን። አሁን ከፍተኛ ነው ይላል መታገስ። አዲሱ የታይፎይድ ክትባት ውጤታማ ነው ተባለ የጽዳት ዘመቻውን ለመለየት እንዲያመቻቸው አንድ ሁለት ሦስት እያሉ ቅዳሜዎችን በመሰየም ኛውን ቅዳሜ አልፈዋል። በጣም የቆሸሹ ስፍራዎችን አጽድተዋል። የእምቦጭ አረምን ነቅለዋል። ወጣቶቹ በብዛት የጽዳት ሥራውን የሚያከናውኑት በፋሲሎ ክፍለ ከተማ ነው። ወይዘሮ አሻገሩ አሊ የክፍለ ከተማው የአካበቢ ጥበቃ፣ ጽዳትና ውበት ተጠሪ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ናቸው። ኃላፊዋ የወጣቶቹን ተግባር በርካታ ለውጥ ያመጣ ነው ሲሉ ይገልጹታል። የከተማው የበጎ ፈቃደኞች ቡድን በብዛት የሚሠሩት በፋሲሎ ክፍለ ከተማ ነው። ይህ ደግሞ ከተማዋ እምብርት ነው ነው ይላሉ። ብዙ ለውጥ አምጥተናል የምትለው በጎ ፍቃደኛዋ አሳሱ ነች። አሳሱ አካባቢያቸውን እናጸዳ እና ትምህርት እንሰጣቸዋለን። አብዛኛዎቹ ደግሞ ተግበራዊ ያደርጉታል ስትል የበጎ ፍቃድ ሥራቸው ውጤታማነትን ታስረዳለች። የባህር ዳር ከተማ ወጣቶች በጽዳት ላይ አቶ ዘላለም ጌታሁን የባህር ዳር ከተማ የአካባቢ ጥበቃ፣ ጽዳት እና ውበት ጽህፈት ቤት ኃላፊ ናቸው። ወጣቶቹ በጣም የሚያስደስት ሥራ እያከናወኑ ናቸው። ትልቅ እና ለሌሎች ክፍለ ከተሞችም አርዓያ የሚሆን ሥራ እያከናወኑ ነው የሚሉት አቶ ዘላለም ይህንን የወጣቶቹን ተግባር በመመልከት ሌሎች የከተማዋ ወጣቶችም አካባቢያቸውን በየሳምንቱ ማጽዳት መጀመራቸውን ያነሳሉ። የወጣቶቹ አስተባበሪ ለሆነው መታገስ ይህ ብቻ በቂ አይደልም። እኛ በከተማው ያለውን ቆሻሻ አጽድተን እንጨርሳለን ማለት አይደለም። ዋናው የእኛ ሥራ አዕምሮ ላይ መሥራት ነው። ሁሉም ቤቱን እና አካባቢውን ቢያጸዳ ከተማዋ ጽዱ ትሆናለች። ይላል። መታገስ ሰው በቆሻሻ ላይ ያለውን አመለካከት እስኪቀይር ድረስ፤ ቆሻሻን በአግባቡ እስክያሶግድ ድረስ ማጽዳታችንን እንቀጥላለን ሲልም ያክላል። የት ይቀርልሃል አፈር ድሜ ትበላለህ ጋሽ አበራ ሞላ አቶ መስፍን አድማሱ የባህር ዳር ከተማ ነዋሪ ሲሆኑ ይህንን የጽዳት ዘመቻ ዓላማ ተቀብለው ከወጣቶቹ ጋር በየሳምንቱ በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ። ጅምሩን ቢያደንቁም ከከተማው የሚወጣው ቆሻሻ ብዙ ነው። የሚያጸዳው ግን አነስተኛ ነው ሲሉ ስጋታቸውን ያስቀምጣሉ። ይህንን የአቶ መስፍንን ስጋት ወይዘሮ አሻገሩ ይጋሩታል። አሁንም የማህበረሰቡ የአመለካካት ችግር አለ። በተወሰኑ ክፍለ ከተሞች የሚያጸዱ ቢኖሩም ግንዛቤው አልተቀየረም ይላሉ። ለበጎ ፈቃደኞቹ ከመንግስት እና ከግል ድርጅቶች ለጽዳት የሚያገለግሉ አነስተኛ የቁሳቁስ ድጋፍ ቢደረግም ይህ በቂ አይደለም ሲሉ ይገልጻሉ። የአካባቢ ጥበቃ እና የጽዳትና ውበት አብረውን ሊሠሩ ይገባል የሚለው ደግሞ መታገስ ነው። ጣና እየቆሸሸ ነው። ቆሻሻ ወደ ጣና እየተጣለ ነው። ሆቴሎችም ቆሻሻቸውን ወደ ጣና እየጣሉ ነው። ሌላ የቆሻሻ መጣያ ቦታ እስኪያዘጋጁ መጠየቃችንን እንጥላለን ይላል። በጣም ደስ የሚለኝ ያለማንም አስገዳጅነት ያለክፍያ መሥራቴ ነው። ጊዜዬን እና ጉልበቴን ሳፈስ ደስ እያለኝ ነው። በበጎ ፈቃድ መሥራት ደስ ይላል ትላለች አሳሱ። በህይወት እስካለሁ እና ባህር ዳር ጽዱ እስካልሆነች ድረስ ሥራውን እቀጥላለሁ። ሌላም ቦታ ብሄድ መሳተፌን አላቆምም ትላለች። ቅዳሜ ቅዳሜ ሁሌም እዚህች ከተማ እስካለሁ ድረስ ሌላ ፕሮግራም አይኖረኝም የሚለው ደግሞ መታገስ ነው። ትልቅ ነገር ለከተማዬ እንዳበረከትኩ ነው የሚሰማኝ። በጣም ደስ ብሎኝ ነው የምሄደው ሲል ያጠቃልላል። ከዚህ ዜና በተጨማሪ
የሳዑዲ ሮቦት ከሴቶች በላይ ዜግነታዊ መብት ይኖራት ይሆን
ኦክተውበር አጭር የምስል መግለጫ ለመጀመሪያ ጊዜ ዜግነት የተሰጣት የመጀመሪያዋ ሮቦት ሶፊያ ሮቦቷ ሶፊያን ተዋወቁዋት ለመጀመሪያ ጊዜ ሰኞ ቀን በሳዑዲ አረቢያዋ ከተማ ሪያድ በአደባባይ ላይ ታይታለች። በአጭር ጊዜ ታዋቂነትን ማትረፍ የቻለችው ሶፊያ ታሪካዊ በሚባል ሁኔታ ከሁለት ቀናት በፊት የሳዑዲ ዜግነት ተሰጥቷታል፤ ይህም የሆነው ከመቶዎች በላይ ልዑካን በተገኙበት ፊውቸር ኢንቨስትመንት ኢንሺየቲቭ ስብሰባ ላይ ነው። የሶፊያ ፎቶዎችና ቪዲዮዎች በተለያዩ ድረ ገፆች በወጡበት ወቅት በብዙዎች ዘንድ እንዴት ነው አንዲት ሮቦት ከሴቶች በላይ የበለጠ መብት ማግኘት የቻለችው የሚል ጥያቄን አጭሯል። በዚህ ታሪካዊ ቀን በዓለም የመጀመሪያዋ ሮቦት የዜግነት ዕውቅና ተሰጥቷታል። እባካችሁ አዲሷን የሳዑዲ ዜጋን ሶፊያን እንቀበላት የሚል ንግግር በስብሰባውም ተሰምቷል። ሶፊያን የፈጠራት ሃንሰን ሮቦቲክስ የሚባል የሆንግ ኮንግ ኩባንያ ነው። በስብሰባውም ወቅት የሳዑዲ ሴቶች ግዴታ የሆነባቸውን አባያ ሳትለብስ በእንግሊዝኛ ቋንቋ ንግግር አድርጋለች። ለዚህ ለየት ላለ ማዕረግ በመብቃቴ ክብር ተሰምቶኛል። ሮቦት የዜግነት ዕውቅና ስታገኝ የመጀመሪያዋ መሆኑም ታሪካዊ ያደርገዋል ብላለች ሳዑዲዎች ይህንን ዜና በተቀላቀለ መልኩ ሲሆን የተቀበሉት የሳዑዲ ዜግነት ያገኘች ሮቦት በሚል መልዕክትም ዜናው ከተሰማበት ሰዓት ውስጥ ከ ሺዎች በላይ በተለያዩ ማህበራዊ ድረ ገፅ አጋርተውታል። በተቃራኒው ጉዳዩን በስላቅ የወሰዱትም አሉ። ሶፊያ ጠባቂ አትፈልግም በሚል መልዕክት ከ ሺዎች በላይ በተለያዩ ማህበራዊ ድረ ገፅ ፅፈዋል። በሳዑዲ ስርአት መሰረት አንዲት ሴት ብቻዋን መንቀሳቀስ የማይፈቀድላት ሲሆን፤ ከቅርብ ቤተሰብ ወይም አንድ ወንድ ጠባቂ ያስፈልጋታል ይላል። ሶፊያ ጠባቂ የላትም፤ ፊቷን አትሸፋፈንም ። ለምን ይሆን በሚል ጥያቄ ትዊተር ድረ ገፅ ላይ አስተያየታቸውን የሰጡ አልታጡም ሌላኛው አስተያት ሰጪ ደግሞ ሶፊያን ጥቁር ቡርቃ ካለበሳት በኋላ፤ ሶፊያ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ይህንን ነው የምትመስለው ብሏል። ሶፊያን ከሳዑዲ ሴቶች ከማወዳደር በተጨማሪ ዜግነት ያገኘችበት ቅለትና ፍጥነት የመወያያ ርዕስ ሆኗል። ይህቺ ሮቦት ሙሉ ህይወታቸውን በስደተኝነት ከሚሰሩ ሰዎች በፊት ዜግነት ማግኘት ችላለች በማለትሙርታዛ ሑሴን የተባለች ጋዜጠኛ አስተያየቷን ሰጥታለች። በሳዑዲ ህግ መሰረት ከውጭ አገራት የመጡ ሰራተኞች ያለ አሰሪዎቻቸው ፍቃድ መንቀሳቀስ አይችሉም፤ ይህም ሁኔታ መብታቸውን ገድቦታል። በገልፍ አካባቢ ያሉ ግዛቶች ከመቶ ሺዎች በላይ ከውጭ አገር የመጡ የቤት ሰራተኞች ጥገኛ ናቸው። ሰው መሰል ሮቦቷ ሶፊያ የሳዑዲ ዜግነት ማግኘት ችላለች፤ በተቃራኒው ግን መሄጃ የሌላቸው ሀገር የለሽ ሚሊዮኖች አሉ በማለት የሊባኖስ እንግሊዛዊ ጋዜጠኛ ካሪም ቻሐይብ የተናገረ ሲሆን መኖር ደጉ ስንቱን ያሳየናል ብሏል። ሳዑዲ አረቢያ በገልፍ ግዛቶች ላይ ያሉ ህግጋቶችን በማሻሻል ላይ ናት። ሴቶች በሳዑዲ አረቢያ ሀገራዊ ቀን ላይ እንዲሳተፉ እንዲሁም ማሽከርከር ላይ ተጥሎ የነበረውም ዕገዳ ከወር በፊት ተነስቷል። ከዚህም በተጨማሪ በነዳጅ ላይ ብቻ ጥገና የነበረውን የግዛቷን ኢኮኖሚም ለማስፋፋትም በልዑል ሞሐመድ ቢን ሳልማን ራዕይ በሚልም ዕቅድ ተይዟል። ተያያዥ ርዕሶች
የሶፊያ ንብረት የሆነ አንድ ሻንጣ ጠፋ
ጁን ማጋሪያ ምረጥ በጀርመን በርሊን ኤክስፖ ቆይታ ያደረገችው ሮቦት ሶፊያ ዛሬ አዲስ አበባ ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ብትደርስም በፍራንክፈርት የአውሮፕላን ማረፊያ የተወሰነ ክፍሏን የያዘው ሻንጣ መጥፋቱ ታውቋል። ይህም በእርሷ ላይ የተወሰነ ጉድለት የሚፈጥር ቢሆንም ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው አይኮግ ላብስ የቴክኖሎጂ ካምፓኒ ባለሙያዎች ለማስተካከልና የጠፋውን ለመተካት ከፍተኛ ርብርብ እያደረጉ እንደሆነ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚንስትር ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ሶፊያ ከአብይ አሕመድ ጋር የራት ቀጠሮ ይዛለች ለደኅንነትና ግርግርን ለማስወገድ በሚል ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ የአቀባበል ሥነ ሥርዓት ያደረጉላት የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች ብቻ ነበሩም ተብሏል። ቀደም ባለው መርሀ ግብር በአቀባበሉ ላይ ከፍተኛ ባለሥልጣናት እንደሚገተኙ ተነግሮ ነበር። ዛሬ ቀትር ላይ ከድንቅነሽ እስከ ሶፊያ በሚል ርዕስ በብሔራዊ ሙዚየም የሚሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ለመስጠት እየሄዱ እንደሆነ ሚኒስትሩ ከደቂቃዎች በፊት ለቢቢሲ በስልክ ተናግረዋል። የአይኮግ ላብስ ሥራ አስኪያጅ አቶ ጌትነት አሰፋ በበኩላቸው ሻንጣው በጀርመን ፍራንክፈርት የአውሮፕላን ማረፊያ እንዸጠፋ ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። ይሁን እንጂ የቴክኖሎጂ ባለሙያዎቹ የጎደለውን ለመሙላት ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ። ተያያዥ ርዕሶች
የት ይቀርልሃል አፈር ድሜ ትበላለህ ጋሽ አበራ ሞላ
ኦገስት ስለ ማጋራት ተጨማሪ ያጋሩ ማጋሪያ ምረጥ ክራር አናጋሪው ሙዚቀኛና የአካባቢ ተቆርቋሪው ስለሺ ደምሴ ጋሽ አበራ ሞላ ለ ኛው የኢትዮጵያ ባሕልና ስፖርት ፌስቲቫል ስዊዘርላንድ ዙሪክ በተገኘበት ሰሞን ክሎተን በተባለ ቀበሌ፣ አንድ የሕዝብ መናፈሻ ውስጥ አግኝተነው ዘለግ ያለ ቃለ ምልልስ አድርገናል። በአመዛኙ ያወጋነው ከሙዚቃ ይልቅ በወቅታዊ አገራዊ፣ ፖለቲካዊና ከተማዊ ጉዳዮች ላይ ነበር ማለት ይቻላል። ዙሪክ ብዙ ችግኝ ተተክሏል መሰለኝ ፣ እንደምታየው ዙሪያ ገባው ሁሉ አረንጓዴ ነው ሳቅ እውነትህን ነው አራት ቢሊየኑ እዚህ የተተከለ ነው ኮ የሚመስለው ሳቅ በአውሮፓ የኢትዮጵያዊያን ፌስቲቫል፡ ሙዚቃ፣ ኳስ፣ ፍቅርና ቡጢ ይሄን ይሄን አይተህ ቁጭት አንገብግቦህ ነበር እንዴ ያኔ ጠቅልለህ ወደ አገር ቤት ገብተህ አገሩን በዘመቻ ያመስከው አዲስ አበባን ጄኔቭ የምታደርግ መስሎህ ነበር ሳቅ እም ይሄን አይቼ ሳይሆን በፊት ልጅ በነበርንበት ጊዜ፤ ከዚያ በፊት በአያት በቅድም አያቶቻችን ጊዜ ኢትዮጵያ እና እጅ ያህል ደን የነበረበት አገር ነበር የነበረን ። ለም የሆነ አገር። ከዚያ በኋላ የተለያዩ ሥርዓቶች ያንን ሊያስጠብቁ አልቻሉም። የሕዝቡ ቁጥር እየጨመረ መጣ፤ ልቅ የሆነ ሥርዓት ተከተለ። ከሥርዓቱ የሚመጡ አስከፊ ሁኔታዎች ድርቅ አስከተሉ። የአየር ንብረቱ ተዛባ። ሕዝቡም ደኑን መጠቀሚያ አደረገው ላቋርጥህ ጋሽ አበራ ከኋላህ አንድ ወጣት ውሻው መንገድ ላይ ስለተጸዳዳ እሱን ጎንበስ ብሎ እያጸዳ ነው፤ እንደምታየው በእጁ የላስቲክ ጓንት አጥልቆ ይህን አጋጣሚ አልለፈው ብዬ ነው። የት እንደሚጥለው እንመልከት ጋሽ አበራ ፊቱን አዙሮ መታዘብ ጀመረ ፣ እንዳየኽው በቅርብ ርቀት መጣያ አለ። በስተቀኝህ ደግሞ የሕዝብ መጸዳጃ አለ። እዚህ አጠገባችን እጅግ ያማረ ሌላ ቆሻሻ መጣያ ይታያል ። አንተ እነዚህን ነገሮች በአገር ቤት ለመሥራት በተወሰነ ደረጃ ሞክረህ ነበረ። የገነባኻቸው ሽንት ቤቶች ፈርሰዋል። መናፈሻዎችህ የቆሻሻ መጣያ ሆነዋል ለመሆኑ ራስ መኮንን ድልድይ ስትሄድ ምንድነው የሚሰማህ መሸነፍ ተስፋ መቁረጥ አይ ተስፋ አልቆርጥም ግን ለምን ይሆን ብዬ እጠይቃለሁ። የምታገኘው ምላሽ ምንድነው መጀመርያ አካባቢ ለምን እንደዚህ ሆነ ምንድነው ችግሩ እያልኩ እብሰለሰል ነበር። ግን መጨረሻ ላይ ያገኘሁት መልስ ምንድነው፣ አንደኛ ባህሪያችንን መለወጥ አልቻልንም፤ በዕውቀት ማደግን አላወቅንበትም። ለአንድ አገር ሥርዓት ወሳኝ ነው። መልካም ሥርዓት ለአንድ ከተማ ምን እንደሚያስፈልግ ጠንቅቆ ይገነዘባል ። አሁን ተመልከት መንገዱን ያየኸው እንደሆነ፣ መሻገሪያውን ያየኸው እንደሆነ፣ ምልክቶችን ያየኸው እንደሆነ እያንዳንዷ ነገር ታስባ የተሠራች ናት ። ተነግረው ያላበቁት የ ጄል ኦጋዴን የሰቆቃ ታሪኮች ተመልከት ይሄን ቆሻሻ መጣያ ተመልከተው በደንብ ሲጋራ መተርኮሻ ሁሉ አለው በቅርብ ርቀት የተተከለ የቆሻሻ መጣያን እያመላከተ ። በዚህ ደረጃ ታስቦበት ነው የሚሠራው። ይሄን አግዳሚ የሕዝብ መቀመጫን ተመልከተው። ይሄን የእግረኛ መንገድ እይ፣ እዛ ጋ ተመልከት የሆነ በዓል አለ ድንኳን ተክለዋል ተመልከት ሕጻናት ሲቦርቁ ወዲያ ደ ሞ እያንዳንዱ ነገር ታስቦበት ነው። ሁሉ ነገር በሕግ፣ በደንብና በሥርዓት ነው ያለው። ለምን ይሄ ሆነ ብለህ ጠይቅ። የሥርዓቱ ችግር ነው እያልክ ነው እንግዲህ ምንድነው፤ የሰለጠነ አስተሳሰብ ያስፈልጋል። አንድ ባለሥልጣን ስንል ኢትዮጵያ ውስጥ ሥልጣኑን ከያዘ በኋላ የእሱ ምቾትና ሥልጣኑን ማስቀጠል እንጂ ሌላው አያሳስበውም። ሥልጣን የሚለው ቃል ሥልጣኔ ማለት ነው። አንድ ባለሥልጣን እዚህ ቁጭ በል ሲባል ስለሠለጠንክ ሥልጣኔህን ተጠቅመህ ሕዝብ አስተዳድር እንደማለት ነው። እሱ ግን የሚመስለው በቃ ገዢ ሆኖ፣ የበላይ ሆኖ፣ አዛዥ ሆኖ፣ ቁጭ ብሎ፣ መኪና ነድቶ፣ ቁርጥ በልቶ፣ ውስኪ ጠጥቶ መኖር ነው። ሥልጣን ይዘው የተቀመጡ ሰዎች የሥልጣኔ ባህሪውም የላቸውም። ካልሠለጠነ አእምሮ ሥልጡን የሆነ ሥርዓትን እንዴት ትጠብቃለህ የቅድሙን ጥያቄ መልሼ ላምጣው። ፒያሳ ራስ መኮንን ድልድይ ስትሄድ አበቦቹ ደርቀው፣ ችግኞቹ ከስመው፣ አረንጓዴ ያደረከው ቦታ የቆሻሻ ቁልል ሆኖ ስታይ ምን ይሰማኻል ዕድሜህን ያባከንክ አይመስልህም ነገርኩህ እኮ ያን ያደረጉ ሰዎች አልሠለጠኑም፤ ከአፍንጫቸው አርቀው አያስቡም። ለእኔ አይደለም መታዘን ያለበት፤ ለእነሱ ነው እኔ የማዝነው። እነዚህን ሰዎች እንዴት ማሠልጠን ይቻላል ነው ጥያቄው። በአጠቃላይ ሕዝቡን ሳይሆን ሥርዓቶች ናቸው። አንድ ሥርዓት ወድቆ ሌላ ሥርዓት ሲመጣ የተሻለ ነገር ይዞ ከመምጣት ይልቅ በድንቁርና ላይ የተመሠረተ አመራር ነው የሚከተለው ሕግን፣ ደንብን፣ ሥርዓትን ተከትሎ የሚሠራ አስተዳደር ነው የሚያሻው። በመሀል የሆነ ጊዜ ላይ ጨርሶኑ ጠፍተህ ነበር።በሥርዓቱ አኩርፈህ ነበር ልበል ጋሽ አበራ ሞላ ጋሽ አበራ ሞላ፤ አበደ ይሉኻል ጉዳይህ ሳይሞላ የምትለው ነገር ባንተም የደረሰች ይመስልኻል እንደዚያ አይደለም። ሁኔታውን ታየውና ዘዴህን ትቀይራለህ። መንግሥት በዚህ ነገር ካልተሳተፈ እንዴት ግለሰቦችን ታሳትፋለህ ባለሀብቱን እንዴት ታሳትፋለህ ተማሪዎች ስለጽዳት እንዴት ግንዛቤያቸው ሊያድግ ይችላል እያልክ ታስባለህ። ዘዴ ለውጠህ ትሠራለህ። ተስፋ ቆርጬ የተቀመጥኩበት ጊዜ አልነበረም። ቅድም እንዳነሳኸው የደከምንባቸውን ቦታዎች ቆሻሻ መጣያ ሆነዋል። መሬቱን ለመሸጥ፣ ለሆነ ካድሬ ለማስተላለፍ፣ ወይም ደግሞ እከሌ ሠራው የተባለ እንደሆነ መንግሥትን አሳጣ ከሚል መጥፎ ሐሳብ የመነጨ ስለነበረ እኛ በየጊዜው ዘዴያችንን እየለወጥን ቆይተናል። ለዚያም ነው ብዙ እውቅና ያገኘነው። የወንድሙን ገዳይ ለመበቀል ወደ ፈጠራ ሥራ የገባው ኢትዮጵያዊ የእንግሊዝ ፓርላማ ውስጥ ከአፍሪካ አንደኛ ወጥቼ ግሪን ጎልድ አዎርድ አግኝቻለሁ። ከዚያም የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሽልማትን አገኘን። የአፍሪካ አንድነት ድርጅት መቀመጫ ከአዲስ አበባ መነሳት አለበት። አዲስ አበባ ቆሻሻ ናት፤ ተስቦ፣ ማሌሪያ፣ ኮሌራ፣ ታይፈስ፣ ታይፎይድ ከጽዳት ማነስ የሚመጡ በሽታዎች ስላሉ የአፍሪካ ከተማ ከዚህ ተነስቶ ትሪፖሊ መሆን አለበት ብለው እነ ጋዳፊ ዘመቻ በከፈቱበት ሰዓት ነው እንግዲህ ያን ያህል እየታገልን የነበረው። እንዳልኩህ ግፊያው አለ፤ ምቀኝነቱ አለ፤ ሥርዓቱ ተጨመላልቋል። ያም ሆኖ ተስፋ አልቆረጥንም። ከተማውን ያስተዳደሩ የነበሩ ሰዎች ላይ ቅሬታ ያለህ ይመስላል። የከተማው አስተዳዳሪዎች በጣም በሚገርም ሁኔታ ለየት ያሉና ዕውቀቱ የሌላቸው፣ ከተማን የማስተዳደር ባህሪ ጨርሶውኑ ያልነበራቸው ነበሩ። እነሱ ሲመጡ የሠራነው ሁሉ እየፈራረሰ መታየት ጀመረ። አርቆ አለማሰብ አለ፤ ትንሽ ነበር አስተሳሰባቸው፤ መኪና፣ ልብስ፣ አጊጦ መታየት ከዚህ ያልራቀ ዓይነት አመለካከት እያለ ይሄ ይሄ ነው እንግዲህ ችግሮችን ይዞ የቆየው። ይሄ የሰሞኑ ችግኝ ተከላ፤ በችግኝ ቁጥር ክብረ ወሰን መሰበሩ ወዘተ ሰሞነኛ ሆይሆይታ ሆኖ ነው የሚሰማህ ወይስ አነሳሱ ጥሩ ነው፤ ቀጥሎ ምን ይሆናል የሚለው ነው የሚያሳስበኝ። በእርግጥ ቢሊዮን ችግኝ ተተክሏል ወይ የሚለው አንድ ትልቅ ጥያቄ ነው። ቢሊዮን ችግኝ ሁለት ሦስት ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ሐሳብ ታስቦ ተተከለ ለማለት ያስቸግራል። ለ ዓመታት ዴንማርካዊት እህቱን የፈለገው ኢትዮጵያዊ ሀኪም በዚህ ላይ እኛ ልምዱ አለን፤ ብዙ ተክለናል፤ አገሩን ማስተባበር ችለናል። ይሄን በተለያየ ጊዜ ለመንግሥት ሰዎች እንነግራቸዋለን። ነገር ግን የመስማትና የመቀበል ሁኔታቸው ዝቅተኛ ነው። እንኳን አብሮ ለመሥራትና ዕውቅና ሊሰጡህም ፍቃደኛ አይደሉም። ሕዝቡ ምንድነው የሚለው ይሄንን ነገር የጀመርከው አንተ አይደለህም ወይ ይላል። ይሄ ሁሉ እየሆነ በማማከር ደረጃ እንኳ አብረን እንሥራ የሚልህ የለም። ጠቅላይ ሚኒስትሩ አካባቢ እንድታማክር ወይ እንደዚህ ዓይነት ጥያቄ አልቀረበልህም ቅሬታ ያለህ ይመስላል። አንድ መንግሥት ሲመጣ አማካሪ ሆነው አብረው መሥራት የሚፈልጉን ሰዎችን ያየኻቸው እንደሆነ አሁን አንዱ ትልቁ ቅሬታዬ ትናንትና የነበሩ ሰዎች ናቸው ዛሬ ያሉት። ትናንትና በተለያየ ቦታ ላይ ሲያስቸግሩኝ የነበሩ ሰዎች ዛሬም አሉ፤ ትናንት ቀይ ኮት ለብሰው ነበር፤ ዛሬ አረንጓዴ ኮት ለብሰው ቁጭ ብለዋል። ከእነኚህ ሰዎች ምንድነው የምጠብቀው በአርቱ አካባቢም ብታይ ትናንትና ሆይ ሆይ ሲሉ የነበሩ ዛሬ ቅኝት ቀይረው ምናምን ብለው እያዜሙ ነው። እና ይሄ ህልም ነው ቅዠት ነው ምናምን ትላለህ። ዕውቅና ስላልተሰጠህ ቅሬታ ያለህ ይመስላል። ምንድነው መንግሥት እኔን ሪኮግናይዝ ባለማድረጉ ዕውቅና ባለመሥጠቱ እኔ ምንም እንትን አይሰማኝም። እኔን ሪኮግናይዝ ባለማድረጉ የራሱን ሥራ ሪከግናይዝ እንዳይደረግ አድርጎት ይሆናል እንጂ እኔን ምንም እንትን ያለኝ ነገር የለም። የጋሽ አበራ ሞላን ሥራ ሰዉ ቀርቶ ጅቡም ያውቃል። መንግሥት ዕውቅና ሰጠኝ አልሰጠኝ ብዬ አልልም። ምን እያሰብክ ነው በቀጣይነት ከጥቂት ወራት በኋላ ትልቅ ፕሮጀክት ይኖረናል። ሲቪል ሶሳይቲ ይኖረናል። እኛ ከወጣቱ ጋር ከሰሜን፣ ደቡብ፣ ምሥራቅ፣ ምዕራብ ጥሩ ግንኙነት አለን። ለእኛ ቅን አስተሳሰብ አላቸው። በብሔር በጎሳ የተጠረነፉ ሳይሆኑ ይህቺን አገር ትልቅ ለማድረግ ቁጭቱ ያላቸው ብዙ ጉልበት ያላቸው ሰዎች አሉ። ስለዚህ ምንድነው ፕሮጀክትህ ማለት ነው ሲቪል ሶሳይቲ መመሥረት ነው የሚሆነው። አገሪቱ እንዲህ የሆነችው ለምንድነው ያልክ እንደሆነ ኢህአዴግ አንድ ፓርቲ ነው። አጣኙም፣ ቀዳሹም፣ ቄሱም ዘማሪውም እሱ ነው። ኢህአዴግ እንዲህ አደረገ ተብሎ ለሰው ይነገረዋል እንጂ ሰው ይህ ይደረግ አይልም። በዚህ በኩል መንገድ ይውጣ ከተባለ፣ ሰው ተማክሮ ነው እንጂ ማዘጋጃ ቤት ስለፈለገ መሆን የለበትም። የሕዝብ ተሳትፎ መቅደም አለበት። ኢትዮጵያ ውስጥ አሁን ይሄ የለም። የሕዝብ ተሳትፎን ካነሳህ አይቀር አሁን ይሄ ማዘጋጃ ቤት አጠገብ ያለው ሜዳ መጀመርያሜድሮክ ፎቅ ሊሠራበት ነበር። አሁን ደግሞ አድዋ ፓርክ ሊደረግ ነው፤ መልካም ተነሳሽነት ቢሆንም ቅሉ ከዲዛይኑ ጀምሮ የሕዝብ ተሳትፎ አያሻውም ወይ የከተማ ፈርጥ የሚሆን ነገር እንዲሁ ማዘጋጃው ስለፈለገ እሱን ነው የምልህ። አንተ ያልከው ነገር ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ ከተማው ውስጥ ያሉ ግንባታዎች። አምጥቶ እብድ የሚያህል ፎቅ ይገደግድብኻል። ለእግረኛ ማለፊያ የለው፤ መኪና ማቆምያ የለው፤ አረንጓዴ ቦታ የለው የዛሬ እና ዓመት ያለው ሕዝብ አይደለም አሁን ያለው። ክፍት ቦታ የለም። ፎቅ መገጥገጥ ነው ያስጨንቅሃል። ይሄው ተመልከት አንዲት ሴት ልጇን በተንቀሳቃሽ አንቀልባ እየገፋች ታልፋለች ይቺ ሴትዮ ጋሪውን ከእግረኛው ጥርጊያ ለማውረድ ትንሽዬ ራምፕ ተሠርቶላታል። ተመልከት እንግዲህ ይቺ ሁሉ ሳትቀር ታስባ ነው። የአዲስ አበባ ባላደራ ምክር ቤት የፓርላማውን ውሳኔ ተቃወመ ይኸን ተወው ይቅር። አሁን አንዱ ተነስቶ ሕንጻ ሲሠራ ባለቤቱ ይመጣና ጠጠሩን አሸዋውን ይደፋል፤ ትራኩ ምኑ ትርምስ ነው፤ የእግረኛ ማለፊያ የለ፣ ምን የለ፣ ፎቅ ብቻ ሕግ ደንብና ሥነ ሥርዓት ያለው አገር አይመስልም። እኛ ጋር ዝም ተብሎ ነው የሚሠራው። ቀበሌው ምን ይሠራል ክፍለ ከተማው ምን ይሠራል ከተማውን አስተዳድራለሁ የሚለው አካል የት ነው ያለው ግራ ነው የሚገባህ። አረንጓዴ የነበረው ቦታ ቆሻሻ መጣያ ሲሆን፣ አገር ጉድ ሲል፣ እዚያ የአረንጓዴ ልማት ቢሮ የተቀመጠው ሰው ቁጭ ብሎ ያያል። ስለዚህ ምን ማለቴ ነው፣ ሕዝቡ ይሄ ያንተ ከተማ ተብሎ ድርሻ እየተሰጠው እየተሳተፈበት፣ የእኔ ነው እያለ ሲሆን ነው ነገሩ መልክ የሚይዘው። እስካሁን ስናወራ የተረዳሁት በአገሪቱ ብቁ አመራር እንደሌለና ይህም ያሳሰበህ ይመስላል። አንተ ከዚህ በፊት ሕዝብን ማንቀሳቀስ ችለሃል። ተምሳሌት መሆንም ችለሃል። አንዳች ለውጥ ለማምጣት ከፍተኛ ፍላጎት አይብሃለው። ለምን ለከንቲባነት አትወዳደርም ምንድነው ችግሩ ትፈራለህ ፖለቲካ አይ አይ እኔ እንኳን ይሄ ሥልጣን ምናምን አይሆነኝም። ግን እኮ ለውጥ ለማምጣት የምር የምትሻ ከሆነ አይ አይ አይሆንም። አንደኛ እኔ እንደዛ ዓይነት ነገር አልወደውም፤ መሆንም አልፈልግም። ቢሮ ውስጥ ተቀምጬ የወረቀት ሥራ ምናምን ለዚያ የምሆን አይደለሁም። ምን መሰለህ ሐሳቦች አሉ። ሐሳቦችን ማፍለቅ ነው ዋናው። ከሁሉም በላይ የሚልቀው ሐሳብ ነው። ሐሳብህን ወደ ዲዛይን የሚለውጥ አለ። ዲዛይኑን ወደ ተግባር የሚለውጥ አለ። ለዚህ ነው ቅድም ሲቪል ማኅበረሰብ መኖር አለበት ያልኩህ። እራት ለመመገብ አይደለም የምንሄደው በላይነህ ክንዴ በአንድ አገር የሲቪል ማኅበረሰብ ከሌለ ማንኛውም ነገር ሊሠራ አይችልም። መንግሥት አጣኙም እሱ፣ ቀዳሹም እሱ፣ ሰጪውም እሱ፣ ነሺውም እሱ፣ ተጠያቂውም እሱ ይሆናል። በአዲሱ አስተዳደር እነዚህ ሁሉ ነገሮች መልክ መያዝ አለባቸው ነው እያልኩህ ያለሁት። ለዚህ ነው የሲቪል ማኅበረሰብ የሚያስፈልገው። ባለፈው የኢህአዴግ ጊዜ የሲቪል ማኅበረሰብ ለማቋቋም ብለን እነ ብርሃኑ ነጋ፤ ክቡር ገና አንድ አራት አምስት የምንሆን ሰዎች በጋሽ አበራ ሞላ ተነሳሽነት ከተማዋን ለማጽዳት፤ ለማልማት ሲቪል ሶሳይቲ ብንመሰርት ገንዘብ ይዋጣል፤ በእውቀት መንግሥትን ያግዛል ብለን አፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ኢሲኤ ውስጥ ትልቅ ስብሰባ ተደረገ። ማታውኑ ማታውኑ መለስ ዜናዊ ጠርቷቸው እናንተ ምንድናችሁና ነው እኔን አልጠራኝም ምን አግብቷችሁና ነው ሲቪል ሶሳይቲ ብላችሁ እንደዚህ የምትሰባሰቡት ሕዝብ ልታሳምጹ ነው ተብለው እነኛን ሰዎች ማታውኑ አስፈራርተው ሰደዷቸው። አንተ ለምን አልተጠራህም እኔ ስብሰባ ውስጥ ተጠራሁ። እሱ ያመጣው ሐሳብ ትልቅ ሐሳብ ነው። በአንድ ግለሰብ የመጣ ሐሳብ አገር ለውጧል። ይሄ ሁሉ ኅብረተሰብ ደግሞ ቢሳተፍበት ምን ያህል ለውጥ ሊመጣ ይችላል በሚል ስለዚህ የሲቪል ማኅበረሰብ የሆነ አካል ሲኖር የበለጠ ብዙ ነገር ሊሠራ ይችላል። ይሄንን እናዳብረው ነው እንግዲህ። ዲያስፖራው ይመጣል። ዕውቀት ያለው ይመጣል፤ ጉልበት ያለው ይመጣል፤ እነዚህ እነዚህ በሙሉ ታሰባስብና ለውጥ የሚመጣበትን ሁኔታ ታመቻቻለህ። እና የዚያን ጊዜ እንደዚያ ሆኖ ከሸፈ ። አሁንም መታወቅ ያለበት ሕዝብ ተዋናይ እንጂ ተመልካች መሆን የለበትም። አንተ አብዝተህ በእግር ስለምትንቀሳቀስአሁን መገናኛና ሜክሲኮ አካባቢ ስትሄድ ምንድነው የሚሰማህ ምን አ ርግ ነው የምትለኝ በሚል ስሜት በረዥሙ ተነፈሰ ምን እኮ ያው እንደምታየው ነው። መገናኛና ሜክሲኮ ብቻ ሳይሆን የትስ ቦታ ብትሄድ ጉድ ነው እኮ የሕዝቡ ብዛት፣ ውጥንቅጡ ትርምሱ ቅድም እኮ አወራን ። እዚህ ተመልከት፤ እያንዳንዱ ነገር እኮ በቀመር ነው የተሠራው፤ በአጋጣሚ አይደለም። አገሩ በሙሉ ነቅሎ ከሰሜን፣ ከደቡብ፣ ከምሥራቅ፣ ከምዕራብ፣ ገበሬው፣ ወጣቱ፣ እናቱ፣ ምኑ ምኑ ሳይቀር በየቀኑ ይገባል ወደ አዲስ አበባ። እኔ የሚገርመኝ እነዚህ በሥልጣን ላይ ያሉ ሰዎች በዚህ እየተጋፉ ነው የሚሄዱት፤ ግን መኪና ውስጥ ናቸው። መኪና ውስጥ ቢሆኑ አሁን የከተማው አስተዳዳሪዎች ይሄን ሁሉ ትርምስ ሲያዩ ምንድነው የሚሰማቸው እላለሁ። እኔ እውነት ለመናገር አንድ እግዚአብሔር የነሳን አንድ የሆነ ነገር አለ እንዳናይ ያደረገን የጠቅላይ ሚኒስትሩ ሚሊዮን ችግኞች እንጂ ዓለም እዚህ በደረሰበት ሰዓት እኛ እንዲህ ትርምስምስ ባለ ጎሳዊ፣ ጎጣዊ፣ ግላዊ አመለካከት ውስጥ እንሆን ነበር ምን ለማለት ፈልጌ ነው መንገዱ ላይ ስትሄድ የለማኙ ብዛት ቁጥር ስፍር የለውም። አልፎ ተርፎ ልጅ እየወለዱ መንገድ ላይ ሺህ የሚሆኑ አራሶች ግራና ቀኝ ተደርድረው ይታያሉ። ሽማግሌዎች ሲለምኑ ታያለህ። ቅድም እንዳልከው መገናኛና ሜክሲኮ ስትሄድ ከሆነ ፕላኔት ላይ የወረድን ሰዎች እንጂ የምንመስለው እውነት በምጣኔ ላይ ተመሥርተን ተወልደን በሥርዓት አድገን ለመኖር የመጣን ሰዎች አንመስልም። የሳልቫጁ እቃ ራሱ አብሮ ከሰማይ የወረደ ነው የሚመስለው፤ ሻጩም አብሮ የወረደ ይመስላል፤ ገዢውም አብሮ የወረደ ይመስላል። ዱብ ዱብ ብለው የወረዱ ነው የሚመስለው። ማታ ደግሞ ስታያቸው የሉም። ከሌላ ስፔስ የመጡ እኛን የሚመስሉ ሰዎች ናቸው ወይስ ትርምሱ እየገረመኝ እተክዛለሁ። እና እኔ ንጃ ደንብ፣ ሕግ ሥርዓት ያለን ሕዝቦች አንመስልም ብቻ እንደምታየው እንዲህ እያወጋን አዛውንቶች፣ ሕጻናት እዚህ መናፈሻ ላይ ደስ የሚል ጊዜ እያሳለፉ ነው። አዲስ አበባ ውስጥ አረጋዊያን የት ይሂዱ፤ ሕጻናት የት ይጫወቱ አረጋዊያኑ ቤት ይዋሉ፤ ሕጻናቱም ቤት ነው የሚቀመጡት፤ ምናልባት ለወደፊት ቤቱ ሲሞላ ጣሪያም ላይ ሊቀመጡ ይችላሉ በምጸት ዓይነት ። ምክንያቱም ቦታ የሚባል ነገር የለማ። ቅድም እንዳልኩህ ነው። በየቦታው የበሬ ግንባር በምታህል ቦታ እንኳ ስትገኝ ፎቅ ነው። መሬትን መሸጥ ነው የተያዘው። በተሸጡ መሬቶች መሀል እንኳ ምናለ እንደው ካሬ እንኳ ለአዛውንት ለሕጻናት ተብሎ ቢተው። አሁን እንደዚህ ከሆንን ከዚህም በላይ ቁጥራችን እየበዛ በሚሄድ ጊዜ ምን ልንሆን ነው ብዬ አስባለሁ። የወንዝ ዳር ልማቱ ተሳክቶ አንተ በእነዚያ መናፈሻዎች የእግር ጉዞ የምታደርግ ይመስልሃል ቢሊዮን ችግኞች ጸድቀው በሕይወትህ የምታያቸው ይመስልሃል አሁን ያልናቸው ነገሮች የሚሳኩ ከሆነ፤ ሕዝቡን የምታሳትፍ ከሆነ ለምን አይሆንም አሁን በዚህ በወንዞች ዳርቻ ልማት ፕሮጀክት አለሁበት። የአካባቢዎቹን ታሪኮች የጻፍኩት እኔ ነኝ። እንጦጦ ምንድነው አፍንጮ በር ምንድነው ኪሎ፣ ቃሊቲ፣ አቃቂ የሚሄደው ይሄ ሁሉ የወንዝ ዳር ፕሮጀክት በአካባቢው ስም፣ በአካባቢው ምሳሌ፣ በአካባቢው ተረት፣ ያንን ወዙን፣ ያንን ለዛውን፣ ያንን ማዕረጉን፣ ያንን ታሪኩን፣ ዘይቤውን፣ እንቆቅልሹን ይዞ የሚሄድ እንዲሆን በሚያስችል መንገድ ነው የጻፍኩት። ጠቅላይ ሚኒስትሩም ደስ ብሏቸው ተጀምሯል። ትልቅ ፕሮጀክት ነው። የጨርቆስም ትልቅ ፕሮጀክት ነው። እና ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥሩ ህልም አላቸው። ግን እዚህ ላይ የሚያማክሩ አብረው የሚሠሩ ሰዎችን ቅድም እንዳልኩህ ሲቪል ማኅበራት ያስፈልጋሉ። ወጣቱ አዛውንቱ ሁሉ መሳተፍ ይኖርበታል። ችግኙም እንደዚሁ። ዝም ብሎ ይሄንን ያህል ተተከለ ለማለት ሳይሆን ችግኝ ስትተክል አእምሮ ውስጥ ነው መጀመርያ የምትተክለው። እኔ እንደሚመስለኝ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢሊዮን ችግኝ ሲል የሕዝብ አእምሮ ላይ ለመትከል ያሰበው እቅድ ነው የሚመስለኝ። እንጂ ዝም ብሎ የችግኝ ቁጥር አይመስለኝም። የአረንጓዴነት ስሜቱንና አስተሳሰቡን ሰው አእምሮ ውስጥ ለመትከል ያሰበ ነው የሚመስለኝ። እስኪ ጋሽ አበራ አሁን ደግሞ በአጫጭር ጥያቄዎች እረፍት እናድርግ። ለመጨረሻ ጊዜ ሱፍ የለበስከው መቼ ነው ለብሼ አላውቅም እኔ። አንድ ቀን ብቻ ኦፕራህ ዊንፍሬይ የመጣች ቀን ልበስ ተብዬ ለበስኩ። ከዚያ ሰዎች ሲፈልጉኝ አጡኝ። እኔኮ አጠገባቸው ተቀምጫለሁ። ለካስ እነሱ በሱፍ አያውቁኝም። ሳቅ መኪና አለህ ጋሽ አበራ ሞላ መኪና ይኖራል ግን ምንድነው አቅም ማነስ ነው ሕዝቡ ማዋጣት ካለበትም ይነገረው ሳቅ አይ እኔ መኪና የሌለኝ ስለምቸኩል ነው። በቀን ውስጥ ምን ያህል ኪሎ ሜትር በእግር ትጓዛለህ፣ በአማካይ ለምሳሌ አያት አካባቢ ነው ሰፈሬ። እንግዲህ ቦሌ መሄድ ካለብኝ ጠዋት እነሳለሁ፤ አንድ ወይ ኪሎ ሜትር በየቀኑ ሥጋ ቁርጥ እንደዚህ ነገር ትበላለህ ሥጋ እበላለሁ ግን እስከዚህም ሥጋ በላተኛ አይደለሁም። አልፎ አልፎ ከሰዎች ጋር ካልሆነ ብዙም ታዲያ የምታዘወትረው ምግብ ምንድነው እኔ ከምግብና ከገንዘብ ጋር ብዙም ግንኙነት የለኝም። ብዙ ጊዜ እስጢፋኖስ ቤ ክርስቲያን ፊትለፊት ካፌ ቁጭ ብለህ እመለከትሃለሁ፤ ጥሞና ታበዛለህ። ምንድነው የሕይወት ፍልስፍናህ ያው እንግዲህ እኔ ምድር ላይ ብኖር ዓመት ነው። ለዚህች አጭር ዕድሜዬ ብዬ ብዙ አልጨነቅም ሳቅ ፤ እናንተ ዓመት ለመኖር ነው የምትጨነቁት። እኔ ቀስ እያልኩ ነው የማረጀው፤ እናንተ ቶሎ ታረጃላችሁ። የምር ፍልስፍናህን ንገረኝ አየህ ሰዎች ሱስ ውስጥ ይገባሉ። ምን ዓይነት ሱስ መሰለህ ማቴሪያል የመውደድ ሱስ። ወይ መኪና የመውደድ፣ ወይ ኑሮ ማለት ለነሱ ገንዘብ የማከማቸት። አእምሯቸውን፣ ልባቸውንና አጠቃላይ ሕይወታቸውን ወደ ውጭ አውጥተው እዚያ ላይ ያስቀምጡታል። ሕይወት ግን ወደ ውስጥ ነው። የተተከሉት ችግኞች እንዴት ተቆጠሩ መጀመሪያ ሕይወት ያለው አንተ ውስጥ ነው። ያንን ሕይወት፣ ሕይወት ልታደርገው የምትችለው አንተ ነህ እንጂ፣ ውጭ ያለው ነገር አይደለም ላንተ ሕይወት የሚሰጥህ። ራስህን አውጥተህ ስትሰጥ ማንነትህን እያጣህ ትመጣለህ። ውስጥ ያለው መንፈስህ እየወጣ፣ እየደከምክ አቅም እያጣህ ትመጣለህ። ከዚያ ጭንቀት ይቆጣጠርሃል። ተጠራጣሪና ፈሪ ትሆናለህ። ከሰው ጋር ለመግባባት ትቸገራለህ። ስለ ገንዘብ ምን ታስባለህ እኔ ገንዘብን ብዙም አላቀርበውም፤ እዚያ ጋ ይቀመጣል፤ ከዚያ ስፈልግ ና እዚህ ጋ እለዋለሁ። ቤት ኪራይ ይከፍላል፤ ይሄዳል። ገንዘብ ይታዘዝልኛል እያልከን ነው አዎ ሳቅ ገንዘብ አልሰበሰብ እያለ አስቸግሮህ፤ ሩቅ ሆኖብህ እንዳይሆን ሩቅ ሆኖብኝ አይደለም። በአንድ በኩል ሩቅም ነው። አሁን እነዚህ ሚሊዮን ብር ያላቸው አንድ ሰው ይሄን ብር ከየት ያመጣል ካልሰረቀ ካልዘረፈ በስተቀር። ሠርቶ የሚያገኘው ምናልባት ጥቂት ሰው ነው የሚሆነው። አእምሮን መንፈስን ኮራፕት አድርገን ተላምደን ኖረናል ለብዙ ጊዜ። ይሄንን ኖርማል አድርገን ይዘነው ነው ብዙዎች ሀብታም ነን የሚሉት። እንጂ ከየት ያመጣሉ የትኛው ዕውቀታቸው ነው ይሄን ያህል ገንዘብ እንዲያገኙ የሚያስችላቸው የትኛው ነጋዴ ነው እንዴ እናውቃለን እኮ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ እኮ ያውቃል። ማን ብሩን እንዴት እንዳገኘው። ሀበሻ ፍልስፍናው በተረት ውስጥ ነው ያለው። አንድ ተረት ልንገርህ ሰጎን አሉ መሀል በረሃ ላይ ይቺን የምታክል አፏን አሸዋ ላይ ቀብራ አንገቷና ሰውነቷ ውጭ ነው ያለው። ኋላ ሰው ሄደና ሰጎን ሰጎን ምን እያረግሽ ነው አፍንጫና ዓይንሽን ቀብረሽ ሰውነትሽ ዝሆን አክሎ ቢሏት ሰው እንዳያየኝ ተሸሽጌ ነው አለች አሉ። እነኚህ ሰዎች ይሄንን ሚሊዮን ብር ከየት እንዳመጡት የኢትዮጵያ ሕዝብ ያውቃል። ነገር ግን አንገቱን የቀበረው ሰውዬ ስለ ኔ ሰው አያውቅም ብሎ አንገቱን እንደ ሰጎን አሸዋ ውስጥ ቀብሮታል። በንጽሕና የተገኘ ሀብት የለም እያልኩህ ግን አይደለም። ጥቂት ነው። አጭር የምስል መግለጫ ስዊዘርላንድ፤ ዙሪክ ኅብረተሰባችን የሞራል ልዕልናው እየተሸረሸረ ይመስልሃል በጣም እንጂ ህልውናውን ያጣበት ዘመን ነው፤ ታዲያ ህልውናውን ባያጣ በሄድክበት ከዚህ በፊት ሐዋሳ መሄድ ስታስብ ኤጀቶ እንደዚህ ያደርገኛል፤ ኦሮሚያ ብትሄድ ቄሮ እንዲህ ይለኛል፣ አማራ ብትሄድ ፋኖ ምናምን ይለኛል ትላለህ እንዴ ወጣቱ ሁሉ በዘር በሃይማኖት በጎሣ ተበጣጥሶ እያንዳንዱ ሰው እየጠበበ፣ ዱላ እየያዘ እርስ በርሱ ይደባደባል እንዴ ከዚህ የበለጠ ህልውና ማጣት ምን ይኖራል ምን ያልሆነው አለ እስቲ አሁን ሰው እየሰቀልን ሰው እየቆራረጥን፤ ሰው እየገደልን፤ ሺህ ሰው እያፈናቀልን ምን ያልሆነው አለ እስቲ ኢትዮጵያ ውስጥ ምንድነው ያልተሆነው ንገረኝ እንዴት በአንድ ጊዜ እዚህ ደረስን ግን በአንድ ጊዜ አይደለም። ትንሽ ዓመት ነው እንዴ እስኪ አስበው። በደርግ ጊዜ ተጀመረ። በኢህአዴግ ጊዜ አለቀ። ዓመት በለው የኢህአዴግን ዕድሜ። ያ ዓመት ወደ ዓመት ሊሆን እኮ ነው። ግማሽ ክፍለ ዘመን ቀላል ነው እንዴ ታዲያ ዓመት ጆሮው ላይ ስለክፍፍል ሲጮኽበት የነበረ ሰው እንዴት አድርጎ ነው ልዕልና የሚኖረው ተጠላልፈን በድንበር ተከፋፍለን፣ ባንዲራ አሲዘውን አእምሯችን ላይ ድንበር ሠርተው፣ በሃይማኖት አጥረውን፣ በክልል አጥረውን፣ በጎሣ አጥሮን አንተ እንዴት እኔን ትወደኛለህ ይሄ ኅብረተሰብ ቪክቲም ሰለባ ነው። የዚህ ድምር ሥርዓት ውጤት ነው። ታዲያ በምን ሂሳብ ነው የተሻለ ነገር የምትጠብቀው አረም ዘርተህ ስንዴ ትጠብቃለህ እንዴ ትሰጋለህ ይቺ አገር እልቂት ውስጥ ትገባለች ብለህ ዘለግ ካለ ትካዜ በኋላ ሶሪያ ምን ሆነ የመን ምን ሆነ ሶማሌ ምን ሆነ ጎረቤትህ እኮ ነው። የግድ አንተ ቤት መምጣት አለበት እንዴ ጎረቤትህ ምን እየሆነ እንዳለ እያየህ አንተ ምን ሆንን እኛ ብለህ የተቀመጥክ እንደሆነ የት ይቀርልሃል አፈር ድሜ ትበላለህ ቀልድ እንዳይመስልህ። የሚመጣውን መገመት የማትችል ከሆነ ሲኦል ነው የምትገባው። ማነው ተጠያቂው ግን አሉ የዘር በሽታ የያዛቸው። ኦሮሞ በል፣ አማራ በል፣ ትግሬ በል በለው እያሉ በቃ በዘር የተለከፉ በሽተኞች አሉ፤ እነኚህን በሽተኞች መለየት ያስፈልጋል። አሉ እዚህ ምንም የማይሻሻሉ፤ እዚህ የሰለጠነ ዓለም እየኖሩ እንኳ ያልሰለጠኑ ሰዎች አሉ። እነኚህን በሽተኞች ወደዚያ አግልለህ ወዴት በሕግ፣ በደንብ በሥነ ሥርዓት ጠፍንገህ ታስረዋለሃ። ቆጣ ባለ ስሜት ምን ያረጋል መንግሥት ኃላፊነቱ ይሄ አይደለም እንዴ ይሄን ሁሉ መከራና አመጽ የሚያመጡ ሰዎች እኮ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች አይደሉም። ጥቂት ሰዎች ናቸው። እዚህና እዚያ ጥቅማቸው እንዳይቀርባቸው ነው ክብሪት እየለኮሱ ብዙኃኑን የሚያፈናቅሉ። እነኚህ ሰዎች በደንብ ይታወቃሉ። ምንጫቸው ይታወቃል። ምንጩን ማድረቅ አለብህ። እነዚህ የምትላቸውን ማሰር ወደ ባሰ ቀውስ አይከተንም ብዙ ወጣት ተከታይ አላቸው እኮ እሱ ልክ ነህ፤ ሁለት ነገር አለ። ዛሬ ስንት እጁ ነው ወጣት ምን ያህሉ ነው ሥራ ያለው። ሁሉም ቦዘኔ ነው። ትግራይ ብትገባ ያ ሁሉ ወጣት ሥራ የለውም፤ ግን እዚያ ያለው ሥርዓት ምን ይለዋል ልክ እሱ አርበኛ እንደሆነ፣ ጀግና እንደሆነ፣ በወሬ እያሞካሸ አንተ እንደዚህ ነህ እያለ ዝም ብሎ ያወጣዋል ያንን ወጣት። አዲስ አበባም በለው የትም የትም እንደዚህ ነው የሚያደርጉት። ጀሌውን የሚመራውን ነው መያዝ፤ ፋኖ ነኝ፣ ኤጄቶ ነኝ፣ ቄሮ ነኝ ምንድነኝ የሚለው ሌሎች ይጠቀሙበታል እንጂ ሥራ ነው የሚፈልገው። ድሃ በመሆኑ ነው ሊጠቀሙበት የሚፈልጉት፤ ድሃ ባይሆንማ ዝም ብሎ አይነሳላቸውም። ግን ጋሽ አበራ ነጻና እውነተኛ ዲሞክራሲ ቢኖር ምርጫ አትወዳደርም እርግጠኛ ነህ አይ አላደርገውም፤ እውነት ለመናገር እኔ እዚያ ነገር ውስጥ ብገባ እኔነቴን አጣዋለሁ። ሁሉም ሰው ሥልጣን አይዝም። ሁሉም ሰው ቤት አይሠራም፤ አንዱ ቤት ይሠራል፤ ሌላው ቤት ይከራያል። ተያያዥ ርዕሶች
ግሬታ ተንበርግ፡ አዲስ የጥንዚዛ ዝርያ በአየር ንብረት ለውጥ ተሟጋቿ ስም ተሰየመች
ኦክተውበር ስለ ማጋራት ተጨማሪ ያጋሩ ማጋሪያ ምረጥ አዲስ የተገኘችው የጥንዚዛ ዝርያ በአየር ንብረት ለውጥ ተሟጋቿ ግሬታ ተምንበርግ ስም ተሰየመች። ግሬታ ተንበርግ የአየር ንብረት ለውጥን አስመልክቶ ሰልፍ በመጥራት ያስተባበረች ታዳጊ ስትሆን፤ ሰልፉ ከአውስትራሊያ እስከ ኒውዮርክ፣ ከእስያ እስከ አፍሪካ፤ ከሊቅ እስከ ደቂቅ እንደተሳተፉበት ተነግሯል። ይህ ሰልፍ፤ የሠው ልጅ ያስከተለውን የዓለም ሙቀት መጨመር በመቃወም የተደረገ ትልቁ ሠልፍ ነው ተብሏል። የተመራውም በታዳጊዋ ግሬታ ተንበርግ ነበር። የ ዓመቷ ግሬታ በዘንድሮው የኖቤል የሠላም ሽልማትም ያሸንፋሉ ተብለው ከፍተኛ ግምት ከተሰጣቸው መካከል ነበረች። በአየር ንብረት ለውጥ ተሟጋቿ ስም የተሰየመችው ኒሎፕቶድስ ግሬቴ የተሰኘችው ጥንዚዛ ቁመቷ ከአንድ ሚሊ ሜትር ያነሰች ስትሆን፤ ክንፍም ሆነ ዐይን የላትም። እንደ አንቴና ያሉ ሁለት ረጅም የአሳማ ዓይነት ጅራቶች አሏት። ተመራማሪው ዶክተር ማይክል ዳርቢይ ስያሜውን ለምን እንደመረጡት ሲናገሩ፤ በስዊድናዊቷ የአየር ንብረት ለውጥ ተሟጋች በጣም ከመደነቃቸው የተነሳ እንደሆነ ተናግረዋል። በአጭሩ ኤን ግሬቴ የተባለችው ነፍሳት ለመጀመሪያ ጊዜ በአውሮፓዊያኑ በዊሊያም ብሎክ በኬንያ የተገኘች ሲሆን፤ ናሙናዎቹንም እአአ በ በለንደን ለሚገኝ የተፈጥሯዊ ታሪክ ሙዚየም ለግሰዋል። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በሙዚየሙ ውስጥ ተቀምጣ ትገኛለች። ዶክተር ማይክል ስም ያልተሰጣቸው ስም የለሽ የሆኑ ዝርያዎችን በሚያጠኑበት ወቅት የእነዚህንም ነፍሳቶች ዝርያ ስብስብ ሲያጠኑ ነበር። አጭር የምስል መግለጫ ግሬታ ተንበርግ የዓለም የአየር ንብረት ለውጥ የተቃውሞ እንቅስቀሴን መርታለች አዲስ የተገኘችውን ጥንዚዛ በታዳጊዋ ግሬታ ስም በመሰየም አካባቢን በተመለከቱ ጉዳዮች ላይ ግንዛቤ ለመፍጠር ያደረገችውን አስደናቂ አስተዋፅኦ እውቅና ለመስጠት እንደፈለጉ ተመራማሪው አስረድተዋል። አሁን ጥንዚዛዋ በ ኢንቶሞሎጅስቶች የነፍሳት ተመራማሪዎች ወርሃዊ መፅሔት ላይ ስሟ በይፋ ሰፍሯል። ሙዚየሙ ውስጥ ያሉትን ጥንዚዛዎች ላይ ክትትል የሚያደርጉት ዶክተር ባርክሌይ በበኩላቸው፤ የተሰጠው ስም ተገቢ ነው ይላሉ። ምክንያታቸውን ሲያስቀምጡም ያልተለዩ ዝርያዎች ሁል ጊዜ የመጥፋት እድላቸው የሰፋ ነው ፤ የሚጠፉትም ተመራማሪዎች ለእነሱ ስም ከመስጠታቸው በፊት ነው ምክንያቱም የብዝሃነት እጦት ነው ብለዋል። በመሆኑም ይላሉ ዶክተር ባርክሌይ አዲስ ግኝቱ ለአደጋ የተጋለጡ ዝርያዎችን ለመጠበቅ ለአየር ንብረት ለውጥ ተግታ በሠራችው ታዳጊ ስም መሰየሙ ተገቢ ነው ሲሉም ጨምረው ተናግረዋል። ስማቸው ለእንስሳት መጠሪያ የዋለ ዝነኞች እነማን ናቸው ለተመራማሪዎች አዲስ የተገኙ ዝርያዎችን ስያሜ መስጠት ቀላል አይደለም ፤ አዲስ ፈጣሪ መሆን ይጠበቅባቸዋል። አንድ ጥገኛ ተህዋስ የእውቁን ጃማይካዊ የሬጌ ሙዚቃ አቀንቃኝ የቦብ ማርሌን ስያሜ አግኝቷል ግናሺያ ማርሌይ በሚል። ሌላ የአሳ ዝርያም ከእንግሊዛዊው የእንስሳት ባህርይ፣ ዝግመተ ለውጥ እና የሥነ ሕይወት ተመራማሪ ሪቻርድ ዳውኪንስ ስም ዳውኪንሺያ ተብሎ ይጠራል። በአንድ አነስተኛ ፓርክ የሚገኙ በሕይወት የሚገኙና የጠፉ ዝርያዎችም በእንግሊዛዊው ጋዜጠኛ ዴቪድ አቶንቦሮው ተሰይመዋል። የጣና ሐይቅን ሌሎችም አረሞች ያሰጉታል የቢቢሲ ጋዜጠኛ ዴቪድ አቶንቦሮው ተከታታይ በሆኑትና የተፈጥሮ ታሪኮችን በተመለከቱ ዘጋቢ ፊልሞች ይታወቃሉ። አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ተመራማሪዎቹ በሚያደንቋቸው ዝነኞችን እና እውቅ ሰዎች እንስሳትን ይሰይማሉ። ለምሳሌ በአየር ንብረት ለውጥ ተሟጋቿ ግሬታ ተንበርግ እንደተሰየመችው ኤን ግሬቴ የተሰኘች ይህችን ጥንዚዛ ወይም በእውቁ አሜሪካዊ ተዋናይና የአካባቢ ጥበቃ አምበሳደር ሊኦናርዶዲካርፒዮ ስም ስፒንታረስ ሊኦናርዶዲካርፒዮ እንደተባለው ሸረሪት። በሌላ ጊዜ ደግሞ ዝነኞች በተለየ ከሚወዷቸው እንስሳት ጋር በማያያዝ ስያሜው ይሰጣሉ። ሌሙር ተብለው የሚታወቁት እንስሳት በእንግሊዛዊው ተዋናይ እና ኮሜዲያን ጆን ክሊስ ስም አቫሂ ክሊሲ ተብለው ይጠራሉ። ሌላኛው ደግሞ የእንስሳቶቹ መልክ ከዝነኞቹ ጋር ተቀራራቢነት ካለው በዚያ ሰው ስም ይሰየማሉ። ለምሳሌ ወርቃማ ፀጉር ያለው ዝንብ በአሜሪካዊቷ ድምፃዊና ተዋናይት ቢዮንሴ ስካፕሺያ ቢዮንሴ ተብሎ ተሰይሟል። ኒኦፓልፓ ዶናልድ ትራምፒ ም ተብሎ በአሜሪካው ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ስም የተሰየመ የእሳት እራት አለ። ስያሜው በሥነ ሕይወት ተመራማሪው ቫዝሪክ ናዛሪ ከሁለት ዓመታት በፊት የተሰጠ ነው። የእሳት እራቱ ወርቃማ ጭንቅላት ያለው ሲሆን በአንፃራዊነት ትንሽ የመራቢያ አካል ያለው ነው። ባሳለፍነው ዓመት ሌላ እንስሳም በፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ስም ተሰይሟል። እንስሳው በአሸዋ ውስጥ ጭንቅላቱን በመቅበር የሚታወቀው የውሃ ውስጥ እንስሳ ነው። ዘ ደርሞፊስ ዶናልድ ትራምፒ የተባለው እንስሳ ይህንን ስያሜ ያገኘው ፕሬዚደንቱ በአየር ንብረት ለውጥ ላይ የሰጡትን አስተያየት ተከትሎ ነው። የሆሊውዱ ሃኪም ገብረወልድን ያውቁታል የቤት እንስሳትም ቢሆኑ የራሳችሁን ስም ካለወጣችሁላቸው በስተቀር በሳይንሳዊ መንገድ የተሰጣቸውን ስም ይዘው መቀጠላቸው እሙን ነው። ታዲያ አንዳንዴ እንዲህ ዓይነት ስያሜ መስጠት አደገኛ ሊሆን ይችላል። ዐይነ ስውር የዋሻ ጥንዚዛ አኖፍታልመስ ሂትለሪ ተብሎ በአውሮፓዊያኑ በጀርመናዊ አድናቂው አማካኝነት በናዚ ፓርቲ መሪና ፖለቲከኛ በነበረው አዶሊፍ ሂትለር ስም ከተሰየመ በኋላ ስሙን ይዞ ቀጥሏል። ተያያዥ ርዕሶች