topic
stringlengths
16
333
news
stringlengths
16
46.2k
የህንድ ፊልም አፍቃሪዎች ወተት እየሰረቁ ነው
ጃንዩወሪ ማጋሪያ ምረጥ በደቡባዊ ህንድ ታሚል ናዱ ግዛት የሚገኙ ወተት ሻጮች መጠነ ሰፊ የወተት ዝርፊያ እየተካሄደባቸው መሆኑን ለፖሊስ ገልጸዋል። ህንድ ውስጥ በአንዳንድ ሃይማኖታዊ ሥርዓቶች ላይ ለመልካም ዕድል እየተባለ አማልክት ላይ ወተት ማፍሰስ የተለመደ ነው። ታዲያ ይህንን ባህል በመከተል በግዛቲቱ የሚገኙ የፊልም አፍቃሪዎች የሚወዱት ፊልም ስኬታማ እንዲሆን በማለት ግዙፍ ማስታወቂያዎች ላይ ወተት ማፍሰስ ከጀመሩ ሰነባብተዋል። ወተቱን የሚያመጡት ደግሞ ከሻጮች በመስረቅ መሆኑ ነገሩን ትንሽ ለየት ያደርገዋል። የወተት ሻጮቹ በፊልም አፍቃሪዎቹ ምክንያት ከባድ ኪሳራ እንደደረሰባቸው በምሬት ለፖሊስ አስታውቀዋል። የወተት ሻጮች ማህበሩ ፕሬዝዳንት ደግሞ ይህ ሥነ ሥርዓት የሚካሄደው ለአማላክት እንጂ ለፊልም ተዋናዮች አይደለም ሲሉ ተቃውሟቸውን አሰምተዋል። ፖሊስ አፋጣኝ እርምጃ እንዲወስድ ማህበሩ የጠየቀ ሲሆን ፖሊስም አታስቡ እርምጃ እወስዳለሁ ብሏቸዋል። ፓላቢሼካም በመባል የሚታወቀው ሥነ ሥርዓት የሚካሄደው ፊልሙን ለማስተዋወቅ በተሰቀሉ ግዙፍ ማስታወቂያዎች ላይ እና የፊልም ተዋናዮቹ ትንንሽ ምሥሎች ላይ ወተት በማፍሰስ ነው። ይህ ለ ዓመታት ሲደረግ ነበር ሥነ ሥርዓት አድናቂዎቹ የወደዱት ፊልም ስኬታማ እንዲሆን ያደርገዋል ተብሎ ይታመናል። በታሚል ናዱ ግዛት የሚገኙት የወተት አከፋፋዮች በትልልቅ መኪናዎች የሰበሰቧቸውን ወተቶች በየሱቆቻቸው ደጃፍ ላይ በማስቀመጥ ነው የሚሸጧቸው። እነዚህ ለማዳ የተባሉት የወተት ቀበኞች ታዲያ አሳቻ ሰዓት በመጠበቅና ባለሱቆቹ ሲዘናጉ የቻሉትን ያህል ወተት ተሸክመው ይሮጣሉ፤ አልያም በመኪናቸው ይዘው ይሰወራሉ። ታማሚዋን ያስረገዘው ነርስ በቁጥጥር ስር ዋለ ታዋቂው የቦሊዉድ ፊልም ተዋናይ ሲላምባርሳን አዲስ የለቀቀው ፊልሙ ተወዳጅ እንዲሆንለት አድናቂዎቹ በየመንገዱ የተሰቀሉ ማስታወቂያዎችን ወተት በወተት አድርገዋቸዋል። እሱም ወተት እንዲያፈሱለት የተማጽኖ መልእክት አስተላልፎ ነበር። ታዲያ ታዋቂው ፊልም ተዋናይ የለቀቀው ተንቀሳቃሽ ምሥል በታሚል ናዱ ግዛት ብዙ ተቀባዮችን ማግኘቱ የወተት ሻጮችን ሕይወት ከባድ አድርጎታል እየተባለ ነው። ተያያዥ ርዕሶች
የአማራ ክልል ተፈናቃዮች ስለ ንግድ ባንክ እርዳታ ምን ይላሉ
ማርች ማጋሪያ ምረጥ በአማራ ክልል የሚገኙ ከ ሺህ በላይ የሚሆኑ ተፈናቃዮችን መልሶ ለማቋቋም የተለያዩ ጥረቶች እየተደረጉ ነው። በዚሁ መሰረት ተቋማትና ግለሰቦች እጃቸውን እየዘረጉ ነው። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክም በአገሪቱ የተለያዩ ክልሎች በተለያየ ምክንያት ለተፈናቀሉ ዜጎች ድጋፍ ይሆን ዘንድ ገንዘብ ለግሷል። ንግድ ባንክ ተፈናቃዮችን ለመደገፍ የመደበው መቶ ሚሊዮን ብር ሲሆን ከዚህ ውስጥ ለአማራ ክልል ተፈናቃዮች የመደበው ሚሊዮን ብር ሲሆን የክልሉ የድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ ይህን እርዳታ አልቀበልም ማለቱ ብዙ አስብሏል፤ ብዙዎችንም አነጋግሯል። የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ተፈናቃዮች ለችግር ተዳረግን አሉ ለተፈናቃዮች የሚውል የእርዳታና የድጋፍ ያለህ እየተባለ ባለበት በዚህ ወቅት እንዴት እርዳታ አያስፈልገኝም ይባላል ድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴው እርዳታውን እንደማይቀበል ማሳወቁን ተከትሎ ብዙዎች ያነሱት ጥያቄ ነው። የክልሉ የድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ አገኘሁ ተሻገር ምክንያታችን ለንግድ ባንክ ካለን ክብር የመነጨ ምላሽ ነው የሰጠነው ይላሉ። ተፈናቃዮችን ለማቋቋም ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የድጋፍ ጥያቄ አቅርበን ነበር የሚሉት ሰብሳቢው ንግድ ባንክ በመላ አገሪቱ ያሉ ተፈናቃዮችን ለመደገፍ እንደሚፈልግ እንደገለፀላቸው ያነሳሉ። እርሳቸው እንደሚሉት ከተለያዩ ባንኮች ከ ሚሊዮን ብር ጀምሮ የተለያዩ ድጋፎችን ተቀብለዋል። ይሁን እንጂ ከንግድ ባንክ ያገኙት የድጋፍ ክፍፍል የችግር መጠን ያላገናዘበና ከሚፈለገው በታች ሆኖ ስላገኙት ድጋፉን ላለመቀበል መወሰናቸውን ይናገራሉ። የድጋፍ አሰጣጡ ቀመር ስላልገባን ይህንን ድጋፍ ተቀብለን የንግድ ባንክን ክብር ከምንነካ፣ ይህ ዝቅተኛ ድጋፍ ለአማራ ህዝብ የሚመጥን ባለመሆኑ አለመቀበል ይሻላል በሚል ከውሳኔው ላይ እንደደረሱ ለቢቢሲ ገልፀዋል። ጌዲዮ በዐቢይ ጉብኝት ማግስት ንግድ ባንክ እርዳታውን የበጀተበትን ቀመር አለማወቅ ብቻም ሳይሆን ቀመር መስራትም አያስፈልገው ነበር ሲሉ ይከራከራሉ አቶ አገኘሁ። እሳቸው እንደሚሉት ንግድ ባንክ ማድረግ የነበረበት የመደበውን የእርዳታ ገንዘብ ለዚሁ ዓላማ በመንግሥት ለተቋቋመው ለአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን በመስጠት ኮሚሽኑ በተፈናቃይ ልክና በጉዳት መጠን ለክልሎች እንዲያከፋፍል መተው ነበር። ያነጋገርናቸው በአማራ ክልል ጊዜያዊ መጠለያ የሚገኙ አንዳንድ ተፈናቃዮች በበኩላቸው ያገኙትን ድጋፍ ይዘው ወደ ቀያቸው የመመለስ ከፍተኛ ፍላጎት ያላቸው ከመሆኑ አንፃር ይህን የንግድ ባንክ ድጋፍ አልቀበልም ማለት ትክክል እንዳልሆነ ገልፀውልናል። ይህ ነገር ስህተት ነው፤ ምክንያቱም ብዙ ሰዎች አደጋ ላይ ነው ያሉት። ለምሳሌ እንደ ግራር አውራጃ ብዙ ሰዎች ቤታቸው ተቃጥሏል፣ ንብረታቸው ወድሟል፣ አምስትም አስር ብርም ቢደርሳቸው ለእነሱ ጥቅም ነው ብዬ ነው የማስበው ስትል ሳሮን ባይሳ የተባለች ተፈናቃይ ለቢቢሲ ተናግራለች። ቻይና የኤርባስ አውሮፕላኖችን ልትገዛ ነው ይህ ውሳኔ ያለምክንያት እንዳልሆነ የሚገምቱ ተፈናቃዮችም ያሉ ሲሆን የዚህ አይነት ስሜት ካላቸው ሌላኛው ተፈናቃይ አንዱዓለም ነበይ መቼም ከውስጡ የሆነ ነገር ይኖረዋል እንጂ ህብረተሰቡ በችግር ላይ ነው ያለው፤ እርዳታው ተፈላጊ ነው ብለውናል። በክልሉ ነፍሰጡር እናቶች፣ ህፃናትና አዛውንት ተፈናቃዮች ከባድ ችግር ውስጥ እንደሚገኙ ቢቢሲ ከጥቂት ሳምንታት በፊት በርካታ ተፈናቃዮች በሚገኙበት በአይምባ መጠለያ ተገኝቶ ዘገባ ሰርቶ ነበር። የአሜሪካው ኩባንያ በኬንያ ካናቢስ ለማብቀል ፍቃድ አገኘ ተባለ በክልሉ ተፈናቃዮች ያሉበትን ፈታኝ ሁኔታ በመገንዘብ እርዳታውን አልቀበልም ያለው የድጋፍ አሰባሳቢው ኮሚቴ ላይ ኩራት ወይስ ዳቦ የሚል ጠንካራ ትችት የሰነዘሩም እንዳሉ ያነሳንላቸው የኮሚቴው ሰብሳቢ አቶ አገኘሁም የዚህ አይነቱ ሃሳብ የፅንፈኞችና ለአማራ ክልል ህዝብ ንቀት ያላቸው ሰዎች ሃሳብ ነው በማለት ጠንከር ያለ ምላሽ ይሰጣሉ። የአማራ ህዝብ አይኮራም፤ ኮርቶም አያውቅም። ከኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ጋር በእኩልነት የሚያምን ህዝብ ነው ይላሉ። የድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴውን መግለጫ ተከትሎ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሰጠው ምላሽ እንደሌለ አቶ አገኘሁ ጨምረው ተናግረዋል። ተያያዥ ርዕሶች
የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ ሰማኒያ ሚሊዮን ብር እንዴት ተዘረፈ
ጃንዩወሪ ማጋሪያ ምረጥ ከጥቂት ሳምንታት በፊት የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ ንብረት የሆነ ገንዘብ ከአንድ ቅርንጫፍ ወደ ሌላው ሲዘዋወር እንደተዘረፈ ተሰምቷል። ታህሳስ ፣ ዓ ም በምዕራብ ሐረርጌ ዞን ዋና ከተማ ጭሮ ውስጥ የሚገኘው የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ ሚሊዮን ብር ወጭ ያደርጋል። ገንዘቡን ወደ ደብረ ዘይት ቅርንጫፉ ለማዘዋወርም ጉዞ ይጀምራል። ሆኖም ገንዘቡን የጫነው መኪና የታሰበበት ሳይደርስ መኤሶ ወረዳ አሰቦት አካባቢ መሳሪያ በያዙ ሰዎች ተከበበ። ከዚያስ የምዕራብ ሐረርጌ ዞን ፖሊስ መምሪያ ሐላፊ ኮማንደር ጋዲሳ ንጉሳ በዚህ ጉዳይ ላይ የሚከተለውን ብለዋል የተወሰኑ ኃይሎች ሽጉጥ የያዙ እንዲሁም ባዶ እጃቸውን የነበሩ ግለሰቦች መኪናውን መንገድ ላይ አስቆሙት። ሾፌሩን አስፈራርተው በማስወረድ አሰቦት ወደምትባል አካባቢ መኪናዋን ወሰዷት ከተዘረፈው ሚሊዮን ብር ውስጥ በሽምግልና፣ በድርድርና በፍተሻ ማስመለስ የቻሉት ገንዘብ እንዳለም ይናገራሉ። ይህን ያህል ገንዘብ አስመልሰናል ለማለት ሰነድ ባያጠናቅሩም እጅ ከፍንጅ የተያዘ ገንዘብ የለም። አብዛኛው ብር የተመለሰው በጥቆማ ነው። በርካታ መኪና ይዘው ሲሄዱ በፍተሻ የተያዙ አሉ ብለዋል። ጫትን ማገድ ፈፅሞ የሚቻል አይደለም ዶ ር ዘሪሁን መሃመድ ለመሆኑ አንድ ባንክ ከአንድ ቅርንጫፍ ወደ ሌላ ቅርንጫፍ ገንዘብ ሲያዘዋውር የሚደረግለት የጥበቃ ኃይል ወደየት ሄዶ ነው ዝርፊያው ሊፈፀም የቻለው በሚል ቢቢሲ ኮማንደሩን ጠይቋል። በወቅቱ አብረው የነበሩት ፖሊሶች ከአቅማቸው በላይ ስለሆነ መያዝ አልቻሉም። ወደ ሌላ እርምጃ ከተገባ በነሱም ደህንነት ላይ አደጋ ስለሚመጣ በልመናና በድርድር ገንዘቡን መውሰድ እንዲያቆሙ ለማድረግ ተሞክሯል። ማስፈራራትና ወደ ሰማይም ተተኩሷል። ዘራፊዎቹ በቁጥር ብዙ እንደነበሩ የሚናገሩት ኮማንደሩ፤ ዘራፊዎቹ ገንዘቡን ከዘረፉበት ቦታ ወደ ከተማ ይዘው ከሄዱ በኋላ ለመከፋፈል ሲሞክሩ የከተማው ከንቲባ የሕዝብ ንብረት ነው ብለው በድርድር ለማስቆም ቢሞክሩም እንዳልተሳካላቸው ይገልጻሉ። ፎርቹን ጋዜጣ፤ ብሩ ወደ አዲስ አበባ መጓጓዝ ላይ እንደነበር ጠቅሶ ግለሰቦች በዝርፊያው ተጠርጥረው ተይዘዋል ሲል ዘግቧል። እናትና ልጇቿ ለወር አበባ በተገለለ ጎጆ ህይወታቸው አለፈ ከዘረፋው ጀርባ ያሉ ሰዎችን ማንነት ለማወቅ ምርመራ እየተደረገ መሆኑን ኮማንደሩ ቢናገሩም፤ ዘራፊዎቹ ከሩቅ የመጡ አይደሉም የሚል ጥቆማ ሰጥተዋል። ከዚህ ቀደም የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ ከድሬዳዋ ቅርንጫፍ ሚሊዮን ብር ጭኖ በመኢሶ ወረዳ ሲተላለፍ ነበር። ያኔ ገንዘቡን ይዞ ይጓዝ የነበረው መኪና አሽከርካሪ አህያ ገጭቶ በአካባቢው ፖሊስ ተይዟል። በወቅቱ የተገኘው ገንዘብና አጓጓዡ የያዘው ሰነድ ላይ የሰፈረው የገንዘብ መጠን መካከል ልዩነት ተፈጥሮ እንደነበር ይታወሳል። ገንዘቡን መጫን የነበረበት መኪና ሰሌዳ ቁጥርና በፖሊስ የተያዘው መኪና ታርጋ ቁጥርም የተለያየ ነው ተብሎ ነበር። ለመሆኑ የዚህ ገንዘብ ጉዳይ ከምን ደረሰ ኮማንደር ጋዲሳ ምላሽ አላቸው። አምሳ ሚሊዮኑን የሚያሳይ ሰነድ በገንዘብ ያዡ እጅ አልነበረም። ይህም ከኔትወርክ ችግር ጋር የተያያዘ ነው። መንገድ ላይ በኢሜይል እንልክላችኋለን የሚል ነገር ነበር ገንዘቡ ከወጣበት ቅርንጫፍ ጀምሮ ስለነበረው ሂደት ምርመራ ተእየተደረገ መሆኑንም ተናግረዋል። መጀመሪያ ገንዘቡን ይጭናል ተብሎ የነበረው መኪና ሰሌዳው ቁጥር ሌላ ሲሆን፤ ይህም በአጋጣሚ ገንዘቡን ይጭናል ተብሎ የታሰበው ሾፌር በህመም ላይ ስለነበር ነው ብለዋል። ስለ ሹፌር ለውጥ የሚገልጽ ደብዳቤ ሳይቀየርብ ሌላ መኪና በመተካቱ ነው ሲሉ የድሬዳዋ ስራ አስኪያጅ እንደነገሯቸው ኮማንደሩ ገልፀዋል። ገንዘቡ ህጋዊ መሆኑን ነው የምናውቀው። አሁን ምርመራ ላይ ነው። በቅርብ ይፈታል የሚል እምነት አለኝ ብለዋል። መኪና ውስጥ የተገኘው ገንዘብ ጉዳይ እስኪጣራ ድረስ ገንዘቡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዳማ ቅርንጫፍ ውስጥ እንዲቆይ መወሰኑንም ኮማንደር ጋዲሳ ገልፀዋል። ተያያዥ ርዕሶች
ብሄራዊ ባንክ ከዓለም አቀፉ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን ጋር የግሉን ዘርፍ ለማገዝ ስምምነቶችን አደረገ
ዲሴምበር ስለ ማጋራት ተጨማሪ ያጋሩ ማጋሪያ ምረጥ የዓለም አቀፉ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስኪያጅ ፍሊፕ ለ ዌሩ በኢትዮጵያ በነበራቸው የስድስት ቀናት ይፋዊ ጉብኝት ወቅት ብሄራዊ ባንክ ከኮርፖሬሹ ጋር የግሉን ዘርፍ ለማገዝ ስምምነቶችን አደረገ ነው። የመጀመሪያው ስምምነት ዓለም አቀፉ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን ለተመረጡ የኢትዮጵያ ባንኮች በዓለም አቀፍ የንግድ ፋይናንስ መርኃ ግብር አማካይነት ድጋፍ የሚያደርግበት ሲሆን ሁለተኛው ስምምነት ደግሞ ኮርፖሬሽኑ ለኢትዮጵያ በብር ብድር የሚያቀርብበት ነው ተብሏል። የዛሬው ስምምነት ኢትዮጵያ ለግሉ ዘርፍ ዕድገት ያላትን ቁርጠኛነት ይጠቁማል ሲሉ በፊርማ ስነ ስርዓቱ ላይ የተናገሩት የፋይናንስ እና የኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ ናቸው።አቶ አህመድ ጨምረውም መንግሥት የፋይናንስ ዘርፉን ለማሳደግ ከፖሊሲ ምርመራ አንስቶ እየሰራ መሆኑን አስረድተዋል። የብሄራዊ ባንክ ገዥ ይናገር ደሴ በበኩላቸው ስምምነቶቹ ኢትዮጵያ ላጋጠማት የውጭ ምንዛሬ እጥረት ችግር የመፍትሄ አካል ከመሆኑም በላይ ለግሉ ዘርፍ ፋይናንስ በማቅረብ ረገድ ከፍ ያለ ሚና አለው ብለዋል። ቁርስ የቀኑ እጅግ አስፈላጊ ምግብ ነውን ለግሉ ዘርፍ የፋይናንስ ምንጩን ማብዛት አለብን፤ ይህ የዚህ ስምምነት አንደኛው አካል ነው ብለዋል ገዥው።ከዚህም በተጨማሪ የግሉን ዘርፍ ባካተተ ሁኔታ የካፒታል ገበያ በኢትዮጵያ አውድ እንዴት ሊሠራ እንደሚችል ጥናት እያካሄድን ነው ሲሉ የባንኩ ገዥ አክለው ተናግረዋል።ዓለም አቀፉ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን አይኤፍሲ በዓለም ባንክ ሥር የግሉን ዘርፍ የሚመለከት ክንፍ ሆኖ የተቋቋመው እ ኤ አ በ ዎቹ አጋማሽ ሲሆን በማደግ ላይ ባሉ አገራት የግሉን ዘርፍ ዕድገት የማበረታትን ሥራ ይከውናል። አይኤፍሲ አባል ሆነው በመሠረቱት አገራት ባለቤትነት የተያዘ እና የሚተዳደር ተቋም ነው። ፈረንሳይዊው ፍሊፕ ለ ዌሩ እ ኤ አ ከመጋቢት አንስቶ የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሆነው በማገልገል ላይ ይገኛሉ።ሥራ አስኪያጁ በኢትዮጵያ የስድስት ቀናት ቆይታቸው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ እና ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴን ጨምሮ ከከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ጋር የተገናኙ ሲሆን የሃዋሳ ኢንዱስትሪያል ፓርክንም ጎብኝተዋል። ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን የሥራ ኃላፊዎች ጋር በነበራቸው ቆይታ የመንግስት እና የግሉ ዘርፍ እርስ በእርስ እንዲተማመኑ እንደሚያስፈልግ መናገራቸውን የኮሚሽኑ ኮሚሽነር አቶ ፍፁም አረጋ በትዊተር ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት ፅሁፍ ጠቅሰዋል። ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የንግድ ሥራ ክንውን የሚያቀላጥፉ የማሻሻያ እርምጃዎችን ለመውሰድ በኮሚሽኑ እና በኮርፖሬሽኑ መካከል የትብብር ስምምነት ላይ መደረሱንም አቶ ፍፁም አክለው ገልፀዋል።ሥራ አስጂያጁ በልጅነታቸው ወቅት አዲስ አበባ በሚገኘው የሊሴ ገብረማርያም ትምህርት ቤት ትምህርታቸውን ተከተታትለው የነበረ ሲሆን በቆይታችው ወቅት ትምህርት ቤቱን እንደጎበኙ ዛሬ ሰኞ ቀትር ላይ ለጋዜጠኞች ባደረጉት ገለፃ ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ባንኮች ከተለያዩ የዓለም አገራት ባንኮች ጋር የብድር ስራን በሚያከናውኑበት ወቅቅ በቂ የሆነ የውጭ ምንዛሬ ክምችት ካልተገኘ በስራው ላይ ችግሮች እንደሚፈጠሩ ያስረዱት የብሄራዊ ባንክ ገዥ ይናገር ደሴ፤ የዛሬው ስምምነት አይኤፍሲ ዋስትና እንደሚሰጥ የሚያረጋግጥ በመሆኑ፤ ይህም የኢትዮጵያ ባንኮች ከውጭ አገራት አቻዎቻቸው ጋር ያላቸውን ስራ የሚያቀል ነው ብለዋል። ሲጠቃለሉ ሁለቱ ስምምነቶች ተጨማሪ ዶላር ላገሪቱ ያስገኛሉ፤ ለግሉ ዘርፍ ተጨማሪ ኢንቨስትመንት ያመጣል፤ ላገጠመን የውጭ ምንዛሬ ችግር ዋስትና ይሰጣል ሲሉ ተናግረዋል። ተያያዥ ርዕሶች
ኢትዮጵያና ኤርትራ፡ አዲስ ዓመትን በቡሬና በዛላምበሳ
ሴፕቴምበር ማጋሪያ ምረጥ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድና ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ሁለቱን ሃገራት በሚያዋሰኑባቸው በቡሬ በዛላምበሳ አካባቢዎች ተገኝተው ከሕዝቡና ሠራዊታቸው ጋር አዲስ ዓመትን አከበሩ። ይህ በሁለቱ ሃገራት መካከል የተጀመረውን ግንኙነትን የማሻሻል እርምጃን ተከትሎ ተዘግተው የነበሩትን የሁለቱን ሃገራት የድንበር መተላለፊያዎች በመክፈት በኩል ትልቁ እርምጃ ነው ተብሏል። በትናንትናው ዕለት ከሃያ ዓመታት በፊት ሁለቱ የሃገራት የድንበር ጦርነት ሲቀሰቀስ ጀምሮ ተዘግቶ የነበረው ከዛላምበሳ ወደ ሰንዓፈ የሚወስደውን መንገድ ተከፍቷል። መቐለ በምፅዋ በአካባቢው የነበሩ የዓይን እማኞች እንደተናገሩት ከዚህ በተጨማሪ በስፍራው የነበረው የኤርትራ ጦር ምሽግም እንዲፈርስ ተደርጓል። ሁለቱን ሃገራት የሚያገናኘው የድንበር መተላለፊያ አካባቢ ተቀብረው የነበሩ ፈንጂዎችን ማፅዳት ሥራ በሁለቱም ሠራዊት አባላት በጋራ ሲያከናውኑ ማየታቸውን የዓይን እማኞቹ ተናግረዋል። የሁለቱ ሃገራት መሪዎች በሌላኛው ሃገር ያደረጉትን ጉብኝት ተከትሎ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን ከማደሳቸው ባሻገር የአየር ትራንስፖርት ተጀምሯል። ከፍተኛ ትኩረት የተሰጠው ከጂቡቲ በተጨማሪ ኢትዮጵያ ለወጪና ለገቢ ቁሳቁሶች ማንቀሳቀሻ ሁለቱን የኤርትራ ወደቦችን እንድትጠቀም ማስቻል ቀጣዩ እርምጃ እንደሚሆን ተነግሯል።
የዱቄት ወተት እና የእናት ጡት ወተት ምንና ምን ናቸው
ኖቬምበር ማጋሪያ ምረጥ መርዛማ ጋዝ እና የቀለጠ አለት ተቀላቅለው ከ ታምቦራ ተራራ በንፋስ ፍጥነት ሺዎችን እየገደሉ ይንደረደራሉ። ግዙፉ የታምቦራ ተራራ በ ሜትር አጥሯል። ይህ የሆነው በ ነበር። ቀስ በቀስ የአመድ እሳተገሞራ ወደ ሰሜናዊው ንፍቀ ክበብ በማምራት ፀሀይን ጋረዳት። በ አውሮጳ ያለ ክረምት ያለፈ ዓመት ሆነ ፤ ሰብሎች ደረቁ። ረሃብ የጠናባቸው ሰዎች አይጦችን፣ድመቶችን እና ሳር ተመገቡ። በጀርመኗ ዳርምስታድት ከተማ የዚህ ጉስቁልና ጥልቀት ለ ዓመቱ የፈጠራ ሃሳብ ፈነጠቀለት። ጀስተስ ቮን ሊይቢግ አባቱን በስራ ቦታው ቀለም በመቀባት፣ በመወልወል እና በማቀራረብ ማገዝ ይወድ ነበር። ጥልቅ ጥናት ሊይቢግ ርሃብን የመከላከል ምኞትን ሰንቆ ምርጥ የኬሚስትሪ ባለሙያ ሆኖ አደገ። በማደበሪያ ላይ የተደረጉ የቀደሙ ምርምሮችን ሰርቷል። የስነምግብ ሳይንስ ምርምርም ፈርቀዳጅ ነው። ይህ ብቻ አይደለም ሌላም ነገር ፈጥሯል፡ የዱቄት ወተትን። ሊይቢግ በ ያስተዋወቀው ለህፃናት ያዘጋጀው ሟሚ ምግብ ከላም ወተት፣ከስንዴና ከብቅል ዱቄት እንዲሁም ከ ፖታሺየም ካርቦኔት የተዘጋጀ ነበር። ይህ የእናት ጡት ወተትን ተክቶ ለገበያ የቀረበ የመጀመሪያው የምርምር ውጤት ነበር። ሊይቢግ እንዳስተዋለው ሁሉም ህፃን ጡት የሚያጠባው እናት የለውም። ዘመናዊ ህክምና ሳይስፋፋ በፊት ከ ነፍሰጡር እናቶች መካከል አንዷ በወሊድ ምክንያት ትሞት ነበር። ዛሬ ይህ ቁጥር በድሃ አገራት በመጠኑ የተሻሻለ ነው። አንዳንድ እናቶች ደግሞ ጡታቸው ወተት አያግቱምም፤ ቁጥሩ አከራካሪ ቢሆንም ከሃያ እናቶች መካከል አንዷ ይህ አይነት ነገር እንደሚገጥማት ይገመታል። ታዲያ የዱቄት ወተት ከመፈብረኩ በፊት እነዚህ ህፃናት ምን ይውጣቸው ነበር አቅሙ ያላቸው ወላጆች ልጃቸውን የሚያጠባላቸው ነርስ ይቀጥሩ ነበር፤ ከሊይቢግ ፈጠራ በፊት ጥሩ ገቢ የሚገኝበት ስራ ነበር። አንዳንዶች ደግሞ ፍየል ወይም አህያን ይጠቀሙ ነበር። አጭር የምስል መግለጫ ጀስተስ ቮን ሊይቢግ የፈጠራ ሃሳቡ የመጣለት አዳጊ እያለ የተመለከተው ረሃብ ነበር ጥሩ ግጥምጥሞሽ በርካቶች ለጨቅላዎቻቸው ዳቦ በውሃ አላቁጠው ይመግቡ ነበር፤ ይህ ደግሞ የመመገቢያ እቃው በቀላሉ በባክቴሪያ ስለሚበከል የጨቅላው ጤና አደጋ ላይ ይወድቃል። በ ዎቹ የመጀመሪያ አመታት የእናታቸውን ጡት ወተት ማግኘት ካልቻሉ ሶስት ህፃናት መካከል ሁለቱ ብቻ ነበሩ በህይወት መኖር የሚችሉት። የሊይቢግ የዱቄት ወተት በዚህ ወሳኝ ወቅት ነበር ገበያውን የተቀላቀለው። የጀርም ቲየሪ በሚገባ ተዋውቆ ነበር፤ የጡጦ ጫፍም ተፈብርኮ ነበር። በዚህ ወቅት የዱቄት ወተትም ጡት ማጥባት ካልቻሉ እናቶች በላይ ፈጥኖ ተሰራጨ። የሊይቢግ ለህፃናት የተዘጋጀ ሟሚ ምግብ ቀደም ሲል ጥሩ የኑሮ ዘይቤ ለሚመሩ ብቻ የነበረው አስቀርቶ ለሁሉም መድረስ ቻለ። አሁን ደግሞ ዘመናዊ የስራ ቦታን መልክ ለመስያዝ የሚመረጥ ሆኗል። ከወለዱ በሗላ ወደ ስራ መመለስ ለሚፈልጉ በርካታ እናቶች የዱቄት ወተት የፈጣሪ በረከት ሆኖ ቀረበ። የገቢ ክፍተት በቅርቡ የቺካጎ ዩኒቨርስቲ ከማስተርስ ዲግሪ መርሃ ግብር ወጥተው በማማከር እና በፋይናንስ አለም ወደስራ የገቡ ከፍተኛ ሃላፊነት ያላቸው ወንዶችና ሴቶች ላይ ጥናት አድርጎ ነበር። መጀመሪያ ላይ በወንዶች እና በሴቶች መካከል ያለው የገቢ መጠን ተመሳሳይ ይመስል ነበር። ከጊዜ በሗላ ላይ ግን ከፍተኛ የሆነ የገቢ ልዩነት መታየት ጀመረ። ይህ ደግሞ የሆነው በወሊድ ጊዜ ነው። ሴቶች ሲወልዱ ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ከስራ እረፍት ይወስዳሉ በምላሹ ቀጣሪዎች አነስተኛ ክፍያ ይከፍሏቸዋል። በተገላቢጦሽ ከሴቶች የበለጠ ልጅ ያላቸው ደግሞ ወንዶች ናቸው። ነገር ግን የስራ ጊዜያቸውን አይቀይሩም። ሴቶች ብቻ አምጠው መውለድ የመቻላቸውን ሀቅ ልንቀይረው አንችልም፤ነገር ግን የስራ ቦታ ባህሉን ልናስተካክለው እንችላለን። አንዲት ወላድ እናት ከወሊድ በሗላ ወደ ስራዋ ስትመለስ አባቶች ልጃቸውን ለመንከባከብ የዱቄት ወተት ቀላል ያደርግላቸዋል። በርግጥ የጡት ማለቢያ አማራጭ አለ። ነገር ግን ለአንዳንዶች ይህ ከዱቄት ወተት በላይ ጥረት የሚጠይቅ ነገር ነው። በ በህክምና የጥናት መፅሄቶች ላይ የዱቄት ወተት የጎንዮሽ ጉዳቶችን የሚያሳዩ በርካታ ጥናቶች ታትመዋል። የዱቄት ወተት የሚጠጡ ህፃናት የእናታቸውን ጡት ከሚጠቡ ህፃናት በበለጠ ይታመማሉ፤ በዚህም የተነሳ ወላጆች የህክምና ወጪያቸው ይጨምራል፤ እንዲሁም ከስራ ገበታቸው ላይ በተደጋጋሚ ይቀራሉ። ጡት በማጥባት ብቻ ግማሽ ያህል የህፃናት ተቅማጥን እና ሶስት እጅ የሚሆነውን ከመተንፈሻ አካላት ጋር የተያያዘ ኢንፌክሽንን መከላከል እንደሚቻል ይታመናል። በዚህ ጥናት መሰረት የእናት ጡት ወተት በአመት ያህል የህፃናት ሞትን መከላከል ያስችላል። ታዲያ ሕይወት ለመታደግ ለፈለገው ጀስተስ ቮን ሊይቢግ ይህ አስደንጋጭ ነው። አጭር የምስል መግለጫ ጨቅላ ህፃናትን የእናት ጡት ማጥባት በአመት ከ በላይ የህፃናት ሞትን እንደሚከላከል አጥኒዎች ያምናሉ ኢኮኖሚያዊ አንድምታው እርግጥ ነው ባደጉት ሃገራት የተበከለ ወተት እና ውሃ ጉዳይ ያን ያህል ራስ ምታት አይደለም። የዱቄት ወተት ግን ሌላ ኢኮኖሚያዊ ገፅታ አለው። በላንሰንት ጥናት መሰረት የእናታቸውን ጡት እየጠቡ ያደጉ ልጆች የአይ ኪው መጠናቸው ከሌሎቹ በሶስት ነጥብ ከፍ ያለ ነው። ይህ ታዲያ ትውልዱን ሁሉ ባለ ምጡቅ አዕምሮ ለማድረግ ምን ያህል ይሆናል ጥናቱ ይህንንም አስልቶታል። በአመት ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር ያህል ያስወጣል። ይህ ደግሞ የአለም የዱቄት ወተት ገበያ ያህልን ይሆናል። ሊይቢግ ራሱ ለህፃናት ያዘጋጀው ሟሚ ምግብ ከእናት ጡት ወተት ይበልጣል ብሎ ተወራርዶ አያውቅም፤ በተቻለ መጠን በንጥረ ነገር ተመሳሳይ የሆነ ነገር እንደፈጠረ ግን ተናግሯል። ተያያዥ ርዕሶች
ኢትዮጵያና ኤርትራ የመጨረሻውን የሠላም ስምምነት ፈረሙ
ሴፕቴምበር አጭር የምስል መግለጫ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ፣ ንጉሥ ሳልማንና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ የኢትዮጵያና የኤርትራ መሪዎች እሁድ ግንኙነታቸውን የበለጠ የሚያጠናክር ነው የተባለ የሰላም ስምምነት ጅዳ ሳኡዲ አረቢያ ውስጥ ተፈራረሙ። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድና በፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ስለተፈረመው ስለዚህ ስምምነት ዝርዝር ይዘት ይፋ የተደረገ ነገር እስካሁን ባይኖርም፤ የኢትዮጵያ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ስምምነቱን ባለሰባት ነጥብ ስምምነት ብቻ ሲል ገልጾታል። የጅዳው ስምምነት ተብሎ ስለሚጠራው ስምምነት የሳኡዲ ባወጣው መግለጫ ሁለቱ ሃገራት ሕዝብ መካከል ባለው የመልካምድር፣ የታሪክና የባህል የቅርብ ትስስር የሰላም ስምምነቱ በመንግስታቱ መካከል መደበኛ ግንኙነት እንዲፈጠር ያደርጋል ብሏል። ኢትዮጵያና ኤርትራ፡ አዲስ ዓመትን በቡሬና በዛላምበሳ ሁለቱ መሪዎች ስምምነቱን በቀይ ባሕሯ የወደብ ከተማ ጅዳ ላይ በተፈራረሙበት ወቅት የሳኡዲው ንጉሥ ሳልማን፣ አልጋ ወራሽ ሞሃመድ ቢን ሰልማን፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ሼክ አብዱላህ ቢን ዛይድ አል ናህያን እና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬስ ተገኝተዋል። በአፍሪካ ቀንድ ተስፋ የሚሰጥ ንፋስ እየነፈሰ ነው ሲሉ ጉቴሬስ ከፊርማው ሥነ ሥርዓት በኋላ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል። የሰላም ስምምነቱ በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል ብቻ የሚቆም ሳይሆን በኤርትራና በጂቡቲ መካከልም የሚፈፀም ይሆናል ብለዋል። የሰላም ስምምነቱን ተከትሎ ንጉሥ ሳልማን ለኢትዮጵያና ለኤርትራ መሪዎች አብዱልአዚዝ አል ሳኡድ የተባለውን የሃገሪቱን ከፍተኛ ሜዳሊያ አበርክተውላቸዋል። መሪዎቹ ቀደም ሲልም ተመሳሳይ የክብር ሽልማት ከተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ተሰጥቷቸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይና ፕሬዝዳንት ኢሳያስ በሐምሌ ወር አሥመራ ላይ በተገናኙበት ወቅት ባለአምስት ነጥብ የሰላምና የወዳጅነት ባለአምስት ነጥብ ስምምነትን በመፈራረም ለሁለት አስርት ዓመታት የዘለቀውን ጠላትነታቸው እንዲያበቃ አድርገዋል። ተያያዥ ርዕሶች
በየቀኑ ወደ ምድር የሚመጡ እንስሳት ቁጥር ሲሰላ ስንት ይሆን
ጁን ማጋሪያ ምረጥ አእዋፍት፣ ንቦችም፣ ትሎችም ሳይቀሩ ይዋለዳሉ። ምድራችን ወደ ሚሊየን የሚሆኑ እንስሳት መኖሪያ ናት። እነዚህ እንስሳት እንደ ሰው ልጆች በፍቅር ክንፍ ሲሉ ባይታዩም ይዋለዳሉ። ዘር ይቀጥላሉ። ለመሆኑ በየቀኑ በአለም ዙሪያ ስንት እንስሳት ይወለዳሉ ብለው ያስባሉ ቢቢሲ ሞር ኦር ለስ የተሰኘ መርሀ ግብር አለው። ታዲያ ከዝግጅቱ አድማጮች አንዱ አለም በየቀኑ ስንት እንስሳትን ትቀበላለች ሲል ጠየቀ። ዘር በመተካት ረገድ ጥንቸሎች ተወዳዳሪ የላቸውም። ከየትኛውም እንስሳ በላቀ ይዋለዳሉ። እንግሊዝን እንደምሳሌ ብንወስድ የእንግሊዝ የዱር ጥንቸሎች ርቢ ሚሊየን ይደርሳል። አንዲት ጥንቸል ከሶስት ወደ ሰባት ጥንቸሎችን ታፈራለች በሚለው ስሌት በየቀኑ ጥንቸሎች ይወለዳሉ ማለት ነው። ሆኖም ከጥንቸሎች ውስጥ ተወለወደው ብዙም ሳይቆዩ የሚሞቱ አሉና አለም ከምትቀበላቸው ጥንቸሎች ብዙዎቹን ታጣለች። በአንዳንድ አካባቢዎች ብቻ ተወሰወነው የሚኖሩ ብርቅዬ እንስሳትን ደግሞ እንመልከት። በቺሊና ፔሩ የሚኖሩት ሀምቦልት ፔንግዊኖች ጥሩ ምሳሌ ናቸው። እነዚህ እንስሳት የሚራቡት እንቁላል በመጣል ነው። በአንዴ የሚጥሉት ሁለት እንቁላል ሲሆን፣ እያንዳንዳቸው በአመት ሁለት እንቁላል ይጥላሉ። ስለዚህም በቀን ሀምቦልት ፔንግዊኖች እንዲሁም በአመት ይጣላሉ። ወደ ዶሮ አለም እንዝለቅ። የተባበሩት መንግስታት የምግብና እርሻ ዘርፍ ክፍል በቀን ሚሊየን ዶሮዎች ወደ ምድር ይመጣሉ ይላል። በአንጻሩ ንቦች በሞቃትና በቀዝቃዛ ወቅት ዘራቸውን የሚተኩበት ፍጥነት ይለያያል። በሞቃት ወራት ንግስቲቷ ንብ በየቀኑ እንቁላል ትጥላለች። ባጠቃላይ ሞቃታማ ጊዜ ላይ እንቁላል ይጥላሉ። በለንደን ዙስ ኢንስቲትዪት ኦፍ ዙኦሎጂ የምትሰራው ሞኒካ ቦሀም እንደመሚሉት የእንስሳትን አለም ከሀ እስከ ፐ ማወቅ አልተቻለምና ስለሚራቡበት መንገድ የተሟላ መረጃ የለም። የክዊን ሜሪ ዩኒቨርስቲው ፕሮፌሰር ኣክሰል ሮስበርግ በበኩሉ የእንስሳት አካል ግዝፈት ከሚራቡበት መጠን ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት አለው ይላሉ። ጥቃቅን እንስሳት በብዛት ሲራቡ ግዙፎቹ የሚወዋለዱበት ፍጥነት ዝግ ይላል። በፕሮፌሰሩ ስሌት መሰረት በምድር ላይ ካሉ ዝሆኖች የንቦች መጠን ይበልጣል ማለት ነው። ለምሳሌ ኔማቶድ የተባሉት አነስተኛ ትሎች ከመጠናቸው ትንሽነት አንጻር በአንድ ካሬ ሜትር ሶስት ሚሊየን ይገኛሉ። አጭር የምስል መግለጫ በአንድ ካሬ ሜትር ሶስት ሚሊየን ኔማቶዶች ይገኛሉ ከትሉ ዝርያዎች መሀከል በአንድ ሰአት አምስት እንቁላል የሚጥለው ይጠቀሳል። ከ እንቁላሎች አንዱ ስለሚፈለፈል በየቀኑ ካትሪልየን ይወለዳሉ ማለት ነው። የተለያዩ ዝርያዎች በየቀኑ ወደ ምድር የሚያመጧቸውን እንስሳት ብንደምር ያጠቃላይ እንስሳት ቁጥር ላይ መድረስ ይቻላል። ተያያዥ ርዕሶች
ጥሩ ሰው ምን አይነት ነው
ጁላይ ማጋሪያ ምረጥ የሰዎችን ጥሩ ጎን በቀላሉ ማየት ይችላሉ ወይስ ሁሉም ሰው ሊያጠቃዎት እንደሆነ ያስባሉ ከሰዎች ጋር በሚያደርጉት ንግግር ሁሌም ግልጽ ነዎት ወይስ ሁሉንም ነገር አስልተውና ተጠንቅቀው ነው የሚናገሩት ለእነዚህ ጥያቄዎች የሚሰጡት ምላሽ በዕለት ተዕለት የህይወት ዘይቤዎ በቀላል አገላለጽ ቅዱስ የሚባሉ አይነት ሰው ስለመሆንዎ እና አለመሆንዎ የመናገር አቅም አላቸው። በቅርቡ የሥነ አእምሮ ባለሙያዎች ባወጡት መዘርዝር መሰረት ሰዎችን ጥሩ የሚያስብሏቸው ምን አይነት ባህሪያት እንደሆኑና መጥፎም የሚያስብሏቸው የትኞቹ እንደሆነ አስቀምጠዋል። ጓደኛ ለማፍራት ማወቅ ያለብን ጠቃሚ ነጥቦች ከሁለት አስርታት በፊት የወቅቱ የሥነ አእምሮ ባለሙያዎች የሰው ልጅን ጥሩም ሆነ መጥፎ ባህሪያትን ለመረዳት በማሰብ ሦስት ዋና ዋና መገለጫዎችን ለይተው ነበር። የመጀመሪያው ከእራስ ጋር በፍቅር መውደቅ ወይም ናርሲሲዝም ተብሎ የሚታወቀው ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ የራስን ጥቅም ለማስጠበቅ የትኛውንም ነገር ለማድረግ ዝግጁ መሆንን የተመለከተ ነው። የመጨረሻው መገለጫ ደግሞ ከባድ የሥነ ልቦና ችግር ማስተናገድ ነው። ከዚህ ግኝት በኋላ የዘመኑ የሥነ ልቦና ባለሙያዎች እነዚህን መገለጫዎች ግምት ውስጥ በማስገባት ሰዎች በሥራ ቦታ እንዴት ስኬታማ እንደሚሆኑ፣ ግንኙነቶች እንዴት እንደሚመሰረቱና እንደሚፈርሱ እንዲሁም ውስጣዊ እርካታ እንዴት እንደሚገኝ ለማጥናት ሞክረዋል። በኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ የሥነ ልቦና ባለሙያና መምህር የሆኑት ስኮት ቤሪ ኮፍማን እንደሚሉት ሰዎች ብዙ ጊዜ ከጥሩው ባህሪያቸውና ማንነታቸው ይልቅ ወደ መጥፎውና በመጠራጠር የተሞላውን ውስጣዊ ስሜት እንደሚመርጡ ይናገራሉ። ልናበረታታውና ሁሌም ልንንከባከበው የሚገባንን ባህሪ ለምን ገሸሽ እንደምናደረገው አይገባኝም ይላሉ። ስኮት ቤሪ ኮፍማን ከጓደኞቻቸው ጋር በመሆን በሰሩት ጥናት መሰረት ደግሞ ሰዎች ጥሩ ባህሪ እንዳላቸው ማሳያ ሊሆኑ የሚችሉ መገለጫዎችን አስቀምተዋል። በዚህም መሰረት በጥናቱ የተሳተፉት ሰዎች፤ የሰዎችን ጥሩ ጎን በቀላሉ ማየት እና ይቅር ባይነት፣ የሌሎችን ስኬት ማድነቅ እንዲሁም ሰዎችን ያለፍላጎታቸው አንድ ነገር እንዲያደርጉ ከማስገደድ ጋር በተያያዘ የተለያዩ ምልክቶችን አሳይተዋል። የመጀመሪያው መገለጫ ሂዩማኒዝም ወይም ሰብአዊነት ነው። ይህም የሰዎችን ክብርና ሙሉ አቅም በቀላሉ መረዳት መቻል ነው። ሁለተኛው ካንቲያኒዝም የሚባል ሲሆን ስያሜው ኢማኑኤል ካንት ከተባለው ፈላስፋ የመጣ ሲሆን ሰዎችን ከእራሳችን መነጽር ብቻ መመልከት እንደሌለብን የሚያትት ነው። ሦስተኛው ደግሞ ፌዝ ኢን ሂዩማኒቲ በሰው ልጆች እምነት መጣል እንደ ማለት ሲሆን በዚህኛው መገለጫ ሰዎች ሁሌም ጥሩ ናቸው ብሎ መረዳትና የትኛውም ሰው ማንንም ለመጉዳት አያስብም ብሎ ማሰብን ያካትታል። የ ምን ልታዘዝ ድራማ ሰምና ወርቅ የሥነ ልቦና ባለሙያው ዊሊያም ፍሊሰን እንደሚለው የሰው ልጆች በባህሪያቸው ጥሩ ናቸው ብሎ ማሰብ የሁሉም ነገር መሰረት ነው። እሱ እንደሚለው ሰዎች በአጠቃላይ ጥሩ ናቸው ብለን ባሰብን ቁጥር እራሳችንን ከሰዎች መከላከል አለብን የሚለው ተፈጥሮአዊ ስሜት እየቀነሰ ይመጣል። ስለዚህም መጥፎ ነገር እንኳን ቢፈጽሙ ለመቅጣት ወይም ተመጣጣኝ እርምጃ ለመውሰድ ከማሰብ ይልቅ ይቅርታ ማድረግ ቀላል ይሆናል ማለት ነው። ስኮት ቤሪ ኮፍማን አረጋግጫለሁ እንደሚሉት በሄዱበት ሁሉ ለሰዎች ደግነትንና ጥሩነትን የሚያሳዩ ሰዎች በህይወታቸው ደስታና የእርካታ ስሜትን በቀላሉ ማግኘት ይችላሉ። ከዚህም ባለፈ ከፍ ያለ የራስ መተማመንና በሰዎች ዘንድ ተቀባይነት ይስተዋልባቸዋል። ነገር ግን የጥሩ ሰዎች መገለጫዎች ምንድናቸው ፍቅር፣ ደግነት፣ የቡድን ሥራ፣ ይቅር ባይነት፣ አመስጋኝነት፣ በሰዎች ስኬት አለመቅናት፣ አሳቢነት ወይስ ለብዙዎች ጥቅም መቆም መረር ያለና መጥፎ ሊባል የሚችል አይነት ባህሪ ያላቸው ሰዎች ብዙ ጊዜ ነገሮችን በቀላሉ ማከናወን የሚችሉና ደፋሮች ናቸው። ከዚህም በተጨማሪ ሰዎችን የመምራትና የፈጠራ አቅማቸው ከፍ ያለ እንደሆነ ጥናቱ ይጠቁማል። ስለዚህ ሙሉ በሙሉ ጥሩ የሚባል ባህሪ ያላቸው ሰዎች ያለምንም ችግር ስኬታማ ይሆናሉ ማለት ከባድ ነው። ምክንያቱም አንዳንድ ጊዜ መጥፎ የሚባሉትን ባህሪዎች መቀላቀል ከባድና አስቸጋሪ የሚባሉ ሁኔታዎችን ለመወጣት በእጅጉ ሊጠቅሙ ይችላሉ። ዋናው ሚስጥር ያለው ጥሩ በሚባሉትና መጥፎ በሚባሉት ባህሪያት መካከል ማረፍያ ቦታ ማግኘት መቻል ነው። ተያያዥ ርዕሶች
ሊብራ፡ አዲሱ የፌስቡክ ዲጅታል ገንዘብ እና አፍሪካ
ጁላይ ማጋሪያ ምረጥ ከቀጣዩ የፈረንጆቹ ዓመት መጀመሪያ ጀምሮ ፌስቡክ ወደ ሁለት ቢሊዮን ለሚጠጉ ተጠቃሚዎቹ በዋትስአፕ፣ ኢንስታግራም እና በፌስቡክ መተግበሪያዎቹ አማካኝነት ግብይትን እንዲፈጽሙ ለማስቻል እየሰራ ይገኛል። ሊብራ ተብሎ በሚጠራው ክሪፕቶ ከረንሲ ሚሊዮን በአፍሪካ የሚገኙ የፌስቡክ ተጠቃሚዎችም ግብይት መፈጸም ይችላሉ ተብሏል። ከምዕራባውያን ሃገራት ከወዳጅ ዘመዶች በገንዘብ አስተላላፊዎች ከፍተኛ ገዘንብ የምትቀበለው አፍሪካ፤ ፌስቡክ ይህን መሰል ቀላል እና ቀልጣፍ የገንዘብ ዝውውር ማድረጊያ አማራጭን ማምጣቱ ለአፍሪካ አህጉር ጠቀሜታው ላቅ ያለ ነው ተብሏል። አምስቱ የአፍሪካ ቴክኖሎጂ ጎዳናዎች በ የቴክኖሎጂ ጋዜጠኛው አንዲሌ ማሱኩ በደቡብ አፍሪካ ነው የምኖረው። ከውጪ ሃገር የተላከልኝን ገንዘብ ተቀብዬ ወደ ዚምባብዌ ለመላክ ያለኝ ስጋት ከፍተኛ ነው። የተቀበልኩትን ገንዘብ በጠራራ ጸሐይ ልዘረፍ እችላለሁ በማለት ይናገራል። ጋዜጠኛ አንዲሌ የፌስቡክ እቅድ ይህን መሰል ስጋቶችን ከመቅረፍም አልፎ ሰዎች ወደ ትውልድ ሃገራቸው ገንዘብ ለመላክ ከገንዘብ አስተላላፊዎች የሚጠየቁትን ከፍተኛ የማስተላለፊያ ዋጋ መቀነስ ያስችላል ይላል። ባሳለፍነው ዓመት የዓለም ባንክ ያወጣው ሪፖርት እንደጠቆመው ከሰሐራ በታች ወዳሉ ሃገራት ገንዘብ መላክ ከየትኛው የዓለማችን ከፍል ብዙ የማስተላለፊያ ወጪን ይጠይቃል። እንደምሳሌም የአሜሪካ ዶላር በዌስተርን ዩኒያን ወይም በመኒግራም ለመላክ ዶላር መላኪያ ገንዘብ ያስከፍላል። አጭር የምስል መግለጫ የደቡብ አፍሪካ ራንድ በሌላ በኩል በርካታ የአፍሪካ መንግሥታት በክሪብቶ ካረንሲዎች ላይ የላቸው የደህንነት ጥርጣሬ የፌስቡክም ሆነ የሌሎች ዲጅታል ከረንሲዎች ውጤታማነትን ጥያቄ ውስጥ መክታቱ አልቀረም። በአንድም ሆነ በሌላ መልኩ የክሪፕቶ ካረንሲ መጠቀሚያነትን ካገዱ ሃገራት መካከል ናይጄሪያ እና ዚምባብዌ ይጠቀሳሉ። ክሪፕቶ ካረንሲዎችን በመጠቀም የግዢው ማንነት ይፋ ሳይደረግ ግብይት መፈጸም ይቻላል። በዚህም ሕገ ወጥ ቡድኖች የጦር መሳሪያዎች እና እጾችን ሊገዙ እና ሊሽጡ ይቻላሉ፣ ሕገ ወጥ የገንዘብ ዝውውር እና አሸባሪዎችን ለመደገፍ ያስችላል በማለት ቢትኮይንን ጨምሮ ሌሎች ክሪይፕቶከረንሲዎች ላይ ያላቸውን ስጋት የሚያነሱ ሃገራት አሉ። ክሪይፕቶ ከረንሲን ምንድነው ኦክስፎርድ መዝገበ ቃላት ክሪይፕቶ ከረንሲን ፤ የገንዘብ ልውውጦችን ደህንነት የሚያረጋግጥ፣ የተጨማሪ አሃዶችን መፈጠርን የሚቆጣጠር እና ገንዘብ መተላለፉን የሚያረጋግጥ ጠንካራ ክራፕቶግራፊ የሚጠቀም መገበያያ እንዲሆን ተደርጎ የተቀረጸ ዲጂታል ገንዘብ ሲል ይገልጸዋል። ቢትኮይን ምንድነው ቢትኮይን ማለት በቀላል ቋንቋ፤ ዲጂታል ገንዘብ መገበያያ በማለት ማጠቃለል ይቻላል። ይህ መገበያያ በኪሳችን ተሸክመን እንደምንዞረው የብር ኖት ወይም ሳንቲም ሳይሆን ኦንላይን የሚቀመጥ ዲጂታል ገንዘብ ነው። ሌላው የቢትኮይንና የተቀሩት የክሪይፕቶከረንሲዎች ልዩ ባህሪ በመንግሥታት እና በባንኮች አለመታተማቸው እንዲሁም ቁጥጥር አለመደረጉ ነው። ቢትኮይን የሚፈጠረው ማይኒንግ በሚባል ሂደት ነው። ሊብራ ከቢትኮይን በምን ይለያል፡ ሊብራ ልክ እንደ ቢትኮይን የሚፈጠረው ማይኒንግ በሚባለው ሂደት ነው። ልዩነታቸው ሊብራ በሚታወቁ ኩባንያዎች ቁጥጥር ይደረግበታል። ቢትኮይን እና ሌሎች ክሪፕቶ ከረንሲዎች በመንግሥታት እና በባንኮች አይታተሙም፤ ቁጥጥርም አይደረግባቸውም። የፌስቡኩ ሊብራ ግን በመንግሥታት እና በማዕከላዊ ባንኮች ቁጥጥር ይደረግበታል በተጨማሪም በጥሬ ገንዘብ ተቀማጭ ይኖረዋል። ሊብራ ከአሁኑ ከቪዛ፣ ማስተርካርድ፣ ኡበር እና ሰፖቲፋይ ተቀባይነትን አግኝቷል። የፌስቡክ ዲጂታል ገንዘብ ለአፍሪካውን ሁነኛ የመገበያያ አማራጭን ይዞ ይመጣል የሚሉ በርካቶች እንዳሉ ሁሉ፤ የአፍሪካ መንግሥታት ዜጎች የፌስቡክ ዲጅታል ገንዘበ አጠቃቀም ካልተዋጠላቸው በቀላሉ አገልግሎቱን ማቋረጥ መቻላቸው ስጋትን ፈጥሯል። የኢንተርኔት አገልግሎት አቅራቢ አገልግሎቱን ሆነ ብሎ ቢያቋርጥ በፌስቡክ፣ ዋትስአፕ እና በሌሎች መተግበሪያዎች የሚደረጉ የገንዘብ ዝውውር ወዲያው ይቋረጣል። በዚህም ምክንያት ሊብራ ላይ መሞርኮዝ እንደማይቻል ባለሙያዎች ስጋታቸውን ያስቀምጣሉ። ተያያዥ ርዕሶች
ጠቅላይ ሚንስትሩ ወደ አሥመራ ካቀኑ እነሆ አንድ ዓመት፤ ምን ተለወጠ
ጁላይ አጭር የምስል መግለጫ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ እና ፕሬዝዳንት ኢሳያስ በአሥመራ ኢትዮጵያና ኤርትራ ደም አፋሳሽ የድንበር ጦርነት ካደረጉ በኋላ ጉዳያቸውን ለግልግል ዳኝነት አቅርበው ውሳኔ ከተሰጠም በኋላ ፍጥጫቸው ለሁለት አስርት ዓመታት ዘልቆ ያለምንም ግንኙነት ቆይተው ነበር። ኢትዮጵያን ለሦስት አስርት ዓመታት ሲያስተዳደር የቆየው ኢሕአዴግ ለዓመታት በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች ሲካሄድ የቆየውን ተቃውሞ ተከትሎ ባካሄደው የመሪ ለውጥ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ወደ ስልጣን ሲመጡ ከወሰዷቸው ቀዳሚ እርምጃዎች መካከል ከኤርትራ ጋር ያለውን ግንኙነት ማሻሻል ዋነኛው ነው። በዚህም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ከዛሬ ነገ ጦርነት ይቀሰቀሳል ተብሎ ሲሰጋበት የነበረውን ፍጥጫ በማርገብ በዓለም ዙሪያ አድናቆትን ያስገኘላቸውን ጉዞ ወደ አሥመራ ልክ የዛሬ ዓመት አደረጉ። ወደ አሥመራ ለመጓዝ ማወቅ የሚገባዎ ነጥቦች ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከፍተኛ የመንግሥታቸውን ባለስልጣናት አስከትለው ባዳረጉት በዚህ ጉዞ ከሃያ ዓመታት በኋላ ኤርትራን ለመጎብኘት በመጓዝ የመጀመሪያው የኢትዮጵያ መሪ ሆኑ። ይህ ጉዞ የተደረገው የዛሬ ዓመት ልክ በዛሬዋ ዕለት ነበር። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ በጉዟቸው ተበላሽቶ የቀየውን የሁለቱን ሃገራት ግንኙነት የሚያሻሽሉ ስምምነቶችን ከኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር መፈራረማቸው ይታወሳል። በኢትዮጵያ በኩል በተነሱ ጥያቄዎች ምክንያት ተግባራዊ ሳይሆን እንደቆየ ይነገር የነበረውን የአልጀርሱን የድንበር ኮሚሽን ውሳኔ ኢትዮጵያ ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ ለማድረግ መወሰኗን ተከትሎ የተደረገው የጠቅላይ ሚኒስትሩ የአሥመራ ጉዞ የሁለቱን ሃገራት ግንኙነትን ለማሻሻል ትልቅ እርምጃ እንደሆነ ይታመናል። ተከትሎም ከጦርነቱ መቀስቀስ ጀምሮ ተዘግቶ የቆየው የሁለቱ ሃገራት ድንበር ተከፍቶ ከሁለቱም ወገን እንቅስቃሴ ሲጀመር ለዓመታት ተለያይተው የቆዩ ቤተሰቦች እንዲገናኙ እንዲሁም የድንብር ላይ የንግድ እንቅስቃሴ እንዲጀመር ምክንያት ሆኗል። በብዙ መልኩ ከአካባቢያዊና አህጉራዊ ተቋማት ተገልላና እራሷን አግልላ የቆየችው ኤርትራ፤ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይን ጉብኝት ተከትሎ ከሌሎች የአካባቢው ሃገራትና ተቋማት ጋር ያላትን ግንኙነት ለማሻሻል ጥረት ማድረግ ጀምራለች። ኢትዮጵያም ባደረገችው ድጋፍ በኤርትራ ላይ ተጥለው የቆዩ ማዕቀቦች የተነሱ ሲሆን ከሌሎች ሃገራት ጋር ያላትም ግንኙነትን ለማሻሻል በር ከፍቷል። የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር በኤርትራ ያደረጉትን ጉብኝትና በሁለቱ መሪዎች መካከል የተፈረሙ ስምምነቶች ዝርዝር ይዘት ሳይታወቅ በተከፈቱት የድንበር መተላለፊያዎች በኩል የሚደረገው ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ በጣም ከፍተኛ እንደነበረ ተነግሯል። ካለፈቃድ በዛላምበሳ ድንበር በኩል ማለፍ ተከለከለ ለዓመታት ተለያይተው የቆዩ ቤተሰቦች ለመገናኘት ጊዜ ሳያጠፉ ነበር ድንበር ማቋረጥ የጀመሩት። በተጨማሪም ነጋዴዎች በሁለቱም ወገን የሚፈለጉ የተለያዩ ምርቶችና የሸቀጦችን በማዘዋወር በድንበር አካባቢ ያለው የንግድ ልውውጥ እንዲጧጧፍ ምክንያት ሆነ። ከዚህ ባሻገርም ለኤርትራዊያን ወጣቶች ሽሽት ምክንያት የሆነውን የብሔራዊ አገልግሎት ለማምለጥ ይጠባበቁ የነበሩ በርካታ ወጣቶችም ነጻ በተለቀቁት የድንበር መተላለፊያዎች በኩል ወደ ኢትዮጵያ መሻገራቸው ይነገራል። ይህ ነጻ የድንበር ላይ ዝውውር ግን ለወራት ነበር የቆየው። አንድ በአንድ ኢትዮጵያንና ኤርትራን የሚያገናኙት የድንበር መተላለፊያዎች የተዘጉ ሲሆን ለዚህም ከሁለቱ መንግሥታት ይፋዊ ምክንያት ባይሰጥም፤ ሃገራቱ የቪዛና የቀረጥ ጉዳዮችን መልክ ለማስያዝ የወሰዱት እርምጃ እንደሆነ ይነገራል። አንድ ዓመት ስለሞላው የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ የአሥመራ ጉዞና የሁለቱ ሃገራትን ግንኙነት ለማሻሻል ስለተወሰዱ እርምጃዎች ቢቢሲ ኒውስ ዴይ የኢትዮጵያና የኤርትራ ጉዳይን በቅርበት የሚከታተሉትን የዩኒቨርሲቲ መምህር የሆኑትን ዶክተር ዮሐንስ ወልደማሪያምን አናግሯቸዋል። የሁለቱ ሃገራት የድንበር መተላለፊያዎች መዘጋታቸውን የሚያረጋግጡት ዶ ር ዮሐንስ፤ አሁንም ድረስ ነገሮች አልጠሩም ይላሉ። ስምምነቱን ተከትሎ ድንበሮች በተከፈቱበት ወቅት ሰዎች እንዳሻቸው መንቀሳስ መጀመራቸው ኢሳያስን ሳያስጨንቃቸው አልቀረም የድንበር በሮቹ የተዘጉት ከኤርትራ በኩል ነው የሚል እምነት እንዳለቸው ዶ ር ዮሐንስ ይናገራሉ። በሁለቱ ሃገራት መካከል ሰላም ሲወርድ ኤርትራ ህዝብ ቀዳሚው ነገር የድንበር ማካለል ሥራ ነው የሚሉት ዶ ር ዮሐንስ፤ አሁንም ድረስ ድንበር የማካለሉ ሥራ አልተሰራም ለዚህም ምክንያቱ ፕሬዝድንቱ ቅድሚያ የሚሰጡት ጉዳይ አለመሆኑ ነው ይላሉ። ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር በደረሰችው ስምምነት ከሕዝቡ ይልቅ ፕሬዝደንት ኢሳያስ ተጠቃሚ መሆናቸውን ይናገራሉ። ተጥሎ የነበረው ማዕቀብ ተነስቷል፣ ዓለም አቀፍ መገለሉ ቀርቷል። ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይም ቢሆን ከኤርትራ ጋር የተደረሰው ስምምነት ዓለም አቀፍ እውቅናን አስገኝቶላቸዋል ይላሉ። ዶክተር ዮሐንስ እንደሚሉት ከሆነ የኤርትራ መንግሥት ለህዝቡ ምን እየተከናወነ እንደሆነ የገለጸው ነገር የለም። ኤርትራዊያ ስለሁለቱ ሃገራት ስምምነት መረጃ የሚያገኙት የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃንን እየሰሙ ነው። የኤርትራ መንግሥት ምንም ያለው ነገር የለም ይላሉ። ተያያዥ ርዕሶች
ባለ አምስት ኮከቡ የኖርዌይ እስር ቤት
ጁላይ አጭር የምስል መግለጫ በሀልደን እስር ቤት የጸሎት ቤት የዮጋ አስተማሪዋ ከፊት ለፊት ቆማ አሁን ደግሞ እስኪ የእግራችሁን አውራጣቶች ሰብሰብ በማድረግ መቀመጫችሁን ወደ ኋላ በጣም ጥሩ አሁን ደግሞ ትላለች። የሚሆኑ እስረኞች የዮጋ ምንጣፋቸው ላይ ናቸው። ጥሞና ላይ። ይህ የዮጋ ሥልጠና በአንድ ሀብታም ሰፈር የተከፈተ ጂም ውስጥ አይደለም ያለው። በኖርዌይ እጅግ ነውጠኛ የሚባሉ ታሳሪዎች የሚቀፈደዱበት ሀልደን ማረሚያ ቤት ውስጥ ነው። የሚቀፈደዱበት የሚለው ቃል ለዚህ ታሪክ እንደማይመጥን የምትረዱት ይህንን ታሪክ አንብባችሁ ስትጨርሱ ነው። እነዚህ ታሳሪዎች ዮጋ ብቻ ሰርተው ወደየክፍሎቻቸው አይሄዱም። ከዮጋው በኋላ ደግሞ ገና ሳውና ባዝ ይገባሉ። እንዲህ የሚቀማጠሉት ታዲያ ሴት የደፈሩ፣ የሰው ነፍስ ሲጥ ያደረጉ፣ አደገኛ እጽ ያዘዋወሩ የአገር ጠንቅ የነበሩ መሆናቸው ነው። አብረዋቸው ከሚሰሩት መሀል ደግሞ ጠባቂዎቻቸው ይገኙበታል። ዮጋ ሲሰሩ ይረጋጋሉ ይላል ሆይዳል የተባለው የእስር ቤቱ አለቃ። እዚህ ቦታ ቁጣና ነውጥ አንሻም፤ እዚህ ሰላምና እርጋታ ነው የሚያሻን፤ እየሆነ ያለውም ይኸው ነው ይላል። ሰላምና መረጋጋት እንዲሁ ዝምብሎ የሚመጣ ነገር አይደለም። ዋጋ ያስከፍላል። የዚህ የኖርዌይ እስር ቤት ዓመታዊ ወጪ ለምሳሌ እጅግ ውድ ነው። ሺህ ፓንድ። ይህ ብዙ ቁጥር ነው። በእንግሊዝ የአንድ እስር ቤት ዓመታዊ ወጪ በአማካይ ከ ሺህ ፓውንድ አይበልጥም። በግቢው ስንዘዋወር አንድ የእስረኞች ጠባቂ ስኩተር የምትባለዋን ብስክሌት እየነዳ ሲያልፍ ፈገግታን መገበን። ከርሱ ጎን ደግሞ ሁለት እስረኞች በቁምጣ ዱብ ዱብ ይላሉ። በፍጹም የአዳኝ ታዳኝ ወይም የወንጀለኛና የጠባቂ ግንኙነት የላቸውም። እስር ቤቱን እያስጎበኘን የነበረው የግቢው አለቃ በኔ የመደነቅ ፊት ተደንቆ ሳቁን ለቀቀው። እኔ ግን የማየው ሁሉ አግራሞትን ፈጥሮብኝ ፈዝዤ አለሁ። አጭር የምስል መግለጫ የእስር ቤቱ አለቃ ይህንን ዳይናሚክ ጥበቃ ብለን እንጠረዋለን አለኝ። ምን ማለት ነው እስረኞችና ጠባቂዎቻቸው በሁሉም እንቅስቃሴዎች አብረው ናቸው። ጓደኛሞች ወዳጆች ናቸው። አብረው ይበላሉ። የእጅ ኳስ እና ቅርጫት ኳስ አብረው ይጫወታሉ፤ ስፖርት አብረው ነው የሚሠሩት ወዘተ። ይህ ሁኔታ ደግሞ እንዲቀራረቡ ያደርጋቸዋል። የጄል ኦጋዴን እስር ቤት ኃላፊ ተይዞ ለኢትዮጵያ ተሰጠ የእስር ቤቱ አለቃ ሆይዳል ሥራ የጀመረው በ ዎች አካባቢ ነበር። ያኔ ነገሮችን እንዲህ እንዳልነበሩ ያስታውሳል። ያኔ ይገርመኻል በጉልበት ነበር የምናምነው። ታራሚዎችን እንደ ወንጀለኛ ነበር የምንቆጣጠራቸው፤ እናም እስረኞች ከተፈቱ በኋላም በሌላ ወንጀል ተመልስው ጥፋተኛ የመሆን አዝማሚያቸው ከ እስከ በመቶ ደረሰ። ልክ እንደ አሜሪካ። የእስር ቤቱ አለቃ ነገሮችን መቼ መቀየር እንደጀመሩ ይናገራል። ከ ዎቹ ወዲህ አዲስ ፍልስፍና መከተል ጀመረች ኖርዌይ። ጥፋተኞችን ከመቅጣትና ከመበቀል ወደ ማለዘብና ማረም ተሸጋገረ። ቀድሞ አንድ ክፍል ውስጥ ተቆልፎባቸው ይውሉ የነበሩ እስረኞች ለተከታታይ መዝናኛ፣ ትምህርትና ስልጠና እንዲሁም ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ሲጋበዙ መልካም ዜጋ መሆን ጀመሩ። በዚህ እስር ቤት የእስረኛ ጠባቂዎችም ራሳቸውን እስረኛ አዳኝና ተቆጣጣሪ አድርገው አያስቡም። ወዳጆች ናቸው። ልክ እንደ ሆስፒታል ነርስ ጠባቂ እስረኛን ይንከባከባል። እኛ ምሳሌ መሆን ነው የምንፈልገው። እውነተኛ ወዳጅና አማካሪዎቻቸውም ነን ይላል የእስረኞቹ አለቃ። የዪኒቨርስቲ ካምፓስ ወይስ እስር ቤት የእስር ቤቱ ሥነ ሕንጻ ገጽታም ቢሆን ከኑሮና ከኅብረተሰቡ የተገለለ፣ ማጎሪያ እንዳይመስል ብዙ ተለፍቷል። እስረኞቹ ራሳቸውን ታሳሪ አድርገው እንዳያስቡ ከአንድ ሰፈር ጋ ጎረቤት ሆነው ነው ያሉት። እንዲያውም እስር ቤቱን ዲዛይን የሰራው ድርጅት ሚሊዮን ፓውንድ ቢያስከፍልም ቀላልና ምቹ እስር ቤት በማነጹ ተከታታይ ዓለማቀፍ ሽልማቶችን አግኝቷል። በእንጆሪ ዛፎች፣ በውብ አበቦች፣ በወይን ተክል የተከበበው ይህ እስር ቤት ያሳሳል። ኑሩብኝ ኑሩብኝ ይላል። ከእስር ቤትነት ይልቅ ለዪኒቨርስቲ ካምፓስነት ይቀርባል። ያሻችሁን ብሉ፣ ጠጡ፣ አጭሱ ጤና ጥበቃ ሚኒስትሯ በግላጭ የሚታይ አንድም የኤሌክትሪክ አጥርም ሆነ አዳኝ ካሜራ የለም። የእስረኞችን እንቅስቃሴ የሚከታተል ሴንሰር ዲቴክተር ግን አለ። የእስር ቤቱ አለቃ እንደነገረኝ አንድም ሰው ለማምምለጥ ሞክሮ አያውቅም። የእስረኞች ማደሪያም ቢሆን መጠነኛ የሆቴል ክፍል እንጂ ማጎሪያን አይመስልም። የራሱ ሻወር ሽንት ቤት፣ ቅንጡ ቴሌቪዥን ጠረጴዛና ወንበር እንዲሁም ወደሚያምረው ለምለምና አረንጓዴ መስክ የሚያሳየው መስኮት ይገኛል። በጋራ መጠቀሚያ ኮሪደሩ በኩል ደግሞ ሁሉን የሟላ ማብሰያ ክፍል አላቸው። ይሄ ቅንጦት ግን አልበዛም አልኩት፤ የእስረኞቹን አለቃ የበዛ ሊመስልህ ይችላል። ሆኖም ነጻነትን መነጠቅ ቀላል ነገር አድርገህ አትየው። በኖርዌይ ትልቁ ቅጣት ነጻነትን መነጠቅ ነው። ሌሎች መብቶችህ ግን አብረውህ ይኖራሉ። ለምሳሌ የመምረጥ፣ ትምህርትና ጤና አቅርቦት እና ማንኛውም ኖርዌጂያዊ የሚያገኛቸውን ጥቅሞች እስረኞችም ያገኛሉ። አጥፍተው በመታሰራቸው የሚያጡት ነጻነትን ብቻ ነው። ይህ ቅጣት ደግሞ ለሰው ልጅ ትልቁ ቅጣት ነው። አጭር የምስል መግለጫ እስረኞች የሚሰሩበት ጋራዥ ጋራጅ፣ የሙዚቃ ስቱዲዮና ዲዛይን ክፍሎች ጋራዥ ስገባ ሁለት እስረኞች የጋራጅ ቱታቸውን ለብሰው ተፍ ተፍ ይላሉ። አንዲት ፔዦ መኪናን ይፈታታሉ። ብሎን ያጠብቃሉ፤ ያላላሉ። እንደ ሁሉም እስረኞች ከክፍላቸው ወደ ሥራ የሚወጡት ጠዋት ፡ ላይ ነው። ከዚያ በኋላ ለአንድ ሰዓት እረፍት ወደ መኝታቸው ይሄዳሉ። ከዚያ በኋላ ተመልሰው ጋራዥ ውስጥ መሥራት ነው። እስከ ማታ ፡ ድረስ። በቃ ልክ ውጭ የሚኖሩትን ዓይነት ሕይወት ነው የሚመሩት። እዚህ ጋራጅ ብቻ ሳይሆን እንጨት መሰንጠቂያ፥ የቢሮና የቤት እቃ ማምረቻ ዎርክሾፕ፣ የሙዚቃ ስቱዲዮ፣ የግራፊክስ ስቱዲዮና ሌሎችም በርካታ የሥራ መስኮች አሉ። ከኅብረተሰቡ የሚቀላቀሉበትን ሁኔታ ማሰብ የምንጀምረው ገና ተፈርዶባቸው ወደ እስር ቤት የመጡ እለት ነው ይላል የእስር ቤቱ አለቃ። በኖርዌይ የሞት ቅጣት የለም። ሁሉም ታሳሪ ፍርዱን ሲጨርስ ይፈታል። ስለዚህ ከእስር ቤት ወጣሁ የሚል ስሜት የለም። ወደ ጎረቤት የመሄድ ያህል ነው የሚሰማቸው። ታሳሪዎቹን ልክ እንደ እንሰሳ ብናንገላታቸው ሲወጡም እንደዚያው ነው የሚሆኑት፤ ስለዚህ እንደ ሰው እንከባከባቸዋለን፤ ሰው ሆነው ኀብረተሰቡን ይቀላቀላሉ ይላል። አጭር የምስል መግለጫ ፍሬድሪክ እስር ቤቱ ሆኖ ለጻፈው መጽሐፍ እስር ቤት ዲዛይን ትምህርት ወስዶ የሰራው የሽፋን ገጽ ዓመት የተፈረደበት ፍሬድሪክ በዲዛይን ክፍል ቁጭ ብሎ በቅርቡ ለሚያሳትመው የምግብ አበሳሰል መጽሐፍ የሚሆን የሽፋን ዲዛይን ሰርቷል። የእስር ቤት ቆይታዬ ከራሴ ጋር እንድታረቅ አድርጎኛል ይላል። በግራፊክ ዲዛይን ዲፕሎማውን ያገኘው እዚሁ እስር ቤት ውስጥ ነው። አጭር የምስል መግለጫ የእስረኞች የጋራ ክፍል ይህንን ዜና ያጋሩ ስለማጋራት
የህንድ ፊልም አፍቃሪዎች ወተት እየሰረቁ ነው
ጥር ይህንን ለማጋራት በ ዋትስአፕ በደቡባዊ ህንድ ታሚል ናዱ ግዛት የሚገኙ ወተት ሻጮች መጠነ ሰፊ የወተት ዝርፊያ እየተካሄደባቸው መሆኑን ለፖሊስ ገልጸዋል። ህንድ ውስጥ በአንዳንድ ሃይማኖታዊ ሥርዓቶች ላይ ለመልካም ዕድል እየተባለ አማልክት ላይ ወተት ማፍሰስ የተለመደ ነው። ታዲያ ይህንን ባህል በመከተል በግዛቲቱ የሚገኙ የፊልም አፍቃሪዎች የሚወዱት ፊልም ስኬታማ እንዲሆን በማለት ግዙፍ ማስታወቂያዎች ላይ ወተት ማፍሰስ ከጀመሩ ሰነባብተዋል። ወተቱን የሚያመጡት ደግሞ ከሻጮች በመስረቅ መሆኑ ነገሩን ትንሽ ለየት ያደርገዋል። የወተት ሻጮቹ በፊልም አፍቃሪዎቹ ምክንያት ከባድ ኪሳራ እንደደረሰባቸው በምሬት ለፖሊስ አስታውቀዋል። የወተት ሻጮች ማህበሩ ፕሬዝዳንት ደግሞ ይህ ሥነ ሥርዓት የሚካሄደው ለአማላክት እንጂ ለፊልም ተዋናዮች አይደለም ሲሉ ተቃውሟቸውን አሰምተዋል። ፖሊስ አፋጣኝ እርምጃ እንዲወስድ ማህበሩ የጠየቀ ሲሆን ፖሊስም አታስቡ እርምጃ እወስዳለሁ ብሏቸዋል። ፓላቢሼካም በመባል የሚታወቀው ሥነ ሥርዓት የሚካሄደው ፊልሙን ለማስተዋወቅ በተሰቀሉ ግዙፍ ማስታወቂያዎች ላይ እና የፊልም ተዋናዮቹ ትንንሽ ምሥሎች ላይ ወተት በማፍሰስ ነው። ይህ ለ ዓመታት ሲደረግ ነበር ሥነ ሥርዓት አድናቂዎቹ የወደዱት ፊልም ስኬታማ እንዲሆን ያደርገዋል ተብሎ ይታመናል። በታሚል ናዱ ግዛት የሚገኙት የወተት አከፋፋዮች በትልልቅ መኪናዎች የሰበሰቧቸውን ወተቶች በየሱቆቻቸው ደጃፍ ላይ በማስቀመጥ ነው የሚሸጧቸው። እነዚህ ለማዳ የተባሉት የወተት ቀበኞች ታዲያ አሳቻ ሰዓት በመጠበቅና ባለሱቆቹ ሲዘናጉ የቻሉትን ያህል ወተት ተሸክመው ይሮጣሉ፤ አልያም በመኪናቸው ይዘው ይሰወራሉ። ታማሚዋን ያስረገዘው ነርስ በቁጥጥር ስር ዋለ ታዋቂው የቦሊዉድ ፊልም ተዋናይ ሲላምባርሳን አዲስ የለቀቀው ፊልሙ ተወዳጅ እንዲሆንለት አድናቂዎቹ በየመንገዱ የተሰቀሉ ማስታወቂያዎችን ወተት በወተት አድርገዋቸዋል። እሱም ወተት እንዲያፈሱለት የተማጽኖ መልእክት አስተላልፎ ነበር። ታዲያ ታዋቂው ፊልም ተዋናይ የለቀቀው ተንቀሳቃሽ ምሥል በታሚል ናዱ ግዛት ብዙ ተቀባዮችን ማግኘቱ የወተት ሻጮችን ሕይወት ከባድ አድርጎታል እየተባለ ነው። ቢቢሲ ማስተባበያ
የአማራ ክልል ተፈናቃዮች ስለ ንግድ ባንክ እርዳታ ምን ይላሉ
መጋቢት ይህንን ለማጋራት በ ዋትስአፕ በአማራ ክልል የሚገኙ ከ ሺህ በላይ የሚሆኑ ተፈናቃዮችን መልሶ ለማቋቋም የተለያዩ ጥረቶች እየተደረጉ ነው። በዚሁ መሰረት ተቋማትና ግለሰቦች እጃቸውን እየዘረጉ ነው። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክም በአገሪቱ የተለያዩ ክልሎች በተለያየ ምክንያት ለተፈናቀሉ ዜጎች ድጋፍ ይሆን ዘንድ ገንዘብ ለግሷል። ንግድ ባንክ ተፈናቃዮችን ለመደገፍ የመደበው መቶ ሚሊዮን ብር ሲሆን ከዚህ ውስጥ ለአማራ ክልል ተፈናቃዮች የመደበው ሚሊዮን ብር ሲሆን የክልሉ የድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ ይህን እርዳታ አልቀበልም ማለቱ ብዙ አስብሏል፤ ብዙዎችንም አነጋግሯል። የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ተፈናቃዮች ለችግር ተዳረግን አሉ ለተፈናቃዮች የሚውል የእርዳታና የድጋፍ ያለህ እየተባለ ባለበት በዚህ ወቅት እንዴት እርዳታ አያስፈልገኝም ይባላል ድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴው እርዳታውን እንደማይቀበል ማሳወቁን ተከትሎ ብዙዎች ያነሱት ጥያቄ ነው። የክልሉ የድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ አገኘሁ ተሻገር ምክንያታችን ለንግድ ባንክ ካለን ክብር የመነጨ ምላሽ ነው የሰጠነው ይላሉ። ተፈናቃዮችን ለማቋቋም ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የድጋፍ ጥያቄ አቅርበን ነበር የሚሉት ሰብሳቢው ንግድ ባንክ በመላ አገሪቱ ያሉ ተፈናቃዮችን ለመደገፍ እንደሚፈልግ እንደገለፀላቸው ያነሳሉ። እርሳቸው እንደሚሉት ከተለያዩ ባንኮች ከ ሚሊዮን ብር ጀምሮ የተለያዩ ድጋፎችን ተቀብለዋል። ይሁን እንጂ ከንግድ ባንክ ያገኙት የድጋፍ ክፍፍል የችግር መጠን ያላገናዘበና ከሚፈለገው በታች ሆኖ ስላገኙት ድጋፉን ላለመቀበል መወሰናቸውን ይናገራሉ። የድጋፍ አሰጣጡ ቀመር ስላልገባን ይህንን ድጋፍ ተቀብለን የንግድ ባንክን ክብር ከምንነካ፣ ይህ ዝቅተኛ ድጋፍ ለአማራ ህዝብ የሚመጥን ባለመሆኑ አለመቀበል ይሻላል በሚል ከውሳኔው ላይ እንደደረሱ ለቢቢሲ ገልፀዋል። ጌዲዮ በዐቢይ ጉብኝት ማግስት ንግድ ባንክ እርዳታውን የበጀተበትን ቀመር አለማወቅ ብቻም ሳይሆን ቀመር መስራትም አያስፈልገው ነበር ሲሉ ይከራከራሉ አቶ አገኘሁ። እሳቸው እንደሚሉት ንግድ ባንክ ማድረግ የነበረበት የመደበውን የእርዳታ ገንዘብ ለዚሁ ዓላማ በመንግሥት ለተቋቋመው ለአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን በመስጠት ኮሚሽኑ በተፈናቃይ ልክና በጉዳት መጠን ለክልሎች እንዲያከፋፍል መተው ነበር። ያነጋገርናቸው በአማራ ክልል ጊዜያዊ መጠለያ የሚገኙ አንዳንድ ተፈናቃዮች በበኩላቸው ያገኙትን ድጋፍ ይዘው ወደ ቀያቸው የመመለስ ከፍተኛ ፍላጎት ያላቸው ከመሆኑ አንፃር ይህን የንግድ ባንክ ድጋፍ አልቀበልም ማለት ትክክል እንዳልሆነ ገልፀውልናል። ይህ ነገር ስህተት ነው፤ ምክንያቱም ብዙ ሰዎች አደጋ ላይ ነው ያሉት። ለምሳሌ እንደ ግራር አውራጃ ብዙ ሰዎች ቤታቸው ተቃጥሏል፣ ንብረታቸው ወድሟል፣ አምስትም አስር ብርም ቢደርሳቸው ለእነሱ ጥቅም ነው ብዬ ነው የማስበው ስትል ሳሮን ባይሳ የተባለች ተፈናቃይ ለቢቢሲ ተናግራለች። ቻይና የኤርባስ አውሮፕላኖችን ልትገዛ ነው ይህ ውሳኔ ያለምክንያት እንዳልሆነ የሚገምቱ ተፈናቃዮችም ያሉ ሲሆን የዚህ አይነት ስሜት ካላቸው ሌላኛው ተፈናቃይ አንዱዓለም ነበይ መቼም ከውስጡ የሆነ ነገር ይኖረዋል እንጂ ህብረተሰቡ በችግር ላይ ነው ያለው፤ እርዳታው ተፈላጊ ነው ብለውናል። በክልሉ ነፍሰጡር እናቶች፣ ህፃናትና አዛውንት ተፈናቃዮች ከባድ ችግር ውስጥ እንደሚገኙ ቢቢሲ ከጥቂት ሳምንታት በፊት በርካታ ተፈናቃዮች በሚገኙበት በአይምባ መጠለያ ተገኝቶ ዘገባ ሰርቶ ነበር። የአሜሪካው ኩባንያ በኬንያ ካናቢስ ለማብቀል ፍቃድ አገኘ ተባለ በክልሉ ተፈናቃዮች ያሉበትን ፈታኝ ሁኔታ በመገንዘብ እርዳታውን አልቀበልም ያለው የድጋፍ አሰባሳቢው ኮሚቴ ላይ ኩራት ወይስ ዳቦ የሚል ጠንካራ ትችት የሰነዘሩም እንዳሉ ያነሳንላቸው የኮሚቴው ሰብሳቢ አቶ አገኘሁም የዚህ አይነቱ ሃሳብ የፅንፈኞችና ለአማራ ክልል ህዝብ ንቀት ያላቸው ሰዎች ሃሳብ ነው በማለት ጠንከር ያለ ምላሽ ይሰጣሉ። የአማራ ህዝብ አይኮራም፤ ኮርቶም አያውቅም። ከኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ጋር በእኩልነት የሚያምን ህዝብ ነው ይላሉ። የድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴውን መግለጫ ተከትሎ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሰጠው ምላሽ እንደሌለ አቶ አገኘሁ ጨምረው ተናግረዋል። ቢቢሲ ማስተባበያ
የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ ሰማኒያ ሚሊዮን ብር እንዴት ተዘረፈ
ጥር ይህንን ለማጋራት በ ዋትስአፕ ከጥቂት ሳምንታት በፊት የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ ንብረት የሆነ ገንዘብ ከአንድ ቅርንጫፍ ወደ ሌላው ሲዘዋወር እንደተዘረፈ ተሰምቷል። ታህሳስ ፣ ዓ ም በምዕራብ ሐረርጌ ዞን ዋና ከተማ ጭሮ ውስጥ የሚገኘው የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ ሚሊዮን ብር ወጭ ያደርጋል። ገንዘቡን ወደ ደብረ ዘይት ቅርንጫፉ ለማዘዋወርም ጉዞ ይጀምራል። ሆኖም ገንዘቡን የጫነው መኪና የታሰበበት ሳይደርስ መኤሶ ወረዳ አሰቦት አካባቢ መሳሪያ በያዙ ሰዎች ተከበበ። ከዚያስ የምዕራብ ሐረርጌ ዞን ፖሊስ መምሪያ ሐላፊ ኮማንደር ጋዲሳ ንጉሳ በዚህ ጉዳይ ላይ የሚከተለውን ብለዋል የተወሰኑ ኃይሎች ሽጉጥ የያዙ እንዲሁም ባዶ እጃቸውን የነበሩ ግለሰቦች መኪናውን መንገድ ላይ አስቆሙት። ሾፌሩን አስፈራርተው በማስወረድ አሰቦት ወደምትባል አካባቢ መኪናዋን ወሰዷት ከተዘረፈው ሚሊዮን ብር ውስጥ በሽምግልና፣ በድርድርና በፍተሻ ማስመለስ የቻሉት ገንዘብ እንዳለም ይናገራሉ። ይህን ያህል ገንዘብ አስመልሰናል ለማለት ሰነድ ባያጠናቅሩም እጅ ከፍንጅ የተያዘ ገንዘብ የለም። አብዛኛው ብር የተመለሰው በጥቆማ ነው። በርካታ መኪና ይዘው ሲሄዱ በፍተሻ የተያዙ አሉ ብለዋል። ጫትን ማገድ ፈፅሞ የሚቻል አይደለም ዶ ር ዘሪሁን መሃመድ ለመሆኑ አንድ ባንክ ከአንድ ቅርንጫፍ ወደ ሌላ ቅርንጫፍ ገንዘብ ሲያዘዋውር የሚደረግለት የጥበቃ ኃይል ወደየት ሄዶ ነው ዝርፊያው ሊፈፀም የቻለው በሚል ቢቢሲ ኮማንደሩን ጠይቋል። በወቅቱ አብረው የነበሩት ፖሊሶች ከአቅማቸው በላይ ስለሆነ መያዝ አልቻሉም። ወደ ሌላ እርምጃ ከተገባ በነሱም ደህንነት ላይ አደጋ ስለሚመጣ በልመናና በድርድር ገንዘቡን መውሰድ እንዲያቆሙ ለማድረግ ተሞክሯል። ማስፈራራትና ወደ ሰማይም ተተኩሷል። ዘራፊዎቹ በቁጥር ብዙ እንደነበሩ የሚናገሩት ኮማንደሩ፤ ዘራፊዎቹ ገንዘቡን ከዘረፉበት ቦታ ወደ ከተማ ይዘው ከሄዱ በኋላ ለመከፋፈል ሲሞክሩ የከተማው ከንቲባ የሕዝብ ንብረት ነው ብለው በድርድር ለማስቆም ቢሞክሩም እንዳልተሳካላቸው ይገልጻሉ። ፎርቹን ጋዜጣ፤ ብሩ ወደ አዲስ አበባ መጓጓዝ ላይ እንደነበር ጠቅሶ ግለሰቦች በዝርፊያው ተጠርጥረው ተይዘዋል ሲል ዘግቧል። እናትና ልጇቿ ለወር አበባ በተገለለ ጎጆ ህይወታቸው አለፈ ከዘረፋው ጀርባ ያሉ ሰዎችን ማንነት ለማወቅ ምርመራ እየተደረገ መሆኑን ኮማንደሩ ቢናገሩም፤ ዘራፊዎቹ ከሩቅ የመጡ አይደሉም የሚል ጥቆማ ሰጥተዋል። ከዚህ ቀደም የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ ከድሬዳዋ ቅርንጫፍ ሚሊዮን ብር ጭኖ በመኢሶ ወረዳ ሲተላለፍ ነበር። ያኔ ገንዘቡን ይዞ ይጓዝ የነበረው መኪና አሽከርካሪ አህያ ገጭቶ በአካባቢው ፖሊስ ተይዟል። በወቅቱ የተገኘው ገንዘብና አጓጓዡ የያዘው ሰነድ ላይ የሰፈረው የገንዘብ መጠን መካከል ልዩነት ተፈጥሮ እንደነበር ይታወሳል። ገንዘቡን መጫን የነበረበት መኪና ሰሌዳ ቁጥርና በፖሊስ የተያዘው መኪና ታርጋ ቁጥርም የተለያየ ነው ተብሎ ነበር። ለመሆኑ የዚህ ገንዘብ ጉዳይ ከምን ደረሰ ኮማንደር ጋዲሳ ምላሽ አላቸው። አምሳ ሚሊዮኑን የሚያሳይ ሰነድ በገንዘብ ያዡ እጅ አልነበረም። ይህም ከኔትወርክ ችግር ጋር የተያያዘ ነው። መንገድ ላይ በኢሜይል እንልክላችኋለን የሚል ነገር ነበር ገንዘቡ ከወጣበት ቅርንጫፍ ጀምሮ ስለነበረው ሂደት ምርመራ ተእየተደረገ መሆኑንም ተናግረዋል። መጀመሪያ ገንዘቡን ይጭናል ተብሎ የነበረው መኪና ሰሌዳው ቁጥር ሌላ ሲሆን፤ ይህም በአጋጣሚ ገንዘቡን ይጭናል ተብሎ የታሰበው ሾፌር በህመም ላይ ስለነበር ነው ብለዋል። ስለ ሹፌር ለውጥ የሚገልጽ ደብዳቤ ሳይቀየርብ ሌላ መኪና በመተካቱ ነው ሲሉ የድሬዳዋ ስራ አስኪያጅ እንደነገሯቸው ኮማንደሩ ገልፀዋል። ገንዘቡ ህጋዊ መሆኑን ነው የምናውቀው። አሁን ምርመራ ላይ ነው። በቅርብ ይፈታል የሚል እምነት አለኝ ብለዋል። መኪና ውስጥ የተገኘው ገንዘብ ጉዳይ እስኪጣራ ድረስ ገንዘቡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዳማ ቅርንጫፍ ውስጥ እንዲቆይ መወሰኑንም ኮማንደር ጋዲሳ ገልፀዋል። ቢቢሲ ማስተባበያ
ኢስላማዊ ባንክ ለኢትዮጵያ ምን ይፈይዳል
ለመሆኑ ኢስላማዊ ባንክ እስከናካቴው ቢቀርብን ምን ይቀርብናል የብሔር ዘመም ባንኮች አልበቃ ብሎ አሁን ደግሞ ሃይማኖታዊ ባንክ መምጣቱ አደጋ የለውም ደግሞስ እንዴት ነው ባንኩ ያለ ወለድ አትራፊ የሚሆነው ላለፉት ለ ዓመታት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ፋከልቲ ያስተማሩትንና የዓለም አቀፉ የቢዝስ ጥናት ኩባንያ ዴሎይት የኢትዯጵያ ቢሮ የሂውማን ካፒታል ሥራ አስኪያጅ የነበሩትን አቶ ሙከሚል በድሩን አነጋግረናቸዋል።
በስህተት ከባንክ የተሰጣቸውን ሚሊየን ብር የመለሱት መምህር
ግንቦት ይህንን ለማጋራት በ ዋትስአፕ አቶ ዓለሙ ተስፋዬ ዶ ር ባህርዳር በሚገኘው የአቢሲኒያ ባንክ በተንቀሳቃሽ ደብተራቸው የገባውን ገንዘብ ለማውጣት በጣና ቅርንጫፍ የተገኙት ሚያዝያ ቀን ዓ ም ነበር። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን፤ ማኅበረ ቅዱሳን በሚያስተባብረውና አቶ ዓለሙ በሚሳተፉበት ፕሮግራም የአብነት ትምህርት ቤቶችና ገዳማትን ለማደራጀት የተሰበሰበ አንድ ሚሊየን ሁለት መቶ ሦስት ሺ ብር በስማቸው ገብቶ ነበር። ብር ለአንድ ሕጻን በገበያ አካባቢ በሚገኘውና የሥራ ጫና በሚበዛበት የጣና ቅርንጫፍ ያሉ ሠራተኞች የተለመደ የዕለት ከዕለት ሥራቸውን በማከናወን ላይ ሳሉ አቶ ዓለሙ ከፍጠኛ መጠን ያለው ገንዘብ ለማውጣት መጠየቃቸውን የጣና ቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጅ አቶ ቢራራ መላኩ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ደንበኛው የጠየቁት የገንዘብ መጠን አንድ ሚሊየን ሁለት መቶ ሦስት ሺ ብር ነበር። አቶ ቢራራ እንደሚሉት፤ የገንዘቡ መጠን ከፍ ያለ ስለነበረ ፊትለፊት የነበረው ገንዘብ ከፋይ ለደንበኛው ብሩን ብቻ እንዲሰጣቸው ተደርጎ፤ ቀሪውን ሚሊየን ብር ወደ ውስጥ ገብተው እንዲወስዱ ተደርጓል። ወደ ውስጥ ከገቡ በኋላ ብሩን አብረን ቆጥረን እንዲረከቡ አደረግን። ደንበኛው ከጠየቁት አንድ ሚሊየን ብር ጭማሪ ተሰጥቷቸው ገንዘቡን ገቢ ወደሚያደርጉበት ቦታ ሄዱ። አቶ ቢራራ እንደሚሉት፤ ለአቶ ዓለሙ አንድ ሚሊየን ብር ተጨማሪ መሰጠቱንና ከባንኩ ብር መጉደሉን አላወቁም ነበር። አቶ ዓለሙ በስህተት የተሰጣቸውን ገንዘብ በጆንያ ጭነው እስከተመለሱበት ጊዜ ድረስ ምንም እንዳልጠረጠሩ ያስረዳሉ። የተፈጠረውን ነገር እጅግ አስገራሚ ሲሉም ይገልጹታል። ደንበኛው በመጀመሪያ ገንዘቡን ይዘው ሲመለሱ ትርፍ ብር ሊመልሱልን እንደሆነ አላወቅኩም ነበር። ሀሳባቸውን ቀይረው ብሩን ገቢ ሊያደርጉት እንደሆነ ነበር ያሰብነው። ሁለት እምነቶችን በአንድ ጣራ ለአስርታት ያሳደሩ ጥንዶች አቶ ዓለሙ ግን የራሳቸውን ገንዘብ ገቢ ሊያደርጉ ሳይሆን ባንኩ በስህተት የሰጣቸውን ተጨማሪ አንድ ሚሊየን ብር ሊመልሱ ነበር ወደ ቅርንጫፉ የተመለሱት። በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የኬሚስትሪ ትምህርት ክፍል ኃላፊ የሆኑት አቶ ዓለሙ ተስፋዬ፤ ወደ ውስጥ ከገባን በኋላ ብሩ ሲቆጠር አጠገቡ ቁጭ ብዬ ስለነበር መጠኑ ትክክል መሆኑን እያረጋገጥኩ ወደ ጆንያ ውስጥ አስገባ ነበር ሲሉ ይናገራሉ። አቶ ዓለሙ ብሩን ከተረከቡ በኋላ አብሯቸው ከነበረ ግለሰብ ጋር ለሥራ ማስኬጃ ብሩን ወደ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ገቢ ለማድረግ ተንቀሳቀሱ። ንግድ ባንክ ሲደርሱ ግን ፈጽሞ ያልጠበቁት ነገር አጋጠማቸው። የባንኩ ሠራተኛ ብሩን እንደተመለከተው ከመቁጠሩ በፊት ሚሊየን ነው አይደል ብሎ ጠየቃቸው። እንደዛ ብሎ ሲጠይቀን፤ የብሩ መጠን ሚሊየን ነው ብለን መለስንለት። ብሩን አብረነው በድጋሚ ስንቆጥረው እውነትም ሚሊየን ብር ሆኖ አገኘነው በማለት አቶ ዓለሙ ስለሁኔታው ያስረዳሉ። የራሳችን የሆነውን ሚሊየን ብር ገቢ ካደረግን በኋላ ቀሪውን ብር ለመመለስ ወደ አቢሲኒያ ባንክ ጣና ቅርንጫፍ ተመለስን የባንኩ ሥራ አስኪያጅ የቀን ገቢ ሂሳብ የሚሠራበት ሰአት ባለመድረሱ ገንዘቡ መጉደሉን እንዳላወቁ ይናገራሉ። ብሩ ይጉደል አይጉደል ለማወቅ ሂሳብ መዝጋት ነበረብን ይላሉ። የፍስሀ ተገኝ የቤተሰብ ፍለጋ ጉዞ አቶ ቢራራ እንደሚሉት፤ አቶ ዓለሙ ብር በስህተት ሰጥታችሁኛልና ልመልስ ሲሏቸው፤ በመጀመሪያ ነገሩ ቀልድ መስሏቸው ነበር። ኋላ ላይ ነገሩ እውነት ሆኖ ሲገኝ ግን ግርምትም ድንጋጤም እንደፈጠረባቸው ይናገራሉ። አቶ ዓለሙ ገንዘቡን ባይመልሱ ምን ይፈጠር ነበር የሚል ጥያቄ ያቀረብንላቸው አቶ ቢራራ፤ የሥነ ምግባር እርምጃዎች ሊያስከትል ይችል ነበር ይላሉ። ስህተቱ በሥራ ጫና ምክንያት ወይም ባለማወቅ የተፈጠረ እንደሆነ በምንም አይነት መንገድ ማረጋገጥ ስለማይቻል ሆነ ተብሎ እንደተፈጸመ ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል። ደንበኛው የሰሩት ስህተት ባለመኖሩና ባንኩ ክፍያ ፈጽሞላቸው ወደጉዳያቸው ስለሄዱ ገንዘቡን ለመመለስ የሚያስገድዳቸው የሕግ አሰራር አልነበረም። የአቶ ዓለሙን ስብዕና በቃላት ለመግለጽ እጅግ ከባድ ነው፤ ከህሊና በላይ ነው፤ ፈጣሪ በላባቸው ሠርተው ያገኙትን ገንዘባቸውንና ትዳራቸውን እንዲባርክላቸው እመኝላቸዋለሁ ብለዋል አቶ ቢራራ። ምግብ ማብሰልና ማጽዳት የቤት ውስጥ ጥቃቶችን ለመቀነስ አቶ ቢራራ ይህ ለትውልድ አርአያ የሚሆን ተግባር ነው። እድሜ ልካቸውን ሊኮሩበት የሚገባ ተግባር ነው። እኔም ብሆን እድሜ ዘመኔን በሙሉ አስታውሰዋለሁ። የመልካም ሥራ አርአያ አድርጌ የማስታውሳቸው ሰው ይሆናሉ በማለት የተሰማቸውን ደስታ በመግለጽ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። አቶ ዓለሙ በበኩላቸው፤ ተግባሩ ብዙ ሰዎች ሊያደርጉት የሚችሉት ነው በማለት፤ የባንኩን ሠራተኛ ከብዙ እንግልት በማዳናቸው ደስተኛ እንደሆኑና የህሊና እርካታ እንደተሰማቸው ገልጸዋል። ቢቢሲ ማስተባበያ
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከስድሳ በላይ የኢትዮጵያ አምባሳደሮችን ያገኛሉ
ጃንዩወሪ ስለ ማጋራት ተጨማሪ ያጋሩ ማጋሪያ ምረጥ በሚቀጥለው ሰኞ ጥር ቀን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከፍተኛ አመራሮች እና በዓለም ዙርያ በተለያዩ ሚሲዮኖች ኢትዮጵያን ከሚወክሉ ከስድሳ በላይ አምባሳደሮች እንደሚወያዩ ተገለፀ። ውይይቱ በልዩ ልዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ የሚያጠነጥን ሲሆን በተለይም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እየተካሄደ ያለው የመዋቅር ማሻሻያ ምን ደረጃ ላይ እንደደረሰ እንዲሁም ባለፉት አስር ወራት በውጭ ግንኙነት መስክ የተከናወኑ እርምጃዎች ይገመገማሉ ሲል ተሰናባቹ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ አቶ መለስ አለም ዛሬ ተናግረዋል። በቅርቡ በኬንያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው የተሾሙት አቶ መለስ ከአስር በላይ የአገር መሪዎች ባለፉት አስር ወራት ኢትዮጵያን መጎብኘታቸውን አስታውሰዋል።
ኢትዮጵያና ኤርትራ፡ አዲስ ዓመትን በቡሬና በዛላምበሳ
መስከረም ይህንን ለማጋራት በ ዋትስአፕ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድና ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ሁለቱን ሃገራት በሚያዋሰኑባቸው በቡሬ በዛላምበሳ አካባቢዎች ተገኝተው ከሕዝቡና ሠራዊታቸው ጋር አዲስ ዓመትን አከበሩ። ይህ በሁለቱ ሃገራት መካከል የተጀመረውን ግንኙነትን የማሻሻል እርምጃን ተከትሎ ተዘግተው የነበሩትን የሁለቱን ሃገራት የድንበር መተላለፊያዎች በመክፈት በኩል ትልቁ እርምጃ ነው ተብሏል። በትናንትናው ዕለት ከሃያ ዓመታት በፊት ሁለቱ የሃገራት የድንበር ጦርነት ሲቀሰቀስ ጀምሮ ተዘግቶ የነበረው ከዛላምበሳ ወደ ሰንዓፈ የሚወስደውን መንገድ ተከፍቷል። መቐለ በምፅዋ በአካባቢው የነበሩ የዓይን እማኞች እንደተናገሩት ከዚህ በተጨማሪ በስፍራው የነበረው የኤርትራ ጦር ምሽግም እንዲፈርስ ተደርጓል። ሁለቱን ሃገራት የሚያገናኘው የድንበር መተላለፊያ አካባቢ ተቀብረው የነበሩ ፈንጂዎችን ማፅዳት ሥራ በሁለቱም ሠራዊት አባላት በጋራ ሲያከናውኑ ማየታቸውን የዓይን እማኞቹ ተናግረዋል። የሁለቱ ሃገራት መሪዎች በሌላኛው ሃገር ያደረጉትን ጉብኝት ተከትሎ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን ከማደሳቸው ባሻገር የአየር ትራንስፖርት ተጀምሯል። ከፍተኛ ትኩረት የተሰጠው ከጂቡቲ በተጨማሪ ኢትዮጵያ ለወጪና ለገቢ ቁሳቁሶች ማንቀሳቀሻ ሁለቱን የኤርትራ ወደቦችን እንድትጠቀም ማስቻል ቀጣዩ እርምጃ እንደሚሆን ተነግሯል።
ይህ የመኪና ውስጥ ካሜራ ኖርዌይ ውስጥ የተከሰተ ተዓምር ቀርፆ አስቀርቷል
ይህ የመኪና ውስጥ ካሜራ ኖርዌይ ውስጥ የተከሰተ ተዓምር ቀርፆ አስቀርቷል ህዳር
ይህንን ለማጋራት በ ዋትስአፕ
የሰዎችን ጥሩ ጎን በቀላሉ ማየት ይችላሉ ወይስ ሁሉም ሰው ሊያጠቃዎት እንደሆነ ያስባሉ ከሰዎች ጋር በሚያደርጉት ንግግር ሁሌም ግልጽ ነዎት ወይስ ሁሉንም ነገር አስልተውና ተጠንቅቀው ነው የሚናገሩት ለእነዚህ ጥያቄዎች የሚሰጡት ምላሽ በዕለት ተዕለት የህይወት ዘይቤዎ በቀላል አገላለጽ ቅዱስ የሚባሉ አይነት ሰው ስለመሆንዎ እና አለመሆንዎ የመናገር አቅም አላቸው። በቅርቡ የሥነ አእምሮ ባለሙያዎች ባወጡት መዘርዝር መሰረት ሰዎችን ጥሩ የሚያስብሏቸው ምን አይነት ባህሪያት እንደሆኑና መጥፎም የሚያስብሏቸው የትኞቹ እንደሆነ አስቀምጠዋል። ጓደኛ ለማፍራት ማወቅ ያለብን ጠቃሚ ነጥቦች ከሁለት አስርታት በፊት የወቅቱ የሥነ አእምሮ ባለሙያዎች የሰው ልጅን ጥሩም ሆነ መጥፎ ባህሪያትን ለመረዳት በማሰብ ሦስት ዋና ዋና መገለጫዎችን ለይተው ነበር። የመጀመሪያው ከእራስ ጋር በፍቅር መውደቅ ወይም ናርሲሲዝም ተብሎ የሚታወቀው ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ የራስን ጥቅም ለማስጠበቅ የትኛውንም ነገር ለማድረግ ዝግጁ መሆንን የተመለከተ ነው። የመጨረሻው መገለጫ ደግሞ ከባድ የሥነ ልቦና ችግር ማስተናገድ ነው። ከዚህ ግኝት በኋላ የዘመኑ የሥነ ልቦና ባለሙያዎች እነዚህን መገለጫዎች ግምት ውስጥ በማስገባት ሰዎች በሥራ ቦታ እንዴት ስኬታማ እንደሚሆኑ፣ ግንኙነቶች እንዴት እንደሚመሰረቱና እንደሚፈርሱ እንዲሁም ውስጣዊ እርካታ እንዴት እንደሚገኝ ለማጥናት ሞክረዋል። በኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ የሥነ ልቦና ባለሙያና መምህር የሆኑት ስኮት ቤሪ ኮፍማን እንደሚሉት ሰዎች ብዙ ጊዜ ከጥሩው ባህሪያቸውና ማንነታቸው ይልቅ ወደ መጥፎውና በመጠራጠር የተሞላውን ውስጣዊ ስሜት እንደሚመርጡ ይናገራሉ። ልናበረታታውና ሁሌም ልንንከባከበው የሚገባንን ባህሪ ለምን ገሸሽ እንደምናደረገው አይገባኝም ይላሉ። ስኮት ቤሪ ኮፍማን ከጓደኞቻቸው ጋር በመሆን በሰሩት ጥናት መሰረት ደግሞ ሰዎች ጥሩ ባህሪ እንዳላቸው ማሳያ ሊሆኑ የሚችሉ መገለጫዎችን አስቀምተዋል። በዚህም መሰረት በጥናቱ የተሳተፉት ሰዎች፤ የሰዎችን ጥሩ ጎን በቀላሉ ማየት እና ይቅር ባይነት፣ የሌሎችን ስኬት ማድነቅ እንዲሁም ሰዎችን ያለፍላጎታቸው አንድ ነገር እንዲያደርጉ ከማስገደድ ጋር በተያያዘ የተለያዩ ምልክቶችን አሳይተዋል። የመጀመሪያው መገለጫ ሂዩማኒዝም ወይም ሰብአዊነት ነው። ይህም የሰዎችን ክብርና ሙሉ አቅም በቀላሉ መረዳት መቻል ነው። ሁለተኛው ካንቲያኒዝም የሚባል ሲሆን ስያሜው ኢማኑኤል ካንት ከተባለው ፈላስፋ የመጣ ሲሆን ሰዎችን ከእራሳችን መነጽር ብቻ መመልከት እንደሌለብን የሚያትት ነው። ሦስተኛው ደግሞ ፌዝ ኢን ሂዩማኒቲ በሰው ልጆች እምነት መጣል እንደ ማለት ሲሆን በዚህኛው መገለጫ ሰዎች ሁሌም ጥሩ ናቸው ብሎ መረዳትና የትኛውም ሰው ማንንም ለመጉዳት አያስብም ብሎ ማሰብን ያካትታል። የ ምን ልታዘዝ ድራማ ሰምና ወርቅ የሥነ ልቦና ባለሙያው ዊሊያም ፍሊሰን እንደሚለው የሰው ልጆች በባህሪያቸው ጥሩ ናቸው ብሎ ማሰብ የሁሉም ነገር መሰረት ነው። እሱ እንደሚለው ሰዎች በአጠቃላይ ጥሩ ናቸው ብለን ባሰብን ቁጥር እራሳችንን ከሰዎች መከላከል አለብን የሚለው ተፈጥሮአዊ ስሜት እየቀነሰ ይመጣል። ስለዚህም መጥፎ ነገር እንኳን ቢፈጽሙ ለመቅጣት ወይም ተመጣጣኝ እርምጃ ለመውሰድ ከማሰብ ይልቅ ይቅርታ ማድረግ ቀላል ይሆናል ማለት ነው። ስኮት ቤሪ ኮፍማን አረጋግጫለሁ እንደሚሉት በሄዱበት ሁሉ ለሰዎች ደግነትንና ጥሩነትን የሚያሳዩ ሰዎች በህይወታቸው ደስታና የእርካታ ስሜትን በቀላሉ ማግኘት ይችላሉ። ከዚህም ባለፈ ከፍ ያለ የራስ መተማመንና በሰዎች ዘንድ ተቀባይነት ይስተዋልባቸዋል። ነገር ግን የጥሩ ሰዎች መገለጫዎች ምንድናቸው ፍቅር፣ ደግነት፣ የቡድን ሥራ፣ ይቅር ባይነት፣ አመስጋኝነት፣ በሰዎች ስኬት አለመቅናት፣ አሳቢነት ወይስ ለብዙዎች ጥቅም መቆም መረር ያለና መጥፎ ሊባል የሚችል አይነት ባህሪ ያላቸው ሰዎች ብዙ ጊዜ ነገሮችን በቀላሉ ማከናወን የሚችሉና ደፋሮች ናቸው። ከዚህም በተጨማሪ ሰዎችን የመምራትና የፈጠራ አቅማቸው ከፍ ያለ እንደሆነ ጥናቱ ይጠቁማል። ስለዚህ ሙሉ በሙሉ ጥሩ የሚባል ባህሪ ያላቸው ሰዎች ያለምንም ችግር ስኬታማ ይሆናሉ ማለት ከባድ ነው። ምክንያቱም አንዳንድ ጊዜ መጥፎ የሚባሉትን ባህሪዎች መቀላቀል ከባድና አስቸጋሪ የሚባሉ ሁኔታዎችን ለመወጣት በእጅጉ ሊጠቅሙ ይችላሉ። ዋናው ሚስጥር ያለው ጥሩ በሚባሉትና መጥፎ በሚባሉት ባህሪያት መካከል ማረፍያ ቦታ ማግኘት መቻል ነው። ከዚህ ዜና በተጨማሪ
ጠቅላይ ሚንስትሩ ወደ አሥመራ ካቀኑ እነሆ አንድ ዓመት፤ ምን ተለወጠ
ሐምሌ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ እና ፕሬዝዳንት ኢሳያስ በአሥመራ ኢትዮጵያና ኤርትራ ደም አፋሳሽ የድንበር ጦርነት ካደረጉ በኋላ ጉዳያቸውን ለግልግል ዳኝነት አቅርበው ውሳኔ ከተሰጠም በኋላ ፍጥጫቸው ለሁለት አስርት ዓመታት ዘልቆ ያለምንም ግንኙነት ቆይተው ነበር። ኢትዮጵያን ለሦስት አስርት ዓመታት ሲያስተዳደር የቆየው ኢሕአዴግ ለዓመታት በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች ሲካሄድ የቆየውን ተቃውሞ ተከትሎ ባካሄደው የመሪ ለውጥ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ወደ ስልጣን ሲመጡ ከወሰዷቸው ቀዳሚ እርምጃዎች መካከል ከኤርትራ ጋር ያለውን ግንኙነት ማሻሻል ዋነኛው ነው። በዚህም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ከዛሬ ነገ ጦርነት ይቀሰቀሳል ተብሎ ሲሰጋበት የነበረውን ፍጥጫ በማርገብ በዓለም ዙሪያ አድናቆትን ያስገኘላቸውን ጉዞ ወደ አሥመራ ልክ የዛሬ ዓመት አደረጉ። ወደ አሥመራ ለመጓዝ ማወቅ የሚገባዎ ነጥቦች ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከፍተኛ የመንግሥታቸውን ባለስልጣናት አስከትለው ባዳረጉት በዚህ ጉዞ ከሃያ ዓመታት በኋላ ኤርትራን ለመጎብኘት በመጓዝ የመጀመሪያው የኢትዮጵያ መሪ ሆኑ። ይህ ጉዞ የተደረገው የዛሬ ዓመት ልክ በዛሬዋ ዕለት ነበር። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ በጉዟቸው ተበላሽቶ የቀየውን የሁለቱን ሃገራት ግንኙነት የሚያሻሽሉ ስምምነቶችን ከኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር መፈራረማቸው ይታወሳል። በኢትዮጵያ በኩል በተነሱ ጥያቄዎች ምክንያት ተግባራዊ ሳይሆን እንደቆየ ይነገር የነበረውን የአልጀርሱን የድንበር ኮሚሽን ውሳኔ ኢትዮጵያ ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ ለማድረግ መወሰኗን ተከትሎ የተደረገው የጠቅላይ ሚኒስትሩ የአሥመራ ጉዞ የሁለቱን ሃገራት ግንኙነትን ለማሻሻል ትልቅ እርምጃ እንደሆነ ይታመናል። ተከትሎም ከጦርነቱ መቀስቀስ ጀምሮ ተዘግቶ የቆየው የሁለቱ ሃገራት ድንበር ተከፍቶ ከሁለቱም ወገን እንቅስቃሴ ሲጀመር ለዓመታት ተለያይተው የቆዩ ቤተሰቦች እንዲገናኙ እንዲሁም የድንብር ላይ የንግድ እንቅስቃሴ እንዲጀመር ምክንያት ሆኗል። በብዙ መልኩ ከአካባቢያዊና አህጉራዊ ተቋማት ተገልላና እራሷን አግልላ የቆየችው ኤርትራ፤ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይን ጉብኝት ተከትሎ ከሌሎች የአካባቢው ሃገራትና ተቋማት ጋር ያላትን ግንኙነት ለማሻሻል ጥረት ማድረግ ጀምራለች። ኢትዮጵያም ባደረገችው ድጋፍ በኤርትራ ላይ ተጥለው የቆዩ ማዕቀቦች የተነሱ ሲሆን ከሌሎች ሃገራት ጋር ያላትም ግንኙነትን ለማሻሻል በር ከፍቷል። የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር በኤርትራ ያደረጉትን ጉብኝትና በሁለቱ መሪዎች መካከል የተፈረሙ ስምምነቶች ዝርዝር ይዘት ሳይታወቅ በተከፈቱት የድንበር መተላለፊያዎች በኩል የሚደረገው ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ በጣም ከፍተኛ እንደነበረ ተነግሯል። ካለፈቃድ በዛላምበሳ ድንበር በኩል ማለፍ ተከለከለ ለዓመታት ተለያይተው የቆዩ ቤተሰቦች ለመገናኘት ጊዜ ሳያጠፉ ነበር ድንበር ማቋረጥ የጀመሩት። በተጨማሪም ነጋዴዎች በሁለቱም ወገን የሚፈለጉ የተለያዩ ምርቶችና የሸቀጦችን በማዘዋወር በድንበር አካባቢ ያለው የንግድ ልውውጥ እንዲጧጧፍ ምክንያት ሆነ። ከዚህ ባሻገርም ለኤርትራዊያን ወጣቶች ሽሽት ምክንያት የሆነውን የብሔራዊ አገልግሎት ለማምለጥ ይጠባበቁ የነበሩ በርካታ ወጣቶችም ነጻ በተለቀቁት የድንበር መተላለፊያዎች በኩል ወደ ኢትዮጵያ መሻገራቸው ይነገራል። ይህ ነጻ የድንበር ላይ ዝውውር ግን ለወራት ነበር የቆየው። አንድ በአንድ ኢትዮጵያንና ኤርትራን የሚያገናኙት የድንበር መተላለፊያዎች የተዘጉ ሲሆን ለዚህም ከሁለቱ መንግሥታት ይፋዊ ምክንያት ባይሰጥም፤ ሃገራቱ የቪዛና የቀረጥ ጉዳዮችን መልክ ለማስያዝ የወሰዱት እርምጃ እንደሆነ ይነገራል። አንድ ዓመት ስለሞላው የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ የአሥመራ ጉዞና የሁለቱ ሃገራትን ግንኙነት ለማሻሻል ስለተወሰዱ እርምጃዎች ቢቢሲ ኒውስ ዴይ የኢትዮጵያና የኤርትራ ጉዳይን በቅርበት የሚከታተሉትን የዩኒቨርሲቲ መምህር የሆኑትን ዶክተር ዮሐንስ ወልደማሪያምን አናግሯቸዋል። የሁለቱ ሃገራት የድንበር መተላለፊያዎች መዘጋታቸውን የሚያረጋግጡት ዶ ር ዮሐንስ፤ አሁንም ድረስ ነገሮች አልጠሩም ይላሉ። ስምምነቱን ተከትሎ ድንበሮች በተከፈቱበት ወቅት ሰዎች እንዳሻቸው መንቀሳስ መጀመራቸው ኢሳያስን ሳያስጨንቃቸው አልቀረም የድንበር በሮቹ የተዘጉት ከኤርትራ በኩል ነው የሚል እምነት እንዳለቸው ዶ ር ዮሐንስ ይናገራሉ። በሁለቱ ሃገራት መካከል ሰላም ሲወርድ ኤርትራ ህዝብ ቀዳሚው ነገር የድንበር ማካለል ሥራ ነው የሚሉት ዶ ር ዮሐንስ፤ አሁንም ድረስ ድንበር የማካለሉ ሥራ አልተሰራም ለዚህም ምክንያቱ ፕሬዝድንቱ ቅድሚያ የሚሰጡት ጉዳይ አለመሆኑ ነው ይላሉ። ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር በደረሰችው ስምምነት ከሕዝቡ ይልቅ ፕሬዝደንት ኢሳያስ ተጠቃሚ መሆናቸውን ይናገራሉ። ተጥሎ የነበረው ማዕቀብ ተነስቷል፣ ዓለም አቀፍ መገለሉ ቀርቷል። ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይም ቢሆን ከኤርትራ ጋር የተደረሰው ስምምነት ዓለም አቀፍ እውቅናን አስገኝቶላቸዋል ይላሉ። ዶክተር ዮሐንስ እንደሚሉት ከሆነ የኤርትራ መንግሥት ለህዝቡ ምን እየተከናወነ እንደሆነ የገለጸው ነገር የለም። ኤርትራዊያ ስለሁለቱ ሃገራት ስምምነት መረጃ የሚያገኙት የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃንን እየሰሙ ነው። የኤርትራ መንግሥት ምንም ያለው ነገር የለም ይላሉ። ከዚህ ዜና በተጨማሪ
ሊብራ፡ አዲሱ የፌስቡክ ዲጅታል ገንዘብ እና አፍሪካ
ሐምሌ ይህንን ለማጋራት በ ዋትስአፕ ከቀጣዩ የፈረንጆቹ ዓመት መጀመሪያ ጀምሮ ፌስቡክ ወደ ሁለት ቢሊዮን ለሚጠጉ ተጠቃሚዎቹ በዋትስአፕ፣ ኢንስታግራም እና በፌስቡክ መተግበሪያዎቹ አማካኝነት ግብይትን እንዲፈጽሙ ለማስቻል እየሰራ ይገኛል። ሊብራ ተብሎ በሚጠራው ክሪፕቶ ከረንሲ ሚሊዮን በአፍሪካ የሚገኙ የፌስቡክ ተጠቃሚዎችም ግብይት መፈጸም ይችላሉ ተብሏል። ከምዕራባውያን ሃገራት ከወዳጅ ዘመዶች በገንዘብ አስተላላፊዎች ከፍተኛ ገዘንብ የምትቀበለው አፍሪካ፤ ፌስቡክ ይህን መሰል ቀላል እና ቀልጣፍ የገንዘብ ዝውውር ማድረጊያ አማራጭን ማምጣቱ ለአፍሪካ አህጉር ጠቀሜታው ላቅ ያለ ነው ተብሏል። አምስቱ የአፍሪካ ቴክኖሎጂ ጎዳናዎች በ የቴክኖሎጂ ጋዜጠኛው አንዲሌ ማሱኩ በደቡብ አፍሪካ ነው የምኖረው። ከውጪ ሃገር የተላከልኝን ገንዘብ ተቀብዬ ወደ ዚምባብዌ ለመላክ ያለኝ ስጋት ከፍተኛ ነው። የተቀበልኩትን ገንዘብ በጠራራ ጸሐይ ልዘረፍ እችላለሁ በማለት ይናገራል። ጋዜጠኛ አንዲሌ የፌስቡክ እቅድ ይህን መሰል ስጋቶችን ከመቅረፍም አልፎ ሰዎች ወደ ትውልድ ሃገራቸው ገንዘብ ለመላክ ከገንዘብ አስተላላፊዎች የሚጠየቁትን ከፍተኛ የማስተላለፊያ ዋጋ መቀነስ ያስችላል ይላል። ባሳለፍነው ዓመት የዓለም ባንክ ያወጣው ሪፖርት እንደጠቆመው ከሰሐራ በታች ወዳሉ ሃገራት ገንዘብ መላክ ከየትኛው የዓለማችን ከፍል ብዙ የማስተላለፊያ ወጪን ይጠይቃል። እንደምሳሌም የአሜሪካ ዶላር በዌስተርን ዩኒያን ወይም በመኒግራም ለመላክ ዶላር መላኪያ ገንዘብ ያስከፍላል። የደቡብ አፍሪካ ራንድ በሌላ በኩል በርካታ የአፍሪካ መንግሥታት በክሪብቶ ካረንሲዎች ላይ የላቸው የደህንነት ጥርጣሬ የፌስቡክም ሆነ የሌሎች ዲጅታል ከረንሲዎች ውጤታማነትን ጥያቄ ውስጥ መክታቱ አልቀረም። በአንድም ሆነ በሌላ መልኩ የክሪፕቶ ካረንሲ መጠቀሚያነትን ካገዱ ሃገራት መካከል ናይጄሪያ እና ዚምባብዌ ይጠቀሳሉ። ክሪፕቶ ካረንሲዎችን በመጠቀም የግዢው ማንነት ይፋ ሳይደረግ ግብይት መፈጸም ይቻላል። በዚህም ሕገ ወጥ ቡድኖች የጦር መሳሪያዎች እና እጾችን ሊገዙ እና ሊሽጡ ይቻላሉ፣ ሕገ ወጥ የገንዘብ ዝውውር እና አሸባሪዎችን ለመደገፍ ያስችላል በማለት ቢትኮይንን ጨምሮ ሌሎች ክሪይፕቶከረንሲዎች ላይ ያላቸውን ስጋት የሚያነሱ ሃገራት አሉ። ክሪይፕቶ ከረንሲን ምንድነው ኦክስፎርድ መዝገበ ቃላት ክሪይፕቶ ከረንሲን ፤ የገንዘብ ልውውጦችን ደህንነት የሚያረጋግጥ፣ የተጨማሪ አሃዶችን መፈጠርን የሚቆጣጠር እና ገንዘብ መተላለፉን የሚያረጋግጥ ጠንካራ ክራፕቶግራፊ የሚጠቀም መገበያያ እንዲሆን ተደርጎ የተቀረጸ ዲጂታል ገንዘብ ሲል ይገልጸዋል። ቢትኮይን ምንድነው ቢትኮይን ማለት በቀላል ቋንቋ፤ ዲጂታል ገንዘብ መገበያያ በማለት ማጠቃለል ይቻላል። ይህ መገበያያ በኪሳችን ተሸክመን እንደምንዞረው የብር ኖት ወይም ሳንቲም ሳይሆን ኦንላይን የሚቀመጥ ዲጂታል ገንዘብ ነው። ሌላው የቢትኮይንና የተቀሩት የክሪይፕቶከረንሲዎች ልዩ ባህሪ በመንግሥታት እና በባንኮች አለመታተማቸው እንዲሁም ቁጥጥር አለመደረጉ ነው። ቢትኮይን የሚፈጠረው ማይኒንግ በሚባል ሂደት ነው። ሊብራ ከቢትኮይን በምን ይለያል፡ ሊብራ ልክ እንደ ቢትኮይን የሚፈጠረው ማይኒንግ በሚባለው ሂደት ነው። ልዩነታቸው ሊብራ በሚታወቁ ኩባንያዎች ቁጥጥር ይደረግበታል። ቢትኮይን እና ሌሎች ክሪፕቶ ከረንሲዎች በመንግሥታት እና በባንኮች አይታተሙም፤ ቁጥጥርም አይደረግባቸውም። የፌስቡኩ ሊብራ ግን በመንግሥታት እና በማዕከላዊ ባንኮች ቁጥጥር ይደረግበታል በተጨማሪም በጥሬ ገንዘብ ተቀማጭ ይኖረዋል። ሊብራ ከአሁኑ ከቪዛ፣ ማስተርካርድ፣ ኡበር እና ሰፖቲፋይ ተቀባይነትን አግኝቷል። የፌስቡክ ዲጂታል ገንዘብ ለአፍሪካውን ሁነኛ የመገበያያ አማራጭን ይዞ ይመጣል የሚሉ በርካቶች እንዳሉ ሁሉ፤ የአፍሪካ መንግሥታት ዜጎች የፌስቡክ ዲጅታል ገንዘበ አጠቃቀም ካልተዋጠላቸው በቀላሉ አገልግሎቱን ማቋረጥ መቻላቸው ስጋትን ፈጥሯል። የኢንተርኔት አገልግሎት አቅራቢ አገልግሎቱን ሆነ ብሎ ቢያቋርጥ በፌስቡክ፣ ዋትስአፕ እና በሌሎች መተግበሪያዎች የሚደረጉ የገንዘብ ዝውውር ወዲያው ይቋረጣል። በዚህም ምክንያት ሊብራ ላይ መሞርኮዝ እንደማይቻል ባለሙያዎች ስጋታቸውን ያስቀምጣሉ። ቢቢሲ ማስተባበያ
እዩ ጩፋ፡ ማን ነው ነብይ ያለህ
ጁን ስለ ማጋራት ተጨማሪ ያጋሩ ማጋሪያ ምረጥ ነብይ እዩ ጩፋ ነብይና ሃዋርያ ተብለው ከተነሱ ብዙዎች አንዱ ነው። ክራይስት አርሚ ኢንተርናሽናል የተሰኘ የፕሮቴስታንት ቤተክርስትያን መስርቶ በርካታ ተከታዮችን ማፍራት ችሏል። ክራይስት አርሚ በተሰኘው የቴሌቪዥን ጣቢያው በሚተላለፉ የፈውስ ትዕይንቶች ፣ አጋንንትን በካራቴ በመጣል ና በሌሎችም በርካታ ምክንያቶች አነጋጋሪና አወዛጋቢ ስለመሆኑ ጠይቀነው ምላሽ ሰጥቷል። ደቡብ ውስጥ ነብያትና ሃዋርያት በዝተዋል ይባላል፤ በዚህ ውስጥ ራስህን እንዴት ነው የምታየው ነብይ እዩ ጩፋ፡ እውነት ነው ኢትዮጵያ ውስጥ የሚያገለግሉ የብዙ ነብያትና ሃዋርያት መነሻ ደቡብ ነው፤ እኔም ከዚያው ነኝ። ምናልባት እግዚአብሔር ቃል ኪዳን ሊኖረው ይችላል። ደቡቡም ሰሜኑም የእግዚአብሔር ነው። ነገር ግን እኔ የተወለድኩበት ወላይታ አካባቢ ብዙ ዋጋ የከፈሉ የወንጌል አባቶች የነበሩበት በመሆኑ ከዚያ ጋርም ሊያያዝ ይችላል ብዬ አምናለሁ። ሐሰተኛ ነብያት በብዛት የሚነሱበት ጊዜ እንደሚመጣ በመፅሃፍ ቅዱስም ተፅፏል።እነዚህ ነብያትና ሃዋርያት ሁሉም እውነተኛ ናቸው እዩ ጩፋ፡ በዚህ ጊዜ ሐሰተኛም እውነተኛም ነብያት አሉ። የሚታወቁት ደግሞ በሥራቸው፤ በፍሬያቸው ነው። እኔ ግን የእግዚአብሔብርን ወንጌል እያገለገልኩ የምገኝ የእግዚአብሔር ነብይ ነኝ ብዬ አምናለሁ። ግን አንተም ገንዘብ ከፍሎ ምስክርነት ያሰጣል፤ ወደ ንግድነት ያደላ ሐይማኖታዊ አካሄድ ይከተላል ትባላለህ እዩ ጩፋ፡ እውነት ነው ገንዘብ ከፍሎን ነው የሚል ነገር ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ተለቆ ነበር። ገንዘብ ከፍሎ የሚለው ነገር ፈጽሞ ውሸት እንደሆነ ግልፅ ማድረግ ስለነበረብኝ እኔም አንዴ መልስ ሰጥቼ ነበር። አጋንንት እስራት ውስጥ ያሉትን ነፃ ለማውጣት ነው የተቀባሁት። ከፍዬ አጋንንት ማስጮኸው ለምንድን ነው ከፍዬ የማስጮህ ከሆነ የቀን ገቢዬ አስር ሚሊዮን እንኳ ቢሆን አያዋጣኝም። ሰው ደግሞ የማያዋጣውን አይሰራም። ማነው ነብይ ብሎ የሾመህ እዩ ጩፋ፡ በዚህ ዓለም ሰው ሰውን የሚሾም ቢሆንም እውነተኛ ሿሚ እግዚአብሔር ነው። በቤተክርስትያን ከእኛ የቀደሙ ሰዎች በእኛ ላይ የተገለፀውን ፀጋ አይተው ወንጌላዊ፣ ዘማሪ ወይም ነብይ ብለው ይሾማሉ። እኔም በጣም በማከብራቸውና በምወዳቸው ቄስ በሊና ነው ሃዋርያ ተብዬ ሹመት የተሰጠኝ። ነገር ግን ከእሳቸው በፊት ቦዲቲ በሚባል ቦታ በማገለግልበት ወቅት ነብይ ሆኜ በቤተክርስትያን ሰዎች ተሹሜአለሁ። እንጂ እራሴን ነብይ ብዬ አልሾምኩም። በአንተ ቤተክርስትያን የሚያመልኩ ባለስልጣናት ወይም ታዋቂ ሰዎች አሉ እዩ ጩፋ፡ ስማቸውን መጥራት ባያስፈልግም እስከ ሚኒስትር ደረጃ ያሉ አሉ። ግን ሰው ስለሚበዛ የስልጣን ደረጃቸው ከሕዝብ ጋር ተቀላቅለው እንዲገቡ የማይፈቅድላቸው አሉ። እነዚህን ሰዎች በተለይ እንደ ሰዉ አጠራር ቪአይፒ አግኝቼ የማገለግልበት ጊዜ አለ። የእግዚአብሔር ክብር ከእኔ ይበልጣል ብለው ቦታ ተይዞላቸው ከሰው ጋር ተጋፍተው የሚገለገሉም አሉ። ከአገር ውጪም ለትልልቅ ሰዎች ጸልዬ አውቃለሁ። ለምሳሌ ባለፈው ሱዳን ሄጄ ለፕሬዘዳንት ሳልቫኪር ቤተ መንግሥት ገብቼ ጸልያለሁ። ትልልቅ ሰዎችንም ወደ ቤተ ክርስትያን ጋብዤ አውቃለሁ። አጋንንት ማውጣትና ካራቴን ምን አገናኛቸው ካራቴ ታበዛለህ። እዩ ጩፋ፡ ካራቴ የተማርኩት አጋንንት ለማውጣት አይደለም። የለየለት ካራቲስትም አደለሁም። እኛ ጋ ከባህልና ከሁኔታዎች ጋር የተለመደ ነገር አለ። ከተለመደው ውጪ ሌላ አቅጣጫ ይዘሽ ስትነሺ ያስገርማል። አዲስ ነገር ነውና ካራቴው ያስገረመው፣ ያደናገረውና ያስደሰተውም አለ። ሁሌ ካራቴ ሁሌ አጋንንትን ጩኸና ውጣ አልልም። መንፈስ እንዳዘዘኝ ነው ማደርገው። በጌታ በእየሱስ ስም ጩኸና ውጣ ብዬ አዝዤ የወደቀውን መንፈስ አንስተው ሲያመጡ በካራቴ መታሁት፣ በቴስታ መታሁት ምን ጉዳት አለው በእጅም በእግርም ጥዬ አውቃለሁ ይህን የማደርገው አጋንንት የተመታና የተዋረደ መሆኑን ለማሳየት ካለኝ ፍላጎት የተነሳ ነው። እግዚአብሔር መላ ሰውነቴን እንደሚጠቀም ማሳያም ነው። እኔ በካራቴ ከእኔ በኋላ ደግሞ በሌላ ስታይል አጋንንትን የሚመቱ ሊነሱ ይችላሉ፤ ይህ የራሴ ስታይል ነው። አንዳንዶች ካራቴውን የሚቃወሙት በቅናት፣ ሌሎች ደግሞ ከመፅሐፍ ቅዱስ ውጪ ነው በማለት ነው። ከካራቴም የተሻለ አሰራር ያላቸው ካሉ ግብዣዬ ነው። በቀይ ቦኔቶች ተከበህ ስትንቀሳቀስ ይታያል። እንዴት ነው እንዲህ በወታደሮች የምትጠበቀው እዩ ጩፋ፡ አንድ ሚሊዮን ሁለት ሚሊዮን ሰዎች በሚገኙበት የሜዳ ላይ መንፈሳዊ ኮንፈረንስ ለህዝብ ደኅንነት ሲባል መንግሥት የጥበቃ ኃይል ያሰማራል። አንዱ ተጠባቂ እኔ ነኝ፤ ከጌታ በታች እኔን ይጠብቃሉ። ብዙ ሰው ግን እኔ ከፍዬ ያመጣኋቸው ይመስለዋል። ብዙ የፖሊስና የወታደር ልብስ የለበሱን ከኋላህ አሰልፈህ የእየሱስ ወታደር ነኝ ን ስታዘምር የሚታይበት ቪዲዮም አለ እዩ ጩፋ፡ እሱ እኔ በክልል ባዘጋጀሁት ኮንፈረንስ ከመንግሥት የተቀበሉትን ሃላፊነት ሦስት ቀን በሥራ ላይ በታማኝነት በማሳለፋቸው በመዝጊያው ቀን ኑ ፖሊሶች ብዬ ጠርቼ የፀለይኩበት ነው። ምክንያቱም ለመንግሥት ለአገርም መፀለይ ስላለብን። እነሱም የመንግሥት አንድ አካል ናቸው። ወደ አገር ጉዳይ ከመጣን፤ በአሁኑ ወቅት በርካታ ፕሮቴስታንቶች በመንግሥት ከፍተኛ ስልጣን ላይ ናቸው ይባላል። ይህ ላንተ የተለየ ትርጉም አለው እዩ ጩፋ፡ በአሁኑ ወቅት በጠላት አይን አገር እየፈረሰ ያለ ይመስላል በእኔ እይታ ግን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ከመጣ በኋላ አገር እየተገነባ ነው። ትልቅ ለውጥ መጥቷል። አንደኛው ለውጥ እግዚአብሔርን የሚያውቅና የሚፈራ መሪ ኢትዮጵያ ላይ መምጣቱ ነው። ስለኢትዮጵያ የቤተ ክርስቲያን ስዕሎች ምን ያህል ያውቃሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ስልጣን ከመምጣታቸው በፊት እግዚአብሄር በትንቢታዊ መንገድ የሰጠኝን መልእክት አስተላልፌ ነበር። ዩ ቲውብ ላይ ይገኛል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደሚመጡ ቀድሞ እግዚአብሄር ተናግሮኝ ተናግሬአለሁ።የፖለቲካ መናጋቱና መናወጡ በየትኛውም ዘመን አለ። ኢትዮጵያ ከመቼውም በላይ ወደ ተነገረላት ከፍታ እየሄደች ያለችበት ጊዜ ላይ ነን። ስለ ኢትዮጵያ ብልፅግና ካነሳህ የልምላሜ ተስፋ የተጣለበት የህዳሴው ግድብ ተሰርቶ የሚያልቅ፤ እውን የሚሆን ይመስልሃል እዩ ጩፋ፡ በእምነት የምትናገሪው ነገር አለ። እኔም የእምነት ቃል መስጠት እችላለሁ። በግሌ እንደ ቤተክርስትያን የጀመርናቸው ትልልቅ ፕሮጀክቶች አሉ። ሰው ሲያይ የማያልቅ የሚመስለው እኔ ግን እንደሚያልቅ አምናለሁ። ያልቃል የምለው ገንዘብ ስላለ ወይም በሌላ ምክንያት ሳይሆን አማኝ ሰው ስለሆንኩና እምነት የሁሉ ነገር ተስፋ ስለሆነ ነው። እንደዚሁ በእምነት አባይም ተገድቦ ያልቃል ብዬ አምናለሁ። የፕሮቴስታንት እምነት ተከታይ የሆኑ ባለስልጣናት ስለመብዛታቸው ጠይቄህ ነበር እዩ ጩፋ፡ ፕሮቴስታንት ስለሆኑ ብቻ ሳይሆን እግዚአብሔርን የሚያውቁና የሚፈሩ በሚለው ብናገር ደስ ይለኛል። ከዚህ በፊት የነበሩት ባለስልጣናት እግዚአብሔርን ካለማወቃቸው የተነሳ ስልጣናቸውን ሰዎችን ለመጉዳት ተጠቅመውበታል። አሁን ግን ፕሮቴስታንት ባለስልጣናቱ ጌታን ስለሚፈሩ ጥሩ ሥራ ይሰራሉ ብዬ አምናለሁ እየሰሩም ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩን ወደ ቤተክርስትያንህ ጋብዘሃቸው ታውቃለህ እዩ ጩፋ፡ አንድ ጊዜ ጋብዣቸው ነበር ግን በጊዜው ለሥራ ወደ ውጪ ሃገር ሄዱ። ከዚህ በኋላ ግን አንድ ፕሮግራም አለ እዚያ ላይ እንዲገኙ ደግሜ እጋብዛቸዋለሁ፤ እንደሚገኙም ተስፋ አደርጋለሁ። ከጥቂት ዓመታት በፊት አትታወቅም ነበር።ያጣህ የነጣህ ደሃ ሆነህ ታውቃለህ እዩ ጩፋ፡ እዚህ ደረጃ ከመድረሴ በፊት ሰው በሚያልፍበት መንገድ አልፌአለሁ። ከመታወቄ በፊት ስለ እኔ ሰምተው የማያውቁ በሦስት በአራት ዓመት ወደ ስኬት እንደመጣሁ አድርገው ያስባሉ። ነገር ግን እጅግ አስቸጋሪና ዋጋ በሚያስከፍል መንገድ ነው የመጣሁት። ብዙ ተከታዮች አሉህ ብዙ ሰዎች የተማሩና በኢኮኖሚም ጥሩ ቢሆኑ ይህን ያህል ተከታይ የሚኖርህ ይመስልሃል እዩ ጩፋ፡ እንደ አሜሪካ የሰለጠነና የበለፀገ አገር ላይም ቢሆን ተከታይ ይኖረኛል ብዬ ነው ማስበው። በጥረቴም በፍልስፍናም አይደለም ሰው የሚከተለኝ። ህዝቡ እንዲከተለኝ የሚያደርግ የእግዚአብሄር ሞገስ ስላለ እንጂ። ሰዎች ድሃ ስለሆኑና ስላልተማሩ ይከተሉኛል ብዬ አላስብም። ጥግ ድረስ የተማሩና ባለፀጎችም አብረውኝ አሉ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያዘጋጁት ገበታ ለሸገር ላይ ጋብዘውህ ነበር እዩ ጩፋ፡አልሰማሁም አጋጣሚ አገር ውስጥም አልነበርኩም። አረቦች ለፈውስ ወደ አንተ እንደመጡ የሚያሳዩ የተለያዩ ቪዲዮዎችን አይቻለሁ። የሶሪያ ስደተኞች ናቸው ወይስ አንተን ብለው የመጡ እዩ ጩፋ፡ እስከማውቀ እኔ ጋር እግረ መንገዱን የመጣ የውጭ አገር ሰው የለም። ፕሮግራም አስይዘው ትኬት ቆርጠው ነው የሚመጡት። ከኢራን፣ ኢራቅ፣ ዱባይና ኦማን ፕሮግራም አስተርጉመው የሚሆነውን ተአምራት እያዩና እየሰሙ ይመጣሉ። ምን ያህል ሃብት አለህ እዩ ጩፋ፡ ሃብቴ የማይመረመር የማይቆጠር ሰማያዊ በረከት ነው። በዓለማዊው የባለጠጋ መለኪያ ራሴን እንዴን እንደምገልጽ ግን እንጃ። አገልጋይ ነን ቤተክርስትያንን የምናንቀሳቅስበት ብር ይመጣል። መባ፣ አስራትና ስጦታ እያገኘን ያንን ደግሞ መልሰን ለአገልግሎት እናውላለን። እንደሚታወቀው በአንድ ጊዜ አስራ አራት ሺህ ሰው የሚያስተናግድ ሚሊዮን ብር የሚያስወጣ የአዳራሽ ግንባታ እያካሄድን ነው። በአንድ ዓመት ውስጥ ያልቃል። በግል ያለህ ምድራዊ ሃብትስ እዩ ጩፋ፡ እስካሁን ያለኝ የማሽከረክረው መኪና ነው። ወንጌልን ከመስበክ ይልቅ ፈውስና ተዓምራት ላይ ያተኩራል እየተባልክ ትተቻለህ እዩ ጩፋ፡ ቅድሚያ የምሰጠው ለወንጌል ነው። ተዓምራት ወንጌል ከሌለ የለም። ቃል ለወጣበት ዘይት የተፀለየበት ዘይት እስከ ሁለት ሺህ ብር ታስከፍላለህም ይባላል እዩ ጩፋ፡ የተፀለየበት ዘይት አኖይንቲንግ ኦይል ሰዎች እኔ መድረስ የማልችልባቸው ቦታዎች እየወሰዱ እንዲፈወሱበት ነው ያዘጋጀነው። አሜሪካ፣ አውሮፓና አረብ አገር እየገባ ነው። አገር ውስጥም በየሰው ቤት እየገባ ነው። እኛ ቤተ ክርስትያን የገባ ሁሉ ይውሰድ የሚል መመሪያ ግን የለም። በነፃ ግን አይሰጥም ምክንያቱም ቤተክርስትያናችን የዘይት ፋብሪካ የላትም። ዘይቱ የሚመጣው ከውጭ ተገዝቶ ነው። ዘይቱ የሚታሸግበት ጠርሙስም የሚመጣው ከውጭ ነው። የጠርሙስ ክዳን፣ ጠርሙስ ላይ የሚለጠፍ ስቲከርም ማምረቻ ፋብሪካ የለንም። ይህን ሁሉ በገንዘብ ስለምናገኝ ነው በገንዘብ የምንቀይረው። የምትጠይቁት ብር የተጋነነ አይደለም ወይ እዩ ጩፋ፡ አልተጋነነም እንዲያውም እኛ እንደ ቢዝነስ ሰው ብናስብ፤ ዶላር ስለጨመረ ዘይት ጨምሯል ብለን ዋጋ መጨመር እንችላለን። ለቲቪ በወር እስከ ሺህ ብር እንከፍላለን። የቤተክርስትያን ኪራይ፣ የወንበር ኪራይ፣ የአገልጋዮች ክፍያና የሳውንድ ሲስተም የመሰሉ ወጪዎችም አሉ። ወንጌላይ የተሰኘው መዝሙር ክሊፕህ፤ ይህንኑ መዝሙር መድረክ ላይ ስትዘምረውም እንቅስቃሴው የወላይተኛ ጭፈራ ነው። እንዴት ነው እንዲህ ፈጣሪ የሚመሰገነው የሚሉ ሰዎች አሉ። እዩ ጩፋ፡ ጨፋሪዎች ናቸው ከእኛ የኮረጁት። የወላይታ ባህል ጭፈራ ምን እንደሆነ ሳላቅ ለእግዚአብሔር ጨፍሬአለሁ። በቤተክርስትያን ሰው የለመደው ሽብሸባ ተነስቶ እያሸበሸበ ስለሆነ ነው። ይሄኛው እንቅስቃሴ ለዘፈን፤ ያ ለእግዚአብሄር ተብሎ የተፃፈ ነገር የለም፤ ሁሉም የእግዚአብሔር ነው። ስለዚህ እኛ ወደፊት የዘፋኞችን እንቅስቃሴ ሁሉ ለእግዚአብሔር ገቢ እናደርጋለን። አለባበስህ ለየት ያለ ነው የልብስ ዲዛይነር አለህ እዩ ጩፋ፡ አዎ ዲዛይነሮቼ ግብፃዊያን ናቸው ልብሴ እዚያ ነው የሚሰራው። ተያያዥ ርዕሶች
አዲሷ የኖርዌይ ጤና ጥበቃ ሚኒስትር ያሻችሁን ብሉ፣ ጠጡ፣ አጭሱ ማለታቸው አስወገዛቸው
ሜይ ማጋሪያ ምረጥ ኖርዌይ የጤና ጥበቃ ሚንስትር አድርጋ የሾመቻቸው ግለሰብ ዜጎች የፈለጉትን ያህል ይብሉ፣ ይጠጡ፣ ያጭሱ በማለታቸው መነጋገሪያ ሆነዋል። ሲልቪያ ሊስታውግ ጤና ጥበቃ ሚኒስትር ተደርገው የተሾሙት አርብ እለት ሲሆን፤ አጫሾች መገለል እንዲሰማቸው ሲደረጉ መኖራቸውንም ተናግረዋል። እኚህ ልወደድ ባይ ናቸው የተባሉት የጤና ጥበቃ ሚኒስትር በፀረ ስደተኛ አቋማቸው ይታወቃሉ። ከዓመት በፊትም ከነበራቸው የመንግሥት ኃላፊነት የወረዱት የሀገሪቱን ደህንነት ስጋት ውስጥ የሚጥል ውሳኔ ደግፈዋል በሚል በቀረበባቸው ተቃውሞ ነበር። አቶ ጌታቸው አሰፋ ላይ ክስ ተመሰረተ የሚኒስትሯን ሃሳብ የሚያብጠለጥሉ ግለሰቦች፤ ስለ ማህበረሰብ ጤና አንድም እውቀት የላቸውም ሲሉ ይኮንኗቸዋል። ሚኒስትሯ ግን ለሀገሪቱ መገናኛ ብዙሃን በሰጡት ምላሽ ላይ የማህበረሰብ ጤና እውቀት የላትም ለሚለው ውንጀላ ያለኝ መልስ ቀላል ነው። የሞራል ልዕልናን ለማስጠበቅ የምቆም ፖሊስ ሆኜ ሰዎች ህይወታቸውን እንዴት መኖር እንዳለባቸው ለመንገር አልሞክርም። ነገር ግን ሰዎች መረጃ አግኝተው የራሳቸውን ውሳኔ እንዲወስኑ አደርጋለሁ ብለዋል። አክለውም ዜጎች የሚፈልጉትን ያህል እንዲያጨሱ፣ እንዲጠጡ እና ስጋ እንዲበሉ መፈቀድ አለበት፤ ዜጎች የትኛው ጤናማ እንደሆነና እንዳልሆነ ያውቃሉ፤ ባለስልጣናት የሚጠበቅባቸው መረጃ መስጠት ብቻ ይመስለኛል ብለዋል። ሚኒስትሯ ከዚህ ቀደም አዘውትረው ያጨሱ የነበሩ ሲሆን አሁን ግን አልፎ አልፎ ብቻ እንደሚያጨሱ ይናገራሉ። ቦይንግ አደጋው ከመድረሱ በፊት ችግሩን አውቅ ነበር አለ የሚያጨሱ ሰዎች እንዲሸማቀቁ፣ ተደብቀው እንዲያጨሱ ይደረጋል፤ ይህ ረብ የለሽ ነው። ማጨስ ጤና ቢጎዳም ግለሰቦች ይህንን መወሰን ያለባቸው ራሳቸው ናቸው። እንደ መንግሥት ማድረግ ያለብን መረጃ መስጠት ብቻ ነው ሲሉም አቋማቸውን ግልፅ ያደርጋሉ። ግለሰቧ ከዚህ ቀደም በሽብር ተግባር የተጠረጠሩ ግለሰቦች የኖርዌይ ዜግነታቸውን እንዲነጠቁ የሚፀድቅ ሕግ ሲፀድቅ በመቃወማቸው የተነሳ ከሀገሪቱ ደህንነት ይልቅ ለአሸባሪዎች መብት ቆመዋል በሚል ከነበራቸው ኃላፊነት እንዲነሱ መደረጋቸው እታወቃል። ተያያዥ ርዕሶች
በሶማሌ ክልል የጄል ኦጋዴን እስር ቤት ኃላፊ ተይዞ ለኢትዮጵያ ተሰጠ
ሜይ ማጋሪያ ምረጥ አጭር የምስል መግለጫ ሐሰን ኢስማኤል ኢብራሂም ሐሰን ዴሬ ኢትዮጵያ ውስጥ በሚገኘው የሶማሌ ክልል ውስጥ በርካታ አሰቃቂ ድርጊቶች ሲፈጸምበት እንደቆየ የሚነገርለት የጄል ኦጋዴን እስር ቤት ኃላፊ የነበረው ግለሰብ በቁጥጥር ሥር ዋለ። አብዲ ሞሃመድ ኡመር በቁጥጥር ስር ዋሉ የቀድሞው የእስር ቤቱ ኃላፊ ሐሰን ኢስማኤል ኢብራሂም በቅጽል ስሙ ሐሰን ዴሬ ሶማሊያ ውስጥ በቁጥጥር ሥር ውሎ ለኢትዮጵያ ተላልፎ በመሰጠቱ ወደ ጅግጅጋ ተወስዷል። ግለሰቡ ክስ ወደ ተመሰረተበት አዲስ አበባ ሊወሰድ እንደሚችልም ተነግሯል። ምንጮች ለቢቢሲ እንደተናገሩት ግለሰቡ የተያዘው ሶማሊያን ከኢትዮጵያ ጋር በምታዋስነው ጎልደጎብ ተብላ በምትጠራው የድንበር ከተማ ውስጥ ነዋሪዎች ለጸጥታ ኃይሎች በሰጡት ጥቆማ አማካይነት ነው። ግለሰቡ በሶማሌ ክልል ውስጥ በሚገኙ የተለያዩ እስር ቤቶች ውስጥ በተለይ ደግሞ ጄል ኦጋዴን ተብሎ በሚታወቀው እስር ቤት ውስጥ ተፈጽመዋል በሚባሉ ሰቆቃዎችና የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ውስጥ ዋነኛ ሚና አለው ተብሎ ሲፈለግ ቆይቷል። አቶ ገዱም ሆነ ደመቀ እኛም ብንፈተሽ ግድፈት አለብን ማለታቸውን አስታውሳለሁ የአቶ ታደሰ ጥንቅሹ ባለቤት ሐሰን ኢስማኤል ሐሰን ዴሬ የቀድሞውን የክልሉን ፕሬዝዳንት አብዲ መሐመድ ኦማርን ጨምሮ በሶማሌ ክልል ውስጥ በተፈጸሙ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ምክንያት ክስ ከተመሰረተባቸው ያህል ተጠርጣሪዎች መካከል አንዱ እንደሆነም ተነግሯል። ግለሰቡ በቀድሞው የሶማሌ ክልል መስተዳደር ውስጥ በከፍተኛ የደኅነትና የጸጥታ ኃላፊነቶች ላይ በተለያዩ ጊዜያት የሰራ ሲሆን ከእነዚህም መካከል የሶማሌ ክልል የጸጥታ ዘርፍ ኃላፊ፣ የማረሚያ ቤቶች ኃላፊ፣ የጄል ኦጋዴን ኃላፊ እና በክልሉ ልዩ ፖሊስ ውስጥም በኮሎኔልነት አገልግሏል። በሶማሌ ክልል የሚገኙ እስር ቤቶች በተለይ ደግሞ ጄል ኦጋዴን ውስጥ ተይዘው የነበሩ እስረኞች ላይ አሰቃቂ ድርጊቶች ይፈጸሙባቸው እንደነበር የፌደራል መንግሥቱና የክልሉ መንግሥት ይፋ ማድረጋቸው ይታወሳል። በእስር ቤቱ ይገኙ በነበሩ በመቶች በሚቆጠሩ እስረኞች ላይ ይፈጸሙ ከነበሩት ድርጊቶች መካከል ከመሬት በታች ባሉ ጨለማ ጉድጓድ ውስጥ ማስቀመጥ፣ የተለያዩ ዓይነት ሰቆቃዎች፣ ከአደገኛ የዱር እንስሳት ጋር እስረኞችን ማስቀመጥ፣ አስገድዶ መድፈርና የመሳሰሉ ድርጊቶች እንደነበሩ ተገልጿል። ተያያዥ ርዕሶች
ኤርትራ በምሽት በሰርሃና ዛላምበሳ ድንበርን ማቋረጥ ከለከለች
ሴፕቴምበር ስለ ማጋራት ተጨማሪ ያጋሩ ማጋሪያ ምረጥ ከኤርትራ ወደ ኢትዮጵያ በሚያስገባው ሰርሃ አካባቢ በሚገኘው ጊዜያዊ ፍተሻ ከምሽቱ ሰአት በኋላ መኪና መግባት እና መውጣት እንደማይችል የኤርትራ የፀጥታ ኃይሎች አስታወቁ። ይህ ከትናንትና ጀምሮ የተተገበረ ሲሆን ሰንዓፈ ደርሶ ወደ አዲግራት ሲመለሱ ከነበሩት መካከል አንዱ የሆነው ሙሉብርሃን ገብረዋህድ ከአስመራ ሲመጡ ከነበሩ ሰዎች ጋር ማለፍ እንደማይፈቀድለት ተነግሮት ሰርሃ ለማደር እንደተገደዱ ለቢቢሲ ገልጿል። ለምን ማለፍ እንዳልቻሉ የኤርትራ የፀጥታ ኃይሎችን እንደጠየቁ የተናገረው ሙሉብርሃን ማታ የሚያጋጥም የመኪና አደጋ እየበዛ ስለሆነ መግባት እና መውጣት እንድንከለክል ታዘናል የሚል ምላሽ እንደተሰጣቸውም ጨምሮ ተናግሯል። በዚህም የተነሳ በርካታ መኪኖች መንገድ ላይ እንዳደሩ እሱም መኪና ውስጥ ማደሩን ይናገራል። የትግራይ ምስራቃዊ ዞን አስተዳደር ስለዚህ ጉዳይ መረጃ ይኖረው እንደሆን ጠይቀን የሚያውቁት ነገር እንደሌለ የዞኑ አስተዳዳሪ አቶ ጌታቸው ፈረደ ተናግረዋል። የእርሶ መሳሪያ ሚዲያ ፕሌይ ባክን ማጫወት ኣልተቻለም። ለሁለት አስርት ዓመታት ተፋጠው የነበሩት ኤርትራና ኢትዮጵያ ጉዟቸው ምን ይመስላል ተያያዥ ርዕሶች
ለመኖሪያ ቤት ኪራይ ቀብድ ግማሽ ሚሊዮን ብር የሚጠየቅባት ከተማ
ኖቬምበር ማጋሪያ ምረጥ አቅምን ያገናዘበ አነስ ያለ ጎጆ ፈልጎ እንደው የራስ ንብረት ማድረግ ባይቻል እንኳ መከራየት የወጣቶች ራስ ምታት ከሆነ ሰንበትበት አለ። በናይጄሪያዋ የንግድ ከተማ ሌጎስ ውስጥ አነስ ያለች ክፍል ለመከራየት ግማሽ ሚሊዮን ብር ያስፈልግዎታል። ቪክቶሪያ አይላንድ በተሰኘችው የሌጎስ ቅልጥ ያለች ክፍል ባለሁለት መኝታ ቤተ መከራየት ፈለጉ እንበል። በትንሹ እስከ ሺህ ዶላር ግማሽ ሚሊዮን ብር ገደማ ቅድሚያ ክፍያ መጠየቅዎ ሳይታለም የተፈታ ነው። ታድያ ይህ የሚጠየቀው ቅድሚያ ክፍያ ዓመታዊ ነው። ከ ሺህ ዶላር ጀምሮ እስከ ሺህ ዶላር ድረስ ሊጠየቁ ይችላሉ። ታድያ ኑሮ እንደ ቀትር ፀሐይ በሚፋጅባት ሌጎስ አከራዮች የሚጠይቁትን ዶላር ይዞ መገኘት ለወጣቶች እጅግ ከባድ ነው። አከራዮች ይህን ያህል ገንዘብ የሚጠይቁበት ምክንያት ሌጎስ ውስጥ የመሬት እና የግንባታ ዋጋ እጅግ ከበድ ያለ በመሆኑ ነው። ቤት መከራየት ለሚሹ ወጣቶች የሚሆን አነስ ያለ ባለአንድ ክፍል ወይም ባለአንድ መኝታ ቤት ማግኘትም የማይታሰብባት ከተማ ናት፤ ሌጎስ። ዓመታዊ ቅድመ ክፍያ አከራዮች ቀድመው ማስከፈልን ይመርጣሉ፤ ለዚያውም ዓመታዊ። የኪራይ ዋጋ ሺህ ብር ከሆነ ዓመታዊ ሂሳብ ሺህ ይሆናል። ይህንን ግንዘብ ሆጭ ማድረግ የማይችል ተከራይ ውሃ በላው ማለት ነው። ከ ዓመት በፊት ጠ ሚ ዐብይ መረጃ አቀብለውት እንደነበር ኦነግ ገለጸ እንደውም አሁን ሕጉ ተሻሽሎ እንጂ አከራዮች የሁለት ዓመት ቅድመ ክፍያ መጠየቅ ይችሉ ነበር። ይህንን የቤት ኪራይ ራስ ምታት መቋቋም ያቃታቸው የሌጎስ ወጣቶች ታድያ ያላቸው አማራጭ ሰብሰብ ብለው በጋራ መኖር ነው። ከተመረቀ በኋላ መኖሪያ ቤት ማግኘት ሥራ ከማግኘት እኩል የከበደው ኦሉዋፌሚ ከሌሎች አጋሮቹ ጋር በመሆን ምንጣፍ ዘርግቶ ይተኛ ነበር። ከቤት ኪራይ እኩል ሌላኛው የሌጎስ ቤት ፍለጋ መከራ ለኮረንቲ እና ውሃ የሚጠየቀው ዋጋ ነው። አከራይ ከፈቀደ ለውሃ እና ለመብራት ከቤት ኪራይ ሂሳብ ላይ ቀነሶ ይከፍላል። አይሆንም ካለ ግን ተከራይ የውሃ እና መብራት ወጪን መሸፈን ግዴታው ነው። ጎሬላ ሚሊየን ናይራ በላ ተባለ ይህንን ችግር ያስተዋሉ ወጣቶች ተሰባስበው አንድ ድርጅት አቋቋሙ፤ ፋይበር የሚባል። ይህ አከራይ እና ተከራይን በበይነ መረብ የሚያጣምር ድርጅት የቅድሚያ ክፍያን ለማስቀረትና ወጣቶች የሚሿቸውን ብዙም ያልተቀናጡ መኖሪያ ቤቶችን ለማቅረብ ቆርጦ ተነስቷል። ድርጅቱ አከራዮች አሉት። ቤት ለመከራየት ተመዝግበው የሚጠብቁ ደንበኞችን ይዟል። እርግጥ ነው ሚሊዮኖች ለሚኖሩባት ሌጎስ ይህ ውቅያኖስን በማንኪያ እንደ መጭለፍ ቢሆንም ወጣቶቹ ያ ቅማቸውን እያደረጉ እንዳሉ ብዙዎች ይከራከራሉ። የኮራ የደራ ሥራ ያለኝ ነኝ፤ ደሞዜም ወፍራም ነው ብሎ ኪራይን በወር ለመክፈል ማሳመን የማይታሰብ ነው። ቢሆንም ሌጎስ ቀንም ማታም ሚስማር ስትመታ፤ ሲሚንቶ ስታቦካ ነው ውላ የምታድረው። የሪል ስቴት ባለቤቶች ለወጣቶች የሚሆን አነስተኛ ክፍል ወይም ባለአንድ መኝታ ክፍል ቤቶች እየሠሩ ነው። ምናልባት እኒህ ግንባታዎች ሲጠናቀቁ የሌጎስ ወጣቶች ችግር ይቀረፍ ይሆናል።
ለሱዳን ቅርብ የሆነው ሁመራ ኦመሃጀር ድንበር በቅርቡ መከፈቱ ይታወሳል። ድንበሩ መከፈቱን ተከትሎም በድንበር አቅራቢያ ከፍተኛ የሆነ የትራፊክ ፍሰት እየተስተዋለ ነው።
አጭር የምስል መግለጫ ኢትዮ ኤርትራ ሁመራ ኦመሃጀር ድንበር በሁመራ ገንዘብ መንዛሪዎች ከመቼውም በላይ ንግድ ደርቶላቸዋል። አንድ ዶላር የሚመነዘረው በ ናቅፋ ገደማ ሲሆን፤ አንድ ዶላር ደግሞ ብር ገደማ ይመነዘራል። በአካባቢውም ብር ወደ ናቅፋ የሚመነዝሩ ነጋዴዎች ይገኛሉ። አጭር የምስል መግለጫ በሁመራም የሚገኙ ገንዘብ መንዛሪዎች በምስሉ ላይ የሚታየውን አልጋ የሚሰሩ እና የሚሸጡ ሰዎች የደንበኞቻቸው ቁጥር እየጨመረ መሆኑን ይናገራሉ። አካባቢው እጅጉን ሞቃታማ ከመሆኑ የተነሳ ሰዎች በእነዚህ አልጋዎች ላይ ከቤት ውጪ ይተኛሉ። በሁለቱ ሀገራት መካከል ተከስቶ በነበረው ግጭት የአንድ ቤተሰብ አባላት በሁለት ሀገራት ተከፍለው ለዓመታት ሳይገናኙ ቆይተዋል። የሰላም ስምምነት ላይ ከተደረሰ በኋላ ለዓመታት ተለያይተው የቆዩ ሰዎች እየተገናኙ ነው። የኢትዮ ኤርትራ ጦርነት መጀመሩን ተከትሎ ቤት ንብረታቸውን ጥለው ሀገር ጥለው የወጡ በርካቶች ናቸው። ከእነዚህ መካከል ከዚህ በታች የሚታዩት ኤርትራውያን ይገኙበታል። እኚህ ሁለት ሰዎች እንደሚሉት፤ ከሁለት አሰርት ዓመታት በፊት ጥለው የሄዱትን ንብረት ይገባኛል የሚል ጥያቄ ሊያነሱ ሁመራ ተገኝተዋል። አጭር የምስል መግለጫ እኚህ ሁለት ሰዎች እንደሚሉት፤ ከሁለት አሰርት ዓመታት በፊት ጥለው የሄዱትን ንብረት ይገባኛል የሚል ጥያቄ ሊያነሱ ሁመራ ተገኝተዋል። ተያያዥ ርዕሶች
ወደ አሥመራ ለመጓዝ ማወቅ የሚገባዎ ነጥቦች
ጁላይ ማጋሪያ ምረጥ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለሃያ ዓመታት ተቋርጦ የነበረውን የአሥመራ በረራውን ማክሰኞ ሐምሌ ዓ ም ሊጀምር መሆኑን አሳውቋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ በኤርትራ ያደረጉትን ይፋዊ ጉብኝት ተከትሎ የሁለቱ አገራት መሪዎች ከደረሱባቸው ስምምነቶች መካከል አንዱ የሆነው የአየር ግንኙነትን የመጀመር ውሳኔን ተከትሎ ነው ይህ ይፋ የሆነው። በአሁኑ ወቅት ወደ ኤርትራ ለመጓዝ ያሰበ ሰው ምን ማድረግ ይጠበቅበታል ቪዛ ኢትዮጵያዊያን ኤርትራ ሲደርሱ ቪዛ ይሰጣቸዋል። በተመሳሳይ መልኩ ኤርትራውያን ኢትዮጵያ ሲገቡ የመዳረሻ ቪዛ ይሰጣቸዋል። ከቀናት በፊት በአዲስ አበባ የሚገኙ የኤርትራ ዲፕሎማቶች ለጉብኝት የሚሄዱ ኢትዮጵያዊያን አሥመራ ሲደርሱ ቪዛ ማግኘት ይችላሉ። ከጉዞ በፊትም የተጓዦች የፓስፖርት ኮፒ ወደ አሥመራ ይላካል ብለው ነበር። የአውሮፕላን ቲኬት የኢትዮጵያ አየር መንገድ በመጀመሪያ በረራው ከአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ከጠዋቱ ሰዓት በመነሳት በቀጥታ ወደ አሥመራ ጉዞ ያደርጋል። ለምሳሌ ሐምሌ ዓ ም ጉዞውን ወደ አሥመራ አድርጎ ሐምሌ ወደ አዲስ አበባ የሚመለስ ተጓዥ ለአየር ቲኬት ብር እንዲከፍል ይጠየቃል። የጉዞ ቲኬት ከኢትዮጵያ አየር መንገድ የሞባይል መተግበሪያ አሊያም ከአየር መንገዱ ድረ ገጽ ላይ አሁን መግዛት ይቻላል። ሰዓት ከ ደቂቃ በሚፈጀው በረራ ጥቅም ላይ ይውላል የተባለው ድሪም ላይነር ከ መንገደኞች በላይ የማሳፈር አቅም አለው። የገንዘብ ምንዛሬ አሥመራ ላይ በብር መገበያየት አይቻልም። የኤርትራ መገበበያ ገንዘብ ናቅፋ ይባላል። የአሜሪካን ዶላር በ ናቅፋ ይመነዘራል። ሆቴል ከአዲስ አበባ ጋር ሲነጻጻር በአሥመራ በርካታ የሆቴል አማራጮች ላይገኙ ይችላሉ። በአሥመራ መሃል ከተማ ለአንድ ቀን አዳር በአማካይ ከ የአሜሪካን ዶላር ሊጠየቁ ይችላሉ። ይህን ያህል ዋጋ የሚጠየቅባቸው አብዛኛዎቹ ሆቴሎች ቁርስ የተካተተባቸው ሲሆን ነጻ የኢንተርኔት አገልግሎትም የሚሰጡ ናቸው። ከላይ ከተጠቀሰው ዋጋ የሚያንሱ የአንግዳ ማረፊያዎች ፔኒሲዮኖች በአሥመራ ከተማ ውስጥ ይገኛሉ። ምግብ እና መጠጥ አማካይ በሆነ የአሥመራ ምግብ ቤት ውስጥ አንድ ጥብስ ከ ናቅፋ የአሜረካ ዶላር ድረስ ሊሸጥ ይችላል። የለስላሳ መጠጦች ናቅፋ ገደማ ይጠየቅባቸዋል። በኤርትራ አሥመራ ሜሎቲ የሚባል አንድ የቢራ አይነት ብቻ ነው ያለው። ለአንድ አሥመራ ሜሎቲ ቢራ ናቅፋ ይከፍላሉ። የትራንስፖርት አገልግሎት ከአሥመራ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ እሰከ መሃል ከተማ ለመጓዝ የህዝብ አውቶብስ ወይም ታክሲዎችን መጠቀም ይችላሉ። የህዝብ አውቶብስ ከተጠቀሙ ናቅፋ ብቻ የሚከፍሉ ሲሆን ሰው የምትይዘውን ታክሲ ከመረጡ ግን ናቅፋ ሊጠየቁ ይችላሉ። በኤርትራ ቆይታዎ ከአሥመራ በሰሜን ምሥራቅ አቅጣጫ ኪ ሜ ርቀት ላይ የምትገኘውን ምፅዋንም መጎብኘት የሚሹ ከሆነ የህዝብ አውቶብስ በመያዝ ከሁለት ተኩል ጉዞ በኋላ መድረስ ይችላሉ። ከላይ የተጠቀሱት ዋጋዎች አማካይ ግምት ወይም ከሦስተኛ አካል የተገኙ ናቸው። ዋጋዎቹ ግብር ያካተቱ ቢሆንም በአንዳንድ ቦታዎች ላይ የዋጋ ልዩነት ሊኖር ይችላል።
እጅግ ከፍተኛ ደስታ ላይ ነኝ በማለት ስሜታቸው ያጋሩን ካፒቴን ዮሴፍ ኃይሉ የሚያበሩት አውሮፕላን የሰላም ጠያራ በሚል የተሰየመ ነው። አብራሪውም በኤርትራ ምድር የቀድሞ ወዳጆቻቸውን እንደሚያገኙ ተስፋ ሰንቀዋል።
ወደ አደግኩበት ስፍራ ነው ተመልሼ የምበረው። በእውነቱ ተደስቻለሁ በማለት ለቢቢሲ ተናግረዋል። አጭር የምስል መግለጫ የዛሬው በረራ ላይ መስተንግዶ በከፊል አውሮፕላኑ በውስጡ ባለስልጣናትን፣ ታዋቂ ግለሰቦች እና ከወዳጅ ዘመድ ጋር ከዓመታት መራራቅ በኋላ ለመገናኘት የተመኙ ተሳፋሪዎችን ይዞ ነበር። የቀድሞው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ ከተሳፋሪዎች መካከል አንዱ ነበሩ። ከአዲስ አበባ ወደ አስመራ የሚወስዱ አውራ ጎዳናዎች አቶ ኃይለማሪያም የዚህ ጉዞ ተሳታፊ በመሆናቸው ምን ያህል ደስተኛ መሆናቸውን ባጋሩበት አፍታ በረራውን ለሁለቱም ሀገራት እና ህዝቦች ወርቃማ ክስተት ሲሉ አሞካሽተውታል። ስልጣናቸውን በራሳቸው ፈቃድ የለለቀቁትን ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝን ከሦስት ወራት በፊት የተኩት ዐብይ አህመድ ዶ ር ከኤርትራው ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር የደረሱበት የሰላም ስምምነት በሁለቱ ሀገራት መካከል የከረመው ቁርሾ ማክተሚያ ሆኗል። በስምምነቱ መሰረት ዛሬ የተጀመረው የአየር በረራ ገና በዋዜማው የብዙዎችን ቀልብ እና ፍላጎትን ለመሳብ ችሏል። ወደ አሥመራ የሚገዙ ሰዎች ቁጥራቸው ከፍ ያለ ስለነበረ ሁለት ውሮፕላኖች ነበሩ የተጓዙት። ኤኤፍፒ እነደዘገበውም የመጀመሪያው አውሮፕላን መሬት ከለቀቀ ከ ደቂቃ በኋላ ሁለተኛ ዙር ተሳፋሪዎችን የያዘ አውሮፕላን ወደ አሥመራ አቅንቷል። የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት ከመቋረጡ በፊት ከኢትዮጵያ ወደ ኤርትራ የሚያደርሱ የበረራ መስመሮች ነበሩ። የዛሬዎቹ በረራዎች የተጠቀሙት ከአዲስ አበባ መቀሌ አሥመራ የሚያደርሰውን መስመር ነው። ቀሪ አራቱ ከሰሞኑ ለሥራ ክፍት እንደሚሆኑና ነባሩ በረራ እንደሚቀጥል ይጠበቃል። ተያያዥ ርዕሶች
ፕሬዝዳንት ኢሳያስ በአዲስ አበባና ሃዋሳ ጉብኝት ያደርጋሉ
ጁላይ አጭር የምስል መግለጫ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ እና ፕሬዝዳንት ኢሳያስ በአሥመራ የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በኢትዮጵያ ጉብኝታቸው ከአዲስ አበባ ባሻገር ወደ ሃዋሳ እንደሚያቀኑ የኢትዮጵያ መንግሥት ኮምኒዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ሚንስትር አቶ አህመድ ሽዴ አስታወቁ። እንዲሁም ሚንስትር መሥሪያ ቤቱን ጠቅሶ ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደዘገበው በአዲስ አበባ የሚገኘው የኤርትራ ኤምባሲ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጉብኝት በሚያደርጉበት ወቅት እንደገና ይከፈታል። ሚንስትሩ በመግለጫቸውም በአዲስ አበባ ከተማ ስታዲየም ፊት ለፊት የሚገኘው የቀድሞ የኤርትራ ኤምባሲ እድሳት እንደተደረገለት አስታውቀዋል። ሚንስትሩ ሕዝቡ ለፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ደማቅ አቀባበል እንዲያደርግ ጥሪ ባደረጉበትና በጽህፈት ቤታቸው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንደተናገሩት ፕሬዝዳንቱ አትዮጵያ ውስጥ በሚቆዩበት ጊዜ የተለያዩ ዝግጅቶች ይኖራሉ። የዐብይ ቀጣይ ፈተናዎች ከእነዚህም መካከል እሁድ ዕለት በሚሊኒየም አዳራሽ ሺህ ሰው የሚታደምበት ዝግጅት እንዳለና በዚሁ ስፍራ ሁለቱም መሪዎች ተገኝተው ንግግር እንደሚያደርጉ ጨምሮ ተገልጿል። በዝግጅቱ ላይ ኢትዮጵያዊያንና የዓለም አቀፍ ማህበረሰብ አባላት እንደሚገኙ አመልክተዋል። ኢሳያስ አፈወርቂ ለጉብኝት ቅዳሜ ሐምሌ ዓ ም ወደ አዲስ አበባ እንደሚመጡ እራሳቸው ፕሬዝዳንቱ ባደረጉት ንግግር ማረጋገጣቸውን የማስታወቂያ ሚኒስትሩ ገልፀው ነበር። የኤርትራ ማስታወቂ ሚኒስትር አቶ የማነ ገብረመስቀል እንደገለፁት ሳዋ ውስጥ በተደረገ ሥነ ሥርዓት ላይ ፕሬዝዳንቱ ባደረጉት ንግግር በሁለቱ ሃገራት መካከል የተጀመረውን ግንኙነት ለማጠናከር በፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የሚመራ ልዑክ ለይፋዊ ጉብኝት ወደ ኢትዮጵያ ይጓዛል ብለዋል። የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ጽህፈት ቤት ሃላፊ የሆኑት አቶ ፍፁም አረጋ በትዊተር ገፃቸው ላይ እንዳሰፈሩት ፕሬዝዳንት ኢሳያስ በኢትዮጵያ የሚደርጉት ጉብኝት ለሦስት ቀናት እንደሚቆይ አመልክተዋል። የእርሶ መሳሪያ ሚዲያ ፕሌይ ባክን ማጫወት ኣልተቻለም። የጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ በ የሥራ ቀናት የት የት ሄዱ ምን ምን ሠሩ የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ አዲስ አበባ እንደሚመጡ በተለያዩ የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ከትናንት ጀምሮ ሲዘገብ የቆየ ቢሆንም ከኢትዮጵያም ሆነ ከኤርትራ በኩል ማረጋገጫ አልተገኘም ነበር፡፡ ይህ የፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጉብኝት ከሃያ ዓመታት በላይ ከዘለቀ ጊዜ በኋላ በኤርትራ ከፍተኛ ባለስልጣን የሚደረግ የመጀመሪያው ይፋዊ ጉብኝት ይሆናል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ባለፈው ሳምንት ወደ አሥመራ ተጉዘው ከፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂና ከከፍተኛ የሃገሪቱ ባለስልጣናት ጋር በመገናኘት በሁለቱ ሃገራት መካከል ተቋርጦ የነበረውን ግንኙነት የሚያሻሽሉ ስምምነቶችን መፈራረማቸው ይታወሳል። በኢትዮጵያ መንግሥት በኩል ለፕሬዝዳንቱ ደማቅ አቀባበል ለማድረግ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ምንጮች የጠቆሙ ሲሆን ፕሬዝዳንት ኢሳያስ በሚታደሙበት ዝግጅት ላይ የተለያዩ ታዋቂ ድምፃዊያን ዜማቸውን እንደሚያቀርቡም ለመንግሥት ቅርብ የሆኑ ምንጮች እየተናገሩ ነው። እስካሁን ማረጋገጥ ባይቻልም አሊ ቢራ፣ ቴዎድሮስ ካሳሁን ቴዲ አፍሮ እና ሃጫሉ ሁንዴሳ ስማቸው እየተነሳ ካሉት ድምፃዊያን መካከል ቀዳሚዎቹ ናቸው። ተያያዥ ርዕሶች
አምስቱ የአፍሪካ ቴክኖሎጂ ጎዳናዎች በ
ጃንዩወሪ ስህተት አልባ የመሬት ምዝገባ በአፍሪካ አብዛኛውን ጊዜ ማስረጃዎች በአግባቡ ስለማይያዙ የመሬት ይዞታ ጉዳይ ሁሌም ያጋጫል።አሉ ተብለው የሚቀርቡ ማስረጃዎችም ብዙ ጊዜ የተሳሳቱ ሆነው ይገኛሉ።ነገር ግን የማይሰረዝና የማይሳሳት ማስረጃ ብሎክቼን በተሰኘ መንገድ ሊዘጋጅ ይችላል።ብሎክቼን መሬትን የሚመለከቱ መረጃዎች የሚደራጅበት ዲጂታል አሰራር ነው።ይህ በብሎክቼን የተደራጀ መረጃ ደግሞ በጥቂት ኮምፒውተሮች ላይ ብቻ ተወስኖ የሚቀር ሳይሆን በሺዎች ወደ ሚቆጠሩ ኮምፒውተሮች የሚላክ ነው።ከዚህ አሰራር ጋር ግንኙነት ያለው ኮምፒውተር ሁሉ በየጊዜው የተሻሻለ መረጃ ይደርሰዋል።ስለዚህ አሰራሩ ግልፅና ተአማኒነት ያለው ነው።ይህን ቴክኖሎጂ በሩዋንዳ ተግባራዊ የሚያደርገው ዋይዝኪ የተሰኘ የመረጃ መረብ ደህንነት ኩባንያ ነው።እንደ አውሮፓውያኑ ላይ የሩዋንዳ መንግስትን የብሎክቼን ተጠቃሚ ለማድረግ ከማይክሮሶፍት ጋር መፈራረሙን ዋይዝኪ አስታውቋል።የመጀመሪያው እርምጃ በሩዋንዳ የመሬት ምዝገባና ስነዳን ዲጅታላይዝ ማድረግ ነው።ኩባንያው በሩዋንዳ የብሎክቼን ማእከል ያቋቋመ ሲሆን በ እንደ ቢትኮይን የሩዋንዳን ክሪፕቶከረንሲ ምናባዊ የኢንተርኔት መገበያያ ለመስራት እቅድ አለው። የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ስራዎችን ለአፍሪካ ማስተላለፍ አለም የሶፍትዌር ሰሪዎች እጥረት አለባት።በሌላ በኩል አፍሪካ ደግሞ በወጣት ህዝብ የተሞላች ነች።አሜሪካና አውሮፓ አፍሪካዊ ሶፍትዌር ሰሪዎችን ቢያሰለጥኑ በዚህ የሰው ሃይል ይጠቀማሉ።አንዲላ ሶፍትዌር ሰሪዎችን ናይጄሪያ ውስጥ አሰልጥኖ በአለም አቀፍ ድርጅቶች የሚያስቀጥር ኩባንያ ነው።በዚህ መልኩ አንዲላ እንደ አውሮፓውያኑ ባለፈው ዓመት ያሰለጠናቸውን በማስቀጠር ሚሊዮን ዶላር አግኝቷል።በ ደግሞ ከፌስቡኩ ማርክ ዙከርበርግ ሚሊዮን ዶላር አግኝቷል።በ ደግሞ አንዲላ በግብፅም ማዕከል እንደሚከፍት ይጠበቃል። ማንኛውንም ክፍያ ቀላል ማድረግ በአፍሪካ ብዙ ሰዎች የባንክ ሂሳብ የላቸውም።በሌላ በኩል የሞባይል ክፍያ ስርአት ውጤታማ እንደሆነ ታይቷል።በጥናት እንደታየው አፍሪካ መቶ ሚሊዮን ሰዎች የሞባይል የገንዘብ ሂሳብ የከፈቱባት አህጉር በመሆን አለምን ከሚመሩ ተርታ ተሰልፋለች።በአሁኑ ወቅት የሞባይል የፋይናንስ አገልግሎት ብድርና ቁጠባን፣መድህንንና ሃዋላን ያካትታል።ችግሩ በዚህ መልኩ የሚሰሩ ስርአቶች በርካታ መሆናቸውና አንድላይ አለመስራታቸው ነው።ይህ ማለት ደግሞ አፍሪካ ውስጥ እቃዎችን በኢንተርኔት መግዛት አለመቻል ነው።ለምሳሌ ፍለተርዌቭ የተባለው ስርአት በመላ አፍሪካ ለባንኮችና ለሌሎች ኩባንያዎችም የሞባይል ክፍያ ስርአት ዝርጋታን እውን አድርጓል።በአውሮፓውያኑ የመጀበሪያው ሶስት ወር ውስጥ ፍለተርዌቭ ሚሊዮን ዶላር በናይጄሪያ፣ጋናና ኬንያ አዘዋውሯል።ከመጀበሪያው ጀምሮ ኩባንያው በአስር ሚሊዮን ዝውውሮች ቢሊዮን ዶላር አስተላልፏል።በዚያው ዓመት ኩባንያው ከአሜሪካ የአስር ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ አግኝቷል።ይህ ድጋፍ ለኩባንያው ትልቅ አቅም እንደሚፈጥርለት የሚጠበቅ ሲሆን በአፍሪካ ሰዎች በኢንተርኔት በቀላሉ የፈለጉትን መግዛት የሚችሉበትን ስርዓት እንደሚዘረጋ ይጠበቃል። በድሮን መልዕክት ማድረስ አለም ላይ በድሮን አነስተኛ ነገሮችን ከቦታ ወደ ቦታ የማመላለስ አገልግሎት የመስጠት ከፍተኛ ፍላጎት አለ።በርግጥ በአቬሽን ህግ ምክንያት ይህ በአሜሪካና በአውሮፓ ተከልክሏል።በተወሰኑ የአፍሪካ አገራት ለምሳሌ በሩዋንዳ ሃሳቡ ተቀባይነት አግኝቷል።የገጠር መንገዶች ምቹ አለመሆንና የበረራዎች ሰፊ ቦታዎችን አለመሸፈን ለድሮን መልዕክት አገልግሎት አፍሪካን ምቹ ያደርጋታል።ዚፕላየን የተሰኘው ኩባንያ እንደ ደም፣ክትባትና ሌሎች መድሃኒቶችን አይነት ቀላል ነገሮችን የሚያደርሱ ድሮኖች አሉት።የአለም የመጀመሪያው የድሮኖች ወደብ የተከፈተው እንደ አውሮፓውያኑ በ በሩዋንዳ ነበር።በወቅቱ ወደቡ በታንዛኒያም እንደሚከፈት ተገልፆ ነበር።በ የታንዛኒያው ዶዶማ ድሮን ወደብ ስራ ይጀምራል ተብሎ ይጠበቃል።በአብዛኛው የሚያመላልሰውም መድሃኒት ነክ ነገሮችን ይሆናል።ፎርብስ እንዳለው ይህ በአለም ትልቁ የድሮን መልዕክት ማድረስ ስርአት ይሆናል። ያለ ኤሌክትሪክ ሃይል ማሰራጫዎች መብራት እንዲኖር ማድረግ ፔግ አፍሪካ ከኤሌክትሪክ ማሰራጫዎች ሃይል ለማይደርሳቸው ሶላር ፓኔሎችን የሚሸጥ ድርጅት ነው።ሶላር ፓኔል መግዛት ለብዙዎች ውድ በመሆኑ ሰዎች በአነስተኛ የሞባይል ክፍያዎች ኤሌክትሪክ ሃይል ማግኘት የሚችሉበትን ሁኔታም ኩባንያው አመቻችቷል።በዚህ መልኩ እንደ አውሮፓውያኑ ላይ ፔግ ሚሊዮን ዶላር አግኝቷል።ፔግ አፍሪካ በጋናና በአይቮሪኮስት እየተስፋፋ ነው። ተያያዥ ርዕሶች
የአፍሪካ ብሔራዊ ቡድኖችና ከገንዘብ ጋር የተያያዙ የአንጫወትም ማስፈራሪያዎች
ጁላይ ማጋሪያ ምረጥ ከጨዋታዎች በኋላ ከሚሰጥ የክፍያ ገንዘብ ጋር በተያያዘ ብዙ የአፍሪካ ሃገራት ብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾች አንጫወትም እያሉ ሲያስፈራሩ መስማት የተለመደ ነገር ሆኗል። በ ኛው አፍሪካ ዋንጫም የዩጋንዳ ብሄራዊ ቡድን ተጫዋቾች ከምድባቸው ማለፋቸው ካረጋገጡ በኋላ የሀገሪቱ እግር ኳስ ፌደሬሽን የሽልማት ክፍያውን ከፍ የማያደርግ ከሆነ እንደማይጫወቱ አስታውቀው ነበር። ተጫዋቾቹ ስልጠናም አንሰራም በማለት ተቃውሟቸውን ገልጸዋል። የሀገሪቱ እግር ኳስ ማህበርም ልምምዳችሁን ቀጥሉ እኛ ገንዘቡን እንጨምራለን በማለት መደራደር መጀመሩ ይታወሳል። በመጨረሻም ከምድባቸው በማለፋቸው ብቻ ለእያንዳንዱ ተጫዋች ዶላር ለመክፈል ተስማምቷል። ለአፍሪካ ዋንጫ የሚፋለሙት ኃያላን እንስሳት ይህ አጋጣሚ በዚህኛው አፍሪካ ዋንጫ ብቻ አራተኛው ክስተት ነው። የናይጄሪያ ብሄራዊ ቡድን አባላት ቃል የተገባልን ሺ ዶላር ካልተሰጠን ወደ ስልጠና አንሄድም ብለው ነበር። በተመሳሳይ የካሜሩን ብሔራዊ ቡድን አባላት ከእግር ኳስ ማህበሩ ጋር በተፈጠረ ገንዘብ ነክ አለመግባባት ለውድድሩ ወደ ግብጽ ያቀኑት አርፍደው ነበር። የዚምባብዌ ተጫዋቾችም ውድድሩን አቋርጠን እንመለሳለን ማለታቸው የሚታወስ ነው። የአፍሪካ ብሔራዊ ቡድኖች አመፅ ምክንያት ብሔራዊ ብድኖች ወደ ቀጣዮቹ ዙሮች ባለፉ ቁጥር የሚሰጣቸው የክፍያ መጠን ከፍ እያለ ይሄዳል። ይህ ማለት ደግሞ ብሔራዊ ቡድኑ በሚያገኘው ስኬት ላይ ተመስርቶ የሃገራቱ የእግር ኳስ ማሕበራት ጠቀም ያለ ገንዘብ ያገኛሉ። በዚህ ምክንያት በውድድሩ በመሳተፋቸው ብቻ ተጫዋቾቹ ተጨማሪ ክፍያ ማግኘት ያለባቸው ሲሆን ወደ ቀጣይ ዙሮች ሲያልፉ ደግሞ ተጨማሪ ማበረታቻዎች ማግኘት አለባቸው። በተለያዩ የአውሮፓ ሊጎች ለሚጫወቱ ተጫዋቾች ምናልባት የማበረታቻው ገንዘብ ክለቦቻቸው ሚከፍሏቸው ጋር ሲነጻጸር ምንም ማለት ላይሆን ይችላል፤ ነገር ግን በየሃገራቱ ሊጎች ለሚጫወቱት ተጫዋቾች ብዙ ትርጉም አለው። ለምሳሌ ሁሉም የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾች በዓለም ዋንጫው ለዕሩብ ፍጻሜ በመድረሳቸው ያገኙትን የማበረታቻ ገንዘብ ሙሉ በሙሉ ለበጎ አድራጎት ድርጅት ለግሰዋል። በአፍሪካ ሊጎች ለሚጫወቱትና በተለያዩ ውድድሮች ሃገራቸውን ወክለው የሚሄዱት ተጨዋቾች ግን ይህንን የማድረግ እድሉም የላቸውም። እንደውም ከሃገራቱ የእግር ኳስ ፌደሬሽኖች ማግኘት የሚገባቸው የማበረታቻ ገንዘብ ሲዘገይ አንዳንዴም ከነጭራሹ ሳይሰጣቸው ሲቀር ይስተዋላል። ይህ ደግሞ ተጫዋቾቹን ወደ አመጽና ውድድሩን አቋርጠን እንመለሳለን ወደሚሉ ውሳኔዎች ይገፏቸዋል። ተጫዋቾች አንጫወትም ባሉ ቁጥር ለሃገሪቱ እግር ኳስ ፌደሬሽን መጥፎ ስም ከማሰጠቱ ባለፈ ያለአግባብ ለግለሰቦች ጥቅም የሚውለው ገንዘብ ትኩረት ያገኛል፤ ከብክነትም ይድናል። እንደ ዲዲየር ድሮግባ እና ጆርጅ ዊሃ ያሉ ትልልቅ ተጫዋቾች በሃገራቸው ሊግ ለሚጫወቱ የብሄራዊ ቡድን አባላት ድጋፍ በማድረግ ፌደሬሽኖች ላይ ጫና እስከማሳደርም ደርሰው ነበር። ተያያዥ ርዕሶች
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አገልግሎት ለምን ተስተጓጎለ
ኦገስት ማጋሪያ ምረጥ በመላው ሃገሪቱ ባሉት ቅርንጫፎችና በትልቅነቱ ቀዳሚ እንደሆነ የሚነገርለት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለአራት ተከታታይ ቀናት ተስተጓጉሎ የነበረውን አገልግሎት አስተካክሎ መደበኛ አገልግሎቱን መስጠት እንደጀመረ የባንኩ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ የአብሥራ ከበደ ለቢቢሲ ገለፁ። የአማራ ክልል ተፈናቃዮች ስለ ንግድ ባንክ እርዳታ ምን ይላሉ ከሰሞኑ አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ አካባቢዎች ከሚገኙ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች የተለመደውን አገልግሎት ማግኘት እንዳልቻሉ ተገልጋዮች ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከ ሚሊዮን በላይ ደንበኞችና ከ በላይ ቅርንጫፎች እንዳሉት የገለፁት ኃላፊው፤ ከባለፈው ሳምንት አርብ ጀምሮ ሲስተሙ የመዘግየት ችግር እንዳጋጠመውና ሙሉ በሙሉ ተስተጓጉሎ እንደነበር አረጋግጠዋል። ይሁን እንጂ ባሳለፍነው እሁድ ወደ መደበኛ አገልግሎት ተመልሶ የኤትኤም ማሽኖች ሙሉ በሙሉ አገልግሎት ሲሰጡ እንደነበር ገልጸዋል። ይኽው አገልግሎት እንደገና ሰኞ ጠዋት ጀምሮ በድጋሚ መስተጓጎል ገጥሞት የነበረ ቢሆንም ማክሰኞ ከሰዓት ጀምሮ መደበኛ አገልግሎታቸውን እየሰጡ ይገኛሉ ብለዋል። በአጠቃላይ ለአንድ ቀን ተኩል ያህል ነበር አገልግሎቱ የተቋረጠው የሚሉት ኃላፊው አገልግሎቱ ከተስተካከለ በኋላ በየቅርንጫፎቹ የደንበኞች ቁጥር ጨምሮ ነበር ይላሉ። ስለ ሲስተሙ መጨናነቅ የተጠየቁት አቶ የአብሥራ እንዲህ ነው ተብሎ የሚገለፅ ነገር የለም፤ ግን ቴክኖሎጂ በባህሪው ድንገት የሚፈጠሩ ችግሮችን ያስተናግዳል ሲሉ ምላሻቸውን ሰጥተዋል። የሲስተም መጨናነቅ በባንኩ ውስጥ አሊያም በውጭ በሚፈጠሩ የኢንተርኔትና የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ ምክንያት ሊፈጠር እንደሚችል የሚያስረዱት ኃላፊው፤ አሁን ያጋጠመው ችግር ግን በራሱ በባንኩ ሲስተም መጨናነቅ ምክንያት የተፈጠረ ነው ብለዋል። እርሳቸው እንደሚሉት ባንኩ ለሚመጡት ዓመታት የሚያገለግል ዘመናዊ የመረጃ ቋት ያለው ቢሆንም ያጋጠመው እክል አንዳንድ ጊዜ በቴክኖሎጂ ላይ በሚፈጠሩ ጊዜያዊ ችግሮች ነው። በነበረው መስተጓጎል የደረሰውን ኪሳራ አስመልክተን ጥያቄ ያነሳንላቸው አቶ የአብሥራ ባንኩ የደንበኞች አገልግሎት ላይ ትኩረት አድርጎ ሲሰራ ነበር እንጂ፤ ባጋጠመው መስተጓል ያጋጠመው ኪሳራ ስሌት ውስጥ አልገባም ብለዋል። ኃላፊው አክለውም ወደፊት ተመሳሳይ ችግር እንዳያጋጥም እየሠሩ መሆናቸውን አስረድተዋል። የደንበኞች ቁጥር በጨመረ ቁጥርም እንዲህ ዓይነት መጨናነቆች እንዳይከሰቱ ባንኩ አስፈላጊውን ሁሉ እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል። ከዚህም ባሻገር የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሞባይል ባንክ፣ የኢንተርኔት፣ ሲቢኢ ብር፣ በካርድ አገልግሎት ክፍያ መፈፀሚያ ማቅረቡን በመግለፅ ደንበኞች ሳይንገላቱና ሳይደክሙ አገልግሎቱን መጠቀም እንደሚችሉ ጠቁመዋል። እንደ አማራጭ የቀረቡት መንገዶች ከኢንተርኔት አገልግሎት ላይ የተመሰረቱ ናቸው። በኢትዮጵያ ያለው የኢንተርኔት ተደራሽነትና ፍጥነት በርካቶች የሚማረሩበት ነው። እንዲያም ሲል በተለያዩ ምክንያቶች በተለያዩ ጊዜያት መዘጋቱ ጉዳዩን የከፋ ያደርገዋል። በመሆኑም እነዚህ ንግድ ባንክ ያስቀመጣቸው አማራጭ አገልግሎቶች የበለጠ ጫናው ላይ አይወድቁም ወይ ስንል ለኃላፊው ጥያቄ አንስተን ነበር። ኃላፊውም ችግሮች መኖራቸውን አምነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለችግሮቹ እልባት ለመስጠት ሃገሪቱ ውስጥ ያለውን እንዲሁም የራሱንም መሠረተ ልማት አጣምሮ እንደሚጠቀም ገልፀዋል። በዚህ መካከል የሚፈጠሩ ችግሮችን ለመፍታት ጥረት እየተደረገ ደንበኞች ፈጣን አገልግሎት እንዲያገኙ ይደረጋል ብለዋል። እስካሁን ከ ሚሊዮን በላይ የኤትኤም ካርድ ተጠቃሚዎች እና ከ ሚሊዮን በላይ የሞባይል ባንክ ተጠቃሚዎች አሉ የሚሉት ኃላፊው በኢትዮጵያ ካለው የሕዝብ ብዛት ጋር ሲነፃፀር በጣም አነስተኛ እንደሆነ ጠቅሰዋል። ይሁን እንጂ በአገሪቱ የሚፈጠሩ ክፍተቶቹን ባንኩ እየሞላ አገልግሎት መስጠታቸውን እንደሚቀጥሉ ያስረዳሉ። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያጋጠመው መስተጓጎል ተፈታ ካለ በኋላ በአንዳንድ አካባቢዎች የሚገኙ ተጠቃሚዎችና የባንኩ ሠራተኞችን በመጠየቅ ለማረጋገጥ ባደረግነው ሙከራ የነበረው ችግር መፈታቱን የገለጹ ሲሆን በተወሰኑ ቦታዎች ላይ የሲስተም ዘገምተኛ መሆን እንዳለ ገልጸዋል። ስለ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ኃላፊው እንደነገሩን ከ ሚሊየን በላይ ደንበኞች አሉት የተቀማጭ ገንዘብ መጠኑ ቢሊየን ብር ደርሷል አጠቃላይ ሃብቱ ከ ቢሊየን ብር በላይ ነው ከ ሚሊየን በላይ የኤ ቲ ኤም ካርድ ተጠቃሚዎች አሉት ከ ሚሊየን በላይ የሞባይል ባንክ ተጠቃሚዎችን ያስተናግዳል ሺህ ሠራተኞች አሉት የደበኞች ቁጥር በየዓመቱ በ እና ሚሊየን ብልጫ ያሳያል። ተያያዥ ርዕሶች
የባንክና የኢንሹራንስ ዘርፍ ለኢትዮጵያዊያን ብቻ የተተዉ ይሆናል
ዲሴምበር ማጋሪያ ምረጥ ኢትዮጵያ የባንክና የኢንሹራንስ ተቋማትን ለውጪ ባለሃብቶች ተሳትፎ ክፍት እንደማታደርግ ሮይተርስ ጉዳዩን በሚመለከት የተዘጋጀን ረቂቅ ሕግን ዋቢ አድረጎ ዘገበ። ኢትዮጵያ የተለያዩ የኢኮኖሚ ዘርፎችን ለውጪ ባለሃብቶች ክፍት ለማድረግ የተለያዩ ተግባራትን እያከናወነች ቢሆንም የባንክና የኢንሹራንስ ዘርፎች ግን አሁንም ዜጎቿ ብቻ የሚሳተፉባቸው መስኮች ሆነው እንዲቆዩ ልታደርግ መሆኑን ሮይተርስ አየሁት ባለው ረቂቅ ሕግ ላይ ሰፍሯል ብሏል። የተለያዩ የውጪ ባለሃብቶችና ተቋማት ኢትዮጵያ ክፍት ታደርጋቸዋለች ተብለው የሚጠበቁ ተቋማትን ለመግዛትና በመንግሥት እጅ ስር ብቻ ተይዘው በነበሩ ዘርፎች ላይ ለመሳተፍ ያላቸውን ፍላጎት እየገለጹ ነው። ኢስላማዊ ባንክ ለኢትዮጵያ ምን ይፈይዳል የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድን ወደ ስልጣን መምጣትን ተከትሎ የአገሪቱን ኢኮኖሚ ለማሳደግና ኢትዮጵያን ወደ መካከለኛ ገቢ ለማሳደግ በመንግሥት ቁጥጥር ስር የነበሩ ዘርፎች ላይ የውጪ ባለሃብቶች ክፍት እንደሚሆኑ ተገልጾ ነበር። ሮይተርስ የጠቀሰው ረቂቅ የኢንቨስትመንት ሕግ ላይ እንዳመለከተው የባንክ፣ የኢንሹራንስ፣ አነስተኛ የቁጠባና የብድር የገንዘብ ተቋማት ለአገር ውስጥ ባለሃብቶች ብቻ የተተዉ ዘርፎች ይሆናሉ። የአገሪቱ የባንክ ዘርፍ በአፍሪካ በመንግሥት ከፍተኛ ቁጥጥር የሚደረግ ነው። ባለፈው ሐምሌ የአገሪቱ ምክር ቤት አምስት ሚሊዮን ለሚሆኑ የሌላ አገር ዜግነት ያላቸው ትውልደ ኢትዮጵያዊያን የባንኮችን አክሲዮን ለመግዛት እንዲችሉ የሚፈቅድ ሕግ ሲያወጣ፤ በበርካቶች ዘንድ ቀስ በቀስ ዘርፉ ለውጪ ባለሃብቶችም ክፍት ሊደረግ ይችላል የሚል ተስፋን ፈጥሮ ነበር። እውን ድህነትን እየቀነስን ነው በጠቅላይ ሚኒስትሩ እየተወሰዱ ካሉ የኢኮኖሚ ማሻሻያ እርምጃዎች መካከል ትላልቆቹን የስኳር ማምረቻ ፋብሪካዎች ወደ ግል ይዞታነት የማዘዋወሩ እርምጃ ከወራት በኋላ ይጀመራል ተብሎ ይጠበቃል። በተጨማሪም መንግሥት ለሁለት የሞባይል ስልክ አገልግሎት አቅራቢ ድርጅቶች ፈቃድ ለመስጠትና የመንግሥት ንብረት ከሆነው ኢትዮ ቴሌኮም ላይ ደግሞ የተወሰነ ድርሻን ለባለሃብቶች ለመሸጥ ዕቅድ አለው። በሮይተርስ የተጠቀሰው ረቂቅ የኢንቨስትመንት ሕግ በቀጣዮቹ ሁለት ወይም ሦስት ሳምንታት ውስጥ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቦ ውይይት ከተደረገበት በኋላ ይጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል። ኢትዮጵያ በፍጥነት እየጨመረ የሚሄድና ወጣት ሕዝብ ያላት ሲሆን ኢኮኖሚዋም ከአስር ዓመታት በላይ በሁለት አሃዞች ሲያድግ ቆይቷል። ነገር ግን በአገሪቱ የሚስተዋለው ብሔርን መሰረት ያደረገ ውጥረትና ግጭት ኢኮኖሚው ላይ ስጋትን ፈጥሯል። ተያያዥ ርዕሶች
በስህተት የገባላቸውን አንድ ሚሊየን የመለሱት የመቀለ ነዋሪ
ጃንዩወሪ ማጋሪያ ምረጥ ደሳለኝ ብስራትና አንበሳ ባንክ ከሰሞኑ በስህተት የተላከላቸው ሚልዯን ብር ለባንኩ ወስደው ያስረከቡት የመቀለ ከተማ ነዋሪው ድርጊት ብዙዎችን አጀብ አሰኝቷል። የገንዘቡ ባለቤትም ገንዘቡን ተቀብሏል። ነገሩ ወዲህ ነው። ባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪ ባጃጅ የንግድ ስራ ላይ የተሰማሩት አቶ ደሳለኝ ብስራት ዕለተ ቅዳሜ ታኃሣሥ አመሻሽ ላይ ቁጭ ባሉበት በተንቀሳቃሽ ስልካቸው አንድ መልዕክት ይደርሳቸዋል። ይህም አንበሳ ኢንተርናሸናል ከተባለ የተላከ መልዕክት ሚልዮን ብር ገብቶልሃል ሲል ይነበባል። ስህተት መሆኑ ገባኝ የአንበሳ ባንክ አካውንቴ አዲስ መሆኑን ሳስብ ነው። ሌላ አካውንት ቢሆን ሰው አድርጎልኛል ብዬ አስብ ነበር። አካውንቱ አዲስ ስለሆነ ግን ብዙ ሰው አያቀውም ተሳስተው ነው ብዬ ሰኞ ጥዋት ወደ ባንክ ቤት ሄድኩኝ። ስህተቱ እንዴት ሊፈጠር ቻለ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ አንድ የመርካቶ ነጋዴ ከአንድ ሌላ ቻይናዊ ጋር ባላቸው ውል መሠረት ሚሊዮን ብር ለሌላ ግለሰብ መላክ ነበረባቸው። ቻይናዊው ብር የሚላክለትን ግለሰብ የሂሳብ ደብተር ቁጥርም ይሰጣቸዋል፤ እኝህ ግለሰብም እነደተባሉት ገንዘቡን ለመላክ ወደ አንበሳ ባንክ ያመራሉ። ባንክ ሲደርሱ ግን የተሰጣቸው የሂሳብ ደብተር ቁጥር እና የባለቤቱ ስም እሚመሳሰል አልነበረም። በግዜውም ጉዳዩን ለማጣራት የሞከሩት የገንዘቡ ላኪ ወደ ቻይናዊው አጋራቸው ደውለው ሁኔታውን ያስረዱታል። ነገር ግን ወከባ ውስጥ የነበረው ቻይናዊ አጋራቸው እንግዲህ እኔ ስም ተሳስቼ ይሆናል እንጂ ቁጥሩስ ትክልል ነው ግድየለህም አስገባው ይላቸዋል። አንድ ሚሊዮን ብሩም ዘሎ የአቶ ደሣለኝ አካውንት ወስጥ ዘው ማለት። የአንበሳ ባንክ የራጉኤል ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጅ አቶ መድሃንዬ ኪዳነ ከመቐለ ወደ ቅርንጫፋቸው ሲደወል በወቅቱ እኛ የተሳሳትን መስሎን ነበር ይላሉ። ሆኖም ብሩ የተላከበት ማስረጃ ሲታይ ምንም ስህተት የለም። ይሄኔ ለገንዘቡ ላኪ ደውለው ሁኔታውን እነደነገሯቸው ያስረዳሉ። ላኪው የመርካቶ ነጋዴ ሁኔታውን ሲሰሙ እግጅ እንደተደናገጡ ያወሳሉ። ተጠቀምበትና ጠያቂ ከመጣ በኋላ ትመልሰዋለህ ክስተቱን የሰሙ የአቶ ደሣለኝ ወዳጆች በሁኔታው አፋቸውን ሸፍነው ተገረሙ። ግማሹ መልካም ነገር ነው ያደረግከው ይለኛል፤ ግማሹ ደግሞ ምነው ደሣለኝ የሚል አስተያየት ይሰጣቸዋል። አውጥተህ አሰቀምጠው ፤ ዝም ብለህ ተጠቀምበትና ጠያቂ ከመጣ በኋላ ትመልሰዋለህ ያሏቸውም እነደነበሩ አልደበቁም። እሳቸው ግን መመለስ ካለብኝ በጊዜ ነው መመለስ ያለብኝ ብዬ መልሽላሁ ይላሉ። ደሳለኝ ብስራት አቶ ደሳለኝ በምላሹ ምን አገኙ አንበሳ ባንክ ለአቶ ደሣለኝ የምስጋና ደብዳቤ በመስጠት ለቅን ተግባራቸው እውቅና እንደሰጣቸው አቶ መድሃዬ ይናገራሉ። የአቶ ደሳለኝ ተግባር ከአእምሮ በላይ ነው ብዙ ነገር በሚበላሽበት ዘበን ሲሉ ክስተቱን ይገልፁታል። ተገልጋዮችም የሚልኩበትን የሂሳብ ደብተር ቁጥር በትክክል ከቻሉም የሂሳብ ደብተሩ ባለቤት ስም ከአባት እና አያት ጭምር ቢያውቁ መልካም ነው ሲል ምክር የጣል ያደርጋሉ። ተያያዥ ርዕሶች
ገብርኤል ንጋቱ፡ የአፍሪካ ልማት ባንክ ቁልፍ ሰው
ጃንዩወሪ ስለ ማጋራት ተጨማሪ ያጋሩ ማጋሪያ ምረጥ አዲስ አበባ ውስጥ ተወልደው ያደጉት አቶ ገብርኤል ንጋቱ በአህጉራዊና በዓለም አቀፍ ግዙፍ ተቋማት ውስጥ በከፍተኛ የኃላፊነት ቦታ ላይ ከሚገኙ ጥቂት ኢትዮጵያዊን መካከል አንዱ ናቸው። በአፍረካ አገራት ውስጥ በሚካሄዱ የምጣኔ ሃብትና የልማት ተግባራት ላይ ቁልፍ ድርሻ ባለው የአፍሪካ ልማት ባንክ ውስጥ ወሳኝ ከሚባሉ የባንኩ ባለስልጣናት አንዱ በመሆን ከ ዓመታት በላይ በ የአፍሪካ አገራት ውስጥ አገልግለዋል። አቶ ገብርኤል ከአርባ ዓመታት በፊት ደርግ ወደ ስልጣን ላይ በወጣበት ጊዜ ነበር ከኢትዮጵያ ወጥተው ለአጭር ጊዜ አውሮፓ ውስጥ ከቆዩ በኋላ አሜሪካ ውስጥ ለበርካታ ዓመታት ኖረዋል። ከኮርኔል በኮምፒውተር ሳይንስ ፒኤችዲ በማግኘት የመጀመሪያዋ ጥቁር ሴት የሆነችው ረድኤት አበበ አሜሪካ ውስጥ በስደት መኖር ሲጀምሩ ኢትዮጵያ ውስጥ የነበረው ሁኔታ አስቸጋሪ እንደነበር የሚያስታውሱት አቶ ገብርኤል፤ መጀመሪያ ላይ አሜሪካ ውስጥ ለመኖር የሚያስፈልጋቸውን የመኖሪያ ፈቃድ ለማግኘት እንደተቸገሩና ትምህርት ሳይጀምሩ ለተወሰነ ጊዜ መቆየታቸውን ይናገራሉ። ኢትዮጵያ ውስጥ የነበረው ሁኔታ ሲባባስ ሕጋዊ የመኖሪያ ሰነድ ማግኘት ስለቻሉ ትምህርት ጀመሩ። ካሊፎርኒያ ስቴት ዩኒቨርስቲ ውስጥ የመጀመሪያ ዲግሪ በፕላኒንግ፣ ሁለተኛ ዲግሪን ደግሞ ከፒትስበርግ ዩኒቨርስቲ፣ ከዚያም በኋላ ሃርቫርድ ዩኒቨርስቲ እንዲሁም እንግሊዝ አገር ማንቺስትር ዩኒቨርስቲና ሌሎችም ቦታዎች ተምረዋል። የስደት ፈተናና ጥረት በንጉሡ የስልጣን ዘመን ማብቂያ ላይ ወደ አሜሪካ የመጡት አቶ ገብርኤል ህጋዊ በሆነ መንገድ ወደ አሜሪካ ስላልገቡ በስደት ውስጥ ኑሮን ማሸነፍ ፈታኝ ነበር ይላሉ። የመኖሪያ ፈቃድ እኪያገኙ ድረስም በተለያዩ ችግሮች ውስጥ ማለፋቸውንና የሥራ ፈቃድ ስላልነበራቸው የጽዳት ሥራን ተደብቀው ይሰሩ እንደነበርም ያስታውሳሉ። በቴክኖሎጂ ኢ ፍትሐዊነትን የምትታገለው ኢትዮጵያዊት የንጉሡ ወዳጅ የነበሩት አሜሪካኖች ደርግ ስልጣኑን ይዞ ይወስዳቸው የነበሩትን እርምጃዎች ከተመለከቱ በኋላ ግን ለኢትዮጵያዊያን የመኖሪያ ፈቃድ መስጠት ሲጀምሩ በነጻነት የመኖርና የመስራት እድልን አገኙ። ኢትዮጵያዊ በተለይ ከአገሩ ሲወጣ ጠንካራ ነው የሚሉት አቶ ገብርኤል ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ የሚችሉትን ሁሉ እየሰሩ ለመማርና የተሻለ ህይወት ለመኖር መጣር ነበረባቸው። ቢሆንም ግን ዝቅ ያለ ሥራ በመስራት የዕለት ተዕለት ወጪን ሸፍኖ ለመማር ከባድ እንደነበር የሚገልጹት አቶ ገብርኤል፤ ከሌሎች ሰዎች ጋር ተዳብለው በአንድ ላይ ቤት በመከራየት ከዚያም የተለያዩ ሥራዎችን በፈረቃ በመስራት ዛሬ ለደረሱበት ደረጃ ያበቃቸውን ትምህርት በፈታኝ ሁኔታ ውስጥ ሆነው መማር ጀመሩ። የወጣትነት ፈተናዎች በአፍላ የወጣትነት ዕድሜያቸው ከአገር የወጡት አቶ ገብርኤል ንጋቱ፤ መጀመሪያ ጣሊያን ለተወሰኑ ወራት መቆየታቸውንና ከዚያም ወደ አሜሪካ ሲሄዱም ከቤተሰብ ቁጥጥር ነጻ መሆን ከእድሜ ጋር ተያይዞ የራሱ ፈተና አለው ይላሉ። ነጻነቱ እንዲሁም ቁጥጥር የማይደረግበት የተወሰነ ገንዘብ በእጅ መኖር ወደ ተለያዩ አላስፈላጊ ልማዶች ሊመሩ የሚችሉበት አጋጣሚዎች እንደነበሩና በዚያ ሁኔታ ውስጥ ደግሞ ራስን የመግዛት ጥንካሬ ያስፈልግ እንደነበር ያስታውሳሉ። ዝነኞቹ ቮልስዋገኖችና ድንቅ ታሪኮቻቸው ነገር ግን የቤተሰባቸው አስተዳደግና በኃይማኖት ተቀርጸው እንዲያድጉ መደረጋቸው ከቤተሰብ ርቀው ባገኙት ነጻነት ወዳልተፈለገ አቅጣጫ እንዳይሄዱ እንዳደረጋቸውም ያምናሉ። አቶ ገብርኤል በወጣትነት ዘመናቸው ከትክክለኛው የሕይወት መስመር የሚያወጡ በርካታ ፈተናዎች የነበሩ ቢሆንም ወደዚያ ባለመሄዳቸው ለስኬት በቅተዋል። ነገር ግን ጥቂት የማይባሉ ጓደኞቻቸው ለፈተናዎቹ ተሸንፈው ሕይወታቸው መመሳቀሉንና ለተለያዩ ችግሮች መዳረጋቸውን ያስታውሳሉ። የአፍሪካ ልማት ባንክ አቶ ገብርኤል ጋብቻ መስርተው ልጆች ሲወልዱ ወደ ወጡበት አህጉር ተመልሰው ልጆቻቸውን የማሳደግ ፍላጎት እንዳደረባቸው፤ ለዚህም ከባለቤታቸው ጋር ተስማምተው ሥራ ሲያፈላልጉ፤ አፍሪካ ልማት ባንክ አይቮሪኮስት ውስጥ ዩኒሴፍ ደግሞ ኬንያ ውስጥ ላሏቸው ክፍት ቦታዎች ላወጡት ሥራ ተወዳደሩ። ሁለቱም ተቋማት አቶ ገብርኤል ለተወዳደሩበት ቦታ ከሌሎች ልቀው መገኘታቸውን በማመልከት አንዳቸው አንዳቸውን ተከትለው ሥራ እንዲጀምሩ ጋበዟቸው። አቶ ገብርኤልም ምርጫቸው አፍሪካ ልማት ባንክ ላይ አርፎ ቤተሰባቸውን ይዘው ከአሜሪካ ወደ ምዕራብ አፍሪካ አቀኑ። የአፍርካ ልማት ባንክ ኢትዮጵያን ጨምሮ የአህጉሪቱ አገራት በባለቤትነት የሚያስተዳደሩት ሲሆን ከአፍሪካ ውጪ ደግሞ በተለያዩ አህጉራት የሚገኙ አገራትም በባንኩ ውስጥ የባለቤትነት ድርሻ አላቸው። አቶ ገብርኤል በአፍሪካ ልማት ባንክ ውስጥ ሥራ ሲጀምሩ ከዝቅተኛው የሙያተኛ ደረጃ የተነሱ ቢሆንም በየሁለትና በየሦስት ዓመቱ እየተወዳደሩ በማደግ በድርጅቱ ውስጥ ባሉ ኃላፊነት ቦታዎች ውስጥ አልፈው ዋና ዳይሬክተር ከሚባለው ከፍተኛ ቦታ ላይ ለመድረስ ችለዋል። አቶ ገብርኤል እንደሚሉት ባንኩ እርሳቸው በመሩት መልሶ የማዋቀር ሥራ በአምስት ቀጠናዎች ተከፋፍሎ እንዲሰራ የሚያስችለውን ሥራ አከናውነዋል። ከዘዚህ በኋላም አቶ ገብርኤል በአፍሪካ ልማት ባንክ ውስጥ ካሉ አምስት የዋና ዳይሬክተርነት ቦታዎች ውስጥ አንዱን በመምራት በባንኩ ታሪክ የመጀመሪያው ዋና ዳይሬክተር ለመሆን ከመብቃታቸው ባሻገር ለዚህ የኃላፊነት ቦታም በመብቃት የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ናቸው። አቶ ገብርኤል በአፍሪካ ልማት ባንክ የምሥራቅ አፍሪካ አገራት ዋና ዳይሬክተር በመሆን ለበርካታ ዓመታት ከማገልገላቸው በፊት በሰላሳ ሁለት አገራት ውስጥ የሚሰራውን የባንኩን የመዋዕለ ነዋይ አስተዳደር ክፍልን በማቋቋምና ለበርካታ ዓመታት በመምራትም ጉልህ አሻራቸውን እንዳኖሩ ይነገርላቸዋል። ከባንኩ ዋና ዋና ክፍሎች አንዱ የሆነውና መቀመጫውን ኬንያ ውስጥ ያደረገውን የ አገራትን የሚከታተለው የባንኩን የምሥራቅ አፍሪካ ቅርንጫፍን የመሰረቱት እንዲሁም ለረጅም ዓመታት የመሩት አቶ ገብርኤል ንጋቱ ናቸው። ባንኩ የአገራትን ሕዝብና የምጣኔ ሃብት ዕቅድን መሰረት በማድረግ የሚያማክር ሲሆን አስፈላጊ በሚሆንበት ጊዜም በብድርም ሆነ በዕርዳታ የሚያስፈልጋቸውን ገንዘብ እንዲገኝና ዕቅዳቸው በተገቢው ሁኔታ ተግባራዊ እንዲሆን ክትትልና ድጋፍ በማድረግ በኩል ሚናው ከፍተኛ ነው። ፈተናና ስኬት አቶ ገብርኤል በአፍሪካ ልማት ባንክ ውስጥ የቆዩበት ጊዜ በስኬት ብቻ የተሞላ አልነበረም፤ የዛሬ ዓመት ገደማ የዓለም የኢኮኖሚ ቀውስ በተከሰተበት ጊዜ በአፍሪካ ሃብታም ከሚባሉ ጥቂት አገራት መካከል አንዷ የነበረችው ቦትስዋናን ለመደገፍ የተደረገው ጥረት እጅጉን በሥራ ሕይወታቸው ፈታኙ ነበር። እጅግ ውድ የነበረውና ቦትስዋና በስፋት የምትታወቅበት የአልማዝ ምርት ገበያ በወቅቱ በመውደቁ አገሪቱ ከባድ የኢኮኖሚ ቀውስ ውስጥ በመውደቋ የአገሪቱ መንግሥት የአፍሪካ ልማት ባንክ ድጋፍ እንዲያደርግለት ጥሪ አቀረበ። ለዚህ ሥራ ደግሞ በባንኩ ውስጥ ቀዳሚ ተመራጭ ሆነው የቀረቡት አቶ ገብርኤል ንጋቱ ነበሩ። ኃላፊነቱ እንደተሰጣቸው ለሥራው የሚያስፈልጋቸውን ቡድን አዋቅረው በመምራት ወደ ቦትስዋና ሄደው ድርድር በማድረግና ውድቀት አፋፍ ላይ የነበረውን የቦትስዋናን ኢኮኖሚ ለመታደግ የሚያስፈልጉ ፕሮጀክቶችን የመቅረጽ ሥራን ጀመሩ። ኢትዮጵያ ከውጭ ምንዛሬ እጥረት አዙሪት እንዴት ትውጣ በወቅቱ አገሪቱ የገጠማት የኢኮኖሚ ቀውስ እጅግ አሳሳቢ ስለነበረ የሚያስፈልጋትን ድጋፍ ለይቶ በማወቅና መደረግ ያለባቸውን የማሻሻያ ዕርምጃዎች በማቅረብ በቶሎ እርምጃ ካልተወሰደ ፖለቲካዊ ቀውስ ሊፈጠር የሚችልበት ዕድል ስለነበረ፤ በአቶ ገብርኤል የሚመራው ቡድን ለአንድ ወር ያህል ለ ሰዓታት ያለዕረፍት በመስራት ጥረት አድርጓል። ፕሮጀክት በማዘጋጀት፣ የፖሊሲ ሃሳቦችን በመቅረጽና ከመንግሥት ባለስልጣናት ጋር በመደራደር ቡድናቸው በቀንና በሌሊት ፈረቃ ተከፍሎ መፍትሄዎችን ለማምጣት ጥረት ማድረጋቸውን የሚናገሩት አቶ ገብርኤል ሥራው እጅግ አስጨናቂና ውጥረት የተሞላበት ነበር ይላሉ። ይህ ለአንድ ወር የተሰራው ሥራ በመጨረሻም የቦትስዋና መንግሥት ማድረግ የሚገባውን የማሻሻያ ሃሳቦች ለባንኩ ቦርድ ቀርቦ ከስምምነት ላይ በመደረሱ በአፍሪካ ልማት ባንክ ታሪክ በወቅቱ ለአንድ ፕሮጀክት የተሰጠ ከፍተኛው ገንዘብ ለመሆን ችሏል። ይህም ለቦትስዋና የተፈቀደ ከፍተኛው ብድር ቢሊየን ዶላር ሲሆን አቶ ገብርኤልም ሐሳቦችን ከመቅረጽ አንስቶ ከመንግሥት ባለስልጣናት ጋር የሚደረገውን ድርድር በመምራት ወሳኝ ሚና ነበራቸው። ይህም በአቶ ገብርኤል የአፍሪካ ልማት ባንክ የሥራ ህይወታቸው ውስጥ እጅግ የተጨነቅኩበትና ለስኬቱም አጥብቄ የጸለይኩበት ጉዳይ ነበር ሲሉ ያስታውሱታል። በአፍሪካ ጠንካራ ኢኮኖሚ ካላቸው አገራት አንዷ የሆነችው ቦትስዋናም ከአሳሳቢው የውድቀት አፋፍ ተመልሳ አሁን የተረጋጋ ኢኮኖሚ እንዲኖራት በማድረጋቸው አድናቆትን አግኝተዋል። ኢትዮጵያና የአፍሪካ ልማት ባንክ አቶ ገብርኤል ንጋቱ ከአፍሪካ ልማት ባንክ ጋር በተያያዘ አገራቸው ኢትዮጵያን በሚመለከት ከፍ ያለ ፈተና ገጥሟቸው እንደነበር ያስታውሳሉ። ወቅቱ አወዛጋቢው የ ዓ ም ብሔራዊ ምርጫን ተከትሎ በአገሪቱ ቀውስና አለመረጋጋት ያጋጠመበት ነበር ይላሉ። በአገሪቱ በተከሰቱ ግድያዎች ሳቢያ የዓለም የገንዘብ ተቋማት ለኢትዮጵያ የገንዘብ ድጋፍ እንዳይሰጡ ግፊት በሚደረግበት ጊዜ ውሳኔው መንግሥትን ብቻ ሳይሆን ሕዝቡንም የሚጎዳ በመሆኑ ሌላ አማራጭ እንዲፈልግ ጥረት አድርገዋል። በዚህም አቶ ገብርኤል የሚሰጠው ድጋፍ ወደ መንግሥት እጅ ከመግባት ይልቅ ቁጥጥር እየተደረገበት ለሕዝቡ የሚቀርቡ መሰረታዊ አገልግሎቶችን ለመጠበቅ የሚያስችል ፕሮግራም በመንደፍ አሁን ድረስ የዘለቀ አማራጭን አቅርበዋል። ከዚህ በተጨማሪም አቶ ገብርኤል በባንኩ ድጋፍ ኢትዮጵያ ውስጥ የተካሄዱ ትልልቅ ፕሮጀክቶችን ጨምሮ የኢትዮጵያን የኤሌክትሪክ አቅርቦት ከጎረቤት አገራት ጋር ለማገናኘት እንዲሁም የመንገድ ግንባታዎችን በተመለከቱ ወሳኝ ፕሮጀክቶች ውስጥ ሚና ነበራቸው። አማካሪ አያስፈልገኝም ብሎ የሚያስብ መሪ አልገባውም ማለት ነው ፕሮፌሰር አለማየሁ ገዳ ምንም እንኳን አቶ ገብርኤል ከነበሩበት ኃላፊነት አንጻር ሁሉም የአፍሪካ አገራት አገራቸው እንደሆኑ ቢናገሩም ኢትዮጵያን በሚመለከት ግን ልባቸው የሚደላባቸው አጋጣሚዎች እንዳሉ አይሸሽጉም። በአፍሪካ ልማት ባንክ ውስጥ የአገራቸውን ጥቅም የሚነካ ነገር ካለ በዝምታ አያልፉም ይባልላቸዋል። ባልደረቦቻቸውም ይህንን ስለሚያውቁ ይህንን ገብርኤል አይቀበለውም በማለት አስቀድመው እንደሚረዱ ገልጸው፤ ነገር ግን ይህ ድርጊታቸው ኢትዮጵያ ከሌሎች በተለየ እንድትጠቀም ሳይሆን የኢትዮጵያ እንዳትበደልና የኢትዮጵያዊያን መብት እንዳይነካ የቻልኩትን ከማድረግ አንጻር ብቻ ነው ይላሉ። ነገር ግን ከሌሎች ጋር ከሚያደርጉት በተለየ ለአገራቸው ባለስልጣናት ጠቃሚ መረጃዎችንና ምክሮችን በመስጠት አገራቸውና ሕዝቡ እንዲጠቀም ከሙያቸው ሥነ ምግባር ሳይወጡ ካላቸው ኃላፊነት አንጻር የሚችሉትን ሁሉ ባገኙት አጋጣሚ ሲያደርጉ መቆየታቸውን ይናገራሉ። ኢትዮጵያዊያን በዓለም አቀፍ ተቋማት ውስጥ ኢትዮጵያ ከአፍሪካ በሕዝብ ብዛት ሁለተኛ ብትሆንም ዜጎቿ በአህጉራዊና በዓለም አቀፋዊ ተቋማት ውስጥ ያለቸው ተሳትፎ ዝቅተኛ መሆኑ የሚያሳዝን ነው ይላሉ አቶ ገብርኤል። እንደምሳሌም የምዕራብ አፍሪካ አገር የሆነችው ጋምቢያን ያነሳሉ፤ ጋምቢያ በጣም ትንሽ የሕዝብ ቁጥር ቢኖራትም በአፍሪካ ልማት ባንክ ውስጥ በሚሰሩ ዜጎቿ ቁጥር ኢትዮጵያን በብዙ ዕጥፍ ትበልጣለች ይላሉ። ለዚህም ከኃይለ ሥላሴ ሥርዓት መውደቅ በኋላ በነበሩት ጊዜያት ወደ ውጪ አገራት ሄዶ ለመማር የነበረው ዕድል መዘጋቱና ወደ ውጪ የሄዱትም ተምረው በትልልቅ ዓለም አቀፍ ተቋማት ውስጥ ከመግባት ይልቅ፤ የዕለት ኑሮን ለማሸነፍና ቤተሰብ ለመርዳት በተለያዩ ሥራዎች ላይ በመሰማራታቸው እንደሆነ ያስባሉ። ወደ ተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት ለመግባት በዋናነት የሚያስፈልገው ብቃት መሆኑን የሚጠቅሱት አቶ ገብርኤል ከዚህ ባሻገር ግን የመንግሥት ድጋፍ ወሳኝ ነው። መንግሥት ዜጎቹ ለተወዳደሩበት ተቋማት ባሉት የግንኙነት መስመሮች ሁሉ ድጋፍ ከሰጠና ተጽዕኖ መፍጠር ከቻለ ተቀባይነት ለማግኘት ወሳኝ እንደሆነ ይጠቅሳሉ። ከዚህ አንጻር ግን ኢትዮጵያዊያን ብቃቱ ኖሯቸው ከመንግሥታቸው ድጋፍ ለማግኘት ስለሚቸገሩ የአገራቸውን ድጋፍ በሚያገኙ ሌሎች ተወዳዳሪዎች በመበለጥ ዕድሉን ያጣሉ። ከ ዓመት በኋላ የኢትዮጵያ ዕጣ ፈንታ ምን ይሆናል ላለፉት የኢትዮጵያ መንግሥታት እንዲዚህ አይነቱን ድጋፍ ለዜጎቻቸው ለመስጠት ኢትዮጵያዊ መሆን ብቻ በቂ አልነበረም፤ ነገሮች በፓርቲ አባልነት የሚወሰኑ ሆነው ቆይተዋል የሚሉት አቶ ገብርኤል ይህ ግን አሁን እንደሚቀየር ያምናሉ። ብዙ ኢትዮጵያዊያን ተምረውና ሰርተው ውጤታማ መሆንን የሚያስቡት በአገራቸው ውስጥ ነው። ከዚህ ወጥተን ራሳችንን በዓለም ደረጃ ተወዳዳሪ መሆን እንደምንችልና በብቃታችን የሚገባንንም ለማግኘት አስከመጨረሻው መጠየቅና ገፍቶ መሄድ መልመድ አለብን ብለዋል። ለዚህ ደግሞ በተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት ውስጥ የሰሩ የተወሰኑ ኢትዮጵያዊያን በሥራቸው ብቁና የተመሰከረላቸው ስለሆኑ በችሎታ በኩል ኢትዮጵያዊያን ደፍረው መውጣት ከቻሉ ከማንም የሚያንሱበት የሥራ መስክ የለም ብለው ያምናሉ። ለዚህ ደግሞ ማበረታታትና ድጋፍ አስፈላጊ ነው። ከዚህ አንጻር ለዜጎቻቸው ድጋፍ የሚያደርጉ አገራትን ሲያነሱ ሴኔጋልን በምሳሌነት ይጠቅሳሉ፤ በዓለም አቀፍ ተቋማት ውስጥ ለመስራት ለሚያመለክቱና ለሚሰሩ ዜጎቻቸው ድጋፍ የሚሰጥ ጽህፈት ቤት በአገሪቱ የውጪ ጉዳይ መስሪያ ቤቱ ውስጥ አለ። ከዚህ በሻገርም አንድ ሴኔጋላዊ በየትኛውም ዓለም አቀፍ ድርጅት ውስጥ ለመቀጠር አመልክቶ ድጋፍ ካስፈለገው ፕሬዝዳንቱ ሳይቀሩ ለተቋማቱ ኃላፊዎች በመደወል ዕድሉ እንዲሰጣቸው እስከመጠየቅ የሚደርስ ድጋፍ ያደርጋሉ። ይህም የሚሆነው በፖለቲካ አመለካከት፣ በዕምነት ወይም በብሔር ሳይሆን ዜጋ በመሆን የሚሰጥ ድጋፍ ነው ይላሉ አቶ ገብርኤል። ስንብት ለ ዓመታት ከዘለቀው ትዳራቸው የሦስት ልጆች አባት የሆኑት አቶ ገብርኤል ንጋቱ፤ ከሃያ ዓመታት በላይ በአፍሪካ ልማት ባንክ ውስጥ በከፍተኛ የኃላፊነት ቦታ ላይ ቆይተው አክብሮትና ዝናን አትርፈዋል። የአቶ ገብርኤል ዕውቅና ባገለገሉበት ድርጅት ውስጥ ብቻ ሳይሆን በተለያዩ የአፍሪካ አገራት መሪዎችና ከፍተኛ ባለስልጣናት ዘንድም ንጋቱ እየተባሉ አክብሮትን አግኝተዋል። በዚህ ዓመት በጡረታ ከአፍሪካ ልማት ባንክ ሲሰናበቱ አቶ ገብርኤል በተለያዩ አገራት መሪዎች እየተጋበዙ ሽኝት ተደርጎላቸዋል፤ ድርጅታቸውም በአገልግሎት ዘመናቸው ላበረከቱት ከፍተኛ አስተዋጽኦ በክብር ነበር የሸኛቸው። በቀጥታ ለአገሬና ለሕዝቧ ሰርቼ አላውቅም የሚሉት አቶ ገብርኤል በውጪ አገር ለረጅም ዘመን ሰርተው ጡረታ ወጥተዋል። አሁን ባላቸው ዕውቀትና ልምድ አገራቸውን በሚጠቅሙ በተለያዩ መንገዶች ኢትዮጵያን ለማገልገል ፍላጎት እንዳላቸው ይናገራሉ። በዳያስፖራ ትረስት ፈንዱ ውስጥ የአማካሪ ምክር ቤት አባል ሲሆኑ፣ ከተወሰነ የዕረፍት ጊዜ በኋላ በተለያዩ መስኮች ላይ በመሰማራት አገራቸውንና ሕዝቡ የሚጠቅሙ ሥራዎችን ለማከናወን ዕቅድ አላቸው። ተያያዥ ርዕሶች
ትግራይ ውስጥ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደንበኞች የሚፈልጉትን ገንዘብ ለማውጣት ተቸገርን አሉ
ጃንዩወሪ ማጋሪያ ምረጥ ትግራይ ውስጥ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደንበኞች ገንዘብ ማውጣት አለመቻላቸው ተናገሩ። ካለፈው ሰኞ ጀምሮ በተለያዩ የትግራይ ክልል ከተሞች የሚገኙ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች ደንበኞች ገንዘብ ማውጣት አለመቻላቸውን ለቢቢሲ ገለጸዋል። በአብዛኞቹ የኢዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች ከአንድ ሺህና ከሁለት ሺህ ብር በላይ ማውጣት እንደማይችሉ ተነግሮናል ይላሉ። ለምሳሌ በዓድዋ ከተማ ሰሎዳ ዓዲኣቡን በተባለው ቅርንጫፍ ብር ለማውጣት የሄደችው ተጠቃሚ ወጣት፤ ከሁለት ሺህ ብር በላይ ማውጣት አትችይም መባሏን ለቢቢሲ ትናገራለች። በዚህ ከተማ የሚገኙ ሌሎች ቅርንጫፎች ደግሞ ከ ሺህ እስከ ሺህ ሲሰጥ እንደዋለ ከዚያ በላይ ግን ብር የለም በማለት አልስጥም መባላቸውን ተገልጋዮች ለቢቢሲ ገልጸዋል። በተመሳሳይ በውቅሮ ክልተውላዕሎ የሚገኘው ቅርንጫፍ ከአንድ ሺህ ብር በላይ አልሰጥም ማለቱን የባንኩ ደንበኞ ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። አምስት ሺህ ለማውጣት ወደ ቅርንጫፉ ሂዳ፤ አንድ ሺህ ብር ብቻ የተሰጣት አንድ ነዋሪም በተመሳሳይ የገጠማትን ተናግራለች። ከዚህ መጠን በላይ ማውጣት አትችሉም ተብለው የተከለከሉት የከተማዋ ነዋሪዎች ተጨንቀው እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል። እንዲሁም ደግሞ ደመወዛቸው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሚከፈላቸው የክልሉ የመንግሥት ሠራተኛ በተመሳሳይ ብር የለም ጠብቁ መባላቸውን ምንጮች ይናገራሉ። በመቀለ የሚገኘው የቢቢሲ ሪፖርተር ተዘዋወሮ እንተመለከተው፤ በመቀለ የሚገኙ ቅርንጫፎችም በወረፋ መጨናነቃቸውንና የጠየቁት ብር ሳይሰጣቸው ስለቀረ ሲበሳጩና በቁጣ ሲናገሩ ታዝቧል። ኢህአዴግ ነፃ ገበያም፣ ነፃ ፖለቲካም አላካሄደም ፀደቀ ይሁኔ ኢንጂነር ስሙ እንዲጠቀስ ያልፈለገው አንድ በመቀለ ቅርንጫፍ በኃላፊነት ላይ የሚገኝ የባንኩ ሠራተኛ፤ ባንኩ የገንዘብ እጥረት እንዳጋጠመው ይናገራል። በተለይ በትግራይ የሚገኙ ቅርንጫፎች ምንም ብር እንደሌላቸው ተናግሯል። ለዚህ እንደምክንያት የተጠቀሰውም የተለያዩ ሰዎች ገንዘባቸው ከባንኩ እያወጡ እንደሆነ ነው። ችግሩ በሌሎች አከባቢዎችና በሌሎች የግል ባንኮችም፤ ሊከሰት እንደሚችል አመላክቷል። የባንኩ ሠራተኛ አክሎም በትግራይ ውስጥ፤ ከብሔራዊ ባንክ ፍቃድ የተሰጣቸው አራት ዋና ዋና አከፋፈይ ማዕከላት በመቀለ፣ በማይጨው፣ በዓድዋና ሽረ እንዳሥላሰ የሚገኙ ሲሆን፤ በእነዚህ ማዕከላት ውስጥ የብር እጥረት ስለአጋጠመ ነው ወደ ቅርንጫፎች ብር ያልተላከው ይላል። ስሙ እንዳይጠቀስ የጠየቀው ይኸው ኃላፊ እንጋለው ብሔራዊ ባንክ ችግሩን በጥቂት ቀናት ለመፍታት እየሰራ እንደሆነ አክሎ ተናግሯል። ቢቢሲ ያናገራቸው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አልሰን አሰፋ ግን የገንዘብ ዕጥረት እንደሌለ ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የገንዘብ ዕጥረት አልገጠመውም። ምናልባች የኔትወርክ ችግር ቢኖርበት ነው በማለት የተባለው ውሸት እንደሆነ ጠቅሰዋል። ጨምረውም ከ ሺህ ብር በላይ አታወጡም የሚል ህግም የለም የሚሉት አቶ አልሰን፤ ያለው ችግር ከቴሌ ጋር የሚያያዝ እንደሆነም ይናገራሉ። ገንዘብ የማውጣት ገደቡንም በተመለከተ ይሄ ፈጽሞ ሊሆን አይችልም። የባንኩ አሰራርም አይደለም ብለዋል። ማንኛውም ሰው በባንኩ ያስቀመጠውን ብር በየትኛውም ቅርንጫፍ የማውጣት መብት አለው። ይህንን መብቱ የመከልከል መብት የለንም። የተባለው ችግር በትግራይ ካለ ለምን የእዚያ አከባቢ ቅርንጫፍ ኃላፊዎች አላነሱልንም እንደሱ የሚባል መረጃ አልደረሰንም ብለዋል። ተያያዥ ርዕሶች
ዓለም ሁሉ የሚያወራለት ክሪይፕቶከረንሲ ምንድነው
ፌብሩወሪ የጥንታዊው የሰው የዛፍ ፍሬ ለቅሞ እና እንስሳት አድኖ ህይወትን አስቀጥሎ ከዚህ ደርሷል። በጊዜ ሂደት እና በቴክኖሎጂ እድገትም የአኗኗር ዘያችን በፍጥነት እየተቀየረ መጥቷል። ለዚህም ማሳያ የሚሆነን ደግሞ ዲጂታል ገንዘቦችን ለምርት እና አገልግሎት መገበያያነት ማዋል መቻላቸው ሊጠቀስ ይችላል። ኛው ክፍለዘመን ካስተዋወቀን የቴክኖሎጂ ምጡቅ ቃላት መካከል ብዙ እየተባለለት ያለው ክሪይፕቶከረንሲ አንዱ ነው። ኦክስፎርድ መዝገበ ቃላት ክሪይፕቶከረንሲን እንዲህ ሲል ይገልጸዋል፤ የገንዘብ ልውውጦችን ደህንነት የሚያረጋግጥ፣ የተጨማሪ አሃዶችን መፈጠርን የሚቆጣጠር እና ገንዘብ መተላለፉን የሚያረጋግጥ ጠንካራ ክራፕቶግራፊ የሚጠቀም መገበያያ እንዲሆን ተደርጎ የተቀረጸ ዲጂታል ገንዘብ። ከላይ የተጠቀሰውን መስፈርት የሚያሟሉ በርካታ አይነት ክሪፕቶካረንሲዎች አሉ። በስፋት ከሚታወቁት መካከል ቢትኮይን፣ ኤቴሪያም፣ ሪፕል እና ቢትኮይን ካሽ የሚባሉት ከበርካታ ክሪፕቶካረንሲዎች መካከል ሊጠቀሱ ይችላሉ። በቅድሚያ የ ዲጂታል ከረንሲውን ተቀላቅሏል ሚባልለት እና በስፋት በሚታወቀው ቢትኮይን ላይ ትኩረታችንን እናድርግ። ቢትኮይን ምንድነው ቢትኮይን ማለት በቀላል ቋንቋ፤ ዲጂታል ገንዘብ መገበያያ በማለት ማጠቃለል ይቻላል። ይህ መገበያያ በኪሳችን ተሸክመን እንደምንዞረው የብር ኖት ወይም ሳንቲም ሳይሆን ኦንላይን የሚቀመጥ ዲጂታል ገንዘብ ነው። በአሁኑ ወቅት በጣም ተፈላጊ የሆኑ የዲጂታል ዘርፍ ሥራዎች የትኞቹ ናቸው ሌላው የቢትኮይንና የተቀሩት የክሪይፕቶከረንሲዎች ልዩ ባህሪ በመንግሥታት እና በባንኮች አለመታተማቸው እንዲሁም ቁጥጥር አለመደረጉ ነው። ቢትኮይን የሚፈጠረው ማይኒንግ በሚባል ሂደት ነው። በመላው ዓለም በኔትወርክ በተሳሰሩ ኮምፒውተሮች ቁጥጥር ይደረግበታል። ቢትኮይንን የፈጠረው ግለሰብ ቡድን በዓለም ላይ ሚሊዮን ቢትኮይኖች ብቻ እንዲፈጠሩ ገደብ እንዳስቀመጠ ጡ ይታመናል። የብሎክቼይን መረጃዎች እንደሚያሳዩት እስካሁን ሚሊዮን ያህል ቢትኮይኖች ማይን ተደርገዋል። የቢትኮይን ዋጋ መዋዠቅ ከአንድ ዓመት በፊት እአአ የካቲት የአንድ ቢትኮይን ዋጋ የአሜሪካ ዶላር ነበር። ከአንድ ዓመት በኋላ ማለትም የካቲት የአንድ ቢትኮይን ዋጋ ወደ የአሜሪካ ዶላር ዝቅ ብሏል። ቢትኮይን ከተፈጠረ ዓመታት ተቆጠረዋል። ባለፉት አስር ዓመታትም የቢትኮይን ዋጋ እጅጉን እየጨመረ መጥቷል። የካቲት ዓ ም የአንድ ቢትኮይን ዋጋ ከ ሺህ ዶላር በላይ ደርሶ ነበር። ከሁለት ዓመት ከነበረው ዋጋ ጋር ሲነጻጸርም ከ እጥፍ በላይ ጨምሯል። አሁን ላይ ደግሞ ከአንድ ዓመት በፊት ከነበረው ዋጋ ጋር ሲነጻጸር ወደ እጥፍ በሚጠጋ ዋጋ ቀንሷል። ከሁለት ዓመታት በፊት ዋጋ በፍጥነት ሲጨምር ለዋጋው መጨመር ምክንያቱ በትክክል ይህ ነው ማለት አልተቻለም። አንዳንድ የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎች ግን ኢንቨስተሮች እድሉን እንዳያልፋቸው ከሚገባው በላይ ፈሰስ እያደረጉበት ነው የሚል ምክንያት ያቀርባሉ። ሌሎች ደግሞ የቢትኮይን ተቀባይነት እየጨመረ በመምጣቱ ዋጋው እንደጨመረ ያስቀምጣሉ። በቢትኮይን ግብይት መፈጸም ይቻላል አዎ። ለሚያቀርቡት ምርት እና አገልግሎት ቢትኮይንን በክፍያ መልክ የሚቀበሉ በርካቶች ድርጅቶች አሉ። ማይክሮሶፍት፣ የፈጣን ምግብ አቅራቢዎቹ ኬኤፍሲ እና ሰብዌይ፣ የጉዞ ወኪሉ ኤክስፔዲያን ከመሳሰሉ ባለብዙ ሚሊዮን ገንዘብ ኩባንያዎችን አንስቶ እስከ ሆቴሎች እና ካፊቴሪያዎች ቢትኮይንን በክፍያ መልክ ይቀበላሉ። በቢትኮይን አማካኝነት ክፍያ ሲፈጸም የገዢውን ማንነት ይፋ አለማድረግ ያስችላል። ይህም በርካቶች በኢንተርኔት አማካኝነት ማንነታቸውን ሳይገልጡ አገልግሎቶችን እንዲያገኙ ስለሚያስችላቸው በቢትኮይን አማካኝነት የሚደረጉ የንግድ ልውውጦች ቁጥር እጅጉን ጨምሯል። ቢትኮይን እንደስጋት አሸረትስ በተባለ የፋይናንስ ተቆጣጣሪ ኩባንያ ውስጥ ባለሙያ የሆኑት ብራደሊይ ራይስ በቢትኮይን ላይ ምንም አይነት ቁጥጥር እንደማይደረግበት ያስታውሳሉ። ቢትኮይንን በመጠቀም የገዢው ማንነት ይፋ ሳይደረግ በየትኛውም ሰዓት እና በየትኛውም ስፍራ የቢትኮይን ዝውውር ማድረግ ይቻላል። የግዢው ማንነት ይፋ ሳይደረግ ግብይት መፈጸም ይቻላል። በዚህም ሕገ ወጥ ቡድኖች የጦር መሳሪያዎች እና እጾችን ሊገዙ እና ሊሽጡ ይቻላሉ፣ ሕገ ወጥ የገንዘብ ዝውውር እና አሸባሪዎችን ለመደገፍ ያስችላል በማለት ቢትኮይንን ጨምሮ ሌሎች ክሪይፕቶከረንሲዎች ላይ ያላቸውን ስጋት የሚያነሱ በርካቶች ናቸው። በሌላ በኩል በርካታ የፋይናንስ ባለሙያዎች ቢትኮይን ላይ ምንም አይነት ቁጥጥር አለመደረጉ ተፈላጊነቱን እንደጨመረው ያወሳሉ። በቢትኮይን የሃገራት ምልከታ እአአ ላይ ከበርካቶች ጋር የተዋወቀው ቢትኮይን፤ ሕጋዊ ነው ወይስ አይደለም በሚሉ ጥያቄዎች ታጅቦ ቆይቷል። ሕጋዊ ነው ወይስ አይደለም ለሚለው ጥያቄ ምላሽ የምናገኘው ግን የት የሚለው ሲካተትበት ብቻ ነው። አሜሪካ፣ ካናዳ፣ የአውሮፓ ህብረት እና አውስትራሊያን የመሳሰሉ የዓለማችን ግዙፍ ኢኮኖሚዎች ለቢትኮይን አዎንታዊ ምልከታ አላቸው። ከላይ በተጠቀሱት ስጋቶች ምክንያት ቬትናም፣ ቦሊቪያ፣ ኮሎምቢያ እና ኢኳዶር በቢትኮይን መገበያየትን ከከለከሉ ሃገራት መካከል ይገኙበታል። ቢትኮይን ዓመታት ቢያስቆጥርም አሁንም ቢሆን በርካታ የዓለማችን ሃገራት ክሪፕቶከረንሲዎችን በተመለከተ ግልጽ ሕግ የላቸውም። ክሪይፕቶከረንሲዎችን መቆጣጠር የማይቻል በመሆኑም ለመንግሥታት ፈተና ሆኖ ቆይቷል። ተያያዥ ርዕሶች
ኢትዮጵያ በዲፕሎማቶቿ ላይ ሽግሽግና ለውጥ ልታደርግ ነው
ኖቬምበር ስለ ማጋራት ተጨማሪ ያጋሩ ማጋሪያ ምረጥ ኢትዮጵያ በተለያዩ የዓለም ሃገራት ያሉ ግማሽ ያህል ዲፕሎማቶቿን ቀደም ሲል ከነበሩባቸው የዲፕሎማቲክ መቀመጫዎች ወደ ሌላ ቦታ እንደሚዘዋወሩና አዲስ ከሚሾሙ አምባሳደሮች መካከልም ምሁራንና ታዋቂ ግለሰቦች እንደሚካተቱ ተጠቆመ። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ አቶ መለስ አለም እንደተናገሩት ሚኒስትር መስሪያ ቤቱ በሃምሳ ዘጠኝ ኤምባሲ እና ቆንስላ ፅህፈት ቤቶች የሠራተኛ ድልድል አጠናቅቆ ተግባራዊ ማድረግ ጀምሯል። የአምባሳደሮች ሹመት በቅርቡ የሚጠበቅ ሲሆን፤ በመስሪያ ቤቱ ካገለገሉ ዲፕሎማቶች በተጨማሪ ምሁራንና ታዋቂ ግለሰቦችንም ያካተት እንዲሆን ይደረጋል በማለት ምደባው ዕውቀትን እና ሙያዊ ብቃትን ብቻ መሰረት ያደረገ ነው ብለዋል። ጥፍር መንቀል ሕጋዊ አይደለም ስንለው ብሔሩ ውስጥ ለመደበቅ ይሞክራል ጠ ሚ ዐብይ የአምባሳደሮቹ በጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚሰየሙ ሲሆን እነማን እንደሆኑና ቁጥራቸው ምን ያህል እንደሆነ ቃል አቀባዩ ከመጥቀስ ተቆጥበዋል። በዚህም መሰረት ኢትዮጵያ በየኤምባሲው እና የቆንስላ ፅህፈት ቤቱ ካሏት ዲፕሎማቶች ግማሽ ያህሉ ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ እንዲዛወሩ ይደረጋል ብለዋል ቃል አቀባዩ። ሠራተኞች አዲሱን ምደባቸውን እንዲያውቁ ተደርጓል፤ አዲስ መዋቅር ደግሞ ከባለፈው ሳምንት ጀምሮ ሥራ ላይ ውሏል ያሉት አቶ መለስ በዚሁ መዋቅር መሰረት አምስት ቋሚ ተጠሪዎች ሥራ ላይ መሰየማቸውን ገልፀዋል። የአሁኑ ድልድልና የባለፈው ሳምንት የመዋቅር ማሻሻያ መስሪያ ቤቱን ከወትሮው በተለየ ከፍ ያለ እርምጃ ነው ብለን እናስባለን ሲሉም አክለው ተናግረዋል። ለዘመነ ሉላዊነት ከሚጠብቅበት ኃላፊነት አንፃር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ራሱን መፈተሽ እንዳለበት መገንዘቡን ያስረዱት አቶ መለስ የሚገባውን ሠራተኛ ከተገቢው የሥራ ድርሻ ጋር የማገናኘት ዓላማን ያነገበ ሽግሽግ ማደረጉን ገልፀዋል።
የ ምን ልታዘዝ ድራማ ሰምና ወርቅ
ሜይ ማጋሪያ ምረጥ ኢትዮጵያ ውስጥ ማኅበራዊና ፖለቲካዊ ይዘት ያላቸው ድራማዎች በተለያየ ዘመን ታይተዋል፤ ባለጉዳይ ፣ ማን ገደላት ፣ ገመና ፣ ቤቶች እና ሌሎችም ትችት አዘል የቴሌቪዥን ድራማዎች ይጠቀሳሉ። የቅርብ ጊዜው ምን ልታዘዝ የነዚህን ድራማዎች ዝርዝር የተቀላቀለ ይመስላል። ከላይ የተጠቀሱት ድራማዎች ማኅበራዊ ህጸጽን አጉልተው ሲያሳዩ ምን ልታዘዝ በአንጻሩ ፖለቲካዊ ሽሙጥን በሚገባ ይጠቀማል። ድራማው በቴሌቪዥን መተላለፍ የጀመረው ኢትዮጵያ ውስጥ በተለያዩ ከተሞች ተቃውሞ በገነነበት፣ የፖለቲካው አካሄድ ሚናው ባልለየበት ወቅት ነበር። ድራማው በዚህ ወቅት በድፍረት ፖለቲካውን መሸንቆጡ ተወዳጅ አድርጎታል። የ ምን ልታዘዝ መቼት አንድ ካፌ ነው። የካፌው ባለቤት እትዬ ለምለም ቢሆኑም በበላይነት የሚመሩት አቶ አያልቅበት ናቸው። አቶ አያልቅበት፤ የካፌው አስተናጋጆች፤ ዕድል፣ የንጉሥና ደግሰውን ክልል ከፋፍለው እንዲሠሩ መድበዋቸዋል። በየወቅቱም ስብሰባ ይወዳሉ። ይህንን የካፌ ዓለም ከኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ ጋር የሚያነፃፅሩ ተመልካቾች አሉ። ነፃነት ተስፋዬና ታመነ በአመቻቸው ጊዜ ሁሉ ድራማውን ይከታተላሉ። ድራማው የአገሪቱን ነባራዊ ሁኔታ እየተከታተለ የሰላ ትችት እንደሚያቀርብ ይስማማሉ። ረጋ ያለው፣ ጢማሙ ባሬስታ ዳኜ፣ ጋዜጣ አዟሪው ሱዳን፣ የልጥ ፓርቲ ሊቀ መንበር፣ ጨርቦሌ፣ ደራሲው ዶኒስና ሦስቱ የባንክ ሠራተኞች የድራማው ገፀ ባህሪያት ናቸው። ሌሎች ቋሚና አልፎ ሂያጅ የካፌው ደንበኛ ገፀ ባህሪያትም አሉት። ታዲያ ታመነ በገፀ ባህሪያቱ ብሽቅ ይላል። ለምን ስንለው ይልፈሰፈሱብኛል ነው መልሱ። ካፌው ውስጥ በየሳምንቱ የሚነሱ ጉዳዮች ፖለቲካዊ ናቸው። በየወቅቱ አገሪቱ ውስጥ የሚካሄዱ ነገሮች በአቃቂር ተለብጠው፣ በሳቅ ተከሽነው ወደተመልካች ይደርሳሉ። ድራማው በፋና ቴሌቪዥን መቅረቡ ለአንዳንዶች ግርምት አጭሯል። ታመነ እንደሚለው፤ ማኅበረቡ ውስጥ ያለውን፣ የሚብላላውን ነገር ከማቅረብ ባለፈ ጠንካራ መልእክት የለውም። ነፃነትም በሀሳቡ ይስማማል። ሆኖም ገፀ ባህሪያቱ የገሀዱ ዓለም ወካይ መሆናቸውን ያምናል። ድራማው የብዙሀን መነጋገሪያ ርዕሰ ጉዳይ መሆኑ ታመነና ነፃነትን የሚስማማ ሌላው ጉዳይ ነው። የአዲስ አበባ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊና ለዓመታት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ቴአትር ያስተማሩት ረዳት ፕሮፌሰር ነብዩ ባዬ፤ የ ምን ልታዘዝ ፖለቲካዊ አቃቂር ለኢትዮጵያ የድራማና ቴአትር ዘርፍ አዲስ አይደለም ይላሉ። ኢትዮጵያ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሠራው ቴአትር ፖለቲካዊ ይዘት እንደነበረውም ያጣቅሳሉ። በጅሮንድ ተክለኃዋርያት ተክለማርያም የጻፉት ግንባር ቀደሙ ኢትዮጵያዊ ቴአትር የ አውሬዎች ኮመዲያ መሳለቂያ ከአንዴ በላይ ለመታየት እድል አለማግኘቱን በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የሚያስተምሩት አቶ ዘሪሁን ብርሃኑ ይናገራሉ። ምክንያቱ ደግሞ የወቅቱ ባለስልጣናት በጭብጡ በመቆጣታቸው ነው ይላሉ። ትችትን በቴአትር ማቅረብ ለኢትዮጵያውያን አዲስ እንዳልሆነ ሁለቱም ይስማማሉ። ኢትዮጵያ ውስጥ ፖለቲካዊ ትችትን በቅኔ ማቅረብ አዲስ አይደለም የሚሉት ረዳት ፕሮፌሰር ነብዩ፤ ሸፈንፈን አድርጎ ማቅረብ ሥነ ጽሁፋዊ ባህላችን ነው ሲሉ ያክላሉ። አቶ ዘሪሁንም ምን ልታዘዝ እውነት አለው፤ ውበትም እንዲሁ በማለት ሀሳባቸውን ያጠናክራሉ። ባለጥርሱ ምን ልታዘዝ በየሳምንቱ እሁድ ከሰዓት በኋላ የሚቀርበው የቴሌቪዥን ድራማ፤ ወቅታዊ ጉዳዮችን እግር በእግር ተከታትሎ ለመተቸት እድሉን አግኝቷል። በፋና ብሮድካስቲንግ የመዝናኛ ፕሮግራሞች ዋና አዘጋጅና የተባባሪ ፕሮግራሞች ክፍል ኃላፊ ዘካሪያስ ብርሃኑ፤ የ ምን ልታዘዝ ፕሮፖዛል ወደቢሯቸው ሲሄድ አላማው ፖለቲካዊ ጉዳዮችን መተቸት እንደነበር ያስታውሳሉ። የፋና ብሮድካስቲንግ ባለሙያዎች ከደራሲዎቹ ጋር በመወያየት አሁን ያለውን ቅርፅ እንዲይዝ ማድረጋቸውንም ያስታውሳሉ። አውዳዊነትንና አሁናዊነትን አጣምሮ ፖለቲካዊና ማኅበራዊ ትችቱን ለማቅረብ እድል ያገኘው ምን ልታዘዝ ፤ ተወዳጅነት ካተረፈባቸው ምክንያቶች አንዱ ብዙሀኑ በሚመለከቱት ቴሌቪዥን መተላለፉ መሆኑን ረዳት ፕሮፌሰር ነብዩ ይናገራሉ። አቶ ዘሪሁን በበኩላቸው፤ አይነኬ ናቸው የምንላቸውን ጉዳዮች የደፈረ ነው ይላሉ። ባለፉት እና ዓመታት ፖለቲካውን ደፍረው በጥበብ ሥራቸው የነኩ ባለሙያዎች እየተሳደዱ፣ ጫና ውስጥ የመውደቅ እድላቸው ሰፊ ነበር በማለት የበጅሮንድን ተውኔት ይጠቅሳሉ። በአሁን ሰዓት ቴሌቪዥን ከፍተኛ ቁጥር ባላቸው ሰዎች ስለሚታይ ምን ልታዘዝ በአገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የመታየት እድል አግኝቷል የሚሉት ረዳት ፕሮፌሰር ነብዩ፤ ለመወደዱ እንደምክንያት ያቀረቡት ሌላ አስረጅ የደራሲያኑን ችሎታ ነው። የሰላ ትችት የሚቀርብበትን መንገድ በደንብ አውቀውታል የሚሉት ረዳት ፕሮፌሰሩ፤ ይህንን ገፀ ባህሪቱን በማንሳት ያስረዳሉ። ገፀ ባህሪያቱ ቋሚ ሆነው፣ ባህሪያቸውም ታውቆ ሁሌም አዳዲስ ነገሮችን ያቀርባሉ። አቶ አያልቅበት፣ ጨርቦሌ፣ ባሬስታው ዳኜ፣ ጋዜጣ አዟሪው ሱዳን በባህሪያቸው ይታወቃሉ። በባህሪያቸውና በድርጊታቸውም ያስቁናል። አቶ ዘሪሁን እንደሚናገሩት፤ ተመልካች በገፀ ባህሪያቱ ድርጊትና ንግግር ከመሳቅ ባሻገር፤ ንግግራቸውን ሳይዘነጋ ለቀናትና ለሳምንታትም ፈገግ ይላል። የ ምን ልታዘዝ ጉልበት የሚመነጨው በማሳቁ ወይንም በመተቸቱ ብቻ ሳይሆን፤ በየሳምንቱ የሚታወሱ ቃለ ተውኔቶች እንዲሁም ክስተቶች በማቀበሉ መሆኑን ሁለቱ ባለሙያዎች ይስማማሉ። በገፀ ባህሪያቱ ስም አወጣጥ፤ ልጥ ልማታዊ ጥምረት እና ጨርቦሌ ከጨርቆስ እስከ ቦሌ ውስጥም እንዲህ አይነት ነገር ይስተዋላል ሲሉም ያክላሉ። የታሪክ መማሪያ መጻሕፍት ለምን ይከለሳሉ ጉልበቱ ሳቅ መፍጠር ሳይሆን ትችት መሰንዘር ነው የሚሉት ረዳት ፕሮፌሰር ነብዩ፤ ሰዎች ሲስቁ ነገ ያንን ድርጊት ላለመደገም፣ መሳቂያ መሳለቂያ ላለመሆንም ትምህርት እየወሰዱ መሆኑን ይገልጻሉ። ምን ልታዘዝ መጀመሪያ አካባቢ ፖለቲካውን ብቻ ሳይሆን ማኅበራዊ ጉዳዮችንም ይዳስስ እንደነበር አቶ ዘሪሁን ያስታውሳሉ። የፖለቲካው ሁኔታ ሲለወጥ ግን የድራማው ሂስም ጠንከር ማለቱን ይጠቅሳሉ። ጸሀፊዎቹ ካለው የፖለቲካ እውነታ መውጣት አይችሉም ሲሉም ያስረዳሉ። አስቂኝ ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማ ሲትኮም ማኅበራዊ ጉዳይ የመሄስና ወቅታዊ ጉዳይ እያዋዛ የመተቸት ባህሪ አለው። ምን ልታዘዝ ይህን ማሳካት መቻሉን ይገልጻሉ። የደራሲያኑ አቋም መታየትና መከበር እንዳለበት መሥራት የምንፈልገው ፖለቲካዊ ሳታየር ነው ካሉ አቋማቸው ሊከበር ይገባል ሲሉም ያስረዳሉ። የፋና ብሮድካስቲንግ ባልደረባ አቶ ዘካሪያስም፤ የአገሪቱ ፖለቲካ ሲከር ፖለቲካውን አምርረው መተቸታቸው ተጠባቂ ነገር ነው ይላሉ። ጥበብ እንደፈቺው ነው ለአቶ ዘሪሁን፤ በድራማው ውስጥ በአልፎ ሂያጅም ሆነ በዋናነት የተሳሉ ገፀ ባህሪያት፤ እኛን መስለው እኛን አክለው የተሳሉ ሰዎች ናቸው። ለረዳት ፕሮፌሰር ነቢዩ ግን ምን ልታዘዝ ኢትዮጵያዊ ብቻ አይደለም። ለኢትዮጵያውያን የቀረበ ዓለም ቢፈጥሩም፤ የሚቃኙት ግን በአፍሪካና በተቀረው ዓለም ላይ የሚካሄዱ አበይት ክስተቶችን ነው ይላሉ። ገፀ ባህሪያቱ ሁሌም ከገሀዱ ዓለም ጋር በአቻነት የቆሙ ናቸው በሚለው ረዳት ፕሮፌሰሩም ሆነ መምህሩ አይስማሙም። ጋዜጣ አዟሪው ዛሬ እከሌ የሚባለውን ጋዜጠኛ ቢመስል፣ ነገ ደግሞ ሌላ ጋዜጠኛ ይመስላል፣ በሚቀጥለው ሳምንት ደግሞ ሌላ ሰው ይወክላል። ተቃዋሚ ፓርቲውንም ሆነ አክቲቪስቱን የሚመስሉ ገፀ ባህሪያት ውክልናም ይለዋወጣል። የተፎካካሪ ፓርቲዎችንና የአክቲቪስቶችን ፅንሰ ሀሳብ ወክለው የተሳሉ እንጂ የአንድ ሰው ቅጂ ናቸው ብዬ አላስብም ይላሉ ረዳት ፕሮፌሰር ነብዩ። አቶ ዘሪሁን በበኩላቸው፤ ተመልካች የራሱን ትርጉም የመስጠት እድል እንዳለው መዘንጋት እንደሌለበት ያስታውሳሉ። በጎ ምላሽ እንደሚሰጠው ሁሉ ያልተገባ ትርጉም ተሰጥቶት ልንሰማ እንደምንችልም ያነሳሉ። በድራማው ላይ የሚስተናገዱ አካላት የአንድ ክልል ወይም ክፍለ ከተማ ወካይ ናቸው ብሎ አስተያየት መስጠት አይቻልም ይላሉ ረዳት ፕሮፌሰር ነብዩ። የተለያዩ ተመልካቾች ቅሬታቸውንም ሆነ ሙገሳቸውን ወደቢሯቸው መውሰዳቸውን የሚያስታውሱት አቶ ዘካሪያስ፤ እንደተመልካች እከሌ እከሌን ይመስላል ማለት ከባድ ነው ይላሉ። ከቀረቡ ጥያቄዎች አንዱ ድራማው ከፋና ኤዲቶሪያል ፖሊሲ ጋር ይጣረሳል የሚለው ሲሆን፤ አቶ ዘካርያስ ከፖሊሲያቸው ጋር እንደማይጋጭ ይናገራሉ። በ ምን ልታዘዝ ውስጥ ያሉ ገፀ ባህሪያት አንዳቸው ከሌላቸው የተለዩ ተደርገው ስለተቀረጹ የሚያፈልቋቸው ሀሳቦች የተለያዩ ናቸው። አቶ አያልቅበት ከጨርቦሌ፣ ደግሰው ከዕድል የተለየ ሀሳብ ያላቸው ገፀ ባህሪያት መሆናቸው ጥንካሬ ሰጥቷቸዋል ይላሉ ረዳት ፕሮፌሰሩ። ይህ ልዩነት ገፀ ባህሪያቱ በቀላሉ በተመልካች አንዲለዩ ብቻ ሳይሆን፤ ግጭት ለመፍጠርና የድራማውን ታሪክ ለማንቀሳቀስ የበኩሉን አስተዋፅኦ አበርክቷል። የገፀ ባህሪያቱ ሥነ ልቦና፣ ሞራልና ማኅበራዊ ሁኔታ ቁልጭ ብሎ የሚታይ በመሆኑ በተመልካች ዘንድ ገፀ ባህሪያቱን ከእውኑ ዓለም ሰዎች ጋር በማመሳከር ጨርቦሌ እንትና ነው፣ ልጥ ደግሞ እንትና ነው ይባላል። ይህ የሆነው ገፀ ባህሪያቱ በደንብ ተደርገው ስለተሳሉ ነው ይላሉ። በ ምን ልታዘዝ ድራማ የሚስቅ ተመልካች ምን ያተርፋል ድራማው ለማስተማር የተዘጋጀ አይደለም የሚሉት አቶ ዘካርያስ፤ ከማዝናናት ባሻገር የአገሪቱ ፓለቲካ፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ሕይወት ላይ የበኩሉን አስተዋፅኦ የመተው ግብ አለው ይላሉ። ረዳት ፕሮፌሰር ነብዩ በበኩላቸው፤ ሥነ ጥበብ ሕሊናን በመሸንቆጥ፤ ሰልፍ ላይ ወጥቶ ድንጋይ ከመወርወር፣ መስታወት ከመስበርና ሕይወት ከሚጠፋ፣ ነገሮች እንዲስተካከሉ እድል ይሰጣል ይላሉ። ሥነ ጥበብ የመማር እድል ይሰጣል የሚሉት ባለሙያዎቹ፤ ገፀ ባህሪያቱ ባደረጉት ነገር ስንስቅ እግረ መንገዳችንን እየተማርን መሄድ አለብን ይላሉ። የ ምን ልታዘዝ የመተቸት ነፃነት ከየት መጣ ምን ልታዘዝ በአገሪቱ ውስጥ የሚካሄዱ ፖለቲካዊ እርምጃዎች ዜና በሆኑ ማግስት ለሳቅና ለስላቅ ያበቃቸዋል። ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ መነጋገሪያ የሆኑትን እንከኖች በጥበብ አሽቶና አዋዝቶ ያቀርባቸዋል። ይህ ነፃነቱን ከሌሎች ድራማዎች በተለየ ከወዴት አገኘው የሥነ ጥበብ ነፃነት ከመናገር ነፃነት ጋር የተያያዘ ነው የሚሉት ረዳት ፕሮፌሰር ነብዩ፤ ሕገ መንግሥቱ ሀሳብን በነጻነት መግለጽ ቢፈቀድም በተለያየ ጊዜ በተለያየ ምክንያት አንዳንዴ ስንጠቀምበት ሌላ ጊዜ ስንተወው ነበር ይላሉ። በአሁን ወቅት በነጻነቱ ተናዶ ጡንቻውን የሚያሳይ ስለሌለ በጥሩ ሁኔታ እየኮመኮምን ይላሉ። አቶ ዘካሪያስ በበኩላቸው፤ ከድራማው ነፃነት የተነሳ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ድራማው ሊቋረጥ ነው እና ደጋፊ አካላት ውላቸውን አቋረጡ ተብሎ ሲወራ መስማታቸውን በመግለጽ፤ ፋና ውስጥ ሁሌም የምንቆምለት ነገር የመናገር ነፃነት ነው። ድራማዎቻችንም የዚህ ማሳያ ናቸው ይላሉ። በጣቢያቸው ስለሚተላለፉ ድራማዎች ሁልጊዜ እንደሚወያዩ ገልጸው፤ ከሕዝብ የሚላኩ አስተያየቶች ላይ ከ ምን ልታዘዝ ደራሲዎችና ፕሮዲውሰሮች ጋር እንደሚወያዩ ያስረዳሉ። የድራማው ቡድን አባላትም እርስ በእርስ እንደሚወያዩ ያክላሉ። ምን ይሻሻል ረዳት ፕሮፌሰር ነብዩ፤ ምን ልታዘዝ ማኅበራዊ ሂሱንም፣ ፖለቲካውንም ኢኮኖሚውንም የሚሄስ ነው ይላሉ። ወደአንድ ኢኮኖሚያዊ ወይም ማኅበራዊ ጎን ያደላ ባለመሆኑ ደራሲያኑም ሆነ አዘጋጆቹም በእውቀት እንደሚሠሩት ያሳያል በማለት የፈጠራ ችሎታቸውን ያደንቃሉ። የደራሲዎቹን እና የፕሮዲውሰሮቹ ልምድ ለዚህ ድራማ ተወዳጅነት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማድረጉን አቶ ዘካሪያስም ይጠቅሳሉ። በሌላ በኩል ረዳት ፕሮፌሰር ነብዩ፤ የሀሳብ መደጋገም መመልከታቸውን በማንሳት፤ በአገሪቱ የሚታዩ ፓለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ ሕፀፆችን እንደሚተቹ ሁሉ በግለሰቦች ዙሪያም ቢያተኩሩ መልካም ነው ይላሉ። ገፀ ባህሪያቱ በፍቅር፣ በገንዘብ፣ በሥነ ልቦና፣ በአስተዳደግ ምክንያት ችግር ሊገጥማቸው እንዲሁም እርስ በእርሳቸው በሚኖራቸው ግንኙነት ምክንያት እንቅፋት ሊገጥማቸው ይችላል። እንደዚህ ያሉ በግለሰብ ደረጃ የሚያጋጥሙ ችግሮችን በማምጣት ለማሳየት ቢሞክሩ ሲሉም አስተያየት ይሰነዝራሉ። አቶ ዘሪሁንም ፖለቲካዊ ጉዳዮች መብዛታቸውን ይጠቅሳሉ። ያላየናቸውን ሌሎች ማኅበራዊ ጉዳዮችን ማሳየት እና ሀሳብ ማፈራረቅም መልካም ነው ሲሉ ይመክራሉ። ለአቶ ዘካሪያስ ግን ፖለቲካዊ ሂስ የ ምን ልታዘዝ ካስማ ነው። እናም ፖለቲካው እስካለ፣ የደራሲያኑ ብዕር እስካልነጠፈ ድረስ ይቀጥላል ይላሉ። ተያያዥ ርዕሶች
ጓደኛ ለማፍራት ማወቅ ያለብን ጠቃሚ ነጥቦች
ኦክተውበር ህጻናት ሁሌም በውስጣቸው ጓደኛ የመፈለግ ስሜት አለ። በተፈጥሯቸው ብቸኝነትን ማስተናገድ አይችሉም። ታድያ ትልቅ ሰዎች ስንሆን ለምን እንቀየራለን አዋቂ መሆንስ ምን ማለት ነው ጓደኛ ማፍራትን ቀላል የሚያደርግ አንድ አረፍተ ነገር አለ። ጓደኛዬ ትሆኛለሽ ወይም ትሆናለህ ማለት ነው። አዋቂ ሰዎች ብዙ ጊዜ ስለ ብቸኝነት ሲያወሩ ይሰማሉ። በእንግሊዝ ብቻ ሚሊዮን ሰዎች እጅግ የከፋ ብቸኝነት ያሰቃያቸዋል። ነገር ግን ይህን ችግር በቀላሉ መፍታት ይቻላል። ጓደኛ ለማፍራት የሚጠቅሙ ነጥቦች አነሆ። የመንገድ አቅጣጫ እየጠፋብዎ ተቸግረዋል ጠቃሚ ነጥቦች እነሆ አንድ ቡድን ይቀላቀሉ አንድ የሚወዱት ነገር ያሰባሰባቸው ሰዎችን ፈልገው ይቀላቀሉ። እነዚህን ሰዎች ያገናኛቸው ነገር እርስዎንም ወደ ቡድኑ የማይስብበት ምንም ምክንያት የለም። ብዙ ጊዜ ሰዎች ምን እንደሚያስደስታቸው ስለማያውቁ እንደዚህ አይነት ቡድኖችን ሲቀላቀሉ የሚወዱትንና የሚጠሉትን ነገር ለመለየት ይረዳዎታል። አዲስ ነገርን ለመሞከር ፈፅሞ አይፍሩ። ቴክዋንዶ ወይንም የስዕል ትምህርት ቢጀምሩስ ሊወዱት ይችላሉ፤ በዚያውም ጓደኞች ያፈሩበታል። ካልወደዱት ግን ሌላ ነገር ይሞክሩ። በመጨረሻ የሚወዱትን ነገር ከጥሩ ጓደኞች ጋር ያገኙታል። በበጎ ፈቃድ ሥራ ላይ ይሳተፉ በሚወዱት ጉዳይ ላይ ወይንም ሰዎችን መርዳት በሚፈልጉበት ዘርፍ በበጎ ፈቃድ ማገልገል ከሚያስቡት በላይ እርካታ ከመስጠቱ በላይ ብዙ ሰዎችን ለመተዋወቅ እጅግ አመቺው ቦታ ነው። ብዙ ጊዜ በጎ ፈቃደኞች አዛኝና ቸር ናቸው። ይሄ ደግሞ ጥሩ የጓደኛ መለኪያ ነው። ስልክ ቁጥር ይለዋወጡ ጓደኛዬ ቢኖራት ወይም ቢኖረው ብለው የሚያስቡትን ባህሪ በአንድ ሰው ላይ ሲያገኙ ፈጥነው ሌላ ጊዜ መገናኘት የሚችሉበትን መንገድ ያመቻቹ። ይህንን ለማድረግ የመጀመሪያው መንገድ ደግሞ ስልክ ቁጥር መለዋወጥ ነው። ምናልባት አንድን ሰው ድንገት ስልክ ቁጥር መጠየቅ ሊያስፈራ ይችላል፤ ነገር ግን ጓደኝነቱ ከይሉኝታው ሊበልጥ የሚችልበት አጋጣሚ ከፍተኛ ነው። ደግመን መገናኘት እንችላለን ስላገኘሁሽ ደስ ብሎኛል ወይም ስላገኘሁህ ደስ ብሎኛልና ብንደግመውስ የሚሉት ጥያቄዎች ለመጠየቅ አይፍሩ። እሺ ይበሉ አዲስ የተዋወቁት ጓደኛ እራት እንብላ፣ ፊልም እንመልከት አልያም አንዳንድ ሰዎች ላስተዋውቅዎ ሲልዎት ሁሌም ቢሆን እሺ ይበሉ። ከማያውቁት ሰው ጋር ረጅም ጊዜ ማሳለፍ ሊከብድ ይችላል፤ ነገር ግን ደፈር ብለው የመጀመሪያውን እርምጃ ካልተራመዱ የሚወዱትና የሚያምኑት ጓደኛ ማግኘት ሊከብድዎ ይችላል። በመጀሪያው ግብዣ ቢቀሩ እንኳን ለቀጣዩ እንደሚሄዱ ቃል ይግቡ። መገፋትን አይፍሩ መርሳት የሌለብዎት ነገር ጓደኛዎ እንዲሆኑ የፈለጓቸው ሰዎች ሁሉ ጓደኛዎት ላይሆኑ እንደሚችሉ ነው። ይሄ ግን ብዙ ሊያሳስብዎ አይገባም፤ ምክንያቱም የተዋወቁት ሰው ሁሉ ጓደኛዎ የሚሆን ቢሆን ኖሮ ይህንን ጽሁፍ አያነቡም ነበር። ደፈር ብለው አዲስ ጓደኛ ለማፍራት የቻሉትን ነገር ሁሉ ያድርጉ። እንገናኝ በተባለው ቦታና ሰዓት ሴትዮዋ ወይም ሰውዬው ባይገኙ ምንም ማለት አይደለም። የሥራ ባልደረባዎችን ጓደኛ ያድርጓቸው አብዛኛዎቻችን ከቤተሰቦቻችን ጋር ከምናሳልፈው ጊዜ በላይ ከሥራ ባልደረቦቻችን ጋር ብዙ ጊዜ ስለምናሳልፍ፤ የቅርብ ጓደኛ ብናደርጋቸው ከጉዳቱ ጥቅሙ ያመዝናል። ምናልባት ከባልደረቦች ጋር ከሥራ ያለፈ ነገር ማውራት ላይለመድ ይችላል፤ ነገር ግን ደፍረው ግንኙነቱን ወደ ጓደኝነት ለመቀየር ከሞከሩ ጥሩ ጓደኞች ሊያገኙ ይችላሉ። ከሥራ ባልደረባዎ ጋር ወጣ ብለው ከሥራ ጋር ጋር ያልተገናኙ ነገሮችን ያድርጉ። ስለሰው ለማወቅ ይሞክሩ ስለራስዎ ለማውራት የሚፈሩ ከሆነ አልያም የሚያወሩት ነገር የሚጠፋብዎ ከሆነ ሰዎች ስለራሳቸው እንዲነግርዎ ይጠይቁ። ብዙ ሰዎች ስለራሳቸው ማውራት ላይከብዳቸው ይችላል። በዚያው ደግሞ ሌሎች ጥያቄዎችም አብረው ስለሚመጡ ይህኛው መንገድ ይበልጥ ውጤታማ ነው። የሚያስደስታቸውን ነገር ያድርጉ ትንሽ ሊመስሉ የሚችሉ እንደ ልደት ያሉ አጋጣሚዎችን በአግባቡ መጠቀም ያስፈልጋል። ሰዎች ልደታቸውን አስታውሰን ስጦታ ስንሰጣቸውና መልካም ምኞታችንን ስንገልጽላቸው በጣም ደስተኛ ይሆናሉ። አንድ ሰው ጥሩ በማይባል ሁኔታ ውስጥ ካለም ለመርዳት መሞከርና ቅርበትን ማሳየት ጠቃሚ ነው። ለብዙ ነገሮች ክፍት ይሁኑ እርስዎ ለጓደኛ ብለው የሚያስቧቸው ሰዎች የሚፈልጉትን ሁሉ መመዘኛዎች ላያሟሉ ይችላሉ። ስለዚህ ካሉት የተሻለውን ጓደኛ መርጦ ግንኙነት መመስረት የተሻለ ይሆናል። እርስዎ ውሻ ቢወዱ ምናልባት ጓደኛዎች ድመት ልትወድ ወይም ሊወድ ይችላል። ይህ ቀላል ምሳሌ ነው። ልዩነቱ በብዙ ነገሮች ሊገለጽ ይችላል። አይቸኩሉ በአጭር ጊዜ ውስጥ ውድ ጓደኛ ማግኘት የማይታሰብ ነው። በአንድ ጊዜ አንድ ጓደኛ ብቻ ሊኖርዎት አይገባም። ዋናው ነጥብ መሆን ያለበት በተቻለ መጠን ብዙ ጓደኞች እንዲኖርዎት እድርገው ከጊዜ ብዛት የቅርብ የሚሉት ጓደኛ መምረጡ ላይ ነው። ተያያዥ ርዕሶች
አብዲ ሞሃመድ ኡመር በቁጥጥር ስር ዋሉ
ኦገስት የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንት የነበሩት አብዲ ሞሃመድ ኡመር በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለጸ። አብዲ ሞሃመድ ኡመር ትናንት ከክልሉ ፕሬዚዳንትነታቸው መነሳታቸው ቢገለጽም የኢትዮጵያ ሶማሌ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ኢሶዴፓ መሪ ሆነው ይቀጥላሉ ተብሎ ነበር። የቀድሞው የክልሉ ፕሬዝዳንት በመከላከያ ሠራዊት አባላት በቁጥጥር ሥር እንዲውሉ ከተደረጉ በኋላ ጅግጅጋ ከሚገኘው ቤተ መንግሥት እንደተወሰዱ ምንጮች ለቢቢሲ ሶማልኛ ገልጸዋል። ከቅዳሜ አንስቶ በጂግጂጋ እና በሌሎች የክልሉ ከተሞች የተከሰተውን ሁከት ተከትሎ የሃገር መከላከያ ሠራዊት እና የፌደራል ፖሊስ ወደ ክልሉ ገብቶ ሰላም እንዲያስከብር መታዘዙ የታወሳል። አህመድ አብዲ ሞሃመድ የቀድሞውን ፕሬዝዳንት በመተካት መሾማቸውም ይታወሳል። መከላከያ ሠራዊት እና የፌደራል ፖሊስ ሶማሌ ክልል ገብቶ ሰላም እንዲያስከብር ታዘዘ አዲሱ የክልሉ ፕሬዚዳንት አህመድ አብዲ ሞሃመድ የሶማሌ ክልል ፋይናንስ እና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ሃላፊ በመሆን አገልግለዋል። አህመድ አብዲ ሞሃመድ ከቢቢሲ ሶማልኛ ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ የቀድሞው ፕሬዚዳንት ስልጣናቸውን አስረክበው በሰላም የስልጣን ሽግግር መካሄዱን ተናግረው ነበር። አህመድ አብዲ ሞሃመድ አብዲ ሞሃመድ ሥልጣን መልቀቃቸውን ተከትሎ የክልሉ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አዲስ መሪ መርጧል። የቀድሞው ፕሬዚዳንት ሰላማዊ በሆነ ሁኔታ ጂግጂጋ በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ውስጥ እየኖሩ ይገኛሉ ሲሉም ትናንት ተናግረው ነበር።
በሶማሌ ክልል የጄል ኦጋዴን እስር ቤት ኃላፊ ተይዞ ለኢትዮጵያ ተሰጠ
ግንቦት ይህንን ለማጋራት በ ዋትስአፕ ሐሰን ኢስማኤል ኢብራሂም ሐሰን ዴሬ ኢትዮጵያ ውስጥ በሚገኘው የሶማሌ ክልል ውስጥ በርካታ አሰቃቂ ድርጊቶች ሲፈጸምበት እንደቆየ የሚነገርለት የጄል ኦጋዴን እስር ቤት ኃላፊ የነበረው ግለሰብ በቁጥጥር ሥር ዋለ። አብዲ ሞሃመድ ኡመር በቁጥጥር ስር ዋሉ የቀድሞው የእስር ቤቱ ኃላፊ ሐሰን ኢስማኤል ኢብራሂም በቅጽል ስሙ ሐሰን ዴሬ ሶማሊያ ውስጥ በቁጥጥር ሥር ውሎ ለኢትዮጵያ ተላልፎ በመሰጠቱ ወደ ጅግጅጋ ተወስዷል። ግለሰቡ ክስ ወደ ተመሰረተበት አዲስ አበባ ሊወሰድ እንደሚችልም ተነግሯል። ምንጮች ለቢቢሲ እንደተናገሩት ግለሰቡ የተያዘው ሶማሊያን ከኢትዮጵያ ጋር በምታዋስነው ጎልደጎብ ተብላ በምትጠራው የድንበር ከተማ ውስጥ ነዋሪዎች ለጸጥታ ኃይሎች በሰጡት ጥቆማ አማካይነት ነው። ግለሰቡ በሶማሌ ክልል ውስጥ በሚገኙ የተለያዩ እስር ቤቶች ውስጥ በተለይ ደግሞ ጄል ኦጋዴን ተብሎ በሚታወቀው እስር ቤት ውስጥ ተፈጽመዋል በሚባሉ ሰቆቃዎችና የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ውስጥ ዋነኛ ሚና አለው ተብሎ ሲፈለግ ቆይቷል። አቶ ገዱም ሆነ ደመቀ እኛም ብንፈተሽ ግድፈት አለብን ማለታቸውን አስታውሳለሁ የአቶ ታደሰ ጥንቅሹ ባለቤት ሐሰን ኢስማኤል ሐሰን ዴሬ የቀድሞውን የክልሉን ፕሬዝዳንት አብዲ መሐመድ ኦማርን ጨምሮ በሶማሌ ክልል ውስጥ በተፈጸሙ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ምክንያት ክስ ከተመሰረተባቸው ያህል ተጠርጣሪዎች መካከል አንዱ እንደሆነም ተነግሯል። ግለሰቡ በቀድሞው የሶማሌ ክልል መስተዳደር ውስጥ በከፍተኛ የደኅነትና የጸጥታ ኃላፊነቶች ላይ በተለያዩ ጊዜያት የሰራ ሲሆን ከእነዚህም መካከል የሶማሌ ክልል የጸጥታ ዘርፍ ኃላፊ፣ የማረሚያ ቤቶች ኃላፊ፣ የጄል ኦጋዴን ኃላፊ እና በክልሉ ልዩ ፖሊስ ውስጥም በኮሎኔልነት አገልግሏል። በሶማሌ ክልል የሚገኙ እስር ቤቶች በተለይ ደግሞ ጄል ኦጋዴን ውስጥ ተይዘው የነበሩ እስረኞች ላይ አሰቃቂ ድርጊቶች ይፈጸሙባቸው እንደነበር የፌደራል መንግሥቱና የክልሉ መንግሥት ይፋ ማድረጋቸው ይታወሳል። በእስር ቤቱ ይገኙ በነበሩ በመቶች በሚቆጠሩ እስረኞች ላይ ይፈጸሙ ከነበሩት ድርጊቶች መካከል ከመሬት በታች ባሉ ጨለማ ጉድጓድ ውስጥ ማስቀመጥ፣ የተለያዩ ዓይነት ሰቆቃዎች፣ ከአደገኛ የዱር እንስሳት ጋር እስረኞችን ማስቀመጥ፣ አስገድዶ መድፈርና የመሳሰሉ ድርጊቶች እንደነበሩ ተገልጿል። ከዚህ ዜና በተጨማሪ
በ ሰዎች ግድያ የ ሄጎ ቡድን አባላት እጅ አለበት፡ ፖሊስ
አቶ አብዲ ጨምረውም ምቹ ባልሆነ እስር ቤት መታሰራቸውን፣ የአዕምሮ ህመምተኛ የሆነ ታራሚ የታሰሩበትን ክፍል በር ገንጥሎ በመግባት ሁለት ቀን ጉዳት ሊያደርስባቸው እንደሞከረና ይህም በደህንነቴ ላይ ስጋት ፈጥሮብኛል በማለት ለፍርድ ቤቱ እንዳስረዱ ኢቲቪ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎትን ጠቅሶ ዘግቧል። ፖሊስ በአቶ አብዲ መሐመድ የክስ መዝገብ ተጨማሪ መረጃ ለማሰባሰብ የ ቀናት የምርመራ ጊዜ እንዲሰጠው ፍርድ ቤቱን የጠየቀ ሲሆን፤ ፍርድ ቤቱም ፖሊስ የምርመራውን ውጤት ለጥቅምት ቀን ዓ ም ይዞ እንዲቀርብ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል። ይህንን ዜና ያጋሩ ስለማጋራት
ኢትዮጵያ ከዓለም ጥቂት አጫሾች ያሉባት አገር ናት
ሜይ አጭር የምስል መግለጫ አንድ ሚሊዮን የሚጠጉ ፈረንሳዊያን የትምባሆ ነገር በቃን ብለዋል ትምባሆ ማጤስ በማቆም ፈረንሳዊያንን የሚያህል አልተገኘም። በአንድ ዓመት ውስጥ ብቻ አንድ ሚሊዮን ዜጎች የትምባሆን ነገር በቃን ብለዋል። ይህም ከ እስከ ብቻ የሆነ ነው። በርካታ አገራት የትምባሆ ስርጭትን ለመግታት ፖሊሲያቸውን ከልሰዋል። ያም ሆኖ በዓለም ላይ የአጫሾች ቁጥር ሲጨምር እንጂ ሲቀንስ አይታይም። ዛሬ የዓለም ትምባሆ ያለማጤስ ቀን ከመሆኑ ጋር አስታከን የአጫሽ አገራትን ዝርዝር አቅርበናል። ኪሪባቲ ኪሪባቲ የምትባል የማዕከላዊ ፓሲፊክ ደሴት በአጫሾች ቁጥር በዓለም ቀዳሚዋ ናት። ከሕዝቧ ሁለት ሦስተኛ ወንዶች ትምባሆ የሚያጤስ ነው። ከሴቶች ደግሞ አንድ ሦስተኛ የሚሆኑት ደግሞ አጫሾች ናቸው። አጭር የምስል መግለጫ ኪሪባቲ ደሴት በትምባሆ ላይ የምትጥለው ግብር ትንሽ ነው በዚህች አገር ሕዝብ ይኖራል። በትምባሆ ላይ የተጣለው ግብር አነስተኛ ሲሆን ሕዝቡ በቀላሉ በየትም ቦታ ትምባሆን ማግኘት ይችላል። ሞንቴኔግሮ ምሥራቅ አውሮፓዊቷ አገር ሞንቴኔግሮ ከአውሮፓ በአጫሽ ቁጥር የሚያህላት የለም። በመቶ ሕዝቧ ሱሰኛ ሆኗል። የባልካኗ ሞንቴኔግሮ የሕዝብ ቁጥሯ የሚጠጋ ሲሆን ሲጋራዎች በየቀኑ በአዋቂዎች ይጨሳሉ። ምንም እንኳ በአደባባይና ሕዝብ በተሰበሰበባቸው ቦታዎች ማጤስ በአገሪቱ ሕግ የተከለከለ ቢሆንም ሕዝቦቿ ግን በቢሮዎች፣ በምግብ ቤቶች፣ ብሎም በሕዝብ መጓጓዣ ውስጥ እንደልብ ትምባሆን ይምጋሉ። አጭር የምስል መግለጫ በግሪክ የጠቅላላ ወንድ ሕዝቦቿ እኩሌታ ትምባሆ ያጨሳል ግሪክ ግሪክ ኛው ከፍተኛ የአጫሽ ቁጥር እድገት ያስመዘገበች አገር ናት። ከወንድ ዜጎቿ ግማሹ ትምባሆን ከአፋቸው አይነጥሉም። የሚገርመው በመቶ የሚሆኑ ግሪካዊያን ሴቶችም ቢሆን ማጤስን ማዘውተራቸው ነው። ምንም እንኳ ከ ጀምሮ በሕዝብ አደባባዮች ሲጃራ ማቡነን በሕግ የተከለከለ ቢሆንም ሕጉ ትዝ የሚለው አጫሽ ግን የለም። ብዙ ግሪካዊያን ዛሬም በየአደባባዩ ትምባሆን ያምቦለቡላሉ። ከግሪክ ቀጥሎ ኢስቲሞርና ራሺያ በርካታ አጫሾች ያሉባቸው አገራት ናቸው። አጭር የምስል መግለጫ በኢስቲሞር ፓኬት ሲጋራ ከአንድ ዶላር በታች ይሸጣል ራሺያ ራሺያ በዓለም አጫሾች ዝርዝር አምስተኛዋ አገር ናት። ከመቶ የሚሆኑ ለአቅመ ማጤስ የደረሱ ወንድ ዜጎቿ ትምባሆ አይለያቸውም። የሴቶች ድርሻ ከመቶ ነው። ሥራ ቦታና የሕዝብ መጓጓዣዎች ላይ ማጤስ ክልክል ቢሆንም የማያቋርጥ የሲጃራ ማስታወቂያዎች መበራከታቸው የአጫሾችን ቁጥር ሳያሳድገው አልቀረም። በአንዳንድ የራሺያ ሱቆች ፓኮ ሲጋራ ከአንድ ዶላር በታች ይገኛል። የራሺያ የትምባሆ ገበያ ቢሊዮን ዶላር እንደሚሆን ይገመታል። አጭር የምስል መግለጫ የራሺያ የትምባሆ ገበያ ከ ቢሊዮን ዶላር በላይ እንደሆነ ይገመታል ጥቂት አጫሾች የሚገኙባቸው አገራት እንደመታደል ሆኖ ከነዚህ አገራት ውስጥ ኢትዯጵያ አንዷ ሆናለች። ጋና፣ ናይጄሪያ፣ ጎረቤት ኤርትራና ፓናማም በዝርዝሩ ይገኙበታል። አጭር የምስል መግለጫ በበርካታ የአፍሪካ አገራት ሴቶች ትምባሆ ማጤሳቸው እንደ ነውር ይታያል ከአፍሪካዊያን ከመቶዎቹ አጫሾች ሲሆኑ የወንዶች ድርሻ እስከ ከመቶ ይደርሳል። የሴቶች ቁጥር ዝቅተኛ መሆኑ የኢኮኖሚ ጥገኛ ከመሆናቸው ጋር ይያያዛል ተብሏል። የሴቶች ሲጃራ ማጤስ እንደ ማኅበረሰብ ነውር መታየቱ የአፍሪካ ሴት አጫሾችን ቁጥር ሳይቀንሰው አልቀረም። አጭር የምስል መግለጫ ጫት መቃም ከፍ ያለ ጊዚያዊ መነቃቃትና ምርቃና ውስጥ ይከታል ከሲጃራ ይልቅ ጫት በአፍሪካ ቀንድ ተወዳጅ እየሆነ መምጣቱ የትምባሆ ወዳጆች ቁጥር በቃሚዎች ሳይተካ አልቀረም። የዓለም የጤና ድርጅት እንደሚለው በዓለም ሚሊዮን የሚሆኑ ሕዝቦች ጫት ይቅማሉ። ሴት አጫሾች ዴንማርክ በሴት አጫሾች ቁጥር የሚስተካከላት የለም። በዚያች አገር ትምባሆን በመማግ ከወንዶች ይልቅ የሴቶች ቁጥር ይበልጣሉ። ከመቶ የሚሆኑ ዴንማርካዊያን ሴቶች ትምባሆን የሙጥኝ ብለዋል። አጭር የምስል መግለጫ በዴንማርክ ከወንድ አጫሾች ቁጥር የሴቶቹ ላቅ ያለ ነው በየዓመቱ ትምባሆ ሚሊዮን የዓለም ዜጎችን ይገድላል። ተያያዥ ርዕሶች
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሴት ሰራተኞች ብቻ አገልግሎት የሚሰጥ ቅርንጫፍ ከፈተ
ኤፕረል የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአዲስ አበባ፣ አትላስ አካባቢ በሴት ሠራተኞች ብቻ አገልግሎት የሚሰጥ ቅርንጫፍ መክፈቱን አስታወቀ። ቅርንጫፉ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ኛው ቅርንጫፍ ሲሆን ከሥራ አስኪያጅ ጀምሮ በባንኩ አገልግሎት የሚሰጡት ሁሉም ሠራተኞቹ ሴቶች ብቻ መሆናቸው ተገልጿል። ሴቶች የተቆጣጠሩት የስፔን ካቢኔ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ በልሁ ታከለ ሴቶች በአንድ አገር ሁለንተናዊ እድገት ከፍተኛ ድርሻ ቢኖራቸውም የሚገባቸውን ቦታ ባለማግኘታቸው የሴቶችን ተሳትፎ ለማጎልበትና ለማበረታታት ሲባል ቅርንጫፉ እንደተከፈተ ለቢቢሲ ገልፀዋል። ሴቶች ከወንዶች በተሻለ ደንበኞችን በጥሩ እንክብካቤ በማስተናገድ ከደንበኞቻችን ጋር ያለንን ግንኙነት ሲያጠናክሩ በተግባር አይተናል የሚሉት አቶ በልሁ በሴቶች ብቻ የተቀላጠፈና የተደራጀ አገልግሎት መስጠት እንደሚቻል ማሳየትም ሌላኛው ዓላማው ነው ብለዋል። ቅርንጫፉ ከሌሎች ባንኮች የተለየ አገልግሎት ባይሰጥም የሴቶችን የሥራ ፈጠራና የፋይናንስ አቅም ለማጠናከር የሴቶች የብድር አገልግሎት ለመጀመር ቅድመ ዝግጅት እያደረጉ መሆናቸውን ዳይሬክተሩ ተናግረዋል። ሠራተኞቹ ከተለያዩ የባንኩ ቅርንጫፎች የተውጣጡ እንደሆነም ታውቋል። ቅርንጫፉ በኢንዱስትሪው ውስጥ ትልቅ ድርሻ ባላቸው አንጋፋ የባንክ ባለሙያ አቶ ለይኩን ብርሃኑ ተሰይሟል። ተያያዥ ርዕሶች
ለአፍሪካ ዋንጫ የሚፋለሙት ኃያላን እንስሳት
ጁን ስለ ማጋራት ተጨማሪ ያጋሩ ማጋሪያ ምረጥ ለሚቀጥሉት ሦስት ሳምንታት ግብጽ ብምታስተናግደው የአፍሪካ ዋንጫ ላይ የ ሃገራት ቡድኖች ይሳተፋሉ። ቡድኖቹ ከነገቡት የሃገር ባንዲራና ስም ባሻገር መጠሪያ ቅጽል አላቸው። በአፍሪካ እግር ኳስ ውስጥ ቅጽል ስሞች ጉልህ ቦታ አላቸው። እነዚህ ስሞች ለቡድኖቹ ደጋፊዎች መለያ ከመሆን በተጨማሪ ተጫዋቾችን በማነቃቃት በኩልም ይጠቅማሉ። የብሔራዊ ቡድኖች ቅጽል ስም፣ በቀለማት ካሸበረቁ ደጋፊዎችና የከበሮ ድምፅ ጋር የአፍሪካ ዋንጫ መለያ ድምቀቶች ናቸው። ተምዘግዛጊዎቹ ንስሮች የናይጄሪያ ብሔራዊ ቡድን በሚለብሰው አረንጓዴ ማሊያ ተለይቶ የሚታወቅ ቢሆንም ንስሮቹ የሚለው ስያሜያቸው ግን የበለጠ መለያቸው ነው። ብድኑ ይህን ስያሜ የወሰደው ከሃገሪቱ ብሔራዊ መለያ ላይ ነው። ቱኒዚያ ከካርቴጅ ሥልጣኔ ጋር በነበራት ግንኙነት የተነሳ ቡድኗ የካርቴጅ ንስር የሚል መጠሪያን አግኝቷል። ብሔራዊ መለያቸውም ንስር ነበረ። እዚህ ጋር የማሊ ንስሮችም ሊዘነጉ አይገባም። በተጨማሪም ኡጋንዳም የበራሪ አእዋፍ ሽመላ መለያ ነው ያላት። የጫካው ግብግብ እዚህ የእግር ኳስ ሜዳውም ውስጥ ልክ እንደጫካው ዓለም የበላይነት ለማግኘት የሚደረግ ፍልሚያ አለ። ከአንበሳ እስከ እባብ፣ ከአቦሸማኔ እስከ ዝሆን ያሉት የዱር እንስሳት በዚህ ዓመቱ የአፍሪካ ዋንጫ ላይ ቦታ አላቸው። ካሜሩን አይበገሬዎቹ አናብስት፣ ስያሜው ቡድኑ ከዚህ በፊት ካሳየው ጥንካሬና ዝና ጋር አብሮ የሚሄድ እንደሆነ ይነገርለታል፤ ያለፈውን ውድድር ጨምሮ አራት ጊዜ ዋንጫውን ለማንሳት ችለዋል። ሞሮኮ የአትላስ አናብስት ኮት ዲቯር ዝሆኖቹ፡ ሃገሪቱ በዝሆን ጥርስ ንግድ በነበራት ዝና ምክንያት ዝሆን የኮትዲቯር መለያ ምልክት ነው። ቤኒን ሸለውለዊቶቹ፡ ቡድኖች ካላቸው ስያሜ መካከል ትንሿ እንስሳ ናት አንጎላ ግዙፎቹ ድኩላዎች
የአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታዎችን ውጤት ይገምቱ
ጁን ሁሉም ሰዓቶች በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ናቸው። ቢቢሲ ለሚደረጉ የሰዓት ለውጦች ሃላፊነትን አይወስድም። የቀጣዩን ጨዋታ ውጤት ይገምቱ ሴኔጋል ከ አልጄሪያ በምታደርገው ጨዋታ እንደምታሸንፍ ገምተዋል። አቻ ትወጣለች ሴኔጋል ከ አልጄሪያ በምታደርገው ጨዋታ አቻ እንደምትወጣ ገምተዋል። ትሸነፋለች ሴኔጋል ከ አልጄሪያ በምታደርገው ጨዋታ እንደምትሸነፍ ገምተዋል። ሁሉም ሰዓቶች በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ናቸው። ቢቢሲ ለሚደረጉ የሰዓት ለውጦች ሃላፊነትን አይወስድም።
በኢኮኖሚው የላቀ ድርሻ የተያዘው በጥቂት ሙሰኞች ከመሆኑ በላይ እነዘህ ግለሰቦች በተለያየ መንገድ በዝባዥ መሆናቸው ያሰጋቸዋል።
ግለሰቦቹ ያላቸውን የአቅም የበላይነት ተገን አድርገው ኢኮኖሚውን ጠልፈው መጣል የሚችሉ መሆናቸው የአዲሱ አስተዳደር ራስ ምታት ይሆናል። መምህሩ በአሁን ወቅት አሳሳቢ ደረጃ ላይ የደረሰውን የዶላር እጥረት በአብነት ይጠቅሳሉ። ባለፉት አራት ወራት የተባባሰውን የዶላር እጥረት ብንመለከት ለነዚህ ግለሰቦች ዶላርን ከመደበኛው ገበያ ወደ ጥቁር ገበያ ማዘዋወር እጅግ ቀላል ነው ሲሉ ይገልጻሉ። ይህም የዋጋ ንረትና የስራ አጥነት መንሰራፋትን ያስከትላል። ህዝቡ በዚህ ሳቢያ ወደ ተቃውሞ ካመራ ሀገሪቱ ዳግም ባለመረጋጋት መናጧ እንዳማይቀር ይገልጻሉ። መንግስታዊ ተቋማት ወደ ግለሰቦች ይዞታ የሚዘዋወሩበት ውሳኔ መተላለፉም ሌላው ስጋታቸው ነው። ውሳኔው አገሪቱን የባሰ የኢኮኖሚ ውጥንቅጥ ውስጥ እንደሚዘፍቃት ያስረዳሉ። እንደ ምክንያት የሚያስቀምጡት መንግስታዊ ተቋማቱን የመግዛት አቅም ያላቸው ሙሰኞችና ኪራይ ሰብሳቢዎች መሆናቸውን ነው። የኋላ ኋላ በማህበረሰቡ መሀከል ያለው የገንዘብ አቅም ልዩነት እየሰፋ ስለሚሄድ ሀገሪቱም ትታመሳለች የሚሉት ዶ ር ነመራ መንግስት ጠንካራና የማያዳግም እርማጃ እንዲወስድ ያሳስባሉ። ቀጠናዊ ትስስርና የወደፊት ፈተናዎች ጠቅላይ ሚንስትሩ ስልጣን ከያዙ በኋላ ከአገር ውጪ መጀመሪያ የጎበኙት ጅቡቲን ነበር። አስከትለውም ኤርትራና ኬንያን ጨምሮ ወደ ቀጠናው ሌሎች አገሮችም አቅንተዋል። በጉብኝቶቹ ከአቻዎቻቸው ጋር በዋነኛነት ስለኢኮኖሚያዊ ትስስር ተነጋግረዋል። የምስራቅ አፍሪካ ቀጠና አገሮችን በኢኮኖሚ ከማስተሳሰር ባሻገር የቀጠናውን ሰላምና መረጋጋት በማስጠበቅ ረገድ ውይይቶቹ ጠቃሚ መሆናቸውን በአዲስ አበባ ዪኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስና አለም አቀፍ ግንኙነት ትምህርት ክፍል መምህሩ አቶ አዳነ አለማየሁ ይናገራሉ። የኤርትራን ጉብኝት ብንወስድ የሁለቱ ሀገሮች ለሰላማዊ ግንኙነት ማኮብኮብ ከአገራቱ ባሻገር ለቀጠናውም አለመረጋጋትም እልባት ይሰጣል። ለኢትዮጵያ አለመረጋጋት ተጠያቂ የሚሆኑ ኤርትራ ያስጠለለቻቸው ሀይሎች ለማስከን ይረዳል ይላል መምህሩ። የብር የመግዛት አቅም መቀነስ አንድምታዎች ላለፉት አመታት ሁለቱ አገራት ሳይታኮሱ ጦርነት ውስጥ ነበሩ። ሰላም ማጣት ብቻ ሳይሆን ኢኮኖሚያቸው ላይም ተጽእኖ አሳድሯል። የአገራቱ መሪዎች ፊት ለፊት ተገናኝቶ መነጋገር እሰየው ቢያሰኝም በጥንቃቄ መታየት ያለባቸው ነጥቦችም አሉ። ሁለቱ አገሮች እርቀ ሰላም አውርደው እንደ ሁለት አገራት እንዲቀጥሉ በመሀከላቸው ያሉ መሰረታዊ መስመሮች መጠበቅ አለባቸው። የሁለቱ ሀገር ዜጎች አንዳቸው በሌላቸው ሀገር ምን መብት ይኖራቸዋል የሚለውም የህግ ማእቀፍ ያስፈልገዋል።ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት መጀመር ፍጹም ሰላም ነግሷል ማለት አይደለምና። በመምህር አዳነ አገላለጽ ዝም ብሎ ድንበር ከፍቶ ኑ ግቡ ኑ ውጡ መባባሉ የተጨማሪ ግጭቶች መነሻ እንዳይሆን ጥንቃቄ ያስፈልጋል። ጥያቄን ያዘለው የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን ሁለቱ አገራት በራሳቸው ተነሳሽነት ማለትም ያለ ሶስተኛ ወገን አሸማጋይነት ወደ ስምምንት መምጣታቸው መልካም ነው። ይህን መሰረት በማድረግም ስለ አልጀርስ ስምምነት አፈጻጸም ተወያይተው አንዳች ውጤት እንደሚያስመዘግቡ ብዙዎች ተስፋ አድርገዋል። ሁለቱ አገሮች የጀመሩት የሰላም ጉዞ ምናልባትም አለመተማመናቸውን ይሽር ይሆናል። የጎሪጥ መተያየትን ማስቀረት ግን የነገሩ መጨረሻ አይደለም። ለወደፊት ለሚጠበቁ ውሳኔዎች ግብአት እንጂ። መልካም ግንኙነቱ ካደገ ኢትዮጵያ ጥቅሟን የምታስከብርበት መንገድ መቀየስ እንዳለባት አቶ አዳነ ያስረዳሉ። ወደብ አልባዋ ኢትዮጵያ ከጎረቤቶቿ የምትፈልገው ወደብ ነው የሚሉት መምህሩ በዋነኛነት የጅቡቲ፣ የኤርትራና የሱዳን ጉብኝት ፍሬያማ እንደሚሆን ያምናሉ። የኢትዮጰያ ኢኮኖሚ ተሽመድምዶ እንዳይቀር የአጎራባቾቿን ወደብ መጠቀም የግድ ይላታል። ለዚህም ቁልፉ የቀጠናው ሀገራት ራሳቸው እየተጠቀሙ ጎረቤቶቻቸውንም የሚጠቅሙበትን ትስስር እውን ማድረግ ነው። የቀጠናው አገሮች በኢኮኖሚ ከተሳሰሩ ለጥቅማቸው ሲሉ ወደ ግጭት ከመግባት እንደሚቆጠቡ መምህሩ መላ ምቱን እንዲህ ያስቀምጣሉ። ኢትዮ ቴሌኮም ወዴት ወዴት የጠቅላይ ሚንስትሩ ንግግርና እንቅስቃሴ የቀጠናው ሀገራትን ወንድማማችነት ያጠናክራል። አገሮቹ ኢትዮጵያ ላይ ያላቸውን ጥርጣሬ ያጠፋል። መንግስታቱም ጥሩ ምላሽ ሰጥተዋል። በሌላ በኩል የቀጠናው አገሮች በውስጣዊ የፖለቲካ ቀውስ፣ በተዳከሙ ወይም አቅም ባጡ መንግስታት፣ በምዕራባውያን ጣልቃ ገብነትና በአክራሪነት ይፈተናሉ። ቀጠናው የአሜሪካ፣ የቻይና የቱርክና የሌሎች አገሮችም ፍላጎት አለበት። መምህሩ እንደሚለው ቻይና በክልሉ ያለኝን ኢንቨስትመንት ለመጠበቅ ብላ ወታደሮች ለማስፈር እንቅስቃሴ መጀመሯ ለህልውናችን አደጋ ነው ይላሉ። ከቀጠናው አገሮች መሀከል የመንግስታት አቅም ማጣት የመፈራረስ ስጋት የፈጠረባቸው መኖራቸው እሙን ነው። ጠንካራ መንግስት ማጣታቸው የግጭት መንስኤ መሆኑ ከአገራቱ አልፎ ለቀጠናውም አስጊ ነው። ከቀጠናው አገሮች ምን ያህሉ ዴሞክራሲያዊ ናቸው ሌላው ጥያቄ ነው። የመንግስታቱ አምባገነንነት እርስ በእርስ የሚፈጸሟቸው ስምምነቶች ፍሬያማ መሆናቸው ላይ ጥያቄ እንደሚያጭር መምህሩ ይናገራሉ። ሌላው ፈተና አክራሪነት ነው። አልሸባብ በምስራቅ አፍሪካ እስላማዊ መንግስት ማቋቋም ይፈልጋል። ለጥቅማቸው ሲሉ ይህንን ተግባር የሚደግፉ አገራትም ስጋት ናቸው። የአካባባቢው መንግስታት የሽብር ጥቃቶችን እንዴት ይቋቋማሉ ከኢትዮጵያ ጀምሮ በተቀሩትም የቀጠናው አገሮች ጽንፍ የወጣ ጎሰኝነትና ብሄርተኛነት አጥልቷል። እነዚህ መሰናክሎች እልባት እስካልሰጣቸው ዘላቂ ለውጥ ለማምጣት ያዳግታል። ተያያዥ ርዕሶች
ስለ ማጋራት ተጨማሪ ያጋሩ
ማጋሪያ ምረጥ ፀደቀ ይሁኔ ወልዱ ኢንጂነር የፍሊንት ስቶን ኢንጂነሪንግ መስራችና ባለ አክሲዮን ናቸው። በዚህ ዓመትም በ ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ያስገነቡትና በአባታቸው ስም የሰየሙት አዳሪ ትምህርት ቤት በደሴ ሥራውን ጀምሯል። በቅርቡም ሾተል የሚል መጽሐፍ ለንባብ አብቅተዋል። በመጽሐፉና በሙያቸው ዙሪያ ከቢቢሲ ጋር ቆይታ አድርገዋል። መጽሐፍዎት ምን ላይ የሚያተኩር ነው ፀደቀ ይሁኔ፦ የእድገትና የትራንስፎርሜሽን እቅዱ ላይ ነው የፃፍኩት። የእድገትና የትራንስፎርሜሽን እቅዱ ባለ ሁለት ስለት ቢላ ነው። በአግባቡ ካልተያዘ በአንድ በኩል ሰውን ይጎዳል በአንድ በኩል ሊያለማ ይችላል የሚል ነገር ነው ያለው። በመጽሐፉ ውስጥ አምስቱ ቁልፍ ችግሮቻች ያልኳቸው የከተማ ልማት፣ ኮንስትራክሽን፣ ንግድ፣ ትራንስፖርት እና ፋይናንስን በሚገባ ለማየት ሞክሬያለሁ። በቴክኖሎጂ ኢ ፍትሐዊነትን የምትታገለው ኢትዮጵያዊት አሁን ያለነው ሁለተኛው የእድገት እና የትራንስፎርሜሽን እቅድ ላይ ነው። ይህ የሁለተኛው እድገትና ትራንስፎርሜሽን ምርመራ ያስፈልገዋል በማለት ለመፃፍ የተነሱት መቼ ነው ፀደቀ ይሁኔ፦ መጀመሪያ ላይ ያሰብኩት በበራሪ ወረቀት መልኩ ሀሳቤን ለማካፈል ነበር። ከተማ ልማት፣ ኮንስትራክሽን፣ ንግድ፣ ትራንስፖርትና ፋይናንስ እነዚህን አምስቱ ጉዳዮችን በማንሳት ውይይት እናድርግ በሚል ለሀገሪቱ ከፍተኛ አመራሮች በኢሜል እየላኩ ብቆይም ብዙም ሀሳቤን አልቀለቡትም። ከዚያ ግራ ተጋባሁ፤ በኋላ ላይ ደግሞ አንድ ሰው ሌሎቹንም ጨምራቸው ሲለኝ ኢንዱስትሪንና ግብርናን ጨምሬ እንደገና ላኩላቸው። በዚህ ሂደት ላይ እያለሁ ነው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የመጡት። እርሳቸው እንደተመረጡ የእድገትና የትራንስፎርሜሽኑ ግምገማ ህዝባዊ መድረኮች መካሄድ ጀመሩ። ሕዝባዊ መድረኮቹ ላይ ህዝቡ የሚያነሳቸውና አመራሩ የሚረዳበት መንገድ አልገጠመልኝም። ለአውሮፕላኑ መከስከስ ፓይለቶች ተጠያቂ ሊሆኑ አይችሉም አቶ ተወልደ ገብረማርያም ሕብረተሰቡ እሮሮውን በግልፅ ነው የሚያስረዳው። አመራሩ ግን በእሮሮ ውስጥ ችግሮቹንና መፍትሄዎቹን የመቅለብ አቅሙ ዝቅተኛ ሆነብኝ። እና አሁንም ሌላ ጠበብ ያለ መድረክ እናዘጋጅ ብዬ ፋና ብሮድካስቲንግና ብሔራዊ የፕላን ኮሚሽን አንድ ላይ ሆነው እኔ ትንሽ እገዛ አድርጌ የዛሬ ዓመት ገደማ አንድ መድረክ አዘጋጀን። እዚያ መድረክ ላይም የተነሱት ነገሮችን ስመለከታቸው ብዙ ሰው የታየው ነገር የለም። ስለዚህ ይህንን ነገር በደንብ ባየው ይሻላል በማለት ትንሽ ጽፌበት በመጽሀፍ መልክ ቀላል መረዳት ኮመን ሴንስ የሚጠይቁትን ነገሮች ባሰፍር፤ በዚህ በለውጥ ወቅት ብዙ ሰው ትራንስፎርሜሽንን ተገንዝቦ አዲሱን የለውጥ አመራር ያግዛል ብዬ በዚያ መልክ ጀመርኩት። በኋላ ግን ሳየው፤ መረጃዎችን ስሰበስብ ውስጡ ብዙ ችግሮች አሉት። እና ይኼ በ ገፅ በራሪ ወረቀት ሊሆን አይችልም አልኩ። ምክንያቱም ፋይናንስ ብቻ ገፅ ሆነብኝ። ለዚያውም ቆራርጨው ነው አንጂ የሰራሁት አጠቃላይ ወደ ገፅ ነበር። ከዚያ ለሕትመት እንዲሆን በማለት ወደ ገጽ አሳጠርኩት። የቴክኖሎጂ ፈጣሪዎች ልጆቻቸው ሞባይል እንዳይጠቀሙ የሚያግዱት ለምን ይሆን የኢህአዴግ አብዮታዊ ዲሞክራሲ መስመር ህፀጾች አሉበት። በነፃነትና በእኩልነት የሚያምን ድርጅት ነፃነትና እኩልነትን አላራመደም። በገበያውና በፖለቲካ ውስጥ ነፃ ገበያንና ነፃ ፖለቲካን ዋና ምሰሶዎቼ ናቸው ብሎ የተነሳ ድርጅት ነፃ ገበያም አላካሄደም ነፃ ፖለቲካም አላካሄደም። ገና በ ዓ ም ነፃነት ፖለቲካው ላይ ትንሽ ብቅ ሲል ደነገጠና ዝግት አደረገው። ልክ የፖለቲካውን ነፃነት ሲዘጋው ነፃ ገበያውም በነፃ ፖለቲካው ማፈኛ ሥርዓት ነፃ ገበያውን የሚቆጣጠሩ ኃይሎች መጡና የነበረውን እንዳልነበር አደረጉት። ያንን ነው በማስረጃ አስደግፌ ከንድፈ ሃሳባዊ መነሻ ጋር ለማየት የሞከርኩት። ለምሳሌ የኢትዮጵያ መንግሥት ስለታይዋን በጣም ነው አድንቆ የሚያወራው። ታይዋን ማለት ግን የነዋሪውን ብዛት የቆዳውንም ስፋት ስታየው ከአዲስ አበባ የማይተልቅ ኢኮኖሚ ያላት ሀገር ነች። በዚህ ብዝኀነት በበዛበት ሀገር የታይዋንን ሞዴል እጭናለሁ ማለት ከዲሞክራሲ ጋር የሚሄድ አይደለም። ማነሷ ብቻ አይደለም መሪዎቿ የደሴቲቱን ነዋሪዎች እንደ ሁለተኛ ዜጋ ጨቁነው ያሳደጓት ሀገር ናት። እንደዛ ተጨቁኖ ሊያድግ የሚፈልግ የኢትዮጵያ ሕዝብ የለም። ጭቆናውን የሚፈቅድ ሕዝብ ባለበት የታይዋን ሞዴል ሊሰራ ይችላል። ጭቆናውን የማይፈቅድ ማህበረሰብ ባለበት ግን መጀመሪያ ላይ የዛሬ ዓመት መለስ ዜናዊ ዲሞክራሲ፣ ነፃ ገበያ አማራጭ ሳይሆን የሕልውና ጉዳይ ነው ብሎ ጽፎታል። መንገድም ግብም ነው ብሎ ነው የሚጀምረው። ፈጣን እድገት ሁሉንም አሳታፊ የሆነ፣ ከተመፅዋችነትና ከፖሊሲ ተጽዕኖ የራቀ ብሎ ያስቀመጠ ድርጅት በኋላ ግን የሁሉም መጫወቻ ነው የሆነው። አሁን ያንን መመለስ ይቻላል። የተጻፈ ነገር ስለሆነ ያንን ተከትሎ መሄድ ይቻላል። የሰው ሀሳብ ነው ገጣጥሜ የጻፍኩት የራሴ ሀሳብ የለበትም። በእርስዎ ሀሳብ የእድገትና የትራንስፎርሜሽን እቅዱ መሬት ላይ ወርዷል ስኬታማ ነበር ፀደቀ ይሁኔ፦ የመጀመሪያው አምስት ዓመት መለስ በሕይወት ስለነበር በደንብ ነው የሄደው። በተለይ ደግሞ እስከ ዓ ም ድረስ የነበረውን ነፃ አካሄድ ከዐዕቅዱም በፊት በድህነት ቅነሳ ስትራቴጂ ውስጥ ነበረው እንቅስቃሴ ውስጥ የነበረው ነፃ አስተሳሰብ መልሶ ማምጣት ይቻል ነበር። ያንን ማድረግ አልቻለም። እንደሚመስለኝ ከ በኋላ በጂቲፒ የበለጠ ነፃ ፖለቲካና ኢኮኖሚ ለማካሄድ ታስቦ፣ እንኳን ከውጪ ነፃነት ሊኖር በዛው በኢህአዴግ ውስጥም ነፃ ወስጠ ድርጅት ዲሞክራሲ ጠፋ። በዚያ ዲሞክራሲ በጠፋበት ጊዜ ደግሞ ኃያል የሆኑ ሰዎች በፈቀዱት መንገድ መሩት። ለሕዝብ ያልወገነ ሁሉም ለየራሱ የቆመበት አካሄድ ስለሆነ የሄደው መጨረሻው እንደምናየው ታሪክ ነው የሆነው። አንድ ቀን ያ እንዴት እንደሆነ ከእኔ የበለጠ የሚያውቁ ሰዎች መፃፋቸው አይቀርም። ኢሳያስን ለመጣል ያለመው ይበቃል የተሰኘው የኤርትራውያን እንቅስቃሴ አሁን ግን የታቀደው ምን ነበር ወዴት ነው የምንሄደው ካልክ ዘጠና በመቶ በሥራ ላይ የዋለው ህብረተሰብ በመቶው ለራሱ ሥራ የፈጠረ ነው። በመቶ በግብርና በመቶው በግሉና በመንግሥት ተቀጥሮ ነው ያለው። ብዙ ጊዜ የምንሟገተው በግሉና በመንግሥት ተቀጥሮ ስላለው በመቶው ነው። በመቶውን ሕብረተሰብ የሚያስተናግድ ሥራ ሳንሰራ፣ ስለእርሱ ሳናወራ ትራንስፎርሜሽን ማምጣት አንችልም። መጽሐፉ ውስጥ ዝርዝር ነገሮች ተቀምተዋል። ብዙ ስህተቶች ሊኖሩት ይችላሉ። የዓላማ ስህተት ግን እንደሌለው አረጋግጥልሀለው። ጂቲፒው ተመልሶ መስመር ውስጥ መግባት አለበት። መንግሥት የተለያዩ የሕዝብ ንብረቶችን ወደ ግሉ ዘርፍ ለማዘዋወር እየተንቀሳቀሰ ነው፤ እርስዎ በዚህ እርምጃ ላይ ያለዎት አቋም ምንድን ነው ፀደቀ ይሁኔ፦ ልማት ምርጫ አይደለም። ልማታዊ መንግሥት ያልሆነ የለም። መንግሥት ነው ካልን ልማት አለ። ያልለማ ሀገር ላይ አለመልማት ጭራሽ የሚታሰብም ነገር አይደለም። ልማት ምን ጊዜም ቢሆን የፖለቲካ አጀንዳ ከመሆን አይቆምም፤ በበለፀጉት ሀገሮችም እንኳ ቢሆን። ጥያቄው ልማትን ማን ያልማ የሚል ነው። መንግሥት ያልማ ወይስ የግሉ ዘርፍ። በእርሱም ደግሞ ሙግት የለም። መንግሥት ሊያለማ አይችልም። መንግሥት መሠረተ ልማት ነው የሚያለማው ሌላውን ነገር የግሉ ዘርፍ ያለማል። ገንዘብን የሚያውቀው፣ ለገንዘብ የሚቆመው የግሉ ዘርፍ ነው። የሕዝብ ሀብት ስቴት ካፒታል በማን ስር ይሁን ካፒታሉን ማን ይቆጣጠረው ቢባል፣ የስቴት ካፒታሉ ይብዛ ቢባል፣ እንደ አሜሪካ ግዙፍ ስቴት ካፒታል ያለበት ሀገር የለም። በአሜሪካ በቢሊየን የሚቆጠሩ ሀብቶች የሚያንቀሳቅሰው ጦር ሠራዊቱ ያለው ኢንደስትሪ ነው፤ የወደብ አስተዳደሩ ትልቁ ነገራቸው ነው። ትራንስፖርት ዘርፉ እንዳለ የእነርሱ ነው። ስለዚህ ብዙ ካፒታል የስቴት ካፒተታል ነው አሁንም ቢሆን። መንግሥት ካፒታል አይኑረው ከሆነ በሎሌነት ለሌሎች ሀገሮች ወይ ለሌሎች ካፒታሊስቶች እንደር ካልሆነ በስተቀር፤ በሀገር ጉዳይ ላይ ስቴት ካፒታል አይኑረን የሚል መንግሥት አይመጣም። ሊመጣም አይችልም። ቢመጣም አሁን ባለው የንቃተ ህሊና ደረጃ በአጭር ጊዜ ከሥልጣን ይወርዳል። ዲሞክራሲ ስር ባልሰደደበት ሀገር ሁለት መንገድ ብቻ ነው ያለው። አንዱ ምንድን ነው የኢኮኖሚ ተሳታፊዎቹ ድንበር ዘለል ወደ ሆነ ወደ ድብቅ ኮንትሮባንድ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ውስጥ ይገቡና መንግሥትን ያንቁታል። ብር ሲያጣ ይወድቃል። ሌላው ኢኮኖሚውን ይተውና ኢኮኖሚ ውስጥ ያልተሳተፉ ሰዎች አማፂ ይሆናሉ። በዚህም ያፈርሱታል። ዲሞክራሲ ስር ቢሰድ ኖሮ ግን በምርጫ ብቻ ነበር ከስልጣን የሚወርደው። አሁን ግን ዲሞክራሲው ስር ስላልሰደደ መጀመሪያ ዲሞክራሲውን ስር የማስያዝ ሥራ መስራት አለብን። የመጀመሪያው የመንግሥት ሥራ ምን ልሽጥና ምን አልሽጥ ሳይሆን እንዴት አድርጌ ዲሞክራሲውን መሰረት ላስይዝ ነው መሆን ያለበት። ለምሳሌ የአካባቢ ምርጫ ላይ መካሄድ ሲኖርበት አልተካሄደም። ስለዚህ ይህ ምርጫ ድረስ ዘግይቶ ከሀገራዊ ምርጫ ጋር የሚካሄድበት ምክንያት የለም። ድሮም ሕገ መንግሥቱ በአንድ ጊዜ የሕዝብ ሥርዓቱ አንዳይፈርስ ለማድረግ የአካባቢና ሀገራዊ ምርጫ የሚካሄዱበትን ነገሮች እንዲንገጫገጩ አድርጓቸዋል። ክትባት ከየት ተነስቶ የት ደረሰ ስለዚህ መጀመሪያ በአካባቢ ምርጫ መሰረት ላይ የቆሙ ክልሎችና አካባቢዎች መኖር አለባቸው። ያ ሕዝባዊ ተቋም በአግባቡ ሳይቆም ሀገራዊ ምርጫ ማካሄድም አይቻልም። ድርጅቶቹን የሚገዙትስ ቢሆኑ በድርድር ሰዓት ቀጣይነት በሌለው መንግሥት ምንድን ነው የሚደራደሩት የአንድ ነገር እሴት እኮ የረዥም ግዜ ትርፉ ነው። ስለዚህ የሚቀጥለው ምርጫ ውጤቱ ምን እንደሆነ ሳያውቁ ምንድን ነው የሚገዙት ያለንን የሕዝብ ሀብት ወደ ግል ለማዘዋወር ብቻ ካልሆነ በስተቀር የምንሸጠው ውጤታማ የሆነ ዘርፍ ለማምጣት ከሆነ መጀመሪያ መደረግ ያለበት የመቀመጫዬን ነው። መጀመሪያ ዲሞክራሲው መስፈን አለበት። በእርግጥ ዲሞክራሲ እስኪሰፍን ድረስ ተብሎ ስለ ኢኮኖሚው ሳይወራ አይቀርም። ግን ቢያንስ ቢያንስ የአካባቢ ምርጫ ተካሂዶ ህብረተሰቡ በራሱ ጉዳይ፣ በእለታዊ አጀንዳዎቹ የሚጠመድበትን የፖለቲካና የኢኮኖሚ ምህዳር ማደላደል አለብን። ያንን ሳናደርግ ቴሌንና መብራት ኃይልን መሸጥ የሚባለው ነገር አያስኬድም። እነዚህ አገልግሎቶች የሚተሳሳሩት ከወረዳና ከቀበሌዎች ከከተሞች ጋር ነው። የገበያ ሁኔታን ሳታረጋጋ ቴሌን የምትሸጥበት መንገድ ምንድን ነው የገንዘብ፣ የኢኮኖሚም ሆነ የፖለቲካ ትርጉም አይሰጥም። ከነበሩት አለመረጋጋቶች ጋር በተያያዘ የኮንስትራክሽን ዘርፉ መቀዛቀዝ ይታይበታል ይባላል፤ እርስዎ በዘርፉ ላይ እንደተሰማራ አንድ ግለሰብ ሁኔታውን እንዴት ነው የሚገመግሙት ፀደቀ ይሁኔ፦ እኔ ኮንስራክሽኑን የማየው እንደ ሁለት ነገሮች ነው። አንዱ ኪራይ ሬንት ነው። መሸሸጊያ ነው። የመንግሥት በጀት ላይ ጥገኛ ስለሆንን ከአንዱ ነጥቄ ወደ አንደኛው እንዴት ላምጣው በሚለው ሙግት ውስጥ ነው ያለነው። ሁለተኛው ግን ማንኛውም ባለሀብት የሚበዘብዘው በምንድን ነው ባለሀብት ማለት በዝባዥ ማለት ነው፣ ሳትበዘብዝ ካፒታል አታጠራቅምም ሳቅ ። የሚበዘበዘው ጉልበት ነው። የሚበዘበዝ ጉልበት በጣም በብዛት ያለው ደግሞ ገጠር ውስጥ ነው። የገጠሩ አርሶ አደር የገፋውን አምራች ኃይል ሥራ ፍለጋ መንገድ ላይ ይቆማል። ከዚያ ደግሞ አልፎ ወደ ከተማ ይመጣል። ስለዚህ ኮንስትራክሽን ላይ ይህ የሰው ኃይል ነው ያለው። ቃሊቲ ማረሚያ ቤት ትምህርት ቤት ሆኖኛል ደበበ እሸቱ ለሰራተኛው ደህንነት ግድ ሳይሰጠን ከፎቅ ላይ ሰው እየፈጠፈጥን፣ ሚስማር አየወጋው፣ ከተገቢው በታች እየከፈልነው ነው የምናተርፈው። ስለዚህ ይኼ ከአርሶ አደሩ በተበዘበዘ ገንዘብ በመንግሥት በጀት ጥገኛ የሆነ ዘርፍን እንዴት እናስተካከለው የሚለው ነው የመጀመሪያ ጥያቄ። የትኛውም መንግሥት ቢመጣ ይኼንን ሳያስተካክል የመንግሥት ግዢ ስላለበት፤ መንግሥት የመሰረተ ልማት ግዢ ውስጥ ያለውን ግፍና ሌብነት ሳያስተካክል የመደብ ለውጥ አይመጣም። የመደብ ለውጥ ሳያመጣ እንዲሁ አርሶ አደር እንደሆነ መቀጠል የለበትም፤ መቼም። ያንን ለማምጣት ከፈለገ የሕብረተሰቡን ገንዘብ የሚበላውን ነገር ማስተካከል አለበት። ከተሞችና ኮንስትራክሽን አብረው አርሶ አደሮቹን መበዝበዣዎች ናቸው፤ እርሱን መጀመሪያ ማስተካከል አለብን። ይኼ መሰረታዊ የፖለቲካል ኢኮኖሚ ሀሳብ ነው። አሁን ግን ሌሎች ሌብነቶችም ወደ ኮንስትራክሽን ዘርፉ እየገቡ ነው። ለምሳሌ ብረትን ብትወስድ ብዙ አስመጪዎች ሲያስመጡ ታክስ የለባቸውም ነገር ግን ዶላሩ በእጃቸው ስለማይገባ ብዙ ፐርሰንት ይወስድባቸዋል። ፐርሰንት ይመስለኛል ዶላሩንም ቢሆን እንደፈለጉ ስለማይገዙ የአርማታ ብረት ብዙ አስመጪዎች የውጪ ምንዛሬ የሚመነዝሩበት ሆኗል። የውጪ ምንዛሬ እጥረት ተፈጠረ ከተባለ በኋላ የብረት ዋጋ በ ፐርሰንት ጨምሯል። በኪሎ ከ ብር የነበረው ብር ነው የገባው። ብሄራዊ ባንክ የሚያወጣውን መረጃ ብናይ ብር ተገቢ ያልሆነውን ዋጋ እንደተሰጠው ያሳያል። ላኪው ይህንን የብርን ያልተገባ ዋጋ የሚያካክሰው ቡናውንም ሰሊጡንም በርካሽ ዋጋ ይሸጥና ከውጪ የሚመጣውን ብረት ውድ ያደርገዋል። ስለዚህ ብረት አሁን ወርቅ ሆነ፤ የኮንስትራክሽን ዘርፉን የሚቆጣጠሩት ብሔራዊ ባንክንና የውጪውን ንግድ የሚቆጣጠሩት ኃይሎች ናቸው። ስለዚህ እኛ ዝም ብለን አስተላላፊ ነን። የውጪ ምንዛሬ እናገላብጣለን እንጂ ሥራ አንሰራም። ይኼ ቢከፈት ግን ቀጥታ ማስመጣት ብንችል ላኪውም ያ መንገድ ስለሌለው ወደ አገልግሎት ሰጪ ዘርፎች ወይንም ወደ ካፒታል ኢንቨስትመንት ይሄዳል። ወደ ኮንስትራክሽን ዘርፉ መግባት ለሚፈልጉ ወጣቶች ምን ትመክራቸዋለህ ኮንስትራክሽን በእኔ ግምት በየትኛውም ሀገር ውስጥ በቀላሉ የሌብነት ጫካ መሆን የሚችል ዘርፍ ነው። የመሰረተ ልማት ግዢ ግዙፍ ስለሆነ በርካታ ነገሮች በቀላሉ አይታወቁም። አንድ የሽንት ቤት መቀመጫ አምስት ሺህ ዶላርም አምስት ዶላርም ሊሆን እችላል። በእነዚህ ነገሮች ውስጥ አንዱን ዋጋ ሰጥተህ አንደኛውን ማቀበል ዋናው የትርፍ ምንጭ ነው። ሌላው የትርፍ ምንጭ ደግሞ በወዛደሩ ጉዳት ማትረፍ ነው። እነዚህ ነገሮች መስተካከል አለባቸው። አዳዲስ ወደ ገበያው የሚገቡ ወጣቶች የዋህነታቸው ሳይጠፋ የሀገር ተልእኳቸውን እንዲጨምሩበት ማስቻል አለብን። ይህ ለየትኛውም ዘርፍ ይሰራል። ኮንስትራክሽን ዘርፉ ላይ ደግሞ ለሰው ልጆች ብሎ የቆመ ከሁሉም የላቀ ውጤት ያገኛል ብዬ አምናለሁ። እኔ እንደዛ ነው እዚህ የደረስኩት። መጥፎ ሳልሆን ቀርቼ ሳይሆን መጥፎዋን መንገድ ቀድሜ ስለተውኩት ነው። ተያያዥ ርዕሶች
የብር የመግዛት አቅም መቀነስ አንድምታዎች
ኦክተውበር ስለ ማጋራት ተጨማሪ ያጋሩ ማጋሪያ ምረጥ የዓለም ባንክ ኢትዮጵያ የገንዘቧን የመግዛት አቅም ዝቅ እንድታደርግ ግፊት ሲያደርግ ቢቆይም የብርን የመግዛት አቅም እንዲቀንስ ማድረግ ከሚያስገኘው ጥቅም ይልቅ ጉዳቱ ያመዝናል በማለት መንግሥት ሳይቀበለው ለረጅም ጊዜ ቆይቷል። አሁን ግን የተቀዛቀዘው የወጪ ንግድን እንዲያንሰራራ ለማድረግ የብር የውጭ ምንዛሬ ዋጋ በ በመቶ እንዲቀንስ ተደርጓል። ይህ እርምጃ በህብረተሰቡና በገንዘብና በምጣኔ ሃብት ባለሙያዎች ዘንድ ትልቅ ስጋትን ፈጥሯል። በተለይ ይህ ከፍተኛ የመግዛት አቅም ማሽቆልቆል ወትሮም በፍጆታ እቃዎች እጥረት እየተቸገረ ለሚገኘው ሸማቹ ህብረተሰብ አስደንጋጭ ክስተት ነው። በየወሩ የሚደረገውን የነዳጅ ዋጋ ክለሳን ተከትሎ በፍጆታ ምርቶች ላይ የሚታየው የዋጋ ጭማሪ ያስመረራቸው የአዲስ አበባ ነዋሪው አቶ ደቻሳ በዚህ እርምጃ ምክንያት እየተጋፈጥነው ያለው ችግር ከቁጥጥር ውጪ ይሆናል ብለው እንደሚሰጉ ይናገራሉ። የመዋዕለ ነዋይ ባለሙያው አብዱልመናን መሃመድም ይህንን ስጋት ይጋሩታል። ከውጪ በሚመጡ የፍጆታ ምርቶች፣ የጥሬ ዕቃና የማምረቻ መሳሪያዎች ግዢ ምክንያት የንግድ ጉድለት እየሰፋ በሚመጣበት ሃገር ውስጥ፤ በዚህ መጠን የብርን የመግዛት አቅም እንዲቀንስ ማድረግ በአጭር ጊዜ ውስጥ የዋጋ መጋሸብን ያስከትላል በማለት ሊያስከትል የሚችለውን ጫና አስቀምጠዋል። የብር የመግዛት አቅም እንደሚቀንስ ከተነገረ በኋላ በምርቶችና በአገልግሎት ዋጋ ላይ ከፍ ያለ ለውጥ እንደሚኖር በእርግጠኝነት የሚናገሩት አቶ ደቻሳ በዕለታዊ ሥራና እንደኔ ተቀጥሮ ለሚተዳደረው ብዙ ህዝብ ይህ ለውጥ ከባድ ችግርን የሚያስከትል ይመስለኛል ይላሉ። አክለውም የታሰበው ለውጥ መምጣቱን እርግጠኛ ለመሆን በማይቻልበት የውጪ ንግድ ሲባል ድሃው መስዋዕት መሆን አለበት ወይ በማለት ይጠይቃሉ። ግብይት የኢንቨስትመንት አማካሪ የሆኑት አቶ ጌታቸው ተክለማርያም እንደሚሉት የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በአብዛኛው መሠረቱን ከውጭ በሚመጡ ምርቶች ላይ ያደረገ በመሆኑ፤ በመጋዘን ምርት ያለው ነጋዴ እንኳን ወደፊት የሚጠብቀውን የኢትዮጵያ ብር መጠንን በወጪነት እያሰላ የዋጋ ጭማሪ ማድረጉ አይቀርም ይላሉ። ይህም ምግብ፣ አልባሳትና መድኃኒትን ጨምሮ ለየዕለት ፍጆታም ሆነ ለዘላቂ ኑሮ የምንጠቀምባቸውን አብዛኞቹ ህብረተሰቡ የሚፈልጋቸው ምርቶች ላይ የምንዛሪ ለውጡን መሠረት ያደረገ ጭማሪ መከሰቱ አይቀሬ መሆኑን አቶ ጌታቸው ያክላሉ። መርካቶና ካዛንችዝ አካባቢ በፍጆታና ቋሚ ምርቶች ንግድ ላይ የሚገኙ ነጋዴዎችን ጠይቀን እንደተረዳነው፤ የብር የመግዛት አቅም እንዲቀንስ በመደረጉ ምክንያት በአቅርቦታቸው ላይ የዋጋ ጭማሪ እንደሚኖር እርግጠኛ ቢሆኑም በምን ያህል መጠን የሚለው ላይ ለመወሰን የገበያው ሁኔታና የነጋዴውን ስምምነት እየጠበቁ መሆናቸውን ገልፀውልናል። አቶ ጌታቸው እንደሚሉት የብር የመግዛት አቅም አንሷል የምንለው በጥቁር ገበያ እና በባንኮች የብር ምንዛሬ መካከል የሰፋ ልዩነት ሲታይ ነው። ይህ የሚያሳየው በገበያ ውስጥ ያለው የውጭ ምንዛሪ ፍላጎትና አቅርቦት ከፍተኛ አለመመጣጠን ስለሚታይበት ነው በማለት ያስረዳሉ። ከዚህ አንፃር አሁን የተወሰደው የብርን የመግዛት አቅም የመቀነስ እርምጃ ይህንን ክፍተት ከማጥበብ አንጻር አወንታዊ ሚና ሊኖረው ይችላል ተብሎ እነደሚታሰብ አቶ ጌታቸው ይናገራሉ። ስጋት ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ አንድ ደሴ ከተማ ውስጥ በንግድ ሥራ ላይ የተሰማሩ ግለሰብ እነደነገሩን ለገበያ የሚቀርቡ ሸቀጦች በዶላር እጥረት ምክንያት ከገበያ እየጠፉ ባሉበት ሁኔታ የብር የመግዛት አቅም በከፍተኛ ደረጃ መቀነሱ በህብረተሰቡም ሆነ በነጋዴው ላይ ከባድ ጫናን መፍጠሩ አይቀርም ይላሉ። ይህ የመንግሥት እርምጃ ወትሮውንም የተቀዛቀዘውን የንግድ ሥራቸውን የበለጠ ሊጎዳው እንደሚችልም ይሰጋሉ። ሁለቱም የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎች ይህን ያህል የብር የመግዛት አቅም ቅነሳ መንግሥት ያሰበውን ያህል ወጤት ቢያመጣለት እንኳን ዘለቄታው ላይ ጥርጣሬ አላቸው። አቶ አብዱልመናን እንደሚሉት ከሰባት ዓመት በፊት የብር የመግዛት አቅም እንዲቀንስ ሲደረግ በወጪ ንግድ ላይ የታየውን አይነት ውስን ለውጥ ያመጣል። ነገር ግን ለውጪ ንግድ ምርት የሚያስፈልጉ ግብዓቶች ዋጋ ስለሚጨምር ይህ አውንታዊ ለውጥ ዘላቂነት አይኖረውም ሲሉ፤ አቶ ጌታቸውም በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ውስጥ የሚታዩ ብዙ ችግሮች አሉ፤ ስለዚህ ይህ እርምጃ የሚታየውን የማክሮ ኢኮኖሚ ያለመመጣጠን ችግርን ይቀርፈዋል ማለት አይደለም ይላሉ። በመንግሥት በኩል ለዚህ እርምጃ የሚቀርበው ምክንያት የውጪ ንግድን ለማበረታታት እንደሆነ ቢነገርም አቶ ደቻሳም ሆኑ የደሴዋ ነጋዴ ህዝቡ ላይ የሚፈጠረውን ጫናና የኑሮ ውድነትን በምን እንዲቋቋመው ታስቦ እነደሆነ ይጠይቃሉ። የብር የመግዛት አቅም እንዲቀንስ ሲደረግ የውጭ ምንዛሪ መጠን አብሮ ይለወጣል። ይህ ደግሞ በምርቶች አቅርቦት ላይ ስለሚንፀባረቅ ችግሮች ይከሰታሉ። የሚያጋጥመው የዋጋ ጭማሪም ከተቀነሰው የብር የመግዛት አቅም በላይ ሊሆን ይችላል የሚሉት አቶ አብዱልመናን የህብረተሰቡ ስጋት ተገቢ መሆኑን ያሰምሩበታል። ሌላ ዕዳ የብርን የመግዛት አቅም በመቀነስ የወጪ ንግድን ማበረታት ይቻላል የሚለው የፖሊሲ አውጪዎች ዕይታ የራሱ የሆኑ ፈተናዎች አሉት የሚሉት አቶ ጌታቸው፤ እንዴት የብርን የመግዛት አቅም በመቀነስ ብቻ ነው የወጪ ንግድን ማበረታታ ይቻላል ላኪዎች በዓለምአቀፍ ገበያ ውስጥ ያላቸው ተወዳዳሪነትስ የተገደበው በብር የመግዛት አቅም ምክንያት ነው በማለት ይጠይቃሉ። ይህ እርምጃ በሃገሪቱ ላይም ከበድ ያለ ጫናን እነደሚፈጥር የሚያምኑት አቶ አብዱልመናን የብር የመግዛት አቅም መቀንስ በመንግሥት የልማት ድርጅቶችና በመንግሥት የውጪ ብድር ላይ ከፍ ያለ ተፅዕኖ ይኖረዋል። እስከ ሰኔ ድረስ ሃገሪቱ ከ ቢሊዮን ዶላር በላይ የውጪ ብድር ዕዳ አለባት። የብር የመግዛት አቅም በ በመቶ እንዲቀንስ ሲደረግ የሃገሪቱ ዕዳ በአስር ቢሊዮን ብሮች ያሻቅባል ማለት ነው በማለት ይገልፃሉ። ይህም ሃገሪቱ ያለባትን የብድር ጫና ከማክበዱ በተጨማሪ ሌሎች ችግሮችን ያስከትላል። ከሁሉ አሳሳቢው ደግሞ የዋጋ ግሽበት እንዲጨምርና ሌሎች ምጣኔ ሃብታዊ ቀውሶች እንዲከሰቱ ሊያደርግ ይችላል። የብርን የመግዛት አቅም ዝቅ በማድረግ ሊከሰቱ የሚችሉ አሳሳቢ ሁኔታዎች አቶ አብዱልማናንና አቶ ጌታቸው እንዲህ ያስቀምጧቸዋል። ከውሳኔው በፊት የነበረው የቅርብ ጊዜ የዋጋ ግሽበት በመቶ እንደሆነ የሚናገሩት አቶ ጌታቸው ገና ከጅምሩ ይህ ግሽበት በጣም ከፍ ሊል ይችላል ሲሉ፤ አቶ አብዱልመናን ድግሞ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ከውጪ ንግድ የሚገኘው ገቢ ቀድሞ በነበረበት ይቀጥላል። ይህ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እርምጃ ወደማያቋርጥ የብር የመግዛት አቅም ቅነሳና የዋጋ ግሽበት አዙሪት ውስጥ ያስገባናል በማለት ያጠቃልላሉ። ተያያዥ ርዕሶች
የአፍሪካ እግር ኳስ ዋንጫ ውድድር
ጁን ሰኔ አየር መከላከያ ስታዲየም፤ ካይሮ ሰኔ አየር መከላከያ ስታዲየም፤ ካይሮ ሰኔ አየር መከላከያ ስታዲየም፤ ካይሮ ሰኔ አየር መከላከያ ስታዲየም፤ ካይሮ ምድብ ለ ሰኔ አየር መከላከያ ስታዲየም፤ ካይሮ ሰኔ አየር መከላከያ ስታዲየም፤ ካይሮ ሰኔ አየር መከላከያ ስታዲየም፤ ካይሮ ሰኔ አየር መከላከያ ስታዲየም፤ ካይሮ ሰኔ አየር መከላከያ ስታዲየም፤ ካይሮ ሰኔ አየር መከላከያ ስታዲየም፤ ካይሮ ሁሉም ሰዓቶች በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ናቸው። ቢቢሲ ለሚደረጉ የሰዓት ለውጦች ሃላፊነትን አይወስድም።
ስለ ማጋራት ተጨማሪ ያጋሩ
ማጋሪያ ምረጥ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ወደ ሥልጣን ከመጡ እነሆ መንፈቅ አለፋቸው። ታድያ ጠቅላዩ መንበረ ሥልጣን ከያዙ ወዲህ ሃገሪቱን ያሳድጋሉና መሆን አለባቸው ብለው ከወሰዷቸው እርምጃዎች መካከል ምጣኔ ሃብታዊ ይዘት ያላቸው ይገኙበታል። ቴሌንና አየር መንገድን የመሰሉ አሉ የሚባሉ የመንግሥት ድርጅቶችን ወደግሉ ዘርፍ ለማዘዋወር ከመወጠን አንስቶ ከጎረቤት ሃገሮች ጋር ያለውን ግንኙነት እስከማጠናከር ድረስ። የዳይስፖራ ትረስት ፈንድ የአደራ ገንዘብ እንበለው እና ለአፍሪካውያን እህት ወንድሞቻችን ቪዛ አየር መንገድ ሲደርሱ መስጠትን ጨምሮ ያሉ ከዚህ በፊት የማናውቃቸው ክንውኖች መታየት ጀምረዋል። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የማክሮና ዓለም አቀፍ ኢኮኖሚክስ ምሁሩ ፕሮፌሰር አለማየሁ ገዳ ጠቅላይ ሚኒስትሩ እስካሁን ያከናወኗቸው ጉዳዮች መልካም ሆነው ሳለ በምጣኔ ሃብት ጉዳይ አማካሪ ያሻቸዋል ይላሉ። እውን ጠቅላዩ ወደሥልጣን ከመጡ ወዲህ የምጣኔ ሃብት ፖሊስ ለውጥ አይተናል ወይ ትልቁ ጥያቄ ነው። የምር የሆነ የፖሊሲ ለውጥ የለም ግን ሃሳብ አለ፤ የመለወጥ አዝማሚያ ታያለህ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከመጡ ወዲህ ይህ ነው ፖሊሲዬ በዚህ መልኩ ነው የምሄደው ያሉን ነገር የለም። ሃዋሳ በነበረው ጉባዔ የኢህአዴግ ላይም የተናገሩት ይሄንኑ ነው። በፊት የነበረው የኢኮኖሚ አስተሳሰብ እንዳለ እንደሚቀጥል ነው ፍንጭ የሰጡት። በአንፃሩ ደግሞ ከዚያ ቀድም ብሎ አንዳንድ ትላልቅ የምንላቸውን የመንግሥት ኩባንያዎች በከፊል ለመሸጥ ሃሳብ እንዳላቸው አሳውቀዋል። ይህ የሚያሳይህ በፊት ከነበረው ለየት ባለ መልኩ ከፈት በማድረግ፤ የመንግሥት ሚና ብቻ ከጎላበት ኢኮኖሚ የግሉም ዘርፍ የሚሳተፍበት ኢኮኖሚ ለመመሥረት ቢያንስ ሃሳብ እንዳላቸው ያሳያል ይላሉ ፕሮፌሰሩ። የመንግሥት ድርጅቶችን የመሸጥ ጉዳይ ግን አከራካሪነቱ እንደቀጠለ ነው፤ ሃገር መሸጥ ነው በሚሉና እንዲህ ካልሆነ አናድግም የሚል ሃሳብ በሚያነሱ መካከል። ለፕሮፌሰር አለማየሁ ግን ዋናው ጉዳይ ወዲህ ነው፤ መለየትና ማመቻቸት። ወደ ገበያ ተኮር ኢኮኖሚ የምንሄድበት ዋናው ምክንያት ውድድር ለማምጣት ነው፤ ውድድር ለማምጣት ደግሞ መወዳደሪያ ሜዳውን ማስተካከል አለብን። ውድድሩን የሚመራ፤ የሚቆጣጠር አካል ማደርጀት ያስፈልጋል። አለበለዚያ ዝም ብሎ ከመንግሥት ወደ ግል መሄድ፤ ሞኖፖሊውን ከመንግሥት ወደግል መቀየር ነው። የግል ሞኖፖል ደግሞ ተጠያቂነት የለበትም፤ ብሩን የት ያጥፋው የት አይታወቅም፤ የሞራል ኃላፊነትም የለበትም። ምሁሩ ምሳሌ ልስጥህ ይላሉ፤ ምሳሌ ልስጥህ፤ ኢትዮ ቴሌኮም በጣም ደካማ ነው፤ እናውቀዋለን። ሶማሊያ እንኳን ያለው የቴሌኮም አገልግሎት የተሻለ ነው። ኬንያማ አንደርስባቸውም። ስለዚህ እንደ ቴሌኮም ዓይነቱን ምን ማድረግ ነው በከፊል መሸጥ። ችሎታው ላላቸው፤ ቢቻል ደግሞ አፍሪቃዊ ለሆኑ ድርጅቶች፤ በዚያውም ቀጣናዊ ግንኙነቱን ማጠናከር። እንደዚህ አድርጎ ተወዳዳሪነቱን ማጎልበት። ይህንን ውድድር የሚቆጣጠር ሥርዓት መዘርጋት፤ ከዚያ ለውድድር መክፈት። እንዲህ ነው መሆን ያለበት። አሁን በሌላ በኩል ደግሞ ስትመጣ አየር መንገድ አለ። አየር መንገድ በእኔ እምነት እንኳን ሊሸጥ፤ ለመሸጥ መታሰብ ራሱ የለበትም። ምክንያቱም በጣም ትርፋማ የሆነ ድርጅት ነው። በዓለም አቀፍ ደረጃ በጣም ተወዳዳሪ የሆነ ድርጅት ነው፤ በጣም ያለው ንብረት ወደ ቢሊዮን ብር በላይ ነው፤ ዕዳው ቢሊዮን ገደማ ነው። ስለዚህ ንብረቱ በአያሌው ይበልጣል። በመንገደኛ የሚያገኘው ገቢ ቶፕ ሰባት ከምትላቸው የአሜሪካ አየር መንገዶች ይበልጣል። ይህ እንግዲህ ኢኮኖሚያዊ መከራከሪያ ነው፤ ወደ ባህላዊው ስትመጣ አየር መንገድ ቅርሳችን ነው፤ ዓለም ላይ ምንም ሳይሳካልን ሲቀር እንኳ አየር መንገዳችን ስኬታማ ነበር፤ ምልክታችን ነው። ፕራይቬታይዜሽን ለውድድር ነው ካልን፤ በትንሽ ዋጋ ህዝቡን ለማገልገል ነው የምንል ከሆነ አየር መንገድን መሸጥ አዋጭ አይደለም። እኔ እንደ ኢኮኖሚስትም እንደ ዜጋም አልቀበለውም። ምክረ ሃሳብ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ በርካታ ምሁራንና ታዋቂ ግለሰቦችን ያካተተ የህግ አማካሪ ያዋቀሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ መሰል ውሳኔ በምጣኔ ሃብቱ በኩል እንዲያሳልፉ መወትወት ከተጀመረ ውሎ አድሯል። እውን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ ያስፈልጋቸዋል ወይ የሚል ጥያቄ የሚያነሱም አልጠፉም። ምንም ጥያቄ የለውም ይላሉ ፕሮፌሰር አለማየሁ። ምንም ጥያቄ የለውም፤ አማካሪ ያስፈልጋቸዋል። ያደገ ሃገር ሆኖ ያለአማካሪ ያደገ እኔ አላውቅም። ከዚህም አንድ ደረጃ ፈቅ ማድረግ እችላለሁ። ያደገ ሃገር ሆኖ በቋንቋው ሳያስተምር ያደገ ሃገር እኔ አላውቅም። ቻይና ብትል ጃፓን፤ ጀርመን፣ አሜሪካ እኔ አስተማሪ ስለሆንኩ ተማሪዎቼን ሳያቸው ከትምህርቱ እኩል ቋንቋ ችግር ነው። እንኳን የኢኮኖሚ አማካሪ ይቅርና ማለቴ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሁሉን ነገር መሆን አይችሉም፤ ኢኮኖሚው ደግሞ የረቀቀ ነው። መዓት ፈርጆች አሉት። በእኔ ግምት ማንኛውም መሪ ያለኢኮኖሚ አማካሪ እሠራለሁ ካለ አልገባውም ማለት ነው። ከሩቅ ዘመድ የቅርብ ጎረቤት ጠቅላዩ ከተመረጡ ወዲህ የመጀመሪያ ካሏቸው ሥራዎች መካከል ወደጎረቤት ሃገራት ብቅ ብሎ ወዳጅነትን ማጠንከር ነበር። ጅቡቲ፣ ሱዳን፣ ኬንያ፣ ሶማሊያ ታሪካዊ የሆነው ከኤርትራ ጋር የተደረገው እርቀ ሰላም በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ዘመን ከተከወኑ መካከል እንደስማቸው አብይ ሆኖ የሚጠቀስ ነው። የኛ ፖለቲካ እንደምታውቀው በጣም እየጠበበ፤ እየጠበበ እየሄደ ወደ ጎሳ፤ ከጎሳ ደግሞ ቀጥሎ ወደ መንደር፤ ከመንደር ደግሞ ወደ ቀበሌ መሄዱ አይቀርም በዚሁ ከቀጠለ። ሊህቃን ፍላጎታቸውን ለሟሟላት ሰዎችን የሚያደራጁበት መንገድ ነው የሚፈልጉት። ብትፈልግ ሶሻሊዝምና ካፒታሊዝም ይልሃል፤ ብትፈልግ ቀይ ሽብር፣ ነጭ ሽብር ይልሃል፤ አማራ፣ ኦሮሞ፣ ትግሬ፣ ቤኒሻንጉል ይልሃል፤ ማደራጃ ነው የሚፈልጉት በእኔ እምነት። ቀጣናዊ የሆነው የኢኮኖሚ አስተሳሰብ ከእንደዚህ ዓይነት አናሳ ከሆኑ አስተሳሰቦች አውጥቶ በሰፊው እንድናይ ስለሚያደርገን ከፖለቲካ አንፃር ጥሩ መነፅር ነው ብዬ ነው የምገምተው። በፍትህ ተቋማት ላይ የለውጥ እርምጃ ይፋ ይሆናል ጠ ሚ ዐብይ አሁን ወደ ኤርትራ እንምጣ ነፃ የሆነ የህዝብ ፍሰት፤ ነፃ የሆነ የካፒታል ፍሰት፤ ነፃ የሆነ እንቅስቃሴ የመጨረሻው የዕድገት ደረጃ ነው። አውሮጳውያን ከ ዓመታት በላይ ነው ያ ጫፍ ለመድረስ የፈጀባቸው። በኢትዮጵያና በኤርትራ ጉዳይ ግን ባለፉት ጥቂት ወራት የሆነው የ ዓመቱን በአንድ ቀን እንደማድረግ ነው። የኔ ሪኮሜንዴሽን ምክር ምንድነው፤ ቆንጆ ነው ሃሳቡ፤ ህዝብን ከህዝብ ለማቀራረብ የሚደረገው፤ ነገር ግን ኤክስፐርቶች ባለሙያዎች ያስፈልጉናል። በዚህ መንገድ ነው የምንሄደው፤ በመርህ ደረጃ ሁላችንንም ተጠቃሚ የሚያደርግ፤ የሰላሙን ዘላቂነት የሚያረጋግጥ ሥርዓት ይህ ነው ብለው የሚመክሩ ኤክስፐርቶች ማዘጋጀት ነበረባቸው የሚል ሃሳብ ነው ያለኝ። እነ ዓለም ባንክ ይታመናሉ የዓለም ባንክ፣ የዓለም የገንዘብ ተቋም እና መሰል አበዳሪ ድርጅቶች ከኢትዮጵያ ጋር ያላቸው ግንኙነት ይህን ያህል የሻከረ የሚባል አይደለም። በቅርቡ የዓለም የገንዘብ ተቋም ኢትዮጵያ በሚቀጥለው የፈረንጆች ዓመት መልካም የሚባል ዕድገት ታስመዘግባለች የሚል ትንበያ ይዞ ብቅ ብሏል። የዓለም ባንክም ለወዳጄ ኢትዮጵያ ያለሆነ ዶላር አፈር ይብላው በሚል ቢሊዮን ዶላር ብድር ሰጥቷል። እኔ እነ ዓለም ባንክ ብድር ሲፈቅዱ ሃሳብ ነው የሚገባኝ። ለምን ብትለኝ፤ ከጀርባ የሆነ ነገር አለ ማለት ነው። እንጂ ዝም ብለው አይፈቅዱልህም። ወይ ፕራይቬታይዝ አድርግ ብለውሃል ወይ የሆነ ነገር ሽጥ ብለውሃል ማለት ነው። እነሱ የቆሙላቸው የምዕራብ ሃገር ድርጅቶች ከኋላ ሊገዙ ተሰልፈዋል ብዬ ነው የማስበው። ከአጠቃላይ የሃገር ውስጥ ምርታችን በመቶ ዕዳ ነው። ይህ አሁን ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ችግር አይደለም፤ የበፊቶቹ እንጂ፤ ቢሆንም ይህንን ዕዳ ወርሰውታል። ምሁሩ ሲቀጥሉ አሁን እንዴት ይፍቱት ነው ዋናው ቁም ነገር ይላሉ። እኔ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ብሆን፤ እግዚአብሔር አያድርገኝና ሳቅ ፤ ምንድነው የማደርገው፤ ምዕራብም ምስራቅም አልልም። ከኢትዮጵያ ጥቅም አንፃር ነገሮችን አይቼ ጠቃሚው ላይ ትኩረቴን አድርጌ ፖሊሲዬን በዛ ነበር የምቀርፀው። ምጣኔ ሃብቱን ማሳደጉ ይቅርብንና ሰላሙ ይቅደም የሚሉ ድምፆች መሰማት ከጀመሩ ውለው አድረዋል። ለፕሮፌሰር አለማየሁ እና መሰሎቻቸው ግን መፍትሄው ሁለቱን አንድ ላይ ማስኬድ ነው። ሁሉቱን አንድ ላይ ነው ማስኬድ ያለብን። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይን ያመጣው ወደሥልጣን ፖለቲካ ብቻ አይደለም፤ ኢኮኖሚውም እንጂ። ለምሳሌ ወጣት ሥራ አጦችን እንውሰዳቸው። ኦፊሻል ቁጥሩ በመቶ ሥራ አጥ ወጣቶች እንዳሉ ነው የሚያሳየን። እኔ ያደረግኩት ጥናት እንደሚያሳው በመቶ የሚሆኑ ወጣቶች ኢ መደበኛ በሚባለው ዘርፍ ውስጥ ነው ያሉት፤ ሥራ አጥነት ማለት በሌላ ቋንቋ። ስለዚህ ለዚህ ሥራ አጥ ወጣት ሥራ ካልሰጡት ሊነሳባቸው ይችላል። ፋንዳሜንታል መሠረታዊ ችግሩ ምንድነው ድህነት፣ ሥራ አጥነትና ፍትሃዊ ያልሆነ የገቢ ሥርጭት ነበር። ለኔ አብይን ካመጣው አብዮት ጀርባ ይሄ ጥያቄ አለ። ከላይ ያለው አይድዮሎጂ ላዕላይ መዋቅሩ ነው። ውስጡ ግን ይሄ ነው። ስለዚህ ከፖለቲካው እኩል ኧረ እንደውም በበለጠ ይህንን ችግር ለመፍታት መንገድ ካልጀመሩ እሳቸውም ላይ ይመጣል።
ኢትዮጵያ ከውጭ ምንዛሬ እጥረት አዙሪት እንዴት ትውጣ
ኤፕረል ማጋሪያ ምረጥ በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ ያላት መጠባበቂያ የውጭ ምንዛሬ ክምችት የሁለት ወር ከስድስት ቀን ፍላጎትን የሚሸፍን እንደሆነና ይህም ለመድሃኒትና ለነዳጅ የሚውል እንደሆነ ከጥቂት ቀናት በፊት ተዘግቧል። አገሪቱ የሁለት ወር ተኩል ብቻ መጠባበቂያ የውጭ ምንዛሬ ክምችት ነው ያላት ማለት ምን ማለት ነው ለኢኮኖሚ ኤክስፐርቱ ዶ ር አሰፋ አድማሴ ያነሳነው ጥያቄ ነበር። አገሪቱ በመደበኛ ሁኔታ ባለፉት ዓመታት ከሶስት ወር የሚበልጥ መጠባበቂያ የውጭ ምንዛሬ ክምችት ኖሯት አያውቅም። ያለው መጠባበቂያ የውጭ ምንዛሬ ክምችት ለሁለት ወር ብቻ የሚሆነው ማለት ያለውን አሟጠን እጃችንን አጣጥፈን እንቀመጣለን ማለት አይደለም በማለት በተጠቀሰው ሁለት ወር እና ጥቂት ቀናት ጊዜ ውስጥ ከውጭ በሚላክ ገንዘብ፣ በእርዳታ ፣ በብድርና በወጪ ንግድም የሚመጣ የውጭ ምንዛሬ ይኖራል ይላሉ። ከውጭ እቃዎችን ለማስገባት የሚውል መጠባበቂያ የውጭ ምንዛሬ ክምችት አስፈላጊ ቢሆንም አገሪቱ ለሁለት ወራትና ጥቂት ቀናት የሚሆን ነው ያላት ማለት የሚያሸብር ነገር እንዳልሆነ ያስረግጣሉ። በርግጥም ክምችቱ ትንሽ ነው ስጋትም ያሳድራል ነገር ግን በዚሁ አበቃ ማለት አይደለም ይላሉ። አገራት ምን ያህል ክምችት እንዲኖራቸው ይመከራል ምንም እንኳ በተፃፈ ህግ ባይሆንም እንደ አሰራር የአለም የገንዘብ ድርጅት አይ ኤም ኤፍ አገራ ከሶስት እስከ ስድስት ወር መጠባበቂያ የውጭ ምንዛሬ ክምችት እንዲኖራቸው ይመክራል። ያነጋገርናቸው ሌላው የኢኮኖሚ ኤክስፐርት ዶ ር እዮብ ተስፋዬ የሶስት ወር ክምችት በቂ ሊባል የሚችል ሲሆን ብዙ ጊዜ ችግሮች ሊከሰቱ የሚችሉት መጠባበቂያ የውጭ ምንዛሬ ከሶስት ወር በታች ሲሆን እንደሆነ ይገልፃሉ። እንደ ኢትዮጵያ ላሉ አገራት የሶስት ወር ክምችት መያዝ ጥሩ እንደሆነ ቢመከርም መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ከሶስት ወር ያነሰ መጠባበቂያ የውጭ ምንዛሬ ክምችት ይዞ መገኘትን የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ የተላመደው እንጂ እንግዳው አለመሆኑን ነው። በአስቸጋሪ፤ በመደበኛ ሁኔታም እውነታው ይህው ነው። ለሶስት ወር የተባለውም መሻሻል እንጂ ሁልጊዜ ሶስት ወር ሆኖ መቅረትም ግን የለበትም። የመጠባበቂያ የውጭ ምንዛሬ በደርግ መውደቂያ፣ በኢትዮጵያና ኤርትራ ጦርነት ወቅትም የአስር ቀን ነበር የሚሉት ዶ ር እዮብ የዛሬ ዓመት በተመሳሳይ ወቅት የመጠባበቂያ ክምችቱ የሶስት ሳምንት ብቻ እንደነበርም ያስታውሳሉ። እናም የዛሬው ክምችት ከዚያ እያለ እያለ ያደገ ነው። ከኤክስፖርት የሚገኘው ገቢ በጣም ውስን በመሆኑ ፣ ከውጭ ከሚላክ ገንዘብ የሚገኘው የውጭ ምንዛሬም የተሻሻለው በቅርብ በመሆኑና አሁንም ብዙው በጥቁር ገበያ የሚተላለፍ በመሆኑ ፣ ከአገልግሎት ሰጪ ዘርፉ የሚገኘው የውጭ ምንዛሬ የኢትዮጵያ አየር መንገድን ጨምሮ የተሻሻለው ገና በቅርቡ በመሆኑ የመጠባበቂያ ክምችቱ ሊያድግ እንዳልቻለም ያስረዳሉ። ነገር ግን የአሁኑን የአገሪቱ መጠባበቂያ የውጭ ምንዛሬ ክምችት አነስተኛ መሆንን የተለየ የሚያደርገው የውጭ እዳ ጫና የበረታበት ጊዜ ላይ መሆኑ እንደሆነ ይገልፃሉ። ስለዚህም በዚህ የእዳ ጫና ምክንያት መጠባበቂያው ሳይነካ ከውጭ ለሚገቡ እቃዎች የሚቀርብ የውጭ ምንዛሬም ከፍተኛ እጥረት አለ። ይህ ከዚህ ቀደምም ሞልቶም አያውቅም። የመይሳው ካሳ የልጅ ልጆች የመጠባበቂያ የውጭ ምንዛሬ ክምችት አገልግሎት ምንድን ነው በዓለም አቀፍ ገበያ ባልተጠበቀ መልኩ የነገሮች ዋጋ ሲንር ፤ ለምሳሌ የነዳጅ ዋጋ ሳይታሰብ ቢጨምር ወይም በአገራት መካከል በተፈጠረ ግጭት የእቃዎች ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ ሲጨምር የሚፈጠር ችግርን ለመቋቋም የሚውል ነው። ከዚህ በተጨማሪም ለኢንቨስተሮች መተማመኛም ነው። ኢንቨስተሮች መዋእለ ነዋያቸውን ለማፍሰስ ሲያስቡ የሚያዩት የመጀመሪያ ነገር የአገሪቱ መጠባበቂያ የውጭ ምንዛሬ ክምችት ምን ያህል ነው እንዲሁም የውጭ ምንዛሬ አያያዙ ምን ይመስላል የሚለውን እንደሆነ ዶ ር እዮብ ይናገራሉ። የውጭ ምንዛሬ ዋጋን በማስተካከል እረገድም ምን ይደረግ የሚለውን አቅጣጫ ጠቋሚም ነው። ለምሳሌ የዶላር ዋጋ ከፍ ሲል ገበያውን ለማስተካከል ይረዳል። ከውጭ ምንዛሬ እጥረት አዙሪት እንዴት ይወጣ አገሪቱን ለዓመታት እየተሽከረከረችበት ካለው የውጭ ምንዛሬ እጥረት ችግር ለመታደግ የወጪ ንግድ ላይ በርትቶ ከመስራት ውጪ ሌላ አማራጭ አለ ብለው እንደማያምኑ ዶ ር አሰፋ ይናገራሉ። መንግሥትም ብዙ ኢንዱስትሪ ፓርኮችን እየገነባ ያለው ለዚሁ ሲባል ቀጥተኛ የውጭ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ እንደሆነ ይጠቅሳሉ። ከዚህ አንፃር የአገሪቱ የወጪ ንግድ ያለበት ሁኔታ መፍትሄ ለመሆን ተስፋ የሚጣልበት ነው ወይ የሚለው ወሳኝ ጥያቄ ነው። መረጃዎች እንደሚያሳዩት ከወጪ ንግድ የሚገኘው ገቢ እየቀነሰ ፤ የወጪ ንግድን እንደ ዋነኛ ዘርፍ ያለመቁጠር አዝማሚያም እየተፈጠረ ነው። ጥቂት የማይባሉ በወጪ ንግድ ላይ የተሰማሩት ፈልገውት ሳይሆን ይልቁንም ለማስመጣት ስራቸው እንዲረዳቸው ብለው ነው። በአገሪቱ ሳይፈታ እየተሽከረከረ ያለው የውጭ ምንዛሬ እጥረትን ለመፍታት የዘላቂ ስትራቴጂ አስፈላጊነትን አፅንኦት የሚሰጡት ዶ ር እዮብ ፤ ለወጪ ንግድ እየተሰጠ ያለው ትኩረት ሊቀጥል ቢገባም የአቅጣጫ ለውጥ ያስፈልጋል ይላሉ። በዓለም አቀፍ ዋጋ መውረድ ከቡና ብዙ ማግኘት አልቻልንም የዚህ ዓመት አፈፃፀሙ ጥሩ አይደለም እያሉ ማለፍ ሳይሆን ይህ ባይሳካ ያንን እያሉ አማራጮችን ማስቀመጥ እንሚያስፈልግ ያሳስባሉ። እንደ ግብርና ፣ ንግድ፣ ኢንዱስትሪ እንዲሁም ማእድን ሚኒስቴር ያሉ የተለያዩ መስሪያቤቶች በተናጥል የወጪ ንግድን እናበረታታለን ይላሉ። ነገር ግን ይህ የተበታተነ አሰራርን ሰብስቦ አገሪቱ የተቀናጀ የወጪ ንግድ ስትራቴጂ እንዲኖራት ማድረግ ግድ ነው ይላሉ ዶ ር እዮብ። እንደ እሳቸው አስተያየት ከውጭ ከሚላክ ገንዘብ የውጭ ምንዛሬ ለማግኘትና ለመጠቀምም የሚያዋጣ አካሄድ መከተል አስፈላጊ ነው ይላሉ። ምክንያቱም ብዙዎች ፊታቸውን ያዞሩት ወደ ጥቁር ገበያው ነውና። ቱሪዝም ትኩረት ይደረግበት የሚሉት ሌላ ዘርፍ ሲሆን ተስፋ የተጣለበት ኢንዱስትሪ ፓርክስ እንደተባለለት ነው ወይ ብሎ መመርመር የሚያስፈልግም ይመስለኛል ሲሉ ያክላሉ። መንግሥት የውጭ ምንዛሬ ተመንን ገበያው እንዲወስን ማድረግን ቀጣይ አቅጣጫ አድርጎ ያስቀመጠ መሆኑን በተመለከተም በሚቀጥሉት ሁለትና ሶስት ዓመታትም የሚሳካ እንደማይመስላቸው ግምታቸውን ያስቀምጣሉ።
ቀኝ ዘመሙ እና አክራሪው ቦልሶናሮ የብራዚል ፕሬዝደንት ሆነው ተመረጡ
ኦክተውበር ቀኝ ዘመሙ ፕሬዝዳንታዊ ዕጩ ጃይር ቦልሶናሮ በጉጉት የተጠበቀውን የብራዚል ምርጫ ማሸነፍ ችለዋል። ቦልሶናሮ በመቶ ድምፅ በማምጣት ነው ዋነኛ ተቀናቃኛቸው የነበሩት የሰራተኞች ፓርቲው ፈርናንዶ ሃዳድን መርታት የቻሉት። ሙስናን ነቅዬ አጠፋለሁ፤ በሃገሩ የተስፋፋውን ወንጀልም እቀንሳለሁና ምረጡኝ ሲሉ ነበር ቦልሶናሮ ቅስቀሳ ሲያካሂዱ የሰነበቱት። የምርጫ ቅስቀሳ ሂደቱ በጣም ከፋፋይ እንደበር ብዙዎች የተስማሙበት ሲሆን ሁለቱም ወገኖች አጥፊ እየተባባሉ ሲወቃቀሱ ከርመዋል። ወግ አጥባቂው ሚሼል ቴሜር በሙስና ምክንያት ከሥልጣን በወረዱት ዴልማ ሩሴፍ ምትክ ብራዚልን ላለፉት ሁለት ዓመታት ቢያስተዳድሩም ህዝቡ ዓይንዎትን ለአፈር ብሏቸዋል። ከጠቅላላ ህዝብ በመቶ ብቻ ተወዳጅነት ያገኙት ቴሜር አሁን ሥልጣናቸውን በሰላማዊ መንገድ ማስረከብ ይጠበቅባቸዋል። ተቀናቃኛቸውን በ በመቶ ድምፅ የረቱት ቦልሶናሮ ለሃገራቸው ህዝብ ለውጥ ለማምጣት አማልክትን ጠርተው ምለዋል። ዲሞክራሲን ጠብቄ አስጠብቃለሁ፤ እውነት እውነት እላችኋለሁ የሃገራችንን ዕጣ ፈንታ አብረን እንቀይራለን ሲሉም ቃላቸውን ሰጥዋል አዲሱ መሪ። የአዲሱ ተመራጭ ቦልሶናሮ ተቃዋሚዎች ግን ሰውየው ያለፈ ሕይወታቸው ከውትድርና ጋር የተያያዘ ስለሆነ ረግጥህ ግዛ እንጂ ዲሞክራሲ አያውቁም ሲሉ ይወርፏቸዋል። ቦልሶናሮ በምርጫ ቅስቀሳ ወቅት ያሰሟቸው የፆታ ምልክታን፣ ሴቶችን እንዲሁም ዘርን አስመልክተው የሰጧቸው አጫቃጫቂ አስተያየቶችም ያሳሰቧቸው አልጠፉም። ዋነኛው ተቀናቃኝ ፈርናንዶ ሃዳድ በበኩላቸው ድምፁን ለእኔ የሰጠው ሕዝብ አደራ አለብኝ ብለዋል፤ በተቃዋሚ ፖለቲከኛነት እንደሚቀጥሉ ፍንጭ በመስጠት። ብራዚል በፈረንጆቹ ባሉት ዓመታት ያክል በግራ ዘመም የሰራተኞች ፓርቲ ስትመራ ብትቆይም አሁን ግን ወደ ቀኝ ዘማለች።
መምህር ሥዩም ቦጋለ፡ የተማሪዎቻቸውን ገላና ልብስ የሚያጥቡት መምህር
ፌብሩወሪ ማጋሪያ ምረጥ ስድስት የውሃ መቅጃ ጀሪካንና ሁለት ሳፋ ጥሽት አላቸው። እስካሁን በግምት ከ በላይ ህጻናት ተማሪዎችን ገላ አጥበዋል። በአማካይ አንድን ተማሪ ለማጠብ ደቂቃ ይፈጅባቸዋል። በሳምንት ሁለት ቀናት ማለትም ረቡዕና አርብ የ ተማሪዎችን ልብስ ያጥባሉ። የተማሪዎቻቸው ንፅህና ተጠብቆና በትምህርታቸው ልቀው ማየት ህልማቸው ነው። ካላቸው አነስተኛ ደመወዝ አንድ ሦስተኛውን ለዚህ በጎ ስራቸው ለማዋል በጅተውታል። የሙያውን ፈተና ለመጋፈጥ ከከተማ ርቆ የሄደው ሐኪም የአገሬው ሰው ምን ሀጢያት ቢሰራ ነው፤ እንዲህ ያለ እዳው ጎንበስ ቀና የሚለው እያሉ ያጉመተምቱ ነበር ነገሩ እስከሚገባቸው ነው ታዲያ። ከገባቸው በኋላማ አንተ እንትፍ እንትፍ ብለህ ከመረቅካቸውም ይበቃል ሲሉ ያሞግሷቸዋል። የሚያውቋቸው ጋሸ እያሉ ነው የሚጠሯቸው። ሲበዛ ያከብሯቸዋል። የእርሳቸውን ነገር ለማውራትም ይከብዳል ይላሉ። እንዲያው በአጭሩ ለትውልድ ነው የተፈጠሩት ሲሉ ይገልጿቸዋል። ተማሪዎቻቸው ከአንድ ክፍል ወደ ሌላ ክፍል ቢሸጋገሩም እርሳቸው የሚያስተምሩበትን አንደኛ ክፍል ላለመልቀቅ ሲሉ ምነው እንደ ሊቁ ያሬድ ሰባት ጊዜ በወደቅኩ ብለው ይመኛሉ አሉ። እኝህ ሰው ማን ናቸው መምህር ሥዩም ቦጋለ የእንግሊዘኛ መምህር ሲሆኑ በ ዓ ም ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ ተመርቀው በመምህርነት እያገለገሉ ይገኛሉ። ከበፊት ጀምሮም በቤተሰብ ውስጥ የሚፈጠሩ ችግሮችን የማየትና ለዚያም መፍትሔ የማፈላለግ ፍላጎት እንደነበራቸው ይናገራሉ። በእርግጥ የእርሳቸው አስተዳደግም የተንደላቀቀ ባለመሆኑ ለችግር ብዙም ሩቅ አይደሉም። እንዲህ ዓይነት የበጎ ሥራን ማከናወን የጀመሩት አባታቸው በ ዓመት እድሜያቸው በሞት ከተለዩ በኋላ ከእርሳቸው በታች ያሉ እህትና ወንድማቸውን የማስተማር ኃላፊነት ከተረከቡበት ጊዜ አንስቶ ነው። እነርሱን በሚፈለገው እውቀትና የሥነ ምግባር ደረጃ ለማብቃት የራሴን ሕይወት ከፍያለሁ፤ የልፋቴን ዋጋም በእነርሱ ማየት ችያለሁ ይላሉ። በአሁኑ ሰዓት ደካማ እናታቸውን እየረዱ ይኖራሉ። የቤት ውስጥ የሚባል ማንኛውንም ሥራ ያከናውናሉ። ምንም የሚቀራቸው የለም። ይሄው ልማድም ጎልብቶ ወደ ሙያቸው እንደመጣ ያስረዳሉ መምህር ሥዩም። የሃምዛ ሃሚድ ገመድ አልባ የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ በሚያስተምሩበት አካባቢ ወላጆች እድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ቤት እንዲልኩ ለመቀስቀስ ጋራና ሸንተረሩን ያቋርጣሉ። ሰለቸኝ ደከመኝ አይሉም። ሠርግ፣ ለቅሶ፣ እድር ላይ የአገሬውን ሰው መስለው ይሳተፋሉ። የአገሬው ሰው ቢሆኑም ቀለም ቀምሻለሁ ብለው ግን እራሳቸውን አያመፃድቁም። ከዚያም የማትለያቸውን ማስታወሻ ደብተር አውጥተው የሚሰሟቸውን ቤተሰባዊ ችግሮች እየጠየቁ ይመዘግባሉ። ሁሉም ሰው ችግራችንን ይጠይቀናል፤ ግን ከንፈር ከመምጠጥ ባለፈ መፍትሔ የሰጠን የለም የሚል ተደጋጋሚ መልስ ነው የሚያገኙት። አንድ ቀን አንዲት ተማሪ ልብሴ ቀዳዳ በመሆኑ፤ የተቀደደ ልብስ ለብሼ ትምህርት ቤት መምጣት አልፈልግም ስትል ትምህርት ቤት ላለመግባቷ መልስ የሰጠቻቸውን ያስታውሳሉ። በወቅቱ የሰሙት ነገር ከእንቅልፋቸው ያባንናቸው ነበር። ይህን ስሜታቸውን ለማስታገስ ቢያንስ ሁለት ተማሪ መርዳት እንዳለባቸው ከራሳቸው ጋር ተነጋግረው ወሰኑ። ልብስ አሰፍተው፣ የትምህርት ቁሳቁስ በሚችሉት አሟሉላት። እርሷም አላሳፈረቻቸውም። ከክፍሏ ቀዳሚ በመሆን ትምህርቷን እንዳጠናቀቀችና እርሳቸው እንደሚሉት ይህች ልጅ በምህንድስና ተመርቃ ሥራ ላይ ትገኛለች። የእርሷ ለስኬት መብቃት ትውልድ እየቀጨጨና እየጠፋ ያለው በእኛ ምክንያት ነው ሲሉ ጣታቸውን ወደ የቀለም አባቶች እንዲቀስሩ ምክንያት ሆናቸው። ችግሩ ያለው ከትውልዱ ሳይሆን ከቀራፂው መሆኑን አመኑ። ለዚሁ ጥያቄ ምላሽ ለማግኘት ረዳት የሌላቸውንና የአቅመ ደካማ ልጆችን ንፅህና መጠበቅ እንዲሁም የትምህርት ጥራት የበጎ ሥራቸው ዋና ማጠንጠኛቸው ሆነ። ይህ ብቻም አይደለም። ቀደም ብሎ የ ኛ እና የ ኛ ክፍል የእንግሊዘኛ አስተማሪ በነበሩበት ጊዜ ተማሪዎቹ እና የእንግሊዝኛ ፊደል መለየት ሲያዳግታቸው ያዩት መምህር ሥዩም እነዚህ ተማሪዎች እዚህ የደረሱት በየት ተንሳፈው ቢመጡ ነው ምን ዓይነት መምህር ቢያስተምራቸው ነው የሚለው የዘወትር ጥያቄያቸው ነበር። ስለሆነም እንዲህ ዓይነት ትውልድ እንዴት እናፈራለን ሲሉ በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር፣ ፋግታ ለኮማ ወረዳ ትምህርት ፅ ቤት አቤት አሉ። ለዚህም መፍትሔ ይሆን ዘንድ ከደረጃቸው ዝቅ ብለው አንደኛ ክፍል ማስተማር እንደሚፈልጉ ጥያቄ አቀረቡ። ይሁን እንጂ እንዳሰቡት ቀላል አልሆነላቸውም። አንደኛ ክፍልን ለማስተማር መሰልጠን ያለብዎትን ሥልጠና አላገኙም የሚል ጥያቄ ሞገታቸው። የሚያበቃኝን ሥልጠና ስጡኝ ሲሉ በአቋማቸው ጸኑ፡፡ የኋላ ኋላ ተሳክቶላቸው አንደኛ ክፍልን ብቻ ማስተማር ጀመሩ። የእርሳቸው ሥራ ከታች ተማሪዎችን አብቅቶ ለቀጣዩ መምህር ማቀበል ብቻ ሆነ። ለካ ትውልድ እየቀጨጨና እየጠፋ ያለው በእኛ ምክንያት ነው፤ ችግሩ ከትውልዱ ሳይሆን ከቀራፂው ነው። ሥዩም ቦጋለ መምህር በሥራ ተወጥሮ ለሚውል አርሶ አደር፣ ውሃ በቀላሉ በማይገኝበት የገጠር አካባቢ፤ ምን አልባትም ውሃ ለመቅዳት በእግር ብዙ ርቀት መጓዝን በሚጠይቅ የኑሮ ሁኔታ አልያም ምርኩዝ ይዞም ቢሆን ውሃ ከወንዝ መቅዳት ለማይሆንለት ቤተሰብ፤ የራስንም ሆነ የልጆችን ንጽህና መጠበቅ ዘበት ሊሆን ይችላል። ይህ ሌላኛው የሚያሳስባቸው ጉዳይ ነው ለመምህሩ። ከዚህ በኋላ ነበር ሳሙናዎችንና የማጠቢያ ሳፋ ጥሽት በመግዛት የተማሪዎችን ንፅህና ለመጠበቅ ሲሉ ልብሳቸውንና ገላቸውን ማጠብ የጀመሩት። መምህር ሥዩም በዘንድሮው ዓመት በሁለት ፈረቃ ተማሪዎችን ያስተምራሉ። ማስተማር ብቻ ሳይሆን ንፅህናቸውን መጠበቅ፣ ዐይናቸው በትራኮማ በሽታ እንዳይጠቃ ፊታቸውን ማጠብ፣ በሳምንት ሁለት ጊዜ ልብሳቸውን ማጠብና ገላቸውን ማጠብ ለራሳቸው የሰጡት ኃላፊነት ነው። ዘወትር ሀሙስ ጠዋት ሁሉንም ተማሪዎቻቸውን ተቀያሪ ልብስ በመያዝ ከትምህርት ሰዓታቸው ቀደም ብለው እንዲመጡ ይጠሯቸዋል። ምንም እንኳን በትምህርት ቤቱ በእጅ እየተወዘወዘ የሚፈስ ቧንቧ ቢኖርም ብዙ ስለሚያለፋቸው ከእርሱ ጋር መታገል አይፈልጉም። ከትምህርት ቤቱ ሜትር ርቀት ላይ ኩልል እያለች የምትፈስ ንፁህ የመስኖ ውሃን መጠቀምን ይመርጣሉ። ከዚያም ባሏቸው ጀሪካኖች ውሃ በመቅዳት ለዚሁ አገልግሎት ብለው በገዙት ማጠቢያ ሳፋ ለሴት ተማሪዎቹ ቅድሚያ በመስጠት ገላቸውን በየተራ ያጥቧቸዋል። ለዚህ ተግባራቸው የአሸዋ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር የሆኑት አቶ ያረጋል ካሳሁን ምስክር ናቸው። ርዕሰ መምህር አቶ ያረጋል በትምህርት ቤቱ መስራት ከጀመሩ አራት ዓመታትን አስቆጥረዋል። ምንም እንኳን መምህር ሥዩም ይህንን ድርጊታቸውን ቀደም ብለው የጀመሩት ቢሆንም በቆዩባቸው አራት ዓመታት ጊዜ ውስጥ ሥራቸውን በቅርብ ሆነው እንደሚከታተሉ ይናገራሉ። ከትምህርት ቤቱ ድጋፍ እንዳናደርግላቸው አቅም ባለመኖሩ፤ በዚህ ዓመት ለሳሙና መግዣ እንኳን ቢውል ብለን ብር ብቻ ድጋፍ አድርገንላቸዋል ይላሉ። የ ዓመቷ የህክምና ዶክተርና ኢንጅነር ዕልልታ ጉዞ አቶ ያረጋል እንደሚሉት የመምህር ሥዩም ድርጊት በሌሎች መምህራን ላይም መነሳሳትን ፈጥሯል። በዚህም ምክንያት ትምህርት ቤቱ በትምህርት አሰጣጥ በወረዳው ካሉ የተሻለ ሆኖ መገኘት ችሏል። በወረዳው በተካሄዱ የተለያዩ የትምህርት ቤቶች የቀለም ውድድርም ማሸነፍ ለመቻላቸው የእርሳቸውን አስተዋፅኦ ያነሳሉ። በእርሳቸው ክፍል የሚያቋርጥ ተማሪ የለም፤ ሁሉም የዓመቱን ትምህርት ያጠናቅቃሉ፤ ወላጆችም ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ቤት የመላክ ፍላጎት አላቸው ሲሉ ያክላሉ። ከተማሪዎቹ ወላጆች የሚያገኙት ግብረ መልስ ምን እንደሆነ የጠየቅናቸው ርዕሰ መምህሩ አስተያየቱ አዎንታዊ እንደሆነና እንደ አባት ሙሉ እምነት እንደጣሉባቸው ያስረዳሉ። መምህር ሥዩም ይህን በጎ ተግባር ከጀመሩ ከ ዓመታት በላይ እንደሚሆናቸው የሚናገሩት አቶ ያረጋል ሁሉም የትምህርት ቤቱ ተማሪዎች በእርሳቸው የእንክብካቤ እጅ ስለሚያልፉ ከሁለተኛ ክፍል በላይ ያሉ ተማሪዎችም ሌላ ቅናት አያድርባቸውም። እንዲያውም መስከረም ሲመጣ ወደ ኛ ክፍል ያለፉ ተማሪዎች እርሳቸውን ጥለው ለመሄድ ይቸገራሉ፤ ህፃናትም ስለሆኑ ሁልጊዜ አንደኛ ክፍል ቢማሩ ደስታቸው ነው ለእርሳቸው ሲሉ በማለት የትምህርት ቤቱ ተማሪዎች ለእርሳቸው ያላቸውን አክብሮት ይገልፃሉ። በተለይ ተማሪዎችን በትምህርት ለማብቃት የሚከተሉትን ሥነ ዘዴ ለማየት ከተለያዩ ትምህርት ቤቶች ጎብኝዎችም እንደሚመጡ ያስረዳሉ። ፈቃዱ እጅጉ አዲስ አበባ በመንግሥት ሥራ ላይ የሚገኝ ሲሆን እርሳቸውን በቅርበት ያውቃቸዋል። ለእርሱ ባይደርሱም ታናናሾቹን ያስተማሯቸው መምህር ሥዩም ናቸው። ሙያውን ያከብራሉ፤ ደግነታቸው የበዛ ነው ይላል። በአካባቢው ተወዳጅ የሆኑ ሰው እንደሆኑ ይመሰክራል። የተቸገረን በመርዳት እንደሚታወቁ ይናገራል። አንድ ተማሪ ቸገረን ሲል ለምን ስዩምን አትጠይቁም ይባል እንደነበር ያስታውሳል። መምህር ሥዩም በዚህ በጎ ሥራቸው የተለያዩ ሽልማቶች የተበረከተላቸው ሲሆን በ ዓ ም በተካሄደው ኛው የበጎ ሰው ሽልማት በመምህርነት ዘርፍ እጩ ሆነው ተመርጠዋል። የዋንጫና የገንዘብ ሽልማትም ተበርክቶላቸዋል። በወረዳና በፌዴራል ደረጃ ሜዳሊያና የተለያዩ የምስክር ወረቀቶችን አግኝተዋል። ተያያዥ ርዕሶች
ታዋቂ ኢትዮጵያዊያን አርቲስቶች ለመዋብ ምን ያህል ይከፍላሉ
ፌብሩወሪ አጭር የምስል መግለጫ ፍቅር መዋቢያና ዮሐንስ ሲስተርስ ዲዛይን ኢትዮጵያ ውስጥ ታዋቂ አርቲስቶችን በትልልቅ መድረኮች እና ፕሮግራሞች ከማየት ባለፈ፤ በማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው አማካይነት የአኗኗር ዘይቤያቸዉን በተለይም አለባበሳቸዉንና መዋቢያ መንገዳቸዉን መመልከት ተለምዷል። አርቲስቶች ወደ ፋሽን ኢንዱስትሪዉ እንዲያማትሩ ከሚያደርጓቸው ምክንያቶች መካከል የፊልም ሠሪዎች የሽልማት ፕሮግራሞች፣ ቃለ መጠይቆች፣ የአልበም ወይም የፊልም ምርቃቶችን እና የማህበራዊ ሚዲያ የፎቶ ስብስቦች ይጠቀሳሉ። አጭር የምስል መግለጫ የፍቅር ዲዛይን ድምጻዊት ፀደንያ ገብረማርቆስ ለአለባበስ እና አቀራረብ የሚሰጠውን ትኩረት ስትገልፅ፣ ከማቀርበዉ ሙዚቃ ባሻገር ለመታየትም መዘጋጀት አለብኝ፤ ታዋቂ ስትሆኚ ደግሞ ሰዎች አንቺን ለማየት ይጓጓሉ፤ ዘንጠሽ እንድትወጪ ይጠብቃሉ ትላለች። በፍቅረኞች ቀን የፍቅር ስጦታ ለሴት ተማሪዎች ብዙዎቹ አርቲስቶች በትልልቅ ፕሮግራሞች ላይ ለልብሶቻቸዉ አይከፍሉም። ለምን ቢከፍሉ ኖሮ ምን ያህል ገንዘብ ያወጡ ነበር የፋሽን ዘርፉ ገና ታዳጊ ስለሆነ አርቲስቶችን የምንጠቀማቸዉ እንደ ማስተዋወቂያ ነዉ። እነሱ አንድን ልብስ ከለበሱት በኋላ ብዙ ሰዎች ልብሱን ያዛሉ በማለት ዲዛይነር ዮርዳኖስ አበራ ትናገራለች። አጭር የምስል መግለጫ እንቁ ዲዛይን ዲዛይነር ሊሊ የዮሃንስ ሲስተርስ ዲዛይን መስራች እንደምትናገረው፤ ለተለያዩ ፕሮግራሞች የሚዘጋጁ የሴት አርቲስቶች አልባሳት በትንሹ ከ ብር ጀምሮ ይቀርባሉ። ከፍ እያለ ሲመጣ ከ እስከ ብርም ሊደርስ ይችላል። የወንዶች አልባሳት ዋጋ ከሴቶች ጋር ሲወዳደር ሰማይ እና መሬት ነዉ በማለት አክላም ታስረዳለች። ብዙ ጊዜ ባይሆንም ለሠርግ የወንድ ልብስ ለወራት ዲዛይን ተደርጎ በጣም ቢበዛ ከ እስከ ብር ያወጣል። ዲዛይነር እንቁጣጣሽ ክብረት የእንቁ ዲዛይን መስራች እኔ ዲዛይን ያደረኳቸውን ልብሶች አርቲስቶችን ማልበስ አንዱ ስኬታማ የሆነ የማስታቂያ መንገዴ ነው ትላለች። የፋሽን ዘርፉ ቅድሚያ የሚሰጠው ለሴቶች ነው በሚል ቅሬታ የሚያቀርቡ ወንዶች እንዳሉም ትገልጻለች። አጭር የምስል መግለጫ ዮርዲ ዲዛይን የማርዜል ሜካፕ ባለቤት የማሪያምወርቅ አለማየሁ ስለ ፊት መዋቢያ ዋጋ ስትገልጽ፣ ዛሬ ዛሬ የፊት መዋቢያ በፋሽን ዘርፉ መታወቅ ጀምሯል። ብዙዎቹ ታዋቂ ግለሰቦች ዝግጅት ሲኖራቸው ለመዋብ ይመጣሉ ትላለች። ብዙዎቹ አርቲስቶች ሲዋቡ ተፈጥሯዊ ዉበትን የሚያጎላ የፊት መዋቢያ እንደሚጠይቁ የምትናገረው የማርያምወርቅ ብዙ ኢትዮጵያዊያን የተጋነነ የፊት መዋቢያ አይወዱም በማለት ትገልፃለች።
የመንገድ አቅጣጫ እንዳይጠፋብን የሚረዱ አንዳንድ ነጥቦች
ኦክተውበር ማጋሪያ ምረጥ ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ለመሄድ አቅጣጫ መለየት ያስቸግሮታል ወይስ ጠፍቼ ይሆን ብለው እራስዎን በተደጋጋሚ ይጠይቃሉ እንግዲያውስ እነዚህ ምክሮች ይጠቅሞት ይሆናል። በዝምታ የምትጠማ ከተማ ሐረር ጉዞዎን ቀደም ብለው ያስቡት መሄድ የሚፈልጉበት ሃገር ወይም ማንኛውም ቦታ ከመሄድዎ በፊት የመንገዶቹን ምስሎች ማግኘት ከቻሉ በደንብ ይመልከቷቸው። እራስዎን በእነዚያ መንገዶች ላይ ሲንሸራሸሩ በጭንቅላትዎ ለመሳል ይሞክሩ። ዘና ይበሉ ጠፋሁ አልጠፋሁ እያሉ የሚጨነቁ ከሆነ ተፈጥሯዊ የሆነውን አቅጣጫ የመለየት ችሎታዎን ያጠፋዋል። ጉዞ ከመጀመርዎ በፊት ቀድመው መዘጋጀትዎ ይህንን ጭንቀት ለመቀነስ ይረዳዎታል። ትኩረት ይስጡ ጉዞ በሚያደርጉ ጊዜ ስልክ የሚያወሩ ከሆነ፣ የጽሁፍ መልዕክት የሚላላኩ ከሆነ አልያም ስለሌላ ነገር የሚያስቡ ከሆነ፤ አካባቢዎን ለማስተዋል ይቸገራሉ። ሙሉ ትኩረትዎን በአንድ ሥራ ላይ ብቻ ያድርጉ። ይሄ ደግሞ በጉዞ ወቅት ትኩረትዎ አካባቢዎ ላይ ብቻ ይሆናል ማለት ነው። የተለዩ ምልክቶች ይፈልጉ እርሶ ከሚያውቁት ነገር ጋር የሚመሳሰል ወይም ለየት ብሎ የሚታይ ነገር በአካባቢዎ ይፈልጉ። በትልቅ ከተማ ውስጥ ከሆነ ያሉት በአካባቢው በጣም ትልቁን ህንጻ ለይተው በምልክትነት ይያዙት። እያንዳንዱ እንቅስቃሴዎን ከህንጻው አንጻር ያድርጉት። በሥራ ቃለ መጠይቅ ወቅት ልንላቸው የማይገቡ ነጥቦች ወደ ኋላ ይመልከቱ ብዙ ጊዜ ሰዎች ትኩረታቸውን የሚያደርጉት ከፊታቸው ያሉት ነገሮች ላይ ብቻ ነው። ነገር ግን ወደ ኋላ መመልከት መግቢያና መውጫዎን ለመለየት ይረዳዎታል። ወደ ኋላ መመልከት የጥሩ አቅጣጫ አዋቂዎች መገለጫ ነው ተብሏል። በተለይ ደግሞ በተመሳሳይ መንገድ የሚመለሱ ከሆነ ወደ ኋላ መመልከት እጅግ ጠቃሚ ነው። ትውስታዎን ከቦታዎች ጋር ያዛምዱ ይሄ ዘዴ የሄዱባቸውን ቦታዎች በትክክል ለማስታወስ እጅግ ጠቃሚ ነው። በተንቀሳቀሱባቸው የተለያዩ ቦታዎች የሰሟቸው ዘፈኖች ቦታዎቹን በትክክል ለማስታወስ እንደሚረዱ ጥናቶች ያሳያሉ። በተለይ ደግሞ በሄዱበት መንገድ የሚመለሱ ከሆነ ሙዚቃ ጥቅም ይኖረዋል። ማስታወሻ ምስል ያስቀሩ የጎበኟቸውን ቦታዎች ደግመው ለማየት የሚያስቡ ከሆነ በእያንዳንዱ ቦታ ማስታወሻ ምስሎችን ያስቀሩ። ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከተንቀሳቃሽ ምስል በተሻለ መልኩ ምስል ማንሳት አቅጣጫዎችን ለመለየት ይረዳል። ጉዞዎትን መለስ ብለው ያስቡት ጉዞዎን ካጠናቀቁ በኋላ መለስ ብሎ ማሰብ የማስታወስ ችሎታዎን ለመጨመር ይረዳል። ከላይ የተጠቀሱትን ነገሮች ሁሉ ካደረጉ በኋላ አሁንም የማስታወስ ችሎታዎ ካላስተማመንዎት ዘመነኛ ስልክዎን በመጠቀም መግቢያ መውጫዎን ማየት ይችላሉ። መልካም መንገድ
ሞባይልዎ ላይ ችግር የሚያስከትሉ መተግበሪያዎች የትኞቹ ናቸው
ኦክተውበር ማጋሪያ ምረጥ መቼስ በዚህ ወቅት ጫኑኝ የማይል የስልክ መተግበሪያ የለም። ዓለም ራሷ የስልክ መተግበሪያዎች ውስጥ ተከናንባ እየገባች ይመስላል። የደም ግፊት መጠንን ከሚለኩት ጀምሮ ቋንቋ መማሪያዎች፣ ቀን መቁጠሪያዎች፣ ቁርስ ምሳ ማዘዣዎች፣ ታክሲ መጥሪያዎች፣ ባንክ ሂሳብ ማንቀሳቀሻዎች፤ ብቻ የሌለ ዓይነት የስልክ መተግበሪያ የለም። ፈተናው ሐሰተኛውን ከእውነተኛው መለየት ነው። በዚህ በኩል እኛ እንርዳዎት የሚከተሉት ሦስት የስልክ መተግበሪያዎችን ጫኑ ማለት መከራን ስልክዎ ላይ ጫኑ እንደማለት ነው። ስልክዎን ለጤና መቃወስ የሚያጋልጡ ሐሰተኛ መተግበሪያዎች የሚከተሉት ናቸው። የባትሪ ዕድሜን እናራዝማለን የሚሉ የሞባይል ባትሪ እንደ ቋንቋ ነው፤ ይወለዳል፣ ያድጋል ይሞታል። ልዩነቱ በምን ፍጥነት ይሞታል የሚለው ነው። በዚህ ረገድ የባትሪው ኦሪጅናልነትና የአገልግሎት ዘመን ቁልፍ ጉዳይ ነው። አንዳንድ ጊዜ ባትሪ ቶሎ እየሞተ ሲያስቸግር ያነጫንጫል። በዚህ ጊዜ የባትሪዎን ዕድሜ ላራዝምልዎ የሚል መተግበሪያ ሲመጣ ያጓጓል። ጫኑኝ ጫኑኝ ይላል። አይቸኩሉ የቴክኖሎጂ ጋዜጠኛ የሆነው ኤሪክ ሄርማን የባትሪ ዕድሜን የሚያቆይ ምንም ዓይነት መተግበሪያ የለም ይላል። የስልክዎን ባትሪን ለረዥም ጊዜ ለመጠቀም ይልቅ የባትሪ ዕድሜን ለማራዘም መፍትሄው ብዙ ዳታ የሚያሟጥጡ መተግበሪያዎችን ለጊዜው ዝም ማሰኘት ነው። እምብዛምም የማያስፈልጉ መተግበሪያዎች ከጀርባ ሆነው ባትሪን ይመዘምዛሉ። የስልክዎ የብርሃን ድምቀት፣ የኢንተርኔት ዳታ፣ የዋይ ፋይ ማብሪያ ማጥፊያ ባትሪን ይመገባሉ ቢባል ማጋነን አይሆንም። ስልክዎን ናይት ሞድ ወይም ባትሪ ቆጥብ የሚለው ማዘዣ ላይ ያድርጉት። ሌላው መፍትሄ ባትሪ ኮንፊገሬሽን ላይ ገብቶ የባትሪን እድሜ እየበሉ ያሉትን ዝርዝሮች ማየትና ያንን ለይቶ ዝም ማሰኘት ነው። ስልክዎን እናጸዳለን የሚሉ መተግበሪያዎች ስልክዎትን እናጸዳለን የሚሉ መተግበሪያዎች በአመዛኙ ውሸት ናቸው። እንዲያውም ለቫይረስ ያጋልጣሉ። ክሊን ማስትር የሚባለው መተግበሪያ ዋንኛው ነው። ስፔናዊው የቴክኖሎጂ አዋቂ ጆስ ጋርሺያ እንደሚለው ክሊን ማስተር የተባለው መተግበሪያ የስልክን ፍጥነት ይቀንሳል፣ የራሱን ገበያ ለማድመቅም ብዙ መተግበሪያዎችን እንድንጭን ያባብለናል። አጭር የምስል መግለጫ የሞባይል ስልክን ፀሐይ ላይ አለመተው ስልክዎ ትኩሳት ከተሰማው ችግር አለ ማለት ነው። የስልክ ትኩሳት በተለያየ ምክንያት ሊከሰት ይችላል። ለረዥም ሰዓት ለፀሐይ ብርሃን ከተጋለጠ፤ በቫይረስ ከተጠቃ፤ ወይም ደግሞ ጤናማ ያልሆነ ባትሪ ከተገጠመለት አልያም ደግሞ ያለ ዕረፍት ለብዙ ሰዓታት አገልግሎት ላይ ከዋለ ስልክ እንደ ብረት ምጣድ ይግላል። ይህን ችግር እንቀርፋለን የሚሉ የስልክ መተግበሪያዎች ሐሰት ናቸው። መፍትሄም አያመጡም። እንዲያውም ትኩሳቱን ያብሱበታል። ስልክዎ በአዲስ መንፈስ እንዲሰራ ከፈለጉ አጥፍተው ያሳርፉት። ለስልክዎ ጠቅላላ ጤና የሚከተሉትን ያስታውሱ መተግበሪያዎችን ስልክዎ ላይ ሲጭኑ ምንነታቸው ከተረጋገጠላቸው ሁነኛ የስልክ መደብሮች ብቻ ያውርዱ። አፕል ስቶር እና ጉግል ስቶር የታወቁት ናቸው። የፋይል ስማቸው በኤፒኬ ፊደል እንደሚጨርስ ከሚታዩ መተግበሪያዎች ይጠንቀቁ ራሳቸውን ተአምራዊ ሥራ እንሠራለን እያሉ ከሚያሞካሹ መተግበሪያዎች ይጠንቀቁ ስልክዎትን በየጊዜው አፕዴት በማድረግ ያድሱ ተያያዥ ርዕሶች
በሥራ ቃለ መጠይቅ ወቅት ልንላቸው የማይገቡ ነጥቦች
ኦክተውበር ማጋሪያ ምረጥ በሥራ ቃለ መጠይቅ ወቅት ያልተጠበቁ ነገሮች ይፈጠራሉ። ለምሳሌ መቼ እረፍት እንደሚወጡ የሚጠይቁ፣ ስልክ የሚያናግሩ፣ ስለቀድሞ አለቃቸው መጥፎ ነገር የሚያወሩ እና ሌሎችም እነዚህ ነገሮች ብዙ ሲሆኑ የማይገባ ነገር በመናገርም ሥራውን የማጣት ዕጣም ይገጥማል። በሥራ ቃለ መጠይቅ ወቅት ልንናገሯቸው የማይገቡ ነገሮችን ከቅጥር ባለሙያዎች ጋር በመነጋገር እንደሚከተለው ቀርበዋል። አለቃዬ ብቁ አይደለም ባለሙያዎች በዚህ ሃሳብ ይስማማሉ። የቀድሞ አለቃዎትን የሚያጣጥል ነገር የሚያወሩ ከሆነ ቀጣይ አለቃዎን ስላለማጣጣልዎ ምንም ማረጋገጫ አይገኝም ይላሉ የቢቢሲ ሙንዶው ሠራተኞች ዳይሬክተር ሉዊስ ሪቫስ። ስለዚህ ከቀድሞ አለቃችን ጋር አለመግባባት ካለ ብንተወዉ ይመረጣል። የአሁኑን ሥራዬን አልወደውም ይህ ትክክል ቢሆንም ማለቱ ግን ተገቢ አይደለም። አሉታዊ ስሜት ያለውን አስተያየት ወደጎን መተው አስፈላጊ መሆኑን እና እንደ አዲስ ፈተና ለመቀበል ዝግጁ ነኝ የሚሉ አይነት አስተያየቶችን እንድንጠቀም ባለሙያዎች ይመክራሉ። ምንም ደካማ ጎን የለኝም ይህ ቃለ መጠይቅ የሚደረገውን ሰው እብሪት ከማሳቱም በላይ እራስን መለስ ብሎ ለመመልከት የማይፈልግ ሰው እንደሆንና በበጎ መልኩ የሚሰጡ አስተያየቶችንም ለመቀበል አለመፈለግ እንዳለ የሚያሳይ ነው። ብቸኛው ችግሬ ሁሉም ነገር ፍጹም እንዲሆን መጠበቄ ነው የሚል አይነት የተለመዱ አገላለጾችን ማስወገድ እንደሚገባም ባለሙያዎች ይጠቁማሉ። ይህ ሥራ ምን ያህል የዕረፍት ቀናት አሉት የመጀመሪያ የሥራ ቃለ መጠይቅ ከሆነ ሥራውንም እንዳገኘን ስላልተረጋገጠ እና የሚከፈለው የደሞዝ መጠንና ጥቅማጥቅሞችን ጨምሮ ሌሎች ነጥቦች ስለማይታወቁ በጥልቀት ወደ ጉዳዮች መግባት አያስፈልግም። ለዕረፍት የሚሆን ትኬቶች አገኛለሁ ተብሎ የሚጠየቀው ሥራውን እንዳገኘን ሲነገረን ወይም ሥራው ቢሰጠን ምን ያህል ጊዜ ውስት እንደምንጀምር ስንጠየቅ ብቻ ነው። ድርጅትዎ ምን ይሠራል ይህንን በፍጹም ልንጠይቅ አይገባም። ብዙ ጊዜ ስለድርጅቱ የሚነሱ ጥያቄዎችን መመለስ አለብዎት ሲሉ በሠራተኞች ጉዳይ ባለሙያ የሆኑት አሊሰን ዶይል ለቢቢሲ ዎርልድ ገልጸዋል። ቀጣሪዎችዎ እነማን እንደሆኑ ያጥኑ፣ ድረ ገጻቸውን ይጎብኙ፣ የማህበራዊ ሚዲያዎቻቸውን እና ስለድርጅቱ የሚያትቱ ዜናዎችን መከታትል አስፈላጊ ነው ብለዋል። ስለድርጅቱ በይፋ የማይታወቁ ነገር ግን በምናውቃቸው ሠዎች በኩል የሚገኙ መረጃዎች ካሉ መፈለግ ጥሩ መሆኑን ዶይል ያብራራሉ።
ከ ዓመታት በኋላ ለዕይታ የበቃው ኢትዮጵያዊ ተውኔት
ኤፕረል ማጋሪያ ምረጥ የተውኔቱ ጭብጥ በሕክምና ተቋማት ላይ የሚታዩ ሙያዊ ደባዎች ላይ የሚያጠነጥን ሲሆን ሙያቸውን ለግል ጥቅማቸው የሚያውሉትን የሚተችና የሚያስተምር ታሪክ ነው። በአስክሬን ሽያጭ፣ በመድሃኒት አቅርቦት፣ ከአስክሬን ላይ ስለሚደረጉ ዘረፋዎች ገልጦ ያሳያል ነቃሽ። ፍቅር እስከ መቃብር ን በአይፎን ነቃሽ በዮሐንስ ብርሐኑ ተደርሶ ለዕይታ የበቃው ከዛሬ ዓመታት በፊት በአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት የባህልና ቲያትር አዳራሽ ነበር። ይህ ተውኔት ከዓመታት በኋላ በተስፋ የኪነጥበብ ኢንተርፕራይዝ በአርቲስት ተፈራ ወርቁ አዘጋጅነት ዳግም ለዕይታ በቅቷል። በአዲስ አበባ ነዋሪ የሆኑት አቶ የማነ ታዬ ተውኔቱን የተመለከቱት በሃያዎቹ መጀመሪያ የዕድሜ ክልል ላይ እያሉ በአንድ ጓደኛቸው ጋባዥነት ነበር። በወቅቱ ከፍተኛ ተወዳጅነት ነበረው የሚሉት አቶ የማነ በአዲስ አበባ ማዘጋጃ የነበረውን ረጅም ሰልፍ ተቋቁመው እንዳዩት ያስታውሳሉ። ከተውኔቱ በተለይ አልአዛር ሳሙኤል የተጫወተው እኩይ ገፀ ባህሪ ሊቀረድ ከአዕምሯቸው አልጠፋም። ከአስክሬን ላይ የወርቅ ጥርሶችን የሚሰርቅ ገፀባህሪ ነበር እና በዚያ ዘመንና እድሜ እንዲህ ዓይነት ነገር ይፈጠራል ብዬ ስለማላምን በአግራሞት በአዕምሮዬ ተቀርፆ ቀርቷል ይላሉ። አሁንም ተውኔቱ በድጋሚ በመቅረቡ ደስተኛ መሆናቸውን ገልፀው በድጋሜ ለማየት እንደጓጉ ነግረውናል። ዓመታትን ያስቆጠሩ ተውኔቶች ተመልሰው ለተመልካች ዕይታ ሲበቁ እንዲሁም ተመልካች ኖረውም አልኖረውም ለዓመታት ከመድረክ ሳይወርዱ የሚቆዩበት አጋጣሚ ይስተዋላል። ለዚህም የተውኔት ጸሐፊዎች ብዕር ነጥፏል፣ ገንዘብ ወዳድ ስለሆኑ የተሻለ ገንዘብ የሚያስገኝላቸውን ፊልም ይመርጣሉ፣ የቀደሙትን ቲያትሮች በብስለትም በሃሳብም የሚስተካከላቸው ስለሌለ ተደጋግመው ቢታዩም ይወደዳሉ፤ የሚሉ የተለያዩ አስተያየቶችን የሚሰጡ በርካቶች ናቸው። ትንሳኤን አድማቂ ገጣሚያን በእነዚህ ሃሳቦች መካከል ባቢሎን በሳሎን፣ የጠለቀች ጀምበር የሚሉና ሌሎች ተውኔቶችም በድጋሚ ለተመልካች ቀርበዋል። አሉ የተሰኘ ትርጉም ተውኔትም ከ ዓመታት በኋላ በድጋሚ ሊወጣ መሆኑን ሰምተናል። በቅርቡ በሀገር ፍቅር ቲያትር የተከፈተው ነቃሽ ተውኔትም አንዱ ሆኗል። ነቃሽ በወቅቱ እንደ ሼክስፔር ሥራዎች ያህል ተወዳጅ ስለነበር ከወቅቱ ጋር አስማምተን በድጋሚ ለዕይታ እንዲበቃ ሆኗል የሚለው አዘጋጁ፣ በተውኔቱ ላይ ከዛሬ ዓመታት በፊት ከተወኑት ተዋናዮች ሁለቱ አሁንም የቀደመውን ገፀ ባህሪያቸውን ወክለው ተጫውተዋል አልአዛር ሳሙዔልና ፋንቱ ማንዶዬ። በድጋሜ በተውኔቱ ላይ የመተወን ዕድሉን ያገኘው አርቲስት ፋንቱ ማንዶዬ ቲያትሩን በድጋሚ ለመጫወት ጥያቄ ሲቀርብለት ደስታው ወደር አልነበረውም። በዚያን ጊዜም ሲሰራ ወቅቱን የጠበቀ ቲያትር ነበር፤ አሁንም ተሻሽሎ በመቅረቡ ተመልካች ይወደዋል ይላል የቀደመውን በማስታወስ። እርሱ እንደሚለው የድርሰቱ ሃሳብ ዘመን የሚሽረው አይደለም፤ በተለይ የተነሳው የህክምናው ዘርፍ ከመድሃኒት አቅርቦት ጋር በተየያዘ የሚሰሩ ደባዎችን የሚያጋልጥና ለመንግስት አቅጣጫ የሚያሲዝ ነው። በተውኔቱ ላይ የሆስፒታሉ የጥበቃ ክፍል ሆኖ የሚተውነው አርቲስት ፋንቱ አሁንም ተመሳሳይ ገፀ ባህሪይ ይዞ ይጫወታል። ዓመታት ወደ ኋላ ተጉዘው ቃለ ተውኔቱን ሙሉ በሙሉ ባያስታውስም ዋናውን ገፀ ባህሪ ውድነህን በተመለከተ ውድነህ ለድሃ ገንዘቡን የሚሰጥ እንጂ እሱ ከድሃ አይዘርፍም የሚለውን ንግግር አይረሳውም። ከወጡት ስራዎቼ ይልቅ ገና የሚወጡት ናቸው ትልቅ ቦታ ያላቸው አለማየሁ ገላጋይ አርቲስት ፋንቱ ተውኔቶች በድጋሜ ወደ መድረክ መምጣታቸው መልካም ቢሆንም ደራሲያን ወደ ፊልሙ ማዘንበላቸው ግን አዳዲስ ተውኔቶች እንዳይቀርቡ እንደ አንድ ምክንያት ያነሳል። የቀደሙት አንጋፋና ዘመን አይሽሬ ድርሰቶችን የሚያበረክቱት አንጋፋ ደራሲያን ዛሬ በሕይወት አለመኖራቸውም ሌላኛው ተያያዥ ምክንያቱ ነው። እኛ በፊት የምንሰራውም፣ የምንተውነውም ፤ በአብዛኛው ህዝቡ እንዲያይልን ፣ እንዲወድልን ፣ እንዲያጨበጭብልን ነው የሚለው አርቲስቱ ትምህርት ለኑሮ፤ ሙዚቃ ለአዕምሮ በሚል በነፃ ሜዳው ላይ የሚያቀርቡት ዝግጅት እንደነበር ያስታውሳሉ። ዘመኑ ያለ ገንዘብ ለመኖር አዳጋች ቢሆንም፣ ሁሉ ነገር ወደ ገንዘብ መቀየር አለበት ማለቱ ተገቢ እንዳልሆነ ያሰመረበት ጉዳይ ነው። አርቲስት አልአዛር ሳሙዔልም ከዚህ የተለየ ሃሳብ የለውም። ተውኔቱ በድጋሚ እንዲመጣ ፍላጎቱ ነበረኝ የሚለው አልዓዛር አሁንም አዳዲስ ተውኔቶች እየተፃፉ ነው የሚል አቋም አለው። ነቃሽ በዛን ጊዜ የነበረውን የተውኔት ተመልካችን ፍላጎት ያሟላ ስለነበር አሁንም ያንን በድጋሚ ማሳየቱ ጥሩ ነው ይላል። የቆዩ ተውኔቶች ለምን በድጋሜ ይመጣሉ የተውኔቱ አዘጋጅ አርቲስት ተፈራ ወርቁ በተለያየ ጊዜ በአዘጋጃቸው ተውኔቶች በመጠይቅ ከተሰበሰቡ የተመልካች ምርጫ ውስጥ አንዱ ነቃሽ ሆኖ በማግኘታቸው በድጋሚ እንደተዘጋጀ ይናገራል። አዘጋጁ እንደሚለው እነዚህ ተመልካቾች ተውኔትን በቋሚነት የሚያዩ ሲሆን ዕድሜያቸው ከ እስከ የሚገመቱ ናቸው ብሏል። አሁንም አዳዲስ ተውኔቶች ይወጣሉ፤ ነገር ግን የድሮዎቹም በድጋሚ መሰራታቸው ያላየው ትውልድ እንዲመለከተው ዕድል የሚሰጥ ነው የሚለው አዘጋጁ አዳዲስ ተውኔቶች ቢፃፉና ለዕይታ ቢበቁ ምርጫው እንደሆነ ይናገራል። ይሁን እንጂ አንዳንድ ተውኔቶች ለዓመታት መድረክ ተፈናጠው የሚቆዩበትን ምክንያቶች የተውኔት ፅሁፍ አለማግኘት፣ ደራሲዎች ከሚያገኙት ክፍያ ጋር በተያያዘ ከተውኔት ይልቅ ፊልምን መምረጣቸውና ከተውኔት መሸሻቸውን ከብዙ በጥቂቱ ይዘረዝራል። የተውኔት ዘርፉ ከድርሰት ጋር በተያያዘ ካለበት ፈተና በተጨማሪ ሌሎች በርካታ ተግዳሮቶችን እንደሚያስተናግድም ተደጋግሞ ይነሳል። አበረታች አይደለም፤ ለባለሙያዎች ጥሩ ክፍያ መክፈል አልተቻለም፤ ቢሮክራሲው፣ የትኬት ቀረጥ፣ የመግቢያ ዋጋ አነስተኛ ብር መሆኑ ኢንዱስትሪውን ቁልቁል እንዲሄድ አድርጎታል ሲል ያስረዳል። በተለይ በግል ተውኔትን ለሚያቀርቡት ፈተናው ያይላል። ፊልሞች በተውኔት ላይ ተፅእኖ አሳድረው ነበር፤ አሁን ግን እየተመለሰ ነው የሚለው አርቲስት አልአዛር፤ ለዚህም የቀደመው ትውልድ የሚያስታውሰውን መድገሙ አስተዋፅኦ ሳይኖረው አይቀርም ይላል። በመሆኑም የቀደሙት ተውኔቶች ድጋሚ መቅረባቸው ሊበረታታ እንደሚገባ ይናገራል። ነቃሽ ተውኔት ዘወትር ማክሰኞ ከ ፡ ሰዓት ጀምሮ በሀገር ፍቅር ቲያትር ቤት ከትናንት ሚያዚያ ዓ ም መታየት ጀምሯል። ተያያዥ ርዕሶች
ሀሳብን እንደልብ በአደባባይ መግለጽ ያስገድል፣ ያሳስር፣ አካል ያስጎድል፣ ያሰድድ፣ የነበረበት ወቅት እንደነበረ አይዘነጋም።
ካርቱን መልዕክት ማስተላፍ የሚቻልበት መሳሪያ ነው። ግን አደጋ ነበረው ካርቱኖቹን እንግሊዝ ሆኖ መስራቱ በተወሰነ ደረጃ ስጋቱን ቢያቀልለትም፤ ከሀገር ርቆም ከጫና አላመለጠም። የሚሠራቸውን ካርቱኖች ተከትሎ ማስፈራሪያ ይደርሰው ነበር። የጥቃት ሙከራ እንደተደረገበትም ይናገራል። ካርቶኖቹን የሚያሰራጭበት ፌስቡክ የበርካቶች መንደር ነው። ሥነ ጥበብ የሚወዱ፣ የሚያደንቁ፣ የፖለቲካ ግንዛቤ ያላቸው፣ እንዲሁም ለጥበቡ ግድ የሌላቸው፣ ፖለቲካውም ከአንድ አቅጣጫ ብቻ እንዲታይ የሚፈልጉም ሀሳባቸውን ያለ ገደብ በፌስቡክ ይገልጻሉ። በወቅታዊ ፖለቲካ ላይ በሚያተኩሩ ሥራዎቹ ይታወቃል። አጭር የምስል መግለጫ ከዓመታት ስደት በኋላ ወደሀራቸው የተመለሱ የጥበብ ሰዎችን ያሳየበት ሥራ ሰዎች ጉዳት ሊያደርሱብኝ የሞከሩበት ጊዜ ነበር። ሦስት አራት ጊዜ ጥቃት ተሞክሮብኛል። ለፖሊስ ሪፖርት አድርጌ ሰዎቹ በአካባቢዬ እንዳይደርሱም ተደርጓል እንግሊዝ በመሆኑ ሊሠራቸው የቻላቸው ካርቱኖች ኢትዮጵያ ቢሆን እንደማይሞከሩ ይናገራል። ኢትዮጵያ ብሆን እሞት ወይም አንዱ ጆሮዬን፣ አንዱ ጥፍሬን ነቅሎት ነበር። እጁን መቁረጥ ነው የሚሉ ሰዎች እዛ ኢትዮጵያ ብሆን ይሳካላቸው ነበር ሥራው የግል ህይወቱን ማደነቃቀፉም አልቀረም። አለማየሁ እንደሚለው፣ የሀበሻ ሬስቶራንት፣ ጭፈራ ቤት የማይሄድባቸው ወቅቶች ነበሩ። ዓመት በዓመት ላይ ሲደረብ፣ ሀገሪቱ በሕዝባዊ ተቃውሞ ተንጣ፣ ዛሬ ላይ ደግሞ አንጻራዊ ለውጥ ይስተዋላል እየተባለ ነው። ካርቱን ለአለማየሁ የሂደቱ ነጸብራቅ ነው። ሆኖም የአንጻራዊ ለውጥ መኖር ካርቱንን ክፍተቶችን ነቅሶ ከማውጣት ሚናው እንደማይገታው ይናገራል። ዘመናት በአለማየሁ ካርቱኖች ሲገለጹ ካርቱን የመንቀፍ፣ የማሳቅ፣ ለለውጥ የማነሳሳት፣ ለሀሳብ ወይም ለክርክር የመጋበዝ ባህሪ አለው። አለማየሁ ሥራዎቹ ሙገሳም ወቀሳም ቢያስከትሉበትም ከሙያው ሕግጋት ዝንፍ የሚል አይመስልም። አጭር የምስል መግለጫ ጠቅላይ ሚንስትሩ የኢትዮጵያን ካርታ ይዘው ሲሮጡ፣ በሌላ በኩል ደግሞ ዘራፊዎች የሰረቁትን ይዘው ሲሸሹ ከአንድ ወገን ምስጋና ከሌላ ወገን ኩነኔ ካመጡበት ሥራዎቹ መካከል የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ ከዚህ ዓለም በሞት ሲለዩ የሰራውን አይዘነጋም። መለስ በህይወት ሳለ ከአየር መንገድ ወደ ቤተ መንግሥት በሚሄድበት ሰዓት ህጻን፣ አዋቂ ሳይባል የመንገድ ጥግ ይዘው ፊታቸውን ያዞራሉ። ደህንነት የለም በሚል እሱና ሕዝቡ ፊትና ኋላ ይሆኑ ነበር። ከሞተ በኋላ፤ ሬሳው በመኪና ተደርጎ ሲሄድ ሰዎች ከየአካባቢው እየመጡ መኪናው ላይ እየተንጠለጠሉ፣ እየተደፉ ያለቅሱ ነበር ሥራው የሁለት ዘመናትን ተቃርኖ የሚያሳይ ነው። ኑሮ ሲወደድ፣ ሚዲያ ለፕሮፖጋንዳ መንዣ ሲውል መመልከት እርሳሱን እንዲያነሳ ይስገድደዋል። የዓመቱ ኮከብ ሆዶች እና ወያኔ ስትቆነጠጥ የተሰኙ ካርቱኖቹን ሲገልጽ፤ ዛሬ ዘርፈዋል ተብለው የተከሰሱ ሰዎችን እኔ ድሮ ራቁታቸውን ሰርቻቸዋለሁ። በእስልምናና ክርስትና መካከል ግጭት ለመፍጠር ተብሎ የተሰራ ዘጋቢ ፊልም ነበር። ወያኔ ስትቆነጠጥ በሚል የሰራሁት ካርቱን የእስልምናና ክርስትና ሀይማኖት መሪዎችን ሲቆነጥጡ ያሳያል። እነዚህ ካርቱኖች ዛሬ ላይ በሀገሪቱ ላይ ለሚስተዋለው አንጻራዊ ለውጥ የድርሻቸውን አስተዋጽኦ እንዳበረከቱ ያምናል። ያለፉት ዓመታት ልፋቴ ከንቱ አልቀረም የሚለውም ያለ ምክንያት አይደለም። አንድ ሀገር ከአንድ አስተዳደር ወይም ከአንድ የፖለቲካ ሥርዓት ወደሌላው ብትሸጋገርም፤ ሁሌም መሰናክሎች ስለማይጠፉ ችግሮችን ነቅሶ በማውጣት የለውጥ ድምጽ መሆን ያስፈልጋል። አጭር የምስል መግለጫ ካርቱን ሁሌም ይተቻል ለውጥ ሰው የሚያስፈልገውን ነገር በአጠቃላይ አያሟላም። ወደፊትም አያሟላም። ስለዚህ ካርቱን ሁሌም ይተቻል። አለማየሁ እንደሚለው፤ ካርቱኒስት በሥራዎቹ እይታውን ይገልጻል። የሚዝናናበት፣ የሚበሳጭበት፣ የሚቆረቆርበትን ለሕዝብ ያካፍላል። እንደ ካርቱኒስ በመደመርም በመቀነስም ውስጥ መኖር የለብኝም። ምክንያቱም እንደ ካርቱኒስት በችግሮች ዙሪያ ሂውመር ፈገግታ ለመፍጠር ነው የምሞክረው። የሙያው ግዴታ ነው። ጎራ ተይዞ የሚሰራ አይደለም። ሁሌም ውጪ ሆኖ ነው የሚሠራው። መሠራት ያለበት በሕዝብ ወገን ነው። የሕዝብ ድምጽ ነው። ነጻነታቸውን ያጡ፣ ሀሳባቸውን በነጻነት መግለጽ የማይችሉትን ለመግለጽ ለመወከል ነው የምንሞክረው። ዛሬም ችግሮች እንዳሉ ለማሰየት ከሠራቸው አንዱ ጠቅላይ ሚንስትር ዓብይ አሕመድ የኢትዮጵያን ካርታ ይዘው ሲሮጡ፣ በሌላ በኩል ደግሞ ዘራፊዎች የሰረቁትን ይዘው ሲሸሹ፣ በየክልሉ ያለውን ሽኩቻም ያሳያል። ካርቱን የትግል መሳሪያ ካርቱኖች መንግሥት ትኩረት እንዲሰጣቸው የተፈለጉ ነገሮች ማሳያ ሆነው ያገለግላሉ። በፖለቲካ ካርቱኖች ሙሰኞች፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ የፈጠሩ ግለሰቦችና፣ ሰብአዊ መብት የጣሱ ሰዎች በጥበባዊ መንገድ ይገለጻሉ። አጭር የምስል መግለጫ ካርቱንን ለነጻነት ትግል ቁልፍ መሳሪያ ነው ተምሳሌታዊ በሆነ መንገድ ሙሰኛው ሆዱ ተቆንዝሮ፣ ጠብ አጫሪው ተንኮል በአእምሮው ሲመላለስ፣ ገዳይ በደም ተነክሮ ይሳላል። ሸረኛ በእባብ እንዲሁም ሌሎች ሰዎችንም እንደየባህሪያቸው በተለያዩ እንስሳት መመሰል ሌላው መንገድ ነው። አለማየሁ ካርቱንን ለነጻነት ትግል ቁልፍ መሳሪያ ነው ይለዋል። ከተቀረው ዓለም አንጻር ኢትዮጵያ ውስጥ ካርቱንን የማየት፤ እንደ ሀሳብ ማስተላለፊያ የመጠቀም ልምድ ባይዳብርም፤ የማኅበረሰቡን ድምጽ ለማስተጋባት የዋለባቸው ጊዜያት ይጠቀሳሉ። አሁን ላይ ካለው በላቀ ካርቱን በነጻነት የሚሰራበት ወቅት እንደሚመጣ ያምናል። ካርቱኒስቶችን የሸበቧቸው ስጋቶች እየተቀረፉ እንደሚሄዱም ተስፋ ያደርጋል። ካርቱን ሲሠራ የግል ወይም የቡድን ጨዋታ ሳይሆን ሀሳብ ላይ ያተኮረ ትችት መኖር አለበት። በእርግጥ በቂ የካርቱን ሙያተኛ የለም። ያሉትም ጎልተው መውጣት አልቻሉም። ሙያተኞቹ ሀሳባቸውን በነጻነት ለመግለጽ ከመቸገራቸው ባሻገር ለሥራቸው ተመጣጣኝ ክፍያ አለማግኘታቸውም ሌላ ጫና ይፈጥራል። አለማየሁ ወደኋላ እና ወደፊት ያደገው አዲስ ከተማ አካባቢ፣ ለሥነ ጥበብ በተመቸ ቤተሰብ ውስጥ ነው። እናቱ ወረቀት፣ ቀለም ያቀርቡለታል። የፋሽን ዘርፍ ይማርከው ስለነበረም የፋሽን ዲዛይን መጽሔት ይሰጠው ነበር። በልጅነቱ ስኬች ከማድረግ ተነስቶ የመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ ተማሪ ሳለም በሥነ ጥበቡ ገፋበት። አለ የሥነ ጥበብና ዲዛይን ትምህርት ቤት ሳለ ዓመታዊ መጽሄት እንዲሠራ ተሰጠው። ያ የመጀመሪያው የኅትመት ውጤቱ ነው። ካርቱን ከተማሪነት ዘመኑ አንስቶ ይስበዋል። ለካርቱን ዝንባሌ ብቻ ሳይሆን ተፈጥሯዊ ስጦታ እንዳለውም ያምናል። ከኢትዮጵያ ወደ እንግሊዝ ሲሄድ ነበር ካርቱን የተከበረ ጥበብ መሆኑን የተገነዘበው። እዛው እንግሊዝ ውስጥ ሀበሻኒ የሚል አስቂኝ የፖለቲካ ኮሚክ መጽሐፍ አሳተሟል። የተለያዩ ዘመናት ነጸብራቅ የሆኑ ሥራዎቹን አሰባስቦ ለማሳተምም ከፀሀይ ፐብሊሸርስ ጋር ተስማምቷል። ከካርቱኖቹ ጎን ለጎን ዋነኛ የገቢ ምንጩ የአኒሜሽን ፕሮዳክሽን፣ የኢሉስትሬሽን መጽሐፍና ስቶሪ ቦርድ ሥራ ነው። ካርቱኖች ሲሠራ ፖለቲካውን እንዲሁም ፈገግታ ለማጫር የፈለገበትን መንገድ የሚረዱ ወዳጆቹን ያማክራል። ሆኖም ካርቱን በስቱድዮ፣ በሙያተኞች በውይይት ቢሰራ ይመርጣል። ካርቱን እንደ ሀገር ትልቅ ሀላፊነት የሚጠይቅ ነው። ጠንካራ የፖለቲካና ኤድቶሪያል ብቃት ያለው ተቋም ያስፈልጋል። በስቱዲዮና በባለሙያ ታግዞ ሙሉ ሰዓት የሚሰራም ነው። የእርሶ መሳሪያ ሚዲያ ፕሌይ ባክን ማጫወት ኣልተቻለም። ፖለቲካዊ እውነታዎች በአለማየሁ ተፈራ እርሳስ ተያያዥ ርዕሶች
በሶማሌ ክልል በተከሰተው ቀውስ በአንድ ቀን ሰዎች መገደላቸው ተገለጸ
ኦገስት ማጋሪያ ምረጥ በሶማሌ ክልል በተከሰተው ቀውስ በአንድ ቀን ሰዎች መገደላቸውን የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄኔራል ዘይኑ ጀማል ለቢቢሲ ገልፀዋል። ሰዎቹ የተገደሉት ቀውሱ በተነሳበት የመጀመርያው ቀን ሐምሌ ፣ ዓ ም ሲሆን፤ በሶማሌ ክልል ዋና ከተማ ጅግጅጋን ጨምሮ በክልሉ የተለያዩ ከተሞች ግድያው መፈጸሙን ተናግረዋል። ሰዎቹ የተገደሉት በአሰቃቂ ሁኔታ መሆኑን ተናግረው፤ ሀይማኖትና ብሔርን ለይቶ የተሰነዘረ ጥቃት እንደሆነ አክለዋል። ከዘር ጭፍጨፋ አይተናነስም ብለዋል። መነሻው የክልሉ አመራሮች አቅደው፤ ተግባሩን የሚፈጽሙ ሰዎች አሰልጥነውና አሰማርተው መሆኑን ኮሚሽነሩ ገልጸዋል። እስከ አሁን የክልሉን የቀድሞ ፕሬዘዳንት አቶ አብዲ ሞሀመድ ኡመርን ጨምሮ ሰባት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ተናግረዋል። አብዲ ሞሃመድ ያለመከሰስ መብታቸው ተገፈፈ ሄጎ በመባል የሚታወቀው ቡድን በግድያው እጁ ስለመኖሩ ቢቢሲ ላቀረበላቸው ጥያቄ፤ በዋናነት በግጭቱ ተሳትፈዋል የሚባሉት ሄጎ በሚባለው ቡድን አባላት ናቸው። ሄጎ የሚባለውን የፈጠሩ፣ እቅዱን ያቀነባበሩ የክልሉ የፖለቲካ አመራሮች፣ የክልሉ የካቢኔ አባላትና ሌሎች የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣኖችን በቁጥጥር ስር የማዋል ስራ እየሰራን ነው ብለዋል። ልዩ ፖሊስ በግድያው ተሳትፎ ስለመሆኑ ከቢቢሲ ለቀረበላቸው ጥያቄ ማን በምን ደረጃ ተሳተፈ የሚለው ተጣርቶ ለህዝብ ይፋ ይደረጋል ሲሉ ኮሚሽነሩ አስረድተዋል። በጅግጅጋ የሚኖሩ የተለያዩ አካባቢዎች ተወላጆች ስጋት እንዳላቸው የሚናገሩት ጄኔራል ዘይኑ፤ የፌደራል ፖሊስና የመከላከያ ሰራዊት የክልልሉን ዋና ዋና ከተማዎች መቆጣጠሩ አንጻራዊ ሰላም ማስፈኑን ገልጸዋል። በአሁን ወቅት አዲሱ የክልሉ ፕሬዘዳንት አቶ ሙስጠፋ ኡመር በተለያዩ አካባቢዎች እየተዘዋወሩ ህብረተሰቡን እየጎበኙ መሆኑን ተናግረዋል። የተፈናቀሉ ሰዎችን ወደ አካባቢው መመለስ ቀጣዩ ስራ መሆኑን ተናግረው፤ በዚህ ረገድ የአካባቢው ማህበረሰብ እየተባበራቸው እንደሚገኝ ጠቁመዋል። ተያያዥ ርዕሶች
አንድ ሚሊዮን ፈረንሳዊያን ማጨስ አቆሙ
ሜይ ማጋሪያ ምረጥ አጭር የምስል መግለጫ በፈረንጆች ዎቹ ትምባሆ ማጤስ እንደ ዝመና የሚታይበት ዘመን ነበር። የዚያ ዘመን እውቁ ሙዚቀኛ ሰይሽ ገኒሽቡህ ከአፉ ትምባሆ ተለይቶት አያውቅም ነበር። በፈረንሳይ የአጫሾች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ ቀንሷል። ባለፉት ዐሥርታት ከሕዝበ ፈረንሳዊያን በእንዲህ ያለ ቁጥር የትምባሆ አጫሾች በቃን ሲሉ ታይቶም፣ ተሰምቶም አይታወቅም። የፈረንሳይ ጤና ቢሮ ባካሄደው በዚህ ጥናት እንዳመለከተው አፍላ ወጣቶች፣ ጎረምሶች፣ እንዲሁም በዝቅተኛ ገቢ የሚተዳደሩ ዜጎች በአያሌው ማጤስ ማቆማቸውን ጠቁሟል። ጥናቱ ይህ ውጤት እንዴት ሊመዘገብ እንደቻለ መላምቱን ጨምሮ ያስቀመጠ ሲሆን ፈረንሳይ ባለፉት ዓመታት በትምባሆ አሉታዊ ውጤቶች ላይ ያተኮሩ ተከታታይ ዘመቻዎችና እርምጃዎች መውሰዷን ጠቅሷል። ፈረንሳይ በቅርብ ዓመታት ውስጥ ትምባሆ ማጤስን የሚያቆሙ ዜጎቿን የሚያበረታቱ በርካታ እርምጃዎችን መውሰዷን ያስታወሰው ጥናቱ ከነዚህ መሐል የሲጃራ ዋጋን መቆለልና ከሲጃራ ነጻ የሆነ ወር በአገር አቀፍ ደረጃ ማወጅን ይጨምራል። ይህ የናሙና ጥናት እንዳመላከተው በ ብቻ ዕድሜያቸው ከ የሆኑ በየዕለቱ አጫሽ የነበሩ ሲሆን ከዚያ ቀደም ባለው ዓመት ግን አጫሽ ነበሩ። በዚህም መሠረት ሚሊዮን አጫሾች የነበሩባት ፈረንሳይ ቁጥራቸው በአንድ ሚሊዮን ቀንሶ ሚሊዮን የትምባሆ ወዳጆች ብቻ ቀርተዋል። በዓለም ደረጃ ከአስር ሰዎች ሞት የአንዱ ትምባሆን ከመማግ ጋር የተያያዘ ነው። ከነዚህ ሟቾች ግማሾቹ የሚገኙት ደግሞ በቻይና፣ በሕንድ፥ በአሜሪካና በራሺያ እንደሆነ የዓለም ጤና ድርጅት ገልጧል። ተያያዥ ርዕሶች
ኢትዮጵያ ከዓለም ጥቂት አጫሾች ያሉባት አገር ናት
ግንቦት አንድ ሚሊዮን የሚጠጉ ፈረንሳዊያን የትምባሆ ነገር በቃን ብለዋል ትምባሆ ማጤስ በማቆም ፈረንሳዊያንን የሚያህል አልተገኘም። በአንድ ዓመት ውስጥ ብቻ አንድ ሚሊዮን ዜጎች የትምባሆን ነገር በቃን ብለዋል። ይህም ከ እስከ ብቻ የሆነ ነው። በርካታ አገራት የትምባሆ ስርጭትን ለመግታት ፖሊሲያቸውን ከልሰዋል። ያም ሆኖ በዓለም ላይ የአጫሾች ቁጥር ሲጨምር እንጂ ሲቀንስ አይታይም። ዛሬ የዓለም ትምባሆ ያለማጤስ ቀን ከመሆኑ ጋር አስታከን የአጫሽ አገራትን ዝርዝር አቅርበናል። ኪሪባቲ ኪሪባቲ የምትባል የማዕከላዊ ፓሲፊክ ደሴት በአጫሾች ቁጥር በዓለም ቀዳሚዋ ናት። ከሕዝቧ ሁለት ሦስተኛ ወንዶች ትምባሆ የሚያጤስ ነው። ከሴቶች ደግሞ አንድ ሦስተኛ የሚሆኑት ደግሞ አጫሾች ናቸው። ኪሪባቲ ደሴት በትምባሆ ላይ የምትጥለው ግብር ትንሽ ነው በዚህች አገር ሕዝብ ይኖራል። በትምባሆ ላይ የተጣለው ግብር አነስተኛ ሲሆን ሕዝቡ በቀላሉ በየትም ቦታ ትምባሆን ማግኘት ይችላል። ሞንቴኔግሮ ምሥራቅ አውሮፓዊቷ አገር ሞንቴኔግሮ ከአውሮፓ በአጫሽ ቁጥር የሚያህላት የለም። በመቶ ሕዝቧ ሱሰኛ ሆኗል። የባልካኗ ሞንቴኔግሮ የሕዝብ ቁጥሯ የሚጠጋ ሲሆን ሲጋራዎች በየቀኑ በአዋቂዎች ይጨሳሉ። ምንም እንኳ በአደባባይና ሕዝብ በተሰበሰበባቸው ቦታዎች ማጤስ በአገሪቱ ሕግ የተከለከለ ቢሆንም ሕዝቦቿ ግን በቢሮዎች፣ በምግብ ቤቶች፣ ብሎም በሕዝብ መጓጓዣ ውስጥ እንደልብ ትምባሆን ይምጋሉ። በግሪክ የጠቅላላ ወንድ ሕዝቦቿ እኩሌታ ትምባሆ ያጨሳል ግሪክ ግሪክ ኛው ከፍተኛ የአጫሽ ቁጥር እድገት ያስመዘገበች አገር ናት። ከወንድ ዜጎቿ ግማሹ ትምባሆን ከአፋቸው አይነጥሉም። የሚገርመው በመቶ የሚሆኑ ግሪካዊያን ሴቶችም ቢሆን ማጤስን ማዘውተራቸው ነው። ምንም እንኳ ከ ጀምሮ በሕዝብ አደባባዮች ሲጃራ ማቡነን በሕግ የተከለከለ ቢሆንም ሕጉ ትዝ የሚለው አጫሽ ግን የለም። ብዙ ግሪካዊያን ዛሬም በየአደባባዩ ትምባሆን ያምቦለቡላሉ። ከግሪክ ቀጥሎ ኢስቲሞርና ራሺያ በርካታ አጫሾች ያሉባቸው አገራት ናቸው። በኢስቲሞር ፓኬት ሲጋራ ከአንድ ዶላር በታች ይሸጣል ራሺያ ራሺያ በዓለም አጫሾች ዝርዝር አምስተኛዋ አገር ናት። ከመቶ የሚሆኑ ለአቅመ ማጤስ የደረሱ ወንድ ዜጎቿ ትምባሆ አይለያቸውም። የሴቶች ድርሻ ከመቶ ነው። ሥራ ቦታና የሕዝብ መጓጓዣዎች ላይ ማጤስ ክልክል ቢሆንም የማያቋርጥ የሲጃራ ማስታወቂያዎች መበራከታቸው የአጫሾችን ቁጥር ሳያሳድገው አልቀረም። በአንዳንድ የራሺያ ሱቆች ፓኮ ሲጋራ ከአንድ ዶላር በታች ይገኛል። የራሺያ የትምባሆ ገበያ ቢሊዮን ዶላር እንደሚሆን ይገመታል። የራሺያ የትምባሆ ገበያ ከ ቢሊዮን ዶላር በላይ እንደሆነ ይገመታል ጥቂት አጫሾች የሚገኙባቸው አገራት እንደመታደል ሆኖ ከነዚህ አገራት ውስጥ ኢትዯጵያ አንዷ ሆናለች። ጋና፣ ናይጄሪያ፣ ጎረቤት ኤርትራና ፓናማም በዝርዝሩ ይገኙበታል። በበርካታ የአፍሪካ አገራት ሴቶች ትምባሆ ማጤሳቸው እንደ ነውር ይታያል ከአፍሪካዊያን ከመቶዎቹ አጫሾች ሲሆኑ የወንዶች ድርሻ እስከ ከመቶ ይደርሳል። የሴቶች ቁጥር ዝቅተኛ መሆኑ የኢኮኖሚ ጥገኛ ከመሆናቸው ጋር ይያያዛል ተብሏል። የሴቶች ሲጃራ ማጤስ እንደ ማኅበረሰብ ነውር መታየቱ የአፍሪካ ሴት አጫሾችን ቁጥር ሳይቀንሰው አልቀረም። ጫት መቃም ከፍ ያለ ጊዚያዊ መነቃቃትና ምርቃና ውስጥ ይከታል ከሲጃራ ይልቅ ጫት በአፍሪካ ቀንድ ተወዳጅ እየሆነ መምጣቱ የትምባሆ ወዳጆች ቁጥር በቃሚዎች ሳይተካ አልቀረም። የዓለም የጤና ድርጅት እንደሚለው በዓለም ሚሊዮን የሚሆኑ ሕዝቦች ጫት ይቅማሉ። ሴት አጫሾች ዴንማርክ በሴት አጫሾች ቁጥር የሚስተካከላት የለም። በዚያች አገር ትምባሆን በመማግ ከወንዶች ይልቅ የሴቶች ቁጥር ይበልጣሉ። ከመቶ የሚሆኑ ዴንማርካዊያን ሴቶች ትምባሆን የሙጥኝ ብለዋል። በዴንማርክ ከወንድ አጫሾች ቁጥር የሴቶቹ ላቅ ያለ ነው በየዓመቱ ትምባሆ ሚሊዮን የዓለም ዜጎችን ይገድላል። ቢቢሲ ማስተባበያ
አዲስ አበባ ለኑሮ ምቹ ያልሆነችው ከተማ
ኦክተውበር ማጋሪያ ምረጥ ከተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች የሰው ጎርፍ ወደ አዲስ አበባ ይፈሳል። ሁሉም ህልማቸውን ሰንቀው፣ ነጋቸውን አልመው፣ አዲስ አበባ ቤቴ ን እያንጎራጎሩ ወደ አዲስ አበባ ይተማሉ። አዲስ አበባ ግን ሞልታ ትፈስ ጀምራለች። በቂ የመኖሪያ ስፍራ፣ የንፅህና ቤት፣ መናፈሻ ስፍራ እና ሌሎች መሰረተ ልማት የላትም ይላሉ ያነጋገርናቸ የኪነህንፃ ባለሙያዎች። ከተማዋ እንግዶቿን አትምጡብኝ እያለች መግፋት ከጀመረች መቆየቷን ጨምረው ያስረዳሉ። የከተማ ሕይወት መምራት የሁሉም ሰው ምኞት ይመስላል። ከተማ ውስጥ መኖር የብዙ ዕድሎችን በር ይከፍት ይሆናል። ከተሜ መሆን ስልጡንነት ነው። ግን ከተሞቻችን ለመኖሪያ ምቹ ናቸውን ስንል ለሐዋሳ ዩኒቨርስቲ የኪነ ሕንፃ መምህሩ አቶ ኑረዲን መሐመድ ጥያቄ አቅርበናል። በቴክኖሎጂ ኢ ፍትሐዊነትን የምትታገለው ኢትዮጵያዊት እጥረት የተረፋት ከተማ እንደ አቶ ኑረዲን ዜጎች ከተሞች ለመኖሪያነት ምቹ ናቸው እንዲሉ ከገጠሪቱ የሀገራችን ሁኔታ የተሻለ ሕይወት መምራት መቻል አለባቸው ይላሉ። ለአቶ ኑረዲን ከተሞች የስራ እድልን ጨምሮ ንፁህ አየር፣ መዝናኛ ስፍራዎች፣ ውሃ፣ መብራትና ለመኖሪያ ብቁ የሆነ ቤትን አሟልተው ማቅረብ ይገባቸዋል። አቶ ታደሰ ግርማይ የኪነ ህንፃና የከተማ ፕላን እንዲሁም የአርኪዎሎጂና የቅርፅ ጥበቃና እንክብካቤ ባለሙያ ሲሆኑ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ መምህር ናቸው። እንደ እርሳቸው አንድ ከተማ በተወሰነ የጊዜ ገደብ ከየት ተነስቶ የት ይደርሳል የሚለው መታወቅ ይኖርበታል። ይህ ካልሆነ ልክ እንደዛሬዋ አዲስ አበባ የመሰረተ ልማት ችግር ይገጥማል ይላሉ። እንደ አቶ ታደሰ፤ ከተማ በእቅድ ታስቦበት ሲሰፋ መልካም የሆነውን ያህል ያለእቅድ በዘፈቀደ የሚደረግ ማስፋፊያ ችግር ውስጥ እንደሚጥል አፅንኦት ሰጥተው ይናገራሉ። ከተሞች ያላቸውን የተፈጥሮ ኃብት በአግባቡ ላላቸው ህዝብ የማያዳርሱ ከሆነ የመሰረተ ልማት እጥረቶቹ የጎዳና ተዳዳሪዎች ቁጥር እንዲጨምር፣ ወንጀል እንዲስፋፋ፣ ቆሻሻ እና የአየር ብክለት እንደሚያበዛ የሚናገሩት አቶ ታደሰ በዚህም የተነሳ ውጤታማ ያልሆነ ማህበረሰብ ወደ መፍጠር ሊኬድ እንደሚችል ያስረዳሉ። አዲስ አበባ ከዚህም ጋር ተያይዞ በርካታ ችግሮች ያሉባት ከተማ እንደሆነች ያነሱት አቶ ታደሰ የከተማዋ አቀማመጥ ለጥ ያለ ካለመሆኑ የተነሳ በርካታ ህገወጥ ግንባታዎች የሚገነቡባት፣ በግንባታ ላይ ያሉ ህጎችን በአግባቡ ለማስፈፀም ችግር የገጠማት ከተማ መሆኑን እናያለን ብለዋል። በአዲስ አበባ የሚገኙ አረንጓዴ ስፍራዎች ቢኖሩም በአግባቡ አገልግሎት እየሰጡ ስላልሆነ እንደሌሉ ነው የሚቆጠሩት የሚሉት አቶ ታደሰ ክረምት ሲመጣ በውሃ የሚጥለቀለቁ መንገዶች፣ ህገ ወጥ ሰፈራዎች፣ የመሰረተ ልማት እጥረቶች በከተማዋ በሰፊው እንደሚታዩ ጨምረው ይናገራሉ። አጭር የምስል መግለጫ አንዳንድ የከተማዋ ስፍራዎች ከሚገባው በላይ በፎቆች የተሞሉና ምንም አይነት የመናፈሻ ስፍራ በሌለበት በአንድ ላይ ታጭቀው መተንፈስን እንኳ አስቸጋሪ አድርገውታል። ሕይወት ከነትንታጓ የከተመችባቸውን ስፍራዎች በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ አካባቢዎች ህይወት የማያንቀላፋባቸው ስፍራዎች መፈጠራቸውን የጠቀሱት አቶ ታደሰ እነዚህ ስፍራዎች ግን መተንፈስ አይችሉም ይላሉ። ቦሌ መድኃኒያዓለም ኤድና ሞልና ካዛንቺስ ኢንተር ኮንቲኔንታል ሆቴል ጀርባን ያነሱት አቶ ታደሰ በጣም ከሚገባው በላይ በፎቆች የተሞሉና ምንም አይነት የመናፈሻ ስፍራ በሌለበት መኖሪያ ቤት፣ ንግድ ቤት፣ ቢሮዎች በአንድ ላይ ታጭቀው መተንፈስን አስቸጋሪ አድርገውታል ይላሉ። እነዚህ ህንፃዎች ሲሰሩ አረንጓዴ ስፍራዎች ታሳቢ መሆን ነበረባቸው ያሉት አቶ ታደሰ ፈረንሳይ አካባቢ፣ እንጦጦ ሲወጣ ያለውን አየር ከፒያሳ እስከ ሜክሲኮ ካለ አየር ጋር በማነፃፃር መሐል ከተማው ለመተንፈስ አስቸጋሪ መሆኑን ጠቅሰዋል። አቶ ኑረዲን በበኩላቸው አንድ የአዲስ አበባ ነዋሪ በወጣትነት ዘመኑ የአካል አንቅስቀሰሴ የሚያዘወትርበት፣ የሕይወትን ትሩፋቶች ቁጭ ብሎ የሚያጣጥምበት እንዲሁም ህዝባዊ በዓሎችን የሚያከብርበት ስፍራ ቢፈልግ ከወዴት ያገኛል ሲሉ ይጠይቃሉ። ለአቶ ኑረዲን አዲስ አበባ አንድ አለኝ የምትለው እንዲህ ያለስፍራ መስቀል አደባባይን ብቻ እንደሆነ በማንሳት በወጣትነት ጊዜም ሆነ በጉልምስና አረፍ ብሎ ለመቆዘምም ሆነ ለመሳቅ አረንጓዴ ስፍራዎች አስፈላጊ መሆናቸውን ያነሳሉ። ከአዲስ አበባ ውጭ ያሉ ከተሞች የኢትዮጵያን ከተሞች ምቹነት ካነሳን ምናልባት አንድ ወይም ሁለት ከተሞችን ልንጠቅስ እንችላለን ይላሉ አቶ ኑረዲን። እነዚህ ከተሞችም ሀዋሳ እና ባሕርዳር እንደሆኑ የጠቀሱት አቶ ኑረዲን የከተሞቹ እቅድ ሰዎች መስፈር ከመጀመራቸው በፊት በሚገባ ስለተሰራ በቂ አረንጓዴ ስፍራ፣ ፍሳሽ ማስወገጃ እንዲሁም መንገድና ሌሎች መሰረተ ልማቶች አሏቸው ይላሉ። አዲስ አበባ ለመኖሪያ ምቹ ካልሆኑ የአለማችን ከተማ አንዷ ናት የሚሉት አቶ ኑረዲን አዲስ አበባ ካላት ይልቅ የሌላት ነገር እንደሚበዛ ተናግረዋል። ለአቶ ታደሰ ከባህር ዳርና ከሀዋሳ በተጨማሪም ጅማ እና አክሱም የህዝብ ቁጥራቸውም አነስተኛ መሆኑ ለመኖሪያ ምቹ ከሆኑ መካከል ሊጠቀሱ እንደሚችሉ ይናገራሉ። ከቁመት ያላለፉ ሕጎች አዲስ አበባን መልከ ጥፉ ካደረጓት መካከል የሚገነቡት ህንፃዎች መሆናቸውን አንዳንዶች ይናገራሉ። ተመሳሳይ፣ በመስታወት የተለበጡ ህንፃዎች ከሽሮሜዳ እስከ ቃሊቲ ከአያት እስከ አስኮ ሞልተዋል። ለአቶ ታደሰ አዲስ አበባ ያሏት ከህንፃ ጋር የተገናኙ ህጎች ከቁመት ያልዘለሉ መሆናቸው ለዚህ አስተዋፅኦ ማድረጋቸውን ያምናሉ። አዲስ አበባ በአንድ አካባቢ ምን ያህል ቁመት ያለውና በስፋትም ቢሆን ምን ያህል ድረስ መገንባት እንደምንችል ይነግረን ይሆናል እንጂ እንደ ሌሎች ሀገሮች የግንባታውን ቁሳቁስ አይነት የሚወስኑ ተዛማጅ ህጎች የሉንም ይላሉ። እነዚህ ባለመኖራቸው እና ግንባታውን የሚያከናውነው ባለሙያው አቅም ውሱን መሆን የአዲስ አበባን የህንፃ መልከ ጥፉ እንዳደረገው ይናገራሉ። በአንድ ስፍራ ከ ፎቅ እስከ ፎቅ ድረስ መገንባት ይቻላል የሚል ህግ መኖሩ አቅም ያለው የሌለው ደግሞ ድረስ መገንባቱ ለአይንም ለመንፈስም አዋኪ የሆኑ ህንፃዎች እንድናይ እንዳደረገን ይናገራሉ። ከዚህም በተጨማሪ ይላሉ አቶ ታደሰ ማስተር ፕላኑ ላይ ለአረንጓዴ ቦታ የታሰበው ስፍራ በሆነ አጋጣሚ ህንፃ ተሰርቶበት የሚታይበት አጋጣሚ አንዳንዴ ያጋጥማል ብለዋል። ይህ ደግሞ ማስተር ፕላኑ ላይ ያለውን በአግባቡ የማስፈፀም ክፍተት መኖሩን ወይም ለማስፈፀም ብቃትና ጥራት እንደሚያንስ ያሳያል ይላሉ። ከዚህ ሁሉ በተጨማሪ ግን በህንፃ ግንባታው ዘርፍ ሙያዊ ስነምግባር አለመኖሩ በርካታ ችግሮች እንደፈጠረ የሚያነሱት አቶ ታደሰ የሙያ ስነምግባር ከሌለ ህጎች በራሳቸው አያስኬዱም ሲሉ ሃሳባቸውን ይቋጫሉ። ተያያዥ ርዕሶች
የኬንያ ዳኞችን አለባበስ የቀየረች ኢትዮጵያዊት
ሴፕቴምበር አጭር የምስል መግለጫ ኮከብ ለሽልማቱ ከአምስት አፍሪካውያን ዲዛይነሮች ጋር ትወዳደራለች የኬንያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞች በተለይም በምርጫ ማግስት የብዙዎች ዓይን ያርፍባቸዋል። ከነዚህ ዳኞች ጀርባ ደግሞ አንዲት ኢትዮጵያዊት አለች ዲዛይነር ኮከብ ዘመድ። በአውሮፓውያኑ በቅኝ ከተገዙባት ብሪታኒያ የመጣው አለባበስ የነጻይቱ ኬንያ ተምሳሌት በሆነ ልብስ ለመጀመሪያ ጊዜ የተቀየረው ኮከብ በምትመራው ኮኪ ዲዛይንስ ነው። በዳኞቹ ልብስ ላይ አረንጓዴው ጨርቅ የኬንያን ህገ መንግስት ሲወክል በዙሪያው ያለው ወርቃማ ቀለም ደግሞ የፍርድ ቤቱ ህንጻ ተምሳሌት ነው። ይህ ስራ ኮከብ ከስራዎቿ ሁሉ በጣም የምትደሰትበትና የምትኮራበት ነው። ከወራት በፊት ልብሱ በአዲስ መልክ ቢቀየርም ፈር ቀዳጅ በመሆኑ በፍርድ ቤቱ ሙዚየም ለእይታ ቀርቧል። የእርሶ መሳሪያ ሚዲያ ፕሌይ ባክን ማጫወት ኣልተቻለም። የኬንያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞች ከነጻነት በኋላ ራሳቸውን የሚወክል ካባ መልበስ የጀመሩት በኢትዮጵያዊቷ ኮከብ በተሰራላቸው ልብስ ነው። አጭር የምስል መግለጫ ይህ የኬንያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞች ልብስ ለአራት ዓመታት አገልግሏል ወደ ቤቷ ስንሄድ የተቀበለችንም ከስድሳ ዓመታት በፊት አያቷ ሲያጌጡበት በነበረው የሀገር ባህል ልብስ ላይ ባለፈው ዓመት ከሱፍ ጨርቅ ያዘጋጀችውን የአንገት ልብስ ያለውን ካባ ደረብ አድርጋ ነው። ፋሽንና ባህል ሊነጣጠሉ አይችሉም፤ ይልቅስ አንዱ ሌላውን ይደግፋል የምትለው የኮኪ ዲዛይንስ መስራችና ባለቤት ኮከብ ዘመድ ፋሽን ባህልን ወደፊት የማሻገር ሚና የ ዓመታት ልዩነትን ባስታረቀ አለባበሷ ትመሰክራለች። ናይሮቢ መኖር ከጀመረች ዓመታት ቢያልፉም በመኖሪያዋም ሆነ በመስሪያ ቦታዋ ያሉት ቁሳቁሶ፣ የሃገር ባህል አልብሳትና ጥልፎች ዘወትር ከሚጎዘጎዘው ቡና ጋር ተዳምረው ከኢትዮጵያ ውጪ መሆኑን ያስረሳል። ኮከብ ከአውሮፓውያኑ ጀምሮ ባቋቋመችው ኮኪ ዲዛይንስ የኢትዮጵያና ሌሎች የአፍሪካ አልባሳትን እያዋሃደች የአፍሪካን ባህል በማስተሳሷሯ በናይሮቢ እውቅናን እያገኘች ነው። በእኛ ጨርቅ ላይ በመመስረት ኮትና ቀሚስ እሰራለሁ፤ ወይም ደግሞ በየቀኑ የሚለበስ ልብስ ላይ ጥለቱን ብቻ አድርጌ ከሌላ ጨርቅ ጋራ አዋህደዋለሁ፤ መጀመሪያ አልፈለግኩትም ነበር፤ ምክንያቱም ያለፈውን መሰባበር ወይም መቀየጥ ሆኖ ነበር የሚታየኝ ፤ አሁን ግን ሳስበው እንደውም ትንሽ ጥለት ኖሮት የኛንም ባህል ቢያስተዋውቅስ በሚል ትጠይቃለች። አጭር የምስል መግለጫ የኢትዮጵያ ጥለቶች ከሌሎች ጨርቆች ጋር በቅይጥ ይሰራሉ። ከደንበኞቿ አብዛኞቹ ኬንያውያን ናቸው፤ የኢትዮጵያን ባህላዊ ጨርቆችና ጥለቶች በጣም ይወዷቸዋል ትላለች ኮከብ። ከእነዚህና ከጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞች ልብስ በተጨማሪ ደግሞ ሌሎች አፍሪካውያን የሚቀምሙላትን ባህላዊና ዘመናዊ ልብሶች ታዘጋጃለች። ለሴቶች ፣ ለወንዶችና ለልጆች ለልዩ ዝግጅት፣ ለስራ ቦታና ለበዓላት የሚሆኑ ንድፎችን ቀርጻ በተለያዩ የፋሽን ትርዒቶች ላይ ታሳያለች፤ ለገበያም ታቀርበለች። አሁን ደግሞ ለ ምርጥ የምስራቅ አፍሪካ ዲዛይነር ሽልማት እጩ ሆና ተመርጣለች። እዚሁ ኬንያ የተመረቱ ጨርቆችን ተጠቅሜ አዳዲስ ዲዛይኖችን ሰርቻለሁ፤ የኢትዮጵያንም የሃገር ቤት ስሪት የሆኑ ልብሶችን ነው በአዲስ እይታና ዲዛይን የምሰራው፡ በዛ ላይ ደግሞ ከአውሮፓውያኑ እስካሁን በኢንዱስትሪው ተወዳዳሪ ሆኜ መዝለቄም ለእጩነቴ መንገድ ከፍቶልኝ ይሆናል ትላለች ውድድሩ ራሷን ወደ ዓለም ገበያ ለመቀላቀል ጥሩ አጋጣሚ እንደሚፈጥርላት የምትጠብቀው ኮከብ። የሽልማቱ አላማ በኢንዱስትሪው የራሳቸውን አዲስ እይታ ተጠቅመው ከፍተኛ አስተዋፅኦ ላበረከቱ ዲዛይነሮች ክብር መስጠት እንደሆነ በአዘጋጆቹ ድረገጽ ላይ ሰፍሯል። የመገምገሚያ መስፈርቶቹ ደግሞ አዳዲስ ፈጠራ ፣ ጥሩ የዲዛይን አጨራረስ፣ የግል ምልከታ የሚታይባቸውና ለሌሎች አርአያ መሆናቸውን ይጨምራል። ኮከብ ለዚህ ሽልማት ከኬንያ፣ ከሩዋንዳና ከታንዛኒያ እጩ ከሆኑ አምስት ሌሎች ዲዛይነሮች ጋር ትፎካከራለች። አጭር የምስል መግለጫ በ በሰባት የፋሽን ትርዒቶች ላይ ተሳትፋለች የሽልማት ስነስርዓቱ በድረ ገጽ ከአድናቂዎች የሚሰጡ ድምጾች ከባለሙያዎች ዳኝነት ጋር ተዳምረው ውጤቱ መስከረም ይካሄዳል።። ታዲያ ኮከብ ባለፉት ስምንት ዓመታት ሁሉ ነገር አልሰመረላትም ፤ በተለይም በጅማሬዋ አካባቢ በዙ ተማርኩባቸው የምትለውን ስህተቶች ሰርታለች። መጀመሪያ የሰራሁት ልብስ አሁንም ድረስ አለ፤ በርካሽ ጨርቅ ናሙና ሰርቼ መሞከር ነበረብኝ። እኔ ግን ሳላውቅ በራሱ በሳባ ቀሚስ ሰራሁትና ጥሩ ስላልነበር ገዢ አጣ ፤ እኔም ከነኪሳራዬ ይሁን ብዬ ዝም አለኩ በእርግጥ እናቷ ገና በልጅነቷ ጥልፍ አስተምረዋታል ፤ እርሷም ብትሆን የተለየ ልብስ መልበስና ለልጆቿም ልብስ መስፋትን ትወድ ነበር። ነገር ግን ይህንን እንደመዝናኛ እንጂ እንደስራ ለማሰብ ብዙ ዓመታትን ፈጅቶባታል፤ ይህም ዋጋ አስከፍሏታል። በራስ መተማመኑን አሰራሩንም ሆነ ቴክኒኩን ከመጀመሪያው አዳብሬው ቢሆን ኖሮ ድሮ ነበር ዲዛይነር የምሆነው። ስጀምርም እውቀቱ ስላልነበረኝ ማን ነው የሚገዛኝ ለማንስ ነው የምሰራው የሚለው ነገር አላሳሰበኝም ነበር ኮከብ በጅማሬዋ ለኬንያም ሆነ ለዘርፉ እንግዳ ነበረችና ሁኔታዎችን በአግባቡ ለመረዳት ጊዜ ወስዶባታል። ሂደቱን ግን ያቀለለልኝ የኬንያውያን አቀባበልና አዲስ ነገር ለመሞከር ያሳዩት ፍላጎት ነው ባይ ነች ኮከብ ። በዚህ በመበረታታት ኮኪ ዲዛይንን ባቋቋመች በሶስተኛ ወሯ የመጀመሪያውን የፋሽን ትርዒት አቀረበች። ኮከብ እንደምትለው ያለፉት ስምንት ዓመታት ስኬቶች ሁሌም ጅማሬያቸው ሃሳብ ነው። ብዙ ጊዜ ሃሳቡ ሲመጣልኝ ሌሊት ብድግ እላለሁ፤ አዲስ ነገር አስቤ ጠዋት እስክሰራው ድረስ ልቤ አትረጋም፤ ቶሎ ተነስቼ ንድፉን እስለዋለሁ። አጭር የምስል መግለጫ የዲዛይን ንድፎች ሁልጊዜም ስራዬን ያቀላጥፉልኛል ሁልጊዜም የመጀመሪያ ስራዎቿን የምትሞክረው በራሷ ላይ ነው ። ምክንያቷ ደግሞ ደንበኞቼ ላይ የሚፈጥረውን ስሜት በትክክል እረዳበታለሁ የሚል ነው። ውጥን ሃሳቤ በተግባር ምን እንደሚመስል ትክክለኛ ስሜቱን አገኘዋለሁ፤ የማይንቀሳቀሱና የተዋጣ ሰውነት የተሰራላቸው ግዑዝ አሻንጉሊቶች ውበቱን እንጂ ተግባራዊነቱን አያሳዩንም ኮከብ ድርጅቷ ኮኪ ዲዛይንስ ከአምስት ዓመታት በኋላ ይበልጥ የተደራጀና ዘላቂ ሥራ ይዞ ምርቱን ለዓለም አቀፍ ገበያ የሚያደርስ ትልቅ የፋሽን ቤት እንዲሆን ወጥናለታለች። እስከዛው ግን እቅዶቿን በቶሎ ለማሳካት ተስፋ የጣለችበትን የ የምስራቅ አፍሪካ ምርጥ ዲዛይነሮች ሽልማት በጉጉት ትጠብቃለች። ተያያዥ ርዕሶች
የእርሶ መሳሪያ ሚዲያ ፕሌይ ባክን ማጫወት ኣልተቻለም።
ከክር የተሠራ ጫማ ለመጫማት ዝግጁ ይሁኑ ዘወትር ማልዳ እየተነሳች የሊስትሮ ዕቃዋን ሸክፋ ፒያሳ ጣይቱ ሆቴል አካባቢ ትሄድና ጫማ ልጥረግሎት ይወልወል ወይስ ቀለም ላድርግሎት እያለች አልፎ ሂያጁን ትጣራለች። በለስ ቀንቷት ሰው ካገኘች እሰየው በትጋትና በቅልጥፍና ጫማ ትሰፋለች፣ ትጠርጋለች፣ በቀለም ታስውባለች። የሊስትሮ ገበያው ተቀዛቅዞ እጆቿ ስራ ሲፈቱ ደግሞ ኪሮሽና ክር እያስማማች ዳንቴል ትሰራለች። ይህ ራሷን በስራ ለመለወጥ ዘወትር የምታትረው መሰረት ፈጠነ የአራት ዓመታት እውነታ ነው። ምንጊዜም ቢሆን ነገ የተሻለ ቀን እንደሚሆን ተስፋ ታደርጋለች፤ ትናንት ያስተማራትም ይህንኑ ነው። ከ ሶፍትዌር ቀማሪነት ወደ ሥነ ጥበብ ባለሟልነት ድንጋይ ከምረን ከላይ ሸራ አድርገን ነበር የምንኖረው መሰረት በ ዓ ም ነበር ከቢሾፍቱ ወደ አዲስ አበባ አምርታ በቤት ሰራተኛነት የተቀጠረቸው። ቀኑን በስራ እየደከመች ማታ ደግሞ የገጠማትን ፈተና እየታገለች ለሶስት ወራት ቆየች። ሁለት ጎረምሶች ያስቸግሩኝ ነበር፤ እኔ የምተኛበት የማዕድ ቤት በር አልነበረውም፤ እነሱ ደግሞ ሳሎን እያደሩ ያስቸግሩኝ ነበር። አንድ ቀን ስራ ስላልነበረ ቤት ውስጥ በር ቆልፈውብኝ ሊታገሉኝ ሞከሩ፤ ጩኸቴ በቤቱ ሲያስተጋባ ተድናግጠው ተዉኝ። መሰረት በጊዜው በአካባቢው ሰው በመኖሩ ከጥቃቱ ብትተርፍም አንድ ትልቅ ውሳኔ ላይ ደረሰች። ምርር ስላለኝ በቃ ካሁን በኋላ የመኪና አደጋም ቢደርስብኝ፤ ምንም ቢሆን ሰው ቤት አልገባም ብዬ ወጣሁ። ለሃገሩ ባዳ የነበረቸው መሰረት ማደሪያ ስላልነበራት ከዚያን ቀን ጀምሮ መዋያዋ ማደሪያዋም ጎዳና ሆነ። የኢትዮጵያ ተረት ገፀ ባህሪን በአኒሜሽን የእለት ጉርሷን በተገኘው ትርፍራፊ እየሞላች ስታጣም አንጀቷን እያጠፈች ማደር ጀመረች። ቆየት ብሎ ደግሞ እዛው በጎዳና ከተዋወቀችው ወጣት ጋር በመጣመር እንደ አቅሟ ጎጆ ቀለሰች። ስድስት ኪሎ ዩኒቨርሲቲው አምስተኛ በር አካባቢ ድንጋይ ከምረን ከላይ ሸራ አድርገን ነበር የምንኖረው፤ አንዳንድ ቀን ፖሊሶች ያባርሩናል፤ ዝናብ ሲሆን ድንገት ይመጡብናል፤ በተለይም ስብሰባ ካለ በጣም ያስቸግር ነበር መሰረት ከኑሮ ጋር የያዙት ግብ ግብ እስከመቼ እንደሚቀጥል በተደጋጋሚ ራሷን ትጠይቅ እንደነበረ ትናገራለች። ባለቤቷ በዱቤ የወሰደው የሊስትሮ ሳጥን የተስፋ ጭላንጭል ይዞላት ቢመጣ ብላ አንድ ቀን እሱ በሌለበት የራሷን እርምጃ ወሰደቸ። ድንገት ተነስቼ ጫማ ይጠረግ ጫማ ይጠረግ ብዬ መጮህ ጀመርኩኝ፤ ሊስትሮ እሰራለሁ ብዬ አስቤ አላውቅም ግን ራሴን አሳመንኩኝ፤ ያኔ የጫማ ማሰሪያ መፍታትም ሆነ ማሰር አልችልም ነበር፤ የመጀመሪያው ሰው ሲቀመጥልኝ ካልሲውን ቀለም አስነክቼበት ተናዶብኝ ነበር። መሰረት የሊስትሮ ስራውን እንዲህ ጀምራው ለሁለት ወራት ከሰራች በኋላ ኑሮ ሲፈትናት በመሃል ወደ ባለቤቷ ሃገር ወላይታ ብትሄድም አሁንም ተመልሳ የሊስትሮ ስራዋን በፒያሳ ጣይቱ ሆቴል አካባቢ ቀጠለች። አጭር የምስል መግለጫ መሠረት ልጇን ታቅፋ የስድስት ቀን ጨቅላ ይዤ ወደ ስራ ተመልሻለሁ ፈተና ከእሷ ብዙም አልራቀምና መሰረት የሶስት ወር ጽንስ መያዟን አወቀች። ስምንት ወር እስኪሆናት ድረስ አጎንብሳ ጫማ መጥረጓን አላቆመችም ነበር። ወልጄም ከስድስተኛ ቀን ጀምሮ እዛው ተመልሼ ሰርቻለሁ። ያው በስድስት ቀን ስወጣ እንግዲህ ጨቅላዋ አትታዘልም ገና ደም ናት፤ ስለዚህ ትንሽዬ ነገር አንጥፌ አጠገቤ አስተኛትና ከዛ በጥላ እከልላታለሁ፤ እንዲያውም በአጋጣሚ ድምጽ ስታሰማ ሰዎች ይደነግጡ ነበር። ለሶስት ወራት ገደማ በዚህ ሁኔታ ከሰራች በኋላ ክረምት ሲገባ ህጻኗን ብርድ ይመታብሻል የሚል ተግሳጽ ቢያይልባት ተመልሳ ልጇን ይዛ ወደ ገጠር ገባች። ጥቂት ቆይታ ስትመለስም ልጇን እዚያው አጠገቧ እያደረገች በየአካባቢው እየዞረች ስትሰራ ቆይታ ሲቪል ሰርቪስ አካባቢ እንደወትሮው ሁሉ ገበያው በተቀዛቀዘበት ጊዜ ዳንቴሉን ስትሰራ የተመለከተቻት አንዲት ሴት ያቀረበችላት ጥያቄ ለዛሬው ፈጠራዋ መንገድ ቀየሰላት። ዳንቴል ከቻልሽ እኔ አሰራሻለሁ ብላኝ ለወር አካባቢ እኔ ቤት ውስጥ እየሰራሁኝ የዳንቴል ስራውን እያጋመስኩላት እርሷ ደግሞ እያጠናቀቀችው ጫማ ሲሆን አየሁ። ግን ለወር አካባቢ ሰርቼ በህመም ምክንያት አቋረጥኩት። አጭር የምስል መግለጫ መሠረት የምትሠራቸውን ምርቶች ስታሳይ ያለአንዳች ማሽን የምትሰራው የዳንቴል ጫማ መሰረት በጊዜ ሂደት እሷ ዳንቴል ከመሰራት የዘለለ ሚና ባልነበራት ስራ የጎደለውን እውቀት ለመሙላት መፍጨርጨር ጀመረች። እስከ ሶስተኛ ክፍል ብቻ የዘለቀችበት ትምህርት ለዚህ ምንም እንደማይጠቅማት ብታውቅም ተስፋ አልቆረጠችም። መጀመሪያ በሰው እግር እየለካሁኝ ይሄ ተጠቅጥቆ ጫማ መሆን ይችላል እንዴ እያልኩኝ በወንድ ጫማ መሞከር ጀመርኩኝ፤ የሚሆን አልመሰለኝም ነበር፤ ግን በመጨረሻ ተሳካልኝ። ከዛ የሴት ጫማ እያልኩኝ፣ ነጠላ ጫማ እያልኩኝ የወንድ ሸበጥ እያልኩኝ ቀጠልኩ። መሰረት አሁን የሙከራ ሂደትን አልፋ ክፍትና ሽፍን የወንድና የሴት ጫማዎችን፣ የአንገት ልብስ፣ ቀበቶና አልጋ ልብስ በዳንቴል ያለምንም የፋብሪካም ሆነ የማሽን እገዛ በእጆቿ ትሰራለች። የምሰራበት ክር በጣም ጠንካራ ነው፤ ከጅማትም ይጠነክራል፤ ጅማት እንደውም ብዙ ጊዜ እኔ ሊስትሮ እያለሁ ስታገለው ወይ ደግሞ ጫማው በጣም ደረቅ ከሆነ ስስበው የሚበጠስበት አጋጣሚ ነበር። ክር ግን ከዚያም ይጠነክራል፤ ሶሉ ትንሽ ስለሚያስቸግር ነው እንጂ አንድ ሰው እስከ አምስት ዓመት ይሄን ጫማ እንደሚያደርግ እተማመናለሁ። መሰረት የአንድ ንድፉ ያለቀለትን ጥንድ ጫማ የዳንቴል ሥራ በአንድ ቀን ውስጥ ታጠናቅቃለች። አጭር የምስል መግለጫ የመሠረት ጫማዎች ቀጣዩ ሥራዋ ደግሞ ዳንቴሉን በእግር ቅርጽ በተሰራ የጫማ መወጠሪያ አድርጎ በመርካቶ ለመቀየሪያነት የሚሸጡ ማጫሚያዎችን ሶሎችን በመጠቀም በማስቲሽ ማያያዝ ነው። ጉርድ ሾላ አካባቢ ከአምስት ዓመት ልጇ ጋር ተከራይታ በምትኖርበት ጠባብ ባለ አንድ ክፍል ቤት ውስጥ አዳዲስ ዲዛይኖች እያወጣች ወደ ተግባር ትቀይራለች። አምስት የነጠላ ጫማ ዲዛይን አለኝ። ቀጭን ሶል ባላቸው ፍላት ደግሞ ለሴትም ለወንድም በሸራ መልክ ሁለት አይነት ጫማ እሰራለሁ፤ ቡትሶች፤ ቦርሳዎችና ቀበቶዎችም አሉኝ። መሰረት ጫማዎቹን መስራት ከጀመረች ሁለት ዓመታት ቢቆጠሩም በጣም ትልቅ ስራ ሰራሁ የምትለው ባለፈው ሰኔ በትዕዛዝ የሰራቻቸውን ጫማዎች ነው። በቂ ትዕዛዝ አላገኝም፤ በሰፊው ለገበያ ለማቅረብም የገንዘብ አቅም የለኝም፤ በወር አንድ ወይም ሁለት ጫማ ሊመጣ ይችላል። ከዚህ በፊት ይሄ እንጀራዬ ነው ለብዙዎችም ምሳሌ እሆናለሁ በሚል ተነሳሽነት ትዕዛዝ ኖረም አልኖረም ሰዓት እሰራ ነበረ፤ አሁን ግን እጅ ላለመስጠት እየታገልኩ ነው። መሰረት በዚህ ስሜት ውስጥም አንደበቷ አሁንም ነገን ተስፋ የሚያደርጉ ቃላትን ከመወርወር አይመለስም። ወደፊት ነገሮች ተሳክተውልኝ ከዚህም የተሻለ ፈጠራ ፈጥሬ ሃገሬን የማስጠራበት ጊዜ እንደሚመጣ እጠብቃለሁ። ተያያዥ ርዕሶች
ከፋሽን ጥበብ ጋር ያወዳጀውን ነገር ሲያስታውስ ቤተሰቦቼ፣ ከአያቴ ከወይዘሮ ንግሥቲ ጀምሮ፣ ወንዱም ሴቱም አለባበስ አዋቂ፣ ሽቅርቅር ነበሩ ይላል፤ በተለይ ሴቶቹ ዘናጭ ናቸው ሲል ያሞካሻቸዋል።
አያቱ ወይዘሮ ንግሥቲ ነርስ ነበሩ፤ ዘመናቸውን ሁሉ የሃገር ባህል ልብስ ነበር የለበሱት። ይኖሩበት በነበረው አዳማ ናዝሬት የሚያያቸው ሁሉ የሚያስታውሳቸው እንደ ወተት ነጭ በሆነ ቀሚሳቸውና በሹሩባቸው ነው። ዘወትር ይሳለሟት በነበረችው የማርያም ቤተ ክርስቲያን፣ ይቀመጡበት በነበረው ስፍራ ሰው ሁሉ ያውቃቸዋል የሚለው አሮን ሁሉም ሰው በመልካምነታቸው የሚያውቃቸው አያቱ ወ ሮ ንግሥቲን አርዓያ በማድረግ እ ኤ አ በ በስማቸው የፋሽኑን ሃሳብ እውን አደረገ። ከወንጀልነት ወደቀዳሚ መዋቢያነት የተሸጋገረው የከንፈር ቀለም ሁሌም ይህንን የሕይወት ድግግሞሽ ያለማዛነፍ ለዓመታት ኖረውበታል ይላል ስለአያቱ ሲናገር። ይህንን የእማዬን የአለባበስ ዘዬ ሳስብ ከእራሷ አለመጣላቷ ይታሰበኛል። ሌሎችን ለማስደሰትና ለመመሳሰል ተብሎ የሚቀየር ነገር አልነበራትም። አሁንም እኔ በዲዛይኔ የሌሎችን ዱካ የማይከተል፣ የእራሴን ደማቅ መስመር ለማስመር፣ የእራሴን የፋሽን ዓለም ለመፍጠር እየሠራሁ ነው ይላል። ንግሥቲን የሰባት ዓመት ልጅ እያለሁ ነው የጀመርኩት ያለን አሮን ያኔ ግን ስም አልነበራትም፤ ዝም ብዬ የተለያዩ ነገሮችን እነድፍ ነበር ይላል። ከአስተዳደጉ ባሻገር ስምንት ዓመት የኖረባት ፈረንሳይ ስለፋሽን የአቅሟን ማዋጣቷንም ይመሰክራል። ጅማሮ እ አ አ በ ፈረንሳይ ሃገር የሬስቶራንት ባለቤት የሆነች አንዲት ግለሰብ በየዓመቱ የምታዘጋጀው የፋሽን ትርዒት ላይ ልታካትተው እንደምትፈልግ ነገረችው። ፈቃደኛ ሆነና ከሃገሩ ሲወጣ ቢበርደኝ የምደርበው ብሎ የያዘውን ጋቢ ተጠቅሞ የፋሽን ትርዒቱን ተቀላቀለ። ሴት ጓደኞቹን ጠርቶ በጋቢው የተለየዩ የፈጠራ ሥራዎቹን አሳየ። አያቴ ሰነፍ ሆና አታውቅም፤ የምመርጣቸውም ሞዴሎች ሰነፍ አይደሉም፤ እኔም ሰነፍ አይደለሁም። ስለዚህ የምሠራው ሥራ በስንፍና የታጀበ የአረም እርሻ እንዲሆን አልፈልግም። ዘመን የሚሻገር፣ ዘመኑን የሚከተል በጥናት ላይ የተመሠረተ ሥራ ነው የምሠራው ይላል አሮን ስለሥራዎቹ ሲናገር። በኢትዮጵያ ለካንሰር ተጋላጮች እነማን ናቸው በመቀጠልም እኔ የምሠራው ሴቶችን የበለጠ ውብ የሚያደርጉና ደጀን የሚሆኑ ቦርሳዎችን ነው ይላል። ወደ ሃገሩ ሲመለስ፣ የዛሬ ዓመት ቮግ ኢታሊያ፣ ጎተ ኢኒስቲትዩትና ኤፍ ኤ ቱ ፋይቭ ፎር፣ የሚባሉ ማህበራት ባዘጋጁት ውድድር ላይ ሰዎች እንዲወዳደር ጋበዙት። ግብዣውን ተቀብሎ ለውድድር ንግሥቲን ይዞ ቀረበ እናም ለፍፃሜ ደረሰ። ንግሥቲ የሴቶች ፋሽን አብዮት ንግሥቲ የምታተኩረው ሴቶች ላይ ነው። የወንድ ፋሽን ያስቸግረኛል ይላል፤ ቲሸርትና ሸሚዝ ብዙም ጥበብ የማይታይባቸው ፈጠራን የሚያመክኑ ነገሮች ይመስሉታል። የሴቶች ነገር ለፈጠራ የሚያነሳሳኝ ሲሆን የወንዶች ምርጫ ግን በትንሽ ነገር ስለታጠረ ስሜት አይሰጠኝም። አሮን ቀልቡንና ሃሳቡን አዋህዶ የሚጠበብባቸው የፋሽን ሥራዎች ዘመናዊነትን ግለሰባዊ ማንነትን እንዲያሳዩ ይጥራል። የሚሠራቸው ሥራዎች የሴቶች ቦርሳዎች ብቻ አይደሉም፤ አልባሳትም ዲዛይን ያደርጋል። ኢትዮጵያዊያን ለምን ሥጋ አይመገቡም በእራስ መተማመን ያላቸው፣ እራሳቸውን በሃሳብም በቀለምም መግለፅ የሚፈልጉ ሴቶች፤ ችምችም ካለው የሰው ነዶ መካከል ተለይተው መታየት የሚፈልጉ የፋሽን ተከታዮች የእርሱ የገበያ ትኩረት ናቸው። በንግሥቲ የሚሠሩት ቦርሳዎችን ስም ያወጣላቸዋል። ስሞቹ ለእራስ ቅርብ የማድረግ ኃይል እንዳላቸው ያምናል። ለምሳሌ አክሱም ብሎ የሰየመው ቦርሳ የአክሱም ሐውልትን መነሻ አድርጎ የሠራው ነው። ንጉሱ ብሎ የሰየመው ሥራው በሴቶች መካከል የተገኘ ብቸኛው ወንድ ነበር። ስራውን በዚያ ሰየመው። ኮቼላ የተሰኘው ሥራው ደግሞ በአምስት መልኩ መያዝ ይቻላል። ሲቀመጥ ደግሞ እግር ኖሮት ሸረሪት ይመስላል ይላል። ኮቼላ በአሜሪካ የሚዘጋጅ ትልቅ የሙዚቃ ድግስ ነው የሚለው አሮን፣ ቦርሳው እንዲህ ዓይነት ድግስ ላይ የሚገኝ ሰው የሚይዘው ነው ይላል። በከረዩዎችና በኃይለ ሥላሴ መነሻነት የተሠሩ ቦርሳዎችም የእጅ ሥራው ውጤቶች ናቸው። በጥንቸል መነሻነት የተሠራው ሌላው ሥራ ምናለበት የተሰኘው ነው። ሥራዎቹን ለማስተዋወቅ የሚጠቀመው ኢንስታግራምን ሲሆን ከሄሎ ካሽ ጋር በመሆን የእራሱን ድረ ገፅ እየሠራ እንደሆነ ይናገራል። ከድምፃዊ ቤቲ ጂ ጋር የጀመራቸውን ፕሮጀክቶች በቀጣዮቹ ዓመታት በተለያዩ ዓለም አቀፍ መድረኮች ላይ መገኘት ይፈልጋል። ከልጅነቴ ጀምሮ የፍሬንች ሃውስን ዲዛይን ባደርግ ደስ ይለኛል እል ነበር ያለው አሮን ዛሬም ያ የልጅነት ህልሙ ቢሳካ ደስ ይለዋል። ደንበኞች ኢትዮጵያዊያን በሁሉም አቅጣጫ በፋሽን በደንብ አልተገለፁም ብሎ የሚያምነው አሮን ሽሮሜዳና መርካቶ የሚሸጡ የባህል አልባሳት የፋሽን አስተሳሰባችንን ቀፍድደው ሳይዙት አልቀሩም ይላል፤ የፋሽኑ ዓለምም በሚፈለገው መጠን ሲበረታታ አይታይም። የሚታዩ የዲዛይነር ሥራዎችም ጥበብን ማዕከል ያላደረጉ ይበዛሉ ይላል። በቴክኖሎጂ ኢ ፍትሐዊነትን የምትታገለው ኢትዮጵያዊት አሮን የቀደምት አባቶችና እናቶቻችን የፈጠራ እና የጥበብ ውጤት የሆኑትን ሥራዎች በመመልከት በእነርሱ ደረጃ የውሃ ልክነት የእራሱን ሥራዎች መሥራት ይፈልጋል። ላሊበላን በማነፅ ድንቅ የሥነ ሕንፃ ባለሙያነትን ያስመሰከሩ፣ አክሱምን አልያም ፋሲለደስን በማቆም የፈጠራ ልህቀታቸውን መስመር ያሰመሩ ኢትዮጵያዊያን፤ ለፈጠራ እና ለዲዛይን ሥራዬ የመስፈርቴ ጣሪያ ናቸው ይላል። አሮን ኢትዮጵያዊያን በፋሽኑ ዓለም ከምዕራባዊያንም ሆነ ከአፍሪካውያን እንደሚለዩ ተረድቷል። ስለዚህ የፋሽን ሥራዎቹ ሴትነትን የበለጠ እንዲያጎሉ፣ በሚደምቁበት አደባባይም የተሰማሩበትን ተግባር እያከናወኑ፣ የሚከተሉት ፋሽን ደጀን እንዲሆናቸው ይፈልጋል። ሥራዎቹንም ኢትዮጵያዊ አሻራን ከዘመናዊነት ጋር ያጣመሩ እንዲሆኑ ይጥራል።
እሷ ማናት የበለስ ማርማላታ ወደ ውጪ የምትልከው ኢትዮጵያዊት
የሁለት ልጆች እናት ነች። በጽዳትና ተላላኪነት እየሰራች ባለችበት ድርጅት ውስጥ ድንገት ባገኘችው ሥልጠና ታግዛ፤ ከበለስ ማርማላታ በማምረት ለተለያዩ ድርጅቶች መሸጥ ጀመረች። እናት መሆን፣ ቤተሰብ መምራት እንዲሁም የግል ሥራን ማስተዳደር ያሉባት ተደራራቢ ኃላፊነቶች ቢሆኑም በጽናት ሁሉንም ከስኬት ለማድረስ እንደምትጥር ከቢቢሲ ጋር በነበራት ቆይታ ተናግራለች።
የሀዋሳ ታቦር ተማሪዎች የሰብአዊነት ገድል
የሀዋሳ ታቦር ተማሪዎች የሰብአዊነት ገድል ሰኔ ተሻሽሏል ሰኔ ልብን የሚያሞቀው ነጠላ ፎቶ በማህበራዊ ገፆች ላይ በተሰራጨ በጥቂት ሰዓታት ውስጥ ብዙ ሺ ሰዎች ተቀባብለውታል። ምስጋና እና አድናቆትን ያዘሉ አስተያየቶችንም ከብዙ ኢትዮጵያዊያን አግኝቷል። የብዙ ኢትዮጵያዊንን ልብ የነካው የተማሪዎች አድራጎት ቀጣዩ መሰናዶ የሀዋሳ ታቦር መሰናዶ ት ቤት ተማሪዎችን የሰብአዊነት ገድል በትንሹ ያስቃኝችኃል።
በፌስቡክ ከመቶ አምሳ ሺህ ተከታዮች በላይ ያሏት ሕይወት እምሻው
ሴፕቴምበር ማጋሪያ ምረጥ ለመጀመሪያ ጊዜ በማኅበራዊ ሚዲያ ፖስት ያደረግሽው እ ረጂም ጊዜ ነው። በዕውነት አላስታውስም፤ ስለ ሴቶች የሰውነት ቅርፅን ያልጠበቀና ቦታን ያላገናዘበ አለባበስ በተመለከተ የጻፍኩት ይመስለኛል። በከፍተኛ ቁጥር የተወደደው ፖስት እናትና አባቴን በተመለከተ የጻፍኩት ነው። በተለይ በወቅቱ ፈር እየለቀቀ የመጣውን የዘር ፖለቲካ ይመለከት ነበር፤ እናትና አባቴ እንዴት እንደተገናኙ ከዚያም ምን ዓይነት ልጆች እንደተወለድን የጻፍኩበት ነበር። ብዙ ሰዎች ተጋርተውታል፤ ወደውታል፤ ወደ ገደማ ሰው ወዶታል። በዝቅተኛ ደረጃ የተወደደ ሳቅ በጣም ከባድ ነው እውነቱን ለመናገር ስንት ሰው ወደደው ብዬ አልቆጥርም። ቁጥሩን በውል ባላስታውሰውም ግን ከጋርዲያን ጋዜጣ ላይ ተርጉሜ የጻፍኩት ስላቅ ብዙ ሰው አልወደደውም፤ የስላቅና የትርጉም ሥራ ስጽፍ ብዙ ወዳጆችን አያገኝም። ፌስቡክ ላይ የሚያሳዝነው ንባብን የምንለካው በመወደድ ቁጥር ነው። ከ ሶፍትዌር ቀማሪነት ወደ ሥነ ጥበብ ባለሟልነት ያልተጠበቀ የውስጥ መስመር መልዕክት ድምፃዊት ብፅአት ስዩም በውስጥ መስመር የምትጽፊው ጥሩ ነው ስትለኝ ቀኑን ሙሉ ስዘል ነው የዋልኩትን ሳቅ ፤ ደራሲ አዳም ረታም አንዲሁ ሲለኝ ደስ ይለኛል፤ አንዳንዴ የጻፉልኝን በፍሬም አድርጌ መስቀል እፈልጋለሁ። አንድ ጊዜ ደግሞ አውስትራሊያ የሚኖር ኢትዮጵያ በጻፍኩት ታሪክ ተነክቶ አገር ቤት ለመምጣት ወሰነ። ኢትዮጵያ ውስጥ መጥቼ የእናቴን መቃብር ማየት እፈልጋለሁ ብሎ ጻፈልኝ፤ አላየሁትም። በተደጋጋሚ መልዕክቶችን ልኮልኝ አላየሁትም። መጨረሻ ላይ ቢሮ እንግዳ መቀበያ ክፍል ትፈለጊያለሽ ተባልኩ። አንድ ጎልማሳ ሰው ቆሟል። የጻፍሽውን ታሪክ አንብቤ የእናቴን መቃብር ልይ ብዬ ነው የመጣሁት አለኝ። ሽቶና ሌሎችም ስጦታዎች ይዞልኝ መጥቶ ነበር። ያልጠበቅኩት ነገር ነው የሆነው። ፌስቡክ ሳታይ የቆየሽበት ረጅም ጊዜና ምክንያት ባለፈው ዓመት ለ ወራት ለሚጠጋ ጊዜ ጠፍቼ ነበር፤ ፌስቡክ ለከት ያጣበትና የስድብና የጦርነት አውድማ የሆነበት፤ ደስ የሚል ነገር የማይገኝበት፣ የማነበው ሁሉ በአገሬ ተስፋ እንድቆርጥ የሚያደርግበት፤ የሆነ ነገር ስትጽፊ የምትወገሪበት የሆነበት ጊዜ። ያ ነው እጅግ አስቂኙ አስተያየት ሸሌ ነኝ የሚለውን ጽሑፍ ከለጠፍኩ በኋላ የደረሰኝ ነው ዘለግ ያለ ሳቅ ከአገር ከወጣሁ ዓመታት አልፎኛል፤ ነገር ግን አዲስ አበባ ኑሮ ከባድ እንደሆነ አውቃለሁ፤ እንደዚህ ዓይነት አስቀያሚ ሥራ እንድትሠሪ ካስገደደሽ እኔ በየወሩ ዶላር እየላኩ ላስተዳድርሽ እችላለሁ፤ እባክሽን ይሄን ሥራ ተይው የሚል ነበር።
ሌላ መሣሪያ ለመምረጥ ይህን ይለፉ
በቅርቡ በሃገር አሜሪካ የተካሄደ ጥናት እንደጠቆመው ወደ ስራ ቦታ ከማቅናታቸው በፊት ሊፕስቲክ የሚቀቡ ሴቶች ከማይቀቡት የተሻለ ይከፈላቸዋል። የውበት መጠበቂያ ምርት ኢንዱስትሪ በዓመት ቢሊዮን ያንቀሳቅሳል። ተቺዎች የውበት መጠበቂያ ምርት ማስታወቂያዎች ከእውነታው የራቀ ውበት እንደሚያጎናጽፉ ተደርገው ይቀርባሉ ይላሉ። በአንዳንድ የእስያ ሃገራት ቆዳን የሚያነጡ ምርቶችም ለገበያ ይውላሉ። ከእነዚህ ምርጫዎች መካከል የሚፈልጉትን ዕቃ ይምረጡና እንዴት የጭቆና መሣሪያ እንደሆነ ይመልከቱ። መዋቢያ ቁሳቁስ
በሆሄ የስነ ጽሁፍ ሽልማት በእውቀቱ ስዩም፣ አለማየሁ ገላጋይና ዳንኤል ወርቁ ተሸለሙ
ኦገስት አጭር የምስል መግለጫ ዓመታዊው ሆሄ የስነ ጽሁፍ ሽልማት ለንባብ ከበቁ መፃሕፍት መካከል በአንባቢዎች እንዲሁም በሥነ ጽሁፍ ሀያሲያን ዓይን የተደነቁ ሥራዎች የሚሞገሱበት ሆሄ የሥነ ጽሁፍ ሽልማት በይፋ ከተጀመረ ዓመት ሞላው። በሆሄ፤ በተለያዩ የሥነ ጽሁፍ ዘርፎች የላቀ ሥራ ያበረከቱ ጸሃፍት ይሸለማሉ። የሥነ ጽሁፉ ባለውለታዎችም ይሞገሳሉ። የዘንድሮው የሆሄ ሽልማት ሲካሄድ በረዥም ልቦለድ ዘርፍ አለማየሁ ገላጋይ በፍቅር ስም በተሰኘ መጽሀፉ፣ በልጆች መፃሕፍት ዘርፍ ዳንኤል ወርቁ ቴዎድሮስ በተባለ ሥራውና በእውቀቱ ስዩም የማለዳ ድባብ በሚለው የግጥም መድበሉ ለሽልማት በቅተዋል። ለዓመታት መፃሕፍትና አንባቢዎችን በማገናኘት የሚታወቁት መፅሐፍ ሻጩ ተስፋዬ አዳል፣ እንዲሁም እውቆቹ ጸሃፍት ነጋድራስ ገብረህይወት ባይከዳኝ፣ አማረ ማሞ እንዲሁም የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኛ ሴቶች ማህበር ስለ አበርክቷቸው ተመስግነዋል። አጭር የምስል መግለጫ ከተሸማሚዎቹ አንዱ ዳንኤል ወርቁ ደራስያን ያላቸው ሀብት እውቅና ማግኘት ነው የሚለው ዳንኤል ወርቁ፤ ከላይ የተጠቀሱት አንጋፋ ጸሀፍት በተመሰገኑበት መድረክ በመሸለሙ ክብር እንደሚሰማው ይናጋራል። ሥነ ጽሁፍ ደጋግሞ እየወደቀ በሚነሳበት ሀገር መሰል ሽልማቶች ቢበራከቱ ደራስያንን እንደሚያበረታቱም ያምናል። የሥነ ጽሁፍ ሽልማቶች ለደራስያን እውቅና ከመስጠት ባሻገር ለማህበረሰቡ እስኪ ይህን መፅሐፍ አንብቡ የሚል መልዕክት በማስተጋባት ዘርፉን ማበረታታቸው እሙን ነው። ስለ ጠልሰም ወይም በተለምዶ የአስማት ጥበብ ተብሎ ስለሚጠራው ምን ያህል ያውቃሉ ሆሄ በየዓመቱ ከሚታተሙ መፃሕፍት መካከል በሥነ ጽሁፍ መስፈርቶች የተሻሉ የሚባሉትን በሙያተኞች ያስገመግማል። አንባቢያንም ድምጽ በመስጠት የወደዱትን መጽሐፍ እንዲጠቁሙ እድል ይሰጣቸዋል። የንባብ ባህሉ አልዳበረም እየተባለ በሚተች ማህበረሰብ ውስጥ መጽሐፍ አሳትሞ አመርቂ ውጤት ማግኘት ፈታኝ መሆኑን የሚናገረው ዳንኤል፤ የሥነ ጽሁፍ ሽልማቶች መፃሕፍትና ደራሲያንን አስከብረው ዘርፉንም እንደሚያሳድጉ ተስፋ ያደርጋል። አጭር የምስል መግለጫ አለማየሁ ገላጋይ በፍቅር ስም በተሰኘ መጽሀፉ ተሸልሟል ዳንኤል እየተዳከመ የመጣው የረዥም ልቦለድ መጻሕፍት ህትመት እንዲሁም ብዙም ትኩረት ያልተቸረው የልጆች መጻሕፍት ዘርፍ በሽልማቱ መካታቸውን እንደ ምሳሌ ይጠቅሳል። በሀገር አቀፍ ደረጃ በሥነ ጽሁፍ ብቻ ሳይሆን በሌሎች ዘርፎችም ሽልማት መስጠት አዲሰ አይደለም። የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ የሽልማት ድርጅትና የ ዎቹ የኪነ ጥበባትና መገናኛ ብዙኃን ድርጅትም አይዘነጉም። ሁለቱም ግን መዝለቅ አልቻሉም። ከሁለቱ ሽልማቶች በተጨማሪ በግለሰቦች ተነሳሽነት የተጀመሩ ሽልማቶችም ይጠቀሳሉ። ሆኖም ብዙዎቹ ከጥቂት ዓመታት ሲሻገሩ አይስተዋልም። ሆሄ የተወጠነው ለዘርፉ አስተዋጽኦ በማበርከት እንዲዘልቅ ቢሆንም የአቅም ውስንነት እንደሚፈታተናቸው የሽልማቱ አስተባባሪ ዘላለም ምሕረቱ ይናገራል። ከዚህ ቀደም ተጀምረው የተቋረጡ ሽልማቶች ተመሳሳይ ተግዳሮት አንደነበረባቸው ደራሲው ዳንኤልም ይገምታል። ዘላለምና ዳንኤል መሰል የሽልማት መሰናዶዎች ድጋፍ ካልተደረገላቸው ቀጣይነታቸው እንደማያስተማምን ይስማሙበታል። አጭር የምስል መግለጫ መጽሀፍ ሻጩ ተስፋዬ አዳል ለአበርክቷቸው ተመስግነዋል የሽልማት መሰናዶዎች ድጋፍ ካገኙ ዘላቂነታቸውን ከማረጋገጥ ባሻገር አድማሳቸውንም ማስፋት ይችላሉ። ሥነ ጽሁፍ ዘርፈ ብዙ እንደመሆኑ ከልቦለድና ሥነ ግጥም በተጨማሪ ወግ፣ አጫጭር ልቦለዶች፣ የተውኔት ጽሁፍ፣ ኢ ልቦለድ የጽሁፍ ሥራዎችም በውድድሩ ማካተት ይቻላል። በዘላላም ገለጻ ብዙዎች መርሀ ግብሩን ይወዱታል። በገንዘብ መደገፍ ላይ ግን ሁሉም ወደ ኋላ ይላል። ገንዘባቸውን ትርፋማ በሚሏቸው ዘርፎች ማፍሰስ ይመርጣሉ። የሽልማት ዝግጅቶች ብዙ ርቀት የማይራመዱት አንድም በበጀት ውስንነት ሲሆን፤ ከሽልማት አሰጣጥ ጋር በተያያዘ የሚነሱ የፍትሀዊነት ጥያቄዎች እንቅፋት የሆኑባቸውም ይገኙበታል። የኢትዮጵያ ደራስያን ማህበር የሬድዯ መርሀ ግብር ዋና አዘጋጅ ጌታቸው አለሙ አንጋፋና አማተር ደራስያንም ሥራቸው እንደተወደደላቸው የሚመሰከርባቸው የሥነ ጽሁፍ መድረኮች መበራከት አለባቸው ይላል። መፃሕፍትን የማስተዋወቅ፣ ደራስያንን በአንድ መድረክ የማገናኘት ሚና እንዳላቸውም ያክላል። መሰል ሽልማት በትልቅ ተቋም መሰጠት ቢኖርበትም ሆሄ በወጣቶች ተነሳሽነት የተጀመረ ተስፋ ሰጪ ዝግጅት ነው ሲል ሽልማቱን ይገልጻል። የሽልማት መሰናዶዎች ደራስያንን ያሸለሙ ሥራዎች ጎልተው እንዲወጡ፣ በማህበረሰቡ ዘንድ እንዲነበቡ፣ የውይይት መነሻ እንዲሆኑም ያበረታታሉ። ተያያዥ ርዕሶች
ካለሁበት ፡ ራሴንና ልጆቼን የሰሜን ተራሮች ላይ ባገኝ በጣም ደስ ይለኝ ነበር
ዲሴምበር ፌቨን ተወልደ እባላለሁ፤ የምኖረው በፈረንሳይ ፓሪስ ነው ። እዚህ ከመምጣቴ በፊት በአዲስ አበባ ሊሴ ገብረማርያም ትምህርት ቤት በአውሮፓውያኑ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቴን እንደጨርስኩኝ በሊዮን ከተማ የዩኒቨርሲቲ ትምህርት ዕድል አግኝቼ ነበር። እዚያው የመጀመሪያ ዲግሪዬን ከጨረስኩኝ በኋላ ደግሞ ለአንድ ዓመት በዩናይትድ ኪንግደም በርሚንግሃም በትምህርት ልውውጥ መርሃግብር አሳለፍኩኝ። ከዚያ ስመለስ ግን ባለቤቴ ፓሪስ ሥራ ስላገኘ የመጨረሻውን ዓመት በፓሪስ ነው የተማርኩት። አሁን እኔም በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት የባህልና የሳይንስ ተቋም ዩኔስኮ ኢትዮጵያ በምትወክልበት ክፍል ውስጥ እሠራለሁ። የፓሪስን ሥነ ሕንፃ ጥበብ፣ እንደ አይፍል ማማ ያሉ ልዩ መስህቦቿን፣ አስገራሚ ታሪካዊ መገለጫዎችና ልዩ የመታሰቢያ ሃውልቶቿን ሳይ ታሪኳንና ባህሏን የምትገልጽበት መንገድ በጣም ለየት እንደሚያደርጋት አስባለሁ። ከምግቦቿ ደግሞ ታርቲፍሌት የሚባለውን ከድንች ቺዝና ከሥጋ የሚሠራ ምግብ በጣም ደስ እያለኝ ነው የምበላው። በተለይ በብርድ ጊዜ በደንብ ስለሚያሞቅ፣ ሆድም በደንብ ስለሚሞላ በደንብ ነው የምመገበው። አጭር የምስል መግለጫ ከፈረንሳይ ምግቦች ታርቲፍሌት የተሰኘውን ምግብ ነው ከኢትዮጵያ ከምንም በላይ የሚናፍቀኝ ተሰብስቦ ቡና መጠጣቱ ሳይቻኮሉ ጊዜ ወስዶ ከሰው ጋር መወያየቱ ነው፤ እዚህ ለሁሉም ነገር ጊዜ ያጥራል። በፓሪስ ቤቴ ቁጭ ብዬ በማዕድ ቤቴ መስኮቴ በኩል የሚታየኝ አነስ ያለ ግን ዓይን የሚሞላ አረንጓዴ ቦታ ሲሆን ደስ የሚለኝ ውብ ዕይታዬ ነው። ምክንያቱም እዚህ ሀገር ሁሉም ዕይታ ከወቅቱ ጋር ሰለሚቀያየር ለውጦቹን በደንብ የሚነግረኝም፣ የሚያስታውሰኝም ይህ ቦታ ነው። አጭር የምስል መግለጫ የሁለት ወቅቶች ዕይታ በፓሪስ በጣም ያስገረመኝና በሀገሬ ከለመድኩት ታላላቆቻችንን የማክበር ልምድ ጋር የሚቃረነብኝ ነገር በባቡርም ሆነ በአውቶብስ ስሄድ በዕድሜ የገፉ ሰዎችን አይቼ በመነሳት ይመርቁኛል ብዬ ስጠብቅ እነርሱ ግን ትልቅ ናቸው ብዬ ማሰቤ ሲያናድዳቸው አያቸዋለሁ። የመቻል አቅማቸውን የተጠራጠርኩ አድረገው ሲወስዱ በተደጋጋሚ ስለገጠመኝ ከዚያ በኋላ ብዙ አስቤ፣ ተጠንቅቄ ነው የምነሳው። አንድ ቀን ግን በእግሬ ወደ ቤቴ ስመለስ አንዲት በዕድሜ የገፉ ምናልባትም ወደ የተቃረቡ እናት መራመድ አቅቷቸው ድክም ብለው ሳይ አላስችል አለኝና ፈራ ተባ እያልኩ ተጠጋሁ። በአጋጣሚ ግን እውነትም እርዳታ የሚፈልጉ ነበሩና ደስ ብሏቸው እባክሽን ቤቴ ድረስ ደግፈሽኝ እንሂድ፤ እያዞረ እየጣለኝ ነው ሲሉኝ ሀገሬ እያለሁ ይህን በማድረጌ ብቻ ይዘንብልኝ የነበረውን ምርቃት አስብኩኝ ። ሌላው የታዘብኩት እኛና ፈረንሳውያንን የሚያመሳስለን ነገር ለባህላችን የምንሰጠው ቦታ ነው። እዚህም ልክ እንደ ኢትዮጵያውያን ሁሉ በባህሉ በጣም የሚኮራና ከየትኛውም ሀገር የተለየ እንደሆነ የሚያስብ ሕዝብ ነው ያለው። ይህ አቋማቸው በሥልጣኔ አለመደብዘዙ ይገርመኛል። አጭር የምስል መግለጫ ፌቨን ከባለቤቷ እና ከልጆቿ ጋር ሌላው ሁሌም ኢትዮጵያን የሚያስታውሱኝ ፓሪስ የሚገኙት የሚሆኑት የሀገር ቤት ባህላዊ ምግብ ቤቶች ናቸው ። በሙዚየም ውስጥ ስለኢትዮጵያ ታሪክና ባህል የሚዘከርበት ቦታ ብዙ ነው። በእስካሁኑ ቆይታዬ ያዘንኩበት ነገር ልክ ትምህርቴን እንደጨረስኩኝ የትምህርትና የሥራ ልምዴን ሳደራጅ ሲቪ ሳዘጋጅ በወቅቱ የነፃ አገልግሎት የምሰጥበት ክፍል ኃላፊ ዕድሜዬን አይቶ የትዳር ሁኔታ የሚለውን ያላገባ በይው አለኝ። ያኔ ዓመቴ ነበር እና ለምን ስለው ከዚ በኋላ አግብታለች፣ ቀጣዩ ነገር ደግሞ መውለድ ነው ብለው ስለሚያስቡ ሥራ ማግኘት ከባድ ይሆንብሻል አለኝ። በሰለጠነችው አውሮፓ ይህን ስሰማ የሴት እኩልነት ጉዳይ እንዲህ ባፈጠጠ መልኩ እንዳለ መቀበል ከብዶኝ ነበር። ከዚህ ውጩ በፓሪስ ከተማ ውስጥ አንዳች ነገር የመቀየር አቅሙ ቢኖረኝ ኖሮ ከጋራ መኖሪያ ቤት ይልቅ መሬት ላይ ግቢ ያለው ቤት ቢኖረኝ ብዬ እመኛለሁ፤ ልክ እንደ ኢትዮጵያ ኑሮ ማለት ነው። ይህን ለማድረግ ደግሞ ከሥራ ቦታዬ ራቅ ማለት ስላለብኝ ቤት እስክደርስ ብዙ ጊዜ ይፈጅብኛል። ነገር ግን ሁለት ልጆች ስላሉኝ ሩቅ ከሄድኩ ልጅ የሚይዝልኝ ያስፈልገኛል። በሌላ በኩል ደግሞ ከልጆቼ ጋር ማሳለፍ የምችለውን ጊዜ ይገድብብኛል፤ ስለዚህ ሁለቱን ማስታረቅ ስለማልችል ለልጆቼ አደላለሁ። ሆኖልኝ ራሴን በቅጽበት ወደ ኢትዮጵያ መውሰድ ብችል እራሴንና ልጆቼን የሰሜን ተራሮች ላይ ባገኝ በጣም ደስ ይለኝ ነበር። ለክሪስቲን ዮሐንስ እንደነገረቻት
አዲስ አበባ የሁላችንም ከተማ ናት ከንቲባ ታከለ ኡማ
ጁላይ ማጋሪያ ምረጥ አዲሱ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ በንቲ ኢንጂነር የድሃውን ማህረሰብ ፍላጎት ለሟሟላት ተግተው እንደሚሰሩ ለቢቢሲ ተናገሩ። በሥራ ዘመናቸው የከተማዋ ነዋሪ ዋነኛ ችግር የሆነውን የመኖሪያ ቤት እጥረትን ጨምሮ፣ የውሃ እና የትራንስፖርት አገልግሎቶችን በመካከለኛ እና ዝቀተኛ ገቢ ለሚኖሩ የከተማዋ ነዋሪዎች ለማዳረስ ሀሳብ መሰነቃቸውን አክለው ገልጸዋል። የኬሚካል ኢንጂነሪንግ ምሩቅ የሆኑት አቶ ታከለ፤ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አባል ስላልሆኑ በምክትል ከንቲባነት የተሾሙ ቢሆንም የከንቲባውን ሥራ እንደሚሰሩ ተገልጿል። የዲያስፖራው አንድ ዶላር ሹመታቸው ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ የበርካቶች መነጋገሪያ ሆነውም ቆይተዋል። ሹመታቸውን የሚቃወሙ ወገኖች ከሚከራከሩባቸው ምከንያቶች መካከል፤ የከተማዋ ተወላጅ ስላልሆኑ ከተማዋን ለማስተዳደር የውክልና ጉድለት አለባቸው፣ ብሔር ዘመም አቋማቸው የበርካታ ብሔረሰቦች መናገሻ የሆነችው አዲስ አበባን ካለ አድልዎ ለመምራት ያላቸው አቋም አጠራጣሪ ነው የሚሉት ይገኙበታል። በሌላ በኩል ሹመታቸውን የሚደግፉ ሰዎች የሥራ አፈጻጸም ችሎታቸው እንጂ ብሔራቸው ከጥያቄ ውስጥ መግባት የለበትም፣ ተሰናባቹን ከንቲባን ጨምሮ በርካታ የኦሮሞ ተወላጆች ለተከታታይ በርካታ ዓመታት ከተማዋን አስተዳድረዋል የኢንጂነር ታከለ ጉዳይም ከዚህ የተለየ አይሆንም ሲሉ ይከራከራሉ። በእነዚህ ሀሳቦች ላይ ያላቸውን ምላሽ የተጠየቁት አዲሱ ከንቲባ ታከለ ኡማ ለተሰነዘሩት የድጋፍ እና የነቀፌታ አስተያየቶች አክብሮት እንዳላቸው ገልፀዋል። የኤርትራ ኢኮኖሚያዊ ዕቅድ የተነደፈው በኢትዮጵያ ሃብት ላይ ነበር አምባሳደር አውዓሎም ወልዱ አዲስ አበባ የኢትዮጵያዊነታችን መገለጫ፣ የሁላችንም ከተማ ናት ብዬ አምናለሁ። ከኢትዮጵያዊነት አልፎም የአፍሪካዊነት መገለጫ ናት፤ ምክንያቱም የአፍሪካ ህብረት መቀመጫም ናትና። ይህ እምነቴ ዛሬ የመጣ ሳይሆን ከልጅነቴ ጀምሮ አብሮን ያደገ ነው ብለዋል። አዲሱ ከንቲባ ከአዲስ አበባ ብዙም ሳይርቁ መወለዳቸውና ማደጋቸው በከተማዎ ውስጥ የሚኖሩ ብሔር ብሔረሰቦችን ባህል እና ሥነ ልቦናን እንዲረዱት እንዳገዛቸው ተናግረዋል። ለወደፊቱ የከተማዋን ነዋሪዎች በእኩል ዓይን የማስተዳደር፤ በተለይ ደግሞ የድሃውን ማህበረሰብ ፍላጎት ከምንጊዜም በላይ ለማሟላት የተቻላቸውን እንደሚያደርጉም አክለዋል። አቶ ታከለ ከነቲባ ሆነው እስከ ተሾሙበት ጊዜ የኦሮሚያ የትረስንፖርት ቢሮ ኅላፊ ሆነው ሲያገለግሉ ነበር። ከዚያ ቀደምም የተለያዩ የኦሮሚያ ከተሞች ከንቲባ ሆነው አገልግለዋል። ከሦስት ዓመታት በፊት በመላው ኦሮሚያ ተቀጣጥሎ ለነበረው ተቃውሞ ዋነኛ መነሻ ተደርጎ የሚወሰደው የአዲስ አበባ እና የኦሮሚያ ልዩ ዞን የተቀናጀ ማስተር ፕላን የተባለው የመንግሥት እቅድ ነበር። ዕቅዱ ለህዝብ ውይይት ሳይቀርብ የመንግሥት ኅላፊዎች በዕቅዱ ላይ ተወያይተው ነበር። አቶ ታከለም በኦሮሚያ ክልል ቴሌቪዥን በተላለፈ ውይይት ላይ ስለ ዕቅዱ የሰጡት አስተያየት የብዙዎችን ቀልብ የያዘ ነበር። አቶ ታከለ በሰጡት አስተያየት የአንድ ከተማ ፍላጎት ሳይሆን ይህ የማንነት ጥያቄ ነው። አዲስ አበባ እና በዙሪያዋ የሚገኙ ከተሞችን ሊያሳድግ የሚችል ዕቅድ ሲታሰብ የኦሮሞን ማንነት፣ ፖለቲካ፣ ባህል እና ታሪክ ሊጎዳ በማይችል መልኩ መሆን አለበት። አርሶ አደሮችን እየገፋ የሚያድግ ኦሮሚያም ሆነ አዲስ አበባ እኔ በግሌ አልፈልግም ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተው ነበር። የእርሶ መሳሪያ ሚዲያ ፕሌይ ባክን ማጫወት ኣልተቻለም። የልማት ዋጋ ምን ሊሆን ይገባዋል አቶ ታከለም ከቢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ ማስተር ፕላኑን አስመልክቶ የሰጡት አስተያየት የበርካቶች የተቃውሞ ምክንያት መሆን የለበትም ብለዋል። በወቅቱ የሰጠሁት አስተያየት በተለየ መልኩ መተርጎም የለበትም፣ የስጋት ምንጭም መሆን የለበትም ይላሉ። አዲስ አበባ ብቻ ሳትሆን የትኛውም ከተማ ደሃውን ህብረተሰብ መግፋት የለበትም። አሁንም ቢሆን ጥቂት ግለሰቦች የአርሶ አደሩ መሬት ላይ ባለጸጋ ሆነው አርሶ አደሩንና የአርሶ አደሩን ልጅ ጥበቃ እና የጉልበት ሰራተኛ ሆኖ ማየት አልፈልግም። ይህ ደግሞ ኦሮሞን ብቻ የሚመለከት ብቻ ሳይሆን በከተማዋ እና በዙሪያዋ የሚኖሩትን ሁሉ የሚመለከት ነው ብለዋል አቶ ታከለ። ከሳምንታት በፊት ከንቲባ ድሪባ ኩማን የተኩት ታከለ ኡማ የአዲስ አበባ ኛው ከንቲባ ናቸው። ታከለ ኡማ ማን ናቸው አቶ ታከለ ዓ ም በምዕራብ ኦሮሚያ አምቦ አቅራቢያ ተወለዱ። የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን በጎሮ ሶሌ እና ቶኬ ተምረዋል። የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ደግሞ በጉደር እና አምቦ ተከታትለዋል። የ ኛ ክፍል መልቀቂያ ከፍተኛ ውጤት በማምጣት አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከተመደቡ በኋላ በኬሚካል ኢንጂነሪንግ ተመረቁ። በ ዓ ም ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በአካባቢ ምህንድስና ኢንቫይሮመንታል ኢንጂነሪንግ ሁለተኛ ዲግሪያቸውን አግኝተዋል። አቶ ታከለ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪ ሳሉ ንቁ የፖለቲካ ተሳትፎ ነበራቸው። በተማሪነት ዘመናቸው በዶ ር መረራ ጉዲና ይመራ የነበረው የኦሮሞ ብሔራዊ ኮንግረስ ኦብኮ ደጋፊ እንደነበሩ ይናገራሉ፤ በኋላም በ ኦህዴድን ተቀላቅለዋል። አቶ ታከለ የአዲስ አበባ ምክትል ከነቲባ ሆነው ከመሾማቸው በፊት በኦሮሚያ ክልል ደረጃ በተለያዩ የሥራ ሃላፊነቶች አገልግለዋል። ከእነዚህም መካከል የኦሮሚያ ትራንስፖርት ቢሮ ሃላፊ፣ የሱሉልታ ከተማ ከንቲባ እና የሆለታ ከተማ ከንቲባ ሆነው ማገልገላቸው ይጠቀሳሉ። ተያያዥ ርዕሶች
ስለ ማጋራት ተጨማሪ ያጋሩ
ማጋሪያ ምረጥ በኦሮሚያ ውስጥ ከፍተኛ ተቃውሞን ቀስቅሶ የነበረው አዲስ አበባን በዙሪያዋ ካሉ የኦሮሚያ ከተሞች ጋር ያስተሳስራል የተባለው ማስተር ፕላን ተራማጅና አንድ ቀን ተመልሶ ይመጣል ብለው እንደሚያስቡ ኦህዴድ ሊቀ መንበር እና የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት የነበሩት አቶ ኩማ ደመቅሳ ለቢቢሲ ተናገሩ። ባለፈው ሳምንት ኦዴፓ የቀድሞው ኦህዴድ በጅማ ከተማ ድርጅታዊ ጉባኤውን ባደረገበት ወቅት ተሳታፊ የነበሩት አቶ ኩማ ከቢቢሲ ጋር ባደረጉት አጭር ቆይታ አወዛጋቢ ስለነበሩና እርሳቸው በከፍተኛ የስልጣን ሃላፊነት ላይ በነበሩበት ጊዜ ስለታቀዱና ተግባራዊ ስለተደረጉ ጉዳዮች ምላሽ ሰጥተዋል። ኦሮሞ እና አማራን የሚነጣጥሉ አይሳካላቸውም በተለይ በኦሮሚያ ውስጥ ተቀስቅሶ ለረጅም ጊዜ ለዘለቀው ሕዝባዊ ተቃውሞ መነሻ ምክንያት እንደሆነ የሚነገርለትና ከ ጀምሮ ተግባራዊ ይደረጋል ተብሎ የነበረው የአዲስ አበባና በዙሪያዋ ያሉ የኦሮሚያ ከተሞች የተቀናጀ ማስተር ፕላንን በተመለከተ የተሳሳተ አመለካከት እንዳለ ተናግረዋል። ጉዳዩ ከመፈናቀል ጋር አብሮ ስለመጣ እንጂ ተራማጅ አስተሳሰብ ነው ብዬ አስባለሁ በማለት የሚናገሩት አቶ ኩማ፤ ጊዜ ሊወስድ ይችላል እንጂ ማስተር ፕላኑ አንድ ቀን ተመልሶ ይመጣል ብለው እንደሚያስቡ ገልፀዋል። ከዚህ በተጨማሪም በተመሳሳይ ኦሮሚያ ውስጥ ለጠንካራ ጥያቄና ተቃውሞ ምክያት የነበረው የአዳማ ከተማን የኦሮሚያ ክልል መዲና እንድትሆንና የክልሉ መስሪያ ቤቶች ወደዚያው እንዲዘዋወሩ መደረጋቸው ይጠቀሳል። ኦህዴድ አብዮታዊ ዴሞክራሲንና ዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነትን ታሪክ ሊያደርጋቸው ይሆን ስለዚህ ጉዳይ የተጠየቁት አቶ ኩማ ውሳኔው ስህተት እነደሌለበት ያምናሉ። አሁንም ወደኋላ መለስ ብለው ሲመለከቱ አሁንም ያኔ የነበረኝ አቋም ስህተት ነው ብዬ አላምንም ካሉ በኋላ፤ አዳማ የክልሉ ዋና ከተማ ሆና እንደተቀየረች ብትዘልቅ ኖሮ ከተማዋ ታድግ እንደነበር ሲሉ ገልጸዋል። አክለውም ዋና ከተማን በመምረጥ ረገድ ሁሉንም እንቅስቃሴ ተቆጣጥሮ ሥራ ለማከናወን የተሻለው እንደሚመረጥ ጠቁመዋል። በውሳኔው ውስጥም ግፊት እንዳልተደረገባቸው ሲያስረዱም ያኔ ይህንን ያደረገው ሌላ ኃይል ነው የተባለው ውሸት ነው። ውሳኔውን የወሰነው እኔና ከእኔ ጎን የነበሩት ናቸው ብለዋል። ይህም ሆኖ የኦሮሞ ህዝብን መብት የሚነካ ውሳኔ አስተላልፈው እንደማያውቁ በግሌ የኦሮሞ ህዝብ ፋይዳና መብት ላይ ተደራድሬ አላውቅም በማለት አስረግጠዋል ተናግረዋል። ከሰው የሚያገኙትን የድጋፍ ወይም የነቀፋ ምላሽ እንደማያስቡ ተናግረው የኦሮሞን ህዝብ የሚጠቅም ሀሳብ ሁሌም አራምዳለሁ ብለዋል። የካማሼ ዞን አመራሮች በታጣቂዎች ተገደሉ አቶ ኩማ ደመቅሳ የቀድሞው የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት ኦህዴድ ያሁኑ የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ኦዴፓ በክብር ካሰናበታቸው መስራችና ነባር አባላቱ መካከል አንዱ ሲሆኑ፤ በእሳቸው እይታ ትግል የሚካሄደው ማዕከላዊ ኮሚቴ ውስጥ ሆኖ ብቻ ስላልሆነ፤ ከኮሚቴው መሸኘታቸው ከትግል እንደማያግዳቸው ትግል በተለያየ ደረጃ ይካሄዳል በማለት ገልጸዋል። የስንብት ሥነ ሥርዓቱ ሲካሄድ ታላቅ ደስታ እንደተሰማቸው የሚናገሩት አቶ ኩማ፤ ለረዥም ጊዜ የቆዩበትን የትግል ጊዜ በማስታወስ ከእኛ ጎን የነበሩና የተሰዉ ሰዎች ይህንን እድል አላገኙም። እኔ ይህንን እድል ስላገኘሁ ደስታዬ ወሰን የለውም ብለዋል። አቶ ኩማ ደመቅሳ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳደር፣ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ እንዲሁም በተለያዩ የፌደራልና የኦሮሚያ ክልል ከፍተኛ የሃላፊነት ቦታዎች ላይ ለረጅም ጊዜ ሰርተዋል። ተያያዥ ርዕሶች
ይህንን ለማጋራት በ ዋትስአፕ
ከክር የተሠራ ጫማ ለመጫማት ዝግጁ ይሁኑ ዘወትር ማልዳ እየተነሳች የሊስትሮ ዕቃዋን ሸክፋ ፒያሳ ጣይቱ ሆቴል አካባቢ ትሄድና ጫማ ልጥረግሎት ይወልወል ወይስ ቀለም ላድርግሎት እያለች አልፎ ሂያጁን ትጣራለች። በለስ ቀንቷት ሰው ካገኘች እሰየው በትጋትና በቅልጥፍና ጫማ ትሰፋለች፣ ትጠርጋለች፣ በቀለም ታስውባለች። የሊስትሮ ገበያው ተቀዛቅዞ እጆቿ ስራ ሲፈቱ ደግሞ ኪሮሽና ክር እያስማማች ዳንቴል ትሰራለች። ይህ ራሷን በስራ ለመለወጥ ዘወትር የምታትረው መሰረት ፈጠነ የአራት ዓመታት እውነታ ነው። ምንጊዜም ቢሆን ነገ የተሻለ ቀን እንደሚሆን ተስፋ ታደርጋለች፤ ትናንት ያስተማራትም ይህንኑ ነው። ከ ሶፍትዌር ቀማሪነት ወደ ሥነ ጥበብ ባለሟልነት ድንጋይ ከምረን ከላይ ሸራ አድርገን ነበር የምንኖረው መሰረት በ ዓ ም ነበር ከቢሾፍቱ ወደ አዲስ አበባ አምርታ በቤት ሰራተኛነት የተቀጠረቸው። ቀኑን በስራ እየደከመች ማታ ደግሞ የገጠማትን ፈተና እየታገለች ለሶስት ወራት ቆየች። ሁለት ጎረምሶች ያስቸግሩኝ ነበር፤ እኔ የምተኛበት የማዕድ ቤት በር አልነበረውም፤ እነሱ ደግሞ ሳሎን እያደሩ ያስቸግሩኝ ነበር። አንድ ቀን ስራ ስላልነበረ ቤት ውስጥ በር ቆልፈውብኝ ሊታገሉኝ ሞከሩ፤ ጩኸቴ በቤቱ ሲያስተጋባ ተድናግጠው ተዉኝ። መሰረት በጊዜው በአካባቢው ሰው በመኖሩ ከጥቃቱ ብትተርፍም አንድ ትልቅ ውሳኔ ላይ ደረሰች። ምርር ስላለኝ በቃ ካሁን በኋላ የመኪና አደጋም ቢደርስብኝ፤ ምንም ቢሆን ሰው ቤት አልገባም ብዬ ወጣሁ። ለሃገሩ ባዳ የነበረቸው መሰረት ማደሪያ ስላልነበራት ከዚያን ቀን ጀምሮ መዋያዋ ማደሪያዋም ጎዳና ሆነ። የኢትዮጵያ ተረት ገፀ ባህሪን በአኒሜሽን የእለት ጉርሷን በተገኘው ትርፍራፊ እየሞላች ስታጣም አንጀቷን እያጠፈች ማደር ጀመረች። ቆየት ብሎ ደግሞ እዛው በጎዳና ከተዋወቀችው ወጣት ጋር በመጣመር እንደ አቅሟ ጎጆ ቀለሰች። ስድስት ኪሎ ዩኒቨርሲቲው አምስተኛ በር አካባቢ ድንጋይ ከምረን ከላይ ሸራ አድርገን ነበር የምንኖረው፤ አንዳንድ ቀን ፖሊሶች ያባርሩናል፤ ዝናብ ሲሆን ድንገት ይመጡብናል፤ በተለይም ስብሰባ ካለ በጣም ያስቸግር ነበር መሰረት ከኑሮ ጋር የያዙት ግብ ግብ እስከመቼ እንደሚቀጥል በተደጋጋሚ ራሷን ትጠይቅ እንደነበረ ትናገራለች። ባለቤቷ በዱቤ የወሰደው የሊስትሮ ሳጥን የተስፋ ጭላንጭል ይዞላት ቢመጣ ብላ አንድ ቀን እሱ በሌለበት የራሷን እርምጃ ወሰደቸ። ድንገት ተነስቼ ጫማ ይጠረግ ጫማ ይጠረግ ብዬ መጮህ ጀመርኩኝ፤ ሊስትሮ እሰራለሁ ብዬ አስቤ አላውቅም ግን ራሴን አሳመንኩኝ፤ ያኔ የጫማ ማሰሪያ መፍታትም ሆነ ማሰር አልችልም ነበር፤ የመጀመሪያው ሰው ሲቀመጥልኝ ካልሲውን ቀለም አስነክቼበት ተናዶብኝ ነበር። መሰረት የሊስትሮ ስራውን እንዲህ ጀምራው ለሁለት ወራት ከሰራች በኋላ ኑሮ ሲፈትናት በመሃል ወደ ባለቤቷ ሃገር ወላይታ ብትሄድም አሁንም ተመልሳ የሊስትሮ ስራዋን በፒያሳ ጣይቱ ሆቴል አካባቢ ቀጠለች። መሠረት ልጇን ታቅፋ የስድስት ቀን ጨቅላ ይዤ ወደ ስራ ተመልሻለሁ ፈተና ከእሷ ብዙም አልራቀምና መሰረት የሶስት ወር ጽንስ መያዟን አወቀች። ስምንት ወር እስኪሆናት ድረስ አጎንብሳ ጫማ መጥረጓን አላቆመችም ነበር። ወልጄም ከስድስተኛ ቀን ጀምሮ እዛው ተመልሼ ሰርቻለሁ። ያው በስድስት ቀን ስወጣ እንግዲህ ጨቅላዋ አትታዘልም ገና ደም ናት፤ ስለዚህ ትንሽዬ ነገር አንጥፌ አጠገቤ አስተኛትና ከዛ በጥላ እከልላታለሁ፤ እንዲያውም በአጋጣሚ ድምጽ ስታሰማ ሰዎች ይደነግጡ ነበር። ለሶስት ወራት ገደማ በዚህ ሁኔታ ከሰራች በኋላ ክረምት ሲገባ ህጻኗን ብርድ ይመታብሻል የሚል ተግሳጽ ቢያይልባት ተመልሳ ልጇን ይዛ ወደ ገጠር ገባች። ጥቂት ቆይታ ስትመለስም ልጇን እዚያው አጠገቧ እያደረገች በየአካባቢው እየዞረች ስትሰራ ቆይታ ሲቪል ሰርቪስ አካባቢ እንደወትሮው ሁሉ ገበያው በተቀዛቀዘበት ጊዜ ዳንቴሉን ስትሰራ የተመለከተቻት አንዲት ሴት ያቀረበችላት ጥያቄ ለዛሬው ፈጠራዋ መንገድ ቀየሰላት። ዳንቴል ከቻልሽ እኔ አሰራሻለሁ ብላኝ ለወር አካባቢ እኔ ቤት ውስጥ እየሰራሁኝ የዳንቴል ስራውን እያጋመስኩላት እርሷ ደግሞ እያጠናቀቀችው ጫማ ሲሆን አየሁ። ግን ለወር አካባቢ ሰርቼ በህመም ምክንያት አቋረጥኩት። መሠረት የምትሠራቸውን ምርቶች ስታሳይ ያለ አንዳች ማሽን የምትሰራው የዳንቴል ጫማ መሰረት በጊዜ ሂደት እሷ ዳንቴል ከመሰራት የዘለለ ሚና ባልነበራት ስራ የጎደለውን እውቀት ለመሙላት መፍጨርጨር ጀመረች። እስከ ሶስተኛ ክፍል ብቻ የዘለቀችበት ትምህርት ለዚህ ምንም እንደማይጠቅማት ብታውቅም ተስፋ አልቆረጠችም። መጀመሪያ በሰው እግር እየለካሁኝ ይሄ ተጠቅጥቆ ጫማ መሆን ይችላል እንዴ እያልኩኝ በወንድ ጫማ መሞከር ጀመርኩኝ፤ የሚሆን አልመሰለኝም ነበር፤ ግን በመጨረሻ ተሳካልኝ። ከዛ የሴት ጫማ እያልኩኝ፣ ነጠላ ጫማ እያልኩኝ የወንድ ሸበጥ እያልኩኝ ቀጠልኩ። መሰረት አሁን የሙከራ ሂደትን አልፋ ክፍትና ሽፍን የወንድና የሴት ጫማዎችን፣ የአንገት ልብስ፣ ቀበቶና አልጋ ልብስ በዳንቴል ያለምንም የፋብሪካም ሆነ የማሽን እገዛ በእጆቿ ትሰራለች። የምሰራበት ክር በጣም ጠንካራ ነው፤ ከጅማትም ይጠነክራል፤ ጅማት እንደውም ብዙ ጊዜ እኔ ሊስትሮ እያለሁ ስታገለው ወይ ደግሞ ጫማው በጣም ደረቅ ከሆነ ስስበው የሚበጠስበት አጋጣሚ ነበር። ክር ግን ከዚያም ይጠነክራል፤ ሶሉ ትንሽ ስለሚያስቸግር ነው እንጂ አንድ ሰው እስከ አምስት ዓመት ይሄን ጫማ እንደሚያደርግ እተማመናለሁ። መሰረት የአንድ ንድፉ ያለቀለትን ጥንድ ጫማ የዳንቴል ሥራ በአንድ ቀን ውስጥ ታጠናቅቃለች። የመሠረት ጫማዎች ቀጣዩ ሥራዋ ደግሞ ዳንቴሉን በእግር ቅርጽ በተሰራ የጫማ መወጠሪያ አድርጎ በመርካቶ ለመቀየሪያነት የሚሸጡ ማጫሚያዎችን ሶሎችን በመጠቀም በማስቲሽ ማያያዝ ነው። ጉርድ ሾላ አካባቢ ከአምስት ዓመት ልጇ ጋር ተከራይታ በምትኖርበት ጠባብ ባለ አንድ ክፍል ቤት ውስጥ አዳዲስ ዲዛይኖች እያወጣች ወደ ተግባር ትቀይራለች። አምስት የነጠላ ጫማ ዲዛይን አለኝ። ቀጭን ሶል ባላቸው ፍላት ደግሞ ለሴትም ለወንድም በሸራ መልክ ሁለት አይነት ጫማ እሰራለሁ፤ ቡትሶች፤ ቦርሳዎችና ቀበቶዎችም አሉኝ። መሰረት ጫማዎቹን መስራት ከጀመረች ሁለት ዓመታት ቢቆጠሩም በጣም ትልቅ ስራ ሰራሁ የምትለው ባለፈው ሰኔ በትዕዛዝ የሰራቻቸውን ጫማዎች ነው። በቂ ትዕዛዝ አላገኝም፤ በሰፊው ለገበያ ለማቅረብም የገንዘብ አቅም የለኝም፤ በወር አንድ ወይም ሁለት ጫማ ሊመጣ ይችላል። ከዚህ በፊት ይሄ እንጀራዬ ነው ለብዙዎችም ምሳሌ እሆናለሁ በሚል ተነሳሽነት ትዕዛዝ ኖረም አልኖረም ሰዓት እሰራ ነበረ፤ አሁን ግን እጅ ላለመስጠት እየታገልኩ ነው። መሰረት በዚህ ስሜት ውስጥም አንደበቷ አሁንም ነገን ተስፋ የሚያደርጉ ቃላትን ከመወርወር አይመለስም። ወደፊት ነገሮች ተሳክተውልኝ ከዚህም የተሻለ ፈጠራ ፈጥሬ ሃገሬን የማስጠራበት ጊዜ እንደሚመጣ እጠብቃለሁ። ቢቢሲ ማስተባበያ
የአፍሪካ ዋንጫ በየአራት ዓመቱ እንዲካሄድ ሀሳብ ቀረበ
ፌብሩወሪ ማጋሪያ ምረጥ የፊፋ ፕሬዝዳንት ጂያኒ ኢንፋንቲኖ የአፍሪካ ዋንጫ በየሁለቱ ዓመቱ መካሄዱ ቀርቶ በአራት አመት አንዴ ብቻ አንዲካሄድ ለአፍሪካ እግር ኳስ ማህበር ካፍ ሃሳባቸውን አቅርበዋል። ኢንፋንቲኖ በሞሮኮ እየተካሄደ በሚገኘው የካፍ ስብሰባ ላይ ባደረጉት ንግግር በየሁለት ዓመቱ የሚካሄደው አፍሪካ ዋንጫ አውሮፓውያኑ ከሚያስገኙት ሲነጻጸር ገቢው በሃያ እጥፍ ያነሰ ነው። በዚህ አካሄድ በየሁለት ዓመቱ ማካሄዱ አዋጪ ነው እስቲ በየአራት ዓመቱ ማካሄድን ከግምት ውስጥ እናስገባው ብለዋል። አፍሪካ የዓለም ዋንጫን ለማዘጋጀት አዲስ አሰራር እንዲኖር ትፈልጋለች ቀጣዩ የአፍሪካ ዋንጫ በጎርጎሳውያኑ በካሜሩን አዘጋጅነት የሚካሄድ ሲሆን ልክ እንደ ቀድሞው ጥርና የካቲት ላይ ሀገራት ውድድር ያደርጋሉ። ባለፈው ዓመት የአፍሪካ ዋንጫ ቀድሞ ከሚካሄድበት ወቅት በተለየ መልኩ ሰኔ እና ሐምሌ ላይ ግብጽ ውስጥ ተካሂዶ ነበር። በዚሁ ውድድር ተሳታፊ ሀገራት ቁጥርም ወደ ከፍ እንዲል ተደርጓል። የፊፋው ፕሬዝዳንት በንግግራቸው አክለውም ለአፍሪካ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሄዎችን ማዘጋጀት ያስፈልጋል። በእኛ በኩል ሶስት መፍትሄ የሚያስፈልጋቸው ነጥቦችን ለይተናል፤ እነሱም ዳኝነት፣ መሰረተ ልማት እና ውድድሮች ናቸው ብለዋል። አክለውም አሁን ስለአፍሪካ እግር ኳስ እድገት ብቻ የምናወራበት ሰአት ሳይሆን እርምጃ የምንወስድበት ጊዜ ላይ ነው ያለነው። የትኛውም የአፍሪካ ሀገር ዓለም ዋንጫን አሸንፎ አያውቅም፤ ለምን ብለን መጠየቅም ይገባናል። የአፍሪካ እግር ኳስ ቅሌት ከዳኝነት ጋር በተያያዘ ፊፋ የተመረጡ ዳኞችን በገንዘብና በስልጠና በመገደፍ ለአህጉሪቱ እግር ኳስ እድገት የበኩላቸውን እንዲወጡ ለማድረግ እንዳሰበም ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል። ከዚህ በተጨማሪም የአፍሪካ እግር ኳስ አሁን ካለበት ደረጃ ከፍ በማድረግ በዓለማቀፍ ደረጃ ተፎካካሪ ለማድረግ ፊፋ ቢሊየን ዶላር ፈሰስ ለማድረግና በእያንዳንዱ አባል ሀገር አንድ ዘመናዊ ስታዲየም ለመገንባት እቅድ መያዙም በስብሰባው ላይ ተገልጿል። ተያያዥ ርዕሶች
እራስን መፈለግ፣ እራስን መሆን ፣ እራስን ማሸነፍ
ኤፕረል ማጋሪያ ምረጥ ጥበብን ለዕለት ጉርስ ማግኛ ሳይሆን እራስን ለመግለጥ ብቻ ትጠቀምበት እንደነበር ትናገራለች ሐይማኖት። የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቷን ካጠናቀቀች በኋላ ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋም መግባት የመረጠችው የቤተሰቦቿን ደስታ ላለማክሸፍ ብላ እንጂ በርግጥም በተማረችበት ሙያ ተቀጥራ መንፈሷንም ኪሷንም በእርካታ መሙላት እንደማትችል ቀድሞ ገብቷት ነበር። በቅድሚያ ሠዓሊ እንደምሆን አውቅ ነበር የምትለው ሐይማኖት የሥዕል ችሎታ እንደነበራት እና እንደምትስልም ወደ ኋላ መለስ ብላ ታስታውሳለች። እርሷ ወደ ሥዕሉ ብትሳብም ቤተሰቦቿ ግን ለኪነ ጥበቡ ያላቸው ግንዛቤ ተሰጥኦዋን በትምህርት እንዳታስደግፈው አድርጓታል። ከዚህም ባለፈ እርሷ የሕግ ትምህርት ቤት ብገባ ብላ ታስብ ስለነበር ያ ሳይሆን ሲቀር የቤተሰቦቿን ደስታ ብቻ ለማሳካት የአስተዳደር ሙያ አጥንታ ተመረቀች። በከፍተኛ ትምህርት ተቋም ውስጥ እያለች ወዳጆቿ በተለያዩ የኪነ ጥበብ ዘርፍ የተሰማሩ ነበሩ። እነርሱ በሚያዘጋጇቸው የተለያዩ አውደ ጥበቦች ላይ እየተገኘች ተሰጥዖዋን ለማሳየት ትጥር ጀመር። የሥዕል ችሎታዋንም ለማዳበር አጫጭር ኮርሶችን ወስዳለች። አጭር የምስል መግለጫ እናትና ልጅ ጎዳና ላይ እየሄዱ ያነሳችው ይህ ፎቶግራፍ መቼም አይረሳትም የፎቶግራፍ ጥበብ ሐይማኖት ሠዓሊ የመሆን ፍላጎቷን የመኮትኮትና የማሳደግ ሕልሟ በውስጧ እንዳለ ቢሆንም ፎቶ ግራፍ የማንሳት ጥበብ ዝንባሌዋ ደግሞ እያየለ መጣ። ስለዚህ የተለያዩ ፎቶዎችን በስልኳ እያነሳች ለባልንጀሮቿ ታሳይ ጀመር። ከጓደኞቿ የምታገኘው አድናቆትና ውዳሴ ልቧን ያሸፍተው ጀመር። ከዚያ በኋላ መደበኛ ካሜራ በመጠቀም ስሥዬ ሆይ ብላ ፎቶ ማንሳቱን ገባችበት። ሐይማኖት ፎቶ ስታነሳ እንደሠርግ እና ልደት ያሉ ከበራዎች ላይ ተገኝታ ማንሳት ምርጫዎቿ እንዳልሆኑ ትናገራለች። ከዛ ይልቅ የጎዳና ላይ ትዕይንቶችን እየተከተሉ እና እየፈለጉ በማንሳት የምትፈልጋቸው ቁምነገሮች ጎልተው በሌሎች ዓይን እንዲታዮላት ትፈልጋለች። ባለፈው ዓመትም ያነሳቻቸውን ፎቶዎች ሰብሰብ አድርጋ ለሕዝብ እይታ እንዳበቃች ታስረዳለች። እነዚህ ፎቶዎች ስሜቷን ለመግለጥ ብቻ ሳይሆን የዕለት ጉርሷንም ለመሸፈን ረድቷታል። ሐይማኖት ሥራዎቿን ለማስተዋወቅ የማህበራዊ ድረ ገፆችን እንደመንገድ እንደምትጠቀምበት ትናገራለች። ካነሳቻቸው ምስሎች ባጠቃላይ የማትረሳው እናትና ልጅ ጎዳና ላይ እየሄዱ ያነሳችውን ነው። ይህንን ፎቶ ስታስታውስም ፎቶ ማንሳት በሽርፍራፊ ሰከንድ ውስጥ ያሉ ኹነቶችን ቶሎ ለቀም አድርጎ መያዝ ነው። ያ ፎቶም እነዚያን ሽርፍራፊ ሰኮንዶችን ያስቀረሁበት ስለነበር በርካቶች ወደውታል ትላለች። አጭር የምስል መግለጫ የተለያዩ የዲዛይን ጥበብ ሥራዎቿ የዲዛይን ጥበብ ሐይማኖት በተማረችበት ሙያ ለሁለት ዓመት ያህል በተለያየ ቦታ ተቀጥራ ሠርታለች። የፎቶግራፍ ጥበብን እንደ የሕይወት ጥሪ ተቀብላ የጎዳና ላይ ፎቶዎችን እያነሳች እና ፎቶዎችን እየሸጠች ደግሞ በቋሚ ገቢ ማግኛነት መጠቀም እንደማትችል ተረዳች። ይሄኔ እራሷን በእራሷ ወዳስተማረችው የተለያዩ ነገሮችን የማስዋብ ሙያ ፊቷን አዞረች። በሁለት ዓመት ውስጥ ሦስት ሥራዎችን ቀያይሬ ነበር የምትለው ሐይማኖት፤ ቋሚ የወር ገቢ የምታገኝበትን ሥራዋን ትታ ወደጥበብ ሥራዎች ፊቷን ስትመልስ ቤተሰቦቿም ሆነ ወዳጆቿ ሐይማኖት ምን ነክቶሻል የሚል ተግሳፅ እንደገጠማት ታስረዳለች። ማንም በተሰጥዖዋ ውስጥ እራሷን እንድትፈልግ እና እራስዋን እንድትሆን እንዳላበረታታት የምትናገረዋ ሐይማኖት ይህ ደግሞ ፈታኝ እንደነበረባት አልሸሸገችም። የተለያዩ ነገሮችን እየሠራሁ ለእራሴም ሆነ ለባልንጀሮቼ እሰጥ ነበር የምትለው ሐይማኖት፤ ለመጀመሪያ ጊዜ የሠራቻቸውን ጆሮ ጌጦች ይዛ በአካባቢዋ ወደሚገኘው ድንቅ የአርት ጋለሪ አመራች። እውነቱን ለመናገር ሥራዎቼ ጥሩ አልነበሩም። አዲስ ነገር ለመሥራት ሙከራ ያደረኩባቸው ነበሩ የምትለዋ ሐይማኖት በአርት ጋለሪው ያገኘቻቸው ሰዎች ምክር እንደለገሷት አትረሳም። እነዚያን ምክሮች ወስዳ የእራሷን የእጅ አሻራዎች በማሳረፍ መሥራት ቀጠለች። በኋላም በጥሩ ሁኔታ የሠራቻቸውን ጌጣ ጌጦች እዛው ጋለሪ ውስጥ መሸጥ ጀመረች። ሐይማኖት ሥራዎቿን ለማስዋብም ሆነ የእራሷን አሻራዎች ለማሳረፍ የምዕራብ አፍሪካዊያንን የተለያዩ ውጤቶች እንደምትጠቀም ትናገራለች። ሁልጊዜም ቢሆን አዲስ ነገር ለመሞከር እና እራሷን ለማስተማር እንደምትተጋም ታስረዳለች። አነስተኛ ጌጣ ጌጦችን ብቻ ሳይሆን የእራስጌ መብራቶችን፣ የትራስ ጨርቆችን ጥለቶችን በመጠቀም እያስዋበች ለሃገር ውስጥ እና ለውጭ ሃገር ደንበኞቿ ትሸጣለች። አጭር የምስል መግለጫ የተለያዩ የእጅ ሥራዎቿ የእጅ ሥራ ውጤትና ኢትዯጵያውያን እኛ ሃገር በእጅ ለሚሠሩ ውጤቶች የሚተመነው ዋጋ እጅግ በጣም ዝቅ ያለ ስለሆነ ብዙ ደንበኞች ለማግኘት ያስቸግራል ትላለች ሐይማኖት። ስለዚህ ሥራዎቿን ለመግዛት ከኢትዮጵያውያን ይልቅ የውጭ ሃገር ዜጎች ይደፍራሉ። ተቀጥሮ መሥራት በገቢ ደረጃ የምትተማመንበት ነገር እንዲኖር ያደርጋል የምትለዋ ሐይማኖት፤ ቋሚ የወር ገቢን ትቶ የእራስን ተሰጥዖ ተጠቅሞ ገቢ ማግኘት ፈተና እንደሆነም አልሸሸገችም። በመቀጠልም ሐይማኖት ገበያ ለማግኘትም ሆነ ቋሚ የመሥሪያ እና የመሸጫ ቦታ እንዲኖራት ጥረት እያደረገች እንደሆነ ትናገራለች። ነገር ግን ጥረቷን እንደሥራ ፍሬዋ በመውሰድ እና በምታገኛቸው ትናንሽ ውጤቶች ደስተኛ በመሆን ዛሬን እየኖርኩ ነገን ትልቅ አልማለሁ ትላለች። አሁን ከተማዋ ውስጥ የተለያዩ እንቅስቃሴዎች መኖራቸው ለሥራዎቿ ገበያ ለማግኘት እንዳገዛት ታስረዳለች። በተለይ አውደ ርዕዮች ሲበዙ እና ቀን እና ለሊት ከእንቅልፍ ተፋትታ የምትሠራቸው ሥራዎች የበለጠ እንደሚመስጧት ትናገራለች። የእርሶ መሳሪያ ሚዲያ ፕሌይ ባክን ማጫወት ኣልተቻለም። ሐይማኖት ሆነልኝ ውልደቷ እድገቷ አዲስ አበባ ነው። ተያያዥ ርዕሶች
ዕድሜ ጠገቧ የጥድ መፃሕፍት ቤት መደብር ባለቤት አቶ ተስፋዬ አዳል
ጁላይ ስለ ማጋራት ተጨማሪ ያጋሩ ማጋሪያ ምረጥ በአሁኑ ወቅት መጽሐፍ የሚፈልግ ቢያሻው ወደ ብሔራዊ ቲያትር ካልሆነም ፒያሳ ጊዮርጊስ ማቅናት የተለመደ ነው። የጠፉ መጻሕፍትን የሚፈልግ ደግሞ ሜክሲኮ ሊወርድ ወይም መርካቶ ሊወጣ ይችላል። የአጋጣሚ ነገር ሆኖ የመጻሕፍት ጉልቶች እጅብ ብለው ነው የሚገኙት። ከአቶ ተስፋዬ በቀር። አቶ ተስፋዬ ጋንዲ ሆስፒታል አካባቢ አድቬንቲስት ቤተ ክርስቲያን አጥር ጥግ በፅድ ተከርክሞ በተሠራ መጽሐፍ መሸጫ ውስጥ ተቀምጠው ለደንበኞቻቸው መጻሕፍትን ሲያከራዩና ሲሸጡ ለዘመናት ኖረዋል። ከወጡት ስራዎቼ ይልቅ ገና የሚወጡት ናቸው ትልቅ ቦታ ያላቸው አለማየሁ ገላጋይ በአፄ ኃይለሥላሴ ዘመነ መንግሥት ሥራ ሲጀምሩ ጋዜጣ በመሸጥ ነበር። በወቅቱ የነበሩትን እነ ታይም፣ አዲስ ዘመን፣ ኒውስ ዊክ፣ የዛሬይቱ ኢትዮጵያ፣ ሪደርስ ዳይጀስት፣ አፍሪካ ጆርናል፣ ሄራልድ ትሪቢዩን፣ የኤርትራ ድምፅ፣ የድሮዋን ቁም ነገር መጽሔት፣ ጎህን እያዞሩ ይሸጡ ነበር። በንጉሱ ስርዓት መውደቂያ አካባቢ ከመፅሔቶቹ ይልቅ የማኦ ሴቱንግ መፃህፍቶች እየበዙ እንደመጡ ይናገራሉ። እነዚህን መጻሕፍት ከአከፋፋዮች አንዱን በ ሳንቲም ዋጋ ተረክበው ሲቀና መቶ ሳይሆን ሀምሳውን በአንድ ቀን ሸጠው ያድራሉ። በወቅቱም ለነዚህ መፃህፍት ከፍተኛ ፍላጎት እንደነበር ያስታውሳሉ። በዚህም የተነሳ አንዳንድ የሀገር ውስጥ አሳታሚዎች የማኦ ጥቅስን የያዙ፣ የፖለቲካ የኢኮኖሚ ሥራዎችን፣ አራቱ ድርሰቶች፣ የቦልሼቪክ ፓርቲ፣ የሴቶች ጥያቄ፣ የቬትናም አብዮት የሚሉ የወቅቱን እንቅስቃሴ የሚያንፀባርቁ መጽሐፎች ብቅ ብቅ ማለት እንደጀመሩ ይናገራሉ። እነዚህ መጻሕፍት ሲመጡ በከተማው ፈላጊያቸው ብዙ እንደነበር ከትዝታ ከረጢታቸው ፈትተው አጫውተውናል። አቶ ተስፋዬ እና ባልደረቦቻቸው እነዚህን መጻሕፍት እያመጡ ይቸበችቡት ያዙ። ከዚህ በኋላ ደግሞ በሀገር ውስጥ የነበሩ መፃህፍት የቀድሞ ታላላቅ የሀገራችን ሰዎች የተማሩባቸው፣ ታሪክን የሚነግሩ፣ ከየትምህርት ቤቱ እና ከየድርጅቱ እየወጡ መጣል ጀመሩ። እነዚህ መጽሐፎች የሚጣሉና የሚወድቁ አልነበሩም ይላሉ አቶ ተስፋዬ። ፍቅር እስከ መቃብር ን በአይፎን በወቅቱ የነበረው መንግሥት ግን መጻሕፍቱ እንዲጣሉ አልያም ተሰብስበው እንዲቃጠሉ ያደርግ እንደነበር አቶ ተስፋየ ያስታውሳሉ። የየትምህርት ቤቶቹ ርዕሳነ መምህራን ግን እነ አቶ ተስፋዬን እየጠሯቸው ሳይቃጠል ከተጣለበት እንዲወስዱ ያደርጉ ነበር። ስለዚህም እነዚህን መጻሕፍት በትንሽ ዋጋ እየገዙ መሸጥ ጀመሩ። ያኔ እነዚህን መጻሕፍት እያዞሩ መሸጥ መዘዝ ነበረው። መጻሕፍቱ ውስጥ የጃንሆይ ምስል ከተገኘበት ያለምንም ጥያቄ አምስት ወራትን ያሳስር ነበር። ስለዚህ የጃንሆይን ምሥሎች እየፈለጉ መገንጠልና ማስወገድ የግድ ነበር። በመጻሕፍት የተነሳ ታስሬ አውቃለሁ የታሰሩበትንም ምክንያት ሲያስረዱም በደርግ ሥርዓት ውስጥ የሹራብ ነጋዴውም፣ የካልሲ ነጋዴውም አፈሳ ተብሎ ልቅምቅም ተደርጎ ታፈሰ በማለት ይጀምራሉ። መጽሐፍት ነጋዴውም ሕገ ወጥ ነው ብለው ያዙን። ስድስተኛ ፖሊስ ጣቢያ እስከ መጽሐፎቻችን ታሰርን። አቶ ተስፋዩ እና ሌሎች መፃሕፍት ሻጮች ለ ቀን ያህል በእስር ሳሉ ደራሲ ማሞ ውድነህ ለግል ጉዳያቸው ስድስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ይመጣሉ። በሩ ላይ መጽሐፍ ተደርድሮም ያያሉ። ቀዩን ረዥሙን ደራሲ ማሞ ውድነህን ፖሊሱ አላወቃቸውም ነበር። ጋሽ ማሞ ሰዓት ላይ በእጃቸው ላይ የሆነች ወረቀት ይዘው ነው ወደ ስድስተኛ የገቡት። ቀና ብለው ሲያዩ መጽሐፍ ተደርድሯል። አቶ ማሞ ለካ መጀመርያ መጽሐፉን ሲያዩ ለእስረኞች እንዲያነቡት የመጣላቸው ነው የመሰላቸው። ዛሬስ ለእስረኞቻችሁ መጽሐፍ ቤት ከፈታችሁ እንዴ በማለት እንዳደነቁ አቶ ተስፋዬ ይናገራሉ። የጥበቃ ጓዱ ከመጻሕፍት ነጋዴዎች ጋር አብረው የታሰሩ መጻሕፍት እንደሆኑ አስረዳቸው። ማሞ ውድነህ ሐዘን ገባቸው። በተለይም የኢትዮጵያ ታላላቅ ደራሲያን መፃሕፍትን፣ እነ ፍቅር እስከ መቃብር፣ እነ ከአድማስ ባሻገር፣ የከበደ ሚካኤል፣ የራሳቸው የማሞ ውድነህ እነዚህ ሁሉ መጻሕፍት ታስረውና ያለፍርድ እዛ ተቀምጠው ሲመለከቱ ማሞ ውድነህ ከፋቸው። በዚህን ጊዜ አቶ ማሞ ከጥበቃ ጓዱ ጋር እሰጥ አገባ ገጠሙ። የጣቢያውን አዛዥም ቢሮው ገብተው ጎትተው በማምጣት ከመፃሕፍቱ ክምር ጋር አፋጠጡት። አዛዡ አላወቅኩም ብሎ ካደ። ወቅቱ በራሪ ወረቀት የሚበተንበት ስለነበር ይላሉ አቶ ተስፋዬ፣ ማሞ ውድነህ በራሪ ወረቀት በእጃቸው እንዳይገኝ መክረው በሌላ ጉዳይ ግን ከጎናቸው መሆናቸውን ጠቅሰው የጣብያው አዛዡንም የመጻሕፍት ሻጮቹን ዳግመኛ እንዳይታሰሩ አደራ ብለው አስፈቷቸው። አቶ ተስፋዬም መጻሕፎቻቸውን ይዘው ወደ መሸጫቸው አመሩ። መጽሐፍን እንደ ጉቦ ከዚያ በኋላም ቢሆን አቶ ተስፋዬ መጽሐፍ ሲሸጡ ከአብዮት ጥበቃ ጋር እየታገሉ እንደነበር አይዘነጉም። ልክ እንደዛሬዎቹ የጎዳና ላይ ነጋዴዎች ሁሉ ያኔም አብዮት ጥበቃ ሲመጣ መጽሐፎቻቸውን ሰብስበው እየሮጡ፣ ዞር ሲል ደግሞ እየዘረጉ በዚሁ ንግድ ላለፉት ዓመታት ኖረዋል። አቶ ተስፋዬ መጽሐፍን እንደጉቦ ለአብዮት ጥበቃዎቹ ይከፍሉ እንደነበር አይዘነጉትም። ለልጆቻቸው እንዲያነቡ እያልን እንሰጣቸው ነበር። ይላሉ። አቶ ተስፋዬ አብረዋቸው ይሸጡ የነበሩ ሰዎች በተለያየ ምክንያት እየተንጠባጠቡ እርሳቸው ብቻ እንደቀሩ ያወሳሉ። እርሳቸው ብቻቸውን ሲቀሩ ደግሞ የአብዮት መጽሐፍ ተፈላጊነት እየቀነሰ መጣ። የነማኦ ሴቱንግ፣ የነካርል ማርክስ መጻሕፍት አንባቢ አጥተው ማዛጋት ጀመሩ። መንግስትም አድሃሪያን ኢምፔሪያሊስቶች ሲል አወገዘ። አንዳንድ ወጣቶች ግን ሹልክ እያሉ እየመጡ ይገዟቸውም ይሸጡላቸው ነበር። ፖስታ ቤት አንድ ግሪካዊ ሚስተር ጃኖቡለስ የሚባል አከፋፋይ እንደነበር የሚናገሩት አቶ ተስፋየ እርሱ መጽሐፍትን እያሾለከ ይሸጣቸው ነበር። የሶሻሊስት መጻሕፍት እየከሰሙ ሲመጡ በፊት ገዝተው ያነቡ የነበሩ ሰዎች እርሳቸው ጋር እያመጡ ይሸጡላቸዋል። አንባቢም የጠፋ መጽሐፍ ሲፈልግ እርሳቸው ጋር መምጣት ጀመረ። እንዲህ እንዲህ እያሉ አቶ ተስፋዬ ያኛውን ትውልድ ከዚህኛው ጋር በንባብ ያጋመዱ ሆነው እስካሁን ዘለቁ። በተከረከመ ጥድ የተሸፈነው መደብራቸው ለልማት በሚል የፈረሰ ሲሆን ይህ የአቶ ተስፋዬ መፈናቀል በርካታ መፃህፍት አፍቃሪን ያሳዘነ ጉዳይ ነው። የዘመናት ደንበኞቻቸው በተለይም ወጣቶች ጉዳዩን ወደ ማኅበራዊ መገናኛ ብዙኃን በመውሰድ ትኩረት እንዲያገኝ አድርገዋል። አብይ ታደሰ ከነዚህ መካከል አንዱ ነው። እርሱ እንደሚለው የአቶ ተስፋዬ ታሪካዊዋ የጽድ መደብር እንድትፈርስ የሆነው በመንገድ ሥራ ምክንያት ነው። አቶ ተስፋዬን ከድሮ ጀምሮ ያውቃቸው እንደነበር የሚናገረው አብይ፣ ወዳጆቻቸው ባደረጉት ርብርብ መንግሥት በዚያው አቅራቢያ የቆርቆሮ መደብር እንዲያዋቅሩ ፈቅዶላቸዋል። እነ አብይም ይህንኑ በማስተባበር ላይ ናቸው። እርሳቸው ከሰጡት አገልግሎት አንፃር ይህ ሲያንሳቸው ነው ይላል አብይ። ለምሁሩ፣ ወጣቱ እንዲሁም ለከተማው አንባቢ ዕድሜያቸውን የሰጡ እኚህን ሰው እንዴት መጽሐፍ መሸጫ ሥፍራ ያጣሉ ሲልም ይጠይቃል። እንደ አብይ ሁሉ ሃወኒ ደበበም ከልጅነቷ ጀምሮ የማንበብ ሱሷን ያስታገሰችው ወደ እርሳቸው ጋር በመምጣት ነበር። በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተፃፉ መጻሕፍት ማንበብ ስትፈልግ ጓደኞቼና መምህሮቿ በጠቋሟት መሰረት አቶ ተስፋዬ ጋር እየመጣች ትከራይ ነበር። ያኔ የእንግሊዘኛ መጽሐፍ አይሸጡም ነበር ትላለች። አሁን የአቶ ተስፋዬን የዘመን ውለታ ለመመለስ ከሚጣጣሩ ወጣቶች መሐል አንዷ ሆናለች። ዓውደ ርዕይ በማዘጋጀትና በልዩ ልዩ ዘዴዎች ገቢ በማሰባሰብ ያቺን ታሪካዊ መጻሕፍት መደብር ወደ ሥፍራዋ ለመመለስ እየሞከረች ነው። በጽድ እንኳ ባይሆንም በቆርቆሮ ተያያዥ ርዕሶች
የቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ካማሼ ዞን አመራሮች በታጣቂዎች ተገደሉ
ሴፕቴምበር ማጋሪያ ምረጥ በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል በታጣቂዎች በደረሰ ጥቃት የካማሼ ዞን አመራሮች ሲገደሉ የተወሰኑ መቁሰላቸውን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽነርን ጠቅሰው የኮሚዩኒኬሽን ባለሙያው አቶ በፍቃዱ አዳነ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ከቤንሻንጉል ጉምዝና ከኦሮሚያ ክልል የተውጣጡ አመራር አባላት በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ላይ መስከረም በአሶሳ ላይ ስብሰባ አካሂደው ነበር። ስብሰባውንም ጨርሰው የካማሼ ዞንና የአምስት ወረዳ አመራሮች በሚመለሱበት ወቅት በካማሼና ነዶ መካከል በምትገኝ ቦታ በተከፈተ ተኩስ አራት የካማሼ ዞን አመራሮች እንደተገደሉ አቶ በፍቃዱ ገልፀዋል። አቶ በፍቃዱ ጥቃት አድራሾቹን ማንነት ፀረ ሰላም ኃይሎች ከማለት ውጭ ያሉት የለም። ከአመራሮቹም በተጨማሪ የፀጥታ ኃይል አባላት በዚህ ተኩስ እንደቆሰሉ ገልፀው፤ በህይወት ያሉት የት እንዳሉ እንደማይታወቁ ና አቶ በፍቃዱ የክልሉን ፖሊስ ኮሚሽነር አቶ ሰይፈዲን ሃሮን እንዳስታወቁ ገልፀዋል። ሁኔታውን ለማረጋጋት የመከላከያ ኃይል ወደ ቦታው የገባ መሆኑንም ጨምረው ተናግረዋል። ተያያዥ ርዕሶች
ኦህዴድ አብዮታዊ ዴሞክራሲንና ዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነትን ታሪክ ሊያደርጋቸው ይሆን
ሴፕቴምበር ማጋሪያ ምረጥ የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት ኦህዴድ በአዲስ የፖለቲካ ፍልስፍና እንደሚመጣ ትናንት በጅማ ከተማ ዘጠነኛ ድርጅታዊ ጉባኤውን ሲጀምር አስታውቋል። የላቀ ሃሳብ ለተሻለ ድል በሚል መሪ ቃል ለተከታታይ ቀናት በሚካሄደው በድርጅቱ ጉባኤ መክፈቻ ላይ የኦህዴድና የኢህአዴግ ሊቀ መንበርና የሃገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ባደረጉት ንግግር ድርጅታቸው ለውጦችን በማድረግ አዲስ የፖለቲካ ፍልስፍና ይዞ እንደሚመጣ ገልፀዋል። ሊቀ መንበሩ አዲሱ ፍልስፍና ምን እንደሆነ ፍንጭ ባይሰጡም ድርጅታቸው ለኦሮሞ ህዝብ ብቻ ሳይሆን ለኢትዮጵያንና ለተቀረው የአፍሪካ ቀንድ አካባቢ የሚጠቅም አዲስ የፖለቲካ ፍልስፍና ይዞ ይመጣል ብለዋል። ኦህዴድ ከስሙና ከአርማው ባሻገር የድርጅቱን ፖለቲካዊ ርዕዮተ ዓለም እንዲሁም የኦሮሞ ህዝብ የሚያደርገውን ትግል ከፍ ወዳለ ደረጃ የሚያደርሱ አዳዲስና ወጣት አመራሮችን ይፋ እንደሚያደርግም ተገልጿል። ኦህዴድ ፍልስፍናዬን እቀይራለው ሲል ምን ማለቱ ይሆን ተብሎ ጥያቄ የቀረበላቸው የፖለቲካ ተንታኙ ዶ ር ግርማ ጉተማ በጥቅሉ ሲመልሱ ኢህአዴግን እንደ አዲስ መፍጠር ነው። ህወሃት ሲየጠቀምባቸው የነበሩትን እንደ አብዮታዊ ዲሞክራሲና ዲሞክራሲ ማዕከላዊነት ያሉ ነገሮችን አራግፎ ማስቀጠል ነው የሚመስለኝ ይላሉ። የኢትዮጵያ ችግር ሊፈታ የሚችለው በአካባቢው መነፅር ሲታይ ነው የሚል እምነት በፓርቲው የተያዝ የሚመስላቸው መሆኑንም ይጠቅሳሉ። እሳቸው እንደሚሉት ለምሳሌ የኦሮሞ የኢትዮጵያን ብሄርተኝነትም ከአፍሪካኒዝም ጋር በማያያዝ ነው ችግሩ ሊፈታ የሚችለው። አካባቢው አንድ አይነት ህዝቦች ብዙ ቦታ የተከፋፈሉበት ከመሆኑ አንፃር ደግሞ የኦሮሚያን ችግር ለመፍታት ኦሮሚያ ላይ ብቻ መስራት ዋጋ እንደማይኖረው የተገነዘቡ ይመስላል። ይልቁንም በአካባቢያዊ ደረጃ መስራትና ችግሩን መፍታት እንደሚያስፈልግ በማመን ድርጅቱ አቅጣጫውን ሊለውጥ ይችላል። በዚህም ይዞ የሚመጣው አዲስ ፍልስፍናም ይህን መሰረት ያደረገ እንደሚሆን ምልከታቸውን ያስቀምጣሉ። በተመሳሳይ እርምጃውን በአዎንታዊነቱ የሚመለከቱት የፍልስፍና መምህሩ ዶ ር ዳኛቸው አሰፋ ለውጡ ፓርቲው የሰራቸውን ስህተቶች ማረሚያ መንገድ ነው ብለውም ያምናሉ። ሥርዓቱ የተናጋው በድሮው መንገድ በድሮው አካሄድ ሊቀጥል ስላልቻለ ነው። አሁን ከዚያ አይነት ቀኖናዊ እርምጃ ተላቀናል ማለት ነው ይላሉ። እርምጃው አብዮታዊ ዲሞክራሲ ለሁሉም መልስ አለው፣ ሃሳብ ከአንድ ግንባር ብቻ ይመነጫል የሚሉትና መሰል ሃሳቦች እየተፈተሹ እንደሆነ ፤ ከሌሎች ጋር ለመጣመር የፓርቲያቸውን መሰረትና ድጋፍ ለማስፋትም እድሎች እንዳሉ አመላካች እንደሆነም ዶ ር ዳኛቸው ያምናሉ። ህወሃት ማእከል ነበረች ያ ግን አሁን ቀርቷል መኪናውን የሚዘውረው ህወሃት አይደለም። አራቱም ተስማምተው ቢሄዱ ጥሩ ነው ይላሉ።
ስለ ማጋራት ተጨማሪ ያጋሩ
ማጋሪያ ምረጥ የኦሮሞ ሕዝብ አንድነት እና አንገብጋቢ የወቅቱ ጉዳዮችን አስመልክቶ ኦነግ፣ ኦፌኮ፣ የተባበሩት ኦነግ፣ የኦሮሚያ ነፃነት አንድነት ግንባር እና የኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ግንባር የጋራ መግለጫ አውጥተዋል። ፓርቲዎቹ በጋራ ባወጡት መግለጫ አምስት ዋና ዋና ነጥቦች ላይ አተኩረዋል። አነሱም የኦሮሞ ማንነትን ለማጥፋት እየተደረገ ያለው ሙከራ፣ አዲስ አበባ ጉዳይ፣ ሕዝብን ከሕዝብ የሚያጋጩ ሚድያዎች፣ በሃገሪቱ እየታየ ያለው ለውጥን እና በቋንቋ ላይ የተመሰረተ ፌዴራሊዝምን የሚመለከቱ ናቸው። መቼም ደህንነት አይሰማኝም የኦሮሞ ማንነት ፓርቲዎቹ ሰሞኑን አደርግነው ባሉት ውይይት ጠላቶቻችን የኦሮሞን ሕዝብ ለማጥፋት አሰቃቂ ግድያ ከመፈፀም አልፎ በኦሮሞ ሕዝብ ሰም የሚጠሩ ተቋማትን በማውደም ከፍተኛ ዝርፍያ ፈፅመዋል ብለዋል። ከዚህ ጀርባ ፀረ ኦሮሞ አቋም ያለው የተደረጃ የፖለቲካ ቡድን ስለመኖሩ የሚያመለክቱ በርካታ መረጃዎች ተገኝተዋል ይላል መግለጫው። በማንነታችን ላይ የተቃጣውን ድርጊት ከማንኛውም ጊዜ በላይ እናወግዛለን፤ ድርጊቱን የፈፀሙ በህግ እንዲጠየቁ እንጠይቃለን በማለት ፓርቲዎቹ መግለጫቸው ላይ አትተዋል። አዲስ አበባን በተመለከተ ዛሬ አዲስ አበባ የምትገኝበት ሥፍራ የጥንት የኦሮሞ ጎሳዎች የእምነት፣ ፖለቲካ እና ኢኮኖሚ ማዕከል የነበረ መሆኑ አይካድም የሚለው መግለጫው ጎሳዎቹ መሬታቸውን ተነጥቀው እንዲጠፉ ተደርገዋል ሲል ያክላል። ፓርቲዎቹ እኛ ኦሮሞ ድርጅቶች አዲስ አበባ ሁሌም የኦሮሞ ሕዝብ ናት፤ ይህ ማለት ግን ከኦሮሞ ውጭ መኖር አይችልም ማለት አይደለም ሲሉ በመግለጫቸው አትተዋል። ሆኖም አንዳንድ የፖለቲካ ድርጀቶች ይህን በመካድ ከተማዋን እያሸበሩ መሆናቸውን ታዝበናል፤ አልፎም በኦሮሞ እና አማራ ሕዝብ መካል ጥርጣሬ እንዲፈጠር ደፋ ቀና እያሉ ይገኛሉ። ቢሆንም አይሳካላቸውም፤ የኦሮሞ እና የአማራ ሕዝቦች ለውጥ ለማምጣት አብረው ታግለዋልና ይላል መግለጫው። መላው ሕዝብ የእኒህን ኃይሎች ሴራ ለማክሸፍ አብሮ መቆም አለበትም ሲል መግለጫው ያክላል። ሕዝብን ከሕዝብ የሚያጋጩ ሚድያዎች ለወገናዊ ፖለቲካ የሚያደሉ ሚድያዎች ሕዝብን ከሕዝብ ለማጋጨት ተግተው እየሰሩ እንደሆነ መግለጫው አትቷል። ስለዚህ ውጭም ሆነ ሃገር ቤት ያላችሁ ሃገር አማሽ ሚድያዎች በህግም በታሪክም ፊት ተጠያቂ መሆናችሁን አውቃችሁ ከድርጊታችሁ ታቀቡ በማለት መግለጫው አስገንዝቧል። በሃገሪቷ እየታየ ያለውን ለውጥና ሽግግር በተመለከተ በሃገሪቱ ውስጥ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየታየ የመጣውን ለውጥና ፖለቲካዊ መነቃቃት ለውጡን በሚፈልጉ የሥርዓቱ አካላት የተገኘ እንደሆነ እናምናለን የሚለው መግለጫው በዚህ የሽግግር ወቅት ስልጣን ላይ ያሉ አካላት ዘላቂ ለውጥ እንዲያመጡ ሁኔታዎችን እናመቻቻለን የሚል አቋም ይዟል። ነገር ግን እንደማይሳካላቸው የተገነዘቡ የፖለቲካ ቡድኖች በሃሰት የብር ኖቶች ዜጎችን በማታለል የሃይማኖትና የብሄር ግጭት በማስነሳት መንግስት የሌለ ለማስመሰል እየተሯሯጡ እንደሆነ ግልጽ ነው። በመሆኑም አሁን ያሉ ተቋማት በህገ መንግሥቱ መሰረት በትክክል እንዲሰሩ ተደርጎ በነጻ፣ ተአማኒና በቂ ፉክክር በተደረገበት ህዝባዊ ምርጫ ወደ ዴሞክራሲ የሚደረገውን ሽግግር ብቻ የምንደግፍ መሆኑን እንገልጻለን ሲሉ ድርጀቶቹ አቋማቸውን አንፀባርቀዋል። በቋንቋ ላይ የተመሰረተ ፌደራሊዝምን በተመለከተ ለዘመናት ኢትዮጵያ ውስጥ የነበረውን የህዝቦች የማንነት ጥያቄ ለማክበር የተዘረጋውን የፌደራሊዝም ሥርዓት ደንታ የሌላቸው ኃይሎች ሥርዓቱ የችግሩ መንስኤ እንደሆነ አድርገው ለማቅረብ እየሞከሩ ነው ሲል መግለጫው ይወቅሳል። አንዳንድ ሚዲያዎችም ይህንኑ ተግባር ተያይዘውታል። ስለዚህ እኛ የኦሮሞ የፖለቲካ ድርጅቶች ፈጽሞ የማንቀበለው መሆኑንና በህልውናችን ላይ የተቃጣ አደጋ አድርገን እንደምንመለከተው እንገልጻለን በማለት ድርጀቶቹ መግለጫቸውን አጠናቀዋል። ተያያዥ ርዕሶች
በአንድ ዓመት ተኩል ኪሎ ግራም ክብደት የቀነሰችው ሴት
በአንድ ዓመት ተኩል ኪሎ ግራም ክብደት የቀነሰችው ሴትበአንድ ዓመት ተኩል ኪሎ ግራም ክብደት የቀነሰችው ሴት በአንድ ዓመት ተኩል ኪሎ ግራም ክብደት የቀነሰችው ሴት
በሆሄ የስነ ጽሁፍ ሽልማት በእውቀቱ ስዩም፣ አለማየሁ ገላጋይና ዳንኤል ወርቁ ተሸለሙ
ነሐሴ ዓመታዊው ሆሄ የስነ ጽሁፍ ሽልማት ለንባብ ከበቁ መፃሕፍት መካከል በአንባቢዎች እንዲሁም በሥነ ጽሁፍ ሀያሲያን ዓይን የተደነቁ ሥራዎች የሚሞገሱበት ሆሄ የሥነ ጽሁፍ ሽልማት በይፋ ከተጀመረ ዓመት ሞላው። በሆሄ፤ በተለያዩ የሥነ ጽሁፍ ዘርፎች የላቀ ሥራ ያበረከቱ ጸሃፍት ይሸለማሉ። የሥነ ጽሁፉ ባለውለታዎችም ይሞገሳሉ። የዘንድሮው የሆሄ ሽልማት ሲካሄድ በረዥም ልቦለድ ዘርፍ አለማየሁ ገላጋይ በፍቅር ስም በተሰኘ መጽሀፉ፣ በልጆች መፃሕፍት ዘርፍ ዳንኤል ወርቁ ቴዎድሮስ በተባለ ሥራውና በእውቀቱ ስዩም የማለዳ ድባብ በሚለው የግጥም መድበሉ ለሽልማት በቅተዋል። ለዓመታት መፃሕፍትና አንባቢዎችን በማገናኘት የሚታወቁት መፅሐፍ ሻጩ ተስፋዬ አዳል፣ እንዲሁም እውቆቹ ጸሃፍት ነጋድራስ ገብረህይወት ባይከዳኝ፣ አማረ ማሞ እንዲሁም የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኛ ሴቶች ማህበር ስለ አበርክቷቸው ተመስግነዋል። ከተሸማሚዎቹ አንዱ ዳንኤል ወርቁ ደራስያን ያላቸው ሀብት እውቅና ማግኘት ነው የሚለው ዳንኤል ወርቁ፤ ከላይ የተጠቀሱት አንጋፋ ጸሀፍት በተመሰገኑበት መድረክ በመሸለሙ ክብር እንደሚሰማው ይናጋራል። ሥነ ጽሁፍ ደጋግሞ እየወደቀ በሚነሳበት ሀገር መሰል ሽልማቶች ቢበራከቱ ደራስያንን እንደሚያበረታቱም ያምናል። የሥነ ጽሁፍ ሽልማቶች ለደራስያን እውቅና ከመስጠት ባሻገር ለማህበረሰቡ እስኪ ይህን መፅሐፍ አንብቡ የሚል መልዕክት በማስተጋባት ዘርፉን ማበረታታቸው እሙን ነው። ስለ ጠልሰም ወይም በተለምዶ የአስማት ጥበብ ተብሎ ስለሚጠራው ምን ያህል ያውቃሉ ሆሄ በየዓመቱ ከሚታተሙ መፃሕፍት መካከል በሥነ ጽሁፍ መስፈርቶች የተሻሉ የሚባሉትን በሙያተኞች ያስገመግማል። አንባቢያንም ድምጽ በመስጠት የወደዱትን መጽሐፍ እንዲጠቁሙ እድል ይሰጣቸዋል። የንባብ ባህሉ አልዳበረም እየተባለ በሚተች ማህበረሰብ ውስጥ መጽሐፍ አሳትሞ አመርቂ ውጤት ማግኘት ፈታኝ መሆኑን የሚናገረው ዳንኤል፤ የሥነ ጽሁፍ ሽልማቶች መፃሕፍትና ደራሲያንን አስከብረው ዘርፉንም እንደሚያሳድጉ ተስፋ ያደርጋል። አለማየሁ ገላጋይ በፍቅር ስም በተሰኘ መጽሀፉ ተሸልሟል ዳንኤል እየተዳከመ የመጣው የረዥም ልቦለድ መጻሕፍት ህትመት እንዲሁም ብዙም ትኩረት ያልተቸረው የልጆች መጻሕፍት ዘርፍ በሽልማቱ መካታቸውን እንደ ምሳሌ ይጠቅሳል። በሀገር አቀፍ ደረጃ በሥነ ጽሁፍ ብቻ ሳይሆን በሌሎች ዘርፎችም ሽልማት መስጠት አዲሰ አይደለም። የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ የሽልማት ድርጅትና የ ዎቹ የኪነ ጥበባትና መገናኛ ብዙኃን ድርጅትም አይዘነጉም። ሁለቱም ግን መዝለቅ አልቻሉም። ከሁለቱ ሽልማቶች በተጨማሪ በግለሰቦች ተነሳሽነት የተጀመሩ ሽልማቶችም ይጠቀሳሉ። ሆኖም ብዙዎቹ ከጥቂት ዓመታት ሲሻገሩ አይስተዋልም። ሆሄ የተወጠነው ለዘርፉ አስተዋጽኦ በማበርከት እንዲዘልቅ ቢሆንም የአቅም ውስንነት እንደሚፈታተናቸው የሽልማቱ አስተባባሪ ዘላለም ምሕረቱ ይናገራል። ከዚህ ቀደም ተጀምረው የተቋረጡ ሽልማቶች ተመሳሳይ ተግዳሮት አንደነበረባቸው ደራሲው ዳንኤልም ይገምታል። ዘላለምና ዳንኤል መሰል የሽልማት መሰናዶዎች ድጋፍ ካልተደረገላቸው ቀጣይነታቸው እንደማያስተማምን ይስማሙበታል። መጽሀፍ ሻጩ ተስፋዬ አዳል ለአበርክቷቸው ተመስግነዋል የሽልማት መሰናዶዎች ድጋፍ ካገኙ ዘላቂነታቸውን ከማረጋገጥ ባሻገር አድማሳቸውንም ማስፋት ይችላሉ። ሥነ ጽሁፍ ዘርፈ ብዙ እንደመሆኑ ከልቦለድና ሥነ ግጥም በተጨማሪ ወግ፣ አጫጭር ልቦለዶች፣ የተውኔት ጽሁፍ፣ ኢ ልቦለድ የጽሁፍ ሥራዎችም በውድድሩ ማካተት ይቻላል። በዘላላም ገለጻ ብዙዎች መርሀ ግብሩን ይወዱታል። በገንዘብ መደገፍ ላይ ግን ሁሉም ወደ ኋላ ይላል። ገንዘባቸውን ትርፋማ በሚሏቸው ዘርፎች ማፍሰስ ይመርጣሉ። የሽልማት ዝግጅቶች ብዙ ርቀት የማይራመዱት አንድም በበጀት ውስንነት ሲሆን፤ ከሽልማት አሰጣጥ ጋር በተያያዘ የሚነሱ የፍትሀዊነት ጥያቄዎች እንቅፋት የሆኑባቸውም ይገኙበታል። የኢትዮጵያ ደራስያን ማህበር የሬድዯ መርሀ ግብር ዋና አዘጋጅ ጌታቸው አለሙ አንጋፋና አማተር ደራስያንም ሥራቸው እንደተወደደላቸው የሚመሰከርባቸው የሥነ ጽሁፍ መድረኮች መበራከት አለባቸው ይላል። መፃሕፍትን የማስተዋወቅ፣ ደራስያንን በአንድ መድረክ የማገናኘት ሚና እንዳላቸውም ያክላል። መሰል ሽልማት በትልቅ ተቋም መሰጠት ቢኖርበትም ሆሄ በወጣቶች ተነሳሽነት የተጀመረ ተስፋ ሰጪ ዝግጅት ነው ሲል ሽልማቱን ይገልጻል። የሽልማት መሰናዶዎች ደራስያንን ያሸለሙ ሥራዎች ጎልተው እንዲወጡ፣ በማህበረሰቡ ዘንድ እንዲነበቡ፣ የውይይት መነሻ እንዲሆኑም ያበረታታሉ። ቢቢሲ ማስተባበያ
በአንድ ዓመት ተኩል ኪሎ ግራም ክብደት የቀነሰችው ሴት
በአንድ ዓመት ተኩል ኪሎ ግራም ክብደት የቀነሰችው ሴት ጥቅምት ጃኔት ክብደቷ ኪሎ ግራም ነበር። ይህ ውፍረቷ ግን ተጨማሪ የጤና እክሎችን በጃኔት ላይ አስከተለ። በደንብ ተኝታ መተንፈስ የማይታሰብ ነበር። ምግብ በአግባቡ መመገብ አለመቻልና የሚለካትን ልብስ ማግኘትም የጃኔት ተጨማሪ ችግሮች ነበሩ። ችግር የተደራረበባት ጃኔት ክብደት የምትቀንስበትን አማራጭ ፈለገች። አርሱም አመጋገቧን ማስተካከልና ሰፖርት መስራት ነበር። ይህንን እንቅስቃሴ ለአንድ ዓመት ተኩል ካደረገች በኋላ ታዲያ ጃኔት ኪሎ ግራም ክብደት መቀነስ ችላለች።
ምዕራባዊያን ከሁሉ በላይ ልጅ ለመውለድ ቅድሚያ ይሰጣሉ
ኦክተውበር አጭር የምስል መግለጫ ነፍሰ ጡር ሴት የስዋንሲ ዩኒቨርሲቲ በምዕራቡና በምሥራቁ የዓለማችን ክፍል ውስጥ ያሉ ሰዎች ለትዳርና ለልጅ ያላቸውን ፍላጎት በተመለከተ ጥናት አካሂዷል። በጥናቱ መሠረት ምዕራባዊያን ከሁሉ በላይ ልጅ ለመውለድ ቅድሚያ የሚሰጡ ናቸው። ጥናቱ እንደሚያመለክተው በተለይ የእንግሊዝና የአውስትራሊያ ዜጎች ልጅ ለመውለድ ቅድሚያ የሚሰጡ አጋሮችን ይመርጣሉ። ሴት አስገድዳ ከወንድ ጋር ወሲብ ብትፈጽም፤ አስገድዶ መድፈር ይባላል በስዋንሲ ዩኒቨርሲቲ አጥኚ የሆኑት ዶክተር አንድሩ ቶማስ እንደሚሉት ለዚህ ምክንያቱ ባላቸው የተሻለ የቤተሰብ ዕቅድ አገልግሎት አማራጮች ምክንያት ነው። የትዳር አጋርን ወይም የፍቅር ጓደኛን ለመምረጥ በሁለቱም ጾታና በሁሉም አገራት መልከ መልካም መሆንና የመልካም ባህሪ ባለቤት መሆን ከፍተኛውን ቦታ ይይዛሉ። ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች የተውጣጡ ምሁራን ይህንን ጥናት ያከናወኑት ሰዎችን በመምረጥ ሃሳባዊ ገንዘብ ሰጥተው የትዳር ጓደኛ እንዲሆኗቸው የሚፈልጓቸው ሰዎች ላይ ማግኘት በሚፈልጉት ባህሪይ ላይ ገንዘቡን እንዲያውሉት ተፈቀደላቸው። ገንዘቡንም ማዋል የሚችሉት የሕይወት አጋር በሚፈልጉበት ጊዜ ቅድሚያ በሚሰጧቸው ጉዳዮች ላይ ብቻ ነው። በዚህም መሠረት ምዕራባዊያን ሴቶች በመቶ እና ምዕራባዊያን ወንዶች በመቶ የሚሆነውን በጀት የትዳር ጓደኛ አግኝተው ልጅ የመውለድ ፍላጎት ባላቸው ተጣማሪዎች ላይ እንዳጠፉት ጥናቱ አመላክቷል። ሰውነቴ ወሲብ እንድፈጽም አይፈቅድልኝም የብዙ ሴቶች የጤና እክል ቻይናን፣ ኢንዶኔዥያንና ማሌዥያን በመሳሰሉት የምሥራቅ እስያ አገራት ደግሞ ወንዶች በመቶ እና ሴቶች በመቶ የሚሆነውን በጀታቸውን ተመሳሳይ ባህሪይ ባላቸው ተጣማጆቻቸው ላይ ማዋላቸውን ጥናቱ አረጋግጫለሁ ብሏል። ጥናቱን ካጠኑት መካከል አንዱ የሆኑት ዶ ር ቶማስ ልዩነቱ በምዕራባዊ ባህል ሰዎች የሚፈልጉትን የቤተሰብ እቅድ አማራጮችን ማግኘት መቻላቸው ነው ይላሉ። በምዕራባዊያን ዘንድ ልጅ መውለድ፣ አለመውለድ ወይም የሚወለዱትን ልጆች ቁጥር መወሰን በተጋቢዎች ይሁንታ የሚወሰን ነው። በምዕራባውያን ባህል የእርግዝና መቆጣጠሪያ ማግኘት ችግር አይደለም፤ ውርጃም ይፈቀድልናል ብለዋል ዶ ር ቶማስ። ነገሮችን ለመተው አማራጮች አሉን። እንደ ምዕራባዊ ሰው ልጅ አልፈልግም ማለት ትችላለህ፤ በምሥራቃዊያን ባህል ግን አንድ ሰው በትዳር ውስጥ የሚገባው ተፈጥሯዊ በሆነ አጋጣሚ ነው ባይ ናቸው ዶ ር ቶማስ። ኢንተርኔትን የሚሾፍረው የወሲብ ፊልም ይሆን በሁለቱም ባህሎች ከሁሉ በላይ ቅድሚያ የሚሰጠው የጋራ መስፈርት መልካምነት ነው። ይህም በምሥራቃዊያን በኩል በሁለቱም ጾታና በምዕራባዊያን ሴቶች የተረጋገጠ ሲሆን ምዕራባዊያን ወንዶች ግን አካላዊ ውበትን ያስቀድማሉ። በምዕራባዊያን ባህል ዘንድ ጨዋታ አዋቂ መሆንም ቅድሚያ የሚሰጠው መስፈርት ነው፤ ሴቶች በመቶ በጀታቸውን የጨረሱበት ሲሆን ወንዶች ደግሞ በመቶ የሚሆነውን በጀታቸውን ጨዋታ አዋቂ ሴት በመሻት አጥፍተውታል ይላል ጥናቱ። ምሥራቃዊያን ደግሞ በአንጻሩ ጨዋታ አዋቂነት ብዙም ግድ አይሰጣቸውም። ከተሰጣቸው በጀት መካከል ሴቶቹ በመቶ የሚሆነውንና ወንዶቹ በመቶ የሚሆነውን በጀታቸውን ብቻ ተጫዋች የፍቅር ጓደኛ በመፈለግ አውጥተዋል ይላል የስዋንሲ ዩኒቨርሲቲው ጥናት። ጥናቱ አክሎም ለምሥራቃዊያን ሃይማኖታዊ መሆንና ለአጋር ታማኝ መሆን ለትዳር ፈላጊዎች ቅድሚያ የሚሰጡ መስፈርቶች ሲሆኑ በምዕራባዊያን በኩል ግን እነዚህ ጉዳዮች ብዙም የሚያሳስቡ አይደሉም። ተያያዥ ርዕሶች
በዚህ ሳምንት ምን እንጠብቅ ከአዲስ አበባ እስከ አሜሪካ
ጁላይ ሰኞ ነው። የሳምንቱ መጀመሪያ የሥራ ቀን። በዚህ ሳምንት በቀጠሮ ከተያዘላቸው ኹነቶች መካከል አራቱ፡ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ዛሬ ሰኞ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው ዓመታዊ የመንግሥት አፈጻጸም ሪፖርትን ያቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል። ጠቅላይ ሚንስትሩ ሪፖርቱን ለተወካዮች ምክር ቤት ያቀርባሉ ተብሎ የተጠበቀው የዛሬ ሳምንት ነበር። ይሁን እንጂ በአዲስ አበባ እና በባህርዳር የተከሰቱ የመንግሥት ባለስልጣናት ግድያን ተከትሎ ወደ ዛሬ እንዲሸጋገር ሆኗል። ኢህአዴግ ነፃ ገበያም፣ ነፃ ፖለቲካም አላካሄደም ፀደቀ ይሁኔ ኢንጂነር ለአሜሪካ ሰላምታ እንሰጣለን አሜሪካውያን በየዓመቱ ጁላይ ሰኔ ከብሪታኒያ ነጻ የወጡበትን የነጻነት ቀን ያከብራሉ። የፊታችን ሃሙስ በሃገረ አሜሪካ በገፍ ይበላል፣ ቢራ ይጠጣል፣ ርችት ይተኮሳል፣ የሙዚቃ ድግሶች ይኖራሉ ብቻ ፌሽታ ይሆናል። ከወራት በፊት ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የጁላይ ዕለት በዋሽንግተን ታሪክ ታይቶ የማይታወቅ በርካታ ህዝብ ይሰበሰባል ብለው ነበር። ትራምፕ ዕለቱም ሰላምታ ለአሜሪካ ይባላል። ከምትወዱት ፕሬዝደንታችሁም ንግግር ትሰማለችሁ ሲሉ ተናግረው ነበር። በርካታ ስፖርታዊ ውድድሮች ይኖራሉ የአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታዎች መካሄዳቸውን ይቀጥላሉ። በግብጽ እየተካሄድ የሚገኘው የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ጨዋታ መጠቃለያ ጨዋታዎች ይካሄዳሉ። የአፍሪካ ዋንጫ ብቻ አይደለም፤ ዌምበልደን የቴኒስ ውድድር ዛሬ ሰኞ ይጀምራል። የፊታችን ቅዳሜ ደግሞ ተወዳጁ የብስክሌት ውድድር፤ ቱር ደ ፈራንስ በቤልጄም ይጀምራል። የሴቶች የዓለም ዋንጫም በፈረንሳይ ይቀጥላል። በቴክሳስ ግዛት አውሮፕላን ተከስክሶ ሰዎች ሞቱ ግሪክና ዴሞክራሲ በሚቀጥሉት ቀናት ግሪክ ዴሞክራሲ የውልደት ቦታ ስለመሆኗ የሚገልጹ ብዙ መረጃዎች እንደሚወጡ ይጠበቃል። በመጪው እሁድ ሃገሪቱ አጠቃላይ ምርጫ የምታካሂድ ሲሆን ከአውሮፓውያኑ በኋላ የመጀመሪያው ነው። ተያያዥ ርዕሶች
ዕድሜያችን የማቱሳላን ሲሶ እንኳ መሄድ የተሳነው ለምን ይሆን
ኦክተውበር ማጋሪያ ምረጥ ላለፉት ሁለት ክፍለ ዘመናት የሰው ልጅ አማካይ ዕድሜ ከዚያ ቀደም ከነበሩት ክፍለ ዘመናት መሻሻል አሳይቷል፤ ከጊዜ ጊዜም እያደገ ነው። በፈረንጆቹ ገደማ ሰዎች አማካይ የመኖሪያ ጣራቸው ዓመት ነበር። የተመጣጠነ ምግብ፣ ንፅህና እንዲሁም የመጠለያ መስፋፋት ሲጀምር ጣራው ወደ ያድግ ጀመር። ይህ የሆነው በ ዎቹ ነው። ኛው ክፍለ ዘመን ሁለት የዓለም ጦርነቶች የተስተናገዱበት ነው። እኒህ ጦርነቶች ከተካሄዱባቸው ዓመታት ውጭ ባሉት ዓመታት የሰው ልጅ የመኖር መጠን እያደገ እንጂ እየቀነሰ አልመጣም። ለወሲብ ትክክለኛው ዕድሜ የቱ ነው በተለይ ዎቹ ላይ ስትሮክ እና ድንገተኛ ልብ ሕመምን የሚከላከሉ መድሃኒቶች መገኘታቸው ለውጥ እንዲታይ አደረገ። አልፎም ኛው ክፍለ ዘመን መባቻ ላይ የሴቶች አማካይ ዕድሜ ፤ የወንዶቹ ደግሞ ደርሶ ነበር። ነገር ግን ድንገት ማሽቆልቆል ያዘ፤ በተለይ ደግሞ ላይ። ደግሞ ከፍተኛ የሞት መጠን የታየበት ዓመት ሆኖ አለፈ። የዛን ዓመት የነበረው የአየር ፀባይም እጅግ ለኑሮ አመቺ ያልሆነው ተብሎ ይነገራል። ለዚህ ማሽቆልቆል ምክንያቱ ምን ይሆን ብለው የመረመሩ ባለሙያዎች ምናልባትም አማካይ የመኖሪያ ዕድሜው ጣሪያ መጨረሻ ላይ ደርሰን ይሆናል ሲሉ መላ ምት ያስቀምጣሉ። ምድር ላይ በርካታ ዓመታት መኖራቸው በይፋ የተመዘገበላቸው ፈረንሳዊቷ ሴት ጂን ካልሜንት ሲሞቱ ዕድሜያቸው ነበር። እቺን ዓለም ከተሰናበቱም ዓመት አለፋቸው። አጭር የምስል መግለጫ ምድር ላይ በርካታ ዓመታት መኖራቸው በይፋ የተመዘገበላቸው ፈረንሳዊቷ ሴት ጂን ካልሜንት ሲሞቱ ዕድሜያቸው ነበር አንድ ጥናት የሰው ልጅ ቢኖር ቢኖር እንጂ እንደ አዛውንቷ ካልሜንት አይረግጥም ሲል ቢያትትም ይህን ሃሳብ የሚቃወሙ በርካቶች ናቸው። አሜሪካዊው የዘረ መል ጥናት ባለሙያ ዴቪድ ሲንክሌር ላይፍስፓን ብለው በሰየሙት መፅሃፋቸው ላይ የዘር ቅንጣቶችን በመደባለቅ በርካታ ዓመታት መኖር የሚችል ሰው መፍጠር ይቻላል ሲሉ ይሞግታሉ። በዓለማችን የተሻለ የዕድሜ ጣሪያ ካላቸው ሃገራት መካከል ጃፓን አንዷ ናት። የጃፓን የዕድሜ ጣራ ከእንግሊዝ የተሻለ ነው። እንግሊዝ ደግሞ አሜሪካን በጠባብ ርቀት ትረመራታለች። እስራኤል በቁፋሮ መስጂድ አገኘች ባለፉት ጥቂት ዓመታት የቁጥሩ ማሽቆልቆል ያሳሳባቸው ሰዎች በርካታ መላምቶችን ያመጣሉ። ከእነዚህም በየጊዜው የተለያዩ ዓይነት በሽታዎች መምጣት አንዱ ነው። በልብ ሕመም እና ስትሮክ የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር እጅጉን እየቀነሰ ቢመጣም ከዕድሜ መግፋት ጋር ተያይዘው የሚመጡ ዲሜንሺያን የመሳሰሉ በሽታዎች ሌላ የሞት ምክንያት መሆን ጀምረዋል። ወጣም ወረደ እንደ ማቱሳላ በርካታ መቶ ዓመታት መኖር ባንችል እንኳ ለምን መቶ አንደፍንም የብዙዎች ጥያቄ ነው። ጥያቄው መልስ ባያገኝም፤ ጥናቱ ግን ቀጥሏል። ተያያዥ ርዕሶች
በጠርሙስ በላኩት መልዕክት ሕይወታቸው የተረፈው ቤተሰብ
ሴፕቴምበር አጭር የምስል መግለጫ በሕይወት የተረፈው ቤተሰብ አሜሪካ ውስጥ ባላሰቡት ሁኔታ የውሃ ፏፏቴ ውስጥ ገብተው አደጋ ላይ የነበሩ ሦስት የቤተሰብ አባላት ለማንኛውም ብለው የድረሱልን መልዕክታቸውን በጠርሙስ ላይ ጽፈው ወደ ወንዝ ከተው ነበር። በሚያስገርም ሁኔታ በጠርሙሱ ላይ የነበረውን መልዕክት ሰዎች አግኝተው የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች ሕይወታቸውን መታደግ ችለዋል። ከርቲስ ዊትሰን፣ የፍቅር ጓደኛውና የ ዓመት ልጃቸው ባሳለፍነው ሰኔ ወር ላይ ነበር ወደ ማዕከላዊ ካሊፎርኒያ ግዛት በመሄድ የቤተሰብ ጉዟቸውን የጀመሩት። እቅዳቸው ደግሞ አሮዮ ሴኮ የተባለውን ወንዝ በመከተል መጨረሻ ላይ የሚገኘውን ፏፏቴ መመልከት ነበር። ልክ ፏፏቴው ጋር ሲደርሱም በገመድ ታግዘው በመውረድ እዛው አካባቢ ጊዜያዊ መጠለያቸውን ሠርተው ለመቆት ነበር ያሰቡት። በሦስተኛው ቀን ግን ከትልልቅ ቋጥኞች ሥር መውጣት በማይችሉበት ሁኔታ እራሳቸውን አግኝተዋል። ቋጥኞቹ በሁለቱም በኩል ሜትር ወደላይ ከፍታ ያላቸው ሲሆን፤ ይዘውት የነበረውም ገመድ ወደታች ለመውረድ እንጂ ወደላይ ለመውጣት የሚያገለግል አልነበረም። በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንዲሉ፤ እነሱ የነበሩበትና በቋጥኞቹ መካከል ያለው ቦታ ከወንዙ በሚመጣ ውሃ መሞላት ጀመረ። ውሃው ከፍ እያለ ሲመጣና ምን አይነት አደጋ ውስጥ እንደገባን ስረዳ ልቤ ቀጥ ብላ ነበር ብሏል ከርቲስ ከሲኤንኤን ጋር ባደረገው ቆይታ። የሠላም ተጓዧ ሉሲ ድንቅነሽ ምን ደረሰች ምንም አይነት የስልክ ኔትዎርክ በቦታው ስላልነበር የድረሱልን መልዕክት ማስተላለፍ እንኳን አቅቶት የቆየው ቤተሰብ በመጨረሻ ያለውን አማራጭ ለመጠቀም ወሰነ። በእጃቸው ላይ የነበረውን ጠርሙስ በመፈቅፈቅ በፏፏቴው በኩል መውጣት አቅቶን ተይዘናል፤ እባካችሁ ድረሱልን የሚል መልእክት ጽፈው ወደ ወንዙ ወረወሩት። አጭር የምስል መግለጫ መልዕክቱ የተጻፈበት ጠርሙስ ጠርሙሱ ግማሽ ኪሎ ሜትር ያህል በወንዙ ላይ እየተንሳፈፈ ከተጓዘ በኋላ በአካባቢው ጉዞ እያደረጉ የነበሩ ሁለት ሰዎች ያገኙታል። ወዲያውም ጉዳዩን ለአደጋ ጊዜ ሠራተኞች ያሳውቃሉ። የአደጋ ጊዜ ሠራተኞችም ወዲያው ፍለጋቸውን የጀመሩ ሲሆን፤ እኩለ ሌሊት አካባቢ ሦስቱንም የቤተሰብ አባለት ከባድ የሚባል ጉዳት ሳይደርስባቸው አግኝተዋቸዋል። ከርቲስ ዊትሰን እና ቤተሰቡ ሕይወታችን በመትረፉ እጅግ ደስተኞች ነን። ሕይወታችንን ያተረፉት እነዛ ሁለት ተጓዦችን አግኝተን ማመስገን እንፈለጋለን ብለዋል። ተያያዥ ርዕሶች
ደግነት ለጤንነት ብቻ ሳይሆን ለረዥም እድሜ ይጠቅማል
ኖቬምበር ማጋሪያ ምረጥ ደግነት ምን ያስገኛል ምናልባት ደስ የሚል ስሜት አዎ በእርግጥም መልካምነት በሕይወታችን ጥሩ ነገሮችን ያስከትላል። ተመራማሪዎች ደግነት ከሚፈጥርልን አወንታዊ ስሜት ባሻገር እድሜያችንንም እንደሚያረዝም ደርሰንበታል ይላሉ። በእርግጥ ደግነት ስንል ምን ማለታችን ነው ለምንስ አስፈላጊ ነው የሚለውን ጥያቄ ተመራማሪዎቹ አንስተው በዝርዝር ለመረዳት ሲነሱ ነገሩ በሰው ሕይወት ውስጥ ወሳኝ ነገር ሊሆን እንደሚችል እርግጠኛ ሆነው ነበሩ። ምርምሩን የመሩት ዳንኤል ፌስለር በተለይ ሌሎች መልካም ሲያደርጉ የሚመለከቱ ሰዎች እንዴት ደግ ለመስራት ሊነሳሱ እንደሚችሉ በቅርበት በመፈተሽ ተላላፊ ደግነት ያሉት ክስተት ማንን በተለይ በአወንታዊ መልኩ እንደሚነካ መርምረዋል። በፌስቡክና በዩቲዩብ ብዙ ተከታይ ያላቸው ሰዎች ምን ያህል ገንዘብ እንደሚያገኙ ያውቃሉ ተመራማሪው በአሁኑ ዘመን ደግነት በራቀው ዓለም ውስጥ እንገኛለን በማለት በዓለም ዙሪያ በፖለቲካ አመለካከትና በሐይማኖት ሰበብ በሰዎች መካከል የሚከሰተው ግጭት እየጨመረ መሆኑን ይናገራሉ። ደግነት ሌሎችን ለመጥቀም ከሚደረጉ አስተሳሰቦችን፣ ስሜቶችንና እምነቶችን ከሚያንጸባርቁ ተግባራት ጋር የተያያዙ እንደሆኑ በመግለጽ፤ እነዚህም በውጤታቸው ሌሎችን የሚጠቅሙ ሲሆኑ ሌላ ውጤት ለማምጣት የምንጠቀምበት እንዳልሆነ ተመራማሪው ይናገራሉ። በተቃራኒው ደግ ወይም መልካም አለመሆን ሌሎችን ያለመቀበል፣ ለሌሎች ደህንነት ዋጋ ያለመስጠት ማሳያ ነው ይላሉ። መጻሕፍትን ማንበብና መጻፍ ለአዕምሮ ጤና ይህ በደግነት ላይ የተደረገው ምርምር ያስፈለገው ደግነት ስለምን በዘመናዊው ዓለም ተጓደለ የሚለውን ለመረዳት እንደሆነ ለጥናቱ የገንዘብ ድጋፍ የሰጠው ተቋም ባለቤቶች ተናግረዋል። ተመራማሪው ዳንኤል ፌስለር እንደሚሉት ደግነት ብዙ ገጽታዎች አሉት የደግነት ተግባር ለሰው ስናደርግና ለእኛም ሲደረግልን በሁሉም መልኩ ለጤናችን ጠቃሚ ነው። አደገኛ የሆነን ውጥረት ወይም ጭንቀትን በማስወገድ በጎ ውጤት አለው ይላሉ። ደግነት ወይም መልካምነት ትልልቅ ድርጊቶች በመፈጸም ብቻ የሚገለጹ ሳይሆኑ ቀላል የሚባሉ ንግግሮችና የሰላምታ ልውውጦችም ከዚሁ አንጻር ሊታዩ ይችላሉ። አጭር የምስል መግለጫ ለራሳችን ይልቅ ለሌሎች በጎ ማድረግ ቀላል ነው ብዙም ግድ ባንሰጠውም በመደብር ውስጥ የሚገኙ አስተናጋጆች የሚያሳዩን ፈገግታና የሚሰጡን ሰላምታ በአጠቃላይ ጤናችን ላይ የእራሱ የሆነ አውንታዊ ውጤት እንዳለው ጥናቱ አመልክቷል። ለሌሎች መልካም ስለመሆን ማሰብና በደግነት ድርጊቶች ውስጥ መሳተፍ የደም ግፊትን ዝቅ ያደርጋል። በተጨማሪም ድብርትና ጭንቀትን የማከም ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው። በኮለምቢያ ዩኒቨርስቲ ዶክትር የሆኑት ኬሊ ሃርዲንግ በቅርብ ባሳተሙት መጽሐፋቸው ላይ እንዳሰፈሩት መልካምነት የሰውነታችንን በሽታን የመከላከል አቅም ይገነባል፣ የደም ግፊትን ዝቅ በማድረግ ሰዎች በረጅም እድሜ የተሻለ ሕይወት እንዲኖራቸው ያደርጋል ብለዋል። ጠቃሚ ነጥቦች ደግነት ለተሞላበት ሕይወት የሚሰሙ መስለው መልስ ለመስጠት እራስዎን ከማዘጋጀት ይልቅ በሐቅ ሌሎች የሚሉትን ማድመጥ ይጀምሩ በመጥፎ ሁኔታ ምላሽ ለሚሰጥዎት ሰው በመልካምነት ይመልሱ። የሚያመነጫጭቅዎትን ሰው ያስቡና ወዳጅነት በተሞላበት ሁኔታ ቀንህ ሽ ጥሩ አልነበረም ብለው ይጠይቋቸው። በዚህም ውጥረት የተሞላበትን ሁኔታ በቀላሉ ማርገብ ይችላሉ በሰዎች ሕይወት ውስጥ ከሚያጋጥሙ ነገሮች ሁሉ ችላ መባል፣ አለመፈለግና አለመፈቀር የሰውነትን ክብር የመግፈፍ ያህል ስለሆነ ችላ የተባለን ሰውን ያቅርቡ። ይህን ሲያደርጉ ለሰዎች ዋጋን ይሰጣሉ። ከመልካምነት የራቀ ድርጊት ሲፈጸም ሲገጥምዎ የእርሶ ችግር አለመሆኑን ይረዱ። ለድርጊቱ ምላሽ እንዲሰጡ ሲገፋፉም እራስዎን ይቆጥቡና በጥልቀት ትንፋሽ ወስደው እራስዎን ያርቁ። ዶክትር ኬሊ ደግነት በዙሪያችን ያሉ ነገሮችን በመለወጥ በዓለም ላይ ያሉ ነገሮችን እንድንፈትሽ ይረዳናል በማለት በአብዛኛው ከእራሳችን ይልቅ ለሌሎች ሰዎች መልካም ለመሆን ይቀለናል ሲሉ አክለዋል። ለእራሳችንም ሆነ ለሌሎች ደግ መሆንን ለማበረታታት በርካታ መንገዶች አሉ። በሥራ ቦታ፣ በትምህርት ቤትና በቤታችን ውስጥ ደግና ሩህሩህ በመሆን መልካም ውጤትን ለማግኘት እንችላለን ይላሉ። በህክምና በኩል ቴክኖሎጂው እየተሻሻለ ሊሆን ይችላል፤ ነገር ግን የተንከባካቢን ደግነት ያህል ትልቅ ነገርን ግን መፍጠር አይቻለንም ይላሉ ዶክተሯ። በተለይ ደግሞ በአእምሮ ጤናና አካላዊ ጤና መካከል ያለው ትስስር እጅግ ወሳኝነት በመጥቀስ። ትምህርት ዕድሜን እንደሚያስረዝም በጥናት ተረጋገጠ ሰዎች ሌሎች የደግነት ተግባርን ሲፈጽሙ ሲመለከቱ ተመሳሳዩን ለመፈጸም ይነሳሳሉ ይላሉ ባለሙያዎች። ስለዚህ የምንፈጽማቸው በጎ ነገሮች በእኛ ድርጊት ላይ ብቻ የሚቆሙ ሳይሆኑ በሌላ ጊዜ ለሌሎች ሰዎች ለሌሎች እንዲፈጸሙ እያገዝን መሆኑን መረዳት ያስፍለጋል። ግጭቶችና ጥላቻ በተበራከተበት ዓለም የመልካምነት ድርጊቶች ጎልተው ይሰማሉ፤ ያዩ የሰሙ እንዲሁም የተደረገላቸው ጭምር ሳይቀሩ ደግ ማድረግን ይለምዳሉ፤ ለሌሎችም ያስተላልፋሉ። በአንደኛው የዓለም ክፍል የሚፈጸም የደግነት ተግባር አየርና ባሕሩን አቋርጦ ከአድማስ ባሻገር በመጓዝ በሌላ ቦታ ይሰማል ይፈጸማል። ለዚህ ነው ደግንት መልካምነት ተላላፊ ነው የሚባለው። ተያያዥ ርዕሶች
በፈረንሳይ ልማደኛው ሌባ የአንበሳ ደቦል ሰርቆ ተያዘ
ኦክተውበር አጭር የምስል መግለጫ ባለሥልጣናቱ የዱር እንሰሳትን እንደለማዳ እንሰሳ ቤት ውስጥ ማቆየት ወንጀል ስለመሆኑ ሲናገሩ ነበር የ ዓመቱ ፈረንሳዊ በመኖሪያ ቤቱ ውስጥ የአንበሳ ደቦል ደብቆ በመገኘቱ በቁጥጥር ስር ውሏል። እንደ ፈረንሳይ መገናኛ ብዙኃን ዘገባ ከሆነ ፖሊስ መረጃው የደረሰው ግለሰቡ የስድስት ሳምንት ዕድሜ ያላትን ደቦል በ ሺህ ዮሮ ለመሸጥ ሲያስማማ ነው። ማክሰኞ ዕለት ጎረቤቶቹ ቤት ቁምሳጥን ውስጥ የደበቃት ሲሆን ደቦሏ ግን የሕፃን አልጋ ላይ ተገኝታለች። ደቦሏ በጥሩ ጤንነት ላይ እንደምትገኝ የተነገረ ሲሆን ለዱር አራዊት ባለሥልጣናትም ተላልፋ ተሰጥታለች። እንደ የፈረንሳይ መገናኛ ብዙኃን ዘገባ ወንጀለኛው ልማደኛ ሌባ ነበር ተብሏል። ፖሊስ በሕገወጥ መልኩ በሰዎች መኖሪያ ውስጥ የዱር እንስሳትን ሲያገኝ የመጀመሪያ ጊዜው አይደለም። በ አንድ ግለሰብ በምግብ እጥረት የተጎዳ የአንበሳ ደቦል ሰው በማይኖርበት ሕንፃ ውስጥ ደብቆ መገኘቱ ይታወቃል። ወንጀለኛው የተደረሰበትም ከደቦሏ ጋር ምሥለ ራስ ፎቶ ሰልፊ ተነስቶ ፎቶውን ከተሠራጨ በኋላ ነው። የኋላ ኋላ ደቦሉ ወደ ደቡብ አፍሪካ የእንስሳት ማቆያ ተወስዷል። በዚህ ወርም ኔዘርላንዳዊ መንገደኛ አንድ ደቦል በመንገድ ላይ ተጥሎ አግኝቷል። ተያያዥ ርዕሶች
ማላዊያን የራስተፈሪ እምነት ተከታዮች በድሬድሎክ ት ቤት እንዲገቡ ተፈቀደላቸው
ጃንዩወሪ ማላዊ፤ ራስተፈሪያን ከነ ድሬድሎካቸው ትምህርት ቤት እንዲገቡ ፈቀደች። የማላዊ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የራስተፈሪ እምነት ተከታይ ተማሪዎች ከነ ድሬድሎካቸው ትምህርት ቤት እንዲማሩ መንግሥት እንዲፈቅድ ትዕዛዝ ሰጥቷል። ጊዜያዊ የሆነው ውሳኔ የተላለፈው፤ ፍርድ ቤቱ የአንዲት ራስተፈሪ እምነት ተከታይ ጉዳይን ተከትሎ ነው። የራስ ተፈሪ እምነት ተከታዮች ፀጉራቸውን በረዥሙ በማሳደግ ይታወቃሉ። ይህ የፀጉር አስተዳደግ ዓይነት ድሬድሎክ በመባል ይታወቃል። ፍርድ ቤቱ በ ድሬድሎክ ምክንያት የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለመመዝገብ የተከለከለችውን ሕፃን ጉዳይ ሲያይ መቆየቱን የአገሪቷ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል። ኬንያ ራስተፈሪያኒዝም ኃይማኖት ነው ስትል በየነች ተማሪዋ በትምህርት ቤቱ አስተዳደር ድሬድሎኳን እንድትቆርጥ ተጠይቃ ነበር። ይህንን የክስ ጉዳይ ሲያዩ የነበሩት ዳኛ ትምህርት ቤቱ ተማሪዋን እንዲቀበልና ውሳኔ እስከሚሰጥ ድረስ ያለፋትን ትምህርትም ተጨማሪ ጊዜ በማስተማር እንዲያካክሱ ትዕዛዝ አስተላልፎ ነበር። ታዲያ ፍርድ ቤቱ ድሬድሎክ ን አስመልክቶ ፍርድ ቤቱ ባስተላለፈው ትዕዛዝ በማላዊ የሚገኙ ዳኞች ደስተኛ መሆናቸውን ገልፀዋል። የማላዊ የሕግ ባለሙያ ሴቶች ማኅበር ፀጉራቸውን ድሬድሎክ ያደረጉ ሁሉም የራስተፈሪ እምነት ተከታይ ተማሪዎች ትምህርት ቤት መግባት እንዲችሉ መንግሥትን ሲያሳስቡ ቆይተዋል። የማህበሩ ፕሬዚደንት ታዳላ ችንክዌዙሌ በመግለጫቸው የትምህርት ሚንስትር ፍርድ ቤቱ ያስተላለፈውን ትዕዛዝ ለመተግበር መመሪያ ያወጣል የሚለው በጣም አሳሳቢ ነበር ብለዋል። ተማሪዎችን ብቻ ሳይሆን ሁሉንም ራስ ተፈሪያን ህፃናት በራሳቸው የመኩራት መብት፣ የመማር መብት እና ሃይማኖት በፖሊሲ ተፅዕኖ ሊደረግበት እንዳይገባ ከግምት ውስጥ በማስገባቱ በውሳኔው በጣም ደስተኞች ነን ሲሉ የተሰማቸውን ገልፀዋል። ፀጉሯን ድሬድሎክ ማድረጓን ተከትሎ ከትምህርት ቤት የተከለከለችው ተማሪ ጉዳይ ማህበሩ በወካይነት እየተከራከረ ነው። ፍርድ ቤቱም ጊዜያዊ ትዕዛዝ ያስተላለፈ ሲሆን የተማሪዋ የክስ ሂደት እስከሚጠናቀቅ እና የመጨረሻ ብይን እስከሚሰጥ ድረስ ተግባራዊ ይሆናል። ከዚህ ቀደም ኔሽን ጋዜጣ በማላዊ የሚገኙ የራስ ተፈሪ እምነት ተከታዮች በሚደርስባቸው መገለል መንግሥትን እንደሚከሱ ዘግቧል። በፈረንጆቹ ኅዳር ድሬድሎክ ምክንያት ትምህርት ቤት እንዳይገቡ መከልከላቸውን ተከትሎም የተቃውሞ ሰልፍ አካሂደው ነበር። ተያያዥ ርዕሶች
የኢትዮጵያዊው ጉዞ፡ ከኬኒያ የስደተኞች ካምፕ እስከ ሜልቦርን ዩኒቨርሲቲ
ጃንዩወሪ ኤልሻዳይ ጌትነት አጭር የምስል መግለጫ ኤልሻዳይ እና ቤተሰቦቹ ኤልሻዳይ ጌትነት ይባላል፤ በሜልቦርን ዩኒቨርሲቲ የጥርስ ቀዶ ጥገና የዶክትሬት ተማሪ ነው። ኤልሻዳይ ከስደተኞች ካምፕ ተነስቶ እስከ ካናዳ ያደረገውን ጉዞ አካፍሎናል። አባቱ በደርግ ዘመን የነበረውን ወታደራዊ ግዴታ ካጠናቀቁ በኋላ ከእናቱ ጋር በመሆን ከኢትዮጵያ ለቀው ለመውጣት ተስማሙ። አገራቸውን ለቀው ወደ ኬንያ ለመሰደድ ሲያቅዱ ሁለቱም በአሥራዎቹ እድሜ ክልል ውስጥ ነበር የሚገኙት። እንደውም እናቴ እንደነገረችኝ ለሴት አያቴ ቡና ከምታፈላበት ድንገት ተነስታ መጣሁ ብላ እንደወጣች ነው ኬንያ የገባችው። ከዛም ከአባቴ ጋር ተያይዘው ጉዞ ወደ ኬንያ ጀመሩ። በእግር እና በመኪና የተደረገው ጉዟቸው እጅግ አስቸጋሪና ፈታኝ ነበር። ጫካዎችን በሚያቋርጡበት ወቅት አንዳንዶቹ ስደተኞች በአንበሳ እንደተበሉም ወላጆቹ የነገሩትን ኤልሻዳይ ያስታውሳል። መጻሕፍትን ማንበብና መጻፍ ለአዕምሮ ጤና ቤተሰቦቹ ከአዲስ አበባ ተነስተው የኬንያ ድንበር ለመድረስ ቀናት የፈጀባቸው ሲሆን፤ በመጀመሪያ መርሰቢት የሚባለው የስደተኞች ማቆያ ውስጥ ነበር የገቡት። የደርግ ሥርዓት መውደቅን ተከትሎ ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ቢነገራቸውም አንዴ ወጥተናል አንመለስም ብለው ሌላ አማራጭ መፈለግ ያዙ። አንድ ከብቶቹን ወደ ኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ የሚወስድ ገበሬ አግኝተው፣ እነሱንም ይዟቸው እንዲሄድና በምላሹ ገንዘብ ሊከፍሉት ተስማሙ። በመጨረሻም ከከብቶች ጋር መኪና ውስጥ ተጭነው በድብቅ ናይሮቢ ገቡ። ናይሮቢ ከደረሱ በኋላም በኬንያና ሶማሊያ ድንበር ላይ ወደሚገኝ ዳዳብ ወደተባለ የስደተኞች ማቆያ ተዘዋወሩ። ከአንድ ዓመት በኋላ ኤልሻዳይ በስደተኞች ካምፕ ውስጥ ተወለደ። አጭር የምስል መግለጫ ኤልሻዳይ እና አባቱ አቶ ጌትነት እናቴ ኤልሻዳይ የሚለውን ስም የሰጠችኝ በምክንያት ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ኤልሻዳይ ማለት ሁሉን ቻይ ማለት ነው። እኔ የተወለድኩት በስደተኞች ማቆያ ውስጥ ሲሆን፤ እዛ የተወለዱ ብዙ ህጻናት በወባና በምግብ እጥረት ምክንያት ሕይወታቸው ያልፍ ነበር። እናቴ በምንም አይነት ተስፋ አስቆራጭ ሁኔታ ውስጥ ብትሆን ፈጣሪ እንደሚጠብቀኝ ተስፋ ታደርግ ነበር። ለዚህም ነው ይህንን ስም የሰጠችኝ። ምንም እንኳን በዛ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ልጆችን ማሳደግ ከባድ ቢሆንም፤ በአካባቢው የነበሩ ሌሎች ስደተኞችም ጭምር ተባብረው ልጆችን ያሳድጉ እንደነበር ኤልሻዳይ ያስታውሳል። እኛ የነበርንበት የስደተኞች ማቆያ በብዛት ሶማሌዎች የሚገኙበት ነበር። የባህል እንዲሁም የሃይማኖት ልዩነት ቢኖርም ያለምንም ችግር ነበር ያደግኩት። ሁሉም ሰው ይንከባከበኝ ነበር። አፉን በአማርኛ የፈታው ኤልሻዳይ፤ አራት ዓመት ሲሞላው ሶማልኛ እና ስዋሂሊ በተጨማሪነት አቀላጥፎ መናገር ይችል ነበር። በነበረው አስቸጋሪ የኑሮ ሁኔታ ምክንያት እናቴ የራሷን ልብሶች እየቀደደች ለኔ ልብስ ትሰፋልኝ ነበር። አባቴም ቢሆን በዛ በረሃ ውስጥ ጫማ እንኳ ሳያደርግ የጉልበት ሥራ እየሠራ ለእኔ ጫማ ይገዛልኝ ነበር። በወር የሚሰጠን ቀለብም እጅጉን ትንሽ ነበር። ለአንድ ቤተሰብ በወር ኪሎ ምግብ ብቻ ነበር የሚሰጠው። ነገር ግን ስደተኞቹ ተሰባስበው ህጻናቱ እንዳንራብ ይጥሩ ነበር ሲል ያስታውሳል። የካምፑ ነዋሪዎች ከፍተኛ የምግብ እጥረት ቢገጥማቸውም፤ ሁሌም ቢሆን አዋቂዎች በቅድሚያ ለህጻናት ምግብ ይሰጡ ነበር ይላል ኤልሻዳይ። ሌላው ቀርቶ የወለዱ እናቶች የሌላ ሰው ልጆችን ጭምር ያጠቡ ነበር። በስደተኞች ማቆያው ውስጥ መኖሪያ ቤት ማግኝት ከባድ እንደነበርም ያስታውሳል። እኔና ቤተሰቦቼ የምንኖረው በትንሽዬ ጎጆ ውስጥ ነበር። አባቴ ወታደር ስለነበር ጠንካራ እንድሆንና በቀላሉ እጅ እንዳልሰጥ አድርጎ አሳድጎኛል ይላል። የኤልሻዳይ አባት የኢትዮጵያን ጀግኖች ታሪክ ይተርኩለት እንደነበርም ይናገራል። ሁሌም ቢሆን ስለ ኢትዮጵያውያን ጀግኖች ታሪክ ይነግረኝ ነበር። ስለ አፄ ቴዎድሮስ፣ ጉንደት ላይ የግብፅን ጦር ስላሸነፈው አፄ ዮሃንስ፣ ሙሉ ኢትዮጵያን አንድ አድርጎ ቅን ገዢ ጣልያኖችን ከኢትዮጵያ ስላባረረው አፄ ምኒሊክ እንዲሁም በዲፕሎማሲ ሥራቸው ስለሚታወቁት አፄ ኃይለሥላሴ ታሪክ እየሰማሁ ነው ያደግኩት። በተጨማሪም እንደ ባልቻ ሳፎ፣ ራሥ ጎበና፣ ንግሥት ጣይቱና ሌሎችም ጀግኖች ሕይወትና አኗኗር መስማት በልጅነቴ ትልቅ ቦታ ነበራቸው። የስደተኞች ካምፕ ውስጥ ብዙ ህጻናት ስላልነበሩ ከሌሎች ህጻናት ጋር ተቀላቅሎ የማደግ እድልን አላገኘም ነበር ኤልሻዳይ። አጭር የምስል መግለጫ የኤልሻዳይና የወላጆቹ የህይወት ጉዞ ጉዞ ወደ ካናዳ በስደተኞች ካምፕ ውስጥ ለአምስት ዓመታት ከቆየን በኋላ ወደ ካናዳ የምንሄድበት እድል ተፈጠረ። ሕይወታችንም ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ተቀየረ። በመጀመሪያ በኖቫ ስኮሺያ ግዛት ሃሊፋክስ ከተማ ለአንድ ዓመት ቆየን። በመቀጠል ደግሞ ካልጋሪ ወደምትባል ከተማ ተዘዋውረን አዲስ ሕይወት መሰረትን። ልክ እንደማንኛውም ስደተኛ ከፍተኛ የሆነ የባህል መጣረስ ቢያጋጥመንም ቀስ በቀስ በራስ መተማመናችን እየጨመረና እየተላመድነው መጣን። የጄኔራል ደምሴ ቡልቶ ልጅ መራር ትዝታ ኤልሻዳይ የትምህርት ውጤቱ በጣም ጥሩ ስለነበር የካልጋሪ ዩኒቨርሲቲ በሳይንስ ዲግሪ ፕሮግራም ተቀበለው። በሰዓቱ ምን አይነት ዘርፍ ላይ መሰማራት እንደሚፈልግ እርግጠኛ ባይሆንም በጤናው አካባቢ ግን ፍላጎት እንዳለው ያውቅ ነበር። ከዩኒቨርሲቲው የመጀመሪያ ዓመት ቆይታው በአንዱ ቀን፤ ወደተለያዩ አገራት በመጓዝ ነጻ የጥርስ ህክምና ይሰጥ የነበረ ዶክተር ራልፍ ዱቤኒስኪ የሚባል ግለሰብ ከዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ጋር በመሆን ወደ ኢትዮጵያና ሩዋንዳ እንደሚጓዝ ነግሮት አብሮት እንዲሄድ ጥያቄ አቀረበለት። ኤልሻዳይ አይኑን ሳያሽ ነበር ሃሳቡን የተቀበለው። እ አ አ በ ከዶክተር ራፍ ጋር በመሆን ወደ ኢትዮጵያ በመጓዝ አገሬን በአይኔ ለመመልከት በቃሁ። አዲስ አበባንና ቤተሰቦቼ ያደጉበት ልደታ ሰፈርንም ለማየት እድሉን አገኘሁ። ምንም እንኳን ኢትዮጵያ ስሄድ የመጀመሪያዬ ቢሆንም ልክ ስደርስ ቤቴ የተመለስኩ አይነት ስሜት ነበር ተሰማኝ ሲል ወቅቱን ያስታውሳል። ዶክተር ራልፍና ኤልሻዳይ ከወሊሶ ወጣ ብላ ወደምትገኝ ሃርቡ ጩሉሌ ወደምትባል ትንሽ መንደር ተጉዘውም ነበር። በነበራቸው ቆይታ ወላጅ አልባ ለሆኑ ህጻናት ቤት ሲገነቡ፣ የጥርስ ህመም ለነበረባቸው ሰዎች ህክምና ሲሰጡና ቀላል ቀዶ ጥገና ሲያደርጉ እንደቆዩ ይናገራል። እሱ የህክምና ሥራዎቹን ሲሠራ አብሬው እየሄድኩ አግዘው ስለነበር የአካባቢው ልጆች እኔም የህክምና ባለሙያ መስያቸው ዶክተር እያሉ ይጠሩኝ ነበር። በዚህ ሁኔታ በጣም ነበር የተገረምኩት። የአገራቸው ሰው ህክምና ላይ ተሰማርቶ በመመልከታቸው በጣም ተደስተው ህጻናት ሲያደንቁኝ ማየት ተጨማሪ መነሳሳትና ጉጉትን ፈጥሮብኝ ነበር። ጉዞዬን ጨርሼ ወደ ካናዳ ስመለስ በአገሬ ባህልና ታሪክ በእጅጉ ተነክቼና አዲስ ሰው ሆኜ ነበር የተመለስኩት። የቀደሙት አባቶቼ እንደ ላሊበላ አብያተ ክርስቲያናት፣ የጎንደሩ ቤተ መንግሥትና አክሱም ሀውልት ያሉ ቅርሶችን በራሳቸው መገንባት ከቻሉ፤ እኔም ምንም አያቅተኝም የሚል ስሜት አደረብኝ። አጭር የምስል መግለጫ ኤልሻዳይ ጌትነት ኤልሻዳይ በካልጋሪ ዩኒቨርሲቲ በነበረው ቆይታ ከትምህርቱ ጎን ለጎን ሁለት ወይም ሦስት ተጨማሪ ሥራዎች ይሠራ ነበር። ቀላል አልነበረም ግን መድረስ የምፈልግበትን ቦታ አውቅ ስለነበር ያለምንም ችግር ተወጥቼዋለው ይላል። የመጨረሻው ዓመት ላይ በጥርስ ቀዶ ህክምና በእጅጉ በሚታወቀው የአውስትራሊያው ሜልቦርን ዩኒቨርሲቲ ለተጨማሪ ትምህርት አመለክቶ ነበር። እ አ አ በ መጨረሻ አካባቢ ደግሞ ከሜልቦርን ዩኒቨርሲቲ ሙሉ በሙሉ እንደተቀበሉት የሚገልጽ ኢሜይል ደረሰው። እውነቱን ለመናገር በሕይወቴ እጅግ በጣም አስደሳቹ ቀን ነበር ማለት እችላለሁ። አስታውሳለሁ መልዕክቱ ሲደርሰኝ ማልቀስ ጀመርኩ፤ ቤተሰቦቼም ምን ሆነ ብለው ተደናግጠው ነበር። ምናልባት የቤተሰብ አባል ወይም ከጓደኞቼ መካከል አንዳቸው መጥፎ ነገር ያገጠማቸው ነበር የመሰላቸው። ልክ የኢሜይል መልእክቱን ሳሳያቸው እናቴ እግዚአብሔር ይመስገን ብላ መሬት ላይ ወደቀች። በተደጋጋሚ እግዚአብሔር ይመስገን ትል ነበር። አባቴ ደግሞ በቆመበት ከአይኖቹ እንባ እየወረደ እንደነበር አስታውሳለው። ሦስታችንም ተቃቅፈን ቆየን። ለቤተሰቦቼ በጣም ትልቅ አጋጣሚ ነበር፤ ምንያቱም ከስደተኞች ካምፕ እስከ ካናዳ ያደረጉትን የመከራ ጉዞ የሚያስረሳ ስለሆነ ነው። ልፋታቸው ሁሉ መና ባለመቅረቱ እነሱም እኔም በጣም ደስተኞች ነን። በአሁኑ ወቅት በሜልቦርን ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያ ዓመት ትምህርቱን ሊያጠናቅቅ እንደተቃረበ የሚናገረው ኤልሻዳይ፤ በእያንዳንዱ ቀን ከባድና አስቸጋሪ ፈተናዎችን ማለፍ ግድ እንደሆነ ያስረዳል ሆኖም ግን ከአቅሜ በላይ የሚሆን ነገር የለውም። ማንኛውንም አይነት ፈተና ለማለፍ ዝግጁ ነኝ ይላል። በትምህርት ክፍሉ ብቸኛው ኢትዮጵያዊ መሆኔ ደግሞ አገሬን በአግባቡ እንድወክልና ጠንክሬ እንድሠራ አድርጎኛል። ኤልሻዳይ አንዳንዴ ለትምህርት ወደ ክፍል ሲገባ ጋቢ ይለብሳል። የክፍል ጓደኞቹና አስተማሪዎቹም በጣም እንደወደዱትና ሁሉም ጋቢ እንፈልጋለን እንዳሉትም ይናገራል። ክሊኒክ ውስጥ ሲሆን ደግሞ ገዋኑ ላይ አረንጓዴ፣ ቢጫ፣ ቀይ የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ያደርዳል።
የዘረኝነት ጥቃቱ ከዚህም በላይ ሊከፋ ይችላል ንጎሎ ካንቴ
ዲሴምበር አጭር የምስል መግለጫ የቶትንሃምና የቼልሲ ተጫዋቾች ሜዳ ውስጥ ትናንት ምሽት በነበረው የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ቶትንሃም ከቼልሲ ጋር ሲጫወቱ በጥቁር ተጫዋቾች ላይ በተለይም በቼልሲው ተከላካይ አንቶንዮ ሩዲገር ላይ ያነጣጠረ የዘረኝነት ስድብ ከደጋፊዎች በኩል ተሰምቷል። ይህንንም ተከትሎ የአገሪቱ ፕሮፌሽናል የእግር ኳስ ተጫዋቾች ማህበር መንግሥት ከእግር ኳስ ጨዋታዎች ላይ የሚከሰቱትን የዘረኝነት ድርጊቶች መርምሮ እርምጃ እንዲወስድ ጠይቋል። የቶተንሃም ቡድንም በክስተቱ ላይ ጥልቅ ምርመራ እንደሚያደርግና ጠንከር ያለ እርምጃ እንደሚወስድም አሳውቋል። በጥቁር ተጫዋቾች ላይ የተሰነዘረውን የዘረኝነት ድርጊት ተከትሎ ጨዋታው ለአጨር ጊዜ ተቋርጦ የነበረ ሲሆን፤ በስታዲየሙ ውስጥ ባሉ የድምጽ ማጉያዎች በኩል የዘረኝነት ባህሪ በጨዋታው ላይ እንቅፋት እየሆነ መሆኑ ለተመልካቾች ተገልጾላቸዋል። ከጨዋታው መጠናቀቅ በኋላ ከቢቢሲ ጋር ቆይታ ያደረገው የቼልሲው የመሃል ሜዳ ተጫዋች ንጎሎ ካንቴ የእግር ኳሱ የበላይ ኃላፊዎች ጉዳዩን በአንክሮ ካልመረመሩት የዘረኝነት ጥቃቱ ከዚህም በላይ የከፋ ሊሆን ይችላል በማለት የጉዳዩን አሳሳቢነት ተናግሯል። በጉዳዩ ላይ ከዚህም በላይ መነጋገር ለተጫዋቾች የግድ አስፈላጊ ነው ብሎ ያምናል ካንቴ። በሁለተኛው አጋማሽ ደጋፊዎች ሲናገሩት የነበረው ነገር አጸያፊ ነው፤ በእግር ኳስ ውስጥ ይህ መኖር አልነበረበትም። ነገር ግን ጤናማ እግር ኳስ ይኖረን ዘንድ እኛም ተገቢውን ምላሽ ሰጥተን ማስተካከል የሚኖርብን ይመስለኛል ብሏል የቼልሲው ኮከብ። በእርግጥ የተባለውን ነገር አልሰማሁም ነበር የሚለው ካንቴ የቡድኑ አምበል አዝፒሊኬታ ጉዳዩን ለዳኛው ሲያመለክት ነበር ጥቃት እየሰነዘሩብን እንደነበር የገባኝና እኔም ማዳመጥ የጀመርኩት በማለት በጨዋታው የደረሰባቸውን የዘረኝነት ጥቃት እንዴት እንደተረዳ ለቢቢሲ አስረድቷል። ይህንን ድርጊት ለማስተካከል በየደረጃው የሚገኙ የእግር ኳሱ የበላይ ጠባቂዎች የመፍትሔ አማራጮችን እንዲያስቀምጡም ካንቴ ጥሪውን አቅርቧል። ዳኞች አሉ፣ የፕሪሚየር ሊጉ የበላይ አካል አለ፤ ስለዚህ እነሱ መፍትሔ ያመጣሉ ብለን ተስፋ እናደርጋለን። መፍትሔው እንዲመጣ ግን የሆነውን ነገር ለሚመለከታቸው አካላት ማመልከት ከእኛ የሚጠበቅ ነው ያለው ካንቴ ችግሩን ለመቅረፍ እየሞከሩ እንደሆነ አምናለሁ፤ ነገር ግን እንዴት ሊያስተካክሉት እንደሚችሉ በጋራ የምናየው ይሆናል ብሏል የፈረንሳይና የቼልሲው የመሃል ሜዳ ተጫዋች ንጎሎ ካንቴ። ተያያዥ ርዕሶች
ቱርክ የፈረንሳዩን ፕሬዝደንት ሽብርን ይደግፋሉ ስትል ከሰሰች
ኖቬምበር አጭር የምስል መግለጫ የቱርኩ የውጪ ጉዳይ ሚንስትር ሜቭሉት ካቩሶግሉ የቱርኩ የውጪ ጉዳይ ሚንስትር፤ የፈረንሳዩ ፕሬዝደንት ኢማኑኤል ማክሮን ሽብርተኝነትን ይደግፋሉ ሲሉ ተቹ። የፈረንሳይ ባለስልጣናት ቱርክ በሶሪያ የወሰደችውን እርምጃ መተቸታቸውን ተከትሎ ነው የቱርኩ የውጪ ጉዳይ ሚንስትር ሜቭሉት ካቩሶግሉ ይህን ትችት የሰነዘሩት። የውጪ ጉዳይ ሚንስትሩ ማክሮን የአውሮፓ መሪ መሆን ቢፈልጉም፤ መረጋጋት እንኳ አልቻሉም በማለት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። ባለፈው ወር ማክሮን በኩርዶች የሚመሩትን የሶሪያ ዲሞክራቲክ ኃይል ተቀብለው ማነጋገራቸው ቱርክን እጅጉን አበሳጭቶ እንደነበረ ይታወሳል። የፕሬዝደንት ማክሮን ጽ ቤት የሶሪያ ዲሞክራቲክ ኃይልን ተቀብለው ያነጋገሩት አይኤስን በመዋጋት ረገድ ለሚያሳዩት አጋርነት እውቅና ለመስጠት እና ቱርክ በሰሜን ሶሪያ ላይ ልትወስደው ስላሰበችው የጦር እርምጃ ለመምክር መሆኑን አስታውቆ ነበር። ኩርዶች በቱርክ፣ ኢራቅ፣ ኢራን እና ሶሪያ ውስጥ ተበታትነው የሚኖሩ ሲሆን፤ የራሳቸውን ሉዓላዊት፣ ነጻ አገር ለመመስረት ይታገላሉ። በቱርክ ብቻ ወደ ሚሊዮን የሚጠጉ ኩርዶች እንደሚኖሩ የሚገመት ሲሆን፤ ቱርክ ነጻ አገርን ለመመስረት የሚታገሉትን ኩርዶች አሸባሪ ስትል ትፈርጃቸዋለች። የፈረንሳዩ ፕሬዝደንት ኢማኑኤል ማክሮን ከሦስት ሳምንታት በፊት ባደረጉት ንግግር የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃልኪዳን ድርጅት ኔቶ ቱርክ በሰሜን ሶሪያ ለጀመረችው ወታደራዊ እርምጃ ምላሽ መስጠት ባለመቻሉ ክፉኛ ኮንነውታል። ማክሮን ኔቶን አዕምሮው ሞቷል ሲሉም ገልጸውታል። በተጨማሪም የኔቶ አባል አገራት ወሳኝ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ውይይት ማድረግ እና ከውሳኔ መድረስ እንደተሳናቸው ተናግረዋል። አጭር የምስል መግለጫ የቱርክ እና ሩሲያ ጥምር ኃይል በሰሜናዊ ሶሪያ የምድር ቅኝት እያደረጉ ይገኛሉ። የቱርኩ የውጪ ጉዳይ ሚንስትር ሜቭሉት ካቩሶግሉ፤ ትናንት ከአገሪቱ የሕዝብ እንደራሴዎች ፊት ቀርበው፤ እሱ ማክሮን የአሸባሪ ደጋፊ ነው። በተደጋጋሚ ወደ ቤተ መንግሥት እየጠራ ያስተናግዳቸዋል። ወዳጆቼ አሸባሪ ኃይሎች ናቸው ካለ ከዚህ በላይ ምንም ማለት አይቻልም ብለዋል። ቱርክ ወደ ሰሜን ሶሪያ ዘልቃ በመግባት ደህንነቱ የተረጋገጠ ቀጠና ለመፍጠር ከ በላይ ኪሎ ሜትሮችን ዘልቃ በመግባት የጦር እርምጃዎችን ስትወስድ ቆይታለች። በዚሁ ቀጠና የቱርክ እና ሩሲያ ጥምር ኃይል የምድር ቅኝት እያደረጉ ይገኛሉ። ቱርክ ከወራት በፊት ዘመናዊ ሩሲያ ሰራሽ ኤስ የተሰኙ ከምድር ወደ አየር ሚሳኤል ሥርዓቶችን ከክሬምሊን መግዛቷን ተከትሎ ከኔቶ አባል አገራት ጋር ያላት ወዳጅነት ሻክሯል። ተያያዥ ርዕሶች
ቦርሳቸው ውስጥ የሞተ ሰው እጅ የተገኘባቸው ሩስያዊ ፕሮፌሰር በቁጥጥር ሥር ዋሉ
ኖቬምበር ማጋሪያ ምረጥ የሴይንት ፒተርስበርግ ፖሊስ ቦርሳቸው ውስጥ የተቆረጥ የሰው ልጅ እጅ አግኝቼባቸዋለሁ ያላቸውን የታሪክ ምሁር በቁጥጥር ሥር አዋለ። ፕሮፌሰሩም ፍቅረኛቸውን እንደገደሉ አምነዋል። ጉምቱው ፕሮፌሰር ኦሌግ ሶኮሎቭ ሰክረው ወንዝ ውስጥ ወድቀው ነው የተገኙት። ወንዝ አካባቢ የተገኙትም እጁን ሊጥሉት ሳይሆን አይቀርም ተብሏል። ሰውዬው ከተያዙ በኋላ ቤታቸውን የፈተሸው ፖሊስ የፕሮፌሰሩ የቀድሞ ተማሪ የነበረች የ ዓመት ወጣት ሬሳ አግኝቷል። የፕሮፌሰሩ ቤት ውስጥ ጭንቅላቷ ተቆርጦ ሬሳዋ የተገኘችው ሴት አናስታሲያ የሺቼንኮ ከፕሮፌሰሩ ጋር በርካታ ፅሑፎች ያሳተመች ተማሪ ናት። አብራሞቪች ስዊዘርላንድ እንዳይገቡ ተከለከሉ የናፖሌዮን ታሪክ ተመራማሪ የሆኑት ፕሮፌሰር ሶኮሎቭ በፈረንሳይ የሌጌዎን ክብር የተሰጣቸው ሰው ናቸው። የግለሰቡ ጠበቃ የሆኑ ሰው ፕፎፌሰሩ ፍቅረኛቸው የነበረችውን ወጣት መግደላቸውን አምነዋል ሲሉ ተናግረዋል። የ ዓመቱ ፕሮፌሰር የወጣቷን ሬሳ ካስወገዱ በኋላ እንደናፖሌዮን ለብሰው አደባባይ ላይ ራሳቸውን ሊያጠፉ አስበው እንደነበርም ታውቋል። ግለሰቡ ከፍቅረኛቸው ጋር ባለመግባባታቸው ምክንያት እንደገደሏትና ጭንቅላቷን እንደቆረጡ ለፖሊስ አምነዋል።