topic
stringlengths
16
333
news
stringlengths
16
46.2k
ግብር አጭበርባሪዎች በማኅበራዊ ሚዲያ ፖስት ሊታደኑ ነው
ዲሴምበር ፈረንሳይ የዜጎቿን የማኅበራዊ ሚዲያ ገጽ በመፈተሽ ግብር አጭበርባሪዎችን ልትለይ ነው። የማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች በገጻቸው ላይ የሚለጥፉትን ፎቶግራፍና የግል መረጃ ዝርዝር ፕሮፋይል በማየት ግብር የከፈሉና ያልከፈሉ እንደሚለዩ ተገልጿል። ድንጋጌው ባለፈው ሳምንት ከግብር ክፍያ ጋር በተያያዘ የወጣው ሕግ አካል ነው። የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች እና የፈረንሳይ የመረጃ ደህንነት ክፍል ሕጉ እንደሚያሰጋቸው ተናግረዋል። ሕጉን ያፀደቀው ምክር ቤት፤ እርምጃው የዜጎች ራስን በነፃነት የመግለጽ መብት ላይ ጫና ሊያሳድር ቢችልም፤ ድንጋጌው የሚተገበርበት ቅድመ ሁኔታዎች አሉ ብሏል። ከቅድመ ሁኔታዎቹ አንዱ በሚስጥራዊ ይለፍ ቃል ፓስወርድ የተቆለፉ ገጾችን ሰብሮ አለመግባት ሲሆን፤ የግብር ክፍያ ክፍሉ ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ለሕዝብ ይፋ የተደረጉ መረጃዎችን መጠቀም ግን ይችላል። የፈረንሳይ መንግሥት የዜጎቹን የድረ ገጽ እንቅስቃሴ የሚቃኝበት የሦስት ዓመት እቅድ ነድፏል። ግብር ያልከፈሉ ሰዎችን ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ በሚለጥፉት መረጃ ማግኘት የዚሁ እቅድ አካል ነው። የፈረንሳይ የመረጃ ደህንነት ክፍል የሦስት ዓመት እቅዱ ሕጋዊ አግባብነት ቢኖረውም፤ ግብርን በተመለከተ የወጣው ድንጋጌ የዜጎችን ነፃነት ይጋፋል ብሏል። የበጀት ሚንስትሩ ጄራልድ ዳርማኒን በበኩላቸው አጭበርባሪዎችን የምንገታበት አንድ መንገድ ነው ሲሉ ሕጉን ገልጸውታል። በዚህ ዓመት ፈረንሳይ አልኖርኩም ብለሽ፤ ኢንስታግራም ላይ የፈረንሳይ ፎቶዎችን ብትለጥፊ ችግር አለ ማለት ነው ሲሉ ለ ለ ፊጋሮ ጋዜጣ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
ፈረንሳይ ኩሽና ውስጥ ተሰቅሎ የተገኘው ሥዕል ብሔራዊ ሐብት ነው አለች
ዲሴምበር አጭር የምስል መግለጫ ሥዕሉ ለበርካታ ዓመታት በኩሽና ውስጥ ከማብሰያ ምድጃ በላይ ግድግዳ ላይ ተንጠልጥሎ ቆይቷል። በአንዲት ፈረንሳዊት አዛውንት ኩሽና ውስጥ የተገኘው ጥንታዊ ስዕል የሥነጥበብ ባለሙያዎችን ሲያስደንቅ ቆይቶ አሁን ላይ የፈረንሳይ መንግሥት ብሔራዊ ቅርስ ነው በማለት ወደ ሌላ ሃገር እንዳይላክ እገዳ ጥሏል። በእውቅ ጣሊያናዊ ሰዓሊ ተስሎ የነበረው እና ለረዥም ዓመታት ጠፍቶ የቆየው ይህ ሥዕል በአንዲት አዛውንት ፈረንሳዊት ሴት ኩሽና ውስጥ ከተገኘ በኋላ ሪከርድ በሆነ በ ሚሊዮን ዩሮ ዋጋ በጨረታ መሸጡ ይታወሳል። ይህ የሥዕል ሥራ ከሁለት ወራት በፊት ነበር በሰሜናዊ ፈረንሳይ ነበር የተገኘው። ካናዳን በጥበብ ሥራው ያስዋበው ኢትዮጵያዊ ሚሊዮን ዩሮ ከፍሎ የገዛው አካል ማን እንደሆነ በአጫራቾቹ በይፋ ባይነገርም፤ የፈረንሳይ መገናኛ ብዙሃን ግን ሥዕሉን የገዙት የጣሊያን የጥንት የሥዕል ሥራዎችን በመሰበሰብ የሚታወቁ ነዋሪነታቸው በአሜሪካ የሆኑ ሁለት የቺሊ ዜጎች መሆናቸውን ዘግበዋል። የፈረንሳይ መንግሥት ይህን የሥዕል ሥራ መልሶ ከግለሰቦች እጅ ለመግዛት የሚያስፈልገውን ገንዘብ ምንጭ እስኪያገኝ ድረስ ለ ወራት ሥዕሉ ከሃገር እንዳይወጣ ወስኗል። ሥዕሉ ለበርካታ ዓመታት በኩሽና ውስጥ ከማብሰያ ምድጃ በላይ ግድግዳ ላይ ተንጠልጥሎ ቆይቷል። አንድ የሥዕል ባለሙያ እና አጫራች ሥዕሉን ከተመለከተ በኋላ ባለቤቶቹ የሥዕሉን ዋጋ ለማስተመን ባለሙያዎችን እንዲያማክሩ ሲወተውት ነበር ተብሏል። ባለቤቶቹ ግን ሥዕሉ እድሜ ጠገብ ሃይማኖታዊ ምልክት ያለው ሥዕል ከመሆን ባለፈ ብዙ ዋጋ ያለው የጥበብ ሥራ መስሎ አልታያቸውም። በሥዕሉ ላይ የተደረጉ ጥልቅ ምርምሮች ሥዕሉ የጣሊያናዊው ሰዓሊ ሶኒ ዲ ፔፖ መሆኑን አረጋግጠዋል። በጣሊያን ፍሎረንስ የተወለደው ሶኒ ዲ ፔፖ በ ኛው ክፈለ ዘመን መጨረሻ ላይ እና በ ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ላይ የሥዕል ሥራዎችን ሰርቷል። ይህ የጥበብ ሥራ በመጠን አነስተኛ ሲሆን ሲ ሜትር በ ሴንቲ ሜትር ያክላል። ሥዕሉ የአንድ የሥዕል ሥራ አካል ሲሆን የተቀሩት ሥዕሎች ሎንደን እና ኒው ዮርክ በሚገኙ የሥዕል ማሳያ ማዕከል ውስጥ ይገኛሉ። ተያያዥ ርዕሶች
የፈረንሳዩ ኩባንያ ኢትዮጵያ ውስጥ የፊልም ቻናል ሊከፍት ነው
ፌብሩወሪ ማጋሪያ ምረጥ የፈረንሳዩ የቴሌቪዥን ድርጅት ካናል ኢትዮጵያ ውስጥ የራሱን ቻናል ከፍቶ ፊልሞችን ለማሳየት የሚያስችለውን ስምምነት ከድርጅታቸው ጋር መፈራረሙን የኖላዊ ፊልም ፕሮዳክሽን ሥራ አስኪያጅ ሐኒ ወርቁ ለቢቢሲ ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ፊልም ፕሮዲውሰሮች ማህበር ሰብሳቢ የሆኑት ቢንያም አለማየሁ በበኩላቸው፣ ካናል ፕሉስ ብቻ ሳይሆን ሌሎች የውጪ ድርጅቶችም የኢትዮጵያን ፊልሞች ለማሳየት ፍላጎት ኖሯቸው ወደ ማህበራቸው መምጣታቸውን ይናገራሉ። የሚከፈተው ቻናል የተመረጡ የኢትዮጵያ ፊልሞች ብቻ የሚታዩበት መሆኑን የሚናገሩት ሥራ አስኪያጇ፤ ለተወሰኑ ወራት አዳዲስ ፊልሞችን በመከራየት ለማሳየት መስማማታቸውን ገልፀዋል። ሥምምነቱ የተለያዩ ዝርዝር ጉዳዮችን የያዘ መሆኑን የገለፁት ሥራ አስኪያጇ፤ ከፕሮዲውሰር ማኅበር ጋር በመሆን የሚታዩ ፊልሞችን የመምረጥ ሥራው እንደሚሠራ አስታውቀዋል። ካናል ፕሉስ፣ በኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች የተሰሩ ፊልሞችን ብቻ ለተወሰነ ጊዜ ለማሳየት መዋዋሉን የሚገልፁት አቶ ቢንያም፣ የሲኒማ ጊዜያቸውን ጨርሰው የወረዱ አዳዲስ ፊልሞች፣ ሌሎች የማሳያ አማራጮችን እንደ ዩቱብ ያሉን ከመጠቀማቸው በፊት በቴሌቪዥን የሚቀርቡ መሆኑን ያስረዳሉ። ምን ልታዘዝ አልተቋረጠም ፋና ብሮድካስቲንግ ሐኒ እንደሚሉት ይህ ስምምነት የፊልም ፕሮዲውሰሮችን እንዲሁም በፊልም ሥራ ላይ የተሳተፉ አካላትን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ አስረድተዋል። የሚታዩት ፊልሞች የሃገራችንን ገጽታ የሚገነቡ፣ ፊልሙ የደረሰበትን ደረጃ የሚያሳዩ ይሆናሉ ያሉት ሥራ አስኪያጇ፤ ቻናሉ ሙሉ በሙሉ የኢትዮጵያን ፊልም ብቻ እንደሚያሳይ ተናግረዋል። በኢትዮጵያ ውስጥ ፊልሞች ገቢያቸውን የሚሰበስቡት በአብዛኛው በሲኒማ ቤቶች ከሚያሳዩት ነው የሚሉት የኖላዊ ፊልም ፕሮዳክሽን ሥራ አስኪያጅ፣ ቴሌቪዥን ጣቢያዎች ሲገዙም በርካሽ ዋጋ ነበር ይላሉ። ሥራ አስኪያጇ አክለውም እነዚህ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች እስከዛሬ ድረስ ፊልሞቹን ሲገዙ የባለቤትነት መብቱንም አብረው እንደሚወስዱ አስታውሰው፤ ተጠቃሚ አላደረገንም በማለት የነበረውን ክፍተት ያስረዳሉ። ካናል ፕሉስ ግን ከዚህ በተለየ አዳዲስ ፊልሞችን ለስድስት ወር ብቻ የማሳየት ፈቃድ እንደሚወስድ አስረድተው የተሻለ ክፍያም ይከፍላል ብለዋል። ከስድስት ወር በኋላ ፕሮዲውሰሩ ለፈለገው ጣቢያ የመሸጥ መብት ይኖረዋል ያሉት ሥራ አስኪያጇ ይህንን ማስጠበቅ መቻል ትልቅ ድል ነው ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ፊልሞች በተለያየ መንገድ እንደሚሸጡ ያስታወሱት ሐኒ፤ በሲኒማ ቤቶች ማሳየት፣ በኦንላይን እንዲታይ ማድረግና የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ለተወሰነ ጊዜ መብቱን ወስደው እንዲያሳዩ ማድረግ እንደሚገኙባቸው አስረድተዋል። ይህ ሥምምነት ሁለት ዓመት መፍጀቱን የሚናገሩት አቶ ቢኒያም በበኩላቸው፣ የኢትዮጵያን ፊልሞች ለኢትዮጵያውያን በአገር ውስጥ ለማሳየት ፈልገው መምጣታቸውን ይናገራሉ። ፊልም በተለያየ መንገድ ሊሸጥ ይችላል የሚሉት አቶ ቢኒያም፣ ከሲኒማ ቤት ውጪ፣ በሲዲ፣ በዩቱብ፣ በቴሌቪዥን በመሸጥ መጠቀም እንደሚቻል ያስረዳሉ። የካናል ፕሉስም መምጣት ፊልም ሠሪዎቹ የተሻለ ገንዘብ ለማግኘት የሚያስችል በመሆኑ እንደ ፕሮዲውሰር ብቻ ሳይሆን እንደ ባለሙያም ትልቅ አቅም ይፈጥራል ሲሉ ይናገራሉ። ከዚህ በፊት ባለቤትነታቸውን አሳልፈው የተሸጡ ፊልሞች በጣቢያቸው እንደማይታዩ የሚገልፁት የኖላዊ ሥራ አስኪያጅ፤ ነገር ግን ለተወሰነ ጊዜ ብቻ በተለያዩ ጣቢያዎች ሲታዩ የነበሩ ካሉ ኮንትራታቸውን ከጨረሱ በጣቢያው ሊታዩ እንደሚችሉ ጠቁመዋል። ካናል ፕሉስ በኢትዮጵያ ውስጥ የራሱን ቻናል ሲከፍት ኢትዮጵያዊ ስም የሚኖረው ሲሆን፤ ስምምነቱ በቴሌቪዥን ማሳየት ብቻ እንጂ ኦንላይን ሥርጭቱን እንደማይመለከተው ገልፀዋል። ኖላዊ ፊልም ፕሮዳክሽን ከተመሠረተ ዓመት የሆነው ሲሆን የተለያዩ ፊልሞችንና ዘጋቢ ፊልሞችን በመሥራት ይታወቃል። ፕሮዳክሽኑ እንደ ይግባኝ ያሉ ፊልሞችን ፕሮዲውስ በማድረግ ለሕዝብ ዕይታ ማብቃቱ ይታወሳል። ካናል ፕሉስ ተቀማጭነቱን በፈረንሳይ ያደረገ የሚዲያ ተቋም ሲሆን በዓለም አቀፍ ደረጃ ከ ሚሊየን በላይ ተከታዮች አሉት። ካናል ፕሉስ፣ የሚዲያ እና የፊልም ኩባንያ ለኢትዮጵያ ገበያ የሳተላይት የቴሌቪዥን አገልግሎቶችን በመስጠትና ፊልሞችን ፕሮድዩስ በማድረግ ከ ሚሊዮን ዩሮ በላይ ኢንቨስት እያደረገ ነው ሲሉ በፈረንሳይ ኢትዮጵያ አምባሳደር የሆኑት ሔኖክ ተፈራ ሻውል በሊንክዲን ገጻቸው ላይ አስታውቀው ነበር። አምባሳደሩ ድርጅቱ ያደረገውን ስምምነት ለአገራችን የባህል ኢንዱስትሪ ልማት የላቀ አስተዋፅዖ ይኖረዋል ሲሉ ነበር የገለፁት። የፊልም ፕሮዲውሰሮችም ሆነ ሠሪዎች በዚህ ሥምምነት ደስተኛ መሆናቸውን የሚናገሩት አቶ ቢኒያም፣ በዚህ ዓመት መጨረሻ አስፈላጊውን ዝግጅት ጨርሶ ማሳየት ይጀምራል የሚል ተስፋ እንዳላቸው ለቢቢሲ ገልፀዋል። ተያያዥ ርዕሶች
የወጣቶች ጅምላ እሥር በአዲስ አበባ
ሴፕቴምበር ማጋሪያ ምረጥ ዕለተ ረቡዕ መስከረም ፤ ወ ሮ መሠለች ተክሌ እና ቤተሰቦቻቸው የ ቀን ልጅ ልጃቸውን ትንሽ አመም አርጓት ኖሮ ወደ ሆስታል ያቀናሉ። ቤተሰቡ ሃገር ሰላም ብሎ፤ ከሆስፒታል ተመልሶ ምሳ ለመብላት ሲሳናዳ ግን ያልታሰበ ነገር ተከሰተ። የደንብ ልብሳቸውን በወጉ የታጠቁ አራት አምስት የሚሆኑ የፀጥታ ኃይሎች ልጄን አቶ መኮንንን ፍለጋ በክፍት መኪና መጡ ይላሉ። አንድ ጉርሻ እንኳን ይጉረስ ብላቸው እምቢ አሉኝ ይላሉ ወ ሮ መሠለች። በሃገሪቱ የተከሰቱት ቀውሶችና አዲስ አበባ የፀጥታ ኃይሎቹና ልጃቸው መኮንን ወደ አሥር ሰዓት ገደማ ወደቤት መጥተው ፖሊሶቹ ፍተሻ እንዳደረጉ ወ ሮ መሠለች ያስታውሳሉ። ለጥያቄ ነው የምንፈልገው ይመለሳል ብለው ነው የወሰዱት የሚሉት እናት መሠለች ልጃቸው መኮንን ግንቦት ወደ ሃገር ቤት ሲገባ ለማስተባበር የተሰለፈው ኮሚቴ አባል እንደሆነ ያወሳሉ። ነገር ግን ልጃቸው መኮንን ፍርድ ቤት በቀረበ ወቅት ከቡራዩ እና አሸዋ ሜዳ ግርግሮች ጋር በተያያዘ እንደተያዘ ተነግሮታል ይላሉ። ከአርበኞች ግንቦት ሰባት ንቅናቄ ተገንጥሎ የሚወጣ አካል የለም ኤፍሬም ማዴቦ እናቴ እና እህት ወንድሞቼ ቡራዩ የተከሰተውን ግድያ በመሸሽ እኔ ጋር ተጠልለው ነው ያሉት፤ እኔ እንዴት እንዲህ ዓይነት ነገር አደርጋለሁ፤ ብሎ ተክራክሯል በማለት የፍርድ ቤት ውሎውን ያስታውሳሉ ወ ሮ መሠለች። ኛ ፖሊስ ጣብያ መጀመሪያ ላይ ታስረውበት የነበረው ቦታ ለጤና ምቹ ያልሆነ፣ ጨለማ እና የሽንት ሽታ የነበረው እንደሆነ ወ ሮ መሰለች ነግረውናል። አሁን ግን ይላሉ፤ አሁን ግን የተሻለ ሁኔታ ላይ ነው ያሉት በማለት ያክላሉ። እንደሳቸው ልጅ ላለ የልብ ህመም እና የሳይነስ አለርጂ ላለበት ቀርቶ ለማንም የሚመች እንዳልሆነም ይጨምራሉ። ከኦሮሞ ነፃ አውጭ ግንባር ኦነግ ወደ ሃገር ቤት መመለስ ዋዜማ ጀምሮ ሰላም ርቋት የቆየችው አዲስ አበባ ከሰሞኑ ደግሞ በየቦታው በሚስተዋሉ ጅምላ እሥሮች ድንጋጤ ላይ ያለች ትመስላለች። በፌስቡክ ስሙ የሚታወቅ ሰው ከፈረንሳይ አካባቢ ኳስ በመመልከት ላይ ሳለ ከምሽቱ አራት ሰዓት ገደማ ከሌሎች ሰዎች ጋር በጅምላ እንደታሰረ በገፁ ፅፏል። ከእሥር በኋላ ነው ሁሉም ከየተያዘበት በቡድን በቡድን ሆኖ እንዲሰለፍ የተደረገው የሚለው አቤል የእሥሩ ዓላማ ሰውን ማስደንበር ሳይሆን አይቀርም ይላል። ዛሬ ከሰዓት የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ባወጣው መረጃ መሠረት ከመስከረም ባሉት ቀናት ሰዎች ተገድለዋል፡፡ ከእነዚህም መሀከል ቱ በፖሊስ የተገደሉ ሲሆኑ አንድ ሰው በስህተት የተገደለ ነው ብሏል ፖሊስ፡፡ ከዚው ውጭ የሚወጡ መረጃዎች ፖሊስ የሚያውቃቸው አይደለም ሲሉ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሜጀር ጄነራል ደግፌ በዲ በዛሬው እለት በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል። ፖሊስ ሁከቱን ለማስቆም ባደረገው ሙከራም በህገ ወጥ ተግባራት ላይ ተሰማርተው የተገኙ በርከት ያሉ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋሉንም ኮሚሽነሩ አብራርተዋል። በአሁኑ ወቅትም በሁከቱ ላይ ቀጥተኛ ተሳታፊ የነበሩ ሺህ የሚሆኑ ግለሰቦችን ከተለያዩ አካባቢዎች በመሰብሰብ በቀጣይ ሌላ ጥፋት ላይ እንዳይሳተፉ ለማድረግ ሰንዳፋ እንዲቆዩ ከተደረገ በኋላ ለተሃድሶ ስልጠና ወደ ጦላይ እንዲገቡ መደረጉንም ኮሚሽነሩ አክለዋል። ኮሚሽነሩ ሰዎች በህግ ይጠየቃሉ፤ ሌሎች ከ በላይ ደግሞ ከሺሻ ቤት እና ቁማር ቤቶች የተያዙና በርካታ ገንዘቦች ያሏቸው ናቸው ብለዋል። ወ ሮ መሠለች ልጃቸው በቁጥጥር ሥር ሲውልም ሆነ ፍተሻ ሲደረግበት የፍርድ ቤት ማዘዣ እንዳልነበር ይናገራሉ። እግዚአብሔር ካለ መስከረም ገደማ ይፈታል ብለን እንጠብቃለን ሲሉ ወ ሮ መሠለች ተሰፋ ያደርጋሉ።
በኬንያ የሚገኙ ኦሮሞ ስደተኞች ፖሊስ እገዳ እንዳበዛባቸው ይገልጻሉ
ኦክተውበር ማጋሪያ ምረጥ አጭር የምስል መግለጫ በኬንያ ናይሮቢ በ የተከበረው የኢሬቻ በዓል የኬንያ ባለስልጣናት በኢትዮጵያ መንግሥት ግፊት በሃገራቸው የሚገኙ ስደተኞች ላይ እገዳ እየጣሉባቸው መሆኑን የስደተኞች ቡድንና ሂውማን ራይትስ ዋች ገለጹ። የኦሮሞ ስደተኞች መስከረም ዓ ም የኢሬቻ በዓልን በይፋ ለማክበር ያቀረቡት ጥያቄ ውድቅ መሆኑን ተከትሎ ጥቅምት በዓሉን በግል ይዞታ ላይ አክብረዋል። እነሱ እንደሚሉት ይህ በተከታታይ በኬንያ ባለስልጣናት ከሚጣሉባቸው ገደቦች አንዱ ነው። ዲሪርሳ ቀጄላ በኬንያ የሚገኘው የኦሮሞ ስደተኞች ማህበር የህዝብ ኮሙኒኬሽን ኃላፊ ነው። ዲሪርሳ እንደሚለው ችግሩ የጀምረው እ አ አ በ በእድሜ ባለጸጋው የባህል እና የታሪክ አዋቂው ዳበሳ ጉዮ የት እንደደረሱ ከጠፉ በኋላ ነው። ግለሰቡ ከናይሮቢ ቤታቸው የጠፉት በዚያ ዓመት ከተካሄደው ኢሬቻ ክብረ በዓል በኋላ ነበር። በ የተከበረው የኢሬቻ ክብረ በዓል ከመጀመሩ በፊትም ኦሮሞዎች በኬንያ ፖሊስ በቁጥጥር ስር ውለዋል። ናይሮቢ ውስጥ ህገወጥ የኦሮሞ ማህበረሰብ ሊያቋቁሙ ነው በሚል ነው የተያዙት። የኢትዮጵያ መንግሥትን ሊያስቆጣ ይችላል ባለፉት ዓመታት ኢሬቻን እያከበርን ብንቆይም ዘንድሮ ለማክበር ያቀረብነው ህጋዊ ጥያቄ ውድቅ ተደርጎብናል ሲል ዲሪርሳ ለቢቢሲ ተናግሯል። የዓመታዊውን ክብረ በዓል ዓላማ እና እስከ የሚደርሱ ሰዎች እንደሚሳተፉበት በመጥቀስ በናይሮቢ ሲቲ ፓርክ ለማክበር የጽሑፍ ጥያቄ ቀርበው ነበር። የከተማዋ ፖሊስ ኮሚሽን ጥያቄውን ለጊጊሪ ፖሊስ ጣቢያ ቢመራውም ጥያቄያቸው ውድቅ መደረጉን ዲሪርሳ አስታውቋል። ማህበሩ ስለጉዳዩ ናይሮቢ ከሚገኘውን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ፈቃድ መጠየቅ እንዳለበት ተገልጾላቸዋል። ፖሊስ ፈቃዱን የሚሰጠው ከኤምባሲው ፈቃድ ከተገኘ በኋላ ነው ተብለዋል። የፖሊስ ጣቢያው አዛዥ በፖለቲካዊ ምክንያቶች ኦሮሞዎች እንዲሰበሰቡም ሆነ በዓል እንዲያከብሩ ፈቃድ እንደማይሰጡ ገልጸውልናል። ሆኖም እነዚህ ፖለቲካዊ ምክንያቶች ምን እንደሆኑ ግልጽ አላደረጉልንም ሲል ዲሪርሳ አስታውቋል። እንደዲሪርሳ አገላለጽ ከሆነ ኤምባሲውን ሳያማክሩ ክብረ በዓሉ እንዲካሄድ ቢፈቅዱ የኢትዮጵያ መንግሥትን ሊያስቆጣ ይችላል ተብለዋል። አጭር የምስል መግለጫ ዳበሳ ጉዮ በ ኬንያ በተከበረው የኢሬቻ በዓል ላይ የስደተኖች ጉዳይ በኬንያ የህዝብ ሥነ ምግባር ህግ አንቀጽ እንደሰፈረው ከሆነ ለማህበራዊ፣ ባህላዊ እና ለበጎ ፈቃድ አገልግሎት መሰባሰብ ፈቃድ አያስፈልገውም። በዚህ መሠረት ኢሬቻ እንዳይከበር የሚከለክል ምክንያት አልነበረም። ኢሬቻ ባህላዊ ክብረ በዓል ቢሆንም ኦሮሞ አክቲቪስቶችን ጨምሮ የተለያዩ ወገኖች ክብረ በዓሉን ፖለቲካዊ ተቃውሞዎች የሚሰሙበት ሲያደርጉ ቆይተዋል። የማህበሩ አባላት ስደተኞች በመሆናቸው ከኤምባሲው ጋር ግንኙነት መፍጠር አለመቻላቸውን ለቢቢሲ አስታውቀዋል። ስደተኞች በመሆናችን ስለጉዳዩ ኤምባሲውን ለመጠየቅ መብት የለንም ይላል ዲሪብሳ። ብዙዎቹ ስደተኞች ኢትዮጵያን ለቀው የወጡት በፖለቲካ ምክንያት ነው። ደህንነት አይሰማኝም ይላል። እታሰራለሁ ወይንም ታፍኜ ወደ ኢትዮጵያ ልመለስ እችላለሁ የሚል ፍራቻ አለኝ። እስከማውቀው ድረስ የኬንያ ፖሊስና ኢትዮጵያ መንግሥስት ይህንን በተደጋጋሚ ሲያደርጉት ቆይተዋል ብሏል። ይህንንም እንደስደተኞች ጉዳይ እና ለተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽን ላሉ ድርጅቶች በተደጋጋሚ መረጃ ሰጥቻለሁ ሲል ይገልጻል። ተደጋጋሚ እገዳዎች የሂውማን ራይትስ ዋች የምሥራቅ አፍሪካ ከፍተኛ ተመራማሪ የሆኑት ፌሊክስ ሆርን በኬንያ ፖሊስ እና በኢትዮጵያ ኤምባሲ መካከል ጠንካራ ግንኙነት መኖሩን ለቢቢሲ ተናግረዋል። ሁለቱ አካላት በጋራ በመሆን ኢትዮጵያዊያን ስደተኞችንና ጥገኝነት ጠያቂዎችን በተደጋጋሚ ጊዜ ሲያንገላቱ፣ ሲያስፈራሩ ወይንም በዘፈቀደ ሲያስሩ እንደነበር ሂውማን ራይትስ ዋች መረጃዎች አሉት ይላሉ። የኦሮሞ ማህበረሰብ አባላት ተሰባስበው ኢሬቻን እንዳያከብሩ መከልከሉ፤ ስደተኞችን የማስፈራራትና የማንገላታት አዲሱ ስትራቴጂ ነው ሲሉ ያስረዳሉ። ድሪብሳ የሂውማን ራይትስ ዋች ጥናት ትክክል ነው ይላል። እሱ እንደሚለው የመሰብሰብ መብታቸውን ለኢሬቻ ብቻ ሳይሆን በሌሎች ማህበራዊ ጉዳዮች ላይም ለመገናኘት ተቸግረዋል። ማህበራችንን በኬንያ የማህበረሰብ ህግ መሠረት አስመዝግበን ፈቃዱን በየወቅቱ ብናድስም የመሰባሰብ መብታችንን ተከልክለናል ይላል ድሪብሳ። የኃላፊዎች ምላሽ የኢሬቻ በዓልን ለማክበር ከየትኛውም ድርጅት ጥያቄ እንዳልቀረበላቸው በኬንያ የኢትዮጵያ አምበሳደር ዲና ሙፍቲ ለቢቢሲ አስታውቀዋል። የኬንያ ፖሊስ ፈቃድ ስለመከልከሉ ምንም እንደማያውቁም ገልጸዋል። በቅርቡ ሂውማን ራይትስ ዋች የኬንያ ባለስልጣናትና ኢትዮጵያ መንግሥት በጋራ በመሆን ኢትዮጵያዊያን ስደተኞችን ከማንገላታት ባለፈ ለኢትዮጵያ አሳልፈው ይሰጣሉ ለሚለው ሪፖርት አምባሳደሩ ምላሽ ሰጥተዋል። እኛ ማንንም ከኬንያ አልወሰድንም፤ ለኬንያም አሳልፈን አልሰጠንም። በሁለቱ ሃገራት መካከል ያለውን የሁለትዮሽ ግንኙነት አጠናክረን ለመቀጠል እንሰራለን። ይህ ልብወለድ ነው ብለዋል። የናይሮቢ ፖሊስ ኮሚሽን፣ የጊጊሪ ፖሊስ ጣቢያ ኃላፊና ብሔራዊ የፖሊስ ህዝብ ግንኙነት ኃላፊን ለማናገር ሙከራ ቢደረግም ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆኑም። ተያያዥ ርዕሶች
ከእንግሊዝ ፈረንሳይ በባህር የሚያሻግረው ባቡርከእንግሊዝ ፈረንሳይ በባህር የሚያሻግረው ባቡር
ከእንግሊዝ ፈረንሳይ በባህር የሚያሻግረው ባቡር
ማላዊያን የራስተፈሪ እምነት ተከታዮች በድሬድሎክ ት ቤት እንዲገቡ ተፈቀደላቸው
ጥር ማላዊ፤ ራስተፈሪያን ከነ ድሬድሎካቸው ትምህርት ቤት እንዲገቡ ፈቀደች። የማላዊ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የራስተፈሪ እምነት ተከታይ ተማሪዎች ከነ ድሬድሎካቸው ትምህርት ቤት እንዲማሩ መንግሥት እንዲፈቅድ ትዕዛዝ ሰጥቷል። ጊዜያዊ የሆነው ውሳኔ የተላለፈው፤ ፍርድ ቤቱ የአንዲት ራስተፈሪ እምነት ተከታይ ጉዳይን ተከትሎ ነው። የራስ ተፈሪ እምነት ተከታዮች ፀጉራቸውን በረዥሙ በማሳደግ ይታወቃሉ። ይህ የፀጉር አስተዳደግ ዓይነት ድሬድሎክ በመባል ይታወቃል። ፍርድ ቤቱ በ ድሬድሎክ ምክንያት የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለመመዝገብ የተከለከለችውን ሕፃን ጉዳይ ሲያይ መቆየቱን የአገሪቷ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል። ኬንያ ራስተፈሪያኒዝም ኃይማኖት ነው ስትል በየነች ተማሪዋ በትምህርት ቤቱ አስተዳደር ድሬድሎኳን እንድትቆርጥ ተጠይቃ ነበር። ይህንን የክስ ጉዳይ ሲያዩ የነበሩት ዳኛ ትምህርት ቤቱ ተማሪዋን እንዲቀበልና ውሳኔ እስከሚሰጥ ድረስ ያለፋትን ትምህርትም ተጨማሪ ጊዜ በማስተማር እንዲያካክሱ ትዕዛዝ አስተላልፎ ነበር። ታዲያ ፍርድ ቤቱ ድሬድሎክ ን አስመልክቶ ፍርድ ቤቱ ባስተላለፈው ትዕዛዝ በማላዊ የሚገኙ ዳኞች ደስተኛ መሆናቸውን ገልፀዋል። የማላዊ የሕግ ባለሙያ ሴቶች ማኅበር ፀጉራቸውን ድሬድሎክ ያደረጉ ሁሉም የራስተፈሪ እምነት ተከታይ ተማሪዎች ትምህርት ቤት መግባት እንዲችሉ መንግሥትን ሲያሳስቡ ቆይተዋል። የማህበሩ ፕሬዚደንት ታዳላ ችንክዌዙሌ በመግለጫቸው የትምህርት ሚንስትር ፍርድ ቤቱ ያስተላለፈውን ትዕዛዝ ለመተግበር መመሪያ ያወጣል የሚለው በጣም አሳሳቢ ነበር ብለዋል። ተማሪዎችን ብቻ ሳይሆን ሁሉንም ራስ ተፈሪያን ህፃናት በራሳቸው የመኩራት መብት፣ የመማር መብት እና ሃይማኖት በፖሊሲ ተፅዕኖ ሊደረግበት እንዳይገባ ከግምት ውስጥ በማስገባቱ በውሳኔው በጣም ደስተኞች ነን ሲሉ የተሰማቸውን ገልፀዋል። ፀጉሯን ድሬድሎክ ማድረጓን ተከትሎ ከትምህርት ቤት የተከለከለችው ተማሪ ጉዳይ ማህበሩ በወካይነት እየተከራከረ ነው። ፍርድ ቤቱም ጊዜያዊ ትዕዛዝ ያስተላለፈ ሲሆን የተማሪዋ የክስ ሂደት እስከሚጠናቀቅ እና የመጨረሻ ብይን እስከሚሰጥ ድረስ ተግባራዊ ይሆናል። ከዚህ ቀደም ኔሽን ጋዜጣ በማላዊ የሚገኙ የራስ ተፈሪ እምነት ተከታዮች በሚደርስባቸው መገለል መንግሥትን እንደሚከሱ ዘግቧል። በፈረንጆቹ ኅዳር ድሬድሎክ ምክንያት ትምህርት ቤት እንዳይገቡ መከልከላቸውን ተከትሎም የተቃውሞ ሰልፍ አካሂደው ነበር። ከዚህ ዜና በተጨማሪ
ከብሔርም ከሐይማኖትም በላይ ሰውነት ከሰሃራ በረሃ ስቃይ አውጥቶኛል
ኖቬምበር አጭር የምስል መግለጫ በብሔርና በሃይማኖት ያቻቻለን የሰሃራ በረሃ ስቃይ ሃሩን አሕመድ ከሰሃራ በረሃ ሃሩር፣ ከደላሎች ዱላና እንግልት ተርፎ ጀርመን የሚኖረው ሃሩን አሕመድ፣ በበረሃው ውስጥ አቅም አጥቶ ሲወድቅ የደገፉትን፣ ሲታረዝ ያለበሱትን፣ በውሃ ጥም የከሰለ ከንፈሩን ያረሰረሱለትን ሲያስታውስ የሰው ልጅ በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ ተቻችሎ መኖር እንዳለበት ብዙ ተምሬያለሁ ይላል። በባሌ ዞን አጋርፋ የተወለደው ሃሩን፣ እንደማንኛውም ወጣት በፖለቲካ ምክንያት ችግር ቢደርስበትም እርሱ ግን ከሀገር የወጣሁት በግል ምክንያት ነው ይላል። እኤአ በ ከሻሸመኔ ተነስቶ ወደ ሱዳን አመራ። ከአንድ ዓመት የሱዳን ኑሮ በኋላ እዚያ ከሚገኙ ከአራት ጓደኞቹና ከሌሎች ስደተኞች ጋር በ መጀመሪያ ወደ ሊቢያ ጉዞ ጀመሩ። ህወሓት፡ ሃገራዊ ምርጫ የሚራዘም ከሆነ ትግራይ የራሷን ምርጫ ታካሂዳለች ከካርቱም ትንሽ ወጣ ያለ ቦታ ላይ ከኤርትራዊያን፣ ሶማሊያዊያንና ሱዳናዊያንና ከኢትዮጵያ ከተለያዩ አካባቢዎች ከመጡ ስደተኞች ጋር ሰበሰቡን ሲል በወቅቱ የነበረውን ያስታውሳል። ስቃያችን የጀመረው ገና ከካርቱም ስንነሳ ነው የሚለው ሃሩን፤ ሁሉንም በጋራ የሰበሰቡበት ስፍራ ከመድረሳቸው በፊት የያዙትን አራግፈው እንደወሰዱባቸው ሲናገር ሴቶችን ልብስ አስወልቀው ጭምር ነበር የፈተሿቸው በማለት ወርቅና ገንዘባቸውን እንደወሰዱባቸው ይገልጻል። ሁለት ቀን እዚያ በረሃ ውስጥ ካሳደሯቸው በኋላ ወደ ሰሃራ የሚወስደዳቸው ግለሰብ መጥቶ መንገድ ጀመሩ። በአንድ መኪና ላይ ከ በላይ ሰዎች ሲጫኑ ሁሉም እንደትውውቃቸው፣ እንደመጡበት ሀገርና አካባቢ ብሔራቸውን ጭምር መሰረት አድርገው መቧደናቸውን ያስታውሳል። እሷ ማናት፡ ዘቢብ ካቩማ ለዩኤን እሠራለሁ ብዬ አስቤ አላውቅም አራት ቀንና ሌሊት ከተጓዙ በኋላ መኪናዋ ላይ የተሳፈሩ ስደተኞች ጥል እየተካረረ መጣ። ሰዎች ከፍርሃትና ከተስፋ መቁረጥ የተነሳ የራሳቸውን ምግብና ውሃ እየደበቁ የሌላ ግለሰብ ስንቅ መስረቅ በመጀመራቸው አለመግባባቱ ወደ ድብድብ አደገ። መጎሻሸሙ፣ ቡጢውና ጉልበት መፈታተሹ እርስ በእርስ ብቻ ሳይሆን ወደ ሰሃራ ይዟቸው እየሄደ ከነበረው ግለሰብ ጋርም ሆነ። ጉዞ በጀመሩ በሰባተኛው ቀን ሱዳን፣ ግብጽንና ሊቢያን የሚያዋስነው ድንበር ላይ ስደተኞችን የሚለዋወጡበት ስፍራ ደረሱ። ስፍራው ላይ ሲደርሱ ግን እድል ከእነርሱ ጋር አልነበረችም። ከሊቢያ ሊቀበላቸው የመጣው ግለሰብ በታጣቂዎች ተይዞ ጠበቃቸው። ቀደም ብሎ እኔ ስለተያዝኩ አታምጣቸው ብሎ ይዞን እየሄደ ለነበረው ሰው መልዕክት ልኮለት ነበር የሚለው ሃሩን እርሱ ግን ከእኛ ጋር ተጣልቶ ስለነበር የራሳቸው ጉዳይ በሚል ስሜት ነበር ይዞን ሄደ ይላል። በሦስቱ ሃገራት ድንበር ላይ ሲደርሱ ወደ ስምንት የሚሆኑ መኪኖች ከብበዋቸው፣ መሳሪያ ከደቀኑባቸው በኋላ እነ ሃሩንንም ሆነ ከሱዳን ይዟቸው የሄደውንና ከሊቢያ ሊወስዳቸው የመጣውንም አንድ ላይ ወሰዷቸው። መሳሪያ መታጠቃቸውን እንጂ ምን እንደሆኑና ማን እንደሆኑ የሚያውቀው ነገር እንደሌለ የሚገልፀው ሃሩን ከበርሃ ወጥተው እንደከበቧቸው ያስታውሳል። እነዚህ ታጣቂዎች ያለምንም ምግብና ውሃ ሁለት ቀንና ሌሊት ይዘውን ከሄዱ በኋላ የማይታወቅ በረሃ ውስጥ አወረዱን። ለአንድ ሰው ሺህ ዶላር ካልከፈልን ከዚያ መንቀሳቀስ እንደማንችል ነገሩን። እኛ ብቻ ሳንሆን ከሊቢያ ሊወስደን የመጣው ሰውዬም ያለንበትን ስፍራ አያውቀውም ነበር። ኢትዮጵያ ወይስ ናይጄሪያ የትዊተር አለቃ የፈጠረው ክርክር ከዚህ በኋላ ሺህ ዶላሩን መክፈል የምትችሉ መኪና ላይ እንዲወጡ የማይችሉ ግን እዚያው እንዲቆዩ ተነገራቸው። ኤርትራዊያንና ሱዳኖች እንከፍላለን ብለው መኪና ላይ መውጣታቸውን የሚናገረው ሃሩን፤ ሁሉም ኢትዮጵያዊያኖች ግን ገንዘብ ለመክፈል እንደማይችሉ ተናግረው እዚያወቅ ለመቆየት መወሰናቸውን ያስታውሳል። በኋላም ኤርትራዊያኑንና ሱዳናዊያኑን ይዞ የሄደው መኪና መንገድ ከጀመረ በኋላ ተመልሶ በመምጣት በመሳሪያና በዱላ እያስፈራሩ መኪናው ላይ እንዳሳፈሯቸውና እንደወሰዷቸው ይናገራል። አጭር የምስል መግለጫ ሃሩን አህመድ የተጓዘበት መስመር ጉዞ ወደ ሊቢያ ሦስት ቀን ያለማቋረጥ ከተጓዙ በኋላ አንድ ቦታ መድረሳቸውንወ የሚናገረው ሃሩን፤ ስፍራው ሰዎች እንደ ባሪያ የሚሸጡበት መሆኑን ያስታውሳል። ስፍራው ላይ ከደረሱ አራት ወርና ከዚያ በላይ የሆናቸው፣ ልብሳቸው ላያቸው ላይ የነተበ፣ ሰው የማይመስሉ ከ በላይ ስደተኞች፣ አብዛኛዎቹ ሶማሊያዊያን መሆናቸው ማግኘታቸውን ያስታውሳል። እዚያ እንቆያለን ብለን ስላላሰብን የቀረችንን ስንቅም ውሃም ሰጠናቸው። እነሃሩን እንዳሰቡት ሳይሆን የስደተኛ አቀባባዮቹ እንደፈቀዱት ሆነ። ትልቅ ዋጋ ተከፍሎበት ዋጋ ያላገኘሁበት ቢኖር ትምህርት ነው ይዘዋቸው የመጡ ታጣቂዎች አራት አራት ሺህ ዶላር ካልከፈሉ በስፍራው እንዳቆይዋቸው እና ከሰውነት ጎዳና የወጡ ስደተኞች እንደሚሆኑ በመንገር አስፈራሯቸው። ማስፈራራቱ ከስፍራው ባለመንቀሳቀስ ጸና። ቀና ቢሉ ጠራራ ጸሀይ፣ ዞር ቢሉ ጎስቋላ ስደተኛ፣ ድካም ያዛለው፣ ውሃ ጥም ያቃጠለው የሀገር ልጅ በሚያዩበት ምድረ በዳ መጋዘን ተገኝቶ እዚያ ውስጥ ታሰሩ። አሳሪዎቻቸው እጃቸው የተፈታ ቀን፣ በቀን አንዴ ሆዳቸው የጨከነ እለት ደግሞ፣ በሁለት ቀን አንዴ ምግብ ይሰጧቸዋል። ሌሊት ሌሊት ደግሞ ይደበድቡናል የሚለው ሃሩን በአጠቃላይ ለአራት ወራት በዚያ ስፍራ መታሰራቸውን ይናገራል። አራት ወር ሲሞላቸው ልብሳቸው አልቆ፣ አብረዋቸው ከተሰደዱት ጋር ተረሳስተው፣ የት ለመሄድ እንደሚፈልጉ ዘንግተው እስትንፋሳቸውን ማቆየት ብቻ የህይወት ግባቸው ሆኖ እንደነበር ይናገራል። በዚህ ስፍራ በረሃውንና የደረሰባቸውን ድብደባና ስቃይ መቋቋም ያቃታቸው አንድ ኢትዮጵያዊ ጓደኛችንን ጨምሮ አስራ ሁለት ሶማሌያዊያንን ቀብረናል። በዚህ ሁሉ ስቃይ ውስጥ ይላል ሃሩን የመጡበት ሃገርን፣ ብሔራቸውንና ዘራቸውን ዘንግተው ሰው መሆናቸውን ብቻ ያስታውሱ እንደነበር የሚናገረው ሃሩን በመካከላቸው መደጋገፉና መረዳዳቱ ጠንካራ እንደነበር ይናገራል። የመረዳዳታቸውን ጣሪያ ሲያስታውስ ከመካከላቸው አንድ ሰው በውሃ ጥም ሞቶ ለሌሎች ከንፈራቸውን የሚያረጥቡበት ውሃ እንዲያገኙ ለማድረግ እስከመፍቀድ እንደነበር ይገልጻል። የኩላሊት ገበያ አንድ ቀን ይላል ሃሩን ኩላሊት የሚገዙ ሰዎች ወደ ታሰርንበት መጋዘን መጡ የሚገዛው ግለሰብ ግን የበረሃው ሃሩርና ውሃ ጥም ያከሰላቸውን ስደተኞች ተመልክቶ፣ እነዚህማ ለራሳቸውም ደክመዋል ምንስ ኩላሊት አላቸው በማለት ትቷቸው መሄዱን ይጠቅሳል። ስደተኞቹ ኩላሊታቸው ተሸጦ ዋጋ እንደማያወጡ፣ ቤተሰቦቻቸው ገንዘብ ልከውም እንደማይከፈላቸው የተረዱት ደላሎች ለሌላ ነጋዴ አሳልፈው ሸጧቸው። የገዛቸው ሰው ለእያንዳንዳቸው ሦስት ሺህ ዶላር እንዳወጣና ገንዘቡን እንዲከፈለው እንደሚፈልግ ቀጭን ማሳሰቢያ አዘል ማስፈራሪያ ተናገረ። በበረሃው የተዳከሙ፣ በተስፋ መቁረጥ የሚዋልሉ ስደተኞች ከዚህ ብቻ አውጣን እንጂ እንከፍልሃለን በሚል ተስማምተው አብረውት ሄዱ። ከዚህ ሰውዬ ጋር ቀንና ሌሊት ለአራት ቀን ከተጓዙ በኋላ ሳባ የምትባል የሊቢያ ከተማ ላይ ደረሱ። የሴቶች ዘብ የነበሩት ዶ ር ቦጋለች ገብሬ ይዘዋቸው የሚሄዱት ሰዎች የደረሱበትን የሚያውቁት ካርታ ዘርግተው፣ የፀሐይን አቅጣጫ አይተው ወይንም ነዋሪውን ጠይቀው አይደለም። አሸዋውን ዘገን አድርገው ብቻ የት ሃገር እንደደረሱ ይናገራሉ። ዓይን ማየት የቻለበት ርቀት ሁሉ አሸዋ ለሆነበት ስደተኛ፣ የአንዱ ሀገር አሸዋ ከሌላኛው ሀገር የሚለይበት መልክ አይገለጥለትም። ለሀገሬው ግን አቅጣጫ ጠቋሚ፣ ሀገር አመላካች ነው። እነ ሃሩንን ሳባ የወሰዳቸው ግለሰብ በከተማዋ እንደ ሃገረ ገዢ እንደሚታይ ግን ማወቅ ችለዋል። የተጠየቀውን ገንዘብ የከፈለ ስደተኛ በሳባ ውስጥ እንዳሻው የመውጣት የመግባት ነጻነትን ይጎናጸፋል። እኛ ግን ገንዘብ ስላልነበረን ይላል ሃሩን ትልቅ መጋዘን ውስጥ አስገባን። ገንዘብ የሌላቸውና መጋዘን ውስጥ የታጎሩት እነሃሩን የተፈጠሩበትን ቀን እስኪረግሙ ድረስ ድብደባ ይደርስባቸው ጀመር። ወገባችንን በብረት፣ እጆቻችንን ወደኋላ አስረው እየደበደቡ ውሃ የተሞላ በርሜል ውስጥ በጭንቅላታችን ዘቅዝቀው ይከቱንና ከዚያ አውጥተው ቤተሰቦቻችን ጋር ደውለን ገንዘብ እንድናስልክ ስልክ ይሰጡናል ሲል ያስታውሰዋል። በዚህ ሁኔታ ቤተሰቦቻችን ጋር ደውለን ያላቸውንም ሸጠው ተበድረውም ሆነ ተለቅተው ገንዘብ ይልኩልን ነበር። ቀድሞ ገንዘብ ከቤተሰቡ የሚላክለት ሰው ቀደሞ ከዚያ አሰቃቂ እስር ቤት የሚወጣ ሲሆን ቀሪው ግን እስኪላክለት ድረስ እዚያው ይቆያል። ሃሩን በዚህ ስፍራ አንድ ወር ቆየ። ከእርሱ ቀድመው የወጡ የበረሃ ጓደኞቹ፣ እንዲሁም ቤተሰቡ ያላቸውን ሳንቲም በማዋጣት ሦስት ሺህ ዶላር መክፈሉን ይናገራል። እዚህም በገንዘብም ሆነ በሌሎች ጉዳዮች ሲተጋገዙ፣ ብቸኛው ግምት ውስጥ የሚያስገቡት አብረው የሚያሳልፉትን የሰቆቃ ጊዜያት፣ ሰው መሆናቸውን እንጂ መነሻቸው ላይ የነበረው የአንድ አገር ልጅነት እንዳልነበር ይናገራል። ኢትዮጵያ የጥላቻ ንግግርና የሐሰተኛ መረጃን የተመለከተ አዋጅን ልታጸድቅ ነው መጀመሪያ ላይ በቋንቋ በብሔር በሃይማኖትና በዘር ስንጣላ የነበርን ሰዎች ከዚያ ሁሉ ስቃይ ሁሉ በኋላ የቀረልን ሰው መሆናችን ብቻ ነበር። ሰው መሆን ከሁሉ ነገር በፊት የሚቀድም መሆኑ የገባኝ ያኔ ነበር በማለትም ከእስር ቤቱ ቀድመው የወጡ እንዴት እንደረዷቸው ያስረዳል። ሳባ ከነበረው እስር ቤት ቀድማቸው የወጣች ጽጌ የምትባል ኤርትራዊት ለቤተሰቦቻቸው በመደወል ገንዘብ እንዲላክላቸውና የጎደላቸውን ከሌሎች በማሟላት እንዲወጡ እንዳገዘቻቸው ይመሰክራል። በዚህ መደጋገፍና መረዳዳት መካከል አዲስ አሸናፊ ከምትባል ልጅ ጋር ፍቅር ጀመረ። እርሱ የእስልምና ዕምነት ተከታይ ሲሆን እርሷ ደግሞ ክርስትያን ነበረች። ነገር ግን እዚያ በነበረው እንግልትና ስቃይ ሁለቱ ወጣቶች በፍቅር ተጋመዱ። እስር ቤት ውስጥ በጭካኔና በኃይል የሚደበደቡት ወንዶች ስለነበሩ ለእርሷ የተላከላትን ገንዘብ ለእኔ ከፍላ እኔ እንድወጣ አደረገች በማለት የሁለቱ የፍቅር ታሪክ በራሱ በተቃርኖ ውስጥ ሲጋጩ ለሚኖሩ ሌሎች ትምህርት እንደሚሆን ያነሳል። ትሪፖሊ ሃሮን ፍቅረኛውና ቤተሰቦቹ በማዋጣት በከፈሉት ገንዘብ ሳባ ከሚገኘው እስር ቤት ከወጣ በኋላ ወደ ትሪፖሊ ጎዞ ጀመረ። ነገር ግን በክፉ አጋጣሚ ትሪፖሊ ከመድረሱ በፊት በሌሎች ሰዎች እጅ ወድቆ እስር ቤት ተወረወረ። እነዚህ አሳሪዎቹ በቀን አንዴ ደረቅ ዳቦ እየሰጧቸው፣ ሌሊት ሌሊት ደግሞ ገንዘብ አምጡ እያሉ እደበድቧቸው እንደነበር ይናገራል። ፍቅረኛውን አዲስን ጨምሮ ሌሎች ከሱዳን አብረው የተነሱና ሳባ አብረው ታስረው የነበሩ ስደተኞችም በሂደት ተቀላቀሏቸው። ከ ቀናት እስር በኋላ እንደ ከዚህ ቀደሙ ተረዳድተው ስድስት ስድስት መቶ ዶላር በመክፈል ተለቀቁ። ከዚህ በመቀጠል ያመሩት በቀጥታ ትሪፖሊ ክሪሚያ የምትባል ስደተኞች በብዛት የሚያርፉባት መንደር ነበር። ሶስት ጊዜ ለተለያዩ ነጋዴዎች ተሽጫለሁ ክሪሚያ ወደ አውሮፓ በባህር ለማቋረጥ ወረፋ የሚጠብቁና ከባህር ላይ ተይዘው የተመለሱ ስደተኞች በብዛት ያሉባት መንደር ናት። ሃሩንና አዲስ ያገኙትን እየሰሩ ለእለት ጉርስ ለነገ ደግሞ ስንቅ እያኖሩ ከሌሎች መንገድ ላይ ከተዋወቋቸው ሰዎች ጋር ቤት ተከራይተው ለሰባት ወራት በክሪሚያ ኖሩ። በሰባት ወር ቆይታቸው በመንደሯ በየዕለቱ የሚሰማው ወሬ የባህር ተሻጋሪ ስደተኞች ሞት አልያም በሰላም ወደ አውሮፓ መሻገር ነበር። ይህንን በየማለዳው የሚሰሙት ሃሩንና አዲስ በየሃይማኖታቸው በሰላም የሜዴትራኒያንን ባህር ተሻግረው የሚያልሙት አውሮፓ እንዲደርሱ ይጸልዩ ነበር። በወቅቱ ይላል ሃሩን አንዳችን የሌላኛችንን ሃይማኖት ለማስቀየር ወይም እንደ ክፍተት በመቁጠር ተነጋግረን አናውቅም። ክሪሚያ የከተመ ስደተኛ ሰርቶ ያገኘውን አጠራቅሞ፣ ቤተሰብ የላከለትን ቋጥሮ ሲሞላለት፣ በጀልባ ተሳፍሮ ወደ አውሮፓ ጉዞ ይጀምራል። ያንን ሁሉ በረሃ አቋርጠው፣ ስቃይና እንግልቱን ችለው ክሪሚያ የደረሱ መጥፎ ዕጣ ከገጠማቸው ሜዴትራኒያን ባህር ውስጥ ሰጥመው ይሞታሉ። ሃሮንም በዚህ ሁኔታ ብዙ ሰው ነው ያለቀው በማለት ባህር ውስጥ ሰጥመው የሞቱ በርካታ ጓደኞቻችን አሉ ይላል። መጀመሪያ በባህር ወደ ጣሊያን ከዚያም ወደ ጀርመን ያቀናውና አሁን እዚያ የሚኖረው ሃሩን፤ በሃይማኖት በብሔር ወገን ለይቶ መጠላላትና መጋደል አስፈላጊ እንዳልሆነ በመግለጽ የእርሱ የስደትና የመከራ ሕይወት ይህንን እንዳስተማረው ይገልጻል። ሃሩንና አዲስ በስደት እያሉ አንድ ልጅ የወለዱ ሲሆን ጀርመን ከገቡ በኋላ ሁለቱም በየሃይማኖታቸው ለመቆየት በመወሰናቸው፣ ልጃቸውን በጋራ ለማሳደግ ተስማምተው ለየብቻቸው እየኖሩ ነው። ተያያዥ ርዕሶች
የህንዶቹን አስራ አንድ አንበሶች ምን ገደላቸው
ሴፕቴምበር ማጋሪያ ምረጥ በህንድ የሚገኙ የእንስሳት ጥበቃ ባለሙያዎች እንደገለጹት ባልተለመደ መልኩ በጉጅራት ግዛት ሞተው የተገኙትን የእስያ አንበሶች የሞት ምክንያት እያጣሩ ነው። የእስያ አንበሶች እ አ አ ከ ጀምሮ በመጥፋት ስጋት ላይ ያሉ እንሰሳት ተብለው ነበር። በጉጅራት እንስሳት መጠበቂያ ውስጥ በመቶዎች የሚቆጠሩ የእስያ አንበሶች ይገኛሉ። ነገር ግን ይህን ያክል ቁጥር ያላቸው አንበሶች በተመሳሳይ ሰአት መሞታቸው በእንስሳት መጠበቂያው ውስጥ ያለውን አስቸጋሪ ሁኔታ የሚያሳይ ነው ተብሏል። እስካሁን ድረስ ለአንበሶቹ ሞት ምክንያት የሆነው ነገር ባይታወቅም፤ አንበሶቹ በመጠበቂያ ውስጥ የአደንና የማረፊያ ቦታ ለማግኘት በሚደርጉት ፍልሚያ ሳይሆን እንዳልቀረ ባለሙያዎቹ ገምተዋል። የእንስሳት ጥበቃ ባለሙያው ጂኬ ሲንሃ እንደተናገረው ከሌላ አካባቢ የመጡ ሶስት አንበሶች መጠለያ ውስጥ የነበሩ ሶስት ደቦሎችን የገደሉ ሲሆን፤ የዚህ አይነት ባህሪ በአንበሶች ዘንድ የተለመደ ነው ብሏል። የተቀሩት ስምንት አንበሶች ግን በምን ምክንያት እንደሞቱ የታወቀ ነገር የለም። በህንዷ ጉጅራት ግዛት በሚገኘው የእንስሳት መጠበቂያ ውስጥ የሚኖሩት አንበሶች ከቦታው ጠባብነት የተነሳ የሚበሉትን ምግብም ሆነ መጠለያ ለማግኘት ከፍተኛ ትግል ማድረግ አለባቸው። በእንስሳት መጠበቂያው ከሚኖሩ አንበሶች መካከል በመቶ የሚሆኑት የሚሞቱት በተፈጥሯዊ ምክንያት ሲሆን የተቀሩት በመቶዎች ግን ተፈጥሯዊ ባልሆኑና ምክንያታቸው ባልታወቁ አጋጣሚዎች ይሞታሉ። የዕለት ከዕለት ኑሮን የሚለውጡ ፈጠራዎች የአንበሶች አማካይ የመኖሪያ ዕድሜ ከ እስከ ዓመት ሲሆን፤ ከ ዓመት በኋላ ግን አድኖ የመብላትና የመንቀሳቀስ አቅም ስለማይኖራቸው በአንድ አካባቢ ተወስነው የእርጅና ጊዜያቸውን ያሳልፋሉ። የእንስሳት ጥበቃ ባለሙያው ጂኬ ሲንሃ ሌላ መላ ምት አስቀምጧል። ለቢቢሲ እንደተናገረው ሲዲቪ የተባለ በውሾች የተላለፍ ቫይረስ ሊሆን ይችላል አንበሶቹን የገደላቸው። የእንስሳት መጠበቂያው በቂ ጥበቃ ስለማይደረግለት አንበሶች ወደ ሰዎች መኖሪያ የሚወጡ ሲሆን፤ ውሻዎችም ቢሆን ወደ ጥብቅ ክልሉ ይገባሉ። ተያያዥ ርዕሶች
ስለ ማጋራት ተጨማሪ ያጋሩ
ማጋሪያ ምረጥ ከጥቂት ሳምንታት በፊት የቢቢሲ ጋዜጠኞች በኤርትራ አዘጋጅነት ሲካሄድ የነበረውን ከ ዓመት በታች የሴካፋ ውድድርን እንድንዘግብ ፍቃድ ተሰጥቶን ወደ ኤርትራ እቅንተን ነበር። በኤርትራ በነበርን ቆይታ ያየነውን እና የሰማነውን በሦስት ክፍሎች አሰናድተናል። ሁለተኛውን ክፍል እንደሚከተለው ቀርቧል። የመጀመሪያውን ክፍል ለማንበብ ከታች ያለውን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ። ማስታወሻ፡ በኤርትራ በነበረን ቆይታ የዘገባ ርዕሶቻችን እና እንቅስቃሴዎቻችን የተገደቡ ነበሩ። በጽሁፉ ውስጥ የተጠቀሱት ዓመታት እንደ ጎርጎሪሳውያኑ አቆጣጠር ነው። ብዙ ነገር አንድ የሆነባት ሃገር ኤርትራ በኤርትራ አንድ ብቻ የሆኑ ብዙ ነገሮች አሉ። አንድ አይነት ቢራ፣ አንድ አውሮፕላን፣ አንድ ሥርዓት ያለው የባንክ አገልግሎት፣ እንድ የቴሌኮም አገልግሎት አቅራቢ፣ አንድ የፖለቲካ ፓርቲ፣ አንድ የቴሌቪዝን ጣቢያ አጭር የምስል መግለጫ ሜሎቲ ወይም አሥመራ ቢራ ከእአአ ጀምሮ በኤርትራ ሲጠመቅ ቆይቷል። አንድ ቢራ ሜሎቲ ወይም አሥመራ ቢራ ከ ጀምሮ በኤርትራ ሲጠመቅ ቆይቷል። ይህ ለኤርትራ ብቸኛ የሆነው ቢራ በበርካቶች ዘንድ ትዝታ እና ተወዳጅነትን ያተረፈ ነው። የቢራ ፈላጊውን እና የአቅርቦት መጠኑ ተመጣጣኝ ስላልነበረ ከቅርብ ዓመታት በፊት አንድ ሰው ሁለት ቢራ ብቻ ገዝቶ እንዲጠጣ ነበር የሚፈቀድለት። አሥመራ፡ የአዛውንቶች ከተማ ከሁለት በላይ ደጋግሞ መጠጣት የፈለገ፤ ቢራ የማይጠጣ ሰው ወደ መጠጥ ቤት ይዞ በመሄድ የዚያን ሰው ኮታ ይጠጣ እንደነበር ሰምተናል። አሁን ላይ በቢራ ፋብሪካው በተካሄደ ለውጥ የቢራ አቅርቦቱን በቀላሉ ማግኘት ይቻላል። ከኢትዮጵያ ጋር የሚያዋስኑ የድንበር በሮች በተከፈቱ ጊዜ የኢትዮጵያ ቢራ ምርቶች አሥመራን አጥለቅልቀዋት እንደነበረ በዚህም የአንድ ሜሎቲ ቢራ ዋጋ ከ ናቅፋ ከ እንደወረደ ነዋሪዎች ነግረውናል። አጭር የምስል መግለጫ ናቅፋ አንድ አይነት የባንክ ሥርዓት በኤርትራ የሚገኙት ባንኮች በመንግሥት ባለቤትነት የሚተዳደሩ ናቸው። በቁጥር ሦስት የሆኑት የመንግሥት ባንኮች በአድናቆት አፍ የሚያስከፍት ሕግ አላቸው። ይህም የባንኩ ደንበኞች በባንኩ ካላቸው ገንዘብ በወር ከ ሺህ ናቅፋ በላይ እንዲያወጡ አይፈቅድም። መኪና ለመግዛት ሺህ ናቅፋ በጥሬ ገንዘብ ያስፈለገው ወጣት ይህን ያክል ገንዘብ በጥሬ ለማግኘት ወር እየጠበቀ ናቅፋ ሲያወጣ አንድ ዓመት እንደስቆጠረ ነግሮናል። ቀነኒሳ ከሞት እንደመነሳት ነው ባለው ሁኔታ ማራቶንን አሸነፈ መንግሥት ይህን መሰል ውሳኔ ማስተላለፍ ለምን እንደፈለገ የጠየቅናቸው ነዋሪዎች፤ ሁለት የተለያየ አተያዮች አሏቸው። የመጀመሪያው መንግሥት ከዚህ ውሳኔ የደረሰው የዋጋ ግሽበትን ለመቆጣጠር እና የህዝቡን የቁጠባ ባህል ለማዳበር ነው ሲሉ ሌሎች ደግሞ መንግሥት ምንም አይነት የንግድ እንቅስቃሴ እንዲኖር ስለማይፈልግ የገንዘብ ዝውውር እንዳይኖር አድርጓል ይላሉ። ኤቲኤም ገንዘብ መክፈያ ማሽን በኤርትራ የለም። አሥመራ በነበረን ቆይታ ያገኘነው ወጣት፤ ድንበር ክፍት በተደረገ ጊዜ ወደ መቀሌ አቅንቶ በነበረበት ወቅት ሰዎች ከማሽን ብዙ ገንዘብ ወጪ ሲያደርጉ ማየቱ በእጅጉ እንዳስደነቀው አጫውቶናል። ኤቲኤም በሌለባት ሃገረ ኤርትራ ሌላው ያስተዋልነው፤ በምግብ እና መጠጦች ላይ ተጨማሪ የእሴት ታክስ አለመጣሉ ነው። አጭር የምስል መግለጫ ሲም ካርድ በቀላሉ ማግኘት ስለማይቻል አብዛኛው ህብረተሰብ የህዝብ ስልኮችን ይጠቀማል። ቀኝ አሥመራ ከተማ ልብስ መሸጫ ሱቅ ውስጥ አገልግሎት እየሰጠ የሚገኝ ስልክ። አንድ የቴሌኮም ኩባንያ ልክ እንደ ኢትዮጵያ ሁሉ በኤርትራ ያለው የቴሌኮም አገልግሎት አቅራቢ ድርጅት በመንግሥት ባለቤትነት የሚተዳደር ሲሆን ኤሪቴል ይባላል። በኤርትራ የቴሌኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት ደካማ ነው። ሲም ካርድ ማግኘት እጅግ አዳጋች ነው። ጎብኚዎች ሲም ካርድ ማግኘት አይችሉም። ነዋሪዎችም ቢሆኑ ሲም ካርድ ማውጣት ቢፈልጉ በየደረጃው የሚገኙ የመንግሥት መስሪያ ቤቶች ይሁንታንና ፈቃድን ሲያገኙ ነው የሲም ካርድ ባለቤት የሚሆኑት። ብሎ የሚጀምረው የኤርትራ የሞባይል ስልክ ቁጥር ባለ አሃዝ ብቻ ነው። ለምሳሌ የኤርትራ ሞባይል ቁጥር ይህን ሊመስል ይችላል ። አብዛኛው ማህብረሰብ በፈቀደው ወቅት የሲም ካርድ ባለቤት መሆን ስለማይችል አብዝቶ የሚጠቀመው የመንገድ ላይ የሕዝብ ስልኮችን ነው። የተለያዩ ዋጋ ያላቸውን ካርዶች ከኤሪቴል መደብሮች ብቻ በመግዛት ወደ ሃገር ውስጥ እና ከሃገር ውጪ መደወል ይቻላል። በኢትዮ ኤርትራ ድንበር ንግድ ተጧጡፏል ሲም ካርድ ቢገኝም፤ የሞባይል ዳታ የለም። በስልክዎ ላይ ኢንተርኔት መጠቀም የሚችሉት የዋይፋይ አገልግሎት በሚገኙባቸው ስፍራዎች ብቻ ነው። ዋይፋይ ቢገኝም፤ የኢንተርኔት ፍጥነት እጅግ ቀሰስተኛ ነው። ማህበራዊ ሚዲያዎችን ለመቃኘት ደግሞ ቪፒኤን መጠቀም ግድ ይላል። ዓለም አቀፍ የቴሌኮሚዩኒኬሽን ሕብረት ሪፖርት እንደሚጠቁመው፤ ከኤርትራ ሕዝብ ውስጥ የኢንተርኔት ተጠቃሚው ብዛት ከ በመቶ በታች ነው በማለት አገልግሎቱ ምን ያህል ዝቅተኛ መሆኑን ይጠቁማል። አንድ የቴሌቪዥን ጣቢያ በመንግሥት ባለቤትነት የተያዘው ኤሪ ቲቪ ከኤርትራ ሆኖ በብቸኝነት የሚያሰራጭ የቴሌቪዥን ጣቢያ ነው። በቅርቡ ኤርትራ በዓለማችን ቁጥር አንድ የመገናኛ ብዙሃን አፈና የሚፈጸምባት ሃገር ናት ተብለ ተፈርጃ ነበር። የጋዜጠኞችን እስር፣ ጋዜጠኞችን ለመሰለል የሚፈቅዱ ሕጎችን እንዲሁም በኢንተርኔት እና በማህበራዊ ሚዲያ አገልግሎት ላይ የሚጣለውን ገደብ ከግምት ውስጥ በማስገባት የጋዜጠኞች መብት ተሟጋቹ ሲፒጄ ኤርትራ ከሰሜን ኮሪያ በላይ ቁጥር አንድ አፈና የሚፈጸምባት ሃገር ናት ይላል። ኤርትራ በምሽት ድንበር ማቋረጥን ከለከለች ከኤርትራ በመቀጠል ሰሜን ኮሪያ፣ ቱርኬሚስታን፣ ሳዑዲ አረቢያ፣ ቻይና፣ ቬትናም፣ ኢራን፣ ኢኳቶሪያል ጊኒ፣ ቤላሩስ እና ኩባ ከ ኛ እስከ ኛ ደረጃን ይዘው ተቀምጠዋል። በኤርትራ መገናኛ ብዙሃን የመንግሥት ልሳን ሆነው ነው የሚያገለግሉት የሚለው ሲፒጄ፤ ገለልተኛ የሆኑ ጋዜጠኞች ወደ ሃገራቱ ሲያቀኑም ቅርብ ክትትል ይደረግባቸዋል። አንድ የፖለቲካ ፓርቲ ሃገሪቷን የሚያስተዳድረው እና በፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የሚመራው የሕዝባዊ ግንባር ለዴሞክራሲና ፍትህ ፓርቲ ሕግዴፍ በሃገሪቱ የሚንቀሳቀሰው ብቸኛው የፖለቲካ ፓርቲ ነው። ሦስት አስርት ዓመታትን ሊደፍን የተቃረበው የፕሬዝዳንት ኢሳያስ አስተዳደር ዘመን በኤርትራ የሚንቀሳቀስ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ ታይቶ አታውቅም። ይህ ብቻም አይደለም ሥራ ላይ ውሎ የሚያውቅ ሕገ መንግሥት የለም። ምርጫ ተካሂዶ አያውቅም። ወደፊትም ስልጣን ላይ የሚገኘው መንግሥት ምርጫ የማካሄድ ሃሳብ የለውም ሲሉ ተቺዎች ይናገራሉ። የኃይማኖት ነጻነት በኤርትራ ፍቃድ ያላቸው እና መንግሥት እውቅና የሰጣቸው ኃይማኖቶች አራት ብቻ ናቸው። የኦርቶዶክስ ክርስትና፣ የሱኒ እስልምና፣ የሮማ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን እና የሉተራን ወንጌላዊ ቤተ ክርስቲያን ናቸው። ኤርትራ ፖለቲከኞችን እና ጋዜጠኞችን እንድትለቅ ተጠየቀ ሌሎች የእምነት ተቋማት እንደ ሕገ ወጥ ነው የሚቆጠሩት። መንግሥት የተቀሩትን የእምነት ተቋማትን የውጪ ሃገራት አጀንዳ ማስፈጸሚያ መሳሪያዎች ናቸው ሲል ይገልጻቸዋል። የአሜሪካ መንግሥት ዓለም አቀፍ የኃይማኖት ነጻነት ኮሚሽን የ ሪፖርት እንደሚጠቁመው ከሆነ፤ ዛሬ ላይ በመቶዎች የሚቆጠሩ ኤርትራዊያን በእምነታቸው ምክንያት ለእስር እንደተዳረጉ ናቸው። የጆሆቫ ምስክሮች በእምነት ተከታዮች በኃይማኖታቸው ምክንያት በብሔራዊ አገልግሎት ላይ ለመሳተፍ ፍቃደኛ ባለመሆናቸው ዜግነት ይከለከላሉ፣ መታወቂያ ደብተር ማግኘት አይችሉም። የድንበር በሮች መከፈት ሁለቱን ሃገራት የሚያገናኙ አራት የድንበር በሮች ይገኛሉ። አራቱ የድንበር በሮች ዛላምበሳ ሰርሃ፣ ራማ ክሳድ ዒቃ፣ ሁመራ ኦማሃጀር እና ቡሬ ደባይ ሲማ ናቸው። በሁለቱ ሃገራት የሰላም ስምምነት ከተደረሰ በኋላ በተለያዩ ጊዜያት ክፍት ተደርገው የነበሩት አራቱ የድንበር በሮች አሁን ላይ ሁሉም ተዘግተዋል። ለድንበር በሮቹ መዘጋት በሁለቱም መንግሥታት የተሰጠ ምክንያት ባይኖርም ይፋዊ ያልሆኑ መረጃዎች የድንበር በሮቹ የተዘጉት፤ የቪዛ እና የቀረጥ ጉዳዮችን መልክ ማስያዝ በማስፈለጉ እንደሆነ ይጠቁማሉ። ዛላምበሳ ሰርሃ፣ ራማ ክሳድ ዒቃ እና ለሱዳን ቅርብ የሆነው ሁመራ ኦማሃጀር በትግራይ ክልል በኩል ኢትዮጵያን ከኤርትራ ጋር የሚያገናኙ የድንበር በሮች ሲሆኑ፣ ቡሬ ደባይ ሲማ ደግሞ በአፋር ክልል በኩል ኢትዮጵያን ከኤርትራ የሚገናኝ የደንበር በር ነው። የድንበር በሮቹ ክፍት ተደርገው በነበረበት ወቅት ከፍተኛ የሆነ የንግድ እንቅስቃሴ ድንበር እቅራቢያ ተስተውሎ ነበር። በአሥመራም የድንበር በሩ መከፈት በተለያዩ ሸቀጦች ላይ የዋጋ ለውጥ አምጥቶ እንደነበር በቆይታችን ሰምተናል። ለምሳሌ ድንበር ከመከፈቱ በፊት እስከ ሺህ ናቅፋ ይሸጥ የነበረው አንድ ኩንታል ጤፍ ድንበሩ ሲከፈት ዋጋው በሚያስደንቅ ሁኔታ አሽቆልቁሎ እንደነበር ነዋሪዎች ይናገራሉ። በአሁኑ ወቅት በድንበር በሮቹ ላይ የተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ በመገደቡ የአንድ ኩንታል ጤፍ አሥመራ ውስጥ የተጋነነ ባይሆንም ጭማሪ አሳይቷል። ተያያዥ ርዕሶች
የኢትዮጵያዊው ጉዞ፡ ከኬኒያ የስደተኞች ካምፕ እስከ ሜልቦርን ዩኒቨርሲቲ
ጥር ኤልሻዳይ ጌትነት ኤልሻዳይ እና ቤተሰቦቹ ኤልሻዳይ ጌትነት ይባላል፤ በሜልቦርን ዩኒቨርሲቲ የጥርስ ቀዶ ጥገና የዶክትሬት ተማሪ ነው። ኤልሻዳይ ከስደተኞች ካምፕ ተነስቶ እስከ ካናዳ ያደረገውን ጉዞ አካፍሎናል። አባቱ በደርግ ዘመን የነበረውን ወታደራዊ ግዴታ ካጠናቀቁ በኋላ ከእናቱ ጋር በመሆን ከኢትዮጵያ ለቀው ለመውጣት ተስማሙ። አገራቸውን ለቀው ወደ ኬንያ ለመሰደድ ሲያቅዱ ሁለቱም በአሥራዎቹ እድሜ ክልል ውስጥ ነበር የሚገኙት። እንደውም እናቴ እንደነገረችኝ ለሴት አያቴ ቡና ከምታፈላበት ድንገት ተነስታ መጣሁ ብላ እንደወጣች ነው ኬንያ የገባችው። ከዛም ከአባቴ ጋር ተያይዘው ጉዞ ወደ ኬንያ ጀመሩ። በእግር እና በመኪና የተደረገው ጉዟቸው እጅግ አስቸጋሪና ፈታኝ ነበር። ጫካዎችን በሚያቋርጡበት ወቅት አንዳንዶቹ ስደተኞች በአንበሳ እንደተበሉም ወላጆቹ የነገሩትን ኤልሻዳይ ያስታውሳል። መጻሕፍትን ማንበብና መጻፍ ለአዕምሮ ጤና ቤተሰቦቹ ከአዲስ አበባ ተነስተው የኬንያ ድንበር ለመድረስ ቀናት የፈጀባቸው ሲሆን፤ በመጀመሪያ መርሰቢት የሚባለው የስደተኞች ማቆያ ውስጥ ነበር የገቡት። የደርግ ሥርዓት መውደቅን ተከትሎ ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ቢነገራቸውም አንዴ ወጥተናል አንመለስም ብለው ሌላ አማራጭ መፈለግ ያዙ። አንድ ከብቶቹን ወደ ኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ የሚወስድ ገበሬ አግኝተው፣ እነሱንም ይዟቸው እንዲሄድና በምላሹ ገንዘብ ሊከፍሉት ተስማሙ። በመጨረሻም ከከብቶች ጋር መኪና ውስጥ ተጭነው በድብቅ ናይሮቢ ገቡ። ናይሮቢ ከደረሱ በኋላም በኬንያና ሶማሊያ ድንበር ላይ ወደሚገኝ ዳዳብ ወደተባለ የስደተኞች ማቆያ ተዘዋወሩ። ከአንድ ዓመት በኋላ ኤልሻዳይ በስደተኞች ካምፕ ውስጥ ተወለደ። ኤልሻዳይ እና አባቱ አቶ ጌትነት እናቴ ኤልሻዳይ የሚለውን ስም የሰጠችኝ በምክንያት ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ኤልሻዳይ ማለት ሁሉን ቻይ ማለት ነው። እኔ የተወለድኩት በስደተኞች ማቆያ ውስጥ ሲሆን፤ እዛ የተወለዱ ብዙ ህጻናት በወባና በምግብ እጥረት ምክንያት ሕይወታቸው ያልፍ ነበር። እናቴ በምንም አይነት ተስፋ አስቆራጭ ሁኔታ ውስጥ ብትሆን ፈጣሪ እንደሚጠብቀኝ ተስፋ ታደርግ ነበር። ለዚህም ነው ይህንን ስም የሰጠችኝ። ምንም እንኳን በዛ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ልጆችን ማሳደግ ከባድ ቢሆንም፤ በአካባቢው የነበሩ ሌሎች ስደተኞችም ጭምር ተባብረው ልጆችን ያሳድጉ እንደነበር ኤልሻዳይ ያስታውሳል። እኛ የነበርንበት የስደተኞች ማቆያ በብዛት ሶማሌዎች የሚገኙበት ነበር። የባህል እንዲሁም የሃይማኖት ልዩነት ቢኖርም ያለምንም ችግር ነበር ያደግኩት። ሁሉም ሰው ይንከባከበኝ ነበር። አፉን በአማርኛ የፈታው ኤልሻዳይ፤ አራት ዓመት ሲሞላው ሶማልኛ እና ስዋሂሊ በተጨማሪነት አቀላጥፎ መናገር ይችል ነበር። በነበረው አስቸጋሪ የኑሮ ሁኔታ ምክንያት እናቴ የራሷን ልብሶች እየቀደደች ለኔ ልብስ ትሰፋልኝ ነበር። አባቴም ቢሆን በዛ በረሃ ውስጥ ጫማ እንኳ ሳያደርግ የጉልበት ሥራ እየሠራ ለእኔ ጫማ ይገዛልኝ ነበር። በወር የሚሰጠን ቀለብም እጅጉን ትንሽ ነበር። ለአንድ ቤተሰብ በወር ኪሎ ምግብ ብቻ ነበር የሚሰጠው። ነገር ግን ስደተኞቹ ተሰባስበው ህጻናቱ እንዳንራብ ይጥሩ ነበር ሲል ያስታውሳል። የካምፑ ነዋሪዎች ከፍተኛ የምግብ እጥረት ቢገጥማቸውም፤ ሁሌም ቢሆን አዋቂዎች በቅድሚያ ለህጻናት ምግብ ይሰጡ ነበር ይላል ኤልሻዳይ። ሌላው ቀርቶ የወለዱ እናቶች የሌላ ሰው ልጆችን ጭምር ያጠቡ ነበር። በስደተኞች ማቆያው ውስጥ መኖሪያ ቤት ማግኝት ከባድ እንደነበርም ያስታውሳል። እኔና ቤተሰቦቼ የምንኖረው በትንሽዬ ጎጆ ውስጥ ነበር። አባቴ ወታደር ስለነበር ጠንካራ እንድሆንና በቀላሉ እጅ እንዳልሰጥ አድርጎ አሳድጎኛል ይላል። የኤልሻዳይ አባት የኢትዮጵያን ጀግኖች ታሪክ ይተርኩለት እንደነበርም ይናገራል። ሁሌም ቢሆን ስለ ኢትዮጵያውያን ጀግኖች ታሪክ ይነግረኝ ነበር። ስለ አፄ ቴዎድሮስ፣ ጉንደት ላይ የግብፅን ጦር ስላሸነፈው አፄ ዮሃንስ፣ ሙሉ ኢትዮጵያን አንድ አድርጎ ቅን ገዢ ጣልያኖችን ከኢትዮጵያ ስላባረረው አፄ ምኒሊክ እንዲሁም በዲፕሎማሲ ሥራቸው ስለሚታወቁት አፄ ኃይለሥላሴ ታሪክ እየሰማሁ ነው ያደግኩት። በተጨማሪም እንደ ባልቻ ሳፎ፣ ራሥ ጎበና፣ ንግሥት ጣይቱና ሌሎችም ጀግኖች ሕይወትና አኗኗር መስማት በልጅነቴ ትልቅ ቦታ ነበራቸው። የስደተኞች ካምፕ ውስጥ ብዙ ህጻናት ስላልነበሩ ከሌሎች ህጻናት ጋር ተቀላቅሎ የማደግ እድልን አላገኘም ነበር ኤልሻዳይ። የኤልሻዳይና የወላጆቹ የህይወት ጉዞ ጉዞ ወደ ካናዳ በስደተኞች ካምፕ ውስጥ ለአምስት ዓመታት ከቆየን በኋላ ወደ ካናዳ የምንሄድበት እድል ተፈጠረ። ሕይወታችንም ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ተቀየረ። በመጀመሪያ በኖቫ ስኮሺያ ግዛት ሃሊፋክስ ከተማ ለአንድ ዓመት ቆየን። በመቀጠል ደግሞ ካልጋሪ ወደምትባል ከተማ ተዘዋውረን አዲስ ሕይወት መሰረትን። ልክ እንደማንኛውም ስደተኛ ከፍተኛ የሆነ የባህል መጣረስ ቢያጋጥመንም ቀስ በቀስ በራስ መተማመናችን እየጨመረና እየተላመድነው መጣን። የጄኔራል ደምሴ ቡልቶ ልጅ መራር ትዝታ ኤልሻዳይ የትምህርት ውጤቱ በጣም ጥሩ ስለነበር የካልጋሪ ዩኒቨርሲቲ በሳይንስ ዲግሪ ፕሮግራም ተቀበለው። በሰዓቱ ምን አይነት ዘርፍ ላይ መሰማራት እንደሚፈልግ እርግጠኛ ባይሆንም በጤናው አካባቢ ግን ፍላጎት እንዳለው ያውቅ ነበር። ከዩኒቨርሲቲው የመጀመሪያ ዓመት ቆይታው በአንዱ ቀን፤ ወደተለያዩ አገራት በመጓዝ ነጻ የጥርስ ህክምና ይሰጥ የነበረ ዶክተር ራልፍ ዱቤኒስኪ የሚባል ግለሰብ ከዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ጋር በመሆን ወደ ኢትዮጵያና ሩዋንዳ እንደሚጓዝ ነግሮት አብሮት እንዲሄድ ጥያቄ አቀረበለት። ኤልሻዳይ አይኑን ሳያሽ ነበር ሃሳቡን የተቀበለው። እ አ አ በ ከዶክተር ራፍ ጋር በመሆን ወደ ኢትዮጵያ በመጓዝ አገሬን በአይኔ ለመመልከት በቃሁ። አዲስ አበባንና ቤተሰቦቼ ያደጉበት ልደታ ሰፈርንም ለማየት እድሉን አገኘሁ። ምንም እንኳን ኢትዮጵያ ስሄድ የመጀመሪያዬ ቢሆንም ልክ ስደርስ ቤቴ የተመለስኩ አይነት ስሜት ነበር ተሰማኝ ሲል ወቅቱን ያስታውሳል። ዶክተር ራልፍና ኤልሻዳይ ከወሊሶ ወጣ ብላ ወደምትገኝ ሃርቡ ጩሉሌ ወደምትባል ትንሽ መንደር ተጉዘውም ነበር። በነበራቸው ቆይታ ወላጅ አልባ ለሆኑ ህጻናት ቤት ሲገነቡ፣ የጥርስ ህመም ለነበረባቸው ሰዎች ህክምና ሲሰጡና ቀላል ቀዶ ጥገና ሲያደርጉ እንደቆዩ ይናገራል። እሱ የህክምና ሥራዎቹን ሲሠራ አብሬው እየሄድኩ አግዘው ስለነበር የአካባቢው ልጆች እኔም የህክምና ባለሙያ መስያቸው ዶክተር እያሉ ይጠሩኝ ነበር። በዚህ ሁኔታ በጣም ነበር የተገረምኩት። የአገራቸው ሰው ህክምና ላይ ተሰማርቶ በመመልከታቸው በጣም ተደስተው ህጻናት ሲያደንቁኝ ማየት ተጨማሪ መነሳሳትና ጉጉትን ፈጥሮብኝ ነበር። ጉዞዬን ጨርሼ ወደ ካናዳ ስመለስ በአገሬ ባህልና ታሪክ በእጅጉ ተነክቼና አዲስ ሰው ሆኜ ነበር የተመለስኩት። የቀደሙት አባቶቼ እንደ ላሊበላ አብያተ ክርስቲያናት፣ የጎንደሩ ቤተ መንግሥትና አክሱም ሀውልት ያሉ ቅርሶችን በራሳቸው መገንባት ከቻሉ፤ እኔም ምንም አያቅተኝም የሚል ስሜት አደረብኝ። ኤልሻዳይ ጌትነት ኤልሻዳይ በካልጋሪ ዩኒቨርሲቲ በነበረው ቆይታ ከትምህርቱ ጎን ለጎን ሁለት ወይም ሦስት ተጨማሪ ሥራዎች ይሠራ ነበር። ቀላል አልነበረም ግን መድረስ የምፈልግበትን ቦታ አውቅ ስለነበር ያለምንም ችግር ተወጥቼዋለው ይላል። የመጨረሻው ዓመት ላይ በጥርስ ቀዶ ህክምና በእጅጉ በሚታወቀው የአውስትራሊያው ሜልቦርን ዩኒቨርሲቲ ለተጨማሪ ትምህርት አመለክቶ ነበር። እ አ አ በ መጨረሻ አካባቢ ደግሞ ከሜልቦርን ዩኒቨርሲቲ ሙሉ በሙሉ እንደተቀበሉት የሚገልጽ ኢሜይል ደረሰው። እውነቱን ለመናገር በሕይወቴ እጅግ በጣም አስደሳቹ ቀን ነበር ማለት እችላለሁ። አስታውሳለሁ መልዕክቱ ሲደርሰኝ ማልቀስ ጀመርኩ፤ ቤተሰቦቼም ምን ሆነ ብለው ተደናግጠው ነበር። ምናልባት የቤተሰብ አባል ወይም ከጓደኞቼ መካከል አንዳቸው መጥፎ ነገር ያገጠማቸው ነበር የመሰላቸው። ልክ የኢሜይል መልእክቱን ሳሳያቸው እናቴ እግዚአብሔር ይመስገን ብላ መሬት ላይ ወደቀች። በተደጋጋሚ እግዚአብሔር ይመስገን ትል ነበር። አባቴ ደግሞ በቆመበት ከአይኖቹ እንባ እየወረደ እንደነበር አስታውሳለው። ሦስታችንም ተቃቅፈን ቆየን። ለቤተሰቦቼ በጣም ትልቅ አጋጣሚ ነበር፤ ምንያቱም ከስደተኞች ካምፕ እስከ ካናዳ ያደረጉትን የመከራ ጉዞ የሚያስረሳ ስለሆነ ነው። ልፋታቸው ሁሉ መና ባለመቅረቱ እነሱም እኔም በጣም ደስተኞች ነን። በአሁኑ ወቅት በሜልቦርን ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያ ዓመት ትምህርቱን ሊያጠናቅቅ እንደተቃረበ የሚናገረው ኤልሻዳይ፤ በእያንዳንዱ ቀን ከባድና አስቸጋሪ ፈተናዎችን ማለፍ ግድ እንደሆነ ያስረዳል ሆኖም ግን ከአቅሜ በላይ የሚሆን ነገር የለውም። ማንኛውንም አይነት ፈተና ለማለፍ ዝግጁ ነኝ ይላል። በትምህርት ክፍሉ ብቸኛው ኢትዮጵያዊ መሆኔ ደግሞ አገሬን በአግባቡ እንድወክልና ጠንክሬ እንድሠራ አድርጎኛል። ኤልሻዳይ አንዳንዴ ለትምህርት ወደ ክፍል ሲገባ ጋቢ ይለብሳል። የክፍል ጓደኞቹና አስተማሪዎቹም በጣም እንደወደዱትና ሁሉም ጋቢ እንፈልጋለን እንዳሉትም ይናገራል። ክሊኒክ ውስጥ ሲሆን ደግሞ ገዋኑ ላይ አረንጓዴ፣ ቢጫ፣ ቀይ የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ያደርዳል።
ኡጋንዳዊቷ ፕሮፌሰር ፍርድ ቤቱ የወሰነባትን እስር በመቃወም እርቃኗን ወጣች
ኦገስት ማጋሪያ ምረጥ ኡጋንዳዊቷ ምሁር ፕሮፌሰር ስቴላ ንያንዚ የአገሪቷን ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቪኒን አፀያፊ ቃል በመሰንዘር አዋርደሻል በሚል የአስራ ስምንት ወራት እስር ተፈረዳባት። የኢንተርኔት ትንኮሳ በሚል ወንጀል ፍርድ ቤቱ እስር መወሰኑን ተከትሎ ፍርዱን የኡጋንዳ ሐሳብብ በነፃነት የመግለፅ መብትን የሸረሸረ በሚል የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች እየተቹት ነው። አርብ እለት የተካሄደውን የፍርድ ሂደት በቪዲዮ የታደመችው ፕሮፌሰር ስቴላ ውሳኔውን ስትሰማ ጡቶቿን በማውጣት ተቃውሞዋን ገልፃለች። አፀያፊ ኮሚዩኒኬሽን በሚልም ክስ ቀርቦባት የነበረ ሲሆን እሱ ግን ውድቅ የተደረገው ከዚህ ውሳኔ በአንድ ቀን ቀደም ብሎ ሐሙስ እለት። ይህ ውሳኔ ከተሰማ በኋላ በስሜት የተሞላ ንግግር ያደረገችው ፕሮፌሰሯ በውሳኔው ማዘኗን ስትገልፅ ደጋፊዎቿም ድጋፋቸውን ገልፀዋል። ሙሴቪኒን የማበሳጨት እቅድ አለኝ፤ አምባገንነቱ አድክሞናል፣ በቃን ብላለች። የመናገር ነፃነትን በተመለከተ ኡጋንዳ ብዙም የማያወላዳ አካሄድ እንዳላት ሪፖርተርስ ዊዝ አውት ቦርደርስ የገለፀ ሲሆን ሙሴቪኒንም ምንም አይነት ትችትን አይቀበሉም ብሏቸዋል። በዚህ አመት መጀመሪያ ህገወጥ የመንግሥት መድኃኒት ሽያጭ ላይ የምርመራ ጋዜጠኝነት እየሰሩ የነበሩ የቢቢሲ ጋዜጠኞችም መታሰራቸው የሚታወስ ነው። የ አመቷ ስቴላ በምርምሩ ዘርፍ የላቀች ስትሆን በምስራቅ አፍሪካ ውስጥ አንቱታን ከተቸራቸው ዩኒቨርስቲዎች አንዱ በሆነው ማኬሬሬ ዩኒቨርስቲም ታስተምር ነበር። ፌስቡክ ላይ በፀረ መንግሥት ፅሁፎቿ የምትታወቀው ፕሮፌሰሯ፤ ፅሁፎቿም የግጥምን መልክ የያዙ ሲሆን በስድብ የተሞሉ ናቸው የሚሉም አስተያቶች ይሰማሉ። በዚህ ፍርድ ቤት እንደ ተጠርጣሪና እስረኛ መቅረቤ የሰፈረውን አምባገነንነት ማሳያ ነው። ስርአቱ ምንያህል አምባገነን እንደሆነ አጋልጫለሁ በማለት ከፍርድ ውሳኔው በኋላ ፌስቡክ ገጿ ላይ የፃፈች ሲሆን አክላም አምባገነኖችን ለማስወገድ በሚደረገው ትግል ታዛቢ ብቻ መሆን አልፈልግም ብላለች። በኢንተርኔት ትንኮሳ የሚለው ክስ የቀረበባት ባለፈው አመት ፌስቡክ ገጿ ላይ የ አመቱን አዛውንት ፕሬዚዳንት ከእናቱ ማህፀን ሲወጣ ምነው በፈሳሹ ተቃጥሎ ቢሆን የሚል ነገር መፃፏን ተከትሎ ነው። ኢንጅነር አይሻ መሃመድ የሃገር መከላከያ ሚኒስትር ሆነው ተሾሙ አምነስቲን ጨምሮ ብዙ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች የፍርዱ ውሳኔ ተቀልብሶ ለሰባት ወራት እስር የቆየችው ስቴላ ነፃ እንድትወጣ ጠይቀዋል። የፍርድ ቤቱ ውሳኔ በፍፁም ተቀባይነት የሌለው ነው። የኡጋንዳ መንግሥት ሐሳብን በነፃነት የመግለፅ የማስከበር ግዴታውን አልተወጣም፤ ይህም የሚያሳየው ምንያህል መንግሥት ለትችቶች ቦታ እንደሌለው ነው በማለት የምስራቅ አፍሪካ ዳይሬክተር ጆአን ንያንዩኪ ገልፀዋል። ከዚህ ቀደምም ፕሬዚዳንቱን ጥንድ ቂጥ በማለት በፌስቡክ ገጿ ላይ ፅፋ ለእስር ተዳርጋ የነበረ ሲሆን የፍርድ ሂደቱም እስካሁን አላለቀም። ተያያዥ ርዕሶች
የእየሱስ ትክክለኛ ገፅታ በታሪክ አጥኚዎች አይን
ኤፕረል ከብዙ ክፍለ ዘመናት በኋላም በጥበብም ሆነ በእምነት አውሮፓን ማዕከል ያደረገው ምልከታ እየሱስ ላይ ያለንን ምስል ቀርፆታል። ይህም ቆዳው ነጭ፣ ፂም ያለው፣ ቡናማ ረዥም ፀጉርና ሰማያዊ አይን ያለው ነው። በዓለም ላይ በሚገኙ ቢሊዮን ክርስቲያኖችም ይህ ምስል የሚታወቅ ሲሆን ከእውነታው ጋር የሚገናኝ አይደለም። በዘርፉ ላይ ያሉ የታሪክ ምሁራን እንደሚሉት እየሱስ ጥቁር፣ ፀጉሩ አጠር ያለና በዚያን ጊዜ የነበሩ ይሁዳውያንንም ሊመስል እንደሚችል ነው። የእየሱስ መልክ ምን እንደሚመስል የኢየሱስን የህይወት ታሪክ በሚተርከው አዲስ ወንጌል ምን እንደሚመስል አለመጠቀሱ ሰዎች ብዙ መላምቶችን እንዲሰጡ አድርጓቸዋል። መፅሀፍ ቅዱስ ኢየሱስ መልኩም ይሁን በአጠቃላይ የውጭ አካሉ ምን እንደሚመስል ፍንጭ አይሰጥም። ረዥም ይሁን አጭር፤ ውብ ይሁን ጠንካራ ምንም አይልም። ተቀራራቢ እድሜ የሚሰጥ ሲሆን ይህም ዓመት ነው በማለት ኢየሱስ ምን ይመስል ነበር የሚለው መፅሀፍ ደራሲና በለንደን በሚገኘው ኪንግስ ኮሌጅ የስነ መለኮትና የሀይማኖት ጥናት ኒውዚላንዳውው የታሪክ ምሁር ፕሮፌሰር ጆአን ቴይለር ይናገራሉ። የመረጃ እጥረት በጣም ጎልቶ ይታያል። የእየሱስ ተከታይ የነበሩት የመጀመሪያዎቹ ሰዎች ስለዚህ መረጃ የተጨነቁ አይመስሉም። ለነሱ ከውጫዊ አካሉ በላይ በመልዕክቶቹ ላይ አትኩሮት ሰጥተዋል። የሚሉት ደግሞ የታሪክ ምሁሩ፣ በብራዚል በሚገኝ ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰርና ታሪካዊው ኢየሱስ፡ አጭር መግቢያ ደራሲ አንድሬ ሊዮናርድ ናቸው። የአንደኛው ክፍለ ዘመን የራስ ቅል አፅም በአውሮፓውያኑ ቢቢሲ ያዘጋጀው ጥናታዊ ፊልም ላይ እንደተዘገበው ሪቻርድ ኒቭ የተባለ ሳይንቲስት ሳይንሳዊ እውቀቱን ተጠቅሞ የእየሱስ መልክ ምን እንደሚመስል ለማወቅ ሞክሮ ነበር። በዚህም መሰረት በሶስተኛው ክፍለ ዘመን የጥንት አይሁዳውያን የራስ ቅሎች አፅምን ሞዴል በመጠቀም ኢየሱስ የሚመስለውን ቅርፅ ሰርተዋል። የይሁዳውያን አፅመ ቅሬት እንደሚያሳየው የአማካኝ ቁመታቸው ሜትር እንዲሁም አብዛኛው ወንዶች ከአምሳ ኪሎ በትንሽ በለጥ እንደሚሉ ነው። ቴይለርም የእየሱስን ውጫዊ አካላዊ አቋም በተመለከተ ተመሳሳይ መደምደሚያ ላይ ደርሷል። በዚያን ወቅት የነበሩ ይሁዳውያን አሁን ካሉት ኢራቃውያን ጋር ይመሳሰላሉ። ሳስበው እየሱስ ጠቆር ያለ ወይም ቡናማ ቀለም ፀጉር ነበረው፤ ቡናማ አይኖችና ጠየም ያለ ቆዳ ያለው እንደ መካከለኛ ምስራቃዊ ሰው ይመስለኛል ይላሉ። ጠየም ያለና ረዥም ፀጉር ብራዚላዊው የግራፊክ ዲዛይነር ባለሙያ ሲሴሮ ሞራኤስ የእየሱስን ፊት ሳይንሳዊ በሆነ መልኩ ምን ሊመስል እንደሚችል ቀርፆት ነበር። ሞራኤስ እንደሚለው እየሱስ በርግጠኛነት ጥቁር ነበር። በተለይም በቀጠናው የነበረውን መልክ በማየት፤ እንዲሁም በበረሀና ሀሩር ፀሀይ ባለበት የሚኖሩ ወንዶችን በማጥናት ነው እዚህ መደምደሚያ ላይ የደረስኩት ይላሉ። ሌላኛው ጥያቄ የእየሱስ ፀጉር ነው። የመፅሀፍ ቅዱስም አንዱ ክፍል በሆነው በጳውሎስ ወደ ቆሮንቶስ መልዕክት ወንድ ልጅ ረዥም ፀጉር ሊኖረው ነውር ነው ስለሚል ብዙ ጊዜ እንደሚሳለው እየሱስ ረዥም ፀጉር ሊኖረው አይችልም። በሮማውያን ዘንድ ለወንድ ተቀባይነት ያለው የተላጨ ፂምና አጭር ፀጉር ነበር። ምናልባት በጥንት ጊዜ ፈላስፋዎች ፂማቸውን ያስረዝሙ ነበር በማለት የታሪክ ምሁሩ ይናገራሉ። ፕሮፌሰር ሊዮናርዶ ቼቪታሪዝ ታሪካዊው እየሱስ፡ አጭር መግቢያ የሚለው መፅሀፍ ደራሲ ሲሆኑ ሶስተኛው ክፍለ ዘመን ላይ የነበረው የእየሱስ ምስል ወጣትና አጭር ፀጉር የነበረው ነው ይላሉ። ከፂማም አምላክ ይልቅ ወጣት ፈላስፋና መምምህር ነበር የሚመስለው በማለት ይገልፃሉ። ዊልማ ስቴጋል የተባሉ በብራዚል በሚገኝ ዩኒቨርሲቲ የስነ መለኮት ተመራራማሪ ክርስትና ጅማሮ ላይ የተለያየ ገፅታ እንደነበረው ከነዚህም ውስጥ በጊዜው እንደነበሩ ፈላስፋና መምህራን ፂም፤ ፂም የሌለው እንዲሁም ከጭንቅላቱ ጀርባ የፀሀይ አምላክ እንደሆነ ተደርጎ ይሳል ነበር። መለኮታዊ ገፅታ ቴይለር በበኩላቸው እነዚህ ምስሎች ለዘመናት እየሱስን መለኮታዊ ገፅታ እንዳለው፣ የአምላክ ልጅ አድርገው ሲሆን የሰው ልጅ የሆነውን እየሱስን አይስሉትም ነበር። ይህ ሁሌም የሚያስደንቀኝ ነገር ነው። እየሱስን ባየው ደስ ይለኝ ነበር በማለት ይናገራሉ። ፂም የተሞላበት ፊት ያለው የእየሱስ ምስል በመካካለኛው ክፍለ ዘመን በተለይም በባይዛንታይን ኢምፓየር ከፍተኛ ዕውቅናን አግኝቷል። ፕሮፌሰር ቼቪታይዝ እንደሚሉት የእየሱስ ምስል የሚሳለው እንደ ዘመኑ ከነበሩት ነገስታት አካላዊ ገፅታ ሉዓላዊነትን በተጎናፀፈ መልኩ ነበር። የማህበረሰብ አጥኚው ፍራንቼስኮ ቦርባ ሪቤይሮ ኔቶ በሳኦ ፖሎ በሚገኘው የካቶሊክ ዩኒቨርሲቲ አስተባባሪ ሲሆኑ እሳቸው እንደሚሉትም በታሪክ ውስጥ የእየሱስ ገፅታ በክርስትና መጀመሪያ ወቅት ፍልስጥኤማውያንን መምሰሉ ለብዙዎች አሳሳቢ ጉዳይ አልነበረም ይላሉ። በምስራቃዊ ካቶሊክ ቤተክርስቲያኖች ዘንድ የእየሱስ ገፅታን ለመሳል ጥብቅ የሆነ ህግም በማውጣት፤ ከአለማዊው ውጭም መንፈሳዊ የሆኑ ጥበቦችንም ሊያሳይ ይገባል ተብሎ እንደሚታመን ይናገራሉ። ከተለያዩ ሰዎች ጋር በሚሳልበት ወቅት ከሁሉም ተለቅ ብሎ እንዲታይና ሲሆን ይህም ያለውን ታላቅነት ምሳሌ ነው። ከዚህም በተጨማሪ በመስቀል ላይ ተሰቅሎም በህይወት እንዳለና ከአጠቃላይ ፀጋው ጋር ነው የሚሳለው ይላሉ። የምዕራቡ ዓለም ቤተክርስቲያን እነዚህን ህግጋትንም ሆነ ባህል ስለማይከተሉ በዘመናትም ውስጥ የእየሱስን ምስል በዘፈቀደና እንደፈለጉት አድርገው ይስሉ ነበር ይላሉ። በእምነቶች ላይ ያሉ ታሪካዊ ሰዎች የባህል የበላይነት ያለበት አካል ነፀብራቅ እየሆኑ እንደመጡ ይናገራሉ። የእየሱስ ክርስቶስ ምስል ሰማያዊ አይን መሆንና ብሎንድ ፀጉር ያለው መሆኑ ችግር የለውም ችግሩ የሚመነጨው ግን ይህ መለኮታዊ ኃይል መወከል ያለበት በአውሮፓውያን ነው ተብሎ ሲታሰብ ነው ይላሉ። በፖርቹጋል ቅኝ ግዛት ስር በነበረችው ጥንታዊ ቻይና በቻይና አለባበስ ተስሏል እንዲሁም በኢትዮጵያ ጠይም መልክ ያለው የእየሱስ ምስሎችም እንዳሉ ይገልፃሉ። ተያያዥ ርዕሶች
ቦርሳቸው ውስጥ የሞተ ሰው እጅ የተገኘባቸው ሩስያዊ ፕሮፌሰር በቁጥጥር ሥር ዋሉ
ኅዳር ይህንን ለማጋራት በ ዋትስአፕ የሴይንት ፒተርስበርግ ፖሊስ ቦርሳቸው ውስጥ የተቆረጥ የሰው ልጅ እጅ አግኝቼባቸዋለሁ ያላቸውን የታሪክ ምሁር በቁጥጥር ሥር አዋለ። ፕሮፌሰሩም ፍቅረኛቸውን እንደገደሉ አምነዋል። ጉምቱው ፕሮፌሰር ኦሌግ ሶኮሎቭ ሰክረው ወንዝ ውስጥ ወድቀው ነው የተገኙት። ወንዝ አካባቢ የተገኙትም እጁን ሊጥሉት ሳይሆን አይቀርም ተብሏል። ሰውዬው ከተያዙ በኋላ ቤታቸውን የፈተሸው ፖሊስ የፕሮፌሰሩ የቀድሞ ተማሪ የነበረች የ ዓመት ወጣት ሬሳ አግኝቷል። የፕሮፌሰሩ ቤት ውስጥ ጭንቅላቷ ተቆርጦ ሬሳዋ የተገኘችው ሴት አናስታሲያ የሺቼንኮ ከፕሮፌሰሩ ጋር በርካታ ፅሑፎች ያሳተመች ተማሪ ናት። አብራሞቪች ስዊዘርላንድ እንዳይገቡ ተከለከሉ የናፖሌዮን ታሪክ ተመራማሪ የሆኑት ፕሮፌሰር ሶኮሎቭ በፈረንሳይ የሌጌዎን ክብር የተሰጣቸው ሰው ናቸው። የግለሰቡ ጠበቃ የሆኑ ሰው ፕፎፌሰሩ ፍቅረኛቸው የነበረችውን ወጣት መግደላቸውን አምነዋል ሲሉ ተናግረዋል። የ ዓመቱ ፕሮፌሰር የወጣቷን ሬሳ ካስወገዱ በኋላ እንደናፖሌዮን ለብሰው አደባባይ ላይ ራሳቸውን ሊያጠፉ አስበው እንደነበርም ታውቋል። ግለሰቡ ከፍቅረኛቸው ጋር ባለመግባባታቸው ምክንያት እንደገደሏትና ጭንቅላቷን እንደቆረጡ ለፖሊስ አምነዋል።
ኢትዮጵያና ኤርትራ የት ድረስ አብረው ይራመዳሉ
ጁን ማጋሪያ ምረጥ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ስልጣን ሲረከቡ ፓርላማ ቀርበው ባደረጉት ንግግር ከኤርትራ ጋር ሰላም ለማውረድ እንደሚፈልጉ አስታውቀው ነበር። በወቅቱ ከኤርትራ በኩል የተሰጠው ምላሽ ኢትዮጵያ ሰላም ማውረድ ከፈለገች የአልጀርሱን ስምምነት ተግባራዊ ማድረግ ቀዳሚው እርምጃ ነው የሚል ነበር። ኢትዮጵያ የአልጀርሱን ስምምነት ተግባራዊ እንደምታደርግ ስታስታውቅ በአገር ውስጥ ውሳኔውን የመቃወም ድምፆች ተሰምተው ነበር። በኤርትራ በኩል ግን ምንም የተባለ ነበር አልነበረም። ዛሬ ግን ዝምታው ተሰብሮ የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ወደ አዲስ አበባ ልኡካን እንደሚልኩ አስታውቀዋል። በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካል ሳይንስ መምህር የሆነው መኃሪ ዮሃንስ ዘላቂ ሰላምን ያመጣል የሚለው ጉዳይ ዛሬ ላይ የሚመለስ ባይሆንም እርምጃው ግን በራሱ ትልቅ ነው ይላል። እርምጃው ትልቅ ነው የሚለው የእስከዛሬውን የሁለቱ አገራት ግንኙነት ከግምት በማስገባት ነው። የሁለቱ አገራት መንግስታት ላለፉት ሃያ ዓመታት ደረቅ አቋም ይዘው የኢትዮጵያ መንግስት የድንበር ኮሚሽኑን ውሳኔ በመርህ ደረጃ ተቀብለነዋል ነገር ግን ትግበራው ውይይት ይፈልጋል ፤ የኤርትራ መንግስት ደግሞ ውሳኔው ያለምንም ቅድመ ሁኔታ መፈፀም አለበት ሲሉ ከመቆየታቸው አንፃር እርምጃው የፖሊሲ ለውጥ ነውም ይላል። ከፕሬዝዳንት ኢሳይያስ ንግግር እንደተረዳው ዋናው ችግር የነበረው በኤርትራው ገዥ ፓርቲና በህዝባዊ ወያነ ሃርነት ትግራይ ህወሃት መካከል እንደነበርና አሁን ግን በኢትዮጵያ የአመራር ለውጥ መምጣቱ ፕሬዝዳንቱን ለውሳኔው አብቅቷቸዋል። ይህን በሁለቱ አገራት መሪዎች መካከል መናበብ ያለ ይመስላል በማለት ይገልፀዋል መኃሪ። የኤርትራ መንግስት ልኡክ ለመላክ በመወሰን የወሰደው እርምጃ ምን ያህል ጉልህ ነው የሚለው የሚመዘነው ልኡካኑ መጥተው በሚያደርጉት ውይይት እንደሆነ መኃሪ ያስረዳል። ልኡካኑ ከኢትዮጵያ አቻዎቻቸው ጋር የሁለቱ አገራት መሪዎችን ለማገናኘት ነገሮችን ለማመቻቸት ወይስ በድንበር ጉዳዩ ላይ ለመነጋገር የሚለውን ማወቅ እርምጃውን ለመመዘን ወሳኝ እንደሆነ ያምናል። እርምጃው ዘላቂ ሰላምን ያመጣል አያመጣም የሚለው ጊዜው ደርሶ የውይይቱን ርእሰ ጉዳዮች ማወቅ ይጠይቃል ብሏል። ከሁለት አስርታት በላይ በአገራቱ መካከል የዘለቀውን ዝምታ ለሰበሩት ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ትልቅ ዋጋ እንደሚሰጡ የሚናገሩት ኤርትራዊው የህግ ባለሙያና ግጭት አፈታት ኤክስፐርት አቶ ኤልያስ ሃብተስላሴ የኤርትራ መንግስት ወደዚህ ነገር የገባው ተገዶ ነው ይላሉ። ቢሆንም ግን ለንግግር በር መክፈቱ ትልቅ ግምት የሚሰጠው እንደሆነ ያምናሉ። እርምጃው ምን ድረስ የሚዘልቅ ነው የሚለውን ለማወቅ ጊዜ እንደሚጠይቅ ምን ያህል ነው በሩን ክፍት ያደረገው የሚው በጊዜው የሚታይ ነው በማለት በመኃሪ ሃሳብ ይስማማሉ። እሳቸው እንደሚሉት ላለፉት ሁለት አስርት ዓመታት የኤርትራ መንግስት ወጣቱን በብሄራዊ ግዳጅ ሲያስገድድና ህዝቡ ላይ የተለያዩ ተፅእኖዎችን ሲያሳደር ኢትዮጵያ የድንበር ኮሚሽኑን ውሳኔ ተግባራዊ ላለማድረግ እንቢተኛ ሆናለች በሚል ነበር። በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ መንግስት ባደረጋቸው ውሳኔዎች ምክንያት የኤርትራ መንግስት በቀደመው አቋሙ እንዳይቀጥል ሆኗል የሚል እምነት አላቸው። በሁለቱ አገራት ግጭት በደረሱ ዘርፈ ብዙ ችግሮች ምክንያት ግን ጅማሮውን ከዳር ማድረስና በሁለቱ አገራት መካከል ሰላም ማስፈን ብዙ ስራ የሚጠይቅ እንደሚሆን አቶ ኤልያስ ይገልፃሉ። እንደ እሳቸው አገላለፅ በሁለቱ አገራት መንግስታት ምክንያት ሞት፣አካል ጉዳት፣መፈናቀል በአጠቃላይ ማህበራዊና ኢኮኖሚ ቀውሶች በሁለቱም ህዝቦች ላይ ደርሰዋል።በተለይም በሁለቱም በኩል ድንበር ላይ ያሉ ህዝቦች ይበልጥ ተጎድተዋል። ስለዚህም በሁለቱ አገራት ሰላም የማስፈን ነገር በመሪዎች ስምምነት ብቻ የሚጠናቀቅ ጉዳይ እንዳልሆነ አቶ ኤልያስ ያስረዳሉ። ይልቁንም የተጎጅዎች ካሳ ፣ሁለቱን ህዝብ የማገናኘትና ወደ ቀደመ ዝምድናው የመመለስ ጉዳይ ሊተኮርበት እንደሚገባ ያምናሉ። ለዚህ ደግሞ ስምምነቱ ኢኮኖሚና ማህበራዊ ገፅታ ሊኖረውና ሲቪል ማህበራትን ፣ የሃይማኖት ተቋማትንና በሁለቱም አገራት በኩል የሚመለከታቸውን እንዲሁም አህጉራዊና አለም አቀፍ አካላትን ሊያሳትፍ እንደሚገባ ያስረዳሉ። ይህ ካልሆነ ግን አዎንታዊው ጅማሮ ግቡን አይመታም የሚል ስጋት አላቸው። ተያያዥ ርዕሶች
ከዘጠኝ ዓመታት በፊት ኤርትራ ላይ የተጣለው ማዕቀብ ተነስቷል
ኖቬምበር የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት በኤርትራ ላይ ተጥሎ የነበረውን ማዕቀብ አነሳ። አባላት ያሉት የፀጥታው ምክር ቤት ሰኞ ዕለት ማእቀቡን ለማንሳት ስምምነት ላይ የደረሱ ሲሆን፤ የማንሳት ረቂቁም በእንግሊዝ መንግሥት አማካኝነት እንደቀረበ ተገልጿል። የማዕቀቡን መነሳት በተመለከተ ያነጋገርናቸው በቤልጄም የቀድሞው የኤርትራ አምባሳደር አቶ አምደብርሃን ወልደጊዮርጊስ፤ ኤርትራ ላይ ተጥሎ የነበረው ማዕቀብ ፍትሐዊ አልነበረም ብለዋል። የፖለቲከኛ እስረኞች ይፈቱ፣ የፕሬስ ነጻነት ይረከበር የሚሉ ጥያቄዎች ሲነሱ፤ የኤርትራ መንግሥት ማዕቀቡን እንደ ምክንያት ሲጠቀምበት እንደነበር ጥያቄዎቹ ሲነሱ ጦርነት ላይ ነን፤ ማዕቀብ ላይ ነን ሲባል ቆይቷል በማለት ገልጸዋል። የጠቅላይ ሚንስትር ጽሕፈት ቤት ማምሻውን ባወጣው መግለጫ፤ የኤርትራን ሕዝብና መንግሥት እንኳን ደስ አላችሁ ብሏል። ማዕቀቡ መነሳቱ በአፍሪካ ቀንድ ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን አስተዋጽኦ ያበረክታል ተብሏል። በቀጠናው ሀገሮች መካከል ዘላቂ ሰላም ለማስፈንና በሀገራቱ መካካል ጤናማ ግንኙነት ለመፍጠር እንደሚረዳም ተግልጿል። ለዘጠኝ ዓመታት ያህል የቆየው ይህ ማዕቀብ የጦር መሳሪያ ዝውውርን ከመገደብ በተጨማሪ፣ ከፍተኛ የኤርትራ ባለስልጣናት እንቅስቃሴያቸው እንዲገደብና ሀብታቸውን እንዳያንቀሳቅሱ የሚል ነው። ለሁለት አስርት አመታት ተፋጠው የነበሩት የኢትዮጵያና የኤርትራ መንግሥት እርቅ መፈፀማቸውን ተከትሎ፤ የኤርትራ መንግሥት ከሌሎች ጎረቤት ሀገራትም ጋር ግንኙነቱ በመሻሻሉ ምክንያት ማዕቀቡ ሊነሳ እንደተቻለ ተገልጿል።
በፈረንሳይ ልማደኛው ሌባ የአንበሳ ደቦል ሰርቆ ተያዘ
ጥቅምት ባለሥልጣናቱ የዱር እንሰሳትን እንደለማዳ እንሰሳ ቤት ውስጥ ማቆየት ወንጀል ስለመሆኑ ሲናገሩ ነበር የ ዓመቱ ፈረንሳዊ በመኖሪያ ቤቱ ውስጥ የአንበሳ ደቦል ደብቆ በመገኘቱ በቁጥጥር ስር ውሏል። እንደ ፈረንሳይ መገናኛ ብዙኃን ዘገባ ከሆነ ፖሊስ መረጃው የደረሰው ግለሰቡ የስድስት ሳምንት ዕድሜ ያላትን ደቦል በ ሺህ ዮሮ ለመሸጥ ሲያስማማ ነው። ማክሰኞ ዕለት ጎረቤቶቹ ቤት ቁምሳጥን ውስጥ የደበቃት ሲሆን ደቦሏ ግን የሕፃን አልጋ ላይ ተገኝታለች። ደቦሏ በጥሩ ጤንነት ላይ እንደምትገኝ የተነገረ ሲሆን ለዱር አራዊት ባለሥልጣናትም ተላልፋ ተሰጥታለች። እንደ የፈረንሳይ መገናኛ ብዙኃን ዘገባ ወንጀለኛው ልማደኛ ሌባ ነበር ተብሏል። ፖሊስ በሕገወጥ መልኩ በሰዎች መኖሪያ ውስጥ የዱር እንስሳትን ሲያገኝ የመጀመሪያ ጊዜው አይደለም። በ አንድ ግለሰብ በምግብ እጥረት የተጎዳ የአንበሳ ደቦል ሰው በማይኖርበት ሕንፃ ውስጥ ደብቆ መገኘቱ ይታወቃል። ወንጀለኛው የተደረሰበትም ከደቦሏ ጋር ምሥለ ራስ ፎቶ ሰልፊ ተነስቶ ፎቶውን ከተሠራጨ በኋላ ነው። የኋላ ኋላ ደቦሉ ወደ ደቡብ አፍሪካ የእንስሳት ማቆያ ተወስዷል። በዚህ ወርም ኔዘርላንዳዊ መንገደኛ አንድ ደቦል በመንገድ ላይ ተጥሎ አግኝቷል። ከዚህ ዜና በተጨማሪ
የኤርትራ መንግሥት የሐይማኖት እሥረኞችን ፈታ
ጁላይ ማጋሪያ ምረጥ የኤርትራ መንግሥት በሃይማኖት ምክንያት የታሠሩ እሥረኞች ትላንት ምሽት አካባቢ መፍታቱ ተሰምቷል። እሥረኞቹ የተፈቱት ማይስርዋ ተብሎ ከሚታወቀው ማረሚያ ቤት ነው። ከተፈቱት ግለሰቦች መካከል ሴቶች ሲገኙ የጴንጤቆስጤ ቤተክርስትያን አባላት መሆናቸው ታውቋል። ትላንት ከሰዓት ገደማ ዎቹ እንደተለቀቁ ከተሰማ በኋላ ማምሻው ላይ ደግሞ የተቀሩቱ ግለሰቦች ከእሥር ተፈተዋል። ከተፈቱት መካከል ታናሽ ወንድሙ የሚገኝበት ዳንኤል ወንድሜ መፈታቱ እጅግ አስደስቶኛል ሲል ስሜቱን ለቢቢሲ አጋርቷል። እንደ ዳንኤል ገለፃ ታናሽ ወንድሙ በሐይማኖቱ ምክንያት ለ ዓመት ከ ወራት በተለያዩ ማረሚያ ቤቶች ለእሥር ተዳርጓል፤ ቤተሰቦቹም ታሣሪ ልጃቸውን ፍለጋ ብዙ ተንገላተዋል። ከ ግለሰቦቹ አንዱ ለ ዓመታት ያክል እሥር ቤት እንደቆየ የተቀሩቱ ደግሞ ከ እስከ ዓመት ድረስ እንደታሰሩ ሰምተናል። ማይስርዋ ከከረሙት እሥረኞች ከሶስት ሳምንታት በፊት እንደሚፈቱ ተነግሯቸው ቅፅ እንደሞሉ ነገር ግን ወዲያው እንዳልተፈቱ ታውቋል። ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ ምንጮች ለቢቢሲ እንደተናገሩት የእሥረኞቹ መፈታት ኤርትራና ኢትዮጵያ ከደረሱት የሰላም ስምምነት ጋር የሚገናኝ አይደለም።
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እስካሁን ፕሬዝዳንቶች ነበሩት
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እስካሁን ፕሬዝዳንቶች ነበሩት ጥር አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰር አንድርያስ እሸቴን፣ ፕሮፌሰር አለማየሁ ተፈራን እና ዶ ር ታየ ጉልላትን ጨምሮ እስካሁን ፕሬዝዳንቶች ነበሩት።
የሳዑዲዋ ልዕልት በፓሪስ የቧንቧ ሠራተኛውን በማገቷ ተፈረደባት
ሴፕቴምበር አጭር የምስል መግለጫ የሳዑዲው ልዑል መሐመድ ቢን ሰልማን የሳዑዲዋ ልዕልት በፈረንሳይ በሚገኘው ቅንጡ መኖሪያዋ የቧንቧ ሠራተኛ በመደብደብና በማገት ተከሳ፤ ከዚህ በኋላ ሌላ ጥፋት ካጠፋች ተፈፃሚ የሚሆን የአሥር ወር ቅጣት ተፈረደባት። የሳዑዲው ልዑል መሐመድ ቢን ሰልማን እህት የሆነችው የ ዓመቷ ሐሳ ቢንት ሳልማን የንጉሥ ሰልማን ሴት ልጅ ነች። የግል ጠባቂዋ ቧንቧ ሠራተኛውን እንዲደበድብ አዛለች ተብላ የተከሰሰች ሲሆን፤ የሠራተኛው ጥፋት ነው ያለችው ደግሞ የቤቷን የውስጥ ክፍል ፎቶ ማንሳቱን ነበር። የቧንቧ ሠራተኛው አሽራፍ ኢድ እንደተናገረው፤ የግል ጠባቂዋ ጠፍንጎ ካሰረው በኋላ የልዕልቷን እግር እንዲስም አስገድዶታል። ሐሙስ ዕለት ችሎት የዋለው የፈረንሳይ ፍርድ ቤት፤ ልዕልቷ በተመሰረተባት ክስ ጥፋተኛ ነች ሲል ፍርዱን ሰጥቷል። ልዕልቷ በቁጥጥር ሥር እንድትውል ዓለም አቀፍ ማዘዣ የወጣባት ሲሆን፤ በተአቅቦ የ ሺህ ዩሮ ቅጣት እንድትከፍል ተወስኖባታል። ከፍርድ ቤቱ ውሳኔ በኋላ፤ የልዕልቷ ጠበቃ የሆኑት ኢማኑዔል ሞይኔ፤ የቧንቧ ሠራተኛው ውንጀላ በምኞት የተሞላ ነው በማለት ይግባኝ እንደሚሉ ተናግረዋል። ምን ነበር የሆነው እኤአ በ መስከረም ወር ላይ፣ ኢድ ፈረንሳይ ውስጥ ወደሚገኝ የልዕልቷ ቅንጡ መኖሪያ አፓርትመንት አምስተኛ ፎቅ የተበላሸ የእጅ መታጠቢያ እንዲጠግን ጥሪ ቀረበለት። ግብፃዊው ሠራተኛ፤ መታጠቢያ ክፍሉን ሲመለከተው አላስቻለውም። ስልኩን መዥረጥ አድርጎ አውጥቶ ፎቶ ማንሳት ጀመረ። በእርግጥ ለሥራዬ የሚረዳኝ ነገር ስላየሁ ነው ያነሳሁት ብሏል። ነገር ግን ልዕልቷ በመስታወት ውስጥ የሚታየው ምስሏ ፎቶ ውስጥ መግባቱ አስቆጣት። ከዚያም የግል ጠባቂዋን ሰይድን ጠርታ አስሮ እንዲገርፈው አዘዘች። ቧንቧ ሠራተኛው እንደሚለው፤ እግሯን እንዲስም ተገዷል፤ ለበርካታ ሰዓታትም እንዳይወጣ ታግቶ ቆይቷል። እንደውም ልዕልቷ የሆነ ሰዓት ላይ ብልጭ ብሎባት ይህንን ውሻ ግደለው፤ ሊኖር አይገባውም ብላ ነበር ብሏል። የአምባቸው ሕልም የተጠናከረ አማራን፣ የበለጸገች ኢትዮጵያን ማየት ነበር አቶ ቹቹ አለባቸው የልዕልቷ ጠባቂ ሐምሌ ወር ላይ ፍርድ ቤት ቀርቦ እንዳስረዳው፤ ወደ መታጠቢያ ቤት የሄደው የልዕልቲቱን የድረሱልኝ ጩኸት ሰምቶ ነበር። ሲደርስም ልዕልቲቱና ቧንቧ ሠራተኛው ስልኩን ይዘው ይታሉ ነበር። ከዛም የዚህ ሠራተኛ ዓላማ ምን እንደሆን ባለማወቄ በጉልበት ስልኩን አስጥየዋለሁ ብሏል። ምስሉን ሊሸጠው አስቦ ይሆናል ሲል ግምቱንም ለፍርድ ቤቱ ተናግሯል። በሳዑዲ ሕግ መሰረት ልዕልቲቱን ፎቶ ማንሳት ክልክል ነው። የልዕልቲቱ ጠበቃ፤ የቧንቧ ሠራተኛው ከክስተቱ በኋላ በተከታታይ ወደ አፓርታማው እንደሄደና የ ሺህ ዩሮ ክፍያ እንደጠየቀ ተናግሯል። የሳዑዲዋ ልዕልት ሐሳ፤ በበጎ አድራጎቷ እና በሴቶች መብት ተከራካሪነትዋ የምትንቆለጳጰስ ናት። ተያያዥ ርዕሶች
ኢራን የአውሮፓ አገራትን ውንጀላ አጣጣለች
ሴፕቴምበር አጭር የምስል መግለጫ ኢማኑኤል ማክሮን፣ አንግላ መርከልና ቦሪስ ጆንሰን በተባበሩት መንግሥታት ድረጅት ዋና ጽሕፈት ቤት ፈረንሳይ፣ ጀርመን እና ዩናይትድ ኪንግደም በጥምረት፤ በሳዑዲ ነዳጅ ማቀነባበሪያ ላይ ከደረሰው ጥቃት ጀርባ ያለችው ኢራን ናት ቢሉም፤ ኢራን ውንጀላቸውን አጣጥላዋለች። የኢራን የውጪ ጉዳይ ሚንስትር የሦስቱን አገራት ክስ የአሜሪካን ከንቱ ክስ ያስተጋባ ሲሉ ውድቅ አድርገዋል። አሜሪካ ጦሯን ወደ ሳዑዲ ልትልክ ነው የአውሮፓ አገራት መሪዎች እንዳሉት፤ ከጥቃቱ ጋር በተያያዘ ከኢራን ውጪ ማንም ላይ ጣት መቀሰር አይቻልም። ኢራን የምትደግፈው የየመኑ የሁቲ አማጽያን ቡድን ጥቃቱን የሰነዘርኩት እኔ ነኝ ሲል ኃላፊነቱን ቢወስድም፤ አሁንም ተጠያቂ የተደረገችው ኢራን ናት። ስምንት ሰው አልባ አውሮፕላኖች እና ሰባት ሚሳኤሎች የሳዑዲን የነዳጅ ማቀነባበሪያ ከመቱ በኋላ፤ ሳዑዲ እንዲሁም አሜሪካ ኢራንን ወንጅለዋል። ኢራን በበኩሏ በጥቃቱ እጄ የለበትም ማለቷ ይታወሳል። መሪዎቹ ምን አሉ የእንግሊዙ ጠቅላይ ሚንስትር ቦሪስ ጆንሰን፣ የፈረንሳዩ ፕሬዘዳንት ኢማኑኤል ማክሮን እና የጀርመኗ መራሔተ መንግስት አንግላ መርኬል በጋራ በሰጡት መግለጫ፤ ኢራን ለጥቃቱ ተጠያቂ ናት ብለዋል። እየተካሄደ ያለውን ምርመራ እንደሚደግፉም አሳውቀዋል። ኢራን በኒውክሌር ፕሮግራሟ ላይ ለድርድር ዝግጁ መሆን የሚጠበቅባት ጊዜ ላይ ነን ሲሉም መሪዎቹ ተናግረዋል።
ከ ሚሊዮን ዶላር በላይ የሚያወጣ ስእል በአንዲት አዛውንት ማእድ ቤት ተገኘ
ሴፕቴምበር ማጋሪያ ምረጥ በፈረንሳይዋ ፓሪስ አቅራቢያ በአንዲት አዛውንት ኩሽና ተገኘ የተባለው የስእል ስራ በአስራ ሶስተኛው ክፍለ ዘመን እንደተሰራ የሚታመን ነው። ለረዥም ጊዜያት የት እንደገባ ጠፍቶ የነበረው እሄ የስእል ስራ ባለቤት ጣልያናዊው ሲምባው ወይም ሲኒ ዲ ፒፖ እንደሆነም ኤክስፐርቶች አስታውቀዋል። እርግጥም ይህ የጥበብ ስራ የዚህ ጣልያናዊ መሆኑን ለማረጋገጥ በኢንፍራሪድ ምርመራም ተካሂዷል። ስእሉ እአአ በሚቀጥለው ወር ለጨረታ የሚቀርብ ሲሆን ሚሊዮን ዶላር ድረስ ሊያወጣ እንደሚችል ተገልጿል። ዘመናትን የተሻገረውና ከፍተኛ ዋጋ ያለው ይህ ስእልን ያስቀመጡት አዛውንት ስእሉ ትልቅ የጥበብ ዋጋ ያለው ሃይማኖታዊ ስእል እንደሆነ ያምኑ እንደነበርም ተገልጿል።
የሱዳን ስደተኞች ቡድን የፈረንሳዩን ባንክ በዘር ጭፍጨፋ ሊከስ ነው
ሴፕቴምበር ማጋሪያ ምረጥ የሱዳን ስደተኞች ቡድን ቢኤንፒ ፓሪባስ የተባለውን የፈረንሳይ ባንክ በሱዳን ዘር ጭፍጨፋ ላይ ሚና ነበረው በሚል ፍርድ ቤት ሊያቆመው ነው። ሱዳን በነበረው የዘር ጭፍጨፋ ጥቃት ደርሶብናል የሚለው ይህ ቡድን ባንኩ መንግሥት የፈፀማቸውን ግፎችም ሲደግፍ ነበር በማለት በዛሬው ዕለት ፖሪስ በሚገኘው ፍርድ ቤት የሚያቆሙት። መቀመጫቸውን አሜሪካ ያደረጉት ሃያ አንዱ ስደተኞች ባንኩ ኒውዮርክ በሚገኘው ቅርንጫፉ በሱዳን መንግሥት የተፈፀሙ ግድያዎችን፣ መደፈር፣ ስቃይ እንዲሁም ሆን ብሎ የኤችአይቪ ቫይረስን ማስተላለፍ ግፎች ላይ ሚና በመጫወትና ህገወጥ የሆኑ የገንዘብ ዝውውሮችን ሂደት በማቀላጠፍ ወንጅለውታል። በሱዳን ላይ የተፈፀመውን የዘር ጭፍጨፋ ላይ ከተወነጀሉ የመጀመሪያ አለም አቀፍ ድርጅቶች አንዱ ነው። ባለፈው አንድ ዓመት ከ ሰዎች በላይ መገደላቸውን ጠቅላይ አቃቤ ህግ አስታወቀ ከሳሾቹ የፈረንሳይ ዳኞች በባንኩ ላይ የወንጀል ምርምራ እንዲከፈት የጠየቁ ሲሆን ይህም ባንኩን ወይም በባንኩ ውስጥ በከፍተኛ ኃላፊነት ያለ ሰው ከገንዘብ ቅጣት ጀምሮ፣ እስር እንዲሁም ማዕቀብ ሊጣልበት እንደሚችልም ተጠቁሟል። ከጎርጎሳውያኑ አቆጣጠር ከ ባሉት ጊዜያት የሱዳን ባንክ ተብሎ የሚጠራው ይህ ባንክ በአሜሪካ፣ በተባበሩት መንግሥታትና በአውሮፓ ህብረት የኢኮኖሚ ማዕቀብ በተጣለበት ጊዜም ለአልበሽር መንግሥት የባንክ አገልግሎት በዋነኝነት ይሰጥ ነበር ተብሏል። በዚህም ወቅት ዳርፉር ላይ ከፍተኛ ግድያዎች የደረሱ ሲሆን የአለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤትም የዘር ጭፍጨፋ ተፈፅሟል ይላል። የኢኮኖሚ ማዕቀቡን በመጣስ ከሱዳን፣ ከኢራንና ኪዩባ ጋር የገንዘብ ግንኙነት በመፍጠር በአሜሪካ ቢሊዮን ዶላር ቅጣት ተጥሎበታል። ተያያዥ ርዕሶች
በፓሪስ ውስጥ አንድ ግለሰብ አራት ፖሊሶችን በስለት ገደለ
ኦክተውበር ማጋሪያ ምረጥ በፈረንሳዩዋ ዋና ከተማ ፓሪስ አንድ ግለሰብ በፖሊስ ዋና መስሪያ ቤት በር ላይ ስለት በመጠቀም በፈጸመው ጥቃት አራት የፖሊስ አባላት ህይወታቸው ማለፉን የሃገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ዘገቡ። ጥቃት ፈጻሚው የፖሊስ ዋና መስሪያ ቤቱ የሚገኝበት ህንጻ ውስጥ ተቀጥሮ የሚሰራ የነበረ ሲሆን ጥቃቱን በፈጸመበት ቦታ ላይ በፖሊሶች በተተኮሰበት ጥይት ህይወቱ ማለፉም ታውቋል። ለሥራ ከከተማ የወጣ ሰራተኛ ወሲብ ሲፈጽም በመሞቱ ቀጣሪው ኃላፊነቱን ይውሰድ ተብሏል ኢል ዴ ላ ሲቴ የተባለው የፈርሳይ ፖሊስ ዋና መስሪያ ቤት የሚገኝበት አካባቢ ከማንኛውም እንቅስቃሴ መዘጋቱ ተገልጿል። ይህ ጥቃት የተፈጸመው የፈረንሳይ ፖሊሶች በአባላሎቻቸው ላይ የሚደርሱ ጥቃቶች እንዲቆሙና እራሳቸውን የሚያጠፉ ፖሊሶች ቁጥር መጨመሩ አሳስቦናል በማለት በመላው ሀገሪቱ ተቃውሞ ካካሄዱ ከአንድ ቀን በኋላ መሆኑ ብዙዎችን አስቆጥቷል። የፈረንሳዩ የሃገር ውስጥ ሚንስትር ክሪስቶፍ ካስታነር ጥቃቱ የተፈጸመበት መገኘታቸውም ተነግሯል።
ለሥራ ከከተማ የወጣ ሰራተኛ ወሲብ ሲፈጽም በመሞቱ ቀጣሪው ኃላፊነቱን ይውሰድ ተብሏል
ሴፕቴምበር ማጋሪያ ምረጥ በአንድ የፈረንሳይ ድርጅት ውስጥ ተቀጥሮ ይሰራ የነበረ ግለሰብ ለሥራ ከከተማ ወጣ በለበት አጋጣሚ ወሲብ ሲፈጽም ህይወቱ በማለፉ ድርጅቱ ተጠያቂ ይሆናል መባሉ እያነጋገረ ነው። ሰውዬው ለድርጅቱ ሥራ በሄደበት ድንገት የልብ ድካም አጋጥሞት ስለሞተ ቤተሰቦቹ ከቀጣሪው ድርጅት ካሳ ማግኘት አለባቸው ሲል በፓሪስ የሚገኝ ፍርድ ቤት ብይን አስተላልፏል። እንግሊዛውያን የወሲብ ሕይወታቸው ደካማ ነው ተባለ ድርጅቱ ደግሞ ሰውዬው ምንም እንኳን ለስራ ቢሆንም የሄደው፤ ህይወቱ ያለፈው ግን የድርጅቱን ሃላፊነት ሲወጣ ሳይሆን ባረፈበት ሆቴል ከምትገኝ ሌላ እንግዳ ክፍል ውስጥ ገብቶ የግብረስጋ ግንኙነት ሲፈጽም ባጋጠመው የልብ ድካም ስለሆነ ተጠያቂ መሆን የለብኝም ብሎ ተከራክሯል። ነገር ግን በፈረንሳይ ህግ መሰረት አንድ ተቀጣሪ በስራ ጉዞ ወቅት ለሚያጋጥመው ማንኛውም አይነት አደጋም ሆነ መጉላላቶች ቀጣሪው ድርጅት ሙሉ በሙሉ ተጠያቂ መሆኑን የፍርድ ቤቱ ዳኛ ገልጸዋል። ዣቪዬር የተባለው ግለሰብ በባቡር ስራዎች ላይ ትኩረት አድርጎ የሚሰራ ቲኤስኦ በተባለ ድርጅት ውስጥ በማህንዲስነት ነበር ተቀጥሮ የሚሰራው። የዣቪዬር ጤና መድህን አቅራቢ ድርጀት ደንበኛዬ በስራ ጉዞ ወቅት ባጋጠመው ድንገተኛ የጤና እክል ህይወቱ ስላለፈች ካሳውን ሊከፍል የሚገባው ቀጣሪው ድርጅት ነው በማለት ሲከራከር ነበር። ሴት አስገድዳ ከወንድ ጋር ወሲብ ብትፈጽም፤ አስገድዶ መድፈር ይባላል ምናልባት የልብ ድካሙ ገላውን ሲታጠብ አልያም ለስራ ሲወጣ ሊያጋጥመው የችል ነበር። ማንኛውም ሰው የሚያደርገውን ነገር እያደረገ ነው ህይወቱ ያለፈው፤ ስለዚህ እንደተለየ ነገር መወሰድ የለበትም የሚል መከራከሪያ አቅርቧል። ፍርድ ቤቱም የሃገሪቱን ህግ እና የመከራከሪያ ነጥቦች ከግምት ውስጥ በማስገባት ቲኤስኦ የተባለው ድርጅት ለሰራተኛው ሞት ካሳ እንዲከፍ የመጨረሻ ውሳኔውን አስተላልፏል። ተያያዥ ርዕሶች
ከእንግሊዝ ፈረንሳይ በባህር የሚያሻግረው ባቡር
ከእንግሊዝ ፈረንሳይ በባህር የሚያሻግረው ባቡር ጥቅምት
ደግነት ለጤንነት ብቻ ሳይሆን ለረዥም እድሜ ይጠቅማል
ኅዳር ይህንን ለማጋራት በ ዋትስአፕ ደግነት ምን ያስገኛል ምናልባት ደስ የሚል ስሜት አዎ በእርግጥም መልካምነት በሕይወታችን ጥሩ ነገሮችን ያስከትላል። ተመራማሪዎች ደግነት ከሚፈጥርልን አወንታዊ ስሜት ባሻገር እድሜያችንንም እንደሚያረዝም ደርሰንበታል ይላሉ። በእርግጥ ደግነት ስንል ምን ማለታችን ነው ለምንስ አስፈላጊ ነው የሚለውን ጥያቄ ተመራማሪዎቹ አንስተው በዝርዝር ለመረዳት ሲነሱ ነገሩ በሰው ሕይወት ውስጥ ወሳኝ ነገር ሊሆን እንደሚችል እርግጠኛ ሆነው ነበሩ። ምርምሩን የመሩት ዳንኤል ፌስለር በተለይ ሌሎች መልካም ሲያደርጉ የሚመለከቱ ሰዎች እንዴት ደግ ለመስራት ሊነሳሱ እንደሚችሉ በቅርበት በመፈተሽ ተላላፊ ደግነት ያሉት ክስተት ማንን በተለይ በአወንታዊ መልኩ እንደሚነካ መርምረዋል። በፌስቡክና በዩቲዩብ ብዙ ተከታይ ያላቸው ሰዎች ምን ያህል ገንዘብ እንደሚያገኙ ያውቃሉ ተመራማሪው በአሁኑ ዘመን ደግነት በራቀው ዓለም ውስጥ እንገኛለን በማለት በዓለም ዙሪያ በፖለቲካ አመለካከትና በሐይማኖት ሰበብ በሰዎች መካከል የሚከሰተው ግጭት እየጨመረ መሆኑን ይናገራሉ። ደግነት ሌሎችን ለመጥቀም ከሚደረጉ አስተሳሰቦችን፣ ስሜቶችንና እምነቶችን ከሚያንጸባርቁ ተግባራት ጋር የተያያዙ እንደሆኑ በመግለጽ፤ እነዚህም በውጤታቸው ሌሎችን የሚጠቅሙ ሲሆኑ ሌላ ውጤት ለማምጣት የምንጠቀምበት እንዳልሆነ ተመራማሪው ይናገራሉ። በተቃራኒው ደግ ወይም መልካም አለመሆን ሌሎችን ያለመቀበል፣ ለሌሎች ደህንነት ዋጋ ያለመስጠት ማሳያ ነው ይላሉ። መጻሕፍትን ማንበብና መጻፍ ለአዕምሮ ጤና ይህ በደግነት ላይ የተደረገው ምርምር ያስፈለገው ደግነት ስለምን በዘመናዊው ዓለም ተጓደለ የሚለውን ለመረዳት እንደሆነ ለጥናቱ የገንዘብ ድጋፍ የሰጠው ተቋም ባለቤቶች ተናግረዋል። ተመራማሪው ዳንኤል ፌስለር እንደሚሉት ደግነት ብዙ ገጽታዎች አሉት የደግነት ተግባር ለሰው ስናደርግና ለእኛም ሲደረግልን በሁሉም መልኩ ለጤናችን ጠቃሚ ነው። አደገኛ የሆነን ውጥረት ወይም ጭንቀትን በማስወገድ በጎ ውጤት አለው ይላሉ። ደግነት ወይም መልካምነት ትልልቅ ድርጊቶች በመፈጸም ብቻ የሚገለጹ ሳይሆኑ ቀላል የሚባሉ ንግግሮችና የሰላምታ ልውውጦችም ከዚሁ አንጻር ሊታዩ ይችላሉ። ለራሳችን ይልቅ ለሌሎች በጎ ማድረግ ቀላል ነው ብዙም ግድ ባንሰጠውም በመደብር ውስጥ የሚገኙ አስተናጋጆች የሚያሳዩን ፈገግታና የሚሰጡን ሰላምታ በአጠቃላይ ጤናችን ላይ የእራሱ የሆነ አውንታዊ ውጤት እንዳለው ጥናቱ አመልክቷል። ለሌሎች መልካም ስለመሆን ማሰብና በደግነት ድርጊቶች ውስጥ መሳተፍ የደም ግፊትን ዝቅ ያደርጋል። በተጨማሪም ድብርትና ጭንቀትን የማከም ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው። በኮለምቢያ ዩኒቨርስቲ ዶክትር የሆኑት ኬሊ ሃርዲንግ በቅርብ ባሳተሙት መጽሐፋቸው ላይ እንዳሰፈሩት መልካምነት የሰውነታችንን በሽታን የመከላከል አቅም ይገነባል፣ የደም ግፊትን ዝቅ በማድረግ ሰዎች በረጅም እድሜ የተሻለ ሕይወት እንዲኖራቸው ያደርጋል ብለዋል። ጠቃሚ ነጥቦች ደግነት ለተሞላበት ሕይወት የሚሰሙ መስለው መልስ ለመስጠት እራስዎን ከማዘጋጀት ይልቅ በሐቅ ሌሎች የሚሉትን ማድመጥ ይጀምሩ በመጥፎ ሁኔታ ምላሽ ለሚሰጥዎት ሰው በመልካምነት ይመልሱ። የሚያመነጫጭቅዎትን ሰው ያስቡና ወዳጅነት በተሞላበት ሁኔታ ቀንህ ሽ ጥሩ አልነበረም ብለው ይጠይቋቸው። በዚህም ውጥረት የተሞላበትን ሁኔታ በቀላሉ ማርገብ ይችላሉ በሰዎች ሕይወት ውስጥ ከሚያጋጥሙ ነገሮች ሁሉ ችላ መባል፣ አለመፈለግና አለመፈቀር የሰውነትን ክብር የመግፈፍ ያህል ስለሆነ ችላ የተባለን ሰውን ያቅርቡ። ይህን ሲያደርጉ ለሰዎች ዋጋን ይሰጣሉ። ከመልካምነት የራቀ ድርጊት ሲፈጸም ሲገጥምዎ የእርሶ ችግር አለመሆኑን ይረዱ። ለድርጊቱ ምላሽ እንዲሰጡ ሲገፋፉም እራስዎን ይቆጥቡና በጥልቀት ትንፋሽ ወስደው እራስዎን ያርቁ። ዶክትር ኬሊ ደግነት በዙሪያችን ያሉ ነገሮችን በመለወጥ በዓለም ላይ ያሉ ነገሮችን እንድንፈትሽ ይረዳናል በማለት በአብዛኛው ከእራሳችን ይልቅ ለሌሎች ሰዎች መልካም ለመሆን ይቀለናል ሲሉ አክለዋል። ለእራሳችንም ሆነ ለሌሎች ደግ መሆንን ለማበረታታት በርካታ መንገዶች አሉ። በሥራ ቦታ፣ በትምህርት ቤትና በቤታችን ውስጥ ደግና ሩህሩህ በመሆን መልካም ውጤትን ለማግኘት እንችላለን ይላሉ። በህክምና በኩል ቴክኖሎጂው እየተሻሻለ ሊሆን ይችላል፤ ነገር ግን የተንከባካቢን ደግነት ያህል ትልቅ ነገርን ግን መፍጠር አይቻለንም ይላሉ ዶክተሯ። በተለይ ደግሞ በአእምሮ ጤናና አካላዊ ጤና መካከል ያለው ትስስር እጅግ ወሳኝነት በመጥቀስ። ትምህርት ዕድሜን እንደሚያስረዝም በጥናት ተረጋገጠ ሰዎች ሌሎች የደግነት ተግባርን ሲፈጽሙ ሲመለከቱ ተመሳሳዩን ለመፈጸም ይነሳሳሉ ይላሉ ባለሙያዎች። ስለዚህ የምንፈጽማቸው በጎ ነገሮች በእኛ ድርጊት ላይ ብቻ የሚቆሙ ሳይሆኑ በሌላ ጊዜ ለሌሎች ሰዎች ለሌሎች እንዲፈጸሙ እያገዝን መሆኑን መረዳት ያስፍለጋል። ግጭቶችና ጥላቻ በተበራከተበት ዓለም የመልካምነት ድርጊቶች ጎልተው ይሰማሉ፤ ያዩ የሰሙ እንዲሁም የተደረገላቸው ጭምር ሳይቀሩ ደግ ማድረግን ይለምዳሉ፤ ለሌሎችም ያስተላልፋሉ። በአንደኛው የዓለም ክፍል የሚፈጸም የደግነት ተግባር አየርና ባሕሩን አቋርጦ ከአድማስ ባሻገር በመጓዝ በሌላ ቦታ ይሰማል ይፈጸማል። ለዚህ ነው ደግንት መልካምነት ተላላፊ ነው የሚባለው። ከዚህ ዜና በተጨማሪ
ፓርላማው የኦነግ፣ ኦብነግና ግንቦት የሽብርተኝነት ፍረጃ መነሳትን አፀደቀ
ጁላይ ማጋሪያ ምረጥ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ በመደበኛ ስብሰባው ኦነግ፣ኦብነግና ግንቦት ሽብርተኛ መባላቸው ይሰረዝ ዘንድ ሚኒስትሮች ምክር ቤት የላከለትን ረቂቅ የውሳኔ ሃሳብ ከተወያየበት በኋላ አፅድቋል። ምክር ቤቱ ከዓመታት በፊት እነዚህን የፖለቲካ ድርጅቶች እንዲሁም አልቃይዳንና አልሻባብን አሸባሪ ማለቱ ይታወሳል። በሌላ በኩል ምክር ቤቱ ዛሬ በ ዓ ም በጀት ላይ የተወያየ ሲሆን በነገው እለት በቀረበለት በጀት ላይ ውሳኔ ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል። የሚኒስትሮች ምክር ቤት ለ ዓ ም በጀት ቢሊየን ሚሊየን ሺህ ብር እንዲሆን ወስኖ ደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ልኳል። ተያያዥ ርዕሶች
የአርበኞች ግንቦት አቀባበል ኮሚቴ አባል ብርሃኑ ተክለያሬድ ፍርድ ቤት ቀረበ
ሴፕቴምበር አጭር የምስል መግለጫ ብርሃኑ በቅርቡ ከእስር ከተፈቱ የፖለቲካ እስረኞች መካከል አንዱ ነው። የአርበኞች ግንቦት አቀባበል ኮሚቴ አባል የሆነው ወጣቱ ፖለቲከኛ ብርሃኑ ተክለያሬድን ጨምሮ በአዲስ አበባ እና በአዲስ አበባ ዙሪያ ሁከት እንዲፈጠር ረድተዋል በሚል የተጠረጠሩ ፍርድ ቤት ቀረቡ። ፖሊስ ምርመራውን ለማጠናቀቅ የጠየቀው የ ቀን የጊዜ ቀጠሮም ተፈቅዶለታል። በልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ኛ ምድብ ችሎት የቀረቡት ተጠርጣሪዎች በበኩላቸው ሰብዓዊ መብትን የሚጥስ አያያዝ እየተተገበረባቸው እንደ ሆነ ለፍርድቤቱ ተናግረዋል። የተጠርጣሪዎቹ ጠበቃ የሆኑት ሄኖክ አክሊሉ ደንበኞቻቸው በጨለማ እና ቀዝቃዛ ክፍል እንዲታሰሩ መደረጋቸውን፣ ከህገ መንግስቱ በተፃራሪ ፍርድ ቤት የቀረቡት ከ ሰዓታት በኋላ መሆኑን እንዲሁም ወጣት ብርሃኑ ተክለ ያሬድ በተለይ የአዕይምሮ ህመም አለበት ተብሎ ከሚጠረጠር ሰው ጋር እንዲታሰር መደረጉ ለህይወቱ አስጊ መሆኑን ለፍርድ ቤቱ ማስረዳታቸውን ለቢቢሲ ተናግረዋል። ፍርድ ቤቱም ተጠርጣሪዎች በተገቢው መንገድ እንዲያዙ ፖሊስን ማሳሰቡንም አክለው ነግረውናል። ፖሊስ ተጠርጣሪዎች ሁከትን በማስተባበር እና በመፍጠር ውስጥ ያላቸውን ተሳትፎ ያሳያሉ ያላቸውን ሰነዶች እና የባንክ ደብተር እንዳሉት ሆኖም ተጨማሪ ማስረጃ ለማሰባሰብ ተጨማሪ ቀን ያስፈልገኛል በማለት የጊዜ ቀጠሮ ጠይቋል። ብርሃኑ ተክለያሬድ ከዚህ ቀደም በሰማያዊ ፓርቲ ውስጥ በነበረው ተሳትፎ ፣ቆየት ብሎ ደግሞ የአርበኞች ግንቦት ንቅናቄን ሊቀላቀል ሞክሯል በሚል ለእስር መዳረጉ አይዘነጋም። ብርሃኑ በቅርቡ ከእስር ከተፈቱ የፖለቲካ እስረኞች መካከል አንዱ ነበር። ይህንን ዜና ያጋሩ ስለማጋራት
ከብሔርም ከሐይማኖትም በላይ ሰውነት ከሰሃራ በረሃ ስቃይ አውጥቶኛል
ኅዳር በብሔርና በሃይማኖት ያቻቻለን የሰሃራ በረሃ ስቃይ ሃሩን አሕመድ ከሰሃራ በረሃ ሃሩር፣ ከደላሎች ዱላና እንግልት ተርፎ ጀርመን የሚኖረው ሃሩን አሕመድ፣ በበረሃው ውስጥ አቅም አጥቶ ሲወድቅ የደገፉትን፣ ሲታረዝ ያለበሱትን፣ በውሃ ጥም የከሰለ ከንፈሩን ያረሰረሱለትን ሲያስታውስ የሰው ልጅ በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ ተቻችሎ መኖር እንዳለበት ብዙ ተምሬያለሁ ይላል። በባሌ ዞን አጋርፋ የተወለደው ሃሩን፣ እንደማንኛውም ወጣት በፖለቲካ ምክንያት ችግር ቢደርስበትም እርሱ ግን ከሀገር የወጣሁት በግል ምክንያት ነው ይላል። እኤአ በ ከሻሸመኔ ተነስቶ ወደ ሱዳን አመራ። ከአንድ ዓመት የሱዳን ኑሮ በኋላ እዚያ ከሚገኙ ከአራት ጓደኞቹና ከሌሎች ስደተኞች ጋር በ መጀመሪያ ወደ ሊቢያ ጉዞ ጀመሩ። ህወሓት፡ ሃገራዊ ምርጫ የሚራዘም ከሆነ ትግራይ የራሷን ምርጫ ታካሂዳለች ከካርቱም ትንሽ ወጣ ያለ ቦታ ላይ ከኤርትራዊያን፣ ሶማሊያዊያንና ሱዳናዊያንና ከኢትዮጵያ ከተለያዩ አካባቢዎች ከመጡ ስደተኞች ጋር ሰበሰቡን ሲል በወቅቱ የነበረውን ያስታውሳል። ስቃያችን የጀመረው ገና ከካርቱም ስንነሳ ነው የሚለው ሃሩን፤ ሁሉንም በጋራ የሰበሰቡበት ስፍራ ከመድረሳቸው በፊት የያዙትን አራግፈው እንደወሰዱባቸው ሲናገር ሴቶችን ልብስ አስወልቀው ጭምር ነበር የፈተሿቸው በማለት ወርቅና ገንዘባቸውን እንደወሰዱባቸው ይገልጻል። ሁለት ቀን እዚያ በረሃ ውስጥ ካሳደሯቸው በኋላ ወደ ሰሃራ የሚወስደዳቸው ግለሰብ መጥቶ መንገድ ጀመሩ። በአንድ መኪና ላይ ከ በላይ ሰዎች ሲጫኑ ሁሉም እንደትውውቃቸው፣ እንደመጡበት ሀገርና አካባቢ ብሔራቸውን ጭምር መሰረት አድርገው መቧደናቸውን ያስታውሳል። እሷ ማናት፡ ዘቢብ ካቩማ ለዩኤን እሠራለሁ ብዬ አስቤ አላውቅም አራት ቀንና ሌሊት ከተጓዙ በኋላ መኪናዋ ላይ የተሳፈሩ ስደተኞች ጥል እየተካረረ መጣ። ሰዎች ከፍርሃትና ከተስፋ መቁረጥ የተነሳ የራሳቸውን ምግብና ውሃ እየደበቁ የሌላ ግለሰብ ስንቅ መስረቅ በመጀመራቸው አለመግባባቱ ወደ ድብድብ አደገ። መጎሻሸሙ፣ ቡጢውና ጉልበት መፈታተሹ እርስ በእርስ ብቻ ሳይሆን ወደ ሰሃራ ይዟቸው እየሄደ ከነበረው ግለሰብ ጋርም ሆነ። ጉዞ በጀመሩ በሰባተኛው ቀን ሱዳን፣ ግብጽንና ሊቢያን የሚያዋስነው ድንበር ላይ ስደተኞችን የሚለዋወጡበት ስፍራ ደረሱ። ስፍራው ላይ ሲደርሱ ግን እድል ከእነርሱ ጋር አልነበረችም። ከሊቢያ ሊቀበላቸው የመጣው ግለሰብ በታጣቂዎች ተይዞ ጠበቃቸው። ቀደም ብሎ እኔ ስለተያዝኩ አታምጣቸው ብሎ ይዞን እየሄደ ለነበረው ሰው መልዕክት ልኮለት ነበር የሚለው ሃሩን እርሱ ግን ከእኛ ጋር ተጣልቶ ስለነበር የራሳቸው ጉዳይ በሚል ስሜት ነበር ይዞን ሄደ ይላል። በሦስቱ ሃገራት ድንበር ላይ ሲደርሱ ወደ ስምንት የሚሆኑ መኪኖች ከብበዋቸው፣ መሳሪያ ከደቀኑባቸው በኋላ እነ ሃሩንንም ሆነ ከሱዳን ይዟቸው የሄደውንና ከሊቢያ ሊወስዳቸው የመጣውንም አንድ ላይ ወሰዷቸው። መሳሪያ መታጠቃቸውን እንጂ ምን እንደሆኑና ማን እንደሆኑ የሚያውቀው ነገር እንደሌለ የሚገልፀው ሃሩን ከበርሃ ወጥተው እንደከበቧቸው ያስታውሳል። እነዚህ ታጣቂዎች ያለምንም ምግብና ውሃ ሁለት ቀንና ሌሊት ይዘውን ከሄዱ በኋላ የማይታወቅ በረሃ ውስጥ አወረዱን። ለአንድ ሰው ሺህ ዶላር ካልከፈልን ከዚያ መንቀሳቀስ እንደማንችል ነገሩን። እኛ ብቻ ሳንሆን ከሊቢያ ሊወስደን የመጣው ሰውዬም ያለንበትን ስፍራ አያውቀውም ነበር። ኢትዮጵያ ወይስ ናይጄሪያ የትዊተር አለቃ የፈጠረው ክርክር ከዚህ በኋላ ሺህ ዶላሩን መክፈል የምትችሉ መኪና ላይ እንዲወጡ የማይችሉ ግን እዚያው እንዲቆዩ ተነገራቸው። ኤርትራዊያንና ሱዳኖች እንከፍላለን ብለው መኪና ላይ መውጣታቸውን የሚናገረው ሃሩን፤ ሁሉም ኢትዮጵያዊያኖች ግን ገንዘብ ለመክፈል እንደማይችሉ ተናግረው እዚያወቅ ለመቆየት መወሰናቸውን ያስታውሳል። በኋላም ኤርትራዊያኑንና ሱዳናዊያኑን ይዞ የሄደው መኪና መንገድ ከጀመረ በኋላ ተመልሶ በመምጣት በመሳሪያና በዱላ እያስፈራሩ መኪናው ላይ እንዳሳፈሯቸውና እንደወሰዷቸው ይናገራል። ሃሩን አህመድ የተጓዘበት መስመር ጉዞ ወደ ሊቢያ ሦስት ቀን ያለማቋረጥ ከተጓዙ በኋላ አንድ ቦታ መድረሳቸውንወ የሚናገረው ሃሩን፤ ስፍራው ሰዎች እንደ ባሪያ የሚሸጡበት መሆኑን ያስታውሳል። ስፍራው ላይ ከደረሱ አራት ወርና ከዚያ በላይ የሆናቸው፣ ልብሳቸው ላያቸው ላይ የነተበ፣ ሰው የማይመስሉ ከ በላይ ስደተኞች፣ አብዛኛዎቹ ሶማሊያዊያን መሆናቸው ማግኘታቸውን ያስታውሳል። እዚያ እንቆያለን ብለን ስላላሰብን የቀረችንን ስንቅም ውሃም ሰጠናቸው። እነሃሩን እንዳሰቡት ሳይሆን የስደተኛ አቀባባዮቹ እንደፈቀዱት ሆነ። ትልቅ ዋጋ ተከፍሎበት ዋጋ ያላገኘሁበት ቢኖር ትምህርት ነው ይዘዋቸው የመጡ ታጣቂዎች አራት አራት ሺህ ዶላር ካልከፈሉ በስፍራው እንዳቆይዋቸው እና ከሰውነት ጎዳና የወጡ ስደተኞች እንደሚሆኑ በመንገር አስፈራሯቸው። ማስፈራራቱ ከስፍራው ባለመንቀሳቀስ ጸና። ቀና ቢሉ ጠራራ ጸሀይ፣ ዞር ቢሉ ጎስቋላ ስደተኛ፣ ድካም ያዛለው፣ ውሃ ጥም ያቃጠለው የሀገር ልጅ በሚያዩበት ምድረ በዳ መጋዘን ተገኝቶ እዚያ ውስጥ ታሰሩ። አሳሪዎቻቸው እጃቸው የተፈታ ቀን፣ በቀን አንዴ ሆዳቸው የጨከነ እለት ደግሞ፣ በሁለት ቀን አንዴ ምግብ ይሰጧቸዋል። ሌሊት ሌሊት ደግሞ ይደበድቡናል የሚለው ሃሩን በአጠቃላይ ለአራት ወራት በዚያ ስፍራ መታሰራቸውን ይናገራል። አራት ወር ሲሞላቸው ልብሳቸው አልቆ፣ አብረዋቸው ከተሰደዱት ጋር ተረሳስተው፣ የት ለመሄድ እንደሚፈልጉ ዘንግተው እስትንፋሳቸውን ማቆየት ብቻ የህይወት ግባቸው ሆኖ እንደነበር ይናገራል። በዚህ ስፍራ በረሃውንና የደረሰባቸውን ድብደባና ስቃይ መቋቋም ያቃታቸው አንድ ኢትዮጵያዊ ጓደኛችንን ጨምሮ አስራ ሁለት ሶማሌያዊያንን ቀብረናል። በዚህ ሁሉ ስቃይ ውስጥ ይላል ሃሩን የመጡበት ሃገርን፣ ብሔራቸውንና ዘራቸውን ዘንግተው ሰው መሆናቸውን ብቻ ያስታውሱ እንደነበር የሚናገረው ሃሩን በመካከላቸው መደጋገፉና መረዳዳቱ ጠንካራ እንደነበር ይናገራል። የመረዳዳታቸውን ጣሪያ ሲያስታውስ ከመካከላቸው አንድ ሰው በውሃ ጥም ሞቶ ለሌሎች ከንፈራቸውን የሚያረጥቡበት ውሃ እንዲያገኙ ለማድረግ እስከመፍቀድ እንደነበር ይገልጻል። የኩላሊት ገበያ አንድ ቀን ይላል ሃሩን ኩላሊት የሚገዙ ሰዎች ወደ ታሰርንበት መጋዘን መጡ የሚገዛው ግለሰብ ግን የበረሃው ሃሩርና ውሃ ጥም ያከሰላቸውን ስደተኞች ተመልክቶ፣ እነዚህማ ለራሳቸውም ደክመዋል ምንስ ኩላሊት አላቸው በማለት ትቷቸው መሄዱን ይጠቅሳል። ስደተኞቹ ኩላሊታቸው ተሸጦ ዋጋ እንደማያወጡ፣ ቤተሰቦቻቸው ገንዘብ ልከውም እንደማይከፈላቸው የተረዱት ደላሎች ለሌላ ነጋዴ አሳልፈው ሸጧቸው። የገዛቸው ሰው ለእያንዳንዳቸው ሦስት ሺህ ዶላር እንዳወጣና ገንዘቡን እንዲከፈለው እንደሚፈልግ ቀጭን ማሳሰቢያ አዘል ማስፈራሪያ ተናገረ። በበረሃው የተዳከሙ፣ በተስፋ መቁረጥ የሚዋልሉ ስደተኞች ከዚህ ብቻ አውጣን እንጂ እንከፍልሃለን በሚል ተስማምተው አብረውት ሄዱ። ከዚህ ሰውዬ ጋር ቀንና ሌሊት ለአራት ቀን ከተጓዙ በኋላ ሳባ የምትባል የሊቢያ ከተማ ላይ ደረሱ። የሴቶች ዘብ የነበሩት ዶ ር ቦጋለች ገብሬ ይዘዋቸው የሚሄዱት ሰዎች የደረሱበትን የሚያውቁት ካርታ ዘርግተው፣ የፀሐይን አቅጣጫ አይተው ወይንም ነዋሪውን ጠይቀው አይደለም። አሸዋውን ዘገን አድርገው ብቻ የት ሃገር እንደደረሱ ይናገራሉ። ዓይን ማየት የቻለበት ርቀት ሁሉ አሸዋ ለሆነበት ስደተኛ፣ የአንዱ ሀገር አሸዋ ከሌላኛው ሀገር የሚለይበት መልክ አይገለጥለትም። ለሀገሬው ግን አቅጣጫ ጠቋሚ፣ ሀገር አመላካች ነው። እነ ሃሩንን ሳባ የወሰዳቸው ግለሰብ በከተማዋ እንደ ሃገረ ገዢ እንደሚታይ ግን ማወቅ ችለዋል። የተጠየቀውን ገንዘብ የከፈለ ስደተኛ በሳባ ውስጥ እንዳሻው የመውጣት የመግባት ነጻነትን ይጎናጸፋል። እኛ ግን ገንዘብ ስላልነበረን ይላል ሃሩን ትልቅ መጋዘን ውስጥ አስገባን። ገንዘብ የሌላቸውና መጋዘን ውስጥ የታጎሩት እነሃሩን የተፈጠሩበትን ቀን እስኪረግሙ ድረስ ድብደባ ይደርስባቸው ጀመር። ወገባችንን በብረት፣ እጆቻችንን ወደኋላ አስረው እየደበደቡ ውሃ የተሞላ በርሜል ውስጥ በጭንቅላታችን ዘቅዝቀው ይከቱንና ከዚያ አውጥተው ቤተሰቦቻችን ጋር ደውለን ገንዘብ እንድናስልክ ስልክ ይሰጡናል ሲል ያስታውሰዋል። በዚህ ሁኔታ ቤተሰቦቻችን ጋር ደውለን ያላቸውንም ሸጠው ተበድረውም ሆነ ተለቅተው ገንዘብ ይልኩልን ነበር። ቀድሞ ገንዘብ ከቤተሰቡ የሚላክለት ሰው ቀደሞ ከዚያ አሰቃቂ እስር ቤት የሚወጣ ሲሆን ቀሪው ግን እስኪላክለት ድረስ እዚያው ይቆያል። ሃሩን በዚህ ስፍራ አንድ ወር ቆየ። ከእርሱ ቀድመው የወጡ የበረሃ ጓደኞቹ፣ እንዲሁም ቤተሰቡ ያላቸውን ሳንቲም በማዋጣት ሦስት ሺህ ዶላር መክፈሉን ይናገራል። እዚህም በገንዘብም ሆነ በሌሎች ጉዳዮች ሲተጋገዙ፣ ብቸኛው ግምት ውስጥ የሚያስገቡት አብረው የሚያሳልፉትን የሰቆቃ ጊዜያት፣ ሰው መሆናቸውን እንጂ መነሻቸው ላይ የነበረው የአንድ አገር ልጅነት እንዳልነበር ይናገራል። ኢትዮጵያ የጥላቻ ንግግርና የሐሰተኛ መረጃን የተመለከተ አዋጅን ልታጸድቅ ነው መጀመሪያ ላይ በቋንቋ በብሔር በሃይማኖትና በዘር ስንጣላ የነበርን ሰዎች ከዚያ ሁሉ ስቃይ ሁሉ በኋላ የቀረልን ሰው መሆናችን ብቻ ነበር። ሰው መሆን ከሁሉ ነገር በፊት የሚቀድም መሆኑ የገባኝ ያኔ ነበር በማለትም ከእስር ቤቱ ቀድመው የወጡ እንዴት እንደረዷቸው ያስረዳል። ሳባ ከነበረው እስር ቤት ቀድማቸው የወጣች ጽጌ የምትባል ኤርትራዊት ለቤተሰቦቻቸው በመደወል ገንዘብ እንዲላክላቸውና የጎደላቸውን ከሌሎች በማሟላት እንዲወጡ እንዳገዘቻቸው ይመሰክራል። በዚህ መደጋገፍና መረዳዳት መካከል አዲስ አሸናፊ ከምትባል ልጅ ጋር ፍቅር ጀመረ። እርሱ የእስልምና ዕምነት ተከታይ ሲሆን እርሷ ደግሞ ክርስትያን ነበረች። ነገር ግን እዚያ በነበረው እንግልትና ስቃይ ሁለቱ ወጣቶች በፍቅር ተጋመዱ። እስር ቤት ውስጥ በጭካኔና በኃይል የሚደበደቡት ወንዶች ስለነበሩ ለእርሷ የተላከላትን ገንዘብ ለእኔ ከፍላ እኔ እንድወጣ አደረገች በማለት የሁለቱ የፍቅር ታሪክ በራሱ በተቃርኖ ውስጥ ሲጋጩ ለሚኖሩ ሌሎች ትምህርት እንደሚሆን ያነሳል። ትሪፖሊ ሃሮን ፍቅረኛውና ቤተሰቦቹ በማዋጣት በከፈሉት ገንዘብ ሳባ ከሚገኘው እስር ቤት ከወጣ በኋላ ወደ ትሪፖሊ ጎዞ ጀመረ። ነገር ግን በክፉ አጋጣሚ ትሪፖሊ ከመድረሱ በፊት በሌሎች ሰዎች እጅ ወድቆ እስር ቤት ተወረወረ። እነዚህ አሳሪዎቹ በቀን አንዴ ደረቅ ዳቦ እየሰጧቸው፣ ሌሊት ሌሊት ደግሞ ገንዘብ አምጡ እያሉ እደበድቧቸው እንደነበር ይናገራል። ፍቅረኛውን አዲስን ጨምሮ ሌሎች ከሱዳን አብረው የተነሱና ሳባ አብረው ታስረው የነበሩ ስደተኞችም በሂደት ተቀላቀሏቸው። ከ ቀናት እስር በኋላ እንደ ከዚህ ቀደሙ ተረዳድተው ስድስት ስድስት መቶ ዶላር በመክፈል ተለቀቁ። ከዚህ በመቀጠል ያመሩት በቀጥታ ትሪፖሊ ክሪሚያ የምትባል ስደተኞች በብዛት የሚያርፉባት መንደር ነበር። ሶስት ጊዜ ለተለያዩ ነጋዴዎች ተሽጫለሁ ክሪሚያ ወደ አውሮፓ በባህር ለማቋረጥ ወረፋ የሚጠብቁና ከባህር ላይ ተይዘው የተመለሱ ስደተኞች በብዛት ያሉባት መንደር ናት። ሃሩንና አዲስ ያገኙትን እየሰሩ ለእለት ጉርስ ለነገ ደግሞ ስንቅ እያኖሩ ከሌሎች መንገድ ላይ ከተዋወቋቸው ሰዎች ጋር ቤት ተከራይተው ለሰባት ወራት በክሪሚያ ኖሩ። በሰባት ወር ቆይታቸው በመንደሯ በየዕለቱ የሚሰማው ወሬ የባህር ተሻጋሪ ስደተኞች ሞት አልያም በሰላም ወደ አውሮፓ መሻገር ነበር። ይህንን በየማለዳው የሚሰሙት ሃሩንና አዲስ በየሃይማኖታቸው በሰላም የሜዴትራኒያንን ባህር ተሻግረው የሚያልሙት አውሮፓ እንዲደርሱ ይጸልዩ ነበር። በወቅቱ ይላል ሃሩን አንዳችን የሌላኛችንን ሃይማኖት ለማስቀየር ወይም እንደ ክፍተት በመቁጠር ተነጋግረን አናውቅም። ክሪሚያ የከተመ ስደተኛ ሰርቶ ያገኘውን አጠራቅሞ፣ ቤተሰብ የላከለትን ቋጥሮ ሲሞላለት፣ በጀልባ ተሳፍሮ ወደ አውሮፓ ጉዞ ይጀምራል። ያንን ሁሉ በረሃ አቋርጠው፣ ስቃይና እንግልቱን ችለው ክሪሚያ የደረሱ መጥፎ ዕጣ ከገጠማቸው ሜዴትራኒያን ባህር ውስጥ ሰጥመው ይሞታሉ። ሃሮንም በዚህ ሁኔታ ብዙ ሰው ነው ያለቀው በማለት ባህር ውስጥ ሰጥመው የሞቱ በርካታ ጓደኞቻችን አሉ ይላል። መጀመሪያ በባህር ወደ ጣሊያን ከዚያም ወደ ጀርመን ያቀናውና አሁን እዚያ የሚኖረው ሃሩን፤ በሃይማኖት በብሔር ወገን ለይቶ መጠላላትና መጋደል አስፈላጊ እንዳልሆነ በመግለጽ የእርሱ የስደትና የመከራ ሕይወት ይህንን እንዳስተማረው ይገልጻል። ሃሩንና አዲስ በስደት እያሉ አንድ ልጅ የወለዱ ሲሆን ጀርመን ከገቡ በኋላ ሁለቱም በየሃይማኖታቸው ለመቆየት በመወሰናቸው፣ ልጃቸውን በጋራ ለማሳደግ ተስማምተው ለየብቻቸው እየኖሩ ነው። ከዚህ ዜና በተጨማሪ
ብዙ ነገር አንድ የሆነባት ሃገር ኤርትራ
ጥቅምት ይህንን ለማጋራት በ ትዊተር ይህንን ለማጋራት በ ዋትስአፕ ከጥቂት ሳምንታት በፊት የቢቢሲ ጋዜጠኞች በኤርትራ አዘጋጅነት ሲካሄድ የነበረውን ከ ዓመት በታች የሴካፋ ውድድርን እንድንዘግብ ፍቃድ ተሰጥቶን ወደ ኤርትራ እቅንተን ነበር። በኤርትራ በነበርን ቆይታ ያየነውን እና የሰማነውን በሦስት ክፍሎች አሰናድተናል። ሁለተኛውን ክፍል እንደሚከተለው ቀርቧል። የመጀመሪያውን ክፍል ለማንበብ ከታች ያለውን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ። ማስታወሻ ፡ በኤርትራ በነበረን ቆይታ የዘገባ ርዕሶቻችን እና እንቅስቃሴዎቻችን የተገደቡ ነበሩ። በጽሁፉ ውስጥ የተጠቀሱት ዓመታት እንደ ጎርጎሪሳውያኑ አቆጣጠር ነው። ብዙ ነገር አንድ የሆነባት ሃገር ኤርትራ በኤርትራ አንድ ብቻ የሆኑ ብዙ ነገሮች አሉ። አንድ አይነት ቢራ፣ አንድ አውሮፕላን፣ አንድ ሥርዓት ያለው የባንክ አገልግሎት፣ እንድ የቴሌኮም አገልግሎት አቅራቢ፣ አንድ የፖለቲካ ፓርቲ፣ አንድ የቴሌቪዝን ጣቢያ ሜሎቲ ወይም አሥመራ ቢራ ከእአአ ጀምሮ በኤርትራ ሲጠመቅ ቆይቷል። አንድ ቢራ ሜሎቲ ወይም አሥመራ ቢራ ከ ጀምሮ በኤርትራ ሲጠመቅ ቆይቷል። ይህ ለኤርትራ ብቸኛ የሆነው ቢራ በበርካቶች ዘንድ ትዝታ እና ተወዳጅነትን ያተረፈ ነው። የቢራ ፈላጊውን እና የአቅርቦት መጠኑ ተመጣጣኝ ስላልነበረ ከቅርብ ዓመታት በፊት አንድ ሰው ሁለት ቢራ ብቻ ገዝቶ እንዲጠጣ ነበር የሚፈቀድለት። አሥመራ፡ የአዛውንቶች ከተማ ከሁለት በላይ ደጋግሞ መጠጣት የፈለገ፤ ቢራ የማይጠጣ ሰው ወደ መጠጥ ቤት ይዞ በመሄድ የዚያን ሰው ኮታ ይጠጣ እንደነበር ሰምተናል። አሁን ላይ በቢራ ፋብሪካው በተካሄደ ለውጥ የቢራ አቅርቦቱን በቀላሉ ማግኘት ይቻላል። ከኢትዮጵያ ጋር የሚያዋስኑ የድንበር በሮች በተከፈቱ ጊዜ የኢትዮጵያ ቢራ ምርቶች አሥመራን አጥለቅልቀዋት እንደነበረ በዚህም የአንድ ሜሎቲ ቢራ ዋጋ ከ ናቅፋ ከ እንደወረደ ነዋሪዎች ነግረውናል። ናቅፋ አንድ አይነት የባንክ ሥ ርዓት በኤርትራ የሚገኙት ባንኮች በመንግሥት ባለቤትነት የሚተዳደሩ ናቸው። በቁጥር ሦስት የሆኑት የመንግሥት ባንኮች በአድናቆት አፍ የሚያስከፍት ሕግ አላቸው። ይህም የባንኩ ደንበኞች በባንኩ ካላቸው ገንዘብ በወር ከ ሺህ ናቅፋ በላይ እንዲያወጡ አይፈቅድም። መኪና ለመግዛት ሺህ ናቅፋ በጥሬ ገንዘብ ያስፈለገው ወጣት ይህን ያክል ገንዘብ በጥሬ ለማግኘት ወር እየጠበቀ ናቅፋ ሲያወጣ አንድ ዓመት እንደስቆጠረ ነግሮናል። ቀነኒሳ ከሞት እንደመነሳት ነው ባለው ሁኔታ ማራቶንን አሸነፈ መንግሥት ይህን መሰል ውሳኔ ማስተላለፍ ለምን እንደፈለገ የጠየቅናቸው ነዋሪዎች፤ ሁለት የተለያየ አተያዮች አሏቸው። የመጀመሪያው መንግሥት ከዚህ ውሳኔ የደረሰው የዋጋ ግሽበትን ለመቆጣጠር እና የህዝቡን የቁጠባ ባህል ለማዳበር ነው ሲሉ ሌሎች ደግሞ መንግሥት ምንም አይነት የንግድ እንቅስቃሴ እንዲኖር ስለማይፈልግ የገንዘብ ዝውውር እንዳይኖር አድርጓል ይላሉ። ኤቲኤም ገንዘብ መክፈያ ማሽን በኤርትራ የለም። አሥመራ በነበረን ቆይታ ያገኘነው ወጣት፤ ድንበር ክፍት በተደረገ ጊዜ ወደ መቀሌ አቅንቶ በነበረበት ወቅት ሰዎች ከማሽን ብዙ ገንዘብ ወጪ ሲያደርጉ ማየቱ በእጅጉ እንዳስደነቀው አጫውቶናል። ኤቲኤም በሌለባት ሃገረ ኤርትራ ሌላው ያስተዋልነው፤ በምግብ እና መጠጦች ላይ ተጨማሪ የእሴት ታክስ አለመጣሉ ነው። ሲም ካርድ በቀላሉ ማግኘት ስለማይቻል አብዛኛው ህብረተሰብ የህዝብ ስልኮችን ይጠቀማል። ቀኝ አሥመራ ከተማ ልብስ መሸጫ ሱቅ ውስጥ አገልግሎት እየሰጠ የሚገኝ ስልክ። አንድ የቴሌኮም ኩባንያ ልክ እንደ ኢትዮጵያ ሁሉ በኤርትራ ያለው የቴሌኮም አገልግሎት አቅራቢ ድርጅት በመንግሥት ባለቤትነት የሚተዳደር ሲሆን ኤሪቴል ይባላል። በኤርትራ የቴሌኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት ደካማ ነው። ሲም ካርድ ማግኘት እጅግ አዳጋች ነው። ጎብኚዎች ሲም ካርድ ማግኘት አይችሉም። ነዋሪዎችም ቢሆኑ ሲም ካርድ ማውጣት ቢፈልጉ በየደረጃው የሚገኙ የመንግሥት መስሪያ ቤቶች ይሁንታንና ፈቃድን ሲያገኙ ነው የሲም ካርድ ባለቤት የሚሆኑት። ብሎ የሚጀምረው የኤርትራ የሞባይል ስልክ ቁጥር ባለ አሃዝ ብቻ ነው። ለምሳሌ የኤርትራ ሞባይል ቁጥር ይህን ሊመስል ይችላል ። አብዛኛው ማህብረሰብ በፈቀደው ወቅት የሲም ካርድ ባለቤት መሆን ስለማይችል አብዝቶ የሚጠቀመው የመንገድ ላይ የሕዝብ ስልኮችን ነው። የተለያዩ ዋጋ ያላቸውን ካርዶች ከኤሪቴል መደብሮች ብቻ በመግዛት ወደ ሃገር ውስጥ እና ከሃገር ውጪ መደወል ይቻላል። በኢትዮ ኤርትራ ድንበር ንግድ ተጧጡፏል ሲም ካርድ ቢገኝም፤ የሞባይል ዳታ የለም። በስልክዎ ላይ ኢንተርኔት መጠቀም የሚችሉት የዋይፋይ አገልግሎት በሚገኙባቸው ስፍራዎች ብቻ ነው። ዋይፋይ ቢገኝም፤ የኢንተርኔት ፍጥነት እጅግ ቀሰስተኛ ነው። ማህበራዊ ሚዲያዎችን ለመቃኘት ደግሞ ቪፒኤን መጠቀም ግድ ይላል። ዓለም አቀፍ የቴሌኮሚዩኒኬሽን ሕብረት ሪፖርት እንደሚጠቁመው፤ ከኤርትራ ሕዝብ ውስጥ የኢንተርኔት ተጠቃሚው ብዛት ከ በመቶ በታች ነው በማለት አገልግሎቱ ምን ያህል ዝቅተኛ መሆኑን ይጠቁማል። አንድ የቴሌቪዥን ጣቢያ በመንግሥት ባለቤትነት የተያዘው ኤሪ ቲቪ ከኤርትራ ሆኖ በብቸኝነት የሚያሰራጭ የቴሌቪዥን ጣቢያ ነው። በቅርቡ ኤርትራ በዓለማችን ቁጥር አንድ የመገናኛ ብዙሃን አፈና የሚፈጸምባት ሃገር ናት ተብለ ተፈርጃ ነበር። የጋዜጠኞችን እስር፣ ጋዜጠኞችን ለመሰለል የሚፈቅዱ ሕጎችን እንዲሁም በኢንተርኔት እና በማህበራዊ ሚዲያ አገልግሎት ላይ የሚጣለውን ገደብ ከግምት ውስጥ በማስገባት የጋዜጠኞች መብት ተሟጋቹ ሲፒጄ ኤርትራ ከሰሜን ኮሪያ በላይ ቁጥር አንድ አፈና የሚፈጸምባት ሃገር ናት ይላል። ኤርትራ በምሽት ድንበር ማቋረጥን ከለከለች ከኤርትራ በመቀጠል ሰሜን ኮሪያ፣ ቱርኬሚስታን፣ ሳዑዲ አረቢያ፣ ቻይና፣ ቬትናም፣ ኢራን፣ ኢኳቶሪያል ጊኒ፣ ቤላሩስ እና ኩባ ከ ኛ እስከ ኛ ደረጃን ይዘው ተቀምጠዋል። በኤርትራ መገናኛ ብዙሃን የመንግሥት ልሳን ሆነው ነው የሚያገለግሉት የሚለው ሲፒጄ፤ ገለልተኛ የሆኑ ጋዜጠኞች ወደ ሃገራቱ ሲያቀኑም ቅርብ ክትትል ይደረግባቸዋል። አንድ የፖለቲካ ፓርቲ ሃገሪቷን የሚያስተዳድረው እና በፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የሚመራው የሕዝባዊ ግንባር ለዴሞክራሲና ፍትህ ፓርቲ ሕግዴፍ በሃገሪቱ የሚንቀሳቀሰው ብቸኛው የፖለቲካ ፓርቲ ነው። ሦስት አስርት ዓመታትን ሊደፍን የተቃረበው የፕሬዝዳንት ኢሳያስ አስተዳደር ዘመን በኤርትራ የሚንቀሳቀስ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ ታይቶ አታውቅም። ይህ ብቻም አይደለም ሥራ ላይ ውሎ የሚያውቅ ሕገ መንግሥት የለም። ምርጫ ተካሂዶ አያውቅም። ወደፊትም ስልጣን ላይ የሚገኘው መንግሥት ምርጫ የማካሄድ ሃሳብ የለውም ሲሉ ተቺዎች ይናገራሉ። የኃይማኖት ነጻነት በኤርትራ ፍቃድ ያላቸው እና መንግሥት እውቅና የሰጣቸው ኃይማኖቶች አራት ብቻ ናቸው። የኦርቶዶክስ ክርስትና፣ የሱኒ እስልምና፣ የሮማ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን እና የሉተራን ወንጌላዊ ቤተ ክርስቲያን ናቸው። ኤርትራ ፖለቲከኞችን እና ጋዜጠኞችን እንድትለቅ ተጠየቀ ሌሎች የእምነት ተቋማት እንደ ሕገ ወጥ ነው የሚቆጠሩት። መንግሥት የተቀሩትን የእምነት ተቋማትን የውጪ ሃገራት አጀንዳ ማስፈጸሚያ መሳሪያዎች ናቸው ሲል ይገልጻቸዋል። የአሜሪካ መንግሥት ዓለም አቀፍ የኃይማኖት ነጻነት ኮሚሽን የ ሪፖርት እንደሚጠቁመው ከሆነ፤ ዛሬ ላይ በመቶዎች የሚቆጠሩ ኤርትራዊያን በእምነታቸው ምክንያት ለእስር እንደተዳረጉ ናቸው። የጆሆቫ ምስክሮች በእምነት ተከታዮች በኃይማኖታቸው ምክንያት በብሔራዊ አገልግሎት ላይ ለመሳተፍ ፍቃደኛ ባለመሆናቸው ዜግነት ይከለከላሉ፣ መታወቂያ ደብተር ማግኘት አይችሉም። የ ድ ንበር በሮች መከፈት ሁለቱን ሃገራት የሚያገናኙ አራት የድንበር በሮች ይገኛሉ። አራቱ የድንበር በሮች ዛላምበሳ ሰርሃ፣ ራማ ክሳድ ዒቃ፣ ሁመራ ኦማሃጀር እና ቡሬ ደባይ ሲማ ናቸው። በሁለቱ ሃገራት የሰላም ስምምነት ከተደረሰ በኋላ በተለያዩ ጊዜያት ክፍት ተደርገው የነበሩት አራቱ የድንበር በሮች አሁን ላይ ሁሉም ተዘግተዋል። ለድንበር በሮቹ መዘጋት በሁለቱም መንግሥታት የተሰጠ ምክንያት ባይኖርም ይፋዊ ያልሆኑ መረጃዎች የድንበር በሮቹ የተዘጉት፤ የቪዛ እና የቀረጥ ጉዳዮችን መልክ ማስያዝ በማስፈለጉ እንደሆነ ይጠቁማሉ። ዛላምበሳ ሰርሃ፣ ራማ ክሳድ ዒቃ እና ለሱዳን ቅርብ የሆነው ሁመራ ኦማሃጀር በትግራይ ክልል በኩል ኢትዮጵያን ከኤርትራ ጋር የሚያገናኙ የድንበር በሮች ሲሆኑ፣ ቡሬ ደባይ ሲማ ደግሞ በአፋር ክልል በኩል ኢትዮጵያን ከኤርትራ የሚገናኝ የደንበር በር ነው። የድንበር በሮቹ ክፍት ተደርገው በነበረበት ወቅት ከፍተኛ የሆነ የንግድ እንቅስቃሴ ድንበር እቅራቢያ ተስተውሎ ነበር። በአሥመራም የድንበር በሩ መከፈት በተለያዩ ሸቀጦች ላይ የዋጋ ለውጥ አምጥቶ እንደነበር በቆይታችን ሰምተናል። ለምሳሌ ድንበር ከመከፈቱ በፊት እስከ ሺህ ናቅፋ ይሸጥ የነበረው አንድ ኩንታል ጤፍ ድንበሩ ሲከፈት ዋጋው በሚያስደንቅ ሁኔታ አሽቆልቁሎ እንደነበር ነዋሪዎች ይናገራሉ። በአሁኑ ወቅት በድንበር በሮቹ ላይ የተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ በመገደቡ የአንድ ኩንታል ጤፍ አሥመራ ውስጥ የተጋነነ ባይሆንም ጭማሪ አሳይቷል። ቢቢሲ ማስተባበያ
አንበሶችን ያባረረው ወጣት ምን አጋጠመው
ጁላይ አጭር የምስል መግለጫ ሪቻርድ ቱሬሬ እንስሳቱን ከእንበሳ ለመከላከል የሚያስችል ዘዴ ሲያፈልቅ ገና ታዳጊ ነበር። አንበሳ እወዳለሁ ፤ የማልወድበት ምክንያት አይታየኝም ላሞቼ ደህና ከሆኑና ከተጠበቁልኝ ከአንሰቦቹ ጋር ያለምንም ችግር መኖር እንችላለን። ይህን ከአንድ የኬንያ ማሳይ እረኛ መስማት ያልተመለደ ነገር ነው። ዋነኛው ሥራቸው በማናቸውም መንገድ ቢሆን ላሞቻቸውን ከጥቃት መከላከል ነው። የ ዓመቱ ሪቻርድ ቱሬሬ ግን እንደማንኛውም የማሳይ እረኛ አይደለም። በወቅቱ ቤተሰቦቹ በአንድ ሳምንት ከ ያላነሱ ከብቶቻቸው በአንበሶች ተበልተውባቸው ስለነበር የ ዓመት ልጅ እያለ በፀሐይ ኃይል የሚሰራ አንበሶችን ከከብቶች በረት የሚያባርር መብራት ፈጠረ። የዕለት ከዕለት ኑሮን የሚለውጡ ፈጠራዎች እያንዳንዱ ላም እስከ ዶላር ዋጋ ያሚያወጣ በመሆኑ ቤተሰቦቹ ኪሳራውን መቋቋም ተስኗቸው ነበር። በከብቶቻችን ላይ የሚፈጸሙት ጥቃቶች መጠነ ሰፊና በየቀኑ የሚያጋጥሙን ነበሩ ይላሉ የሪቻርድ እናት ቬሮኒካ። ከመብራቶቹ በኋላ ግን ከአንበሶቹ ጋር ምንም ችግር አልገጠመንም። ሪቻርድ ይህንን ፈጠራውን ስኬታማ ለማድረግ የተወሰነ ጊዜ ፈጅቶበታል። በመጀመሪያ ሰው የሚመስሉ ቅርጾችን በአካባቢው ቢያቆምም አንበሶቹ ከቁብ ሳይቆጥሩት ቀሩ። በመቀጠል ደግሞ አንበሶቹ የእርባታውን የውስጥ ክፍል ማየት እንዳይችሉ ጥቁር መከለያ ቢሰራም የላሞቹን ጠረን ከማሽተት አላገዳቸውም። አንድ ቀን ግን የእጅ ባትሪ ይዞ በተንቀሳቀሰበት ምሽት አንበሶቹ ለመጀመሪያ ጊዜ ለማጥቃት ሳይመጡ ቀሩ። ሪቻርድም የእጅ ባትሪውን የሚንቀሳቀስ በማስመሰል ስላዘጋጀው ሌሊቱን ሙሉ እንቅልፍ አጥቶ ከመጠበቅ የገላገለውን ላየን ላይትስ መብራትን ሰራ። አጭር የምስል መግለጫ አንበሶች በርካታ ከብቶችን ይገድላሉ ራስን ማስተማር ነገሮችን በመሰባበር ነው ስለ ኤሌክትሮኒክስ መማር የጀመርኩት ይላል ሪቻርድ። የእናቴን አዲስ ሬድዮ ሰብሬ በጣም ተናዳ ልትገድለኝ ደርሳ ነበር። በእያንዳንዱ ስሪት ላይ አዳዲስ ማሻሻያዎችን እያደረገ አሁን ላየን ላይትስ በሪቻርድ ማህበረሰብና በሌሎች አካባቢዎች በ መኖሪያዎች ጥቅም ላይ እየዋለ ነው። ሰዎች እንዴት እንደሚሰሩ በውል ስለማያውቁ ብዙ ጊዜ መብራቶቹን ለመጠገን እጥራለሁ ብሏል ሪቻርድ። ራሳቸው ለመጠገን ጥረት ያደርጋሉ፤ ይህን ሳይ አሰራሩን አውቶማቲክ የማድረግ ሃሳብ አመነጨሁ። ላየን ላይትስ ን ለመስራት ዶላር ወይም ፓውንድ ይፈጃል። ብዙ ጊዜ ከዚህ ወጪ ግማሹ መንግሥታዊ ባልሆኑ ግብረሰናይ ድርጅቶች ቀሪው ደግሞ በከብት አርቢዎቹ ይሸፈናል። ይህ ስሪት የተለያዩ የመብራት አማራጮች አሉት። የሪቻርድ የመጨረሻው የተሻሻለ ፈጠራ በደመና ምክንያት የፀሐይ ኃይል አቅም ሲቀንስ ቤት ውስጥ የተሰራ ለቀናት የሚቆይ የነፋስ ማጦዣ አለው። አጭር የምስል መግለጫ ሪቻርድ ብዙ ጊዜ እራሱ እየሄደ መብራቶቹን መጠገን አለበት የላም ባንኮች ሪቻርድ የሚኖርበት ማህበረሰብ የሰዎችና የዱር እንስሳት ግጭት በተደጋጋሚ የሚከሰትበት ነው። በናይሮቢ ብሔራዊ ፓርክና በኪቴንጌላ ከተማ መካከል የሚገኘውን የማህበረሰቡ መሬት ከፓርኩ የዱር እንስሳት የሚለየው አነስተኛ ወንዝ ብቻ ነው። ሁልጊዜ ማታ ማታ የዱር እንስሳትና የሜዳ አህያ ለምለም የግጦሽ መሬት ፍለጋ መሬታቸውን ያቋርጣሉ፤ አንበሶችም ወዲያው ይከተላሉ። አንበሶች ትልቅ ችግር ናቸው። ለእነርሱ ላሞችና በጎችን መግደል በጣም ቀላል ነው፤ በተለይ ደግሞ በማታ ይላሉ የማሳይ ማህበረሰብ ሰባኪና አርብቶ አደሩ ሬቨረንድ ካልቪን ታፓያ። ሆኖም ላሞችና በጎች ለእኛ ባንኮቻችን ናቸው፤ ገንዘባችንን የምናከማቸው እነርሱ ጋር ነው። ሪቻርድ እስካሁን ከመንግሥት ምንም ዓይነት የገንዘብ ድጋፍ ባያገኝም የእርሱ ፕሮጀክት የሀገሪቱን ብሄራዊ ፓርኮች ለሚያስተዳደረው የኬንያ የዱር እንስሳት አገልግሎት እገዛ እያደረገ እንደሆነ ያስባል። ድርጅቱ እንደሚለው ላለፉት አስር ዓመታት ኬንያ በየዓመቱ አንበሶችን እያጣች ሲሆን አሁን በዱር የሚሆኑት ብቻ ቀርተዋል። ከእነዚህ ሞቶች መካከል የተወሰኑት በሰዎች ምክንያት የተከሰቱ ናቸው። አጭር የምስል መግለጫ የሪቻርድ ቱሬሬ ሃሳብ ዓለምን አዳርሷል በቀል በአውሮፓውያኑ ሁለት ሴት አንበሶችና ሁለት ደቦሎች በኪቴንጋ መኖሪያ ቤቶችን በመውረራቸው ግር ብለው በወጡባቸው ሰዎች ተገድለዋል ። የሪቻርድ ላየን ላይት ልክ እንደርሱ ሁሉ ማህበረሰቡ ከብቶቹን እንዲከላከል እስካስቻለው ድረስ አንበሶችንም ከሰው ጥቃት ይታደጋቸዋል። ከአውሮፓውያኑ ጀምሮ ከበፊቱ ይልቅ ለበቀል ተብለው የሚፈጸሙ የአንበሶች ግድያ ተበራክቷል የዱር እንስሳት ባለሙያዋ የአፍሪካ ጥበቃ ማዕከል ዋና ዳይሬክተር ሉሲ ዋሩይነጊ አንደሚናገሩት። ለማሳዮችም ሆነ ለዱር እንስሳቱ የቀረው መሬት አነስተኛ በመሆኑ ከበፊቱ ይልቅ አሁን ተቀራርበዋል አሁን የተጎዱትን የሚደግፍ አማራጭ ስርዓት አልተዘረጋም፤ ላየን ላይትስ እንደሞከረው በአንበሶችና በሰዎች መካከል የሚፈጠረውን ግጭት ለመከላከል እንኳ ጥረት አልተደረገም። በ የኬንያ መንግሥት በሰዎችና በዱር እንስሳት መካከል በሚፈጠር ግጭት ጉዳት የደረሰባቸውን የካሳ ተጠቃሚ የሚያደርግ ህግ አውጥቶ ነበር። ይሁንና በተግባር የሚካሱት ጥቂት ክስተቶች ብቻ በመሆናቸው አሁንም ጥያቄዎች እንደተከማቹ ናቸው። የእንስሳት፣ የንብረትና የሰብል ካሳን ሙሉ በሙሉ መፈጸም አልቻልንም ምክንያቱም ገና በፓርላማ ያልጸደቁ መመሪያዎች አሉ ብለዋል በናይሮቢ ብሔራዊ ፓርክ ያሉ የማሀበረሰብ ጠባቂ፡፡ አጭር የምስል መግለጫ ሪቻርድ ቤት ውስጥ ያገኛቸው የነበሩ የተወሰኑ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን ይገጣጥም የሪቻርድ የፈጠራ ሥራ በብዙ መልኩ ህይወቱን ቀይሮታል። በናይሮቢ በሚገኝ ስመ ጥር ትምህርት ቤት በነጻ የመማር ዕድልም አስገኝቶለታል። ቻይናዊውን የአሊባባ መስራች ጃክ ማ እንዲያገኝው ተጋብዞ ለክብሩ የተዘጋጀውን ትምህርት ተከታትሏል። እርሱም በኬንያ ስመ ጥር ሆኗል። እስከ አርጀንቲናና ህንድ ድረስ ያሉ ሌሎች ማህበረሰቦችም የእርሱን የፈጠራ ውጤት መሰረት አድርገው የተሰሩ መብራቶችን ይጠቀማሉ። ተጨማሪ ድጋፍ ያስፈልጋል የሪቻርድ ሃሳብ አድማስ ቢሻገርም ከቅርብ ዓመታት ወዲህ አንደ አንድ ወጣት የፈጠራ ሰው የሚደረግለት ድጋፍም ሆነ የ ላየን ላይትስ መብራት አፈጻጸም ቀንሷል። ኬንያ እንደእርሱ ላሉ ወጣት የፈጠራ ሰዎች ከዚህ የተሻለ ድጋፍ ማድረግ እንደምትችል ያምናል። በኬንያ ከእኔም የተሻለ አስደናቂ ሃሳቦች ያሏቸው ብዙ ወጣቶች አሉ፤ የሚፈልጉት ድጋፍ ብቻ ነው ብሏል ሪቻርድ ። ይህ ሃሳብ በጣም አሪፍ ነው፤ የኬንያን ብሎም የዓለምን ማህበረሰብ እንዲያግዝ እናሳድገው የሚላቸው ሰው ይፈልጋሉ። አጭር የምስል መግለጫ ሪቻርድ ቱሬሬ የፍየሎቹን ደህንነት መጠበቅ ይፈልጋል። እንደ ላየን ላይትስ ያሉ ፈጠራዎች ለኬንያ ብቻ አይደለም የሚያስፈልጉት ይላሉ ሉሲ ዋሩይነጊ። የሰብዓዊ ልማት በመላው ዓለም በፍጥነት እያደገ በመሆኑ መንግሥታት ከዱር አራዊት ጋር ግጭት ውስጥ ለመግባት የተገደዱ ማህበረሰቦቻቸውን ማገዝ አለባቸው። መንግሥታት የፈጠራ ሰዎች ተግባር ላይ ሊውሉ የሚችሉ ሃሳቦችን እንዲያካፍሉ መድረኮችን ማመቻቸት አለባቸው ሲሉ ያክላሉ። እነዚህን ሃሳቦች ወደ ንግድ ሥራ በማሳደግ እንደ ሪቻርድ ያሉ ሰዎች ማህበረሰባቸውን በመደጎም እነርሱም ተጠቃሚ እንዲሆኑ። ሪቻርድ እንደ ላዮን ላይትስ ፈጣሪነቱ በአግባቡ ተጠቃሚ ካልሆነባቸው ምክንያቶች መካከል፤ ምንም እንኳ በ ዓመቱ የኬንያ በዕድሜ ትንሹ የፈጠራ ባለቤት ቢሆንም ሃሳቡን በጊዜ አለማስመዝገቡ ነበር። ይህንን ስህተት በድጋሚ እንደማይሰራ ይናገራል፤ አሁንም በርከት ያሉ የፈጠራ ስራዎቹ በሂደት ላይ ናቸው። ይህ ነው የምወደው ሥራ። ቴክኖሎጂ እወዳለሁ፤ እጆቼን መጠቀምና ተግባራዊ ሥራ ላይ መሳተፍም ያስደስተኛል፤ ወደፊት መራመድ እንድችል የሚያግዘኝም ይሄው ነው። የእርሶ መሳሪያ ሚዲያ ፕሌይ ባክን ማጫወት ኣልተቻለም። ይህ የአፍሪካ ዋነኛው የፈጠራ አካባቢ ይሆን ተያያዥ ርዕሶች
ቀነኒሳ ከሞት እንደመነሳት ነው ባለው ሁኔታ ማራቶንን አሸነፈ
ሴፕቴምበር ማጋሪያ ምረጥ ከሩጫው መድረክ ጠፍቶ የከረመው የኦሊምፒክና የዓለም ሻምፒዮኑ ቀነኒሳ በቀለ ዛሬ በተካሄደው የበርሊን ማራቶን ላይ ለውድድሩ ክብረወሰን ሁለት ሰከንዶች የቀሩት ውጤት በማስመዝገብ አሸነፈ። ቀነኒሳ በቀለ ከማራቶን ክብረ ወሰን ቀጥሎ ሁለተኛው ምርጥ ሰዓት ነው በተባለ ሰዓት ከአንድ ደቂቃ ከአርባ አንድ ሰከንድ በማስመዝገብ ነው የበርሊን ማራቶንን ማሸነፍ የቻለው። ቀነኒሳ ከውድድሩ በኋላ ለቢቢሲ እንደተናገረው የዚህን ውድድር ውጤት ከሞት እንደመነሳት ነው የምመለከተው ሲል ጠቅሶ ምክንያቱንም ሲያስረዳ ለረጅም ጊዜ በህመም ምክንያት ከሩጫ ውድድር እርቆ መቆየቱን ይገልጻል። በዶሃ የሴቶች ማራቶን ሦስት ኢትዮጵያውያን ሯጮች አቋርጠው ወጡ በቀጣይ በጤናው ላይ ምንም ችግር ካላጋጠመው የዓለም የማራቶን ክብረ ወሰንን ለመስበር እንደሚሰራ ተናግሯል። ህመም ላይ ስለነበርኩ ክብረወሰኑን ለመስበር የሚያስችል በቂ ልምምድ አላደረግኩም የሚለው ቀነኒሳ ለዚህ ውጤት ያልተቋረጠ የወራት ልምምድ እንደሚያስፈልግ ጠቅሶ በቅርቡ የማራቶን ክብረ ወሰን ወደ ኢትዮጵያ ይመለሳል ሲል ተናግሯል። በሴቶቹ የማራቶን ውድድር አንደኛና ሁለተኛ በመውጣት ኢትዮጵያዊያን ያሸነፉ ሲሆን አንደኛ አሸቴ በከሬ ሁለተኛ ማሬ ዲባባ በመሆን ተከታትለው አሸናፊነቱን ተቆጣጥረውታል። በወለደች በ ደቂቃ ውስጥ የተፈተነችው ተማሪ ስንት አስመዘገበች በወንዶቹ ውድድር በአንደኛነት ካሸነፈው ቀነኒሳ በቀለ በተጨማሪ ኢትዮጵያዊያኑ ብርሐኑ ለገሰ ሁለተኛ እንዲሁም ሲሳይ ለማ ሦስተኛ በመውጣት በሁለቱም ጾታዎች የበርሊን ማራቶን ውድድር በኢትዮጵያዊያን የበላይነት ተጠናቋል። የ ዓመቱ ቀነኒሳ በቀለ ከዚህ በፊት በተካሄዱ የኦሊምፒክና የዓለም ሻምፒዮና ውድድሮች ላይ በተከታታይ የወርቅ ሜዳሊያ ባለቤት ሲሆን ክብረ ወሰኖችንም ያሻሻለ ኮከብ አትሌት ነው። በኬንያዊው ኢሉድ ኪፕቾጌ የተያዘው የማራቶን ክብረወሰን ላይ ለመድረስ ሁለት ሰከንዶችን ዘግይቶ ውድድሩን የጨረሰው ቀነኒሳ አዝናለሁ፤ እድለኛ አልነበርኩም። ነገር ግን ተስፋ አልቆርጥም፤ ክብረ ወሰኑንም ለመስበር እችላለሁ ሲል ከበርሊኑ ድሉ በኋላ ተናግሯል። ተያያዥ ርዕሶች
አሥመራን አየናት፡ ከቅኝ ግዛት በኋላ ባለችበት ያለችው አሥመራ
ሴፕቴምበር ስለ ማጋራት ተጨማሪ ያጋሩ ማጋሪያ ምረጥ ቢቢሲ በኤርትራ አዘጋጅነት ሲካሄድ የነበረውን ከ ዓመት በታች የሴካፋ ውድድርን እንድንዘግብ ፍቃድ ተሰጥቶን ወደ ኤርትራ አቅንተን ነበር። በኤርትራ በነበርን ቆይታ ያየነውን እና የሰማነውን በሦስት ክፍሎች አሰናድተናል። የመጀመሪያው ክፍል እንደሚከተለው ቀርቧል። ማስታወሻ፡ በኤርትራ በነበረን ቆይታ የዘገባ ርዕሶቻችን እና እንቅስቃሴዎቻችን የተገደቡ ነበሩ። በጽሁፉ ውስጥ የተጠቀሱት ዓመታት እንደ ጎሮጎሳውያኑ አቆጣጠር ነው። መግቢያ ከ ዎቹ መጀመሪያ እስከ በነበሩት ዓመታት ቅኝ ገዢዎቹ አውሮፓዊያን፤ አፍሪካን የመቀራመት እቅዳቸውን የወጠኑበት እና ያሳኩበት ዓመታት ነበሩ። ላይ ጣሊያን ኤርትራ የእርሷ ቅኝ ግዛት መሆኗን አወጀች። ዎቹ መጀመሪያ ላይ ሞሶሎኒ ወደ ስልጣን መምጣቱን ተከትሎ ኤርትራ የአዲሲቷ ሮማ ግዛት አካል ሆነች። ከአምስት አስርት ዓመታት በላይ በኤርትራ የቆየው የጣሊያን ኃይል፤ በኤርትራ ቆይታው በመንገድ፣ በባቡር እና በህንጻ ግንባታዎች ላይ ተሳትፏል። በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት በ ዓ ም ላይ የእንግሊዝ ጦር የጣሊያን ጦርን ከረን ላይ ድል አደረገ። ጣሊያን እና አጋሮቿ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ሽንፈትን መከናነባቸውን ተከትሎ፤ ጣሊያን ኤርትራን ጨምሮ በአፍሪካ የነበሯትን ቅኝ ግዛቶች ለመልቀቅ ተገደደች። ከጣሊያን ቅኝ ግዛት በኋላ ኤርትራ ከ ያሉትን ዓመታት በእንግሊዝ ጦር አስተዳደር ስር ነበረች። በወቅቱ ኤርትራዊያን ነጻ ኤርትራን ማየት ናፍቀዋል። እንግሊዝ በበኩሏ ኤርትራ በኢትዮጵያ እና በሱዳን መካከል እንድትከፈል ፍላጎቷ ነበር። አሜሪካ ግን ኤርትራ በፌዴሬሽን መልክ ከኢትዮጵያ ጋር እንድትዋሃድ ምክረ ሃሳብ አቀረበች። የኃያሏ አሜሪካ ፍላጎት ተግባራዊ ሆኖ ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር በፌዴሬሽን መልክ ተዋሃደች። ሉዓላዊ የሆነች ሃገር መፍጠርን ግብ ያደረጉ ኤርትራዊያን ከተለያዩ ሁለት የኢትዮጵያ መንግሥታት ጋር ለ ዓመታት ያክል የትጥቅ ትግል ሲያደርጉ ቆይተው እአአ ላይ የኤርትራን ነጻነትን አወጁ። አጭር የምስል መግለጫ ፕሬዝደንት ኢሳያስ ከሁለት አዛውንት መካከል ሆነው። የተራዘመው የኤርትራዊያን የትጥቅ ትግል በዓለማችን ከታዩ እጅግ ውጤታማ የሽምቅ ውጊያዎች አንዱ ነው ይባልለታል። ላይ ነጻነትን የተቀናጀችው ኤርትራ ላይ ሕዝብ ውሳኔ ከተካሄድ በኋላ ነበር በይፋ ነጻነቷን አውጃ በተባበሩት መንግሥታት እውቅና የተቸራት። በተባበሩት መንግሥታት በቅርበት ክትትል የተደረገበት ሕዝበ ውሳኔ፤ በመቶ የሚሆኑት ኤርትራውያን ነጻነትን እንሻለን ሲሉ ድምጻቸውን ሰጥተዋል። ከመኪኖች ይልቅ ብስክሌቶች የሚበዙባት ከተማ በሁለቱም ወገን ብዙ ደም ያፋሰሰው የኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ተቀሰቀሰ። ለሁለት ዓመታት ገደማ በዘለቀው ጦርነት በ ሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በሁለቱም ወገን ለሞት ተዳርገዋል። የአልጀርሱ ስምምነት በጦር ግንባር ላይ የነበረውን ጦርነት ያስቁመው እንጂ፤ ለ ዓመታት በሁለቱ ሃገራት መካከል ሰላምም ጦርነትም የሌለበት ሁኔታ ውስጥ ቆይተዋል። የጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ወደ ስልጣን መምጣትን ተከትሎ በሁለቱ ሃገራት መካከል ቆይቶ የነበረው ቁርሾ ተገፎ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነቱ ተጀምሯል። እኛም ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ አሥመራ አቅንተናል። አጭር የምስል መግለጫ አሥመራ ቆሻሻ የማይታይባት፤ ጽዱ ከተማ። ፃዕዳ አሥመራ ሃገሬው አሥመራን ፃዕዳ አሥመራ እያለ ይጠራታል። ፃዕዳ በትግርኛ ነጭ ማለት ነው። እውነት ነው አሥመራ ንጹሕ ነች። ቆሻሻ የማይታይባት፤ ጽዱ ከተማ። በእድሜ ጠገብ ህንጻዎች የተሞላችው አሥመራ፤ ከሁለት ዓመታት በፊት በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስ እና የባህል ድርጅት ዩኔስኮ ታሪካዊ ከተማ በመባል የዓለም የቅርስ መዝገብ ላይ ተመዝግባለች። የኤርትራ መዲና አሥመራ ከ ዎቹ ጀምሮ የቅኝ ገዢው የጣሊያን ጦር መቀመጫ ሆና ማገልገል ጀምራ ነበር። ቅኝ ገዢው በአሥመራ ጣሊያናዊ በሆነ የሥነ ሕንጻ ጥበብ ስልት ግንባታዎች ማከናወን ጀመረ። ሰማይ ላይ ወልዳ አሥመራ የምትታረሰው ኢትዮጵያዊት በወቅቱ ቅንጡ የሆኑ ለመንግሥት አገልግሎቶች የሚውሉ ህንጻዎች፣ አብያተ ክርስቲያናት፣ መኖሪያ ቤቶች፣ ሆቴሎች እና የሲኒማ ቤቶች ግንባታ ተከናውነዋል። ከ እስከ ድረስ የተገነቡት እነዚህ ህንጻዎች ዘመን ተሻግረው ዛሬ ላይ ታሪክን ያስታውሳሉ። የነዋሪው ቆሻሻን የመጠየፍ ባህሪ ካለው የፍሳሽ ማስወገጃ ሥርዓት ጋር ተደማምሮ ከተማዋን ንጹህ አድርጓታል። ጎዳናዎቿ ንጹሕ ናቸው። ስለዚህም የአፍንጫን ሰላም የሚነሳ ጠረን በአሥመራ ከተማ አልገጠመንም። አጭር የምስል መግለጫ በጥንቃቄ በመስመር የተተከሉት ዘንባባ እና ሽባካ ተክሎች ሌላኛው የከተማዋ ውበት ናቸው። ቅኝ ገዢዎቹ ጣሊያኖች በአሥመራ አሻራቸውን ጥለው ካለፉባቸው ነገሮች አንዱ የፍሳሽ አወጋገድ ሥርዓት ግንባታ አንዱ ነው። ፍሳሽ ማስወገጃ ቱቦዎች በከተማዋ ጎዳናዎች ሥር ተገንብተው እንደሚገኙ ከነዋሪዎች ሰምተናል። በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግሥት ከተማዋ ጠዋት ከሥራ ስዓት በፊት ትታጠብ እንደነበርም ተነግሮናል። ይህ ብቻም አይደለም፤ በአሥመራ ሲጓዙ ቢያድሩ አባ ከና የሚልዎ አይኖርም። ሃገሬውም ሆነ የውጪ ዜጋው ከመሸ እንደፈቀደው በእግሩ ይጓዛል። በአሥመራ አንድ ምሽት እንዳሳለፉ ስለከተማዋ ሰላማዊነት ሌላ እማኝ አያሻዎትም። ትሮቪላ፣ ፍራንሲስኮ፣ ዳንተ፣ ቪሊያጆ፣ ሳንታ ዓና፣ ቦላጆ እኚህ ስሞች በሃገረ ጣሊያን የሚገኙ የከተማ ስሞች አይደሉም፤ የአሥመራ ሰፈሮች መጠሪያ እንጂ። የአሥመራ ሰፈሮች ብቻ አይደሉም፤ ብዙ የአሥመራ ካፍቴሪያዎችና ምግብ ቤቶች ጨምር መጠሪያቸውን ያገኙት ከጣሊያን ቋንቋ ነው። ሌላኛው የአሥመራ ውበት በጥንቃቄ በመስመር የተተከሉት ዛፎች ናቸው። ዘንባባ እና ሽባካ ተብሎ የሚጠራው ዛፍ ለከተማዋ ልዩ ገጽታን አጎናጽፏታል። አጭር የምስል መግለጫ የብሌን ብሄርሰብ ተወላጆች ግራ የአፍር ወጣት እየጨፈረች ቀኝ ኤርትራ ኤርትራ በደቡብ ከኢትዮጵያ፣ በደቡብ ምሥራቅ ከጅቡቲ፣ በምዕራብ ከሱዳን፣ በምሥራቅ በኩል ደግሞ ከቀይ ባሕር ጋር ትዋሰናለች። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኤርትራ የህዝብ ብዛት ወደ ሚሊዮን ይገመታል ይላል። ወደ ሺህ የሚጠጉት ደግሞ መኖሪያቸውን በመዲናዋ አድረገዋል። በስድስት ዞኖች የምትከፋፈለው ኤርትራ፤ ትግር፣ ትግርኛ፣ አፋር፣ ኩናማ፣ ብሌን፣ ሳሆ እና ራሻይዳን ጨምሮ እውቅና የሚሰጣቸው ብሔሮች ኖሩባታል። በኤርትራ የሚገኘው አፋር በጅቡቲ እና ኢትዮጵያ ጋር ከሚኖሩት አፋሮች ጋር ተመሳሳይ ቋንቋ እና ባህል አላቸው። አጭር የምስል መግለጫ የራሻይዳ ሴት ከአምስት ዓመቷ ጀምሮ ከዓይኗ በስተቀረ የተቀረ ፊቷን በደማቅ ጨሌ ባማረ ጨርቅ ትሸፍናለች። ከተቀሩት የኤርትራ ብሔረሰቦች በመልክ እና በአኗኗር ዘዬ ለየት የሚሉት የራሻይዳ ህዝቦች ናቸው። መነሻቸው ሳዑዲ አረቢያ እንደሆነ የሚነገርላቸው ራሻይዳዎች አረብኛ ቋንቋ ተናገራሪዎች እና የእስልምና ዕምነት ተከታዮች ናቸው። አርብቶ አደር እና ከመካከለኛው ምሥራቅ የሚገቡ ሸቀጣ ሸቀጦችን በጭነት መኪና በመነገድ የሚታወቁት ራሻይዳዎች ቀይ ባህርን ተከትለው በኤርትራ በረሃማ ቦታዎች ላይ ይኖራሉ። የራሻይዳ ሴት ከአምስት ዓመቷ ጀምሮ ከዓይኗ በስተቀር የተቀረ ፊቷን በደማቅ ጨሌ ባማረ ጨርቅ ትሸፍናለች። የሰዓት እና ቀን አቆጣጠር አገልግሎት ፍለጋ አርፍደው በደረሱበት ስፍራ ነገ ጠዋት ሰዓት ላይ ኑ ልትባሉ ትችላለችሁ። ኤርትራዊያን ሰዓት የሚቆጥሩት ልክ እንደ ምዕራባውያኑ ነው። የቀን አቆጣጠር ሥርዓታቸውም ቢሆን እንደ ጎርጎርሳዊያኑ ነው። አጭር የምስል መግለጫ የኤርትራ መገበያያ ገንዘብ ናቅፋ ባለ ፣ ፣ ፣ ፣ እና ኖቶች አሉት። መገበያያ ገንዘብ የኤርትራ መገበያያ ገንዘብ ናቅፋ ይባላል። ባለ ፣ ፣ ፣ ፣ እና ኖቶች አሉት። አንድ የአሜሪካ ዶላር በ ናቅፋ በሕጋዊ መንገድ ይመነዘራል። በኤርትራ ዶላር በጥቁር ገበያ ላይ ለመመንዘር መሞከር ቀይ መስመር እንደማለፍ ከባድ ጥፋት ነው። ዶላር መመንዘር የሚቻለው በብቸኛው የኤርትራ ንግድ ባንክ ብቻ ነው። በአሁኑ ወቅት በባንክ እና በጥቁር ገበያ ላይ ያለው ልዩነት ሰፊ አይደለም። አንድ ዶላር በጥቁር ገብያ ላይ ናቅፋ ብቻ ነው የሚመነዘረው። አጭር የምስል መግለጫ ሁነኛ የትራንስፖርት አማራጭ ብስክሌቶች ቢሆኑም፤ አውቶብሶች እና ቢጫ ታክሲዎችም ደንበኞቻቸውን ከቦታ ቦታ ያመላልሳሉ። የትራንስፖርት አማራጮች እንደ ዝርግ ሳህን ለጥ ባሉት የአሥመራ ጎዳናዎች ነዋሪው ብስክሌቶች እንደ ሁነኛ የትራንስፖርት አማራጭ የመረጠ ይመስላል። ትልቅ ትንሹ በብስክሌት ሽር ይላል። ቦርሳ በጀርባቸው ያነገቡ ታዳጊዎች በብስክሌት ወደ ትምህርት ቤት ያቀናሉ። ሰራተኛው ጉዳዩን ለመፈጸም በብስክሌት ይንቀሳቀሳል። አውቶብሶች እና ቢጫ ታክሲዎችም ደንበኞቻቸውን ከቦታ ቦታ ያመላልሳሉ። የዛሬ ዓመት የኮ ል መንግሥቱ አውሮፕላን ለምን አልጋየም በኤርትራ አነስተኛ ደሞዝ፣ ወደ ሃገር ውስጥ በሚገቡ መኪኖች ላይ የሚጫነው ከፍተኛ ግብር እንዲሁም ከፍተኛ የነዳጅ ዋጋ ተደማምረው የግል መኪና ባለቤት መሆንን ከባድ ያደርጉታል። በዚህም በከተማዋ የሚስተዋሉት የተሽከርካሪዎች ቁጥር እጅግ አነስተኛ የሚባል ነው። ለመኪኖች በቅደም ተከተል የሚሰጠውን የሰሌዳ ቁጥር ከግምት ውስጥ በማስገባት፤ በኤርትራ የሚገኙ የግል መኪኖች ብዛት ከ ሺህ እንደማይዘሉ ማስላት ይቻላል። አሥመራ የትራፊክ መጨናነቅ የማያቃት ከተማ በመሆኗ ትራፊክ አልባዋ መዲና የሚል ስያሜ ተሰጥቷታል። ወደየትኛውም አቅጣጫ መኪና ይዘው ቢንቀሳቀሱ በሌሎች የአፍሪካ ከተሞች የሚያስተውሉትን አይነት የትራፊክ መጭናነቅ አይመለከቱም። ፒዛ ወይስ ላዛኛ የሚበላ ፍለጋ ወደ አንዱ ሬስቶራንት ጎራ ቢሉ፤ በምግብ ዝርዝር አማራጭ ውስጥ በቅድሚያ ተዘርዝረው የሚመለከቱት እነ ፓስታ፣ ላዛኛ እና ፒዛን የመሳሰሉ ምግቦችን ነው። ኤርትራዊያን የሚያሰናዱት ፓስታ እና ፒዛ እጅግ ድንቅ ጣዕም አላቸው። እንጀራ ከከጀሉ እንዲሁ በቀላሉ የሚያገኙት ሳይሆን ባህላዊ ምግብ የሚያዘጋጅ ምግብ ቤት መፈለግ ግድ ይልዎታል። የአሥመራ መስህብ ስፍራዎች እግር ጥሎዎት ወደ አሥመራ ካቀኑ ከተማዋ ለእንግዶቿ ጀባ ከምትላቸው በርካታ የመስህብ ስፍራዎች ቢያንስ የሚከተሉትን ሳይመለከቱ አይመለሱ። አጭር የምስል መግለጫ የሥነ ሕንጻ ባለሙያው ፊያትን ለመገንባት እቅዱን ለአከባቢው መስተዳድሮች ሲያቀርብ፤ ሜትር ርዝመት ያላቸው ክንፎች ያለድጋፍ ማቆም አይቻልም በማለት እቅዱን ውድቅ ተደርጎበት ነበር። ፊያት ታግሊኤሮ ፊያት ታግሊኤሮ ተገንብቶ የተጠናቀቀው እአአ ሲሆን የነዳጅ ማደያ፣ ጋራዥ እና የመኪና እጥበት አገልግሎት ይሰጥበት ነበር። ከታሪካዊነቱ በተጨማሪ ይህን በአውሮፕላን ክንፍ ቅርጽ የተገነባን ግንባታ ለየት የሚያደርገው፤ ወደ ጎን ሜትር የሚረዝሙት ክንፎቹ ያለ ምሶሶ መቆማቸው ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኤርትራ ውስጥ መኪና ሲያሽከረክሩ የሚያሳየው ቪዲዮ ፊያት የተገነባው በጣሊያኒያዊው የሥነ ሕንጻ ባለሙያ ጁሴፔ ፔታዚ ሲሆን፤ አስጎብኚዎች ስለዚህ ህንጻ ግንባታ አንድ አስደናቂ ታሪክ ይናገራሉ። የሥነ ሕንጻ ባለሙያው ጁሴፔ ፊያትን ለመገንባት ሃሳቡን ለአካባቢው መስተዳድሮች ባቀረበላቸው ወቅት፤ ሜትር ርዝመት ያላቸው ክንፎች ያለድጋፍ ማቆም አይቻልም በማለት እቅዱን ውድቅ አደርገውበት ነበር ይላሉ። በዚህ የተበሳጨው ጁሴፔ ይሄ ግንባታ ከፈረሰ እራሴን አጠፋለሁ ብሎ ዝቶ ንድፉን ከልሶ ቋሚ ድጋፎችን ያስገባ በማስመሰል ግንታውን መጨረሱ ይነገራል። ፊያት በወቅቱ ከአሥመራ ተነስተው ወደ ኢትዮጵያ እና የወደብ ከተሞች ለሚያቀኑ መኪኖች ነዳጅ የሚሞሉበት ብቸኛው ስፍራ ነበር። ዛሬ ላይ ከ ዓመታት በኋላ አገልግሎት ሳይሰጥ ብቻውን ተትቶ ቆሞ ይገኛል። አጭር የምስል መግለጫ አሥመራ የቅንጡ የሲኒማ፣ የቲያትር ቤቶች፣ የሬስቶራንቶች እና ካፍቴሪያዎች መገኛ ከተማ ነበረች። የአሥመራ ሲኒማ ቤቶች አሥመራ ዛሬ ላይ ሲያጤኗት ጭር ያለች ከተማ ናት። ከብዙ አስርት ዓመታት በፊት የነበራት ገጽታ ግን ሌላ ነበር። ቅንጡ የሲኒማና የቲያትር ቤቶች እንዲሁም የሬስቶራንቶች እና ካፍቴሪያዎች መገኛ ከተማ ነበረች። ዛሬ ላይ ባዷቸውን የቀሩት እነ ሲኒማ ሮማ፣ ሲኒማ ካፒቶል፣ ኦዲዮን ሲኒማ እና ሲኒማ አሥመራ ለዚህ እማኝ ናቸው። በ ዎቹ እና ዎቹ የተገነቡት እነዚህ ሲኒማ ቤቶች፤ በዘመናቸው አሉ የተባሉ የእንግሊዝኛ እና ጣሊያንኛ ፊልሞች የሚታዩባቸው ነበሩ። አሁን ላይ ገሚሱ ባዶውን ቀርቷል፤ የተቀሩት ደግሞ ሃገር በቀል ፊልሞችን እና የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የእግር ኳስ ጨዋታዎችን ያሳያሉ። አጭር የምስል መግለጫ በተለያዩ ወቅቶች በኤርትራ በተደረጉ ጦርነቶች ከጥቅም ውጪ ሆኑ የጦር ተሽከርካሪዎች በአንድ ሥፍራ ተሰብስበው ይገኛሉ። የታንክ መቃብር ስፍራ በተለያዩ ወቅቶች በኤርትራ የተደረጉ ጦርነቶች ምን ያክል አስከፊ እንደነበሩ ይህን ስፍራ በመጎብኘት መገንብ ይቻላል። በዚህ ታንክ ግሬቭ ያርድ የታንክ የመቃብር ቦታ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ በጦርነት የወደመ የጦር ተሽከርካሪ አይነት አንድም የቀረ አይመስልም። ከታንክ እስከ አየር መቃወሚያ፤ ከአውቶቡስ እሰከ መድፍ፤ ብቻ ሁሉም አይነት ተቃጥሎ እና ወላልቆ በአንድ ቦታ ላይ ተሰብስበው ይገኛሉ። ቀረብ ብለው ሲመለከቱ የወደሙትን የተሽከርካሪ አካላት መኖሪያ ቤታቸው ያደረጉ ሰዎችን ያስተውላሉ። አጭር የምስል መግለጫ በቅኝ ግዛት ወቅት ህይወታቸው በኤርትራ ያለፈ ጣሊያውያን ይቀበሩ የነበረበት ሥፍራ። የጣሊያኖች የመቃብር ስፍራ በቅኝ ግዛት ወቅት ህይወታቸው በኤርትራ ያለፈ ጣሊያዊያን ይቀበሩ የነበረበት ሥፍራ ነው። በጥሩ ሁኔታ ተይዞ የሚገኘው ይህ የመቃብር ስፍራ አሁንም ድረስ ከጣሊያን ድረስ እየመጡ በዘመዶቻቸው የመቃብር ላይ የአበባ ጉንጉን የሚያኖሩ ሰዎች እንዳሉ ይነገራል። ካቴድራል ቤተክርስቲያን፣ ሲኒማ ሮማ፣ እንዳ ማርያም ቤተክርስቲያን እና ሌሎች የጣሊያን ቅኝ ግዛት ዘመን የሥነ ሕንጻ ጥበብ ያረፈባቸው የሚጎበኙ ታሪካዊ ስፍራዎችም በአሥመራ ይገኛሉ። ተያያዥ ርዕሶች
ከዘጠኝ ዓመታት በፊት ኤርትራ ላይ የተጣለው ማዕቀብ ተነስቷል
ኅዳር የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት በኤርትራ ላይ ተጥሎ የነበረውን ማዕቀብ አነሳ። አባላት ያሉት የፀጥታው ምክር ቤት ሰኞ ዕለት ማእቀቡን ለማንሳት ስምምነት ላይ የደረሱ ሲሆን፤ የማንሳት ረቂቁም በእንግሊዝ መንግሥት አማካኝነት እንደቀረበ ተገልጿል። የማዕቀቡን መነሳት በተመለከተ ያነጋገርናቸው በቤልጄም የቀድሞው የኤርትራ አምባሳደር አቶ አምደብርሃን ወልደጊዮርጊስ፤ ኤርትራ ላይ ተጥሎ የነበረው ማዕቀብ ፍትሐዊ አልነበረም ብለዋል። የፖለቲከኛ እስረኞች ይፈቱ፣ የፕሬስ ነጻነት ይረከበር የሚሉ ጥያቄዎች ሲነሱ፤ የኤርትራ መንግሥት ማዕቀቡን እንደ ምክንያት ሲጠቀምበት እንደነበር ጥያቄዎቹ ሲነሱ ጦርነት ላይ ነን፤ ማዕቀብ ላይ ነን ሲባል ቆይቷል በማለት ገልጸዋል። የጠቅላይ ሚንስትር ጽሕፈት ቤት ማምሻውን ባወጣው መግለጫ፤ የኤርትራን ሕዝብና መንግሥት እንኳን ደስ አላችሁ ብሏል። ማዕቀቡ መነሳቱ በአፍሪካ ቀንድ ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን አስተዋጽኦ ያበረክታል ተብሏል። በቀጠናው ሀገሮች መካከል ዘላቂ ሰላም ለማስፈንና በሀገራቱ መካካል ጤናማ ግንኙነት ለመፍጠር እንደሚረዳም ተግልጿል። ለዘጠኝ ዓመታት ያህል የቆየው ይህ ማዕቀብ የጦር መሳሪያ ዝውውርን ከመገደብ በተጨማሪ፣ ከፍተኛ የኤርትራ ባለስልጣናት እንቅስቃሴያቸው እንዲገደብና ሀብታቸውን እንዳያንቀሳቅሱ የሚል ነው። ለሁለት አስርት አመታት ተፋጠው የነበሩት የኢትዮጵያና የኤርትራ መንግሥት እርቅ መፈፀማቸውን ተከትሎ፤ የኤርትራ መንግሥት ከሌሎች ጎረቤት ሀገራትም ጋር ግንኙነቱ በመሻሻሉ ምክንያት ማዕቀቡ ሊነሳ እንደተቻለ ተገልጿል።
የህንዶቹን አስራ አንድ አንበሶች ምን ገደላቸው
መስከረም ይህንን ለማጋራት በ ዋትስአፕ በህንድ የሚገኙ የእንስሳት ጥበቃ ባለሙያዎች እንደገለጹት ባልተለመደ መልኩ በጉጅራት ግዛት ሞተው የተገኙትን የእስያ አንበሶች የሞት ምክንያት እያጣሩ ነው። የእስያ አንበሶች እ አ አ ከ ጀምሮ በመጥፋት ስጋት ላይ ያሉ እንሰሳት ተብለው ነበር። በጉጅራት እንስሳት መጠበቂያ ውስጥ በመቶዎች የሚቆጠሩ የእስያ አንበሶች ይገኛሉ። ነገር ግን ይህን ያክል ቁጥር ያላቸው አንበሶች በተመሳሳይ ሰአት መሞታቸው በእንስሳት መጠበቂያው ውስጥ ያለውን አስቸጋሪ ሁኔታ የሚያሳይ ነው ተብሏል። እስካሁን ድረስ ለአንበሶቹ ሞት ምክንያት የሆነው ነገር ባይታወቅም፤ አንበሶቹ በመጠበቂያ ውስጥ የአደንና የማረፊያ ቦታ ለማግኘት በሚደርጉት ፍልሚያ ሳይሆን እንዳልቀረ ባለሙያዎቹ ገምተዋል። የእንስሳት ጥበቃ ባለሙያው ጂኬ ሲንሃ እንደተናገረው ከሌላ አካባቢ የመጡ ሶስት አንበሶች መጠለያ ውስጥ የነበሩ ሶስት ደቦሎችን የገደሉ ሲሆን፤ የዚህ አይነት ባህሪ በአንበሶች ዘንድ የተለመደ ነው ብሏል። የተቀሩት ስምንት አንበሶች ግን በምን ምክንያት እንደሞቱ የታወቀ ነገር የለም። በህንዷ ጉጅራት ግዛት በሚገኘው የእንስሳት መጠበቂያ ውስጥ የሚኖሩት አንበሶች ከቦታው ጠባብነት የተነሳ የሚበሉትን ምግብም ሆነ መጠለያ ለማግኘት ከፍተኛ ትግል ማድረግ አለባቸው። በእንስሳት መጠበቂያው ከሚኖሩ አንበሶች መካከል በመቶ የሚሆኑት የሚሞቱት በተፈጥሯዊ ምክንያት ሲሆን የተቀሩት በመቶዎች ግን ተፈጥሯዊ ባልሆኑና ምክንያታቸው ባልታወቁ አጋጣሚዎች ይሞታሉ። የዕለት ከዕለት ኑሮን የሚለውጡ ፈጠራዎች የአንበሶች አማካይ የመኖሪያ ዕድሜ ከ እስከ ዓመት ሲሆን፤ ከ ዓመት በኋላ ግን አድኖ የመብላትና የመንቀሳቀስ አቅም ስለማይኖራቸው በአንድ አካባቢ ተወስነው የእርጅና ጊዜያቸውን ያሳልፋሉ። የእንስሳት ጥበቃ ባለሙያው ጂኬ ሲንሃ ሌላ መላ ምት አስቀምጧል። ለቢቢሲ እንደተናገረው ሲዲቪ የተባለ በውሾች የተላለፍ ቫይረስ ሊሆን ይችላል አንበሶቹን የገደላቸው። የእንስሳት መጠበቂያው በቂ ጥበቃ ስለማይደረግለት አንበሶች ወደ ሰዎች መኖሪያ የሚወጡ ሲሆን፤ ውሻዎችም ቢሆን ወደ ጥብቅ ክልሉ ይገባሉ። ቢቢሲ ማስተባበያ
አምነስቲ የማይናማሯን መሪ ሳን ሱ ኪን ከፍተኛ የተባለውን ሽልማት ነጠቀ
ኖቬምበር አምነስቲ የማይናማሯን መሪ ሳን ሱ ኪ ከፍተኛ የሚባለውን የህሊና አምባሳደር ሽልማት ነጥቋቸዋል። የሰላም የኖቤል ሽልማት አሸናፊዋ ፓለቲከኛ ይህንን ሽልማት የተቀበሉት በአውሮፓውያኑ ሲሆን በወቅቱም በቤት እስር ላይ ነበሩ። የመብት ተሟጋቹ ድርጅት እንዳስታወቀው ይህንን እርምጃ ለመውሰድ የተገደደው በአገሪቱ ውስጥ የሮሂንጃን ጥቃት መከላከል ባለመቻላቸው እንደሆነ አስታውቋል። ከነዚህ ውስጥ ሺ ህዝብ በላይ ወታደራዊ ጥቃትን በመፍራት ሸሽተዋል። ሙገሳ እና ወቀሳ የተፈራረቀባቸው ሳን ሱ ኪ የ ዓመት ዕድሜ ባለፀጋዋ አን ሳን ሱ ኪ ይህ ሽልማት በቅርብ ጊዜ ካጧቸው ሽልማቶች አንዱ እንደሆነም ተገልጿል። የሰላም፣ የፅናትና የግለሰቦችን ሰብዓዊ መብት በመከላከል ረገድ የነበረሽ ተምሳሌነት አሁን የለም። ያንንም ስለማትወክይ እናዝናለን በማለት የአምነስቲ ዋና ፀሐፊ ኩሚ ናይዱ ለማይናማሯ መሪ በፃፉት ደብዳቤ አስታውቀዋል። ጨምረውም በሮሂንጃ ላይ የደረሰውን ጭካኔያዊ ተግባርና የግፉን መጠን መካዷ ሁኔታውን ለማስተካከል ምንም ፍላጎት እንደሌለ አሳይ ነው ብለዋል። ምንም እንኳን የተባበሩት መንግሥታት ባደረገው ምርመራ መሪዋ ቀጥታ በባለፈው ዓመት የሮሂንጃ የዘር ጭፍጨፋ ቀጥታ ተሳታፊ አለመሆናቸውን ቢያረጋግጥም፤ ስልጣናቸውን በመጠቀም በሰራዊቱ የደረሱ ግድያዎችንና መደፈሮችን ማስቆም እንደተሳናቸው ገልጿል። በአንድ ወቅት አምነስቲ የዲሞክራሲ ቁንጮ ብሏቸው የነበረ ሲሆን፤ ይህንንም ውሳኔ ያስተላለፈው የአን ሳን ሱ ኪ የቤት ውስጥ እስር ስምንተኛ አመት ክብረ በዓል ላይ ነው። ለዲሞክራሲ ያደርጉት በነበረው ትግል የማይናማር አምባገነን መንግሥት ለ ዓመታት ያህል በቤት ውስጥ እስር አቆይቷቸዋል። በዚህም ምክንያት የተለያዩ መንግሥታት፣ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ክብራቸውን ለግሰዋቸው ነበር። ተያያዥ ርዕሶች
በጋዛ የእስራኤልና የፍልስጥኤም ግጭት እየተባባሰ ነው
ኖቬምበር አጭር የምስል መግለጫ አውቶቡስ ላይ በተሰነዘረ ጥቃት አንድ እስራኤላዊ በፅኑ ተጎደቷል እስራኤል እሁድ እለት በጋዛ ያደረገችውን ስውር ወታደራዊ ተልኮ ተከትሎ ሰባት ታጣቂዎችና አንድ እስራኤላዊ ወታደር ሞተዋል። ታጣቂዎቹ ሮኬቶችንና ሞርታሮችን እስራኤል ላይ አስወንጭፈዋል። በተለይም አንደኛው ሮኬት አወቶብስ መትቶ በአቅራቢያው የነበረ ወታደርን በፅኑ ማቁሰሉ ተዘግቧል። በአፀፋው ደግሞ እስራኤል የሃማስና የኢዝላሚክ ጂሃድ ይዞታ ናቸው ባለቻቸው ቦታዎች ላይ ከ በላይ የአየር ጥቃቶችን ፈፅማለች። በዚህም ሶስት ፍልስጥኤማዊያን የተገደሉ ሲሆን ሁለቱ ወታደሮች ናቸው። ሃማስ የሚያስተዳድረው ይዞታ ጤና ጥበቃ በጥቃቱ ዘጠኝ ሰዎች መጎዳታቸውን አስታውቋል። በእስራኤል በኩልም በተመሳሳይ አስር ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል ተብሏል።
ሜጀር ጄኔራል ክንፈ ዳኘው ጠበቃ ራሳቸው እንዲያቆሙ ተወሰነ
ኖቬምበር ማጋሪያ ምረጥ ሜጄር ጄኔራል ክንፈ ዳኘውና ሌሎችም ተጠርጣሪዎች በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ኛ የወንጀል ችሎት ቀርበዋል። በትናንትናው የፍርድ ቤት ውሎ ሜጄር ጄኔራል ክንፈ፤ ደሞዜ አነስተኛ ስለሆነ ፍርድ ቤቱ ጠበቃ እንዲያቆምልኝ እጠይቃለሁ በማለታቸው ፍርድ ቤቱ ለዛሬ ከሰዓት ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱ ይታወሳል። በትላንትናው የፍርድ ቤት ውሎ፤ ሜጀር ጀነራል ክንፈ ከጡረታ የማገኘው ገንዘብ ብር ስለሆነ ፍርድ ቤቱ ጠበቃ እንዲያቆምልኝ እጠይቃለሁ ሲሉ ለዳኞች አስታውቀዋል። ዛሬ ፖሊስ ሜጄር ጄኔራል ክንፈ ጠበቃ የማቆም አቅም እንዳላቸው የሚያረጋግጥ ማስረጃ አለኝ ብሏል። ፖሊስ እንደሚለው፤ ሜጄር ጄኔራል ክንፈ በጸረ ሙስና ኮሚሽን ያስመዘገቡት የሃብት መጠን እና በአንድ ባንክ ውስጥ ያላቸው ተቀማጭ ሂሳብ ጠበቃ የማቆም አቅም እንዳላቸው ያመላክታል። ፖሊስ ከ ቀን በፊት አንድ መቶ ሺህ ብር ከባንክ ሂሳባቸው ወጪ መደረጉን እና በስማቸው ቤት እንዲሁም ሺህ ብር የሚያወጣ መኪና ተመዝግቦ እንደሚገኝ ለፍርድ ቤቱ አስረድቷል። ሜጀር ጄኔራል ክንፈ በበኩላቸው ፖሊስ የጠቀሰው ንብረት እና ገንዘብ የእኔ አይደለም ሲሉ ለፍርድ ቤቱ ምላሽ የሰጡ ሲሆን፤ ቤት የለኝም፣ መኪና የለኝም፣ ንብረት የለኝም። ያለኝ ሰውነቴ ብቻ ነው በማለት ለፍርድ ቤቱ አስረድተዋል። ሆኖም ፍርድ ቤቱ ሜጄር ጄኔራል ክንፈ የራሳቸውን ጠበቃ እንዲያቆሙ ውሳኔ አስተላልፏል። ሜጄር ጄኔራሉ እና ወንድማቸው አቶ ኢሳያስ ዳኘው ለህዳር ፣ ዓ ም ቀጠሮ ተሰጥቷቸዋል። ከሜጄር ጄኔራሉ ጋር የቀድሞ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ጋዤጠኛ ፍጹም የሺጥላ፣ ሳጅን ኪዳኔ አሰፋ፣ ትዕግስት ታደሰ እና አቶ ቸርነት ፍርድ ቤት ቀርበዋል። አጭር የምስል መግለጫ ወ ሮ ፍጹም የሺጥላ ወ ሮ ፍጹም የሺጥላ ከሜቴክ የስራ ኃላፊዎች ጋር ያልተገባ የጥቅም ግንኙነት በመፍጠር ፍጹም ኪነ ጥበባት በሚሰኝ የንግድ ስም ህጋዊ ባልሆነ መንገድ የ ሺህ ብር የስራ ስምምነት ከሜቴክ ጋር ተዋውለዋል የሚል ክስ ቀርቦባቸዋል። ወ ሮ ፍጹም የቤተሰብ አስተዳዳሪ መሆናቸውን እና ከሕግ ለማምለጥ ሙከራ አለማድረጋቸውን በመጥቀስ የዋስትና መብት እንዲከበርላቸው ቢጠይቁም ፍርድ ቤቱ ግን የዋስትና መብት ከልክሏል። ከሙስና ወንጀል ጋር በተያያዘ ዛሬ ፍርድ ቤት ከቀረቡት መካከል የሜጄር ጀነራል ክንፈ ዳኘው ወንድም ኢሳያስ ዳኘው ይገኙበታል። እንደ ሜጀር ጀነራል ክንፈ ወንድማቸው አቶ ኢሳያስ ዳኘውም ገንዘብ ከፍለው ጠበቃ ማቆም እንደማይችሉ በመጥቀስ፤ መንግሥት ጠበቃ እንዲያቆምላቸው መጠየቃቸው ይታወሳል። የኢትዮቴሌኮም ሰራተኛ ሳሉ የግዢ ስርዓቱ በማይፈቅድ መልኩ ሜቴክ ጨረታ እንዲያሸንፍ በማድረግ ወንጀል ተጠርጥረው ፍርድ ቤት የቀረቡት አቶ ኢሳያስ ወራሃዊ ደሞዜ ሺህ ብር በመሆኑ ጠበቃ ማቆም አልችልም ብለው ነበር። ሜጀር ጄነራል ክንፈ ዳኘው ማክሰኞ እለት በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ይታወሳል። ፋና ብሮድካስቲንግ፤ ሜጀር ጄነራል ክንፈ ወደ ሱዳን ለመውጣት ሲሞክሩ በቁጥጥር ሥር ዋሉ ብሎ የዘገበ ሲሆን፤ ኢቢሲ ደግሞ በትግራይ ክልል ባካር ተብሎ በሚጠራ ስፍራ በኩል ለማምለጥ ሲሞክሩ በትግራይ ክልል ልዩ ፖሊስ በቁጥጥር ሥር ውለዋል ሲል ዘግቧል። በሰብዓዊ መብት ጥሰትና በሙስና የተጠረጠሩት ግለሰቦች ሰኞ ዕለት ከፍተኛ ፍርድ ቤት ኛ የወንጀል ችሎት ቀርበው ነበር። ፍርድ ቤት ከቀረቡት መካከል ቱ በሰብዓዊ መብት ጥሰት ወንጀል ተጠርጥረው እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን፤ ቱ ከብሄራዊ መረጃና ደህንነት፣ ስድስቱ ከፌዴራል ፓሊስ ምርመራ ቢሮ፣ ሁለቱ ከአዲስ አበባ ፓሊስ ኮሚሽን፣ ስምንቱ ከፌዴራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ሲሆኑ፤ ሶስቱ ግለሰቦች ደግሞ ተጠርጣሪን በማስመለጥና ሰነድ በማጥፋት የተጠረጠሩ ናቸው። ብርጋዲየር ጄኔራል ጠና ኩርዲንን ጨምሮ የሜቴክ ሰራተኞችም በሙስና ተጠርጥረው ፍርድ ቤት የቀረቡ ሲሆን፤ የስኳር ገንዘብን ያለአግባብ በመጠቀም፣ የህዳሴ ግድብና የያዩ ማዳበሪያ ፕሮጀክቶች ላይ ህግን ያልተከተለ ግዢ በመፈፀም ተከሰዋል። ከዚህም በተጨማሪ ሁለት መርከቦችን ለህገወጥ ንግድ በመገልገል ክስ የተወነጀሉ ሲሆን፤ የግራ ቀኙን ክርክር ያዳመጠው ፍርድ ቤትም የተጠርጣሪዎችን የዋስትና ጥያቄ ውድቅ በማድረግ ፖሊስ የጠየቀውን የ ቀን ጊዜ የፈቀደ ሲሆን፤ ለህዳር ቀን ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል። የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ አቶ ብርሀኑ ጸጋዬ፤ የቀድሞ የብሄራዊ ደህንነት እና መረጃ ኤጀንሲ አመራሮች እና አባላት በሽብር እና ከሽብር ጋር በተያያዘ ተጠርጥረው የተያዙ ግለሰቦች ላይ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ሲፈጽሙ ነበር ብለዋል። ከሰብዓዊ መብት ጥሰትና ከሙስና ጋር በተያያዘ የተሰሩ ወንጀሎችን በተመለከተ ባለፉት አምስት ወራት ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ሲያከናውን የነበረውን የምርመራ ውጤት ሕዳር ቀን ዓ ም ይፋ አድርጓል። ጠቅላይ አቃቤ ሕጉ በመግለጫቸው፤ በግለሰቦችና በተቋማት ደረጃ ተፈጽመዋል ያሏቸውን የሰብዓዊ መብት ጥሰትና የሙስና ወንጀሎች ዘርዝረዋል። የሰብዓዊ መብት ጥሰቶቹ ሲፈጸሙ የነበረው በኃላፊዎች ነው። የሙስና ወንጀሉ ሰፊና ውስብስብ ስለሆነ የምርመራ ሂደቱ ቀላል አልነበረም ብለዋል። ጠቅላይ አቃቤ ሕጉ ሰዎቹን ሳናስራቸው በፊት ከሕግና ከአሰራር አንጻር መረጃና ማሰረጃ ለማደራጀት ሰፊ ጊዜ ወስዶብናል በማለት እስካሁን ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር ያልዋሉበትን ምክንያት አስረድተዋል።
የሱዳን ስደተኞች ቡድን የፈረንሳዩን ባንክ በዘር ጭፍጨፋ ሊከስ ነው
መስከረም ይህንን ለማጋራት በ ዋትስአፕ የሱዳን ስደተኞች ቡድን ቢኤንፒ ፓሪባስ የተባለውን የፈረንሳይ ባንክ በሱዳን ዘር ጭፍጨፋ ላይ ሚና ነበረው በሚል ፍርድ ቤት ሊያቆመው ነው። ሱዳን በነበረው የዘር ጭፍጨፋ ጥቃት ደርሶብናል የሚለው ይህ ቡድን ባንኩ መንግሥት የፈፀማቸውን ግፎችም ሲደግፍ ነበር በማለት በዛሬው ዕለት ፖሪስ በሚገኘው ፍርድ ቤት የሚያቆሙት። መቀመጫቸውን አሜሪካ ያደረጉት ሃያ አንዱ ስደተኞች ባንኩ ኒውዮርክ በሚገኘው ቅርንጫፉ በሱዳን መንግሥት የተፈፀሙ ግድያዎችን፣ መደፈር፣ ስቃይ እንዲሁም ሆን ብሎ የኤችአይቪ ቫይረስን ማስተላለፍ ግፎች ላይ ሚና በመጫወትና ህገወጥ የሆኑ የገንዘብ ዝውውሮችን ሂደት በማቀላጠፍ ወንጅለውታል። በሱዳን ላይ የተፈፀመውን የዘር ጭፍጨፋ ላይ ከተወነጀሉ የመጀመሪያ አለም አቀፍ ድርጅቶች አንዱ ነው። ባለፈው አንድ ዓመት ከ ሰዎች በላይ መገደላቸውን ጠቅላይ አቃቤ ህግ አስታወቀ ከሳሾቹ የፈረንሳይ ዳኞች በባንኩ ላይ የወንጀል ምርምራ እንዲከፈት የጠየቁ ሲሆን ይህም ባንኩን ወይም በባንኩ ውስጥ በከፍተኛ ኃላፊነት ያለ ሰው ከገንዘብ ቅጣት ጀምሮ፣ እስር እንዲሁም ማዕቀብ ሊጣልበት እንደሚችልም ተጠቁሟል። ከጎርጎሳውያኑ አቆጣጠር ከ ባሉት ጊዜያት የሱዳን ባንክ ተብሎ የሚጠራው ይህ ባንክ በአሜሪካ፣ በተባበሩት መንግሥታትና በአውሮፓ ህብረት የኢኮኖሚ ማዕቀብ በተጣለበት ጊዜም ለአልበሽር መንግሥት የባንክ አገልግሎት በዋነኝነት ይሰጥ ነበር ተብሏል። በዚህም ወቅት ዳርፉር ላይ ከፍተኛ ግድያዎች የደረሱ ሲሆን የአለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤትም የዘር ጭፍጨፋ ተፈፅሟል ይላል። የኢኮኖሚ ማዕቀቡን በመጣስ ከሱዳን፣ ከኢራንና ኪዩባ ጋር የገንዘብ ግንኙነት በመፍጠር በአሜሪካ ቢሊዮን ዶላር ቅጣት ተጥሎበታል። ቢቢሲ ማስተባበያ
ኢትዮጵያና ኤርትራ የት ድረስ አብረው ይራመዳሉ
ሠኔ ይህንን ለማጋራት በ ዋትስአፕ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ስልጣን ሲረከቡ ፓርላማ ቀርበው ባደረጉት ንግግር ከኤርትራ ጋር ሰላም ለማውረድ እንደሚፈልጉ አስታውቀው ነበር። በወቅቱ ከኤርትራ በኩል የተሰጠው ምላሽ ኢትዮጵያ ሰላም ማውረድ ከፈለገች የአልጀርሱን ስምምነት ተግባራዊ ማድረግ ቀዳሚው እርምጃ ነው የሚል ነበር። ኢትዮጵያ የአልጀርሱን ስምምነት ተግባራዊ እንደምታደርግ ስታስታውቅ በአገር ውስጥ ውሳኔውን የመቃወም ድምፆች ተሰምተው ነበር። በኤርትራ በኩል ግን ምንም የተባለ ነበር አልነበረም። ዛሬ ግን ዝምታው ተሰብሮ የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ወደ አዲስ አበባ ልኡካን እንደሚልኩ አስታውቀዋል። በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካል ሳይንስ መምህር የሆነው መኃሪ ዮሃንስ ዘላቂ ሰላምን ያመጣል የሚለው ጉዳይ ዛሬ ላይ የሚመለስ ባይሆንም እርምጃው ግን በራሱ ትልቅ ነው ይላል። እርምጃው ትልቅ ነው የሚለው የእስከዛሬውን የሁለቱ አገራት ግንኙነት ከግምት በማስገባት ነው። የሁለቱ አገራት መንግስታት ላለፉት ሃያ ዓመታት ደረቅ አቋም ይዘው የኢትዮጵያ መንግስት የድንበር ኮሚሽኑን ውሳኔ በመርህ ደረጃ ተቀብለነዋል ነገር ግን ትግበራው ውይይት ይፈልጋል ፤ የኤርትራ መንግስት ደግሞ ውሳኔው ያለምንም ቅድመ ሁኔታ መፈፀም አለበት ሲሉ ከመቆየታቸው አንፃር እርምጃው የፖሊሲ ለውጥ ነውም ይላል። ከፕሬዝዳንት ኢሳይያስ ንግግር እንደተረዳው ዋናው ችግር የነበረው በኤርትራው ገዥ ፓርቲና በህዝባዊ ወያነ ሃርነት ትግራይ ህወሃት መካከል እንደነበርና አሁን ግን በኢትዮጵያ የአመራር ለውጥ መምጣቱ ፕሬዝዳንቱን ለውሳኔው አብቅቷቸዋል። ይህን በሁለቱ አገራት መሪዎች መካከል መናበብ ያለ ይመስላል በማለት ይገልፀዋል መኃሪ። የኤርትራ መንግስት ልኡክ ለመላክ በመወሰን የወሰደው እርምጃ ምን ያህል ጉልህ ነው የሚለው የሚመዘነው ልኡካኑ መጥተው በሚያደርጉት ውይይት እንደሆነ መኃሪ ያስረዳል። ልኡካኑ ከኢትዮጵያ አቻዎቻቸው ጋር የሁለቱ አገራት መሪዎችን ለማገናኘት ነገሮችን ለማመቻቸት ወይስ በድንበር ጉዳዩ ላይ ለመነጋገር የሚለውን ማወቅ እርምጃውን ለመመዘን ወሳኝ እንደሆነ ያምናል። እርምጃው ዘላቂ ሰላምን ያመጣል አያመጣም የሚለው ጊዜው ደርሶ የውይይቱን ርእሰ ጉዳዮች ማወቅ ይጠይቃል ብሏል። ከሁለት አስርታት በላይ በአገራቱ መካከል የዘለቀውን ዝምታ ለሰበሩት ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ትልቅ ዋጋ እንደሚሰጡ የሚናገሩት ኤርትራዊው የህግ ባለሙያና ግጭት አፈታት ኤክስፐርት አቶ ኤልያስ ሃብተስላሴ የኤርትራ መንግስት ወደዚህ ነገር የገባው ተገዶ ነው ይላሉ። ቢሆንም ግን ለንግግር በር መክፈቱ ትልቅ ግምት የሚሰጠው እንደሆነ ያምናሉ። እርምጃው ምን ድረስ የሚዘልቅ ነው የሚለውን ለማወቅ ጊዜ እንደሚጠይቅ ምን ያህል ነው በሩን ክፍት ያደረገው የሚው በጊዜው የሚታይ ነው በማለት በመኃሪ ሃሳብ ይስማማሉ። እሳቸው እንደሚሉት ላለፉት ሁለት አስርት ዓመታት የኤርትራ መንግስት ወጣቱን በብሄራዊ ግዳጅ ሲያስገድድና ህዝቡ ላይ የተለያዩ ተፅእኖዎችን ሲያሳደር ኢትዮጵያ የድንበር ኮሚሽኑን ውሳኔ ተግባራዊ ላለማድረግ እንቢተኛ ሆናለች በሚል ነበር። በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ መንግስት ባደረጋቸው ውሳኔዎች ምክንያት የኤርትራ መንግስት በቀደመው አቋሙ እንዳይቀጥል ሆኗል የሚል እምነት አላቸው። በሁለቱ አገራት ግጭት በደረሱ ዘርፈ ብዙ ችግሮች ምክንያት ግን ጅማሮውን ከዳር ማድረስና በሁለቱ አገራት መካከል ሰላም ማስፈን ብዙ ስራ የሚጠይቅ እንደሚሆን አቶ ኤልያስ ይገልፃሉ። እንደ እሳቸው አገላለፅ በሁለቱ አገራት መንግስታት ምክንያት ሞት፣አካል ጉዳት፣መፈናቀል በአጠቃላይ ማህበራዊና ኢኮኖሚ ቀውሶች በሁለቱም ህዝቦች ላይ ደርሰዋል።በተለይም በሁለቱም በኩል ድንበር ላይ ያሉ ህዝቦች ይበልጥ ተጎድተዋል። ስለዚህም በሁለቱ አገራት ሰላም የማስፈን ነገር በመሪዎች ስምምነት ብቻ የሚጠናቀቅ ጉዳይ እንዳልሆነ አቶ ኤልያስ ያስረዳሉ። ይልቁንም የተጎጅዎች ካሳ ፣ሁለቱን ህዝብ የማገናኘትና ወደ ቀደመ ዝምድናው የመመለስ ጉዳይ ሊተኮርበት እንደሚገባ ያምናሉ። ለዚህ ደግሞ ስምምነቱ ኢኮኖሚና ማህበራዊ ገፅታ ሊኖረውና ሲቪል ማህበራትን ፣ የሃይማኖት ተቋማትንና በሁለቱም አገራት በኩል የሚመለከታቸውን እንዲሁም አህጉራዊና አለም አቀፍ አካላትን ሊያሳትፍ እንደሚገባ ያስረዳሉ። ይህ ካልሆነ ግን አዎንታዊው ጅማሮ ግቡን አይመታም የሚል ስጋት አላቸው። ቢቢሲ ማስተባበያ
ከ ሚሊዮን ዶላር በላይ የሚያወጣ ስእል በአንዲት አዛውንት ማእድ ቤት ተገኘ
መስከረም ይህንን ለማጋራት በ ዋትስአፕ በፈረንሳይዋ ፓሪስ አቅራቢያ በአንዲት አዛውንት ኩሽና ተገኘ የተባለው የስእል ስራ በአስራ ሶስተኛው ክፍለ ዘመን እንደተሰራ የሚታመን ነው። ለረዥም ጊዜያት የት እንደገባ ጠፍቶ የነበረው እሄ የስእል ስራ ባለቤት ጣልያናዊው ሲምባው ወይም ሲኒ ዲ ፒፖ እንደሆነም ኤክስፐርቶች አስታውቀዋል። እርግጥም ይህ የጥበብ ስራ የዚህ ጣልያናዊ መሆኑን ለማረጋገጥ በኢንፍራሪድ ምርመራም ተካሂዷል። ስእሉ እአአ በሚቀጥለው ወር ለጨረታ የሚቀርብ ሲሆን ሚሊዮን ዶላር ድረስ ሊያወጣ እንደሚችል ተገልጿል። ዘመናትን የተሻገረውና ከፍተኛ ዋጋ ያለው ይህ ስእልን ያስቀመጡት አዛውንት ስእሉ ትልቅ የጥበብ ዋጋ ያለው ሃይማኖታዊ ስእል እንደሆነ ያምኑ እንደነበርም ተገልጿል።
በተያዘው ዓመት ለሁለት የቴሌኮም ኦፕሬተሮች ፍቃድ ይሰጣል ተባለ
ሴፕቴምበር አጭር የምስል መግለጫ የኢትዮጵያ ኮሚዩኒኬሽን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ባልቻ ሬባ። የኢትዮጵያ የኮሚኒኬሽን ባለስልጣን በያዝነው አዲሱ ዓመት ለሁለት የቴሌኮም ተቋማት ፍቃድ እንደሚሰጥ አስታወቀ። ይህን ያሉት በቅርቡ በጠቅላይ ሚንሰትር ዐብይ አሕምድ የኢትዮጵያ ኮሚዩኒኬሽን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ተደርገው የተሾሙት አቶ ባልቻ ሬባ ናቸው። በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባጸደቀው አዋጅ ቁጥር መሰረት፤ የኢትዮጵያ ኮሚዩኒኬሽን ባለስልጣን የቴሌኮም ዘርፉን በመቆጣጠር በዘርፉ ለሚሰማሩ የግል ተቋማት የውድድር ገብያውን ምቹ ለማድረግ የተቋቋመ ነው። የውጪ ሀገር ጥሪዎች ለምን በኢትዮጵያ ቁጥር ይወጣሉ አቶ ባልቻ ሬባም ተቋሙን ከያዝነው አዲስ ዓመት ጀምሮ በዋና ዳይሬክተርነት እንዲመሩ ተሹመዋል። ይህ ተቋም በዚህ ዓመት ለመፈጸም ካቀዳቸው ዋና ተልዕኮዎች መካከል፤ ለሁለት በቴሌ ኮሚዩኒኬሽን ኦፐሬሽን ለሚሰሩ ተቋማት ፍቃድ መስጠት ነው በማለት ለቢቢሲ ተናግረዋል። መንግሥት ከዚህ በፊት በመቶ የሚሆነውን የኢትዮ ቴሌኮም ድርሻ በእራሱ ሥር አቆይቶ በመቶውን ደግሞ ወደ ግል ለማዘዋወር ፍላጎት እንዳለው ማስታወቁ ይታወሳል። የጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ መንግሥት የቴሌኮም ዘረፉ ለግል ድርጅቶች ክፍት እንደሚደረግ ይፋ ካደረገ በኋላ በርካታ ዓለም አቀፍ የቴሌኮም ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ገብያ ላይ ፍላጎት ሲያሳድሩ ቆይተዋል። አየር መንገድንና ቴሌን ለሽያጭ ለማቅረብ ትክክለኛው ጊዜ አሁን ነው ከስድስት ወራት በኋላ ፍቃድ ወደመስጠቱ ሥራ እንገባለን የሚሉት አቶ ባልቻ የአውሮፓውያኑ ከመጠናቀቁ በፊት የቴሌኮሚኒኬሽን ኦፕሬሽን ፍቃድ ይሰጣል ተብሎ ነበር ይላሉ። ዋና ዳይሬክተሩ እንደሚሉት ከሆነ የኢትዮጵያ ኮሚዩኒኬሽን ባለስልጣን ፍላጎት ያላቸው ተቋማት የንግድ ሃሳባቸውን እንዲያስገቡ ጥሪ ሲያቀርብ በዘርፉ መሰማራት የሚፈልጉ ተቋማት ጥሪውን መሰረት አድርገው ገቢ ያደርጋሉ። እስከዛው ግን የንገድ ሃሳብ ገቢ ማድረግ እንደማይቻል ይናገራሉ። የቴሌኮሚዩኒኬሽን ኦፐሬሽን ፍቃድ የሚሰጣቸው ተቋማት የውጪ ሃገር፣ የሃገር ውስጥ ወይም በሽርክና የሚሰሩ ሊሆኑ ይችላሉ ብለዋል። ተጠሪነቱ ለጠቅላይ ሚንስትሩ የሆነው ይህ ባለስልጣን ያልተገቡ የገበያ ውድድሮችን ከመቆጣጠር እስከ የቴሌኮም አገልግሎት ፍቃድ እስከመሰጠት ስልጣን ተሰጥቶታል። ለቴሌኮም ኦፕሬተሮች ፍቃድ ይሰጣል፣ የቴሌኮሚዩኒኬሽን እና ፖስታ አገልግሎት ላይ መሰማራት ለሚፈልጉም ፍቃድ ይሰጣል፤ እንዲሁም ኦፐሬተሮች ለህዝብ የሚሰጡት የአገልግሎት ደረጃን ይወስናል ይላሉ። ፍቃድ የተሰጣቸው የቴሌኮም ኦፐሬተሮች አገልግሎት የሚሰጡበትን ታሪፍ ለባለስልጣኑ ካቀረቡ በኋላ ባለስልጣኑ የመጨረሻውን ውሳኔ እንደሚሰጥበትም ተናግረዋል። መንግሥት ከፍተኛ ገቢ የሚያስገኝለትን ኢትዮ ቴሌኮምን የ በመቶ ድረሻ ለግል ለማዘዋወር ክፍት ማድረጉ ስህተት ነው የሚሉም አልታጡም። አቶ ባልቻ ግን መንግሥት በብቸኝነት ከኢትዮ ቴሌኮም ሲያገኝ ከነበረው በላይ ገቢ እንደሚያገኝ ይናገራሉ። ይህም የሚሆነው ከግብር እና ከፍሪኩዌንሲ ከሚገኝ ገቢ እንደሆነ ይናገራሉ። ለሞባይል ኦፐሬተሮች ፍቃድ የምንሰጥበት ፍሪኩዌንሲ ከፍተኛ ገቢ የሚያመጣ ነው ብለዋል። እስካሁን ኢትዮ ቴሌኮም ፍሪኩዌንሲ በነጻ እየተጠቀመ ነበር ማለት ይቻላል የሚሉት አቶ ባልቻ፤ ከአሁን በኋላ የሚመጡት ተቋማት ግን ብዙ ገንዘብ እንደሚከፍሉ ያስረዳሉ። በተጨማሪም፤ የቴሌኮም አገልግሎት አቅራቢ ድርጅቶች ወደ ሃገር ውስጥ መግባታቸው የቴሌኮም ኢንቨስትመንትን ያስፋፋል፣ የጥራት አገልግሎት ያሳድጋል፣ የቴሌኮም አገልግሎት ወጪን ይቀንሳል እንዲሁም የኢንተርኔት አገልግሎትን ያሻሽላል በማለት ጠቀሜታውን ያስረዳሉ። አቶ ባልቻ ሬባ ማናቸው አቶ ባልቻ በኤሌክትሪካል ኢንጂነሪንግ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን አግኝተዋል። በቀድሞው የኢትዮጵያ ቴሌኮሙዩኒኬሽን ኤጀንሲ ከ ዎቹ አጋማሽ ጀምሮ እስከ ተጠባባቂ ዋና ዳይሬክተርነት ባሉ በሃላፊነቶች አገልግለዋል። ለ ዓመታት በመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጅ ሚኒስቴር የስታንዳርድና ቁጥጥር ዳይሬክተር ሆነው አገልግለዋል። አቶ ባልቻ የኢትዮጵያ የኮሚኒኬሽን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሆነው ከመሾማቸው በፊት በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የቴሌ ኮም፣ ፖስታ እና ኮሚዩኒኬሽን የስታንዳርድና ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በመሆንም አገልግለዋል። ይህንን ዜና ያጋሩ ስለማጋራት
ባለፈው አንድ ዓመት ከ ሰዎች በላይ መገደላቸውን ጠቅላይ አቃቤ ህግ አስታወቀ
ሴፕቴምበር ማጋሪያ ምረጥ ባለፈው ዓ ም በመላ የአገሪቱ አካባቢዎች በተከሰቱ ግጭቶች ሰዎች ህይወታቸውን እንዳጡ ጠቅላይ አቃቤ ህግ በፌስቡክ ገፁ አስታውቋል። በግጭቶቹ ተሳትፈዋል የተባሉ ተጠርጣሪዎች ላይ ክስ ተመስርቶ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው እየታየ መሆኑንና የሚሆኑ ተጠርጣሪዎች ደግሞ እንዳልተያዙ ፤ የ ተጠርጣሪዎች ክስም በምህረት መነሳቱን በኢፌዲሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የተደራጁ ድንበር ተሸጋሪ ወንጀሎች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ፍቃዱ ፀጋ ገለጹ፡፡
በአፍ መፍቻ ቋንቋ መማርን ዛሬም፣ ነገም፣ ወደፊትም የምከራከርበት ነው ገነት ዘውዴ ዶ ር
ሴፕቴምበር ማጋሪያ ምረጥ አዲሱን ዓመት አስመልክተን ከመገናኛ ብዙኃን ጠፍተው የቆዩ ሰዎችን ማፈላለጋችንን ቀጥለናል። አዲሱ የትምህርት ፖሊሲ ሲነሳ ስማቸው አብሮ የሚነሳውን ገነት ዘውዴ ዶ ር ን ፈልገን አግኝተናቸዋል። ገነት ዘውዴ ዶ ር በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቴክኒካል ቲቸርስ ኤዱኬሽን በረዳት መምህርነት አገልግለዋል። በዚያው ዩኒቨርሲቲ ረዳት ፕሮፌሰር፣ መምህር፣ የቢዝነስ ትምህርት ክፍል ኃላፊ ሆነው ሠርተዋል። በቦስተን በንከር ሂል ኮሚዩኒቲ ኮሌጅ በትምህርት ክፍል የሥራ ልምምድ እንዳደረጉም መረጃዎች ያመለክታሉ። ታሪክ እየቀየሩ ያሉት ሴቶች ከ ዓ ም በፊት ባሉት ጊዜያት በኬንያ፤ ኬንያታ ዩኒቨርሲቲ ከሌላ ዩኒቨርሲቲ የተመደቡ ፈታኝ ሆነው አገልግለዋል። በኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ምክትል ሚንስትር፣ ከዚያም ከ በኋላ በትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ሆነው ሠርተዋል። በሕንድ የኢትዮጵያ አምባሳደርም ነበሩ። የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ድግሪያቸውን በቢዝነስ ትምህርት ከአሜሪካ አገር አግኝተዋል። የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን በኒው ሃምፕሸር ፤ ሁለተኛ ድግሪያቸው ሰፎክ ዩኒቨርሲቲ ቦስተን ነው ያጠናቀቁት። ሦስተኛ ድግሪያቸውን ከሕንድ አገር ጃዋህራል ኔህሩዩኒቨርሲቲ በዓለም አቀፍ ግንኙነት አግኝተዋል። በትምህርት ሚኒስቴር የመጀመሪያዋ ሴት ሚንስትርም እንደነበሩ ገልፀውልናል። ገነት ዘውዴ ዶ ር ሁለት መጻሕፍትን ጽፈዋል። አንዱ በሴቶች ላይ፣ ሌላው ደግሞ በትምህርት ፖሊሲው ላይ የሚያተኩር ነው። የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ሴቶች ትግል የሚል ሲሆን በአማርኛ ተተርጉሟል። ሁለተኛው መጽሐፍ ወደ አማርኛ ባይመለስም ከሁለት ዓመታት በፊት ነው የወጣው። የሚልና ስለ ትምህርት ፖሊሲው የሚያትት ነው። ከርሳቸው ጋር ያደረግነውን አጭር ቆይታ እነሆ። አሁን ምን ላይ ነው ያሉት ምን እየሠሩ ነው አሁን ጡረታ ወጥቻለሁ። ጡረታ ከወጣሁ ሦስት ዓመት ሆኖኛል፤ ነገር ግን ጡረታ ከወጣሁ ጊዜ ጀምሮ የሴቶች ልማታዊ ስትራቴጅክ ሴንተር አቋቁሜ እዚያ ላይ በጥናት እና የቅስቀሳ ሥራ እየሠራሁ ነው። ተቋሙ ምንድን ነው የሚያከናውነው በዝርዝር ይንገሩኝ እስኪ በሴቶች ሕይወት ዙሪያ ጥናቶች እያደረኩ ነው። አንዳንድ ጊዜ ሥልጠናም እንሰጣለን የአመራርነትና የሥራ ፈጠራ ሥልጠናዎች አሉት። አንዳንድ ጊዜ ደግሞ በሚዲያም የቅስቀሳ ሥራ እንሠራለን ስለ ሴቶች ሕይወት። በሚዲያ ላይ የሚተላለፍ ፕሮግራም ነበረዎት ልበል አዎ፤ የቴሌቪዥን ፕሮግራም ነበረኝ። እናንተም ቢኖራችሁ እንዴት ደስ ይለኝ ነበር። የሕይወት ወግ የሚል በዋልታ ቴሌቪዥን የሚቀርብ ነበር። ነገር ግን በ ስፖንሰር የገንዘብ ድጋፍ መቋረጥ ምክንያት አሁን ተቋርጧል ለትንሽ ጊዜ። በጣም ጥሩ ፕሮግራም ነበር። ከአንድ ዓመት በላይም ተላልፏል። በፕሮግራሙ በሴቶች ሕይወት ዙሪያ ውይይቶች ነበሩ። የተለያዩ የሴቶችን ጉዳዮች እያነሳን ነበር የምንወያየው። በድህነት ምክንያት ቀረ። ትምህርት ዕድሜን እንደሚያስረዝም በጥናት ተረጋገጠ በትምህርቱ ዘርፍ ለበርካታ ዓመታት አገልግለዋልና ከዚህ ጋር በተያያዘ የሚሠሩት አለ ይሄ አይበቃኝም እንዴ በዚህ ዕድሜ ዘለግ ያለ ሳቅ ይሄ በጣም ብዙ ሥራ ነው። በጣም ብዙ ጥናት፣ ሥልጠና፣ ቅስቀሳ አለው ለአሮጊት ይሄ አነሰው ብለሽ ነው ሳቅ ዕድሜዎ ስንት ነው ዶክተር ዕድሜ አይጠየቅም ይባላል። ግን ግድ የለም። አሁን እኔ ባል ስለማልፈልግ ግድ የለም። ሳቅ ዓመቴ ነው። አማካሪ ሆነው የሠሩበት አጋጣሚ አለ አይ የለም። ምክር ለጠየቀኝ ሰው ግን እሰጣለሁ። ስለ ልጅነት፣ ስለ ሴትነት፣ ስለ አሮጊትነት ምናምን የትምህርት ፖሊሲው ከእርስዎ ጊዜ ጀምሮ እንደተዳከመ ይወራል፤ እርስዎም ላይ ትችት ሲቀርብ ይሰማል። እንዲያውም እርስዎ ሚንስትር በነበሩበት ጊዜ በተቀረፀው ፖሊሲ እየተማሩ ያሉት ትውልዶች የገነት ዘውዴ ልጆች የሚል ተቀፅላ ወጥቶላቸዋል። እርስዎ ይሰማሉ ስለዚህ እሰማለሁ፤ ግን የለሁበትም። ከትምህርት ሥርዓቱ ከወጣሁኝ ዐሥር ዓመታትን በሕንድ ዲፕሎማት ነበርኩ። አሁን ጡረታ ከወጣሁ ሦስት ዓመቴ ነው። ስለዚህ ከትምህርት ሥርዓቱ ዓመታት ተለይቻለሁ። እናም እሰማለሁ ግን በዚህኛው ሥራ ሴቶች ላይ ስለማተኩር ብዙም እንትን አላልኩም መስማቱን ግን እሰማለሁ። ሲሰሙ የሚሰጡት ምላሽ ምንድን ነው ያው እንግዲህ ጊዜ ኖሮኝ ቁጭ ብየ የሚባለው ነገር እውነት ነው፤ አይደለም ምንድ ነው ችግሩ ብዬ ባጠናው ደስ ይለኝ ነበር። ነገር ግን አላጠናሁትም። ወደ ፊት ለማጥናት አላሰቡም እሱ እንግዲህ እንዴ እኔ አኮ አርጅቻለሁ ሳቅ ምን ማለትሽ ነው የተሰማኝን ትምህርት ፖሊሲው ምን እንደነበር፣ እንዴት እንደነበር ጽፌያለሁ። ከዚያ በኋላ የፈለገ ሰው ያንን እየጻፈ ደግሞ ይቀጥል። ሁል ጊዜ አንድ ሰው ላይ ብቻ አይደለም መቀባበል። አለ አይደል የድምፅዎ ጉልበት ግን እርጅና ላይ ያሉ አይመስሉም ሳቅ ስለዚህ እኔ የሚሰማኝን መጽሐፍ ላይ አስቀምጫለሁ። ከዛ በኋላ ደግሞ እየተቀባበሉ፤ ያንን እያስተካከሉ፤ እየተቀባበሉ መሄድ ደግሞ የአዲሱ ትውልድ ነው። አንድ ሰው ብቻ መሆን የለበትም። አይመስልሽም ከዚሁ ከትምህርት ፖሊሲ ሳንወጣ፤ ሚንስትር በነበሩበት ጊዜ የተለያዩ ብሔር ብሔረሰቦች በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው እንዲማሩ ሐሳቡን ያመጡት እርስዎ ነዎት ይባላል። እዚህ ላይ ምን ይላሉ ይሄ እኮ እኔ ዝም ብዬ በጭንቅላቴ ያመጣሁት አይደለም። የዩኔስኮ፣ የዓለም አቀፍም ትኩረት ነው። ትምህርት እየተስፋፋ፣ ዘመናዊ እየሆነ በመጣ ቁጥር በጣም ብዙ ምርምሮች ይወጣሉ። እናም ልጆች መጀመሪያ በአፍ መፍቻ ቋንቋ ነው መማር ያለባቸው። ትምህርት ደግሞ ማሰብን ፣ ማሰላሰልን ይጠይቃል። የሰው ልጅ የሚያስበው የሚያሰላስለው በአፍ መፍቻ ቋንቋው ነው። በመሆኑም ይህ የዩኔስኮም፣ የዓለም አቀፉም እንትን ነው ገነት ስብሰባ ላይ ዱብ ያደረገችው አይደለም። በወቅቱ ብዙ እንደተሟገቱ ስለሰማሁ ነው በጣም በጣም አሁንም ቢሆን ነገም ከነገ ወዲያም እሟገታለሁ። ልንገርሽ አይደል እኔ አንደኛ ደረጃም አይደለም፤ ሁለተኛ ደረጃም እንደዚያ እንዲሆን ከአሁኑ ጀምረን እያሰብን የቋንቋ አካዳሚዎችን እያቋቋምን ምን እያልን ዩኒቨርሲቲዎችም በቋንቋቸው እንዲሆን ብዬ አምናለሁ የሕንድን ተሞክሮ ያነሳሉ እንዲህ መሆኑ ችግሮች የሉትም ብለው ያስባሉ አዎ ችግሮች ይመጣሉ። ችግር የሌለው ነገር አለ አንዴ ችግር እየፈታን እንሄዳለን እንጅ፤ ችግር ይመጣል ብለን ከችግር አንሸሽም። ቋንቋ የማንነት ጥያቄ ብቻ ሳይሆን ወደ ትምህርት ፣ ወደ ሳይንስ ስንሄድ በጣም ትልቅ መሣሪያ ነው። እኔ ዛሬም ፣ ነገም፣ ከነገ ወዲያም የምከራከርበት ነው። በእኛ አገር ተጨባጭ ሁኔታ እንዲህ መሆኑ አይለያየንም ለጋራማ፤ የጋራ ቋንቋ አለን እኮ የፌደራል ቋንቋው አማርኛ እና እንግሊዝኛ ነው። ትምህርት ላይ ሲሆን ግን በእንግሊዝኛ ቋንቋም አይደለም ። እስከ አምስት ስድስት ዓመቱ በቋንቋው ሲቦርቅ የነበረን ልጅ አምጥተሽ፤ አንደኛ ክፍል አስገብተሽ በሌላ ቋንቋ ተማር ስትይው ፍትሃዊ ነው የፍትሃዊነት ጉዳይ ብቻ ሳይሆን ይገባዋል እና ቀላል ነገር አይደለም። በጣም ከቋንቋው ጋር የተያያዘ ነው። እኔ እንደ ቀላል ለምን እንደሚያዩት አይገባኝም። ስለዚህ ነገም ከነገ ወዲያም የምከራከርበት ጉዳይ ነው። እስኪ አሁን ደግሞ፤ የግል ሕይወትዎን ያጫውቱኝ የሁለት ሴቶች ልጆች እናት ነኝ። አሁን ደግሞ ሁለቱ ሴት ልጆቼ የሦስት ልጆች አያት አድርገውኛል። በግል ሕይወቴ በጣም ደስተኛ ነኝ ያው ትዳር ፈት እንደሆንኩ ታውቂያለሽ ብዬ ነው። ሳቅ ግን በጣም ደስተኛ ነኝ። ከልጆቼ ጋር ጥሩ ግንኙነት አለኝ። በተለይ ከልጅ ልጆቼ ጋር በቃ ፍቅር ይዞኝ ፍቅር ወደታች አይደል ከእነሱ ጋር ነው ትርፍ ጊዜዬን የማሳልፈው። በሕይወት ያሉ ጓደኞቼም አሉ ከእነርሱም ጋር እ ማንበብ እወዳለሁ፤ አነባለሁ ይሄ ነው የግል ሕይወቴ። ምን ዓይነት መጽሐፍ ነው የሚያነቡት ማንኛውንም። በኢትዮጵያ የተጻፉም በዓለም ላይ ያሉ የኢኮኖሚ፣ የትምህርት ምናምን ድሮ ወጣት ሆኜ ልብ ወለድ ነበር የምወደው፤ አሁን ግን ጠንከር ያሉ መጻሕፍትን ልብ ወለድ ድሮ ልጅ እያለሁ እወድ ነበር፤ አሁን ግን አረጀሁ ሳቅ ግን ምርጫዎ የማን ነበር በእኛ ግዜ አጋታ ክርስቲ፣ ዳኔላ ስቲል፤ ከኢትዮጵያ ደግሞ ፍቅር እስከመቃብርን ። ፍቅር እስከ መቃብርን ሦስት ጊዜ አንብቤዋለሁ። ሦስት ጊዜም ሳነበው አዳዲስ ነገር አግኝቸበታለሁ። ኦሮማይ ፣ ወንጀለኛው ዳኛ ድሮ አያቴ መጽሐፍ ታነብ ነበር፣ እናም መጽሐፍ ማንበብ ያስተማረችኝ እርሷ ናት። ሙዚቃስ ሙዚቃና እስክስታማ በጣም እወዳለሁ። እስክስታው አለ። አሁን ግን እያረጀሁ ጉልበቴም እየቀነሰ ብዙም አይደለሁ። ግን አሁንም ቢሆን ሙዚቃ ከሰማሁ ነሸጥ ያደርገኛል። እነ አስቴርን፣ ብዙዬን፣ ጥላሁን ገሠሠን እና በተለይ ደግሞ የበዛወርቅን ግጥሞቿን በጣም እወደዋለሁ። በተለይ አንድ ግጥም አላት መጽሐፌም ላይ ጠቅሸዋለሁ። የማነሽ ይሉኛል የማን ልበላቸው፣ ብቻየን ብቀርስ ምን አስጨነቃቸው የሚለውን። የተለየ ምክንያት አለው እንዴ ለምን መሰለሽ እኔ ከሴት ልጅ ጋር ነው የማያይዘው። ሁልጊዜ ሴት የማነሽ የሰው ነሽ ነው እኮ። ዕቃ ነሽ ነው፤ የወንድ ዕቃ ነሽ ነው እኮ። ድምጿንም እወደዋለሁ። ከአዳዲሶቹ ቴዲ አፍሮ ደስ ይለኛል። ተያያዥ ርዕሶች
ኢራን የአውሮፓ አገራትን ውንጀላ አጣጣለች
መስከረም ኢማኑኤል ማክሮን፣ አንግላ መርከልና ቦሪስ ጆንሰን በተባበሩት መንግሥታት ድረጅት ዋና ጽሕፈት ቤት ፈረንሳይ፣ ጀርመን እና ዩናይትድ ኪንግደም በጥምረት፤ በሳዑዲ ነዳጅ ማቀነባበሪያ ላይ ከደረሰው ጥቃት ጀርባ ያለችው ኢራን ናት ቢሉም፤ ኢራን ውንጀላቸውን አጣጥላዋለች። የኢራን የውጪ ጉዳይ ሚንስትር የሦስቱን አገራት ክስ የአሜሪካን ከንቱ ክስ ያስተጋባ ሲሉ ውድቅ አድርገዋል። አሜሪካ ጦሯን ወደ ሳዑዲ ልትልክ ነው የአውሮፓ አገራት መሪዎች እንዳሉት፤ ከጥቃቱ ጋር በተያያዘ ከኢራን ውጪ ማንም ላይ ጣት መቀሰር አይቻልም። ኢራን የምትደግፈው የየመኑ የሁቲ አማጽያን ቡድን ጥቃቱን የሰነዘርኩት እኔ ነኝ ሲል ኃላፊነቱን ቢወስድም፤ አሁንም ተጠያቂ የተደረገችው ኢራን ናት። ስምንት ሰው አልባ አውሮፕላኖች እና ሰባት ሚሳኤሎች የሳዑዲን የነዳጅ ማቀነባበሪያ ከመቱ በኋላ፤ ሳዑዲ እንዲሁም አሜሪካ ኢራንን ወንጅለዋል። ኢራን በበኩሏ በጥቃቱ እጄ የለበትም ማለቷ ይታወሳል። መሪዎቹ ምን አሉ የእንግሊዙ ጠቅላይ ሚንስትር ቦሪስ ጆንሰን፣ የፈረንሳዩ ፕሬዘዳንት ኢማኑኤል ማክሮን እና የጀርመኗ መራሔተ መንግስት አንግላ መርኬል በጋራ በሰጡት መግለጫ፤ ኢራን ለጥቃቱ ተጠያቂ ናት ብለዋል። እየተካሄደ ያለውን ምርመራ እንደሚደግፉም አሳውቀዋል። ኢራን በኒውክሌር ፕሮግራሟ ላይ ለድርድር ዝግጁ መሆን የሚጠበቅባት ጊዜ ላይ ነን ሲሉም መሪዎቹ ተናግረዋል።
አሥመራን አየናት፡ ከቅኝ ግዛት በኋላ ባለችበት ያለችው አሥመራ
መስከረም ይህንን ለማጋራት በ ትዊተር ይህንን ለማጋራት በ ዋትስአፕ ቢቢሲ በኤርትራ አዘጋጅነት ሲካሄድ የነበረውን ከ ዓመት በታች የሴካፋ ውድድርን እንድንዘግብ ፍቃድ ተሰጥቶን ወደ ኤርትራ አቅንተን ነበር። በኤርትራ በነበርን ቆይታ ያየነውን እና የሰማነውን በሦስት ክፍሎች አሰናድተናል። የመጀመሪያው ክፍል እንደሚከተለው ቀርቧል። ማስታወሻ፡ በኤርትራ በነበረን ቆይታ የዘገባ ርዕሶቻችን እና እንቅስቃሴዎቻችን የተገደቡ ነበሩ። በጽሁፉ ውስጥ የተጠቀሱት ዓመታት እንደ ጎሮጎሳውያኑ አቆጣጠር ነው። መግቢያ ከ ዎቹ መጀመሪያ እስከ በነበሩት ዓመታት ቅኝ ገዢዎቹ አውሮፓዊያን፤ አፍሪካን የመቀራመት እቅዳቸውን የወጠኑበት እና ያሳኩበት ዓመታት ነበሩ። ላይ ጣሊያን ኤርትራ የእርሷ ቅኝ ግዛት መሆኗን አወጀች። ዎቹ መጀመሪያ ላይ ሞሶሎኒ ወደ ስልጣን መምጣቱን ተከትሎ ኤርትራ የአዲሲቷ ሮማ ግዛት አካል ሆነች። ከአምስት አስርት ዓመታት በላይ በኤርትራ የቆየው የጣሊያን ኃይል፤ በኤርትራ ቆይታው በመንገድ፣ በባቡር እና በህንጻ ግንባታዎች ላይ ተሳትፏል። በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት በ ዓ ም ላይ የእንግሊዝ ጦር የጣሊያን ጦርን ከረን ላይ ድል አደረገ። ጣሊያን እና አጋሮቿ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ሽንፈትን መከናነባቸውን ተከትሎ፤ ጣሊያን ኤርትራን ጨምሮ በአፍሪካ የነበሯትን ቅኝ ግዛቶች ለመልቀቅ ተገደደች። ከጣሊያን ቅኝ ግዛት በኋላ ኤርትራ ከ ያሉትን ዓመታት በእንግሊዝ ጦር አስተዳደር ስር ነበረች። በወቅቱ ኤርትራዊያን ነጻ ኤርትራን ማየት ናፍቀዋል። እንግሊዝ በበኩሏ ኤርትራ በኢትዮጵያ እና በሱዳን መካከል እንድትከፈል ፍላጎቷ ነበር። አሜሪካ ግን ኤርትራ በፌዴሬሽን መልክ ከኢትዮጵያ ጋር እንድትዋሃድ ምክረ ሃሳብ አቀረበች። የኃያሏ አሜሪካ ፍላጎት ተግባራዊ ሆኖ ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር በፌዴሬሽን መልክ ተዋሃደች። ሉዓላዊ የሆነች ሃገር መፍጠርን ግብ ያደረጉ ኤርትራዊያን ከተለያዩ ሁለት የኢትዮጵያ መንግሥታት ጋር ለ ዓመታት ያክል የትጥቅ ትግል ሲያደርጉ ቆይተው እአአ ላይ የኤርትራን ነጻነትን አወጁ። ፕሬዝደንት ኢሳያስ ከሁለት አዛውንት መካከል ሆነው። የተራዘመው የኤርትራዊያን የትጥቅ ትግል በዓለማችን ከታዩ እጅግ ውጤታማ የሽምቅ ውጊያዎች አንዱ ነው ይባልለታል። ላይ ነጻነትን የተቀናጀችው ኤርትራ ላይ ሕዝብ ውሳኔ ከተካሄድ በኋላ ነበር በይፋ ነጻነቷን አውጃ በተባበሩት መንግሥታት እውቅና የተቸራት። በተባበሩት መንግሥታት በቅርበት ክትትል የተደረገበት ሕዝበ ውሳኔ፤ በመቶ የሚሆኑት ኤርትራውያን ነጻነትን እንሻለን ሲሉ ድምጻቸውን ሰጥተዋል። ከመኪኖች ይልቅ ብስክሌቶች የሚበዙባት ከተማ በሁለቱም ወገን ብዙ ደም ያፋሰሰው የኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ተቀሰቀሰ። ለሁለት ዓመታት ገደማ በዘለቀው ጦርነት በ ሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በሁለቱም ወገን ለሞት ተዳርገዋል። የአልጀርሱ ስምምነት በጦር ግንባር ላይ የነበረውን ጦርነት ያስቁመው እንጂ፤ ለ ዓመታት በሁለቱ ሃገራት መካከል ሰላምም ጦርነትም የሌለበት ሁኔታ ውስጥ ቆይተዋል። የጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ወደ ስልጣን መምጣትን ተከትሎ በሁለቱ ሃገራት መካከል ቆይቶ የነበረው ቁርሾ ተገፎ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነቱ ተጀምሯል። እኛም ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ አሥመራ አቅንተናል። አሥመራ ቆሻሻ የማይታይባት፤ ጽዱ ከተማ። ፃዕዳ አሥመራ ሃገሬው አሥመራን ፃዕዳ አሥመራ እያለ ይጠራታል። ፃዕዳ በትግርኛ ነጭ ማለት ነው። እውነት ነው አሥመራ ንጹሕ ነች። ቆሻሻ የማይታይባት፤ ጽዱ ከተማ። በእድሜ ጠገብ ህንጻዎች የተሞላችው አሥመራ፤ ከሁለት ዓመታት በፊት በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስ እና የባህል ድርጅት ዩኔስኮ ታሪካዊ ከተማ በመባል የዓለም የቅርስ መዝገብ ላይ ተመዝግባለች። የኤርትራ መዲና አሥመራ ከ ዎቹ ጀምሮ የቅኝ ገዢው የጣሊያን ጦር መቀመጫ ሆና ማገልገል ጀምራ ነበር። ቅኝ ገዢው በአሥመራ ጣሊያናዊ በሆነ የሥነ ሕንጻ ጥበብ ስልት ግንባታዎች ማከናወን ጀመረ። ሰማይ ላይ ወልዳ አሥመራ የምትታረሰው ኢትዮጵያዊት በወቅቱ ቅንጡ የሆኑ ለመንግሥት አገልግሎቶች የሚውሉ ህንጻዎች፣ አብያተ ክርስቲያናት፣ መኖሪያ ቤቶች፣ ሆቴሎች እና የሲኒማ ቤቶች ግንባታ ተከናውነዋል። ከ እስከ ድረስ የተገነቡት እነዚህ ህንጻዎች ዘመን ተሻግረው ዛሬ ላይ ታሪክን ያስታውሳሉ። የነዋሪው ቆሻሻን የመጠየፍ ባህሪ ካለው የፍሳሽ ማስወገጃ ሥርዓት ጋር ተደማምሮ ከተማዋን ንጹህ አድርጓታል። ጎዳናዎቿ ንጹሕ ናቸው። ስለዚህም የአፍንጫን ሰላም የሚነሳ ጠረን በአሥመራ ከተማ አልገጠመንም። በጥንቃቄ በመስመር የተተከሉት ዘንባባ እና ሽባካ ተክሎች ሌላኛው የከተማዋ ውበት ናቸው። ቅኝ ገዢዎቹ ጣሊያኖች በአሥመራ አሻራቸውን ጥለው ካለፉባቸው ነገሮች አንዱ የፍሳሽ አወጋገድ ሥርዓት ግንባታ አንዱ ነው። ፍሳሽ ማስወገጃ ቱቦዎች በከተማዋ ጎዳናዎች ሥር ተገንብተው እንደሚገኙ ከነዋሪዎች ሰምተናል። በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግሥት ከተማዋ ጠዋት ከሥራ ስዓት በፊት ትታጠብ እንደነበርም ተነግሮናል። ይህ ብቻም አይደለም፤ በአሥመራ ሲጓዙ ቢያድሩ አባ ከና የሚልዎ አይኖርም። ሃገሬውም ሆነ የውጪ ዜጋው ከመሸ እንደፈቀደው በእግሩ ይጓዛል። በአሥመራ አንድ ምሽት እንዳሳለፉ ስለከተማዋ ሰላማዊነት ሌላ እማኝ አያሻዎትም። ትሮቪላ፣ ፍራንሲስኮ፣ ዳንተ፣ ቪሊያጆ፣ ሳንታ ዓና፣ ቦላጆ እኚህ ስሞች በሃገረ ጣሊያን የሚገኙ የከተማ ስሞች አይደሉም፤ የአሥመራ ሰፈሮች መጠሪያ እንጂ። የአሥመራ ሰፈሮች ብቻ አይደሉም፤ ብዙ የአሥመራ ካፍቴሪያዎችና ምግብ ቤቶች ጨምር መጠሪያቸውን ያገኙት ከጣሊያን ቋንቋ ነው። ሌላኛው የአሥመራ ውበት በጥንቃቄ በመስመር የተተከሉት ዛፎች ናቸው። ዘንባባ እና ሽባካ ተብሎ የሚጠራው ዛፍ ለከተማዋ ልዩ ገጽታን አጎናጽፏታል። የብሌን ብሄርሰብ ተወላጆች ግራ የአፍር ወጣት እየጨፈረች ቀኝ ኤርትራ ኤርትራ በደቡብ ከኢትዮጵያ፣ በደቡብ ምሥራቅ ከጅቡቲ፣ በምዕራብ ከሱዳን፣ በምሥራቅ በኩል ደግሞ ከቀይ ባሕር ጋር ትዋሰናለች። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኤርትራ የህዝብ ብዛት ወደ ሚሊዮን ይገመታል ይላል። ወደ ሺህ የሚጠጉት ደግሞ መኖሪያቸውን በመዲናዋ አድረገዋል። በስድስት ዞኖች የምትከፋፈለው ኤርትራ፤ ትግር፣ ትግርኛ፣ አፋር፣ ኩናማ፣ ብሌን፣ ሳሆ እና ራሻይዳን ጨምሮ እውቅና የሚሰጣቸው ብሔሮች ኖሩባታል። በኤርትራ የሚገኘው አፋር በጅቡቲ እና ኢትዮጵያ ጋር ከሚኖሩት አፋሮች ጋር ተመሳሳይ ቋንቋ እና ባህል አላቸው። የራሻይዳ ሴት ከአምስት ዓመቷ ጀምሮ ከዓይኗ በስተቀረ የተቀረ ፊቷን በደማቅ ጨሌ ባማረ ጨርቅ ትሸፍናለች። ከተቀሩት የኤርትራ ብሔረሰቦች በመልክ እና በአኗኗር ዘዬ ለየት የሚሉት የራሻይዳ ህዝቦች ናቸው። መነሻቸው ሳዑዲ አረቢያ እንደሆነ የሚነገርላቸው ራሻይዳዎች አረብኛ ቋንቋ ተናገራሪዎች እና የእስልምና ዕምነት ተከታዮች ናቸው። አርብቶ አደር እና ከመካከለኛው ምሥራቅ የሚገቡ ሸቀጣ ሸቀጦችን በጭነት መኪና በመነገድ የሚታወቁት ራሻይዳዎች ቀይ ባህርን ተከትለው በኤርትራ በረሃማ ቦታዎች ላይ ይኖራሉ። የራሻይዳ ሴት ከአምስት ዓመቷ ጀምሮ ከዓይኗ በስተቀር የተቀረ ፊቷን በደማቅ ጨሌ ባማረ ጨርቅ ትሸፍናለች። የሰዓት እና ቀን አቆጣጠር አገልግሎት ፍለጋ አርፍደው በደረሱበት ስፍራ ነገ ጠዋት ሰዓት ላይ ኑ ልትባሉ ትችላለችሁ። ኤርትራዊያን ሰዓት የሚቆጥሩት ልክ እንደ ምዕራባውያኑ ነው። የቀን አቆጣጠር ሥርዓታቸውም ቢሆን እንደ ጎርጎርሳዊያኑ ነው። የኤርትራ መገበያያ ገንዘብ ናቅፋ ባለ ፣ ፣ ፣ ፣ እና ኖቶች አሉት። መገበያያ ገንዘብ የኤርትራ መገበያያ ገንዘብ ናቅፋ ይባላል። ባለ ፣ ፣ ፣ ፣ እና ኖቶች አሉት። አንድ የአሜሪካ ዶላር በ ናቅፋ በሕጋዊ መንገድ ይመነዘራል። በኤርትራ ዶላር በጥቁር ገበያ ላይ ለመመንዘር መሞከር ቀይ መስመር እንደማለፍ ከባድ ጥፋት ነው። ዶላር መመንዘር የሚቻለው በብቸኛው የኤርትራ ንግድ ባንክ ብቻ ነው። በአሁኑ ወቅት በባንክ እና በጥቁር ገበያ ላይ ያለው ልዩነት ሰፊ አይደለም። አንድ ዶላር በጥቁር ገብያ ላይ ናቅፋ ብቻ ነው የሚመነዘረው። ሁነኛ የትራንስፖርት አማራጭ ብስክሌቶች ቢሆኑም፤ አውቶብሶች እና ቢጫ ታክሲዎችም ደንበኞቻቸውን ከቦታ ቦታ ያመላልሳሉ። የትራንስፖርት አማራጮች እንደ ዝርግ ሳህን ለጥ ባሉት የአሥመራ ጎዳናዎች ነዋሪው ብስክሌቶች እንደ ሁነኛ የትራንስፖርት አማራጭ የመረጠ ይመስላል። ትልቅ ትንሹ በብስክሌት ሽር ይላል። ቦርሳ በጀርባቸው ያነገቡ ታዳጊዎች በብስክሌት ወደ ትምህርት ቤት ያቀናሉ። ሰራተኛው ጉዳዩን ለመፈጸም በብስክሌት ይንቀሳቀሳል። አውቶብሶች እና ቢጫ ታክሲዎችም ደንበኞቻቸውን ከቦታ ቦታ ያመላልሳሉ። የዛሬ ዓመት የኮ ል መንግሥቱ አውሮፕላን ለምን አልጋየም በኤርትራ አነስተኛ ደሞዝ፣ ወደ ሃገር ውስጥ በሚገቡ መኪኖች ላይ የሚጫነው ከፍተኛ ግብር እንዲሁም ከፍተኛ የነዳጅ ዋጋ ተደማምረው የግል መኪና ባለቤት መሆንን ከባድ ያደርጉታል። በዚህም በከተማዋ የሚስተዋሉት የተሽከርካሪዎች ቁጥር እጅግ አነስተኛ የሚባል ነው። ለመኪኖች በቅደም ተከተል የሚሰጠውን የሰሌዳ ቁጥር ከግምት ውስጥ በማስገባት፤ በኤርትራ የሚገኙ የግል መኪኖች ብዛት ከ ሺህ እንደማይዘሉ ማስላት ይቻላል። አሥመራ የትራፊክ መጨናነቅ የማያቃት ከተማ በመሆኗ ትራፊክ አልባዋ መዲና የሚል ስያሜ ተሰጥቷታል። ወደየትኛውም አቅጣጫ መኪና ይዘው ቢንቀሳቀሱ በሌሎች የአፍሪካ ከተሞች የሚያስተውሉትን አይነት የትራፊክ መጭናነቅ አይመለከቱም። ፒዛ ወይስ ላዛኛ የሚበላ ፍለጋ ወደ አንዱ ሬስቶራንት ጎራ ቢሉ፤ በምግብ ዝርዝር አማራጭ ውስጥ በቅድሚያ ተዘርዝረው የሚመለከቱት እነ ፓስታ፣ ላዛኛ እና ፒዛን የመሳሰሉ ምግቦችን ነው። ኤርትራዊያን የሚያሰናዱት ፓስታ እና ፒዛ እጅግ ድንቅ ጣዕም አላቸው። እንጀራ ከከጀሉ እንዲሁ በቀላሉ የሚያገኙት ሳይሆን ባህላዊ ምግብ የሚያዘጋጅ ምግብ ቤት መፈለግ ግድ ይልዎታል። የአሥመራ መስህብ ስፍራዎች እግር ጥሎዎት ወደ አሥመራ ካቀኑ ከተማዋ ለእንግዶቿ ጀባ ከምትላቸው በርካታ የመስህብ ስፍራዎች ቢያንስ የሚከተሉትን ሳይመለከቱ አይመለሱ። የሥነ ሕንጻ ባለሙያው ፊያትን ለመገንባት እቅዱን ለአከባቢው መስተዳድሮች ሲያቀርብ፤ ሜትር ርዝመት ያላቸው ክንፎች ያለድጋፍ ማቆም አይቻልም በማለት እቅዱን ውድቅ ተደርጎበት ነበር። ፊያት ታግሊኤሮ ፊያት ታግሊኤሮ ተገንብቶ የተጠናቀቀው እአአ ሲሆን የነዳጅ ማደያ፣ ጋራዥ እና የመኪና እጥበት አገልግሎት ይሰጥበት ነበር። ከታሪካዊነቱ በተጨማሪ ይህን በአውሮፕላን ክንፍ ቅርጽ የተገነባን ግንባታ ለየት የሚያደርገው፤ ወደ ጎን ሜትር የሚረዝሙት ክንፎቹ ያለ ምሶሶ መቆማቸው ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኤርትራ ውስጥ መኪና ሲያሽከረክሩ የሚያሳየው ቪዲዮ ፊያት የተገነባው በጣሊያኒያዊው የሥነ ሕንጻ ባለሙያ ጁሴፔ ፔታዚ ሲሆን፤ አስጎብኚዎች ስለዚህ ህንጻ ግንባታ አንድ አስደናቂ ታሪክ ይናገራሉ። የሥነ ሕንጻ ባለሙያው ጁሴፔ ፊያትን ለመገንባት ሃሳቡን ለአካባቢው መስተዳድሮች ባቀረበላቸው ወቅት፤ ሜትር ርዝመት ያላቸው ክንፎች ያለድጋፍ ማቆም አይቻልም በማለት እቅዱን ውድቅ አደርገውበት ነበር ይላሉ። በዚህ የተበሳጨው ጁሴፔ ይሄ ግንባታ ከፈረሰ እራሴን አጠፋለሁ ብሎ ዝቶ ንድፉን ከልሶ ቋሚ ድጋፎችን ያስገባ በማስመሰል ግንታውን መጨረሱ ይነገራል። ፊያት በወቅቱ ከአሥመራ ተነስተው ወደ ኢትዮጵያ እና የወደብ ከተሞች ለሚያቀኑ መኪኖች ነዳጅ የሚሞሉበት ብቸኛው ስፍራ ነበር። ዛሬ ላይ ከ ዓመታት በኋላ አገልግሎት ሳይሰጥ ብቻውን ተትቶ ቆሞ ይገኛል። አሥመራ የቅንጡ የሲኒማ፣ የቲያትር ቤቶች፣ የሬስቶራንቶች እና ካፍቴሪያዎች መገኛ ከተማ ነበረች። የአሥመራ ሲኒማ ቤቶች አሥመራ ዛሬ ላይ ሲያጤኗት ጭር ያለች ከተማ ናት። ከብዙ አስርት ዓመታት በፊት የነበራት ገጽታ ግን ሌላ ነበር። ቅንጡ የሲኒማና የቲያትር ቤቶች እንዲሁም የሬስቶራንቶች እና ካፍቴሪያዎች መገኛ ከተማ ነበረች። ዛሬ ላይ ባዷቸውን የቀሩት እነ ሲኒማ ሮማ፣ ሲኒማ ካፒቶል፣ ኦዲዮን ሲኒማ እና ሲኒማ አሥመራ ለዚህ እማኝ ናቸው። በ ዎቹ እና ዎቹ የተገነቡት እነዚህ ሲኒማ ቤቶች፤ በዘመናቸው አሉ የተባሉ የእንግሊዝኛ እና ጣሊያንኛ ፊልሞች የሚታዩባቸው ነበሩ። አሁን ላይ ገሚሱ ባዶውን ቀርቷል፤ የተቀሩት ደግሞ ሃገር በቀል ፊልሞችን እና የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የእግር ኳስ ጨዋታዎችን ያሳያሉ። በተለያዩ ወቅቶች በኤርትራ በተደረጉ ጦርነቶች ከጥቅም ውጪ ሆኑ የጦር ተሽከርካሪዎች በአንድ ሥፍራ ተሰብስበው ይገኛሉ። የታንክ መቃብር ስፍራ በተለያዩ ወቅቶች በኤርትራ የተደረጉ ጦርነቶች ምን ያክል አስከፊ እንደነበሩ ይህን ስፍራ በመጎብኘት መገንብ ይቻላል። በዚህ ታንክ ግሬቭ ያርድ የታንክ የመቃብር ቦታ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ በጦርነት የወደመ የጦር ተሽከርካሪ አይነት አንድም የቀረ አይመስልም። ከታንክ እስከ አየር መቃወሚያ፤ ከአውቶቡስ እሰከ መድፍ፤ ብቻ ሁሉም አይነት ተቃጥሎ እና ወላልቆ በአንድ ቦታ ላይ ተሰብስበው ይገኛሉ። ቀረብ ብለው ሲመለከቱ የወደሙትን የተሽከርካሪ አካላት መኖሪያ ቤታቸው ያደረጉ ሰዎችን ያስተውላሉ። በቅኝ ግዛት ወቅት ህይወታቸው በኤርትራ ያለፈ ጣሊያውያን ይቀበሩ የነበረበት ሥፍራ። የጣሊያኖች የመቃብር ስፍራ በቅኝ ግዛት ወቅት ህይወታቸው በኤርትራ ያለፈ ጣሊያዊያን ይቀበሩ የነበረበት ሥፍራ ነው። በጥሩ ሁኔታ ተይዞ የሚገኘው ይህ የመቃብር ስፍራ አሁንም ድረስ ከጣሊያን ድረስ እየመጡ በዘመዶቻቸው የመቃብር ላይ የአበባ ጉንጉን የሚያኖሩ ሰዎች እንዳሉ ይነገራል። ካቴድራል ቤተክርስቲያን፣ ሲኒማ ሮማ፣ እንዳ ማርያም ቤተክርስቲያን እና ሌሎች የጣሊያን ቅኝ ግዛት ዘመን የሥነ ሕንጻ ጥበብ ያረፈባቸው የሚጎበኙ ታሪካዊ ስፍራዎችም በአሥመራ ይገኛሉ። ቢቢሲ ማስተባበያ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በአሥመራ ጎዳናዎች ላይ መኪና ሲያሽከረክሩ ታይተዋል
ጁላይ ማጋሪያ ምረጥ ለጉብኝት ወደ ኤርትራ የተጓዙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ መኪና እያሽከረከሩ ከኤርትራው ፕሬስዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር የሚታዩበት ቪዲዮ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ መነጋገሪያ ሆኗል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ መኪና እያሽከረከሩ ከውጪ ሃገር መሪ ጋር ሲታዩ ይህ የመጀመሪያቸው አይደለም። ባለፈው ዓመትም የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ልዑል ሞሐመድ ቢን ዛይድ ኢትዮጵያን በጎበኙበት ወቅትም ጠቅላይ ሚኒስትሩ መኪና እያሽረከሩ ታይተዋል። የኢትዮጵያና ኤርትራ ግንኙነት ኢኮኖሚያዊ ትርፍ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ በሁለቱ ሃገራትና በአካባቢያዊ ጉዳዮች ለመመካከር ለሁለት ቀናት ይፋዊ የሥራ ጉብኝት አሥመራ የገቡት ሐሙስ ነበር። ይህ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉብኝት ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ በፍጥጫ የቆየውን ግንኙነት ለማሻሻል ያስቻለውንና ፈር ቀዳጅ የተባለውን የመጀመሪያ ጉዟቸውን ወደ አሥመራ ካደረጉ ከአንድ ዓመት በኋላ የተደረገ ነው። ይህንን ጉብኝት በተመለከተ የኤርትራ መንግሥት ቴሌቪዥን ባሳየው ምስል ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ከልኡካን ቡድናቸው ጋር በአሥመራ ጎዳናዎች ላይ በእግራቸው ሲጓዙ፤ ከዚያም ጠቅላይ ሚኒስትሩ መኪና እያሽከረከሩ ከሁለቱ መሪዎች የጉብኝቱ አካል የሆኑ ስፍራዎችን እየተዘዋወሩ ሲመለከቱ ያሳያል። ይህ ቪዲዮም በተለያዩ የማህበራዊ መገናኛ ዘርፎች ላይ በስፋት እየተዘዋወረ ሲሆን የተለያዩ ሰዎችም በቪዲዮው ላይ አስተያየታቸውን እየሰጡ ነው። ናቲ ብርሃኔ ይፍሩ የተባሉት ግለሰብ በትዊተር ላይ እንዳሰፈሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንግዳ ሆነው ሳለ ስለምን አስተናጋጁን ፕሬዝዳንት አሳፍረው እንደሚያጓጉዙ ይጠይቅና፤ ኤርትራ የተረጋጋች መሆኗን ለማሳየት የተደረገ ገጽታ ግንባታ እንደሆነ ይጠቅሳል። ሁለቱ ሃጋራት ባለፈው ዓመት ግንኙነታቸውን ለማሻሻል የሚጠቅሙ የተለያዩ ስምምነቶችን የተፈራረሙ ቢሆንም የአየር መጓጓዣ አገልግሎት መልሶ መጀመሩና ኤምባሲዎቻቸውን መልሶ ከመክፈት ባሻገር ጉልህ የሆነ እንቅስቃሴ እስካሁን አልታየም። በኢትዮ ኤርትራ ድንበር ንግድ ተጧጡፏል አንዳንዶች በዚህ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉብኝት ባለፈው ዓመት የተጀመሩትን ሥራዎች ወደተግባር ለመቀየርና በሌሎች ጉዳዮችም ላይ በጋራ ለመስራት ሊሆን እንደሚችል ይናገራሉ። በሁለቱ ሃገራት መካከል ያሉት የድንበር መተላለፊያዎች ለተወሰነ ጊዜ ተከፍተው ነጻ የሰዎችና የሸቀጦች ዝውውር የነበረ ሲሆን አሁን ግን መዘጋታቸውን የድንበር አካባቢ ነዋሪዎች ይናገራሉ። በተጨማሪም ለሁለቱ ሃገራት ደም አፋሳሽ ጦርነት ምክንያት የሆነችው ባድመን በተመለከተ የዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት በሰጠው ውሳኔ መሰረት እስካሁን ኢትዮጵያ ቦታውን ለኤርትራ እንዳለቀቀች ይነገራል። ነገር ግን የኤርትራ የማስታወቂያ ሚኒስትር አቶ የማነ ገብረመስቀል በሁለቱ ሃገራት መካከል እየተካሄደ ያለው ግንኙነት ጠንካራና በሂደት ላይ እንደሆነ ይጠቅሳሉ። ተያያዥ ርዕሶች
በዶሃ የሴቶች ማራቶን ሯጮች አቋርጠው ወጡ
ሴፕቴምበር አጭር የምስል መግለጫ በመካከል አቋርጠው ከወጡት መካከል ኢትዮጵያውያኖች ይገኙበታል ትናንት እኩለ ለሊት በኳታር፣ ዶሃ በተጀመረው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የተካሄደው የማራቶን ሩጫ ላይ የተሳተፉ ኢትዮጵያውያን በከፍተኛ ሙቀት ምክንያት ማቋረጣቸው ተሰማ። ሩጫውን በበላይነት ኬኒያዊቷ ሩት ቼፔንጌቲች ያሸነፈች ሲሆን፤ ከ ተወዳዳሪዎች ቱ በሙቀቱ ከባድነት ምክንያት አቋርጠው መውጣታቸው ተዘግቧል። እኩለ ለሊት ላይ የተደረገውን ይህ የሴቶች የማራቶን ውድድር ካቋረጡ ተወዳዳሪዎች መካከል ኢትዮጵያዊቷ ሩቲ አጋ አንዷ ነች። የውድድሩ አዘጋጆች ከዋናው ውድድር ቀድመው የማራቶን ውድድሩ እንዲካሄድ ያደረጉት የአየር ጠባዩ ለማራቶን ምቹ ላይሆን ይችላል በሚል እንደሆነ ተነግሯል። የሴቶች ማራቶን ሲካሄድ፤ የሙቀት መጠኑ ዲግሪ ሴንቲግሬድ እንደነበር የተገለፀ ሲሆን፤ ወበቁ ደግሞ ከ በመቶ በላይ ነበር ተብሏል። የኢትዮጵያ ማራቶን አሰልጣኝ ሀጂ አዲሎ ሮባ፤ የቶኪዮ ማራቶን አሸናፊዋ ሩቲ ነጋን ጨምሮ ሌሎች ሁለት ተወዳዳሪዎች ማቋረጣቸውን ተናግረዋል። በአገራችን ማራቶንን በዚህ የአየር ጠባይ መሮጥ የሚታሰብ አይደለም ካሉ በኋላ ምን ያህሎቹ እንደሚጨርሱ ለማየት ጓጉቻለሁ ብለዋል። የ ዓመቷ ቼፔንጌቲች ሩጫውን በ ሰዓት ከ ደቂቃ ከ ሰከንድ በማጠናቀቅ ወርቅ ስታገኝ፤ የባህሬን ዜግነት ያላት ሯጭ ሁለተኛ፣ ናሚቢያዊቷ ሯጭ ሦስተኛ በመሆን አጠናቀዋል። ቼፔንጌቲች፤ በእንዲህ አይነት ፈታኝ ሁኔታ ውስጥ አሸንፋለሁ ብዬ አልጠበቅኩም በማለት ለፈረንሳዩ የዜና ወኪል ተናግራለች። የብሪታኒያ ፈጣን የማራቶን ሯጭ ቻርሎቴ ፑርዱኤ እና ሌሎች ታዋቂ ሯጮችም አቋርጠው ከወጡት መካከል ናቸው። ተያያዥ ርዕሶች
የዛሬ ዓመት የኮ ል መንግሥቱ አውሮፕላን ለምን አልጋየም
ሜይ ማጋሪያ ምረጥ የዛሬ ዓመት፣ ማክሰኞ ለታ የወጣችው ጨረቃ ጤፍ ታስለቅም ነበር ። ሌ ኮ ካሳዬ ታደሰ ናቸው እንዲያ የሚሉት። እንደ ትናንት ያስታውሷታል፤ የነፍስ ውጭ ነፍስ ግቢ ሌሊት። እርሳቸው ያኔ የ ኛው አየር ወለድ ኢታማዦር ሹም ነበሩ። ዓመት ብዙ ነው። ግንቦት የኾነው ግን ዛሬም ድረስ እንቆቅልሽ ነው። እንደው በደፈናው ተምኔታዊም ተውኔታዊም ነበር ማለቱ ይቀል ይሆን የጦር ኃይሎች ኢታማዦር ሹሙ ጄኔራል መርዕድ ንጉሤ የኢትዮጵያን ባንዲራ ራሳቸው ላይ ጠምጥመው ምናልባትም እንደ መይሳው ካሣ ሽጉጣቸውን የጠጡባት ምሽት። እርግጥ ነው በጄኔራል መርዕድ ዙርያ ብዙ የሚጣረስ ታሪክ አለ። ባንዲራ ለብሰው ነበር ከሚለው ሰነድ አልባ ተረክ ጀምሮ እስከ አሟሟታቸው ድረስ ይኸው ዓመት እንኳ ያልፈታው ምሥጢር ። ኢትዮጵያን ወደተሻለ ስፍራ ሊወስዳት የሚችል ሌላ መሪ የለም የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት ሻምበል እዮብ አባተን እዚህ ጋ እናምጣቸው። ያኔ የወታደራዊ ደኅንነት ባልደረባ ነበሩ። ከዚያ በኋላም ስለ መፈንቅለ መንግሥቱ ጥናት አድርገዋል። ስለ ጄኔራል መርዕድ አሟሟት በስፋት ከሚታመነው በመጠኑም ቢኾን ያፈነገጠ ታሪክ ጽፈው አስነብበዋል። ጄኔራል መርዕድ ራሳቸውን ባጠፉ አፍታ እዚያ ደረስኩ ያለ አንድ የልዩ ብርጌድ ወታደር ነገረኝ ብለው ለቢቢሲ እደተናገሩት ከሆነ ጄ ል መርዕድ ያን ምሽት ራሳቸው ላይ ቢተኩሱም ነፍሳቸው ወዲያውኑ አልወጣችም። ሺህ ወታደር ሲያዝዙ ኖረው ሞት አልታዘዝ አላቸው። አምቡላንስ ተጠርቶ ቢመጣም አምቡላንሷ ወደ ሆስፒታል አልወሰደቻቸውም፤ ወደ ቤተመንግሥት እንጂ። አምቡላንሷ ውስጥ እስከ ንጋት ድረስ እያጣጣሩ ነበር። ቢያንስ ለ ሰዓታት፤ በሁለት ወታደሮች እየተጠበቁ ጣር ። ነገሩ ሆን ተብሎ የተፈጸመ የጭካኔ ተግባር ይመስላል፤ አልያም ደግሞ ዘመኑ የወለደው የበዛ ፍርሃት። በዚያች የነፍስ ውጪ ነፍስ ግቢ ቅጽበት ማን ደፍሮ የመፈንቅለ መንግሥትን አውራ አቀናባሪና ጎንጓኝ ሕክምና ያግኙ ብሎ ይጮኻል አንተን የነዚህ ከሐዲዎች ጠበቃ ማን አደረገህ ብባልስ ይላል የዐይን እማኙ ዝምታን ለምን እንደመረጠ ሲተርክ። በሥራ ስንዋከብ ቆይተን ወደ አምቡላንሷ ከሌሊቱ ሰዓት ስንመለስ የጄኔራሉ ህሊና የሚረብሸውና አንጀት የሚያላውሰው የጣርና የሲቃ ድምጻቸው ከበፊቱ ቀንሶ ይሰማ ነበር። ከልጃቸው አስተዋይ መርዕድ የተገኘ አጭር የምስል መግለጫ ብ ጄኔራል መርዕድ ንጉሤ የኤርትራ አስተዳዳሪ እና የሁለተኛው አብዮታዊ ሠራዊት አዛዥ ሳሉ። በዚህ ረገድ የአየር ኃይሉ አዛዥ ጄኔራል አምሐ ዕድለኛ ነበሩ ማለት ይቻላል። የሟችና የአሟሟት ዕድለኛ ካለው ። ጄ ል አምሐ ሽጉጣቸውን መኪናቸው ውስጥ ረስተውት ነበር ወደ ስብሰባ የገቡት። ሽጉጥ ፍለጋ ተሯሯጡ። መከላከያ አንድ ቢሮ ዘው ብለው ሲገቡ ግድግዳ ተደግፎ የቆመ ክላሽ አገኙ። እስከ ወዲያኛው አሸለቡ። ጄ ል መርዕድ እያጣጣሩ ከሚገኙበት አምቡላንስ ውስጥ፣ በሁለት የልዩ ብርጌድ ወታደሮች እየተጠበቀ ከነበረው አምቡላንስ ውስጥ የእርሳቸውም ሬሳ ተጠቅልሎ እንደነገሩ ተጋድሞ ነበር፤ እንደ ሻምበል እዮብ የማያወላዳ የዐይን እማኝ ከሆነ። ወንዶች የማያወሯቸው አምስት አሳሳቢ ነገሮች ቢቢሲ፡ ሻምበል ግን እኮ ይሄ ጄ ል መርዕድን አሟሟት በተመለከተ የሚሉን ነገር እስከ ዛሬ ያልተሰማ ታሪክ ነው። ነገረኝ የሚሉትን ወታደር ያምኑታል ሻምበል እዮብ፦ የልዩ ጥበቃ ብርጌድ የመምሪያ ረ መኮንን የነበረ ሰው ነው። ይህ መኮንን ጄኔራሎቹ በእስር ላይ እያሉ የአስተዳደራዊ ጉዳያቸውን እንዲፈጽሙ ከተመደቡት መኮንኖቸ አንዱ ነው። ያን ምሽት ያየው ነገር እስከዛሬም ይረብሸዋል። ታሪክ ተዛብቶ ሲነገር ተበሳጭቶ ነው እኔን ያገኘኝ። እውነታውን አስተካክለህ ጻፍ፤ እኔ እዚያው የነበርኩ ወታደር ነኝ ነው ያለኝ። በዚያ ምሽት እሱ እዚያ ስለመኖሩ ከሌሎች አረጋግጫለሁ። ግንቦት ፣ የነፍስ ውጭ፣ ነፍስ ግቢ ዕለት አየር ወለዱ ጄኔራል አበራ አበበ የገዛ አለቃቸውን የመከላከያ ሚኒስትሩን ጄኔራል ኃይለጊዮርጊስን በሽጉጥ ገድለው፣ የዘበኛ ልብስ አስወልቀው፣ የወታደር ዩኒፎርማቸውን ቀይረው፣ ሲኒማዊ ኩነት በሚመስል አኳኋን አጥር ዘለው ከመከላከያ ግቢ ያመለጡበት ቀትር ይህም ታሪክ አሻሚ ነው። ለምን አመለጡ ለምን ሚኒስትሩን ገደሉ እንዴት መፈንቅለ መንግሥት የሚያህልን ነገር እየመሩ አንድ ሚኒስትር ስለገደሉ ብቻ እንደ ተራ ነፍሰ ገዳይ ሊያመልጡ ይችላሉ ዓመት ያልመለሳቸው ጥያቄዎች። ግንቦት ፤ የነፍስ ውጭ፣ ነፍስ ግቢ ዕለት ጄኔራል ፋንታ በላይ ለሦስት ቀን ሦስት ሌሊት ኮንቴይነር ውስጥ የሚላስ የሚቀመስ በሌለበት የተደበቁበት ምሽት ። ጄኔራል ፋንታ የትምህርት ዝግጅታቸውና የአመራር ብቃታቸው ለርዕሰ ብሔርነት አሳጭቷቸዋል። ምናልባትም ስዒረ መንግሥቱ ተሳክቶ ቢኾን ኖሮ ኢትዮጵያን የሚመሯት ፕሬዝዳንት ፋንታ በላይ ነበሩ። ይህን የጄኔራል ፋንታ በላይን ድርጊት ተከትሎ ማሽሟጠጥ የሚቀናው ሰፊው ሕዝብ ተቀኘ ተባለ ፔፕሲ ኮካ ኮላው ከከተማ ጠፍቶ ፋንታ ተገኘ አሉ በኮንቴይነር ሞልቶ በኤርትራ የማህበራዊ ድረ ገጾች አገልግሎት ተቋረጠ ግንቦት ፤ የነፍስ ውጭ፣ ነፍስ ግቢ ምሽት ከሁሉም በላይ ኢትዮጵያ በብዙ ጽናት፣ በብዙ ትጋት አምጣ ያዋለደቻቸው፣ ለወግ ማዕረግ ያበቃቻቸውን እጅግ ውድና ምትክ የለሽ የሚባሉ ጄኔራሎቿን በአንድ ጀንበር ያጣችበት ምሽት። አይደለም አገረ ኢትዮጵያ፣ አህጉር አፍሪካ ሳትቀር ከተቀረው ዓለም ወራሪ ጦር ቢገጥማት ከፊት ልታሰልፋቸው የምትችላቸው ምርጥ ጄኔራሎቿ ነበሩ ። በእርሻ መሣሪያ የተያዘው አርሶ አደር እግሩን ቆረጠ ግንቦት የኾነው በትክክል ምንድነው ጓድ ሊቀመንበር ምሥራቅ ጀርመንን ለመጎብኘት ክብርት ወ ሮ ውባንቺንና ልጃቸውን ትዕግስትን ወይም ትምህርትን አስከትለው፣ በትረ መኮንናቸውን እየወዘወዙ ቦሌ ተገኙ። ረፋድ ላይ። መንጌ ቆቅ ናቸው። ሆን ብለው ሰዓት ያዛባሉ። ጠላትን ለማወናበድ ወይ ረፈድ ወይ ቀደም ይላሉ። እርሳቸው ላይ የሚዶልተው ብዙ ነዋ። ያን ለታም እንዲሁ አደረጉ። ማልጄ ነው ምሳፈረው ብለው ለደኅንነት ሚኒስትራቸው ተናገሩ። ሚኒስትሮቻቸው እውነት መስሏቸው ቦሌ ማልደው ደረሱ። እርሳቸው ግን ረፋድ ላይ ግንባራቸውን ቅጭም አድርገው ከቸች ። ብዙዎቹ ጄኔራሎች እስከዚያች ሰዓት ድረስ ይቁነጠነጡ ነበር። ቶሎ ወደ ቢሮ መመለስ አለባቸዋ። አጣዳፊ ሥራ ነው የሚጠብቃቸው። መንጌን ወደ መንግሥተ ሰማይ ልኮ መሬት ላይ አዲስ መንግሥት የማቆም ብርቱ ሥራ አለባቸው። ጄኔራሎቹ ጦርነት ታክቷቸዋል። በመንጌ ቆራጥ አብዮታዊ አመራር ሺህ የድሀ ልጆችን መማገድ አንገሽግሿቸዋል፤ በአፋቤቴ፣ በቀይ ኮከብ፣ በባሕረነጋሽ ዘመቻ አሥር ሺህዎች እንደቅጠል ረግፈዋል። ጦርነትን እንደ ሥራ የያዘ መንግሥት ሕዝብ ሊመራ እንዴት ይቻለዋል ሲሉ ነበር ድምጻቸውን ዝግ አድርገው የሚያጉረመርሙት። ኢትዮጵያ ሀይቆቿን መጠበቅ ለምን ተሳናት መንግሥቱ ይሄን ማጉረምረም ከሰሙ ጄኔራሎቹን አይምሯቸውም። ማዕረጋቸውን በመቀስ፤ ግንባራቸውን በሽጉጥ ሊነድሉት ይችላሉ፤ አድርገውታልም። የናደው ዕዝ ዋና አዛዥ ብርጋዲየር ጄኔራል ታሪኩ ዓይኔን፣ አሳዛኝ ፍጻሜን የሰማ ከመንጌ ጋር አይቀልድም።፡ የአገሪቱ ምጣኔ ሐብት ደቋል፣ ሕዝብ ተርቧል፤ ወታደሩ ኮቾሮ እየበላ ነው የሚዋጋው። የገዛ ልጁንና ሚስቱን እንኳ ማየት አይፈቀድለትም። ጄኔራሎቹ የገዛ ወገናችንን ትርጉም በሌለው ጦርነት ለምን እናስጨርሳለን ፣ ደግሞስ የሰሜኑ ችግር በፖለቲካ እንጂ በአፈሙዝ ይፈታል እንዴ እያሉ ያጉረመርሙ ነበር፤ መንጌ ሳይሰሙ። ኮ ል መንግሥቱ ግን ሁሉም ነገር ወደ ጦር ግንባር እያሉ ጦርነቱን ገፉበት። በዚያ ላይ ከጦር አዛዦቻቸው ይልቅ ካድሬዎቻቸውን ማመን አበዙ። ይሄ ሰውዬ እኛን የማይሰማ ከሆነ ለምን አናስወግደውም አሉ ጄኔራሎቹ፤ ማንም ሳይሰማቸው። መፈንቅለ መንግሥት ለማካሄድ ዝግጅት ተጧጧፈ። ለዚያ ነው ያን ቀን፣ ግንቦት መንጌን ቶሎ መሸኘት የነበረባቸው ፤ ከሻዕቢያ ጋር ቶሎ ለድርድር መቀመጥ ያሻል። ይሄን የውጭውን ሽርጉድ፣ ገና ድሮ መንጌን የከዱት ሻለቃ ዳዊት ወ ጊዮርጊስ አሰናድተውታል። ጄኔራሎቹ የመንጌን ወደ ምሥራቅ ጀርመን መሸኘት ይቅርታ የመንጌን እስከወዲያኛው መሸኘት በጉጉት እየጠበቁ ያሉት ለዚሁ ነው። የዛሬ ዓመት፤ ግንቦት ፤ ረፋድ ላይ ሰዓቱ አልገፋ አለ ወግ ነውና መሪን መሸኘት ጓድ ሊቀመንበር በሰላም አ ይመልስዎ እያሉ ቀኝ ወ ግራ ተሰይመው ተሰናበቷቸው፤ የገዛ ጄኔራሎቻቸው። መንጌ ያቺን ተወርዋሪ ኮከብ የመሰለች ፈገግታቸውን ቦግ እልም እያደረጉ አጸፋውን መለሱ። ለምን ይሆን ግን ፈጣሪ ለአምባገነኖች ችምችም ያለ፣ የተፈለፈለ በቆሎ የሚመስል ጥርስና ረዥም ዕድሜን የሚቸረው ሚሊዮን ብር ገደማ የሚያወጣ መኪና የሰረቀው አልተያዘም የሚደንቀው ታዲያ በዚያች ዕለት የቦሌ ሽኝት ጄኔራል መርዕድ ንጉሤ አልተገኙም። ይሄ ቀላል ፕሮቶኮሏዊ ህጸጽ ተብሎ ሊታለፍ ይችላል። ጊዜ አጥተው ነው ሊባልላቸውም ይችላል ። ምክንያቱም ዘመኑ የጥድፊያ ነዋ የጦርነት። በየግንባሩ ገንጣይ አስገንጣይን ለመፋለም የወገን ጦር ከሺህ የወንበዴው ጦር ጋር ተናንቆ እየተዋደቀ ነው። ፈንጂ እየረገጠ ነው በእንዲህ ያለ ቀውጢ ጊዜ ለሽኝት መኳኳል ቅንጦት ሊሆን ይችላል። ቢኾንም ጄኔራሉ ደግ አልሠሩም። መርዕድ ምነው ቀረ ምንስ ብርቱ ጉዳይ ቢገጥመው፣ ቆራጡን መሪያችንን መሸኘት አልነበረበትም የምትል የሰናፍጭ ቅንጣት ታህል ጥርጣሬ ሳይገባቸው አልቀረም፤ የደኅንነቱን ሹሙን፤ ኮ ል ተስፋዬ ወልደሥላሴን ። ኢታማዦር ሹሙ ደግ አልሠሩም፤ እንደምንም ብለው አለቃቸውን መሸኘት ነበረባቸው። እርሳቸው በተቃራኒው መከላከያ ሚኒስትር ውስጥ፣ ከኢትዮጵያ ሆቴል ፊት ለፊት፣ ከአምባሳደር ሲኒማ ጎን፣ ከቢሯቸው ቁጭ ብለው የክፍለ ዘመኑን አስገራሚ የስዒረ መንግሥት ተውኔት እየጻፉ ነበር። የመንጌ አውሮፕላን ለምን አልጋየም ጓድ መንግሥቱ ለምሳ ያሰቧቸውን ለቁርስ ማድረግን ተክነውበት ሊሆን ይችላል። በዚያች ዕለት ግን ቁርስም ምሳም እራትም ሊደረጉ የነበሩት እርሳቸው ናቸው። ይህን ፈጽሞ አያውቁም። አውሮፕላኑን የተሳፈሩትም የእሳትራት ኾነው ነው። የተሳፈሩባትን አውሮፕላናቸው ሰማይ ላይ እንዳለ የማጋየቱ ነገር ያበቃለት፣ ተቦክቶ ያለቀ፣ የደቀቀ ጉዳይ ነው። ይህን ያጸደቁት ደግሞ ከሞላ ጎደል ሁሉም የጦር አዛዦች ነበሩ። ድንገት መንጌን ሸኝተው ሲመለሱ ቆፍጣና ወታደራዊ መንፈሳቸው በ ኖና ተ ኖ የባህታዊ ሐሳብ በልባቸው አደረ። ጓዶች ለምን እናጋየዋለን ግን እሱን ለመግደል ብለን የ ንጹሐን ነፍስን ከምናጠፋ ኖኖኖኖ ወደ ኋላ ባንመለስ ነው የሚሻለው በዚህ ጉዳይ ተስማምተን የጨረስነውን አደለም ተስማምተን ሊሆን ይችላል። ነገር ግን ወ ሮ ውባንቺስ፣ ልጃቸውስ አብራሪዎቹስ ወገኖቻችን አይደሉም ምን አጠፉና ነው በዚህ ሰውዬ ጦስ የሚጠፉት ይሄ ሐሳብ ምናልባትም ከአየር ኃይል አዛዡ ጄኔራል አመሃ የመጣ ሳይሆን አይቀርም። እና ምን በጀ ጓዶች ምናልባት እርጋታ የማይለያቸው ሰብሳቢው ጄኔራል መርእድ እንዲያ ጠይቀው ይሆናል። ባይሆን በጦር አውሮፕላን አስገድደን አሥመራ ብናሳርፈው አይሻልም ይሄ ከጄኔራል አመሃ የመጣ መፍትሄ ሊሆን ይችላል። አሥመራ የማይሆን ነው፤ በሙሉ መንጌ መንጌ የሚል አየር ወለድ ነው ያለው በዚህ ጊዜ ምናልባትም የዘመቻ አዛዡ ጄኔራል አበራ እምር ብለው እንዲህ ተናግረው ይሆናል፤ ምንድነው ይሄ ውልውል ተስማምተን ተግባብተን በአንድ ያጸደቅነውን የምን መንሸራተት ነው ይሄኮ ፌዝ አይደለም መፈንቅለ መንግሥት ነው እያካሄድን ያለነው። የሊቀመንበሩን አውሮፕላን ካላጋየን ኋላ የምንጋየው እኛው ነን ውርድ ከራሴ ጄኔራሎቹ መግባባት ተሳናቸው። ይህ ጉዳይ የመጨረሻቸው መጀመርያ ኾነ። ጄኔራሎቹ በመከላከያ ሚኒስትር ግቢ፣ አንደኛ ፎቅ ላይ፣ ፊቷን ወደ ክቡ የብሔራዊ ባንክ ሕንጻ ባዞረች አንዲት የስብሰባ አዳራሽ ታድመው በኢትዮጵያ ዕጣ ፈንታ ላይ እንዲህ ጉንጭ አልፋ ክርክር እያደረጉ ሳለ ጓድ ሊቀመንበር መንግሥቱን የያዘው አውሮፕላን በሰማይ ላይ ሳይጋይ፣ አሥመራም ተገዶ ሳያርፍ የኢትዮጵያን የአየር ክልል እየቀዘፈ ራቀ። ደብረዘይት አየር ኃይል ግቢ አውሮፕላኑን ለመምታት በተጠንቀቅ የነበሩት ጄቶችም ሞተር አጠፉ። ከልጃቸው ደረጀ ደምሴ የተገኘ አጭር የምስል መግለጫ ጄኔራል ደምሴ ቡልቶ በአሥመራ ግን መንጌ ተገድለዋል በአሥመራ የግዙፉ ኛው አብዮታዊ ሠራዊት አድራጊ ፈጣሪ፣ ሥመ ጥሩው ጄኔራል ደምሴ ቡልቶ ናቸው። እንዲያውም የስዒረ መንግሥቱ ሁነኛው ጠንሳሽ ሳይሆኑ አይቀሩም። ምክትላቸውን ጠርተው ነገሩ ሁሉ መልክ መልክ መያዙን አረጋገጡ። ጄኔራል ቁምላቸው በአራት አንቶኖቭ የታጨቁ ልዩ ኮማንዶዎችን አሳፍረው ወደ አዲስ አበባ ጉዞ እንዲጀምሩ አዘዟቸው። በጥሩ ጤንነት ላይ አይደለችም የስምረት ካህሳይ ቤተሰቦች ጄኔራል ቁምላቸው አገሪቱ አለኝ የምትላቸውን የአየር ወለድ አባላት ዳይ ተንቀሳቀስ አሏቸው። በወታደር ቤት አለቃ ሲያዝ አቤት ጌታዬ እንጂ ለምን ጌታዬ አይባልም። ሶቭየት ሠራሽ አንቶኖቭ ውስጥ እንዳሉ ድንገት ጄ ል ቁምላቸው እመር ብለው ተነሱ። የሃሎ ሃሎ መነጋገሪያውን ረዳታቸው አቀበሏቸው። አንድ በራሪ ወረቀት ከኪሳቸው አውጥተው ማንበብ ጀመሩ። መንጌ ተገድሏል። ጦርነት አብቅቷል። እንኳን ደስ ያላችሁ ቁምላቸው ደጀኔ ጄ ል እዚያ አንቶኖቭ ውስጥ ያለው ወታደር በሙሉ በታላቅ ፌሽታ አጨበጨበ። በዚያ አንቶኖቭ ውስጥ የነበሩትና ዛሬም በሕይወት የሚገኙት ሌ ኮ ል ካሳዬ ታደሰ ለቢቢሲ አማርኛ እንደተናገሩት መንግስቱ ተገድሏል ሲባል መጀመርያ ደነገጥኩ፤ ከዚያ ሁሉም ሲያጨበጭብ እኔም ማጨብጨብ ጀመርኩ ሲሉ የወቅቱን ድራማ ገልጸዋል፡፡ ሰማይ ላይ አንቶኖቩ ውስጥ ይህ ሲሆን የአሥመራ ሬዲዮ በበኩሉ መንግሥቱ መገደሉን አወጀ። ከአንድ ሰዓት ተኩል በረራ በኋላ ጄኔራል ቁምላቸው ኮማንዷቸውን ይዘው አዲስ አበባ ጦር ኋይሎች ልደታ አርሚ አቪየሽን ገብተዋል። ግማሾቹን ኮማንዶዎች ደግሞ እዚያው ቦሌ አየር መንገድን እንዲቆጣጠሩ አድርገዋል። የዚህ ልዩ ኮማንዶ ተግባር ሬዲዮ ጣቢያውን መቆጣጠር፣ መከላከያ ሚኒስትር ለሚገኙት መፈንቅለ መንግሥት አድራጊዎች ደግሞ ከለላ መስጠት፤ ድንገት ለመንጌ አንገቴን እሰጣለሁ የሚል ኃይል ካለ አንገቱን እንደ ዶሮ መቀንጠስ ነው። የሚገርመው የአሥመራ ሬዲዮ መንግሥቱ ኃይለ ማርያም እስከወዲያኛው እንደተሰናበቱ ያወጀው ገና ረፋድ ላይ ነበር። በመሆኑም ጄኔራል ቁምላቸውም እስከመጨረሻው የሚያውቁት መንግሥቱ መገደሉን ነው። ሌ ኮ ል ካሳዬም ይህንኑ ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። ከጦላይ የመጣው ሠራዊት መፈንቅለ መንግሥቱን ለማቅናት ከአሥመራ በጄ ል ቁምላቸው እየተመራ አዲስ አበባ ከገባው ኃይል ሌላ ከጦላይም አንድ ሻለቃ ተንቀሳቅሷል። ጄኔራል ውበቱ ፀጋዬ ከሴረኞቹ ጋር በስሱም ቢሆን ሳይመሳጠሩ አልቀሩም። አሁንም ድረስ በሕይወት አሉ፤ አሜሪካን አገር። ወደ አዲስ አበባ የሚላከውን ጦር አዘጋጅተው እሳቸው ከሰሜን ኮሪያ የመጣ ልኡካን ቡድንን ተቀብለው እያነጋገሩ ነበር። ጦላይ ያለው ልዩ ኮማንዶ የቁልምጫ ስሙ ስፖርታ ይባላል። ሰሜን ኮሪያዎች ለከተማ ውጊያ፣ ለጨበጣ ፍልሚያ በልዩ ጥንቃቄ ያሰለጠኑት ጦር ነው። ጄ ል ውበቱ ጥርት ያለ መመርያ ባይደርሳቸውም የሚሆኑትን ምርጥ ምልምሎች በወታደራዊ ሄሊኮፕተር ወደ አዲስ አበባ ላኳቸው። ፖስታ ቤት መገናኛ ሚኒስትር አካባቢ በሚገኝ ሜዳ ላይ ሆነው ትዕዛዝ እንዲጠባበቁ ተደረጉ። ኋላ ላይ ኛ ክፍለ ጦር አምባሳደር ጋ፣ ኢትዮጵያ ሆቴል ጎን፣ መከላከያ ሚኒስትር ውስጥ ከኢትዮጵያ ሆቴል ትይዩ በዋናው የመከላከያ ሕንፃ ኛ ፎቅ የጠቅላይ ኢታማዦር ሹሙ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይገኛል። ይህ አዳራሽ ፊቱን ወደ ወርቃማው የብሔራዊ ባንክ የሰጠ ነው። በዚህ አዳራሽ መፈንቅለ መንግሥት አድራጊዎች ሴራ እየጎነጎኑ ነው። ቁጥራቸው ይጨምራል ይቀንሳል። ሆኖም በአገሪቱ አንድም የቀረ ቱባ ጄኔራል የለም። ያለ እናት የመጀመሪያው የእናቶች ቀን በኢትዮጵያ የመጀመርያው አብዮታዊ ጄኔራል፣ ተወዳጁ፥ ደርባባው፣ አንደበታቸው የረጋው ጄ ል መርዕድን ጨምሮ የባሕር ኃይል አዛዡ ሪር አድሚራል ተስፋዬ ብርሃኑ፣ የአየር ኃይል አዛዡ ጄኔራል አምሐ፣ የምድር ጦር አዛዡ ጄኔራል ኃይሉ፣ የፖሊስ ሠራዊት አዛዡ ጄኔራል ወርቁ ይገኙበታል። ስለ ጀግንነታቸው ሳር ቅጠሉ የመሰከረላቸው እነ ጄኔራል ፋንታ በላይ፣ እነ ጄኔራል አበራ አበበ፣ እነ ጄ ል ደምሴ ቡልቶም አሉበት። ስለነዚህ ጄኔራሎች የጦር ጀብድ እንኳን ወታደሮቻቸው አንዳንድ የሰሜን ተራሮችም አፍ አውጥተው ባይናገሩ ማን ቀረ ታዲያ እርግጥ ነው ጄኔራል ደምሴ ቡልቶ በአካል አምባሳደር ብሔራዊ አካባቢ አይሁኑ እንጂ በመንፈስ አብረዋቸው ናቸው። እርሳቸው አሥመራ ትልቁን የቤት ሥራ ሠርተው ጨርሰዋል። የአገሪቱ ሁለት ሦስተኛ ጦር በርሳቸው ሥር ነው ያለው። አሁንም ድረስ አስገራሚው ነገር ታዲያ የአሥመራ ጦር መጀመሪያ በታቀደው መሠረት የመንጌ አውሮፕላን መመታቷን ነው የሚያውቀው። ይህንኑም በሬዲዮ አስነግሯል። የሥራ ቃለመጠይቅ ማድረግ ያስፈራዎታል እነዚህ የጦር አበጋዞች ግማሽ ሚሊዮን የሚጠጋውን የአገሪቱን ሠራዊት ያዛሉ። ሁሉም በመፈንቅለ መንግሥቱ ጉዳይ ላይ መግባባት ደርሰዋል። ሆኖም እዚያው መከላከያ ሚኒስትር ስብሰባ ላይ ናቸው። ይህ ይሆን መዘናጋትን የፈጠረባቸው ምን ዓይነት ምድራዊ ኃይል መጥቶ ይህን ኩዴታ ሊያከሽፍ ይችላል ስክነት የራቃቸው ጄኔራል አበራ ብቻ ናቸው። እስራኤል ነው የተማሩት። የዘመቻ አዛዡ ጄኔራል አበራ ወትሮም ችኩል ናቸው ይባላል። ቀልባቸው የሆነ ነገር ሳይነግራቸው አልቀረም። በስብሰባው መካከል ወጣ እያሉ ግቢውን ይቃኛሉ። በዚህ መሀል የታንክ ቃቃታ የሰሙ መሰላቸው። የመከላከያ አስተዳደር መምሪያ አዛዡን ጄኔራል ዑመርን አስከትለው የመከላከያ ግቢ የባንዲራ መስቀያው ጋ ቆመው መከላከያ ቢሮ ውስጥ ያለውን ሰው በሙሉ ወደ ግቢው እንዲሰለፍ አዘው ንግግር ማድረግ ጀመሩ፤ የመንጌን ፍጻሜም አበሰሩ። ተጨበጨበ ቪቫ ኩዴታ ተባለ ደረጀ ደምሴ አጭር የምስል መግለጫ መከላከያ ሚንስትሩ ጄ ል ኃይለጊዮርጊስ ለጄ ል ደምሴ ቡልቶ ዕውቅና እየሰጡ። ከመከላከያ ሚንስትሩ ጎን ቆመው የሚታዩት ጄ ል አበራ ናቸው ሟች እና ገዳይ። የመከላከያ ሚኒስትሩ መገደል የደኅንነት ሚኒስትሩ ተስፋዬ ወ ሥላሴ ሴራ ሸትቷቸዋል፤ ባምቢስ ከሚገኘው የደኅንነት ቢሯቸው እየበረሩ ወደ ምኒሊክ ቤተ መንግሥት ነዱ። የመንጌን ልዩ ረዳት መንግሥቱ ገመቹን ጠርተው አስቸኳይ ስብሰባ ጀመሩ። እነ ፍቅረሥላሴ ወግደረስም አሉበት። እንዲያውም ሰብሳቢው እርሳቸው ናቸው። ምንድነው እየሆነ ያለው እነ መርእድ ምንድነው እየዶለቱ ያሉት እረ በፍጹም አሉ ሚኒስትሩ። ሄደው እንዲያጣሩ ሐሳብ ቀረበ። በሄዱበት ይቀራሉ ያለ አልነበረም። ልዩ ነዳጅ መኖሩን አልደረስንበትም የማዕድን፣ የፔትሮሊየምና የተፈጥሮ ጋዝ ሚኒስቴር ሚኒስትሩ ቁልቁል ወደ አምባሳደር በረሩ። ወደ ቢሯቸው ገብተው ወጡ። ጄ ል ኃብተጊዮርጊስ ወትሮም ከጄ ል አበራ ጋር እስተዚህም ናቸው። እረ እንዲያውም ዐይንና ናጫ ። ጄ ል አበራ የሆነ የቀፈፋቸው ነገር ያለ ይመስላል። ጄ ል መርዕድ ከሚመሩት ስብሰባ በየመሀሉ እየወጡ ኮሪደሩን፣ አካባቢውን ይቃኙና ይመለሳሉ። ድንገት ለቅኝት ደረጃውን ሲወርዱ፣ መከላከያ ሚኒስትሩ ደግሞ ደረጃውን ሲወጡ ተገጣጠሙ። አበራ ምንድነው እኔ የማላውቀው ስብሰባ ሳይሉ አልቀሩም። አንዱ ሁለት ተባብለውም ሊሆን ይችላል። ብቻ ጄኔራል አበራ በቅልጥፍና ሽጉጣቸውን አውጥተው መከላከያ ሚኒስትሩ ላይ አከታትለው ተኮሱ። ጦር ኃይሎች ቢወሰዱም አልተረፉም። መከላከያ ሚንስትሩን ጄኔራል ኃብተጊዮርጊስን ጠርተው፣ ለመሆኑ በቢሮህ ምን እየተካሄደ እንደሆነ ታውቃለህ ብለው ጠየቁ። ተስፋዬ ወ ሥላሴ የደኅንነት ሚኒስትሩ ጄኔራል አበራ እንዴት አመለጡ ለምን አመለጡ ይህ ሁሉ ሲሆን ከአሥመራ የመጣው የጄኔራል ቁምላቸው ሠራዊት ጦር ኃይሎች ግቢ ሆኖ በተጠንቀቅ ትእዛዝ ይጠባበቃል። እንዲያውም ስልክ ወደ ጄ ል አበራ ደውሎ አልተነሳለትም። ከጦላይ የመጣውና በሰሜን ኮሪያዎች የሰለጠነው የስፓርታ ጦርም ፖስታ ቤት አካባቢ ሥራ ፈትቶ ሜዳ ላይ ተቀምጧል። ። ሁሉም ታዲያ ሪፖርት የሚያደርጉትም ትእዛዝ የሚቀበሉትም ከጄኔራል አበራ ብቻ ነው። የዘመቻ መምሪያ ኃላፊ እሳቸው ናቸዋ። ጄ ል አበራ ግን ያልተጠበቀ ነገር ፈጽመው ችግር ውስጥ ገብተዋል። መከላከያ ሚኒስትሩን ከገደሉ በኋላ ወደ ቢሮ አልተመለሱም። ልዩ ኮማንዶነት የሰለጠኑት ጄ ሉ በአጥር ዘለው አምልጠዋል። አንዳንዶች ከጎን የሚገኘው ቡና ገበያ ግቢ ገብተው ዘበኛ ማርከው የወታደር ልብሳቸውን አውልቀው የዘበኛ ልብስ ለብሰው ተሰወሩ ሲሉ፣ ሌሎች ደግሞ የለም ከመከላከያ የወጡት በአጥር ሳይሆን በበር ነው፤ የአንድ ሠራተኛ ልብስ ቀይረው ነው ይላሉ። የጄ ል አበራ ከመከላከያ መሰወር ነገሮችን አመሰቃቀለ። ከጦላይና ከአሥመራ የመጣው ኃይል ምን ማድረግ እንዳለበት ግራ ገብቶት እርሳቸውን ይፈልጋል። እርሳቸው ግን ስልክ አያነሱም። ቢሮም የሉም። በዚያ ዘመን ሞባይል የሚባል ነገር አይታወቅ ነገር የሚያክሙን ሙዚቃዎች እንዳሉ ሁሉ የሚያውኩንም አሉ ዶ ር መልካሙ ጄኔራሎቹ ራሳቸውን ለምን አጠፉ ግንቦት ስምንት ቀትር ስምንት ሰዓት ግድም የጀመረው መፈንቅለ መንግሥት ራሱን በራሱ እየተበተበ አንድም ፋይዳ ያለው ነገር ሳያከናውን መሸበት። ደኅንነቱ ተስፋዬ ወ ሥላሴ ሻምበል መንግሥቱ ገመቹን ይዘው መከላከያን አስከበቡ፤ ለዚያውም በታንክና በብረት ለበስ። ከዚያ በፊት ግን ነገሩን በሰላም እንጨርሰው በሚል ሽማግሌ ተልኳል፤ ሌ ኮ አዲስ ተድላና ኮ ል ደበላ ዲንሳ ነበሩ አደራዳሪዎቹ። መፈንቅለ መንግሥቱ ያበቃለት ጉዳይ ነው፤ ምንም ድርድር ብሎ ነገር የለም። ባይሆን አግዙን ሳይሏቸው አይቀርም፣ እነ ጄ ል መርዕድ። ቴምር በረመዳን ለምን ይዘወተራል ዞሮ ዞሮ ሰዓቱ ነጎደ። ማስታወቂያ ሚኒስትር አልተያዘ፣ ሬዲዮ ጣቢያ አልተያዘ፣ ቴሌ አልተያዘ ሰዓቱ ነጎደ። የሳር ቅጠሉ አዛዦች በሙሉ እዚያ መሆናቸው ሳያዘናጋቸው አልቀረም። የጄ ል አበራ ድንገት ሰው ገድሎ መሰወር ግን ነገሮችን አወሳሰበ። የመንጌ ቀኝ እጅ ሞክሼያቸው መንግሥቱ ገመቹ የልዩ ብርጌድ ኃይላቸውን ከ ኪሎ አንቀሳቀሱ። በሂልተን አድርገው አምባሳደር ጋ ሲደርሱ መከላከያ ሚኒስትሩን ክበብ አሉ። ውስጥ እነ ጄ ል ፋንታ በላይ፣ አነ ጄ ል አመሃ፣ እነ ጄ ል መርዕድ ምን እያደረጉ እንዳሉ የሚያውቅ ምድራዊ ኃይል የለም። ሆኖም በዚያ ሰዓት መከበባቸውን እንደተረዱ ከአሥመራ ይመጣል የተባለው ኃይል ባለመድረሱ ተስፋ ቆርጠው ሊሆን ይችላል። ብቻ ጄ ር መርዕድና ጄ ል አመሐ ዛሬም ድረስ ግልጽ ባልሆነ ሁኔታ እዚያው ራሳቸውን አጠፉ። ድኅረ ታሪክ ግንቦት ማታ ኮ ል መንግሥቱ ከምሥራቅ ጀርመን ጉብኝታቸውን አቋርጠው ኮሽታ ሳያሰሙ ተመለሱ። ግንቦት ፣ ጄኔራል ደምሴ ቡልቶ በገዛ ወታደሮቻቸው ተገደሉ፤ ከእርሳቸው ጋር በድምሩ ከፍተኛ መኮንኖች ተመሳሳይ ክፉ እጣ ገጠማቸው። በሟቾቹ ሬሳ ላይ እጅግ የሚቀፍ፣ ታሪክ የሚጸየፈው የሰይጣን ድርጊት ተፈጸመ። ከሦስት ቀን በኋላ ጄኔራል ፋንታ በላይ ከተደበቁበት ኮንቴይነር ወጡ። ለጥቂት ወራት ማዕከላዊ ለብቻቸው ተነጥለው ታስረው ሳሉ እስከዛሬም ይፋ ባልሆነ ሁኔታ ጠባቂያቸውን ገድለው ሊያመልጡ ሲሉ ተገደሉ ተባለ። እንግሊዛውያን የወሲብ ሕይወታቸው ደካማ ነው ተባለ በሦስተኛው ሳምንት መከላከያ ሚኒስትሩን ገድለው ያመለጡት ጄ ል አበራ ጉለሌ አካባቢ ከተደበቁበት ዘመድ ቤት ተከበቡ። በመስኮት ዘለው ጣሪያ ላይ ወጥተው ሊያመልጡ ሲሉ በአንድ ወጣት ፖሊስ ግንባራቸውን ተመትተው ወደቁ። አንዳንድ የሰው መረጃዎች ጄ ል አበራን አሳልፎ የሰጣቸው ዘመድ ዛሬም ድረስ በጸጸት ይኖራል ይላሉ። ከሆኑ ወራት በኋላ የአሥመራውን አየር ወለድ ጦር አዲስ አበባ ይዘው የመጡት ጄኔራል ቁምላቸው በአንዳች ተአምር አምልጠው አሜሪካ ገቡ ተባለ። ሲአይኤ እንዳሾለካቸው ተጠረጠረ። የስኳር ፋብሪካዎችን ለግል ባለሃብቶች የመስጠት ፋይዳና ፈተናዎቹ ከዓመት በኋላ ግንቦት ፣ መፈንቅለ መንግሥቱ ላይ ተሳትፈዋል የተባሉ ጄኔራሎች ድንገት ለውሳኔ ተጠሩ። የወታደራዊ ፍርድ ቤት የመሀል ዳኛው ጄ ል አሥራት ብሩ በብጣሽ ወረቀት የተጻፈችና ከኮ ል መንግሥቱ እንደተላከች የምትገመት አንዲት ወረቀት እንባ እየተናነቃቸው አነበቧት ተባለ። በ ቱ ላይ ሞት ተፈረደ። ፍርደኞቹም እንዲህ እያሉ ይጮኹ ነበር፤ ቤተሰባችንን ሳንሰናበት አትግደሉን ፣ ፈላጭ ቆራጭ አገዛዝ ዕድሜ የለውም ፣ ልጆቻችንን አደራ ። ያንኑ ምሽት ተረሸኑ። ከስዒረ መንግሥት ሙከራው ከ ዓመት በኋላ ግንቦት ቀን ኮ ል መንግሥቱ ከአገር ሸሹ። የኮ ሉን ሽሽት ተከትሎ ለአንድ ሳምንት ርዕሰ ብሔር የሆኑት ጄ ል ተስፋዬ ገብረኪዳን ሞታቸውን እየተጠባበቁ ለነበሩ ጥቂት የመፈንቅለ መንግሥቱ ተከሳሾች ምሕረትን አወጁ። ተያያዥ ርዕሶች
ሰማይ ላይ ወልዳ አሥመራ የምትታረሰው ኢትዮጵያዊት
ማርች ጀነቲ ሁሴን መሐመድ ትባላለች፤ የስምንት ወር ነፍሰ ጡር ነበረች። ኑሮዋን የመሠረተችው ደግሞ ባሕር ማዶ፤ ሳዑዲ። ቅዳሜ ዕለት ታዲያ በቤተሰቦቿ ተከ ባ ለመውለድ፣ በሀገሯ እና በወገኖቿ መካከልም ለመታረስ በማሰብ፣ ከሳውዲ አረቢያ ወደ ኢትዮጵያ ጓዟን ሸካክፋ አውሮፕላን ተሳፈረች። አውሮፕላኑ የኤርትራ አየር ክልል ውስጥ እንደገባ ግን ያላሰበችው ነገር ገጠማት፤ ምጥ ፈትሮ ያዛት። ዕለቱ ቅዳሜ፣ ሰዓቱም ከማለዳው ሰዓት ከሩብ ነበር። ከሳውዲ ስነሳ ደህና ነበርኩ የምትለው ጀነቲ አውሮፕላን ላይ እወልዳለሁ ብላ እንዳላሰበች ለቢቢሲ ተናግራለች። አውሮፕላን ላይ ከመውጣቷ በፊት ክትትል አድርጋ እንደነበር ስንጠይቃትም ከበረራ አንድ ቀን ቀደም ብሎ ጁምዓ ዓርብ ሆስፒታል ሄዳ ዶክተሮች በቅርብ አትወልጂም እንዳሏት ታስታውሳለች። በነገታው ምጧ ይፋፋማል ብሎ ያሰበም ኾነ ያለመ ማን ነበር አውሮፕላኑ ከሳዑዲ ተነስቶ ቅድሚያ ጅዳ ሲያርፍ የሆነ የመርገጥ ስሜትና ፈሳሽ ውሃ ሲፈሰኝ ተሰምቶኛል ትላለች ጀነቲ፤ ሁኔታው የድንጋጤ ወይም የሌላ ህመም ነው ብላ በማሰብ ለማንም አልተነፈሰችም። በቅርብ እወልዳለሁ ብዬ ስላላሰብኩ ዝም አልኩ እነዚህን ምልክቶቿን ከራሷ ውጪ ለሌላ ሰው ያላዋየችው ጀነቲ አውሮፕላኑ ተነስቶ በረራ ሲጀምርም በዝምታዋ ፀናች። ነገር ግን ጢያራው ከተነሳ ወይ ደቂቃ በኋላ ጓደኞቼን አሞኛል፤ አስተናጋጆቹን ንገሯቸው አልኳቸው። አስተናጋጆቹም መጥተው ሽርት ውሃ መፍሰስ ምናምን ከሆነ ምጥ ነው ብለው ወደ ሆነ ቦታ ወሰዱኝ ትላለች። በአውሮፕላኑ ውስጥ የነበረው ቦታ ጥበት ለምጥ እንዳስቸገራት የምትናገረው ጀኒት ሊያስተኟት ሲሉ ሽርት ውኃዋ መፍሰሱን ታስታውሳለች። አስተናጋጆቹ በሁኔታው ተደናግጠው ባለሙያ ከተሳፋሪዎቹ መካከል እንዳለ ቢጠይቁም ባለመገኘቱ እራሳቸው እንደረዷት ትዝ ይላታል። ይህ ሁሉ ሲሆን የነ ጀነቲ አውሮፕላን በአስመራ አየር ክልል እየበረረ እንጂ መሬት አልረገጠም። መንታ በሰማይ ላይ ብዙ ሰዎች ጀነቲ ልጆቿን የተገላገለችው በኤርትራ አስመራ እንደሆነ ነው የገባቸው። እውነታው ትንሽ ይለያል። የመጀመሪያዋ ልጄ አውሮፕላኑ ከማረፉ በፊት የተወለደች ሲሆን ሁለተኛዋ ግን አውሮፕላኑ አርፎ ሞተሩን ለማብረድ እየተንደረደረ ነበር የተወለደችው በማለት መንታ ልጆች የታቀፈችበትን የሰማይ ላይ ድራማ በስሱ ታስታውሳለች። ስም አወጣሽላቸው ብለን ስንጠይቃት ነገሩን እንዳላሰበችበት በሚያሳብቅ አግራሞት፣ ወላሂ ማን እንደምላቸው ገና እያሰብኩበት ነው ብላለች። ጀኒት መንታ ስትወልድ የመጀመሪያዋ ነው። ከዚህ በፊት አንድ ወንድና ሁለት ሴት ልጆች አሏት። አሁን ምድር ላይ የተወለዱ ሦስት ልጆቿን ጨምራ በሰማይ ከተወለዱት ሁለቱ ጋር የአምስት ልጆች እናት ሆናለች። ቅዳሜ ዕለት ልጆቿን አውሮፕላን ላይ በሰላም ከተገላገለች በኋላ በቀጥታ የተወሰደችው በአስመራ ከተማ ትልቅ ወደሚባለው ኦሮታ ሪፈራል ሆስፒታል ነው። የሆስፒታሉ የሕፃናት ሐኪም ዶ ር ዘሚካኤል ዕቁበም ጀኒት በአውሮፕላን ውስጥ በሰላም መውለዷን አረጋግጠው እነርሱ በፍጥነት በስፍራው በመድረስ ድህረ የወሊድ ህክምና እንደሰጧት ገልፀዋል። ጀኒት ቅዳሜ፣ መጋቢት ፣ ብትወልድም እስከዛሬ ድረስ ወደ ሀገሯ ያልተሸኘችው የሁለተኛዋ መንታ ጨቅላ የደም ማነስ ሁኔታ ስለነበራት ነው ብለዋል። አሁን የደምዋ መጠንና አመጋገቧም እየተስተካከለ መጥቷል ያሉት ዶ ር ዘሚካኤል ጨቅላዋ ሙሉ ጤንነቷ ከተመለሰ በኋላ ሁሉም ወደቤታቸው እንደሚሄዱ አረጋግጠዋል። በአስመራ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጉዳዩን በቅርበት እየተከታተለ እንደሆነ የኤምባሲው ሁለተኛ ፀሐፊ የሆኑት አቶ ዘሪሁን መገርሳ ነግረውናል። ለመሆኑ በተርሚናል አምጦ፣ በሰው አገር ሰማይ ወልዶ፣ በአሥመራ ታርሶ የልጆቹ ዜግነት ከወዴት ነው ተያያዥ ርዕሶች
አሥመራ፡ ከመኪኖች ይልቅ ብስክሌቶች የሚበዙባት ከተማ
ማርች ማጋሪያ ምረጥ ጦርነትና ከዓለም መድረክ መነጠልን ጨምሮ በሌሎችም በርካታ ምክንያቶች ታስቦባቸው ባይሆንም ኤርትራን ለብስክሌትና ለብስክሌተኞች ምቹ ስፍራ እንድትሆን አድርጓታል። አሥመራ ሺህ ብቻ ነዋሪዎች ሲኖሯት ዝቅተኛ ደሞዝ፣ ከፍተኛ ቀረጥና የነዳጅ እጥረት ከተማዋ ትንሽ ተሽከርካሪ እንዲኖራት ምክንያት ናቸው። ብዙ ጊዜ የሚታዩት ሰዎችም በተለየ የእድሜ ክልል ውስጥ ናቸው። የአሥመራ መንገዶች በአንፃራዊነት ከመኪና ብቻ አይደለም ነፃ የሆኑት። ሃገሪቱ ዜጎች እንደሚሉት ኤርትራዊያን ባለፉት ዓመታት አካባቢያዊ ግጭት በፈጠረው ጫናና የግዳጅ ብሔራዊ አገልግሎትን ሸሽተው በርካታ ወጣቶች ሃገራቸውን ጥለው ተሰደዋል። አሥመራ በተለያዩ ምክንያቶች በመኪና ከተጨናነቁ ሌሎች የአፍሪካ ከተሞች የተለየ መልክ አላት። ይህ አስገራሚ ከሆነው የከተማዋ አየር ንብረት ጋር ተጨምሮ ብስክሌተኞች በከተማዋ እንዲያንዣብቡ ድንቅ ስፍራ ሆናለች። የ ዓመቱ ወጣትም ብስክሌት መጋለብ አንዱ ባህላችን ሆኗል በማለት ይገልፃል። የአሥመራ የኪነ ሕንፃ ስብስብም በቅርብ በዩኔስኮ የዓለም ቅርስነት የተመዘገበ ሲሆን እ አ አ ከ እስከ የቆየው የጣልያን ቅኝ ግዛት ትሩፋቶች ነው። የብስክሌት መጠገኛ ሱቆች አሥመራ ውስጥ በስፋት ይገኛሉ። ከ ዓመታት ጦርነት በኋላ ከኢትዮጵያ ተነጥላ ሉዓላዊት ሃገር የሆነችው ኤርትራ ከነጻነት በኋላ በገጠማት ከዓለም አቀፍ ግንኙነት መገለል ምክንያት ብስክሌትም ሆነ የመለዋወጫ አካላትን ወደ ሃገሪቷ ማስገባት እጅግ በጣም ውድ እንዲሆን አድርጎታል። ኤርትራዊያን በቀለምም ሆነ በዓይነታቸው የተለያዩ ዓይነት ብስክሌቶችን ይነዳሉ። የተራራ ብስክሌቶች፣ የከተማ ብስክሌቶችና የውድድር ብስክሌቶች ይጠቀሳሉ። ኤርትራዊያን ከህፃን እስከ አዋቂ፣ ሴቶችና ወንዶች፣ አትሌቶችና የቤት እመቤቶች ሁሉም ብስክሌትን ተላምደዋል። የህዝብ አውቶብስ የሚጠቀሙ ነዋሪዎች ከመጠን በላይ የተጨናነቀው አውቶብስ ላይ ከመግባታቸው በፊት ለረጅም ሰዓታት ቆመው መጠበቅ አለባቸው። አውቶብሶች በጣም ጥቂትና ያገጁ ናቸው። በአስመራ ብስክሌት ህይወትን ነው የሚያድነው ትላለች የ ዓመቷ ሰላም። መንግሥት የአካባቢ ጥበቃን ለረጅም ጊዜ ሲቀሰቅስ ቆይቷል። የፕላስቲክ ምርትንና አጠቃቀምን መቀነስ፣ ደንን ማልማት፣ የሃገሪቷን አረንጓዴ ቦታዎች መንከባከብና የቻይናና የዱባይ ብስክሌቶችን መጠቀም ከወሰዳቸው አንዳንድ እርምጃዎች መካከል ናቸው። ለብዙ ኤርትራዊያን መኪኖች ቢኖሩ እንኳን እንደ ብስክሌት ዋጋ ተመጣጣኝ አይደሉም። ከኢትዮጵያ ጋር በቅርብ በተደረገው የሰላም ስምምነት አማካኝነት ድንበሩ በ ዓመታት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ተከፍቷል። አሁን ርካሽ የኢትዮጵያ ሸቀጣ ሸቀጦች በሃገሪቷ ሙሉ ይሸጣሉ፤ ይህም የኑሮ ውድነቱን እያቀለለ ነው። የግጭት፣ ከዓለም መገለልና የተባበሩት መንግሥታት ማዕቀብ ከዘጠኝ ዓመታት በኋላ ባለፈው ህዳር ቢያበቁም፤ በኤርትራ አሁንም የብዙ ምርቶች እጥረት አለ። የነዳጅ እጥረት መኪኖች ለረጅም ሰዓታት እንዲቆሙ በማድረግ ሰዎች በእግራቸው ከመሄድና ብስክሌት ከመንዳት ሌላ ብዙ ምርጫ እንዳይኖራቸው አድርጓል። ብስክሌት መንዳት በኤርትራዊያን ዘንድ በጣም የታወቀ ስፖርት ነው። ለመጀመሪያ ጊዜ በጣልያዊያን የተዋወቀው የብስክሌት ውድድር ለኤርትራ ህዝብ የኩራት ምንጭ ነው። ሞሳና ድበሳይን ያካተተው የሃገሪቱ ብሔራዊ ቡድን በዓለም አቀፍ የውድድር መድረኮች በጣም ስኬታማ ነው። በቅርብ ከኢትዮጵያ ጋር የተደረገው ግንኙነት ብዙ ኤርትራዊያን የሃገራቸው ኢኮኖሚ በፍጥነት እንደሚያድግና የዕለት ከዕለት ኑሯቸውን እንደሚያቀልላቸው ተስፋ ያደርጋሉ። በአንትሮፖሎጂስት ሚሊና ቤሎኒ እና በጋዜጠኛ ጄምስ ጄፍሪ ተያያዥ ርዕሶች
በጋዛ የእስራኤልና የፍልስጥኤም ግጭት እየተባባሰ ነው
ኅዳር አውቶቡስ ላይ በተሰነዘረ ጥቃት አንድ እስራኤላዊ በፅኑ ተጎደቷል እስራኤል እሁድ እለት በጋዛ ያደረገችውን ስውር ወታደራዊ ተልኮ ተከትሎ ሰባት ታጣቂዎችና አንድ እስራኤላዊ ወታደር ሞተዋል። ታጣቂዎቹ ሮኬቶችንና ሞርታሮችን እስራኤል ላይ አስወንጭፈዋል። በተለይም አንደኛው ሮኬት አወቶብስ መትቶ በአቅራቢያው የነበረ ወታደርን በፅኑ ማቁሰሉ ተዘግቧል። በአፀፋው ደግሞ እስራኤል የሃማስና የኢዝላሚክ ጂሃድ ይዞታ ናቸው ባለቻቸው ቦታዎች ላይ ከ በላይ የአየር ጥቃቶችን ፈፅማለች። በዚህም ሶስት ፍልስጥኤማዊያን የተገደሉ ሲሆን ሁለቱ ወታደሮች ናቸው። ሃማስ የሚያስተዳድረው ይዞታ ጤና ጥበቃ በጥቃቱ ዘጠኝ ሰዎች መጎዳታቸውን አስታውቋል። በእስራኤል በኩልም በተመሳሳይ አስር ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል ተብሏል።
ሜጀር ጄኔራል ክንፈ ዳኘው ጠበቃ ራሳቸው እንዲያቆሙ ተወሰነ
ኅዳር ይህንን ለማጋራት በ ዋትስአፕ ሜጄር ጄኔራል ክንፈ ዳኘውና ሌሎችም ተጠርጣሪዎች በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ኛ የወንጀል ችሎት ቀርበዋል። በትናንትናው የፍርድ ቤት ውሎ ሜጄር ጄኔራል ክንፈ፤ ደሞዜ አነስተኛ ስለሆነ ፍርድ ቤቱ ጠበቃ እንዲያቆምልኝ እጠይቃለሁ በማለታቸው ፍርድ ቤቱ ለዛሬ ከሰዓት ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱ ይታወሳል። በትላንትናው የፍርድ ቤት ውሎ፤ ሜጀር ጀነራል ክንፈ ከጡረታ የማገኘው ገንዘብ ብር ስለሆነ ፍርድ ቤቱ ጠበቃ እንዲያቆምልኝ እጠይቃለሁ ሲሉ ለዳኞች አስታውቀዋል። ዛሬ ፖሊስ ሜጄር ጄኔራል ክንፈ ጠበቃ የማቆም አቅም እንዳላቸው የሚያረጋግጥ ማስረጃ አለኝ ብሏል። ፖሊስ እንደሚለው፤ ሜጄር ጄኔራል ክንፈ በጸረ ሙስና ኮሚሽን ያስመዘገቡት የሃብት መጠን እና በአንድ ባንክ ውስጥ ያላቸው ተቀማጭ ሂሳብ ጠበቃ የማቆም አቅም እንዳላቸው ያመላክታል። ፖሊስ ከ ቀን በፊት አንድ መቶ ሺህ ብር ከባንክ ሂሳባቸው ወጪ መደረጉን እና በስማቸው ቤት እንዲሁም ሺህ ብር የሚያወጣ መኪና ተመዝግቦ እንደሚገኝ ለፍርድ ቤቱ አስረድቷል። ሜጀር ጄኔራል ክንፈ በበኩላቸው ፖሊስ የጠቀሰው ንብረት እና ገንዘብ የእኔ አይደለም ሲሉ ለፍርድ ቤቱ ምላሽ የሰጡ ሲሆን፤ ቤት የለኝም፣ መኪና የለኝም፣ ንብረት የለኝም። ያለኝ ሰውነቴ ብቻ ነው በማለት ለፍርድ ቤቱ አስረድተዋል። ሆኖም ፍርድ ቤቱ ሜጄር ጄኔራል ክንፈ የራሳቸውን ጠበቃ እንዲያቆሙ ውሳኔ አስተላልፏል። ሜጄር ጄኔራሉ እና ወንድማቸው አቶ ኢሳያስ ዳኘው ለህዳር ፣ ዓ ም ቀጠሮ ተሰጥቷቸዋል። ከሜጄር ጄኔራሉ ጋር የቀድሞ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ጋዤጠኛ ፍጹም የሺጥላ፣ ሳጅን ኪዳኔ አሰፋ፣ ትዕግስት ታደሰ እና አቶ ቸርነት ፍርድ ቤት ቀርበዋል። ወ ሮ ፍጹም የሺጥላ ወ ሮ ፍጹም የሺጥላ ከሜቴክ የስራ ኃላፊዎች ጋር ያልተገባ የጥቅም ግንኙነት በመፍጠር ፍጹም ኪነ ጥበባት በሚሰኝ የንግድ ስም ህጋዊ ባልሆነ መንገድ የ ሺህ ብር የስራ ስምምነት ከሜቴክ ጋር ተዋውለዋል የሚል ክስ ቀርቦባቸዋል። ወ ሮ ፍጹም የቤተሰብ አስተዳዳሪ መሆናቸውን እና ከሕግ ለማምለጥ ሙከራ አለማድረጋቸውን በመጥቀስ የዋስትና መብት እንዲከበርላቸው ቢጠይቁም ፍርድ ቤቱ ግን የዋስትና መብት ከልክሏል። ከሙስና ወንጀል ጋር በተያያዘ ዛሬ ፍርድ ቤት ከቀረቡት መካከል የሜጄር ጀነራል ክንፈ ዳኘው ወንድም ኢሳያስ ዳኘው ይገኙበታል። እንደ ሜጀር ጀነራል ክንፈ ወንድማቸው አቶ ኢሳያስ ዳኘውም ገንዘብ ከፍለው ጠበቃ ማቆም እንደማይችሉ በመጥቀስ፤ መንግሥት ጠበቃ እንዲያቆምላቸው መጠየቃቸው ይታወሳል። የኢትዮቴሌኮም ሰራተኛ ሳሉ የግዢ ስርዓቱ በማይፈቅድ መልኩ ሜቴክ ጨረታ እንዲያሸንፍ በማድረግ ወንጀል ተጠርጥረው ፍርድ ቤት የቀረቡት አቶ ኢሳያስ ወራሃዊ ደሞዜ ሺህ ብር በመሆኑ ጠበቃ ማቆም አልችልም ብለው ነበር። ሜጀር ጄነራል ክንፈ ዳኘው ማክሰኞ እለት በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ይታወሳል። ፋና ብሮድካስቲንግ፤ ሜጀር ጄነራል ክንፈ ወደ ሱዳን ለመውጣት ሲሞክሩ በቁጥጥር ሥር ዋሉ ብሎ የዘገበ ሲሆን፤ ኢቢሲ ደግሞ በትግራይ ክልል ባካር ተብሎ በሚጠራ ስፍራ በኩል ለማምለጥ ሲሞክሩ በትግራይ ክልል ልዩ ፖሊስ በቁጥጥር ሥር ውለዋል ሲል ዘግቧል። በሰብዓዊ መብት ጥሰትና በሙስና የተጠረጠሩት ግለሰቦች ሰኞ ዕለት ከፍተኛ ፍርድ ቤት ኛ የወንጀል ችሎት ቀርበው ነበር። ፍርድ ቤት ከቀረቡት መካከል ቱ በሰብዓዊ መብት ጥሰት ወንጀል ተጠርጥረው እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን፤ ቱ ከብሄራዊ መረጃና ደህንነት፣ ስድስቱ ከፌዴራል ፓሊስ ምርመራ ቢሮ፣ ሁለቱ ከአዲስ አበባ ፓሊስ ኮሚሽን፣ ስምንቱ ከፌዴራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ሲሆኑ፤ ሶስቱ ግለሰቦች ደግሞ ተጠርጣሪን በማስመለጥና ሰነድ በማጥፋት የተጠረጠሩ ናቸው። ብርጋዲየር ጄኔራል ጠና ኩርዲንን ጨምሮ የሜቴክ ሰራተኞችም በሙስና ተጠርጥረው ፍርድ ቤት የቀረቡ ሲሆን፤ የስኳር ገንዘብን ያለአግባብ በመጠቀም፣ የህዳሴ ግድብና የያዩ ማዳበሪያ ፕሮጀክቶች ላይ ህግን ያልተከተለ ግዢ በመፈፀም ተከሰዋል። ከዚህም በተጨማሪ ሁለት መርከቦችን ለህገወጥ ንግድ በመገልገል ክስ የተወነጀሉ ሲሆን፤ የግራ ቀኙን ክርክር ያዳመጠው ፍርድ ቤትም የተጠርጣሪዎችን የዋስትና ጥያቄ ውድቅ በማድረግ ፖሊስ የጠየቀውን የ ቀን ጊዜ የፈቀደ ሲሆን፤ ለህዳር ቀን ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል። የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ አቶ ብርሀኑ ጸጋዬ፤ የቀድሞ የብሄራዊ ደህንነት እና መረጃ ኤጀንሲ አመራሮች እና አባላት በሽብር እና ከሽብር ጋር በተያያዘ ተጠርጥረው የተያዙ ግለሰቦች ላይ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ሲፈጽሙ ነበር ብለዋል። ከሰብዓዊ መብት ጥሰትና ከሙስና ጋር በተያያዘ የተሰሩ ወንጀሎችን በተመለከተ ባለፉት አምስት ወራት ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ሲያከናውን የነበረውን የምርመራ ውጤት ሕዳር ቀን ዓ ም ይፋ አድርጓል። ጠቅላይ አቃቤ ሕጉ በመግለጫቸው፤ በግለሰቦችና በተቋማት ደረጃ ተፈጽመዋል ያሏቸውን የሰብዓዊ መብት ጥሰትና የሙስና ወንጀሎች ዘርዝረዋል። የሰብዓዊ መብት ጥሰቶቹ ሲፈጸሙ የነበረው በኃላፊዎች ነው። የሙስና ወንጀሉ ሰፊና ውስብስብ ስለሆነ የምርመራ ሂደቱ ቀላል አልነበረም ብለዋል። ጠቅላይ አቃቤ ሕጉ ሰዎቹን ሳናስራቸው በፊት ከሕግና ከአሰራር አንጻር መረጃና ማሰረጃ ለማደራጀት ሰፊ ጊዜ ወስዶብናል በማለት እስካሁን ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር ያልዋሉበትን ምክንያት አስረድተዋል።
የዓመቱ ሐሰተኛ ዜናዎች በአፍሪካ፡ በኢትዮጵያ ሶማሌዎች ጥልቀት ወዳለው መቃብር እየተወረወሩ ነው መባሉ
ኖቬምበር ስለ ማጋራት ተጨማሪ ያጋሩ ማጋሪያ ምረጥ በአፍሪካ ውስጥ የሐሰት ዜና መሰራጨት የብሔር ግጭቶችን ማባባስ፣ በመራጮች ዘንድ ግራ መጋባትን በማምጣትና የገንዘብ መዋዠቅን እንዳስከተለ እየተወነጀለ ነው። ቢቢሲ የሐሰት ዜና በአፍሪካ ምን አይነት ገፅታ አለው በሚለው ጉዳይ ላይ ጥናት ያደረገ ሲሆን በባለፉት ወራት ውስጥም ከፍተኛ ተፅእኖ ማምጣት የቻሉ አምስት ሐሰተኛ ዜናዎችን ተመልክቷል። ናይጀሪዊው የፕሬዚዳንት ተወዳዳሪ በተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪያን ድጋፍ ማግኘቱ ዜናው ምን ነበር በአውሮፓውያኑ ዓ ም ለሚካሄደው የናይጀሪያ ምርጫ ተወዳዳሪ በሆኑት አቲኩ አቡባከር ስም የተከፈተ ሐሰተኛ የትዊተር ገፅ የተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪያን ማህበር የሆነውን አሶሼስን ኦፍ ናይጀሪያን ጌይ ሜን ለድጋፋቸው ምስጋናን ለግሷል። በትዊተር ገፁ የሰፈረው ፅሁፍ እንደሚያመለክተው አቲኩ አቡባከር ፕሬዚዳንት ሆነው ቢመረጡ ቀዳሚ ተግባራቸው በአገሪቱ ውስጥ አከራካሪ የሚባለውን የተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪያን ህግን መቀየር ሲሆን፤ ይህ ህግ ሆኖ የፀደቀው በፕሬዚዳንት ጉድላክ ጆናታን በአውሮፓውያኑ ዓ ም ነው። የተመሳሳይ ፆታ ፍቅርን መመስረት በናይጀሪያ ዓመት ያህል እስር የሚያስቀጣ ሲሆን፤ ጋብቻም የተከለከለ ነው። ዜናው ምንን አስከተለ አጭር የምስል መግለጫ የሐሰተኛ ዜና የወጣበት የጦማርያን ገፅ በመጀመሪያ ይህ ፅሁፍ የሰፈረው በጥቅምት ወር ላይ ሲሆን፤ ቀጥሎም ሁለት ጦማሪያውያን ይህንኑ ዜና አወጡት። በዚያው አላበቃም ከ ቀናት በኋላ በናይጀሪያ ውስት ታዋቂ የሚባሉት ዘ ኔሽንና ቫንጋርድ የተባሉት ጋዜጦችም ዜናውን ባለበት ይዘውት ወጡ። ከዚህም በተጨማሪ ዳይቨርስ የተባለ የተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪዎች ድርጅት አቡበከር ነፃ የሆነ አስተሳሰብ ያላቸው ተወዳዳሪ ናቸው በማለትም ድጋፋቸውን እንደሚለግሱ ገለፁ። ለፕሬዚዳንትነት የሚወዳደሩ ግለሰብ የተመሳሳይ ፆታ ፍቅርን መብት መደገፋቸው ሐሰተኛ ዜና ጠንቅ ሊፈጥር የሚችል ጉዳይ ነው። በናይጀሪያ ውስጥ የተመሳሳይ ፆታ ፍቅርን በመቃወም የሚታወቁት የእስልምናና የክርስትና እምነት መሪዎች ተከታዮቻቸውን እንዳይመርጡ መልዕክት ሊያስተላልፉ ይችላሉ። ሐሰተኛ ዜና መሆኑ እንዴት ታወቀ የትዊተር ገፁ የፖለቲከኛው አቲኩ አቡባከር ሳይሆን፤ የፖለቲከኛው ትክክለኛ የትዊተር አካውንታቸው ገፅ በትዊተር የተረጋጋጠ ሰማያዊ ምልክት እንዳለው ተረጋገጠ። ከዚሀም በተጨማሪ በትዊተር ገፁ፣ በጦማሪዎቹ ፅሁፍም ሆነ በጋዜጦቹ ዜና ላይ የተጠቀሰው የተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪው ድርጅትም ስለመኖሩ ምንም አይነት ማረጋገጫ የለም። ድርጅቱ በናይጀሪያ ህግ መሰረት ህጋዊ ሆኖ መመዝገብ አይችልም። ድርጅቱም ሆነ የድርጅቱ ቃል አቀባይ ተብሎ የሰፈረው ስፒንኪ ቪክተር ሊ የመጀመሪያ ፀሁፋቸውን በትዊተር ካሰፈሩበት ከጥቅምት ወር በፊት በኢንተርኔት ላይ ስማቸው ተጠቅሶ እንደማያውቅም የአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ የዜና ወኪል ሲያጣራ ደርሶበታል። የታዋቂዋ ኬንያዊ ጋዜጠኛ የውሸት ምስጋና ዜናው ምን ነበር የሲኤንኤን የቢዝነስ ፕሮግራም አቅራቢ ሪቻርድ ኩዌስት በኬንያዋ መዲና ናይሮቢ ጥቅምት ወር ላይ ለቲቪ ፕሮግራም ቀረፃ ላይ ነበር። ይህንን ተከትሎም የቀድሞ ዜና አንባቢና ጋዜጠኛ ጁሊ ጊቹሩ በትዊተር ገጿ ሪቻርድ ኩዌስት የኬንያ ቆይታው እንዳስደሰተው ገልፃ ፃፈች። የኬንያን አቀባባል የሚወዳደረው የለም። ይሄው በቀጭኔዎች ተከብቤ ቁርስ እየበላሁ ነው። በአለም ባንክ በአፍሪካ ምርጥ የኢንቨስትመንት መዳረሻ ከተባለች ኃገር ይሄንን አይነት አቀባበል ማግኘቴ የሚገርም አይደለም። በእውነቱ ኬንያ ተአምራዊ ናት የሚል ፅሁፍም እሱን ጠቅሳ በተጨማሪ አሰፈረች። አጭር የምስል መግለጫ ሐሰተኛው ጥቅስ ዜናው ምን አስከተለ ጁሊ በትዊተር ከሚሊዮን በላይ እንዲሁም በኢንስታግራም ከ ሺ በላይ ተከታዮች ያሏት ሲሆን፤ ዜናው በወጣ በደቂቃዎች ውስጥ በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ግለሰቦች ዜናውን አጋሩት። በሚዲያ ኢንዱስትሪው ታዋቂ ከመሆኗ አንፃር እንዲህ አይነት ሐሰተኛ ዜና ማውጣቷ ብዙዎች አፊዘውባታል። ሐሰተኛ መሆኑ እንዴት ታወቀ የሲኤንኤኑ ጋዜጠኛ ትዊቷን ተመልክቶ እንዲህ አይነት መግለጫ እንዳልሰጠ አስታወቀ። በፃፈችውም ፅሁፍ ላይ ተመርኩዞ ትክክል እንዳልሆነ ምላሽ ሰጥቷታል። በምላሹም ጁሊ ጊቹሩ ይቅርታ የጠየቀች ሲሆን የመጨረሻ ፅሁፏንም አጥፍታዋለች። በኢትዮጵያ ሶማሌዎች ጥልቀት ወዳለው መቃብር እየተወረወሩ ነው ዜናው ምን ነበር በሐምሌ ወር በአሜሪካ ተቀማጭነቱን ያደረገው ኢሳት ብሄራቸው ኦሮሞ የሆኑ ግለሰቦች ሶማሌዎችን ጥልቀት ወዳለው መቃብር እየወረወሩ እንደሆነ የሚዘግብ ቪዲዮ ይዞ ወጣ። ቪዲዮው ባለፈው አመት በሁለቱ ህዝቦች አስከፊ ግጭት ባጋተመበት የኢትዮጵያ ኦሮሚያ ክልል የተቀረፀ መሆኑን ተገልጾ ነበር። አጭር የምስል መግለጫ ቪዲዮው ሰዎች ወደ ጥልቅ ጉድጓሱ ሲወረወሩ ያሳያል ዜናው ምን አስከተለ የቢቢሲ አፋን ኦሮሞ ቋንቋ ክፍል እንደዘገበው ይህ ቪዲዮ በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያዎች በከፍተኛ ሁኔታ በመሰራጨቱ በጂቡቲና በሶማሊያ የሚኖሩ ኦሮሞዎች ጥቃት ደርሶባቸዋል። በጂቡቲ ነዋሪ የሆኑ ኦሮሞዎች ለቢቢሲ እንደተናገሩት በቪዲዮ ምክንያት ድብደባ የደረሰባቸው ሲሆን፤ የንግድ ቦታቸውም ተዘርፏል። ሐሰተኛ መሆኑ እንዴት ታወቀ ይህ ቪዲዮ በሰኔ ወርም በካሜሮን ፈረንሳይኛና እንግሊዝኛ ተገንጣዮችም መካከል የተከሰተ ግጭት እንደሆነም ተደርጎ ብዙዎች አጋርተውታል። በኢሳት የቀረበው ቪዲዮ የኦሮሞ ወጣቶችን ድምፅ ከነበረው ትክክለኛ ድምፅ በላይ በማስገባት የቀረበ ነው። ኢሳት ቪዲዮው ትክክለኛ አለመሆኑን ሲያውቅ ወዲያውኑ ቪዲዮውን ከገጹ ላይ በማንሳት በዩቲዩብ ገጹ በኩል በይፋ ይቅርታ ጠይቋል። ነገር ግን ኢሳት ቴሌቪዥን ቪዲዮውን ስለማቀናበሩና ቪዲዮው ሃሰተኛ መሆኑን እያወቀ ስለማሰራጨቱ የሚያመለክት ነገር የለም። ማስተካከያ ዲሴምበር ፡ ይህ ጽሁፍ የኢሳት ቴሌቪዥን ቪዲዮውን አለማቀናበሩን ወይም ቪዲዮው ሃሰተኛ መሆኑን እያወቀ እንዳላሰራጨ ግልጽ ለማድረግ መስተካከያ ተደርጎበታል። የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ጃኮብ ዙማ መልቀቅ ዜናው ምን ነበር በየካቲት ወር የደቡብ አፍሪካው ኤስኤቢሲ ጋዜጠኛ በወቅቱ ፕሬዚዳንት የነበሩት ጃኮብ ዙማ ስልጣን ለመልቀቅ መስማማታቸውን ዘገበ። ባለስልጣናትን እንደምንጭ በመጠቀም ሼቦ ኢካኔንግ በቀጥታ ስርጭቱ ላይ ሰበር ዜና በሚል አስተላለፈው። በወቅቱም የአፍሪካ ናሽናል ኮንግረስ ከፍተኛ አመራር አባላት በቀድሞው ፕሬዚዳንት ጃኮብ ዙማ እጣ ፈንታ ላይ ለመወሰን ስብሰባ ላይ ነበሩ። ሌላኛው የደቡብ አፍሪካ ጋዜጠኛም ይህንኑ ዜና በትዊተር ገፁ አጋራው። ፕሬዚዳንት ጃኮብ ዙማ በተለያዩ የሙስና ቅሌቶች ከፍተኛ ግፊት እየተደረገባቸው የነበረ ሲሆን፤ ከፓርቲያቸውም በተደጋጋሚ እንዲወርዱ ጥያቄ ቀርቦላቸዋል። ሃገሪቷም ፕሬዚዳንቱ ሊለቁ ይችላል የሚለውን ዜና በጉጉት እየጠበቁት ነበር። ዜናው ምን አስከተለ ፕሬዚዳንት ጃኮብ ዙማ ለቀቁ የሚለውን ዜና ተከትሎ በአንድ ፐርሰንት ጨምሮ የነበረው የደቡብ አፍሪካ ራንድ፤ ቃል አቀባዩ የኤስኤቢሲ ሪፖርትን ውሸት ነው ብለው ማጣጣላቸውን ተከትሎ ወደነበረበት ተመልሷል። ዜናው ሐሰት ነበር የፕሬዚዳንት ጃኮብ ዙማ ቃል አቀባይ ሐሰተኛ ዜና ነው በሚል ሪፖርቱን አጣጣለው። ነገር ግን ከሶስት ቀናት በኋላ ጃኮብ ዙማ ከስልጣን ለቀቁ። የታንዛንያው መሪ ሴተኛ አዳሪነትን ለማስቀረት ከአንድ በላይ ሚስት ማግባትን መደገፋቸው ዜናው ምን ነበር የታንዛንያው ፕሬዚዳንት ጆን ማጉፉሊ ሴተኛ አዳሪነትን ለማስቀረት ወንዶች ከአንድ በላይ ሚስት ማግባት እንዳለባቸው ተናግረዋል የሚል ዜና በከፍተኛ መንገድ ተሰራጨ። በፅሁፉ እንደተጠቀሰው ወንዶች በተገኙበት ኮንፍረንስ ፕሬዚዳንቱ ከ ሚሊዮን ታንዛንያውያን መካከል ሚሊዮኖቹ ሴቶች እንደሆኑና ሚሊዮኖች ወንዶች እንደሆኑ ገልፀዋል የተባለ ሲሆን ፤ በወንዶች እጥረት ምክንያት ሴተኛ አዳሪነትና ዝሙት እየጨመረ መምጣቱን ፕሬዚዳንቱ ተናግረዋል ብሎ ፅሁፉ ጠቅሷል። ዜናው ምን አስከተለ በእንግሊዝኛ ቋንቋ በመጀመሪያ በዛምቢያ ኦብዘርቨር በየካቲት ወር የታተመው ዜና ምንም አልፈጠረም ነበር። ነገር ግን በታንዛንያ ብሄራዊ ቋንቋ ስዋሂሊ በኒፓሽኦንላይን ድረገፅ የታተመው ፅሁፍ ከፍተኛ ተነባቢነትን አገኘ። ድረ ገፁንም ተከትሎ በታዋቂው ጃማይ ፎረምስ ድረገፅ መታተሙን ተከትሎ በኬንያ፣ ዛምቢያ፣ ደቡብ አፍሪካና ጋና ድረ ገፆች ለመታተም በቃ። ሐሰተኛ መሆኑ እንዴት ታወቀ የታንዛንያ የመንግሥት ቃል አቀባይ በስዋሂሊ ቋንቋ ፕሬዚዳንቱ እንዲህ አይነት አስተያየት እንደማይሰጡና ሰዎችም ቸላ ሊሉት እንደሚገባ በማውገዝ በትዊተር ገፁ አስቀመጠ። የቢቢሲ ስዋሂሊም እውነተኛነቱን ለማረጋገጥ ባደረገው ምርምር ትክክለኛ አለመሆኑን አረጋግጧል። በሐሰተኛው ዜና ፕሬዚዳንቱ የታንዛንያን የሕዝብ ቁጥር ሚሊዮን እንደሆነና የሴቶች ቁጥር ከወንዶች በአስር ሚሊዮን እንደሚደርስ አስቀምጧል። ነገር ግን በቅርቡ የተባበሩት መንግሥታት ባወጣው የህዝብ ቁጥር ግምት መሰረት የታንዛንያ ህዝብ ቁጥር ከ ሚሊዮን በታች እንደሆነና በፆታዎቹም መካከል ይህ ነው የሚባል ልዩነትም እንደሌለ አስቀምጧል። ይህ ሐሰተኛ ዜና የወጣበት ድረ ገፅም ለብዙ ታንዛንያውያን ከታዋቂው የታንዛንያ ጋዜጣ ኒፓሼ ጋር እንደሚመሳሰልም የቢቢሲ ስዋሂሊ ዘገባ ያሳያል። ነገር ግን ሐሰተኛ ዜና የወጣበት ድረ ገፅና ጋዜጣው ምንም አይነት ግንኙነት እንደሌላቸው ታውቋል። ተያያዥ ርዕሶች
ኦነግ እና መንግሥትን ለማግባባት ወደ ምዕራብ ኦሮሚያ ያቀኑት የሃገር ሽማግሌዎች ወደ አዲስ አበባ ተመለሱ
ኖቬምበር ማጋሪያ ምረጥ በምዕራብ ኦሮሚያ ያጋጠመውን የጸጥታ መደፍረስ በሽምግልና ለመፍታት ወደ ስፍራው አቅንተው የነበሩ የሃገር ሽማግሌዎች ወደ አዲስ አበባ ተመለሱ። ወደ ምዕራብ ኦሮሚያ ካቀኑት የሃገር ሽማግሌዎች መካከል አንዱ የሆኑት ኢንጂነር መስፍን አበበ ለቢቢሲ እንደተናገሩት ነጋዴዎች፣ አባ ገዳዎች እና የሃይማኖት አባቶች ከልዑኩ ቡድን አባላት መካከል ይገኙበታል። አስቀድመን ከነቀምት፣ ጊምቢ እና ደምቢ ዶሎ ከተሞች ነዋሪዎች ጋር ውይይት አድርገናል የሚሉት ኢንጂነር መስፍን የሃገር ሽማግሌዎቹ ከነዋሪዎች የተነሱላቸውን ጥያቄዎች እና አስተያየቶች አድምጠዋል። ከዚያም ጊዳሚ ከሚገኝ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ኦነግ አመራሮች ጋር ውይይት መደረጉን ይናገራሉ። የውይይቱን ውጤት መንግሥት እና ኦነግ መግለጫ የሚሰጡበት ጉዳይ ስለሆነ እኔ በዚህ ላይ ሃሳቤን አልሰጥም ብለዋል። ኢንጅነር መስፍን ጨምረው እንደሚሉት ውይይቱ በአንድ ጊዜ የሚጠናቀቅ ሳይሆን በቀጣይነት ብዙ ወይይት ሊያስፈልግ ይችላል ብለዋል። በጉዟችንም ሆነ በቆይታችን ምንም አይነት ችግር ሳይገጥመን በሰላም ደርሰን ተመልሰናል ይላሉ ኢንጂነር መስፍን። ሌለው የልዑኩ ቡድን አባል የሆኑት የታሪክ መሁሩ ሼክ ሃጂ ኢብራሚም ይገኙበታል። ሼክ ሐጂ እንዳሉት ከተለያዩ የከተማ ነዋሪዎች ጋር በተደረጉት ውይይቶች ላይ በርካታ የመብት ጥያቄዎች ተነስተዋል ብለዋል። ትጥቅ መፍታት ለድርድር አይቀርብም ፡ መንግሥት መሰረተ ልማቶች እንዲገነቡ፣ የኦሮሞ ህዝብ መብት እንዲከበር፣ ኦሮሚያ ውስጥ የሚኖሩ የሌሎች ብሔሮች ተወላጆች መብቶች እንዲከበሩ ለመንግሥት መልዕክት አስተላልፉልን ሲሉ ጠይቀውናል ሲሉ ሼክ ሐጂ ለቢቢሲ ተናግረዋል። በምዕራብ ኦሮሚያ ከሚገኙ የኦነግ ወታደሮች እና አመራሮች ጋር ውይይት ማድረጋቸውን የሚያስታውሱት ሼክ ሐጂ፤ ከፍተኛ አመራሮቻችን አዲስ አበባ ነው ያሉት፤ ከእነሱ ጋር መወያየት ይኖርባችኋል የሚል ምላሽ ከኦነግ ወታደሮች እና አመራሮች እንደተሰጣቸው ይናገራሉ። በተጨማሪም የኦሮሞ ህዝብ መብት ለረዥም ዓመታት ሳይከበር ቆይቷል። የኦሮሞ መብት እንዲከበር እንሻለን። ይህንንም መናገር ያለበት እላይ ያሉት ከፍተኛ አመራሮቻችን ናቸው። ከእነሱ ጋር ተወያይታችሁ ከስምምነት መድረስ ትችላላችሁ እንደተባሉ ሼክ ሐጂ ኢብራሂምም ለቢቢሲ ተናግረዋል። ኦነግ ሀገር ለመገንጠል ነው የምሠራው ብሎ አያውቅም ሽጉጥ ገለታ ዶ ር ወደ ሃገር ውስጥ ሳንገባ በመሪዎቻችን እና በክልሉ ፕሬዚዳንት መካከል የተደረሰው ስምምነት ለምን ተግባራዊ አልተደረገም የሚል ጥያቄ በኦነግ ወታሮች መነሳቱን ሽማግሌዎቹ ገልፀዋል። በሌላ በኩል የኦሮሚያ ክልል መንግሥት ቃል አቀባይ የሆኑት አቶ አድማሱ ዳምጠው ለክልሉ ቴሌቪዥን ጣቢያ ሲናገሩ ወደ ምዕራብ ኦሮሚያ የሄዱት የሃገር ሽማግሌዎች ተደብድበው እና ተዘርፈው የሄዱበትም ዓላማ ሳይሳካ መመለሳቸውን ተናግረዋል። በቄለም ወለጋ ዞን ከሚገኙ ዘጠኝ ወረዳዎች ፖሊስ ጣቢያዎች ውስጥ የጦር መሳሪያ ተዘርፏል የሚሉት አቶ አድማሱ፤ ከአንድ ሺህ በላይ ቀበሌዎች ውስጥ የመንግሥት አስተዳደር እንዲፈርስ ተደርጎ በሌላ ሥርዓት እየተደራጀ ነው ብለዋል። ሼክ ሐጂ ኢብራሂም ግን የተደበደበም ሆነ የተዘረፈ ሰው አላየንም። በሰላም ሄደን በክብር ነው የተሸኘነው ይላሉ። ከውይይታችን መረዳት እንደቻልነው ሁለቱም ወገኖች የሚፈልጉት ሰላም እንዲሰፍን ነው የሚሉት ሼክ ሐጂ፤ ከጥቂት ቀናት በኋላም የኦነግ እና የመንግሥት ባለስልጣናትን አንድ ላይ በማምጣት እንደሚያወያዩ ተናግረዋል። ተያያዥ ርዕሶች
ለኢትዮጵያ ሳተላይት ማምጠቅ ቅንጦት አይደለም የኢትዮጵያ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር
ኖቬምበር አጭር የምስል መግለጫ የመሬት ምልከታ ሳተላይት መሬትን እየቃኘ መረጃዎችን በፎቶ ይመዘግባል የመሬት ምልከታ ሳተላይት የሰው ልጅ በህዋ ሳይንስ ካስመዘገባው ውጤቶች አንዱ ነው። ሳተላይቱ ከምድር ወደ ህዋ ከተመነጠቀ በኋላ መሬትን እየቃኘ መረጃዎችን በፎቶ ይመዘግባል። እንደያስፈላጊነቱም መረጃውን ወደ ምድር ይልካል። አፍሪካ ውስጥ እስካሁን ሳተላይቱን ያመጠቁ በጣት የሚቆጠሩ ሀገሮች ናቸው። ኢትዮጵያም የአምጣቂዎቹን ቡድን ለመቀላቀል መሰናዶ የጀመረችው ከሁለት ዓመት በፊት ነበር። ሳተላይቱን ሀገር ውስጥ ለመስራት እንዲሁም ከኢትዮጵያ ለማምጠቅ የሚያስፈልገው ቴክኖሎጂና የሰው ሀይል ባለመኖሩ ወደ ሩቅ ምሥራቅ ስታማትር፤ ቻይና የገንዘብና የሙያም እገዛ ለመስጠት ተስማማች። ትራምፕ ጠቅላይ አቃቢ ሕጉን አባረሩ ከቻይና ሚሊየን ዶላር ተለግሶ ስራው ተጀመረ። ቻይናውያን ኢንጂነሮች ኢዮጵያውያንን እያሰለጠኑ ሳተላይቱ ቻይና ውስጥ እንዲሁም በከፊል ኢትዮጵያ ውስጥ ተገነባ። ኪሎ ግራም የሚመዝነው ሳተላይት በ ዓ ም መባቻ ላይ ከቻይና ይመጥቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ የኢትዮጵያ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ ር ሰለሞን በላይ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ሳተላይቱ በቻይና እገዛ ከምድረ ቻይና ይምጠቅ እንጂ፤ ተቆጣጣሪዋም፣ አዛዧም ኢትዮጵያ ናት የሚለውን አስምረውበታል። ሳተላይት ማምጠቅ ለምን አስፈለገ የህዋ ጥናት በዓለም ላይ በፍጥነት እየዘመኑ ካሉ ዘርፎች መካከል ይጠቀሳል። የሰው ልጅ ምድር ጠባው አልያም ከምንኖርበት ዓለም ውጪ ያለውን ለማወቅ ጓጉቶ ዘወትር እየቆፈረ ነው። ከህዋ ፍተሻ በተጨማሪ ህዋን ተጠቅሞ መሬትን ማሰስ የመሬት ምልከታ ሳተላይት ተግባር ነው። ሳተላይቱ መረጃ ሲሰበስብ ይህ ቀረህ አይባለውም። ከግዙፍ ክንውኖች እስከ ጥቃቅን እንቅስቃሴዎች ይመዘግባል። እንደ ባለሙያዎች አባባል ሳተላይቱ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ አለው። የአየር ንብረት ለውጥን ለመቆጣጠር፣ የተፈጥሮ አደጋዎች ከመድረሳቸው አስቀድሞ ለመተንበይ፣ ደህንነትን ለመጠበቅ ወዘተርፈ ይውላል። በእርግጥ ብዙዎች በታዳጊ ሀገር የህዋ ጥናት አስፈላጊነቱ ላይ ጥያቄ ቢያነሱም፤ ዶ ር ሰለሞን ህዋ እንደ ኢትዮጵያ ላሉ ሀገሮች የመኖርና ያለመኖር ጥያቄ ነው፤ ቅንጦት አይደለም ይላሉ። የአየር ንብረት ለውጥ የመላው ዓለም ስጋት በሆነበት ዘመን፤ አንዳች ተፈጥሯዊ አደጋ ከመድረሱ በፊት አስቀድሞ መረጃ ማግኘት ብልህነት ነው። የዛፍ ቁጥር፣ የአየር ንብረት ለውጥና ሌሎችም መረጃዎች ከተሰበቡ በኋላ እንደ ጎርፍ ያሉ አደጋዎች ከመከሰታቸው በፊት መተንበይ ይቻላል። በቤታችን ውስጥ ያለ አየር የጤናችን ጠንቅ እንዳይሆን ማድረግ ያለብን ነገሮች ግብርና ቀዳሚ መተዳደሪያ በሆነባት ሀገር የቱ አካባቢ ምርታማ ነው የአየር ንብረት ለውጥ ይኖር ይሆን የሚሉ ጥያቄዎች በቀላሉ እንዲመለሱ የሳተላይቱ መረጃ አስፈላጊ ይሆናል። ዶ ር ሰለሞን እንደሚሉት፤ አንድ የግብርና አካባቢን የሚያሳይ ፎቶግራፍ ስለ እርሻ መሬቱ፣ ስለ ውሀው፣ ስለ አፈሩ ዝርዘር መረጃ ይሰጣል። መረጃዎቹን በመጠቀም ምርታማ የሆኑ አካባቢዎችን መለየት፣ የምርት መጠንን በትክክል ማወቅም ይቻላል። ኢንዱስትሪዎች እየተስፋፉ በመጡባት ኢትዮጵያ፤ ፋብሪካዎች የት መገንባት አለባቸው ለሚለው ጥያቄ የሳተላይቱ መረጃ መልስ ሊሰጥ ይችላል። ሕዝብ መቁጠር ሲያስፈልግ ከዘልማዳዊው መንገድ ሳተላይቱን መጠቀም ይመረጣል። ትክክለኛ መረጃ ከማግኘት፣ ገንዘብና የሰው ሀይል ከማዳን አንጻርም የተሻለው አማራጭ ነው። ሳተላይቱን ደህንነትን ከመጠበቅ ጋር የሚያስተሳስሩት ባለሙያዎች አሉ። ዶ ር ሰለሞን በበኩላቸው በመርህ ደረጃ ህዋ የሚውለው ለሰላማዊ እንቅስቃሴ ነው ብለው፤ ለጦርነት፣ ለጦር መሳሪያ ማሳለጫነት እንደማይውል ያስረዳሉ። የ ኢንተርናሽናል የአውተር ስፔስ ተቋም አባል መሆን፤ ኢትዮጵያን ከመሰል ድርጊቶች እንደሚያግዳትም አክለዋል። ኢትዮጵያ እስካሁን መረጃውን እንዴት ታገኝ ነበር ኢትዮጵያ እነዚህን መረጃዎች ሳተላይት አምጥቀው ፎቶ ከሚያስነሱ ሀገሮች ትሸምት ነበር። ዶ ር ሰለሞን የሚያጣቅሱት ከአራት ዓመት በፊት በተሰራ ጥናት መሰረት ኢትዮጵያ በዓመት ሚሊየን ብር ታወጣለች። ጥናቱ ለደህንነት የሚወጣውንና ዩኒቨርስቲዎች የሚከፍሉትን አያካትትም። ወጪው ከዓመት ወደ ዓመት እንደሚጨምርም ያስረዳሉ። የከተሞች መስፋፋት፣ ኢንቨስትመንቶች እየጨመሩ ሲሄዱም በዛው መጠን የመረጃው አስፈላጊነት ይንራል። የሚወጣው ገንዘብም እንዲሁ። ሳተላይት ማምጠቅ እነዚህን ወጪዎች እንደሚቀንስ ይጠበቃል። አፍሪካ ውስጥ መሰል ሳተላይት ለሌላቸው ሀገሮች መረጃ መሸጥም ይቻላል። የኢትዮጵያ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተሩ ትልቅ ቢዝነስ ነው የሚሉትም ለዚሁ ነው። ሲያስፈልግ መረጃ እንሸጣለን። ከኛ የላቀ ቴክኖሎጂ ካላች ሀገሮች ጋር መረጃ መለዋወጥም ይቻላል፤ ኢትዮጵያ በህዋ ጥናት የት ደረሰች ዓለም በህዋ ጥናት ቴክኖሎጂ እየመጠቀ ሄዷል። ኢትዮጵያ ከተቀረው ዓለም አንጻር ጀማሪ ናት። አፍሪካ ውስጥ ናይጄሪያ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ አልጄሪያና ግብጽ ጥሩ ስም አላቸው። ኢትዮጵያ ህዋ ለልማት የሚል የምሥራቅ አፍሪካ ሀገሮች ትብብር ቢሮ አቋቁማ አበረታች እንቅስቃሴ ማድረጓ ተጠቃሽ ስኬት ነው። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በ ይደረስባቸዋል ብሎ ካስቀመጣው ግቦች አብዛኞቹ የህዋ ቴክኖሎጂን ያማከሉ መሆናቸው፤ ዘርፉን ችላ ማለት እንደማያዋጣ ያመላክታል። ዶ ር ሰለሞን የመሬት ምልከታ ሳተላይት ማምጠቅ ኢትዮጵያ በህዋ ሳይንስ ዘርፍ እንቅስቃሴ እያደረገች ስለመሆኑ ለዓለም መልእክት ማስተላለፊያ መንገድ እንደሚሆን ያምናሉ። ቴክኖሎጂው እጅግ አስፈላጊ ነው፤ ሳተላይቱን ማምጠቅ ኢትዮጵያን በህዋ ዘርፍ ጠንካራ ተወዳዳሪና እኩል ተጽእኖ ፈጣሪ ማድረግ የሚያስችል ነው ሳተላይቱ አንዴ ከመጠቀ በኋላ ከሶስት እስከ አራት ዓመት ያገለግላል። ከዛ በላይ ሊቆይም ይችላል። በዓለም አቀፍ ሕግ መሰረት፤ የመሬት ምልከታ ሳተላይቶች ህዋ ላይ እንዲቆዩ የሚፈቀደው ለስምንት አመት ነው። ኢትዮጵያ ከምታመጥቀው ሳተላይት፤ በየአራት ቀኑ የመላው ኢትዮጵያ መረጃ የዓለም ደግሞ በ ቀን ይገኛል። በህዋ ምርምር ዘርፍ ቅርብ ጊዜ እውን ይሆናሉ ተብለው ከሚጠበቁ ፕሮጀክቶች ውስጥ ላሊበላ ላይ ይገነባል የተባለው ዓለም አቀፍ ኦፕቲክ ቴሌስኮፕ አንዱ ነው። ይህንን ዜና ያጋሩ ስለማጋራት
የ ሚሊዮን ብር መኪና ሰርቆ የተሰወረው ግለሰብ ዱካው ጠፍቷል
ሜይ አጭር የምስል መግለጫ ሚሊየን ዶላር የሚያወጣው መኪና ጀርመን ውስጥ መኪና ለማስተዋወቅ በተዘጋጀ መሰናዶ ላይ ቀርቦ የነበረና ሚሊየን ዶላር ሚሊዮን ብር ገደማ የሚያወጣ መኪና ተሰርቆ እንደነበር ፖሊሶች ይፋ አድርገዋል። ቅንጡ ከሆኑ ተሽከርካሪዎች አንዱ የሆነው ፌራሪ መኪናን ዘርፏል የተባለው ግለሰብ፤ መሰናዶው ላይ ተገኝቶ መኪናውን ለሙከራ ለመንዳት ጥያቄ ያቀርባል። ግለሰቡ መኪናውን የመግዛት ፍላጎት ስላሳየ መኪናውን ነድቶ እንዲሞክረው ተፈቀደለት። ግለሰቡ ግን የመኪናውን መሪ ጨብጦ ብዙም ሳይቆይ መኪናውን በፍጥነት እየነዳ ከአካባቢው ተሰውሯል። ፓሊሶች እንዳሉት፤ መኪናውን ያያችሁ ሰዎች ጠቁሙን የሚል ማሳሳሰቢያ ማስነገራቸውን ተከትሎ መኪናው አንድ ጋራዥ ውስጥ ተደብቆ ተገኝቷል። ተጠርጣሪው ግለሰብ ግን እስካሁን በቁጥጥር ስር አልዋለም። መኪናውን ለሽያጭ ያቀረበው ድርጅት ኃላፊ እንዳሉት፤ ተጠርጣሪው መኪናውን ይዞ ከመሰወሩ በፊት ለድርጅቱ በተደጋጋሚ ይደውል፣ ኢሜልም ይልክ ነበር። አየርላንዳዊው የፎርሙላ ተወዳዳሪ ኤዲ አይርቪን በመኪናው እ አ አ ከ እስከ ተወዳድሮበታል። መኪናው ታሪካዊ እንደመሆኑ በሚሊዮኖች ማውጣቱም ብዙም አያስገርምም። መሰል መኪናዎች ከአንድ እስከ ሦስት ሚሊየን ዶላር ይሸጣሉ። የመኪናው አምራች ድርጅት የተሰረቀው ፌራሪ መኪና ብቻ ነበር የሠራው። ተያያዥ ርዕሶች
አጭር የምስል መግለጫ ድሬ ዳዋ ቀፊራ
በድሬ ዳዋ ከተማ ቀፊራ እና አዲስ ከተማ በሚባሉ አካባቢዎች ግጭት መኖሩን የከተማዋ ነዋሪዎች ለቢቢሲ ገለጹ። አንድ የዓይን እማኝ ለቢቢሲ ሲናገሩ፤ አምቡላንሶች ሰዎችን ወደ ሆሰፒታል ሲያመላልሱ ነበር። ጉዳት ደርሶባቸው ደም የሚፈሳቸው ሰዎችንም ተመልክቻለሁ ብለዋል። የግጭቱ መነሻ ደግሞ አዲስ ከተማ ጋራ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ አዲስ በተገነባው የተክለኃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ላይ ሰዎች ድንጋይ በመወርወራቸው ነው ብለውናል። የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች በተለያዩ ከተሞች ሰልፍ አካሄዱ የአዲስ ከተማ ሰፈር ልጆች ድንጋይ ወረወሩ የተባሉትን ልጆች ደበደቡ ሲባል ነው የሰማነው ብለዋል። ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ አንድ የፖሊስ አባል እንደነገሩ ደግሞ በተሳሳተ ወሬ በቤተ ክርስቲያኑ ላይ ጥቃት ለማድረስ የቀፊራ ሰፈር ሰዎች መጥተዋል የሚል ወሬ ከተናፈሰ በኋላ ነው ድንጋይ መወራወሩ የተጀመረው ይላሉ። የቀፊራ ልጆች ተክለኃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ላይ ጉዳት ሊያደርሱ እየመጡ ነው የሚል ወሬ ነው የተነዛው፤ ከዚያ የአከባቢው ነዋሪዎች ደግሞ እንዴት ይሆናል ብለው ተነሱ። የሰፈር ጸብ ነው እየተካረረ ያለው በማለት ይህ የከተማዋ የፖሊስ አባል ለቢቢሲ ተናግረዋል። በግጭቱ የደረሰው ጉዳት ምን ያክል እንደሆነ የተጠየቁት የፖሊስ አባሉ በትክክል ይህ ነው ማለት ባልችልም፤ ደንጋይ መወራወር ስለነበረ የተፈነካከቱ ብዙ ሰዎች አሉ። ይሁን እንጂ ለህይወት የሚያሰጋ ጉዳት ያጋጠመው የለም ብለዋል። የጸጥታ ኃይሎች በቦታው በመገኘት ሁኔታውን ለማረጋጋት ጥረት እያደረጉ መሆኑን የፖሊስ አባሉ ጨምረው ተናግረዋል። ለደህንነታቸው ሲባል ስማቸውን እንዳይጠቀስ የጠየቁን የዓይን እማኝ አሁንም ድረስ እሁድ ከሰዓት የተኩስ ድምጽ እንደሚሰማ እና የጸጥታ አካላት በአከባቢው በስፋት እንደሚገኙ ነግረውናል። ግጭት ወዳለበት ሰፈሮች ማለፍ አልቻልንም። ምክንያቱም ሰፈሩ በጠቅላለው በፌደራል ፖሊስ ተወሯል ሲሉም ተናግረዋል። በተከሰተው ግጭት በሰው ላይ የደረሰውን ጉዳት ለማወቅ ከሆስፒታልና ከፖሊስ መረጃ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም። ከሰሞኑ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች በተለያዩ ስፍራዎች በቤተክርስቲያኗ፣ በኃይማኖት አባቶች እና በምዕመኖቿ ላይ የሚደርሰው ጥቃት ይቁም በሚል ሰላማዊ ሰልፍ ሲያደርጉ ነበር። ዛሬም በአማራ ክልል መዲና በሆነችው ባህርዳር፣ የሰሜን ወሎ ዞን ዋና ከተማ ወልዲያ እና ምሥራቅ ጎጃም ደብረ ማርቆስ ከተሞች የተቃውሞ ሰልፎች ተካሂደው በሰላም ተጠናቀዋል። ይህንን ዜና ያጋሩ ስለማጋራት
ባለፈው አንድ ዓመት ከ ሰዎች በላይ መገደላቸውን ጠቅላይ አቃቤ ህግ አስታወቀ
መስከረም ይህንን ለማጋራት በ ዋትስአፕ ባለፈው ዓ ም በመላ የአገሪቱ አካባቢዎች በተከሰቱ ግጭቶች ሰዎች ህይወታቸውን እንዳጡ ጠቅላይ አቃቤ ህግ በፌስቡክ ገፁ አስታውቋል። በግጭቶቹ ተሳትፈዋል የተባሉ ተጠርጣሪዎች ላይ ክስ ተመስርቶ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው እየታየ መሆኑንና የሚሆኑ ተጠርጣሪዎች ደግሞ እንዳልተያዙ ፤ የ ተጠርጣሪዎች ክስም በምህረት መነሳቱን በኢፌዲሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የተደራጁ ድንበር ተሸጋሪ ወንጀሎች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ፍቃዱ ፀጋ ገለጹ፡፡
አብጃታን ሀይቅ ለማለት ይከብዳል የአብጃታ ሻላ ሀይቅ ብሔራዊ ፓርክ ኃላፊ
ሜይ ማጋሪያ ምረጥ አብጃታ ሀይቅ በቀጣይ አምስት ዓመታት ውስጥ ሊጠፋ እንደሚችል ይፋ የተደረገው በቅርቡ ነበር። ቀድሞ ስፋቱ ኪሎ ሜትር የነበረው ሀይቅ ዛሬ ኪሎ ሜትር ሆኗል። ጥልቀቱ ደግሞ ከ ሜትር ወደ ሜትር ማሽቆልቆሉ ተገልጿል። የአብጃታ ሻላ ሀይቅ ብሔራዊ ፓርክ ኃላፊ አቶ ባንኪ ሙደሞ እንደሚሉት፤ ሀይቁ ለመጥፋት የተቃረበው የተለያዩ ሰው ሰራሽ ተጽዕኖዎች ስር ስለወደቀ ነው። ሀይቁን ከሚቀላቀሉ ገባር ወንዞች አንዱ ከዝዋይ ሀይቅ የሚሄደው ቡልቡላ ወንዝ ነው። ይህም ወንዝ ሰው ሰራሽ ጫና ውስጥ መውደቁ ወንዙን ሙሉ በሙሉ አድርቆታል። የጣና ሐይቅን ሌሎችም አረሞች ያሰጉታል በዝዋይ አካባቢ የሚገኙ አንዳንድ ድርጅቶች የሚጠቀሙት የወንዙን ውሀ ነው። የሶዳ አሽ ድርጅት ከአቢጃታ ሀይቅ ውሀ በቱቦ እየሳበ ለፋብሪካው ሥራ ያውላል። ወደ ሚሊዮን ሜትር ኪዩብ በዓመት ይጠቀማሉ ይላሉ አቶ ባንኪ። ከዚህ በተጨማሪ በሀይቁ ዙሪያ የሚገኘው ደን ተመናምኗል። የአፈር መሸርሸር ሀይቁ በደለል እንዲሞላ አድርጓል። በደለሉ ምክንያት ሰዎችና የዱር እንስሳትም መንቀሳቀስ አልቻሉም። ፓርኩ ውስጥ ወደ ሺህ የሚጠጉ ሰዎች የሚኖሩ ሲሆን፤ የነዋሪዎቹ እንቅስቃሴ ለሀይቁ መድረቅ ምክንያት መሆኑን ኃላፊው ያስረዳሉ። የቀንድ ከብቶች መሰማራት ያስከተለው ገደብ የለሽ ግጦሽ እንዲሁም የደን ጭፍጨፋ የፓርኩንና የሀይቁንም ደህንነት አደጋ ውስጥ ጥለውታል። አቶ ባንኪ ሀይቁን ሀይቅ ለማለት ይከብዳል ሲሉ አቢጃታ የሚገኝበትን አሳሳቢ ሁኔታ ይናገራሉ። የሀይቁ መጠን ስለቀነሰ ሀይቁ ላይ የሚኖሩ አእዋፋት ቁጥር ተመናምኗል። ቡልቡላ ወንዝን የሚጠቀመው አካል ከድርጊቱ ተቆጥቦ ወንዙ በቀጥታ ወደ ሀይቁ መፍሰስ ካልጀመረ አብጃታ ተስፋ አለው ለማለት ይቸገራሉ። አብጃታ እንደማሳያ ተጠቀሰ እንጂ አብኞቹ የኢትዮጵያ ሀይቆች የመጥፋት አደጋ ተጋርጦባቸዋል። እንደ ሀሮማያ ሀይቅ የጠፉ የውሀ ሀብቶችም አሉ። የአፍሪካ የውሀ ሀብት ማማ እየተባለች የምትሞካሸው ኢትዮጵያ ሀይቆቿን መጠበቅ እንደተሳናት የዘርፉ ባለሙያዎች በተደጋጋሚ ይናገራሉ። ይህ ሀይቅ ሊጠፋ ነው፤ ያ ሀይቅ ሊከስም ይህን ያህል ዓመት ቀርቶታል የሚሉ ዜናዎች መስማትም እየተለመደ መጥቷል። ሀይቅ ለማለት የማያስደፍሩ ሀይቆች አብጃታ ሻላ ሀይቅ ብሔራዊ ፓርክ ከተለያዩ አህጉሮች ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡ ስደተኛ አእዋፋት መገኛ ነበር። ቱሪስቶች ከሚያዘወትሯቸው ፓርኮች አንዱ ሲሆን፤ እንደ ፍላሚንጎ ያለ ወፍን ጨምሮ የተለያዩ እንስሳት መኖሪያ ነው። የአቢጃታ መጥፋት ብዝሀ ሕይወት ላይ ከሚያሳድረው ተጽእኖ ባሻገር የቱሪስት ፍሰት ሲቀንስ ኢኮኖሚያዊ ተጽዕኖም ይኖረዋል። የተለያዩ የኢትዮጵያ ሀይቆች ህልውና ለምን አስጊ ሆነ ስንል የብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት የደንና ግጦሽ መሬት፤ እጽዋት ብዝሀ ህይወት ዳይሬክተር ዶ ር ዴቢሳ ለሜሳን ጠይቀን ነበር። እሳቸው እንደሚሉት፤ እንደ አቢጃታ፣ ጨለለቃ፣ ዝዋይ ያሉ ሀይቆች አሳሳቢ ደረጃ ላይ ከደረሱባቸው ምክንያቶች አንዱ በሀይቆቹ ዙርያ ግብርና መካሄዱ ነው። የእርሻ ሥራ እንደናይትሮጂን፣ ፎስፈረስ ያሉ ንጥረ ነገሮችን ከመውሰዱ በመጨማሪ ደለልም ይፈጥራል። ሀይቅን ጨምሮ ሌሎችም የውሀ አካላት ሲጠፉ አሳ፣ የተለያዩ እጽዋትና አዕዋፍትም ይመናመናሉ። ውሀማ አካላትን ከግምት ያላስገቡ ኢንቨስትመንቶች አንድ የችግሩ መንስኤ ናቸው። ስምጥ ሸለቆ ውስጥ ያሉትን እንደ አቢጃታ ያሉት ሀይቆች በዚህ ተጎጂ ናቸው። አቢጃታ ሻላ አካባቢ የሶዳ አሽና የአበባ ፋብሪካዎች አሉ ይላሉ። የፋብሪካዎች ተረፈ ምርት በአግባቡ አለመወገዱ ወደ ውሀ አካል ከሚለቀቀው ኬሚካል ጋር ተደማምሮ የውሀ አካላት ላይ ተጽዕኖ እያሳደረ ይገኛል። ዶ ር ዴቢሳ እንደ ማሳያ በሚጠቅሱት ጨለለቃ ሀይቅ አካባቢ የጀልባ መዝናኛ ነበር። አሁን ግን ግብርና በመስፋፋቱ የውሀ ሀብቱ እየጠፋ ሰለሆነ ወደ አካባቢው ለመዝናናት መሄድ አይታሰብም። ተፈጥሮ ላይ ሊደርስ ስለሚችለው ተጽዕኖ ተገቢው ጥናት ሳይደረግ የሚሠሩ መንገዶችና ድልድዮች እንስሳትና እጽዋት ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ያሳድራሉ ይላሉ ዳይሬክተሩ። ምን ተጽዕኖ አሳደረ የውሀ አካላት መጥፋት ተፈጥሯዊ፣ ማኅበራዊ፣ ባህላዊና ኢኮኖሚያዊ ተጽዕኖ ያሳድራል። ሀይቅና ሌሎችም የውሀ አካላት መጥፋታቸው ለአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት ከሆኑት መካከል አንዱ ነው። አብዛኛው የመሬት ክፍል ውሀ እንደመሆኑ፤ የውሀ አካል ሲጠፋ ለእንስሳትና እጽዋት ብቻ ሳይሆን ለሰው ልጆች ህልውናም ስጋት ይሆናል። አሁን እያገገመ እንደሆነ የሚነገርለት ሀሮማያ በጠፋበት ወቅት ያነጋገርናቸው የሀሮማያ አካባቢ ነዋሪዎች የሀይቁ መጥፋት በእለት ከእለት ህይወታቸው ላይ ያሳደረውን ተጽዕኖ ገልጸውልን ነበር። በድሪ የሱፍ የተባሉ የአካባቢው ነዋሪ አሳ ማስገር እንዲሁም አትክልትና ፍራፍሬ ማምረት መቸገራቸውን ነግረውን ነበር። በውሀ እጥረት ምክንያት የቀንድ ከብቶቻቸውን እንዳጡ፤ አካባቢውን ለመጎብኘት ከጅቡቲ እና ሌሎችም አካባቢዎች ይሄዱ የነበሩ ቱሪስቶች ፍሰት መቋረጡንም ተናግረዋል። በአካባቢው የሚመረተው ሀረር ቢራና የሀሮማያ ዩኒቨርስቲ ሀሮማያ ሀይቅን መጠቀማቸው ሀይቁ ላይ ተጽዕኖ ማሳደሩን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናገረውም ነበር። እንክብካቤና ጥበቃ ካልተደረገለት ሊጠፋ ተቃርቧል የተባለው አቢጃታ ሀይቅም ተመሳሳይ ስጋት አለበት። ይህም ተፈጥሮውን ተከት የሚመጣውን ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ማጣት ነው። ዶ ር ዴቢሳ የውሀ አካላት የማኅበረሰቡ ባህላዊ ሥነ ሥርዓቶች የሚከናወናወኑባቸው መሆናቸውን የሚናገሩት እንደ እሬቻና ጨንበላላ ያሉ ሥርዓቶችን በማጣቀስ ነው። የሀይቆች ጉዳይ የማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች መነጋገሪያም ነው። ምን መደረግ አለበት ዶ ር ዴቢሳ እንደሚሉት፤ ሀይቆችን ጨምሮ የውሀ ሀብቶች የሚጠበቁበት ግልጽ መርህ ያስፈልጋል። አሁን እንደ ፖሊሲ ያለው እንደመስኖና ኢነርጂ፣ ግብርና፣ ደን ልማት ባሉ ዘርፎች ነው። ራሱን የቻለ የውሀ ክፍልን የሚያስጠቅ ሕግ ያስፈልጋል ይላሉ። የውሀ ሀብት ጥበቃ በተለያዩ ዘርፎች ተበታትኖ የሚሠራ ሳይሆን በአንድ ተቋምና በወጥ መርህ የሚመራ መሆን እንዳለበት ያስረጋጣሉ። አሁን ላይ የውሀ ሀብት ላይ ያተኮረ ፖሊሲ ተረቆ እስከሚጸድቅ እየተጠበቀ ይገኛል። በአንድ አካባቢ የመሰረተ ልማት ዝርጋታ ሲካሄድ ከጀርባው ባሉ ተቋማት መካካል መናበብ ሊኖር እንደሚገባ ይናገራሉ። ኃይል ሲመነጭ ውሀ የሚጠፋ ከሆነ፤ መንገድ ሲሠራ ዛፍ የሚቆረጥ ከሆነ ከጥቅሙ ጉዳቱ እያመዘነ ይሄዳልና። እናት አልባዎቹ መንደሮች ዶ ር ዴቤሳ ሀይቆች ከተጋረጠባቸው አደጋ መውጣት የሚችሉት ሀገር አቀፍ ፖሊሲ ሲጸድቅና ተቋሞች ሲናበቡ ነው ሲሉ፤ አቶ ባንኪ በበኩላቸው ማኅበረሰቡ የተፈጥሮ ሀብቱን መንከባከብ እንዳለበት ይናገራሉ። እሳቸው የሚያስተዳድሩት የአቢጃታ ሻላ ፓርክ አቅራቢያ ያለው ማኅበረሰብ ደን እንዳይጨፈጭፍና ከብቶች እንዳያሰማራ እንዲሁም ወጣቶች አካባቢውን እንዲያለሙ የጀመሯቸው እንቅስቃሴዎች ፍሬያማ ካልሆኑም አቢጃታን ዳግም አናየው ይሆናል። ተያያዥ ርዕሶች
የፌስቡክ በሐሰተኛ መልዕክቶችና የኃይሌ ገብረሥላሴ ስጋትየፌስቡክ በሐሰተኛ መልዕክቶችና የኃይሌ ገብረሥላሴ ስጋት
የፌስቡክ በሐሰተኛ መልዕክቶችና የኃይሌ ገብረሥላሴ ስጋት
በአሜሪካ በእርሻ መሣሪያ የተያዘው አርሶ አደር እግሩን ቆረጠ
ሜይ አጭር የምስል መግለጫ መሣሪያው አንደ መብሻ ድሪል የሚሽከረከር ነው። በአሜሪካ ኔብራስካ ግዛት በእርሻ ሥራ ላይ ሳለ ሰብል መሰብሰቢያ መሣሪያ ውስጥ እግሩ የተቀረቀረበት አርሶ አደር በስለት የራሱን እግር ቆርጦታል። የ ዓመቱ አርሶ አደር ኩርት ካሴር ምርት ለመሰብሰብ የሚረዳውን ማሽን ከአንድ ቦታ ወደ አንድ ቦታ እያዘዋወረ ነበር፤ ማሽኑ ልክ እንደ መብሻ ድሪል ዓይነት ሲሆን የሚሽከረከርም ነው። ግለሰቡ የግሉ በሆነው ሔክታር መሬት ላይ ብቻውን እየሰራ ሳለ ነበር አደጋው ያጋጠመው። በአቅራቢያው ሰዎች ባለመኖራቸው የሚረዳው አላገኘም። ስልክ በመደወል የሰዎችን እርዳታ ለመጠየቅ ቢያስብም ተንቀሳቃሽ ስልኩን አጠገቡ ሊያገኘው አልቻለም። ማሽኑ እግሩን እየከረከረ የበለጠ ወደ ውስጥ እየዘለቀና ከፍ እያለ መጣ። በዚህ ጊዜ ደፋሩ ገበሬ የያዘውን ስለት ሳብ አድርጎ ከማሽኑ የተረፈውንና ከጉልበቱ በታች ያለው የራሱ እግር ላይ እርምጃ ወሰደ። መጥፎ አጋጣሚውን ሲያስታውስም ራሴን ለማላቀቅ ጣርኩ፤ ነገር ግን አጥንቴ ተጣብቆ ቀረ ሲል ለኦማሃ ወርልድ ሄራልድ ተናግሯል። ምንም ምርጫ አልነበረኝም የሚለው አርሶ አደሩ ከታችኛው የእግሩ ክፍል ሴንቲ ሜትር ኢንች የሚሆነውን የራሱን እግር ቆርጦ ጥሎታል። ከዚህ ሁኔታ ከተላቀቀ በኋላ ነበር ስልኩን ወደ አስቀመጠበትና ሜትር ወደ ሚርቀው ቦታ እየተንፏቀቀ ሄዶ ለልጁ የደወለለት። ከዚያም በሊንኮልን ከተማ በሚገኝ የህክምና ተቋም እርዳታ ሲደረግለት ቆይቷል፤ ከጉዳቱ ለማገገምም ሳምንታትን በሆስፒታል አሳልፏል። ግለሰቡ ለኤቢሲ ኒውስ በማሽኑ ላይ የተገጠመውን መከላከያ አውልቆት እንደነበር ተናግሯል። ያንን ነገር ሳላስተካክለው በመቅረቴ በራሴ በጣም ነው የተበሳጨሁት ብሏል በቁጭት። ተያያዥ ርዕሶች
በኤርትራ የማህበራዊ ድረ ገጾች አገልግሎት ተቋረጠ
ሜይ በኤርትራ ውስጥ የማህበራዊ ድረ ገጽ የግንኙነት አገልግሎት መቋረጡን በሃገሪቱ የሚገኙ ምንጮች ለቢቢሲ አመለከቱ። ከጥቂት ቀናት ወዲህ እንደ ፌስቡክና ሜሴንጀር ያሉ ማህበራዊ መድረኮችን መጠቀም እንዳልተቻለ የሃገሪቱ ዜጎች ተናግረዋል። ያገኘነው መረጃ እንሚያመለክተው ነዋሪዎች ከዚህ ቀደም በፌስቡክና በሜሴንጀር መልዕክት መላክና መቀበል ይችሉ ነበር። እነዚህን የተዘጉ የማህበራዊ ግንኙነት መድረኮች ለመጠቀምም ሰዎች ቪፒኤን የተባሉትን እገዳውን ለማለፍ የሚያስችሉ መተግበሪያዎች እንደሚጠቀሙም ምንጮች ለቢቢሲ ተናግረዋል። በኤርትራ በማህበራዊ የትስስር ድረ ገጾች ላይ ተጥሏል ስለተባለው እገዳ ምንነትና ምክንያቱን በተመለከተ እስካሁን በይፋ የተገለጸ ነገር የለም። አንዳንዶች እንደሚሉት ግን በአሁኑ ወቅት ኤርትራ የነጻነት በዓሏን ለማክበር እየተዘጋጀች በመሆኑ ከጸጥታ ጥበቃ ጋር የተያያዘ እርምጃ ሊሆን እንደሚችል ጠቁመው ሌሎች ደግሞ በውጪ ሃገራት ያሉ የመንግሥት ተቃዋሚዎች በማህበራዊ ድረ ገጾች በኩል የሚያስተላልፉትን መልዕክት ለመከላከል የሚደረግ ጥረት እንደሆነ ይናገራሉ። ቢቢሲ ከኤርትራ መንግሥት በኩል በጉዳዩ ላይ ምላሽ ለማግኘት ያደረገው ጥረት አልተሳካም። የዓለም አቀፍ የኢንተርኔት ስርጭት መረጃ እንደሚያመለክተው ባለፈው ዓመት ኤርትራ ወስጥ ሺህ የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ሲኖሩ ይህም ከአጠቃላይ የሃገሪቱ ህዝብ ብዛት በመቶውን ብቻ የሚሸፍን ነው። ኤርትራ በዓለማችን ውስጥ ዝቅተኛ የኢንተርኔት ተደራሽነት ካለባቸው ሃገራት መካከል ትመደባለች። ተያያዥ ርዕሶች
ናይጄሪያ፡ በረመዳን ምግብ የበሉ ሰዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ
ሜይ ማጋሪያ ምረጥ በናይጄሪያዋ ካኖ ግዛት በረመዳን ጾም ወቅት በአደባባይ ምግብ የበሉ ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የግዛቲቱ እስላማዊ ሸሪያ ፖሊስ አስታውቀ። ሂስባህ የሚል ስያሜ ያላቸው እነዚህ የሸሪያ ፖሊሶች በግዛቲቱ በተለያዩ አካባቢዎች ባለፉት ቀናት ቁጥጥር ሲያደርጉ ነው ግለሰቦቹን የያዙት። በፈረንጆቹ የሸሪያ ህግ እንደገና ተግባራዊ ከተደረገባቸው በርካታ የናይጄሪያ ግዛቶች መካከል አንዷ በሆነችው ካኖ ግዛት የሚኖሩ የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች ጸሃይ ወጥታ እስትክጠልቅ ድረስ ምግብ በአፋቸው እንዳይዞር ህጉ ያዛል። የእስልምና ሃይማኖት ተከታይ ያልሆኑ ሰዎች በቤታቸው እንደፈለጉት መመገብ የሚችሉ ሲሆን የእስልምና ተከታዮች ግን በጾም ወቅት በአደባባይ መመገብ አይችሉም። በግዛቲቱ የሸሪያ ህጉም ከመንግሥታዊ ህጉ ጋር ጎን ለጎን በመሆን ይሰራል። በካኖ ግዛት የሂስባህ ቃል አቀባይ የሆኑት አዳሙ ያህያ ለቢቢሲ እንደተናገሩት በአደባባይ በመመገባቸው በቁጥጥር ስር የዋሉት ሁሉም ሙስሊሞች ሲሆኑ የሸሪያ ህጉ የእስልምና ሃይማኖት ተከታይ ያልሆኑት ላይ ተግባራዊ አይሆንም። በቁጥጥር ስር ከዋሉት መካከል አንዳንዶቹ ምግብ የበሉት የረመዳን ጨረቃን እራሳቸው ባለማየታቸው እንደሆነ ሲገልጹ፤ ሌሎቹ ደግሞ የጤና እክልን እንደ ምክንያትነት ቢያቀርቡም ባለስልጣናቱ ግን ተቀባይነት የሌለውና ምክንያት ነው ብለዋል። በቁጥጥር ስር የዋሉት ሰማንያዎቹ ግለሰቦች ተግባሩን ሲፈጽሙ የመጀመሪያቸው በመሆኑ በከባድ ማስጠንቀቂያ መለቀቃቸውን ቃል አቀባዩ አክለዋል። ከዚህ በኋላ በረመዳን ወቅት ከማፍጠሪያ ሰዓት ውጪ ምግብ ሲበሉ ቢገኙም ወደ ፍርቤት ተወስደው ለመዳኘት ቃል ገብተዋል። የሂስባህ አባላቱም በረመዳን የጾም ቀናት ከተማዋን በማሰስ ተመሳሳይ ተግባር የሚፈጽሙ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋላቸውን እንደሚቀጥሉበትም ተገልጿል። ተያያዥ ርዕሶች
የስኳር ፋብሪካዎች፡ ለግል ባለሃብቶች የመስጠት ፋይዳና ፈተናዎቹ
ሜይ ማጋሪያ ምረጥ የኢትዮጵያ መንግሥት የስኳር ፋብሪካዎችን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ለመሸጥ ማስታወቂያ ካወጣበት ቀን ጀምሮ ብዙ የሀገር ውስጥና የውጪ ድርጅቶች እየተመዘገቡና ፍላጎታቸውን እየገለጹ እንደሆነ የኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽን ሥራ አስኪያጅ አቶ ወዩ ሮባ ለቢቢሲ ተናግረዋል። በአውሮፓውያኑ በወጣ መረጃ መሠረት በሃገሪቱ ያሉ ሁሉም ፋብሪካዎች ሚሊዮን ኩንታል ስኳር የሚያመርቱ ሲሆን ሃገሪቱ የሚያስፈልጋት ግን ሚሊየን ኩንታል ነው። መንግስትም ይህንን ክፍተት ለመሙላት ሚሊየን ኩንታል ስኳር ከውጪ በማስገባት ሲያከፋፍል ቆይቷል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ የሀገር ውስጥ ምርቱን ወደ ሚሊዮን ኩንታል ለማሳደግ በማሰብ መንግሥት ተጨማሪ ስኳር ፋብሪካዎችን መገንባት ጀምሮ ነበር። የግንባታ ሥራውን ያከናውን የነበረው ሜቴክ ግንባታውን በታሰበለት ጊዜ ማጠናቀቅ ባለመቻሉ መንግሥት ለተጨማሪ ወጪ ተዳርጓል። ፋብሪካዎቹን መሸጥ ለምን አስፈለገ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ ወደ ሥልጣን ከመጡ ጊዜ አንስቶ ብዙ ለውጦችን ያደረጉ ሲሆን ከእነዚህም መካከል የተለያዩ የመንግሥት ድርጅቶችን ለግል ባለሃብቶች ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሸጥ ሃሳብ ደግሞ አንዱ ነው። ሃገሪቱ ትልቅ የውጭ ምንዛሪ እጥረት ውስጥ ስለነበረችና የተከማቸ የረጅም ጊዜ ብድር መክፈል አለመቻሏ ለዚህ ውሳኔያቸው ገፊ ምክንያት እንደሆነ የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎች ይናገራሉ። የምጣኔ ሃብት ባለሙያ የሆኑትና በቤልጂየም የዶክትሬት የምረቃ ጥናት ወረቀታቸውን በዚሁ ጉዳይ ላይ እየሰሩ የሚገኙት አቶ ተሾመ ተፈራ እንደሚሉት መንግሥት በሁለት ምክንያቶች ፋብሪካዎቹን ለመሸጥ ተገዷል። የመጀመሪያው ምክንያት አብዛኛዎቹ ፋብሪካዎች በብድር ስለተገነቡ ግንባታቸው ገና ሳይጠናቀቅ የመክፈያ ጊዜያቸው መድረሱና መንግሥት በቂ የሆነ የውጪ ምንዛሪ ስለሌለው ለተጨማሪ ወጪ ተዳርጓል። ይህ ደግሞ ፋብሪካዎቹን ለመሸጥ አስገድዶታል ብለው ያምናሉ አቶ ተሾመ። ባለሙያው በሁለተኛነት ያስቀመጡት ምክንያት መንግሥት በአጭር ጊዜ ውስጥ ፋብሪካዎቹ ተሸጠው የተጣራ የውጭ ምንዛሪ ማግኘት መፈለጉን ነው። አቶ ተሾመ አክለውም በረጅም ጊዜ ውስጥ ፋብሪካዎቹን ወደ ግል ማዘዋወሩ ለሃገሪቱ ኢኮኖሚ እድገት አሉታዊ ተጽዕኖ ይኖረዋል። ከዚህ በተጨማሪ ፋብሪካዎቹ በአጭር ጊዜ ማምረት ጀምረው ከሃገር ውስጥ ፍላጎት ያለፈ ጥቅም ሊኖራቸው ስለማይችል ከሽያጩ የተጣራ የውጭ ምንዛሪ ማግኘት ይችላል። በረጅም ጊዜ ደግሞ ወደ ውጪ ከሚላከው ስኳር የውጪ ምንዛሪ ማግኘት እንደሚቻል ይናገራሉ። ዝብርቅርቅ ያለው የስኳር ንግድ ኬንያዊው የምጣኔ ሃብት ባለሙያ ዶክተር ቶኒ ዋቲማ በበኩላቸው ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ቀንድ ሃገራት ፈጣን የሚባል ኢኮኖሚያዊ እድገት እያስመዘገበች ነው በማለት የስኳር ፋብሪካዎችንም ሆነ ሌሎች የመንግሥት ድርጅቶችን ወደግል ከማዘዋወር ጋር በተያያዘ የኬንያን ተሞክሮ ሲያብራሩ፤ በዘርፉ የሚፈጸሙ የሙስናና የበጀት ምዝበራ ለመቆጣጠርና ለመቀነስ ከፍተኛ ሚና አለው ብለዋል። በዘርፉ የተሰማሩ የግል ባለሃብቶች በማንኛውም መልኩ ጊዜያቸውንና ገንዘባቸውን ከመቆጠብ ባለፈ ተገቢውን አገልግሎት ለተጠቃሚዎች ማድረስ ይችላሉ። መንግሥት እነዚህን ፋብሪካዎች ወደ ግል ባለሃብቶች ሲያዘዋውር ለግንባታና ሥራ ማስኬጃ በብድርም ሆነ ከካዝናው የሚመድበውን ገንዘብ ሌሎች ፕሮጀክቶች ላይ ለማዋል እንደሚያግዘው ቶኒ ዋቲማ ይናገራሉ። የኬንያ ተሞክሮም በዚሁ የተቃኘ እንደሆነ አክለዋል። የኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽን ከሽያጩ በኋላ የመንግሥት ሚና ምንድነው የኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽን ሥራ አስኪያጅ አቶ ወዩ ሮባ እንደሚሉት ፋብሪካዎቹ ወደ ግል ባለሃብቶች ሲዘዋወሩ እንዴት መተዳደር አለባቸው የሚለውን በተመለከተ አዲስ መመሪያ እየተዘጋጀ ነው። ሥርጭትና ሌሎችን በተመለከ ደግሞ ወደፊት ውሳኔ የሚሰጥባቸው እንደሆነና ዋጋን በተለመከተ ግን መንግሥት ሳይገባበት በነጻ ገበያው መርህ መሠረት የሚወሰን ይሆናል ብለዋል። ኢትዮጵያ ከውጭ ምንዛሬ እጥረት አዙሪት እንዴት ትውጣ አሁን ባለው አሰራር፣ መንግሥት የስኳር ሥርጭትን በሚቆጣጠርበት ጊዜ፣ እንኳን ነጋዴዎች ስኳሩን በመደበቅ ዋጋ ጨምረው ይሸጣሉ። መንግሥት በስኳር ዙሪያ ያለውን ተሳትፎ እጅጉን ሲቀንስ ደግሞ ተመሳሳይ ተግባሮች እንዳይበራከቱ ስጋት አለ። የምጣኔ ሃብት ባለሙያው አቶ ተረፈ ግን የግል ባለሃብቶች ዋጋውን መቆጣጠራቸውን እንደ ጥሩ አጋጣሚ ነው የሚያዩት። ምክንያቱም ይላሉ፤ ባለሃብቶች ቁጥራቸው በርከት ስለሚልና ከፍተኛ የገበያ ውድድር ስላለባቸው የስኳሩን ዋጋ ዝቅ ማድረጋቸው አይቀርም። የኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽን ስራ አስኪያጅ አቶ ወዩ ሮባም በዚሁ ሀሳብ ይስማማሉ። የኢትዮጵያ መንግሥት ፋብሪካዎቹን ወደግል ባለሃብቶች ከማዘዋወሩ በፊት የአሰራር ህግና ደንቦቹ ላይ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንዳለበት የኬንያው የምጣኔ ሃብት ባለሙያ ቶኒ ዋቲማ ይናገራሉ። ይህን ማድረገም የተጠቃሚዎችን መብት ለማስከበር፣ የሸንኮራ አቅራቢ አርሶአደሮችን ጥቅም ለማስጠበቅና የገበያ ሁኔታውን ለመከታተል ይጠቅመዋል ብለዋል። በተጨማሪም ባለሃብቶቹ ትርፍ ላይ ብቻ ትኩረት አድርገው ሊሰሩ ስለሚችሉ የምርት ጥራትን የሚቆጣጠር ጠንካራ ተቋም መቋቋም እንዳለበት ሃሳብ ሰንዝረዋል። የኬንያ አርሶአደሮች የተወሳሰበውን የዓለም ገበያ ሁኔታ መከታተልና መረዳት ስለማይችሉ ጠንካራ የአርሶአደሮች ማህበር ተቋቁሞላቸዋል፤ መብታቸውን ማስከበር የሚችልና ከዘመኑ አሰራር ጋር መራመድ የሚችሉ የህግ ባለሙያዎችም በማህበሩ ውስጥ አሉ። ሲሉ ያብራራሉ። እሳቸው እንደሚሉት ከምርት በኋላም የማከፋፈል ሥራውን የሚሰሩት ሌሎች ማህበራት ናቸው። ይህ ደግሞ አምራቾች ገበያውን ሙሉ በሙሉ እንዳይቆጣጠሩት ለማድረግ ይረዳል። ይህን የኬንያውያንን ተሞክሮ የኢትዮጵያ መንግሥት ከግምት ውስጥ ሊያስገባው እንደሚገባም ቶኒ ዋቲማ ይመክራሉ። ከዚህ በፊት በነበሩት ተሞክሮዎች የተለያዩ የጨርቃጨርቅ ፋብሪካዎች ለግል ባለሃብቶች ቢሰጡም ግልጽነት ባለመኖሩና ተገቢው የጥንቃቄ እርምጃዎች ባለመወሰዳቸው ስኬታማ እንዳልነበሩ የምጣኔ ሃብት ባለሙያው አቶ ተሾመ ያስታውሳሉ። ከውጪ የሚመጡ ድርጅቶች ፋብሪካው ከሚያወጣው በላይ ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ ብድር ይወስዱና ለአጭር ጊዜ ሰርተው ብድሩን ሳይመልሱ ፋብሪካዎቹን ትተው ካገር ይሸሹ ነበር። ስለዚህ መንግሥት እነዚህን ነገሮች ሁሉ ከግምት ውስጥ ማስገባት የማይችል ከሆነ አሁንም ለከፍተኛ ኪሳራና ስኳር እጥረት ሊዳረግ እንደሚችል ባለሙያው ያሳስባሉ። ተያያዥ ርዕሶች
ኢትዮጵያን ወደተሻለ ስፍራ ሊወስዳት የሚችል ሌላ መሪ የለም የሶማሌ ክልል ም ፕሬዝዳንት
ሜይ ስለ ማጋራት ተጨማሪ ያጋሩ ማጋሪያ ምረጥ ቢቢሲ በየወሩ የሚያዘገጀውና ቢቢሲ ወርልድ ኩዌስችንስ የተባለው አለማቀፍ የክርክር መድረክ ባሳለፍነው ሳምንት በአዲስ አበባ ሂልተን ሆቴል ተካሂዶ ነበር። ከ በላይ ታዳሚያን በተገኙበት ዝግጅት ፖለቲከኞች፣ ተንታኞችና የማህበረሰብ አቀንቃኞች ተሳታፊዎች ነበሩ። የክርክር መድረኩ ዋነኛ ማጠንጠኛ ሃሳብ ደግሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድና ባለፉት ወራት ይዘውት የመጡት ለውጥና እያጋጠሙ ያሉ ፈተናዎች ላይ ነበር። ከ ሚሊዮን በላይ ህዝብ ያላት ኢትዮጵያ እስካሁንም ለምን መረጋጋት ተሳናት ሲል የመድረኩ አዘጋጅ የነበረው ጆናታን ዲሞቢልቢ ጠይቋል። በመድረኩ ከተገኙት መካከል ደግሞ የሶማሌ ክልል ም ፕሬዝዳንት አቶ ሙስጠፋ ኦማር፣ ፕሮፌሰር መራራ ጉዲና፣ የአዲስ ስታንዳርድ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ጸዳለ ለማ እንዲሁም እስክንድር ነጋ ይጠቀሳሉ። ተስፋዬ ገብረአብ ስለ ዶ ር ነጋሶ ጊዳዳ ምን ይላል ከተሳታፊዎች የመጣው የመጀመሪያ ጥያቄ ደግሞ እውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ኢትዮጵያን የበለጸገች፣ ሰላማዊና የተረጋጋች ሃገር ማድረግ ይችላሉ ወይ ነበር። ለዚህ ጥያቄ ምላሽ በመስጠት የጀመሩት የሶማሌ ክልል ም ፕሬዝዳንት አቶ ሙስጠፋ ኦማር ነበሩ። በአሁኑ ሰአት ኢትዮጵያ ያለችበትን ሁኔታ ተረድቶ ወደተሻለ ስፍራ ሊወስዳት የሚችል መሪ ከአሁኑ ጠቅላይ ሚኒስትራችን የተሻለ ሰው ሃገሪቱ ታገኛለች ብዬ አላምንም ብለዋል። በጥላቻና መጠራጠር ተሸብቦ የነበረን ህዝብ ወደ ፍቅርና አንድነት ማምጣት እጅግ ከባድ ፈተና ሊሆን ይችላል፤ ነገር ግን የማይቻል አይመስለኝም በማለት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል። ፕሮፌሰር መራራ ጉዲና በበኩላቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ሃገሪቱን ወደተሻለ ከፍታ ለመውሰድ ከባዱ ፈተና የሚሆንባቸው የኢትዮጵያ ህዝብ ሳይሆን ራሳቸው የሚመሩት ኢህአዴግ ነው ብለዋል። ብዙዎቹ የፓርቲው አባላት ለለውጥ የተዘጋጁ አይደሉም፤ ጠቅላዩ ከሚያመጧቸው የለውጥ ሃሳቦች ጋርም አብረው መጓዝ አይችሉም። አሁንም ቢሆን ፈጣን ለውጥ ማምጣት የማይችሉ ከሆነ ህዝቡ መጠየቅ ይጀምራል። ጋዜጠኛና የሰብአዊ መብት ተሟጋች እስክንድር ነጋ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አሁን እየተከተሉት ባለው አካሄድ ሃገሪቱን ወደ ብልጽግና ይመሯታል ብዬ አላስብም በማለት ተከራክሯል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለውጥ ለማምጣት የመረጡት መንገድ የተሳሳተና ወዳልተፈለገ አቅጣጫ የሚመራ ነው ብሏል። ጋዜጠኛ ጸዳለ ለማ ደግሞ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ፈተናዎች ከሁለት አቅጣጫዎች እንደሚመነጩ ታስረዳለች። ኢትዮጵያ ውስጥ ለውጥና ብልጽግና ሊመጣ የሚችለው ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ የሚመሩት ፓርቲ ራሱን ፈትሾ ለለውጥ ሲዘጋጅና በብሄር ፖለቲካ ሲገዳደል የነበረው ህዝብ ይቅር ለመባባል ሲዘጋጅ ነው ብላለች። ሌላኛው ተሳታፊዎቹን ያከራከረ ሃሳብ በብሄር ላይ የተመሰረተ ፌደራሊዝም ለኢትዮጵያ ያስፈልጋታል ወይስ አያስፈልጋትም የሚለው ጥያቄ ነበር። በዘር የተከፋፈለውና መስማማት የማይችለው የተማረው ሃይል ራሱን ለመቀየርና ልዩነቶቹን አጥብቦ አብሮ ለመስራት እስካልተዘጋጀ ድረስ ምንም አይነት ለውጥ ሊመጣ አይችልም የሚሉት ፕሮፌሰር መራራ ጉዲና በደንብ ከታሰበበት ፌደራሊዝሙ በራሱ ለውጥ ሊያመጣ ይችላል ብለው ያምናሉ። እስክንድር ነጋ በበኩሉ ከሶስት ሚሊየን በላይ ሰዎችን ከመኖሪያ ቀያቸው እንዲፈናቀሉ ምክንያት የሆነው ፌደራሊዝሙ ነው፤ አሁንም ቢሆን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚህ ዙሪያ አልተሳካላቸውም ብሎ የተከራከረ ሲሆን የሶማሌ ክልል ም ፕሬዝዳንት አቶ ሙስጠፋ ኦማር ግን ተቃራኒ ሃሳብ አላቸው። ከዚህ በፊትም ቢሆን በሚሊየኖች የሚቆጠሩ ሰዎች ይፈናቀሉ ነበር። ነገር ግን ይህን ያክል ሰዎች ተፈናቅለዋል ብሎ እንኳን ማውራት አይቻልም ነበር። አሁን ግን ሌላው ቢቀር በነጻነት ስለተፈናቃዮቹ ማውራት ጀምረናል ብለዋል። አክለውም በተለያዩ አካባቢዎች የሚነሳው ግጭት ሙሉ በሙሉ ሃገሪቱ አልተረጋጋችም ለማለት በቂ አይደለም። ህዝቡ የተቃውሞ ሰልፍ ለመውጣት ፍራቻ አለመሳየቱ በራሱ የሚያሳየው ነገር አለ። ሁሌም ቢሆን ለውጥ ሊመጣ ሲል መንገራገጭ ያለ ነው። መረሳት የሌለበት ሌላኛው ነገር በሃገር ውስጥ የሚፈናቀሉት እንዳሉ ሆነው ለውጡን ለመደገፍና የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ለማድረግ ወደሃገር ቤት የተመለሱትስ በማለት አቶ ሙሰጠፋ ሃሳባቸውን አጠናክረዋል። የእርሶ መሳሪያ ሚዲያ ፕሌይ ባክን ማጫወት ኣልተቻለም። የለውጡ ጎዳና እስከየት የጥላቻ ንግግርና የሃሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከል የተዘጋጀው ረቂቅ አዋጅም በመድረኩ ብዙ ሃሳቦችን ያንሸራሸረ ጉዳይ ነበር። ረቂቅ አዋጁ የጥላቻ ንግግር ትርጉም ብሎ ሲያስቀምጥ ሆን ብሎ የሌላ ግለሰብን፣ የተወሰነ ቡድንን ወይም ማህበረሰብን ብሔርን፣ ሃይማኖትን፣ ቀለምን፣ ፆታን አካል ጉዳኝነትን ዜግነትን፣ ስደተኝነትን፣ ቋንቋን፣ ውጫዊ ገፅታን መሰረት በማድረግ ሆነ ብሎ እኩይ አድርጎ የሚስል የሚያንኳስስ፣ የሚያስፈራራ፣ መድልዎ ወይም ጥቃት እንዲፈፀም የሚያነሳሳ ጥላቻ አዘል መልዕክቶችን በመናገር፣ ፅሁፍ በመፃፍ፤ በኪነ ጥበብ እና እደ ጥበብ፣ የድምፅ ቅጂ ወይም ቪዲዮ፣ መልእክቶችን ብሮድካስት ማድረግ ወይም በማህበራዊ ሚዲያ ማሰራጨትን እንደሚመለከት ይገልጻል። ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ እንደሚለው ኢትዮጵያ የጥላቻ ንግግር ህግ ያስፈልጋታል። ነገር ግን አተረጓጎሙ ላይ ከፍተኛ ጥርጣሬና ስጋት አለኝ ብሏል። ልክ የጸረ ሽብር ህጉ የመናገር ነጻነትን እንደገደበው ሁሉ ይሄኛውም ተመሳሳይ ነገር እንዳይፈጠር ጥንቃቄ ሊደረግ ይገባል። ፕሮፌሰር መራራ ጉዲና ደግሞ የጥላቻ ንግግር ህጉ አሳሳቢ ነው በማለት ጀምረዋል። ምክንያቱም ህግ ተርጓሚው አካል በነጻነትና ሙሉ መረጃዎችን ይዞ መስራት የማይችል ከሆነ አሁንም ቢሆን ህጉ በተሳሳተ መልኩ ሊተረጎም ይችላል። ጋዜጠኛ ጸዳለ ለማ ደግሞ በዚህ ጉዳይ ላይ በመንግስት መፍረድ ከባድ ነው ብላለች በቀላሉ በቁጥጥር ስር ሊውሉ የሚችሉ አጋጣሚዎች በማህበራዊ ሚዲያ በተሰራጩ የተሳሳቱና ግጭት በሚያስነሱ መልእክቶች ብቻ ለብዙ ሰዎች ህይወት መጥፋት ምክንያት ሆነዋል። ነገር ግን የህጉ አተገባበር ላይ አሁንም ቢሆን ጥንቃቄ ሊደረግ እንደሚገባ ትስማማለች። የክርክር መድረኩ ከላይ ከተጠቀሱት ሃሳቦች በተጨማሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ የተለያዩ የመንግስት ድርጅቶችና ፋብሪካዎችን ሙሉ በሙሉና በከፊል ወደግል ባለሃብቶች ለማዘዋወር ያቀረቡት ሃሳብ እንዲሁም በቀጣይ ሊደረግ ስለታሰበው ምርጫ ውይይት ተደርጓል። ተያያዥ ርዕሶች
ለኢትዮጵያ ሳተላይት ማምጠቅ ቅንጦት አይደለም የኢትዮጵያ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር
ኅዳር የመሬት ምልከታ ሳተላይት መሬትን እየቃኘ መረጃዎችን በፎቶ ይመዘግባል የመሬት ምልከታ ሳተላይት የሰው ልጅ በህዋ ሳይንስ ካስመዘገባው ውጤቶች አንዱ ነው። ሳተላይቱ ከምድር ወደ ህዋ ከተመነጠቀ በኋላ መሬትን እየቃኘ መረጃዎችን በፎቶ ይመዘግባል። እንደያስፈላጊነቱም መረጃውን ወደ ምድር ይልካል። አፍሪካ ውስጥ እስካሁን ሳተላይቱን ያመጠቁ በጣት የሚቆጠሩ ሀገሮች ናቸው። ኢትዮጵያም የአምጣቂዎቹን ቡድን ለመቀላቀል መሰናዶ የጀመረችው ከሁለት ዓመት በፊት ነበር። ሳተላይቱን ሀገር ውስጥ ለመስራት እንዲሁም ከኢትዮጵያ ለማምጠቅ የሚያስፈልገው ቴክኖሎጂና የሰው ሀይል ባለመኖሩ ወደ ሩቅ ምሥራቅ ስታማትር፤ ቻይና የገንዘብና የሙያም እገዛ ለመስጠት ተስማማች። ትራምፕ ጠቅላይ አቃቢ ሕጉን አባረሩ ከቻይና ሚሊየን ዶላር ተለግሶ ስራው ተጀመረ። ቻይናውያን ኢንጂነሮች ኢዮጵያውያንን እያሰለጠኑ ሳተላይቱ ቻይና ውስጥ እንዲሁም በከፊል ኢትዮጵያ ውስጥ ተገነባ። ኪሎ ግራም የሚመዝነው ሳተላይት በ ዓ ም መባቻ ላይ ከቻይና ይመጥቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ የኢትዮጵያ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ ር ሰለሞን በላይ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ሳተላይቱ በቻይና እገዛ ከምድረ ቻይና ይምጠቅ እንጂ፤ ተቆጣጣሪዋም፣ አዛዧም ኢትዮጵያ ናት የሚለውን አስምረውበታል። ሳተላይት ማምጠቅ ለምን አስፈለገ የህዋ ጥናት በዓለም ላይ በፍጥነት እየዘመኑ ካሉ ዘርፎች መካከል ይጠቀሳል። የሰው ልጅ ምድር ጠባው አልያም ከምንኖርበት ዓለም ውጪ ያለውን ለማወቅ ጓጉቶ ዘወትር እየቆፈረ ነው። ከህዋ ፍተሻ በተጨማሪ ህዋን ተጠቅሞ መሬትን ማሰስ የመሬት ምልከታ ሳተላይት ተግባር ነው። ሳተላይቱ መረጃ ሲሰበስብ ይህ ቀረህ አይባለውም። ከግዙፍ ክንውኖች እስከ ጥቃቅን እንቅስቃሴዎች ይመዘግባል። እንደ ባለሙያዎች አባባል ሳተላይቱ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ አለው። የአየር ንብረት ለውጥን ለመቆጣጠር፣ የተፈጥሮ አደጋዎች ከመድረሳቸው አስቀድሞ ለመተንበይ፣ ደህንነትን ለመጠበቅ ወዘተርፈ ይውላል። በእርግጥ ብዙዎች በታዳጊ ሀገር የህዋ ጥናት አስፈላጊነቱ ላይ ጥያቄ ቢያነሱም፤ ዶ ር ሰለሞን ህዋ እንደ ኢትዮጵያ ላሉ ሀገሮች የመኖርና ያለመኖር ጥያቄ ነው፤ ቅንጦት አይደለም ይላሉ። የአየር ንብረት ለውጥ የመላው ዓለም ስጋት በሆነበት ዘመን፤ አንዳች ተፈጥሯዊ አደጋ ከመድረሱ በፊት አስቀድሞ መረጃ ማግኘት ብልህነት ነው። የዛፍ ቁጥር፣ የአየር ንብረት ለውጥና ሌሎችም መረጃዎች ከተሰበቡ በኋላ እንደ ጎርፍ ያሉ አደጋዎች ከመከሰታቸው በፊት መተንበይ ይቻላል። በቤታችን ውስጥ ያለ አየር የጤናችን ጠንቅ እንዳይሆን ማድረግ ያለብን ነገሮች ግብርና ቀዳሚ መተዳደሪያ በሆነባት ሀገር የቱ አካባቢ ምርታማ ነው የአየር ንብረት ለውጥ ይኖር ይሆን የሚሉ ጥያቄዎች በቀላሉ እንዲመለሱ የሳተላይቱ መረጃ አስፈላጊ ይሆናል። ዶ ር ሰለሞን እንደሚሉት፤ አንድ የግብርና አካባቢን የሚያሳይ ፎቶግራፍ ስለ እርሻ መሬቱ፣ ስለ ውሀው፣ ስለ አፈሩ ዝርዘር መረጃ ይሰጣል። መረጃዎቹን በመጠቀም ምርታማ የሆኑ አካባቢዎችን መለየት፣ የምርት መጠንን በትክክል ማወቅም ይቻላል። ኢንዱስትሪዎች እየተስፋፉ በመጡባት ኢትዮጵያ፤ ፋብሪካዎች የት መገንባት አለባቸው ለሚለው ጥያቄ የሳተላይቱ መረጃ መልስ ሊሰጥ ይችላል። ሕዝብ መቁጠር ሲያስፈልግ ከዘልማዳዊው መንገድ ሳተላይቱን መጠቀም ይመረጣል። ትክክለኛ መረጃ ከማግኘት፣ ገንዘብና የሰው ሀይል ከማዳን አንጻርም የተሻለው አማራጭ ነው። ሳተላይቱን ደህንነትን ከመጠበቅ ጋር የሚያስተሳስሩት ባለሙያዎች አሉ። ዶ ር ሰለሞን በበኩላቸው በመርህ ደረጃ ህዋ የሚውለው ለሰላማዊ እንቅስቃሴ ነው ብለው፤ ለጦርነት፣ ለጦር መሳሪያ ማሳለጫነት እንደማይውል ያስረዳሉ። የ ኢንተርናሽናል የአውተር ስፔስ ተቋም አባል መሆን፤ ኢትዮጵያን ከመሰል ድርጊቶች እንደሚያግዳትም አክለዋል። ኢትዮጵያ እስካሁን መረጃውን እንዴት ታገኝ ነበር ኢትዮጵያ እነዚህን መረጃዎች ሳተላይት አምጥቀው ፎቶ ከሚያስነሱ ሀገሮች ትሸምት ነበር። ዶ ር ሰለሞን የሚያጣቅሱት ከአራት ዓመት በፊት በተሰራ ጥናት መሰረት ኢትዮጵያ በዓመት ሚሊየን ብር ታወጣለች። ጥናቱ ለደህንነት የሚወጣውንና ዩኒቨርስቲዎች የሚከፍሉትን አያካትትም። ወጪው ከዓመት ወደ ዓመት እንደሚጨምርም ያስረዳሉ። የከተሞች መስፋፋት፣ ኢንቨስትመንቶች እየጨመሩ ሲሄዱም በዛው መጠን የመረጃው አስፈላጊነት ይንራል። የሚወጣው ገንዘብም እንዲሁ። ሳተላይት ማምጠቅ እነዚህን ወጪዎች እንደሚቀንስ ይጠበቃል። አፍሪካ ውስጥ መሰል ሳተላይት ለሌላቸው ሀገሮች መረጃ መሸጥም ይቻላል። የኢትዮጵያ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተሩ ትልቅ ቢዝነስ ነው የሚሉትም ለዚሁ ነው። ሲያስፈልግ መረጃ እንሸጣለን። ከኛ የላቀ ቴክኖሎጂ ካላች ሀገሮች ጋር መረጃ መለዋወጥም ይቻላል፤ ኢትዮጵያ በህዋ ጥናት የት ደረሰች ዓለም በህዋ ጥናት ቴክኖሎጂ እየመጠቀ ሄዷል። ኢትዮጵያ ከተቀረው ዓለም አንጻር ጀማሪ ናት። አፍሪካ ውስጥ ናይጄሪያ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ አልጄሪያና ግብጽ ጥሩ ስም አላቸው። ኢትዮጵያ ህዋ ለልማት የሚል የምሥራቅ አፍሪካ ሀገሮች ትብብር ቢሮ አቋቁማ አበረታች እንቅስቃሴ ማድረጓ ተጠቃሽ ስኬት ነው። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በ ይደረስባቸዋል ብሎ ካስቀመጣው ግቦች አብዛኞቹ የህዋ ቴክኖሎጂን ያማከሉ መሆናቸው፤ ዘርፉን ችላ ማለት እንደማያዋጣ ያመላክታል። ዶ ር ሰለሞን የመሬት ምልከታ ሳተላይት ማምጠቅ ኢትዮጵያ በህዋ ሳይንስ ዘርፍ እንቅስቃሴ እያደረገች ስለመሆኑ ለዓለም መልእክት ማስተላለፊያ መንገድ እንደሚሆን ያምናሉ። ቴክኖሎጂው እጅግ አስፈላጊ ነው፤ ሳተላይቱን ማምጠቅ ኢትዮጵያን በህዋ ዘርፍ ጠንካራ ተወዳዳሪና እኩል ተጽእኖ ፈጣሪ ማድረግ የሚያስችል ነው ሳተላይቱ አንዴ ከመጠቀ በኋላ ከሶስት እስከ አራት ዓመት ያገለግላል። ከዛ በላይ ሊቆይም ይችላል። በዓለም አቀፍ ሕግ መሰረት፤ የመሬት ምልከታ ሳተላይቶች ህዋ ላይ እንዲቆዩ የሚፈቀደው ለስምንት አመት ነው። ኢትዮጵያ ከምታመጥቀው ሳተላይት፤ በየአራት ቀኑ የመላው ኢትዮጵያ መረጃ የዓለም ደግሞ በ ቀን ይገኛል። በህዋ ምርምር ዘርፍ ቅርብ ጊዜ እውን ይሆናሉ ተብለው ከሚጠበቁ ፕሮጀክቶች ውስጥ ላሊበላ ላይ ይገነባል የተባለው ዓለም አቀፍ ኦፕቲክ ቴሌስኮፕ አንዱ ነው። ከዚህ ዜና በተጨማሪ
ኦነግ እና መንግሥትን ለማግባባት ወደ ምዕራብ ኦሮሚያ ያቀኑት የሃገር ሽማግሌዎች ወደ አዲስ አበባ ተመለሱ
ኅዳር ይህንን ለማጋራት በ ዋትስአፕ በምዕራብ ኦሮሚያ ያጋጠመውን የጸጥታ መደፍረስ በሽምግልና ለመፍታት ወደ ስፍራው አቅንተው የነበሩ የሃገር ሽማግሌዎች ወደ አዲስ አበባ ተመለሱ። ወደ ምዕራብ ኦሮሚያ ካቀኑት የሃገር ሽማግሌዎች መካከል አንዱ የሆኑት ኢንጂነር መስፍን አበበ ለቢቢሲ እንደተናገሩት ነጋዴዎች፣ አባ ገዳዎች እና የሃይማኖት አባቶች ከልዑኩ ቡድን አባላት መካከል ይገኙበታል። አስቀድመን ከነቀምት፣ ጊምቢ እና ደምቢ ዶሎ ከተሞች ነዋሪዎች ጋር ውይይት አድርገናል የሚሉት ኢንጂነር መስፍን የሃገር ሽማግሌዎቹ ከነዋሪዎች የተነሱላቸውን ጥያቄዎች እና አስተያየቶች አድምጠዋል። ከዚያም ጊዳሚ ከሚገኝ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ኦነግ አመራሮች ጋር ውይይት መደረጉን ይናገራሉ። የውይይቱን ውጤት መንግሥት እና ኦነግ መግለጫ የሚሰጡበት ጉዳይ ስለሆነ እኔ በዚህ ላይ ሃሳቤን አልሰጥም ብለዋል። ኢንጅነር መስፍን ጨምረው እንደሚሉት ውይይቱ በአንድ ጊዜ የሚጠናቀቅ ሳይሆን በቀጣይነት ብዙ ወይይት ሊያስፈልግ ይችላል ብለዋል። በጉዟችንም ሆነ በቆይታችን ምንም አይነት ችግር ሳይገጥመን በሰላም ደርሰን ተመልሰናል ይላሉ ኢንጂነር መስፍን። ሌለው የልዑኩ ቡድን አባል የሆኑት የታሪክ መሁሩ ሼክ ሃጂ ኢብራሚም ይገኙበታል። ሼክ ሐጂ እንዳሉት ከተለያዩ የከተማ ነዋሪዎች ጋር በተደረጉት ውይይቶች ላይ በርካታ የመብት ጥያቄዎች ተነስተዋል ብለዋል። ትጥቅ መፍታት ለድርድር አይቀርብም ፡ መንግሥት መሰረተ ልማቶች እንዲገነቡ፣ የኦሮሞ ህዝብ መብት እንዲከበር፣ ኦሮሚያ ውስጥ የሚኖሩ የሌሎች ብሔሮች ተወላጆች መብቶች እንዲከበሩ ለመንግሥት መልዕክት አስተላልፉልን ሲሉ ጠይቀውናል ሲሉ ሼክ ሐጂ ለቢቢሲ ተናግረዋል። በምዕራብ ኦሮሚያ ከሚገኙ የኦነግ ወታደሮች እና አመራሮች ጋር ውይይት ማድረጋቸውን የሚያስታውሱት ሼክ ሐጂ፤ ከፍተኛ አመራሮቻችን አዲስ አበባ ነው ያሉት፤ ከእነሱ ጋር መወያየት ይኖርባችኋል የሚል ምላሽ ከኦነግ ወታደሮች እና አመራሮች እንደተሰጣቸው ይናገራሉ። በተጨማሪም የኦሮሞ ህዝብ መብት ለረዥም ዓመታት ሳይከበር ቆይቷል። የኦሮሞ መብት እንዲከበር እንሻለን። ይህንንም መናገር ያለበት እላይ ያሉት ከፍተኛ አመራሮቻችን ናቸው። ከእነሱ ጋር ተወያይታችሁ ከስምምነት መድረስ ትችላላችሁ እንደተባሉ ሼክ ሐጂ ኢብራሂምም ለቢቢሲ ተናግረዋል። ኦነግ ሀገር ለመገንጠል ነው የምሠራው ብሎ አያውቅም ሽጉጥ ገለታ ዶ ር ወደ ሃገር ውስጥ ሳንገባ በመሪዎቻችን እና በክልሉ ፕሬዚዳንት መካከል የተደረሰው ስምምነት ለምን ተግባራዊ አልተደረገም የሚል ጥያቄ በኦነግ ወታሮች መነሳቱን ሽማግሌዎቹ ገልፀዋል። በሌላ በኩል የኦሮሚያ ክልል መንግሥት ቃል አቀባይ የሆኑት አቶ አድማሱ ዳምጠው ለክልሉ ቴሌቪዥን ጣቢያ ሲናገሩ ወደ ምዕራብ ኦሮሚያ የሄዱት የሃገር ሽማግሌዎች ተደብድበው እና ተዘርፈው የሄዱበትም ዓላማ ሳይሳካ መመለሳቸውን ተናግረዋል። በቄለም ወለጋ ዞን ከሚገኙ ዘጠኝ ወረዳዎች ፖሊስ ጣቢያዎች ውስጥ የጦር መሳሪያ ተዘርፏል የሚሉት አቶ አድማሱ፤ ከአንድ ሺህ በላይ ቀበሌዎች ውስጥ የመንግሥት አስተዳደር እንዲፈርስ ተደርጎ በሌላ ሥርዓት እየተደራጀ ነው ብለዋል። ሼክ ሐጂ ኢብራሂም ግን የተደበደበም ሆነ የተዘረፈ ሰው አላየንም። በሰላም ሄደን በክብር ነው የተሸኘነው ይላሉ። ከውይይታችን መረዳት እንደቻልነው ሁለቱም ወገኖች የሚፈልጉት ሰላም እንዲሰፍን ነው የሚሉት ሼክ ሐጂ፤ ከጥቂት ቀናት በኋላም የኦነግ እና የመንግሥት ባለስልጣናትን አንድ ላይ በማምጣት እንደሚያወያዩ ተናግረዋል። ከዚህ ዜና በተጨማሪ
የቤት ውስጥ አየር መበከል ለጤናችን ጠንቅ እንደሚሆን አምስት የመፍትሄ ሃሳቦችን እነሆ
ኖቬምበር አጭር የምስል መግለጫ ቤት ውስጥ ሲጋራ ማጨስ የሚያስከትለው ጉዳት ከፍተኛ ነው የአየር ብክለት ለብዙ ሃገራት ፈተና እየሆነ የመጣ ጉዳይ ሲሆን፤ በየዓመቱ እስከ ሰባት ሚሊዮን የሚደርሱ ሰዎች ከዚህ ጋር በተያያዘ ህይወታቸው ያልፋል። አሁን እየኖርንበት ባለው ዓለም ከአስር ሰዎች ዘጠኙ ሲተነፍሱ የሳንባ ካንሰርን ለመሳሰሉ በሽታዎች ይጋለጣሉ። እነዚህ በአይን የማይታዩ በካይ ንጥረ ነገሮች በቤት ውስጥ ስንሆን ደግሞ ጉዳታቸው ከፍተኛ ነው። አዲስ በተሰራ አንድ ጥናት መሰረትም በቤት ውስጥ የሚከሰት ብክለት የሚያደርሰው ጉዳት ከውጪው ጋር ሲነጻጸር ከሁለት እስከ አምስት እጥፍ ይበልጣል። ነገር ግን ይህንን ጉዳት ለመቀነስ የተለያዩ መንገዶችን መጠቀም አሉ። እንዚህ አምስት የመፍትሄ እርምጃዎች በቤት ውስጥ ሊያጋጥመን የሚችልን ብክለት ለመከላከል ጠቃሚ ምክሮኦች ናቸው። አየር እንደልብ እንዲዘዋወር ያድርጉ አየር በቤት ውስጥ በደንብ የማይንሸራሸር ከሆነ፤ በካይ ንጥረ ነገሮች በቤት ውስጥ ይቀራሉ። የቤት ውስጥ በሮችና መስኮቶች ቢያንስ በቀን ከሁለት እስከ ሦስት ጊዜ ቢከፈቱና ለሃያ ደቂቃዎች ቤቱ ቢናፈስ፤ በካይ የሆኑት ንጥረ ነገሮች ከአዲሱ አየር ጋር ተቀላቅለው የመውጣት እድላቸው ሰፊ ይሆናል። ከዚህ በተጨማሪም ምግብ ካበሰሉ በኋላና ገላዎትን ከታጠቡ በኋላም ቤትዎን ማናፈስ ተገቢ ነው። አጭር የምስል መግለጫ የቤትን በርና መስኮት በመክፈት አየር እንዲዘዋወር ማድረግ በቤት ውስጥ ተክሎች እንዲኖሮ ያድርጉ ቤትን በአትክልት መሙላት ከሚኖረው ጥቅም በተጨማሪ ለመመልከትም ማራኪ ነው። አንዳንድ ተክሎች በአየር ውስጥ የሚገኙ ጎጂ ንጥረ ነገሮችን የማስወገድ አቅም ያላቸው ሲሆን፤ ካርቦንዳይ ኦክሳይድን አፍኖ በመያዝ ለአካባቢያችንም ከፍተኛ ጠቀሜታን ያበረከታሉ። ነገር ግን በቤታችን ውስጥ የምናስቀምጣቸው ተክሎች እንክብካቤ የማናደርግላቸው ከሆነ፤ እንደውም ጎጂ የሆኑ ንጥረ ነገሮችን ወደ አየር ሊለቁ ይችላሉ። ስለዚህ ሁሌም ቢሆን ሌላው ቢቀር ውሃና ጥሩ አየር እንዲያገኙ ማድረግ ያስፈልጋል። ሽታ ያላቸው ፈሳሾችን ያስወግዱ በማንኛውም ጊዜ በቤት ውስጥ የሚጠቀሟቸው ሽቶዎች፣ ዲኦድራንቶችና የአየር ጠረን መቀየሪያ ምርቶች ትተውት የሚሄዱት ጎጂ ንጥረ ነገር አለ። ይህ ደግሞ ሰውነታችን ላይ በተለይ ደግሞ ሳንባችን ላይ ያለው አሉታዊ ተጽዕኖው ከፍተኛ ነው። አጭር የምስል መግለጫ የተለያዩ አይነት የቤት ውስጥ ተክሎች መትከል በቤት ውስጥ ሲጋራ አያጭሱ ማጨስ በራሱ ከፍተኛ ጉዳት ያለው ሲሆን፤ ቤት ውስጥ ማጨስ ደግሞ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንደማለት ነው። የሲጋራ ጭስ በቤት ውስጥ ሲጠራቀም በተለይ ደግሞ በሮች ተዘግተው ከሆነ የሚኖረው ጉዳት እንኳን ለማያጨስ ሰው፤ ለሚያጨሰው ሰው በራሱ ከፍተኛ ጉዳት አለው። በቤት ውስጥ ሲጋራ ከሚያጨሱ ቤተሰቦች የሚወለዱ ህጻናት ደግሞ ለድንገተኛ ሞት የተጋለጡ ናቸው።
የማይናማር ግጭትን ለማባባስ ፌስቡክ ጥቅም ላይ መዋሉን ሪፖርት ጠቆመ
ኖቬምበር አጭር የምስል መግለጫ የማይናማር ግጭትን ለማባባስ ፌስቡክ ጥቅም ላይ ውሏል ፌስቡክ የማይናማር ግጭትን ለማባባስ ጥቅም ላይ እንዳይውል መከላከል ተስኖታል የሚለውን ሪፖርት ፌስቡክ እንደሚስማማበት ገልጸ። በፌስቡክ የተዋቀረው ገለልተኛ ሪፖርት እንደጠቆመው በማይናማር የመብት ጥሰቶችን እና ግጭቶችን ለማባባስ ፌስቡክ ምቹ ሁኔታ ፈጥሯል። የተባበሩት መንግሥታት፤ በሮሂንጋ ማኅበረሰብ ላይ የደረሰውን ጥቃትና የሰብዓዊ መብት ጥሰት ለዘር ማጥፋት የቀረበ ሲል ፈርጆት ነበር። ፌስቡክ በማይናማር ከ ሚሊዮን በላይ ተጠቃሚዎች አሉት። ፌስቡክ ለበርካቶች ዋነኛው ወይም ብቸኛው የመረጃና የዜና ምንጭ ነው። የፌስቡክ አስተዳደሮች በማይናማር እየገጠመን ያለውን ችግር ለመቅረፍ እየሠራን ነው። ሆኖም ብዙ ይቀረናል ብለዋል። ባለፈው ዓመት የሮሂንጋ ታጣቂዎች ፖሊስ ጣቢያዎች ላይ ጥቃት መሰንዘራቸውን ተከትሎ የሃገሪቱ ጦር ራክሂን በምትባለው ግዛት ላይ መጠነ ሰፊ ጥቃት ሰንዝሮ ነበር። በሺዎች የሚቆጠሩ ህይወታቸውን ሲያጡ፤ ከ ሺህ በላይ ሰዎች ደግሞ ወደ ጎረቤት ሃገር ባንግላዲሽ ተሰደዋል። በሮሂንጋውያን ላይ የአስገድዶ መድፈር፣ የእርሻ መሬትን መቃጠልና መሰል በደሎች ደርሶባቸዋል። በካሜሮን ከ በላይ ተማሪዎችና መምህራን ታገቱ ሮሂንጋውያን በማይናማር በርማ ተብላ ትጠራ በነበረው ሃገር ውስጥ እንደ ስደተኛ ይቆጠራሉ። በመንግሥት እና በተቀረው ሕዝብ ለበርካታ አስረት ዓመታት ተገልለዋል። ቢዝነስ ፎር ሶሻል ሪስፖንሲቢሊቲ ያቀረበው ባለ ገጽ ገለልተኛ ሪፖርት በማይናማር ግጭትና ጥላቻን ማባባስ ለሚፈልጉ ቡድኖች ፌስቡክ መጠቀሚያ ሆኗል ይላል። ሪፖርቱ፤ ፌስቡክ የጥላቻ ንግግርን በተመለከተ ያለውን ፖሊሲ እንደገና ሊከልሰው ይገባል ሲልም አክሏል። ተያያዥ ርዕሶች
ኢትዮጵያን ወደተሻለ ስፍራ ሊወስዳት የሚችል ሌላ መሪ የለም የሶማሌ ክልል ም ፕሬዝዳንት
ግንቦት ይህንን ለማጋራት በ ትዊተር ይህንን ለማጋራት በ ዋትስአፕ ቢቢሲ በየወሩ የሚያዘገጀውና ቢቢሲ ወርልድ ኩዌስችንስ የተባለው አለማቀፍ የክርክር መድረክ ባሳለፍነው ሳምንት በአዲስ አበባ ሂልተን ሆቴል ተካሂዶ ነበር። ከ በላይ ታዳሚያን በተገኙበት ዝግጅት ፖለቲከኞች፣ ተንታኞችና የማህበረሰብ አቀንቃኞች ተሳታፊዎች ነበሩ። የክርክር መድረኩ ዋነኛ ማጠንጠኛ ሃሳብ ደግሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድና ባለፉት ወራት ይዘውት የመጡት ለውጥና እያጋጠሙ ያሉ ፈተናዎች ላይ ነበር። ከ ሚሊዮን በላይ ህዝብ ያላት ኢትዮጵያ እስካሁንም ለምን መረጋጋት ተሳናት ሲል የመድረኩ አዘጋጅ የነበረው ጆናታን ዲሞቢልቢ ጠይቋል። በመድረኩ ከተገኙት መካከል ደግሞ የሶማሌ ክልል ም ፕሬዝዳንት አቶ ሙስጠፋ ኦማር፣ ፕሮፌሰር መራራ ጉዲና፣ የአዲስ ስታንዳርድ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ጸዳለ ለማ እንዲሁም እስክንድር ነጋ ይጠቀሳሉ። ተስፋዬ ገብረአብ ስለ ዶ ር ነጋሶ ጊዳዳ ምን ይላል ከተሳታፊዎች የመጣው የመጀመሪያ ጥያቄ ደግሞ እውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ኢትዮጵያን የበለጸገች፣ ሰላማዊና የተረጋጋች ሃገር ማድረግ ይችላሉ ወይ ነበር። ለዚህ ጥያቄ ምላሽ በመስጠት የጀመሩት የሶማሌ ክልል ም ፕሬዝዳንት አቶ ሙስጠፋ ኦማር ነበሩ። በአሁኑ ሰአት ኢትዮጵያ ያለችበትን ሁኔታ ተረድቶ ወደተሻለ ስፍራ ሊወስዳት የሚችል መሪ ከአሁኑ ጠቅላይ ሚኒስትራችን የተሻለ ሰው ሃገሪቱ ታገኛለች ብዬ አላምንም ብለዋል። በጥላቻና መጠራጠር ተሸብቦ የነበረን ህዝብ ወደ ፍቅርና አንድነት ማምጣት እጅግ ከባድ ፈተና ሊሆን ይችላል፤ ነገር ግን የማይቻል አይመስለኝም በማለት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል። ፕሮፌሰር መራራ ጉዲና በበኩላቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ሃገሪቱን ወደተሻለ ከፍታ ለመውሰድ ከባዱ ፈተና የሚሆንባቸው የኢትዮጵያ ህዝብ ሳይሆን ራሳቸው የሚመሩት ኢህአዴግ ነው ብለዋል። ብዙዎቹ የፓርቲው አባላት ለለውጥ የተዘጋጁ አይደሉም፤ ጠቅላዩ ከሚያመጧቸው የለውጥ ሃሳቦች ጋርም አብረው መጓዝ አይችሉም። አሁንም ቢሆን ፈጣን ለውጥ ማምጣት የማይችሉ ከሆነ ህዝቡ መጠየቅ ይጀምራል። ጋዜጠኛና የሰብአዊ መብት ተሟጋች እስክንድር ነጋ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አሁን እየተከተሉት ባለው አካሄድ ሃገሪቱን ወደ ብልጽግና ይመሯታል ብዬ አላስብም በማለት ተከራክሯል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለውጥ ለማምጣት የመረጡት መንገድ የተሳሳተና ወዳልተፈለገ አቅጣጫ የሚመራ ነው ብሏል። ጋዜጠኛ ጸዳለ ለማ ደግሞ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ፈተናዎች ከሁለት አቅጣጫዎች እንደሚመነጩ ታስረዳለች። ኢትዮጵያ ውስጥ ለውጥና ብልጽግና ሊመጣ የሚችለው ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ የሚመሩት ፓርቲ ራሱን ፈትሾ ለለውጥ ሲዘጋጅና በብሄር ፖለቲካ ሲገዳደል የነበረው ህዝብ ይቅር ለመባባል ሲዘጋጅ ነው ብላለች። ሌላኛው ተሳታፊዎቹን ያከራከረ ሃሳብ በብሄር ላይ የተመሰረተ ፌደራሊዝም ለኢትዮጵያ ያስፈልጋታል ወይስ አያስፈልጋትም የሚለው ጥያቄ ነበር። በዘር የተከፋፈለውና መስማማት የማይችለው የተማረው ሃይል ራሱን ለመቀየርና ልዩነቶቹን አጥብቦ አብሮ ለመስራት እስካልተዘጋጀ ድረስ ምንም አይነት ለውጥ ሊመጣ አይችልም የሚሉት ፕሮፌሰር መራራ ጉዲና በደንብ ከታሰበበት ፌደራሊዝሙ በራሱ ለውጥ ሊያመጣ ይችላል ብለው ያምናሉ። እስክንድር ነጋ በበኩሉ ከሶስት ሚሊየን በላይ ሰዎችን ከመኖሪያ ቀያቸው እንዲፈናቀሉ ምክንያት የሆነው ፌደራሊዝሙ ነው፤ አሁንም ቢሆን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚህ ዙሪያ አልተሳካላቸውም ብሎ የተከራከረ ሲሆን የሶማሌ ክልል ም ፕሬዝዳንት አቶ ሙስጠፋ ኦማር ግን ተቃራኒ ሃሳብ አላቸው። ከዚህ በፊትም ቢሆን በሚሊየኖች የሚቆጠሩ ሰዎች ይፈናቀሉ ነበር። ነገር ግን ይህን ያክል ሰዎች ተፈናቅለዋል ብሎ እንኳን ማውራት አይቻልም ነበር። አሁን ግን ሌላው ቢቀር በነጻነት ስለተፈናቃዮቹ ማውራት ጀምረናል ብለዋል። አክለውም በተለያዩ አካባቢዎች የሚነሳው ግጭት ሙሉ በሙሉ ሃገሪቱ አልተረጋጋችም ለማለት በቂ አይደለም። ህዝቡ የተቃውሞ ሰልፍ ለመውጣት ፍራቻ አለመሳየቱ በራሱ የሚያሳየው ነገር አለ። ሁሌም ቢሆን ለውጥ ሊመጣ ሲል መንገራገጭ ያለ ነው። መረሳት የሌለበት ሌላኛው ነገር በሃገር ውስጥ የሚፈናቀሉት እንዳሉ ሆነው ለውጡን ለመደገፍና የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ለማድረግ ወደሃገር ቤት የተመለሱትስ በማለት አቶ ሙሰጠፋ ሃሳባቸውን አጠናክረዋል። የለውጡ ጎዳና እስከየት የጥላቻ ንግግርና የሃሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከል የተዘጋጀው ረቂቅ አዋጅም በመድረኩ ብዙ ሃሳቦችን ያንሸራሸረ ጉዳይ ነበር። ረቂቅ አዋጁ የጥላቻ ንግግር ትርጉም ብሎ ሲያስቀምጥ ሆን ብሎ የሌላ ግለሰብን፣ የተወሰነ ቡድንን ወይም ማህበረሰብን ብሔርን፣ ሃይማኖትን፣ ቀለምን፣ ፆታን አካል ጉዳኝነትን ዜግነትን፣ ስደተኝነትን፣ ቋንቋን፣ ውጫዊ ገፅታን መሰረት በማድረግ ሆነ ብሎ እኩይ አድርጎ የሚስል የሚያንኳስስ፣ የሚያስፈራራ፣ መድልዎ ወይም ጥቃት እንዲፈፀም የሚያነሳሳ ጥላቻ አዘል መልዕክቶችን በመናገር፣ ፅሁፍ በመፃፍ፤ በኪነ ጥበብ እና እደ ጥበብ፣ የድምፅ ቅጂ ወይም ቪዲዮ፣ መልእክቶችን ብሮድካስት ማድረግ ወይም በማህበራዊ ሚዲያ ማሰራጨትን እንደሚመለከት ይገልጻል። ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ እንደሚለው ኢትዮጵያ የጥላቻ ንግግር ህግ ያስፈልጋታል። ነገር ግን አተረጓጎሙ ላይ ከፍተኛ ጥርጣሬና ስጋት አለኝ ብሏል። ልክ የጸረ ሽብር ህጉ የመናገር ነጻነትን እንደገደበው ሁሉ ይሄኛውም ተመሳሳይ ነገር እንዳይፈጠር ጥንቃቄ ሊደረግ ይገባል። ፕሮፌሰር መራራ ጉዲና ደግሞ የጥላቻ ንግግር ህጉ አሳሳቢ ነው በማለት ጀምረዋል። ምክንያቱም ህግ ተርጓሚው አካል በነጻነትና ሙሉ መረጃዎችን ይዞ መስራት የማይችል ከሆነ አሁንም ቢሆን ህጉ በተሳሳተ መልኩ ሊተረጎም ይችላል። ጋዜጠኛ ጸዳለ ለማ ደግሞ በዚህ ጉዳይ ላይ በመንግስት መፍረድ ከባድ ነው ብላለች በቀላሉ በቁጥጥር ስር ሊውሉ የሚችሉ አጋጣሚዎች በማህበራዊ ሚዲያ በተሰራጩ የተሳሳቱና ግጭት በሚያስነሱ መልእክቶች ብቻ ለብዙ ሰዎች ህይወት መጥፋት ምክንያት ሆነዋል። ነገር ግን የህጉ አተገባበር ላይ አሁንም ቢሆን ጥንቃቄ ሊደረግ እንደሚገባ ትስማማለች። የክርክር መድረኩ ከላይ ከተጠቀሱት ሃሳቦች በተጨማሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ የተለያዩ የመንግስት ድርጅቶችና ፋብሪካዎችን ሙሉ በሙሉና በከፊል ወደግል ባለሃብቶች ለማዘዋወር ያቀረቡት ሃሳብ እንዲሁም በቀጣይ ሊደረግ ስለታሰበው ምርጫ ውይይት ተደርጓል። ቢቢሲ ማስተባበያ
የስኳር ፋብሪካዎች፡ ለግል ባለሃብቶች የመስጠት ፋይዳና ፈተናዎቹ
ግንቦት ይህንን ለማጋራት በ ዋትስአፕ የኢትዮጵያ መንግሥት የስኳር ፋብሪካዎችን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ለመሸጥ ማስታወቂያ ካወጣበት ቀን ጀምሮ ብዙ የሀገር ውስጥና የውጪ ድርጅቶች እየተመዘገቡና ፍላጎታቸውን እየገለጹ እንደሆነ የኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽን ሥራ አስኪያጅ አቶ ወዩ ሮባ ለቢቢሲ ተናግረዋል። በአውሮፓውያኑ በወጣ መረጃ መሠረት በሃገሪቱ ያሉ ሁሉም ፋብሪካዎች ሚሊዮን ኩንታል ስኳር የሚያመርቱ ሲሆን ሃገሪቱ የሚያስፈልጋት ግን ሚሊየን ኩንታል ነው። መንግስትም ይህንን ክፍተት ለመሙላት ሚሊየን ኩንታል ስኳር ከውጪ በማስገባት ሲያከፋፍል ቆይቷል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ የሀገር ውስጥ ምርቱን ወደ ሚሊዮን ኩንታል ለማሳደግ በማሰብ መንግሥት ተጨማሪ ስኳር ፋብሪካዎችን መገንባት ጀምሮ ነበር። የግንባታ ሥራውን ያከናውን የነበረው ሜቴክ ግንባታውን በታሰበለት ጊዜ ማጠናቀቅ ባለመቻሉ መንግሥት ለተጨማሪ ወጪ ተዳርጓል። ፋብሪካዎቹን መሸጥ ለምን አስፈለገ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ ወደ ሥልጣን ከመጡ ጊዜ አንስቶ ብዙ ለውጦችን ያደረጉ ሲሆን ከእነዚህም መካከል የተለያዩ የመንግሥት ድርጅቶችን ለግል ባለሃብቶች ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሸጥ ሃሳብ ደግሞ አንዱ ነው። ሃገሪቱ ትልቅ የውጭ ምንዛሪ እጥረት ውስጥ ስለነበረችና የተከማቸ የረጅም ጊዜ ብድር መክፈል አለመቻሏ ለዚህ ውሳኔያቸው ገፊ ምክንያት እንደሆነ የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎች ይናገራሉ። የምጣኔ ሃብት ባለሙያ የሆኑትና በቤልጂየም የዶክትሬት የምረቃ ጥናት ወረቀታቸውን በዚሁ ጉዳይ ላይ እየሰሩ የሚገኙት አቶ ተሾመ ተፈራ እንደሚሉት መንግሥት በሁለት ምክንያቶች ፋብሪካዎቹን ለመሸጥ ተገዷል። የመጀመሪያው ምክንያት አብዛኛዎቹ ፋብሪካዎች በብድር ስለተገነቡ ግንባታቸው ገና ሳይጠናቀቅ የመክፈያ ጊዜያቸው መድረሱና መንግሥት በቂ የሆነ የውጪ ምንዛሪ ስለሌለው ለተጨማሪ ወጪ ተዳርጓል። ይህ ደግሞ ፋብሪካዎቹን ለመሸጥ አስገድዶታል ብለው ያምናሉ አቶ ተሾመ። ባለሙያው በሁለተኛነት ያስቀመጡት ምክንያት መንግሥት በአጭር ጊዜ ውስጥ ፋብሪካዎቹ ተሸጠው የተጣራ የውጭ ምንዛሪ ማግኘት መፈለጉን ነው። አቶ ተሾመ አክለውም በረጅም ጊዜ ውስጥ ፋብሪካዎቹን ወደ ግል ማዘዋወሩ ለሃገሪቱ ኢኮኖሚ እድገት አሉታዊ ተጽዕኖ ይኖረዋል። ከዚህ በተጨማሪ ፋብሪካዎቹ በአጭር ጊዜ ማምረት ጀምረው ከሃገር ውስጥ ፍላጎት ያለፈ ጥቅም ሊኖራቸው ስለማይችል ከሽያጩ የተጣራ የውጭ ምንዛሪ ማግኘት ይችላል። በረጅም ጊዜ ደግሞ ወደ ውጪ ከሚላከው ስኳር የውጪ ምንዛሪ ማግኘት እንደሚቻል ይናገራሉ። ዝብርቅርቅ ያለው የስኳር ንግድ ኬንያዊው የምጣኔ ሃብት ባለሙያ ዶክተር ቶኒ ዋቲማ በበኩላቸው ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ቀንድ ሃገራት ፈጣን የሚባል ኢኮኖሚያዊ እድገት እያስመዘገበች ነው በማለት የስኳር ፋብሪካዎችንም ሆነ ሌሎች የመንግሥት ድርጅቶችን ወደግል ከማዘዋወር ጋር በተያያዘ የኬንያን ተሞክሮ ሲያብራሩ፤ በዘርፉ የሚፈጸሙ የሙስናና የበጀት ምዝበራ ለመቆጣጠርና ለመቀነስ ከፍተኛ ሚና አለው ብለዋል። በዘርፉ የተሰማሩ የግል ባለሃብቶች በማንኛውም መልኩ ጊዜያቸውንና ገንዘባቸውን ከመቆጠብ ባለፈ ተገቢውን አገልግሎት ለተጠቃሚዎች ማድረስ ይችላሉ። መንግሥት እነዚህን ፋብሪካዎች ወደ ግል ባለሃብቶች ሲያዘዋውር ለግንባታና ሥራ ማስኬጃ በብድርም ሆነ ከካዝናው የሚመድበውን ገንዘብ ሌሎች ፕሮጀክቶች ላይ ለማዋል እንደሚያግዘው ቶኒ ዋቲማ ይናገራሉ። የኬንያ ተሞክሮም በዚሁ የተቃኘ እንደሆነ አክለዋል። የኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽን ከሽያጩ በኋላ የመንግ ሥ ት ሚና ምንድነው የኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽን ሥራ አስኪያጅ አቶ ወዩ ሮባ እንደሚሉት ፋብሪካዎቹ ወደ ግል ባለሃብቶች ሲዘዋወሩ እንዴት መተዳደር አለባቸው የሚለውን በተመለከተ አዲስ መመሪያ እየተዘጋጀ ነው። ሥርጭትና ሌሎችን በተመለከ ደግሞ ወደፊት ውሳኔ የሚሰጥባቸው እንደሆነና ዋጋን በተለመከተ ግን መንግሥት ሳይገባበት በነጻ ገበያው መርህ መሠረት የሚወሰን ይሆናል ብለዋል። ኢትዮጵያ ከውጭ ምንዛሬ እጥረት አዙሪት እንዴት ትውጣ አሁን ባለው አሰራር፣ መንግሥት የስኳር ሥርጭትን በሚቆጣጠርበት ጊዜ፣ እንኳን ነጋዴዎች ስኳሩን በመደበቅ ዋጋ ጨምረው ይሸጣሉ። መንግሥት በስኳር ዙሪያ ያለውን ተሳትፎ እጅጉን ሲቀንስ ደግሞ ተመሳሳይ ተግባሮች እንዳይበራከቱ ስጋት አለ። የምጣኔ ሃብት ባለሙያው አቶ ተረፈ ግን የግል ባለሃብቶች ዋጋውን መቆጣጠራቸውን እንደ ጥሩ አጋጣሚ ነው የሚያዩት። ምክንያቱም ይላሉ፤ ባለሃብቶች ቁጥራቸው በርከት ስለሚልና ከፍተኛ የገበያ ውድድር ስላለባቸው የስኳሩን ዋጋ ዝቅ ማድረጋቸው አይቀርም። የኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽን ስራ አስኪያጅ አቶ ወዩ ሮባም በዚሁ ሀሳብ ይስማማሉ። የኢትዮጵያ መንግሥት ፋብሪካዎቹን ወደግል ባለሃብቶች ከማዘዋወሩ በፊት የአሰራር ህግና ደንቦቹ ላይ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንዳለበት የኬንያው የምጣኔ ሃብት ባለሙያ ቶኒ ዋቲማ ይናገራሉ። ይህን ማድረገም የተጠቃሚዎችን መብት ለማስከበር፣ የሸንኮራ አቅራቢ አርሶአደሮችን ጥቅም ለማስጠበቅና የገበያ ሁኔታውን ለመከታተል ይጠቅመዋል ብለዋል። በተጨማሪም ባለሃብቶቹ ትርፍ ላይ ብቻ ትኩረት አድርገው ሊሰሩ ስለሚችሉ የምርት ጥራትን የሚቆጣጠር ጠንካራ ተቋም መቋቋም እንዳለበት ሃሳብ ሰንዝረዋል። የኬንያ አርሶአደሮች የተወሳሰበውን የዓለም ገበያ ሁኔታ መከታተልና መረዳት ስለማይችሉ ጠንካራ የአርሶአደሮች ማህበር ተቋቁሞላቸዋል፤ መብታቸውን ማስከበር የሚችልና ከዘመኑ አሰራር ጋር መራመድ የሚችሉ የህግ ባለሙያዎችም በማህበሩ ውስጥ አሉ። ሲሉ ያብራራሉ። እሳቸው እንደሚሉት ከምርት በኋላም የማከፋፈል ሥራውን የሚሰሩት ሌሎች ማህበራት ናቸው። ይህ ደግሞ አምራቾች ገበያውን ሙሉ በሙሉ እንዳይቆጣጠሩት ለማድረግ ይረዳል። ይህን የኬንያውያንን ተሞክሮ የኢትዮጵያ መንግሥት ከግምት ውስጥ ሊያስገባው እንደሚገባም ቶኒ ዋቲማ ይመክራሉ። ከዚህ በፊት በነበሩት ተሞክሮዎች የተለያዩ የጨርቃጨርቅ ፋብሪካዎች ለግል ባለሃብቶች ቢሰጡም ግልጽነት ባለመኖሩና ተገቢው የጥንቃቄ እርምጃዎች ባለመወሰዳቸው ስኬታማ እንዳልነበሩ የምጣኔ ሃብት ባለሙያው አቶ ተሾመ ያስታውሳሉ። ከውጪ የሚመጡ ድርጅቶች ፋብሪካው ከሚያወጣው በላይ ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ ብድር ይወስዱና ለአጭር ጊዜ ሰርተው ብድሩን ሳይመልሱ ፋብሪካዎቹን ትተው ካገር ይሸሹ ነበር። ስለዚህ መንግሥት እነዚህን ነገሮች ሁሉ ከግምት ውስጥ ማስገባት የማይችል ከሆነ አሁንም ለከፍተኛ ኪሳራና ስኳር እጥረት ሊዳረግ እንደሚችል ባለሙያው ያሳስባሉ። ቢቢሲ ማስተባበያ
በረመዳን ፆም ወቅት ሰውነታችን ውስጥ ምን ይካሄዳል
ሜይ ማጋሪያ ምረጥ አጭር የምስል መግለጫ ሙስሊሞች ከጸሐይ መውጫ እስከ ጸሐይ መግቢያ ድረስ ይጾማሉ፨ ይህ ከጤና አንጻር ምን ትጽእኖ ይኖረዋል በየዓመቱ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሙስሊሞች ረመዳንን በጾም ያሳልፋሉ። ጀንበር ወጥታ እስክትጠልቅ ድረስ። ሰውነታችን ከጾም ጋር የሚተዋወቀው ለመጨረሻ ጊዜ ምግብ ከቀመስን ከስምንት ሰዓታት በኋላ ነው። ይህም ማለት አንጀታችን ከተመገብነው ምግብ የሚያገኛቸውን ንጥረ ነገሮች በሙሉ አሟጦ ከጨረሰ በኋላ ነው የሚሆነው። ከዚህ በኋላ ሰውነታችን ተስፋ ይቆርጥና ፊቱን ጡንቻችንና ጉበታችን ውስጥ ወደተከማቸ ጉሉኮስ ያዞራል። የተቀረው የሰውነታችን አካል ጉልበት የሚያገኘውም ከዚህ የመጠባበቂያ ግምጃ ቤት ይሆናል ማለት ነው። ከጡንቻና ከጉበት የጉሉኮስ ክምችት ሲያልቅ ሰውነታችን ሌላ አማራጭ ስለማይኖረው ስብን ማቃጠል ይጀምራል፡፡ ከዚህ በኋላ ሙቀትና ጉልበትን የሚያገኘውም ከሌላ ሳይሆን ስብን በማቃጠል ነው፡፡ በዚህ ሂደት ውስጥ ታዲያ መልካም ነገሮች ይከሰታሉ፡፡ የሚቃጠለው ስብ በመሆኑ ክብደት መቀነስ፣ የኮሌስትሮል መጠን መውረድ ይኖራል፡፡ የስኳር መጠናችን በዚህ ወቅት ዝቅ ማለቱ አይቀርም። ሆኖም በደማችን ውስጥ የሚገኘው የስኳር መጠን ስለሚቀንስ ድካምና መዛልን ያስከትልብናል። ይህን ተከትሎ መጠነኛ ራስ ምታት፣ ማቅለሽለሽና መልካም ያልሆነ የአፍ ጠረን ሊከተል ይችላል። ይህ የሚሆነው በረሀብ ምክንያት ሆዳችንን ሲሞረሙረንና ያለ ምግብ መቆየቱ ለሰውነታችን እየከበደው ሲመጣ ነው። ከ ኛ ቀን፤ ሰውነታችን በፈሳሽ እጥረት የሚጎዳበት ጊዜ ሰውነታችሁ ጾሙን እየተለማመደ ሲመጣ በውስጣችን የሚገኘው ክምችት ስብ እየተሰባበረ ራሱን ወደ የደም ስኳርነት ይለውጣል። የምንወስደው ፈሳሽ መጠን እየቀነሰ መምጣቱ በሰውነታችን ውስጥ ያለው ፈሳሽ ወደመሟጠጥ ዲሀይድሬሽን ስለሚያመራ በ ማፍጠሪያ ሰዓትና ከዚያም በኋላ ባለው የሌሊቱ ክፍለ ጊዜ በርከት ያሉ ፈሳሾችን መውሰድ ይመከራል። በጾም መግደፊያ ሰዓት የምትወስዱት የምግብ መጠን ጉልበት ሰጪ የሆኑ ተመጣጣኝ ምግቦችን ማግኘት ይኖርበታል። በፕሮቲን የበለጸጉ ምግቦች ባሻገር ጨው እና በርከት ያለ ውኃ ከሌሎች የተመጣጠኑ ምግቦች ጋር ማግኘት ለሰውነታችን መልካም ሁኔታን ይፈጥራል። ከ ኛ ኛ ቀናት በዚህ ጊዜ ሰውነታችን ጾሙን ተላምዶታል። በዚህም የተነሳ ድካምና መዛሉ እንደመጀመርያዎቹ ጊዜያት ይሆናል ተብሎ አይጠበቅም። ዶክተር ራዚን ማህሩፍ የአኔስቴሺያና የጽኑ ሕሙማን ሕክምና አማካሪ ናቸው። በካምብሪጅ አዴንብሩክ ሆስፒታል ውስጥ ነው የሚሠሩት። እርሳቸው እንደሚሉት በዚህ ጊዜ ፆሙ ለሰውነታችን ሌላም በጎ ጎን ይዞ ይመጣል። ሙሉ በሙሉ ከወደመ በኋላ እንደገና የተገነባው መስጊድ ለምሳሌ በሌላው ጊዜ በርከታ ያለ ካሎሪ ያላቸው ምግቦችን የምንወስድ ከነበረ ሰውነታችን ሥራዎችን በአግባቡ ለመፈፀም ፈተና ውስጥ ይወድቅ ነበር። ወይም ደግሞ እክል ይገጥመዋል። በጾም ጊዜ ግን ይህ ሁኔታ ይስተካከላል። ምክንያቱም የካሎሪ ክምችት ስለማይበዛበት ሰውነታችን ወደ ሌሎች ሥራዎች ትኩረቱን ያደርጋል ይላሉ ሐኪሙ፡፡ ለዚህም ነው ጾም ኢንፌክሽን በመዋጋትና ጤናን በመመለስ አስተዋጽኦ የሚኖረው። ከ ኛ ኛ ያሉ ቀናት በረመዳን ሁለተኛው ምዕራፍ ከ ኛው ቀን ጀምሮ ሰውነት ሙሉ በሙሉ ጾሙን ይላመዳል። በዚህ ጊዜ እነ ደንዳኔ፣ ጉበት፣ ኩላሊት እንዲሁም ቆዳ ሁሉም ራሳቸውን በማፅዳት ሂደት ዲቶክሲፊኬሽን ውስጥ ነው የሚሆኑት። ዶክተር ማህሩፍ እንደሚሉት በዚህ ወቅት ጤና ተመልሶ፣ ሰውነታችን የቀድሞውን ጉልበቱን የሚያገኝበትና የማስታወስ አቅምና ትኩረት የማድረግ ብቃት ወደ ቀድሞው ሁኔታ የሚመለስበት ጊዜ ነው። በዚህ ጊዜ ሰውነታችን ጉልበት ለማግኘት ወደ ፕሮቲን መሄድ አይኖርበትም። ይህ የሚሆነው ብዙዉን ጊዜ ረሀብ ሲሰማንና ሰውነታችን ከጡንቻዎቻችን እየቀሰመ የሚወስደውን ምግብ ማደን ሲጀምር ነው። በዚህ መንገድ የሚቀጥለው ግን ለቀናትና ለሳምንታት በተከታታይ ስንጾም ነው። የረመዳን ጾም የሚጸናው የየዕለቱ ጀምበር ወጥታ እስክትጠልቅ ብቻ ስለሆነ ሰውነታችን ጉልበት ከምግብ እንዲያገኝ የ ኢፍጣር ሰዓት ዕድል ይሰጠዋል። ፈሳሽም እንደልብ ያገኛል። ይህ ጡንቻዎቻችን ውስጥ ያለን ክምችት ለመጠባበቂያነት ያቆይልናል። የተወሰነ ኪሎ እንድንቀንስም ይረዳናል። ይህም ለሰውነት መልካም ነገር ነው፡፡ እንዲያው በጥቅሉ፣ ጾም ጤናን ይጎዳል የካምብሪጁ አዲንብሩክ ሆስፒታል ሐኪም ዶክተር ማሕሩፍ ምላሻቸው እንደሁኔታው የሚል ነው። እንደርሳቸው አመለካከት በርከት ያሉ ሁኔታዎች ፆምን ለሰውነታችን ጎጂም ጠቃሚም ሊያደርጉት ይችላሉ። ጾም ለሰውነታችን አሪፍ የሚሆንበት አንዱ ምክንያት መቼ ምን መብላት እንዳለብን ትኩረት እንድናደርግ ስለሚያስችለን ነው። ሁለተኛው ክብደታችንን መቆጣጠርና፣ የካሎሪ መጠን መወሰን ስለሚያስችል ነው፡፡ ለወር ያህል መጾም እምብዛምም የሚያመጣው የጤና እክል ባይኖርም ከዚያ በኋላ ግን ለተከታታይ ጊዜ ያለማቋረጥ መጾም ግን አስቸጋሪ ሊሆን እንደሚችል ሐኪሙ ሳይጠቁሙ አያልፉም፡፡ እንደ ሐኪሙ ማብራሪያ ያለማቋረጥ መጾም በቋሚነት ኪሎ ለመቀነስ አይረዳም። ምክንያቱም ከሆነ ጊዜ በኋላ ሰውነታችን ስብን ወደ ጉልበት መቀየር ያቆምል። ከዚያ ይልቅ ፊቱን ወደ ጡንቻዎቸቻችን ነው የሚያዞረው። ይህ ጤናማ አይደለም። ምክንያቱም ሰውነታችን ከሆነ ወቅት በኋላ በመራብ ስሜት ላይ ስለሚቆይ ነው። ሐኪሙ እንደሚሉት ከረመዳን ውጭ መጾም ቢያስፈልግ እንኳ በሳምንት ሁለት ቀን ብቻ እያፈራረቁ መጾም በመደዳ ለተከታታይ ቀናት ከመጾም እጅግ የተሻለ ጤናማ ተግባር ነው። ረመዳን በአግባቡ ከተጾመና በቂ ፈሳሽ በቀን ውስጥ ማግኘት ከተቻለ፣ ጠቃሚ የጡንቻ ክምችቶች ሳይቃጠል ኪሎ መቀነስ ስለሚያስችል የጤና በረከትም ያስገኛል ይላሉ እኚሁ ሐኪም። ተያያዥ ርዕሶች
የኮሚኒስት ሥርዓት መውደቅን ያመለከተ ወሳኝ ክስተትየኮሚኒስት ሥርዓት መውደቅን ያመለከተ ወሳኝ ክስተት
የኮሚኒስት ሥርዓት መውደቅን ያመለከተ ወሳኝ ክስተት
አደገኛ ነው የተባለለት የወባ በሽታ በደቡብ ምሥራቅ እስያ ተስፋፍቷል
ሴፕቴምበር አጭር የምስል መግለጫ የወባ በሽታን የምታስተላልፈው ትንኝ አደገኛ እንደሆነ የተነገረለት የወባ ዓይነት በደቡብ ምሥራቅ እስያ በፍጥነት መዛመቱ ለአፍሪካ አስጊ መሆኑን ተመራማሪዎች አስታወቁ። ይህን መሰሉ የወባ ዓይነት በመደበኛው የወባ መከላከያ መድኃኒት በቁጥጠር ሥር አይውልም ተብሏል። ይህ የወባ ዓይነት መጀመሪያ በካምቦዲያ የታየ ቢሆንም ወደ ደቡብ እስያ ሃገራት ተስፋፍቷል። በባንኮክ የሚገኘው ኦክስፎርድ ትሮፒካል ሜድሲን የምርምር ተቋም ባልደረቦች እንደሚሉት ይህን የወባ ዓይነት ለመዳን አስቸጋሪ ይሆናል። የምርምር ቡድኑ የበላይ የሆኑት ፕሮፌሰር አሪየን ዶንድሮፕ በሽታው በፍጥነት ከመዛመቱም በላይ አፍሪካ ሊደረስ ይችላል የሚል ስጋት አለን ብለዋል። የኢትዮጵያ ተሞክሮ በጤና ጥበቃ ሚንስቴር የወባ ፕሮግራም ባለሙያ ሆኑት አቶ ደረጀ ድሉ እንደሚሉት መስሪያ ቤቱ ስለስጋቱ መረጃው አለው። ወባ በሽታን በመከላከል አበረታች ውጤት እየተገኘ መሆኑን የገለጹት ባለሙያው እ አ አ በ ላይ ሚልዮን የነበረው የህሙማን ቁጥር በ ወደ ሚሊዮን መቀነሱን ጠቁመዋል። እስካሁን ባለው አሰራር ፕላስሞዲየም ፋልሲፓረም እና ፕላስሞዲየም ቫይቫክስ ለተየባሉት የወባ ዓይነቶች መድኃኒቶች ጥቅም ላይ እየዋሉ ነው ብለዋል። እንደባለሙያው ከሆነ የመድኃኒቶቹን ውጤታማነት ለመከታተልም የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስትትዩት በየሁለት ዓመቱ ጥናት ያካሂዳል። የጨነገፉ መድኃኒቶች በወባ ትንኝ በሚዛመተው በዚህ በሽታ ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎች በየዓመቱ የሚያዙ ሲሆን ህጻናትን በመግደል ቀዳሚ ከሆኑት መካከልም ተጠቃሽ ነው። በሽታውን ለመቆጣጠር አርትሚሲኒንን ከፒፐራኩይን ጋር በማሃዋድ መጠቀም ተቀዳሚ ምርጫ ነው። አርትሚሲኒን ያለው ውጤታማነት እየቀነሰ ሲሆን በሽታው ደግሞ ፒፐራኩይንን እየተላመደ ይገኛል። በውህድ መድሃኒቶቹ በሽታውን ለመከላከል የሚደረገው ጥረት በአንዳንድ ቦታዎች እስከ በመቶ ድረስ መቀነሱን ፕሮፌሰር ዶንድሮፕ አስታውቀዋል። መድኃኒቱን የተላመደ ወባ መስፋፋቱ እስከ በመቶ የሚሆነው የወባ በሽታ በሚከሰትበት የአፍሪካ አህጉር የከፋ ችግር ሊያስከትል ይችላል። በአፋጣኝ የሚቀርብ መፍትሔ በሽታው መዳን ከማይቻልበት ደረጃ ደርሶ የሰዎችን ህይወት ከመቅጠፉ በፊት በፍጥነት መስራት ይኖርብናል ብለዋል። እውነቱን ለመናገር በጣም ሰግቻለሁ ሲሉ ፕሮፌሰሩ የክስተቱን አሳሳቢነት ይናገራሉ። የዌልካም ትረስት ሜዲካል ሪሰርች ባልደረባ ሆኑት ማይክል ቼው እንደሚሉት፤ መድኃኒት የተላመደ የወባ በሽታ መስፋፋቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለማህበረሰብ ጤና አስጊ ነው ብለዋል። እስካሁን በዓመት የ ሺህ ሰዎችን ህይወት ሲቀጥፍ የነበረው መድኃኒት የተላመደ የወባ በሽታ፤ ምንም ካልተሰራበት የሟቾች ቁጥር እ አ አ በ በሚሊዮኖች ከፍ ሊል ይችላል ብለዋል። በኢትዮጵያ የአዲሱ የወባ በሽታ ዓይነት አለመከሰቱን አቶ ደረጀ ጠቅሰው፤ መድኃኒት የተላመደ ወባን ለመከላከል እና የመድኃኒቶችን ውጤታማነት ለማረጋገጥ ከኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስትትዩት ጋር የሚደረገው ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል። ተያያዥ ርዕሶች
በአሜሪካ የምክር ቤት ምርጫ ዲሞክራቶች ቢያሸንፉ ትራምፕ ሊከሰሱ ይችላሉ
ኖቬምበር የአሜሪካ ምርጫ ማብቂያ ያለው አይመስልም። ለጊዜው ዋና ዋና ነጥቦችን ብናነሳ አይከፋም። የ ሚድ ተርም ምርጫ ምንድነው ሚድ ተርም የተባለው መሀል ላይ ስለሚካሄድ ነው። ለአራት ዓመት እንዲያገለግል የተመረጠው ፕሬዚዳንት ሁለት ዓመት እንደቆየ የሥራ ዘመኑ ይጋመሳል። በዚህ ወቅት ሚድ ተርም ምርጫ ይከሰታል። ምርጫው ታዲያ በአራት ዓመት አንድ ጊዜ በወርሃ ኖቬምበር ኅዳር ነው የሚካሄደው። ምን ዓይነት ምርጫ ነው የአሜሪካ ምክር ቤት ላዕላይና ታህታይ ምክር ቤቶች አሉት፤ የአማርኛ ስያሜያቸው ሊያከራክር ቢችልም። ታህታዩ ምክር ቤት የሕዝብ እንደራሴዎች ሲኖሩት ሀውስ ኦፍ ሪፕረዘንታቲቭስ ይባላል፤ ላዕላዩ ምክር ቤት አባላት ሲኖሩት ተመራጮቹ ሴናተሮች ተብለው ይጠራሉ። የኅብረት ስማቸው ኮንግረስ ነው። ይህ ሕግ አውጪ ምክር ቤት በድምሩ አባላት ይኖሩታል። በደፈናው አንድ ረቂቅ ሕግ ከላዕላዩም ከታህታዩም ምክር ቤት ሊመነጭ ይችላል ማለት እንችላለን። የሁለቱ ምክር ቤቶች ልዩነት ታዲያ ምንድነው የቅርጽም የግብርም ልዩነቶች አሏቸው። ዝርዝሩ ብዙ ነው። ለምሳሌ በውክልና ይለያያሉ። ግዛቶች የታህታይ ምክር ቤቱ ውክልናቸው እንደ ሕዝብ ስፋታቸው ይወሰናል። በብዙ የሕዝብ እንደራሴ የሚወከሉ እንደ ካሊፎርኒያ ያሉ ግዛቶች የሚደርሱ ተወካዮች እንዳሏቸው ሁሉ በአንድ አባል የሚወከሉ እንደ አላስካ ያሉ ትንንሽ ግዛቶች ደግሞ አሉ። ዋናው ነጥብ የታህታይ ምክር ቤት ውክልናው በሕዝብ ቁጥር ከመሆኑ ላይ ነው። በላእላይ ምክር ቤት ግን ሁሉም ግዛቶች በሁለት በሁለት አባላት ይወከላሉ። የሕዝብ ቁጥራቸው የተለየ ነገር አያስገኝላቸውም። ሁለቱን ምክር ቤቶች ከሚለይዋቸው ነጥቦች ሌላው የአገልግሎት ዘመን ነው። ሴናተሮች የሚመረጡት ለ ዓመታት እንዲያገለግሉ ነው። የሕዝብ እንደራሴዎች ግን ለሁለት ዓመት። የዘንድሮ ምርጫ ለምን አጓጊ ሆነ የዛሬው ምርጫ በዶናልድ ትራምፕ ላይ የሚካሄድ ሕዝበ ውሳኔ ተደርጎ ተወስዷል። ለምን አንዱ ምክንያት ሁለቱም የምክር ቤት ወንበሮች በሪፐብሊካን ወኪሎች አብላጫ ተይዘው መቆየታቸው ነው። ወንበሮቹ ከሪፐብሊካን እጅ ከወጡ ትራምፕ ጉድ ይፈላባቸዋል። ነገሩ ሁሉ ቅድመ ጥናቶች እንደሚያመላክቱት ከሄደ በትራምፕ የተቆጡ ድምጽ ሰጪዎች በነቂስ ወጥተው ለዲሞክራቶች ድምጻቸውን ሊሰጡ ይችላሉ። ይህ ከሆነ ደግሞ ማንም ሊገምት እንደሚችለው ዶናልድ ትራምፕ ግብታዊ ውሳኔዎቻቸውን ለማጸደቅ ምጥ ይሆንባቸዋል ለምሳሌ ከሜክሲኮ ጋር ድንበር የመገንባቱን ሐሳብ ኮንግረሱ ካላጸደቀው ትራምፕ አንዲት ጡብ ማስቀመጥ አይችሉም። ዲሞክራቶች ቢያሸንፉ ትራምፕ ሊከሰሱ ይችላሉ አያደርጉትም አይባልም። ሰውየው ከራሺያ ጋር በተያያዘ እንዲሁም በሴቶች ላይ በሚሰነዝሯቸው መልካም ያልሆኑ አንደበቶች ተብጠልጥለዋል። እርግጥ ነው እስከዛሬ ዲሞክራቶች ስለ ሰውየው መከሰስ ጉዳይ በይፋ ከመናገር ተቆጥበዋል። እንዲህ ዓይነት ሐሳብ ቢነሳና ፕሬዝዳንቱን የሚያስከስስ ጭብጥ ቢገጥም ግን የክስ ድምጽ ሊሰጡባቸው ይችላሉ። በ እንደ ጎርጎሮሲያዊያኑ ክሊንተን ሕግን በማደናቀፍ ወንጀል እንዲከሰሱ ድምጽ ተሰጥቶባቸው እንደነበር ይታወሳል። በአብላጫ ድምጽ ባያልፍም። አይበለውና ተመሳሳይ ነገር በዶናልድ ትራምፕ ቢነሳና ከመቶ ሴናተሮች ሦስት እጁ ይከሰሱ ብሎ ድምጽ ቢሰጥ አሜሪካ በምክትል ፕሬዚዳንት ማይክ ፔንስ ልትመራ የምትችልበት ዕድል ጠባብ አይደለም። ተያያዥ ርዕሶች
ቢቢሲ ለንደን ከሚገኘው ቢሮ ቀጥሎ ግዙፉን ቢሮውን በናይሮቢ አስመረቀ
ኖቬምበር አጭር የምስል መግለጫ ቢቢሲ ወርልድ ሰርቪስ ከእንግሊዘኛ ውጪ በ ቋንቋዎች ይሰራጫል ቢቢሲ እንግሊዝ ውስጥ ካለው ቢሮው ቀጥሎ እጅግ ግዙፍ የሆነውን ቅርንጫፉን ትላንት በይፋ አስመርቋል። በኬንያ መዲና ናይሮቢ የሚገኘው ዘመነኛ ቢሮው ውስጥ ወደ የሚጠጉ ባለሙያዎች ይሰራሉ። ቢቢሲ በመላው አፍሪካ ወደ ያህል ጋዜጠኞች አሉት። የናይሮቢው የቢቢሲ የምስራቅ አፍሪካ ቅርንጫፍ አማርኛ፣ ትግርኛና ኦሮኦምኛን ጨምሮ ሌሎችም ቋንቋዎች የሚሰራጩበት ነው። የቢቢሲ ኒውስ ዳይሬክተር ፍራንቼስካ አንስወርዝ ትልቁ ኢንቨስትመንታችን በሙያ የላቁ አፍሪካዊ ጋዜጠኞችን ማፍራት ነው ብለዋል። በእንግሊዝ መንግሥት የሚደገፈው የቢቢሲ የማስፋፋፊያ ፕሮጀክት ሚሊየን ዶላር ወጥቶበታል። የሴቶች መብት ታጋይዋ ወይዘሮ መዓዛ አሸናፊ ማን ናቸው አዲስ የተመረቀው ቢሮ፤ የቴሌቭዥን ስቱዲዮ፣ የቀጥታ ስርጭት ማስተላለፊያ፣ ሁለት የራድዮ ስቱድዮ እንዲሁም አምስት የቴሌቭዥን አርትኦት ክፍሎች አሉት። በያዝነው ዓመት መባቻ ላይ በናይጄሪያ የቢዝነስ መዲና ሌጎስ ውስጥ ሌላ የቢቢሲ ቢሮ ተከፍቶ ነበር። ከሌጎስ በኢግቦ፣ በዮሩባና በፒጅን ቋንቋዎች መሰናዶዎች ይሰራጫሉ። የፈረናሳይኛ ቋንቋ ስርጭት የሚተላለፈው ደግሞ በሴኔጋል መዲና ዳካር ከተከፈተው ቅርንጫፍ ነው። ቢቢሲ የናይይሮቢውን ቢሮ የከፈተው እንደ አውሮፓውያኑ በ ነበር። አሁን እንግሊዘኛን ጨምሮ በ ቋንቋዎች መርሀ ግብሮቹን ያስተላልፋል። የቢቢሲ ወርልድ ሰርቪስ የምስራቅ አፍሪካ ኃላፊ ሬቸል አኪዲ ቢሮው ትላንት ሲመረቅ አፍሪካውያን ጋዜጠኞችን እያከበርን ነው። የቢቢሲን የሙያ ስነ ምግባር፣ መድልዎ የሌለበትን ዘገባ እንደያዝን እንቀጥላለን ብለዋል። የአዲሱ ቢሮ መመረቅ መኒ ዴይሊ ከተሰኘው አዲስ መሰናዶ መጀመር ጋርም ገጥሟል። የቢዝነስ መርሀ ግብሩ የሚሰራው ናይሮቢ ውስጥ ነው። አጭር የምስል መግለጫ መኒ ደይሊ ሲሰናዳ አፍሪካ አይ የተባለው የምርመራ ዘገባ መሰናዶ በተጀመሩ በአጭር ጊዜ ከተወደዱ ቅንብሮች አንዱ ነው። በአውሮፓውያኑ የዓለም ዋንጫ ስለ አንድ ዳኛ ጉቦ መብላት የተሰራው ዘገባ የአፍሪካ እግር ኳስ ፌደሬሽን ካፍ በይፋ ምርመራ እንዲጀምር ያነሳሳ ነበር። በወርሀ መስከረም ሁለት ሴቶችና ሁለት ህጻናትን የገደሉ የካሜሩን ወታደሮችን ከጥልቅ ምርመራ በኋላ ይፋ ማውጣቱም ይታወሳል።
በካሜሮን ከ በላይ ተማሪዎችና መምህራን ታገቱ
ኖቬምበር በምዕራብ ካሜሮን በርካታ ተማሪዎችና መምህራን ታግተው መወሰዳቸው ተነገረ። ሰኞ ዕለት ተማሪዎችና ርዕሰ መምህሯን ጨምሮ ሶስት መምህራን በካሜሮን ከምትገኘው ባሜንዳ ታፍነው መወሰዳቸውን የመንግስት ባለስልጣናት ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። ከታገቱት ተማሪዎች መካከል ዕድሜያቸው ከ የሚደርሱ ህፃናት የሚገኙበት ሲሆን ይማሩበት የነበረው ትምህርት ቤትም ፕሪስቤቴሪያን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ይሰኛል። የካሜሮን ጦር ሰራዊትን ያካተተ የፍለጋ ቡድን ልጆቹን ለማግኘት አሰሳ ላይ ነው። የአካባቢው አስተዳደር የሆኑት አዶልፍ ሌሌ ላአፍሪክ ልጆቹን ያገቱት ተገንጣየይ ቡድኖች ናቸው ሲሉ ከስሰዋል። ሁለቱ የእንግሊዘኛ ተናጋሪ ክልሎች ነፃነታቸውን እንዲያገኙ የሚፈልጉ አማፅያን ትምህርት የማቆም አድማ ጠርተው ነበር። ነገር ግን አንድም አማፂ ቡድን ልጆቹን ያገትኩት እኔ ነኝ ሲል ኃላፊነቱን አልወሰደም። ግብፅ የኮፕቲክ ክርስቲያኖች ላይ ጥቃት ያደረሱትን በሞት ቀጣች ከአጋቾቹ በአንዱ እንደተቀረፀ የተገመተ ተንቀሳቃሽ ምስል በማህበራዊ መገናኛ ብዙሃን ላይ እየተንሸራሸረ ይገኛል። በተንቀሳቃሽ ምስሉ ላይ በአንድ ጠባብ ክፍል ተፋፍገው የቆሙ ወንድ ህፃናት ተደናግጠው ካሜራውን የያዘው ግለሰብ ስማቸውን እና የመጡበትን አካባቢ እንዲናገሩ ሲጠይቃቸው ይሰማል። እንዲሁም ትናንት ማታ በአምባ ቦይስ ነው የተወሰድኩት። የት እንዳለሁ አላውቅም የሚል አረፍተ ነገርም ያስደግማቸዋል። አምባ የሚለው መጠሪያ ተገንጣዮቹ ቡድኖች ሊፈጥሩት የሚፈልጉት አምባዞኒያ የተሰኘው ሀገር በአጭሩ ሲጠራ ነው። ከተማሪዎቹ አንዱ የሆነው አልጋ ስር ተደብቆ ሳይያዝ የቀረው ልጅ ለቢቢሲ እንደተናገረው አጋቾቹ ትምህርት ቤቱ ውስጥ ከገቡ በኋላ ነገሮች በፍጥነት ነው የተከናወኑት። አንድ ጓደኛዬን ያለርህራሄ ሲደበድቡት ነበር። ድምፄን አጥፍቼ መቆየት ብቻ ነበር የፈለግሁት። አንዳንዶቹን እንደሚተኩሱና እንደሚመቷቸው ይናገሩ ነበር። ትልልቆቹን ልጆች ከበቧቸው ትንንሾቹን ከኋላ ነበር ያደረጓቸው። በትምህርት ቤቱ መምህርት የሆነችው ደግሞ ወታደሮቹ ወደ ትምህርት ቤቱ ከገቡ በኋላ በቀጥታ ወደ ርዕሰ መምህርቷ ቢሮ አመሩ፤ ከዛም በሩን በኃይል በመገንጠል ገቡ። አሁንም ስብርባሪው አለ ስትል ለቢቢሲ ተናግራለች። በትምህርት ቤቱ እና በአማፂያኑ መካከል አሸማጋይ የሆኑት ግለሰብ ለቢቢሲ እንደተናገሩት፤ አጋቾቹ ምንም አይነት ነገር አይፈልጉም። የጠየቁን ትምህርት ቤቱን እንድንዘጋ ብቻ ነው። ስለዚህ ትምህርት ቤቱን እንደምንዘጋ ቃል ገብተንላቸዋል ብለዋል። ተማሪዎቹንና መምህራኖቹን ይለቋቸዋል ብለን ተስፋ እናደርጋለን ሲሉም አክለዋል። አማፂያኑ በሚንቀሳቀሱባቸው ስፍራዎች ተማሪዎች ሲታገቱ ይህ የመጀመሪያው አይደለም። በቅርብ ጊዜ ውስጥ ከአንድ ትምህርት ቤት ውስጥ ተማሪዎች ታግተው የተወሰዱ ሲሆን አስካሁን ድረስ የደረሱበት አልታወቅም። የካሜሮን አማፅያን እንደሚሉት የሀገሪቱ የትምህርት ስርዓት እንግሊዘኛ ተናጋሪ የሆኑትን ይጨቁናል ሲሉ ይከሳሉ።
ይህንን ለማጋራት በ ዋትስአፕ
ሙዚቃ ጥበብ ነው፤ ስሜት ያድሳል፤ ሕመምን ይሽራል። እንኳን ሰው እንስሳትና እፅዋት በሙዚቃ ይደሰታሉ። ለዚህም ነው ያደጉት አገራት ሙዚቃን አንደ አንድ የሕመም መፈወሻ መድሃኒት እየተጠቀሙበት ያለው። ታዲያ ይህ የሕክምና ጥበብ ወደ እኛ አገርም ተሻግሯል። አሻጋሪው ደግሞ ዶክተር መልካሙ መዓዛ ናቸው። ሙዚቃን ለሰላም በቅዱስ ያሬድ ዘመን ሰዎች ሙዚቃና ቅዳሴን በመጠቀም የታመመ ሰውን ስቃይ በመቀነስ ለታማሚው ምድራዊ ገነትን ለመፍጠር ሲጠቀሙበት እንደነበር በማውሳት ይጀምራሉ ዶ ር መልካሙ። በህዳሴ ዘመን ደግሞ የሙዚቃ ሐኪሞች የስሜታችንና የሰውነታችን ተፈጥሯዊ ለውጦችን ለማምጣት ሙዚቃን ለሳይንሳዊ ጥናት እንደተጠቀሙበት ያስረዳሉ። አሁን ወዳለንበት ክፍለ ዘመን ስንመጣ፤ ሙዚቃና ሕክምና በጣም የተሳሰሩበት በተለይ በምዕራባውያን የጤና ተቋማት ውስጥ ሙዚቃን እንደ ደጋፊ የሕክምና ግብዓት እየተጠቀሙበት ይገኛሉ የሚሉት ዶክተር መልካሙ ሙዚቃ ጤናን አስቀድሞ ለመጠበቅ እና ከህመም ለመዳን አስተዋፅዖው ከፍተኛ እንደሆነ ይገልፃሉ። ዶክተር መልካሙ የሙዚቃ አድናቂ ናቸው። ክራር፣ ጊታር፣ ፒያኖና ቶም የተባሉ የሙዚቃ መሳሪያዎችን ይጫዎታሉ። ድፕ አቢሲኒያ ትራይባል ማጂክ የተሰኘ የሙዚቃ አልበምም አሳትመዋል። የቀዶ ሕክምና ባለሙያ የሆኑት ዶ ር መልካሙ የሙዚቃ ዝንባሌ ያደረባቸው ከዛሬ ስድስት ዓመት በፊት በግላቸው ያጋጠማቸው እንደሆነ ይናገራሉ። ተሞክሯቸውን ለቢቢሲ እንዳጋሩት፤ በሥራቸውና በቤተሰባቸው አካባቢ ችግር ገጥሟቸው ለጭንቀት ተዳርገው ነበር፤ ከዚያም ወደ ሙዚቃ ቀረቡ። የሚነጋገሩትም የሚያዋዩት ሙዚቃን ሆነ። በጊዜ ሒደትም ከገቡበት ስሜት እየተላቀቁ መጡ። በራሳቸው ላይ ለውጥ ካዩ በኋላ ለሌላው ሰው ለመትረፍ አብዝተው ማሰብ ጀመሩ፤ በምዕራቡ ዓለም የተለመደውን የሙዚቃ ሕክምና ሳይንስን ለማጥናትና ዘርፉ ላይ ለመስራት ወሰኑ። የሙዚቃ ሕክምና እንዴት ይሰጣል ዶ ር መዓዛ የሙዚቃ ሕክምና የሚሰጥባቸውን ሁለት መንገዶች ያብራራሉ። የሙዚቃ ሕክምና በተቋማት ያሉ ባለሙያዎች ሙዚቃን በመጠቀም ደጋፊ ወይም አማራጭ ሕክምና የሚሰጡበት ዘዴ ሲሆን ሌላኛው ደግሞ በማህበረሰብ ውስጥ የሚደረግ የሙዚቃ ሕክምና ነው። በማሕበረሰብ ውስጥ የሚደረግ የሙዚቃ ሕክምና በማከም ሳይሆን በመከላከል ደረጃ የሚሰጥ ነው። የሕክምናው ዓይነቱም በየቤቱ ታመው የተቀመጡና ማህበረሰቡ ጋር የማይቀላቀሉ ሰዎች በሕይወታቸው ላይ ተስፋ እንዲኖራቸው ለማድረግ የሚሰጥ የሕክምና ዓይነት እንደሆነ ያብራራሉ። አሁን ግን የጥናት ውጤቶችን መሠረት በማድረግ ሕክምናው ከሌሎች የሕክምና ሙያ ዓይነቶች ጋር ተቀናጅቶ እየተሰጠ መሆኑንም ያክላሉ። አዝማሪዎቻችን የሙዚቃ ሳይንቲስቶች ናቸው የሙዚቃ ህክምናው የእድሜ ገደብ የለውም፤ ለህፃናትም ሆነ ለአዋቂዎች ይሰጣል። በተለይ የአዕምሮ ዕድገት ውስንነት፣ የባህሪ ችግር፣ የአካል ጉዳት፣ የስሜት መረበሽ፣ የመናገር፣ ማየትና መስማት ለተሳናቸው፣ የነርቭ እክል ላጋጠማቸው፣ የቀዶ ህክምና ላደረጉ፣ ለካንሰር ህሙማን፣ የአልኮልና አደንዛዥ ዕፅ ተጠቂ ለሆኑ፣ ወሲባዊ ጥቃት ለደረሰባቸው እንዲሁም የአመጋገብ ችግር ላለባቸው ይሰጣል። በተጨማሪም ለእናቶች በቅድመ ወሊድ፣ በወሊድ ወቅት እንዲሁም ከወሊድ በኋላ እንደ አስፈላጊነቱ ህክምናው ሊሰጥ ይችላል ። ሙዚቃ በአንጎል ውስጥ የሚገኙ ዶፓሚንና ሴሮቶኒን የተባሉ ሆርሞኖች በተለያየ ሁኔታ እንዲመነጩ ስለሚያደርግ በሰው ልጆች ተግባቦት፣ ማህበራዊ መስተጋብር፣ የሰውነት እንቅስቃሴ፣ የስሜት ህዋሳት፣ የሥነ ልቦናና የስሜት ለውጥ ላይ ትልቅ አስተዋፅኦ እንደሚያደርግ ይገልፃሉ። ሕክምናው በዋናነት በግል ወይም በቡድን የተቀዳን ሙዚቃ አሊያም የሙዚቃ ሐኪሞች የሚጫወቱትን ማዳመጥ፣ ማንጎራጎር፣ በግል ወይም በቡድን ሐኪሙ በሚያዘው መሰረት ሙዚቃን መጫወት እና የምት ሪትም እንቅስቃሴ ማድረግ እንደሚያካትት ዶክተሩ ተናግረዋል። የሚያክሙን ሙዚቃዎች ዓይነት ዶክተር መልካሙ እንደገለፁልን ለሙዚቃ ሕክምና የትኛውም ዓይነት ሙዚቃ ጥቅም ላይ አይዉልም። ከዚያ ይልቅ ታካሚው ላጋጠመው የህመም ዓይነት የተዘጋጁ የሙዚቃ ዓይነቶች ያስፈልጋል። ከእነዚህም መካከል ቀደም ብለው የተቀዱ ሙዚቃዎች አሊያም ሐኪሙ በቀጥታ ለታካሚው የሚጫወታቸው ሙዚቃዎች ሊሆኑ ይችላሉ። እነዚህ ሙዚቃዎች ታካሚው እንዳለበት የህመም ዓይነትና እንደሚያስፈልገው ሕክምና በምት፣ በቅጥነት፣ በውፍረት፣ በፍጥነት፣ በድምፅ ከፍታና በተለያዩ ሁኔታዎች ሊዘጋጁ ይችላሉ፤ በገበያ ላይ ከምናውቃቸው ሙዚቃዎች ውስጥ በአብዛኛው ክላሲካል የሚባሉት ሙዚቃዎች ለሕክምና ይውላሉ ይላሉ ዶክተር መልካሙ። የሞዛርትንና የቤትሆቨንን ሙዚቃዎች በመጥቀስ ቆየት ባለው ጊዜ የነበሩት ረቂቅ ክላሲካል ሙዚቃዎች በሰው ልጆች ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ ያሳረፉ ሙዚቃዎች መሆናቸውንም ይናገራሉ። ዝነኛው ኤርትራዊ ድምጻዊ የማነ ባርያ ሲታወስ ባለሙያው እንደሚሉት ጤና ላይ አዎንታዊ ውጤት ያላቸው ሙዚቃዎች እንዳሉ ሁሉ ጤናን የሚያውኩ ሙዚቃዎችም አሉ። እነዚህም ሙዚቃዎች በአጠቃላይ ጠንካራ ምት፣ ንዝረትና ፍጥነት ያላቸው እንደ ሮክ፥ ድራም፥ ባዝና ትራንስ ያሉ የሙዚቃ ዓይነቶች ለጤና ጠንቅ ሊሆኑ እንደሚችሉ ጥናቶች አመልክተዋል። በሰው ልጆች ላይ ብቻ ሳይሆን እንደ እነዚህ ያሉ ሙዚቃዎች የሚሰሙበት አካባቢ ያሉ ዕፅዋቶች ሳይቀሩ እድገታቸው እንደሚቀጭጭ ጥናቶችን ያጣቅሳሉ። የሙዚቃ ሕክምና በኢትዮጵያ ሳይንሳዊ የሆነው የሙዚቃ ሕክምና በኢትዮጵያ ገና በጅማሮ ላይ ያለ ነው። ከቅርብ ዓመታት በፊት ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ጋር በመሆን የሙዚቃ ሕክምናን የሚመለከት አንድ የሥራ ሂደት ተቋቁሞ እንቅስቃሴ መጀመሩን የገለፁልን ዶክተር መልካሙ መዓዛ፤ በገፈርሳ የአዕምሮ ህሙማን ማገገሚያና ማከሚያ ማዕከል ውስጥ በሳምንት ለሦስት ቀናት የሙዚቃ ሕክምና በተለይ የምት እንቅስቃሴ ሕክምና መሰጠት መጀመሩን ገልፀዋል። የማይክል ጃክሰን የአፍጢም ዳንስ ምሥጢር ይሁን እንጂ እንደ ሌሎች ሕክምናዎች ሁሉ የሙዚቃ ሕክምና ባለሙያ ቢያስፈልገውም በሃገር ውስጥ ባለሙያዎች ባለመኖራቸውና በሌሎች ወቅታዊ ምክንያቶች ውጤቱ አርኪ እንዳልነበር ይገልፃሉ። ቢሆንም ግን የተጀመረው እንቅስቃሴ ሕክምናውን ለማስጀመርና በሰዎች ዘንድ ግንዛቤ ለመፍጠር የተደረገ ጥረት እንደሆነ ያምናሉ። እርሳቸው እንደሚሉት እንቅስቃሴው የሙዚቃ ሕክምና ባለሙያን ከውጭ አገር በማስመጣት ድጋፍ እንዲገኝም መንገድን አመቻችቷል። እንግሊዝ አገር ከሚገኝ ሚዩዚክ አዝ ቴራፒ ከተሰኘ ግብረ ሰናይ ድርጅት ጋር በተፈጠረ ግንኙነት የሙዚቃ ሕክምና በባለሙያ የሚታገዝበትን ሁኔታ ለማመቻቸት ዝግጅት እያደረጉ እንደሆነ ዶክተር መልካሙ ነግረውናል። ከዚህ ዜና በተጨማሪ
የማይናማር ግጭትን ለማባባስ ፌስቡክ ጥቅም ላይ መዋሉን ሪፖርት ጠቆመ
ኅዳር የማይናማር ግጭትን ለማባባስ ፌስቡክ ጥቅም ላይ ውሏል ፌስቡክ የማይናማር ግጭትን ለማባባስ ጥቅም ላይ እንዳይውል መከላከል ተስኖታል የሚለውን ሪፖርት ፌስቡክ እንደሚስማማበት ገልጸ። በፌስቡክ የተዋቀረው ገለልተኛ ሪፖርት እንደጠቆመው በማይናማር የመብት ጥሰቶችን እና ግጭቶችን ለማባባስ ፌስቡክ ምቹ ሁኔታ ፈጥሯል። የተባበሩት መንግሥታት፤ በሮሂንጋ ማኅበረሰብ ላይ የደረሰውን ጥቃትና የሰብዓዊ መብት ጥሰት ለዘር ማጥፋት የቀረበ ሲል ፈርጆት ነበር። ፌስቡክ በማይናማር ከ ሚሊዮን በላይ ተጠቃሚዎች አሉት። ፌስቡክ ለበርካቶች ዋነኛው ወይም ብቸኛው የመረጃና የዜና ምንጭ ነው። የፌስቡክ አስተዳደሮች በማይናማር እየገጠመን ያለውን ችግር ለመቅረፍ እየሠራን ነው። ሆኖም ብዙ ይቀረናል ብለዋል። ባለፈው ዓመት የሮሂንጋ ታጣቂዎች ፖሊስ ጣቢያዎች ላይ ጥቃት መሰንዘራቸውን ተከትሎ የሃገሪቱ ጦር ራክሂን በምትባለው ግዛት ላይ መጠነ ሰፊ ጥቃት ሰንዝሮ ነበር። በሺዎች የሚቆጠሩ ህይወታቸውን ሲያጡ፤ ከ ሺህ በላይ ሰዎች ደግሞ ወደ ጎረቤት ሃገር ባንግላዲሽ ተሰደዋል። በሮሂንጋውያን ላይ የአስገድዶ መድፈር፣ የእርሻ መሬትን መቃጠልና መሰል በደሎች ደርሶባቸዋል። በካሜሮን ከ በላይ ተማሪዎችና መምህራን ታገቱ ሮሂንጋውያን በማይናማር በርማ ተብላ ትጠራ በነበረው ሃገር ውስጥ እንደ ስደተኛ ይቆጠራሉ። በመንግሥት እና በተቀረው ሕዝብ ለበርካታ አስረት ዓመታት ተገልለዋል። ቢዝነስ ፎር ሶሻል ሪስፖንሲቢሊቲ ያቀረበው ባለ ገጽ ገለልተኛ ሪፖርት በማይናማር ግጭትና ጥላቻን ማባባስ ለሚፈልጉ ቡድኖች ፌስቡክ መጠቀሚያ ሆኗል ይላል። ሪፖርቱ፤ ፌስቡክ የጥላቻ ንግግርን በተመለከተ ያለውን ፖሊሲ እንደገና ሊከልሰው ይገባል ሲልም አክሏል። ቢቢሲ ማስተባበያ
የሮበርት ኤፍ ኬኔዲ ገዳይ ሲርሃን ሲርሃን እስር ቤት በጩቤ ተወጋ
ሴፕቴምበር ማጋሪያ ምረጥ የህግ ባለሙያና አሜሪካን በጠቅላይ አቃቤ ህግነት ያገለገሉት ሮበርት ኤፍ ኬኔዲ ገዳይ ተብሎ የእድሜ ልክ እስራት ቅጣት እስር ቤት የሚገኘው ሲርሃን ሲርሃን በካሊፎርኒያ እስር ቤት በጩቤ እንደተወጋ የአሜሪካ ሚዲያዎች ዘግበዋል። ባለስልጣናቱ እንዳሳወቁት ግለሰቡ የተወጋው አርብ እለት ሲሆን ጥቃቱም እንደደረሰም የእስር ቤቱ ኃላፊዎች በፍጥነት ምላሽ እንደሰጡ ያወጡት መግለጫ አትቷል። ኢትዮጵያውያን የሌሉበት ስለ ኢትዮጵያ የሚዘክረው ሬድ ሲ ዳይቪንግ ሪዞርት ፊልም መግለጫው ጥቃት የደረሰበትን ግለሰብ ማንነት ከመግለፅ ቢቆጠብም የአሜሪካ በርካታ ሚዲያዎች ከተለያዩ በፍትህ ዘርፉ ከተሰማሩ ምንጮች እንደተረዱት የ አመት እድሜ ባለፀጋው ሲርሃን መሆኑን ነው። ሲርሃን የእድሜ ልክ እስር ተፈርዶበት ሪቻርድ ዶኖቫን በሚባል ማረሚያ ቤት ነው ያለው። ጥቃት የደረሰበት ማረሚያ ቤቱ ላይ ባለ ታሳሪ ሲሆን ጥቃቱንም ተከትሎ ለብቻው እንዲገለል መደረጉንም የጥቃቱን ዜና በመጀመሪያ ያስነበበው ቲኤምዚ ገልጿል። ግለሰቡ ለጥቃቱ ምን እንዳነሳሳው ምክንያቱ እየተመረመረ ሲሆን፤ ባለስልጣናቱም ምንም ከማለት ተቆጥበዋል። ሲርሃን ሲርሃን ማን ናቸው ለአሜሪካ ፕሬዚዳንት እጩነት ቀርበው የነበረውን ሮበርት ኬኔዲ ሎስ አንጀለስ በሚገኘው አምባሳደር ሆቴል በነበሩበት ወቅት ሶስት ጊዜ ሲርሃን ሲርሃን ተኩሶባቸዋል። ወቅቱ በጎርጎሳውያኑ አቆጣጠር ሲሆን በሆቴሉ ማዕድ ቤት የተተኮሰባቸው የቀድሞው የሴኔት አባል ፎበርት ኬኔዲ በወቅቱ ካሊፎርኒያ ላይ የነበረውን የዲሞክራቲክ ፓርቲን ድልን ለደጋፊዎቻቸው እያበሰሩ ነበር ተብሏል።
አትክልት ብቻ ስለሚመገቡ ሰዎች ሊያውቋቸው የሚገቡ ነገሮች
ኖቬምበር ማጋሪያ ምረጥ በዓለም ላይ ምንም አይነት የእንስሳት ተዋጽኦ የማይመገቡ ቪጋን በርካታ ሰዎች አሉ። ምንም እንኳን የእንስሳት ተዋጽኦን አለመመገብ በዓለማችን እየተለመደ የመጣ ቢሆንም፤ የሥጋ ተጠቃሚዎች ቁጥር ደግሞ ከእጥፍ በላይ ነው። በእንግሊዝኛው ቪጋን ተብለው የሚጠሩት ሰዎች ምንም አይነት ሥጋ፣ እንቁላል፣ አሳ ወይም ማር በአጠቃላይ የእንስሳት ሥጋና ከእንስሳት የሚገኙ ምግቦችን አይመገቡም። ምንም አይነት የእንስሳት ተዋጽኦን አለመጠቀም የሚለው እሳቤ ለምግብነት ስለሚጠቀሟቸው ነገሮች ብቻ አይደለም፤ በማንኛውም መልኩ በእንስሳት ላይ የሚፈጸምን ብዝበዛ መቃወምም ያካትታል። ይህ ማለት ደግሞ ከእንስሳት ቆዳ የሚሰሩ አልባሳትን እስካለመጠቀም ድረስ ማለት ነው። ይህንን የህይወት መንገድ ለመከተል ጠበቅ ያለ ውሳኔ ማሳለፍ ይፈልጋል። በአለማችን ከሌላው ጊዜ እጅግ በጨመረ መልኩ ሰዎች ከእንስሳት ተዋጽኦ ነጻ የሆኑ ምግቦችን ለመጠቀም ብዙ ገንዘብ እየከፈሉ ነው። ከተክሎች ጋር የተያያዙ ምግቦችም በበይነ መረብ በመላው ዓለም እየተቸበቸቡ ነው። ማንናውም አይነት የእንስሳት ተዋጽኦ ስለማይመገቡ ሰዎች ሊያውቋቸው የሚገቡ አምስት ነገሮች እነሆ። ታሪካዊ አመጣጥ ምንም አይነት የእንስሳት ተዋጽኦ የማይመገቡ ሰዎች ማህበር የተቋቋመው እ አ አ በ እንግሊዝ ውስጥ ነው። ዋትሰን የተባለ ስጋ የማይመገብ ሰው በስጋ ማቀነባበሪያዎች ውስጥ በእንስሳት ላይ የሚፈጸመውን ግፍ ከተመከለተ በኋላ ነው ይህንን አስተሳሰብ ማራመድ የጀመረው። ምንም አይነት ስጋ ነክ ምግቦችን ያለመመገብ አስተሳሰብ ከመጀመሩ ከ ዓመታት በፊት ግን በጥንታዊ ህንድና ምስራቅ ሜዲትራኒያኒያን አካባቢዎች የተለመደ እንደነበር የታሪክ ተመራማሪዎች ይናገራሉ። ህንድ ውስጥ ከፍተኛ የተከታዯች ቁጥር ያለው ሂንዱይዝም ሃይማኖት እንስሳት በተለይ ላሞች ስጋቸው መበላት እንደሌለበት የሚገልጽ ሲሆን፤ የዚህ ዘመነኛ አስተሳሰብ መነሻ ተደርጎም ይወሰዳል። ቡድሂዝም፣ ሂንዱይዝምና ጃኒዝም የተባሉ ሃይማኖት ተከታዮች ሰዎች ማንኛውም አይነት እንስሳ ላይ ህመም ማድረስ የለባቸውም ብለው ያምናሉ። በ ኛው ክፍለ ዘመን የኖረው ታዋቂው ግሪካዊ ፈላስፋና የሂሳብ ባለሙያ ፓይታጎረስ በእንስሳት ላይ የሚፈጸሙ ግፎችን በእጅጉ ይቃወም ነበር። ወደ ስጋችን ሌላ ስጋ ማስገባት ርኩስነት ነው ብሎ ያምን ነበር። የአንድን ሰው ህይወት ለማስቀጠል የሌላውን ፍጥረት ነፍስ ማጥፋት የወንጀሎች ሁሉ ወንጀል በማለት ሲከራከር ኖሯል። የጤና ጥቅሞቹ በቅርቡ እንግሊዝ ውስጥ በተሰራ ጥናት መሰረት ማንኛውም አይነት የእንስሳት ተዋጽኦ ከማይመገቡ ሰዎች በመቶ የሚሆኑት ለጤና ካለው ጥቅም የተነሳ የአመጋገብ ስርአቱን እንደመረጡ ተናግረዋል። ቀይ ስጋ እና ሌሎች በፋብሪካ የተቀነባበሩ የስጋ ምርቶችን የሚመገቡ ሰዎች ለአንጀት ካንሰር ያላቸው ተጋላጭነት ከፍተኛ መሆኑን ጥናቶች ጠቁመዋል። በአውሮፓውያኑ የዓለም ጤና ድርጅት በፋብሪካ የተቀነባበሩ የስጋ ውጤቶችን ካንሰር ከሚያመጡ ንጥረ ነገሮች መካከል የመደባቸው ሲሆን፤ በፋይበርና ሌሎች ቫይታሚኖች የበለጸጉ አትክልትና ፍራፍሬዎችን መመገብ ደግሞ በካንሰር የመያዝ እድልን በከፍተና ሁኔታ እንደሚቀንሱ ገልጿል። የመንገድ አቅጣጫ እየጠፋብዎ ተቸግረዋል ጠቃሚ ነጥቦች እነሆ ምንም አይነት የእንስሳት ተዋጽኦ የማይመገቡ ሰዎች ከሚመገቡ ሰዎች ጋር ሲነጻጸር የተሻለ ጤናማ ህይወት እንዳላቸው የዘርፉ ባለሙያዎች ይናገራሉ። ነገር ግን እነዚህ ሰዎች ለአጥንት እድገት፣ ለተስተካከል የደም ስርአት፣ ለነርቭ ስርአትና ለአንጎል እድገት የሚጠቅሙ እንደ ቫይታሚን ዲ፣ ቫይታሚን ቢ እና አዮዲን የተባሉ ንጥረ ነገሮችን ማግኘት አይችሉም። ይህንን ለማካካስ ደግሞ ወደ ሰው ሰራሽ እንክብሎች ፊታቸውን ማዞር አለባቸው። እሱም ቢሆን የራሱ የሆነ አሉታዊ ውጤት ይኖረዋል። አካባቢ ላይ ያለው ተጽእኖ አሁን አሁን ይህ የአመጋገብ ስርአት ብዙ ተከታዮችን እያፈራ ቢሆንም በአለማችን ያለው የስጋ ተተቃሚ ቁጥር ግን ከግምት በላይ ነው። እንደ ቻይናና ህንድ ባሉ በቢሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ባሉባቸው ሃገራት ዜጎች የምግብ ፍላጎታቸውን ለማርካት ፊታቸውን ወደ ስጋ እያዞሩ ነው። በቅርቡ የተሰሩ የተባበሩት መንግስታት ሪፖርቶች እንደሚያሳዩት እየጨመረ የመጣው የአለም ህዝብ ቁጥር በምድራችን የተፈጥሮ ሃብቶች ላይ ከፍተኛ ጫና እያሳረፈ ነው። እንደ ሪፖርቶቹ ትንበያ የሰው ልጅ የምግብ ፍላጎቱን ለማርካት እየሄደበት ባለው ሁኔታ አሁን ከሚያመርተው በመቶ ተጨማሪ ምግብ ማምረት ካልቻለ፤ እ አ አ በ ዓለማችን ምግብ አልባ ትሆናለች። በ የተባበሩት መንግስታት የምግብና ግብርና ድርጅት ባወጣው ጥናት መሰረት አካባቢን ከሚበክሉ ግሪንሃውስ ጋሶች በመቶ የሚሆኑት የሚመነጩት የቀንድ ከብቶች ከሚለቁት ሚቴን ከተባለ ጋስ ነው። ይህ ደግሞ እያንዳንዱ መኪና፣ ባቡር፣ አውሮፕላንና መርከቦች ወደ ምድር ከሚለቁት ጋስ ጋር እኩል ነው። ከዚህ በተጨማሪ የስጋ ምርት ብዙ የተፈጥሮ ሃብት ያባክናል። ለምሳሌ ግራም የሚመዝን ቆስጣ ለማደግ ሊትር ውሃ የሚጠቀም ሲሆን፤ ተመሳሳይ ክብደት ያለው ስጋ ግን ሺ ሊትር ውሃ ይፈጃል። የተባበሩት መንግስታ የዓለም ህዝብ ቁጥር ቢሊየን እንደሆነ የሚገምት ሲሆን፤ በ ደግሞ ቢሊየን እንደሚደርስ ግምቱን አስቀምጧል። ምንም እንኳን የተረጋገጠ ቁጥር ማግኘት ባይቻልም የአለም አቀፉ የእንስሳት ተዋጽኦ የማይጠቀሙ ሰዎች ማህበር እንደሚለው ቁጥራቸው ከ እስከ ሚሊየን ሊደርስ ይችላል። አዋጪ የስራ ዘርፍ ቪጋኒዝም ወይም የእንስሳት ተዋጽኦ ያለመጠቀም ባህል አሜሪካ ውስጥ ብቻ በመቶ ያደገ ሲሆን፤ እንግሊዝ ውስጥ ደግሞ በመቶ እድገት አሳይቷል። ይህ ዓለም በአዲስ መልክ እየተከተለችው ያለው የአመጋገብ ስርአት ብዙዎችን እየሳበ ነው። ከስጋ ነጻ የሆኑ ምግቦችን የሚያዘወትሩ ሰዎች ቁጥር በ ብቻ በ ፐርሰንት ያደገ ሲሆን፤ በ ደግሞ በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚጨምር ይጠበቃል። በተለይ ደግሞ ታዋቂ ሰዎችና ስፖርተኞች የሚከተሉትን ጤናማ የአመጋገብ ስርአት በተመለከተ ኢንስታግራም በተባለው የማህበራዊ ሚዲያ የሚያሰፍሯቸው መልእክቶች በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን እየሳቡ ነው። ስለ አንጀታችን የማያውቋቸው ስድስት አስገራሚ እውነታዎች እንደ ኔስሌ ያሉ የዓለማችን ትልልቅ የምግብ አምራች ኩባንያዎችም ፊታቸውን ወደ እነዚህ ሰዎች እያዞሩ ነው። ጀስት ኢት የተባለው የተለያዩ ምግቦችን ሰዎች ባሉበት ድረስ የሚያቀርብ ድርጅት በአንደኛ ደረጃ በደንበኞች የሚታዘዙት ምግቦች ከእንስሳት ተዋጽኦ ነጻ የሆኑት እንደሆኑ ገልጿል። ራዕይ አላቸው ተብለው የሚታሰቡ የስራ ፈጠራ ባለሙያዎችም እውቀታቸውንና ገንዘባቸውን በዚህ ዘርፍ ላይ እያዋሉ ነው። በመጪዎቹ ሁለት ዓመታትም ዘርፉ እስከ ቢሊየን ዶላር ድረስ ሊያንቀሳቅስ እንደሚችል ተገምቷል። ልክ ያለፈ አክራሪነት የቪገኒዝም እንቅስቃሴ ገና ከጅምሩ እንስሳት ፍቅርና ክብር ይገባቸዋል በሚል የተጠነሰሰ ቢሆንም፤ አሁን አሁን የሚታዩ ተግባራት ግን ወደ ማክረሩ የተጠጉና ሌሎችን እስከመከልከል ይደርሳሉ። ብዙ የቀንድ ከብት የሚያረቡ ገበሬዎች በአክራሪዎች ፍርድ ቤት ተከሰዋል፣ ስጋ መሸጫዎች ጥቃት ደርሶባቸዋል፤ እንዲሁም ሰዎች ለምን ስጋ ትመገባላችሁ ተብለው እስከ መገለል ደርሰዋል። ገዳይ ወይም ነፍስ አጥፊ ተብለህ ስትጠራ በጣም ያሳዝናል፤ ያስደነግጣል ትላለች እንግሊዝ ውስጥ በግብርና ስራ የምትተዳደረው አሊሰን ዋግ። ተያያዥ ርዕሶች
በደቡብ ኢትዮጵያ ወላይታ ውስጥ የቢጫ ወባ ወረርሽኝ ሰዎችን ገደለ
ኖቬምበር ማጋሪያ ምረጥ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ በቢጫ ወባ ምክንያት አስር ሰዎች መሞታቸውን ተከትሎ የዓለም ጤና ድርጅት በሽታውን ለመከላከል የሚያግዝ ክትባት እያቀረበ መሆኑን ገለፀ። በዚህ አደገኛ በሆነውና በወባ ትንኝ አማካይነት በሚከሰተው በሽታ ሰዎቹ ህይወታቸውን ያጡ ሲሆን ድርጅቱም ለቢጫ ወባ የሚሆን ክትባት ለአስቸኳይ ጊዜ ካዘጋጀው ክምችቱ በማውጣት እንያቀርበ መሆኑን ሮይተርስ ዘግቧል። ወረርሽኙ በደቡብ ክልል ወላይታ ዞን ከሁለት ወራት በፊት በታመመ አንድ ግለሰብ ላይ የተገኘ ሲሆን፤ የሚሆኑ በቢጫ ወባ ተይዘዋል ተብለው የተጠረጠሩ ሰዎችም ተገኝተዋል። የዓለም ጤና ድርጅት እንዳለው ለበሽታው ባለ ከፍተኛ ተጋላጭነትና በክትባት እጦት ሳቢያ የቢጫ ወባ ወረርሽኝ መከሰቱ አሳሳቢ ሆኗል። በበሽታው የተያዙ ሰዎች ትኩሳት፣ የራስ ምታት፣ የጡንቻ ህመም፣ ማቅለሽለሽ፣ ትውከትና የሰውነት መዛል ምልክቶች የሚታዩባቸው ሲሆን የተወሰኑት ላይ ደግሞ ጠንከር ያሉ የህመም ምልክቶች ይታያሉ። በበሽታው ከተያዙት መካከል ግምሽ የሚሆኑት ከሰባት እስከ አስር ቀናት ባሉት ጊዜያት ውስጥ ይሞታሉ። አትክልት ብቻ ስለሚመገቡ ሰዎች ሊያውቋቸው የሚገቡ ነገሮች በወላይታ ዞን በተከሰተው ይህ የቢጫ ወባ ወረሽኝ ሙሉ ለሙሉ የተመዘገበው ኦፋ ወረዳ ውስጥ ሲሆን ከክስተቱ በኋላ በተካሄደ የመከላከያ ክትባት ዘመቻ ተጨማሪ ሰዎች በበሽታው አለመያዛቸው ተገልጿል። ቢሆንም ግን የዓለም የጤና ድርጅት በከፊል በአካባቢው ባለ ግጭት ምክንያትነት በሽታው ሊስፋፋ የሚችልበት አጋጣሚ ሊኖር እንደሚችል አመልክቷል። ጨምሮም ሚሊዮን የሚደርስ ክትባት በስፋት መካሄድ ላለበት የክትባት ዘመቻ ያለምንም ተጨማሪ መዘግየት እንዲቀርብ እየተደረገ ነው ብሏል። ኢትዮጵያ የቢጫ ወባ በስፋት በሚከሰትበት መልክአ ምድር የምትገኝ ስትሆን እስከ ዎቹ ድረስ ተደጋጋሚ ወረርሽኝ አጋጥሟት ነበር። በፈረንጆቹ በደቡብ ክልል ህሙማን እስከተመመዘገቡበት ክስተት ድረስ ችግሩ እንዳልታየ የዓለም የጤና ድርጅት ሪፖርት አመልክቷል። የቢጫ ወባ መከላከያ ክትባትን ከመደበኛ ክትባቶች ጋር በኢትዮጵያ ውስጥ ከሁለት ዓመታት በኋላ ለመስጠት ዕቅድ አለ። ተያያዥ ርዕሶች
የቤት ውስጥ አየር መበከል ለጤናችን ጠንቅ እንደሚሆን አምስት የመፍትሄ ሃሳቦችን እነሆ
ኅዳር ቤት ውስጥ ሲጋራ ማጨስ የሚያስከትለው ጉዳት ከፍተኛ ነው የአየር ብክለት ለብዙ ሃገራት ፈተና እየሆነ የመጣ ጉዳይ ሲሆን፤ በየዓመቱ እስከ ሰባት ሚሊዮን የሚደርሱ ሰዎች ከዚህ ጋር በተያያዘ ህይወታቸው ያልፋል። አሁን እየኖርንበት ባለው ዓለም ከአስር ሰዎች ዘጠኙ ሲተነፍሱ የሳንባ ካንሰርን ለመሳሰሉ በሽታዎች ይጋለጣሉ። እነዚህ በአይን የማይታዩ በካይ ንጥረ ነገሮች በቤት ውስጥ ስንሆን ደግሞ ጉዳታቸው ከፍተኛ ነው። አዲስ በተሰራ አንድ ጥናት መሰረትም በቤት ውስጥ የሚከሰት ብክለት የሚያደርሰው ጉዳት ከውጪው ጋር ሲነጻጸር ከሁለት እስከ አምስት እጥፍ ይበልጣል። ነገር ግን ይህንን ጉዳት ለመቀነስ የተለያዩ መንገዶችን መጠቀም አሉ። እንዚህ አምስት የመፍትሄ እርምጃዎች በቤት ውስጥ ሊያጋጥመን የሚችልን ብክለት ለመከላከል ጠቃሚ ምክሮኦች ናቸው። አየር እንደልብ እ ን ዲ ዘዋወር ያድርጉ አየር በቤት ውስጥ በደንብ የማይንሸራሸር ከሆነ፤ በካይ ንጥረ ነገሮች በቤት ውስጥ ይቀራሉ። የቤት ውስጥ በሮችና መስኮቶች ቢያንስ በቀን ከሁለት እስከ ሦስት ጊዜ ቢከፈቱና ለሃያ ደቂቃዎች ቤቱ ቢናፈስ፤ በካይ የሆኑት ንጥረ ነገሮች ከአዲሱ አየር ጋር ተቀላቅለው የመውጣት እድላቸው ሰፊ ይሆናል። ከዚህ በተጨማሪም ምግብ ካበሰሉ በኋላና ገላዎትን ከታጠቡ በኋላም ቤትዎን ማናፈስ ተገቢ ነው። የቤትን በርና መስኮት በመክፈት አየር እንዲዘዋወር ማድረግ በ ቤት ውስጥ ተክሎች እንዲኖሮ ያድርጉ ቤትን በአትክልት መሙላት ከሚኖረው ጥቅም በተጨማሪ ለመመልከትም ማራኪ ነው። አንዳንድ ተክሎች በአየር ውስጥ የሚገኙ ጎጂ ንጥረ ነገሮችን የማስወገድ አቅም ያላቸው ሲሆን፤ ካርቦንዳይ ኦክሳይድን አፍኖ በመያዝ ለአካባቢያችንም ከፍተኛ ጠቀሜታን ያበረከታሉ። ነገር ግን በቤታችን ውስጥ የምናስቀምጣቸው ተክሎች እንክብካቤ የማናደርግላቸው ከሆነ፤ እንደውም ጎጂ የሆኑ ንጥረ ነገሮችን ወደ አየር ሊለቁ ይችላሉ። ስለዚህ ሁሌም ቢሆን ሌላው ቢቀር ውሃና ጥሩ አየር እንዲያገኙ ማድረግ ያስፈልጋል። ሽታ ያላቸው ፈሳሾችን ያስወግዱ በማንኛውም ጊዜ በቤት ውስጥ የሚጠቀሟቸው ሽቶዎች፣ ዲኦድራንቶችና የአየር ጠረን መቀየሪያ ምርቶች ትተውት የሚሄዱት ጎጂ ንጥረ ነገር አለ። ይህ ደግሞ ሰውነታችን ላይ በተለይ ደግሞ ሳንባችን ላይ ያለው አሉታዊ ተጽዕኖው ከፍተኛ ነው። የተለያዩ አይነት የቤት ውስጥ ተክሎች መትከል በቤት ውስጥ ሲጋራ አያጭሱ ማጨስ በራሱ ከፍተኛ ጉዳት ያለው ሲሆን፤ ቤት ውስጥ ማጨስ ደግሞ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንደማለት ነው። የሲጋራ ጭስ በቤት ውስጥ ሲጠራቀም በተለይ ደግሞ በሮች ተዘግተው ከሆነ የሚኖረው ጉዳት እንኳን ለማያጨስ ሰው፤ ለሚያጨሰው ሰው በራሱ ከፍተኛ ጉዳት አለው። በቤት ውስጥ ሲጋራ ከሚያጨሱ ቤተሰቦች የሚወለዱ ህጻናት ደግሞ ለድንገተኛ ሞት የተጋለጡ ናቸው።
የላሙ ፕሮጀክት ቦርድ አባላት በኢትዮጵያ ጉብኝት ሊያደርጉ ነው
ሜይ አጭር የምስል መግለጫ አምባሳደር መለስ አለም እና የላሙ ፕሮጀክት ዳይሬክተር ጄኔራል ሲልቪስተር ካሱኩ የላሙ ኮሪዶር ልማት ፕሮጀክት የቦርድ አባላት በኢትዮጵያ ጉብኝት ሊያደርጉ መሆኑን በኬንያ የኢትዮጵያ ኤምሳሲ አስታወቀ። በፕሮጀክቱ ዳይሬክተር ጄኔራል ሲልቪስተር ካሱኩ የሚመራው ይህ የልዑክ ቡድን፤ ከሚያዚያ እስከ ግንቦት ቀን ዓ ም በኢትዮጵያ በሚያደርገው ቆይታ ከተለያዩ የመንግሥት አካላት ጋር ውይይት ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል። በዚህ ጉብኝት ላይ የሚሆኑ አባላት የላሙ ኮርደር ልማት የደረሰበትን ደረጃ በተመለከተ ከኢትዮጵያ የመንግሥት ኃላፊዎች ጋር የሚወያይ ሲሆን በተጨማሪ በኬንያ በኩል የደረሰበትን ደረጃ ማብራሪያ እንደሚያቀርብ ኤምባሲው አስታውቋል። አይ ኤስ በጀነራል ካሊፍ ጦር ላይ ጥቃት ሰነዘርኩ አለ ከኬንያ የውጭ ጉዳይ የኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር፣ የላሙ ጉዳዮች ባለስልጣን እና የሌሎች ተቋሞች ኃላፊዎችን ያከተተው ይህ ቡድን፤ በኢትዮጵያ የሚገኙ የኢንዱስትሪ ፓርኮችን እንደሚጎበኝ ተጠቅሷል። ላሙ ወደብ፣ ደቡብ ሱዳን እና ኢትዮጵያ ትራንስፖርት ኮሪዶር ላፕሴት በምስራቅ አፍሪካ ግዙፍ እና ብዙ ተስፋ የተጣለበት የመሠረተ ልማት ግንባታ ሲሆን፤ ኬንያ፣ ኢትዮጵያ እና ደቡብ ሱዳንን የሚያገናኝ ፕሮጀክት ነው። በፕሮጀክቱ የወደብ እና አየር ማረፊያ ልማት፣ ሦስቱን ሃገራት የሚያገናኙ የባቡር መስመር እና መንገድ ግንባታ፣ እንዲሁም ነዳጅ ማስተላለፊያ ቱቦዎች ዝርጋታ ተካተውበታል። በኬንያ የኢ ፌ ዲ ሪ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር መለስ ዓለም እና የላሙ ፕሮጀክት ዳይሬክተር ጄኔራል በቅርብ በሚመረቀው የላሙ ወደብ የመርከቦች ማቆያ ዙሪያ ተወያይተዋል። የላሙ ወደብ ልማት የአካባቢው አገሮች ኢኮኖሚ ለማስተሳሰር አስፈላጊ በመሆኑ ኢትዮጵያ ለስኬታማነቱ እንደምትሰራ አምባሳደሩ ገልፀውላቸዋል። ዳይሬክትር ጄኔራሉ በላሙ ሦስት የመርከቦች ማቆያ ሥራ እየተፋጠነ መሆኑን ገልፀው ይህም የኢትዮጵያን ተጠቃሚነት ያረጋግጣል ብለዋል። ይህንን ዜና ያጋሩ ስለማጋራት
ለመታሰር ብሎ ሰው የገጨው የእድሜ ልክ እስራት ተፈረደበት
ዲሴምበር መኪና ውስጥ የሚኖረው ግለሰብ ለመታሰር ብሎ ሳይክል ነጂ በመግጨቱ የእድሜ ልክ እስራት ተፈረደበት። ግለሰቡ ሥራ አጥ ሲሆን፤ የሚኖረውም መኪና ውስጥ ነበር። እስር ቤት ለመግባት በማሰብ ሆነ ብሎ በሳይክል የሚጓዝ ሰው ከገጨ በኋላ ነው በጀርመን ፍርድ ቤት የእድሜ ልክ እስራት የተፈረደበት። ባለ ሳይክሉ ክፉኛ ጉዳት ደርሶበታል። ተዋናይቷ ቻርሊዝ ቴሮን እናቷ አባቷን የገደለችበትን ምክንያት ይፋ አደረገች ግለሰቡ በኮምፒውተር ሳይንስ ዘርፍ ውስጥ ይሠራ ነበር። ሥራውን ካጣ በኋላ ግን ያለውን ገንዘብ ባጠቃላይ አውሮፓን በመዞር አባክኖታል። የ ዓመቱ ግለሰብ ሥራ እንዲሁም መኖሪያ ቤትም የለውም። ግለሰቡ ሳይክል ነጂውን ከመግጨቱ በፊት፤ እስር ቤት ቢገባ ሊያገኝ የሚችለውን ጥቅም ሲያጠያይቅ ነበር ተብሏል። ግለሰቡ እስር ቤት ቢገባ፤ መጠለያ እንዲሁም ምግብ እንደሚያገኝም በማሰብ ነበር ባለ ሳይክሉን የገጨው። ፍርድ ቤቱ እንዳለው፤ ግለሰቡ ስግብግብ በመሆኑ የ ዓመቱን ባለ ሳይክል ገጭቷል። ክስ የቀረበበትም በግድያ ሙከራ ነው። የፍርድ ቤቱ ቃል አቀባይ እንዳሉት፤ ግለሰቡ በድርጊቱ ጸጸት ስለተሰማው የጡረታ ገንዘቡን ለባለ ሳይክሉ መታከሚያ ለማዋል ተስማምቷል። ተያያዥ ርዕሶች
ኦክስፎርድ ከዓለማችን ቀዳሚው ዩኒቨርስቲ ተባለ
ሴፕቴምበር ኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ በዓለማችን ካሉ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ሁሉ ለተከታታይ አራትኛ ዓመት ቀዳሚ መሆኑ ተገለፀ። የዓለማችን ግዙፍና ስመጥር የትምህርት ተቋማትን ደረጃ የሚያወጣው ተቋም ካምብሪጅን ሶስተኛ ኢምፔሪያል ኮሌጅ ለንደንን አስረኛ አድርጎ በደረጃ ሰንጠረዡ ላይ አስቀምጧል። ነገር ግን ደረጃውን የሚያወጡ አካላት ሌሎች የዩናይትድ ኪንግደም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከሌላ ሀገር ተቋማት ጋር ባለባቸው ፉክክር የተነሳ ደረጃቸውን ይዘው ለመቆየት እየታገሉ ነው ብለዋል። በአውሮጳ ስመጥር ከሆኑ ዩኒቨርስቲዎች መካከል የጀርመን ዩኒቨርስቲዎች የዩናይትድ ኪንግደም አቻዎቻቸውን በመቀናቀን የበላይነቱን ይይዛሉ ሲሉ ግምታቸው በማስቀመጥ አስጠንቅቀዋል። የሼፎች የበዓል ምግብ ምርጫ፡ ሼፍ ዮሐንስ፣ ጆርዳና እና ዮናስ ኦክስፎርድ ዳግመኛ የዓለማችን ምርጡ ዩኒቨርስቲ በመሆን አንደኛነቱን የተቆናጠጠ ሲሆን በሁለተኛነት ደግሞ ካሊፎርኒያ ኢንስቲትዩት ኦፍ ቴክኖሎጂ ሆኗል። የአሜሪካ ዩኒቨርስቲዎች ከምርጥ አስሮቹ መካከል ሰባቱን በመያዝ የደረጃ ሰንጠረዡን በበላይነት የተቆጣጠሩት ሲሆን ከ ዩኒቨርስቲዎች መካከል ደግሞ ዎቹ የአሜሪካ ዩኒቨርስቲዎች ናቸው። የእሲያ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትም ቢሆኑ የዋዛ አለመሆናቸው ነው የሚነገረው። ቻይናና ጃፓን ጠንካራ ተፎካካሪ በመሆን ብቅ እያሉ መጥተዋል። በዚህ ዓመት ሳትጠበቅ ምርጥ የአለማችን ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ እግሯን ያስገባች ጠንካራ ተፎካካሪ አገር ኢራን ናት። የዓለማችን ምርጥ ዩኒቨርስቲዎች
የቦስኒያ ጦርነት፡ በጦርነት ወድሞ የነበረው አላድዛ መስጊድ ተከፈተ
ሜይ አጭር የምስል መግለጫ አላድዛ መስጊድ ሙሉ በሙሉ ከወደመ ከዓመታት በኋላ እንደገና ተገንብቷል በአውሮፓውያኑ ከ በቦስኒያ በተካሄደው ጦርነት የወደመው የአላድዝ መስጊድ ጥገና ተደርጎለት ከሦስት አስርት ዓመታት በኋላ እንደገና ተከፈተ። ቦስኒያ በሚገኘው በዚህ መስጊድ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በመገኘት የመክፈቻ ሥነ ሥርዓቱን ታድመዋል። በፎካ ከተማ የሚገኘው አላድዛ መስጊድ በቦስኒያ እና ሰርቢያ መካከል የብሔር ግጭት ለመቀስቀስ በማሰብ ነበር ኢላማ የተደረገው። በ ኛው ክፍለዘመን በኦቶማን የኪነ ህንፃ ጠበብቶች የተሠራ እንደሆነ የሚነገርለት መስጊዱ በጦርነቱ ከወደመ በኋላ መልሶ ለመገንባት ዓመታትን የወሰደ ሲሆን ቱርክን ጨምሮ ሌሎች አገራት የገንዘብ ድጋፍ አድርገዋል። በጦርነቱ በፈንጂ እስኪወድምም ድረስ አገልግሎት ይሰጥ ነበር ተብሏል። በፍንዳታው የወደቀው ዋናው የመስጊዱ አካል በድንጋይ የተገነባ ሲሆን በአደጋው የፈራረሱትንና የተዳፈኑት በቁፋሮ እንዲወጡ ተደርገዋል። በጦርነቱ ወቅት በፎካ ከተማ ሰርቢያን ያልሆኑ ሰዎች ግድያ ይፈፀምባቸው ነበር። በዚህም ሳቢያ ይህ አካባቢ ሰርቢንጂ ተብሎ የተሰየመ ሲሆን በአውሮፓውያኑ የቦስኒያ ፍርድ ቤት የቀድሞ ስሟ እንዲመለስላት ውሳኔ አስተላልፈዋል። የቻይና ሙስሊሞች ምድራዊ ጀሐነም ሲጋለጥ ታዲያ በዛሬው ዕለት በቦስኒያ የሚገኙ ህዝበ ሙስሊሞችም የመስጊዱን በድጋሜ መከፈት በድምቀት እያከበሩ ይገኛሉ። ዛሬ ሰዎች በዚህ አካባቢ ሰላም እንዳገኙና ደህንነታቸው እንደተመለሰላቸው ለማየት ችለናል ሲሉ የቡድኑ መሪ ሁሴን ካቫዞቪቸ በዝግጅቱ ላይ ሲናገሩ ተደምጠዋል። የቱርክ የባህል ሚንስትር መህምት ኑሪ ኢርሶይ በበኩላቸው ጥላቻና ዘረኝነት ቁሳቁስን ሊያወድም ይችላል፤ ነገርግን የነበረን ባህልና ኃይማኖት ማጥፋት ግን አይችልም ብለዋል በዝግጅቱ ላይ። በቦስኒያ የአሜሪካ መልዕክተኛም ይህ መስጊድ ለወደፊቱን ትውልድ ተስፋን የሚሰጥና የሚያስተሳስር ነው ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። ባለፈው ዓመት የቀድሞው የቦስኒያ ሰርብ ወታደር ፈንጂ በመቅበር ተሳትፈሃል ተብሎ ክስ እንደቀረበበት ይታወሳል። ፎካ ከተማ ከጦርነቱ በፊት ካላት ሺህ ገደማ የህዝብ ብዛት ግማሽ ያህሉ ሙስሊም ሲሆኑ አሁን ግን ቁጥራቸው ከአንድ ሺህ ያነሰ እንደሆነ ሮይተርስ የዜና ወኪል ዘግቧል። ተያያዥ ርዕሶች
በኢትዮጵያ ሙስሊሞች ስብሰባ የተላለፉ ውሳኔዎች ምንድን ናቸው
ሜይ ማጋሪያ ምረጥ ባለፉት ዓመታት የሙስሊሙ ማኅበረሰብ በእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክርቤት ላይ የተለያዩ ቅሬታዎችን ሲያሰማ ቆይቷል። መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ የተቋቋመውም በዚሁ ምክንያት ነበር። ይህንኑ ተከትሎ ትናንት ሚያዚያ ዓ ም የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የተቋማዊ ለውጥና አንድነት አገር አቀፍ ስብሰባ በሸራተን አዲስ ተካሂዶ ነበር። በስብሰባው ላይም የተለያዩ ውሳኔዎች ተላልፈዋል። የሙስሊም ህብረተሰብ መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ የሆኑት ኡስታዝ ካሚል ሸምሱ በዕለቱ የተደረሱ ስምምነቶችን ገልፀውልናል። ኃላፊው ከዚህ በፊት በመጅሊስ አመራርነት የተቀመጡ ሰዎች ህዝበ ሙስሊሙን የሚወክል አይደሉም፤ በመሆኑም ኃላፊነት ላይ ያሉ ሰዎች ሥልጣናቸውን ይልቀቁ የሚል ጥያቄ ሲቀርብ መቆየቱን ያስታውሳሉ። አመራሮቹ በህጋዊ መንገድ ያልመጡና ሙስሊሙን ማኅበረሰቡን የማይወክሉ ናቸው የሚሉ ጥያቄዎችም ሲቀርቡ ቆይተዋል፤ የተለያዩ ሰላማዊ ሰልፎችም ተካሂደዋል። በመሆኑም ትናንት በተካሄደው ስብሰባ በዋነኝነት በሥልጣን ላይ የነበሩ ሰዎች ስልጣናቸውን መልቀቃቸውን ያረጋገጡበት መሆኑን ኡስታዝ ካሚል ይናገራሉ። መሸፈን የተከለከለባቸውን የዓለም አገራት ያውቃሉ ምርጫ እስከሚካሄድም ድረስ ሙስሊሙን ሕዝብ የሚመራና መሠረታዊ ክንውኖችን የሚፈፅም ቴክኒካል ኮሚቴ መዋቀሩን ገልፀውልናል። በህዝበ ሙስሊሙ ዘንድ መጅሊሱ በኃይማኖት አባቶች መመራት አለበት የሚል አቋም የነበር በመሆኑ የሚሆኑ ኡለማዎች የኃይማኖት አባቶች ተመርጠው ከነበረው ዘጠኝ ኮሚቴ ሥልጣኑን ተረክበዋል። ህዝበ ሙስሊሙ ከዚህ በኋላ ጎራ ለይቶ፤ ከዚህኛው ነኝ፤ ከዚያው ነኝ ማለት አያስፈልግም፤ ሁሉም በኃይማኖቱ ለሃገሩ ለመስራት ቃል ተገጋብተዋል ብለዋል ኡስታዝ ካሚል ሸምሱ። ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድም በስብሰባው ላይ ተገኝተው የነበረ ሲሆን ጠንካራ የሙስሊም ማህበረሰብ ለሃገር አንድነት መሠረት ነው ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። የሰላም ሚንስተር ወ ሮ ሙፈሪያት ካሚልም ለተደረገው የመቀራረብ ሂደት የሰላም ቁርጠኝነት ለተሳታፊዎቹ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። ወደፊት ምን ይጠበቃል ይህ ስብሰባ ለህዝበ ሙስሊሙ የዓመታት ጥያቄ ምላሽ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል። ከስብሰባው ተሳታፊዎች አንዷ ሙኒራ አብዱልመናን የምትጠብቃቸውን ለውጦች እንዲህ ትገልፃለች። እርሷ እንደምትለው መጅሊስ ውስጥ የተንሰራፋውን የሙስና አሰራር በማፅዳት ትልቁን ድርሻ ይይዛል። መጅሊሱ የሚያገኛቸው ገቢዎች አሉት ከመስጊድ ሱቆች ኪራእ እንዲሁም ከሃጂ ገቢ ይገኛል ነገር ግን መስጂዶች አሁንም ከምዕመን ተለምኖ ነው የመብራትና ውሃ የሚከፈለው ይህ ብልሹ አሰራር ይስተካከላል ብዬ እጠብቃለሁ ብላለች። የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች እንግልት በመካ የመጅሊሱ አስተዳደሮች ተጠሪነታቸው ለሙስሊሙ ማህበረሰብ እንጂ ለመንግስት ወይም ለፖለቲካ ተጠቃሚነት መሆን እንደሌለብትም ገልፃለች። በአዲሱ አወቃቀር የተለያዩ የተቋቋሙ የወጣቶችና የሴቶች ዳሬክተሮች መቋቋማቸውንና በተቻለ ፍጥነት እንሱን ወደ ስራ ማስገባት በትምህርትም በስነ ምግባርም ኃይማኖታዊ ስርዓትን ለማስተካከል ትልቅ እርምጃ ለማድረግ እንደሚረዳ ትገልፃለች።
በአሜሪካ የምክር ቤት ምርጫ ዲሞክራቶች ቢያሸንፉ ትራምፕ ሊከሰሱ ይችላሉ
ኅዳር የአሜሪካ ምርጫ ማብቂያ ያለው አይመስልም። ለጊዜው ዋና ዋና ነጥቦችን ብናነሳ አይከፋም። የ ሚድ ተርም ምርጫ ምንድነው ሚድ ተርም የተባለው መሀል ላይ ስለሚካሄድ ነው። ለአራት ዓመት እንዲያገለግል የተመረጠው ፕሬዚዳንት ሁለት ዓመት እንደቆየ የሥራ ዘመኑ ይጋመሳል። በዚህ ወቅት ሚድ ተርም ምርጫ ይከሰታል። ምርጫው ታዲያ በአራት ዓመት አንድ ጊዜ በወርሃ ኖቬምበር ኅዳር ነው የሚካሄደው። ምን ዓይነት ምርጫ ነው የአሜሪካ ምክር ቤት ላዕላይና ታህታይ ምክር ቤቶች አሉት፤ የአማርኛ ስያሜያቸው ሊያከራክር ቢችልም። ታህታዩ ምክር ቤት የሕዝብ እንደራሴዎች ሲኖሩት ሀውስ ኦፍ ሪፕረዘንታቲቭስ ይባላል፤ ላዕላዩ ምክር ቤት አባላት ሲኖሩት ተመራጮቹ ሴናተሮች ተብለው ይጠራሉ። የኅብረት ስማቸው ኮንግረስ ነው። ይህ ሕግ አውጪ ምክር ቤት በድምሩ አባላት ይኖሩታል። በደፈናው አንድ ረቂቅ ሕግ ከላዕላዩም ከታህታዩም ምክር ቤት ሊመነጭ ይችላል ማለት እንችላለን። የሁለቱ ምክር ቤቶች ልዩነት ታዲያ ምንድነው የቅርጽም የግብርም ልዩነቶች አሏቸው። ዝርዝሩ ብዙ ነው። ለምሳሌ በውክልና ይለያያሉ። ግዛቶች የታህታይ ምክር ቤቱ ውክልናቸው እንደ ሕዝብ ስፋታቸው ይወሰናል። በብዙ የሕዝብ እንደራሴ የሚወከሉ እንደ ካሊፎርኒያ ያሉ ግዛቶች የሚደርሱ ተወካዮች እንዳሏቸው ሁሉ በአንድ አባል የሚወከሉ እንደ አላስካ ያሉ ትንንሽ ግዛቶች ደግሞ አሉ። ዋናው ነጥብ የታህታይ ምክር ቤት ውክልናው በሕዝብ ቁጥር ከመሆኑ ላይ ነው። በላእላይ ምክር ቤት ግን ሁሉም ግዛቶች በሁለት በሁለት አባላት ይወከላሉ። የሕዝብ ቁጥራቸው የተለየ ነገር አያስገኝላቸውም። ሁለቱን ምክር ቤቶች ከሚለይዋቸው ነጥቦች ሌላው የአገልግሎት ዘመን ነው። ሴናተሮች የሚመረጡት ለ ዓመታት እንዲያገለግሉ ነው። የሕዝብ እንደራሴዎች ግን ለሁለት ዓመት። የዘንድሮ ምርጫ ለምን አጓጊ ሆነ የዛሬው ምርጫ በዶናልድ ትራምፕ ላይ የሚካሄድ ሕዝበ ውሳኔ ተደርጎ ተወስዷል። ለምን አንዱ ምክንያት ሁለቱም የምክር ቤት ወንበሮች በሪፐብሊካን ወኪሎች አብላጫ ተይዘው መቆየታቸው ነው። ወንበሮቹ ከሪፐብሊካን እጅ ከወጡ ትራምፕ ጉድ ይፈላባቸዋል። ነገሩ ሁሉ ቅድመ ጥናቶች እንደሚያመላክቱት ከሄደ በትራምፕ የተቆጡ ድምጽ ሰጪዎች በነቂስ ወጥተው ለዲሞክራቶች ድምጻቸውን ሊሰጡ ይችላሉ። ይህ ከሆነ ደግሞ ማንም ሊገምት እንደሚችለው ዶናልድ ትራምፕ ግብታዊ ውሳኔዎቻቸውን ለማጸደቅ ምጥ ይሆንባቸዋል ለምሳሌ ከሜክሲኮ ጋር ድንበር የመገንባቱን ሐሳብ ኮንግረሱ ካላጸደቀው ትራምፕ አንዲት ጡብ ማስቀመጥ አይችሉም። ዲሞክራቶች ቢያሸንፉ ትራምፕ ሊከሰሱ ይችላሉ አያደርጉትም አይባልም። ሰውየው ከራሺያ ጋር በተያያዘ እንዲሁም በሴቶች ላይ በሚሰነዝሯቸው መልካም ያልሆኑ አንደበቶች ተብጠልጥለዋል። እርግጥ ነው እስከዛሬ ዲሞክራቶች ስለ ሰውየው መከሰስ ጉዳይ በይፋ ከመናገር ተቆጥበዋል። እንዲህ ዓይነት ሐሳብ ቢነሳና ፕሬዝዳንቱን የሚያስከስስ ጭብጥ ቢገጥም ግን የክስ ድምጽ ሊሰጡባቸው ይችላሉ። በ እንደ ጎርጎሮሲያዊያኑ ክሊንተን ሕግን በማደናቀፍ ወንጀል እንዲከሰሱ ድምጽ ተሰጥቶባቸው እንደነበር ይታወሳል። በአብላጫ ድምጽ ባያልፍም። አይበለውና ተመሳሳይ ነገር በዶናልድ ትራምፕ ቢነሳና ከመቶ ሴናተሮች ሦስት እጁ ይከሰሱ ብሎ ድምጽ ቢሰጥ አሜሪካ በምክትል ፕሬዚዳንት ማይክ ፔንስ ልትመራ የምትችልበት ዕድል ጠባብ አይደለም። ከዚህ ዜና በተጨማሪ
ቢቢሲ ለንደን ከሚገኘው ቢሮ ቀጥሎ ግዙፉን ቢሮውን በናይሮቢ አስመረቀ
ኅዳር ቢቢሲ ወርልድ ሰርቪስ ከእንግሊዘኛ ውጪ በ ቋንቋዎች ይሰራጫል ቢቢሲ እንግሊዝ ውስጥ ካለው ቢሮው ቀጥሎ እጅግ ግዙፍ የሆነውን ቅርንጫፉን ትላንት በይፋ አስመርቋል። በኬንያ መዲና ናይሮቢ የሚገኘው ዘመነኛ ቢሮው ውስጥ ወደ የሚጠጉ ባለሙያዎች ይሰራሉ። ቢቢሲ በመላው አፍሪካ ወደ ያህል ጋዜጠኞች አሉት። የናይሮቢው የቢቢሲ የምስራቅ አፍሪካ ቅርንጫፍ አማርኛ፣ ትግርኛና ኦሮኦምኛን ጨምሮ ሌሎችም ቋንቋዎች የሚሰራጩበት ነው። የቢቢሲ ኒውስ ዳይሬክተር ፍራንቼስካ አንስወርዝ ትልቁ ኢንቨስትመንታችን በሙያ የላቁ አፍሪካዊ ጋዜጠኞችን ማፍራት ነው ብለዋል። በእንግሊዝ መንግሥት የሚደገፈው የቢቢሲ የማስፋፋፊያ ፕሮጀክት ሚሊየን ዶላር ወጥቶበታል። የሴቶች መብት ታጋይዋ ወይዘሮ መዓዛ አሸናፊ ማን ናቸው አዲስ የተመረቀው ቢሮ፤ የቴሌቭዥን ስቱዲዮ፣ የቀጥታ ስርጭት ማስተላለፊያ፣ ሁለት የራድዮ ስቱድዮ እንዲሁም አምስት የቴሌቭዥን አርትኦት ክፍሎች አሉት። በያዝነው ዓመት መባቻ ላይ በናይጄሪያ የቢዝነስ መዲና ሌጎስ ውስጥ ሌላ የቢቢሲ ቢሮ ተከፍቶ ነበር። ከሌጎስ በኢግቦ፣ በዮሩባና በፒጅን ቋንቋዎች መሰናዶዎች ይሰራጫሉ። የፈረናሳይኛ ቋንቋ ስርጭት የሚተላለፈው ደግሞ በሴኔጋል መዲና ዳካር ከተከፈተው ቅርንጫፍ ነው። ቢቢሲ የናይይሮቢውን ቢሮ የከፈተው እንደ አውሮፓውያኑ በ ነበር። አሁን እንግሊዘኛን ጨምሮ በ ቋንቋዎች መርሀ ግብሮቹን ያስተላልፋል። የቢቢሲ ወርልድ ሰርቪስ የምስራቅ አፍሪካ ኃላፊ ሬቸል አኪዲ ቢሮው ትላንት ሲመረቅ አፍሪካውያን ጋዜጠኞችን እያከበርን ነው። የቢቢሲን የሙያ ስነ ምግባር፣ መድልዎ የሌለበትን ዘገባ እንደያዝን እንቀጥላለን ብለዋል። የአዲሱ ቢሮ መመረቅ መኒ ዴይሊ ከተሰኘው አዲስ መሰናዶ መጀመር ጋርም ገጥሟል። የቢዝነስ መርሀ ግብሩ የሚሰራው ናይሮቢ ውስጥ ነው። መኒ ደይሊ ሲሰናዳ አፍሪካ አይ የተባለው የምርመራ ዘገባ መሰናዶ በተጀመሩ በአጭር ጊዜ ከተወደዱ ቅንብሮች አንዱ ነው። በአውሮፓውያኑ የዓለም ዋንጫ ስለ አንድ ዳኛ ጉቦ መብላት የተሰራው ዘገባ የአፍሪካ እግር ኳስ ፌደሬሽን ካፍ በይፋ ምርመራ እንዲጀምር ያነሳሳ ነበር። በወርሀ መስከረም ሁለት ሴቶችና ሁለት ህጻናትን የገደሉ የካሜሩን ወታደሮችን ከጥልቅ ምርመራ በኋላ ይፋ ማውጣቱም ይታወሳል።
ሌሎች ሴቶች ላይ የአሲድ ጥቃት ሳይ ይረብሸኛል፤ ህመሜን ያስታውሰኛል ካሚላት መህዲ
ኖቬምበር ስለ ማጋራት ተጨማሪ ያጋሩ ማጋሪያ ምረጥ የ ዓም የገና ዋዜማ ለካሚላት መህዲ እና ለቤተሰቦቿ መልካም ነገር ይዞ አልመጣም። በካሚላትና በእህቶቿ ላይ የደረሰው ብዙዎችን ያስደነገጠ፤ የኢትዮጵያውያንን ልብም በጋራ ቀጥ ያደረገ የካሚላትን ሕይወት ደግሞ የቀየረ ነበር። ካሚላት መህዲ በ ዓ ም የገና ዋዜማ ከእህቶቿ ጋር ከምትሰራበት ሱቅ አምሽታ ወደ ቤቷ ስትሄድ አንድ ሰው ወደ አጠገባቸው መጥቶ አሲድ ፊቷ ላይ ደፍቶ መሰወሩን በወቅቱ መገናኛ ብዙኃን ዘግበውታል። አዲሷ የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ማን ናቸው ካሚላት በወቅቱ በደረሰባት የፊት መቃጠል ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባት ሲሆን በተለያዩ ሆስፒታሎች ህክምና ቢደረግላትም ቃጠሎው ከፍተኛ ስለነበር ከሀገር ወጥታ መታከም እንዳለበት ተገለፀ። ጥቃቱን የፈፀመውም ግለሰብ በቁጥጥር ሥር ዋለ። ከዚያ በኋላ ካሚላት በሼህ መሀመድ አሊ አላሙዲ ድጋፍ በፈረንሳይ ሀገር ሕክምና ለማግኘት ሄደች። ከዚህ የህክምና ጉዞ በኋላ አልፎ አልፎ በመገናኛ ብዙኃን ላይ ስለእርሷ ቢሰማም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ታይታ አታውቅም። በዚህ ሳምንት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ወደ ፈረንሳይ ባመሩበት ወቅት በአየር መንገድ በመገኘት አቀባበል ካደረጉት የተለያዩ ሰዎች ምስል መካከል የካሚላትም አብሮ ታየ። ይሄኔ የካሚላት ጉዳይ ለማህበራዊ ሚዲያው መነጋገሪያ ሆነ። ካሚላት ፈረንሳይ ጠቅልላ መኖር ከጀመረች ስድስት ዓመት ሆኗታል። ባለትዳርና የአንድ ልጅ እናትም ሆናለች። ቢቢሲ አማርኛ፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ወደ ፈረንሳይ እንደሚመጡ ስትሰሚ ምን ተሰማሽ ካሚላት፡ ደስ የሚል ስሜት ነው የተሰማኝ። እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ አንድ ቅን የሆነ መንግሥት ወዳለህበት ሊያይህ ሲመጣ የሚሰማህ ስሜት ነው የተሰማኝ። ቢቢሲ አማርኛ፡አየር መንገድ አቀባበል ከሚያደርጉት ሰዎች መካከል እንድትሆኚ እንዴት ተመረጥሽ ካሚላት፡ እዚህ ለእርሳቸው አቀባበል የተቋቋመ ጊዜያዊ ኮሚቴ ነበር። ዲያስፖራው ከኤምባሲው ጋር በመሆን ማለት ነው። እዛ ላይ ነው የመረጡኝ። እና ተመርጠሻል ሲሉኝ በደስታ ተቀበልኩኝ። ከኤለን ጆንሰን ሰርሊፍ እስከ ሣህለወርቅ ዘውዴ ቢቢሲ አማርኛ፡ለኤምባሲው ቅርብ ነሽ ማለት ነው። ካሚላት፡ ማለት ሁላችንም እዚህ ያለን ኢትዮጵያዊ ኤምባሲ የሚያስፈልገን ሲኖር እንሄዳለን፤ እንጠይቃለን። ከኤምባሲው በተሻለ እዚህ ካሉ ኢትዮጵያውያን ውስጥ ጥሩ ቦታ አለኝ። እኔም ለሰዉ ያለኝ አመለካከት ተመሳሳይ ነው። ቢቢሲ አማርኛ፡ጠቅላይ ሚኒስትሩ አየር መንገድ ሲያገኙሽ ምን አሉ ካሚላት፡ በጊዜው ሰላምታ ብቻ ነው የተለዋወጥነው። በጣም እንደተሰማቸው ያስታውቅ ነበር። እዛ ሰዓት ላይ ግን ምንም መነጋገር አትችልም ነበር። ይበርድ ነበር።ጊዜውም አጭር ነበር። ሰላምታ ብቻ ነው የተለዋወጥነው። ቢቢሲ አማርኛ፡ከዛ በኋላ የማውራት ጊዜ አላገኛችሁም። ካሚላት፡ አላገኘንም። ቢቢሲ አማርኛ፡ፈረንሳይ ኑሮሽን አድርገሻል። ሰዎች ሲያዩሽ ምን ሆነሽ ነው ብለው አይጠይቁም። ካሚላት፡ ይጠይቃሉ። መጀመሪያ ፊታቸው ላይ የምታየው ነገር ይኖራል። ከዛ በትህትና ይጠይቁሃል። እና እነግራቸዋለሁ። ቢቢሲ አማርኛ፡ሁሌ መጠየቅ አይረብሽሽም ካሚላት፡ አይረብሸኝም አልልህም ይረብሻል። ቢቢሲ አማርኛ፡ አሁን አግብተሻል ወልደሻል ኑሮ እንዴት ነው ካሚላት፡ ማግባት፣ መውለድ በጣም ደስ ይላል። ድርብ ኃላፊነት ነው። ኢትዮጵያ መጥቼ ካገባሁ በኋላ ልጄን እዚህ ፈረንሳይ ተመልሼ ነው የወለድኩት። ባለቤቴ ግን አሁንም ኢትዮጵያ ነው ያለው አልመጣም። እና ልጄን ብቻዬን ነው የማሳድገው። ቢቢሲ አማርኛ፡ልጅሽ ወንድ ነው ሴት ካሚላት ወንድ ልጅ ነው፤ አራት ዓመት ሞልቶታል። ቢቢሲ አማርኛ፡ እና ፈረንሳይ ሕይወት እንዴት ነው ካሚላት ደስ ይላል ጥሩ ነው። በርግጥ እንደ ኢትዮጵያ አይደለም። ልጅ ስታሳድግ ብቻህን ነው። የምሄድበት ሁሉ ይዤው ነው የምዞረው። በተጨማሪም ባለቤቴ እዚህ ስላልሆነ የሕክምናዬን ነገር ለጊዜው ገታ አድርጌ ልጄን ማሳደግ ላይ አተኩሬያለሁ። ያው እርሱ ሲመጣ ወደ ሕክምናዬ ተመልሼ እገባለሁ። ቢቢሲ አማርኛ፡ ሕክምናው አላለቀም ማለት ነው ካሚላት፡ አላለቀም እንዳየኸኝ ነው አይደል ያለሁት፤ ስለዚህ አላለቀም። ቢቢሲ አማርኛ፡ ሕክምናው ረዥም ጊዜ ይፈጃል ማለት ነው ካሚላት፡አዎ ቢቢሲ አማርኛ፡ አሁንም ወጪውን ማን ነው የሚሸፍነው ካሚላት፡ በፊት በነበረው ሁኔታ ለአንድ ዓመት በሼክ መሀመድ አሊ አላሙዲ ወጪ ስታከም ነው የነበረው። እዚህ ጠቅልዬ ከመጣሁ በኋላ የፈረንሳይ መንግስት ነው የሕክምና ወጪዬን የሚሸፍነው። ቢቢሲ አማርኛ፡ ልጅሽ ግን ይጠይቅሻል ምን እንደደረሰብሽ ካሚላት፡ ፈገግታ እርሱ ነገር ትንሽ ከባድ ነው። ገና መጠየቅ አልጀመረም። ያው እናት እናት ናት ታውቃለህ። ወደፊት ሳስብ ግን ትንሽ የሚያስጨንቀኝ እርሱ ነው። በምን መልኩ ላስረዳው እንደምችል አላውቅም። ትንሽ ይከብዳል። በፊት ያለኝ ስሜትና አሁን ልጅ ሲኖረኝ ያለኝ ስሜት የተለያየ ነው። ቢቢሲ አማርኛ፡ ሴት ልጅ ብወልድ እንዲህ አይነት ጥቃት ሊደርስባት ይችላል ብለሽ ትሰጊያለሽ ካሚላት፡ አይ ስለነገ አላህ ነው የሚያውቀው። እንደዛ ብዬ ማሰብ አልፈልግም። በአሁኑ ሰዓት የሚጠቃው ወንዱም ሴቱም ነው። ስጋቱ ጾታ ለይቶ ብቻ ሳይሆን የትኛውም ጾታ ላይ ስጋት ይኖርሃል። ቢቢሲ አማርኛ፡በወቅቱ አንቺ ላይ ጥቃት ሲደርስ እህትሽም ላይ ነበር ጥቃት የደረሰው አሁን በምን ሁኔታ ላይ ነች ካሚላት፡ አንዷ ብቻ ሳትሆን ሁለት ናቸው ከኔ ጋር ሆነው ጥቃት የደረሰባቸው። በጊዜው ሕክምና አድርገዋል።አሁን የየራሳቸውን ኑሮ እየኖሩ ነው። ቤተሰቤ አዲስ አበባ ነው ያለው። ቤተሰብ ሁል ጊዜ ሲያዝን ሲሰጋ ነው የሚኖረው።ስጋት ስልህ ከመፍራት አንፃር ሳይሆን ለኔ ይኼ ነገር ባይደርስ ይመርጣሉ። የትም ቦታ ሲያዩህ ከአንተ የበለጠ እነርሱ ናቸው ልባቸው የሚሰበረው። በርግጥ የኔ ማግባት መውለድ እናት አባቴን ቀና ሊያደርግ ይችላል። ምንም ቢሆን ግን ቤተሰብ ናቸውና ሁል ጊዜ አንደተጎዱ ነው። የእነርሱን ጉዳት መቀየር ብችል ደስ ይለኛል። ቢቢሲ አማርኛ፡ሰዎች ጠቅላይ ሚኒስትሩን አየር መንገድ ስትቀበይ ሲያዩሽ የድሮውን ምስልሽን አውጥተው ማጋራት ጀመሩ። ቤተሰቦችሽ ጋር የድሮ ፎቶዎችሽ አልበሙ ውስጥ አለ። ቤት ውስጥ ያንን ምስል እያዩስ የመረበሽ ነገር አለ ካሚላት፡ ቤተሰቦቼ እነዛን ፎቶዎች እንዳያቸው አይፈልጉም። እነርሱም እንዲረበሹበት አናደርግም። በርግጥ እንደዚህ ሰዎች በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ሲያጋሩት ይረብሻል። ለቤተሰብ ብቻ ሳይሆን ለሌላውም። እነዛ ፎቶዎች ለትውስታ መውጣታቸው ጥሩ ቢመስልም እኛ ቤተሰብ ጋር ግን ሁሌ ረብሻ ይፈጥራል። አሁን ደግሞ ልጅ አለኝ። ልጄ ላይ ወደፊት ተፅዕኖ ሊፈጥር ይችላል። ቢቢሲ አማርኛ፡አንቺ ላይ ጥቃት ከደረሰ በኋላ የተለያዩ ሴቶች ላይ ጥቃት ደርሶ ሰምተናል ፤ አንቺ እነዚህን ነገሮች ስትሰሚ የሚፈጥርብሽ ነገር ምንድን ነው ካሚላት፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፍራንክፈርት በአውሮጳ የምንገኝ ኢትዮጵያውያንን ሰብስበው ሲያናግሩ ጥያቄ ያቀረብኩት ይህንን የሚመለከት ነው። የኔ ጥቃት እንደ ዋዛ እንደ ተራ ነገር ሆኖ ለሌሎቹ መጥፎ ምሳሌ ሆኗል። አሁን አሲድ ጥቃት እንደ ፌዝ ነገር ሆኖ የአይን ብርሀንን እስከማጥፋት ደርሷል። ያንን ሳይ የበለጠ በጣም ነው የሚሰማኝ። ምክንያቱም አንተ ላይ ሲሆን የሚሰማህን ስሜት ትቀበለዋለህ። ሌሎች ላይ ሆኖ ሳየው ግን ወደ ስሜቴ እመለሳለሁ። ሕመሜን መልሶ እንዳስታውሰው ያደርገኛል። ይህ በጣም ነው የሚረብሸኝ። ከዚህ አንፃር ነበር ጥያቄ ያነሳሁት። ቢቢሲ አማርኛ፡ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ሴት የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ሾመዋል። ለኢትዮጵያ ሴቶች ፍትህን በማግኘት ረገድ ለውጥ ይኖራል ብለሽ ተስፋ ታደርጊያለሽ ካሚላት፡ ኢንሻ አላህ። ሴት ሚኒስትሮች አሉን። ፕሬዝዳንታችን ሴት ናቸው። አሁን ደግሞ ሴት የከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት አግኝተናል። በጣም የሚያስደስት ነው።ለውጥ ይመጣል ብዬ አስባለሁ። ምክንያቱም ሁሉም ሰው ለውጥ የሚፈልግ ይመስለኛል። ተስፋ አደርጋለሁም ብዙ እጠብቃለሁም። ቢቢሲ አማርኛ፡ አንቺ ላይ ለደረሰው ጥቃት የተሰጠው ፍርድ አነስተኛ ነው በማለት ተሰምቶሽ ያውቃል ካሚላት፡ አዎ በርግጥ በወቅቱ የኢትዮጵያ ሕዝብ በአንድ ድምፅ ተረባርቦልኛል። የተለመደ አይነት ጥቃትም ስላልነበር ሁሉም ሰው ተረባርቧል። ከኔ የበለጠ ሰዉ ነበር ሆ ብሎ የወጣው። ፍርዱ ራሱ ከፍ ያለ ነበር የተሰጠው። የሞት ፍርድ። በኋላ ላይ ነው በይግባኝ የተቀነሰው። እንደገና የሴቶች ጉዳይ አቤት ብሎ ነው እድሜ ልክ ወይንም ዓመት የሆነው። እኔ የማየው ይህ ነገር በሰዓቱ የማያዳግም ውሳኔ ቢወሰን ኖሮ ዛሬ በአሲድ የተጠቃን ሴቶች አንበረክትም ነበር እላለሁ። ለኔ ብቻ ሳይሆን ለሕብረተሰባችን ብሎ ነበር ፍርድ መሰጠት የነበረበት። አሁንም የማያዳግም ቅጣት እስካልተወሰነ ድረስ ይህ ነገር መቀጠሉ አይቀርም። ቢቢሲ አማርኛ፡የሴቶች ጥቃትን ለማስቆም የሚሰራ ትምህርት የሚሰጥ ተቋም የመመስረት ሀሳብ የለሽም ካሚላት፡ አለኝ። አሁን ራሱ እዚህ ፈረንሳይ ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን ጋር ሉሲ ወይም ድንቅነሽ የሚሰኝ ማህበር አቋቁመን እየተንቀሳቀስን ነው። ቢቢሲ አማርኛ፡መቼ ነው ወደ ኢትዮጵያ የምትመጪው ካሚላት፡ ኢንሻ አላህ እኔ ከምመጣ የባለቤቴ መምጫ ቢፈጥንልኝ ይሻላል ሳቅ ተያያዥ ርዕሶች
በኢትዮጵያ የሚገኙ ቤተ እስራኤላውያን ወደ ተስፋይቱ ምድር ፅዮን ውሰዱን ተማፅኖ
ኖቬምበር ማጋሪያ ምረጥ ሰሞኑን በኢትዮጵያ የሚገኙ ቤተ እስራኤላውያን ላምበረት በሚገኘው ምኩራባቸው የእስራኤል መንግሥት የገባልን ቃል አላከበረም በሚል የፀሎት አድማ አካሂደዋል። ወደ እስራኤል እንዲመለሱ ከሶስት አመት በፊት የእስራኤል መንግሥት ቃል ቢገባም ቃሉ እንደታጠፈ ይናገራሉ። ተቃውሞው በኢትዮጵያ ብቻ ውስጥ ሳይሆን በእስራኤል የሚገኙ ቤተ እስራኤላውያን የተቃውሞ ሰልፍ በማድረግ የእስራኤል መንግሥት ቃሉን እንዲያከብር እንደጠየቁ በአዲስ አበባ የሚገኙ ቤተ እስራኤላውያን ማህበር ስራ አስኪያጅ አቶ አንዱአለም ውብ ምህረት ለቢቢሲ ገልጿል። ከጥቂት ዓመታት በፊት በእስራኤል የሚገኙ ቤተ እስራኤላውያን ላይ የዘር ማምከን ወንጀል ተፈፅሟል በሚል አስተዳደሩ ከፍተኛ ውግዘት ደርሶበታል። ዘርንም በመጨፍጨፍ የተለያዩ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ወንጅለውታል። በተደጋጋሚም በቤተ እስራኤላዊያን ላይ የሚደርሱ ተደጋጋሚ የዘረኝነት ጥቃትን በመቃወም ከፍተኛ ተቃውሞዎችም ተካሂደዋል። ምንም እንኳን እስራኤል እንደ ሁለተኛ ዜጋ ብታያቸውም አሁንም ሀገራችን እስራኤል ነው የሚሉ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ ቤተ እስራኤላውያን ፅዮንን ሙጥኝ እንዳሉ ነው። በባቢሎን ወንዞች አጠገብ በዚያ ተቀመጥን፤ ፅዮንንም ባሰብናት ጊዜ አለቀስን እንደሚለው ጥቅስ የፅዮን ማዕከልነትን መቼም እንደማይዘነጉ ይናገራሉ። ለአስርት ዓመታትም ወደ እሥራኤል ለመሔድ በመጠባበቅ ላይ የሚገኙ ቤተ እስራኤላውያን ከሶስት ዓመታት በፊት የእስራኤል መንግሥት ሁሉንም እንደሚወስድ ቃል ቢገባም ቃሉን እንዳላከበረ ኢትዮጵያ ላሉ ቤተ እስራኤላውያን የሚደረጉት እንቅስቃሴዎች ኃላፊ አቶ ንጉሴ ዘመነ አለሙ ይናገራል። እንዲህ የተጓጓተተበት ዋነኛው ምክንያት የእስራኤል መንግሥት በተደጋጋሚ የበጀት እጥረትን ምክንያት በማድረግ የተለያዩ ውሳኔዎች እያስተላለፉ እንደሆነ ገልጿል። ከመጀመሪያው ውሳኔ በተቃርኖም የተቀሩትን ዘጠኝ ሺ ሰዎች አንድ ላይ ሳይሆን በተለያየ ጊዜ ና አንድ ሺ ሰዎች እንደወሰዱ ተናግሯል። ይህ ውሳኔ ደግሞ ቤተሰብን ከሁለት የሚከፋፍል በመሆኑ መጀመሪያ የተወሰነውን ውሳኔ እንዲከበር እየጠየቅን ነው ያለነው ይላል። ከተለያየ ሀገር ለሚመጡ ይሁዲዎች የበረራ ወጪያቸውን የእስራኤል መንግሥት የሚሸፍን ሲሆን ከዚያም በተጨማሪ የቤት መግዣና ለአንድ አመት ያህል ሀገሪቱን እስኪለምዱ ድረስ የሚሰጥ ወርሃዊ የኪስ ገንዘብ ይሰጣቸዋል። ለአቶ ንጉሴ ግን የበጀት እጥረት ነው ቢባልም አሳማኝ እንዳልሆነ ይናገራል። ለዚህም እንደ ምሳሌ የሚያነሳው ከሶስት አመታት በፊት የእስራኤል አዲስ ገቢዎች ሚኒስትር የተናገሩትን ነው። የእስራኤል አዲስ ገቢዎች ቢሮ ትርፍ ብር በየዓመቱ በጀት እየተረፈ ሲመልስ እንጂ ተቸግሮ እንደማያውቅ ሚኒስትሩ ተናግረዋል። በጀት የሚለው ጉዳይ በተለያዩ መስሪያ ቤቶች የሚሰሩ ኃላፊዎች ያመጡት ችግር እንጂ እውነት የበጀት እጥረት ነው ብየ አላምንም ይላል። በእስራኤል ታሪክም በተደጋጋሚ ከመቶ በላይ ኃገራት አዲስ ገቢዎች ሲመጡ የበጀት ችግር አጋጥሞኛል ብላ እስራኤል እንደማታውቅ ይናገራል። ለመጀመሪያ ጊዜ የኢትዮጵያ ይሁዲዎች እንዲመለሱ በተወሰነበት ሰዓት ነው የበጀት ጥያቄ መነሳት የጀመረው አሁን እንደሆነ ጠቅሶ የዘረኝነትና የፖለቲካ ምክንያቶች ሊሆኑ እንደሚችሉ ይጠቅሳል። አቶ አንዱአለም በበኩሉ እንደ ምክንያትነት የሚያቀርበው እስራኤል በአፍሪካውያን ላይ ያላትን እይታ ነው። የቤንያሚን ኔታንያሁ መንግሥት አቅም አንሶት ሳይሆን ዘረኝነት ነው። ኢትዮጵያዊ እንዲሁም አፍሪካዊ በመሆናችን እንጂ ሀገሪቱ የኢኮኖሚ አቅም ችግር አላት ብለን አናምንም ይላል። ለዚህም ምላሽ በእስራኤል የሚገኙ ከ ሺ በላይ የሚገኙ ቤተ እስራኤላውያንም እያቀረቡት ያለውም ሀሳብ ስንመርጥህ ቤተሰቦቻችንን ከኢትዮጵያ እንደምታመጣልን ቃል ስለገባህልን ነው እንዳሉም አቶ አንዱአለም ለቢቢሲ ገልጿል። ብዙዎች ለአስርት ዓመታት ከቤተሰቦቻቸው ተነጣጥለው እንደሚገኙ የሚናገሩት አቶ አንዱአለም እንደ ምሳሌም የሚያነሱት የራሳቸውን ቤተሰቦች ነው። ከሰባ አመት በላይ ዕድሜ ያላቸው አባትና እናቱ ወደ እስራኤል የሄዱ ከ ዓመታት በፊት ሲሆን ሶስት ታናናሽ ወንድሞቹም አብረው ሄደዋል። ከቤተሰቦቻችን ጋር ኢሰብዓዊና ፍትሀዊ በሆነ ሁኔታ ተለያይተናል። ለምን እንደለያዩን አላውቅም፤ ለመኖር በሚከብድ ሁኔታ ላይ ነው ያለነው ይላል አባቱን በሰባት ዓመት ውስጥ አናግሯቸው የማያውቅ ሲሆን የተሰማውንም ለመግለፅ ቃላት ያንሰዋል ህልውናውን ስቶ ሰው እያነሳ እየጣለው ድምፁን እንኳን ሰምቼ አላውቅም። ይህም በስነ ልቦናየ ላይ ከፍተኛ ተፅእኖ አሳድሮብኛል። ጥዋት ማታ ላየው የምፈልገው አባቴን ድምፁን እንኳን መስማት ሲያቅተኝ የሚሰማውን ስሜት መገመት ይቻላል ይላል። ከዚህም በተጨማሪ እናቱም በለቅሶና በሐዘን ላይ መሆናቸውም የአቶ አንዱአለም የሌት ተቀን ራስ ምታት የሆነበት ጉዳይ ነው። እናቴ ሌት ተቀን በማልቀስ አይኗ ሁሉ ጎድጉዶ እንደ ሉሲ በአፅም አለች ማለት ይቻላል። በማለት እናታቸው የደረሰባቸውን ጥልቅ ሀዘንም ይገልፃል። በዚህም ምክንያትም በእስራኤል መንግሥት ላይ ምንም አይነት ተስፋ የለውም ለእስራኤል መንግሥት ጥሩ አመለካከት የለኝም። በኛ ላይ ያደረሰው ጭካኔ ነው ይላል ከዚህም በተጨማሪ ቤተ እስራኤላውያን የእስራኤል ባለስልጣናት የፖለቲካ ፍጆታ ማስፈፀሚያ እንደሆኑም አቶ አንዱአለም ይሰማዋል። ለዚህም እንደምሳሌ የሚያነሳው ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ውስጥ ተገኝተው ያደረጉትን ንግግር ነው። ከአፍሪካ የወሰድናቸውን ኢትዮጵያውያንን ከፍተኛ ስልጣን በመስጠት ላይ ነን፤ ከኛ ተማሩ ማለታቸውን ገልፆ ይህ አባባል ግን ፍፁም ከእውነት የራቀ እንደሆነ ይናገራል። በተቃራኒው አቶ አንዱአለም እኛ ሰው መስለን አንታያቸውም ይላሉ። ለአስርት ዓመታትም እስራኤል እንሄዳለን በሚል ጥበቃ ብዙዎች ከገጠር ተሰደው አዲስ አበባ ላይ ኑሮን መቋቋም እንደከበዳቸው አቶ ንጉሴና አቶ አንዱአለም ይናገራሉ። ኑሮው በጣም ከባድ ነው፤ በእንግልትም ላይ ነው ያሉት ግን ወደ ፅዮን እንሔዳለን ብለው ነው ይህን ያህል መከራ እየከፈሉ ያሉት ይላል አቶ ንጉስ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ መልስ ይሰጡናል የሚል ተስፋ ቢኖራቸውም ጥያቄያቸው መልስ ካላገኘ ምን አይነት እርምጃ ይወስዱ ይሆን አቶ ንጉሴ የሚለው አለው። ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ናታንያሁ ፅዮናዊ ናቸው፤ እንዲሁም በመላው አለም የሚገኙ ይሁዲዎችን ለመመለስ በጣም ከፍተኛ ጥረትም ያደርጋሉ በሚል አቶ ንጉሴ ተስፋውን ገልጿል። ምላሽ ካልተሰጣቸው በእስራኤል የሚገኙ ቤተ እስራኤላውያን በሚሰጡት መመሪያ እንደሚቀጥሉ ይናገራል። የረሀብ አድማ አንዱ የተቃውሞ መንገድ ሊሆን እንደሚችል ጠቁሞ ከዚህም በተጨማሪ በእስራኤል የሚገኙ ቤተ እስራኤላውያን መፍትሔ ለማግኘት ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጉዳዩን ወስደውታል። አቶ አንዱአለም በበኩሉ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ ቤተ እስራኤላውያን አቅም ስለሌላቸው ይህ እንደሚፈፀምባቸው ጠቁሞ ወደ አምላክ ከመጮህ ውጭ ምንም ነገር የለም። የኛ ዋስትና እስራኤል ውስጥ ያሉ ቤተ እስራኤላውያን የሚያደርጉት ጫና ይወሰናል ይላል። የቤተ እስራኤላውያን አመጣጥ የንግሥት ሳባ ልጅ የሆነውን ሚኒልክን አጅቦ ከመምጣት ጋር የሚያይዙት እንዳሉ ሁሉ የእስራኤል በባቢሎናውያን መወረርን ተከትሎ ከተሰደዱት መካከልም እንደሆኑ ታሪክን አጣቅሰው ይናገራሉ። በታሪክ ውስጥም የተለያዩ ስያሜ የተሰጣቸው ሲሆን ቤተ እስራኤል የተባሉትም በአብርሃ ወአፅብሃ ዘመነ መንግሥት ክርስትናን አልቀበልም በማለታቸው እንደሆነ የታሪክ መዛግብት ይጠቅሳሉ። በተለያዩ አመታትም ቤተ እስራኤላውያንን የመመለስ ስራ የተሰራ ሲሆን ከነዚሀም ውስጥ ኦፐሬሽን ሙሴና ኦፐሬሽን ሰለሞን ይጠቀሳሉ። በነዚህም ጉዞዎች በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ቤተ እስራኤላውያን ሄደዋል። ይህንን ዜና ያጋሩ ስለማጋራት
እስራኤል የቀድሞ ሚኒስትሯን በኢራን ሰላይነት ፍርድ ቤት አቆመች
በሺ የሚቆጠሩ ከኢትዯጵያ የሾለኩ ቤተ እስራኤላዊያንን በጥንቃቄ ወደ እስራኤል ምድር ለመጓጓዝ ነበር ይህ ሁሉ የሆነው። ምክንያቱም ሱዳን በዚያን ወቅት ለእስራኤል በጄ የምትል አገር አልነበረችም፤ እንዲያውም ከአረብ ጠላቶቿ አንዷ ነበረች። ይህ ኀቡእ ዘመቻ ታውቆ ቢሆን የብዙ ሺህ ቤተ እስራኤላዊያን ሕይወት አደጋ ላይ ሊወድቅ ይችል ነበር። ጥብቅ የአገር ምስጢር ነበር። ቤተሰቦቼ እንኳ ስለነገሩ የሚያውቁት ነገር አልነበረም ይላል ጋድ ሺምሮን፣ የቀድሞ የሞሳድ ባልደረባ። ኦሪትን የሚከተሉትን ቤተ እስረኤላዊያን ሃይማኖታቸውንም ሆነ ማንነታቸውን ለማንም እንዳይገልጡ፣ ማንነታቸው ከታወቀ ግን በሱዳን የጸጥታ ኃይሎች አደጋ እንደሚጋረጥባቸው ይነገራቸው የነበረው መቀመጫውን በአሮስ መዝናኛ ባደረገው በዚህ ኅቡዕ የሞሳድ ቡድን በኩል ነበር። ቤተ እስራኤላዊያን በተመለከተ መላ ምቱ ብዙ ነው። ከአስሩ የጠፉ የእስራኤል ነገዶች ዝርያቸው የሚመዘዝ እንደሆነ ይነገራል። ሌሎች ሰነዶች ደግሞ ከክርስቶስ ልደት በፊት ዓመተ ዓለም አካባቢ የንግሥት ሳባና የንጉሥ ሰለሞንን ልጅ አጅበው ወደ ኢትዮጵያ ምድር የመጡ እስራኤሎች የልጅ ልጅ ልጆች እንደሆኑ ይገምታሉ። ሌሎች ደግሞ ትልቁ የአይሁድ ቤተ አምልኮ በ ዓመተ ዓለም ሲፈርስ ወደ ሐበሻ ምድር የተሰደዱ እንደሆኑ ይገምታሉ። ሞሳዶች አሮስ መዝናኛን ገንብቶ ለመክፈት ወራትን ወስዶባቸዋል። ከአገሬው የሚሆኑ የቤት ሠራተኞችን፣ ሾፌሮችን፣ የወጥ ቤት ሠራተኞችን ቀጥረዋል። አንዳቸውም ግን የሆቴሉን ኅቡዕ ተግባር አያውቁም ነበር። አለቆቻቸው የሞሳድ ሰዎች እንጂ የወጥ ቤት ሰዎች እንዳልሆኑ ያወቁት ከብዙ ዘመን በኋላ ነበር። ምድር ቤት የሚገኘው እቃ ቤት ግን ማንም ዘው ብሎ ገብቶ አያውቅም፣ እዚያ ከድስቶች ጋር የርቀት መነጋገሪያ ስልኮች ነበሩ። ከቴላቪቭ የሚያገናኙ። ተያያዥ ርዕሶች
አደገኛ ነው የተባለለት የወባ በሽታ በደቡብ ምሥራቅ እስያ ተስፋፍቷል
መስከረም የወባ በሽታን የምታስተላልፈው ትንኝ አደገኛ እንደሆነ የተነገረለት የወባ ዓይነት በደቡብ ምሥራቅ እስያ በፍጥነት መዛመቱ ለአፍሪካ አስጊ መሆኑን ተመራማሪዎች አስታወቁ። ይህን መሰሉ የወባ ዓይነት በመደበኛው የወባ መከላከያ መድኃኒት በቁጥጠር ሥር አይውልም ተብሏል። ይህ የወባ ዓይነት መጀመሪያ በካምቦዲያ የታየ ቢሆንም ወደ ደቡብ እስያ ሃገራት ተስፋፍቷል። በባንኮክ የሚገኘው ኦክስፎርድ ትሮፒካል ሜድሲን የምርምር ተቋም ባልደረቦች እንደሚሉት ይህን የወባ ዓይነት ለመዳን አስቸጋሪ ይሆናል። የምርምር ቡድኑ የበላይ የሆኑት ፕሮፌሰር አሪየን ዶንድሮፕ በሽታው በፍጥነት ከመዛመቱም በላይ አፍሪካ ሊደረስ ይችላል የሚል ስጋት አለን ብለዋል። የ ኢትዮጵያ ተሞክሮ በጤና ጥበቃ ሚንስቴር የወባ ፕሮግራም ባለሙያ ሆኑት አቶ ደረጀ ድሉ እንደሚሉት መስሪያ ቤቱ ስለስጋቱ መረጃው አለው። ወባ በሽታን በመከላከል አበረታች ውጤት እየተገኘ መሆኑን የገለጹት ባለሙያው እ አ አ በ ላይ ሚልዮን የነበረው የህሙማን ቁጥር በ ወደ ሚሊዮን መቀነሱን ጠቁመዋል። እስካሁን ባለው አሰራር ፕላስሞዲየም ፋልሲፓረም እና ፕላስሞዲየም ቫይቫክስ ለተየባሉት የወባ ዓይነቶች መድኃኒቶች ጥቅም ላይ እየዋሉ ነው ብለዋል። እንደባለሙያው ከሆነ የመድኃኒቶቹን ውጤታማነት ለመከታተልም የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስትትዩት በየሁለት ዓመቱ ጥናት ያካሂዳል። የጨነገፉ መድኃኒቶች በወባ ትንኝ በሚዛመተው በዚህ በሽታ ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎች በየዓመቱ የሚያዙ ሲሆን ህጻናትን በመግደል ቀዳሚ ከሆኑት መካከልም ተጠቃሽ ነው። በሽታውን ለመቆጣጠር አርትሚሲኒንን ከፒፐራኩይን ጋር በማሃዋድ መጠቀም ተቀዳሚ ምርጫ ነው። አርትሚሲኒን ያለው ውጤታማነት እየቀነሰ ሲሆን በሽታው ደግሞ ፒፐራኩይንን እየተላመደ ይገኛል። በውህድ መድሃኒቶቹ በሽታውን ለመከላከል የሚደረገው ጥረት በአንዳንድ ቦታዎች እስከ በመቶ ድረስ መቀነሱን ፕሮፌሰር ዶንድሮፕ አስታውቀዋል። መድኃኒቱን የተላመደ ወባ መስፋፋቱ እስከ በመቶ የሚሆነው የወባ በሽታ በሚከሰትበት የአፍሪካ አህጉር የከፋ ችግር ሊያስከትል ይችላል። በአፋጣኝ የሚቀርብ መፍትሔ በሽታው መዳን ከማይቻልበት ደረጃ ደርሶ የሰዎችን ህይወት ከመቅጠፉ በፊት በፍጥነት መስራት ይኖርብናል ብለዋል። እውነቱን ለመናገር በጣም ሰግቻለሁ ሲሉ ፕሮፌሰሩ የክስተቱን አሳሳቢነት ይናገራሉ። የዌልካም ትረስት ሜዲካል ሪሰርች ባልደረባ ሆኑት ማይክል ቼው እንደሚሉት፤ መድኃኒት የተላመደ የወባ በሽታ መስፋፋቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለማህበረሰብ ጤና አስጊ ነው ብለዋል። እስካሁን በዓመት የ ሺህ ሰዎችን ህይወት ሲቀጥፍ የነበረው መድኃኒት የተላመደ የወባ በሽታ፤ ምንም ካልተሰራበት የሟቾች ቁጥር እ አ አ በ በሚሊዮኖች ከፍ ሊል ይችላል ብለዋል። በኢትዮጵያ የአዲሱ የወባ በሽታ ዓይነት አለመከሰቱን አቶ ደረጀ ጠቅሰው፤ መድኃኒት የተላመደ ወባን ለመከላከል እና የመድኃኒቶችን ውጤታማነት ለማረጋገጥ ከኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስትትዩት ጋር የሚደረገው ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል። ቢቢሲ ማስተባበያ
ኦክስፎርድ ከዓለማችን ቀዳሚው ዩኒቨርስቲ ተባለ
መስከረም ኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ በዓለማችን ካሉ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ሁሉ ለተከታታይ አራትኛ ዓመት ቀዳሚ መሆኑ ተገለፀ። የዓለማችን ግዙፍና ስመጥር የትምህርት ተቋማትን ደረጃ የሚያወጣው ተቋም ካምብሪጅን ሶስተኛ ኢምፔሪያል ኮሌጅ ለንደንን አስረኛ አድርጎ በደረጃ ሰንጠረዡ ላይ አስቀምጧል። ነገር ግን ደረጃውን የሚያወጡ አካላት ሌሎች የዩናይትድ ኪንግደም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከሌላ ሀገር ተቋማት ጋር ባለባቸው ፉክክር የተነሳ ደረጃቸውን ይዘው ለመቆየት እየታገሉ ነው ብለዋል። በአውሮጳ ስመጥር ከሆኑ ዩኒቨርስቲዎች መካከል የጀርመን ዩኒቨርስቲዎች የዩናይትድ ኪንግደም አቻዎቻቸውን በመቀናቀን የበላይነቱን ይይዛሉ ሲሉ ግምታቸው በማስቀመጥ አስጠንቅቀዋል። የሼፎች የበዓል ምግብ ምርጫ፡ ሼፍ ዮሐንስ፣ ጆርዳና እና ዮናስ ኦክስፎርድ ዳግመኛ የዓለማችን ምርጡ ዩኒቨርስቲ በመሆን አንደኛነቱን የተቆናጠጠ ሲሆን በሁለተኛነት ደግሞ ካሊፎርኒያ ኢንስቲትዩት ኦፍ ቴክኖሎጂ ሆኗል። የአሜሪካ ዩኒቨርስቲዎች ከምርጥ አስሮቹ መካከል ሰባቱን በመያዝ የደረጃ ሰንጠረዡን በበላይነት የተቆጣጠሩት ሲሆን ከ ዩኒቨርስቲዎች መካከል ደግሞ ዎቹ የአሜሪካ ዩኒቨርስቲዎች ናቸው። የእሲያ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትም ቢሆኑ የዋዛ አለመሆናቸው ነው የሚነገረው። ቻይናና ጃፓን ጠንካራ ተፎካካሪ በመሆን ብቅ እያሉ መጥተዋል። በዚህ ዓመት ሳትጠበቅ ምርጥ የአለማችን ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ እግሯን ያስገባች ጠንካራ ተፎካካሪ አገር ኢራን ናት። የዓለማችን ምርጥ ዩኒቨርስቲዎች
የቦስኒያ ጦርነት፡ በጦርነት ወድሞ የነበረው አላድዛ መስጊድ ተከፈተ
ግንቦት አላድዛ መስጊድ ሙሉ በሙሉ ከወደመ ከዓመታት በኋላ እንደገና ተገንብቷል በአውሮፓውያኑ ከ በቦስኒያ በተካሄደው ጦርነት የወደመው የአላድዝ መስጊድ ጥገና ተደርጎለት ከሦስት አስርት ዓመታት በኋላ እንደገና ተከፈተ። ቦስኒያ በሚገኘው በዚህ መስጊድ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በመገኘት የመክፈቻ ሥነ ሥርዓቱን ታድመዋል። በፎካ ከተማ የሚገኘው አላድዛ መስጊድ በቦስኒያ እና ሰርቢያ መካከል የብሔር ግጭት ለመቀስቀስ በማሰብ ነበር ኢላማ የተደረገው። በ ኛው ክፍለዘመን በኦቶማን የኪነ ህንፃ ጠበብቶች የተሠራ እንደሆነ የሚነገርለት መስጊዱ በጦርነቱ ከወደመ በኋላ መልሶ ለመገንባት ዓመታትን የወሰደ ሲሆን ቱርክን ጨምሮ ሌሎች አገራት የገንዘብ ድጋፍ አድርገዋል። በጦርነቱ በፈንጂ እስኪወድምም ድረስ አገልግሎት ይሰጥ ነበር ተብሏል። በፍንዳታው የወደቀው ዋናው የመስጊዱ አካል በድንጋይ የተገነባ ሲሆን በአደጋው የፈራረሱትንና የተዳፈኑት በቁፋሮ እንዲወጡ ተደርገዋል። በጦርነቱ ወቅት በፎካ ከተማ ሰርቢያን ያልሆኑ ሰዎች ግድያ ይፈፀምባቸው ነበር። በዚህም ሳቢያ ይህ አካባቢ ሰርቢንጂ ተብሎ የተሰየመ ሲሆን በአውሮፓውያኑ የቦስኒያ ፍርድ ቤት የቀድሞ ስሟ እንዲመለስላት ውሳኔ አስተላልፈዋል። የቻይና ሙስሊሞች ምድራዊ ጀሐነም ሲጋለጥ ታዲያ በዛሬው ዕለት በቦስኒያ የሚገኙ ህዝበ ሙስሊሞችም የመስጊዱን በድጋሜ መከፈት በድምቀት እያከበሩ ይገኛሉ። ዛሬ ሰዎች በዚህ አካባቢ ሰላም እንዳገኙና ደህንነታቸው እንደተመለሰላቸው ለማየት ችለናል ሲሉ የቡድኑ መሪ ሁሴን ካቫዞቪቸ በዝግጅቱ ላይ ሲናገሩ ተደምጠዋል። የቱርክ የባህል ሚንስትር መህምት ኑሪ ኢርሶይ በበኩላቸው ጥላቻና ዘረኝነት ቁሳቁስን ሊያወድም ይችላል፤ ነገርግን የነበረን ባህልና ኃይማኖት ማጥፋት ግን አይችልም ብለዋል በዝግጅቱ ላይ። በቦስኒያ የአሜሪካ መልዕክተኛም ይህ መስጊድ ለወደፊቱን ትውልድ ተስፋን የሚሰጥና የሚያስተሳስር ነው ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። ባለፈው ዓመት የቀድሞው የቦስኒያ ሰርብ ወታደር ፈንጂ በመቅበር ተሳትፈሃል ተብሎ ክስ እንደቀረበበት ይታወሳል። ፎካ ከተማ ከጦርነቱ በፊት ካላት ሺህ ገደማ የህዝብ ብዛት ግማሽ ያህሉ ሙስሊም ሲሆኑ አሁን ግን ቁጥራቸው ከአንድ ሺህ ያነሰ እንደሆነ ሮይተርስ የዜና ወኪል ዘግቧል። ከዚህ ዜና በተጨማሪ
ለመታሰር ብሎ ሰው የገጨው የእድሜ ልክ እስራት ተፈረደበት
ታህሳስ መኪና ውስጥ የሚኖረው ግለሰብ ለመታሰር ብሎ ሳይክል ነጂ በመግጨቱ የእድሜ ልክ እስራት ተፈረደበት። ግለሰቡ ሥራ አጥ ሲሆን፤ የሚኖረውም መኪና ውስጥ ነበር። እስር ቤት ለመግባት በማሰብ ሆነ ብሎ በሳይክል የሚጓዝ ሰው ከገጨ በኋላ ነው በጀርመን ፍርድ ቤት የእድሜ ልክ እስራት የተፈረደበት። ባለ ሳይክሉ ክፉኛ ጉዳት ደርሶበታል። ተዋናይቷ ቻርሊዝ ቴሮን እናቷ አባቷን የገደለችበትን ምክንያት ይፋ አደረገች ግለሰቡ በኮምፒውተር ሳይንስ ዘርፍ ውስጥ ይሠራ ነበር። ሥራውን ካጣ በኋላ ግን ያለውን ገንዘብ ባጠቃላይ አውሮፓን በመዞር አባክኖታል። የ ዓመቱ ግለሰብ ሥራ እንዲሁም መኖሪያ ቤትም የለውም። ግለሰቡ ሳይክል ነጂውን ከመግጨቱ በፊት፤ እስር ቤት ቢገባ ሊያገኝ የሚችለውን ጥቅም ሲያጠያይቅ ነበር ተብሏል። ግለሰቡ እስር ቤት ቢገባ፤ መጠለያ እንዲሁም ምግብ እንደሚያገኝም በማሰብ ነበር ባለ ሳይክሉን የገጨው። ፍርድ ቤቱ እንዳለው፤ ግለሰቡ ስግብግብ በመሆኑ የ ዓመቱን ባለ ሳይክል ገጭቷል። ክስ የቀረበበትም በግድያ ሙከራ ነው። የፍርድ ቤቱ ቃል አቀባይ እንዳሉት፤ ግለሰቡ በድርጊቱ ጸጸት ስለተሰማው የጡረታ ገንዘቡን ለባለ ሳይክሉ መታከሚያ ለማዋል ተስማምቷል። ቢቢሲ ማስተባበያ
መምህራንን ተክቶ ያስተማረው ወታደር እየተወደሰ ነው
ሴፕቴምበር አጭር የምስል መግለጫ ጃይረስ ሙሊማ ሒሳብ ሲያስተምር ኬንያ ውስጥ በአንድ ትምህርት ቤት የሚያስተምሩ መምህራን በስራ ገበታቸው ባለመገኘታቸው በአካባቢው የነበረ አንድ ፖሊስ ወደ ክፍል ውስጥ በመግባት ሲያስተምር የሚያሳየው ምስል የሃገሬውን ሰዎች በእጅጉ አስገርሟል። ኬንያውያንም ጀግናችን ነህ እያሉ በማህበራዊ ሚዲያዎች እያሞካሹት ነው። ምስሉን በፌስቡክ ለህዝብ ይፋ ያደረገው መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት እንደገለጸው ጃይረስ ሙሊማ የተባለው የፖሊስ ሃይል አባል በኢትዮጵያ እና ኬንያ ድንበር ላይ በሚገኝ ፎሮሌ በተባለ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ ሂሳብ ሲያስተምር ነበር። የድርጅቱ ሃላፊ ለቢቢሲ እንደተናገሩት ከባለፈው ሳምንት ጀምሮ አካባቢው የደህንነት ስጋት አለበት በማለት መምህራኑ በስራ ገበታቸው ላይ እየተገኙ አይደለም። በዚህም ምክንያት ተማሪዎች በክፍል ውስጥ ያለምንም ትምህርት ተቀምጠው እንዲውሉ ተገደዋል። ከትምህርት ቤቱ ሃላፊ ፍቃድ ካገኘ በኋላ ጃይረስ ሙሊማ አምስተኛ ክፍል በመግባት የሂሳብ ትምህርት ሲያስተምር ነበር ብለዋል ሃላፊው። ትምህርት ቤቱ በሚገኝበት አካባቢ በተለያዩ ጊዜያት ሽፍታዎች ድንገተኛ ጥቃት የሚያደርሱ ሲሆን ጥቂት ለማይባሉ ሰዎችም ህይወት ማለፍ ምክንያት ሆኗል። በርካታ ኬንያውያን ጃይረስ ሙሊማ የሰራው ስራ እጅግ የሚያኮራና ለሁላችንም ምሳሌ መሆን ያለበት ነገር ነው በማለት በማህበራዊ ሚዲያዎች እየተቀባበሉት ነው። ፀረ መውለድ ፍልስፍናን ያውቁታል አንድ ኬንያዊ ያልተዘመረለት ጀግና ሲል አሞካሽቶታል። ጃይረስ ሙሊማ በድንበር አካባቢ የተከሰተውን አለመረጋጋት ለመቆጣጠር ከተመደቡ የጸጥታ ሃይሎች አንዱ ሲሆን በትምህርት ቤቱ አካባቢ ጥበቃ ሲያደርግም ነበር ተብሏል። ጃይረስ የሂሳብ ትምህርት ሲያስተምር በክፍሉ ውስጥ የነበሩት ወደ ትምህርት ቤት ለመምጣት ድፍረት የነበራቸው ጥቂት ሴት ተማሪዎች ብቻ ነበሩ ተብሏል። ተያያዥ ርዕሶች