topic
stringlengths
16
333
news
stringlengths
16
46.2k
የሼፎች የበዓል ምግብ ምርጫ፡ ሼፍ ዮሐንስ፣ ጆርዳና እና ዮናስ
ሴፕቴምበር ስለ ማጋራት ተጨማሪ ያጋሩ ማጋሪያ ምረጥ ዓውደ ዓመትና ምግብ አይነጣጠሉም። ዶሮው፣ ጥብሱ፣ ዱለቱ፣ ቁርጥ ስጋው፣ ክትፎው፣ ድፎ ዳቦው እነዚህን ሁሉ የዓውደ አመት ደስታ፣ ቄጤማና እጣን፣ የሚትጎለጎል የተቆላ ቡና ሽታ ከዛም ጥዑም ቡና ሲያጅባቸው የበዓል ሞገሱ ይገዝፋል። እኛም ሦስት በምግብ ዝግጅት የሚታወቁ ባለሙያዎችን አነጋግረናል። ሼፎቹ ዩሐንስ፣ ጆርዳና እና ዮናስ ሺህ ጉርሻዎች ዮሐንስ ኃይለማርያም ምግብ ማብሰልን እንደ ሙያ ከያዘ ዘጠኝ ዓመት አስቆጥሯል። በቅርቡ የምግብ አዘገጃጀት መጽሐፍ አሳትሟል። በቃና ቴሌቭዥን አዲስ ጓሮ የተባለ መሰናዶ አዘጋጅም ነው። በኃያት ሬጀንሲ በየወሩ የምግብ አሠራር ትምህርት ይሰጣል። ሲድስ ኦፍ አፍሪካ የተራድኦ ድርጅት ውስጥ ስለልጆች አመጋገብ ያማክራል። አንባቢዎቻችን ለበዓል ምን እንዲመገቡ ትመክራለህ እስኪ ከነአሠራሩ ንገረን። እንፍሌ። አሠራሩ፡ የበግ ወይም የፍየል እግር ሥጋው ከአጥንቱ ሳይለያይ ተፈልቅቆ ይነሳል። ሥጋው ከአጥንቱ ጋር እንደተያያዘ ይዘለዘላል። ልክ እንደ ዶሮ ወጥ በሽንኩርት፣ በበርበሬ፣ በቅመማ ቅመም ስልስ ይዘጋጃል፤ ትንሽ ጠጅ ጠብ ይደረግበታል። ከዛ ሥጋው በነዚህ እንፋሎት ይበስላል። አጭር የምስል መግለጫ እንፍሌ በመላው ኢትዮጵያ ስትዘዋወር ከገጠሙህ የምግብ ግብዓቶች እና የምግብ አሠራር ያስገረመህ የቱ ነው ጋምቤላ ውስጥ ከአንድ ቅጠል የሚሠራ ጨው ይጠቀማሉ። ቅጠሉ ተቃጥሎ፣ ከውሀ ጋር ይዋሀድና ይጠላል። ከዛ በጸሐይ ደርቆ ጨው ይሆናል። ሶድየም ስለሌለው ለማንኛውም የእድሜ ክልል ተስማሚ ነው። ላሊበላ ውስጥ የአጃ ቂጣ ሲጋገር እንደእንጀራ አይን እንዲያወጣ በምጣዱ ዙሪያ ልጆች ተሰብስበው ያፏጫሉ። በየትኛውም አገር እንዲህ ያለ አሠራር አልገጠመኝም። ጤፍ ስለሚብላላ በፈርመንቴሽን እንጀራ ሲጋገር አይን ይሠራል። አጃ ግን ግሉተን ስላለው ውስጡ የሚታመቀውን አየር ለማፈንዳት ይከብዳል። ስለዚህ በፉጨት የድምጽ ንዝረት ቫይብሬሽን በመፍጠር አይን እንዲወጣ ይደረጋል። ምግብህ አይጣፍጥም ተብለህ ታውቃለህ ቆይ አሁን ባይጣፍጥ፤ አይጣፍጥም ብዬ የምነግርሽ ይመስልሻል ሳቅ ግን እድለኛ ነኝ ይህ ገጥሞኝ አያውቅም። የምትወደው ምግብ ምንድን ነው በተለያየ ጊዜ እንደስሜቴ የተለያየ ምግብ ያምረኛል። ሁሌ የሚያስደስተኝ ግን ጥሬ ሥጋ ነው። ምግብ ከመሥራት ሂደት የሚያስደስትህ የቱ ነው ሁሉንም ሂደት እወደዋለሁ። ከግብዐት መረጣ ጀምሮ እስከ ማብሰል፤ ከዛ አልፎም እንግዶች ምግቡን ቀምሰው አስተያየት እስኪሰጡ ወይም ፊታቸው ላይ የሚነበበውን እስከማየው ድረስ ደስ ይለኛል። ለምትወደው ሰው የምታበስለው ምግብ ምንድን ነው ሼፍ ስትሆኚ ኃላፊነት አለብሽ። ሁሌም ለምትወጂው ሰው እንደምታበስይ አስበሽ ነው መሥራት ያለብሽ። ግን የሆነ ውድድር ቢኖርብኝ፤ በምን ምግብ አስደምማለሁ ብዬ ሳስብ ስፔሻሊቲዬ የተካንኩበት ስለሆነ ሲ ፉድ ከባህር ውስጥ እንስሳት የሚዘጋጅ ምግብ ይመቸኛል። ቆንጆ ምግበ ማብሰል እንደምትችል አምነህ ሼፍ መሆን እችላለሁ ያልክበት ቅጽበት ትዝ ይልሀል የመጀመሪያ ቀን ምግብ ሰርቼ ይጣፍጣል ብዬ አይደለም ወደሙያው የገባሁት። የመጀመሪያ ዲግሪ የሠራሁት በቪዥዋል አርት የእይታ ሥነ ጥበብ ነው። ከዛ ወደ ከልነሪ አርት ምግብ የማብሰ ጥበብ ገባሁ። ጥብበ በሸራ፣ በድምፅ፣ በፐርፎርማንስ ክዋኔ በብዙ መንገድ ሊገለጽ ይችላል። ብዙ ሰው ጋር ለመድረስ ግን ምግብ የተሻለ ነው። የተማረኩበት ፈረንሳይ የሚገኝ በዓለም እውቅና ያለው ትምህርት ቤት ነው። ጥሩ መሰረት ሰጥቶኛል። እናቴ አንቲካ የሚባል ሬስቶራንት ስላላት ለሙያው ቅርብ ሆኜ ነው ያደግኩት። ምግብህን በልተው ካደነቁህ ሰዎች የማትረሳው ማንን ነው ለመጽሐፌ ምርቃት ኒውዮርክ ሄጄ ነበር። ሴቮር የሚባል በጣም የታወቀ መጽሔት አለ። እዛ የድርቆሽ ቋንጣ ፍርፍር ሠርቼ ነበር። ምግቡ ቀላል ሆኖ ሰውን ያስደነገጠ ነበር። ከነበረው ምግብ ሁሉ ሰው የወደደው እሱን ነበር። ጆርዳና ከበዶም ምግብ የማብሰል ሙያን ያዳበረችው በሬስቶራንቶች በመሥራት ነበር። ሁለት የምግብ አዘገጃጀት መጻሕፍት ለህትመት አብቅታለች። አሁን በፋና ቴሌቭዥን ላይ የምግብ መሰናዶ መርሀ ግብር እያዘጋጀች ታቀርባለች። አንባቢዎቻችን ለበዓል ምን እንዲመገቡ ትመክሪያለሽ እስኪ ከነአሠራሩ ንገሪን። የአበሻ ዳቦ። አሠራሩ፦ በገብስ ወይም በስንዴም ዱቄት ይቦካል። ከዛ እንዲጣፍጥ ቴምር ወይም ቸኮሌት መጨመር ለሁለት ኪሎ ስንዴ ወይም ገብስ ወይም ግራም ቸኮሌት መሀል መሀል ላይ ጣል ማድረግ። እንዳይቀልጥ ጥንቃቄ ያስፈልጋል። ሌላው አማራጭ ቴምር ነው፤ መሀል ላይ ያለው ፍሬ ወጥቶ ጣል ጣል ማድረግ። ከዛ መጋገር። አጭር የምስል መግለጫ ጆርዳና ከበዶም ሼፎች በቴሌቭዥን የሚያሳዩት ግብዓት ገበያ ላይ በቀላሉ የማይገኝ ወይም ውድ የሆነ ነው ይባላል፤ ምን ትያለሽ ፍላጎትና አቅርቦት አለ። ፈረንጆች አሁን ያሉት ድሮ በነበሩበት አይደለም። እየተማሩ ሲሄዱ፣ ግብዓቶች መፈለግ ሲጀምሩ፤ አቅርቦትም መጣ። እኛም አመጋገባችንን እያሻሻልን ስንሄድ የገበያ አቅርቦት እየተሻሻለ ይሄዳል። የኔን ሾው መሰናዶ የሚወቅሱ ሰዎች አሉ። በእኔ እይታ በአቅርቦት ሳይሆን በፍላጎት ይጀምራል። ዛሬ ብር ደሞዝ ያለው ሰው፤ የዛሬ አምስት ዓመት ሺህ ብር ቢያገኝ ምን ምግብ ነው የምሠራው ብሎ ገንዘቡን ይዞ ቁጭ ይላል። የምትወጂው ምግብ ምንድን ነው ሁሉንም ነገር እወዳለሁ። በጣም ጥቂት ነገር ነው የማልወደው። ከሁሉም በላይ እንጀራ በጣም አወዳለሁ። በማንኛውም እኔ በምፈላሰፈው ዲሽ ምግብ እንጀራ እበላለሁ። በቅርቡ የቅቅል አጥንት ከጎመን ጋር ቀይ ወጥ ሰርቼ ጉድ ነበር። እኔ እንደመጣልኝ ነው የምሠራው። መመራመር ነዋ ደስ የሚልሽ በጣም በጣም ግን ሁሉም ግብዓት አብሮ ይሄዳል ይጣፍጣል ፋንታሲ የምኞት ዓለም ነው። ጭንቅላትሽ ክፍት መሆን አለበት። ምግብን የሚያጣፍጠው ቅመማ ቅመም ነው። ዝም ብዬ ጎመን ቀቅዬ እበላለሁ የምትይ ከሆነ አይጣፍጥሽም። ግን ከጎመን ጋር የሚሄዱ ነገሮችን አብሮ መሥራት ይቻላል። ብዙዎቻችን ገበያ ላይ ሽንኩርት፣ ነጭ ሽንኩት፣ ካሮትና ድንች ብቻ ነው የምንፈልገው። ከዛ ወጣ ሲል፤ ቀይ ሥር፣ ፎሰልያ፣ ስኳር ድንችም መግዛት ይቻላልኮ። እኔ ወደነዛ ነው የማተኩረው። ያው ባጀቴም እንዳይቃወስ። ሽንኩርቱን ቀንሼ ሌላ ነገር እገዛለሁ። ከምግብ ሥራ ሂደት የቱ ደስ ይልሻል ፍሬሽ አዲስ የተቀጠፈ ጎመን፣ ጥቅል ጎመን፣ ቅመማ ቅመም ገዝቼ ቤት ስሄድ ደስ ይለኛል። ፍሪጅ ውስጥ አስገብቼ፣ አውጥቼ ስሠራውም የሆነ ነገር ይሰማኛል። የኛን አገር የአመጋገብ ባህል መቀየር እፈልጋለሁ። ከምናውቀው ነገር ውጪ መሞከር አንፈልግም። መመራመር አንፈልግም። ይህ መቀየር አለበት። ሬስቶራንትሽ እንዴት ነው በኪራይ ምክንያት ተዘጋ። ለአምስት ዓመት ቻልኩት። ከዛ ግን ከእጅ ወደ አፍ ሆነ። ማብሰል ብዙ ሰአት ስለሚወስድም ጊዜ ተሻማኝ። ትቼው ወደ ቲቪ እና ወደ መጽሐፌ መሄድ ፈለኩ። ደንበኞቼ ግን አሁንም ይጠይቁኛል። የቲቪ መሰናዶውን ብዙ ሰው እየተማረበት ነው። መለኪያሽ ምንድን ነው ይሄን ሞክረነዋል ብለው እየመጡ የሚያመሰግኑኝ አሉ። ከኔ ሾው በኋላ ወደ ሰው ይደውላል። ይሄን ግብዓት ከየት አመጣሽ ይሄን ግብዓት በዚህ ልተካ እያሉ ይጠይቃሉ። ምግብ ማብሰል ከልጅነቴ ጀምሮ የምወደው ነገር ነው። የእናቴ አክስት የገዳም አብሳይ ነበሩ። ሠርተው ሲጨርሱ እኛ ቤት ይመጡ ነበር። እናቴ ስታበስል ነይ ተሳተፊ እባል ነበር። እናቴ በጣም ባለሙያ ናት። ሙያው ከአክስቷ ወደሷ፣ ከሷ ወደኔ መጣ። እኔ ሼፍ ትምህርት ቤት አልተማርኩም። ወደ ሙያው የገባሁት መብላት ከመውደዴ የተነሳ ነው። ያደግኩት ደሞ ጣልያን ነው። እዛ ምግብ ትልቁ የሕይወት ክፍል ነው። ምግብሽ አይጣፍጥም ተብለሽ ታውቂያለሽ አውቃለሁ። ብዙ ጊዜ ግን አይደለም። እንደዛ ያሉኝ ልጆቼ ናቸው። ይሄ ደሞ ምንድን ነው ሲሉኝ ይከፋኛል። ግን ወዲያው አሻሽለዋለሁ። ምግብ የልብ ነገር ነው። ከፍቶኝ ስሠራ የከፋ ምግብ አመጣለሁ። ደስ ብሎኝ ስሠራ ደግሞ ይጣፍጣል። ምግብ ሕይወት አለው እንዴ እላለሁ። ኩክ ዊዝ ላቭ በፍቅር አብስሉ የምለው ለዛ ነው። ምግብሽን በልተው ካደነቁሽ ሰዎች የማትረሽው ማንን ነው ልጆቼን። ስለምግብ ጥቅምና መጣፈጥ አስተምሬያቸዋለሁ። የትም ሄደው ይሄ ጥሩ ነው፤ ይሄ መጥፎ ነው ማለት ይችላሉ። ምግብ ሳይቀምሱ አይጣፍጥም እንዳይሉም አስተምሬያቸዋለሁ። ለምሳሌ ካንቺ ጋር ቃለ መጠይቅ ከመጀመሬ በፊት ለእንግዶች የሠራሁትን ሱፍ አቀመስኳቸው። ልክ አይደለም አሉኝ። ከዛ በድጋሚ ነጭ ሽንኩርትና ቅመም ጨምሬ አስተካከልኩ። ከዛ አሁን ጣዕም አለው አሉኝ። ዮናስ ተፈራ በሙያው ለ ዓመት ቆይቷል። በሆቴል፣ በሬስቶራንት፣ በእንግዳ ማረፊያም ሠርቷል። ከጓደኞቹ ጋር በከፈተው ቤንቬኒዶ የሆቴል ማሰልጠኛ ውስጥ ለአሥር ዓመት አስተምሯል። አምስት የምግብ አዘገጃጀት መጻሕፍት አሳትሟል። በሸገር ኤፍ ኤም ከሠይፉ ፋንታሁን ጋር ሬሲፔ በተሰኘ መሰናዶ ላይ ሠርቷል። አሁን በኢትዮ ኤፍኤም ላይ የ ምሳና ሙዚቃ መሰናዶ አዘጋጅና አቅራቢ ነው። አንባቢዎቻችን ለበዓል ምን እንዲመገቡ ትመክራለህ እስኪ ከነአሠራሩ ንገረን። የብረት ምጣድ ጥብስ። አሠራሩ፦ መጀመሪያ ከምንጠብሰው ሥጋ ብዛት ይልቅ የምንጠብስበት እቃ ሁለት እጥፍ ትልቅ መሆን አለበት። የምንጠብሰው ሥጋ እርጥበት ከምንጠብስበት እሳት በላይ መሆንም የለበትም፤ እሳቱ ማሸነፍ አለበት። ሥጋውን በትንንሹ እንከትፈዋለን፤ አጥንቱን ለብቻው በትንንሹ እንሰባብረዋለን። ቀይ ሽንኩርት፣ ነጭ ሽንኩርትና ዝንጅብል እንከትፋለን፤ የአበሻ ቅቤና ቃሪያ እናዘጋጃለን። ብረት ምጣዱ ከጣድን በኋላ በደንብ ሲግል፤ ትንሽ ዘይት ወይም ጮማውን ብቻ እየተጠቀምን ሥጋውን እየጠበስን ሲበስል ወደ ሌላ እቃ እንጨምራለን። አጥንቱን ለብቻ ሁለት ቦታ ከፍለን እየጠበስን ቡናማ መልክ ሲይዝ በማውጣት የተጠበሰውን ስጋ ወደ አስቀመጥንበት እቃ እንጨምራለን። ባዶ ብረት ምጣድ ላይ ቀይ ሽንኩርት እናደርጋለን። በትንሽ ዘይት ካቁላላነው በኋላ ነጭ ሽንኩርትና ዝንጅብል ገብቶ ለተወሰነ ሰዓት ይቁላላል። የተጠበሰው ስጋ የተፋውን ውሃ አስቀርተን ከሽንኩሩቱ ጋር በመቀላቀል አብረን እንጠብሳለን። ያስቀረነውን ሥጋው የተፋውን ውሃ ጨምረን ትንሽ እናበስለዋለን። የሀበሻ ቅቤ፣ ቃሪያና ጨው ጨምረን እናወጣዋለን። አጭር የምስል መግለጫ ዮናስ ተፈራ የኢትዮጵያውያንን የምግብ ዝግጅትና የአመጋገብ ባህል እንዴት ታየዋለህ ቅባት እናበዛለን ሳቅ ይሄ ከፍተኛ የጤና ችግር አምጥቶብናል። ዘይት ይበዛል፣ ቅቤ ይበዛል፣ ጮማ ይበዛል። የዚህን ያህል ዘይት አገራችን ከውጪ እንድታስገባም አድርጎናል። በአመጋገብ ስርዓታችን በጎ ነገራችንስ የቱ ነው የጾም ወራት ስለሚበዛ ሳይወዱ በግድ ከቅባት ይራቃል። ያ የጾም ወቅት ባይኖር ኖሮ እንደ አበላላችን የጤናችን ጉዳይ እጅጉን አሳሳቢ ነበር። የጾም ወራት አትክልትና ፍራፍሬ እንድንመገብ ያግዛሉ። ሳይንሱም እንደሚለው፤ ለተወሰነ ሰዓት ራስን ከምግብ ማራቅ፤ ሰውነታችን መርዛማ ነገሮችን እንዲያስወግድ፣ ውስጡ ያከማቸውን ቅባትና ካርቦኃይድሬት እንዲጠቀም እድል ይሰጣል። ምግብህ አይጣፍጥም ተብለህ ታውቃለህ እንዴ ቁጭ አድርጎ ያስበላኝ እንግዳ አለ ሳቅ ግለሰቡ ሼፉን ጥሩት አለ፤ አስተናጋጆቹን። ሄድኩኝ። ቁጭ በልና ብላው አለኝ። በሆቴል ሕግ ከእንግዳ ጋር ቁጭ ብሎ መብላት አይቻልም ስለው፤ አልጣፈጠኝም ቁጭ ብለህ ብላው አለኝ። ሰውየው ሬስቶራንት ውስጥ ግርግር እየፈጠረ ስለነበር ማረጋጋት ነበረብኝ። ቁጭ ብዬ ያዘዘውን ስቴክ ቀመስኩት። ምንም ችግር አላገኘሁበትም። ግን ሰውየውን ለማስደሰትና ለማረጋጋት ትክክል ነህ ጌታዬ፤ ይህ ነገር መቀየር አለበት አልኩና ስሄድ፣ እኮ እኮ ብሎ በጣም ደስ አለው። ወደ ምግብ ማብሰያ ክፍል ሄደን ግማሽ የእሱን ስቴክና ሌላ ስቴክ ጨምረን ላክልነት። ከዛ ኪችን ድረስ ነው ለምስጋና የመጣው። አመስግኖኝ ቲፕ ጉርሻ ሄደ። አንተው ሰርተኸው ያልጣፈጠህ ምግብ አለ አዎ። እኔ ሠርቼው ሳይፍጠኝ፤ ብዙ ሰው የጣፈጠው ምግብ አለ። ውስጤ ስለማይቀበለው ሜኑ የምግብ ዝርዝር ላይ እንዲወጣና እንዲሸጥ አልፈልግም። በአንድ ወቅት ኪችን ውስጥ ሾርባ ሠርተን እኔ አልወደድኩትም ነበር። ረዳት ሼፌ ግን በጣም ወደደችው። ሌሎች የ ኪችን ሰዎችም ወደዱት። በኋላ ኃላፊውን አቀመስነው። ዋው አለ። ሜኑ ላይ መውጣት አለበት ሲል ወሰነ። እኔ ግን ውስጤ ስላልተቀበለው ፈራሁ። ላንተ ምግብ አዘገጃጀት ሳይንስ ነው ጥበብ ከባድ ጥያቄ ነው። ሳይንስን ከጥበብ ያቀናጀ ሙያ ነው። ሳይንሱን የማትከተል ከሆነ ተመጋቢ ትጎዳለህ። ተመጋቢ ለመመገብ አፉን የሚከፍተው እኛን አምኖ ነው። ስለዚህ መታመን አለብን። ክቡር ለሆነው የሰው ልጅ የሚቀርበውን ምግብ ለመሥራት ሳይንሱን መከተል ያስፈልጋል። በየትኛው መንገድ ባበስለው ነው ጤናማ የሚሆነው ብለን ሳይንሱን ካላወቅንና ካልተከተልን ከባድ ነው። ከዚያ ደግሞ መጀመሪያ የሚመገበው ዓይን ነው። ስለዚህ አርቲስቲክ ጥበብ የተሞላው ነገር ይፈለጋል። አበሳሰሉ፣ አቀራረቡም ማማር አለባቸው። ስለዚህ ለኔ የምግብ ዝግጅት ሳይንስና ጥበብን ያቀናጀ ሙያ ነው። ተያያዥ ርዕሶች
የላሙ ፕሮጀክት ቦርድ አባላት በኢትዮጵያ ጉብኝት ሊያደርጉ ነው
ግንቦት አምባሳደር መለስ አለም እና የላሙ ፕሮጀክት ዳይሬክተር ጄኔራል ሲልቪስተር ካሱኩ የላሙ ኮሪዶር ልማት ፕሮጀክት የቦርድ አባላት በኢትዮጵያ ጉብኝት ሊያደርጉ መሆኑን በኬንያ የኢትዮጵያ ኤምሳሲ አስታወቀ። በፕሮጀክቱ ዳይሬክተር ጄኔራል ሲልቪስተር ካሱኩ የሚመራው ይህ የልዑክ ቡድን፤ ከሚያዚያ እስከ ግንቦት ቀን ዓ ም በኢትዮጵያ በሚያደርገው ቆይታ ከተለያዩ የመንግሥት አካላት ጋር ውይይት ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል። በዚህ ጉብኝት ላይ የሚሆኑ አባላት የላሙ ኮርደር ልማት የደረሰበትን ደረጃ በተመለከተ ከኢትዮጵያ የመንግሥት ኃላፊዎች ጋር የሚወያይ ሲሆን በተጨማሪ በኬንያ በኩል የደረሰበትን ደረጃ ማብራሪያ እንደሚያቀርብ ኤምባሲው አስታውቋል። አይ ኤስ በጀነራል ካሊፍ ጦር ላይ ጥቃት ሰነዘርኩ አለ ከኬንያ የውጭ ጉዳይ የኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር፣ የላሙ ጉዳዮች ባለስልጣን እና የሌሎች ተቋሞች ኃላፊዎችን ያከተተው ይህ ቡድን፤ በኢትዮጵያ የሚገኙ የኢንዱስትሪ ፓርኮችን እንደሚጎበኝ ተጠቅሷል። ላሙ ወደብ፣ ደቡብ ሱዳን እና ኢትዮጵያ ትራንስፖርት ኮሪዶር ላፕሴት በምስራቅ አፍሪካ ግዙፍ እና ብዙ ተስፋ የተጣለበት የመሠረተ ልማት ግንባታ ሲሆን፤ ኬንያ፣ ኢትዮጵያ እና ደቡብ ሱዳንን የሚያገናኝ ፕሮጀክት ነው። በፕሮጀክቱ የወደብ እና አየር ማረፊያ ልማት፣ ሦስቱን ሃገራት የሚያገናኙ የባቡር መስመር እና መንገድ ግንባታ፣ እንዲሁም ነዳጅ ማስተላለፊያ ቱቦዎች ዝርጋታ ተካተውበታል። በኬንያ የኢ ፌ ዲ ሪ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር መለስ ዓለም እና የላሙ ፕሮጀክት ዳይሬክተር ጄኔራል በቅርብ በሚመረቀው የላሙ ወደብ የመርከቦች ማቆያ ዙሪያ ተወያይተዋል። የላሙ ወደብ ልማት የአካባቢው አገሮች ኢኮኖሚ ለማስተሳሰር አስፈላጊ በመሆኑ ኢትዮጵያ ለስኬታማነቱ እንደምትሰራ አምባሳደሩ ገልፀውላቸዋል። ዳይሬክትር ጄኔራሉ በላሙ ሦስት የመርከቦች ማቆያ ሥራ እየተፋጠነ መሆኑን ገልፀው ይህም የኢትዮጵያን ተጠቃሚነት ያረጋግጣል ብለዋል። ቢቢሲ ማስተባበያ
ከነፍስ የተጠለሉ የድምፃዊት ዘሪቱ ከበደ ዜማዎች
ሴፕቴምበር አጭር የምስል መግለጫ ድምጻዊት ዘሪቱ ከበደ በመድረክ ላይ ሥራዋን ስታቀርብ ዘሪቱ ከበደ አርተፊሻል በተሰኘው ነጠላ ዜማ ውስጥ ስሜታችን አርተፊሻል ሰው ሰራሽ ፣ ምኞታችን አርተፊሻል፣ ውበታችን አርተፊሻል፣ ሕይወታችን አርተፊሻል ስትል ማኅበራዊ ትዝብቷን ታጋራለች። ድንዛዜ፣ አልበዛም ወይ መፋዘዙ ነቃ በሉ፣ አልበዛም ወይ ማንቀላፋት ኃላፊነትን መዘንጋት ስትል ትጠይቃለች፤ ዘሪቱ በዚሁ ሥራዋ ውስጥ ድንዛዜ በወሬ፣ ያለጥቅም ያለ ፍሬ ድንዛዜ በጭፈራ፣ ያለ ዓላማ ያለ ሥራ ድንዛዜ በከተማ፣ ሰው የሰው ብቻ እየሰማ ስትል የሰላ ትችቷን ታቀርባለች። ዘሪቱ በሊቢያ አንገታቸውን በተቀሉ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች የተሰማትን ቁጣ በገለፀችበት ነጠላ ዜማዋ ላይ ሠይፍህን አንሳ ስትል አቀንቅናለች። ሠይፍህን አንሳ፣ ያበራልሃል ለጠላት መልሱን ያስተምርሃል ሠይፍህን አንሳ፣ ትረፍ ከበቀል ኃይል ይሆንሃል እንድትል ይቅር፤ ስትል ለበደሉ ይቅርታ ማድረግን ትሰብካለች። ዘሪቱ የምንኖርበትን ዓለም አሁን በብርሃን አይቼሻለሁ ብላ መጠየፏን በገለፀችበት ሥራዋ፤ የነበረችበትበን የሕይወት መልክና ልክ ስትገልፅ ማለለ፣ ልቤ ማለለ፣ ታለለ፣ ልቤ ታለለ ሳተ ከቆመበት ተንከባለለ እያለች ታንጎራጉራለች። ለመጨረሻ ጊዜ ያየሁት በትንሳኤ በዓል ነበር የብርጋዴር ጄነራል አሳምነው ፅጌ እናት ድምፃዊት ዘሪቱ በተለያየ ጊዜ በሠራቻቸው እነዚህ ነጠላ ዜማዎች ማኅበራዊ ትችቷን፣ የሕይወት አቋማን ገልጻለች። አርተፊሻል የተሰኘውና ለአካባቢ ጥበቃ እንደተሠራ የምትናገረው ሙዚቃ፣ ሠይፍህን አንሳ የተሰኘውና በሊቢያ አንገታቸውን በአክራሪ ኃይሎች ለተቀሉት ኢትዮጵያውያን ያቀነቀነችው እንዱሁም ውሸታም የተሰኘ ሙዚቃዋ ውስጥ ዓለምን መጠየፍ ይታያል። ዘሪቱ ከእኛ ጋር ለመጨዋወት ፈቅዳ ስትቀመጥ ያቀረብንላት ጥያቄዎችም እነዚሁ ሥራዎቿን የተመለከቱ ናቸው። ቃለ መጠይቁን ከመጀመራችን በፊት ዘሪቱ ጠቆር ያለ ማኪያቶ አዛ እንዲህ አወጋን ቢቢሲ፡ እነዚህ ሦስት ሥራዎች አርተፊሻል ፣ ሠይፍህን አንሳ ፣ እንዲሁም ውሸታም እርስ በእርሳቸው ግንኙነት አላቸው ዘሪቱ፡ የእርስ በእርስ ግንኙነታቸው የኔ መሆናቸው ነው። ሳቅ ከዚያ ውጪ ግን ያው እኔ የትኛውንም ሥራ ስሠራ ወይ ከሕይወቴ ነው፤ ወይ ከማየው ነገር፣ ከተነካሁበት ነገር ተነስቼ ነው የምደርሰው። ስለዚህ ከእኔ ጋር ግንኙነት አለው። መጀመሪያ አርተፊሻል የሚለው ነጠላ ዜማ ሲወጣ ለአካባቢ ጥበቃ ተብሎ አንደተሠራ ተነግሮ ነበር። ነገር ግን ሥራውን ልብ ብሎ ላደመጠው፤ የአካባቢ ጥበቃ ላይ የሚያተኩር አይመስልም። ዘሪቱ፡ ልክ ነው መነሻው እንደዛ ነው። በዚያ ሰዓት ብሪቲሽ ካውንስል የክላይሜት የአየር ጠባይ ለውጥ አምባሳደር ብሎ ከመረጣቸው አርቲስቶች ውስጥ ድምፃዊ እኔ ነበርኩ። በዚያ ሰዓት ኢትዮጵያ አረንጓዴ የሚባል ኢኒሼቲቭ ከሚካኤል በላይነህና ከመሐመድ ካሳ ጋር ጀምረን ለመንቀሳቀስ እንሞክር ነበር። እና በሆነ መንገድ ግንኙነት አለው አርተፊሻል የተሰኘው ስራ ከአካባቢ ጥበቃ ጋር ። በአንድ የጦር አውድማ ላይ ከወላጅ አባቷ ጋር የተፋለመችው ታጋይ ግን አርት ፕሮሰሱ ውስጥ የምትረካበትን ነገር ትፈልጋለህ። ስለዚህ ብሪቲሽ ካውንስል ከአካባቢ ጥበቃ ጋር ተያይዞ አንድ ሙዚቃ ይሠራ ብለው ኢንቨስት ገንዘብ ያወጡበት ያደረጉበት ፕሮጀክት ነው። ግን ምንድን ነው፤ ዳይሬክትሊ በቀጥታ ያንን ጉዳይ ብቻ የሚወክል ሥራ ለመሥራት ተሞክሮ የሚያረካ አልሆን አለ። እና በአጋጣሚ እዚያው ፕሮሰሱ ውስጥ እያለሁ አርተፊሻል የሚለውን ሙዚቃ ፃፍኩት፤ በአጠቃላይ የአካባቢ ጥበቃንም ይመለከታል። ከሁሉም በላይ ግን ተፈጥሮ ውስጥ ሰውም አለ። ስለዚህ ሰውን ጥበቃ ሳቅ ላይ የበለጠ የሚያተኩር ሥራ ሊወለድ ችሏል ማለት ነው። ወደ አውሮጳ ለመሻገር በስደት ላይ እያሉ በሊቢያ አንገታቸው ስለተቀሉ ወጣቶች የሠራሽውደግሞ ሠይፍህን አንሳ ይሰኛል። ለዚያ ሥራ መወለድ አንቺ ውስጥ የነበረው የወቅቱ ስሜት ምን ይመስል እንደነበር እስቲ አስታውሺኝ። ዘሪቱ፡ ኡ ሠይፍህን አንሳ ከከባድ ስሜት ውስጥ ነው የተወለደው። በዚያ ሰዓት በእነዚያ ወጣቶች ላይ የደረሰው ነገር በጣም ያስፈራ ነበር። በጣም ያስቆጭ ነበር። እልህ ያሲይዝ ነበር። ቁጣ እንዴት ብለህ ነው የምትገልፀው ቁጣ ወገን ናቸው፤ የሰው ልጅም ናቸው። በጣም ተገቢ አይደለም። ስለዚህ በጣም ቁጣ ተሰማኝ፤ በውስጤ። ከዚያ ቁጣ በኋላ ግን የትም ልሄድ አልችልም። ምንም ላደርግ አልችልም። ያ ተስፋ መቁረጥ ደግሞ ሌላ የድባቴ መንፈስ፤ ስሜት አስከተለ። ያ ደግሞ የኔ ብቻ ሳይሆን አካባቢዬንም ሳይ ብዙዎቻችን ላይ ያየሁት፣ ሀገሪቱም ላይ፣ አየሩም ላይ የነበረው መንፈስ እንዴት ጨፍጋጋ እንደነበር አስታውሳለሁ። እና በረዥሙ ተንፍሳ የሆነ ነገር ማበርከት እንዳለብኝ ተሰማኝ። በአካባቢዬም በዚያ ስሜት ውስጥ አብረውኝ የነበሩ ወንድም እህቶቼ የሆነ ነገር ማካፈል እንዳለብን ተማመንና በዚያ ጉዳይ መፀለይ ጀመርኩ፤ ማሰብ ጀመርኩ። ስቱዲዮ ውስጥ፣ በዚያ ሰዓት ሳነበው የነበረው መጽሐፍ አለ፤ የሪክ ጆነር ዘ ቶርች ኤንድ ዘ ሶርድ ፣ የሚል መጽሐፍ፤ እዚያ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ያለውን የሠይፍ ምስል ሳየው መልዕክቱ እንደመጣልኝ ተሰማኝ፤ ገባኝ። ከዚያ ስቱዲዮ ውስጥ ነው ዴቬሎፕ ስራው የዳበረው መደረግ የጀመረው። በዓመቱ አነጋጋሪ ከነበሩ ጉዳዮች ጥቂቱ ከዚያ ዳዊት ጌታቸው የሙዚቃ መምህር፣ አቀናባሪና ዘማሪ ጋር ሄድኩኝ። ዳዊት ጌታቸው ሌላ ጊዜ መዝሙር ነው የሚሠራው፤ የእግዚአብሔር ፈቃዱ ሆኖ ይህንን ለመሥራት ፈቃደኛ ሆነ። እናም አብረን ልነሠራው ቻልን። እኔም ሆንኩ ምድሪቱ ከነበርንበት ከዚያ ስሜት ውስጥ ተስፋ ይሆናል፤ መፅናኛ ይሆናል መልስ ይሆናል ብዬ ያሰብኩበትንና የተቀበልኩትን መልዕክት ለማድረስ ነው የተሠራው። ሙዚቀኛ ዳዊትን ስትጠቅሺው ከዚህ በፊት መዝሙር ነው ይሠራ የነበረው አልሽኝ። ይህ ሥራ መዝሙር አይደለም ብለሽ ነው የምታምኚው ዘሪቱ፡ ሳቅ ነው፤ መንፈሳዊ ነው። የምልህ መነሻው መንፈሳዊ ነው። መነሻ የሆነኝም መጽሐፍ መንፈሳዊ ነው። ሠይፍ የሚለውም ቃል የእግዚአብሔርን ቃል፣ የእግዚአብሔርን ኃይል፣ የእግዚአብሔርን ምላሽ መወከሉ መንፈሳዊ ነው። ሃይማኖታዊ ግን አይደለም። ያ ነው ልዩነቱ እንጂ መንፈሳዊ ነው። ከእነዚህ ሥራዎችሽ በኋላ ደግሞ ውሸታም የሚለውን ሥራሽን ስታቀርቢ ዘሪቱ ዓለምን እየተጠየፈች ይሆን አልኩኝ እውነት ዓለምን እየተጠየፍሽ ነው ዘሪቱ፡ አርተፊሻል ፣ ከሁለቱ ዘፈኖች በተለየ በቀጥታ መንፈሳዊ አይደለም። ለምን መነሻው ማኅበራዊ ትዝብት ነው እንጂ ከመንፈሳዊነት የመነጨ አይደለም። መንፈሳዊ አይደልም ማለት ግን አይቻልም። ለምን እንድንሆን የሚመክረው፣ ወይም አልሆንም ብሎ የሚወቅሰው ማንነት፣ እንግዲህ እኔ የማምነው አምላክ፣ እንድንሆንለት ሽቶ በአምሳሉ ከፈጠረው ማንነት ውጪ ሆነናል ነው። ለምን በዚያ ማንነት ውስጥ ያለ ሰው አካባቢውን ይጠብቃል፤ ከሰዎች ጋር አብሮ ይሆናል። በስስት የተያዘ አይሆንም፤ ስለዚህ ሆነናል የተባሉት ነገሮች ሁሉ ሰው ስንሆን ከታለመልን፣ እንድንሆን ከታሰበልን ውጪ ሆነናል፤ ስለሆነም እንደ መንፈሳዊ መልዕክት ኳሊፋይ ያሟላል ያደርጋል ብዬ አስባለሁ። መነሻው ግን አይደለም። ሠይፍህን አንሳና ውሸታም ግን ከመንፈሳዊ ሕይወትና በቀጥታ ከመንፈሳዊ ማንነት ጋር የተገናኙ ናቸው ለእኔ። እና ዓለምን እየሸሽ ነው ዘሪቱ፡ ፈገግታ ያው ከዓለም ወዴት ይኬዳል ሳቅ ዓለማዊ አለመሆን ግን ይቻላል። የዓለም ውሸት፣ የዓለም ሽንገላ፣ ባታለለኝ ወቅት የጻፍኩት ነው። ባለማወቅ የምንሆናቸው ነገሮች አሉ። ካወቅን በኋላ ደግሞ ከእኛ የተሻለ ሲጠበቅ፣ መንገድ አሳይ መሆን ሲጠበቅብን፣ በተላላነት ተይዘን ፈገግታ እንደተሞኘን ሲገባን ፈገግታ ተመልሰን የማውቀውን ይሄንን ምን ነካኝ ብለን የዓለምንና የገዢዋን ሽንገላ ለማጋለጥና ከዚህ በኋላ አንስትም የሚለውን ሳቅ መልዕክት ለማስተላለፍ ነው። በፕሮቴስታንት እምነት ተከታይነቱ ለእስር ተዳርጎ የነበረው ኤርትራዊ ህይወቱ አለፈ ያዘዘችው ጠቆር ያለ ማኪያቶ መጥቶ ጭውውታችንን ለአፍታ አቋረጥን በስምሽ ከተሰየመው አልበምሽ ሌላ ባሉት ከእነዚህ ሦስት ስራዎችሽ ውጪ፣ አዝማሪ ነኝ የሚውም ሥራሽን ስንመለከት በሥራዎችሽ የሕይወት አቋምሽን እየተናገርሽና እያስቀመጥሽ ነው የምትሄጂው ማለት እንችላለን ዘሪቱ፡ ልክ ነው፤ እንደዚያ ነው። የመጀመሪያው ሥራዬ ዘሪቱ አልበም በወቅቱ የነበረኝ ማንነት ነው። በማንነቴ ሳድግ፣ መንፈሳዊነት በውስጤ ማደግ ሲጀምር፣ በዚያ መንገድ እያደግሁ ስመጣ ወይንም ደግሞ በዚያ መንገድ መጓዝ ስጀምር፤ ያው ያንኑ የሚመስል ነገር ነው የሚወጣኝ። ስለዚህ ከአሁን በኋላም ሕይወቴን የሚመስል፣ ያለሁበትን ቦታ የሚመስል ሥራ ነው ከእኔ የሚወጣው። አጭር የምስል መግለጫ ድምጻዊት ዘሪቱ ከበደ ስለዚህ ከአሁን በኋላ እየሠራሽ የምትቀጥይው የሕይወቴ መርሆዎች ናቸው የምትያቸውን ብቻ ነው ማለት ነው ዘሪቱ፡ በፊትም እንደዛ ነው። ሳቅ ምንም አዲስ ነገር አይደለም። ለምን እውነት ለኔ፣ ከመጀመሪያውም ቢሆን ጽሁፍም ሆነ ሙዚቃ፣ እውነትና ራሴን፣ ሕይወቴን፣ ታሪኬንና ኤክስፒሪያንሴን ልምምዴን ከማካፈል ጋር የተገናኘ ነው። ስለዚህ ማንነቴ በሚሄድበት አቅጣጫ፣ ሥራዬም እየተከተለ ይሄዳል። ለምን የሙዚቃ ስራን በሌላ መንገድ አላውቀውም። ወይንም በሌላ መንገድ ላበረክት የምችለውን፤ በጽሑፍም ሆነ በፊልም ሥራም ይሁን የማምንበትንና የሚመስለኝን፣ ለሰው ይጠቅማል ብዬ የማስበውን ወይንም መወከል አለበት ብዬ የማስበውን ማኅበረሰብ፤ ሆን ብዬና መርጬ ነው የማደርገው። እንጂ በዚህ አቅጣጫ የሆነ ነገር ቢፃፍ ገበያ ላይ የሆነ ነገር ያመጣል፣ ወይም ለኔ የሆነ ክብር ይጨምራል በሚል አይደለም። ስለዚህ ከሕይወቴ በማካፈል ነው የምቀጥለው። መርሄንም ይሁን፣ ኤክስፒሪያንሴንም ይሁን፣ አስቂኝ ገጠመኝም ይሁን፣ ጥበብ ስለሆነ ሁሉንም ሳጥን ሰርተን አናስቀምጠውም። አንዳንዱ ሥራ በማንጠብቀው ሁኔታ ይመጣል። አልበምሽ ውስጥ የማይረሱ አገላለጾች እና የቋንቋ አጠቃቀሞች አያለሁ። አሁን የምናወራባቸው ሥራዎች ላይ ግጥሞቹን ብንመለከት ጠንካራ ናቸው። ግጥምና ዜማ ላይ በጎ ተጽዕኖያሳረፈብሽ ባለሙያ አለ ዘሪቱ፡ እ ማንንም ሳላይ ነው መጻፍ የጀመርኩት። መጻፍ የጀመርኩት ከልጅነቴ ስለሆነ። በልጅነት ውስጥ ዝም ብዬ በዜማም ይሁን በግጥም ራሴን መግለጽ የጀመርኩት በተገኙ ርዕሰ ጉዳዮች ሁሉ ነው። በመጀመሪያ ወደ ሙዚቃ ለመሳቤ እነሴሊንዲዮን፣ ማሪያ ኬሪ፣ ዊትኒ ሂውስተን ምክንያት ናቸው። ወደ የሙዚቃ ግጥም አጻጻፍ ስንመጣ ትሬሲ ቻፕማን፣ ቦብ ማርሌና አላኒስ ሞርሴት መነሻዎቼ ናቸው። እነዚህ ሦስት አርቲስቶች ለዘፈን ጽሁፍ ወይም ደግሞ በዘፈን ውስጥ ለሚነገሩ መልእክቶች መነሻዬ ናቸው። አንድን ሰው፣ አንድን አርቲስት ያገኘሁት ያህል፤ አይደንቲቲውን ማንነቱን ፣ መልዕክቱን፣ ጉዞውን፣ ከለሩን፣ ከልጅነቴ ጀምሮ እንዳጣጥም እና እንዲገባኝ አድርገዋል። በተለይ አላኒስ ሞርሴት እኔ የምሞክራቸው ነገሮች ሴንስ ትርጉም እንዲሰጡ ያደረገች አርቲስት ናት። እና እነዚህ ናቸው የመጀመሪያዎቹ ተጽዕኗቸውን ያሳረፉብኝ ከዚያ በኋላስ ዘሪቱ፡ ከዚያ በኋላ በራሴ መንገድ ነው የሄድኩት። ግጥሞችሽን አይተው እነዚህ ለዘፈን አይሆንም ያሉ ነበሩ ዘሪቱ፡ እ ትንሽ አሰብ አድርጋ አይ እንደዚያ ሳይሆን፣ እንደውም በመጀመሪያዎቹ ስቱዲዮ ውስጥ በነበርኩባቸው ጊዜያት በጣም ቀላል ናቸው። ጠንከር ያለ የአማርኛ ግጥም መልክ የላቸውምና አይሆኑም ወይም አያስኬዱም የሚሉኝ ብዙ ሰዎች ነበሩ። ስላልሰሟኋቸው እግዚአብሔር ይመስገን ። ረዥም ሳቅ ። ግን ኤሊያስ በተለየ መልኩ ኢንካሬጅ ያበረታኝ ያደርገኝ ነበር። አቀናባሪ ኤሊያስ መልካ ዘሪቱ፡ አዎ ኤሊያስ መልካ። እንደውም እንደዚህም ይቻላል ለካ። እንደዚህ ነው መሆን ያለበት። ቀላል ሆኖ፣ ከዜማ ጋር ተዋህዶ፣ ሰው ኢንጆይ እንዲያደርገው ዘና እንዲልበት ብሎ ኢንከሬጅ አድርጎኛል አበረታቶኛል ። በመጀመሪያዎቹ ጊዜያት። ኤሊያስን ካነሳን አይቀር፣ ኤሊያስ አለ፣ በሕይወት የሌለው እዮብ አለ፤ ሌሎችም አሁን ስማቸውን ያልጠቀስኳቸው በእናንተ ክበብ ውስጥ ያሉ የሙዚቃ ባለሙያዎች አሉ። እነዚህን የሙዚቃ ሙያተኞች ስናይ፤ የዘመንሽን ሙዚቀኞች በሥራዎቼ በሚገባ ወክያለሁ፣ ገልጫቸዋለሁ ብለሽ ታስቢያለሽ ዘሪቱ፡ በረዥሙ ተንፍሳ እ እኔ በጣም ግለሰባዊ ነኝ መሰለኝ። ሳቅ የሆነን ወገን መወከሌ አይቀርም። ግን ከምንም በላይ እውነትን እና የራሴን ጉዞ እንደወከልኩ፤ በዚያ ውስጥ ደግሞ ብዙዎች የሚወዱህ ሰዎች በሆነ ያህል እንደተወከሉ የሚያስቡ ይመስለኛል። ስለዚህ እነርሱንም የወከልኩና ያሰማሁ ይመስለኛል። ለምንድን ነው እንደዚያ ያልኩት፤ በወንጌላውያን አማኝ ሙዚቀኞች ዘንድ የጦፈ ክርክር ነበር። ሙዚቃና ሙዚቀኝነትን፣ዓለማዊነትንና መንፈሳዊነትን በተመለከተ። በኋላም የዮናስ ጎርፌ ቤት ያጣው ቤተኛ የተሰኘ መጽሐፍ ታትሞ ተነቧል። ይህ የሚያሳየን ከወንጌላዊያን አማኞች የተገኙ ሙዚቀኞች፣ በመንፈሳዊ ዓለም ውስጥ ያላቸውን ስፍራ ለማፅናት፣ እዚህ ጋር ነው ስፍራችን ማለትን ያየሁ ስለመሰለኝ ነው። በዚያ ወቅት ደግሞ አንቺ ሥራዎችሽን በዚህ መልክ ስታቀርቢ እነዚህን ወገኖች ወክላ ይሆን የሚል ጥያቄ አድሮብኝ ነው ዘሪቱ፡ ከረዥም ዝምታ እና ማሰብ በኋላ ብዬ አምናለሁ። ተወክለው ከሆነ እነርሱ ያውቃሉ ይመስለኛል። የአንድ መንፈሳዊ ሰው ሕይወት እኮ አይከፋፈልም። አንድ ሰው መንፈሳዊ ነኝ ካለ በማንኛውም ጊዜ በዚያ ማንነት ውስጥ ነው ሊሆን የሚገባው። በጨዋታም ጊዜ፣ በሥራም ጊዜ፣ በፀሎትም ጊዜ፣ በሁሉም ጊዜ በመንፈሳዊ ማንነት ውስጥ ነው መቆየት ያለበት። ያ መንፈሳዊ ማንነት ደግሞ የሆነ ኃይማኖታዊ መልክ አይደለም። መልካምነት፣ ፍቅር፣ ርህራሄ፣ ሰላም፣ በጎ የሆነ ነገር ሁሉ መንፈሳዊ ነው ብሎ መደምደም ባይሆንም፤ ምክንያቱም ማስመሰልም ስላለ። ግን ሥራዬ መንፈሳዊ ካልሆነ፣ ወይ ከመንፈሳዊነት የሚያጎለኝ ከሆነ፣ ከመንፈሳዊነት የሚጋጭ ከሆነ፣ ባላደርገው ነው የሚመረጠው። ስለዚህ እንደማይጋጭ እያመንኩ ነው እያደረኩት ያለሁት። ዘሪቱ ራሷን ከሙዚቃ ውጪ በምን በምን ትገልፃለች ዘሪቱ፡ ፋሽን ደስ ይለኛል። ስታይል መቀየር ያዝናናኛል። ልንዝናናም ደግሞ ይገባናል። ቁም ነገር የሆኑት ነገሮች እንዳሉ ሆነው፣ በምድር ላይ እስካለን ድረስ የሚያዝናኑን ነገሮች አሉ። ጉዳት የለውም። ስለዚህ በእርሱም ራሴን ኤክስፕረስ አደርጋለሁ እገልጻለሁ ። በተሰማኝ ጊዜ። ሙሉ በሙሉ በእዚያ ማንነት ውስጥ የምኖር ሰው አይደለሁም። ዝም ብዬ ስዘንጥ የምኖር ሰው አይደለሁም። ሳቅ ዘናጭ አይደለሁም። የሙሉ ጊዜ ዘናጭ ረዥም ሳቅ ልክ አሁን ስንገናኝ እንደለበስሽው ቀለል ያለ አለባበስ፣ ጅንስ ሱሪ፣ በሸራ ጫማ በጃኬት ዘሪቱ፡ አዎ ብዙ መታየትም አልወድም። ግን አንዳንዴ ደግሞ ያኛውም ጎን አለኝ። ለወጥ ብሎ፣ ተጫውቶ እንደጨዋታ ነው የማየው። መለስ ብሎ ደግሞ ወደ ተረጋጋው የዘወትር መልኬ ሳቅ በእሱ እጫወታለሁ። ባለኝ በሚያስደስተኝ ሁሉ ራሴን ኤክስፕረስ አድርጌ ገልጬ ሰዎችን ፈገግ አድርጌ፣ አዝናንቼ፣ አካፍዬ ማለፍ ነው የምፈልገው። ትርፍጊዜሽን በምን ማሳለፍ ነው ደስ የሚልሽ ዘሪቱ፡ የሚያስደስተኝ ነገር ወይ ከሥራዬ ጋር የተያያዘ ነው ወይ ከቤተሰቤ ጋር የተያያዘ ነው። ስለዚህ ትርፍ ጊዜ ቢኖረኝም ያንኑ የሚያስደስተኝን ነገር አደርጋለሁ። ወይ አነባለሁ፣ ወይ አጠናለሁ፣ ወይ ከልጆቼ ጋር እሆናለሁ። ፊልም እመለከታለሁ። በሙዚቃ እዝናናለሁ። ትርፍ ጊዜዬም ሥራዬም ተመሳሳይ ነው። ይዘቱ ከቤተሰቤ ራቅ ያለ ነገር አይደለም። በአጠቃላይ ትርፍ ጊዜ ነው ያለኝ ማለት ነው። ሳቅ አጭር የምስል መግለጫ ድምጻዊት ዘሪቱ ከበደ ከሦስት ልጆቿ ጋር ለሁለተኛአልበምሽመዘግየት ምክንያት የሆነውእናት መሆንሽ ነው ዘሪቱ፡ አይደለም። በፍፁም ምንም ግንኙነት የለውም። እንዲሁ የሕይወት ጉዞ፣ ዝግጁ አለመሆን፣ ከራስ ማንነት መሠራት፣ መስተካከል፣ ከዚያ ያንን መፈለግ፤ ከዚያ ትክክለኛው ለጥበብ ምቹ የሆነ ኢነርጂ ኃይል ፣ ፓርትነርሺፕ አጋር አለመመቻቸት፣ ወይ ጊዜው አለመሆን፣ ያ ያ ነው። አብዛኛው ጊዜዬ በስራ ነው የሚያልፈው። ብዙ ሥራም እሠራለሁ። በፊልምም ብዙ ሠርቻለሁ። እናትነት በጣም ቢዚ ባተሌ አድርጎኝ አይደለም። እናትነት ጊዜ ቢወስድም ሙዚቃን ለመሥራት ይኼን ሁሉ ዓመት የሚያስቸግር አልነበረም። ምክንያቱ እርሱ አይደለም። ስንት ፊልሞች ላይ ተሳተፍሽ ዘሪቱ፡ ከ ቀሚስ የለበስኩለት በኋላ ይህ የራሷ ድርሰት ነው ፣ የቅድስት ይልማ ሥራ የሆኑት መባ እና ታዛ ላይ በትወና ተሳትፌያለሁ። ከዚያ አሁን በቅርቡ የወጣ ወጣት በ የሚል ፊልም አለ። አሁን ደግሞ በቅርቡ የሚወጣ ስዊትነስ ኢን ዘ ቤሊ የሚል የዘረሰናይ ብርሃኔ መሀሪ ፊልም አለ። እስካሁን እነዚህ ናቸው። ልክ እንደ ሙዚቃሽ በፊልሙም እኔ የምወክላት እንዲህ አይነት ገጸ ባህሪ መሆን አለባት ትያለሽ ዘሪቱ፡ አዎ። እንደዚያ ባይሆን መሳተፌ አስፈላጊ አይደለም። የምትመስለኝን፣ ልትወከል ይገባታል ብዬ የማምነውን፣ ብትታይ ይገባታል ብዬ የማምነውን ገፀ ባህሪ ወይም ላውቃት፣ መስያት ወይም ሆኛት፣ እርሷና አካባቢዋን ልወቅ ብዬ የመረጥኳትን ገፀ ባህሪ ወይንም ደግሞ ሊተላለፍ ይገባዋል የምለው መልእክት ካልሆነ በስተቀር ተሳትፎዬ ምንም ጥቅም የለውም። ስለዚህ እስካሁንም የተሠሩት ሁሉ እንደዚያ ናቸው። ከአሁን በኋላ ያንቺ ድርሰት የሆነ ፊልምእንጠብቅ ወይስ የሌሎች ሥራዎች ላይ ብቻ ነው የምትሳተፊው ዘሪቱ፡ አስባለሁ። ግን ያው በመጀመሪያ የፊልም ሙከራዬ በጣም ብዙ ነገር ውስጥ ስለተሳተፍኩ ደከመኝ ሳቅ ። ጥንካሬዬ በነበሩት ነገሮች በጣም ጠንካራ ነገር ባመጣም፤ ገና ያልተማርኳቸውና ያላወቅኳቸው ኤክስፒሪያንስ ልምድ የሚያስፈልጉኝ ነገሮች ነበሩ። ስለዚህ እነርሱን ለማግኘትና ለመለማመድ ስል ነው በተለያዩ ሰዎች ፊልም ውስጥ ተሳታፊ የሆንኩት። ጥሩ ልምድ እንዳለኝ አምናለሁ። ሀሳቦች አሉኝ። እንደውም ከዚህ በኋላ የማስበው የራሴን አይዲያ ሀሳብ ፣ የራሴን መልዕክት ብሠራ ነው። ግን መልካም ሆኖ የሚያስደስትና የሚጠቅም ሥራ ከመጣ የሌሎችን ሰዎችም እሠራለሁ። ዘሪቱ የተሰኘ አልበምሽ እንደወጣከነ ሄኖክ መሀሪ ጋርትልልቅየሙዚቃ ድግሶች አዘጋጃችሁ፤ ጉዞ ዘሪቱ የተሰኘ።እንደዚህ አይነት ቋሚ የሆነ የሙዚቃ ኮንሰርት የማዘጋጀት ሀሳብ የለም ዘሪቱ፡ አለ። ከአዲስ አበባ ወጥቶ በክልል ከተሞች ሥራዎችን ማቅረብ በጣም ነው የሚያስደስተኝ። ናፍቆት ስላለ ምላሹ በጣም አርኪ ነው። በመጀመሪያም ያደረግነው እርሱን ነው። መቼም የማይረሳን ጊዜና ታሪካዊ ልምድ ነው የሆነው። ከዚህ በኋላም ልናደርግ እናስባለን። ግን እንደሱ አይነቱን ነገር በሰፊው ለማድረግ ከአዲስ አልበም በኋላ ቢሆን የተሻለ እንደሚሆን በማመን ሳቅ ነው ያላደረግነው። ግን ባለንበት አካባቢ፣ በተመቻቸ ጊዜ ሁሉ እንጫወታለን። አዲስ አልበምሽ መቼ ይወጣል ዘሪቱ፡ ፀልይልኝ። ረዥም ሳቅ እየተሰራ ነው ባለቀ ጊዜ አልበምሽ ወጥቶ አንቺ ሥራዎችሽን በምታቀርቢበት ወቅት ያምቡሌ በጣም ዝነኛ ነበር። ዝግጅትሽን በምታቀርቢበት ስፍራ ላይ በተፈጠረ ጉዳይ ስምሽ በተደጋጋሚ ተብጠልጥሎ ነበር። ያኔ የተፈጠረውምን ነበር ዘሪቱ፡ ምንድነው የሆነው ከተወራው የተለየ ነገር የሆነ አይመስለኝም። አሁን በደንብ የኢትዮጵያ ሙዚቃ ውስጥ ዶሚኔት የተቆጣጠረው ያደረገው ሳውንድ ድምፅ ሲመጣ ያምቡሌ ቀዳሚው ሥራ ነበረ። በሙዚቀኞች አካባቢ እንደ ጨዋታ እያደረግን ብዙ እናነሳው ነበረ። እኔ ደግሞ በዚያን ሰዓት ልሠራበት እየተዘጋጀሁ በነበረበት የፕላቲኒየም ክለብ፣ እየተዘጋጀሁበት የነበረው ሥራ ያምቡሌ ን የማይመስል ወይንም ከኔም ሥራ ወጣ ያለ፣ ከ ፖፑላር ም ሥራ ወጣ ያለ፣ እንደ ጥበብ ሥራ ብቻ ልታጣጥመው የምትችል፣ ብዙ የተደከመበት፣ በጣም የተዋበ፣ አሁን ባለንበት ወቅት የተሻለ ተቀባይነት ያገኝ ነበር። እርሱን የሚመስሉ ብዙ ነገሮች አሉ። ሰው ኢንጆይ ያደረጋቸው። ያኔ ግን እሱ ቅንጦትና ቅብጠት ነበር የሚመስለው እንጂ በፈረንጅ ናይት ክለብ ጉራግኛ ሲደለቅ በፒያኖ የታጀበ ማለትሽ ነው ዘሪቱ፡ በፒያኖ ብቻ አይደለም። ፒያኖ፣ አፕ ራይት ቤዝም አለ። ፒያኖም አፕራይት ቤዝም ከሆነ ከዓመታት በኋላ ነው መድረክ ላይ የወጡት። በኢትዮጵያ ፖፑላር ሙዚቃ ውስጥ ብዙ ጊዜ የማንሰማቸው መሣሪያዎች፣ ለስለስ ያለ፣ ሴትአፑ ም ምኑም ወጣ ያለ ነበር። ያሰብነው ነገር በጣም እንደሚያምር ስላወቅን ምላሹን ለመቀበል ከበደን መሰለኝ። ያው በልጅነትና ባለማወቅ ውስጥ የተመልካቹ ጥፋት እንዳልሆነ ለመረዳት አልቻልኩም ነበር ። በእርግጥ በትክክል ፕሮሞት እንዳልተደረገ እንዳልተዋወቀ የተረዳሁት ቆይቼ ነው። ስለዚህ የመጡት ሰዎች ጥፋት አይደለም። በወቅቱ እንዴት ይሄ አይገባቸውም በሚል ነው እንጂ፤ ቢያውቁና ቢጠብቁ የሚፈልጉት ሰዎች ይመጡ ነበር። እና በአንድ መንገድ ለጥበብ የተደረገ ትግል ስለሆነ ያቺን ልጅ እኮራባታለሁ። በሌላ ወገን ደግሞ ያለመብሰልና ያለማስተዋል ውጤት ነው። ለዛ ነው እንግዲህ ይሄ ካልገባችሁ እንግዲህ ያው ያምቡሌ ይሁንላችሁ ብላ ያለፈችው። ያቺኛዋ ስትይኝ አሁን ያቺ የድሮዋ ዘሪቱ የለችም እያልሽኝ ነው ዘሪቱ፡ መስዋዕትነት ነው እና ያቺኛዋን ዘሪቱም ነኝ። ግን አሁን እንደዛ የማደርግ አይመስለኝም። ማንን መቆጣት እንዳለብኝ የማውቅ ይመስለኛል። ሰሞኑን እያነበብሽ ያለሽው መጽሐፍ አለ ካለ ምንድን ነው ዘሪቱ፡ ኦ መጽሐፍ ነው፤ ይገርምሀል አንድ ጓደኛዬ ይህንን መጽሐፍ ሰጠኝና በቀኟ በኩል ካስቀመጠችው ቦርሳዋን ከፍታ ከመጽሐፍ ቅዱስና ማስታወሻ ደብተሯ ጋር አብሮ ተቀምጦ የነበረ መጽሐፍ በማውጣት ዘ ግሬተስት ፖወር ኢን ዘ ወርልድ ይላል። የካትሪን ኩልማን መጽሐፍ ነው። እርሱን ነው እያነበበብኩ ያለሁት። አሁን እየተነበበ ያለው ይህ ነው። ሳቅ ሰሞኑን የምታደምጪውስ ሙዚቃ ምንድን ነው ዘሪቱ፡ ሰሞኑን ምንድን ነው የማዳምጠው እንደማሰብ አለችና ብዙ መዝሙር እየሰማሁ ነው። ታሻ ኮምስ የምትባል ዘማሪ አለች። እርሷን በጣም እየሰማሁ ነው ። ኢሊቬሸን ወርሺፕ እነርሱንም በጣም እሰማለሁ። አሁን የዘሩባቤል አልበም ወጥቷል። እርሱንም እየሰማሁ ነው። ሳቅ ለአንቺ አዲስ ዓመት የሚሰጠው ስሜት ምንድን ነው ዘሪቱ፡ አዲስ ዓመት ደስ ይለኛል። ኢንከሬጅመንት ማበረታታት ፣ ተስፋ፣ መለስ ብሎ ሪፍሌክት አድርጎ መለስ ብሎ መቃኘት ፣ ያለፈውን ዓመት ጉዞ፣ ፕሮግረስ ለውጥ ያው ሁሉም ነገር በዓመት ባይከፋፈልም፤ የሕይወት ጉዞን እንዲሁ ለማየት ግን ደስ ይላል። በአዲስ ተስፋ በደስታ የምቀበለው ጊዜ ነው። አንዳንዴ በዓመት ውስጥ ብዙ አዲስ ዓመቶች እናሳልፋለን። ሳቅ ሁሌ ዓመት አንጠብቅም። ግን ኢንጆይ አደርገዋለሁ። ለአድናቂዎችሽ የአዲስ አመት መልዕክት አለሽ ዘሪቱ፡ ሰላም ይሁኑ ሰላም ይሁንላቸው ይብዛላቸው ከራሳቸው ጋር መሆን፣ ለሰው መሆን ይሁንላቸው ደስታ ይብዛላቸው ፍቅር ይብዛላቸው የምትወጂው ጥቅስ የቱ ነው ዘሪቱ፡ የምወደው ጥቅስ የቱ ነው አሰብ አድርጋ በሕይወቴ ውስጥ በጣም ብዙ ጥቅስ ከማስተናገዴ የተነሳ ረዥም ሳቅ አሁን አልከሰት አለኝ። ተያያዥ ርዕሶች
በአዲስ አበባ ከተማ ከ ዓመታት በላይ አፋን ኦሮሞ በማስተማር ብዙ ውጣ ውረዶችን ያሳለፉት መምህር
ኦክተውበር ማጋሪያ ምረጥ አጭር የምስል መግለጫ መምህር ተፈራ በዳግማዊ ሚኒሊክ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አፋን ኦሮሞን ያስተምራሉ ስሜ ተፈራ ተኤራ ይባላል። አንዳንድ ሰዎች አምባሳደር እያሉ ይጠሩኛል። ይህን ስም አፋን ኦሮሞን በማስተማሬ ደስተኛ የሆኑ ሰዎች ናቸው ያወጡልኝ። በ ዓ ም ከአሁኑ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የንግድ ሥራ ኮሌጅ በሒሳብ አያያዝ በዲፕሎማ ተመርቄያለሁ። ለጥቂት ዓመታትም በሒሳብ አያያዝ ሙያ ሠርቻለሁ። ከልጅነቴ ጀምሮ ለኦሮሞ ቋንቋና ባህል ጥልቅ ፍቅር ነበረኝ። የሒሳብ ሥራ ሙያዬን እርግፍ አድርጌ በመተው ለብዙ ዓመታት ለመስራት ስመኝ የነበረውን ስራ ጀመርኩ። አጭር የምስል መግለጫ መምህር ተፈራ ተኤራ በ ዓ ም አፋን ኦሮሞ የክልሉ የሥራ ቋንቋ እንዲሆን ከተወሰነ በኋላ አፋን ኦሮሞን የሚያስተምር መፅሐፍ እጄ ገባ። ከዛም ከሌሎች ሰዎች ጋር በመሆን ከኦሮሚያ ባህል እና ቱሪዝም ቢሮ ፍቃድ በመውሰድ በባልቻ አባ ነፍሶ ትምህርት ቤት ውስጥ ማስተማር ጀመርን። ከእኔ ጋር ማስተማር ጀምረው የነበሩት ጓደኞቼ በፖለቲካ እና በተለያየ ምክንያት ለትንሽ ጊዜ ካስተማሩ በኋላ ማስተማራቸውን ለማቋረጥ ተገደዱ። በእኔ ላይም ይደርስ የነበረውን የተለያየ ጫና ተቋቁሜ ማስተማሬን ቀጠልኩ። ባለፉት ዓመታት አፋን ኦሮሞን በማስተማሬ ደስተኛ ያልነበሩ ሰዎች ብዙ ስሞችን አውጥተውልኛል። ቁቤ፣ ላቲን፣ ኦሮሚያ፣ ወሬ እና ሌሎችም ብዙ ስሞች ወጥተውልኝ ነበር። አንድ ቋንቋ ሊያድግ የሚችለው የቋንቋ ተናጋሪዎችስለተናገሩት ብቻ ሳይሆን የሌላ ብሔር ተወላጆችም ቋንቋውን መናገር ሲችሉ እንደሆነ ጥልቅ እምነት አለኝ። ለዚህም ነው መማር የሚፈልጉትን በሙሉ ሳስተምር የኖርኩት። ሰዎች አፋን ኦሮሞን ማንበብ እና መጻፍ እንዲችሉ አስተምራለሁ። በባልቻ አባ ነፍሶ ኛ ደረጃ ት ቤት ውስጥ ከ ዓ ም ጀምሮ ለ ኛ ዙር እያስተማሩ ነው ከ ዓ ም ጀምሮ ደግሞ በሚኒሊክ ት ቤት ለ ኛ ዙር በማስተማር ላይ ይገኛሉ። እስከአሁን ድረስም በወር ብር ብቻ በማስከፈል እያስተማርኩ እገኛለሁ። ማስተማር ስጀምር የነበረው ዋጋ አሁንም አልተቀየረም። በርከት ያሉ ጋዜጠኞች፣ መምህራን፣ ሃኪሞች፣ መሃንዲሶች እንዲሁም የመንግሥት ባለስልጣናት እኔ ጋር መጥተው ተምረዋል። ባለፉት ዓመታት ቋንቋውን በማስተማሬ ብዙ ችግሮችን አሳልፌያለሁ። ማስተማሬን እንዳቆም የተለያዩ ዛቻዎች እና ማስፈራሪያዎች ይደርሱኝ ነበር። በስለት ተወግቼያለሁ፤ የተፈራ ቁቤ ይወድማል ተብሎም ቤቴ በር ላይ ተለጥፏል። በዛ አስቸጋሪ ወቅት ተማሪዎቼ ነበሩ እስከ ቤቴ ድረስ የሚሸኙኝ። አፋን ኦሮሞ አሁን ተፈላጊ ሆኗል የተፈራ ቁቤ ይወድማል ሲሉ የነበሩ፤ ዛቻዎችን እና ማስፈራሪያዎችን ሲልኩ የነበሩ ሰዎች ራሳቸው ዛሬ ላይ አፋን ኦሮሞ አስተምረን እያሉ ነው። አጭር የምስል መግለጫ ትምህርታቸውን ካጠናቀቁ ተማሪዎችጋር ይህም ቋንቋችን ምን ያህል ተፈላጊ እየሆነ እንደመጣ ያሳየኛል። አሁን ጊዜው ተቀይሯል። በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎችን የኦሮሞን ቋንቋና ታሪክ አስተምሬያለሁ። ዘንድሮ በአዲስ አበባ በአፋን ኦሮሞ የሚያስተምሩ ት ቤቶች በመከፈታቸው አጅግ ደስተኛ ነኝ። ድካሜም ከንቱ አልቀረም። በለፉት ዓመታት በስራዬ መልካም የሚባል ጊዜን ባላሳልፈም፣ በህይወቴ የሚያኮራኝን ተግባር የመፀምኩባቸው ዓመታት ናቸው። እድሜዬ ወደ እየተጠጋ ነው። እርጅናም እየተጫጫነኝ ነው። አሁን የምፈልገው ሥራዬን ተረክበው የሚያስቀጥሉ ወጣቶችን ነው። ተያያዥ ርዕሶች
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በተፈፀመ ጥቃት ሰዎች ሞቱ
ኤፕረል ስለ ማጋራት ተጨማሪ ያጋሩ ማጋሪያ ምረጥ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል፤ መተከል ዞን፤ ዳንዱር ወረዳ ላይ በተፈፀመ ጥቃት ሰዎች መገደላቸውን የአማራ ክልል የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ ቤት ኃላፊ አቶ አሰማኸኝ አስረስ ለቢቢሲ አስታወቁ። በስልክዎ ታካሚና አካሚ እናገናኛለን ሥራ ፈጣሪው ወጣት ግጭቱ ሚያዚያ ዓ ም የተፈጠረ ሲሆን በጫኝና አውራጅ ሥራ በተሰማሩ ሁለት ግለሰቦች ግላዊ ጠብ ሰበብ እንደሆነ ተናግረዋል። ኃላፊው እንደሚሉት በጊዜው የነበረው ፌደራል ፖሊስ የሁለቱን ግለሰቦች ግጭት ለማረጋጋት ሲሞክር በመካከል አለመግባባት ተፈጥሮ በተተኮሰ ጥይት አንድ የጉሙዝ ተወላጅ ሕይወቱ ሊያልፍ ችሏል። ከዚህ በኋላ ግጭቱ እንደተባባሰ ኃላፊው ያስረዳሉ። በክልሉ አንድ ጉሙዝ ከተገደለ፤ የቆዳ ቀለማቸው ቀላ ያሉ ሰዎችን የመግደልና የመበቀል ጎጂ ልማዳዊ ድርጊት አለ የሚሉት አቶ አሰማኸኝ፤ በዚህም ምክንያት በየቦታው ያሉ የአማራ ክልል ተወላጆች ላይ ግድያና ንብረቶቻቸውን የመዝረፍ ጥቃት ተፈፅሞባቸዋል። አቶ አሰማኸኝ ቱ ሰዎች በምን አይነት ሁኔታ ተገደሉ ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ፤ በአከባቢው በቀስት እና በጥይት ሰዎችን የመግደል ልማድ አለ። ይሁን እንጂ እኚህ ሰዎች በምን አይነት ሁኔታ እንደተገደሉ የሚያሳይ ዝርዝር መረጃ የለኝም ብለዋል። ግጭቱ ለተከታታይ አራት ቀናት የዘለቀ ሲሆን የ ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተረጋግጧል። ከእነዚህ መካከል አስራ አንዱ የአማራ ክልል ተወላጆች ሲሆኑ ስድስቱ የእዚያው አካባቢ ተወላጆች መሆናቸውን አቶ አሰማኸኝ ተናግረዋል። ለጊዜው ጉዳት ያጋጠማቸው ግለሰቦችን ቁጥር በእጃቸው ባይገኝም ጥቃቱ በተበታተነና በተለያየ አካባቢ በመፈፀሙ የሟቾቹ ቁጥር ሊጨምር ይችላል ብለዋል። አቶ ገዱም ሆነ ደመቀ እኛም ብንፈተሽ ግድፈት አለብን ማለታቸውን አስታውሳለሁ የአቶ ታደሰ ጥንቅሹ ባለቤት በግጭቱ ስጋት ያደረባቸው ሰዎች እንጂ የተፈናቀሉ ሰዎች አለመኖራቸውም አክለዋል። በአካባቢው የፌደራልና የመከላከያ የፀጥታ ኃይሎች እንዲገቡ የተደረገ ቢሆንም አካባቢው ጫካና የተበታተነ የአኗኗር ስርዓት በመኖሩ ለማረጋጋት ቀናት ሊወስድ ችሏል ብለዋል አቶ አሰማኸኝ። ትናንት ሌሊት ፓዊ ወረዳ፤ አባውርኛ ቀበሌ ላይ የሚሆኑ የአካባቢው ተወላጅ ቤቶች የተቃጠሉ ሲሆን ዛሬ ሌሊት በአንፃሩ መረጋጋት እንደታየ ነግረውናል። የአማራ ክልል ከሚደግፋቸው ታዳጊ ክልሎች መካከል አንዱ የቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል መሆኑን የሚጠቅሱት ኃፊው በአካባቢው ባለ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች ምክንያት በአማራ ተወላጆች ላይ በተደጋጋሚ ጥቃት መፈፀሙን ኃላፊው ያስታውሳሉ። ይሁን እንጂ ይህንንም ለመከላከል የሁለቱ ክልል አመራሮች በቅርቡ በእንጂባራ ከተማ ተገናኝተው የመከሩ ሲሆን በጋራም እየሰሩ እንደሚገኙ ገልፀዋል። በዚህ ግጭት ሳቢያም በስጋት የሚፈናቀሉ ሰዎች እንዳይኖሩ ከሁለቱ ክልሎች የተውጣጡ ልዑካን ወደ አሶሳ እያመሩ መሆናቸውን ገልፀውልናል። የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባለስልጣናትን ለማነጋገር ያደረግነው ሙከራ ሳይሳካ ቀርቷል። ተያያዥ ርዕሶች
ኢትዮጵያውያን የሀጅ ተጓዦች በመካ እየተንገላቱ ነው
ኦገስት አጭር የምስል መግለጫ ያረፉበት ክፍል ጠባብና የማይመች ነው ዘይኑ ሻፊ መሀመድ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ መካ ያቀኑት ከ ዓመታት በፊት ነበር። ስፍራው ካለው የላቀ ሀይማኖታዊ ዋጋ አንጻር በመጓዛቸው ደስ ቢላቸውም፤ ለሀጃጆች የሚገባ መስተንግዶ ባለማግኘታቸው ቅር ተሰኝተው ነበር። ከዓመት ዓመት ለውጥ ይመጣል ብለው ተስፋ ማድረጋቸው ባይቀርም፤ ከ ዓመታት በኃላ ዘንድሮ ዳግም ወደ መካ ሲሄዱም ከበፊቱ የባሰ እንጂ የተሻለ መስተንግዶ አላገኙም። በዘንድሮው ጉዞ ከኢዲስ አበባ ተነስተው መዲና ከደረሱ በኃላ የጠበቃቸው መኝታ የማይመች ነበር። ለሁለት ቀናት በመዲና ቆይተው ወደ መካ ሲያመሩ ሁኔታዎች ተባባሱ። እንዲያርፉበት በተዘጋጀላቸው ጠባብ ክፍል ከስምንት ሰዎች ጋር መዳበል ግድ ሆነባቸው። በኮምቦልቻ ከተማ በተከሰተ ግጭት ሰዎች ላይ ጉዳት ደረሰ ዘይኑ እንደሚሉት አንሶላና ትራሱ የነተበ፣ መጥፎ ሽታ ያለው አልጋ ላይ እንዲያርፉ ሆነ። ሁኔታው እንደሳቸው በእድሜ የገፋ ሰውን ብቻ ሳይሆን ወደ ስፍራው ይዘዋቸው የሄዱት ቤተሰቦቻቸውንም አስቀይሟል። ስለ ማረፊያ ክፍላቸው አማረው ሳይጨርሱ ለመዋጥ የሚተናነቅ፣ የቆየና ሽታ ያለው ምግብ ቀረበላቸው። ለቢቢሲ ከመካ እንደተናገሩት በአካባቢያቸው ንጹህ መጸዳጃ የለም። ድንገት የሚታመም ሰው ከህመም ማስታገሻ ያለፈ አያገኝም። ከኢትዮጵያ ሲነሱ ለሀጅ ጉዞና ሙሉ መስተንግዶ የከፈሉትን ገንዘብ ሲያሰሉ ሁኔታው የበለጠ ያሳዝናቸዋል። አጭር የምስል መግለጫ በምጽዋት ለመመገብ ተገደዋል የመካ ጉዞ የበርካቶችን ኪስ የሚፈትሽ ነው። የእርሻ መሬታቸውን ሸጠው፣ ሀብት ንብረታቸውን አሟጠው ወደ ስፍራው የሚያቀኑ ጥቂት አይደሉም። ክፍያቸውን የሚመጥን መስተንግዶ ግን አያገኙም። ከሁሉም የከፋው ምግብ ለማግኘት መቸገራቸው ነው። እናቶቻችንን፣ ሚስቶቻችንን ይዘን የመጣን አለን። ቤተሰቦቻችንን ምን እናብላ በማለት ሁኔታውን በሃዘን ይገልፃሉ። ሀጃጆች የምጽዋት ምግብ ተቀብለው ሲመገቡ የሚያሳዩ ፎቶግራፎችና ቪድዮዎች በማህበራዊ ሚዲያ ተለቀዋል። ኢትዮጵያውያን ስማችን ይህ አልነበረም። ክብራችን ተነክቷል የሚሉትም ለዚህ ነው። ለዘይኑ፤ ኢትዮጵያውያን እየደረሰባቸው ያለው እንግልት ከሌሎች ሀገር ዜጎች የበለጠ ነው። እሮሮው የሳቸው ብቻ ሳይሆን የተቀረው ሙስሊም ማህበረሰብ ጭምርም ሲሆን፤ ጉዞውን የሚያስተባብረውን የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤትን ተጠያቂ ያደርጋሉ። በኢትዮጵያ ሙስሊሞች ጉዳዮች ዙሪያ ምክረ ሀሳብ ለማቅረብ በጠቅላይ ሚንስትር ዓብይ አህመድ የተዋቀረው ኮሚቴ ከሚያያቸው ጉዳዮች አንዱ ይህ ጉዞ ስለሆነ ነገሩ እንደሚቀየር ተስፋ ያደርጋሉ። ኮሚቴው መፍትሄ ያበጅላቸዋል ተብለው ከሚጠበቁ ችግሮች መካከል የሀጅና ኡመራ ጉዞ ይገኝበታል። ከንቲባ ለመሆን ፈተናዎችን የሰበረች መጅሊሱ መለወጥ አለበት። እንግልቱ በኛ መብቃት አለበት። ለቀጣዩ ትውልድ መተላላፍ የለበትም ይላሉ ዘይኑ። ሀሳባቸውን የሚጋራው አቡበከር አለሙ ከሳምንት በፊት ነበር ወደ መካ ያቀናው። ለደርሶ መልስ የአውሮፕላን ትኬት፣ ለምግብ፣ ለአልጋ፣ ከማረፊያ ወደ መስጅድ ለሚደረግ ጉዞ ባጠቃላይ ብር ከፍሏል። ብዙዎች ምክር ቤቱ በሚሄዱበት ሀገር ምቹ መቆያ እንደሚያሰናዳላቸው በማመን ቢከፍሉም የሚገጥማቸው ከእውነታው የራቀ ነው ይላል። በመዲናና መካ በብዛት ኢትዮጵያውያን የሚያርፉባቸው ቦታዎች አልዛሂር፣ አልቤክ፣ ማፊል፣ ሰአድ ሲሆኑ፤ የተሻለው ሰአድ እንደሆነ ይናገራል። እንደየ አማኙ ፍላጎት ከሁለት ሳምንት እስከ አንድ ወር የሚቆዩም አሉ። በኢትዮጵያ ገንዘብ ያደረጉት ክፍያ ወደ ሳዑዲ ሪያል ሲመነዘር ማግኘት ከሚችሉት መስተንግዶና ከሳዑዲ ኑሮ አንጻር ፍትሀዊ እንዳልሆነም ብዙዎች ይገልፃሉ። ገንዘብ ያላቸው ለተጨማሪ ወጪ ሲዳረጉ፤ አብዛኛው ማህበረሰብ በአንጻሩ የስቃዩ ሰለባ ነው። አቡበከር እንደሚለው ለብዙ ዓመታት ስለችግሩ ቢወራም መፍትሄ አልተሰጠንም። የሀጂ ጉዞ ችግር ከሙስናና የመልካም አስተዳዳር እጦት ጋር ይገናኛል። ለሀጅ ጉዞና ሌሎችም የሙስሊሙ ማህበረሰበብ ጥያቄዎች መፍትሄ ያመጣል ተብሎ ተስፋ የተጣለበት ኮሚቴ ህዘዝብ ግንኙነት ካሚል ሸምሱ፤ የአቡበከርና ዘይኑን ቅሬታ ይጋራል። ሀጃጆችን ብቻ ሳይሆንም ኢትዮጵያንም ያሳፈረ ነው ይላል። ካሚል እንደሚለው ችግሩ የሚጀምረው በኢትዮጵያ አየር መንገድ ካለው መስተንግዶ መጓደል ነው። ከጥቂት ቀናት በፊት ሀጃጆች በአየር ማረፊያው መጉላላታቸውን መናገራቸው ይታወሳል። አየር መንገዱ በበኩሉ፤ በሶማሌ ክልል በተከሰተው የጸጥታ ችግር ምክንያት ለጉዞ ዘግይተው የሄዱ ሀጃጆች በሳውዲ አረቢያ አየር መንገድ ሊስተናገዱ ባለመቻላቸው፤ በወቅቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ ባይኖረውም ጉዟቸውን አመቻችቷል ሲል መግለጫ ሰጥቷል። ከሳዑዲ ሲቪል አቪየሽን የበራራ ፍቃድ እስኪገኝም ምግብና መሰል መስተንግዶ ቀርቧል ተብሏል። የሀጅና ኡምራ ጉዞ ማስተባባሪያ የሚካተትበት መጅሊስ መዋቅራዊ ለውጥ እንደሚያስፈልገው ካሚል ይናገራል። ከአዲሱ ኮሚቴ የትኩረት አቅጣጫዎች መካከል ለጉዞው የሚጠየቀውን ክፍያ ፍትሀዊ ማድረግ፣ ጉዞ ምቹ ማድረግና ተገቢ መስተንግዶ መስጠት ይገኙበታል። ፀረ ሙስሊም ደብዳቤ በእንግሊዝ ዘጠኝ አባላት ያለው ኮሚቴው በሌሎች ሀገሮች ስላላው የሀጂ ጉዞ ጥናት በመሰብሰብ ላይ ይገኛሉ። ኮሚቴው ውጤታማ እንዲሆን ከሚጠብቁ አንዷ ሙኒራ አብድልመናን ናት። ሙኒራ ትላንት ምሽት ከሶስት ሰአት እስከ አምስት ሰአት ድረስ በትዊተር ላይ ዘመቻ እያደረገች ነበር። የዘመቻው ዋነኛ ማጠንጠኛ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሀጃጆች ከተጉላሉ በኃላ የሰጠው መልስ እንግልቱን የሚመጥን አይደለም የሚል ነው። አየር መንገዱ ለተነሳው ቅሬታ ተመጣጣኝ ምላሽ አልሰጠም የምትለው ሙኒራ፤ ሀጅ አድራጊዎች ሲጉላሉ የመጀመሪያው ባይሆንም ተቃውሞው በተደራጀ መልከ እንዳልነበር ታስታውሳለች። ኢትዮጵያ ውስጥና እንደሷ ከኢትዮጵያ ውጪ ያሉ ኢትዮጵያውያን የተሳተፉበት የትዊተር ዘመቻው፤ አየር መንገዱ ተጓዦቹን በይፋ ይቅርታ እንዲጠይቅና በቀጣይ ዓመታት ተመሳሳይ እንግልት እንዳይከሰት ማሳሰቢያ ጭምርም ነበር። ጉዳዩ በዋነኝነት የሚመለከተው የሀጅ አዘጋጅ ኮሚቴ እንደመሆኑ ለኛ መብት የሚቆም ጠንካራ ተቋም መኖር አለበት ትላለች። በአሁን ወቅት በመካ ያሉትን እንዲሁም ሀገር ውስጥ የሚገኙትን የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አባላት ለማነጋገር ያደረግነው ጥረት አልተሳካም። ተያያዥ ርዕሶች
እስራኤል የቀድሞ ሚኒስትሯን በኢራን ሰላይነት ፍርድ ቤት አቆመች
በሺ የሚቆጠሩ ከኢትዯጵያ የሾለኩ ቤተ እስራኤላዊያንን በጥንቃቄ ወደ እስራኤል ምድር ለመጓጓዝ ነበር ይህ ሁሉ የሆነው። ምክንያቱም ሱዳን በዚያን ወቅት ለእስራኤል በጄ የምትል አገር አልነበረችም፤ እንዲያውም ከአረብ ጠላቶቿ አንዷ ነበረች። ይህ ኀቡእ ዘመቻ ታውቆ ቢሆን የብዙ ሺህ ቤተ እስራኤላዊያን ሕይወት አደጋ ላይ ሊወድቅ ይችል ነበር። ጥብቅ የአገር ምስጢር ነበር። ቤተሰቦቼ እንኳ ስለነገሩ የሚያውቁት ነገር አልነበረም ይላል ጋድ ሺምሮን፣ የቀድሞ የሞሳድ ባልደረባ። ኦሪትን የሚከተሉትን ቤተ እስረኤላዊያን ሃይማኖታቸውንም ሆነ ማንነታቸውን ለማንም እንዳይገልጡ፣ ማንነታቸው ከታወቀ ግን በሱዳን የጸጥታ ኃይሎች አደጋ እንደሚጋረጥባቸው ይነገራቸው የነበረው መቀመጫውን በአሮስ መዝናኛ ባደረገው በዚህ ኅቡዕ የሞሳድ ቡድን በኩል ነበር። ቤተ እስራኤላዊያን በተመለከተ መላ ምቱ ብዙ ነው። ከአስሩ የጠፉ የእስራኤል ነገዶች ዝርያቸው የሚመዘዝ እንደሆነ ይነገራል። ሌሎች ሰነዶች ደግሞ ከክርስቶስ ልደት በፊት ዓመተ ዓለም አካባቢ የንግሥት ሳባና የንጉሥ ሰለሞንን ልጅ አጅበው ወደ ኢትዮጵያ ምድር የመጡ እስራኤሎች የልጅ ልጅ ልጆች እንደሆኑ ይገምታሉ። ሌሎች ደግሞ ትልቁ የአይሁድ ቤተ አምልኮ በ ዓመተ ዓለም ሲፈርስ ወደ ሐበሻ ምድር የተሰደዱ እንደሆኑ ይገምታሉ። ሞሳዶች አሮስ መዝናኛን ገንብቶ ለመክፈት ወራትን ወስዶባቸዋል። ከአገሬው የሚሆኑ የቤት ሠራተኞችን፣ ሾፌሮችን፣ የወጥ ቤት ሠራተኞችን ቀጥረዋል። አንዳቸውም ግን የሆቴሉን ኅቡዕ ተግባር አያውቁም ነበር። አለቆቻቸው የሞሳድ ሰዎች እንጂ የወጥ ቤት ሰዎች እንዳልሆኑ ያወቁት ከብዙ ዘመን በኋላ ነበር። ምድር ቤት የሚገኘው እቃ ቤት ግን ማንም ዘው ብሎ ገብቶ አያውቅም፣ እዚያ ከድስቶች ጋር የርቀት መነጋገሪያ ስልኮች ነበሩ። ከቴላቪቭ የሚያገናኙ። ከዚህ ዜና በተጨማሪ
ወደ እናት ሃገራችን እስራኤል ውሰዱን
ሜይ ቤተ እስራኤላውያን ለምዕተ ዓመታት በኢትዮጵያ በተለይም በጎንደር፣ ጣና ሀይቅ አካባቢ ከኢትዮጵያውያን ጋር ኖረዋል አሁንም እየኖሩ ነው። ስለ ቤተ እስራኤላውያን አመጣጥ ታሪክ ብዙ ይላል። ንግሥት ሳባ ንጉስ ሰለሞንን ጠይቃ ስትመለስ አብረዋት አጅበው እንደመጡ ታሪካቸውን የሚመዙ አሉ። የእስራኤል ምኩራብ በባቢሎናውያን ከመፍረሱ ጋር ተያይዞ ወደ ግብፅ የተሰደዱ፤ ከዚያም ክሊዎፓትራ ስልጣን እስከያዘችበት ድረስ ቆይተው በአውግስተስ ቄሳር በመሸነፏ ምክንያት ወደ ተለያዩ አገሮች እንደተሰደዱም ይነገራል። ንጉስ ካሌብ ግዛቱን ከማስፋፋቱ ጋር ተያይዞ የመንን በወረረበት ወቅት እንደመጡም ይነገራል። በ ኛው ክፍለ ዘመን መጨረሻ የእስራኤል ባለስልጣናት ሕገ መንግሥታዊ ውይይት ካደረጉ በኋላ ቤተ እስራኤላውያንን ወደ እስራኤል የመመለስ ዘመቻዎች በ ዎቹ ተጀመሩ። በ ዎቹም ነዋሪነታቸውን በሱዳን ያደረጉትን እንዲሁም ከአዲስ አበባ በሙሴ፣ እያሱ እንዲሁም በሰለሞን ዘመቻዎች በእስራኤል ፀጥታ ኃይሎች በመታጀብም በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተወስደዋል። ከነዚህ ዘመቻዎች በኋላ ቤተ እስራኤላውያንን የመውሰድ ሁኔታ እንደተጓተተ ቤተ እስራኤላውያን ይናገራሉ። በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን አሁንም የእስራኤል መንግሥት ከቤተሰቦቻችን ጋር በቀላሉ እንድንገናኝ ፈጣን ምላሽ አልሰጠንም በማለት እያማረሩ ነው። በኢትዮጵያ ለሶስት ቀናት ለስራ ጉብኝት በማድረግ ላይ ለሚገኙት የእስራኤሉ ፕሬዚዳንት ሩቨን ሪቭሊንም ከቤተ እስራኤላውያን ዘንድ የቀረበላቸው ጥያቄ ይሄው ነበር። የቤተ እስራኤላውያን ተወካዮች ለእስራኤሉ ፕሬዚዳንት ያላቸውን ቅሬታ ያቀረቡ ሲሆን ከሰላሳ ዓመታት በፊት የተለዩዋቸውንም ቤተሰቦቻቸውን ማግኘት ከሰማይ እንደራቀባቸው ተናግረዋል። እስራኤል ለመሄድም መውጫ ያጡ ወደ ስምንት ሺ ቤተ እስራኤላውያንም እንዳሉ ተወካዮቹ ይናገራሉ። ፕሬዚዳንቱ ጋር ተገናኝተው ከተወያዩት ቤተ እስራኤላውያን ተወካዮች አንዱ ባየ ተስፋየ ነው። ብዙዎች ከገጠሪቷ ኢትዮጵያ ክፍል እንደመጡና ወደ እስራኤልም እንሄዳለን በሚል ተስፋ ለዓመታት በአዲስ አበባ እንደሚቀመጡና አስቸጋሪ ሁኔታ ላይ እንዳሉ ይናገራል። በአንድ ድርጅት ውስጥ ተጠልለን እንኖር ነበር፤ ትምህርትም የተከታተልነው እዛው ሳለን ነው። ነገር ግን ድርጅቱ ሲዘጋ በርካታ ወጣቶች ትምህርት ለማቋረጥ ተገደዱ። የሚረዳቸው በማጣታቸው ወደጎዳናም ዘለቁ ብዙዎችን ነበሩ ይላል ባየ። በቅርብ ወራትም በኢትዮጵያ ውስጥ ለሚገኙ በሺዎች ለሚቆጠሩ ቤተ እስራኤላውያን ፈጣን ምላሽ ሊሰጣቸው ይገባል በሚል አንዳንድ የፓርላማ አባላት ተቃውሟቸውን በማሰማት እንዲሁም ፓርላማው ላይ ላለመሳተፍ ጥለው እንደወጡም ተነግሯል። በተቃራኒው በእስራኤል ህገወጥ ናቸው የሚሏቸውን አፍሪካውያን ስደተኞች ወደ ሀገራቸው ወይም ወደ ሶስተኛ ሀገር እንዲሄዱ የሚሉ ግፊቶችም አሉ። የእስራኤል ፓርላማ አባል የሆኑት ዶክተር አቭራም ንጉሴ በእንግሊዝ ነዋሪነታቸውን ያደረጉ ቤተ እስራኤላዊ ሲሆኑ ባለው ሁኔታ ደስተኛ እንዳልሆኑም ይናገራሉ። ከቤተሰቦቻቸው ጋር ለመገናኘት ለዓመታት ቢጠብቁም ሊሳካ አልቻለም፤ በዚህም ደስተኛ አይደለሁም፤ ይበቃል ልንል ይገባል። ከሚወዷቸው ቤተሰቦቻቸው ጋር በእስራኤል እስከሚገናኙ ተስፋ አንቆርጥም፤ ድካምም አናሳይም። ጠንክረን እንሰራለን፤ የፓርላማውንም ሆነ የተለያዩ የእስራኤል ባለስልጣናትን ድጋፍ እንድናገኝ እየሰራሁ ነው። እርግጠኛ ነኝ የእስራኤል መንግሥት ላይ ተፅዕኖ መፍጠር የሚያስችለኝ የፕሬዚዳንቱ ድጋፍ አለኝ ይላሉ። በአሁኑ ወቅት ወደ ሺ የሚሆኑ ቤተ እስራኤላውያን በእስራኤል ነዋሪነታቸውን አድርገዋል። ተያያዥ ርዕሶች
ኢትዮጵያዊነቴን ያገኘሁት ሙዚቃ ውስጥ ነው አቨቫ ደሴ
ጁላይ ማጋሪያ ምረጥ ከ ዓመት በፊት ወደ ሱዳን ከተሰደዱ ብዙ ሺህ ኢትዮጵያዊያን መካከል አራት ልጆች ያሏቸው ጥንዶች ይገኙበት ነበር። ሱዳን ውስጥ ወደሚገኝ የስደተኞች መጠለያ ለመድረስ ለሳምንታት በእግር ተጉዘዋል። መጠለያው ውስጥ በቂ ምግብና መድሀኒት አልነበረም። ውጣ ውረዱ የብዙዎችን ሕይወት እንደዋዛ ቀጥፏል። ጥንዶቹም በስደት ላይ ሳሉ ከልጆቻቸው ሁለቱን በሞት ተነጥቀዋል። ኢትዮጵያዊያኑ መጠለያ ውስጥ ለወራት ከቆዩ በኋላ ኦፕሬሽን ሞሰስ ዘመቻ ሙሴ በተባለ ዘመቻ ወደ እስራኤል ተወሰዱ። ይህም ኢትዮጵያዊያን አይሁዶች ወደ እስራኤል ከተወሰዱባቸው ዘመቻዎች አንዱ ነበር። ጥንዶቹ ይመኟት የነበረውን የእስራኤል ምድር ከረገጡ በኋላ ሕይወትን ሀ ብለው ጀመሩ። ናዝሬት ከተማ ውስጥ። እስራኤል በደረሱ በአራተኛው ዓመት አቨቫ የተባለች ልጅ ተወለደች። አቨቫ ደሴ። በፀጉሬ ይስቁብኝ ነበር አቨቫ ያደገችው ኢትዮጵያዊያን በብዛት በሚኖሩበት መንደር ነው፤ ጓደኞቿም ኢትዮጵያዊያን ነበሩ። እስራኤል ለኢትዮጵያዊያን እንዲሁም ለሌሎች ጥቁሮችም ምቹ አገር አለመሆኗን የተገነዘበችው ትምህርት ቤት ስትገባ ነበር። የምትማርበት ክፍል ውስጥ የነበሩት ተማሪዎች ነጮች ብቻ ነበሩ። በቆዳ ቀለሟ ይጠቋቆሙ፣ በባህሏ ይሳለቁ፣ በፀጉሯም ይስቁ ነበር። በእስራኤላዊያን ዘንድ ተቀባይነት ባለማግኘቷ ኢትዮጵያዊ ማንነቷን ጠላችው። እስራኤላዊያንን ለመምሰል ትጣጣርም ጀመር። አሁን ስናገረው ያሳፍረኛል፤ ግን ልጅ ሳለሁ በቤተሰቦቼ አፍር ነበር፤ የቤተሰቤን ጉዞና ታሪክ ረስቼ ነበር ትላለች። አቨቫ እንጀራ አትበላም ነበር። ጓደኞቿ በኢትዮጵያዊነቷ የሚሳለቁባት ስለሚመስላት ወደ ቤቷ ልትጋብዛቸው አትፈልግም። የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ ሳለች ከነበሯት መምህራን አንዷን እንዲህ ታስታውሳታለች። ከነጭ ጓደኞቼ ጋር ስሆን መምህርቷ በጣም በትህትና ሰላም ትለናለች። ከኢትዮጵያዊያን ጓደኞቼ ጋር ስታየኝ ግን እንደ ነጮቹ በትህትና አታዋራንም፤ ትጮህብን ነበር። ወደ ማንነቴ የተመለስኩት በሙዚቃ ነው አቨቫ ሙዚቃ ነፍሷ ነው። ከአራት ታላላቅ እህቶቿ አንዷ የአርኤንድቢ እና ሶል ሙዚቃ ቪድዮ ካሴቶች ታሳያት ነበር። ቤት ውስጥ ታንጎራጉራለች፤ ትደንሳለች። አይን አፋር ስለነበረች ከቤት ውጪ ባታደርገውም። የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ ሳለች ሙዚቃ መጻፍ ጀመረች፤ ነገር ግን ለማንም አታሳይም ነበር። የእስራኤል ወጣቶች ወታደራዊ ግዴታ መወጣት ይጠበቅባቸዋልና አቨቫም ድንበር አካባቢ ተመደበች። የተሳሳተ ቦታ እንደሆንኩ ይሰማኝ ነበር። አገሪቱን ከወታደራዊ አገልግሎት በሌላ መንገድ ማገልገል እንደምችል አምናለሁ። በእርግጥ በወቅቱ ስለ ራሴ ተምሬያለሁ። ያኔ ሙዚቃ እንዲሁ የሚያስደስታት ነገር እንጂ፤ ከዚያ በዘለለ የሕይወቷ ጥሪ እንደሆነ አታስብም ነበር። እንዲያውም ሥነ ልቦና ማጥናት ነበር ምኞቷ። ሆኖም አንድ ክፉ አጋጣሚ ሕይወቷን እስከወዲያኛው ቀየረው። ከባድ የመኪና አደጋ ከአደጋው ለማገገም ወደ ሁለት ዓመት ገደማ ወስዶባታል። በእነዚያ ዓመታት ስለ ሕይወት ስታሰላስል መኖር ያለብኝ የምወደውን ነገር እየሠራሁ ነው ከሚል ውሳኔ ላይ ደረሰች። ዘ ቮይስ የተባለው ታዋቂ የሙዚቃ ውድድር እስራኤል ውስጥ ሲጀመር ተቀላቀለች። ውድድሩ ላይ የአንድ ሙዚቃ ትምህርት ቤት ኃላፊ ተዋውቃ ነበር። ትምህርት ቤቱ ገብታም የጊታርና የድምፅ ትምህርት መውሰድ ጀመረች። በሙዚቃ ትምህርት ቤቱም ስለ አፍሮ ፖፕ ስልት ስትማር ስለ ኢትዮጵያ ሙዚቃም ሰማች። ችላ ካለችው ኢትዮጵያዊ ማንነት ጋር በሙዚቃ ታረቀች። ወደ ማንነቴ ያደረኩት ጉዞ የተጀመረው በሙዚቃ ነው። ስለ ኢትዮጵያ ሙዚቃ መማር ጀመርኩ። ስለ ኢትዮጵያ ባህል ማጥናትና አማርኛ መለማመዱንም ተያያዝኩት። ጊዜ ቢወስድብኝም ቤቴ የምለው አገር እንዳለኝ ተገነዘብኩ። የወላጆቼን ሙዚቃ ወደድኩት። አቨቫ አሁን ዓመቷ ነው። ሦስት አልበሞች አሳትማለች። ኢን ማይ ቶውትስ በሀሳቤ ፣ ሁ አም አይ ማነኝ ፣ አይ አም አቨቫ አቨቫ እባላለሁ የተሰኙ። ሙዚቃዎቿ ዘረኝነትን የሚያወግዙ፤ ፍቅርና ሰላምን የሚሰብኩ ናቸው። ከኢትዮጵያ ሙዚቃና ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ከሆነ ነገር ጋር በፍቅር ወድቄያለሁ የምትለው አቨቫ፤ በሙዚቃዋ የአማርኛ ስንኞች ታካትታለች፤ ዘፈኖቿን በመሰንቆና ክራር ታጅባለች። ቪድዮ ክሊፕ ስትሠራ የአገር ባህል ልብስ ለብሳ፣ ሹሩባ ተሠርታም ነው። ባለፉት ሦስት ዓመታት በተደጋጋሚ ኢትዮጵያን ጎብኝታለች። ሸራተን አዲስ በነበረ የሙዚቃ ትርዒትም ተሳትፋለች። የጥላሁን ገሠሠ፣ የመሀሙድ አህመድ፣ የጂጂ እጅጋየሁ ሽባባው እና የቴዲ አፍሮ ቴዎድሮስ ካሳሁን ሙዚቃዎችን ታቀነቅናለች። በአንድ ወቅት ኢትዮጵያ ሳለች የጂጂን ዘፈን ዳግመኛ ሠርታ እንጦጦ ተራራ ላይ ቪድዮ ክሊፕ ሠርታለች። ፍቅሬ ሆይ እኔ አንተን መውደዴን እንዴት ብዬ ልተው አቨቫ ራሷን በጊታር አጅባ የምታዜመው ዘፈን ነው። ሶል፣ አርኤንድቢና የኢትዮጵያ ሙዚቃ ሦስት የምትወዳቸው ስልቶች ናቸው። ሶል እና አርኤንድቢ ውስጥ መሰንቆና ክራር ብዙም አለመለመዱ ሥራዎቿን ተወዳጅ እንዳደረጋቸው ታምናለች። ጥቁር ስለሆንሽ እልወድሽም ዘረኛነት በተንሰራፋበት ማህበረሰብ ውስጥ መኖር፣ የራስን ማንነት ጥያቄ ውስጥ ማስገባትና በስተመጨረሻም ከራስ ጋር መታረቅ ለአቨቫ ሙዚቃ ግብዓት የሆኑ የሕይወት ተሞክሮዎች ናቸው። ከተሞክሮዎቿ አንዱን እንዲህ ታወሳለች። ከጥቂት ዓመታት በፊት መዋዕለ ህጻናት ውስጥ ሠርቼ ነበር። ሁሉም ህጻናት ነጭ ነበሩ። ልጆቹን ባጠቃላይ ወድጃቸው ነበር። አንድ ቀን አንድ አስተማሪ ልጆቹ ወደ ክፍል እንዲገቡ እንድጠይቃቸው ነገረኝ። ተማሪዎቹን ስጠራቸው አንድ ልጅ ወደ ውስጥ መግባት አልፈለገም ነበር። ከዚያ አናገርኩት እንደምወድህ ታውቃለህ አይደል ስለው እኔ ግን አልወድሽም አለኝ ለምን ስለው ጥቁር ስለሆንሽ አለኝ። ልጁ አምስት ዓመቱ ነበር፤ ብዙ ኢትዮጵያዊያንን አልተዋወቀም። ግን ጥላቻን ተምሮ ነበር። ከጥቂት ወራት በኋላ ከልጁ ጋር ወዳጆች ሆንን። የተናገረውን ነገር ትርጉሙን ተረድቶና ሆነ ብሎ እንዳላላው አውቃለሁ። ይህ ማህበረሰቡ እንዴት እንደሚያስብ ካየችባቸው አጋጣሚዎች አንዱ ነበር። ከማርቲን ሉተር ኪንግ ንግግሮች አንዱን እንደ መነሻ አድርጋ ብላክ ጥቁር የተሰኘ ሙዚቃ የጻፈችውም በዚህ ምክንያት ነበር። በሙዚቃዎቿ ስለ ቤተሰቦቿ ሕይወትም ታወሳለች። ልጅ ሳለች እናቷ ይነግሯት ከነበረው ታሪክ ተነስታ ስለ ቤተሰቦቿ የትውልድ ቀዬ እንፍራዝ ዘፍናለች። ሙዚቃ ሕክምና ነው ሀሳቧን፣ ቢሆን ብላ የምትመኘውንም በሙዚቃዎቿ ታስተላልፋለች። ውስጤ የሚንቀለቀሉና ማውጣት እንዳለብኝ የሚሰሙኝ ስሜቶችን በሙዚቃ እገልጻቸዋለሁ። ሙዚቃ መጻፍ ሕክምና ነው። ብዙዎቹ ዘፈኖቼ ስለ ውጣ ውረድ ይናገራሉ። መልስ ለማግኘት ያለሙም ናቸው። አይ ዋነ ጎ መሄድ እፈልጋለሁ እናቷን አጥታ ግራ ስለተጋባች ትንሽ ልጅ ይተርካል። በፍቅር ከፍታ ውስጥ ሳለሁ የጻፍኩት የምትለው ማይ ኸርት ልቤ የተሠራው የኢትዮጵያ የሙዚቃ ምት፣ እስክስታ ተጨምሮበት ነው። አቨቫ ማየት የምትፈልገውን እኩልነት የሰፈነበት ዓለም በሙዚቃዎቿ ታስተጋባለች። ሰውን በአካል ማጥቃት ብቻ ሳይሆን ዘረኛ ንግግርም ያማል። ኢትዮጵያዊያን ባጠቃላይ ጥሩ ናችሁ ይባላል። ነገር ግን እኛ አንድ ሰው አይደለንም። የተለያየ ባህሪ አለን። በሙዚቃዬ ማሳየት የምፈልገውም ይህንን ነው። ከለር ቀለም የተባለ ዘፈኗ ሁለት የተለያዩ ሰዎች፤ አንዳቸው ሌላቸውን ለመቀየር ሳይሞክሩ በመቻቻል ስለሚኖሩበት ዓለም ይተርካል። የእስራኤል ማህበረሰብ ኢትዮጵያዊያንን እንዳሉት ባለመቀበሉ ራሷን ለመቀየር መሞከሯን ታስታውሳለች። እስራኤላዊ ከመሆንና ኢትዮጵያዊ ከመሆን መካከል መምረጥ እንዳለብኝ ይሰማኝ ነበር። ሁለቱንም መሆን እንደምችል፣ መደበቅ ሳይሆን መኩራት እንዳለብኝ ለመረዳት ዓመታት ወስዶብኛል። እስራኤል የብዙ ባህሎች አገር ናት። ይህም ውብ ነው። ሰዎችን ለመቀየር መሞከሩን ትተን በመከባበርና በመፈቃቀር መኖር አለብን። መንግሥት ለእኛ ቅድሚያ አይሰጥም ኢትዮጵያዊያን በእስራኤል ፖሊሶች የሚደርስባቸውን ጥቃት በመቃወም በርካታ ሰልፎች ተደርገዋል። በትምህርትና በሥራው ዘርፍ ያለውን መድልዎ በመቃወምም በርካቶች ድምጻቸውን አሰምተዋል። ሆኖም ይህ ነው የሚባል ለውጥ የመጣ አይመስልም። ከሳምንታት በፊት ሰለሞን ተካ የተባለ ቤተ እስራኤላዊ ሥራ ላይ ባልነበረ ፖሊስ መገደሉ ይታወሳል። ከዚህ ቀደም ከታዩ የተቃውሞ ሰልፎች በተለየ ጠንካራ ተቃውሞ ተካሂዶ ዋና ዋና አውራ ጎዳናዎች ተዘግተውም ነበር። የተቃውሞ ሰልፍ ሲካሄድ ወደ ኢትዮጵያ መልሷቸው የሚሉ አሳዛኝ መልዕክቶች አያለሁ። በጣም የከፋ ደረጃ ላይ እንደደረስን ይሰማኛል። ህመሙና ተስፋ መቁረጡን እረዳለሁ። በፖሊስ ጭካኔ ምክንያት በተለይ ኢትዮጵያዊያን ወንዶች መንገድ ላይ ለመሄድ እንኳን ይፈራሉ። ለሕይወታቸው እየታገሉ ነው። ለብዙ ጊዜ የታመቀ ቁጣ ነው የገነፈለው ትላለች ሙዚቀኛዋ። መዋዕለ ህጻናት ኢትዮጵያዊያን ህጻናትን መቀበል አይፈልጉም። በሥራ ቦታም ኢትዮጵያዊያን እንደሚገለሉ ትናገራለች። ሁሌም የተቃውሞ ሰልፎች ሲካሄዱ መንግሥት ለውጥ ይመጣል ብሎ ቃል ቢገባም አንዳችም መሻሻል እንዳላዩ ትገልጻለች። መንግሥት ለጥያቄዎቻቸው መልስ የማይሰጠው ለኢትዮጵያዊያኑ ጉዳይ ቅድሚያ ስለማይሰጥ እንደሆነም ታክላለች። ቤተሰቦቼ እስራኤል ከመጡ ጀምሮ ስለዚህ ነገር ይወራል። ያኔም ተቃውሞ ነበር፤ አሁንም አለ። የተለወጠ ነገር ግን የለም። ሆኖም ተስፋ አልቆረጠችም። ነገሮች የተሻሉ እንደሚሆኑም ትጠብቃለች። ሙዚቃዬ ሩስያ መድረሱን አላወኩም ነበር እስራኤል ውስጥ ኢትዮጵያዊያን ሙዚቀኞች መበራከታቸው ማህበረሰቡ ስለ ቤተ እስራኤላዊያን ባህል እንዲረዳ እንደሚያግዝ ታምናለች። ሙዚቃቸው አሁን ካለበት በላይ እንደሚያድግም ተስፋ ታደርጋለች። ከኢትዮጵያዊያንና ከእስራኤላዊያን አድማጮቿም ጥሩ ምላሽ እያገኘች እንደሆነ ትናገራለች። ማኅበራዊ ጉዳዮችን ስዳስስ ድምፅ እየሆንኳቸው እንደሆነ አምናለሁ። ቤተሰቦች ለልጆቻችን አርዓያ ነሽ ሲሉኝ በጣም እኮራለሁ። ምክንያቱም በኔ ትውልድ ብዙም ስኬታማ ጥቁር ሴት አርዓያ የለንም። አቨቫ በሙዚቃ ሕይወቷ እጅግ ከኮራችባቸው ቅጽበቶች አንዱ የገጠማት ሩስያ ሳለች ነው። አንድ ፌስቲቫል ላይ ነው። በሺዎች የሚቆጠሩ ታዳሚዎች ነበሩ። የድምፅ ሙከራ ስታደርግ ሰዎች አብረዋት ይዘፍኑ ነበር ምን በጣም ነው የገረመኝ ሙዚቃዬ ሩስያ መድረሱን አላወኩም ነበር ሙዚቃ ስትጀምር ቤተሰቦቿ እምብዛም አይደግፏትም ነበር። ዛሬ ግን ከትርዒቶቿ አይቀሩም። ልጅ ሳለች እናቷ ያንጎራጉሩላት እንደነበር ታስታውሳለች። አንድ ቀን ከእናቷ ጋር በጥምረት የመሥራት ምኞትም አላት። በአንድ ወቅት ኢትዮጵያዊነት ትርጉም የማይሰጣት አቨቫ ዛሬ ትልቁ ህልሟ ኢትዮጵያ ውስጥ ሙዚቃዎቿን ማቅረብ ነው። እናቷ የተሻለ ሕይወት እንዲኖራቸው ከአንድም ሁለት ሥራ እየሠሩ እንዳሳደጓቸው ታስታውሳለች። በአንድ ወቅት ይህንን ባትገነዘብም አሁን ላይ ተቀይራለች። አሁን ትልቅ ሴት ሆኜ ሳየው ቤተሰቦቼ ጀግኖቼ ናቸው። እናቴ ጀግናዬ ናት። በጣም እኮራባታለሁ። እስራኤል ውስጥ ያለውን መደልዎ በመቃወም ሰልፍ ሲካሄድ እናቷን ተመሳሳይ ጥያቄ ትጠይቃለች። እዚህ በመምጣታችሁ ደስተኛ ናችሁ እናቷ ሁሌም የሚሰጧት መልስ ተመሳሳይ ነው። ቦታዬ እዚህ ነው፤ ሌላ ቦታ መኖር አልፈልግም፤ ብዙ ውጣ ውረድ ቢኖርብንም እዚህ በመኖሬ እኮራለሁ። ተያያዥ ርዕሶች
እስራኤል የቀድሞ ሚኒስትሯን በኢራን ሰላይነት ፍርድ ቤት አቆመች
ጁን የእስራኤል መንግሥት የሚኒስትሮች ምክር ቤት አባል የነበሩትን ጎነን ሰጌቭ ለኢራን ይሰልሉ ነበር በማለት ከሳቸዋለች። በአውሮፓውያኑ ዎቹ የኢነርጂ ሚኒስትር የነበሩትና የህክምና ዶክተር የሆኑት ጎነን ሰጌቭ ናይጀሪያ ይኖሩበት በነበረበት ወቅት በኢራን የደህንንት ሰዎች እንደተመለመሉ የእስራኤል የደህንነት መረጃ ድርጅት ሺን ቤት አስታውቋል። ግንቦት ወር ላይ ኢኳቶሪያል ጊንኒ በሚጎበኙበት ወቅት በቁጥጥር ስር የዋሉት ግለሰብ በእስራኤል ፖሊስ ጥያቄ መሰረት ተላልፈው ተሰጥተዋል። የ ዓመቱ የቀድሞ ሚኒስትር በአውሮፓውያኑ አደንዛዥ ዕፅና ሀሰተኛ የዲፕሎማቲክ ፓስፖርት በመያዝ በቁጥጥር ስር ውለው ለአምስት ዓመታት እስር ተፈርዶባቸው ነበር። በዚህም ምክንያት የህክምና ፈቃዳቸው ታግዷል። ከእስር ከተለቀቁ በኋላ በአውሮፓውያኑ በናይጀሪያ መኖሪያቸውን አድርገው በዶክተርነት ሙያቸውም ያገለግሉ ነበር። ሺን ቤት ሰኞ ዕለት ባወጣው መግለጫ የቀድሞው ሚኒስትር ባለፈው ወር እስራኤል እንደደረሱም በቁጥጥር ስር ውሏል። ከኢራን የደህንነት ወኪሎች ጋር ስላላቸው ግንኙነት እንዲሁም ኢራንን በፀረ እስራኤል አቋሟ በመደገፍ ጥያቄ ውስጥ ገብተዋል። በምርመራውም ወቅት የቀድሞው ሚኒስትር ናይጀሪያ በሚገኘው የኢራን ኤምባሲ ባለስልጣናት እንደተገናኙና በአውሮፓውያኑ ም ሁለት ጊዜ ወደ ኢራን ተጉዘው እንደነበር ሺን ቤት ገልጿል። ከዚህ በተጨማሪ በሌላም ሀገራት ከኢራን ስለላ ተቆጣጣሪያቸው ጋር ተገናኝተው ምስጢራዊ መረጃዎች የተላለፈላቸው ሲሆን በኮድም መልዕክቶችን እንደተቀያየሩ ሺን ቤት ያስረዳል። የቀድሞው ሚኒስትርን የእስራኤልን የኢነርጂ ዘርፍ፣ የፀጥታ ሁኔታ፣ በፖለቲካውና በፀጥታው ዘርፍ ስላሉ ባለስልጣናት ለተቆጣጣሪዎቻቸው መረጃ በማስተላለፍ ሺን ቤት ወንጅሏቸዋል። ከዚህም በተጨማሪ የኢራን ሰላዮችን በንግዱ የተሰማሩ ግለሰቦች በማለት ለእስራኤል ባለስልጣናት እንዳሰተዋወቁም ክሱ ይጨምራል። አርብ ዕለት እየሩሳሌም ፍርድ ቤት በዋለው ችሎትም ጠላትን በጦርነት ጊዜ በማገዝ እንዲሁም በእስራኤል ግዛት ላይ በመሰለልና በሌሎች ወንጀሎችም ክስ ቀርቦባቸዋል። መረጃው ለህዝብ እንዳይቀርብ ጥሎት የነበረውን እገዳ ፍርድ ቤቱ ሰኞ ዕለት ያነሳ ቢሆንም አሁንም ቢሆን አንዳንድ ዝርዝሮች ለህዝብ ግልፅ አይደሉም ተብሏል። የቀድሞው ሚኒስትር ጠበቃ በበኩላቸው ሙሉ ክሳቸው የሺን ቤት ካወጣው መግለጫ በተለየ መልኩ መሆኑን የእስራኤል ሚዲያ ዘግቧል። በአውሮፓውያኑ የእስልምና አብዮትን ተከትሎ የኢራን መሪዎች እስራኤል ህገ ወጥ ወራሪ ናት በሚል እንደ ግዛት መታወቅ እንደሌለባት ሲናገሩ ነበር። እስራኤል በበኩሏ ኢራንን የኒውክሊየር መስፋፋት በመቃወም እንደ ጠላት የምታያት ሲሆን በመካከለኛው ምስራቅ ያላትም ተፅእኖ ያስፈራቸዋል። ተያያዥ ርዕሶች
እየሩሳሌም ለምን የኢትዮጵያዊያን ህልም ሆነች
ዲሴምበር ማጋሪያ ምረጥ በተለይም ከንግስት ሳባ ታሪካዊው የእየሩሳሌም ጉብኝትና በእየሩሳሌም ከሚገኙት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ገዳማት ጋር በተያያዘ ብዙዎች እየሩሳሌምን ያውቋታል። ደጋግመውመም በአእምሯቸው ይስሏታል። ከጥንት ጀምሮ ኢትዮጵያውያን በቡድን በቡድን እየሆኑ ወደ እየሩሳሌም ይሄዱ እነደነበር የታሪክ ድርሳናት ያስረዳሉ። ዛሬ ደግሞ በተለያዩ የጉዞ ወኪሎች አማካኝነት በርካቶች ወደ እየሩሳሌም እየሄዱ ነው። እየሩሳሌም የብዙ እናቶች አባቶችና ወጣቶች ህልም ነች። ህይወቷን ሙሉ ስለ እየሩሳሌም እየሰማች ስለኖረች እየሩሳሌምን ማየት ለእናቴ ትልቅ ነገር ነበር።ይህን ህልሟን ማሳካት ደግሞ ለእኔም እነደዚያው ነው የሚለው ሄኖክ ፀሀዬ ኑሮውን በአሜሪካ ካደረገ ጥቂት አመታት ተቆጥረዋል። ወደ አሜሪካ ሲሄድ ይህን ፍላጎታቸውን እንደሚያሳካ ለእናቱ ቃል ገብቶላቸው ነበር። ነገር ግን እሱ ቃሉን ጠብቆ ባለፈው አመት እናቱ ወደ እየሩሳሌም ሊሄዱ ባሉበት ወቅት አባቱ ከዚህ ዓለም በመለየታቸው እቅዱ ሳይሳካ ቀረ። ሀዘን ውስጥ ቢሆኑም የእናቱ እየሩሳሌምን የመጎብኘት ህልም ግን ያው እንዳለ ነበር። ስለዚህም እናቱን ለመጭው ገና ወደ እየሩሳሌም ለመላክ በዝግጅት ላይ ነው። እናቱም ጉዞውን በጉጉት እየጠበቁ መሆኑን፤ ለእናቱ ይህን በማድረጉ ደግሞ እሱም ከመጠን ባለፈ መልኩ መደሰቱን ይናገራል። የአሜሪካ ለእየሩሳሌም በእስራኤል ዋና ከተማነት እውቅና መስጠትን በሚመለከት ያለውን አስተያየትም ሰንዝሯል። እንደ አውሮፓውያኑ በ የተደረገውንና ለእስራኤል መፈጠር መሰረት የሆነውን የባልፎር ስምምነት በመጥቀስ ያ ለዘመናት ያከራከረ ምድር ከመጀመሪያውም የፍልስጤም ነው ብሎ እንደሚያምን ይናገራል። ስለዚህም ዛሬ ላይ ምእራብ እየሩሳሌም ለእስራኤል ፤ምስራቅ ደግሞ ለፍልስጤም መሆን እንዳለበት አምናለሁ ይላል። ጋዜጠኛና በመንፈሳዊ ኮሌጅ መምህር የሆነው ሄኖክ ያሬድ ደግሞ ቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም ከሃይማኖት፣ ከታሪክ፣ ከባህልና ከቅርስ አንፃር ለኔ ልዩ ቦታና ትርጉም አላት፡፡ አንድም በባሕረ ሐሳባችን ዘመን አቆጣጠራችን የምንጠቀምበት ዓመተ ምሕረት እንዲሁም ዓመተ ዓለም መነሻውና መድረሻው ከቅድስት ሀገር ጋር ይያያዛል፤ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከጽንሰቱ እስከ ዕርገቱ የተመላለሰባት ናትና ይላል። ከአባቱ ጋር ወደ እየሩሳሌም የሄደው ከአምስት ዓመት በፊት ለኢትዮጵያዊያንም ሆነ ለቤተ እስራኤሎቹ የዐዲስ ዓመት መጀመሩያ በሆነው በወርኃ መስከረም ነበር። በመጽሐፍ ቅዱስ፣ በታሪክ ትምህርቶችና በምስል፤ በመስማትም ጭምር የሚያውቃትንና የበርካታ ኢትዮጵያዊያን ሕልም እየሩሳሌምን ማየት ልዩ ስሜት እንዳሳደረበት ያስታውሳል፡፡ ወሬ ባይን ይገባል እንዲሉ የመጽሐፍ ቅዱስን ታሪክ ከምስልና ከንባብ ባሻገር ታሪካዊ ኩነቶች የተፈጸሙበት ሥፍራ ላይ መገኘት ምንኛ ደስ ይላል ዕፁብን ዕፁብ ትለዋለህ እንጂ ምን ሌላ ቃል ታበጅለታለህ እንዲል ያገሬ ሰው ይላል ሄኖክ። ከክርስቶስ ልደት በፊት የንግስት ሳባና ንጉስ ሶሎሞን ታሪክን እንዲሁም የቀዳማዊ ምኒሊክ መወለድን በማስታወስ እነዚህ ነገሮች ኢትዮጵያን ከእየሩሳሌም ጋር እንደሚያቆራኝ ይናገራል። በተጨማሪም በእስራኤል የሚገኙት የኢትዮጵያ ገዳማት ኢትዮጵያውያንን ከእየሩሳሌም ያስተሳሰረ ሌላ ጉዳይ መሆኑን ያስረዳል። ተጓዦችን ወደ እየሩሳሌም ከሚወስዱ የጉዞ ወኪሎች መካከል ቀራኒዮ በእየሩሳሌም አንዱ ነው። ወ ሮ እጅጋየሁ በየነ የድርጅቱ መስራችና ስራ እስኪያጅ ናቸው። ድርጅቱ ዓ ም ላይ እነዴት ተመሰረተ በቀዳማዊ ሐይለስላሴ ስልጣን ዘመን የተመሰረተና ወደ እየሩሳሌም ለኢትዮጵያዊያን ጉዞ የሚያመቻች ማህበር አባል ነበሩ ወ ሮ እጅጋየሁ። አሁንም የዚሁ ማህበር አባል ናቸው። በዚህ ማህበር ወደ እየሩሳሌም ጉዞ ሲያደርጉ በነበረበት ጊዜ የኢትዮጵያዊያን ወደ እየሩሳሌም የመሄድ ፍላጎት ከፍተኛ መሆኑን ማስተዋላቸው ድርጅቱን ለማቋቋም መነሻ እንደሆናቸው ይናገራሉ። ምንም እንኳ ዛሬ ላይ የተለያዩ የጉዞ ወኪሎች ቢኖሩም ፍላጎቱ ከፍተኛ በመሆኑ ተጨማሪ የጉዞ ወኪሎች ወደ ስራው ሊገቡ እንደሚችሉ እምነታቸውን ይገልፃሉ። ዓላማዬ ትርፍ አይደለም።ብዙዎች ያችን ምድር ረግጠው እንዲመለሱ እፈልጋለሁ።እንጀራ ሸጣ ያሳደገች እናትን እንዴት ላስደስት የሚሉ ልጆች ለእናቶቻቸው የሚያደርጉት ነገር ነው ይላሉ። ቀራኒዮ በእየሩሳሌም ስራ ሲጀምር ወደ እየሩሳሌም የወሰደው ሰዎችን ነበር። ያኔ በአመት አንድ ጊዜ ብቻ ነበር ጉዞ የሚያዘጋጀው አሁን ግን በዓመት አራት ጉዞዎችን የሚያዘጋጅ ሲሆን ለምሳሌ ለገና በአል ሰዎችን ለመውሰድ መዝግቧል። እስከ ተጓዦችን የወሰዱበት ጊዜም እንዳለ ወ ሮ እጅጋየሁ ይናገራሉ። መሄድ የማይፈቀድላቸው ሄደው ይቀራሉ ብለው የሚገምቷቸውን ወጣቶች አይወስዱም። መጓዝ እንፈልጋለን ብለው ወደ ቢሯቸው የሚሄዱ ወጣቶችን የተለያዩ ጥያቄዎችን እንዲሁም ማስረጃ እንዲያቀርቡ በመጠየቅ እንደማይቀሩ ካላረጋገጡ እንደማይወስዱ ወ ሮ እጅጋሁ ይናገራሉ። የወጣቶች እዚያ ሄዶ መቅረት በእስራኤልና በኢትዮጵያ መንግስትም ተጠያቂ ያደርጋል። በዚህ ምክንያት የተዘጉ የጉዞ ወኪሎችም አሉ። የሚሉት ወ ሮ እጅጋየሁ ብዙ ጊዜ የሚሄዱት ሴቶች እንደሆኑ ይናገራሉ። በተመሳሳይ የትምህርትና የስልጠና እድል አግኝተውም ይሁን ለጉብኝት ቪዛ ለማግኘት የተለያዩ ኤምባሲዎች የሚገቡ ወጣት ኢትዮጵያዊያን ሄደው ይቀራሉ ተብሎ ስለሚገመት ቪዛ ለማግኘት ይቸገራሉ። በዚህ መልኩ ካገኙት የትምህርትና የስልጠና እድል የተስተጓጎሉ ወጣት ኢትዮጵያዊያን ጥቂት አይደሉም። ጥሩ የሚባል የትምህርትና የስራ ደረጃ ላይ ያሉ ሆነው በተለያዩ ኤምባሲዎች የጉብኝት ቪዛ የተከለከሉ ወጣት ኢትዮጵያዊያን በተመሳሳይ ጥቂት አይደሉም። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በእየሩሳሌም ሰባት ገዳማት አሏት። እነዚህም ዴር ሱልጣን ፣ኪዳነ ምሕረት፣ቅዱስ ፊሊጶስ፣ ቅድስት ሥላሴ፣ ቅዱስ ገብርኤል፣ ቅዱስ አልዓዛርና ቤተልሔም ናቸው፡፡ ከእነዚህ አንዱ የሆነው ዴር ሡልጣን ገዳም በግዕዝ ደብረ ሥልጣን የሚል ትርጉም ያለው ሲሆን ከጌታ ቅዱስ መቃብር ቤተመቅደስ በስተምሥራቅ ይገኛል። ሄኖክ እንደሚለው ዴር ሡልጣን ጥንት ንጉስ ሰሎሞን ከኢትዮጵያ ለተለያዩ በዓላት ወደ እስራኤል የሚሄዱ ጎብኚዎችና መልዕክተኞች ማረፊያ ይሆን ዘንድ ለንግስት ሳባ የሰጣት እነደሆነ የቤተ ክርስትያን ታሪክን በመጥቀስ ይናገራል። ኋላም ገዳም ተመስርቶበት በኢትዮጵያ ነገስታት ሲረዳ መቆየቱን ይገልፃል። ከቀራንዮ በእየሩሳሌም የጉዞ ወኪል ስራ አስኪያጅ ወ ሮ እጅጋየሁ ንግግር መረዳት የሚቻለው ዛሬም ኢትዮጵያዊያን ገዳሙን እንደሚረዱ ነው። የመውደቅ ችግር ለተጋረጠበት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ኢትዮጵውያን እርዳታ ማድረጋቸውን ወ ሮ እጅጋሁ ይናገራሉ። ለዘመናት ያወዛገበች ከተማ ፍልስጤማውያን እስራኤላውያንም መዲናችን ነች እንደሚሏት እየሩሳሌም በመካከለኛው ምስራቅ ለዘመናት አወዛጋቢ የሆነ ጉዳይ የለም። እየሩሳሌም በአለም ዓቀፍ ደረጃም በተመሳሳይ መልኩ አወዛጋቢ ናት። አሁን ደግሞ የአሜሪካ እየሩሳሌምን በእስራኤል መዲናነት እውቅና መስጠትን ተከትሎ የእየሩሳሌም አወዛጋቢነት አይሏል። እየሩሳሌም በተለያዩ ምክንያቶች ለክርስትና፣ለአይሁድና ለሙስሊሙ የተቀደሰች ምድር ናት። በዚህ መልኩ የሶስቱም እምነቶች ትኩረት መሆኗም ለዘመናት እየሩሳሌም አከራካሪ ሆና እንድትዘልቅ አድርጓል። እስራኤል እንደ አውሮፓውያኑ በ እየሩሳሌም መዲናዋ መሆኗን ማወጇን ተከትሎ ፍልስጤማውያንም ምስራቅ እየሩሳሌምን ወደፊት የምትመሰርተው ፍልስጤም መቀመጫ ትሆናለች በማለት የይገባናል ጥያቄአቸውን አንስተዋል። ይህንን ዜና ያጋሩ ስለማጋራት
በኢትዮጵያ የሚገኙ ቤተ እስራኤላውያን ወደ ተስፋይቱ ምድር ፅዮን ውሰዱን ተማፅኖ
ኅዳር ይህንን ለማጋራት በ ዋትስአፕ ሰሞኑን በኢትዮጵያ የሚገኙ ቤተ እስራኤላውያን ላምበረት በሚገኘው ምኩራባቸው የእስራኤል መንግሥት የገባልን ቃል አላከበረም በሚል የፀሎት አድማ አካሂደዋል። ወደ እስራኤል እንዲመለሱ ከሶስት አመት በፊት የእስራኤል መንግሥት ቃል ቢገባም ቃሉ እንደታጠፈ ይናገራሉ። ተቃውሞው በኢትዮጵያ ብቻ ውስጥ ሳይሆን በእስራኤል የሚገኙ ቤተ እስራኤላውያን የተቃውሞ ሰልፍ በማድረግ የእስራኤል መንግሥት ቃሉን እንዲያከብር እንደጠየቁ በአዲስ አበባ የሚገኙ ቤተ እስራኤላውያን ማህበር ስራ አስኪያጅ አቶ አንዱአለም ውብ ምህረት ለቢቢሲ ገልጿል። ከጥቂት ዓመታት በፊት በእስራኤል የሚገኙ ቤተ እስራኤላውያን ላይ የዘር ማምከን ወንጀል ተፈፅሟል በሚል አስተዳደሩ ከፍተኛ ውግዘት ደርሶበታል። ዘርንም በመጨፍጨፍ የተለያዩ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ወንጅለውታል። በተደጋጋሚም በቤተ እስራኤላዊያን ላይ የሚደርሱ ተደጋጋሚ የዘረኝነት ጥቃትን በመቃወም ከፍተኛ ተቃውሞዎችም ተካሂደዋል። ምንም እንኳን እስራኤል እንደ ሁለተኛ ዜጋ ብታያቸውም አሁንም ሀገራችን እስራኤል ነው የሚሉ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ ቤተ እስራኤላውያን ፅዮንን ሙጥኝ እንዳሉ ነው። በባቢሎን ወንዞች አጠገብ በዚያ ተቀመጥን፤ ፅዮንንም ባሰብናት ጊዜ አለቀስን እንደሚለው ጥቅስ የፅዮን ማዕከልነትን መቼም እንደማይዘነጉ ይናገራሉ። ለአስርት ዓመታትም ወደ እሥራኤል ለመሔድ በመጠባበቅ ላይ የሚገኙ ቤተ እስራኤላውያን ከሶስት ዓመታት በፊት የእስራኤል መንግሥት ሁሉንም እንደሚወስድ ቃል ቢገባም ቃሉን እንዳላከበረ ኢትዮጵያ ላሉ ቤተ እስራኤላውያን የሚደረጉት እንቅስቃሴዎች ኃላፊ አቶ ንጉሴ ዘመነ አለሙ ይናገራል። እንዲህ የተጓጓተተበት ዋነኛው ምክንያት የእስራኤል መንግሥት በተደጋጋሚ የበጀት እጥረትን ምክንያት በማድረግ የተለያዩ ውሳኔዎች እያስተላለፉ እንደሆነ ገልጿል። ከመጀመሪያው ውሳኔ በተቃርኖም የተቀሩትን ዘጠኝ ሺ ሰዎች አንድ ላይ ሳይሆን በተለያየ ጊዜ ና አንድ ሺ ሰዎች እንደወሰዱ ተናግሯል። ይህ ውሳኔ ደግሞ ቤተሰብን ከሁለት የሚከፋፍል በመሆኑ መጀመሪያ የተወሰነውን ውሳኔ እንዲከበር እየጠየቅን ነው ያለነው ይላል። ከተለያየ ሀገር ለሚመጡ ይሁዲዎች የበረራ ወጪያቸውን የእስራኤል መንግሥት የሚሸፍን ሲሆን ከዚያም በተጨማሪ የቤት መግዣና ለአንድ አመት ያህል ሀገሪቱን እስኪለምዱ ድረስ የሚሰጥ ወርሃዊ የኪስ ገንዘብ ይሰጣቸዋል። ለአቶ ንጉሴ ግን የበጀት እጥረት ነው ቢባልም አሳማኝ እንዳልሆነ ይናገራል። ለዚህም እንደ ምሳሌ የሚያነሳው ከሶስት አመታት በፊት የእስራኤል አዲስ ገቢዎች ሚኒስትር የተናገሩትን ነው። የእስራኤል አዲስ ገቢዎች ቢሮ ትርፍ ብር በየዓመቱ በጀት እየተረፈ ሲመልስ እንጂ ተቸግሮ እንደማያውቅ ሚኒስትሩ ተናግረዋል። በጀት የሚለው ጉዳይ በተለያዩ መስሪያ ቤቶች የሚሰሩ ኃላፊዎች ያመጡት ችግር እንጂ እውነት የበጀት እጥረት ነው ብየ አላምንም ይላል። በእስራኤል ታሪክም በተደጋጋሚ ከመቶ በላይ ኃገራት አዲስ ገቢዎች ሲመጡ የበጀት ችግር አጋጥሞኛል ብላ እስራኤል እንደማታውቅ ይናገራል። ለመጀመሪያ ጊዜ የኢትዮጵያ ይሁዲዎች እንዲመለሱ በተወሰነበት ሰዓት ነው የበጀት ጥያቄ መነሳት የጀመረው አሁን እንደሆነ ጠቅሶ የዘረኝነትና የፖለቲካ ምክንያቶች ሊሆኑ እንደሚችሉ ይጠቅሳል። አቶ አንዱአለም በበኩሉ እንደ ምክንያትነት የሚያቀርበው እስራኤል በአፍሪካውያን ላይ ያላትን እይታ ነው። የቤንያሚን ኔታንያሁ መንግሥት አቅም አንሶት ሳይሆን ዘረኝነት ነው። ኢትዮጵያዊ እንዲሁም አፍሪካዊ በመሆናችን እንጂ ሀገሪቱ የኢኮኖሚ አቅም ችግር አላት ብለን አናምንም ይላል። ለዚህም ምላሽ በእስራኤል የሚገኙ ከ ሺ በላይ የሚገኙ ቤተ እስራኤላውያንም እያቀረቡት ያለውም ሀሳብ ስንመርጥህ ቤተሰቦቻችንን ከኢትዮጵያ እንደምታመጣልን ቃል ስለገባህልን ነው እንዳሉም አቶ አንዱአለም ለቢቢሲ ገልጿል። ብዙዎች ለአስርት ዓመታት ከቤተሰቦቻቸው ተነጣጥለው እንደሚገኙ የሚናገሩት አቶ አንዱአለም እንደ ምሳሌም የሚያነሱት የራሳቸውን ቤተሰቦች ነው። ከሰባ አመት በላይ ዕድሜ ያላቸው አባትና እናቱ ወደ እስራኤል የሄዱ ከ ዓመታት በፊት ሲሆን ሶስት ታናናሽ ወንድሞቹም አብረው ሄደዋል። ከቤተሰቦቻችን ጋር ኢሰብዓዊና ፍትሀዊ በሆነ ሁኔታ ተለያይተናል። ለምን እንደለያዩን አላውቅም፤ ለመኖር በሚከብድ ሁኔታ ላይ ነው ያለነው ይላል አባቱን በሰባት ዓመት ውስጥ አናግሯቸው የማያውቅ ሲሆን የተሰማውንም ለመግለፅ ቃላት ያንሰዋል ህልውናውን ስቶ ሰው እያነሳ እየጣለው ድምፁን እንኳን ሰምቼ አላውቅም። ይህም በስነ ልቦናየ ላይ ከፍተኛ ተፅእኖ አሳድሮብኛል። ጥዋት ማታ ላየው የምፈልገው አባቴን ድምፁን እንኳን መስማት ሲያቅተኝ የሚሰማውን ስሜት መገመት ይቻላል ይላል። ከዚህም በተጨማሪ እናቱም በለቅሶና በሐዘን ላይ መሆናቸውም የአቶ አንዱአለም የሌት ተቀን ራስ ምታት የሆነበት ጉዳይ ነው። እናቴ ሌት ተቀን በማልቀስ አይኗ ሁሉ ጎድጉዶ እንደ ሉሲ በአፅም አለች ማለት ይቻላል። በማለት እናታቸው የደረሰባቸውን ጥልቅ ሀዘንም ይገልፃል። በዚህም ምክንያትም በእስራኤል መንግሥት ላይ ምንም አይነት ተስፋ የለውም ለእስራኤል መንግሥት ጥሩ አመለካከት የለኝም። በኛ ላይ ያደረሰው ጭካኔ ነው ይላል ከዚህም በተጨማሪ ቤተ እስራኤላውያን የእስራኤል ባለስልጣናት የፖለቲካ ፍጆታ ማስፈፀሚያ እንደሆኑም አቶ አንዱአለም ይሰማዋል። ለዚህም እንደምሳሌ የሚያነሳው ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ውስጥ ተገኝተው ያደረጉትን ንግግር ነው። ከአፍሪካ የወሰድናቸውን ኢትዮጵያውያንን ከፍተኛ ስልጣን በመስጠት ላይ ነን፤ ከኛ ተማሩ ማለታቸውን ገልፆ ይህ አባባል ግን ፍፁም ከእውነት የራቀ እንደሆነ ይናገራል። በተቃራኒው አቶ አንዱአለም እኛ ሰው መስለን አንታያቸውም ይላሉ። ለአስርት ዓመታትም እስራኤል እንሄዳለን በሚል ጥበቃ ብዙዎች ከገጠር ተሰደው አዲስ አበባ ላይ ኑሮን መቋቋም እንደከበዳቸው አቶ ንጉሴና አቶ አንዱአለም ይናገራሉ። ኑሮው በጣም ከባድ ነው፤ በእንግልትም ላይ ነው ያሉት ግን ወደ ፅዮን እንሔዳለን ብለው ነው ይህን ያህል መከራ እየከፈሉ ያሉት ይላል አቶ ንጉስ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ መልስ ይሰጡናል የሚል ተስፋ ቢኖራቸውም ጥያቄያቸው መልስ ካላገኘ ምን አይነት እርምጃ ይወስዱ ይሆን አቶ ንጉሴ የሚለው አለው። ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ናታንያሁ ፅዮናዊ ናቸው፤ እንዲሁም በመላው አለም የሚገኙ ይሁዲዎችን ለመመለስ በጣም ከፍተኛ ጥረትም ያደርጋሉ በሚል አቶ ንጉሴ ተስፋውን ገልጿል። ምላሽ ካልተሰጣቸው በእስራኤል የሚገኙ ቤተ እስራኤላውያን በሚሰጡት መመሪያ እንደሚቀጥሉ ይናገራል። የረሀብ አድማ አንዱ የተቃውሞ መንገድ ሊሆን እንደሚችል ጠቁሞ ከዚህም በተጨማሪ በእስራኤል የሚገኙ ቤተ እስራኤላውያን መፍትሔ ለማግኘት ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጉዳዩን ወስደውታል። አቶ አንዱአለም በበኩሉ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ ቤተ እስራኤላውያን አቅም ስለሌላቸው ይህ እንደሚፈፀምባቸው ጠቁሞ ወደ አምላክ ከመጮህ ውጭ ምንም ነገር የለም። የኛ ዋስትና እስራኤል ውስጥ ያሉ ቤተ እስራኤላውያን የሚያደርጉት ጫና ይወሰናል ይላል። የቤተ እስራኤላውያን አመጣጥ የንግሥት ሳባ ልጅ የሆነውን ሚኒልክን አጅቦ ከመምጣት ጋር የሚያይዙት እንዳሉ ሁሉ የእስራኤል በባቢሎናውያን መወረርን ተከትሎ ከተሰደዱት መካከልም እንደሆኑ ታሪክን አጣቅሰው ይናገራሉ። በታሪክ ውስጥም የተለያዩ ስያሜ የተሰጣቸው ሲሆን ቤተ እስራኤል የተባሉትም በአብርሃ ወአፅብሃ ዘመነ መንግሥት ክርስትናን አልቀበልም በማለታቸው እንደሆነ የታሪክ መዛግብት ይጠቅሳሉ። በተለያዩ አመታትም ቤተ እስራኤላውያንን የመመለስ ስራ የተሰራ ሲሆን ከነዚሀም ውስጥ ኦፐሬሽን ሙሴና ኦፐሬሽን ሰለሞን ይጠቀሳሉ። በነዚህም ጉዞዎች በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ቤተ እስራኤላውያን ሄደዋል። ቢቢሲ ማስተባበያ
በአዲስ አበባ ከተማ ከ ዓመታት በላይ አፋን ኦሮሞ በማስተማር ብዙ ውጣ ውረዶችን ያሳለፉት መምህር
ጥቅምት ይህንን ለማጋራት በ ዋትስአፕ መምህር ተፈራ በዳግማዊ ሚኒሊክ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አፋን ኦሮሞን ያስተምራሉ ስሜ ተፈራ ተኤራ ይባላል። አንዳንድ ሰዎች አምባሳደር እያሉ ይጠሩኛል። ይህን ስም አፋን ኦሮሞን በማስተማሬ ደስተኛ የሆኑ ሰዎች ናቸው ያወጡልኝ። በ ዓ ም ከአሁኑ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የንግድ ሥራ ኮሌጅ በሒሳብ አያያዝ በዲፕሎማ ተመርቄያለሁ። ለጥቂት ዓመታትም በሒሳብ አያያዝ ሙያ ሠርቻለሁ። ከልጅነቴ ጀምሮ ለኦሮሞ ቋንቋና ባህል ጥልቅ ፍቅር ነበረኝ። የሒሳብ ሥራ ሙያዬን እርግፍ አድርጌ በመተው ለብዙ ዓመታት ለመስራት ስመኝ የነበረውን ስራ ጀመርኩ። መምህር ተፈራ ተኤራ በ ዓ ም አፋን ኦሮሞ የክልሉ የሥራ ቋንቋ እንዲሆን ከተወሰነ በኋላ አፋን ኦሮሞን የሚያስተምር መፅሐፍ እጄ ገባ። ከዛም ከሌሎች ሰዎች ጋር በመሆን ከኦሮሚያ ባህል እና ቱሪዝም ቢሮ ፍቃድ በመውሰድ በባልቻ አባ ነፍሶ ትምህርት ቤት ውስጥ ማስተማር ጀመርን። ከእኔ ጋር ማስተማር ጀምረው የነበሩት ጓደኞቼ በፖለቲካ እና በተለያየ ምክንያት ለትንሽ ጊዜ ካስተማሩ በኋላ ማስተማራቸውን ለማቋረጥ ተገደዱ። በእኔ ላይም ይደርስ የነበረውን የተለያየ ጫና ተቋቁሜ ማስተማሬን ቀጠልኩ። ባለፉት ዓመታት አፋን ኦሮሞን በማስተማሬ ደስተኛ ያልነበሩ ሰዎች ብዙ ስሞችን አውጥተውልኛል። ቁቤ፣ ላቲን፣ ኦሮሚያ፣ ወሬ እና ሌሎችም ብዙ ስሞች ወጥተውልኝ ነበር። አንድ ቋንቋ ሊያድግ የሚችለው የቋንቋ ተናጋሪዎችስለተናገሩት ብቻ ሳይሆን የሌላ ብሔር ተወላጆችም ቋንቋውን መናገር ሲችሉ እንደሆነ ጥልቅ እምነት አለኝ። ለዚህም ነው መማር የሚፈልጉትን በሙሉ ሳስተምር የኖርኩት። ሰዎች አፋን ኦሮሞን ማንበብ እና መጻፍ እንዲችሉ አስተምራለሁ። በባልቻ አባ ነፍሶ ኛ ደረጃ ት ቤት ውስጥ ከ ዓ ም ጀምሮ ለ ኛ ዙር እያስተማሩ ነው ከ ዓ ም ጀምሮ ደግሞ በሚኒሊክ ት ቤት ለ ኛ ዙር በማስተማር ላይ ይገኛሉ። እስከአሁን ድረስም በወር ብር ብቻ በማስከፈል እያስተማርኩ እገኛለሁ። ማስተማር ስጀምር የነበረው ዋጋ አሁንም አልተቀየረም። በርከት ያሉ ጋዜጠኞች፣ መምህራን፣ ሃኪሞች፣ መሃንዲሶች እንዲሁም የመንግሥት ባለስልጣናት እኔ ጋር መጥተው ተምረዋል። ባለፉት ዓመታት ቋንቋውን በማስተማሬ ብዙ ችግሮችን አሳልፌያለሁ። ማስተማሬን እንዳቆም የተለያዩ ዛቻዎች እና ማስፈራሪያዎች ይደርሱኝ ነበር። በስለት ተወግቼያለሁ፤ የተፈራ ቁቤ ይወድማል ተብሎም ቤቴ በር ላይ ተለጥፏል። በዛ አስቸጋሪ ወቅት ተማሪዎቼ ነበሩ እስከ ቤቴ ድረስ የሚሸኙኝ። አ ፋ ን ኦሮሞ አሁን ተፈላጊ ሆ ኗ ል የተፈራ ቁቤ ይወድማል ሲሉ የነበሩ፤ ዛቻዎችን እና ማስፈራሪያዎችን ሲልኩ የነበሩ ሰዎች ራሳቸው ዛሬ ላይ አፋን ኦሮሞ አስተምረን እያሉ ነው። ትምህርታቸውን ካጠናቀቁ ተማሪዎችጋር ይህም ቋንቋችን ምን ያህል ተፈላጊ እየሆነ እንደመጣ ያሳየኛል። አሁን ጊዜው ተቀይሯል። በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎችን የኦሮሞን ቋንቋና ታሪክ አስተምሬያለሁ። ዘንድሮ በአዲስ አበባ በአፋን ኦሮሞ የሚያስተምሩ ት ቤቶች በመከፈታቸው አጅግ ደስተኛ ነኝ። ድካሜም ከንቱ አልቀረም። በለፉት ዓመታት በስራዬ መልካም የሚባል ጊዜን ባላሳልፈም፣ በህይወቴ የሚያኮራኝን ተግባር የመፀምኩባቸው ዓመታት ናቸው። እድሜዬ ወደ እየተጠጋ ነው። እርጅናም እየተጫጫነኝ ነው። አሁን የምፈልገው ሥራዬን ተረክበው የሚያስቀጥሉ ወጣቶችን ነው። ቢቢሲ ማስተባበያ
ከነፍስ የተጠለሉ የድምፃዊት ዘሪቱ ከበደ ዜማዎች
መስከረም ድምጻዊት ዘሪቱ ከበደ በመድረክ ላይ ሥራዋን ስታቀርብ ዘሪቱ ከበደ አርተፊሻል በተሰኘው ነጠላ ዜማ ውስጥ ስሜታችን አርተፊሻል ሰው ሰራሽ ፣ ምኞታችን አርተፊሻል፣ ውበታችን አርተፊሻል፣ ሕይወታችን አርተፊሻል ስትል ማኅበራዊ ትዝብቷን ታጋራለች። ድንዛዜ፣ አልበዛም ወይ መፋዘዙ ነቃ በሉ ፣ አልበዛም ወይ ማንቀላፋት ኃ ላፊነትን መዘንጋት ስትል ትጠይቃለች፤ ዘሪቱ በዚሁ ሥራዋ ውስጥ ድንዛዜ በወሬ ፣ ያለጥቅም ያለ ፍሬ ድንዛዜ በጭፈራ ፣ ያለ ዓ ላማ ያለ ሥ ራ ድንዛዜ በከተማ ፣ ሰው የ ሰው ብቻ እየሰማ ስትል የሰላ ትችቷን ታቀርባለች። ዘሪቱ በሊቢያ አንገታቸውን በተቀሉ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች የተሰማትን ቁጣ በገለፀችበት ነጠላ ዜማዋ ላይ ሠይፍህን አንሳ ስትል አቀንቅናለች። ሠይፍህን አንሳ ፣ ያበራልሃል ለጠላት መልሱን ያስተምርሃል ሠይፍህን አንሳ ፣ ትረፍ ከበቀል ኃይል ይሆንሃል እንድትል ይቅር፤ ስትል ለበደሉ ይቅርታ ማድረግን ትሰብካለች። ዘሪቱ የምንኖርበትን ዓለም አሁን በብርሃን አይቼሻለሁ ብላ መጠየፏን በገለፀችበት ሥራዋ፤ የነበረችበትበን የሕይወት መልክና ልክ ስትገልፅ ማለለ ፣ ልቤ ማለለ ፣ ታለለ ፣ ልቤ ታለለ ሳተ ከቆመበት ተንከባለለ እያለች ታንጎራጉራለች። ለመጨረሻ ጊዜ ያየሁት በትንሳኤ በዓል ነበር የብርጋዴር ጄነራል አሳምነው ፅጌ እናት ድምፃዊት ዘሪቱ በተለያየ ጊዜ በሠራቻቸው እነዚህ ነጠላ ዜማዎች ማኅበራዊ ትችቷን፣ የሕይወት አቋማን ገልጻለች። አርተፊሻል የተሰኘውና ለአካባቢ ጥበቃ እንደተሠራ የምትናገረው ሙዚቃ፣ ሠይፍህን አንሳ የተሰኘውና በሊቢያ አንገታቸውን በአክራሪ ኃይሎች ለተቀሉት ኢትዮጵያውያን ያቀነቀነችው እንዱሁም ውሸታም የተሰኘ ሙዚቃዋ ውስጥ ዓለምን መጠየፍ ይታያል። ዘሪቱ ከእኛ ጋር ለመጨዋወት ፈቅዳ ስትቀመጥ ያቀረብንላት ጥያቄዎችም እነዚሁ ሥራዎቿን የተመለከቱ ናቸው። ቃለ መጠይቁን ከመጀመራችን በፊት ዘሪቱ ጠቆር ያለ ማኪያቶ አዛ እንዲህ አወጋን ቢቢሲ፡ እነዚህ ሦስት ሥራዎች አርተፊሻል ፣ ሠይፍህን አንሳ ፣ እንዲሁም ውሸታም እርስ በእርሳቸው ግንኙነት አላቸው ዘሪቱ፡ የእርስ በእርስ ግንኙነታቸው የኔ መሆናቸው ነው። ሳቅ ከዚያ ውጪ ግን ያው እኔ የትኛውንም ሥራ ስሠራ ወይ ከሕይወቴ ነው፤ ወይ ከማየው ነገር፣ ከተነካሁበት ነገር ተነስቼ ነው የምደርሰው። ስለዚህ ከእኔ ጋር ግንኙነት አለው። መጀመሪያ አርተፊሻል የሚለው ነጠላ ዜማ ሲወጣ ለአካባቢ ጥበቃ ተብሎ አንደተሠራ ተነግሮ ነበር። ነገር ግን ሥራውን ልብ ብሎ ላደመጠው ፤ የአካባቢ ጥበቃ ላይ የሚያተኩር አይመስልም። ዘሪቱ ፡ ልክ ነው መነሻው እንደዛ ነው። በዚያ ሰዓት ብሪቲሽ ካውንስል የክላይሜት የአየር ጠባይ ለውጥ አምባሳደር ብሎ ከመረጣቸው አርቲስቶች ውስጥ ድምፃዊ እኔ ነበርኩ። በዚያ ሰዓት ኢትዮጵያ አረንጓዴ የሚባል ኢኒሼቲቭ ከሚካኤል በላይነህና ከመሐመድ ካሳ ጋር ጀምረን ለመንቀሳቀስ እንሞክር ነበር። እና በሆነ መንገድ ግንኙነት አለው አርተፊሻል የተሰኘው ስራ ከአካባቢ ጥበቃ ጋር ። በአንድ የጦር አውድማ ላይ ከወላጅ አባቷ ጋር የተፋለመችው ታጋይ ግን አርት ፕሮሰሱ ውስጥ የምትረካበትን ነገር ትፈልጋለህ። ስለዚህ ብሪቲሽ ካውንስል ከአካባቢ ጥበቃ ጋር ተያይዞ አንድ ሙዚቃ ይሠራ ብለው ኢንቨስት ገንዘብ ያወጡበት ያደረጉበት ፕሮጀክት ነው። ግን ምንድን ነው፤ ዳይሬክትሊ በቀጥታ ያንን ጉዳይ ብቻ የሚወክል ሥራ ለመሥራት ተሞክሮ የሚያረካ አልሆን አለ። እና በአጋጣሚ እዚያው ፕሮሰሱ ውስጥ እያለሁ አርተፊሻል የሚለውን ሙዚቃ ፃፍኩት፤ በአጠቃላይ የአካባቢ ጥበቃንም ይመለከታል። ከሁሉም በላይ ግን ተፈጥሮ ውስጥ ሰውም አለ። ስለዚህ ሰውን ጥበቃ ሳቅ ላይ የበለጠ የሚያተኩር ሥራ ሊወለድ ችሏል ማለት ነው። ወደ አውሮጳ ለመሻገር በስደት ላይ እያሉ በሊቢያ አንገታቸው ስለተቀሉ ወጣቶች የ ሠ ራሽው ደግሞ ሠይፍህን አንሳ ይሰኛል። ለዚያ ሥ ራ መወለድ አንቺ ውስጥ የነበረው የወቅቱ ስሜት ምን ይመስል እንደነበር እስቲ አስታውሺኝ። ዘሪቱ ፡ ኡ ሠይፍህን አንሳ ከከባድ ስሜት ውስጥ ነው የተወለደው። በዚያ ሰዓት በእነዚያ ወጣቶች ላይ የደረሰው ነገር በጣም ያስፈራ ነበር። በጣም ያስቆጭ ነበር። እልህ ያሲይዝ ነበር። ቁጣ እንዴት ብለህ ነው የምትገልፀው ቁጣ ወገን ናቸው፤ የሰው ልጅም ናቸው። በጣም ተገቢ አይደለም። ስለዚህ በጣም ቁጣ ተሰማኝ፤ በውስጤ። ከዚያ ቁጣ በኋላ ግን የትም ልሄድ አልችልም። ምንም ላደርግ አልችልም። ያ ተስፋ መቁረጥ ደግሞ ሌላ የድባቴ መንፈስ፤ ስሜት አስከተለ። ያ ደግሞ የኔ ብቻ ሳይሆን አካባቢዬንም ሳይ ብዙዎቻችን ላይ ያየሁት፣ ሀገሪቱም ላይ፣ አየሩም ላይ የነበረው መንፈስ እንዴት ጨፍጋጋ እንደነበር አስታውሳለሁ። እና በረዥሙ ተንፍሳ የሆነ ነገር ማበርከት እንዳለብኝ ተሰማኝ። በአካባቢዬም በዚያ ስሜት ውስጥ አብረውኝ የነበሩ ወንድም እህቶቼ የሆነ ነገር ማካፈል እንዳለብን ተማመንና በዚያ ጉዳይ መፀለይ ጀመርኩ፤ ማሰብ ጀመርኩ። ስቱዲዮ ውስጥ፣ በዚያ ሰዓት ሳነበው የነበረው መጽሐፍ አለ፤ የሪክ ጆነር ዘ ቶርች ኤንድ ዘ ሶርድ ፣ የሚል መጽሐፍ፤ እዚያ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ያለውን የሠይፍ ምስል ሳየው መልዕክቱ እንደመጣልኝ ተሰማኝ፤ ገባኝ። ከዚያ ስቱዲዮ ውስጥ ነው ዴቬሎፕ ስራው የዳበረው መደረግ የጀመረው። በዓመቱ አነጋጋሪ ከነበሩ ጉዳዮች ጥቂቱ ከዚያ ዳዊት ጌታቸው የሙዚቃ መምህር፣ አቀናባሪና ዘማሪ ጋር ሄድኩኝ። ዳዊት ጌታቸው ሌላ ጊዜ መዝሙር ነው የሚሠራው፤ የእግዚአብሔር ፈቃዱ ሆኖ ይህንን ለመሥራት ፈቃደኛ ሆነ። እናም አብረን ልነሠራው ቻልን። እኔም ሆንኩ ምድሪቱ ከነበርንበት ከዚያ ስሜት ውስጥ ተስፋ ይሆናል፤ መፅናኛ ይሆናል መልስ ይሆናል ብዬ ያሰብኩበትንና የተቀበልኩትን መልዕክት ለማድረስ ነው የተሠራው። ሙዚቀኛ ዳዊትን ስትጠቅሺው ከዚህ በፊት መዝሙር ነው ይሠራ የነበረው አልሽኝ። ይህ ሥ ራ መዝሙር አይደለም ብለሽ ነው የምታምኚው ዘሪቱ፡ ሳቅ ነው፤ መንፈሳዊ ነው። የምልህ መነሻው መንፈሳዊ ነው። መነሻ የሆነኝም መጽሐፍ መንፈሳዊ ነው። ሠይፍ የሚለውም ቃል የእግዚአብሔርን ቃል፣ የእግዚአብሔርን ኃይል፣ የእግዚአብሔርን ምላሽ መወከሉ መንፈሳዊ ነው። ሃይማኖታዊ ግን አይደለም። ያ ነው ልዩነቱ እንጂ መንፈሳዊ ነው። ከእነዚህ ሥ ራዎችሽ በኋላ ደግሞ ውሸታም የሚለውን ሥ ራሽን ስታቀርቢ ዘሪቱ ዓለምን እየተጠየፈች ይሆን አልኩኝ እውነት ዓለምን እየተጠየፍሽ ነው ዘሪቱ፡ አርተፊሻል ፣ ከሁለቱ ዘፈኖች በተለየ በቀጥታ መንፈሳዊ አይደለም። ለምን መነሻው ማኅበራዊ ትዝብት ነው እንጂ ከመንፈሳዊነት የመነጨ አይደለም። መንፈሳዊ አይደልም ማለት ግን አይቻልም። ለምን እንድንሆን የሚመክረው፣ ወይም አልሆንም ብሎ የሚወቅሰው ማንነት፣ እንግዲህ እኔ የማምነው አምላክ፣ እንድንሆንለት ሽቶ በአምሳሉ ከፈጠረው ማንነት ውጪ ሆነናል ነው። ለምን በዚያ ማንነት ውስጥ ያለ ሰው አካባቢውን ይጠብቃል፤ ከሰዎች ጋር አብሮ ይሆናል። በስስት የተያዘ አይሆንም፤ ስለዚህ ሆነናል የተባሉት ነገሮች ሁሉ ሰው ስንሆን ከታለመልን፣ እንድንሆን ከታሰበልን ውጪ ሆነናል፤ ስለሆነም እንደ መንፈሳዊ መልዕክት ኳሊፋይ ያሟላል ያደርጋል ብዬ አስባለሁ። መነሻው ግን አይደለም። ሠይፍህን አንሳና ውሸታም ግን ከመንፈሳዊ ሕይወትና በቀጥታ ከመንፈሳዊ ማንነት ጋር የተገናኙ ናቸው ለእኔ። እና ዓለምን እየሸሽ ነው ዘሪቱ፡ ፈገግታ ያው ከዓለም ወዴት ይኬዳል ሳቅ ዓለማዊ አለመሆን ግን ይቻላል። የዓለም ውሸት፣ የዓለም ሽንገላ፣ ባታለለኝ ወቅት የጻፍኩት ነው። ባለማወቅ የምንሆናቸው ነገሮች አሉ። ካወቅን በኋላ ደግሞ ከእኛ የተሻለ ሲጠበቅ፣ መንገድ አሳይ መሆን ሲጠበቅብን፣ በተላላነት ተይዘን ፈገግታ እንደተሞኘን ሲገባን ፈገግታ ተመልሰን የማውቀውን ይሄንን ምን ነካኝ ብለን የዓለምንና የገዢዋን ሽንገላ ለማጋለጥና ከዚህ በኋላ አንስትም የሚለውን ሳቅ መልዕክት ለማስተላለፍ ነው። በፕሮቴስታንት እምነት ተከታይነቱ ለእስር ተዳርጎ የነበረው ኤርትራዊ ህይወቱ አለፈ ያዘዘችው ጠቆር ያለ ማኪያቶ መጥቶ ጭውውታችንን ለአፍታ አቋረጥን በስምሽ ከተሰየመው አልበምሽ ሌላ ባሉት ከእነዚህ ሦስት ስራዎችሽ ውጪ፣ አዝማሪ ነኝ የሚውም ሥ ራሽን ስንመለከት በ ሥ ራዎችሽ የሕይወት አቋምሽን እየተናገርሽና እያስቀመጥሽ ነው የምትሄጂው ማለት እንችላለን ዘሪቱ፡ ልክ ነው፤ እንደዚያ ነው። የመጀመሪያው ሥራዬ ዘሪቱ አልበም በወቅቱ የነበረኝ ማንነት ነው። በማንነቴ ሳድግ፣ መንፈሳዊነት በውስጤ ማደግ ሲጀምር፣ በዚያ መንገድ እያደግሁ ስመጣ ወይንም ደግሞ በዚያ መንገድ መጓዝ ስጀምር፤ ያው ያንኑ የሚመስል ነገር ነው የሚወጣኝ። ስለዚህ ከአሁን በኋላም ሕይወቴን የሚመስል፣ ያለሁበትን ቦታ የሚመስል ሥራ ነው ከእኔ የሚወጣው። ድምጻዊት ዘሪቱ ከበደ ስለዚህ ከአሁን በኋላ እየ ሠ ራሽ የምትቀጥይው የሕይወቴ መርሆዎች ናቸው የምትያቸውን ብቻ ነው ማለት ነው ዘሪቱ፡ በፊትም እንደዛ ነው። ሳቅ ምንም አዲስ ነገር አይደለም። ለምን እውነት ለኔ፣ ከመጀመሪያውም ቢሆን ጽሁፍም ሆነ ሙዚቃ፣ እውነትና ራሴን፣ ሕይወቴን፣ ታሪኬንና ኤክስፒሪያንሴን ልምምዴን ከማካፈል ጋር የተገናኘ ነው። ስለዚህ ማንነቴ በሚሄድበት አቅጣጫ፣ ሥራዬም እየተከተለ ይሄዳል። ለምን የሙዚቃ ስራን በሌላ መንገድ አላውቀውም። ወይንም በሌላ መንገድ ላበረክት የምችለውን፤ በጽሑፍም ሆነ በፊልም ሥራም ይሁን የማምንበትንና የሚመስለኝን፣ ለሰው ይጠቅማል ብዬ የማስበውን ወይንም መወከል አለበት ብዬ የማስበውን ማኅበረሰብ፤ ሆን ብዬና መርጬ ነው የማደርገው። እንጂ በዚህ አቅጣጫ የሆነ ነገር ቢፃፍ ገበያ ላይ የሆነ ነገር ያመጣል፣ ወይም ለኔ የሆነ ክብር ይጨምራል በሚል አይደለም። ስለዚህ ከሕይወቴ በማካፈል ነው የምቀጥለው። መርሄንም ይሁን፣ ኤክስፒሪያንሴንም ይሁን፣ አስቂኝ ገጠመኝም ይሁን፣ ጥበብ ስለሆነ ሁሉንም ሳጥን ሰርተን አናስቀምጠውም። አንዳንዱ ሥራ በማንጠብቀው ሁኔታ ይመጣል። አልበምሽ ውስጥ የማይረሱ አገላለጾች እና የቋንቋ አጠቃቀሞች አያለሁ ። አሁን የምናወራባቸው ሥ ራዎች ላይ ግጥሞቹን ብንመለከት ጠንካራ ናቸው። ግጥምና ዜማ ላይ በጎ ተጽዕኖ ያ ሳረ ፈ ብሽ ባለሙያ አለ ዘሪቱ፡ እ ማንንም ሳላይ ነው መጻፍ የጀመርኩት። መጻፍ የጀመርኩት ከልጅነቴ ስለሆነ። በልጅነት ውስጥ ዝም ብዬ በዜማም ይሁን በግጥም ራሴን መግለጽ የጀመርኩት በተገኙ ርዕሰ ጉዳዮች ሁሉ ነው። በመጀመሪያ ወደ ሙዚቃ ለመሳቤ እነሴሊንዲዮን፣ ማሪያ ኬሪ፣ ዊትኒ ሂውስተን ምክንያት ናቸው። ወደ የሙዚቃ ግጥም አጻጻፍ ስንመጣ ትሬሲ ቻፕማን፣ ቦብ ማርሌና አላኒስ ሞርሴት መነሻዎቼ ናቸው። እነዚህ ሦስት አርቲስቶች ለዘፈን ጽሁፍ ወይም ደግሞ በዘፈን ውስጥ ለሚነገሩ መልእክቶች መነሻዬ ናቸው። አንድን ሰው፣ አንድን አርቲስት ያገኘሁት ያህል፤ አይደንቲቲውን ማንነቱን ፣ መልዕክቱን፣ ጉዞውን፣ ከለሩን፣ ከልጅነቴ ጀምሮ እንዳጣጥም እና እንዲገባኝ አድርገዋል። በተለይ አላኒስ ሞርሴት እኔ የምሞክራቸው ነገሮች ሴንስ ትርጉም እንዲሰጡ ያደረገች አርቲስት ናት። እና እነዚህ ናቸው የመጀመሪያዎቹ ተጽዕኗቸውን ያሳረፉብኝ ከዚያ በኋላስ ዘሪቱ፡ ከዚያ በኋላ በራሴ መንገድ ነው የሄድኩት። ግጥሞችሽን አይተው እነዚህ ለዘፈን አይሆንም ያሉ ነበሩ ዘሪቱ፡ እ ትንሽ አሰብ አድርጋ አይ እንደዚያ ሳይሆን፣ እንደውም በመጀመሪያዎቹ ስቱዲዮ ውስጥ በነበርኩባቸው ጊዜያት በጣም ቀላል ናቸው። ጠንከር ያለ የአማርኛ ግጥም መልክ የላቸውምና አይሆኑም ወይም አያስኬዱም የሚሉኝ ብዙ ሰዎች ነበሩ። ስላልሰሟኋቸው እግዚአብሔር ይመስገን ። ረዥም ሳቅ ። ግን ኤሊያስ በተለየ መልኩ ኢንካሬጅ ያበረታኝ ያደርገኝ ነበር። አቀናባሪ ኤሊያስ መልካ ዘሪቱ፡ አዎ ኤሊያስ መልካ። እንደውም እንደዚህም ይቻላል ለካ። እንደዚህ ነው መሆን ያለበት። ቀላል ሆኖ፣ ከዜማ ጋር ተዋህዶ፣ ሰው ኢንጆይ እንዲያደርገው ዘና እንዲልበት ብሎ ኢንከሬጅ አድርጎኛል አበረታቶኛል ። በመጀመሪያዎቹ ጊዜያት። ኤሊያስን ካነሳን አይቀር፣ ኤሊያስ አለ፣ በሕይወት የሌለው እዮብ አለ፤ ሌሎችም አሁን ስማቸውን ያልጠቀስኳቸው በእናንተ ክበብ ውስጥ ያሉ የሙዚቃ ባለሙያዎች አሉ። እነዚህን የሙዚቃ ሙያተኞች ስናይ ፤ የዘመንሽን ሙዚቀኞች በ ሥ ራዎ ቼ በሚገባ ወክያለሁ፣ ገልጫቸዋለሁ ብለሽ ታስቢያለሽ ዘሪቱ፡ በረዥሙ ተንፍሳ እ እኔ በጣም ግለሰባዊ ነኝ መሰለኝ። ሳቅ የሆነን ወገን መወከሌ አይቀርም። ግን ከምንም በላይ እውነትን እና የራሴን ጉዞ እንደወከልኩ፤ በዚያ ውስጥ ደግሞ ብዙዎች የሚወዱህ ሰዎች በሆነ ያህል እንደተወከሉ የሚያስቡ ይመስለኛል። ስለዚህ እነርሱንም የወከልኩና ያሰማሁ ይመስለኛል። ለምንድን ነው እንደዚያ ያልኩት ፤ በወንጌላውያን አማኝ ሙዚቀኞች ዘንድ የጦፈ ክርክር ነበር። ሙዚቃና ሙዚቀኝነትን፣ዓለማዊነትንና መንፈሳዊነትን በተመለከተ። በኋላም የዮናስ ጎርፌ ቤት ያጣው ቤተኛ የተሰኘ መጽሐፍ ታትሞ ተነቧል። ይህ የሚያሳየን ከወንጌላዊያን አማኞች የተገኙ ሙዚቀኞች፣ በመንፈሳዊ ዓለም ውስጥ ያላቸውን ስፍራ ለማፅናት፣ እዚህ ጋር ነው ስፍራችን ማለትን ያየሁ ስለመሰለኝ ነው። በዚያ ወቅት ደግሞ አንቺ ሥ ራዎችሽን በዚህ መልክ ስታቀርቢ እነዚህን ወገኖች ወክላ ይሆን የሚል ጥያቄ አድሮብኝ ነው ዘሪቱ፡ ከረዥም ዝምታ እና ማሰብ በኋላ ብዬ አምናለሁ። ተወክለው ከሆነ እነርሱ ያውቃሉ ይመስለኛል። የአንድ መንፈሳዊ ሰው ሕይወት እኮ አይከፋፈልም። አንድ ሰው መንፈሳዊ ነኝ ካለ በማንኛውም ጊዜ በዚያ ማንነት ውስጥ ነው ሊሆን የሚገባው። በጨዋታም ጊዜ፣ በሥራም ጊዜ፣ በፀሎትም ጊዜ፣ በሁሉም ጊዜ በመንፈሳዊ ማንነት ውስጥ ነው መቆየት ያለበት። ያ መንፈሳዊ ማንነት ደግሞ የሆነ ኃይማኖታዊ መልክ አይደለም። መልካምነት፣ ፍቅር፣ ርህራሄ፣ ሰላም፣ በጎ የሆነ ነገር ሁሉ መንፈሳዊ ነው ብሎ መደምደም ባይሆንም፤ ምክንያቱም ማስመሰልም ስላለ። ግን ሥራዬ መንፈሳዊ ካልሆነ፣ ወይ ከመንፈሳዊነት የሚያጎለኝ ከሆነ፣ ከመንፈሳዊነት የሚጋጭ ከሆነ፣ ባላደርገው ነው የሚመረጠው። ስለዚህ እንደማይጋጭ እያመንኩ ነው እያደረኩት ያለሁት። ዘሪቱ ራሷን ከሙዚቃ ውጪ በምን በምን ትገልፃለች ዘሪቱ፡ ፋሽን ደስ ይለኛል። ስታይል መቀየር ያዝናናኛል። ልንዝናናም ደግሞ ይገባናል። ቁም ነገር የሆኑት ነገሮች እንዳሉ ሆነው፣ በምድር ላይ እስካለን ድረስ የሚያዝናኑን ነገሮች አሉ። ጉዳት የለውም። ስለዚህ በእርሱም ራሴን ኤክስፕረስ አደርጋለሁ እገልጻለሁ ። በተሰማኝ ጊዜ። ሙሉ በሙሉ በእዚያ ማንነት ውስጥ የምኖር ሰው አይደለሁም። ዝም ብዬ ስዘንጥ የምኖር ሰው አይደለሁም። ሳቅ ዘናጭ አይደለሁም። የሙሉ ጊዜ ዘናጭ ረዥም ሳቅ ልክ አሁን ስንገናኝ እንደለበስሽው ቀለል ያለ አለባበስ፣ ጅንስ ሱሪ ፣ በሸራ ጫማ በጃኬት ዘሪቱ፡ አዎ ብዙ መታየትም አልወድም። ግን አንዳንዴ ደግሞ ያኛውም ጎን አለኝ። ለወጥ ብሎ፣ ተጫውቶ እንደጨዋታ ነው የማየው። መለስ ብሎ ደግሞ ወደ ተረጋጋው የዘወትር መልኬ ሳቅ በእሱ እጫወታለሁ። ባለኝ በሚያስደስተኝ ሁሉ ራሴን ኤክስፕረስ አድርጌ ገልጬ ሰዎችን ፈገግ አድርጌ፣ አዝናንቼ፣ አካፍዬ ማለፍ ነው የምፈልገው። ትርፍ ጊዜሽን በምን ማሳለፍ ነው ደስ የሚልሽ ዘሪቱ፡ የሚያስደስተኝ ነገር ወይ ከሥራዬ ጋር የተያያዘ ነው ወይ ከቤተሰቤ ጋር የተያያዘ ነው። ስለዚህ ትርፍ ጊዜ ቢኖረኝም ያንኑ የሚያስደስተኝን ነገር አደርጋለሁ። ወይ አነባለሁ፣ ወይ አጠናለሁ፣ ወይ ከልጆቼ ጋር እሆናለሁ። ፊልም እመለከታለሁ። በሙዚቃ እዝናናለሁ። ትርፍ ጊዜዬም ሥራዬም ተመሳሳይ ነው። ይዘቱ ከቤተሰቤ ራቅ ያለ ነገር አይደለም። በአጠቃላይ ትርፍ ጊዜ ነው ያለኝ ማለት ነው። ሳቅ ድምጻዊት ዘሪቱ ከበደ ከሦስት ልጆቿ ጋር ለሁለተኛ አልበምሽ መዘግየት ምክንያት የሆነው እናት መሆንሽ ነው ዘሪቱ፡ አይደለም። በፍፁም ምንም ግንኙነት የለውም። እንዲሁ የሕይወት ጉዞ፣ ዝግጁ አለመሆን፣ ከራስ ማንነት መሠራት፣ መስተካከል፣ ከዚያ ያንን መፈለግ፤ ከዚያ ትክክለኛው ለጥበብ ምቹ የሆነ ኢነርጂ ኃይል ፣ ፓርትነርሺፕ አጋር አለመመቻቸት፣ ወይ ጊዜው አለመሆን፣ ያ ያ ነው። አብዛኛው ጊዜዬ በስራ ነው የሚያልፈው። ብዙ ሥራም እሠራለሁ። በፊልምም ብዙ ሠርቻለሁ። እናትነት በጣም ቢዚ ባተሌ አድርጎኝ አይደለም። እናትነት ጊዜ ቢወስድም ሙዚቃን ለመሥራት ይኼን ሁሉ ዓመት የሚያስቸግር አልነበረም። ምክንያቱ እርሱ አይደለም። ስንት ፊልሞች ላይ ተሳተፍሽ ዘሪቱ፡ ከ ቀሚስ የለበስኩለት በኋላ ይህ የራሷ ድርሰት ነው ፣ የቅድስት ይልማ ሥራ የሆኑት መባ እና ታዛ ላይ በትወና ተሳትፌያለሁ። ከዚያ አሁን በቅርቡ የወጣ ወጣት በ የሚል ፊልም አለ። አሁን ደግሞ በቅርቡ የሚወጣ ስዊትነስ ኢን ዘ ቤሊ የሚል የዘረሰናይ ብርሃኔ መሀሪ ፊልም አለ። እስካሁን እነዚህ ናቸው። ልክ እንደ ሙዚቃሽ በፊልሙም እኔ የምወክላት እንዲህ አይነት ገጸ ባህሪ መሆን አለባት ትያለሽ ዘሪቱ፡ አዎ። እንደዚያ ባይሆን መሳተፌ አስፈላጊ አይደለም። የምትመስለኝን፣ ልትወከል ይገባታል ብዬ የማምነውን፣ ብትታይ ይገባታል ብዬ የማምነውን ገፀ ባህሪ ወይም ላውቃት፣ መስያት ወይም ሆኛት፣ እርሷና አካባቢዋን ልወቅ ብዬ የመረጥኳትን ገፀ ባህሪ ወይንም ደግሞ ሊተላለፍ ይገባዋል የምለው መልእክት ካልሆነ በስተቀር ተሳትፎዬ ምንም ጥቅም የለውም። ስለዚህ እስካሁንም የተሠሩት ሁሉ እንደዚያ ናቸው። ከአሁን በኋላ ያንቺ ድርሰት የሆነ ፊልም እንጠብቅ ወይስ የሌሎች ሥ ራዎች ላይ ብቻ ነው የምትሳተፊው ዘሪቱ፡ አስባለሁ። ግን ያው በመጀመሪያ የፊልም ሙከራዬ በጣም ብዙ ነገር ውስጥ ስለተሳተፍኩ ደከመኝ ሳቅ ። ጥንካሬዬ በነበሩት ነገሮች በጣም ጠንካራ ነገር ባመጣም፤ ገና ያልተማርኳቸውና ያላወቅኳቸው ኤክስፒሪያንስ ልምድ የሚያስፈልጉኝ ነገሮች ነበሩ። ስለዚህ እነርሱን ለማግኘትና ለመለማመድ ስል ነው በተለያዩ ሰዎች ፊልም ውስጥ ተሳታፊ የሆንኩት። ጥሩ ልምድ እንዳለኝ አምናለሁ። ሀሳቦች አሉኝ። እንደውም ከዚህ በኋላ የማስበው የራሴን አይዲያ ሀሳብ ፣ የራሴን መልዕክት ብሠራ ነው። ግን መልካም ሆኖ የሚያስደስትና የሚጠቅም ሥራ ከመጣ የሌሎችን ሰዎችም እሠራለሁ። ዘሪቱ የተሰኘ አልበምሽ እንደወጣ ከነ ሄኖክ መሀሪ ጋር ትልልቅ የሙዚቃ ድግሶች አዘጋጃችሁ ፤ ጉዞ ዘሪቱ የተሰኘ። እንደዚህ አይነት ቋሚ የሆነ የሙዚቃ ኮንሰርት የማዘጋጀት ሀሳብ የለም ዘሪቱ፡ አለ። ከአዲስ አበባ ወጥቶ በክልል ከተሞች ሥራዎችን ማቅረብ በጣም ነው የሚያስደስተኝ። ናፍቆት ስላለ ምላሹ በጣም አርኪ ነው። በመጀመሪያም ያደረግነው እርሱን ነው። መቼም የማይረሳን ጊዜና ታሪካዊ ልምድ ነው የሆነው። ከዚህ በኋላም ልናደርግ እናስባለን። ግን እንደሱ አይነቱን ነገር በሰፊው ለማድረግ ከአዲስ አልበም በኋላ ቢሆን የተሻለ እንደሚሆን በማመን ሳቅ ነው ያላደረግነው። ግን ባለንበት አካባቢ፣ በተመቻቸ ጊዜ ሁሉ እንጫወታለን። አዲስ አልበም ሽ መቼ ይወጣል ዘሪቱ፡ ፀልይልኝ። ረዥም ሳቅ እየተሰራ ነው ባለቀ ጊዜ አልበምሽ ወጥቶ አንቺ ሥ ራዎችሽን በምታቀርቢበት ወቅት ያምቡሌ በጣም ዝነኛ ነበር። ዝግጅትሽን በምታቀርቢበት ስፍራ ላይ በተፈጠረ ጉዳይ ስምሽ በተደጋጋሚ ተብጠልጥሎ ነበር። ያኔ የተፈጠረው ምን ነበር ዘሪቱ፡ ምንድነው የሆነው ከተወራው የተለየ ነገር የሆነ አይመስለኝም። አሁን በደንብ የኢትዮጵያ ሙዚቃ ውስጥ ዶሚኔት የተቆጣጠረው ያደረገው ሳውንድ ድምፅ ሲመጣ ያምቡሌ ቀዳሚው ሥራ ነበረ። በሙዚቀኞች አካባቢ እንደ ጨዋታ እያደረግን ብዙ እናነሳው ነበረ። እኔ ደግሞ በዚያን ሰዓት ልሠራበት እየተዘጋጀሁ በነበረበት የፕላቲኒየም ክለብ፣ እየተዘጋጀሁበት የነበረው ሥራ ያምቡሌ ን የማይመስል ወይንም ከኔም ሥራ ወጣ ያለ፣ ከ ፖፑላር ም ሥራ ወጣ ያለ፣ እንደ ጥበብ ሥራ ብቻ ልታጣጥመው የምትችል፣ ብዙ የተደከመበት፣ በጣም የተዋበ፣ አሁን ባለንበት ወቅት የተሻለ ተቀባይነት ያገኝ ነበር። እርሱን የሚመስሉ ብዙ ነገሮች አሉ። ሰው ኢንጆይ ያደረጋቸው። ያኔ ግን እሱ ቅንጦትና ቅብጠት ነበር የሚመስለው እንጂ በፈረንጅ ናይት ክለብ ጉራግኛ ሲደለቅ በፒያኖ የታጀበ ማለት ሽ ነው ዘሪቱ፡ በፒያኖ ብቻ አይደለም። ፒያኖ፣ አፕ ራይት ቤዝም አለ። ፒያኖም አፕራይት ቤዝም ከሆነ ከዓመታት በኋላ ነው መድረክ ላይ የወጡት። በኢትዮጵያ ፖፑላር ሙዚቃ ውስጥ ብዙ ጊዜ የማንሰማቸው መሣሪያዎች፣ ለስለስ ያለ፣ ሴትአፑ ም ምኑም ወጣ ያለ ነበር። ያሰብነው ነገር በጣም እንደሚያምር ስላወቅን ምላሹን ለመቀበል ከበደን መሰለኝ። ያው በልጅነትና ባለማወቅ ውስጥ የተመልካቹ ጥፋት እንዳልሆነ ለመረዳት አልቻልኩም ነበር ። በእርግጥ በትክክል ፕሮሞት እንዳልተደረገ እንዳልተዋወቀ የተረዳሁት ቆይቼ ነው። ስለዚህ የመጡት ሰዎች ጥፋት አይደለም። በወቅቱ እንዴት ይሄ አይገባቸውም በሚል ነው እንጂ፤ ቢያውቁና ቢጠብቁ የሚፈልጉት ሰዎች ይመጡ ነበር። እና በአንድ መንገድ ለጥበብ የተደረገ ትግል ስለሆነ ያቺን ልጅ እኮራባታለሁ። በሌላ ወገን ደግሞ ያለመብሰልና ያለማስተዋል ውጤት ነው። ለዛ ነው እንግዲህ ይሄ ካልገባችሁ እንግዲህ ያው ያምቡሌ ይሁንላችሁ ብላ ያለፈችው። ያቺኛዋ ስትይኝ አሁን ያቺ የድሮዋ ዘሪቱ የለችም እያልሽኝ ነው ዘሪቱ፡ መስዋዕትነት ነው እና ያቺኛዋን ዘሪቱም ነኝ። ግን አሁን እንደዛ የማደርግ አይመስለኝም። ማንን መቆጣት እንዳለብኝ የማውቅ ይመስለኛል። ሰሞኑን እያነበብሽ ያለሽው መጽሐፍ አለ ካለ ምንድን ነው ዘሪቱ፡ ኦ መጽሐፍ ነው፤ ይገርምሀል አንድ ጓደኛዬ ይህንን መጽሐፍ ሰጠኝና በቀኟ በኩል ካስቀመጠችው ቦርሳዋን ከፍታ ከመጽሐፍ ቅዱስና ማስታወሻ ደብተሯ ጋር አብሮ ተቀምጦ የነበረ መጽሐፍ በማውጣት ዘ ግሬተስት ፖወር ኢን ዘ ወርልድ ይላል። የካትሪን ኩልማን መጽሐፍ ነው። እርሱን ነው እያነበበብኩ ያለሁት። አሁን እየተነበበ ያለው ይህ ነው። ሳቅ ሰሞኑን የምታደምጪውስ ሙዚቃ ምንድን ነው ዘሪቱ፡ ሰሞኑን ምንድን ነው የማዳምጠው እንደማሰብ አለችና ብዙ መዝሙር እየሰማሁ ነው። ታሻ ኮምስ የምትባል ዘማሪ አለች። እርሷን በጣም እየሰማሁ ነው ። ኢሊቬሸን ወርሺፕ እነርሱንም በጣም እሰማለሁ። አሁን የዘሩባቤል አልበም ወጥቷል። እርሱንም እየሰማሁ ነው። ሳቅ ለአ ንቺ አዲስ ዓመት የሚሰጠው ስሜት ምንድን ነው ዘሪቱ፡ አዲስ ዓመት ደስ ይለኛል። ኢንከሬጅመንት ማበረታታት ፣ ተስፋ፣ መለስ ብሎ ሪፍሌክት አድርጎ መለስ ብሎ መቃኘት ፣ ያለፈውን ዓመት ጉዞ፣ ፕሮግረስ ለውጥ ያው ሁሉም ነገር በዓመት ባይከፋፈልም፤ የሕይወት ጉዞን እንዲሁ ለማየት ግን ደስ ይላል። በአዲስ ተስፋ በደስታ የምቀበለው ጊዜ ነው። አንዳንዴ በዓመት ውስጥ ብዙ አዲስ ዓመቶች እናሳልፋለን። ሳቅ ሁሌ ዓመት አንጠብቅም። ግን ኢንጆይ አደርገዋለሁ። ለአድናቂዎችሽ የአዲስ አመት መልዕክት አለሽ ዘሪቱ፡ ሰላም ይሁኑ ሰላም ይሁንላቸው ይብዛላቸው ከራሳቸው ጋር መሆን፣ ለሰው መሆን ይሁንላቸው ደስታ ይብዛላቸው ፍቅር ይብዛላቸው የምትወጂው ጥቅስ የቱ ነው ዘሪቱ፡ የምወደው ጥቅስ የቱ ነው አሰብ አድርጋ በሕይወቴ ውስጥ በጣም ብዙ ጥቅስ ከማስተናገዴ የተነሳ ረዥም ሳቅ አሁን አልከሰት አለኝ። ከዚህ ዜና በተጨማሪ
ነገሩ የተለመደ የሙዚቃ ድግስ ነው። ልዩ የሚያደርገው በማጀቢያ ሙዚቃ ሺህ ሰዎች ሊጎራረሱ መሆኑ ነው።
ኩነቱን ማሰብ በራሱ ያስቃል። ሺህ እንጀራን የጠቀለሉ መዳፎች ወደ ሺህ የተከፈቱ አፎች ሲምዘገዘጉ ማሰብ በራሱ ትን ያስብላል የፊታችን ቅዳሜ ግንቦት በጊዮን ሆቴል ነው ይህ እንዲሆን ቀጠሮ የተያዘው። አሰናጆቹ ክስተቱን ከአንድ ቀን የዘለለ ትርጉም እንዲኖረው ጽኑ ፍላጎት አላቸው። ለምሳሌ ቋሚ የጉርሻ ቀን መሰየም ይፈልጋሉ። በኢትዮጰያ የማይቋረጥ ዓመታዊ የመጎራረስ ፌስቲቫል እንዲኖር ያልማሉ። ከፍ ሲልም ጉርሻን በማይዳሰስ ቅርስነት የማስመዝገብ የረዥም ጊዜ ትልምን ሰንቀዋል። ጉርሻ ግን አይዳሰስም እንዴ ብሎ መጠየቅ የተሰነዘረ ጉርሻን ያስከለክል ይሆን አዘጋጆቹ የጉርሻ ባሕል በኢትዮጵያ አራት መቶ ዓመታትን ያስቆጠረ ነው ሲሉም ይከራከራሉ። አንድ የሚያደርገንን ፌስቲቫል ፍለጋ ኢትዮጵያ ውስጥ ኮስተር ብሎ የሚቆጥር ካለ እያንዳንዱ ቀን በዓል ሆኖ ሊያገኘው ይችላል። ይህ በቋንቋና በባሕል ሀብታም የሆነ አገር ሁሉ ባህሪ ነው። እንደ ጉርሻ ግን የሚያግባባን የለም ይላል ቅዱስ። ጉርሻ እኮ አንዱ ለሌላው የማጉረስ ተግባር ብቻ አይደለም፤ በተጠቀለለው እንጀራ ውስጥ ፍቅር አለ፣ መተሳሰብ አለ፣ አክብሮት አለ ። ይላል ከአሰናጆቹ ፊታውራሪው ቅዱስ አብረሃም። ሐሳቡ እንዴት እንደተጠነሰሰ ሲያብራራም የሌሎች አገሮችን ዕውቅ ፌስቲቫሎች ከመመልከት የመጣ መንፈሳዊ ቅናት የወለደው ነው ይላል። ሕንዶች የቀለም፣ ስፔኖች የቲማቲም፣ ጀርመኖች የቢራ ፌስቲቫል አላቸው። እኛ ግን አውዳመት እንጂ የሚያምነሸንሽ አንድም የጋራ ፌስቲቫል የለንም። ሐሳቡን ያመነጩት የሥራ አጋሩ አቶ ዘላለም እናውጋው መሆናቸውን ጨምሮ ያስገነዝብና እንዴት አንድ ቀላል የጉርሻ ተግባር አገርን ወደ አንድነት መንፈስ ሊመራ እንደሚችል ማስረዳቱን ይቀጥላል። ጉርሻ ዘር፣ ቀለም፣ ሃይማኖት አልያም የገቢ መጠንን አይጠይቅም። ሁላችንንም የሚያግባባን ባሕል ነው፤ ለዚህ ነው ልዩ የሚያደርገው። ደግሞም የኢትዮጵያዊያንና የኤርትራዊያን አንጡራ ባህል እንጂ የማንም አይደለም ይላሉ ቅዱስ። ለዚህ የጉርሻ አገራዊ ፌሽታ ባሕል ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ድጋፍ ማድረጋቸውን አሰናጆቹ ለቢቢሲ ተናግረዋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፐብሊክ ዲፕሎማሲ እንግሊዝ ለሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ደብዳቤ በመጻፍ የጊነስ የድንቃ ድንቅ መዝገብ ዋና ጽሕፈት ቤት ጉዳዩን እንዲከታተለው ማድረጉን ቅዱስ አብራርቷል። ጊነስ እና ጉርሻ ጊነስ እንዲህ ዓይነቶቹን ኩነቶች በማኅደሩ ለማስፈር ከ ሺህ እስከ ሺህ ፓውንድ ይጠይቃል። እነ ዘላለም ይህን ሂደት በማጠናቀቅ ላይ ነበሩ። ሁለት የጊነስ የድንቃ ድንቅ መዝገብ ቢሮ ተወካዮች ይህንን የ ሺህ ሰዎች ጉርሻ ለመታዘብ በቀጣይ ቀናት አዲስ አበባ እንደሚገቡም ይጠበቅ ነበር። ሆኖም በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ምክንያት ጉዟቸው እክል ሳይገጥመው አልቀረም። የድጋፍ ደብዳቤዎችን በመላክ ልናሳምናቸው ሞክረን ነበር ይላል ዘላለም። ሆኖም መልካም ፍቃዳቸው አልሆነም። ይህ ማለት ግን ጊነስ ኩነቱን አይመዘግበውም ማለት እንዳልሆነ ጨምሮ ያብራራል። አማራጭ አሠራር አለ። ይኸውም ገለልተኛ ተቋም ቀጥሮ፣ ለ ጥንዶች በቡድን አንድ አንድ ታዛቢ በመመደብ፣ ክስተቱን ያለማቋረጥ በቪዲዮ ቀርጾ በጊነስ መዝገብ ይፋዊ ድረ ገጽ በማኖር ለዕውቅና ሰርተፍኬት ማመልከት ይቻላል። ይህን ካሟላን ዕውቅናው እንደሚሰጡን ቃል ገብተውልናል ይላል ዘላለም። የጉርሻ ታዛቢዎች ነገር እንግዳ ነው። ሰዎች ሲጎራረሱ ከፊት ለፊት ቆመው እያንዳንዷን ጉርሻ ይቆጣጠራሉ። ልክ የተጫዋቾችን እንቅስቃሴ እንደሚቆጣጠር የእግር ኳስ አራጋቢ ዳኛ፤ ከወዳጅ የተቀባበለው ጉርሻ የተቃራኒ ቡድኑን የአፍ መስመር ማለፍ አለማለፏን ይከታተላሉ። ሂደቱ በራሱ የሚያዝናና ይመስላል። የጉርሻ ክብረወሰን በማን ነው የተያዘው ክብረ ወሰኑ ጃፓኖች ጋር ነው ያለው። ጥንዶች ተጎራርሰው የዓለም ክብረ ወሰንን ይዘውታል። እኛ ይህን ክብረወሰን በዕለቱ በቀላሉ እንሰብረዋለን ይላል ሌላኛው የኩነቱ አሰናጅ ቅዱስ አብረሃም በሙሉ መተማመን። እርሱ ራሱ ክብረ ወሰኑ በጃፓኖች ስለመያዙ ለመጀመርያ ጊዜ የሰማው ግን ከጊነስ ሰዎች ነው። ይሄ የኛና የኤርትራዊያን ባሕል ነው። እንዴት ጃፓኖች ጋ እንደሄደ አልገባኝም። በ ስቲክ ይሁን በእጅ እንዴት እንደተጎራረሱ ራሱ አላውቅም፤ ጊነሶች ናቸው የነገሩኝ ይላል ቅዱስ፤ ግርምት ከወለደው ፈገግታ ጋር። የጾም ነው የፍስክ ሙዚቃውን፣ ምግቡን፣ ቀኑን፣ ሰዓቱን በጥንቃቄ ስለመምረጣቸው አዘጋጆቹ ደጋግመው ያስገነዝባሉ። ለምሳሌ በዕለቱ ምንም ዓይነት መንፈሳዊ ጾም እንደማይኖር ማረጋገጣቸውን ይጠቅሳሉ። የረመዳን ጾም ከመግባቱ ቀደም ብሎ ፌስቲቫሉን ያደረገውን ለዚህ ነው ይላል ቅዱስ። የሸራተን እህት ኩባንያ የሆነው አዲስ ኬተሪንግ ለጉርሻ የሚቀርበውን ምግብ በመከሸን በአጋርነት እንደተሰለፈና ጥብስ፣ ምንቸት፣ ጥብስ ዝልዝል ከምግብ መዘርዝሩ ከፊት የሚሰለፉ የምግብ ዓይነቶች እንደሚሆኑ ተነግሯል። በፊሽካ ነው በደወል ተጎራረሱ የሚለው ይፋ መልዕክት የሚተላለፈው እንዴት ነው ቅዱስ እንደሚለው መድረኩ ላይ የሚሰቀል ለዚሁ ተብሎ የተዘጋጀ ግዙፍ ሰዓት አለ። ይህ የጉርሻ ሰዓት ልክ ፡ ከመሙላቱ በፊት ከላይ ወደ ታች መቁጠር ይጀምራል። ሲል አምስት ሺህ ክንዶች ወደ ተከፈቱ አፎች ይወረወራሉ። ምግቡን ማወራረጃ የነዘሪቱ፣ የነ አቤል ሙሉጌታ፣ የነኃይሌ ሩትስ ሙዚቃ ተዘጋጅቷል። ተቃዋሚዎችና መንግሥት ቢጎራረሱስ ጉርሻ የፍቅር፣ የእርቅ፣ የአክብሮት፣ የህሊና ትስስርና የሞራል ልዕልናን በእንጀራ ጠቅልሎ የያዘ ስለመሆኑ ደጋግመው የሚናገሩት የዝግጅቱ አስተባባሪዎች በዕለቱ የመንግሥት ባለሥልጣናትና ተቃዋሚዎች ተገኝተው ቢጎራረሱ፣ ቢዝናኑ፣ ፍቅር ቢለዋወጡ ደስታንን አንችለውም ይላሉ። ለመሆኑ ጉርሻ የማይዳሰስ ቅርስ መሆን ይችላል ትን የሚያስብል ጥያቄ ነው። ተያያዥ ርዕሶች
በስራ በመወጠር አልያም በሌላ ምክንያት ጊዜ ያጡ ግለሰቦችን ታሳቢ በማድረግ የተጀመረ አገልግሎት ነው።
ለቅሶ ለመድረስ፣ ዘመድ ለመጠየቅ ወይም ለሌላ ጉዳይም ምግብ የሚያሰናዱ ተቋሞችን መቅጠር እየተለመደ መጥቷል። ለምግብ ዝግጅት ብቻ ሳይሆን ለመስተንግዶም ተቋም መቅጠር የሚሹ ግለሰቦች መብዛታቸው ደግሞ ነጋዴዎችን ወደ ዘርፉ እየሳበ ነው። አጭር የምስል መግለጫ በቀን ከ እስከ ትእዛዝ ይቀበላሉ በዘርፉ አዋጭነት ከተሳቡ አንዱ ብስራት በላይነህ ነው። የኢኮኖሚክስ ምሩቅ ነው። የመኪና ኪራይ፣ የኤሌክትሮኒክስ ሽያጭ፣ የቴሌቭዥንና ሬድዮ ማስታወቂያ ይሰራ ነበር። አሁን ግን አትራፊ ወዳለው የምግብ ዝግጅትና አቅርቦት ገብቶ ቤላ ዶናን አቋቁሟል። መነሻ ያደረገው ምሳ ቋጥሮ መሸጥን ነበር። ቤታቸው ምግብ ለማዘጋጀት ጊዜ ወይም ፍላጎቱ ለሌላቸው ሰዎች ቢሯቸው ድረስ ምሳ ቋጥሮ መላክ ከጀመረ ወራት ተቆጥረዋል። ምሳ ሰአት ላይ፤ ምግብ በምሳ እቃ እንዲላክላቸው የሚፈልጉ ሰራተኞች የሚጠበቅባቸው ስልከ መደወል ብቻ ነው። የሚፈልጉትን የምግብ አይነት ያዛሉ። ከዛም ምሳ ሰአት ላይ ትኩስ ምግብ ይወሰድላቸዋል። ለደንበኞቻችን ትኩስ ምግብ፣ በተመጣጣኝ ዋጋ፣ ያሉበት ቦታ ድረስ ለማቅረብ አስበን ነው ስራውን የጀመርነው ይላል። ንግዱ እየተጧጧፈ ሲመጣ ምግብ በአገልግል ወደ ማድረስ ተሸጋገረ። ምግቡ የሚዘጋጀው አዲሱ ገበያ አካባቢ ነው። በምሳ እቃ ሀያ ሁለት፣ ቦሌ፣ መርካቶ፣ አውቶብስ ተራ፣ ጳውሎስ ሆስፒታል አካባቢም ይደርሳል። በአገልግል ሲሆን ግን የሰፈሮች ድንበር አይገድበውም። ሽሮም፣ ዶሮም አለን ብስራት ምግብ በአገልግል ወደማቅረቡ ስራ የገባው በምግብ ዝግጅት ከሰለጠነች ዘመዱ ጋር ነበር። የሚኖሩበት ቤት ውስጥ ምግብ በማዘጋጀት ከጀመሩ በኃላ ስራው ሲሰፋ ተጨማሪ ምግብ አብሳዮች ቀጠሩ። አጭር የምስል መግለጫ የጸምና የፍስክ ምግብ ያቀርባሉ ምግብ መሰናዶውን በአንድ በኩል ሲያካሂዱ፤ ተረክበው በየአስፈላጊው ቦታ የሚያደርሱ ተቀጣሪዎችም አሏቸው። ስለ አገልግሎታቸው የሚያስተዋውቁት በፌስቡክ ሲሆን፤ በማህበራዊ ሚዲያ ያልደረሷቸውን ደግሞ በያሉበት በመሄድ በራሪ ወረቀት ይበትናሉ። ንግዱ በዋነኛነት የሚካሄደው በቢሮዎችና ሱቆች ስለሆነ በነዚህ አካባቢዎች ራሳቸውን ከማስተዋወቅ አይቦዝኑም። በቀን ከ እስከ ትእዛዝ ይቀበላሉ። የምግብ ዝርዝሩ የጾምና የፍስክ፤ የሀገር ውስጥና የባህር ማዶ በሚል ተከፍሏል። ክትፎ፣ ጥብስ ፍርፍር፣ መኮሮኒ፣ ሩዝ ዝርዝሩ ሰፊ ነው። ሽሮና ፓስታን የመሰሉ ምግቦች በምሳ እቃ ከ እስከ ብር ይሸጣሉ። ክትፎ ደግሞ በ ብር። በአገልግል ሲሆን፤ ሰባት የጾም ምግቦች ተካተው ብር ያስከፍላል። ለአምስት አይነት የፍስክ ምግብ ብር ይከፈላል። ወደድ የሚለው በብዙዎች የሚወደደው ዶሮ ነው። ሙሉ ዶሮ ወጥ፣ ከአይብና ከ እንቁላል ጋር ብር ነው። ሰዎች የቤት የቤት የሚል ምግብ ነው ይሉናል የሚለው ብስራት በተለይም መካከለኛ ገቢ ያላቸውን ታሳቢ ማድረጋቸውን ይገልጻል። ወደ አስቤዛ ሸመታ መግባት እንፈልጋለን ዘመነኛ የሚባለው ኑሮ ቤት ውስጥ ይሰሩ የነበሩ ምግቦችን ወደ ተቋም እያዘዋወረ ይመስላል። ብስራትም የማህበረሰቡን ፍላጎት ተንተርሶ የቅመማ ቅመም ዝግጅትና የአስቤዛ ሸመታ ውስጥም ለመግባት አስቧል። አጭር የምስል መግለጫ ምግብ በምሳ እቃ ያደርሳሉ ግባችን የሰውን ህይወት ማቅለል ነው ይላል። ስራውን ሲጀምሩ ብዙ ሰው እውን በአገልግል ያመጣሉ ብሎ ይጠራጠር ነበር። አሁን ግን ተአማኒነት እያገኙ እንደሆነ ያምናል። በብዙ ቦታዎች አገልግል አልተተወም፤ ምናልባት የዘነጉት ወጣቶች ካሉ እያስታወስናቸው እንደሆነ ይሰማኛል ይላል። በጊዜ ሂደት የአስቤዛ ሸመታን እንደሚያስለምዱም ያምናል። ተያያዥ ርዕሶች
ለብቻ ልጆችን ማሳደግ፡ የኢትዮጵያውያን ላጤ እናቶች ምርጫና ተግዳሮት
ጁላይ ማጋሪያ ምረጥ ሴቶች በተለያዩ ምክንያቶች ልጆቻቸውን ብቻቸውን የሚያሳድጉ ላጤ እናት ይሆናሉ። ከአጋራቸው ጋር በሞት አሊያም በፍቺ ሲለያዩ፣ በተፈፀመባቸው ጥቃት ሳቢያ የልጅ እናት ለመሆን ሲገደዱ፤ እንዲሁም የጀመሩት ግንኙነት እንዳሰቡት አልሰምር ሲላቸው ልጃቸውን ልጆቻቸውን ብቻቸውን የማሳደግ ውሳኔ ላይ ከሚደርሱባቸው ምክንያቶች መካከል ይጠቀሳሉ። ነገር ግን ፈልገውና አቅደው፤ ልጅ ብቻ እንዲኖራቸው በማለም ላጤ እናት የሚሆኑ ሴቶችም አሉ። እናት አልባዎቹ መንደሮች በተለያዩ አገራት የተሰሩ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት በተለያየ ምክንያት ልጃቸውን ብቻቸውን የሚያሳድጉ እናቶች ቁጥር እየጨመረ መጥቷል። በአፍሪካ በተለይ በኬንያና በደቡብ አፍሪካ ላጤ እናት የመሆኑ ልማድ እንግዳ አይደለም። ምንም እንኳን የተሰሩ ጥናቶች ባለመኖራቸው ቁጥራቸውና የጉዳዩ ስፋት ምን ያህል እንደሆነ ለማወቅ ባይቻልም በኢትዮጵያ በተለይ በከተሞች አካባቢ ላጤ እናትነት አንዱ የሕይወት ዘይቤ መሆኑ ይነገራል። ሴቶች አስበውና አቅደው ለምን ላጤ እናት ይሆናሉ በሕይወቴ ያሰመርኩት ቀይ መስመር ነበር፤ እርሱን ማለፍ ስለማልችል ላጤ እናት ሆኛለሁ የምትለው የአዲስ አበባ ነዋሪ ናት። ስሟን ያልጠቀስናት የይህች እናት ለትዳር ግን ክብር እንዳላት አልሸሸገችም። በሕይወቷ የምታስበውና የምታልመው ስላልሆነ የግድ በትዳር መታሰር የለብኝም የሚል አቋም ላይ እንደደረሰች ትናገራለች። ይሁን እንጂ ላጤ እናት መሆን በርካታ ተግዳሮቶች እንዳሉበት ታነሳለች። እያንዳንዷ ሴት በሰውነቷ ላይ እንዲሁም በምትመሰርተው ቤተሰብ ላይ ውሳኔዎችን ትወስናለች፤ ውሳኔዋም እንደምትኖረው ሕይወት የተለያየ ነው የሚሆነው የምትለው ደግሞ የሴቶች መብት ተሟጋቿ አክሊል ሰለሞን ናት። ይሁን እንጂ ሴቶች ፈልገውና አቅደው ላጤ እናት የሚሆኑባቸውን ምክንያቶችንም ትጠቅሳለች። በማህበረሰቡ የሴት ልጅ ሕይወት በጊዜ የተገደበ እንደሆነና እስከተወሰነ ዕድሜያቸው ድረስ ማግባትና መውለድ ካልቻሉ ሕይወታቸው እንደተመሳቀለ ተደርጎ መወሰዱ ለእንዲህ ዓይነት ውሳኔ ከሚገፏቸው ምክንያቶች አንዱ እንደሆነ ትናገራለች ። አክሊል እንደምትለው በቀደመው ጊዜ አንዲት ሴት ሳታገባ ብትወልድ ለልጁ ዲቃላ የሚል ስያሜ በመስጠት እናትየዋ ትወገዝ ነበር። አሁን ላይ ግን ይህ ልማድ በትንሹም ቢሆን እየቀረ በመሆኑ ሴቶች እንዲህ ዓይነት ውሳኔ እንዲያሳልፉ አደፋፍሯቸዋል። ከዚህ ቀደም ሴቶች ሥራ በማይሰሩበትና የኢኮኖሚ ጥገኛ በሆኑበት ጊዜ ልጅ ወልደው ለብቻቸው ማሳደግ የማይታሰብ ነበር የምትለው አክሊል የሴቶች የኢኮኖሚ አቅም ማደግም ሌላኛው የላጤ እናትነት ምክንያት ነው ትላለች። እንደ የመብት ተሟጋቿ ከሆነ አንዲት ሴት በሕይወት ያየችው የትዳር ሕይወት እኩልነት የሌለበት፣ ሴቷ ጥገኛ የሆነችበት፣ ጥቃት የሚፈፀምበት፣ የኃይል ሚዛኑ እኩል ያልሆነበት፣ ሁኔታዎች በሙሉ ለሴት የማይመቹ ከነበሩ፤ ይህን ባለመፈለግ ላጤ እናት ልትሆን ትችላለች። ቢሆንም ግን እኩልነትን እያዩ ያደጉትም ሌሎች ምክንያቶች ወደ ውሳኔው ሊያንደረድሯቸው ይችላል። በተለያየ መልኩ የሴቶች አቅም እየጎለበተ ቢመጣም ሴቶች አቅማቸውንና የትዳር ሕይወታቸውን ማጣጣም ተስኗቸዋል የሚሉ እንዳሉ ያነሳንላት አክሊል የሴቶች አቅም እየጎለበተ በመጣ ቁጥር ኃላፊነት እየተደራረበባቸው ነው የመጣው፤ የቤቱን ሳንቀንስ ነው የውጪውን የጨመርንባቸው ስትል ትሞግታለች። ማጣጣም ተስኗቸዋል፤ አልተሳናቸውም ለማለት መጀመሪያ ያለባቸው ጫና ሊቀርላቸው ይገባል ትላለች። በተጨማሪም ላጤ እናት መሆንም ይህንን ጫና አያስቀረውም ብላለች። ልጁን ጡት ያጠባው አባት በአሃ የሥነ ልቦና አገልግሎት አማካሪ የሆኑት አቶ ሞገስ ገ ማሪያም በበኩላቸው ይህ ሁኔታ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተለይ በከተሞች አካባቢ የሚታይ ልማድ ሆኗል ይላሉ። የምክር አገልግሎት ፈልገው ወደ እርሳቸው የሚመጡ ላጤ እናቶች መኖራቸውንም ይገልፃሉ። ባለሙያው እንደሚሉት ጉዳዩ ከሥልጣኔ ጋር ተያይዞ የመጣ ነው። የኢኮኖሚና በራስ የመተማመን አቅም ሲያድግ የባልና የሚስት ግንኙነት ወደ ጎን ተትቶ ግንኙነቱ ኢኮኖሚ ላይ ብቻ የተመሠረተ ሊሆን ይችላል። በዚህም ምክንያት ሌሎች ማህበራዊ፣ አካላዊ፣ መንፈሳዊ እሴት ላይ የተመሰረተ ግንኙነት እንደማያስፈልግ አሊያም እንደ ሁለተኛ ደረጃ ተወስዶ ሴቶች ላጤ እናትነትን በፍላጎት ይመርጣሉ። ለንግግራቸው እኔ በኢኮኖሚ ጥሩ ደረጃ ስለደረስኩኝ፤ ከመጀመሪያውም ጀምሮ የወሰንኩት ሳላገባ ልጅ ለመውለድ ነው ያለቻቸውን ደንበኛቸውን በምሳሌነት ያጣቅሳሉ። እንዲህ ዓይነት ሃሳቦች የባልን የትዳር አጋርን ሚናና ትርጉም ከማዛባት ጋር የተያያዘም ነው ይላሉ አቶ ሞገስ። ባለሙያው እንደሚያስረዱት ላጤ እናትነትን ከኢኮኖሚ ጋር ብቻ ማያያዝ አይቻልም። ጉዳዩ ከራስ ስሜትና አስተሳሰብ ጋር እንዲሁም ካለፈ ታሪክ ጋር የሚያያዝም ነው። በመሆኑም ተፅዕኖውን ውስጣዊና ውጫዊ በማለት ይለዩታል። ውስጣዊ ተፅዕኖ ለአንድ ውሳኔ ትልቁን ድርሻ የሚይዘው የውስጥ ሁኔታ ነው ይላሉ የሥነ ልቦና ባለሙያው አቶ ሞገስ። ይህ የውስጥ ሁኔታ የውጫዊ ተፅዕኖ ነፀብራቅም ይሆናል። ለምሳሌ የውስጥ ፍላጎት፣ አመለካከት፣ ቤተሰብ፣ ጎረቤት ወይም አካባባቢ የሚያሳድረው ተፅዕኖ የውስጥ ውሳኔ ላይ ያደርሳል። ለራሳችን ያለን የጠነከረ አስተሳሰብና ለራስ የምንሰጠው ግምት ከመጠን ያለፈ ሲሆን ነገሮችን ሁሉ እኔ ማድረግ እችላለሁ፤ እኔ ማድረግ የምችል ከሆነ ሌላ አያስፈልገኝም የሚል ስሜት ይመጣል። በመሆኑም ይህንን ሚዛናዊ ማድረግ ካልተቻለ እዚህ ውሳኔ ላይ በቀላሉ ይደረሳል ይላሉ። ውጫዊ ተፅዕኖ እንደ አቶ ሞገስ ከሆነ ፆታን መሠረት ያደረጉ የህብረተሰብ አመለካከትም ለላጤ እናትነት ከፍተኛ ተፅዕኖ ያሳድራሉ። የሚፈጸሙ ጥቃቶች፣ የሚደርስባቸው ጫና፣ ሚዛናዊ ያልሆነ ሚና፣ የወንዶች የበላይነትን በመጥላትና በመፍራት፣ አካባቢያችን ያሉ ወይም በሚዲያ የምንሰማቸውና የምናያቸው አርአያዎች በሚፈጥሩት ተፅዕኖ ሴቶች እዚህ ውሳኔ ላይ እንዲደርሱ ያደርጋቸዋል። በሌላ በኩል ማህበረሰቡ በጉዳዩ ላይ ያለው አቋም ጠንካራ ካልሆነ ሴቶች ውስጣቸው የሚጠይቃቸውን ለማድረግ ዕድሉን ያገኛሉ። የራስ ማንነት እያሸነፈ ሲመጣ፤ አይሆንም የምንላቸው ነገሮች እየበዙ ይመጣሉ። ፍላጎታችንን ማስቀደም ይቀናናል። ስለዚህም ላጤ እናትነት የማህበረሰቡ እሴት እንደተሸረሸረ አንዱ ማሳያ ሊሆን እንደሚችልም ያክላሉ። በላጤ እናቶች ላይ የሚደርስ ጫና ያነጋገርናት እናት እንደምትለው ልጆችን ለብቻ ማሳደግ ከፍተኛ የሆነ የኢኮኖሚና የሃሳብ ጫና አለው። ከማህበረሰቡ፣ ከቅርብ ቤተሰብ እንዲሁም ከልጆች የሚደርሰው ጫናም ቀላል አይደለም። ልጆቸ ራስ ምታት እንኳን ሲያማቸው የማካፍለው ሰው አለመኖሩ በጣም ከባድ እንደሆነ ተመልክቸዋለሁ፤ ግን የራሴ መርህ ስላለና እርሱን መታገስና እንደ እናቶቻችን መቻል ስለማልችል ውሳኔውን ወስኛለሁ ትላለች። ይህች እናት አዘውትረው ከሚጠቀሱት ጫናዎች በዘለለ የወሲብ ሕይወትን ማጣትም ላጤ እናትነትን ይፈትናል ትላለች። ምንም እንኳን እያንዳንዱ ሰው የየራሱ ወሲባዊ ሕይወት ቢኖረውም እርሷ ግን ከሕይወት አጋር ውጪ ወሲብ መፈፀም እንደማትፈልግ ትናገራለች። የመብት ተሟጋቿ አክሊል እንደምትለው ውሳኔው የሚያሳፍር ድርጊት ነው ተብሎ በሚቆጠርበት ማህበረሰብ ውስጥ በፍላጎት ላጤ እናት መሆን ማህበራዊ ጫናው ከፍተኛ ነው። እነዚህን እናቶች የሚያግዝ አሠራር ከሌለ በስተቀር ሁሉም ነገር በአንድ ሰው ትከሻ ላይ ብቻ ስለሚወድቅ ኃላፊነቱ ከባድ ይሆናል። በመሆኑም የኢኮኖሚ ጫናውም ቀላል አይሆንም፤ ይህንን ለማስተካከል ሥራ መስራትና ጊዜን ሥራ ላይ ማጥፋት ይጠይቃል። የልጆች ኃላፊነት መደረብም ሁኔታውን ከባድ ያደርገዋል የምትለው አክሊል በዚህ ሂደት ውስጥ እናትየዋ ለእረፍት ማጣት ስለምትጋለጥ በተለያየ መልኩ ልትጎዳ እንደምትችል ታስረዳለች። ይህንን የተመለከቱ ጥናቶች በአፍሪካ ብዙም የሉም የሚሉት የሥነ ልቦና ባለሙያው ጉዳቱ ከፍ ያለ ነው ይላሉ። ጫናው ከአካላዊ፣ ማህበራዊ መንፈሳዊና ኢኮኖሚያዊ ደህንነት ይጀምራል። በመሆኑም ላጤ እናቶች ካገቡት ይልቅ ለተለያዩ ቀውሶች ሊዳረጉ ይችላሉ። ከእነዚህም መካከል፡ ኢኮኖሚያዊ ጫና ይበረታባቸዋል አካላዊ ጤንነታቸው፤ ከጭንቀትን መቋቋምና ከበሽታ መከላከል አንፃር ይዳከማል የስሜት ጥንካሬና መረጋጋት አይኖራቸውም ማህበራዊና መንፈሳዊ ድጋፋቸውም የላላ ይሆናል ከሥነ ልቦና አንፃር ብቸኝነት፣ ድባቴ፣ ተስፋ መቁረጥ፣ ዋጋ የለኝም ማለት፣ በራስ መተማመን ማጣትና ለማንነት ችግር እንደሚጋለጡም ባለሙያው በዝርዝር ያስረዳሉ። የልጆቹ አባቶችም ከሴቶቹ ባልተለየ መልኩ የችግሮቹ ተጋሪ ይሆናሉ። የስሜት ጫና፣ ድባቴ፣ ማህበራዊ ጫና ፣ የጥፋተኝነት ስሜት፣ ምቾት ማጣት፣ የፀፀት ስሜት ልጄን በሚገባው መልኩ ድጋፍና ክትትል እያደረኩለት አይደለም የሚሉ ሥነ ልቦናዊ ስሜቶች ይታያሉ። ወንዶች፤ ልጆቻቸውን ሙሉ ለሙሉ ከአጠገባቸው ማጣት ብቻም ሳይሆን በሥነ ልቦና አገልግሎት ውስጥ ገና ለገና እንፋታለን ብለው ሲያስቡ ሚዛናቸውን መሳትና ከፍ ወዳለ የሥነ ልቦና ቀውስ ውስጥ እንደሚገቡም ባለሙያው ያክላሉ። በልጆች ላይ ምን ተፅዕኖ ያሳድራል በተለይ ልጆች እድሜያቸው ከፍ እያለ ሲሄድ ለብቻ ማስተዳደር ፈታኝ ነው የምትለው ይህች እናት በቤት ውስጥ ኃላፊነትን በማከፋፈል በሕይወታቸው ውስጥ ሚና እንዲኖራቸው በማድረግ ፈተናውን መቋቋም ችላለች። ቤታችን ፓርላማ ይመስላል፤ ልጆቼ ተነጋግረው ወስነው እኔ ጋር የሚመጡት ለማፅደቅ ነው፤ በሁሉም ነገር ተሳታፊ ናቸው ትላለች። ይህም እነርሱን እንደውም ይበልጥ ጠንካራ እንዳደረጋቸውና ሴት ብቻዋን ልጆች ማሳደግ ትችላለች፤ በማለት እርሷን እንደ አርአያ ማየት እንደጀመሩ ታስረዳለች። በተለይ ወንድ ልጇ በእርሷ መኩራት እንደሚሰማው ትናገራላች። የምታስማማበት ጉዳይ በትዳር ውስጥ ሆኖ ልጆችን በተገቢው መንገድ ማሳደግ መተኪያ እንደሌለው ነው፤ ነገር ግን ትዳር ለመያዝ ተብሎ አሊያም ያልሆነ ትዳር ይዞ ሕይወትን መግፋት ደግሞ የማታምንበት ጉዳይ። የሴቶች መብት ተሟጋቿ አክሊል ቤተሰብ የሚባለው ትርጓሜ ከድሮው በተሻለ ተቀይሯል ትላለች። በመሆኑም ልጆች የአባትና የእናትን ሚና ካለማግኘት በበለጠ ማህበረሰቡ የሚያደርስባቸው ጉዳት ያይላል ትላለች። በተቃራኒው አቶ ሞገስ ልጆች የአባታቸውንና የእናታቸውን ሚና እያዩ ባለማደጋቸው ለተለያዩ የሥነ ልቦና ችግሮች ይዳረጋሉ ይላሉ። በመሆኑም ክሊኒካል ድብርትና ጭንቀት እና ባህሪያዊ የሥነ ልቦና ችግሮች ይታዩባቸዋል ይላሉ። እንደ ባለሙያው ገለፃ ከወንዶች ይልቅ ሴቶች በብዛት ለእንዲህ ዓይነት የሥነ ልቦና ችግር የሚዳረጉ ሲሆን የሚያጋጥማቸውም ክሊኒካል የሚባለው የሥነ ልቦና ችግር ነው። ወንዶች ደግሞ ባህሪያዊ ችግር ያጋጥማቸዋል፤ ከሁኔታዎች ጋር ተስማምቶ መኖር ይቸግራቸዋል። ችግሮቹ እንደ እናቶቹ ባህሪ የሚወሰን ቢሆንም በትምህርት፣ በሥራና በማህበራዊ ስኬቶቻቸው ላይ ተፅዕኖ ያሳድርባቸዋል ብለዋል። አቶ ሞገስ ላጤ እናቶች ሁለት ባህሪ አላቸው ይላሉ። አንደኛው ልጆቻቸው ሕይወት ውስጥ ጥሩ ድርሻ ያላቸው፣ ፍቅርና እንክብካቤ በጥሩ ሁኔታ የሚሰጡ ሲሆኑ ሌላኛው ደግሞ ልጆቻቸውን ችላ የሚሉና በልጆቻቸው ሕይወት ውስጥ የማይገቡ ናቸው። ይሁን እንጂ በሁለቱ የተለያየ ባህሪ የሚያድጉ ልጆች ለተለያዩ ሥነ ልቦና ችግሮች መዳረጋቸው አይቀርም። ጥሩ ድርሻ ያላቸው እናቶች እንክብካቤና ፍቅራቸው ከልክ ያለፈ ስለሚሆን ልጆች ለጥገኝነት መንፈስ ይጋለጣሉ። በሌላ በኩል ግድ የለሽ በሆኑት እናቶች የሚያድጉት ደግሞ ማግኘት ያለባቸውን የስሜት ደህንነት ስለማያገኙ ቀደም ብለው ለተጠቀሱት የሥነ ልቦና ችግሮች ይዳረጋሉ። ለምክር አገልግሎት ወደ እርሳቸው ቢሮ ጎራ ከሚሉት ላጤ እናቶች አብዛኞቹ ስሜታቸው ተመሳሳይ መሆኑንና ልጆቻቸው ላይም የድብርት ስሜት ማየት እንደቻሉም ባለሙያው አካፍለውናል። የሚገጥማቸውን ተግዳሮቶች እንዴት ይፍቱት በተለያየ ምክንያት ልጆቻቸውን ብቻቸውን የሚያሳድጉ እናቶች የሚገጥሟቸውን ተግዳሮቶች እንዴት ሊቋቋሟቸው እንደሚችሉ የሥነ ልቦና ባለሙያው ይመክራሉ። ጤናማ ስሜትና ጤናማ አካል እንዳላቸው ማረጋጋጥ፣ ከውስጥ ግጭት ነፃ መሆን፤ ፍርሃት ካላቸው ለልጆቻቸው እንዳያስተላልፉ መጠንቀቅ ከልጆች ጋር ደረጃ በደረጃ፤ እንደ ዕድሜያቸው ሁኔታ ያለውን ሁኔታ በግልፅ ማሳየት እና ልጆች ከአባታቸው ጋር ግንኙነት ሊያስፈልግ እንደሚችል በማመን ከአባታቸው ጋር እንዲገናኙ እድል ማመቻቸት የእነርሱንም ሆነ የልጆቻቸውን ሕይወት በተወሰነ መልኩም ቢሆን ቀላል ያደርገዋል። በመጨረሻም ብዙ ጊዜ ላጤ እናቶች በኢኮኖሚ፣ በአስተሳሰብ፣ በትምህርት የተሻሉ ናቸው ይባላል። ይህንንኑ ጥያቄ ለሴቶች መብት ተሟጋቿ አክሊል አንስተን ነበር። ለብቃት ሰፊ ትርጓሜ በመኖሩ እነዚህ ሴቶች ብቁ ናቸው አይደሉም ማለት አልችልም ትላለች። ይሁን እንጂ ሰዎች የሚወስኑበት መንገድ ቢለያይም ልጅ ካልወለድኩ ሴት አይደለሁም፤ ስለዚህ ጊዜዬ ሳያልፍ ልጅ መውለድ አለብኝ የምትል ሴት ብቁ እንደሆነች አላምንም፤ ምርጫ ግን ነው ስትልም ታብራራለች። ምንም እንኳን ውሳኔው ላይ በምን ምክንያት ተደረሰ የሚለው ወሳኝ ቢሆንም የአንድ ሰው ዋጋው የሚለካው በልጅ መኖርና አለመኖር አይደለም። በመሆኑም ሴትነቷ የሚለካው ልጅ በመውለድ አቅምና ላጤ እናት በመሆን አለመሆኑን በመግለፅ የግል አስተያየቷን ሰጥታለች። ተያያዥ ርዕሶች
በፕሮቴስታንት እምነት ተከታይነቱ ለእስር ተዳርጎ የነበረው ኤርትራዊ ህይወቱ አለፈ
ሴፕቴምበር ስለ ማጋራት ተጨማሪ ያጋሩ ማጋሪያ ምረጥ የፕሮቴስታንት እምነት ተከታይ በመሆኑ ለእስር ተዳርጎ የነበረው ኤርትራዊው ተኪኤ ተስፋ ዮሃንስ በእስር ቤት ህይወቱ ማለፉን የእስረኞች የእምነት መብት ተሟጋች ድርጅት ሪሊዝ ኤርትራ ዳይሬክተር ዶ ር ብርሃነ አስመላሽ ለቢቢሲ ገልፀዋል። በኤርትራዋ መዲና አስመራ በአንድ የግል መኖሪያ ቤት መቶ አርባ አንድ የሚጠጉ የእምነቱ ተከታዮች መንፈሳዊ ስብስባ ሊያካሂዱ ሲሉ የተያዙት ከአራት ወራት ገደማ በፊት ነበር። ተኪኤ በወቅቱ በቁጥጥር ስር ከዋሉት ውስጥ አንዱ እንደነበር ዶ ር ብርሃነ ያስረዳል። ኤርትራ የሃይማኖት እሥረኞችን ፈታች ግለሰቦቹ በሙሉ ዓዲ ዓቤቶ ወደተሰኘው እስር ቤት ተወስደው የነበረ ሲሆን፤ የተወሰኑት ሊፈቱ ችለዋል። የአምሳ አምስት እድሜ ያለው ተኪኤ ባለትዳርና የሶስት ልጆች አባት ሲሆን ጠንካራ ሰራተኛም እንደነበር ጓደኛው ሃኒባል ዳንኤል ይናገራል። በአካል ጉዳኝነቱ ሳይበገር ሁለት አይነት ስራ እየሰራ ልጆቹንም እያሳደገ እንደነበር ምስክርነቱን ሰጥቷል። በመቀሌ የከተሙት ኤርትራውያን በእርግጥ ከተለያየን ረዥም ጊዜ ሆኖናል። ሆኖም በማውቀው ደረጃ ጠንካራ ሰራተኛና ምሬትም የማያውቅ ሰው ነበር ብሏል። ከኤርትራ ባለስልጣናት መረጃ ማግኘት ከባድ እንደሆነ የሚገልፀው አቶ ሃኒባል መሞቱ እንጂ ህይወቱ ከማለፉ በፊት ህክምና እርዳታ ይደረግለት አይደረግለት፤ እንዲሁም መቼ እንደሞተ የሚታወቅ ነገር የለም በማለት አስረድቷል። በተመሳሳይም ከጥቂት ወራት በፊትም ፍፁም የተባለ ሌላ ወንጌላውያን እምነት ተከታይ በዳህላክ እስር ቤት ህይወቱን እንዳጣ ይናገራል። ተያያዥ ርዕሶች
መንዙማ የትም ሊኖር ይችላል። ግብፅም የመንም፣ ሻምም
መንዙማ የትም ሊዜም ይችላል፤ ታጃኪስታንም፣ ኡዝቤኪስታንም፣ ፓኪስታንም እንደ ወሎ የሚኾን ግን እንጃ የወሎ መንዙማ ቱባ ነው። ኦርጋኒክ አልተቀየጠ፣ አልተከተፈ ፣ አልተነጀሰ ። ደግሞም እንደ ዘመነኛ ነሺዳ በ ኪቦርድ ቅመም አላበደ ። ለዚህ ምሥክር መጥራት አያሻም። የሼኽ መሐመድ አወል ሐምዛን እንጉርጉሮ መስማት በቂ ነው። በጆሮ በኩል ዘልቆ፣ አእምሮን አሳብሮ ወደ ልብ የሚፈስ የድምፅ ፈውስ ። ይለዋል ወጣቱ ገጣሚ ያሲን መንሱር። የመንዙማው ማማ በዚህ ዘመን ህልቆ መሳፍርት መንዙመኞች አሉ። ሼኽ መሐመድ አወል ሐምዛ ግን ከማማው ላይ ናቸው። ከወሎ የፈለቁት ሼኹ ለመገናኛ ብዙኃን ቃል መስጠት እምብዛም ምቾት አይሰጣቸውም። ለቢቢሲ ጥሪም እንዲያ ነው ያሉት። ኾኖም ታሪካቸውን የዘገቡ ሰነዶች የኚህ ሰው የሕይወት መስመር እንደ መንዙማቸው ልስሉስ እንዳልነበረ ያትታሉ። ደቡብ ወሎ የተወለዱት ሼኹ ገና ድሮ ወደ ሸዋ ገብተው ኑሮ ለማደራጀት ከፍ ዝቅ ብለዋል። የሚያምር የአረብኛ የእጅ ጽሕፈት አጣጣል ስለነበራቸው የሃይማኖት ድርሳናትን በእጅ ከትበው በመስጂዶች ቅጥር ማዞር ጀማምረውም ነበር ይባላል። ወዳጆቻቸው እንደነገሩን በአዲሳ ባ የመን ኮሚኒቲ በመምህርነት እስኪቀጠሩ ድረስ የወሎ ምድርና ተፈጥሮ አድልተው ያደሏቸውን መረዋ ድምጽ በመጠቀም በተለያዩ ዝግጅቶች ላይ መንዙማን ያዜሙ ነበር። አንዳንድ መድረኮች ላይ ታዲያ የሼኩ ተስረቅራቂ ድምጽ ለነብዩ ውዳሴ ከሚደረድሩ ጥልቅ መልዕክቶች ጋር ተዳምረው ታዳሚዎችን ስሜታዊ ያደርጓቸው ነበር ይባላል። የእሱ እንጉርጉሮ እንደሁ ያው ታውቀዋለህ ልብ ያሸፍታል አንዳንድ ሼኾች ድምጽ አውጥተው በስሜት ያለቅሱ እንደነበር አስታውሳለሁ ይላሉ ቆየት ካሉ ወዳጆቻቸው አንዱ ለቢቢሲ ትዝታቸውን ሲያጋሩ። በመንዙማ ፍቅር የወደቀው ደርግ መንዙመኛው ሼክ መሐመድ አወል ድሮ ማስታወቂያ ሚኒስቴር ተቀጥረው ነበር አሉ። መንዙማቸውም እንደዋዛ ሬዲዮ ሞገድ ውስጥ ገብቶ ነበር አሉ፤ እንደ ማጀቢያም እንደማዋዣም። ታዲያ ከዕለታት ባንዱ ልበ ደንዳናዎቹ ደርጎች በሰውየው አንጀት አርስ እንጉርጉሮ ልባቸው ረሰረሰ። ከደርጎቹ በአንዱ ላይ ክፉ አሳብ በልቡ አደረ። እንዲህም አለ፣ ይሄ ሰውዬ በነካ እጁ ስለ አብዮቱ ለምን አያዜምልንም ሼኪው ተጠሩ። ድምጽዎ ግሩም ኾኖ አግኝተነዋል፤ እስቲ ስለአብዮታችን አንድ ሁለት ይበሉ ። ያን ጊዜ ያ አላህ አንተው መጀን ብለው ከአገር ሾልከው የወጡ ከስንትና ስንት ዘመን ኋላ የሐበሻን ምድር ተመልሰው የረገጡ። ዓመት ዓመት እንጃ ብቻ በዚህ ሁሉ ዘመን ታዲያ እኚህ እንደ ጨረቃ የደመቁ መንዙመኛ የት ከረሙ ስንል የጠየቅናቸው ወዳጆቻቸው ከፊሎቹ መሐመድ አወል ሐምዛ ሳኡዲ ነው የኖረው ሲሉ፣ ገሚሶቹ ደግሞ የለም እዚህ ጎረቤት ሚስር ፣ አልአዝሃር ዩኒቨርስቲ ትምህርቱን ሲይንበለብለው ነበር ብለውናል። የቱ ነው ትክክል ብሎ ለመጠየቅ እንኳ ሰውየው ሩቅ ናቸው። ያ ጥኡሙ ድምጻቸው መንዙማን ለማዜም ካልሆነ በቀር አይሰማም። እ ሩቅ ነው። መንዙማ የልብ ወጌሻ መንዙማ አልፎ አልፎ መዝናኛ ነው፤ አንዳንዴ የጸሎት ማዳረሻ ነው፤ ብዙዉን ጊዜ የማኅበረሰብን ሰንኮፍ ማሳያም ነው፤ አንዳንዴ የአገር ፍቅር መግለጫም ነው። ብዙዎቹ የመንዙማ ሥንኞች የሥነ ምግባር ተምሳሌት ተደርገው የሚታሰቡትን ነብዩ ሙሐመድን ያወድሳሉ። አፈንጋጮችን ይገስጻሉ፣ ባሕል ከላሾችን ይኮረኩማሉ። አቶ ተመስገን ፈንታው መቀለ ዩኒቨርስቲ ውስጥ ሥነ ጽሑፍና ፎክሎርን ለ ዓመታት አስተምረዋል። በመንዙማ ዙርያ የተሠሩ በርከት ያሉ ጥናታዊ ወረቀቶችን አማክረዋል። የአጋጣሚ ነገር ትውልዳቸውም ወልዲያ ነው። ሴት አያቴ በመንዙማ ነው ያሳደገችኝ ይላሉ ክርስቲያን መሆናቸው መንዙማን ከማጣጣም እንዳላቦዘናቸው ሲያስረዱ። ወሎ ውስጥ መንዙማ ባሕል ነው። የየትኛውንም ዕምነት ተከታይ ሁን መንዙማን ትሰማለህ፤ በአንድም ሆነ በሌላ የወሎ ባሕል ወትሮም ሃይማኖትን ፍዝ ያደርጋል። አያቴ መንዙማን የእስልምና ብላ አይደለም የምትረዳው። እሷ የምታውቀው የወሎዬ መሆኑን ነው። መንዙማ ለእሷ ከአምላክ ጋር መገናኛ፣ መታረቂያ፣ መለማመኛ፣ ስሜቷን መተንፈሻ ነው። ይላሉ። መምህር ተመስገን ይኸው የልጅነት ተጽእኖ ይሁን አይሁን ባያውቁትም አሁንም ድረስ ጥሞናና መመሰጥ ሲያምራቸው ከላፕቶፓቸው ኪስ ያኖሯቸውን እንጉርጉሮዎች ያዘወትራሉ። አቦ ሌላ ዓለም ነው ይዞኝ የሚሄድ መንዙማና ፍልስምና ፍልስምና እስልምናና ፍልስፍናን ያቀፈ ሽብልቅ ቃል መሆኑ ላይ ከተግባባን በመንዙማ ውስጥ ፍልስፍና እንደጉድ እንደሚነሳና እንደሚወሳ ልናወጋ እንችላለን። በመንዙማ ዓለማዊም ኾኑ ዘላለማዊ መጠይቆች በቅኔ ተለውሰው ይዜሙበታል። በግልባጩም የፈጣሪን መኖር የሚጠራጠሩ ኢ አማንያን ከብርቱ አማኒያን ተሞክሮ እየተጨለፈ በምክር ይረቱበታል። ለነገሩ በመንዙማ ስንኞች ፍልስምና ብቻ አይደለም የሚነሳው፤ ምን የማይነሳ አለና ፖለቲካ፣ ግብረ ገብነት፣ መንፈሳዊነት፣ አርበኝነት ኢትዮጵያዊነት በስልክ ማብራሪያ የሰጡን ኡስታዝ አብዱልአዚዝ መሐመድ የነጃሺ መስጂድ ኢማምና የጁምዓ ሶላት ዲስኩረኛ ኻጢብ ናቸው። መንዙማ በኢትዮጵያ የኢስላም ታሪክና ፖለቲካ ውስጥ የነበረውን ቦታ ሦስት የመንዙማ ሊቃውንትን በስም በመጥቀስ ይተነትናሉ። በዘመናዊ የኢስላም ታሪክ ውስጥ ሰሜን ወሎ፣ ራያ ውስጥ ጀማሉዲን ያአኒ የተባሉ ሐበሻ ከአጼ ዮሐንስ ጋር ለሦስት ዓመታት ተፋልመዋል። በመጨረሻ አጼው በርትተው ሲመጡባቸው ድል መነሳታቸው እርግጥ ሆነ። ያን ጊዜ ያዜሙት መንዙማ ዛሬም ድረስ ይወሳል። ዘይኑ ነቢ ዘይኑ ነቢዬ የሚል አዝማች ያለው ሲሆን የመንዙማው ጭብጥ ደግሞ የአጼውን ጭካኔ ማጉላት ነው። እንዲያውም የአጼ ዮሐንስን ጦርነት አርማጌዶን ሲሉት፤ በምጽአት ቀን ቂያማ ይመጣል የሚባለው ሰው ጋር ያመሳስሏቸዋል። ይህ ሰው በኢስላም ደጃል በመባል ይታወቃል። አጼው እኔ ላይ ያለ ጊዜው የመጣ ደጃል ሆነብኝ ሲሉም አዚመዋል። በተመሳሳይ በየጁ ግዛት ይኖሩ የነበሩና አሕመድ ዳኒ የሚባሉ ኢትዮጵያዊ አባት በወቅቱ የነበረው አገረ ገዢ በጣም ቅር እንዳሰኛቸው፣ ዘመኑም እንዳልተመቻቸው ለመግለጽ የሚያንጎራጎሩበት መንዙማ ዛሬም ድረስ ይዜማል። ርዕሱ ሑዝቢየዲ ያረሱላላህ የሚል ሲሆን ከይህ ወዲህ ምድር ላይ መቆየት አልሻም፤ በቃኝ የሚል መልዕክትን የያዘ ነው። ከ ኛው ክፍለ ዘመን መንዙመኞች ደግሞ ሼክ ጫሊ ጎልተው ይወሳሉ። በይዘትም፣ በቋንቋ ልቀትም፣ በቁጥርም፣ በዓይነትም እንደርሳቸው መንዙማን የቀመረ የለም ይባላል። እርሳቸው ታዲያ ከወራሪው ጣሊያን የተፋለሙ ጀግና ነበሩ። ከመንፈሳዊ መንዙማም በላይ ስለ አገር ፍቅር ያዜሙ እንደሆኑ ይነገርላቸዋል። ጣሊያን ወልዲያ፣ ሃራ አካባቢ አባብሎና አግባብቶ ካስጠራቸው በኋላ ተኮሰባቸው፤ በተአምር ተረፉ። እርሳቸውም በመንዙማቸው እንጉርጉሮን አዚመዋል። በአገራችን መኖር አትችሉም አሉን፤ ሻምና ሩም ሂዱ አሉን፤ ምን ጉድ ነው ይሄ የሚሉ ፖለቲካዊ ዜማዎችን አዚመዋል። እንደ ኡስታዝ አብዱልአዚዝ ገለፃ መንዙማና ሥነ ቃል እያንዳንዱ መንዙማ ይነስም ይብዛ ታሪክ ተሸክሟል። የመንዙማ ስንኞች ቢያንስ ቀደምት የኢትዮጵያ ሙስሊሞች እንዴት እንደኖሩ የመተረክ አቅም አላቸው። አሁን ያሉቱ መንዙመኞች ግን ቀደምት ግጥሞችን በአዲስ ቅላጼ የማዜም ነገር ካልሆነ እምብዛምም አዲስነት አይታይባቸውም። በመንዙማ ታሪክ ብቻ ሳይሆን ዕውቀትም ተስፋፍቷል። ማንበብና መጻፍ ሩቅም ብርቅም በነበረበት በያ ዘመን መንዙማ የእስልምና ትምህርት መሠረታዊያንን ለገጠሩ ማኅበረሰብ ለማድረስ አስችሏል ይላሉ ኡስታዝ አብዱልአዚዝ። የመንዙማ ንሸጣ የመንዙማ ግጥሞች ጥልቀትና ከፍታ በታላቅ መነቃቃትና ጥሞና ውስጥ መጻፋቸው ነው። የመንዙማ ደራሲ ድንገት ዋሪዳ መጣብኝ ካለ ቅኔ ሊዘርፍ ነው ማለት ነው። ንሸጣ ውስጥ ገብቻለሁ እንደማለትም ነው። ድሮ ድሮ በግብታዊነት የሚጻፉ፣ በዘፈቀደ የሚሰደሩ ስንኞች አልነበሩም። አሁን አሁን ካልሆነ። ንፁህ አማርኛን ብቻ የሚጠቀሙ መንዙማዎች የሉም ባይባልም በርካታ አይደሉም። የሚበዙቱ አረብኛን ከወሎ አማርኛ ጋር ያዳቀሉት ናቸው። ለምን የወሎ አማርኛ ወትሮም አንዲያ ያደርገዋል። ከአረብኛ ጋር የመጎናጎን ባሕሪው ዘመን የተሻገረ ነው። የወሎ ሕዝብ ችግር መጣብኝ ከማለት ሙሲባ መጣብኝ ነው የሚለው። ሙሲባ አረብኛ ነው ይላሉ ኡስታዝ አብዱልአዚዝ። ይህ ቋንቋን የማዳቀሉ ነገር መንዙማው ላይም ተጋብቶበታል ይላሉ ኡስታዙ። ቢያንስ በሁለት ምክንያት በኢትዮጵያ የኢስላም ታሪክ የወሎዎች ሚና መጉላቱ አንዱ ነው። ቁርዓን፣ ፊቂህ ኢስላማዊ ሕግጋት የቅዱስ መጻሕፍት ትርጉም ታፍሲር ፣ አረብኛ ቋንቋ እና የአብነት ትምህርት ቤቶች ማድራሳ ከወሎና ሀይቅ አካባቢ ነው የመነጩት። ዛሬም ድረስ የበርካታ መዝጊዶች አሰጋጆችና ሊቃውንት ሙፍቲሆች የወሎ ልጆች ናቸው። መንዙማም መንፈሳዊው ሕይወትን የመግለጫ አንድ የጥበብ አምድ መሆኑ ከሌላው የኢትዮጵያ ክፍል ይልቅ በዚያ አካባቢ እንዲጎመራ የተመቻቸ መስክ ሳያገኝ አልቀረም። ይላሉ ኡስታዙ። የአረብኛ ቃላት በመንዙማው እንዲህ በአያሌው መነስነስ ሌላው ምክንያት ደግሞ፤ አንድም የሃይማኖቱ አንኳር ቃላት በአረብኛ መወከላቸው የፈጠረው ሀቅ ሲሆን፣ አንድም ደግሞ የገጣሚዎቹ የቋንቋ ልኅቀት ማሳያ የይለፍ ወረቀት መሆኑ ነው። ሳኡዲን ያስደመመው የሐበሻ መንዙማ የነጃሸዒ መስጂድ ኢማም ኡስታዝ አብዱልአዚዝ ናቸው ይህን ግርድፍ ታሪክ የነገሩን። የቀድሞው የሳኡዲ ዋናው ሙፍቲህ እጅግ የተከበሩት ሼክ ኢብኒባዝ አሁን በሕይወት የሉም ነፍስ ይማር ይርሃመሁላህ አንድ ቀን ምን አሉ እስቲ የናንተ ሐበሾች ጻፉት የሚባለውን መንዙማ አምጡልኝ በዝና ብቻ ነበር አሉ የሐበሻን መንዙማ የሚያውቁት። ቀረበላቸው። ግጥሞቹን ሰምተው ግን ለማመን ተቸገሩ። እንዴት እኛ የአፍ መፍቻ ቋንቋችን አረብኛ የሆንነው ሰዎች ያልቻልነውን በግጥም መራቀቅ እናንተ ቻላችሁበት ብለው መደነቃቸው ይነገራል። ሼኸ ኢብኑባዝን ወሎ ነበር ማምጣት የቅኔ አገር የደረሶች ማንኩሳ የመንዙማ ቀዬ የ መሳኪን ሼኮች ማደሪያ ተያያዥ ርዕሶች
እናቴ የሞተችው ኤች አይ ቪ እንዳለብኝ ሳትነግረኝ ነው
ጁላይ ስለ ማጋራት ተጨማሪ ያጋሩ ማጋሪያ ምረጥ አንዳንድ ወላጆች በደማቸው ውስጥ ኤች አይ ቪ መኖሩን ለማንም ትንፍሽ ሳይሉ ወደ መቃብር ይወርዳሉ። ልጆቻቸው ጤና ሲያጡ እያዩ እንኳ ሚስጥራቸውን እንደያዙ እስከወዲያኛው ያሸልባሉ። ብሪያን ኦሞንዲ ሲወለድ ቫይረሱ በደሙ ይገኝ ነበር። ከ ዓመቱ ጀምሮ የፀረ ኤች አይ ቪ መድሀኒት ይወስድ ነበር። ነገር ግን ዓመት እስኪሞላውና እናቱ እስከሞተችበት ጊዜ ድረስ መድሀኒቱን ለምን እንደሚወስድ አያውቅም ነበር። አሁን የ ዓመት ወጣት የሆነው ብሪያን ትውልድ ይዳን፤ በኛ ይብቃ እያለ በቤተክርስቲያናት አካባቢ ያስተምራል። የኢትዮጵያ አዞ ቆዳና ሥጋ ገበያ አጥቷል ልጅ እያለሁ ታማሚ እንደነበርኩ ትዝ ይለኛል የሚለው ብራያን እየባሰብኝ ሲሄድና ሁኔታዬ ዕለት በዕለት ከመሻሻል ይልቅ እየከፋ ሲሄድ እናቴ ሆስፒታል ወሰደችኝ ይላል። ምርመራ ከተደረገለት በኋላ ኤች አይ ቪ በደሙ ውስጥ ስለተገኘ የፀረ ኤች አይ ቪ መድሀኒት መውሰድ ቢጀምርም እናቱ ግን የሚወስደውን መድሀኒት ለምን እንደሚውጥ ትንፍሽ አላለችም። እናቱ ስትሞት አክስቱ ጋር ሄዶ መኖር ጀመረ። ያኔ የአክስቱ ጎረቤቶች ስለ ህመሙ መንሾካሾክ ጀመሩ። ልጆቻቸውም ይጠቋቆሙበት ነበር። ወላጆች ኤች አይቪ ካለበት ልጅ ጋር ልጆቻቸው እንዲጫወቱ አይፈቅዱም ይላል። የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ እያለ ያገኛት አንዲት ሴት ኤች አይ ቪ አለብህ አይደል እንዳለችው በማስታወስ ስሜቱ እንዴት እንደተሰባበረ ይናገራል። በኬንያና በሌሎች የአፍሪካ አገራትም ህፃናትን ጨምሮ በርካታ ሰዎች በኤች አይ ቪ ይያዛሉ። ቫይረሱ በደማቸው እያለ የሚወለዱ ህፃናት ከቫይረሱ ጋር እንደሚኖሩ ሳያውቁ ሕይወታቸውን ይገፋሉ። በእስክሪብቶ ሳይሆን ክላሽ ተሸክመን ለመዋጋት ዝግጁ ነን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አንዳንዶቹ መድሀኒት ተደብቀው እንደሚወስዱ የሚናገረው ብሪያን፤ ማታ ማታ ሰው መተኛቱን፣ ጭር ማለቱን አይቼ ነበር መድሀኒት የምውጠው ይላል። የ ዓመቷ ዊኒ ኦሮንዲ በ ዓመቷ ኤች አይ ቪ በደሟ እንዳለ ስታውቅ በድንጋጤ ፊቷ ጭው ብሎ እንደነበር ትናገራለች። እናቴ ከሞተች ከሁለት ወራት በኋላ ታላቅ እህቴን ዶክተሩ ጠርቷት ሆስፒታል ብቻዬን እንድመጣና ምርመራ እንዳደርግ ጠየቃት ትላለች። ሐኪሙ እናቷ በኤድስ ምክንያት እንደሞተች ስለሚያውቅ እሷንም ኤች አይ ቪ መመርመር ፈልጓል። እናም በምርመራው ቫይረሱ በደሟ ተገኘ። ለቤታቸው ትንሿ ልጅ እሷ ናት፤ እህትና ወንድሞቿ ከቫይረሱ ነፃ ናቸው። ለምን እኔ ከአራታችን መካከል እኔ ብቻ እንዴት ኤች አይ ቪ ሊገኝብኝ ቻለ የሚለው ሀሳብ ለተወሰነ ጊዜም ቢሆን ጎድቶኛል ለበርካታ ጊዜ መድሀኒቱን ለመጀመር አሻፈረኝ ብላ ቆየች። ነገር ግን በተደጋጋሚ እየታመመች የሆስፒታል አልጋ ስታዘወትር፤ ሐኪሟ ለትምህርት ቤቷ ርዕሰ መምህር ከትምህርት ቤት ለምን በተደጋጋሚ እንደምትቀር ለማስረዳት በሚል ያለችበትን የጤና ሁኔታ አስረዳ። ርዕሰ መምህሩ ለሌላ መምህር፣ ከዛም ሁሉም የትምህርት ቤቱ ማኅበረሰብ ኤች አይ ቪ እንዳለባት ሰማ። ከዚህ በኋላ ሕይወቷ እንደነበረው አልቀጠለም። መገለል ይደርስባት ጀመር። በጣም አዘንኩ፤ ውጤቴን ለራሴ ቢነግሩኝ ምን ነበረበት ራሴን ማጥፋት ፈለግሁ፤ ነገር ግን ራሴን ካጠፋሁ እህቶቼ እንደሚጎዱ ሳስብ ሀሳቤን ጠላሁት በኬንያ ፀረ ኤች አይ ቪ ዘመቻዎች የሚያደርጉ ቡድኖች የሥርዓተ ፆታና የሥነ ወሲብ ትምህርቶች እንዲያስተምሩ ይፈልጋሉ። ዶ ር ግሪፊንስ ማንጉሮ፤ የህፃናት አሳዳጊዎችና ወላጆች ልጆቻቸው ከዘጠኝ እስከ ዓመት ሲሆኑ ስለ ኤች አይ ቪ ውጤታቸው እንዲነግሯቸውና ግልፅ ውይይት እያካሄዱ እንዲያሳድጓቸው ይመክራሉ። ልጁ ስለ ኤች አይ ቪ ምንነት መረዳት ሲችል ኤች አይ ቪ እንዳለበት በመንገር መድሀኒቱን እንዲወስድ ማድረግ ይቻላል በማለት ህፃናቱን ያለምንም መረጃ መተው መድሀኒቱን እንዳይወስዱ ሊያደርግ እንደሚችል ያስጠነቅቃሉ። ብሪያን፤ እናቱ የኤች አይ ቪ ውጤቱን ስላልነገረችው አይኮንናትም። ልትነግረኝ ትችል ነበር፤ ያልነገረችኝ ልትከላከለኝ ፈልጋ ይሆናል፤ ስለዚህ አልወቅሳትም ተያያዥ ርዕሶች
በፈረንጅ ናይት ክለብ ጉራግኛ ሲደለቅ
ሴፕቴምበር ማጋሪያ ምረጥ አጭር የምስል መግለጫ ዲጄ አሌክስ በ ኤይልሃውስ አንድ የሆነ የአውሮጳ ጉራንጉር ውስጥ፣ አንድ ሁለት ለማለት፣ ወደ አንድ የሆነ መሸታ ቤት ጎራ ስትሉ፣ ለአመል እንኳ አንድ ሐበሻ በሌለበት አንድ የፈረንጅ ቡና ቤት፣ አንድ ቀጭን ዘለግ ያለ ፈረንጅ ፣ ከኢትዮጵያ ሙዚቃዎች አንዱን ከፍቶ፣ ትከሻውን ሲሰብቅና ሲያ ሰብቅ ብታዩት ምን ይሰማችኋል ለዚያውም የብዙዬን ፎቅና መርቼዲስ ስሜት አይሰጡኝም፤ እኔ ፍቅር እንጂ ሐብት አያሞኘኝም፤ አያገባው ገብቶ ሰው ይዘባርቃል፤ እኔ ስሜን እንጂ ስሜቴን ማን ያውቃል የሚለውን ወዝዋዥና ወስዋሽ ዜማ ። ይህ ሰው አሌክሳንደር ባውማን ይባላል። ዓመቱ ነው። ዲጄ ስለሆነ አሌክስ እያልን እናቆላምጠዋለን። በስዊዘርላንድ ዙሪክ ጎታርድ እና ከርን በሚባሉ የምሽት ክለቦች ውስጥ የሙዚቃ ሸክላ ያቁላላል ፤ አቁላልቶ ለጆሮ ያጎርሳል፣ አጉርሶ አቅል ያስታል፤ የ ዎቹን የኢትዮጵያን ሙዚቃ፤ የያ የወርቃማውን ዘመን። አሌክስ እንኳን ኢትዮጵያ፣ አፍሪካንም ረግጦ ስለማወቁ እንጃ ። ቱኒዚያና ደቡብ አፍሪካ አንድ ሁለቴ ገባ ብዬ ወጥቻለሁ ያለኝ መሰለኝ። ከዚያ ውጭ ወላ ሃንቲ ። አማርኛም ሆነ ኦሮምኛ፣ ትግርኛም ሆነ ጉራግኛ ጆሮውን ቢቆርጡት አይሰማም። ወላ ሃባ ኾኖም የትኞቹ የኢትዮጵያ ሸክላዎች በምን ቋንቋ ፤ በምን ዘመን፤ ከምን ባንድ ጋር እንደተቀነቀኑ ሲያስረዳ አገር ፍቅር ጓሮ ወይ እሪ በከንቱ ጀርባ ያደገ ነው የሚመስለው። የዘፋኞቻችንን ታሪክና የሙዚቃ አጀማመራቸውን ሳይቀር ለጉድ ይተነትናል ለዚያውም ብ ጥ ር ጥ ር አድርጎ ። የቢቢሲ ዘጋቢ አሌክስን ለመጀመርያ ጊዜ ያገኘው በስዊዘርላንድ፣ ዩኒቨርሲሻትስትራሰ ጎዳና፤ ከታላቁ ዙሪክ ዩኒቨርስቲ ማዶ በሚገኘው ኤይልሀውስ ውስጥ ነበር። ኤይልሃውስ በዓለም ዙርያ የተጠመቁ እልፍ የቢራና የድራፍት መጠጦች የሚሸጡበት ዕውቅ መጠጥ ቤት ነው። ያን ምሽት እዚያ ግቢ ጓሮ ከድራፍቱ ፉት እያሉ እራታቸውን የሚመገቡ በርካታ ስዊሳዊያን ይታዩ ነበሩ። ዲጄ አሌክስ ታዲያ ለታዳሚው የኢትዮጵያን የወርቃማውን ዘመን ሙዚቃዎች በሸክላ እያጫወተ ሲያምነሸንሻቸው አድሯል። በዚያች ድንገተኛ ምሽት ያለቀጠሮ የተገናኙት አሌክስና የቢቢሲ ዘጋቢ አንድ ሁለት እያሉ ለአንድ ሰዓት ያህል ቆይተዋል። ወጋቸው በጥዑም ሙዚቃዎች ሲታጀብ የሚከተለውን መልክ ይይዛል። ፈረንጆች የኢትዮጵያን ሙዚቃ ሲሰሙ ጆሯቸው ግር ይለዋል ዲጄ አሌክስ ሳቂታና ተግባቢ ነው። ዲጄ ኾኖ ድሮስ ሊኮሳተር ያምረዋል እንዴ ከፊትለፊቱ ሸክላ ማጫወቻ ጥንድ ምጣዶች አሉት። ጆሮው የከባድ መኪና ጎማ በሚያካክሉ የአፍኖ ማድመጫ ተለብዷል። ባተሌ ነው። አንድ የጋለ ምጣድ ላይ አንድ የሸክላ ድስት ጥዶ፣ሌላኛው ምጣድ ላይ በስሎ የሚንተከተክ ሸክላን ያወርዳል ። ፋታ ጠብቄ የእግዜር ሰላምታ ሰጠሁት። የቢቢሲ ጋዜጠኛ መሆኔን፣ ከባላገር መምጣቴን በትህትና ገልጬ ፍቃዱ ከሆነ በየሙዚቃ መሀል እንድናወጋ ብጠይቀው ኽረ ምን ገዶኝ አለኝ፤ በትከሻው፣ እንዲሁም በእንግሊዝ አፍ ። ምን ዋጋ አለው ታዲያ አይረጋም። ወጋችን ወግ ለመሆን ገና ወግ ሳይደርሰው ተስፈንጥሮ ይነሳል፤ ሌላ ሸክላ ይጥዳል። የሙዚቃ ባተሌ ነው ብያችሁ የለ ኤይልሀውስ መጠጥ ቤት በረንዳ ላይ ነው ያለነው። በዚያ ላይ ፡ ሰዓት ተኩል አልፏል ኮ። ደግነቱ በአውሮፓ የበጋ ፀሐይ በጣም አምሽታ ነው የምትጠልቀው። ፀሐይዋ ራሱ ፀሐይ ሞቃ አትጠግብም መሰለኝ ለመጥለቅ ትለግማለች። አሌክስ የሚያጫውተው ሙዚቃ ደግሞ ልብ ያሞቅ ነበር። ታዳሚ ፈረንጆቹም በግማሽ ግርታና በግማሽ ፍንደቃ ይሰሙታል። ጥላሁን ያም ሲያማ ያም ሲያማ ወገኔ ለኔ ብለህ ስማ ይላል። ሰይፉ ዮሐንስ የከርሞ ሰው የሚለውን ልብ ገዥ ሙዚቃው ያንቆረቁራል። አሌክስ መቼስ ዓለማየሁ ብልህ ነው የሚቀለው በምን አጋጣሚ ይሆን ከኢትዮጵያ ሙዚቃ ጋር የተዋወቅከው አልኩት። ብሎ ጀመረና በእንግሊዝ አፍ የሚከተለውን አጭር ወግ ጠረቅን፤ ሙዚቃ አጅቦን። አሁን የምትሰማው የኦሮምኛ ሙዚቃ ነው፤ አሊ ሙሐመድ ቢራ ነው ዘፋኙ እሱ የኦሮምኛ ሙዚቃ ንጉሥ ልትለው ትችላለህ አስገራሚ ድምጽ ያለው ሰው ነው ። እኔን በተመለከተ ምን ማወቅ ትፈልጋለህ ታዲያ አሌክስ እባላለሁ፤ ዓመቴ ነው፤ ጀርመናዊ ነኝ፤ የምኖረው ግን እዚህ ዙሪክ ነው። ከዓመት በፊት የጃማይካ ሙዚቃ አጫውት ነበር። ከዕለታት አንድ ቀን ታዲያ ምን ይሆንልሃል የሒሩት በቀለን ሙዚቃ እሰማልኻለሁ በድንገት ሌላ ሸክላ ሊጥድ ተነሳ። የተቀመጥነው እሱ ሸክላዎቹን ከሚጥድበት የሙዚቃ ምድጃ በዐሥር እርምጃ ርቀት ነው። ያን ያደረገው እሱ ነው፤ ቃለምልልሳችን በመቅረጸ ድምጽ ሲቀረጽ እሱ የሚያጫውተው ሙዚቃ የኛን ድምጽ ውጦ እንዳያስቀረነው ስለሰጋ ነው። የድምጽ ሊቅ ም አይደል አዲስ ሸክላ ጥዶ ሲመለስ ወጋችንን ካቆምንበት ቀጠልን ሰዮም ጋብራየስ ። እረ ወላጅ እናቱም ከዚህ በተሻለ አትጠራውም ልለው ፈልጌ እንግሊዝኛ አልሰበሰብልህ አለኝ ስዩም ገብረየስ እንደ ጥላሁን ገሠሠና ዓለማየሁ እሸቴ ላቅ ያለ ዕውቅና ያለው ሞዛቂ እንዳልሆነ፤ የሠራቸው ሙዚቃዎችም በቁጥር ጥቂት እንደሆኑ አጫወተኝ። እውነቱን ንገረኝ ካልከኝ ለኔ ሰዮም ጋብራየስ ታላቅ ሙዚቀኛ ነው። ብሎ ንግግሩን አሳረገ። ከኢትዮጵያ ሙዚቃ ጋር እንዴት እንደተዋወቅህ ጠይቄህ አልመለስክልኝም ኮ አሌክስ ብሎ ሌላ ሸክላ ሊጥድ ተነሳ። ሸክላዎቹን መልክ አሲዞ ተመለሰ። ቢሊኪኒህ ኡጋ ቢልኪኒህ ኡጋ ስሙን እንዲደግምልኝ ተማጸንኩ። ቢሊኪኒህ ኡጋ ቢልኪንህ ኡጋ አለኝ። የጠራው ስም የአገሬ አይመስልም፤ ብቻ ወርቅነህ ይርጋ፣ ወይ ብርቅነህ ይርጋ ወይ ቢልልኝ አጋ የሚባል ዘፋኝ መሆን አለበት እያልኩ፣ ለማንኛውም ቀጥል አልኩት በጥቅሻና በእንግሊዝኛ። በዚህ ጊዜ አልከዳሽም የሚለው ቢሊኪኒህ ኡጋ የተባለውን ሰው ዘፈን ወጋችንን አጅቦት ነበር። መኖሬ ባንቺው ነው እስከመጨረሻ እየተገባደደ ባለው ረዥም ሕይወቴ ሰምቼው የማውቀው ዘፈን አይደለም። ይሄ ቢሊኪነህ ኡጋ እያለ የሚጠራው ዘፋኝ ጥቂት ሙዚቃዎች ብቻ እንዳሉትና በዘመኑ ብዙም ገንኖ ያልወጣ እንደነበር፣ ነገር ግን ድንቅ ሙዚቀኛ እንደሆነ አብራራልኝ ። ስሙ ግራ የሆነብኝ ይህ ኢትዮጵያዊ ዘፋኝ ማን ይሆን ቢሊኪኒህ ኡጋ ብሎ ስም ወደ ናይሮቢ የቢቢሲ ቢሮ ተመልሼ ይህንን ጽሑፍ ለሕትመት በማጠናቅርበት ወቅት የዚህን ዘፋኝ ከፊል የግጥሙን ክፍል ለጉግል አቀብዬ አልከዳሽም የሚል ሸክላ ያለው ኢትዮጵያዊ ዘፋኝ ማነው አልኩት። ጉግል ፈጥኖ መልስ ሰጠኝ፤ ለዚያውም በምሥል የተደገፈ ። ብርቅነህ ውርጋ ይባላል፤ ሄጃለሁ ገጠር የሚል ርእስ ያለው አልበም ያለው፣ ከምድር ጦር ኦርኬስትራ ጋር የሞዘቀ ኢትዮጵያዊ ነው።አትሸኝዋትም ወይ የሚልና ገና ልጅ ናት ጋሜ የሚሉ ሌሎች ሙዚቃዎቸም አሉት። ስለ አገሬ ሞዛቂ አንድ ፈረንጅ የሚያውቀውን ያህል ባለማወቄ ሀፍረት ቢጤ አልሸበበኝም አልልም መቼስ። አጭር የምስል መግለጫ አሌክሳንደር ከጣሊያናዊ ሸሪኩ ጋር በመሆን ኦዲዮአበባ የተሰኘ የዲጄ ግብረኃየል መሥርቷል በፈረንጅ የምሽት ክበብ ውስጥ ጉራጊኛ ዲጄ አሌክስ ስለ ብርቅነህ ውርጋ አውርቶ አይጠግብም። ይገርመሀል እዚህ ዙሪክ ውስጥ የምሽት ክለቦች የኢትዮጵያ ሙዚቃዎችን አጫውታለሁ። አልከዳሽምን ከከፈትኩ ግን የዳንስ ወለሉ በሰው ይጥለቀለቃል። አለኝ። አሌክስዬ የምትለውን ዘፋኝ ብዙ ኢትዮጵያዊያን የሚያውቁት አይመስለኝም፤ እኔንም ጨምሮ እኔ ስለ ኢትዮጵያዊያን ምርጫ ብዙም አላውቅ ይሆናል፤ ልነገርህ የምችለው ግን እኔ በማጫውትበት ክለብ ውስጥ ስላሉ የውጭ አገር አድማጮች ነው ። ዲጄ አሌክስ ይህን ብሎኝ እብስ ብሎ ተነሳ ሸክላ አውርዶ ሸክላ ሊጥድ ማነው ደግሞ አሁን የሚጫወተው አስናቀ ገብረየስን አታውቀውም በአርግጠኝነት እየታዘበኝ ነው፤ ድንቄም ጋዜጠኛ የሚል ይመስላል ሙዚቃው የተቀረጸው ካልተሳሳትኩ ሲሆን በካሴት ነበር መጀመርያ የወጣው። እኔ ሸከላውን ያገኘሁት ከአንድ ዓመት በፊት ነው። ይመስለኛል ፈረንሳይ ያለ አንድ ሰው ነው በሸክላ ያሳተመው፤ በቅርቡ። እኔምልህ አሌክስ ከየት ነው እነዚህን ሸክላዎች ግን የምትለቃቅማቸው። ቅድም ስጠይቅህ ኢትዮጵያ ሄጄ አላውቅም አላልከኝም እንዴ ሸክላ መሰብሰብ የጀመርኩት ከ ዓመቴ ጀምሮ ነው። እንደው ለየት ብሎ ለመታየት አይደለም የምሰበስባቸው። ሙዚቃ ለማጫወት ሌላ ምንም የተሻለ መንገድ ስለማይታየኝ ነው። ለእንደኔ ዓይነቱ የሙዚቃ አጫዋች ሸከላ በብዙ መንገድ የላቀ ነው። ሸክላን ስትዳስሰው ሁሉ ልዩ ስሜት ኮ ነው የሚሰጠው ። ታውቃለህ አይደል ግን አሌክስ ከኢትዮጵያ ሙዚቃ ጋር እንዴት ተዋወቅክ ብዬህ እስካሁን አልመለስክልኝም የሰይፉ ዮሐንስ ኤቦላላ ላላ ኤቦ ላላ እያጀበን ያነሳሁለት ጥያቄ ነበር። ምን መሰለህ፤ ላለፉት ሁለት ዐሥርታት ማለት ይቻላል የጃማይካን ሙዚቃ አጫውት ነበር። በአጋጣሚ በሙዚቃዎች መሀል የኢትዮጵያን ሙዚቃ ሰማሁ። ከዚያ ለረዥም ጊዜ አልተመለስኩበትም። ባለፈው ዓመት የሒሩት በቀለን ዘፈን ስሰማ ተቀሰቀሰብኝ። ምኑ ለኢትዮጵያ ሙዚቃ ያለኝ ስሜት ነዋ ለመጀመርያ ጊዜ የኢትዮጵያ ሙዚቃ ስትሰማ ግን ቶሎ ተዋኸደህ እውነት ለመናገር የመጀመርያው ስሜቴ እንደዚያ አልነበረም። እንደሰማሁት ውድድ አደረገኩት ልልህ አልችልም። ይልቅ ግር ነው ያለኝ። ይሄ ደግሞ እንዴት ያለ እንግዳ ዜማ ነው እንድል ነበር ያደረገኝ። እውነትህን ነው አዎ ነገር ግን እንደ ሙዚቃ አጫዋች አንድ ሙዚቃ ሰምተህ በቃ ይሄ ለኔ የሚሆን አይደለም አትልም። ደግመህ ደጋግመህ ትሰመዋለህ። ይህንኑ አደረኩ። በዚህ ጊዜ ልዩ ፍቅር ውስጥ ወደቅኩ። የሆነ ሰሞን እንዲያውም በሙዚቃችሁ ታመምኩ። በፍላጻው ተወጋሁ፤ የሙዚቃችሁ መብረቅ መታኝ እንደማለት ከዚያን ጊዜ ጀምሮ የኢትዮጵያ ሸክላ ማሳደድ ጀምርኩ። ሌላ ሸክላ ጥዶ ተመለሰ የምትሰማው አሕመድ አብደላን ነው። ኦሮምኛ ነው የሚያዜመው። ይሄንንም ዘፋኝ ብዙ ሰው ያውቀዋል የሚል ግምት የለኝም። አሊ ሸቦን ታውቀዋለህ እንዴት ግሩም የኦሮምኛ አቀንቃኝ መሰለህ እኔ ምልህ ሙዚቃችን ግን ለምን እንደ ማሊ ሙዚቃ ዓለምን ማስደመም ሳይችል ቀረ እንደው በአጠቃላይ ተስፋ ያለው ይመስልኻል ይህን እኔ ለመናገር ይከብደኛል። ሆኖም አቅም የለውም አልልህም። በኢቶፒክስ እና በሙላቱ አስታጥቄ ወደ ዓለም መድረክ የቀረበ ይመስለኛል። ሙላቱ ኮ እዚህ አውሮፓና ሰሜን አሜሪካ ገናና ሰው ነው። የወርቃማ ዘመኑ ሙዚቃችሁም ትልቅ አቅም አለው። የአሁን ሙዚቃችንን ትሰማለህ ማነው ደሞ እሱ የአዲሱ ትውልድ ድምጽ ነው። ዝነኛ ኮ ነው። ይቅርታ እንደነገርኩህ የአሁን ዘመን ከሆነ አላውቅም። ከአሁኖቹ ስሙን የማውቀው ቴዲ አፍሮን ብቻ ነው። ስለዚህ ዘመን ሙዚቃ ለማውራት እኔ ትክክለኛው ነኝ ብዬ አላስብም። ለምንድነው የአሁኖቹን እንዲህ ገሸሽ ያደረካቸው ግን በጥቅሉ ጆሮ ገብ አይደሉማ። ሁለተኛ ሲንተቲክ ነው። ተፈጥሯዊ ወዝ የላቸውም፤ ይሄ ለኢትዮጵያ ሙዚቃ ብቻ ሳይሆን አዘውትሬ ለማጫውተው ለጀማይካም ሙዚቃም፣ ለተቀረውም ዓለም ሙዚቃም ያለኝ ስሜት ነው። እንዴት ነው ግን በወርቃማው ዘመን በኢትዮጵያ ዝነኛ የነበሩትንና ያልነበሩትን የምታውቀው እና ደግሞ እስኪ የድሮ ሸክላዎችን እንዴት እንደምትሰበስባቸው በዚያው ንገረኝ ሸክላ በሁለት መንገድ አገኛለሁ። አንዱ በኦንላይን ኢቤይ ላይ እገዛለሁ። በዋናነት ግን ሁለት ሁነኛ ሰዎች አሉኝ፤ ሁለቱም ኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖሩ ናቸው። የምፈልገውን ሙዚቃ ያውቃሉ። ሸክላ ከየትም አፈላልገው ገዝተው ይልኩልኛል።አሁን ከመቶ በላይ የኢትዮጵያ ሸክለዎች አሉኝ ስንት ያስወጣኻል አንዱ ሸክላ በአማካይ ዶላር ይሆናል። ነገር ግን ብርቅዬ የድሮ ሸክላዎች ደግሞ አሉ፤እነሱ ውድ ናቸው። ለምሳሌ የሙላቱን አታገኘውም። በጥሩ ይዞታ ላይ ያሉ የኢትዮጵያ ሸክላዎች እስከ ሁለት መቶ ዶላር ያስወጡኛል። እንደነገርኩህ አሁን የምትሰማው የኦሮምኛ ዜማ ነው፤ አሕመድ አብደላ ይባላል ትናንትና ማታ እዚህ ዙሪክ ምሽት ክበብ ውስጥ ይሄን አሁን የምትሰማውን ሙዚቃ ጨምሮ ሌሎችንም የወርቃማ ዘመን ሙዚቃዎች ሳጫውተው ነበር። አንዳንድ ፈረንጆች ወደኔ የዲጄ አትሮንስ እየቀረቡ ለመሆኑ ይሄ የምታጫውተው ሙዚቃ ከየት አገር ነው ቋንቋውስ ምንድነው ይሉኝ ነበር። ለጆሯቸው እንግዳ ስለሆነ መሰለኝ። ሙዚቃችን ግራ አጋቢ ነው ማለት ነው ግራ የሚገባቸው ለምን መሰለህ አንደኛ የአሁን ዘመን ሙዚቃ አይደለም። የ ዎቹና የ ዎቹ ነው። ሁለተኛ ከለመዱት የሙዚቃ ቃና እጅግ ያፈነገጠ ነው የሚጎረብጣቸው እንዳሉ ሁሉ እጅግ አድርገው የሚወዱትም ብዙ ናቸው። የዚያ ዘመን ሙዚቃችሁ ውብ ነው፤ ዘርፈ ብዙ ቅኝቶች አሉት፤ ጃዝ አለው፣ ፋንክና ሶል አሉት፤ ከዚያ ባሕላዊ ሙዚቃዎቻችሁ ሌላ መልክ አላቸው። ያፈነገጡ ሆነው ደስ የሚሉ ናቸው፤ የኦሮምኛ ሙዚቃ ከትግርኛ ፍጹም የተለየ ነው። ትግርኛ ከጉራጊኛውም እንዲሁ ክለብ ውስጥ ሙዚቃዎቻችንን ስታጫውት እንደው ድንገት እግር የጣለው ኢትዮጵያዊ ሰምቶህ ጉድ ያለበት ጊዜ የለም እምብዛምም አላጋጠመኝም ግን አንዴ የማልረሳው ሌሎች እንግዶች እየተዝናኑ አንድ ኢትዮጵያዊ እንባው እየወረደ አየሁ። ወደኔ ተጠግቶ በማጫውተው አንድ ሙዚቃ እጅግ ልቡ መነካቱን ነገረኝ። ሙዚቃውን ታስታውሰዋለህ ማሕሙድ አሕመድ ነው አንወድም ጥቃትን በነገርህ ላይ ማሕሙድ ለፌስቲቫሉ እዚህ ዙሪክ ነው ያለው፤ሰምተኻል ለመሆኑ የድሮዎቹን ሙዚቀኞችን አግኝተኻቸውስ ታውቃለህ አዎ ማሕሙድ እዚህ መሆኑን ሰምቻለሁ። ሙላቱ አስታጥቄን አግኝቼው አውቃለሁ። በዚህ ዓመት እዚህ ዙሪክ ኮንሰርት ነበረው። ለአጭር ደቂቃ እንደምንም ብዬ አገኘሁት። ተዋወቅኩት። ተግባቢና ቀና ሰው ነው። ከመድረክ ጀርባ ሄጄ ነበር ያገኘሁት። እሱን በማግኘቴ ምን ያህል እድለኛ ሰው እንደሆንኩ ነገርኩት። የሱን ድ ሮ የሠራቸውን ሙዚቃዎች ያሉበትን ሸክላ ከነሽፋኑ አሳይቼው ፈርምልኝ አልኩትና እሱ ላይ ፈረመልኝ። በቃ ምን ልበልህ ደ ስ አለኝ። አጭር የምስል መግለጫ የዲጄ አሌክስ የምንጊዜም ምርጥ የኢትዮጵያ ሙዚቃዎች በምሥሉ የሚታዩት ናቸው ወደፊት ታዲያ ምን አሰብክ ደግሞ አሌክስ አዲስ አበባማ መሄድ አለብህ ። ይሄን ሁሉ ሙዚቃ እያጫወትክ ኢትዮጵያ ሄጄ አላውቅም ስትል ትንሽ ይከብዳል እውነትህን ነው። አሁን የዲጄ ግብረኃይል አለኝ። አውዲዮአበባ የሚባል። በቡድኑ ውስጥ እኔና አንድ ጣሊያናዊ ጓደኛዬ ነን ያለነው። ቶሚ ይባላል። እሱም ሙዚቃችሁን እንጂ ኢትዮጵያን ፈጽሞ አያውቅም። ሁለታችንም ምን እያሰብን መሰለህ በይበልጥ የኢትዮጵያን ሙዚቃ ለአውሮጳዊያን ለማስተዋወቅ ዕቅድ አለን። ኢትዮጵያ አትሄድም ወይ ላልከው ፤ እንደነገርኩህ ኢትዮጵያን የማውቃት በሙዚቃ ነው፤ ኢትዮጵያ አለመሄዴም ያሳፍረኛል። በዚህ ዓመት መጨረሻ ከቶሚ ጋር አዲስ አበባ ለመሄድ እያሰብኩ ነው። ምን ትላለህ ይቅናህ ሌላ ምን እላለሁ ይቅናህ አሌክስ ይቅናህ ተያያዥ ርዕሶች
መምህራንን ተክቶ ያስተማረው ወታደር እየተወደሰ ነው
መስከረም ጃይረስ ሙሊማ ሒሳብ ሲያስተምር ኬንያ ውስጥ በአንድ ትምህርት ቤት የሚያስተምሩ መምህራን በስራ ገበታቸው ባለመገኘታቸው በአካባቢው የነበረ አንድ ፖሊስ ወደ ክፍል ውስጥ በመግባት ሲያስተምር የሚያሳየው ምስል የሃገሬውን ሰዎች በእጅጉ አስገርሟል። ኬንያውያንም ጀግናችን ነህ እያሉ በማህበራዊ ሚዲያዎች እያሞካሹት ነው። ምስሉን በፌስቡክ ለህዝብ ይፋ ያደረገው መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት እንደገለጸው ጃይረስ ሙሊማ የተባለው የፖሊስ ሃይል አባል በኢትዮጵያ እና ኬንያ ድንበር ላይ በሚገኝ ፎሮሌ በተባለ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ ሂሳብ ሲያስተምር ነበር። የድርጅቱ ሃላፊ ለቢቢሲ እንደተናገሩት ከባለፈው ሳምንት ጀምሮ አካባቢው የደህንነት ስጋት አለበት በማለት መምህራኑ በስራ ገበታቸው ላይ እየተገኙ አይደለም። በዚህም ምክንያት ተማሪዎች በክፍል ውስጥ ያለምንም ትምህርት ተቀምጠው እንዲውሉ ተገደዋል። ከትምህርት ቤቱ ሃላፊ ፍቃድ ካገኘ በኋላ ጃይረስ ሙሊማ አምስተኛ ክፍል በመግባት የሂሳብ ትምህርት ሲያስተምር ነበር ብለዋል ሃላፊው። ትምህርት ቤቱ በሚገኝበት አካባቢ በተለያዩ ጊዜያት ሽፍታዎች ድንገተኛ ጥቃት የሚያደርሱ ሲሆን ጥቂት ለማይባሉ ሰዎችም ህይወት ማለፍ ምክንያት ሆኗል። በርካታ ኬንያውያን ጃይረስ ሙሊማ የሰራው ስራ እጅግ የሚያኮራና ለሁላችንም ምሳሌ መሆን ያለበት ነገር ነው በማለት በማህበራዊ ሚዲያዎች እየተቀባበሉት ነው። ፀረ መውለድ ፍልስፍናን ያውቁታል አንድ ኬንያዊ ያልተዘመረለት ጀግና ሲል አሞካሽቶታል። ጃይረስ ሙሊማ በድንበር አካባቢ የተከሰተውን አለመረጋጋት ለመቆጣጠር ከተመደቡ የጸጥታ ሃይሎች አንዱ ሲሆን በትምህርት ቤቱ አካባቢ ጥበቃ ሲያደርግም ነበር ተብሏል። ጃይረስ የሂሳብ ትምህርት ሲያስተምር በክፍሉ ውስጥ የነበሩት ወደ ትምህርት ቤት ለመምጣት ድፍረት የነበራቸው ጥቂት ሴት ተማሪዎች ብቻ ነበሩ ተብሏል። ቢቢሲ ማስተባበያ
የሼፎች የበዓል ምግብ ምርጫ፡ ሼፍ ዮሐንስ፣ ጆርዳና እና ዮናስ
መስከረም ይህንን ለማጋራት በ ትዊተር ይህንን ለማጋራት በ ዋትስአፕ ዓውደ ዓመትና ምግብ አይነጣጠሉም። ዶሮው፣ ጥብሱ፣ ዱለቱ፣ ቁርጥ ስጋው፣ ክትፎው፣ ድፎ ዳቦው እነዚህን ሁሉ የዓውደ አመት ደስታ፣ ቄጤማና እጣን፣ የሚትጎለጎል የተቆላ ቡና ሽታ ከዛም ጥዑም ቡና ሲያጅባቸው የበዓል ሞገሱ ይገዝፋል። እኛም ሦስት በምግብ ዝግጅት የሚታወቁ ባለሙያዎችን አነጋግረናል። ሼፎቹ ዩሐንስ፣ ጆርዳና እና ዮናስ ሺህ ጉርሻዎች ዮ ሐንስ ኃይለማርያም ምግብ ማብሰልን እንደ ሙያ ከያዘ ዘጠኝ ዓመት አስቆጥሯል። በቅርቡ የምግብ አዘገጃጀት መጽሐፍ አሳትሟል። በቃና ቴሌቭዥን አዲስ ጓሮ የተባለ መሰናዶ አዘጋጅም ነው። በኃያት ሬጀንሲ በየወሩ የምግብ አሠራር ትምህርት ይሰጣል። ሲድስ ኦፍ አፍሪካ የተራድኦ ድርጅት ውስጥ ስለልጆች አመጋገብ ያማክራል። አንባቢዎቻችን ለበዓል ምን እንዲመገቡ ትመክራለህ እስኪ ከነአሠራሩ ንገረን። እንፍሌ። አሠራሩ፡ የበግ ወይም የፍየል እግር ሥጋው ከአጥንቱ ሳይለያይ ተፈልቅቆ ይነሳል። ሥጋው ከአጥንቱ ጋር እንደተያያዘ ይዘለዘላል። ልክ እንደ ዶሮ ወጥ በሽንኩርት፣ በበርበሬ፣ በቅመማ ቅመም ስልስ ይዘጋጃል፤ ትንሽ ጠጅ ጠብ ይደረግበታል። ከዛ ሥጋው በነዚህ እንፋሎት ይበስላል። እንፍሌ በመላው ኢትዮጵያ ስትዘዋወር ከገጠሙህ የምግብ ግብዓቶች እና የምግብ አሠራር ያስገረመህ የቱ ነው ጋምቤላ ውስጥ ከአንድ ቅጠል የሚሠራ ጨው ይጠቀማሉ። ቅጠሉ ተቃጥሎ፣ ከውሀ ጋር ይዋሀድና ይጠላል። ከዛ በጸሐይ ደርቆ ጨው ይሆናል። ሶድየም ስለሌለው ለማንኛውም የእድሜ ክልል ተስማሚ ነው። ላሊበላ ውስጥ የአጃ ቂጣ ሲጋገር እንደእንጀራ አይን እንዲያወጣ በምጣዱ ዙሪያ ልጆች ተሰብስበው ያፏጫሉ። በየትኛውም አገር እንዲህ ያለ አሠራር አልገጠመኝም። ጤፍ ስለሚብላላ በፈርመንቴሽን እንጀራ ሲጋገር አይን ይሠራል። አጃ ግን ግሉተን ስላለው ውስጡ የሚታመቀውን አየር ለማፈንዳት ይከብዳል። ስለዚህ በፉጨት የድምጽ ንዝረት ቫይብሬሽን በመፍጠር አይን እንዲወጣ ይደረጋል። ምግብህ አይጣፍጥም ተብለህ ታውቃለህ ቆይ አሁን ባይጣፍጥ፤ አይጣፍጥም ብዬ የምነግርሽ ይመስልሻል ሳቅ ግን እድለኛ ነኝ ይህ ገጥሞኝ አያውቅም። የምትወደው ምግብ ምንድን ነው በተለያየ ጊዜ እንደስሜቴ የተለያየ ምግብ ያምረኛል። ሁሌ የሚያስደስተኝ ግን ጥሬ ሥጋ ነው። ምግብ ከመሥራት ሂደት የሚያስደስትህ የቱ ነው ሁሉንም ሂደት እወደዋለሁ። ከግብዐት መረጣ ጀምሮ እስከ ማብሰል፤ ከዛ አልፎም እንግዶች ምግቡን ቀምሰው አስተያየት እስኪሰጡ ወይም ፊታቸው ላይ የሚነበበውን እስከማየው ድረስ ደስ ይለኛል። ለምትወደው ሰው የምታበስለው ምግብ ምንድን ነው ሼፍ ስትሆኚ ኃላፊነት አለብሽ። ሁሌም ለምትወጂው ሰው እንደምታበስይ አስበሽ ነው መሥራት ያለብሽ። ግን የሆነ ውድድር ቢኖርብኝ፤ በምን ምግብ አስደምማለሁ ብዬ ሳስብ ስፔሻሊቲዬ የተካንኩበት ስለሆነ ሲ ፉድ ከባህር ውስጥ እንስሳት የሚዘጋጅ ምግብ ይመቸኛል። ቆንጆ ምግበ ማብሰል እንደ ም ትችል አምነህ ሼፍ መሆን እችላለሁ ያልክበት ቅጽበት ትዝ ይልሀል የመጀመሪያ ቀን ምግብ ሰርቼ ይጣፍጣል ብዬ አይደለም ወደሙያው የገባሁት። የመጀመሪያ ዲግሪ የሠራሁት በቪዥዋል አርት የእይታ ሥነ ጥበብ ነው። ከዛ ወደ ከልነሪ አርት ምግብ የማብሰ ጥበብ ገባሁ። ጥብበ በሸራ፣ በድምፅ፣ በፐርፎርማንስ ክዋኔ በብዙ መንገድ ሊገለጽ ይችላል። ብዙ ሰው ጋር ለመድረስ ግን ምግብ የተሻለ ነው። የተማረኩበት ፈረንሳይ የሚገኝ በዓለም እውቅና ያለው ትምህርት ቤት ነው። ጥሩ መሰረት ሰጥቶኛል። እናቴ አንቲካ የሚባል ሬስቶራንት ስላላት ለሙያው ቅርብ ሆኜ ነው ያደግኩት። ምግብህን በልተው ካደነቁህ ሰዎች የማትረሳው ማንን ነው ለመጽሐፌ ምርቃት ኒውዮርክ ሄጄ ነበር። ሴቮር የሚባል በጣም የታወቀ መጽሔት አለ። እዛ የድርቆሽ ቋንጣ ፍርፍር ሠርቼ ነበር። ምግቡ ቀላል ሆኖ ሰውን ያስደነገጠ ነበር። ከነበረው ምግብ ሁሉ ሰው የወደደው እሱን ነበር። ጆርዳና ከበዶም ምግብ የ ማ ብሰል ሙያን ያዳበረችው በሬስቶራንቶች በመሥራት ነበር። ሁለት የምግብ አዘገጃጀት መጻሕፍት ለህትመት አብቅታለች። አሁን በፋና ቴሌቭዥን ላይ የምግብ መሰናዶ መርሀ ግብር እያዘጋጀች ታቀርባለች። አንባቢዎቻችን ለበዓል ምን እንዲመገቡ ትመክሪያለሽ እስኪ ከነአሠራሩ ንገሪን። የአበሻ ዳቦ። አሠራሩ፦ በገብስ ወይም በስንዴም ዱቄት ይቦካል። ከዛ እንዲጣፍጥ ቴምር ወይም ቸኮሌት መጨመር ለሁለት ኪሎ ስንዴ ወይም ገብስ ወይም ግራም ቸኮሌት መሀል መሀል ላይ ጣል ማድረግ። እንዳይቀልጥ ጥንቃቄ ያስፈልጋል። ሌላው አማራጭ ቴምር ነው፤ መሀል ላይ ያለው ፍሬ ወጥቶ ጣል ጣል ማድረግ። ከዛ መጋገር። ጆርዳና ከበዶም ሼፎች በቴሌቭዥን የሚያሳዩት ግብዓት ገበያ ላይ በቀላሉ የማይገኝ ወይም ውድ የሆነ ነው ይባላል፤ ምን ትያለሽ ፍላጎትና አቅርቦት አለ። ፈረንጆች አሁን ያሉት ድሮ በነበሩበት አይደለም። እየተማሩ ሲሄዱ፣ ግብዓቶች መፈለግ ሲጀምሩ፤ አቅርቦትም መጣ። እኛም አመጋገባችንን እያሻሻልን ስንሄድ የገበያ አቅርቦት እየተሻሻለ ይሄዳል። የኔን ሾው መሰናዶ የሚወቅሱ ሰዎች አሉ። በእኔ እይታ በአቅርቦት ሳይሆን በፍላጎት ይጀምራል። ዛሬ ብር ደሞዝ ያለው ሰው፤ የዛሬ አምስት ዓመት ሺህ ብር ቢያገኝ ምን ምግብ ነው የምሠራው ብሎ ገንዘቡን ይዞ ቁጭ ይላል። የምትወጂው ምግብ ምንድን ነው ሁሉንም ነገር እወዳለሁ። በጣም ጥቂት ነገር ነው የማልወደው። ከሁሉም በላይ እንጀራ በጣም አወዳለሁ። በማንኛውም እኔ በምፈላሰፈው ዲሽ ምግብ እንጀራ እበላለሁ። በቅርቡ የቅቅል አጥንት ከጎመን ጋር ቀይ ወጥ ሰርቼ ጉድ ነበር። እኔ እንደመጣልኝ ነው የምሠራው። መመራመር ነዋ ደስ የሚልሽ በጣም በጣም ግን ሁሉም ግ ብዓት አብሮ ይሄዳል ይጣፍጣል ፋንታሲ የምኞት ዓለም ነው። ጭንቅላትሽ ክፍት መሆን አለበት። ምግብን የሚያጣፍጠው ቅመማ ቅመም ነው። ዝም ብዬ ጎመን ቀቅዬ እበላለሁ የምትይ ከሆነ አይጣፍጥሽም። ግን ከጎመን ጋር የሚሄዱ ነገሮችን አብሮ መሥራት ይቻላል። ብዙዎቻችን ገበያ ላይ ሽንኩርት፣ ነጭ ሽንኩት፣ ካሮትና ድንች ብቻ ነው የምንፈልገው። ከዛ ወጣ ሲል፤ ቀይ ሥር፣ ፎሰልያ፣ ስኳር ድንችም መግዛት ይቻላልኮ። እኔ ወደነዛ ነው የማተኩረው። ያው ባጀቴም እንዳይቃወስ። ሽንኩርቱን ቀንሼ ሌላ ነገር እገዛለሁ። ከምግብ ሥራ ሂደት የቱ ደስ ይልሻል ፍሬሽ አዲስ የተቀጠፈ ጎመን፣ ጥቅል ጎመን፣ ቅመማ ቅመም ገዝቼ ቤት ስሄድ ደስ ይለኛል። ፍሪጅ ውስጥ አስገብቼ፣ አውጥቼ ስሠራውም የሆነ ነገር ይሰማኛል። የኛን አገር የአመጋገብ ባህል መቀየር እፈልጋለሁ። ከምናውቀው ነገር ውጪ መሞከር አንፈልግም። መመራመር አንፈልግም። ይህ መቀየር አለበት። ሬስቶራንትሽ እንዴት ነው በኪራይ ምክንያት ተዘጋ። ለአምስት ዓመት ቻልኩት። ከዛ ግን ከእጅ ወደ አፍ ሆነ። ማብሰል ብዙ ሰአት ስለሚወስድም ጊዜ ተሻማኝ። ትቼው ወደ ቲቪ እና ወደ መጽሐፌ መሄድ ፈለኩ። ደንበኞቼ ግን አሁንም ይጠይቁኛል። የቲቪ መሰናዶውን ብዙ ሰው እየተማረበት ነው። መለኪያሽ ምንድን ነው ይሄን ሞክረነዋል ብለው እየመጡ የሚያመሰግኑኝ አሉ። ከኔ ሾው በኋላ ወደ ሰው ይደውላል። ይሄን ግብዓት ከየት አመጣሽ ይሄን ግብዓት በዚህ ልተካ እያሉ ይጠይቃሉ። ምግብ ማብሰል ከልጅነቴ ጀምሮ የምወደው ነገር ነው። የእናቴ አክስት የገዳም አብሳይ ነበሩ። ሠርተው ሲጨርሱ እኛ ቤት ይመጡ ነበር። እናቴ ስታበስል ነይ ተሳተፊ እባል ነበር። እናቴ በጣም ባለሙያ ናት። ሙያው ከአክስቷ ወደሷ፣ ከሷ ወደኔ መጣ። እኔ ሼፍ ትምህርት ቤት አልተማርኩም። ወደ ሙያው የገባሁት መብላት ከመውደዴ የተነሳ ነው። ያደግኩት ደሞ ጣልያን ነው። እዛ ምግብ ትልቁ የሕይወት ክፍል ነው። ምግብሽ አይጣፍጥም ተብለሽ ታውቂያለሽ አውቃለሁ። ብዙ ጊዜ ግን አይደለም። እንደዛ ያሉኝ ልጆቼ ናቸው። ይሄ ደሞ ምንድን ነው ሲሉኝ ይከፋኛል። ግን ወዲያው አሻሽለዋለሁ። ምግብ የልብ ነገር ነው። ከፍቶኝ ስሠራ የከፋ ምግብ አመጣለሁ። ደስ ብሎኝ ስሠራ ደግሞ ይጣፍጣል። ምግብ ሕይወት አለው እንዴ እላለሁ። ኩክ ዊዝ ላቭ በፍቅር አብስሉ የምለው ለዛ ነው። ምግብሽን በልተው ካደነቁሽ ሰዎች የማትረሽው ማንን ነው ልጆቼን። ስለምግብ ጥቅምና መጣፈጥ አስተምሬያቸዋለሁ። የትም ሄደው ይሄ ጥሩ ነው፤ ይሄ መጥፎ ነው ማለት ይችላሉ። ምግብ ሳይቀምሱ አይጣፍጥም እንዳይሉም አስተምሬያቸዋለሁ። ለምሳሌ ካንቺ ጋር ቃለ መጠይቅ ከመጀመሬ በፊት ለእንግዶች የሠራሁትን ሱፍ አቀመስኳቸው። ልክ አይደለም አሉኝ። ከዛ በድጋሚ ነጭ ሽንኩርትና ቅመም ጨምሬ አስተካከልኩ። ከዛ አሁን ጣዕም አለው አሉኝ። ዮ ናስ ተፈራ በ ሙያው ለ ዓመት ቆይቷል። በሆቴል፣ በሬስቶራንት፣ በእንግዳ ማረፊያም ሠርቷል። ከጓደኞቹ ጋር በከፈተው ቤንቬኒዶ የሆቴል ማሰልጠኛ ውስጥ ለአሥር ዓመት አስተምሯል። አምስት የምግብ አዘገጃጀት መጻሕፍት አሳትሟል። በሸገር ኤፍ ኤም ከሠይፉ ፋንታሁን ጋር ሬሲፔ በተሰኘ መሰናዶ ላይ ሠርቷል። አሁን በኢትዮ ኤፍኤም ላይ የ ምሳና ሙዚቃ መሰናዶ አዘጋጅና አቅራቢ ነው። አንባቢዎቻችን ለበዓል ምን እንዲመገቡ ትመክራለህ እስኪ ከነአሠራሩ ንገረን። የብረት ምጣድ ጥብስ። አሠራሩ፦ መጀመሪያ ከምንጠብሰው ሥጋ ብዛት ይልቅ የምንጠብስበት እቃ ሁለት እጥፍ ትልቅ መሆን አለበት። የምንጠብሰው ሥጋ እርጥበት ከምንጠብስበት እሳት በላይ መሆንም የለበትም፤ እሳቱ ማሸነፍ አለበት። ሥጋውን በትንንሹ እንከትፈዋለን፤ አጥንቱን ለብቻው በትንንሹ እንሰባብረዋለን። ቀይ ሽንኩርት፣ ነጭ ሽንኩርትና ዝንጅብል እንከትፋለን፤ የአበሻ ቅቤና ቃሪያ እናዘጋጃለን። ብረት ምጣዱ ከጣድን በኋላ በደንብ ሲግል፤ ትንሽ ዘይት ወይም ጮማውን ብቻ እየተጠቀምን ሥጋውን እየጠበስን ሲበስል ወደ ሌላ እቃ እንጨምራለን። አጥንቱን ለብቻ ሁለት ቦታ ከፍለን እየጠበስን ቡናማ መልክ ሲይዝ በማውጣት የተጠበሰውን ስጋ ወደ አስቀመጥንበት እቃ እንጨምራለን። ባዶ ብረት ምጣድ ላይ ቀይ ሽንኩርት እናደርጋለን። በትንሽ ዘይት ካቁላላነው በኋላ ነጭ ሽንኩርትና ዝንጅብል ገብቶ ለተወሰነ ሰዓት ይቁላላል። የተጠበሰው ስጋ የተፋውን ውሃ አስቀርተን ከሽንኩሩቱ ጋር በመቀላቀል አብረን እንጠብሳለን። ያስቀረነውን ሥጋው የተፋውን ውሃ ጨምረን ትንሽ እናበስለዋለን። የሀበሻ ቅቤ፣ ቃሪያና ጨው ጨምረን እናወጣዋለን። ዮናስ ተፈራ የኢትዮጵያውያንን የምግብ ዝግጅትና የአመጋገብ ባህል እንዴት ታየዋለህ ቅባት እናበዛለን ሳቅ ይሄ ከፍተኛ የጤና ችግር አምጥቶብናል። ዘይት ይበዛል፣ ቅቤ ይበዛል፣ ጮማ ይበዛል። የዚህን ያህል ዘይት አገራችን ከውጪ እንድታስገባም አድርጎናል። በአመጋገብ ስርዓታችን በጎ ነገራችንስ የቱ ነው የጾም ወራት ስለሚበዛ ሳይወዱ በግድ ከቅባት ይራቃል። ያ የጾም ወቅት ባይኖር ኖሮ እንደ አበላላችን የጤናችን ጉዳይ እጅጉን አሳሳቢ ነበር። የጾም ወራት አትክልትና ፍራፍሬ እንድንመገብ ያግዛሉ። ሳይንሱም እንደሚለው፤ ለተወሰነ ሰዓት ራስን ከምግብ ማራቅ፤ ሰውነታችን መርዛማ ነገሮችን እንዲያስወግድ፣ ውስጡ ያከማቸውን ቅባትና ካርቦኃይድሬት እንዲጠቀም እድል ይሰጣል። ምግብህ አይጣፍጥም ተብለህ ታውቃለህ እንዴ ቁጭ አድርጎ ያስበላኝ እንግዳ አለ ሳቅ ግለሰቡ ሼፉን ጥሩት አለ፤ አስተናጋጆቹን። ሄድኩኝ። ቁጭ በልና ብላው አለኝ። በሆቴል ሕግ ከእንግዳ ጋር ቁጭ ብሎ መብላት አይቻልም ስለው፤ አልጣፈጠኝም ቁጭ ብለህ ብላው አለኝ። ሰውየው ሬስቶራንት ውስጥ ግርግር እየፈጠረ ስለነበር ማረጋጋት ነበረብኝ። ቁጭ ብዬ ያዘዘውን ስቴክ ቀመስኩት። ምንም ችግር አላገኘሁበትም። ግን ሰውየውን ለማስደሰትና ለማረጋጋት ትክክል ነህ ጌታዬ፤ ይህ ነገር መቀየር አለበት አልኩና ስሄድ፣ እኮ እኮ ብሎ በጣም ደስ አለው። ወደ ምግብ ማብሰያ ክፍል ሄደን ግማሽ የእሱን ስቴክና ሌላ ስቴክ ጨምረን ላክልነት። ከዛ ኪችን ድረስ ነው ለምስጋና የመጣው። አመስግኖኝ ቲፕ ጉርሻ ሄደ። አንተው ሰርተኸው ያልጣፈጠህ ምግብ አለ አዎ። እኔ ሠርቼው ሳይፍጠኝ፤ ብዙ ሰው የጣፈጠው ምግብ አለ። ውስጤ ስለማይቀበለው ሜኑ የምግብ ዝርዝር ላይ እንዲወጣና እንዲሸጥ አልፈልግም። በአንድ ወቅት ኪችን ውስጥ ሾርባ ሠርተን እኔ አልወደድኩትም ነበር። ረዳት ሼፌ ግን በጣም ወደደችው። ሌሎች የ ኪችን ሰዎችም ወደዱት። በኋላ ኃላፊውን አቀመስነው። ዋው አለ። ሜኑ ላይ መውጣት አለበት ሲል ወሰነ። እኔ ግን ውስጤ ስላልተቀበለው ፈራሁ። ላንተ ምግብ አዘገጃጀት ሳይንስ ነው ጥበብ ከባድ ጥያቄ ነው። ሳይንስን ከጥበብ ያቀናጀ ሙያ ነው። ሳይንሱን የማትከተል ከሆነ ተመጋቢ ትጎዳለህ። ተመጋቢ ለመመገብ አፉን የሚከፍተው እኛን አምኖ ነው። ስለዚህ መታመን አለብን። ክቡር ለሆነው የሰው ልጅ የሚቀርበውን ምግብ ለመሥራት ሳይንሱን መከተል ያስፈልጋል። በየትኛው መንገድ ባበስለው ነው ጤናማ የሚሆነው ብለን ሳይንሱን ካላወቅንና ካልተከተልን ከባድ ነው። ከዚያ ደግሞ መጀመሪያ የሚመገበው ዓይን ነው። ስለዚህ አርቲስቲክ ጥበብ የተሞላው ነገር ይፈለጋል። አበሳሰሉ፣ አቀራረቡም ማማር አለባቸው። ስለዚህ ለኔ የምግብ ዝግጅት ሳይንስና ጥበብን ያቀናጀ ሙያ ነው። ቢቢሲ ማስተባበያ
ሳሙኤል ኤቶ እግር ኳስ ሊያቆም ነው
ሴፕቴምበር አጭር የምስል መግለጫ ሳሙኤል ኤቶ አራት ጊዜ የአፍሪካ የዓመቱ ምርጥ ተጫዋች ተብሎ መመረጥ የቻለው ካሜሩናዊው ሳሙኤል ኤቶ ከ ዓመታት የእግር ኳስ ህይወት በኋላ ጫማውን ሊሰቅል ስለመሆኑ ጠቁሟል። የ ዓመቱ የቀድሞው የካሜሩን ብሄራዊ ቡድንና የባርሴሎናው አጥቂ በኢንስታግራም ገጹ ላይ ባሰፈረው መልእክት ተፈጸመ፤ ወደ ሌላ የፈተና ጉዞ ተጀመረ ሲል ጽፏል። በአውሮፓ የኢትዮጵያዊያን ፌስቲቫል፡ ሙዚቃ፣ ኳስ፣ ፍቅርና ቡጢ ኤቶ ለሃገሩ ካሜሩን በ ጨዋታዎች ግቦችን ማስቆጠር የቻለ ሲሆን በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ በኤልሲና በኤቨርተን ተጫውቷል። ባለፈው ዓመት ደግሞ ለቱርኩ ኮንያስፖር ለአጭር ጊዜ ከተጫወተ በኋላ የኳታሩን ስፖርት ክለብ ተቀላቅሏል። እ አ አ ገና የ ዓመት ታዳጊ እያለ የስፔኑን ሪያል ማድሪድ በ ቢቀላቀልም መጫወት የቻለው ሶስት ጨዋታዎችን ብቻ ነበር። ከዛም በውሰት ለሌጋኔዝ፣ ኤስፓኞል እና ማሎርካ ተጫውቷል። በ ለማሎርካ በ ጨዋታዎች ግቦችን በማስቆጠር የቡድኑ የምን ጊዜም ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ በመሆን ታሪክ ሰርቷል። በ ደግሞ ባርሴሎናን ከተቀላቀለ በኋላ ሶስት ጊዜ የስፔን ላሊጋን ማሸነፍ የቻለ ሲሆን በ እና በ ቡድኑ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ አሸናፊ እንዲሆን አስችሏል። በሁለቱም የፍጻሜ ጨዋታዎችም ግብ አስቆጥሮ ነበር። በ የውድድር ዘመን ለባርሴሎና በ ጨዋታዎች ግቦችን ካስቆጠረ በኋላ በሊጉ የወርቅ ጫማ ማሸነፍ የቻለ ብቸኛው አፍሪካዊ ተጫዋች መሆን ችሏል። በአጠቃላይ በ ጨዋታዎች ግቦችን ለባርሴሎና ያስቆጠረው ኤቶ በ ወደ ኢንተር ሚላን በመሄድ ለሶስተኛ ጊዜ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ዋንጫን ማንሳት ችሏል። የጣሊያን ሴሪ አ እና የፊፋ ክለቦች የዓለም ዋንጫዎችን ከቡድኑ ጋር አንስቷል። በመቀጠል ኤቶ ያመራው ወደ ራሺያ ነበር። አንዚ ማካቻካላ ከሚባለው ቡድን ጋርም ለሁለት ዓመታት ከቆየ በኋላ በ ቼልሲን ተቀላቀለ። ኤቨርተን፣ ሳምፕዶሪያ እና አንታሊያስፖር ደግሞ የተጫወተባቸው ሌሎች ቡድኖች ናቸው። ለካሜሩን ብሄራዊ ብድን ለመጀመሪያ ጊዜ ሲጫወት ሳሙኤል ኤቶ ገና የ ዓመት ታዳጊ ነበር። በ በተካሄደው የዓለም ዋንጫ ሃገሩ ከኮስታሪካ ስትጫወት በመሰለፍ የጀመረው ኤቶ በውድድሩ ትንሹ ተጫዋች ተብሎ ነበር። አንድ አትሌት በህይወቱ የሚያስደስተው የአለም ሪከርድን መስበር ነው ዮሚፍ ቀጀልቻ ከብሄራዊ ቡድን እራሱን እስካገለለበት ጊዜ ድረስ ሃገሩን ወክሎ በአራት የዓለም ዋንጫ ውድድሮች ላይ ተሳትፏል። በ እና በ የተካሄዱትን ተከታታይ የአፍሪካ ዋንጫዎችንም ከሃገሩ ጋር አንስቷል። በውድድሮቹም ጎሎችን በማስቆጠር ኮኮብ ግብ አግቢ ሆኖ መጨረስ ችሎ ነበር። ከዚህም በተጨማሪ በ በተካሄደው ኦሎምፒክ ከቡድን አጋሮቹ ጋር በመሆን ለሃግሩ የወርቅ ሜዳሊያ አስገኝቷል። ተያያዥ ርዕሶች
ይህንን ለማጋራት በ ዋትስአፕ
ባሳለፈነው ቅዳሜ በጊዮን ሆቴል ከ ሺህ በላይ ሰዎች ተሰባስበው በሙዚቃ ድግስ ላይ ተጎራርሰዋል። አዘጋጆቹ ክስተቱ ቋሚ የጉርሻ ቀን ሆኖ እንዲሰየም ይፋልጋሉ። በኢትዮጰያ የማይቋረጥ ዓመታዊ የመጎራረስ ፌስቲቫል እንዲኖር ያልማሉ። ከፍ ሲልም ጉርሻን በማይዳሰስ ቅርስነት የማስመዝገብ የረዥም ጊዜ ትልምን ሰንቀዋል። በቅዳሜው ኩነት ላይ ሺ ሰዎችን በማሳተፍ በጊነስ የድንቃ ድንቅ መዝገብ ላይ ለማስፈር ታቅዶ የነበረ ቢሆንም በተለያየ ምክንያቶች ሳይሳካ ቀርቷል። በፕሮግራሙ ላይ ወደ የሚጠጉ ሰዎች ተገኘተው እንደነበር አስተናጋጆቹ ተናግረዋል። ከአዘጋጆቹ መካከል አንዱ የሆነው ቅዱስ አብረሃም እንደ ጉርሻ ግን የሚያግባባን የለም ጉርሻ እኮ አንዱ ለሌላው የማጉረስ ተግባር ብቻ አይደለም፤ በተጠቀለለው እንጀራ ውስጥ ፍቅር አለ፣ መተሳሰብ አለ፣ አክብሮት አለ። ሲል ከዝግጅቱ በፊት ተናግሮ ነበር።
በስራ በመወጠር አልያም በሌላ ምክንያት ጊዜ ያጡ ግለሰቦችን ታሳቢ በማድረግ የተጀመረ አገልግሎት ነው።
ለቅሶ ለመድረስ፣ ዘመድ ለመጠየቅ ወይም ለሌላ ጉዳይም ምግብ የሚያሰናዱ ተቋሞችን መቅጠር እየተለመደ መጥቷል። ለምግብ ዝግጅት ብቻ ሳይሆን ለመስተንግዶም ተቋም መቅጠር የሚሹ ግለሰቦች መብዛታቸው ደግሞ ነጋዴዎችን ወደ ዘርፉ እየሳበ ነው። በቀን ከ እስከ ትእዛዝ ይቀበላሉ በዘርፉ አዋጭነት ከተሳቡ አንዱ ብስራት በላይነህ ነው። የኢኮኖሚክስ ምሩቅ ነው። የመኪና ኪራይ፣ የኤሌክትሮኒክስ ሽያጭ፣ የቴሌቭዥንና ሬድዮ ማስታወቂያ ይሰራ ነበር። አሁን ግን አትራፊ ወዳለው የምግብ ዝግጅትና አቅርቦት ገብቶ ቤላ ዶናን አቋቁሟል። መነሻ ያደረገው ምሳ ቋጥሮ መሸጥን ነበር። ቤታቸው ምግብ ለማዘጋጀት ጊዜ ወይም ፍላጎቱ ለሌላቸው ሰዎች ቢሯቸው ድረስ ምሳ ቋጥሮ መላክ ከጀመረ ወራት ተቆጥረዋል። ምሳ ሰአት ላይ፤ ምግብ በምሳ እቃ እንዲላክላቸው የሚፈልጉ ሰራተኞች የሚጠበቅባቸው ስልከ መደወል ብቻ ነው። የሚፈልጉትን የምግብ አይነት ያዛሉ። ከዛም ምሳ ሰአት ላይ ትኩስ ምግብ ይወሰድላቸዋል። ለደንበኞቻችን ትኩስ ምግብ፣ በተመጣጣኝ ዋጋ፣ ያሉበት ቦታ ድረስ ለማቅረብ አስበን ነው ስራውን የጀመርነው ይላል። ንግዱ እየተጧጧፈ ሲመጣ ምግብ በአገልግል ወደ ማድረስ ተሸጋገረ። ምግቡ የሚዘጋጀው አዲሱ ገበያ አካባቢ ነው። በምሳ እቃ ሀያ ሁለት፣ ቦሌ፣ መርካቶ፣ አውቶብስ ተራ፣ ጳውሎስ ሆስፒታል አካባቢም ይደርሳል። በአገልግል ሲሆን ግን የሰፈሮች ድንበር አይገድበውም። ሽሮም፣ ዶሮም አለን ብስራት ምግብ በአገልግል ወደማቅረቡ ስራ የገባው በምግብ ዝግጅት ከሰለጠነች ዘመዱ ጋር ነበር። የሚኖሩበት ቤት ውስጥ ምግብ በማዘጋጀት ከጀመሩ በኃላ ስራው ሲሰፋ ተጨማሪ ምግብ አብሳዮች ቀጠሩ። የጸምና የፍስክ ምግብ ያቀርባሉ ምግብ መሰናዶውን በአንድ በኩል ሲያካሂዱ፤ ተረክበው በየአስፈላጊው ቦታ የሚያደርሱ ተቀጣሪዎችም አሏቸው። ስለ አገልግሎታቸው የሚያስተዋውቁት በፌስቡክ ሲሆን፤ በማህበራዊ ሚዲያ ያልደረሷቸውን ደግሞ በያሉበት በመሄድ በራሪ ወረቀት ይበትናሉ። ንግዱ በዋነኛነት የሚካሄደው በቢሮዎችና ሱቆች ስለሆነ በነዚህ አካባቢዎች ራሳቸውን ከማስተዋወቅ አይቦዝኑም። በቀን ከ እስከ ትእዛዝ ይቀበላሉ። የምግብ ዝርዝሩ የጾምና የፍስክ፤ የሀገር ውስጥና የባህር ማዶ በሚል ተከፍሏል። ክትፎ፣ ጥብስ ፍርፍር፣ መኮሮኒ፣ ሩዝ ዝርዝሩ ሰፊ ነው። ሽሮና ፓስታን የመሰሉ ምግቦች በምሳ እቃ ከ እስከ ብር ይሸጣሉ። ክትፎ ደግሞ በ ብር። በአገልግል ሲሆን፤ ሰባት የጾም ምግቦች ተካተው ብር ያስከፍላል። ለአምስት አይነት የፍስክ ምግብ ብር ይከፈላል። ወደድ የሚለው በብዙዎች የሚወደደው ዶሮ ነው። ሙሉ ዶሮ ወጥ፣ ከአይብና ከ እንቁላል ጋር ብር ነው። ሰዎች የቤት የቤት የሚል ምግብ ነው ይሉናል የሚለው ብስራት በተለይም መካከለኛ ገቢ ያላቸውን ታሳቢ ማድረጋቸውን ይገልጻል። ወደ አስቤዛ ሸመታ መግባት እንፈልጋለን ዘመነኛ የሚባለው ኑሮ ቤት ውስጥ ይሰሩ የነበሩ ምግቦችን ወደ ተቋም እያዘዋወረ ይመስላል። ብስራትም የማህበረሰቡን ፍላጎት ተንተርሶ የቅመማ ቅመም ዝግጅትና የአስቤዛ ሸመታ ውስጥም ለመግባት አስቧል። ምግብ በምሳ እቃ ያደርሳሉ ግባችን የሰውን ህይወት ማቅለል ነው ይላል። ስራውን ሲጀምሩ ብዙ ሰው እውን በአገልግል ያመጣሉ ብሎ ይጠራጠር ነበር። አሁን ግን ተአማኒነት እያገኙ እንደሆነ ያምናል። በብዙ ቦታዎች አገልግል አልተተወም፤ ምናልባት የዘነጉት ወጣቶች ካሉ እያስታወስናቸው እንደሆነ ይሰማኛል ይላል። በጊዜ ሂደት የአስቤዛ ሸመታን እንደሚያስለምዱም ያምናል። ቢቢሲ ማስተባበያ
ለብቻ ልጆችን ማሳደግ፡ የኢትዮጵያውያን ላጤ እናቶች ምርጫና ተግዳሮት
ሐምሌ ይህንን ለማጋራት በ ዋትስአፕ ሴቶች በተለያዩ ምክንያቶች ልጆቻቸውን ብቻቸውን የሚያሳድጉ ላጤ እናት ይሆናሉ። ከአጋራቸው ጋር በሞት አሊያም በፍቺ ሲለያዩ፣ በተፈፀመባቸው ጥቃት ሳቢያ የልጅ እናት ለመሆን ሲገደዱ፤ እንዲሁም የጀመሩት ግንኙነት እንዳሰቡት አልሰምር ሲላቸው ልጃቸውን ልጆቻቸውን ብቻቸውን የማሳደግ ውሳኔ ላይ ከሚደርሱባቸው ምክንያቶች መካከል ይጠቀሳሉ። ነገር ግን ፈልገውና አቅደው፤ ልጅ ብቻ እንዲኖራቸው በማለም ላጤ እናት የሚሆኑ ሴቶችም አሉ። እናት አልባዎቹ መንደሮች በተለያዩ አገራት የተሰሩ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት በተለያየ ምክንያት ልጃቸውን ብቻቸውን የሚያሳድጉ እናቶች ቁጥር እየጨመረ መጥቷል። በአፍሪካ በተለይ በኬንያና በደቡብ አፍሪካ ላጤ እናት የመሆኑ ልማድ እንግዳ አይደለም። ምንም እንኳን የተሰሩ ጥናቶች ባለመኖራቸው ቁጥራቸውና የጉዳዩ ስፋት ምን ያህል እንደሆነ ለማወቅ ባይቻልም በኢትዮጵያ በተለይ በከተሞች አካባቢ ላጤ እናትነት አንዱ የሕይወት ዘይቤ መሆኑ ይነገራል። ሴቶች አስበውና አቅደው ለምን ላጤ እናት ይሆናሉ በሕይወቴ ያሰመርኩት ቀይ መስመር ነበር፤ እርሱን ማለፍ ስለማልችል ላጤ እናት ሆኛለሁ የምትለው የአዲስ አበባ ነዋሪ ናት። ስሟን ያልጠቀስናት የይህች እናት ለትዳር ግን ክብር እንዳላት አልሸሸገችም። በሕይወቷ የምታስበውና የምታልመው ስላልሆነ የግድ በትዳር መታሰር የለብኝም የሚል አቋም ላይ እንደደረሰች ትናገራለች። ይሁን እንጂ ላጤ እናት መሆን በርካታ ተግዳሮቶች እንዳሉበት ታነሳለች። እያንዳንዷ ሴት በሰውነቷ ላይ እንዲሁም በምትመሰርተው ቤተሰብ ላይ ውሳኔዎችን ትወስናለች፤ ውሳኔዋም እንደምትኖረው ሕይወት የተለያየ ነው የሚሆነው የምትለው ደግሞ የሴቶች መብት ተሟጋቿ አክሊል ሰለሞን ናት። ይሁን እንጂ ሴቶች ፈልገውና አቅደው ላጤ እናት የሚሆኑባቸውን ምክንያቶችንም ትጠቅሳለች። በማህበረሰቡ የሴት ልጅ ሕይወት በጊዜ የተገደበ እንደሆነና እስከተወሰነ ዕድሜያቸው ድረስ ማግባትና መውለድ ካልቻሉ ሕይወታቸው እንደተመሳቀለ ተደርጎ መወሰዱ ለእንዲህ ዓይነት ውሳኔ ከሚገፏቸው ምክንያቶች አንዱ እንደሆነ ትናገራለች ። አክሊል እንደምትለው በቀደመው ጊዜ አንዲት ሴት ሳታገባ ብትወልድ ለልጁ ዲቃላ የሚል ስያሜ በመስጠት እናትየዋ ትወገዝ ነበር። አሁን ላይ ግን ይህ ልማድ በትንሹም ቢሆን እየቀረ በመሆኑ ሴቶች እንዲህ ዓይነት ውሳኔ እንዲያሳልፉ አደፋፍሯቸዋል። ከዚህ ቀደም ሴቶች ሥራ በማይሰሩበትና የኢኮኖሚ ጥገኛ በሆኑበት ጊዜ ልጅ ወልደው ለብቻቸው ማሳደግ የማይታሰብ ነበር የምትለው አክሊል የሴቶች የኢኮኖሚ አቅም ማደግም ሌላኛው የላጤ እናትነት ምክንያት ነው ትላለች። እንደ የመብት ተሟጋቿ ከሆነ አንዲት ሴት በሕይወት ያየችው የትዳር ሕይወት እኩልነት የሌለበት፣ ሴቷ ጥገኛ የሆነችበት፣ ጥቃት የሚፈፀምበት፣ የኃይል ሚዛኑ እኩል ያልሆነበት፣ ሁኔታዎች በሙሉ ለሴት የማይመቹ ከነበሩ፤ ይህን ባለመፈለግ ላጤ እናት ልትሆን ትችላለች። ቢሆንም ግን እኩልነትን እያዩ ያደጉትም ሌሎች ምክንያቶች ወደ ውሳኔው ሊያንደረድሯቸው ይችላል። በተለያየ መልኩ የሴቶች አቅም እየጎለበተ ቢመጣም ሴቶች አቅማቸውንና የትዳር ሕይወታቸውን ማጣጣም ተስኗቸዋል የሚሉ እንዳሉ ያነሳንላት አክሊል የሴቶች አቅም እየጎለበተ በመጣ ቁጥር ኃላፊነት እየተደራረበባቸው ነው የመጣው፤ የቤቱን ሳንቀንስ ነው የውጪውን የጨመርንባቸው ስትል ትሞግታለች። ማጣጣም ተስኗቸዋል፤ አልተሳናቸውም ለማለት መጀመሪያ ያለባቸው ጫና ሊቀርላቸው ይገባል ትላለች። በተጨማሪም ላጤ እናት መሆንም ይህንን ጫና አያስቀረውም ብላለች። ልጁን ጡት ያጠባው አባት በአሃ የሥነ ልቦና አገልግሎት አማካሪ የሆኑት አቶ ሞገስ ገ ማሪያም በበኩላቸው ይህ ሁኔታ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተለይ በከተሞች አካባቢ የሚታይ ልማድ ሆኗል ይላሉ። የምክር አገልግሎት ፈልገው ወደ እርሳቸው የሚመጡ ላጤ እናቶች መኖራቸውንም ይገልፃሉ። ባለሙያው እንደሚሉት ጉዳዩ ከሥልጣኔ ጋር ተያይዞ የመጣ ነው። የኢኮኖሚና በራስ የመተማመን አቅም ሲያድግ የባልና የሚስት ግንኙነት ወደ ጎን ተትቶ ግንኙነቱ ኢኮኖሚ ላይ ብቻ የተመሠረተ ሊሆን ይችላል። በዚህም ምክንያት ሌሎች ማህበራዊ፣ አካላዊ፣ መንፈሳዊ እሴት ላይ የተመሰረተ ግንኙነት እንደማያስፈልግ አሊያም እንደ ሁለተኛ ደረጃ ተወስዶ ሴቶች ላጤ እናትነትን በፍላጎት ይመርጣሉ። ለንግግራቸው እኔ በኢኮኖሚ ጥሩ ደረጃ ስለደረስኩኝ፤ ከመጀመሪያውም ጀምሮ የወሰንኩት ሳላገባ ልጅ ለመውለድ ነው ያለቻቸውን ደንበኛቸውን በምሳሌነት ያጣቅሳሉ። እንዲህ ዓይነት ሃሳቦች የባልን የትዳር አጋርን ሚናና ትርጉም ከማዛባት ጋር የተያያዘም ነው ይላሉ አቶ ሞገስ። ባለሙያው እንደሚያስረዱት ላጤ እናትነትን ከኢኮኖሚ ጋር ብቻ ማያያዝ አይቻልም። ጉዳዩ ከራስ ስሜትና አስተሳሰብ ጋር እንዲሁም ካለፈ ታሪክ ጋር የሚያያዝም ነው። በመሆኑም ተፅዕኖውን ውስጣዊና ውጫዊ በማለት ይለዩታል። ውስጣዊ ተፅዕኖ ለአንድ ውሳኔ ትልቁን ድርሻ የሚይዘው የውስጥ ሁኔታ ነው ይላሉ የሥነ ልቦና ባለሙያው አቶ ሞገስ። ይህ የውስጥ ሁኔታ የውጫዊ ተፅዕኖ ነፀብራቅም ይሆናል። ለምሳሌ የውስጥ ፍላጎት፣ አመለካከት፣ ቤተሰብ፣ ጎረቤት ወይም አካባባቢ የሚያሳድረው ተፅዕኖ የውስጥ ውሳኔ ላይ ያደርሳል። ለራሳችን ያለን የጠነከረ አስተሳሰብና ለራስ የምንሰጠው ግምት ከመጠን ያለፈ ሲሆን ነገሮችን ሁሉ እኔ ማድረግ እችላለሁ፤ እኔ ማድረግ የምችል ከሆነ ሌላ አያስፈልገኝም የሚል ስሜት ይመጣል። በመሆኑም ይህንን ሚዛናዊ ማድረግ ካልተቻለ እዚህ ውሳኔ ላይ በቀላሉ ይደረሳል ይላሉ። ውጫዊ ተፅ ዕ ኖ እንደ አቶ ሞገስ ከሆነ ፆታን መሠረት ያደረጉ የህብረተሰብ አመለካከትም ለላጤ እናትነት ከፍተኛ ተፅዕኖ ያሳድራሉ። የሚፈጸሙ ጥቃቶች፣ የሚደርስባቸው ጫና፣ ሚዛናዊ ያልሆነ ሚና፣ የወንዶች የበላይነትን በመጥላትና በመፍራት፣ አካባቢያችን ያሉ ወይም በሚዲያ የምንሰማቸውና የምናያቸው አርአያዎች በሚፈጥሩት ተፅዕኖ ሴቶች እዚህ ውሳኔ ላይ እንዲደርሱ ያደርጋቸዋል። በሌላ በኩል ማህበረሰቡ በጉዳዩ ላይ ያለው አቋም ጠንካራ ካልሆነ ሴቶች ውስጣቸው የሚጠይቃቸውን ለማድረግ ዕድሉን ያገኛሉ። የራስ ማንነት እያሸነፈ ሲመጣ፤ አይሆንም የምንላቸው ነገሮች እየበዙ ይመጣሉ። ፍላጎታችንን ማስቀደም ይቀናናል። ስለዚህም ላጤ እናትነት የማህበረሰቡ እሴት እንደተሸረሸረ አንዱ ማሳያ ሊሆን እንደሚችልም ያክላሉ። በ ላጤ እናቶች ላይ የሚደርስ ጫና ያነጋገርናት እናት እንደምትለው ልጆችን ለብቻ ማሳደግ ከፍተኛ የሆነ የኢኮኖሚና የሃሳብ ጫና አለው። ከማህበረሰቡ፣ ከቅርብ ቤተሰብ እንዲሁም ከልጆች የሚደርሰው ጫናም ቀላል አይደለም። ልጆቸ ራስ ምታት እንኳን ሲያማቸው የማካፍለው ሰው አለመኖሩ በጣም ከባድ እንደሆነ ተመልክቸዋለሁ፤ ግን የራሴ መርህ ስላለና እርሱን መታገስና እንደ እናቶቻችን መቻል ስለማልችል ውሳኔውን ወስኛለሁ ትላለች። ይህች እናት አዘውትረው ከሚጠቀሱት ጫናዎች በዘለለ የወሲብ ሕይወትን ማጣትም ላጤ እናትነትን ይፈትናል ትላለች። ምንም እንኳን እያንዳንዱ ሰው የየራሱ ወሲባዊ ሕይወት ቢኖረውም እርሷ ግን ከሕይወት አጋር ውጪ ወሲብ መፈፀም እንደማትፈልግ ትናገራለች። የመብት ተሟጋቿ አክሊል እንደምትለው ውሳኔው የሚያሳፍር ድርጊት ነው ተብሎ በሚቆጠርበት ማህበረሰብ ውስጥ በፍላጎት ላጤ እናት መሆን ማህበራዊ ጫናው ከፍተኛ ነው። እነዚህን እናቶች የሚያግዝ አሠራር ከሌለ በስተቀር ሁሉም ነገር በአንድ ሰው ትከሻ ላይ ብቻ ስለሚወድቅ ኃላፊነቱ ከባድ ይሆናል። በመሆኑም የኢኮኖሚ ጫናውም ቀላል አይሆንም፤ ይህንን ለማስተካከል ሥራ መስራትና ጊዜን ሥራ ላይ ማጥፋት ይጠይቃል። የልጆች ኃላፊነት መደረብም ሁኔታውን ከባድ ያደርገዋል የምትለው አክሊል በዚህ ሂደት ውስጥ እናትየዋ ለእረፍት ማጣት ስለምትጋለጥ በተለያየ መልኩ ልትጎዳ እንደምትችል ታስረዳለች። ይህንን የተመለከቱ ጥናቶች በአፍሪካ ብዙም የሉም የሚሉት የሥነ ልቦና ባለሙያው ጉዳቱ ከፍ ያለ ነው ይላሉ። ጫናው ከአካላዊ፣ ማህበራዊ መንፈሳዊና ኢኮኖሚያዊ ደህንነት ይጀምራል። በመሆኑም ላጤ እናቶች ካገቡት ይልቅ ለተለያዩ ቀውሶች ሊዳረጉ ይችላሉ። ከእነዚህም መካከል፡ ኢኮኖሚያዊ ጫና ይበረታባቸዋል አካላዊ ጤንነታቸው፤ ከጭንቀትን መቋቋምና ከበሽታ መከላከል አንፃር ይዳከማል የስሜት ጥንካሬና መረጋጋት አይኖራቸውም ማህበራዊና መንፈሳዊ ድጋፋቸውም የላላ ይሆናል ከሥነ ልቦና አንፃር ብቸኝነት፣ ድባቴ፣ ተስፋ መቁረጥ፣ ዋጋ የለኝም ማለት፣ በራስ መተማመን ማጣትና ለማንነት ችግር እንደሚጋለጡም ባለሙያው በዝርዝር ያስረዳሉ። የልጆቹ አባቶችም ከሴቶቹ ባልተለየ መልኩ የችግሮቹ ተጋሪ ይሆናሉ። የስሜት ጫና፣ ድባቴ፣ ማህበራዊ ጫና ፣ የጥፋተኝነት ስሜት፣ ምቾት ማጣት፣ የፀፀት ስሜት ልጄን በሚገባው መልኩ ድጋፍና ክትትል እያደረኩለት አይደለም የሚሉ ሥነ ልቦናዊ ስሜቶች ይታያሉ። ወንዶች፤ ልጆቻቸውን ሙሉ ለሙሉ ከአጠገባቸው ማጣት ብቻም ሳይሆን በሥነ ልቦና አገልግሎት ውስጥ ገና ለገና እንፋታለን ብለው ሲያስቡ ሚዛናቸውን መሳትና ከፍ ወዳለ የሥነ ልቦና ቀውስ ውስጥ እንደሚገቡም ባለሙያው ያክላሉ። በልጆች ላይ ምን ተፅ ዕ ኖ ያ ሳድራል በተለይ ልጆች እድሜያቸው ከፍ እያለ ሲሄድ ለብቻ ማስተዳደር ፈታኝ ነው የምትለው ይህች እናት በቤት ውስጥ ኃላፊነትን በማከፋፈል በሕይወታቸው ውስጥ ሚና እንዲኖራቸው በማድረግ ፈተናውን መቋቋም ችላለች። ቤታችን ፓርላማ ይመስላል፤ ልጆቼ ተነጋግረው ወስነው እኔ ጋር የሚመጡት ለማፅደቅ ነው፤ በሁሉም ነገር ተሳታፊ ናቸው ትላለች። ይህም እነርሱን እንደውም ይበልጥ ጠንካራ እንዳደረጋቸውና ሴት ብቻዋን ልጆች ማሳደግ ትችላለች፤ በማለት እርሷን እንደ አርአያ ማየት እንደጀመሩ ታስረዳለች። በተለይ ወንድ ልጇ በእርሷ መኩራት እንደሚሰማው ትናገራላች። የምታስማማበት ጉዳይ በትዳር ውስጥ ሆኖ ልጆችን በተገቢው መንገድ ማሳደግ መተኪያ እንደሌለው ነው፤ ነገር ግን ትዳር ለመያዝ ተብሎ አሊያም ያልሆነ ትዳር ይዞ ሕይወትን መግፋት ደግሞ የማታምንበት ጉዳይ። የሴቶች መብት ተሟጋቿ አክሊል ቤተሰብ የሚባለው ትርጓሜ ከድሮው በተሻለ ተቀይሯል ትላለች። በመሆኑም ልጆች የአባትና የእናትን ሚና ካለማግኘት በበለጠ ማህበረሰቡ የሚያደርስባቸው ጉዳት ያይላል ትላለች። በተቃራኒው አቶ ሞገስ ልጆች የአባታቸውንና የእናታቸውን ሚና እያዩ ባለማደጋቸው ለተለያዩ የሥነ ልቦና ችግሮች ይዳረጋሉ ይላሉ። በመሆኑም ክሊኒካል ድብርትና ጭንቀት እና ባህሪያዊ የሥነ ልቦና ችግሮች ይታዩባቸዋል ይላሉ። እንደ ባለሙያው ገለፃ ከወንዶች ይልቅ ሴቶች በብዛት ለእንዲህ ዓይነት የሥነ ልቦና ችግር የሚዳረጉ ሲሆን የሚያጋጥማቸውም ክሊኒካል የሚባለው የሥነ ልቦና ችግር ነው። ወንዶች ደግሞ ባህሪያዊ ችግር ያጋጥማቸዋል፤ ከሁኔታዎች ጋር ተስማምቶ መኖር ይቸግራቸዋል። ችግሮቹ እንደ እናቶቹ ባህሪ የሚወሰን ቢሆንም በትምህርት፣ በሥራና በማህበራዊ ስኬቶቻቸው ላይ ተፅዕኖ ያሳድርባቸዋል ብለዋል። አቶ ሞገስ ላጤ እናቶች ሁለት ባህሪ አላቸው ይላሉ። አንደኛው ልጆቻቸው ሕይወት ውስጥ ጥሩ ድርሻ ያላቸው፣ ፍቅርና እንክብካቤ በጥሩ ሁኔታ የሚሰጡ ሲሆኑ ሌላኛው ደግሞ ልጆቻቸውን ችላ የሚሉና በልጆቻቸው ሕይወት ውስጥ የማይገቡ ናቸው። ይሁን እንጂ በሁለቱ የተለያየ ባህሪ የሚያድጉ ልጆች ለተለያዩ ሥነ ልቦና ችግሮች መዳረጋቸው አይቀርም። ጥሩ ድርሻ ያላቸው እናቶች እንክብካቤና ፍቅራቸው ከልክ ያለፈ ስለሚሆን ልጆች ለጥገኝነት መንፈስ ይጋለጣሉ። በሌላ በኩል ግድ የለሽ በሆኑት እናቶች የሚያድጉት ደግሞ ማግኘት ያለባቸውን የስሜት ደህንነት ስለማያገኙ ቀደም ብለው ለተጠቀሱት የሥነ ልቦና ችግሮች ይዳረጋሉ። ለምክር አገልግሎት ወደ እርሳቸው ቢሮ ጎራ ከሚሉት ላጤ እናቶች አብዛኞቹ ስሜታቸው ተመሳሳይ መሆኑንና ልጆቻቸው ላይም የድብርት ስሜት ማየት እንደቻሉም ባለሙያው አካፍለውናል። የሚገጥማቸውን ተግዳሮቶች እንዴት ይፍቱት በተለያየ ምክንያት ልጆቻቸውን ብቻቸውን የሚያሳድጉ እናቶች የሚገጥሟቸውን ተግዳሮቶች እንዴት ሊቋቋሟቸው እንደሚችሉ የሥነ ልቦና ባለሙያው ይመክራሉ። ጤናማ ስሜትና ጤናማ አካል እንዳላቸው ማረጋጋጥ፣ ከውስጥ ግጭት ነፃ መሆን፤ ፍርሃት ካላቸው ለልጆቻቸው እንዳያስተላልፉ መጠንቀቅ ከልጆች ጋር ደረጃ በደረጃ፤ እንደ ዕድሜያቸው ሁኔታ ያለውን ሁኔታ በግልፅ ማሳየት እና ልጆች ከአባታቸው ጋር ግንኙነት ሊያስፈልግ እንደሚችል በማመን ከአባታቸው ጋር እንዲገናኙ እድል ማመቻቸት የእነርሱንም ሆነ የልጆቻቸውን ሕይወት በተወሰነ መልኩም ቢሆን ቀላል ያደርገዋል። በመጨረሻም ብዙ ጊዜ ላጤ እናቶች በኢኮኖሚ፣ በአስተሳሰብ፣ በትምህርት የተሻሉ ናቸው ይባላል። ይህንንኑ ጥያቄ ለሴቶች መብት ተሟጋቿ አክሊል አንስተን ነበር። ለብቃት ሰፊ ትርጓሜ በመኖሩ እነዚህ ሴቶች ብቁ ናቸው አይደሉም ማለት አልችልም ትላለች። ይሁን እንጂ ሰዎች የሚወስኑበት መንገድ ቢለያይም ልጅ ካልወለድኩ ሴት አይደለሁም፤ ስለዚህ ጊዜዬ ሳያልፍ ልጅ መውለድ አለብኝ የምትል ሴት ብቁ እንደሆነች አላምንም፤ ምርጫ ግን ነው ስትልም ታብራራለች። ምንም እንኳን ውሳኔው ላይ በምን ምክንያት ተደረሰ የሚለው ወሳኝ ቢሆንም የአንድ ሰው ዋጋው የሚለካው በልጅ መኖርና አለመኖር አይደለም። በመሆኑም ሴትነቷ የሚለካው ልጅ በመውለድ አቅምና ላጤ እናት በመሆን አለመሆኑን በመግለፅ የግል አስተያየቷን ሰጥታለች። ከዚህ ዜና በተጨማሪ
አንበሳዋ እናት፡ የልጃቸውን ደፋሪ የገደሉት እናት ነጻ ወጡ
ኤፕረል ማጋሪያ ምረጥ አጭር የምስል መግለጫ አንበሳዋ እናት ኖኩቦንጋ ኳምፒ ኖኩቦንጋ ኳምፒ በደቡብ አፍሪካ አንበሳዋ እናት በመባል የታወቁት ልጃቸውን ከደፈሩ ሦስት ወንዶች መካከል አንዱን ገድለው ሌሎቹን ካቆሰሉ በኋላ ነው። በግድያ ወንጀል ክስ የተመሰረተባቸው ቢሆንም በሕዝብ ድምፅ ምክንያት ክሱ ተነስቷል። ነገሩ የጀመረው እኩለ ሌሊት ላይ የስልክ ጥሪ ኖኩቦንጋን ከእንቅልፍ ሲቀሰቅሳቸው ነበር። የደወለችውም ሴት ኖኩቦንጋ ሲፎካዚ የተባለችው ሴት ልጃቸው በሚያውቋቸው ሦስት ወንዶች መደፈሯን በዚያ ሌሊት ነበር የነገረቻቸው። ኖኩቦንጋ የመጀመሪያ እርምጃቸው ፖሊስ መጥራት ነበር፤ ነገር ግን የፖሊሶቹ ስልክ አይመልስም። በጊዜው ልጃቸውን መርዳት የሚችሉት እራሳቸው ብቻ ነበሩ። በጣም ፈርቼ ነበር ግን ልጄ ናት፤ መሄድ ነበረብኝ ይላሉ እናት ኖኩቦንጋ። እዚያ እስክደርስ ትሞታለች ብዬ አስቤ ነበር። ምክንያቱ ደግሞ እኛን ስለሚያውቁን እንዳትናገር ፈርተው በሕይወት አይለቋትም ብዬ አስቤ ነው። በጊዜው ሲፎካዚ ጓደኞችዋን ለማግኘት ነበር እግሯን ወደዛች መንደር የመራቸው። በቆይታዋም ጓደኞችዋ በተኛችበት ለብቻዋ ጥለዋት በወጡበት አጋጣሚ ነበር የጠጡት ወንዶች ከተኛችበት ገብተው ጥቃት ያደረሱባት። በመጨረሻ ላይ ሳትስመኝ መሄዷ ይቆጨኛል እናት ቢላ ይዤ የሄድኩት እራሴን እዚያ እስክደርስ ባለው መንገድ ላይ ለመከላከል ብዬ ነበር ሲሉ ኖኩቦንጋ ሁኔታውን ያስታውሳሉ። ከቢላው ጋር ስልኬን ለብርሃን ብዬ ይዤ ነበር። ልጃቸው ወደ ነበረችበት ቤት ሲደርሱ ስትጮህ ሰሟት፤ ቤት ውስጥ ሲገቡም አንዱ ወንድ ልጃቸውን ሲደፍራትና ሌሎቹ ሁለት ወንዶች ደግሞ ሱሪያቸው ወልቆ ተራቸውን ሲጠባበቁ እንዳኟቸው ይናገራሉ። በጣም ስለፈራሁ በር ላይ ቆሜ ምን እያደረጉ እንደሆነ ጠየኳቸው። እኔ እንደሆንኩ ሲያውቁ በቁጣ ተንደርድረው ወደ እኔ መጡ፤ ያኔ ነው እራሴን መከላከል እንዳለብኝ የገባኝ። ክሱን ሲከታተል የነበረው ዳኛ ኖኮቦንጋ ልጃቸው ስትደፍር በአይናቸው ማየታቸው በጊዜው በጣም ስሜታዊ አድርጓቸዋል ብለዋል። ኖኩቦንጋም በጊዜው ይዘውት የነበረውን ቢላ በመጠቀም አንዱን ደፋሪ ገድለው ሌሎቹን በቆሰሉበት ትተው ልጃቸውን በቅርብ ወደ ሚገኝ ጎረቤት ወሰዷት። ፖሊሶችም ከቦታው ደርሰው ቦኩቦንጋን በቁጥጥር ስር ካደረጓቸው በኋላ በአቅራቢያ ወደ ሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ወሰደወቸው። ስለ ልጄ እያሰብኩ ነበር፤ ካዳንኳት በኋላ ስለእሷ ምንም አልሰማሁም። በጣም አስጨናቂ ጊዜ ነበር ይላሉ። አጭር የምስል መግለጫ ልጅና እናት እናትዋ ወደ እስር ቤት ሲወሰዱ ሲፎካዚ ሆስፒታል ሆና ስለእናትዋ እያሰበች ነበር። በፍርድ ቤት ተወስኖባት ለዓመታት የምትታሰር ከሆነ እኔ ቅጣቷን እቀበልላታለሁ እያልኩኝ አስብ ነበር ትላለች። ሲፎካዚ በጊዜው ስለተፈጠረው ነገር እናትዋ ከነገሯት ነገር ውጪ ምንም አታስታውስም ነበር። በጊዜውም እናትና ልጅ አንዳቸው የአንዳቸው ደጋፊ ነበሩ። ቡህሌ ቶኒስ የኖኩቦጋ ጠበቃ ስትሆን ከጥቃቱ አንድ ሳምንት በኋላ ስታገኛቸው እናትና ልጅ በጣም ተስፋ ቆርጠው እንደነበር ታስታውሳለች። ኖኩቦንጋ በጭንቀት ውስጥ ነበረች ትላለች። በጣም ድሃ የሆኑ ሰዎችን ስታገኚ ገንዘብ ስለሌላቸው እናትየዋ ወደ እስር ቤት የምትሄድ ይመስላቸዋል። ይህ ደግሞ ጥብቅና የሚቆምላቸው ሰው አለ ብለው ሰለማያስቡ ነው። ቡህሌ ኖኩቦነጋ ክሱን ማሸነፍ እንደምትችል እርግጠኛ ብትሆንም ቀላል እንደማይሆን ገምታለች። ሁለቱም ግን ያልጠበቁት ነገር ቢኖር የማህበራዊ ሚዲያ የሚያደርግላቸውን ድጋፍ ነበር። በደቡብ አፍሪካ የአስገድዶ መድፈር ጥቃቶች ብዙም የማህበራዊ ሚዲያ ሽፋን አይሰጣቸውም፤ ነገር ግን የኖኩቦንጋ ድርጊት እናት ልጇን ለመከላከል ያላትን አቋም ማሳያ ነው በማለት የማህበራዊ ሚዲያውን ቀልብ ሳበ። የልጃቸውን ማንነት ላለመግለፅ ሲባል የኖኩቦንጋን ስም መጥቀስ ባልተቻለበት ጊዜ አንድ የመገናኛ ብዙሃን ተቋም አንበሳዋ እናት ብሎ ምስላቸውን ሴት አንበሳ ከልጆችዋ ጋር አድርጎ ይፋ አደረገው። ይህም ስም በመላ አገሪቷ አስተጋባ። መጀመሪያ ስሙን ስሰማ አልወደድኩትም ነበር፤ ልክ ግን የጀግንነት ምሳሌ መሆኑን ሳውቅ በጣም ደስ አለኝ ይላሉ እናት። የደቡብ አፍሪካ ሕዝብ የኖኩቦንጋን ክስ በመተቸት የህግ አማካሪ ጠበቃ እንዲኖራት ገንዘብ አሰባሰቡ። ወደ ፍርድ ቤት ስሄድ ስለፈራሁ ጠዋት ተነስቼ ፀለይኩኝ ይላሉ። ኖኩቦንጋ ፍርድ ቤት ሲደርሱ በሰዎች ተሞልቶ ነበር ያገኙት። ከመላዋ ደቡብ አፍሪካ የተሰባሰቡ ሰዎች ነበሩ። ለሰዎቹ አመሰግናለሁ እያልኩኝ እነሱ ሊደግፉኝ በመምጣታቸው በተስፋ ተሞላሁ። ፍርድ ቤት ስደርስ ክሱ እንዲነሳ ተወሰነ። በጣም ደስ አለኝ፤ ያኔ ዳኛው እኔ ሰውን የመግደል ሃሳብ እንዳልነበረኝ እንደተረዳ ገባኝ። ቡህሌ ቶኒስ የፍርድ ቤቱ ውሳኔ ሲፎካዚ ላይ የፈጠረውን ስሜት ታስታውሳለች። ፍርድ ቤቱ ክሱን እንዳነሳ ኖኩቦንጋ ወደ ልጇ ደወለች። ለመጀመሪያ ጊዜ ነበር ሲፎካዚ ስትስቅ የሰማኋት ያኔ ነበር። እሷም ለእናትዋ ወንዶቹ እንዲታሰሩ እንደምትፈልግም ነገረቻት ትላለች። ይህ ፍላጎቷ እውን እንዲሆን ከዓመት በላይ መጠበቅ ነበረባቸው። ከዚያም ባለፈው የታህሳስ ወር ላይ ሁለቱ ወንጀለኞች የ ዓመት እስራት ተወሰነባቸው። ሲፎካዚ በውሳኔው ደስተኛ ነኝ፤ አሁን ደህንነት ይሰማኛል ነገር ግን የእድሜ ልክ እስራት ይገባቸው ነበር ትላለች። ልክ ክሱ ሲጠናቀቅ ሲፎካዚ ሌሎች የዚህ ዓይነት ጥቃት ሰለባ የሆኑ ሴቶችን ለመደገፍ በማለት ማንነትዋን ለህዝብ ይፋ አድርጋለች። ኖኩቦነጋ በበኩላቸው በሚያስገርም ሁኔታ ልጃቸውን የደፈሩት ሰዎች ወደፊት ከእስር ሲወጡ መልካም ነገር ያደርጋሉ፣ ምሳሌም ይሆናሉ ብለው ተስፋ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል። ተያያዥ ርዕሶች
ሴቶችና ወንዶች በምጣኔ ኃብቱ እኩል መብት ያላቸው የት ነው
ማርች በአለማችን ስድስት ሃገራት ብቻ ናቸው ለሴቶችና ለወንዶች እኩል ህጋዊ የምጣኔ ኃብት መብት የሰጡት። እነማን ናቸው የአለም ባንክ አዲስ ባወጣው ሴቶች፣ ቢዝነስ እና ህግ በተባለ መግለጫው ላይ የሴቶችና የወንዶችን የኢኮኖሚ እኩልነት ሙሉ ለሙሉ መፍጠር የቻሉት ከ ሃገራት ስድስት ብቻ ናቸው ብሏል። በዋሽንግተን መቀመጫውን ያደረገው ተቋም የ ዓመታት ገንዘብ ነክና ህጋዊ የሆኑ በሴቶችና ወንዶች መካከል እኩልነት እንዳይሰፍን የሚያደርጉ እንደ በነጻነት የመንቀሳቀስ፣ እናትነት፣ የቤት ውስጥ ጥቃትና ንብረት አስተዳደርን የመሳሰሉ መረጃዎችን ተመልክቷል። በአለም ባንክ መስፈርት መሰረት በእነዚህ መስኮች ላይ የሁለቱን ፆታዎች እኩልነት ሙሉ በሙሉ ማስፈን የቻሉት ስድስት ሃገራት ቤልጂየም፣ ዴንማርክ፣ ፈረንሳይ፣ ላቲቪያ፣ ሉክዘምበርግና ስዊድን ናቸው። ሃገር ቤልጂየም፣ ዴንማርክ፣ ፈረንሳይ፣ ላቲቪያ፣ ሉክዘምበርግና ስዊድን ኦስትሪያ፣ አየርላንድ፣ፖርቹጋል፣ ስፔንና እንግሊዝ በዓለም አቀፍ ደረጃ ሴቶች በአማካይ በመቶ የሚሆነውን ለወንዶች የተሰጠ ተመሳሳይ መብት እንደሚጠቀሙ መረጃው ያሳያል። ከቦታ ቦታ ያለው ያለ ልዩነት አማካይ ውጤቱ እንደየቦታው ይለያያል። ለምሳሌ በአውሮፓና መካከለኛው እስያ በመቶ ሲሆን በመካከለኛው ምስራቅ እና ሰሜን አፍሪካ ደግሞ ወደ በመቶ ዝቅ ይላል። አሜሪካ በመቶ የሚሆን ውጤት ቢኖራትም ከመጀመሪያዎቹ ሀገራት ውስጥ መካተት አልቻለችም። ህጎቿ የሴቶችን መብት በጣም የሚገታው ሳዑዲ አረቢያ ደግሞ በመቶ በሆነ ውጤት የዝርዝሩ መጨረሻ ደረጃን ይዛለች። የመጀመሪያ ስራዋን ከጀመረች አንዲት የ ዓመት ወጣት ወይም ስራዋን እየሰራች ልጆቿን ለማሳደግ ጥረት ከምታደርገው እናት እስከ ጡረታ መውጫዋ የደረሰባትን ሴትን ውሳኔ ታሳቢነት አድርጎ የተሰራው ጥናት ሴቶች የሚወስዷቸው ውሳኔዎች እንዴት በህግ ተፅዕኖ ስር እንደሆኑ ተመልክቷል። በማለት ክሪሰታሊና ጂኦርጂቫ የአለም ባንክ ጊዜያዊ ፕሬዚዳንት ተናግራለች። ብዙ ህግና ደንቦች ሴቶች የስራ መስኩን እንዳይቀላቀሉ ወይም የራሳቸውን ቢዝነስ እንዳይጀምሩ ይከለክሏቸዋል። ይህ ሴቶችን በኢኮኖሚ የማግለል ሂደት በኢኮኖሚው ውስጥ የመሳተፍ እና የስራ ሃይሉን መቀላቀል ላይ ዘላቂ የሆነ ጠባሳ ያስከትላል። መግለጫው በአንዳንድ ሃገራት የተወሰደውንም አበረታች ውሳኔ አካቷል። የአለም ባንክ ባለፉት ዓመታት ሃገራት የፆታ እኩልነትን የሚያሰፍኑ ህግና ደንቦችን ማፅደቃቸውን ገልጿል። ለሴቶች የተከለከለ ተራራን የወጣችው የመጀመሪያ ሴት ሴቶችን በስራ ቦታ መጠበቅ እነዚህ ለውጦች በ ሀገራት የሚገኙ ሴቶችን በስራ ቦታ ከሚደርሱ ጾታዊ ጥቃቶች መከላከል ያስቻሉ ሲሆን የዛሬ አስር ዓመት ከነበረው ቢሊዮን ተጨማሪ ሴቶችን መከላከል ተችሏል። ከሰሃራ በታች ያሉ ሃገራት ባለፉት ዓመታት ብዙ የፆታ እኩልነትን የሚያሰፍኑ የህግ ለውጦችን ያደረጉ ሃገራት ናቸው። የወርልድ ባንክ ዘገባ የሴቶችን ሙሉ የስራ ህይወት ያጠና ሲሆን ስራ ከመፈለግ ጀምሮ፤ ቢዝነስ ማቋቋምን እና ጡረታ የማግኘት እድላቸውን አካቷል። በአለም አቀፍ ደረጃ ሃገራት አባቶች ልጅ ሲወልዱ የስራ ፈቃድ እንዲወስዱ የሚፈቅድ ህግ እና የሚሆኑት ደግሞ በቤት ውስጥ ሴቶች ላይ የሚደርስ ጥቃት ላይ ጠበቅ ያለ ህግ አፅድቀዋል። የፆታ እኩልነትን ለማስፈን ህግ እና ደንቦችን ብቻ ማፅደቅ እና መቀየር በቂ እንዳልሆነ እናውቃለን። ህጎቹ መተግበር አለባቸው። ይህ እንዲሆን ደግሞ የመሪዎች ድጋፍ፣ የሁለቱም ፆታዎች ንቁ ተሳትፎ እና ለረጅም ጊዜ ተይዘው የቆዩ ባህላዊ አመለካከቶችን መቀየር ያስፈልጋል። ብላለች ክርስታሊና ጂኦርጂቫ። በመጨረሻም መረጃው እንደሚያሳየው ህጎች ሴቶችን የሚያጠናክሩ እንጂ ማሳካት ከምንችላቸው ነገሮች ወደ ኋላ የሚጎትቱን መሆን እንደሌለባቸው ነው። ብላለች። ተያያዥ ርዕሶች
በፕሮቴስታንት እምነት ተከታይነቱ ለእስር ተዳርጎ የነበረው ኤርትራዊ ህይወቱ አለፈ
መስከረም ይህንን ለማጋራት በ ትዊተር ይህንን ለማጋራት በ ዋትስአፕ የፕሮቴስታንት እምነት ተከታይ በመሆኑ ለእስር ተዳርጎ የነበረው ኤርትራዊው ተኪኤ ተስፋ ዮሃንስ በእስር ቤት ህይወቱ ማለፉን የእስረኞች የእምነት መብት ተሟጋች ድርጅት ሪሊዝ ኤርትራ ዳይሬክተር ዶ ር ብርሃነ አስመላሽ ለቢቢሲ ገልፀዋል። በኤርትራዋ መዲና አስመራ በአንድ የግል መኖሪያ ቤት መቶ አርባ አንድ የሚጠጉ የእምነቱ ተከታዮች መንፈሳዊ ስብስባ ሊያካሂዱ ሲሉ የተያዙት ከአራት ወራት ገደማ በፊት ነበር። ተኪኤ በወቅቱ በቁጥጥር ስር ከዋሉት ውስጥ አንዱ እንደነበር ዶ ር ብርሃነ ያስረዳል። ኤርትራ የሃይማኖት እሥረኞችን ፈታች ግለሰቦቹ በሙሉ ዓዲ ዓቤቶ ወደተሰኘው እስር ቤት ተወስደው የነበረ ሲሆን፤ የተወሰኑት ሊፈቱ ችለዋል። የአምሳ አምስት እድሜ ያለው ተኪኤ ባለትዳርና የሶስት ልጆች አባት ሲሆን ጠንካራ ሰራተኛም እንደነበር ጓደኛው ሃኒባል ዳንኤል ይናገራል። በአካል ጉዳኝነቱ ሳይበገር ሁለት አይነት ስራ እየሰራ ልጆቹንም እያሳደገ እንደነበር ምስክርነቱን ሰጥቷል። በመቀሌ የከተሙት ኤርትራውያን በእርግጥ ከተለያየን ረዥም ጊዜ ሆኖናል። ሆኖም በማውቀው ደረጃ ጠንካራ ሰራተኛና ምሬትም የማያውቅ ሰው ነበር ብሏል። ከኤርትራ ባለስልጣናት መረጃ ማግኘት ከባድ እንደሆነ የሚገልፀው አቶ ሃኒባል መሞቱ እንጂ ህይወቱ ከማለፉ በፊት ህክምና እርዳታ ይደረግለት አይደረግለት፤ እንዲሁም መቼ እንደሞተ የሚታወቅ ነገር የለም በማለት አስረድቷል። በተመሳሳይም ከጥቂት ወራት በፊትም ፍፁም የተባለ ሌላ ወንጌላውያን እምነት ተከታይ በዳህላክ እስር ቤት ህይወቱን እንዳጣ ይናገራል። ቢቢሲ ማስተባበያ
ሴተኛ አዳሪነት ባህል የሆነበት ማህበረሰብ
ማርች ስለ ማጋራት ተጨማሪ ያጋሩ ማጋሪያ ምረጥ አብዛኛው የህንድ ማህበረሰብ ከሴት ይልቅ ወንድ ልጅ እንዲወለድለት ነው የሚፈልገው። ሂና ስትወለድ ግን ቤተሰቦቿ በተለየ መልኩ ነበር የተደሰቱት። ደስታቸው የመነጨውም ባልተለመደ መልኩ ወደፊት ምን እንደሚያሰሯት በማሰብ ነበር። ራቅ ባለ የህንድ አካባቢ ባቻራ ከተባለው ማህበረሰብ የተገኘችው ሂና ህይወቷን የምትመራው በወሲብ ንግድ ነው። ለብዙ መቶ ዓመታት የዚህ ማህበረሰብ አባላት መጀመሪያ የሚወለዱ ሴት ልጆቻቸውን ከ እስከ ዓመት ሲሞላቸው ለገንዘብ ገላቸውን እንዲሸጡ ይገፏፏቸዋል። የመጀመሪያዋ ሴት ልጅ እድሜዋ ሲገፋ ቀጥላ የምትመጣው ሌላኛዋ የቤተሰቡ ሴት ልጅ እሷን ተክታ ወደ እዚህ ሥራ ትሰማራለች፤ ይህ ደግሞ ሁሉም ተቀብሎት የሚተገብረው የማህበረሰቡ ልምድ ነው። ከትውልድ ትውልድ ሲተላለፍ በኖረው በዚህ ባህል የሚገኘውን ገንዘብ በሙሉ በሚባል ደረጃ የሚጠቀሙት ወንዶቹ ወይም የቤተሰቡ አባወራ ነው። አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ሴቶቹ ሥራቸውን በትክክል መስራታቸውን የሚቆጣጠሩት አባቶች አልያም ወንድሞቻቸው ናቸው። ሌላው ቢቀር የዚህ ማህበረሰብ ሴቶች ሲዳሩ ቤተሰቦቻቸው ለጥሎሽ ረብጣ ገንዘብ ይጠይቃሉ። ምክንያቱ ደግሞ ወደ ወንዱ ቤተሰብ ከሄደች በኋላ ብዙ ገንዘብ እንደምታስገኝላቸው ስለሚታሰብ ነው። ምንም አማራጭ የለኝም ሂና ከተወለደችበት ጊዜ አንስቶ እድሜ ልኳን ለዚህ ተግባር ስትዘጋጅና ስትለማመድ ነው ያደገችው። ገና የ ዓመት ታዳጊ ሳለሁ ወደዚህ ሥራ ተገድጄ ገባሁ። ትምህርቴን ማቋረጥ ነበረበኝ፤ ምክንያቱም የእናቴንና የአያቴን ፈለግ መከተል ግዴታዬ ነበር ስትል ለቢቢሲ ተናግራለች። በእያንዳንዱ ቀን ከገጠር ሃብታሞች እስከ የከባድ ተሽከርካሪ ሾፌሮች ድረስ ደንበኞቿን ታስተናግዳለች። ልክ ዓመት ሲሞላኝ የምሰራው ሥራ ትክክል እንዳልሆነ ይሰማኝ ጀመር። በጣም እናደድ ነበር፤ ግን ምን አማራጭ አለኝ እኔ ይህንን ሰርቼ ገንዘብ ካላገኘሁ ቤተሰቤ በምን ይኖራል ቤተሰቤ ይራባል። የባቻራ ማህበረሰብ አባላት ከሌሎቹ የህንድ ማህበረሰቦች ጋር ሲነጻጸሩ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ሲሆን፤ ገንዘብ ነክ ጥያቄዎቻቸውን የሚመልሱት ሴቶቹ ላይ በመተማመን ነው። በአካባቢው የሚንቀሳቀስ አንድ የበጎ አድራጎት ድርጅት ውስጥ የሚሰራው አካሽ ቾሃን እንደሚለው በዚህ ሥራ ከሚሰማሩት ሴቶች አንድ ሦስተኛ የሚሆኑት ከአስራ ስምንት ዓመት በታች ናቸው። ታዳጊ ህጻናቱ በአካባቢው በሚገኝ የጠፍር አልጋ ላይ ለብቻቸው ወይም ተሰብስበው በመቀመጥ ደንበኞቻቸውን ይጠባበቃሉ። በቅርበት ደግሞ አነስተኛ ሱቆች ይኖራሉ። ብዙ ጊዜ አንድ የቤተሰብ አባል በሱቋ ውስጥ ከደንበኞች ጋር ስለክፍያው መጠን ድርድር ያደርጋል። በድርድሩ መሰረትም አንድ ደንበኛ በአማካይ ከ እስከ ብር ድረስ ይከፍላል። ነገር ግን ከዚህ በፊት ከወንድ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት ያልፈጸመች ከሆነች ክፍያው እስከ ብር ድረስ ከፍ ሊል ይችላል። የህንድ ብሔራዊ ጋዜጣ ባወጣው መረጃ መሰረት ከ የማህበረሰቡ አባላት ላይ የደም ናሙና ተወስዶ በመቶ የሚሆኑት በደማቸው የኤች አይ ቪ ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል። ከመቶ ምናምን ፓርቲ ሴት የምናገኘው አንድ ወይም ቢበዛ ሁለት ሊሆን ይችላል ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ አብዛኞቹ ሴቶች ከሥራው ጋር በተያያዘ ያልተፈለገ እርግዝና ያጋጥማቸዋል የምትለው ሂና እራሷ ከጥቂት ዓመታት በፊት ሴት ልጅ እንደተገላገለች ትናገራለች። ብዙ ሴቶች ወዲያው ያረግዛሉ። ይሄ ሲታወቅ ብዙ ገንዘብ አግኝተው ልጃቸውን እራሳቸው እንዲንከባከቡ በሚል ምክንያት ከሌላ ጊዜው ተጨማሪ ደንበኛ እንዲያስተናግዱ ይገደዳሉ። አጭር የምስል መግለጫ ሂና የወሲብ ንግድ ውስጥ የሚሰተፉ ሴቶች ደግሞ እዚያው ማህበረሰባቸው ውስጥ አባል የሆነ ወንድ ማግባት አይችሉም። ሂና በጊዜ ብዛት ከአንድ በጎ አድራጎት ድርጅት ባገኘችው እርዳታ በመታገዝ ይህንን ልማድ ተፋልማ አሸንፋ መውጣት ችላለች። ነገር ግን አሁንም ብዙ ታዳጊ ሴቶች በዚሁ ልማድ ታስረው እንዳሉ ትናገራለች። በዚህ እርኩስ ልምድ ውስጥ ያለፈ ሰው ብቻ ነው መከራው ሊገባው የሚችለው። ሴቶቹ ምን እንደሚሰማቸው እኔ አውቃለው፤ ስለዚህ ይህንን ልምድ ለማስቀረት እሰራለሁ። የባቻራ ማህበረሰብ እስከ ሺህ የሚደርሱ አባላት ያሉት ሲሆን በመቶ የሚሆኑት ደግሞ ሴቶች ናቸው። የሴቶች ቁጥር ከፍተኛ የሆነበት ምክንያት ደግሞ ትንንሽ ሴት ህጻናት ታፍነው ወደዚህ አካባቢ ስለሚወሰዱ ነው። አካሽ እንደሚለው ባለፉት ጥቂት ወራት ብቻ የሚደርሱ ህጻናትን ከዚህ ንግድ ማዳን ችለዋል። ሌላው ቢቀር ለዚሁ ተግባር ታፍና ተወስዳ የነበረች የሁለት ዓመት ህጻን ወደ አሳዳጊ ቤተሰቦች እንድትላክ አድርገናል። የህንድ መንግሥትና የበጎ አድራጎት ድርጅቶች በሚሰሯቸው የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎች ምክንያት ይህ ተግባር እየቀነሰ የመጣ ይመስላል። ወጣት ሴቶች በወሲብ ንግድ መሳተፍ አንፈልግም እያሉ ቤተሰባቸውን መሞገት ጀምረዋል። አንዳንዶቹም ከአካባቢው ራቅ ብለው በመሄድ ሌላ ሥራ ማፈላለግ ጀምረዋል። ትምህርታቸው ላይ ማተኮር የጀመሩም አሉ። ሂና እሷን ከዚህ ህይወት ካወጣት የበጎ አድራጎት ድርጅት ጋር በመሆን ለውጥ ለማምጣት እየሰራች ነው። ሌሎች ታዳጊ ሴቶች ድጋፍ ማግኘት እንደሚችሉና ከወሲብ ንግድ መውጣት እንደሚቻል ለማሳየት የቻልኩትን ሁሉ አደርጋለው ብላለች። ተያያዥ ርዕሶች
የህጻናትን ዘረ መል ማስተካከል ክልክል ነው
ኖቬምበር ማጋሪያ ምረጥ የሰው ልጆች ተክሎችን ማዳቀልና እንደገና መፍጠር ይችላል። ይህ ብቻም ሳይሆን የእንስሳትን ተፈጥሮ መቀየርና የሰው ልጅ የዘረ መልን እስከ ማስተካከልም ተደርሷል። በቅርቡ አንድ ቻይናዊ ተመራማሪ የመንትዎችን ፅንስ ኤች አይ ቪ ኤድስ እንዳይዛቸው አድርጎ ውስጣዊ አወቃቀራቸውን አስተካክያለው ማለቱም የሰሞኑ ዜና ነው። ነገር ግን የሰው ልጅን ተፈጥሮአዊ የዘረ መል አወቃወር መቀየርና ማስተካከል በብዙዎች ዘንድ ተቀባይነት የሌለውና እንደውም እንደ ወንጀል የሚቆጠር ነው። ቻይናዊው ፕሮፌሰር እንደሚለው ከመንትዮቹ ሽል ውስጥ ለተለያዩ በሽታዎች ተጋላጭ ሊያደርጓቸው የሚችሉ ንጥረ ነገሮችን በማስወገድ ብቻ ኤች አይቪ በሽታ እንዳይዛቸው ማድረግ ችሏል። እንደዚህ አይነቶቹ የዘረ መል ጥናቶች አንዳንድ ከቤተሰብ የሚተላለፉ በሽታዎችንም ለማስቀረት ጥቅም ላይ እየዋሉ ነው። ነገር ግን ገና ባልተወለዱ ህጻናት ላይ የሚከናወነው የዘረ መል ማስተካከልና መቀየር ሂደት ለሚቀጥለው ትውልድ የሚተላለፍ ችግር ሊሆን እንደሚችል የሚሰጉ ብዙዎች ናቸው። በገዛ እራሳችን ምርምር በሽታን ብንፈጥርስ የሚሉም አልጠፉም። ብዙዎቹ ሙከራዎችም በሰዎች ላይ ባይደረጉ ይመርጣሉ። እንግሊዝ ውስጥ ተመራማሪዎች መወለድ የማይችሉ ጽንሶች ላይ የዘረ መል ማስተካከል እንዲያደርጉ የሚፈቀድላቸው ሲሆን፤ ምንም አይነት ችግር የሌለባቸውና ያለምንም ችግር መወለድ የሚችሉ ጽንሶች ላይ ግን ምርምሩን ማካሄድ ክልክል ነው። አሜሪካ ከዚህ ጋር በተያያዘ ቀለል ያለ ህግ ያላት ሲሆን፤ ጃፓን ደግሞ ምረምሩን ለመፍቀድ እያሰበች ነው ተብሏል። ቻይናዊው ሳይንቲስት የሚሰራበት ሸንዘን የሚገኘው ሳውዘርን ዩኒቨርስቲ ኦፍ ሳይንስ ኤንድ ቴክኖሎጂ ስለ ምርምሩ ምንም እንደማያውቅ ጠቅሶ በአስቸኳይ ምርመራ እንደሚጀምርም አሳውቋል። ልባችን ከእድሜያችን ቀድሞ ሊያረጅ እንደሚችል ያውቃሉ በቻይና ህግ መሰረት ገና ባልተወለዱ ህጻናት ላይ የዘረ መል ማስተካከያ ምርምሮችን ማድረግ ክልክል ነው። የሃገሪቱ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ምክትል ሚኒስተር ዡ ናንፒንግ እንደተናገሩት ዜናውን ሲሰሙ በጣም ደንግጠዋል። ሰውዬው የሰራው ምርምርም የቻይናን ህግ የጣሰ ህገወጥ ተግባር ነው ብለዋል። በለንደኑ ሴንት ጆርጅ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ የሚሰሩት ዶክተር ያልዳ ጃምሺዲ እንደሚሉት የዘረ መል ማስተካከል የተደረገባቸው ህጻናት ወደፊት ምን አይነት ችግሮች ሊገጥሟቸው እንደሚችል ማወቅ ከባድ ነው። ከዚህ ለየት ያለ ሃሳብ ያላቸው ደግሞ ምርምሩ ሊያመጣ የሚችለውን ችግር ካለማወቃችን በተጨማሪ ይላሉ፤ የዘረ መል ማስተካከል የተደረገባቸው ህጻናት ከሌሎች የተለዩ ተደርገው ሊቆጠሩ ይችላሉ ይላሉ። ይህ ደግሞ ከሌሎች የተለየ ጥቅም እንዲያገኙ አልያም እንዲገለሉ ሊያደርጋቸው እንደሚችል በመጥቀስ መቅረት አለበት በማለት ይከራከራሉ። አዲስ የፀረ ተህዋስ ዝርያ በአፈር ውስጥ ተገኘ ፅንሱ ላይ የተቀየረው የዘረ መል አይነት ወደፊት ለሚቀጥለው ትውልድ የሚተላለፍ እንደሆነ በመስጋትና በተፈጥሮ ጣልቃ መግባት መሆኑን በማሰብ ብዙዎች መከልከል አለበት ቢሉም፤ ቻይናዊው ሳይንቲስት ግን በሽታ ሳይከሰት በፊት ማስቀረት ምንድነው ችግሩ ባይ ነው። እ አ አ በ የተጀመረው የዘረ መል ማስተካከል ምናልባት ሃያላን ሰዎችን ለመፍጠር ጥቅም ላይ ውሎ በዓለማችን ያለውን የአቅምና የጉልበት ልዩነት ይበልጥ እንዳያሰፋው የሚሰጉም አልጠፉም። ተያያዥ ርዕሶች
ኤች አይ ቪን የሚከላከለው መድሃኒት ተስፋ ሰጪ ነው ተባለ
ሴፕቴምበር ማጋሪያ ምረጥ ዌልስ ውስጥ በሙከራ ደረጃ የሚገኘው የኤች አይ ቪ መከላከያ መድሃኒት ለማግኘት የሚደረገው ምርምር በበሽታው የመያዝ እድልን ለመቀነስ ሊረዳ እንደሚችል እየተገለጸ ነው። የመድሃኒቱን ውጤታማነት ለመፈተሽ ለበሽታው የመጋለጥ ከፍተኛ እድል አላቸው ለተባሉ የሙከራ ጥናቱ ተሳታፊዎች ከለፈው ዓመት ሐምሌ ወር ጀምሮ መድሃኒቱ መስጠት የተጀመረ ሲሆን፤ ከአንድ ዓመት በኋላ በተደረገላቸው ምርመራ ሁሉም ሰዎች ኤች አይ ቪ አልተገኘባቸውም። ይህም ውጤት እጅግ አስደሳችና በበሽታው ዙሪያ ያሉ መጠራጠሮችን የሚቀንስ ነው ተብሎለታል። አዲሱ የማዋለጃ ቦርሳ የእናቶችን ህይወት እየታደገ ነው ምርምሩን የሚያካሂዱት የህክምና ባለሙያዎች እንደገለጹት አብዛኛዎቹ የጥናቱ ተሳታፊዎች ላይ ሌሎች በግብረ ሥጋ ግንኙነት የሚተላለፉ በሽታዎች እንደተገኙባቸውና ከኤች አይ ቪ ነጻ መሆናቸው ደግሞ የመድሃኒቱን ውጤታማነት ያሚያሳይ ነው። መድሃኒቱ ፕሪ ኤክስፖዠር ፐሮፊላክሲስ የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል። በየቀኑ የሚወሰድ ሲሆን በሽታው ከአንድ ሰው ወደ ሌላ የመተላለፍ እድሉን እስከ በመቶ ድረስ ይቀንሳል ተብሏል። እስካሁን ድረስ በወሲብ ንግድ የሚተዳደሩና ሌሎች ለኤች አይ ቪ ተጋላጭ ነን ብለው የሚያስቡ በአሜሪካ፣ ካናዳ፣ አውስትራሊያና ፈረንሳይ የሚገኙ ሰዎች መድሃኒቱን መጠቀም ጀምረዋል። ተያያዥ ርዕሶች
የማትተነፍሰው ከተማ አዲስ አበባ
በዘውዲቱ ሆስፒታል የበሽታ መከላከልና መቆጣጠር ኃላፊ የሆኑት ዶ ር አስቴር ሸዋአማረም በኃላፊዋ ሀሳብ ይስማማሉ። ለኤች አይቪ ምርመራ ወደ ዘውዲቱ ሆስፒታል ከሚሄዱ መካከል እድሜያቸው ከ እስከ የሆነ አፍላ ወጣቶች መካከል የኤች አይቪ ቁጥሩ ከፍ ብሎ አንደሚታይ ይናገራሉ። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኤችአይቪ መከላከያና መቆጣጠያ ፅ ቤት ኃላፊ ሲስተር ብርዛፍ እንደሚሉት አዲስ አበባ ከጋምቤላ ቀጥሎ በከፍተኛ ሁኔታ የኤች አይቪ ስርጭት የሚታይባት ከተማ ናት። በጋምቤላ የኤች አይቪ የስርጭት መጠን መሆኑን አስታውሰው አንዳንድ የሀገሪቱ ከተሞች ላይም የስርጭት መጠኑ ከፍ ማለቱን ጠቅሰዋል። ለዶ ር አስቴር በከተማዋ በአፍላ ወጣቶች ያለው የኤች አይቪ የስርጭት መጠን ከፍ ማለት ምክንያት መዘናጋት ነው። ሲስተር ብርዛፍም ከዚህ የተለየ ሀሳብ የላቸውም፤ መንግስትና አጋር ድርጅቶች ኤች አይቪ ላይ የሚሰጡት የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርቶች መቀዛቀዛቸው በአዲሱ ትውልድ የስርጭት ምጣኔው ከፍ እንዲል ምክንያት መሆኑን አበክረው ገልፀዋል። ከዚህ ቀደም ወደ ህዝቡ ወጥተው ስለ ኤች አይቪ የሚያስተምሩ ቫይረሱ በደማቸው የሚገኝ ግለሰቦች ዛሬ አለመኖራቸውም በአሁኑ ወቅት ለተፈጠረው መዘናጋት አስተዋፆ እንዳለው ሲስተር ብርዛፍ ያምናሉ። ስለኤች አይ ቪ ኤድስ የሚነገሩ የተሳሳቱ አመለካከቶች በአሁኑ ወቅትም ከእነዚህ ግለሰቦች ጋር ለመስራት እቅድ መኖሩን አስረድተው አሁን ከተፈጠረው መዘናጋት የተነሳ አድልኦና መገለል እንደ አዲስ እያገረሸ ስለሆነ የከተማው አስተዳደር መደገፍ በሚገባቸው በኩል ደግፎ እንዲያስተምሩ እንዲያደረግ እንደሚያመቻቹ ተናግረዋል። የኤችአይቪ መከላከያና መቆጣጠያ ፅ ቤት ኃላፊዋ እንደሚሉት በከተማዋ ያለውን የኤች አይቪ የስርጭት መጠን አሳሳቢ የሚያደርገው በአፍላ ወጣቶች መካከል ያለው የስርጭት መጠን ከፍተኛ መሆኑ ነው። ለዚህም ኃላፊዋ እንደምክንያትነት የጠቀሱት ከስራ አጥነት ጋር ተያይዞ ያሉ ችግሮችን ነው። ስራ አጥነት ለኤች አይቪ የሚያጋልጡ ስፍራዎች እንዲውሉ ገፊ ምክንያት ነው የሚሉት ሲስተር ብርዛፍ በከተማዋ ያሉ የኢንዱስትሪና የሆቴሎች መስፋፋት ሌላው እንደምክንያት ያነሱት ነው። በከተማዋ የመጤ ባህሎች መስፋፋትም እንደሚታይ የገለፁት ሲስተር ብርዛፍ የራቁት ዳንስ ቤት፣ የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት፣ ጫት፣ ሺሻና ቡና ቤቶች መበራከታቸው ለኤች አይቪ መስፋፋት አስተዋፅኦ ማድረጉን ገልፀዋል። በአዲስ አበባ ከተማ የሚታየው የኮንስትራክሽን ስራዎች ላይ ለመሰማራት ከተለያዩ ከተሞች የሚመጡ ወጣቶች ቁጥር ከፍ ማለትም የስርጭቱ መጠን ከፍ እንዲል እንዳደረገው አብራርተዋል። ፅህፈት ቤታቸው በከተማዋ ለኤች አይቪ ተጋላጭ ብሎ የለያቸውን የከተማዋ የህብረተሰብ ክፍሎችን ሲዘረዝሩ በትምህርት ቤትም ሆነ ውጭ ያሉ ወጣቶች፣ የቀን ሰራተኞች፣ የከባድ መኪና የረዥም ርቀት አሽከርካሪዎች፣ በወህኒ ቤት የሚገኙ ታራሚዎች፣ በወሲብ ንግድ የተሰማሩ ግለሰቦች፣ እና በቅርቡ በተደረጉ ጥናቶች እንደታየው ደግሞ ባሎቻቸውን በፈቱ ሴቶች የስርጭት ምጣኔው ከፍ ያለ ነው። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶቹ በብዛት በሚገኙባቸው አካባቢዎች የትምህርት ስራውን ሊያውኩና ወጣቶቹን ለኤች አይቪ ሊያጋልጡ የሚችሉ መዝናኛዎችን ከትምህርት ቤት መራቅ አለባቸው የሚል አቋም ይዞ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ለመስራት እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ተናግረዋል። የአለም ጤና ድርጅት እኤአ በ አዲስ በቫይረሱ የሚያዝ ግለሰብ መኖር የለበትም የሚል ራዕይ አስቀምጧል። በኢትዮጵያ የኤች አይቪ የስርጭት መጠኑ በመቶ ነው። ተያያዥ ርዕሶች
አንድ አትሌት በህይወቱ የሚያስደስተው የአለም ሪከርድን መስበር ነው ዮሚፍ ቀጀልቻ
ማርች ማጋሪያ ምረጥ አሜሪካ ቦስተን ውስጥ በተካሄደ የአንድ ማይል ኪሎ ሜትር የቤት ውስጥ ውድድር ከ ዓመታት በፊት በሞሮኳዊው አትሌት ሂሻም አልገሩሽ ተይዞ የነበረውን ሪከርድ ኢትዮጵያዊው አትሌት ዮሚፍ ቀጀልቻ ሰብሮታል። ከትላንት በስቲያ እሁድ እለት በተደረገው በዚህ የቤት ውስጥ ውድድር ፡ ፡ በመግባት ሪከርዱን አሻሽሏል። በዚህ ውድድር ላይ አሜሪካዊው ጆኒ ግሬጎሬክ ፡ ፡ በመግባት በሁለተኛነት አጠናቋል። ሥልጣን ለደም ግፊት አጋልጦኛል ኃይሌ ገብረሥላሴ ሪከርድ መስበር በጣም ደስ ይላል፤ አንድ ሰው የሚሮጠው የሆነ ነገር ለማግኘት ነው። የሚለው አትሌቱ ለሯጭም ከፍተኛ ደረጃ እንደሆነ ይናገራል። አንድ አትሌት በህይወቱ የሚያስደስተው ነገር ኦሎምፒክ ማሸነፍና የአለም ሪከርድ መስበር ነው። ስለዚህ በጣም ደስ ብሎኛል። በማለት ለቢቢሲ ገልጿል። ሪከርድ በመስበሩ የሚያገኘው ገንዘብ ምን ያህል እንደሆነ ከቢቢሲ ለቀረበለት ጥያቄም ከዚህ ቀደም ሪከርድ የሚሰብር የሚያገኘውን ያህል እንደሆነ ተናግሯል። በአልግሩሽ ተይዞ የነበረውን ሬከርድ በአንድ ደቂቃ በአርባ አራት ሰከንዶች ያሻሻለው ዮሚፍ በሶስተኛው ሙከራ ሪከርድ መስበር እንደቻለም ተዘግቧል። ኤኤንሲ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽኑን ውሳኔ ዘረኛ ነው አለ የ አመቱ ዮሚፍ ከሶስት ሳምንታት በፊት ኒውዮርክ ውስጥ በተመሳሳይ ርቀት ውድድር ያደረገ ሲሆን፤ በወቅቱም በ ሴንቲ ሰከንድ ምክንያት ሪከርዱን ሳይሰብር ቀርቷል። በወቅቱ ስለነበረው ስሜትም አትሌቱ ለቢቢሲ ተናግሯል ያኔ በጣም ተሰምቶኝ ነበር፤ ውድድሩን ስጨርስ ዝቅ ብየ ቢሆን ኖሮ ሪከርዱን እሰብረው ነበር። የሚለው አትሌቱ በቀጣይነትም ረጅምና መካከለኛ ርቀት የመሮጥ እቅድ እንዳለው ተናግሯል። ትልቁ ሀሳቤ ከቤት ውጭ በአምስት ሺ ሜትር ሪከርድ መስበር ወይም ፈጣን ሰአት ማስመዝገብ እፈልጋለሁ ብሏል። ዮሚፍ ያስመዘገበው ሰአት በኢትዮጵያም ውስጥ ፈጣኑ ሲሆን ይህም በአማን ወቴ ፡ ፡ ተይዞ የነበረውን አሻሽሎታል ማለት ነው። ተያያዥ ርዕሶች
በአምስት የዓለም ዋንጫዎች ወርቅ እንዲመጣ ምክንያት ነኝ አትሌት ገብረእግዚአብሔር
ኦገስት ማጋሪያ ምረጥ አትሌት ገብረእግዚአብሔር ገብረማርያም ተወልዶ ያደገው በትግራይ ክልል በቀድሞዋ ሐውዜን፣ በአሁኗ ሳዕሲዕ ጻዕዳ እምባ ወረዳ ነው፤ ልዩ ስሟ ጻንቃኔት በተባለች አካባቢ ነው። በ ዓ ም የተወለደው ገብረእግዚኣብሄር፤ ገና ታዳጊ እያለ በ ዓመቱ ጊዜውም በ ዓ ም ሩጫን ሀ ብሎ የጀመረው። በዓለም አቀፍ ደረጃ ለመጀመርያ ጊዜ ኒው ዮርክ በተካሄደው ማራቶን ላይ ተሳትፎ የወርቅ ሜዳልያ አገኘ። ሥልጣን ለደም ግፊት አጋልጦኛል ኃይሌ ገብረሥላሴ ለቁጥር በሚያዳግቱ የተለያዩ ዓለም ዓቀፍ ውድድሮች በግሉም እንዲሁም በሃገርም ደረጃ ተሳትፎ ብዙ ወርቆችን ያስገኘ አትሌት ነው። በአሁኑ ወቅት ከሩጫው ባሻገር በአትሌቲክስ ፌዴሬሽንና በኦሎምፒክ ኮሚቴ ምክትል ኃላፊነት እያገለገለ ሲሆን፤በይፋ ጫማ ባይሰቅልም እምብዛም በሩጫ መድረክ ላይ ሲሳተፍ እየታየ አይደለም። ለዚህም ገብረእግዚአብሔር ምላሽ አለው ሩጫ እንደሚታውቀው ብዙ ትኩረት የሚጠይቅ ነው። ቢዝነስን ጨምሮ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ እሳተፋለሁ። ከዚህ በተጨማሪም በዕድሜም እየገፋሁ ነው። በይፋ ጫማ ባልሰቅልም አሁን ወደዛው ነኝ። በዚህና ወቅታዊ ስፖርታዊ ጉዳዮችን በማስመልከት ቢቢሲ ከገብረእግዚአብሄር ጋር ቆይታ አድርጓል። ለመሆኑ እንዴት ነበር ወደ ሩጫው የገባው አትሌት ገብረእግዚአብሄር ሩጫ በጀመረበት ወቅት ሩጫ በአለም አቀፍ ደረጃ በውድድር ደረጃ ስላለው ስፍራ የጠለቀ እውቀት አልነበረውም። ትምህርቱን የተማረው እንደ ብዙው የኢትዮጵያ የገጠር ልጅ በእግሩ እየሄደ ነበር፤ አብዛኛውን ጊዜ ደግሞ ርቀቷን በሩጫ ፉት ይላታል። እኔ የአርሶ አደር ልጅ ነኝ። ወላጆቼ ያዘዙኝን በሙሉ ሰርቼ በሰዓቱ ትምህርት ቤት ለመድረስ ስለማልችል እየሮጥኩ ነበር የምሄደው። ከትምህርት ቤት ስመለስም እንዲሁ በሩጫ ነበር። ይላል ይሄ የአብዛኛው የአርሶ አደር ልጆች ታሪክ ቢሆንም ለገብረ እግዚአብሄር ግን የተለየ ዕድል እንደፈጠረለት ይናገራል። አጋጣሚው ተፈጥሯዊ አቅምን ፈጥሮልኛል። ሩጫን ከአንድ ቦታ ወደ አንድ ቦታ በፍጥነት ለመድረስ እንጂ በስፖርቱ አለም ያለውን ስፍራም አልተረዳውም ነበር። በስፖርት ይሄን ያህል ታዋቂነት እንደሚገኝም አላውቅም ነበር ይላል። ውድድር ማካሄድ የጀመረው በትምህርት ቤት በነበረበት ወቅት ሲሆን፤ የ ኛ ክፍል ተማሪ ሆኖ በትምህርት ቤቱ በተጀመረው ውድድር ለመጀመርያ ጊዜ አንደኛ ወጥቶ የምስክር ወረቀትም አግኝቷል። ጊነስ ዎርልድ ሪከርድስ፡ ስለተተከሉት ዛፎች ከኢትዮጵያ የደረሰን መረጃ የለም ከትምህርት ቤቱ በተጨማሪ ሌሎችን ውድድሮችን ማካሄድ የጀመረው ገብረእግዚአብሔር በ ዓ ም የ ኛ ክፍል ተማሪ ሆኖም አዲግራት አቅራብያ በምትገኘው ዕዳጋ ሐሙስ ከተማ ትምህርት ቤቱን ቀጢን ቃላይ ወክሎ ነበር የተወዳደረው፤ አንደኛም ወጣ። ቀጥሎም ወረዳውን ወክሎ ኪሜ ተወዳደሮ ማሸነፉን ያስታውሳል። ለመጀመርያ ግዜ ከምስክር ወረቀት በተጨማሪ ሽልማት ያገኘበት መሆኑም ልዩ ያደርገዋል። የብሄራዊ አትሌቲክስ ቡድን ኣባል በ በአየርላንድ የአገር አቋራጭ በባዶ እግሩ የ ሜትር የወርቅ ሜዳልያ በ ዓ ም በኒው ዮርክ ማራቶን የወርቅ ሜዳልያ በ ዓም በኢትዮጵያ ሚሊኒየም የአፍሪካ ሻምፒዮን የወርቅ ሜዳልያ አምቷል። አትሌት ገብረ እግዚአብሄር በተለይ ለእነዚህ ሶስቱ ድሎች የአየርላንድ፣ የኒው ዮርክና አፍሪካ ሻምፒዮን የተለየ ቦታ አለው። በተለይ ደግሞ የአፍሪካ ሻምፕዮን በኢትዮጵያ የተካሄደ በመሆኑና ከፍተኛ ዝናብ የጣለበት ፈታኝ ውድድርም ስለነበር ከፍ ያለ ትርጉም ይሰጠዋል። በኢትዮጵያ የመጀመርያ ውድድርም ስለ ነበር ሌሎች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ወርቅ እንዲያመጡ ጉልበት የሆናቸው ይመስለኛል የሚል እምነት አለው። የአትሌት ገብረ እግዚአብሄር አርአያ ማን ነው ገብረእግዚአብሄር ሩጫን በአጋጣሚ ቢጀምርም በትምህርት ቤት ስለ እነ አትሌት ምሩጽ ይፍጠርና አትሌት ሃይሌ ገብረስላሴ የሩጫ ገድል ሲሰማ በሩጫ ላይ የተለየ ፍላጎት እንዳደረበት ይናገራል። አበበ ቢቂላም ሌላኛው የገብረእግዚአብሄር አርአያ ነው። ለሶስቱ አትሌቶች የተለየ ክብርና አድናቆት እንዳለው ነው የሚናገረው ገብረእግዚአብሄር፤ ሩጫን ለዓለም በደንብ ያስተዋወቅነው እኛ ኢትዮጵያውያን ነን የሚል አቋም አለው። ገብረእግዚአብሄር ከሁሉም በላይ ለኃይሌ ገብረ ስላሴ ያለው ቦታ ከፍ ያለ እንደሆነ ይናገራል። በሩጫ ማሸነፉ ብቻ ሳይሆን በሩጫው ለረዥም ግዜ የቆየበት ፅናቱን እንደ ምሳሌ ይቆጥረዋል። እንዲሁም ደግሞ ከሩጫው በተጨማሪ በቢዝነስ የሚያደርገው እንቅስቃሴና ስኬትም ሌላ የሚያደንቅበት ጉዳይ ነው። አትሌት ምሩጽ ይፍጠር አባቴ ነበር አትሌት ምሩጽ ይፍጠር በአንድ ኦሎምፒክ ሁለት የወርቅ ሜዳልያ ባለቤት መሆኑን ከፍተኛ ስፍራ ከመስጠቱ በተጨማሪ ለመጀመርያ ጊዜ ሩጫን በውድድርነት ሲሰማ የአትሌት ምሩጽ ይፍጠርን ድል ነበር የሰማው። የስድስተኛ ክፍል የሳይንስ መምህሩ ስለ አትሌት ምሩጽ ይፍጠር ማርሽ ቀያሪነት በሚነግሯቸው ወቅት መጀመርያ የሚያወሩት ስለመኪና ማርሽ ይመስለው እንደነደበር በፈገግታ ያስታውሰዋል። ምሩጽ ስሙም ምርጥ ማለት ነው፤ ተግባሩም ምርጥ ነበር። በአካል ሳላውቀው ለረዥም ግዜ በውስጤ ይመላለስ ነበር፤ ምን ዓይነት ሰው ይሆን ብዬ ሁሌ አስብ ነበር ይላል። በኋላም በአካል ተገናኝተው ከተዋወቁ በኋላ ያላቸው ግንኙነት ጠንክሮ እንደ ልጅና አባት ይተያዩ እንደነበር ይናገራል። በህይወት ሳለ እንደ አብሮ አደጎችም ነበር የምንቀራረበው። እንደ አባቴ ነበር የማየው። የሃገሪቱም ሆነ ዓለም ክብር ነበር በማለት በኃዘኔታ ያስታውሳል። ለተወሰኑ ዓመታት አሰልጣኙ እንደነበርም ይናገራል። በተለያዩ ማሕበራዊ ጉዳዮችም ያማክረው እንደነበር ገብረእግዚአብሄር ያስታወሳል። ወቅታዊ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ተተኪ አትሌቶችን ከማፍራት ባለፈ የመቀሌ ከተማና ሌሎች በክልሉ የሚገኙ የቱሪዝም መስህቦችን ማስተዋወቅ አላማ ያለው ናትና ስፖት በሚል ከባለቤቱ ከአትሌት ወርቅነሽ ኪዳነ ጋር ባቋቋሙት ተቋም አማካኝነት ሶስተኛው ናትና የጎዳና ሩጫ ባለፈው ወር መቀሌ ላይ ተከናውኗል። ትግራይ ክልል በደንብ ከተሰራበት ለስፖርት አመቺ የሆነ ሁኔታ አለ የሚለው ገብረእግዚአብሄር ከሩጫው በሚገኘው ገቢ ሶስት የአትሌቲክስ መንደሮች ለማቋቋም አስቧል። የመቀሌ ሰብዓ እንደርታ እግር ኳስ ቡድን ዘንድሮ የኢትዮጵያ ፕሪሚዬር ሊግ ዋንጫን ሲያነሳ በክልሉ የታየው መነቃቃትና መነሳሳት ደግሞ ስፖርት ምን ያህል ጉልበት እንዳለው የሚያሳይ እንደሆነም ያስረዳል። የስፖርት መርህ ሰላምና ፍቅር መሆኑን የሚናገረው አትሌት ገብሬ በተለያዩ ምክንያቶች የሚነሱ ግጭቶችና አለመግባቶች ስለስፖርት ምንነት ጠንቅቆ ካለማወቅ የመነጨ እንዳሆነ ይገልጻል። ኢንቨስትመንትና ማህበራዊ ኃላፊነት ከአትሌት ኃይሌ ገብረስላሴ አገኘኋት በሚለው ተሞክሮ ባገኛት ሳንቲም ኢንቨስት ማድረጉን ይናገራል። አዲስ አበባ ውስጥ ሁለት ሕንጻዎች ሲኖሩት መቀሌ ከተማ ውስጥ ደግሞ ለሆቴል የሚሆን ሕንፃ እያስገነባ እንደሆነ ነግሮናል። ከዚህም በተጨማሪ የስፖርት አልባሳትን ከውጭ ወደ ሃገር ውስጥ በማስገባት የተሰማራው ገብረእግዚአብሄር የመቀሌ ሰብዓ እንደርታ ማልያ በእርሱ ኩባንያ በኩል እንደሚመጣ ይናገራል። አትሌት ገብረ እግዚአብሄር በተለያዩ ሃገራዊ ኃላፊነቶችም በማገልገል ላይ ይገኛል። በአትሌቲክስ ፌዴሬሽንና በኦሎምፒክ ኮሚቴ ውስጥ በአመራርነት ይሳተፋል። ቢሆንም በተለያዩ ጉዳዮች ላይ መሳተፌ ውጤታማነቴ ላይ ድክመት እንዳያስከትልብኝ እፈራለሁ ይላል። ሆኖም በምሰራቸው ስራዎች ደስተኛ ነኝ። ሃገራዊ ግዴታዬን መወጣቴ ደስ ያሰኘኛል። የአንድ ሰው ህይወትም ቢሆን ከቀየርኩ ደስተኛ ነኝ። ፖለቲካ ላይ ለመሳተፍ ፍላጎት እንዳለው ጥያቄ የቀረበለት ገብረእግዚአብሄር ምላሹ አጠር እና ፈርጠም ያለ ነበር፤ በፍጹም ፍላጎት የለኝም የሚል። ሆኖም ይላል ገብረእግዚአብሄር ሰዎች ለውጥ ያመጣል ብለው ካመኑብኝ እሠራለሁ። የወከለኝን ሰው አላሳፍርም። አቅም አለኝ ብየ ግን አይደለም። መስዋእትነት ነበር የምንከፍለው። ወርቄ እያለ አቆላምጦ የሚጠራት ባለቤቱ ወርቅነሽ ኪዳኔም ከሩጫውም ከሚድያውም ርቃለች። ወርቄ ለሀገሯ ብዙ ሠርታለች። ለዛውም ከፍተኛ መስዋዕትነትን እየከፈለች። አሁን ግን እኔም እሷም ወደ መተው ደረጃ ደርሰናል። የምንችለውን አድርገናል ብየ ነው የማስበው። በተለያዩ የአትሌቲክስና ኦሎምፒክ ውድድሮች ኢትዮጵያውያን በቡድን ስራ የተዋጣ ስራ ሲሰሩ እንደነበር አትሌት ገብረ እግአዚአብሄር ይናገራል። ሆኖም ወርቅ ላመጣ ብቻ የሚሰጠው እውቅናና ክብር ግን ያንን የቡድን ስራ ዋጋ እንዳይቀንሰው ይሰጋል። እኛ፤ እኔም ሆነ ቀነኒሳ፤ ጥሩነሽ ሆነች ወርቅነሽ ሁላችንም የምንሰራው ኢትዮጵያ ወርቅ እንድታገኝ ነው። በእኛ ምክንያት ሃገር ማፈር የለባትም ብለን ነው። ስለሆነም ቀነኒሳ ወርቅ አምጥቶ ባንዲራ አንስቶ ሲሮጥ፤ ሁላችንም ተነስተን በደስታ እንጨፍራለን። ይላል። ነገር ግን ወርቅ ያመጣው ላይ ብቻ ከፍተኛ ትኩረት ስለሚሰጥም በመንግሥትና በሚድያዎች ላይ መጠነኛ ቅሬታ እንዳለው ግን አልደበቀም። ወደ አገር ስትመጣ ለእንዲህ ዓይነት የቡድን ስራ ክብር ሲሰጥ አይታይም። ወርቅ ላመጣ ብቻ ክብር መስጠት ራሱን የቻለ ችግር አለበት። ይህንን ደጋግመን ነግረናቸዋል ይላል። አክሎም በእርግጥ እኛ ተሰምቶን አያውቅም። የምንችለውን አድርገናል። መስዋዕትነት ነበር የምንከፍለው። ይሄ ከየት የመጣ ነው ካልከኝ ከወከለን ህዝብ አደራ ነው። በአምስት የአለም ዋንጫዎች ተሳትፌያለሁ። በአምስቱም ወርቅ አላመጣሁም። ወርቅ እንዲመጣ ግን ምክንያት ነኝ። በሁለት ኦሎምፒክ ተሳትፌያለሁኝ። በሁለቱም ወርቅ እንዲገኝ ምክንያት ነኝ። ወርቄ ወርቅነሽ ደግሞ በተመሰሳይ በስድስት የዓለም ዋንጫና በሶስት የኦሎምፒክ ውድድሮች ላይ ተሳትፋለች። እሷም እንደዚሁ። ወርቅ እንዲመጣ የመጀመርያ ተጠሪ እሷ ነች። ዘ ካንትሪ ዉማን ይሉዋታል። ወደፊት ወጥታ ለሁለትና ለሶስት ቆርጣ ደረጃ ታወጣባቸዋለች። ከተሸላሚዎቹ በላይ ወርቅ እንዲመጣ ምክንያት ነች። እነሱም ያምናሉ። ወደ መንግሥት ስትመጣ ግን ሌላ ነው፤ ይሄ የአስተሳሰብ ጠባብነት ነው የሚመስለኝ። ይላል በሩጫ ውድድር ብቻ ሳይሆን በተለያዩ ሌሎች አገራዊ ዘርፎችም እንደዚህ ዓይነት ተመሳሳይ ችግር እንዳለና መስተካከል እንዳለበት ያሳስባል ገብረእግዚአብሄር ለሁሉም በተለይ ደግሞ መስዋዕትነት ለሚከፍለው ዕውቅና መስጠት አስፈላጊ ነው። ጥቅም አይፈልግም በማለት ሃሳቡን ይቋጫል። ተያያዥ ርዕሶች
መንዙማ የትም ሊኖር ይችላል። ግብፅም የመንም፣ ሻምም
መንዙማ የትም ሊዜም ይችላል፤ ታጃኪስታንም፣ ኡዝቤኪስታንም፣ ፓኪስታንም እንደ ወሎ የሚኾን ግን እንጃ የወሎ መንዙማ ቱባ ነው። ኦርጋኒክ አልተቀየጠ፣ አልተከተፈ ፣ አልተነጀሰ ። ደግሞም እንደ ዘመነኛ ነሺዳ በ ኪቦርድ ቅመም አላበደ ። ለዚህ ምሥክር መጥራት አያሻም። የሼኽ መሐመድ አወል ሐምዛን እንጉርጉሮ መስማት በቂ ነው። በጆሮ በኩል ዘልቆ፣ አእምሮን አሳብሮ ወደ ልብ የሚፈስ የድምፅ ፈውስ ። ይለዋል ወጣቱ ገጣሚ ያሲን መንሱር። የመንዙማው ማማ በዚህ ዘመን ህልቆ መሳፍርት መንዙመኞች አሉ። ሼኽ መሐመድ አወል ሐምዛ ግን ከማማው ላይ ናቸው። ከወሎ የፈለቁት ሼኹ ለመገናኛ ብዙኃን ቃል መስጠት እምብዛም ምቾት አይሰጣቸውም። ለቢቢሲ ጥሪም እንዲያ ነው ያሉት። ኾኖም ታሪካቸውን የዘገቡ ሰነዶች የኚህ ሰው የሕይወት መስመር እንደ መንዙማቸው ልስሉስ እንዳልነበረ ያትታሉ። ደቡብ ወሎ የተወለዱት ሼኹ ገና ድሮ ወደ ሸዋ ገብተው ኑሮ ለማደራጀት ከፍ ዝቅ ብለዋል። የሚያምር የአረብኛ የእጅ ጽሕፈት አጣጣል ስለነበራቸው የሃይማኖት ድርሳናትን በእጅ ከትበው በመስጂዶች ቅጥር ማዞር ጀማምረውም ነበር ይባላል። ወዳጆቻቸው እንደነገሩን በአዲሳ ባ የመን ኮሚኒቲ በመምህርነት እስኪቀጠሩ ድረስ የወሎ ምድርና ተፈጥሮ አድልተው ያደሏቸውን መረዋ ድምጽ በመጠቀም በተለያዩ ዝግጅቶች ላይ መንዙማን ያዜሙ ነበር። አንዳንድ መድረኮች ላይ ታዲያ የሼኩ ተስረቅራቂ ድምጽ ለነብዩ ውዳሴ ከሚደረድሩ ጥልቅ መልዕክቶች ጋር ተዳምረው ታዳሚዎችን ስሜታዊ ያደርጓቸው ነበር ይባላል። የእሱ እንጉርጉሮ እንደሁ ያው ታውቀዋለህ ልብ ያሸፍታል አንዳንድ ሼኾች ድምጽ አውጥተው በስሜት ያለቅሱ እንደነበር አስታውሳለሁ ይላሉ ቆየት ካሉ ወዳጆቻቸው አንዱ ለቢቢሲ ትዝታቸውን ሲያጋሩ። በመንዙማ ፍቅር የወደቀው ደርግ መንዙመኛው ሼክ መሐመድ አወል ድሮ ማስታወቂያ ሚኒስቴር ተቀጥረው ነበር አሉ። መንዙማቸውም እንደዋዛ ሬዲዮ ሞገድ ውስጥ ገብቶ ነበር አሉ፤ እንደ ማጀቢያም እንደማዋዣም። ታዲያ ከዕለታት ባንዱ ልበ ደንዳናዎቹ ደርጎች በሰውየው አንጀት አርስ እንጉርጉሮ ልባቸው ረሰረሰ። ከደርጎቹ በአንዱ ላይ ክፉ አሳብ በልቡ አደረ። እንዲህም አለ፣ ይሄ ሰውዬ በነካ እጁ ስለ አብዮቱ ለምን አያዜምልንም ሼኪው ተጠሩ። ድምጽዎ ግሩም ኾኖ አግኝተነዋል፤ እስቲ ስለአብዮታችን አንድ ሁለት ይበሉ ። ያን ጊዜ ያ አላህ አንተው መጀን ብለው ከአገር ሾልከው የወጡ ከስንትና ስንት ዘመን ኋላ የሐበሻን ምድር ተመልሰው የረገጡ። ዓመት ዓመት እንጃ ብቻ በዚህ ሁሉ ዘመን ታዲያ እኚህ እንደ ጨረቃ የደመቁ መንዙመኛ የት ከረሙ ስንል የጠየቅናቸው ወዳጆቻቸው ከፊሎቹ መሐመድ አወል ሐምዛ ሳኡዲ ነው የኖረው ሲሉ፣ ገሚሶቹ ደግሞ የለም እዚህ ጎረቤት ሚስር ፣ አልአዝሃር ዩኒቨርስቲ ትምህርቱን ሲይንበለብለው ነበር ብለውናል። የቱ ነው ትክክል ብሎ ለመጠየቅ እንኳ ሰውየው ሩቅ ናቸው። ያ ጥኡሙ ድምጻቸው መንዙማን ለማዜም ካልሆነ በቀር አይሰማም። እ ሩቅ ነው። መንዙማ የልብ ወጌሻ መንዙማ አልፎ አልፎ መዝናኛ ነው፤ አንዳንዴ የጸሎት ማዳረሻ ነው፤ ብዙዉን ጊዜ የማኅበረሰብን ሰንኮፍ ማሳያም ነው፤ አንዳንዴ የአገር ፍቅር መግለጫም ነው። ብዙዎቹ የመንዙማ ሥንኞች የሥነ ምግባር ተምሳሌት ተደርገው የሚታሰቡትን ነብዩ ሙሐመድን ያወድሳሉ። አፈንጋጮችን ይገስጻሉ፣ ባሕል ከላሾችን ይኮረኩማሉ። አቶ ተመስገን ፈንታው መቀለ ዩኒቨርስቲ ውስጥ ሥነ ጽሑፍና ፎክሎርን ለ ዓመታት አስተምረዋል። በመንዙማ ዙርያ የተሠሩ በርከት ያሉ ጥናታዊ ወረቀቶችን አማክረዋል። የአጋጣሚ ነገር ትውልዳቸውም ወልዲያ ነው። ሴት አያቴ በመንዙማ ነው ያሳደገችኝ ይላሉ ክርስቲያን መሆናቸው መንዙማን ከማጣጣም እንዳላቦዘናቸው ሲያስረዱ። ወሎ ውስጥ መንዙማ ባሕል ነው። የየትኛውንም ዕምነት ተከታይ ሁን መንዙማን ትሰማለህ፤ በአንድም ሆነ በሌላ የወሎ ባሕል ወትሮም ሃይማኖትን ፍዝ ያደርጋል። አያቴ መንዙማን የእስልምና ብላ አይደለም የምትረዳው። እሷ የምታውቀው የወሎዬ መሆኑን ነው። መንዙማ ለእሷ ከአምላክ ጋር መገናኛ፣ መታረቂያ፣ መለማመኛ፣ ስሜቷን መተንፈሻ ነው። ይላሉ። መምህር ተመስገን ይኸው የልጅነት ተጽእኖ ይሁን አይሁን ባያውቁትም አሁንም ድረስ ጥሞናና መመሰጥ ሲያምራቸው ከላፕቶፓቸው ኪስ ያኖሯቸውን እንጉርጉሮዎች ያዘወትራሉ። አቦ ሌላ ዓለም ነው ይዞኝ የሚሄድ መንዙማና ፍልስምና ፍልስምና እስልምናና ፍልስፍናን ያቀፈ ሽብልቅ ቃል መሆኑ ላይ ከተግባባን በመንዙማ ውስጥ ፍልስፍና እንደጉድ እንደሚነሳና እንደሚወሳ ልናወጋ እንችላለን። በመንዙማ ዓለማዊም ኾኑ ዘላለማዊ መጠይቆች በቅኔ ተለውሰው ይዜሙበታል። በግልባጩም የፈጣሪን መኖር የሚጠራጠሩ ኢ አማንያን ከብርቱ አማኒያን ተሞክሮ እየተጨለፈ በምክር ይረቱበታል። ለነገሩ በመንዙማ ስንኞች ፍልስምና ብቻ አይደለም የሚነሳው፤ ምን የማይነሳ አለና ፖለቲካ፣ ግብረ ገብነት፣ መንፈሳዊነት፣ አርበኝነት ኢትዮጵያዊነት በስልክ ማብራሪያ የሰጡን ኡስታዝ አብዱልአዚዝ መሐመድ የነጃሺ መስጂድ ኢማምና የጁምዓ ሶላት ዲስኩረኛ ኻጢብ ናቸው። መንዙማ በኢትዮጵያ የኢስላም ታሪክና ፖለቲካ ውስጥ የነበረውን ቦታ ሦስት የመንዙማ ሊቃውንትን በስም በመጥቀስ ይተነትናሉ። በዘመናዊ የኢስላም ታሪክ ውስጥ ሰሜን ወሎ፣ ራያ ውስጥ ጀማሉዲን ያአኒ የተባሉ ሐበሻ ከአጼ ዮሐንስ ጋር ለሦስት ዓመታት ተፋልመዋል። በመጨረሻ አጼው በርትተው ሲመጡባቸው ድል መነሳታቸው እርግጥ ሆነ። ያን ጊዜ ያዜሙት መንዙማ ዛሬም ድረስ ይወሳል። ዘይኑ ነቢ ዘይኑ ነቢዬ የሚል አዝማች ያለው ሲሆን የመንዙማው ጭብጥ ደግሞ የአጼውን ጭካኔ ማጉላት ነው። እንዲያውም የአጼ ዮሐንስን ጦርነት አርማጌዶን ሲሉት፤ በምጽአት ቀን ቂያማ ይመጣል የሚባለው ሰው ጋር ያመሳስሏቸዋል። ይህ ሰው በኢስላም ደጃል በመባል ይታወቃል። አጼው እኔ ላይ ያለ ጊዜው የመጣ ደጃል ሆነብኝ ሲሉም አዚመዋል። በተመሳሳይ በየጁ ግዛት ይኖሩ የነበሩና አሕመድ ዳኒ የሚባሉ ኢትዮጵያዊ አባት በወቅቱ የነበረው አገረ ገዢ በጣም ቅር እንዳሰኛቸው፣ ዘመኑም እንዳልተመቻቸው ለመግለጽ የሚያንጎራጎሩበት መንዙማ ዛሬም ድረስ ይዜማል። ርዕሱ ሑዝቢየዲ ያረሱላላህ የሚል ሲሆን ከይህ ወዲህ ምድር ላይ መቆየት አልሻም፤ በቃኝ የሚል መልዕክትን የያዘ ነው። ከ ኛው ክፍለ ዘመን መንዙመኞች ደግሞ ሼክ ጫሊ ጎልተው ይወሳሉ። በይዘትም፣ በቋንቋ ልቀትም፣ በቁጥርም፣ በዓይነትም እንደርሳቸው መንዙማን የቀመረ የለም ይባላል። እርሳቸው ታዲያ ከወራሪው ጣሊያን የተፋለሙ ጀግና ነበሩ። ከመንፈሳዊ መንዙማም በላይ ስለ አገር ፍቅር ያዜሙ እንደሆኑ ይነገርላቸዋል። ጣሊያን ወልዲያ፣ ሃራ አካባቢ አባብሎና አግባብቶ ካስጠራቸው በኋላ ተኮሰባቸው፤ በተአምር ተረፉ። እርሳቸውም በመንዙማቸው እንጉርጉሮን አዚመዋል። በአገራችን መኖር አትችሉም አሉን፤ ሻምና ሩም ሂዱ አሉን፤ ምን ጉድ ነው ይሄ የሚሉ ፖለቲካዊ ዜማዎችን አዚመዋል። እንደ ኡስታዝ አብዱልአዚዝ ገለፃ መንዙማና ሥነ ቃል እያንዳንዱ መንዙማ ይነስም ይብዛ ታሪክ ተሸክሟል። የመንዙማ ስንኞች ቢያንስ ቀደምት የኢትዮጵያ ሙስሊሞች እንዴት እንደኖሩ የመተረክ አቅም አላቸው። አሁን ያሉቱ መንዙመኞች ግን ቀደምት ግጥሞችን በአዲስ ቅላጼ የማዜም ነገር ካልሆነ እምብዛምም አዲስነት አይታይባቸውም። በመንዙማ ታሪክ ብቻ ሳይሆን ዕውቀትም ተስፋፍቷል። ማንበብና መጻፍ ሩቅም ብርቅም በነበረበት በያ ዘመን መንዙማ የእስልምና ትምህርት መሠረታዊያንን ለገጠሩ ማኅበረሰብ ለማድረስ አስችሏል ይላሉ ኡስታዝ አብዱልአዚዝ። የመንዙማ ንሸጣ የመንዙማ ግጥሞች ጥልቀትና ከፍታ በታላቅ መነቃቃትና ጥሞና ውስጥ መጻፋቸው ነው። የመንዙማ ደራሲ ድንገት ዋሪዳ መጣብኝ ካለ ቅኔ ሊዘርፍ ነው ማለት ነው። ንሸጣ ውስጥ ገብቻለሁ እንደማለትም ነው። ድሮ ድሮ በግብታዊነት የሚጻፉ፣ በዘፈቀደ የሚሰደሩ ስንኞች አልነበሩም። አሁን አሁን ካልሆነ። ንፁህ አማርኛን ብቻ የሚጠቀሙ መንዙማዎች የሉም ባይባልም በርካታ አይደሉም። የሚበዙቱ አረብኛን ከወሎ አማርኛ ጋር ያዳቀሉት ናቸው። ለምን የወሎ አማርኛ ወትሮም አንዲያ ያደርገዋል። ከአረብኛ ጋር የመጎናጎን ባሕሪው ዘመን የተሻገረ ነው። የወሎ ሕዝብ ችግር መጣብኝ ከማለት ሙሲባ መጣብኝ ነው የሚለው። ሙሲባ አረብኛ ነው ይላሉ ኡስታዝ አብዱልአዚዝ። ይህ ቋንቋን የማዳቀሉ ነገር መንዙማው ላይም ተጋብቶበታል ይላሉ ኡስታዙ። ቢያንስ በሁለት ምክንያት በኢትዮጵያ የኢስላም ታሪክ የወሎዎች ሚና መጉላቱ አንዱ ነው። ቁርዓን፣ ፊቂህ ኢስላማዊ ሕግጋት የቅዱስ መጻሕፍት ትርጉም ታፍሲር ፣ አረብኛ ቋንቋ እና የአብነት ትምህርት ቤቶች ማድራሳ ከወሎና ሀይቅ አካባቢ ነው የመነጩት። ዛሬም ድረስ የበርካታ መዝጊዶች አሰጋጆችና ሊቃውንት ሙፍቲሆች የወሎ ልጆች ናቸው። መንዙማም መንፈሳዊው ሕይወትን የመግለጫ አንድ የጥበብ አምድ መሆኑ ከሌላው የኢትዮጵያ ክፍል ይልቅ በዚያ አካባቢ እንዲጎመራ የተመቻቸ መስክ ሳያገኝ አልቀረም። ይላሉ ኡስታዙ። የአረብኛ ቃላት በመንዙማው እንዲህ በአያሌው መነስነስ ሌላው ምክንያት ደግሞ፤ አንድም የሃይማኖቱ አንኳር ቃላት በአረብኛ መወከላቸው የፈጠረው ሀቅ ሲሆን፣ አንድም ደግሞ የገጣሚዎቹ የቋንቋ ልኅቀት ማሳያ የይለፍ ወረቀት መሆኑ ነው። ሳኡዲን ያስደመመው የሐበሻ መንዙማ የነጃሸዒ መስጂድ ኢማም ኡስታዝ አብዱልአዚዝ ናቸው ይህን ግርድፍ ታሪክ የነገሩን። የቀድሞው የሳኡዲ ዋናው ሙፍቲህ እጅግ የተከበሩት ሼክ ኢብኒባዝ አሁን በሕይወት የሉም ነፍስ ይማር ይርሃመሁላህ አንድ ቀን ምን አሉ እስቲ የናንተ ሐበሾች ጻፉት የሚባለውን መንዙማ አምጡልኝ በዝና ብቻ ነበር አሉ የሐበሻን መንዙማ የሚያውቁት። ቀረበላቸው። ግጥሞቹን ሰምተው ግን ለማመን ተቸገሩ። እንዴት እኛ የአፍ መፍቻ ቋንቋችን አረብኛ የሆንነው ሰዎች ያልቻልነውን በግጥም መራቀቅ እናንተ ቻላችሁበት ብለው መደነቃቸው ይነገራል። ሼኸ ኢብኑባዝን ወሎ ነበር ማምጣት የቅኔ አገር የደረሶች ማንኩሳ የመንዙማ ቀዬ የ መሳኪን ሼኮች ማደሪያ ቢቢሲ ማስተባበያ
የሴት ልጅ ግርዛት ምንድነው የት እና ለምን ይፈጸማል
ፌብሩወሪ ማጋሪያ ምረጥ አጭር የምስል መግለጫ ገራዧ ተብላ የምትታወቀው ይህች ሴት ሞምባሳ ኬንያ ውስጥ ሴቶችን ለመግረዝ የምትጠቀምበትን ምላጭ ይዛ። የተባበሩት መንግሥታት በዓለማችን በህይወት ያሉ ወደ ሚሊዮን የሚጠጉ ሴቶች እና ህጻናት ላይ የተለያየ ደረጃ የግርዛት ተግባራት ተፈጽሞባቸዋል ይላል። የሴት ልጅ ግርዛት በስፋት እየተፈጸመ ያለው ወደ በሚጠጉ የአፍሪካ እና መካከለኛው ምስራቅ ሃገራት ሲሆን፤ በእስያ እና ደቡብ አሜሪካ በሚገኙ ሃገራትም የሴት ልጅ ግርዛት ይፈጸማል። የተባበሩት መንግሥታት እንደሚለው ከሆነ በአውሮፓ፣ ሰሜን አሜሪካ፣ አውስትራሊያ እና ኒው ዚላንድ የሚኖሩ ስደተኞች ህግን በመተላለፍ ሴት ልጆቻቸውን ያስገርዛሉ። የተባበሩት መንግሥታት በዓለም አቀፍ ደረጃ የሴት ልጅ ግርዛት እንዲቆም ጥሪ እያቀረበ ነው። የሴት ልጅ ግርዛት አካላዊ እና አእምሯዊ ጉዳቶችን ሊያስከትል እንደሚችል የቦረና ማህብረሰብ አባል የሆነችው ቢሻራ ሼህክ ሃሞ ትናገራለች። የተገረዝኩት የ ዓመት ልጅ ሳለሁ ነበር። አያቴ ግርዛት ንጹህ የሚያደርግ የሁሉም ሴት ልጅ ግዴታ እንደሆነ ትነግረኝ ነበር ትላለች ቢሻራ ሼክህ። የሴት ልጅ ግርዛት ምንድነው አጭር የምስል መግለጫ የተባበሩት መንግሥትታት እንደሚለው በአፍሪካ፣ ኢሲያ እና መካከለኛው ምስራቅ ቢያንስ ሚሊዮን የሚሆኑ በህይወት ያሉ ሴቶች እና ህጻናት ተገርዘዋል። የሴት ልጅ ግርዛት ሆነ ተብሎ የሴት ልጅን የመራቢያ ክፍል አካል መቁረጥ ማለት ነው። የዓለም ጤና ድርጅት ብዙ ጊዜ የሴት ልጅ ግርዛት ሲፈጸም የብልት ከንፈሮችን እና ቂንጥርን መቁረጥን ያካትታል ይላል። ኦምኒያ ኢብራሂም ግብጻዊት የፊልም ዳይሬክተር እና ጦማሪ ናት። ኦምኒያ ግርዛት በህይወቷ ላይ ከፍተኛ ጫና እንዳሳደረ ትናገራለች። ማህብረሰቡ ያስተማረኝ የሰውነት ክፍል የግብረ ስጋ ግንኙነት አካልና ይህ ደግሞ ሀጢያት መሆኑን ነው። አእምሮዬ ውስጥ ሰውነቴ ሀጢያት እንደሆነ ነበር የምረዳው ትላለች። አጭር የምስል መግለጫ ቢሻራ ሼክህ በግርዛት ምክንያት ከደረሰባት ችግር በመነሳት የሴት ልጅ ግርዛት እንዳይፈጸም የተለያዩ ቅስቀሳዎችን ታደርጋለች ቢሻራ ግርዛት እንዴት እንደተፈጸመባት ስታስታውስ፤ አራት ሴት ህጻናት አብረውኝ ተገርዘዋል። ዓይኔ ተሸፍኖ ነበር። ከዛ እጄን ወደኋላ አሰረች። ሁለት እግሮቼን ከፍተው ከያዙ በኋላ የብልቴን ከንፈር ቆርጣ ጣለች ስትል ታስታውሳለች። የግርዛት አይነቶች አራት አይነት የግርዛት አይነቶች አሉ። ክሊቶሪዲክቶሚይ ፡ ይህ ማለት በቂንጥር እና በአከባቢው የሚገኝ ስስ ቆዳ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ማስወገድ ማለት ነው። ኤክሲሺን ፡ ይህ ማለት ቂንጥርን እና የብልትን የውስጠኛውን ከንፈር ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ማስወገድ ማለት ነው። ኢንፊቢዩሊሽን ፡ ይህ ማለት ቂንጥርን እና የብልት ክንፈሮችን ቆርጦ በመጣል ብልትን በመስፋት የግብረ ስጋ ግንኙነት ምቹ እንዳይሆን ማድረግ ማለት ነው። ይህ ተግባር የሚያስከትለው ህመም ከፍተኛ ከመሆኑም በላይ ለኢንፌክሽን ተጋላጭነትን ከፍ ያደርጋል። በተጨማሪም ሽንት እና የወር አበባ ፍሳሽ በቀላሉ እንዳይወጣ ያደርጋል። ሌላኛው የግርዛት አይነት የሴት ልጅ የመራቢያ አካላትን መውጋት፣ መብሳት፣ መቧጠጥ እና ማቃጠል የመሳሰሉትን ያካትታል። የሴት ልጅ ግርዛት ለምን ይከሰታል አጭር የምስል መግለጫ በአንዳንድ የኬንያ ማያሳ ሴቶች ዘንድ ያልተገረዙ ሴቶች የትዳር አጋር አያገኙም ወይም ከበርካታ ሰዎች ጋር የወሲብ ግንኙነት ሊኖራቸው ይችላል የሚል እምነት አላቸው። የሴት ልጅ ግርዛት ከሚፈፀምባቸው የተሳሳቱ ምክንያቶች መካከል የማህብረሰብ አስተሳሳብ፣ ኃይማኖት፣ ከንጽህና ጋር የተያያዘ የተሳሳተ ዕምነት፣ ድንግልናን ለማቆየት በማሰብ፣ ሴት ልጅ ትዳር እንድታገኝ በማሰብ እና የወንድ ልጅ የወሲብ እርካታን ለመጨመር ይገኙበታል። በበርካታ ማህብረሰብ ዘንድ ሴት ልጅ የምትገረዘው ለትዳር እንደ ቅድመ ዝግጅት ስለሚወሰድ ነው። ምንም እንኳ ግርዛት ለንጽህና የሚያበርክተው አስተዋጽኦ በሳይንስ ባይረጋገጥም፤ ያልተገረዙ ሴቶች ጤነኛ እና ንጹህ ያልሆኑ ተደርገው በበርካታ ማህብረሰብ ዘንድ ይታሰባሉ። አጭር የምስል መግለጫ የሴት ልጅ ግርዛት የሚፈጸምባቸው ሃገራት የሴት ልጅ ግርዛት የት ይፈጸማል የሴት ልጅ ግርዛት በበርካታ የዓለማችን ሃገራት የተከለከለ ተግባር ቢሆንም አሁንም በየቀኑ በተለያየ ሃገራት ይፈጸማል። የተባበሩት መንግሥታት እንደሚለው ምንም እንኳ የሴት ልጅ ግርዛት በ የአፍሪካ እና መካከለኛው ምስራቅ ሃገራት ውስጥ በህግ የተከለከለ ቢሆንም በ ሃገራት ውስጥ በስፋት እንደሚፈፀም ይጠቁማል። በአውሮፓ፣ ሰሜን አሜሪካ፣ አውስትራሊያ እና ኒው ዚላንድ የሚኖሩ ስደተኞች ህግን በመተላለፍ ሴት ልጆቻቸውን እንደሚያስገርዙም እኚህ መረጃዎች ያሳያሉ። በምዕራባውያን ሃገራት የሴት ልጅ ግርዛት የሚፈጸመው በጨቅላ ህጻናት ላይ በመሆኑ ጨቅላዎቹ ወደ ትምህርት ቤት ስለማይሄዱ እና ከእድሜያቸው አንጻር ሪፖርት ማድረግ ስለማይችሉ ተግባሩ እንደተፈጸመባቸው ማወቁ ከባድ መሆኑ ተጠቅሷል። ተያያዥ ርዕሶች
አንበሳዋ እናት፡ የልጃቸውን ደፋሪ የገደሉት እናት ነጻ ወጡ
ሚያዝያ ይህንን ለማጋራት በ ዋትስአፕ አንበሳዋ እናት ኖኩቦንጋ ኳምፒ ኖኩቦንጋ ኳምፒ በደቡብ አፍሪካ አንበሳዋ እናት በመባል የታወቁት ልጃቸውን ከደፈሩ ሦስት ወንዶች መካከል አንዱን ገድለው ሌሎቹን ካቆሰሉ በኋላ ነው። በግድያ ወንጀል ክስ የተመሰረተባቸው ቢሆንም በሕዝብ ድምፅ ምክንያት ክሱ ተነስቷል። ነገሩ የጀመረው እኩለ ሌሊት ላይ የስልክ ጥሪ ኖኩቦንጋን ከእንቅልፍ ሲቀሰቅሳቸው ነበር። የደወለችውም ሴት ኖኩቦንጋ ሲፎካዚ የተባለችው ሴት ልጃቸው በሚያውቋቸው ሦስት ወንዶች መደፈሯን በዚያ ሌሊት ነበር የነገረቻቸው። ኖኩቦንጋ የመጀመሪያ እርምጃቸው ፖሊስ መጥራት ነበር፤ ነገር ግን የፖሊሶቹ ስልክ አይመልስም። በጊዜው ልጃቸውን መርዳት የሚችሉት እራሳቸው ብቻ ነበሩ። በጣም ፈርቼ ነበር ግን ልጄ ናት፤ መሄድ ነበረብኝ ይላሉ እናት ኖኩቦንጋ። እዚያ እስክደርስ ትሞታለች ብዬ አስቤ ነበር። ምክንያቱ ደግሞ እኛን ስለሚያውቁን እንዳትናገር ፈርተው በሕይወት አይለቋትም ብዬ አስቤ ነው። በጊዜው ሲፎካዚ ጓደኞችዋን ለማግኘት ነበር እግሯን ወደዛች መንደር የመራቸው። በቆይታዋም ጓደኞችዋ በተኛችበት ለብቻዋ ጥለዋት በወጡበት አጋጣሚ ነበር የጠጡት ወንዶች ከተኛችበት ገብተው ጥቃት ያደረሱባት። በመጨረሻ ላይ ሳትስመኝ መሄዷ ይቆጨኛል እናት ቢላ ይዤ የሄድኩት እራሴን እዚያ እስክደርስ ባለው መንገድ ላይ ለመከላከል ብዬ ነበር ሲሉ ኖኩቦንጋ ሁኔታውን ያስታውሳሉ። ከቢላው ጋር ስልኬን ለብርሃን ብዬ ይዤ ነበር። ልጃቸው ወደ ነበረችበት ቤት ሲደርሱ ስትጮህ ሰሟት፤ ቤት ውስጥ ሲገቡም አንዱ ወንድ ልጃቸውን ሲደፍራትና ሌሎቹ ሁለት ወንዶች ደግሞ ሱሪያቸው ወልቆ ተራቸውን ሲጠባበቁ እንዳኟቸው ይናገራሉ። በጣም ስለፈራሁ በር ላይ ቆሜ ምን እያደረጉ እንደሆነ ጠየኳቸው። እኔ እንደሆንኩ ሲያውቁ በቁጣ ተንደርድረው ወደ እኔ መጡ፤ ያኔ ነው እራሴን መከላከል እንዳለብኝ የገባኝ። ክሱን ሲከታተል የነበረው ዳኛ ኖኮቦንጋ ልጃቸው ስትደፍር በአይናቸው ማየታቸው በጊዜው በጣም ስሜታዊ አድርጓቸዋል ብለዋል። ኖኩቦንጋም በጊዜው ይዘውት የነበረውን ቢላ በመጠቀም አንዱን ደፋሪ ገድለው ሌሎቹን በቆሰሉበት ትተው ልጃቸውን በቅርብ ወደ ሚገኝ ጎረቤት ወሰዷት። ፖሊሶችም ከቦታው ደርሰው ቦኩቦንጋን በቁጥጥር ስር ካደረጓቸው በኋላ በአቅራቢያ ወደ ሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ወሰደወቸው። ስለ ልጄ እያሰብኩ ነበር፤ ካዳንኳት በኋላ ስለእሷ ምንም አልሰማሁም። በጣም አስጨናቂ ጊዜ ነበር ይላሉ። ልጅና እናት እናትዋ ወደ እስር ቤት ሲወሰዱ ሲፎካዚ ሆስፒታል ሆና ስለእናትዋ እያሰበች ነበር። በፍርድ ቤት ተወስኖባት ለዓመታት የምትታሰር ከሆነ እኔ ቅጣቷን እቀበልላታለሁ እያልኩኝ አስብ ነበር ትላለች። ሲፎካዚ በጊዜው ስለተፈጠረው ነገር እናትዋ ከነገሯት ነገር ውጪ ምንም አታስታውስም ነበር። በጊዜውም እናትና ልጅ አንዳቸው የአንዳቸው ደጋፊ ነበሩ። ቡህሌ ቶኒስ የኖኩቦጋ ጠበቃ ስትሆን ከጥቃቱ አንድ ሳምንት በኋላ ስታገኛቸው እናትና ልጅ በጣም ተስፋ ቆርጠው እንደነበር ታስታውሳለች። ኖኩቦንጋ በጭንቀት ውስጥ ነበረች ትላለች። በጣም ድሃ የሆኑ ሰዎችን ስታገኚ ገንዘብ ስለሌላቸው እናትየዋ ወደ እስር ቤት የምትሄድ ይመስላቸዋል። ይህ ደግሞ ጥብቅና የሚቆምላቸው ሰው አለ ብለው ሰለማያስቡ ነው። ቡህሌ ኖኩቦነጋ ክሱን ማሸነፍ እንደምትችል እርግጠኛ ብትሆንም ቀላል እንደማይሆን ገምታለች። ሁለቱም ግን ያልጠበቁት ነገር ቢኖር የማህበራዊ ሚዲያ የሚያደርግላቸውን ድጋፍ ነበር። በደቡብ አፍሪካ የአስገድዶ መድፈር ጥቃቶች ብዙም የማህበራዊ ሚዲያ ሽፋን አይሰጣቸውም፤ ነገር ግን የኖኩቦንጋ ድርጊት እናት ልጇን ለመከላከል ያላትን አቋም ማሳያ ነው በማለት የማህበራዊ ሚዲያውን ቀልብ ሳበ። የልጃቸውን ማንነት ላለመግለፅ ሲባል የኖኩቦንጋን ስም መጥቀስ ባልተቻለበት ጊዜ አንድ የመገናኛ ብዙሃን ተቋም አንበሳዋ እናት ብሎ ምስላቸውን ሴት አንበሳ ከልጆችዋ ጋር አድርጎ ይፋ አደረገው። ይህም ስም በመላ አገሪቷ አስተጋባ። መጀመሪያ ስሙን ስሰማ አልወደድኩትም ነበር፤ ልክ ግን የጀግንነት ምሳሌ መሆኑን ሳውቅ በጣም ደስ አለኝ ይላሉ እናት። የደቡብ አፍሪካ ሕዝብ የኖኩቦንጋን ክስ በመተቸት የህግ አማካሪ ጠበቃ እንዲኖራት ገንዘብ አሰባሰቡ። ወደ ፍርድ ቤት ስሄድ ስለፈራሁ ጠዋት ተነስቼ ፀለይኩኝ ይላሉ። ኖኩቦንጋ ፍርድ ቤት ሲደርሱ በሰዎች ተሞልቶ ነበር ያገኙት። ከመላዋ ደቡብ አፍሪካ የተሰባሰቡ ሰዎች ነበሩ። ለሰዎቹ አመሰግናለሁ እያልኩኝ እነሱ ሊደግፉኝ በመምጣታቸው በተስፋ ተሞላሁ። ፍርድ ቤት ስደርስ ክሱ እንዲነሳ ተወሰነ። በጣም ደስ አለኝ፤ ያኔ ዳኛው እኔ ሰውን የመግደል ሃሳብ እንዳልነበረኝ እንደተረዳ ገባኝ። ቡህሌ ቶኒስ የፍርድ ቤቱ ውሳኔ ሲፎካዚ ላይ የፈጠረውን ስሜት ታስታውሳለች። ፍርድ ቤቱ ክሱን እንዳነሳ ኖኩቦንጋ ወደ ልጇ ደወለች። ለመጀመሪያ ጊዜ ነበር ሲፎካዚ ስትስቅ የሰማኋት ያኔ ነበር። እሷም ለእናትዋ ወንዶቹ እንዲታሰሩ እንደምትፈልግም ነገረቻት ትላለች። ይህ ፍላጎቷ እውን እንዲሆን ከዓመት በላይ መጠበቅ ነበረባቸው። ከዚያም ባለፈው የታህሳስ ወር ላይ ሁለቱ ወንጀለኞች የ ዓመት እስራት ተወሰነባቸው። ሲፎካዚ በውሳኔው ደስተኛ ነኝ፤ አሁን ደህንነት ይሰማኛል ነገር ግን የእድሜ ልክ እስራት ይገባቸው ነበር ትላለች። ልክ ክሱ ሲጠናቀቅ ሲፎካዚ ሌሎች የዚህ ዓይነት ጥቃት ሰለባ የሆኑ ሴቶችን ለመደገፍ በማለት ማንነትዋን ለህዝብ ይፋ አድርጋለች። ኖኩቦነጋ በበኩላቸው በሚያስገርም ሁኔታ ልጃቸውን የደፈሩት ሰዎች ወደፊት ከእስር ሲወጡ መልካም ነገር ያደርጋሉ፣ ምሳሌም ይሆናሉ ብለው ተስፋ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል። ቢቢሲ ማስተባበያ
ሴቶች ፌሚኒስት መባልን ለምን ይጠላሉ
ፌብሩወሪ ማጋሪያ ምረጥ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የጾታ እኩልነት ጥያቄዎች ገፍተው ወደ አደባባይ እየመጡ ነው። በተለይም በአውሮፓና በሰሜን አሜሪካ ጉዳዩ ሰፊ ትኩረትና ሽፋን አግኝቷል። ያም ኾኖ ብዙ ሴቶች ፌሚኒስት መባልን አይሹም። በአሜሪካና በእንግሊዝ በተደረጉ ተከታታይ የዳሰሳ ጥናቶች እንኳ ብንመለከት ከአምስት ሴቶች አንዷ ብቻ ፌሚኒስት መባልን ትሻለች። ያም ሆኖ በጾታ እኩልነት የሚያምኑ ሴቶች ቁጥር እጅግ ከፍተኛ ነው። ሴቶችን አንድ ያደረጉ ንቅናቄዎች በቅርብ ዓመታት ውስጥ ጾታዊ ንቅናቄዎች ዓለምን ከዳር እስከ ዳር አነቃንቀዋል። ዶናልድ ትራምፕ በ ሥልጣን ሲይዙ ሚሊዮኖች አደባባይ ወጥተው ተቃውመዋቸዋል። የሰልፉ ዓላማ አደጋ ላይ ወድቆ የነበረውን የሴቶች መብትን መከላከል ነበር። በሆሊውድ የሃርቬይ ዌንስን ቅሌት ሴቶች ድምጻቸውን ካሰሙ በኋላ ዓለም ሚ ቱ በሚለው ንቅናቄ ተናውጦ ነበር። ተዋናይት አሊሳ ሚላኖ ጥቃት የደረሰባችሁ ሁሉ እኔም ተጠቅቻለሁ በሉ ካለች ወዲህ በ ሰዓታት ብቻ ግማሽ ሚሊዮን ሴቶች ምላሽ ሰጥተዋል። ይህ ቁልፍ ቃል በ አገራት መጠነ ሰፊ ንቅናቄን ፈጥሯል። ከዚህ ክስተት በኋላ በርካታ ሴት ተዋንያን ፌሚኒስት መሆናቸውን ይፋ አደረጉ። ያም ሆኖ ጥናቶች አሁንም የሚበዙ ሴቶች ፌሚኒስት የሚለው ቃል እንደሚጎረብጣቸው ነው። አሐዞች ምን ይናገራሉ በ በተደረገ አንድ ጥናት በመቶ የሚሆኑ ሴቶች ፌሚኒስት ነን ሲሉ ተናግረዋል። ይህ አሐዝ በ ፣ በመቶ ብቻ ነበር። በቅርብ ዓመታት ወደ አደባባይ የወጡ የጾታ እኩልነት ንቅናቄዎች ያመጡት ለውጥ ማሳያ ተደርጎ ተወስዷል። አሐዙ በአውሮፓ አገራት መካከል እንኳ ሰፊ ልዩነት እንዳለ ያሳያል። መጠይቅ ከተደረገላቸው የጀርመን ሴቶች ከመቶ ብቻ ፌሚኒስት ነን ሲሉ በአንጻሩ እጅ የሚሆኑት የስዊድን ሴቶች ፌሚኒስት ስለመሆናቸው በኩራት ተናግረዋል። ዋናው የጥናቱ ጭብጥ ስለምን ሴቶች ፌሚኒስት መባልን ጠሉ የሚለው ነው። የጥናቱ አስገራሚ ገጽታ ደግሞ ራሳቸውን ፌሚኒስት ብለው መጥራት የማይወዱ ሴቶች ብዙዎቹ በጾታ እኩልነት የማያወላዳ አቋም ያላቸው መሆኑ ነው። በመቶ እንግሊዛዊያን፡ ሴቶች ቤት መዋል አለባቸው ሺህ ሰዎች የተሳተፉበትና በ በአሜሪካ የተደረገ ሌላ ጥናት ከተጠያቂዎች ሁለት እጅ የሚሆኑ በጾታ እኩልነት የሚያምኑ ሆነው ተገኝተዋል። በ ይህ አሐዝ አንድ አራተኛ ብቻ ነበር። በተመሳሳይ በ በእንግሊዝ በተደረገ ሌላ ጥናት ከመቶ ስምንት እጅ የሚሆኑት ብቻ የሴቶች ሚና በቤት ውስጥ መወሰን ይኖርበታል ብለው እንደሚያምኑ ተናግረዋል። የተነጠቀ ልጅነት ሴቶች ልጅ በማሳደግና ምግብ በማብሰል መወሰን አለባቸው ብለው የሚያምኑ ዜጎች ቁጥር በ ዓ ም ከመቶ ደርሶ እንደነበር ማስታወስ ያሻል። ይህ አሐዝ የሚነግረን በዓመታት ውስጥ ትልቅ የአመለካከት ለውጥ መምጣቱን ነው። ጥያቄው አሁንም በዚህ ሰፊ የአስተሳብ ሽግግር በተደረገበት ዘመን እንኳ ፌሚኒስት መባል የማይወዱ ሴቶች ቁጥር ለምን ከፍተኛ ሆነ የሚለው ነው። ቃሉ አሉታዊ ገጽታንተላብሷል በ በተሠራ ሌላ የዳሰሳ ጥናት ከፍ ባለ የቢሮ ሥራ ላይ ያሉት ራሳቸውን ፌሚኒስት ብለው ለመጥራት አያፈገፍጉም። ነገር ግን ዝቅተኛ ሥራ ላይ በተሠማሩት መሀል ቃሉ እምብዛምም አይወደድም። ሌላ ጥናት እንዳሳየው ደግሞ ፌኒዝም በነጮች ዘንድ ካልሆነ በሂስፓኒክ፣ በእሲያና በጥቁሮች ዘንድ ጥሩ ስም የለውም። ሦስት እጅ የሚሆኑ ጥናቱ ላይ የተሳተፉ ሴቶች ፌሚኒዝም የነጭ ሴቶችን ሕይወት ያሻሻለ ነገር አድርገው ነው የሚወስዱት። ሌላው ለቃሉ አለመወደድ ምክንያት ተደርጎ በጥናት የተወሰደው ነባር አስተሳሰቦች ለውጥ አለማሳየታቸው ነው። ስካርሌት ከርቲስ በቅርብ ባሳተመችው በተሰኘው መጽሐፏ እንዳሰፈረችው ፌሚኒስቶች በ ዎቹ ትዳር ያልቀናቸው፣ ወንድ ጠል፣ በወሲብ ምርጫቸውም አፈንጋጭ፣ እንዲሁም ወንዳወንድ ተደርገው ይታሰቡ እንደነበረና ይህ አስተሳሰብ ከመቶ ዓመት በኋላም እንዳልተቀረፈ ታስረዳለች። በዳሰሳ ጥናቱ ላይ የተሳተፉ ብዙዎቹ ሴቶችም ራሳቸውን ፌሚኒስት ከሚል ቃል ማራቅ የሚሹት ሰዎች ከላይ በተጠቀሱት አሉታዊ መገለጫዎች የተነሳ ነው። ተያያዥ ርዕሶች
ፊቼ ጨምበላላ፦ የሲዳማ ሕዝብ አዲስ ዓመት
ሜይ አጭር የምስል መግለጫ የፌቼ ጨምበላላ በዓል ገንዘብ ያበደረ እንዲመለስለት የማይጠይቅበት፣ ከብት የማይታረድበት፣ ዛፍ የማይቆረጥበት፣ ያጠፉ ይቅር የሚባሉበት ዕለት ነው ጨምበላላ። የሲዳማ ሕዝብ የጨረቃና ከዋክብትን አቀማመጥ በማጥናት አዲስ ዓመት ያከብራል። በዓሉም ፊቼ ጨምበላላ ይባላል። ይህ በዓል መከበር ከጀመረ ከ ዓመታት በላይ ማስቆጠሩን የአገር ሽማግሌዎች ይናገራሉ። የባህል አጥኚው አቶ ብርሃኑ ሃንካራ ደግሞ የፊቼ ጨምበላላ በዓል የሲዳማ ሕዝብ ማንነቱን ከተረዳበት ጊዜ አንስቶ ሲከበር የቆየ ነው ይላሉ። የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና ባህል ተቋም ዩኔስኮ በቅርስነት የመዘገበው ይህ በዓል ዛሬ መከበር ጀምሯል። ፊቼ ጨምበላላ በዓል የሚከበርበት ቋሚ ቀን የለውም። በአያንቱዎች ጥቆማ መሰረት በዓሉ የሚከበርበት ቀን ይቆረጣል። ከዚያም ለበዓሉ ሰፊ ዝግጅት ማድረግ ይጀመራል። ከዋዜማው አንስቶ በዓሉ መከበር ይጀምራል። ጎረቤት ተሰብስቦም ከእንሰት የሚዘጋጀውን ቦርሻሜ ተብሎ የሚጠራውን ምግብ በወተት ይመገባሉ። አጭር የምስል መግለጫ ያገቡ ሴቶች ልዩ የሆነ የጸጉር አሰራር አላቸው ለበዓሉ ከሚበሉ ባህላዊ ምግቦችና ከሚከናወኑ ጭፈራዎች በተጨማሪ የተለያዩ ባህላዊ ሁነቶችም ይካሄዳሉ። ቄጠላ፣ ኛፋሮና የመሳሰሉ ሙዚቃዎችም በበዓሉ ይከወናሉ። ቄጠላ በተባለው ባህላዊ ሙዚቃ፤ አገር፣ ዘመን፣ የአገር ሽማግሌዎችና ታዋቂ ግለሰቦች እየተወደሱ ይጨፈራል። አጭር የምስል መግለጫ ቄጠላ የተሰኘው ባህላዊ ጭፈራ በቡድን ሲያዜሙ የፊቼ ጨምበላላ ዋነኛ ትርጉም ሰላም ነው የሚሉት አቶ ብርሃኑ ሃንካራ፤ አንድነትና ፍቅር የበዓሉ መለያ መሆናቸውን ይናገራሉ። የተጣሉ ሰዎች በፊቼ ጨምበላላ በዓል ላይ ይታረቃሉ። ሃዘን ላይ የነበሩ ሰዎችም የሃዘን ልብሳቸውን ይቀይራሉ። ፊቼ ጨምበላላ ዘንድሮ ያገባች ሴት ሙሽርነቷን ጨርሳ ከሌሎች ሴቶች ጋር የምትቀላቀልበት በዓል ነው። በተለያዩ ምክንያቶች ከቀዬው ርቆ የነበረ ሰው ለፊቼ ጨምበላላ ወደቀዬው ይመለሳል። አጭር የምስል መግለጫ በበዓሉ ወቅት ለአካባቢ እና ለእንስሳት ትልቅ ትኩረት ይሰጣል ለዚህ በዓል ተብሎ እርድ አይፈጸምም፤ ስጋም አይበላም። ክብቶችን መምታትም ክልክል ነው። ላሞች ሳር የበዛበት መስክ ላይ ይሰማራሉ። በሲዳማ ሕዝብ ዘንድ በፊቼ ጨምበላላ በዓል ወቅት ማረስ ነውር ነው። ለዚህም ምክንያቱ ደግሞ የፊቼ ጨምበላላ በዓል የሲዳማ ሕዝብ ብቻ ሳይሆን የተፈጥሮም ነው ተብሎ ስለሚታመን ነው።ፊቼ የአዲስ ዓመት በዓል ዋዜማ ሲሆን፤ ጨምበላላ ደግሞ የአዲስ ዓመት መጀመሪያው ቀን ነው። አጭር የምስል መግለጫ የእድሜ ባለጸጎች ሁሉቃ ሲሠሩ ሲዳማ ከአንድ ዓመት ወደሌላው የሚሸጋገርበት ሂደት ሁሉቃ ይባላል። ሁሉቃ ማለት ከሸምበቆና ከአርጥብ ቅጠል ተሠርቶ የሚቆም ነገር ነው። ሁሉቃ በቤተሰብና በማኅበረሰብ ደረጃ የሚሠራ ሲሆን፤ አዲስ ዓመት ሲገባ ሰዎችና ከብቶች ይተላለፉበታል። የሲዳማ ሕዝብ አዲስ ዓመትን ሲቀበሉ፤ ዓመቱ የብልጽግና እንዲሆንላቸው ፊቼ ጄጂ ይላሉ። ተያያዥ ርዕሶች
ኢራናዊና አሜሪካዊ ሰላዮች በእስረኛ ልውውጥ ስምምነት ነፃነታቸውን ተቀዳጁ
ዲሴምበር ኢራንና አሜሪካ ባልተለመደ ሁኔታ ባደረጉት የሁለትዮሽ ስምምነት እስረኛ ለመቀያየር ወስነዋል። ልውውጡ ኢራን ውስጥ ሲሰልል የተገኘ አንድ ትውልደ ቻይናዊ የሆነ አሜሪካዊ ተመራማሪና እንዲሁም በአሜሪካ እስር ቤት የነበረ ኢራናዊ ሳይንቲስት መካከል ነው። ሁለቱም ሃገራት የስለላ ውንጀላውን ክደውታል። የእስረኛ ልውውጡን እወጃ ተከትሎ የኢራኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደስታቸውን ገልፀዋል። አምስቱ ተስፋ የተጣለባቸው አፍሪካውያን ሙዚቀኞች የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በበኩላቸው ከሰዓታት በኋላ በትዊተር ገፃቸው ላይ መልዕክታቸው ያሰፈሩ ሲሆን ፍትሃዊ ስለሆነው ድርድር ኢራንን እናመሰግናለን፤ መስማማት ላይ ልንደርስ እንደምንችልም ይህ ማሳያ ነው ብለዋል። አሜሪካዊው ጁዩ ዋንግአ በኢራን መንግሥት በቁጥጥር ስር የዋለው ከሶስት አመታት በፊት ሲሆን የቀረበበት ክስም ከውጭ ሃገር መንግሥታት ጋር በመመሳጠር የሚል ነው። በወቅቱ በኢራን ዩኒቨርስቲ የምርምር ስራውን እየሰራ የነበረው ጁዩ ጥብቅ መረጃዎችን ለአሜሪካና እንግሊዝ ተቋማት ሊሰጥ ነበር በሚል በስለላ ወንጀል አስር አመት ተፈርዶበትም ነበር። ኢራናዊው ሳይንቲስት ፕሮፌሰር መስዑድ ሶለይማኒ በበኩሉ በቁጥጥር ስር የዋለው ባለፈው አመት ቺካጎ አየር ማረፊያ ላይ ነበር። ኢራን ላይ የተጣለባትን የንግድ ማዕቀብ በመጣስ ለኒውክሌር ፕሮግራም የሚሆን አንዳንድ ቁሳቁሶች ወደ ኢራን ሊያስገባ ሲል ይዘነዋል በሚል ክስ ነው የቀረበበት። ከጊዜ ወደ ጊዜ እየሻከረ በመጣው የሁለቱ ሃገራት ግንኙነት ምክንያትም ምንም አይነት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እንዳይኖራቸው አድርጓል። ይህንንም ተከትሎ ስዊዘርላንድ ሁለቱን ሃገራት በማሸማገል ሚና ተጫውታለች፤ በአፀፋው ሁለቱም ሃገራት ምስጋና ችረዋታል። በስዊዘርላንድ መንግሥት አውሮፕላን ከቴህራን ወደ ዙሪክ የበረረው ጁዩ ዋንግ ሙሉ የህክምና ምርመራ ከተደረገለት በኋላ ወደ ሃገሩ ይገባል ተብሏል። ፕሮፌሰር መስኡድ ሶለይማኒም በተመሰሳይ ወደ ዙሪክ የበረረ ሲሆን ቀጣዩ ጉዞውም ወደ እናት ሃገሩ ኢራን ይሆናል። የልውውጡንም ሆነ የመለቀቃቸውን ዜና ያበሰሩት የኢራኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጃቫድ ዛሪፍ ሲሆኑ ከፕሮፌሰር መስዑድ ጋር የተነሱትንም ፎቶ በትዊተር ገፃቸው አጋርተዋል። ፕሮፌሰር መስዑድ ሶለይማኒ እንዲሁም ጁዩ ዋንግ ተፈትተው ቤተሰቦቻቸውን ሊያገኙ መሆናቸው በጣም አስደስቶኛል የሚል መልእክትም በትዊተራቸው ላይ አስፍረዋል። ዶናልድ ትራምፕ በሰጡት መግለጫ ጁዩ ዋንግ በስለላ ሽፋን ታስሮ ነበር። በአስተዳደራችን ቅድሚያ የምንሰጠው ጉዳይ ቢኖር በተለያዩ ሃገራት በእስር ላይ የሚገኙ ዜጎቻችን ነፃ ማውጣት ነው ብለዋል። የጁዩ ዋንግ ባለቤት ሁዋ ኩ በበኩሏ ቤተሰባችን አሁን ሙሉ ነው። ልጃችን ሻኦፋንና እኔ ሶስት አመታት በሙሉ በሰቀቀን ይህችን ቀን ጠብቀናል፤ የተሰማኝንም ደስታ በቃላት መግለፅ ይከብደኛል። ለረዱን አካላት በሙሉ ምስጋናችን ይድረሳቸው ብላለች በሰጠችው መግለጫ የድህረ ምረቃ ትምህርቱን እየተከታተለበት የነበረው ፕሪንስተን ዩኒቨርስቲ ከእስር የመለቀቁን ዜና በተመለከተ ባወጣው መግለጫ ከፍተኛ ደስታ እንደተሰማቸው በመግለጽ እንኳን ደህና መጣህ ብለውታል። ተያያዥ ርዕሶች
ሕንድ፡ ለሴቶች የተከለከለ ተራራን የወጣችው የመጀመሪያ ሴት
ጃንዩወሪ አጭር የምስል መግለጫ ዳንያ ሳናል ተራራውን የወጣች የመጀመሪያ ሕንዳዊት ናት ዳንያ ሳናል የተባለች ሕንዳዊት ለወንዶች ብቻ የተፈቀደ ተራራ በመውጣት ግንባር ቀደም ሆናለች። ተራራው አግስታይኮዳም ይባላል። ተራራው ጫማ ሜትር ርዝመት አለው። ይህን ተራራውን መውጣት እንደ ሀይማኖታዊ ጉዞ ይቆጠራል። የሕንድ ፍርድ ቤት በቅርቡ ሴቶች ተራራውን እንዲወጡ ከመፍቀዱ በፊት፤ ተራራው ጫፍ መድረስ የተፈቀደው ለወንዶች ብቻ ነበር። ዳንያ ተራራውን በመውጣት ታሪክ ብትሰራም፤ የሂንዱ እምነት ተከታይ የቀዬው ነዋሪዎች ሴቶች ተራራውን እንዲወጡ በመፈቀዱ ደስተኛ አይደሉም። የ ዓመቷ ዳንያ ለቢቢሲ እንደተናረችው፤ ተራራውን ስትወጣ ሊያስቆማት የሞከረ ሰው አልነበረም። የመብት ተሟጋቾች የዳንያ ጉዞ ለሴቶች መብት መከበር የሚያደርጉት ትግል መገለጫ መሆኑን ተናግረዋል። ሴቶች ተራራውን መውጣት እንዲፈቀድላቸው የድጋፍ ፊርማ አሰባስበው ወደ ሕንድ ፍርድ ቤት ያቀኑ ሴቶች ደስታቸውን ገልጸዋል። ከሴቶቹ አንዷ ዲቫያ ዲቫክራን የሴቶችን ጭቆና ለማስቆም አንድ ርቀት ወደፊት ተራምደናል ስትል ለቢቢሲ ተናግራለች። በሕንዷ ካርላ የሚገኘው አግስታይኮዳም ተራራ ከአካባቢው ተራሮች በርዝመት ሁለተኛው ነው። የአካባቢው ተወላጆች ሴቶች ተራራውን እንዲወጡ መፈቀዱ እምነታችንን ይጻረራል ቢሉም ፍርድ ቤቱ አቤቱታቸውን ውድቅ አድርጎታል። ዳንያ ተራራውን እየወጡ ከነበሩ ወንዶች ብቸኛዋ ሴት ነበረች። በቀጣይ ሳምንታት የእሷን ፈለግ በመከተል ወደ ሴቶች ተራራውን ለመውጣት ተመዝግበዋል። ተያያዥ ርዕሶች
የበር መጥሪያ ደወል ኩባንያ ለፌስቡክና ለጉግል መረጃ አሳልፎ እየሰጠ ነው ተባለ
ጃንዩወሪ ማጋሪያ ምረጥ የበር መጥሪያ ደወል ኩባንያ የደንበኞቹን መረጃ አሳልፎ ፌስቡክና ጉግልን ለመሳሰሉ ድርጅቶች አሳልፎ እየሰጠ እንደሆነ አንድ ምርመራ አጋልጧል። የራሱ አፕሊኬሽን መተግበሪያ ያለው ሪንግ አፕ የተሰኘው የበር መጥሪያ ደወል መከታተያ እንዲሁም የደንበኞችን ግላዊ መረጃዎችን መላክ እንዲያስችሉ አድርገው እንደተሰሩ ኤሌክትሮኒክ ፍሮንቲየር ፋውንዴሽን የተሰኘው ድርጅት በሪፖርቱ አመልክቷል። መረጃው እንደሚያሳየው አምስት ኩባንያዎች የተለያዩ መረጃዎችን ለምሳሌም ያህል የደንበኞችን ስም፣ ደንበኞች ስልካቸውን የሚጠቀሙበትን አድራሻና የሞባይል ኔትወርክን የመሳሰሉ አግኝተዋል ተብሏል። አደጋውን ስሰማ በረራው ጠዋት እንዳልሆነ ራሴን አሳመንኩኝ የረዳት አብራሪው ጓደኛ ኩባንያው ሪንግ በበኩሉ አሳልፎ የሰጠው መረጃ የተወሰነ እንደሆነ ነው። ኩባንያው ጊዝሞዶ ለተባለው የእንግሊዝ ሚዲያ እንደተናገረው እንደ ማንኛውም ኩባንያ ሪንግ የሞባይል መተግበሪያውን ለመፈተሽ በዚያውም ያሉትን አገልግሎቶች ለማሻሻል፣ እንዲሁም ደንበኞች በአገልግሎታችን ምን ያህል ረክተዋል የሚለውን ለማየት የሦስተኛ ወገን አገልግሎትን እንጠቀማለን። ኩባንያው ይህንን ይበል እንጂ ፋውንዴሽኑ በበኩሉ የደንበኞችን ግላዊ መረጃ መጠበቅ እንደተሳነውና በተለይም ከክትትል ጋር ተይይዞ ኩባንያው ለማንም የማያጋራው መረጃ እንደሆነ ቢገልፅም የተባለው ተግባራዊ አልሆነም ብሏል። ይህንን መረጃ በማጋራት ደንበኞች በማንኛውም ወቅት የጣት አሻራቸውን በመጠቀም ተንቀሳቃሽ ስልካቸውን በሚጠቀሙበት ወቅት የትኛውንም እንቅስቃሴያቸውን ለመሰለል አስችሏል ተብሏል። ኩባንያው የደንበኞችን መረጃን ያቀበለው ለፌስ ቡክ፣ ብራንች፣ አፕስ ፍላየር፣ ሚክስ ፖናልና ጉግል የመረጃ ኩባንያዎች ነው። የፋውንዴሽኑ ምርመራ እንደሚያሳየው ሪንግ ኩባንያ መረጃዎችን አሳልፎ የሰጠው አንድሮይድ ሶፍትዌሮችን ለሚቀብሉ ስልኮች ነው። ሪንግ የተባለው የበር መጥሪያ ደወልና ለቤት አገልግሎት የሚውሉ ካሜራዎችን እንዲሁም የደህንነት ቁሳቁሶችን የሚያቀርብ ሲሆን ባለቤትነቱም የአማዞን ነው። ኩባንያው ከዚህ ቀደምም ካሜራዎቹንና የደህንነት ቁሳቁሶቹን ለህግ አስከባሪ አካላት ለስለላ ተግባር አውሏል በሚል ተወንጅሏል። ከዚህ በተጨማሪ ጎረቤታሞች የስለላ ተግባር እንዲያከናውኑ በር ከፍቷል፤ እንዲሁም ካሜራዎቹም በተለያዩ አካላት እንደተጠለፉ መረጃዎችም በመውጣት ላይ ናቸው። ተያያዥ ርዕሶች
መነሻ ሀሳብ ወይስ የሙዚቃ ቅጂ መብት ጥሰት
ኦገስት ማጋሪያ ምረጥ አጭር የምስል መግለጫ ብለርድ ላይንስ የተሰኘው ሮቢን ቲኬ ከፋረል ዊሊያምስ ጋር የተጫወቱት ሙዚቃ ከ ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ አስገኝቷል። በአሁኑ ወቅት አርቲስቶች ሙዚቃ ሲሰሩ መነሻ ሀሳቡን ከሌላ ቀደምት አርቲስት መውሰዳቸውን እንዳይናገሩ ይመከራሉ። ምክንያቱም የሙዚቃ ኮፒ መብት ሕግን ተጠቅመው የዋናው ዜማ ባለቤቶች እንዳይከሷቸው። ይህ ነገር ለሙዚቀኞች ፈጠራ መፈናፈኛ ያሳጣቸዉ ይሆን በሙዚቃ ጥበብ ውስጥ ዋና ወይም አዲስ የፈጠራ ስራ የሚባል ነገር የለም የሚለዉ የሙዚቃ አቀናባሪው እና ዜማ ቀማሪው ናይል ሮጀርስ ሙዚቃን ምንማረው በልምምድ ነው ምንድነው የምንለማመደው ንድፍ እና መለኪያውን ነው። ሙዚቃን መስራት ማለት እነዚህ የተማርናቸውን ህጎች ተግባር ላይ ማዋል ማለት ነው። በማለት ጨምሮ ያስረዳል። በዓለም ዙሪያ ያሉ የሙዚቃ ሰንጠረዦቸን ብናጠና ሙዚቃ ሰሪዎች ከሚያደንቋቸው እና እንደ አርኣያ ከሚያይዋቸው ቀደምት እና ዘመናዊ ሙዚቀኞች መነሻ ሀሳብ ያልወሰደ ማግኘት ይከብዳል። በአሁኑ ወቅት ግን ሙዚቀኞቹ መነሻ ሀሳብ የወሰዱበትን ቀደምት አርቲስት ስም እንዳይናገሩ ይበረታታሉ። ይህም ሁኔታ ሮቢን ቲክ እና ፋረል ዊሊያምስ ብለርድ ላይንስ ብለው ለተጫወቱት ሙዚቃ መነሻ ዜማውን ከማርቪን ጌይ ጋ ቱ ጊቭ ኢት አፕ ወስዳችሗል በሚል ለማርቪን ጌይ ቤተሰቦቹ ሚሊዮን ዶላር ካሳ መክፈል ግድ ሆኖባቸዋል። ምንም እንኳን ፍርድ ቤት አሁንም ጉዳዩ በይግባኝ ምክንያት እንደተጠለንጠለ ቢሆንም። ይህ ክስተት ለብዙ ሙዚቀኞች ትልቅ መልዕክት ትቶ ያለፈ እንደሆነ ይነገራል። ፋረል ዊሊያምስ ፍርድ ቤት ቀርቦ ስለ ጉዳዩ አስተያየት ሲሰጥ የማርቪን ጌይ ጋ ቱ ጊቭ ኢት አፕ እና ሌሎች ሙዚቃዎችን እየሰማ ያደገ በመሆኑ የ ዎቹን ሙዚቃ መልሶ ወደ ገበያው ለማምጣት ያደረገው ጥረት እንጂ ኮፒ ለማድረግ አስቦ እንዳልነበረ አሳውቋል። እንደ ሙዚቃ ባለሙያው ፒተር ኦክሰንዴል አባባል መነሻ ሀሳብ አሁን አሁን ከኮፒ መብት ሕግ ጥሰት ጋር እየተያያዘ ስለሆነ ነገሩ ለሙዚቃ ሰሪዎች አሳሳቢ እየሆነ መጥቷል። ፒተር አክሎም ሙዚቃ አምራች ኩባንያዎች አንድ አዲስ ሙዚቃ ቀደም ካለ ሙዚቃ ጋር በሆነ መልኩ ግንኙነት ካለው ጉዳዩ ያስጨንቃቸዋል ይላል። የፉጨት መብት ከማርቪን ጌይ ቤተሰቦች ጋር የሚሰራው ጠበቃው ሪቻርድ ቡስክ እንደሚለው ከሆነ ግን ከብለርድ ላይንስ ጋር ተያይዞ የሚነሳው ጉዳይ ማለትም ክሱ በስሜት ላይ ተሞርኩዞ ነው የተመሰረተው የሚባለው ሀሰት እንደሆነ ይናገራል። ሰማዩ ሊደፋ ነው። ሙዚቀኞች መስራት እየቻሉ አይደለም። በአደባባይ ሟፏጨት እንኳን ያስከስሳል እየተባለ የሚወራው ከነ ፋረል ዊሊያምስ እና ሮብን ቲኬ ሰፈር የተነዛ አሉባልታ ነው ሲል ያጣጥለዋል። እንደውም እንደ እውነታው ከሆነ ጉዳዩ መረን ለቋል። ለምሳሌ በ ብለርድ ላይንስ እና በ ጋ ቱ ጊቭ ኢት አፕ መካከል ወደ የሚሆኑ ቅንብራዊ መመሳሰሎች አሉ። በማለት ሪቻርድ ይናገራል ያም ሆኖ ለእነ ኤድ ሺረን፥ ኤልተን ጆን፥ እንዲሁም ሮሊንግ ስቶን ጠበቃ ሆነው ከሚያገልግሉት አንዱ የሆነው እንግሊዛዊው ሳይመን ዲክሰን ሲናገር በሙዚቃ ኮፒ መብት እና በመነሻ ሀሳብ መካከል ባለው ግጭት ብዙ የሙዚቃ ባለሙያዎች እየተማረሩ ነው። ተመሳሳይ ጉዳየች እዚህ እንግሊዝ ውስጥ ወደ ፍርድ ቤት ቢሄዱ ጉዳዩ ከአሜሪካ በተለየ ሁኔታ ነው የሚዳኘው ይላል ዲከሰን። ሙዚቃ እንግሊዛዊቷ ዘፋኝ እና የግጥም ወዜማ ደራሲ ሎውራ ምቩላ ግን ሙዚቀኞች የራሳቸውን የፈጠራ ስራ መስራት ከቻሉ ሌሎች ነገሮች የሚያሳስቡ አይደሉም ትላለች። ሁላችንም የሆነ የሚያነሳሳን ነገር ይኖራል። ተጽዕኖ የሚፈጥርብንም ነገር አይጠፋም። ነገር ግን የሙዚቀኛው ትልቁ ፈተና ሁሌም አዲስ ነገር ይዞ በመምጣት ወደፊት መጓዝ ነው በማለት ጨምራ ትናገራለች። ሌላኛው ዘፋኝ እና ግጥም ወዜማ ደራሲ ጌሪ ኑማንም በሎውራ ሀሳብ ይስማማል። ሁላችንም ሀሳብ የምናመነጨው ካለ ነገር ነው። ብልጠቱ የሚሆነው ይሄንን ሀሳብ ተጠቅሞ አዲስ ነገር መፍጠሩ ላይ ነው ይላል። ከሁለት ወር ባነሰ ጊዜ ውስጥ የ ብለርድ ላይንስ ጉዳይ በይግባኝ ጥያቄ መሰረት እንደገና ወደፍርድ ቤት ይቀርባል። በአሁኑ የፍርድ ቤት ቀጠሮ የ ብለርድ ላይንስ ዘፋኞች እንደሚሳካላቸው ተስፋ ያደርጋሉ። ወጤቱ ምንም ይሁን ምን ግን የሙዚቃ ኢንዱስትሪው በኮፒ መብት ሕግ ላይ ያለው አቋም አወዛጋቢ እንደሆነ ይቀጥላል። ተያያዥ ርዕሶች
ይህንን ለማጋራት በ ዋትስአፕ
የኢትዮጵያን የሙዚቃ ኢንዱስትሪ ከሚፈታተኑ በርካታ ነገሮች መካከል አንዱ ቴክኖሎጂ ነው። በመጀመሪያ በሸክላ ይደመጥ የነበረው ሙዚቃ ወደካሴት ከዚያም ወደሲዲ ፈቅ እያለም በሶፍት ኮፒ መሸጥ ጀመረ። ሁላችንም የስልካችን ምርኮኛ፤ የስልካችን እስረኛ እየሆንን መምጣታችን ለኢትዮጵያ ሙዚቀኞች የሲዲ ገበያ ቸር ወሬ አልነበረም። ለበርካታ ጊዜያት ጎምቱ ድምጻውያንም ሆኑ አዳዲስ ሙዚቀኞች ሥራዎችን ጨርሰው ለገበያ ለማውጣት እግር ተወርች ከሚያስራቸው ጉዳይ አንዱ የላባቸውን ዋጋ በአግባቡ የሚያገኙበት መሸጫ አለመኖሩ ነበር። ሙዚቃ አቀናባሪው ኤሊያስ መልካ እኔ ጋር እንኳ የበርካታ ድምፃውያን ሥራ አልቆ ቁጭ ብሏል በማለት እማኝነቱን ይሰጣል። ለኤሊያስ የሲዲ ቴክኖሎጂ እየቀረ መምጣቱም ሌላው የሙዚቃ ገበያውን አደጋ ላይ የጣለ ጉዳይ ነው። ሲዲ የሚወስዱ ቴፕ ሪከርደሮች እየቀሩ፣ ጂፓስ በየቤታችን እየገባ፣ መኪኖች ሳይቀር ፍላሽ ብቻ እንዲያጫውቱ እየሆኑ መምጣታቸውን ያስተዋለው ኤልያስ ከዘመኑ ቴክኖሎጂ ጋር የሚሄድ መፍትሔ ከመሞከር አልቦዘነም። የኢትዮጵያ ሙዚቀኞች ማኅበር ፕሬዝዳንት ዳዊት ይፍሩም የኤልያስን ስጋት ይጋራሉ። በኛ አገር ሙዚቀኞች ሥራቸውን ይሠሩና መርካቶ ላሉ አሳታሚዎች በመስጠት ይሸጣሉ በማለት የሙዚቃ ገበያውን አሠራር ያስረዳሉ። በ ፍቅር እስከ መቃብር ላይ ህይወት የዘራው አባቴ ነው አሳታሚው ካሳተመ በኋላ ደግሞ በመላው አገሪቱ በማሰራጨት ሽያጭ ይካሄድ ነበር፤ በማለት የድሮውን የሙዚቃ የገበያ ሥርዓት ያብራራሉ። በዚህ መካከል ድምፃውያን አንዴ በተነጋገሩበት ዋጋ ይሸጣሉ፤ ከዚያ በኋላ ምን ያህል ያወጣል ምን ያህል ያተርፋል የሚለው ላይ እጃቸውን አያስገቡም በማለትም ያክላሉ። ዓመት ዓመትን ሲወልድ አሠራሩ እየተቀየረ መጥትቷል። ካሴት የሚያሳትም የለም። ሲዲ የሚያሳትመውም ቁጥሩ ቀንሷል። ላሳትም ብሎ ደፍሮ ሥራውን ለገበያ የሚያቀርብ ባለሙያም ፈተናው ብዙ ነው። በቀላሉ ኮፒ ተደርገው የሚሸጡበት በመሆኑ ከአጠቃላይ ከሽያጩ እጠቀማለሁ ማለት አይችልም ይላሉ። ባህልን በኤሌክትሮኒክ ሙዚቃ የቀመመው ሮፍናን ለዚህም ነው በዚህ ዘመን አሳታሚ የሌለው ይላሉ አቶ ዳዊት። አሁን ያለው ድምፃዊ ተበድሮም ይሁን ተለቅቶ አንድ ነጠላ ዜማ ካወጣ በኋላ ድምፃዊው ስራው ከተወደደለት ሰርግ ወይንም ግብዣዎች ላይ ሲቀናም ከሀገር ውጪ እየተጋበዘ ይሰራል በማለት ያለውን ውጣ ውረድ ይገልጣሉ። ይህም ከሲዲ ሽያጭ አተርፋለሁ የሚል ድምፃዊ እንዳይኖር አድርጓል። ታዲያ ምን ተሻለ የሙዚቃ አቀናባሪው ኤልያስም ሆነ የሙዚቀኞች ማኅበር ፕሬዝዳንቱ ዳዊት ስጋት ይቀረፍ ዘንድ መፍትሔ ይሆናል በማለት፤ የሙዚቃ ባለሙያዎች ሰብሰብ ብለው ሀሳብ ያወጡ ያወርዱ ከጀመሩ አምስት ዓመት አልፏቸዋል። በኋላም የኢትዮጵያ የሙዚቃ ባለሙያዎች ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር ያዘጋጁት አውታር የሙዚቃ መሸጫ መተግበሪያና ድረ ገጽ ሥራወን በማጠናቀቅ ዓርብ ግንቦት ቀን ዓ ም በይፋ ሥራ ይጀምራል ተባለ። አዲሱ አመተግበሪያ ኢትዮጵያውያን የፈለጉትን ሙዚቃ በፈለጉት ጊዜና ቦታ በእጅ ስልኮቻቸው በኢንተርኔት አማካይነት ለመግዛት ያስችላቸዋል ይላል ኤልያስ። አውታር መልቲ ሚዲያ የተመሰረተው በኤልያስ መልካ፣ ጆኒ ራጋ፣ ዳዊት ንጉሡና ኃይሌ ሩትስ ሲሆን፤ በመተግበሪያው ከሚሸጡት ሙዚቃዎች ኢትዮ ቴሌኮም ድርሻ ይኖረዋል። አዝማሪዎቻችን የሙዚቃ ሳይንቲስቶች ናቸው ድምፃዊት ፀደኒያ ገብረማርቆስ ይህን የሙዚቃ መሸጫ አማራጭ ከሚደግፉት አንዷ ነች። ስልጡን አማራጭ ስትልም ትጠራዋለች። የኢንተርኔት አቅምና ተደራሽነት ከፈቀደ በርካታ ሙዚቃ መሸጥ ይቻላል በማለት ተስፋዋን ትገልጻለች። ሰዎች ዘመናዊ ስልክ መያዝ በመጀመራቸው፣ ኢንተርኔት አጠቃቀማችንም ከፍ እያለ በመምጣቱ እንደዚህ አይነት የመሸጫ መንገድ ማስለመዱ መልካም መሆኑን ትገልፃለች። ድምጻዊት ፀደኒያ እስካሁን ስራዎቿን ወደ አውታር ወስዳ በእናንተ በኩል ይሸጥልኝ ብላ ባትሰጥም፤ አገልግሎቱ ከተጀመረ ግን ይህንን ለማድረግ አይኗን እንደማታሽ ትናገራለች። ታዋቂዎቹ ኤርትራዊያን በሙዚቃቸው ምክንያት ይቅርታ ጠየቁ ብዙ ሰዎች በአንድ ሲዲ ውስጥ ያሉ ሥራዎችን በአጠቃላይ ስለማይወዱት እያለፉ ነው የሚያደምጡት የምትለው ፀደኒያ፤ ግዴታ አስራ ምናምን ዘፈኖች መግዛት አይጠበቅባቸውም ትላለች። ይህ አዲስ መተግበሪያ አንድ ሰው የሚፈልጋቸውንና የሚመርጣቸውን ዘፈኖች ብቻ መርጦ የመግዛት እድል ስለሚሰጥ ተመራጭ መገበያያ መንገድ ነው ስትል ሀሳቧን ታጠናክራለች። አውታር ፡ ችግር የወለደው መፍትሔ ኤልያስና ጓደኞቹ ኢትዮ ቴሌኮም ለተጠቃሚዎቹ አጫጭር መልእክቶችን በጅምላ ሲልክ ሲመለከቱ፤ እኛስ በዚህ መንገድ ለምን ሙዚቃ አንሸጥም የሚል ሀሳብ እንዳፈለቁ ያስታውሳል። ኢትዮ ቴሌኮም ዘንድ ቀርበው ሀሳባቸውን ሲያስረዱ ግን በአጫጭር መልእክት ጽሑፍ እንጂ ድምፅ መላክ እንደማይቻል ተነገራቸው። እነኤልያስ በሙዚቃ ሥራ ውስጥ በየእለቱ ቴክኖሎጂ ሲቀየር ተመልክተዋል። ከካሴት ወደ ሲዲ በሄድንበት ፍጥነት የሲዲ ቴክኖሎጂም ሲቀየር ተመልክተናል ይላል። ስለዚህ በድረገጽ የሚሸጡበት መንገድ ያስቡ ጀመር። ተፈራ ነጋሽ፡ በነገራችን ላይ ሙዚቃ አልተውኩም ይህ ሀሳብ ግን ከዝሆን የገዘፈ ችግር ከፊቱ አለ። ሰዎች ሙዚቃውን መግዛት ቢፈልጉ በምን ሥርዓት መክፈል እንደሚችሉ አይታወቅም። ምክንያቱ ደግሞ የባንክ የክፍያ ስርዓትን በኦን ላየን ግብይት ማድረግ ስለማያስችል ነው። ስለዚህ ያለው አማራጭ ቴሌ ብቻ ነው። ቴሌ ከእሱ ፈቃድ ወስደው አጫጭር መልዕክቶችን ለሚልኩ ድርጅቶች ከተጠቃሚዎች ገንዘብ ቆርጦ የድርሻውን በመውሰድ ለድርጅቱ ደግሞ የድርሻውን ይሰጣል። ቴክኖሎጂው ለጽሑፍ ብቻ ስለሆነ ሙዚቃ መላክ አያስችልም ቢባሉም እነድምፃዊ ኃይሌ ሩትስ ተስፋ ሳይቆርጡ ተመላልሰው ከቴሌ ጋር ተነጋገሩ። ለዚህ ምክንያት የሆናቸው ቴሌ ፓኬጅ ዳታ መሸጥ መጀመሩ ነው። በፓኬጅ ዳታው ከፍ ያለ ሜጋ ባይት ኢንተርኔት ስለሚሸጥ፤ ምናልባት አሁን ሳይቻል አይቀርም የሚል ተስፋ አደረባቸው። የኢትዮ ቴሌኮም ኃላፊ የነበሩት አቶ አንዱዓለም አድማሴም ይቻላል አሏቸው። መነሻ ሀሳብ ወይስ የሙዚቃ ቅጂ መብት ጥሰት ኤልያስ አሁንም ግን ቴሌ ራሱ ከጽሑፍ ውጪ ሌላ መልእክት ለመላክ ዝግጁ ስላልነበር ወደሥራ ለመግባት ፈተና እንደሆነባቸው ይናገራል። የሙዚቃ ባለሙያዎቹ ኤልያስ፣ ጆኒ ራጋ፣ ኃይሌ ሩትስና ዳዊት ንጉሡ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በጋራ የሚሠሩት ይህ የሙዚቃ መሸጫ መተግበሪያ ከ ዎቹ ጀምሮ የተሠሩ፤ የኢትዮጵያ ሙዚቃዎችን ያቀርባል ተብሏል። እነዚህ ሙዚቀኞች ሥራውን ለመሥራት ከቴሌ ጋር ለመሥራት ፈቃድ ማውጣት ያስፈልግ ስለነበር የንግድ ፈቃድ ማውጣት አስፈልጓቸዋል። በዚህ ምክንያት አውታር መልቲ ሚዲያን አቋቋሙ። ድርጀቱ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በጋራ መሥራት የቫስ ፈቃድ ማውጣታቸውንም ገልጠዋል። ሦስቱ የሙዚቃ ባለሙያዎች በመጪው ዓርብ ማታ በሸራተን ይፋ የሚደረገውን የሙዚቃ ሽያጭ ሥርዓት፤ የአገሪቱ የሙዚቃ ኢንዱስትሪ የገጠሙትን ፈተናዎች ለመወጣት ኹነኛ መንገድ ነው የሚል ዕምነት አላቸው። በዚሁ የሽያጭ ሥርዓት ድምፃዊ፣ የግጥም ጸሐፊ፣ የሙዚቃ አቀናባሪ፣ የዜማ ደራሲና ፕሮዲውሰር ትርፍ እንዲከፋፈሉ ይደረጋል። ሙዚቃው በአውታር መተግበሪያ ተጭኖ እንዲሸጥ አምስቱ ባለሙያዎች ተስማምተው መፈረም ይኖርባቸዋል ይላል ኤልያስ። አሁን ሰዎች በአንድ ጊዜ አገልግሎቱን ፈልገው ቢመጡ ሊከሰቱ የሚችሉ መዝረክረኮችን ለማስቀረት እየሞከርን ነው የሚለው ኤልያስ፤ ከአርብ ማታ ጀምሮ መተግበሪያው በጎግል ፕሌይ ስቶር ይገኛል ይላል። በዝማሬ የተካኑት ዓሳ ነባሪዎች ይህንን መተግበሪያ በሞባይሉ ላይ የጫነና በአገር ውስጥ የሚገኝ ማንኛውም ሰው በቀላሉ ሙዚቃውን መጫን የሚችል ሲሆን፤ ካልሆነ ደግሞ ኢትዮ ቴሌኮም ሊንክ የሚልክ ይሆናል በማለት አፕሊኬሽኑን ለማስተዋወቅ የሚጠቀሙበትን መንገድ ያብራራል። ኢትዮ ቴሌኮም ለተጠቃሚዎቹ በአጠቃላይ የሚልከው ጥቅል መልእክት ላይ ማስፈንጠሪያውን አብሮ እንደሚልክ የሚናገረው ኤልያስ፤ ስማርት ስልክ ያላቸው ማስፈንጠሪያውን ሲጫኑ ወዲያውኑ በስልካቸው ላይ መተግበሪያው የሚጫን ሲሆን፤ ስማርት ስልክ የሌላቸው ግን በቁጥር እያስመረጠ እንዲጠቀሙ የሚያስችለው ዩ ኤስ ኤስ ዲ የሚባለው ቴክኖሎጂ ለመጨረስ በሥራ ላይ መሆናቸውን ይገልጣል። የአውታር ትሩፋቶች ምን ምን ናቸው መተግበሪያው ምስሎች፣ ስለዘፋኙና ሌሎች ሙዚቀኞች መረጃ እንዲሁም የዘፈኑን ግጥም የያዘ መሆኑን የሚናገረው ኤልያስ ሙዚቃውም ጥራት አለው ይላል። ይህ የሙዚቃ መሸጫ መተግበሪያ ለኢትዮጵያ የመጀመሪያው ነው ያሉት አቶ ዳዊት፤ አውታር የተባለው መተግበሪያ ሰዎች የገዙትን ሙዚቃ ተገቢ ባልሆነ መንገድ ለሌላ ሰው ከማስተላለፍ የሚከለክል ሥርዓት አለው ሲሉ ለሙዚቀኞች ያለውን ጥቅም ያብራራሉ። ሙዚቃ አቀናባሪው ኤልያስ በበኩሉ፤ መተግበሪያው ላይ የተጫነ አንድ ሙዚቃ በአራት ብር ከአምሳ ሳንቲም እንደሚሸጥ ይናገራል። ይህ በአንጋፋዎቹ የሙዚቃ ባለሙያዎች እና በአዳዲስ ድምፃውያን የተሠሩትን ይጨምራል። መተግበሪያው የኢትዮጵያን ሙዚቃ በውጭ አገራት ስንት ለመሸጥ እንደታቀደ ለጊዜው የታወቀ ነገር የለም ብሏል ኤልያስ። ይህ ጉዳይ የድምፃዊት ፀደኒያም ስጋት ሲሆን፤ እንደሀገር በዚህ ዘርፍ ወደኋላ ቀርተናል በማለት ቁጭቷን ትገልጣለች። መተግበሪያው በተለያዩ የኢትዮጵያ ቋንቋዎች አገልግሎት ይሰጣል የሚለው ኤልያስ በኦሮምኛ፣ በትግሪኛ፣ በአማርኛና በእንግሊዘኛ እንዲሠራ ሆኖ የተዘጋጀ ብቻ ሳይሆን የተለያዩ እምነት ተከታዮችም፤ የሙስሊም፣ የኦርቶዶክስ፣ የፕሮቴስታንት፤ የሚፈልጉትን መንፈሳዊ መዝሙር ወይንም መንዙማ ማግኘት እንዲችሉ ተደርጎ መደራጀቱን ያስረዳል። ፊቼ ጨምበላላ፦ የሲዳማ ሕዝብ አዲስ ዓመት መተግበሪያው በዓመተ ምሕረት፣ በዘውግ፣ በቋንቋ፣ በስልት ተከፋፍሎ የተቀመጠ መሆኑን አብራርቷል። የኢትዮጵያ ሙዚቃ አብዛኛው ገበያ ያለው ኢትዮጵያ ውስጥ ነው የሚለው ኤልያስ፤ ይህ መተግበሪያ ለጊዜው የሚሠራው ኢትዮጵያ ውስጥ መሆኑን ያስረዳል። ነገር ግን ከአገር ውጪ ያሉ አድማጮች ገዝተው መጠቀም እንዲችሉ ከባንክ ጋር እየተነጋገሩ ነው። በአንድ ሙዚቃ ላይ አምስት ሥራዎች አሉ የሚለው ኤልያስ፤ እነዚህም ማቀናበር፣ መዝፈን፣ ግጥም መፃፍ፣ ዜማ መድረስ እንዲሁም ፕሮዲውስ ማድረግ መሆናቸውን ያስረዳል። በአንድ የሙዚቃ ሥራ ውስጥ እነዚህን ሥራዎች አንድ ወይም ሁለት ሰው ደርቦ የሚሠራቸው ሊሆኑ ቢችሉም፤ ክፍያ ሲቀመጥ ግን ለሥራዎቹ እንደሆነ ያስረዳል። ስለዚህ ከአንድ የሙዚቃ ሥራ ላይ እነዚህ አምስት ሥራዎች እያንዳንዳቸው በመቶ ክፍያ ያገኛሉ። ይህ የሙዚቃ መሸጫ መተግበሪያ አርብ ማታ ሥራ ሲጀምር፤ ሰዓት፣ በየትኛውም የአገሪቱ ስፍራ፤ ሰባቱንም ቀን መሸጥ የሚያስችል ቴክኖሎጂ ነው። በተለይ አዲስ ድምፃውያን ወረፋ ሳይጠብቁ በፈለጉበት ወቅት የሙዚቃ ገበያውንና አድማጮቻቸውን ማግኘት ይችላሉ። ዝግጅት በሸክላ የተቀረፁ የድሮ ዘፈኖች፣ በካሴት የተቀዱ የስድሳዎቹና የሰባዎቹ ሥራዎች፣ በሲዲ የነበሩ ሁሉ ተሰብስበው ወደኮምፒውተር ተገልብጠዋል የሚለው ኤሊያስ፤ አንዳንዶቹ ባለቤቶቻቸው በሕይወት ስለሌሉ ከሕጋዊ ወራሾቻቸው ጋር በመነጋገርና በመፈራረም እንዲጫኑ ይደረጋል ብሏል። ሁለት ዘፈኖች ብቻ ከሚይዘው ሸክላና ከሰዎች ላይ ሙዚቃ በማሰባሰብና በመግዛት ወደኮምፒውተር መገልበጥ ዋናው ሥራ እንደነበር የሚያስታውሰው ኤልያስ፤ ሁሉም ሙዚቃ እኛ ጋር ባይኖርም በተቻለ መጠን ሁሉንም ለማሟላት እየሠራን ነው ብሏል። አንድ ድምፃዊ ሥራው አውታር ላይ እንዲጫን፤ ፎርማቱን ወደ ኤም ፒ በመቀየር ኬቢ ወይንም ኬቢ በማድረግ የዘፈኑን ግጥምና ፎቶውን በሶፍት ኮፒ ማስቀመጥ ብቻ በቂ ነው ይላል። ከዚያ የገዙትን ሰዎችና ምን ያህል እንደተሸጠ ለማወቅ የሚረዳውን ኮድ ከማግኘቱ በፊት መፈራረም ይጠበቅበታል። አንድ ነጠላ ዘፈን አራት ብር ከሀምሳ፤ አምስት ዓመት ያልሞላው ሙሉ አልበም አስራ አምስት ብር ይሸጣል። በአንድ ሲዲ ላይ የሚኖረው ዘፈን ምንም ያህል ቁጥር ቢኖረው ሙሉ አልበም ብር እንደሚሸጥ ያሰምርበታል። በታሪካዊው ቤተ መንግሥት ውስጥ ምን አለ አቀናባሪው ተከፍሎት ስለሆነ የሚያቀናብረው እስከአምስት ዓመት ድረስ ሌላ ገንዘብ አይጠይቅም የሚለው ኤልያስ፤ ይህ የድምፃዊው መብት በቅጂና ተዛማጅ መብቶች በኩልም የተጠበቀ ነው በማለት በአምስት ዓመት ውስጥ ወጪውን ሸፍኖ ትርፍ ያገኛል ተብሎ ይታሰባል በማለት ያስረዳል። በዚህ ጊዜ ውስጥ አብዛኛው መብት የዘፋኙ ነው በማለት ያክላል። ከአምስት ዓመት በኋላ ግን ድጋሚ መክፈል ስላለበት ሙዚቃው ተነጥሎ ነው የሚሸጠው የሚለው ኤልያስ፤ ይህ የሆነው በአንድ ካሴት ውስጥ ያሉ ዘፈኖችን የተለያዩ ሰዎች ስለሚያቀናብሯቸው፣ ግጥምና ዜማቸውንም ስለሚደርሱ ለመክፈል በጅምላ መሸጥ ስለማያዋጣ ነው በማለት አሠራራቸውን ያብራራል። ቢቢሲ ማስተባበያ
ታዋቂዎቹ ኤርትራዊያን ስለስደት በሰሩት ሙዚቃ ይቅርታ ጠየቁ
ሜይ አጭር የምስል መግለጫ እህትማቾቹ ድምፃዊያን ዳናይት በግራ እና ሰምሃር በቀኝ ሁለት ታዋቂ ኤርትራዊያን ድምፃዊያን ስደተኞችን በተመለከተው ዘፈናቸው ምክንያት ይቅርታ ጠየቁ። እህትማማቾቹ ድምፃዊያን፤ ዳናይት እና ሰምሃር ይቅርታ የጠየቁት ሙዚቃው ከተለቀቀ ከሁለት ዓመታት በኋላ ሲሆን ስደተኞች ለሃገራቸው ፍቅር እንዳላሳዩ በሚያመለክተው ዘፈናቸው ምክንያት ከአድናቂዎቻቸው ተቃውሞ ስለገጠማቸው ነው። አድናቂዎቻቸው እንደሚሉት ድምፃዊያኑ የወጣቶችን ለውትድርና መመልመልን ጨምሮ በኤርትራ ስላለው አስቸጋሪ ሁኔታ ችላ ብለው በርካታ ኤርትራዊያንና አፍሪካዊያን ወደ አውሮፓ ለመግባት በሚጓዙበት የሜዲትራኒያን ባሕር ላይ የሚሰምጡ ሰዎችን በሙዚቃ ቪዲዮዋቸው ላይ በማሳየት ግድየለሽ ሆነዋል በሚል ነው የሚከሷቸው። ድምፃዊያኑ መጀመሪያ የገጠማቸውን ተቃውሞ የተቋቋሙት ቢሆንም ሰምሃር ስለ ፍቅር የሚያወራ ያወጣችውን አዲስ ሙዚቃ ተከትሎ የህዝቡ ቁጣ አገርሽቷል። ምንም እንኳን አዲሱ ዘፈን ስለ ፖለቲካና ስደት ምንም የሚለው ባይኖርም ቀደም ሲል በሰሩት ዘፈን ላይ ተቃውሞው መልሶ እንዲቀሰቀስ አድርጓል። አዲስ በወጣውና በዩቲዩብ በተለቀቀው ሙዚቃ የአስተያየት መስጫ ላይም ከሁለት ዓመት በፊት ያወጡትን ሙዚቃ የተመለከተ ከአምስት ሺህ በላይ ቅሬታዎች ቀርበውበታል። በመሆኑም ድምፃዊያዊያኑ በሙዚቃው የአድናቂዎቻቸውን ስሜት በመጉዳታቸው በይፋ ይቅርታ መጠየቃቸውን ለቢቢሲ ገልፀዋል። አክለውም ጥረታችንን እንዲጠሉት ሳይሆን፤ ሰዎች ሥራዎቻችንን እንዲወዱልን እንፈልጋለን በማለት አድናቂዎቻቸውን ለመጉዳት ብለው ሙዚቃውን እንዳልሰሩት ተናግረዋል። ድምፃዊያኑ የአንጋፋው ኤርትራዊ ድምፃዊ ዮሐንስ እስጢፋኖስ ልጆች ናቸው። ተያያዥ ርዕሶች
ሴቶችና ወንዶች በምጣኔ ኃብቱ እኩል መብት ያላቸው የት ነው
መጋቢት በአለማችን ስድስት ሃገራት ብቻ ናቸው ለሴቶችና ለወንዶች እኩል ህጋዊ የምጣኔ ኃብት መብት የሰጡት። እነማን ናቸው የአለም ባንክ አዲስ ባወጣው ሴቶች፣ ቢዝነስ እና ህግ በተባለ መግለጫው ላይ የሴቶችና የወንዶችን የኢኮኖሚ እኩልነት ሙሉ ለሙሉ መፍጠር የቻሉት ከ ሃገራት ስድስት ብቻ ናቸው ብሏል። በዋሽንግተን መቀመጫውን ያደረገው ተቋም የ ዓመታት ገንዘብ ነክና ህጋዊ የሆኑ በሴቶችና ወንዶች መካከል እኩልነት እንዳይሰፍን የሚያደርጉ እንደ በነጻነት የመንቀሳቀስ፣ እናትነት፣ የቤት ውስጥ ጥቃትና ንብረት አስተዳደርን የመሳሰሉ መረጃዎችን ተመልክቷል። በአለም ባንክ መስፈርት መሰረት በእነዚህ መስኮች ላይ የሁለቱን ፆታዎች እኩልነት ሙሉ በሙሉ ማስፈን የቻሉት ስድስት ሃገራት ቤልጂየም፣ ዴንማርክ፣ ፈረንሳይ፣ ላቲቪያ፣ ሉክዘምበርግና ስዊድን ናቸው። ሃገር ቤልጂየም፣ ዴንማርክ፣ ፈረንሳይ፣ ላቲቪያ፣ ሉክዘምበርግና ስዊድን ኦስትሪያ፣ አየርላንድ፣ፖርቹጋል፣ ስፔንና እንግሊዝ በዓለም አቀፍ ደረጃ ሴቶች በአማካይ በመቶ የሚሆነውን ለወንዶች የተሰጠ ተመሳሳይ መብት እንደሚጠቀሙ መረጃው ያሳያል። ከቦታ ቦታ ያለው ያለ ልዩነት አማካይ ውጤቱ እንደየቦታው ይለያያል። ለምሳሌ በአውሮፓና መካከለኛው እስያ በመቶ ሲሆን በመካከለኛው ምስራቅ እና ሰሜን አፍሪካ ደግሞ ወደ በመቶ ዝቅ ይላል። አሜሪካ በመቶ የሚሆን ውጤት ቢኖራትም ከመጀመሪያዎቹ ሀገራት ውስጥ መካተት አልቻለችም። ህጎቿ የሴቶችን መብት በጣም የሚገታው ሳዑዲ አረቢያ ደግሞ በመቶ በሆነ ውጤት የዝርዝሩ መጨረሻ ደረጃን ይዛለች። የመጀመሪያ ስራዋን ከጀመረች አንዲት የ ዓመት ወጣት ወይም ስራዋን እየሰራች ልጆቿን ለማሳደግ ጥረት ከምታደርገው እናት እስከ ጡረታ መውጫዋ የደረሰባትን ሴትን ውሳኔ ታሳቢነት አድርጎ የተሰራው ጥናት ሴቶች የሚወስዷቸው ውሳኔዎች እንዴት በህግ ተፅዕኖ ስር እንደሆኑ ተመልክቷል። በማለት ክሪሰታሊና ጂኦርጂቫ የአለም ባንክ ጊዜያዊ ፕሬዚዳንት ተናግራለች። ብዙ ህግና ደንቦች ሴቶች የስራ መስኩን እንዳይቀላቀሉ ወይም የራሳቸውን ቢዝነስ እንዳይጀምሩ ይከለክሏቸዋል። ይህ ሴቶችን በኢኮኖሚ የማግለል ሂደት በኢኮኖሚው ውስጥ የመሳተፍ እና የስራ ሃይሉን መቀላቀል ላይ ዘላቂ የሆነ ጠባሳ ያስከትላል። መግለጫው በአንዳንድ ሃገራት የተወሰደውንም አበረታች ውሳኔ አካቷል። የአለም ባንክ ባለፉት ዓመታት ሃገራት የፆታ እኩልነትን የሚያሰፍኑ ህግና ደንቦችን ማፅደቃቸውን ገልጿል። ለሴቶች የተከለከለ ተራራን የወጣችው የመጀመሪያ ሴት ሴቶችን በስራ ቦታ መጠበቅ እነዚህ ለውጦች በ ሀገራት የሚገኙ ሴቶችን በስራ ቦታ ከሚደርሱ ጾታዊ ጥቃቶች መከላከል ያስቻሉ ሲሆን የዛሬ አስር ዓመት ከነበረው ቢሊዮን ተጨማሪ ሴቶችን መከላከል ተችሏል። ከሰሃራ በታች ያሉ ሃገራት ባለፉት ዓመታት ብዙ የፆታ እኩልነትን የሚያሰፍኑ የህግ ለውጦችን ያደረጉ ሃገራት ናቸው። የወርልድ ባንክ ዘገባ የሴቶችን ሙሉ የስራ ህይወት ያጠና ሲሆን ስራ ከመፈለግ ጀምሮ፤ ቢዝነስ ማቋቋምን እና ጡረታ የማግኘት እድላቸውን አካቷል። በአለም አቀፍ ደረጃ ሃገራት አባቶች ልጅ ሲወልዱ የስራ ፈቃድ እንዲወስዱ የሚፈቅድ ህግ እና የሚሆኑት ደግሞ በቤት ውስጥ ሴቶች ላይ የሚደርስ ጥቃት ላይ ጠበቅ ያለ ህግ አፅድቀዋል። የፆታ እኩልነትን ለማስፈን ህግ እና ደንቦችን ብቻ ማፅደቅ እና መቀየር በቂ እንዳልሆነ እናውቃለን። ህጎቹ መተግበር አለባቸው። ይህ እንዲሆን ደግሞ የመሪዎች ድጋፍ፣ የሁለቱም ፆታዎች ንቁ ተሳትፎ እና ለረጅም ጊዜ ተይዘው የቆዩ ባህላዊ አመለካከቶችን መቀየር ያስፈልጋል። ብላለች ክርስታሊና ጂኦርጂቫ። በመጨረሻም መረጃው እንደሚያሳየው ህጎች ሴቶችን የሚያጠናክሩ እንጂ ማሳካት ከምንችላቸው ነገሮች ወደ ኋላ የሚጎትቱን መሆን እንደሌለባቸው ነው። ብላለች። ቢቢሲ ማስተባበያ
በኢትዮጵያ በመቶ የሚሆኑት ወጣት ሴቶች ስለ ኤችአይቪ እውቀት የላቸውም ተባለ
ዲሴምበር ማጋሪያ ምረጥ በኢትዮጵያ ባለፈው የፈረንጆች ዓመት በተደረገ ጥናት እድሜያቸው ከ የሚሆኑ ወጣቶች ስለኤች አይቪ ያላቸው ግንዛቤ አነስተኛ እንደሆነ ታውቋል። በተለይም ደግሞ በዚህ የእድሜ ክልል ከሚገኙ ሴቶች በመቶ የሚሆኑት የኤች አይቪ መተላለፊያ እና መከላከያ መንገዶችን አያውቁም። ወንዶች ቢሆኑ እውቀቱ ያላቸው በመቶ ብቻ ናቸው። በፌደራል የኤች አይቪ መከላከያ እና መቆጣጠሪያ ፅህፈት ቤት የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ዳንኤል በትረ ለዚህ የተለያዩ አካላት ኃላፊነታቸውን አለመወጣታቸውን ምክንያት ያደርጋሉ። እነዚህ አካላትም የህዝብ ምክር ቤቶች፣ የሐይማኖት ተቋማት፣ ቫይረሱ በደማቸው የሚገኝ ግለሰቦች ማህበራት፣ የመገናኛ ብዙሃን፣ የጎሳ መሪዎችና አጋር ድርጅቶች ናቸው። መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ስለ ኤች አይቪ ኢድስ በንቃት በሚያስተምሩበት ወቅት የዛሬዎቹ ወጣቶች ጨቅላ ህፃናት ነበሩ። አሁን ግን ስለኤች አይቪ በማይወራበት ጊዜ ለአካለ መጠን በመድረሳቸው ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነዋል ይላሉ አቶ ዳንኤል። እነዚህ ወጣቶች በአብዛኛው በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች፣ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣ በትላልቅ የአበባ እርሻዎች፣ በፋብሪካዎች እና በኃይል ማመንጫ ግንባታዎች ላይ የሚገኙ ናቸው። እናም በኢትዮጵያ ከአፍላ ወጣቶች ግንዛቤ ማነስ ጋር በተያያዘ የኤች አይቪ ስርጭትም በዚሁ የእድሜ ክልል ከፍተኛ ምጣኔ ይታይበታል ። አቶ ዳንኤል ጨምረው እንደገለፁት በኤች አይቪ የሚሞቱ ሰዎች እንደሀገር በከፍተኛ ሁኔታ መቀነስ ዝምታንና መዘናጋትን ፈጥሯል። በተቃራኒው ደግሞ በወጣቶች መካከል ለኤች አይቪ የሚያጋልጡ ሁኔታዎች ጨምረዋል። ስለዚህ ምንም እንኳ ዛሬ የስርጭት መጠኑ አነስተኛ ቢሆንም የአጋላጭ ሁኔታዎች እየጨመረ መምጣት ግን ነገ የስርጭት መጠኑ እንዲጨምር ያደርገዋል። አቶ ዳንኤል መዘናጋቱ ነገ ትልቅ ዋጋ ሊያስከፍለን ይችላል በማለት የሁኔታውን አሳሳቢነት ይገልፃሉ። ከነዚህ ወጣቶች ባሻገር ለኤች አይቪ ይበልጥ ተጋላጭ የሆኑት እና የስርጭት መጠኑ ከፍ ያለው በወሲብ ንግድ ስራ ላይ በተሰማሩ ሴቶች፣ የረጅም ርቀት መኪና አሽከርካሪዎች እና በማረሚያ ቤት የሚገኙ ግለሰቦች ላይ ነው። ችግሩ ይህ ብቻ አይደለም፤ በየጊዜው የኤች አይቪ ምርመራ እና ክትትል የሚያደርጉ ሰዎች ቁጥርም አነስተኛ ነው ሲሉ አቶ ዳንኤል ሃሳባቸውን ያጠናክራሉ። ከዚህም በተጨማሪ ምንም እንኳን የትምህርት ሚኒስቴር ከአንደኛ ደረጃ ጀምሮ በቋንቋ፣በሥነ ዜጋ፣ በሥነ ሕይወት የሥርዓተ ትምህርቶች ውስጥ ቢካተትም የተጠበቀውን ያህል ለውጥ እንዳልመጣ አቶ ዳንኤል ይገልፃሉ። በየአመቱ ህዳር የሚከበረው የፀረ ኤች አይቪ ቀን የዘንድሮ መሪ ቃል አሁንም ትኩረት ለኤች አይቪ መከላከል የሚል ነው። ተያያዥ ርዕሶች
ስለ አቶ ዱቤ ጅሎ ሽልማት ምን እናውቃለን
ጁላይ ማጋሪያ ምረጥ በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ቴክኒካል ዳይሬክተርነት እያገለገሉ የሚገኙት አቶ ዱቤ ጅሎ ለኢትዮጵያዊ የመጀመሪያ ነው የተባለውን ሽልማት ሊያገኙ ነው። የአለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አይኤኤፍ ቬተራን ፒን የሚል ስያሜ ያለው ይህ ሽልማት ዜና ከአይኤኤፍ ፕሬዝዳንት ከጥቂት ቀናት በፊት እንደደረሳቸው አቶ ዱቤ ለቢቢሲ ገልፀዋል። በታላቁ ሩጫ ላይ የሚሳተፉ ተወዳዳሪዎች ላይ የአበረታች መድኃኒት ምርመራ ሊካሄድ ነው ይህንን ሽልማት ከዚህ ቀደም ኢትዮጵያዊ አግኝቶት እንደማያውቅም አቶ ዱቤና ሌላ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ተጠባባቂ ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ስለሺ ብስራት ገልፀዋል። ሽልማቱ ከዚህ ቀደም አትሌት የነበሩና ለስፖርቱ ዕድገትና ልማት አስተዋፅኦ ላበረከቱ የሚሰጥ ሲሆን ከዚህም በፊት ኬንያዊው አትሌት ፖል ቴርጋት ተሸልሟል። የአፍሪካው አትሌቲክስ ኮንፌዴሬሽን መርጦ ወደ ዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በመላክ የሽልማቱ ሂደት ይከናወናል። ሽልማቱ መስከረም ወር ላይ ዶሃ በሚዘጋጀው የአለም አቀፍ አትሌቲክስ ሻምፒዮን በመስከረም ወር የሚሰጥ ይሆናል። ታይላንዳዊው ቦክሰኛ በውድድር ሳቢያ ሕይወቱ አለፈ ሽልማቱን ያገኙበት ምክንያት ሽልማቱ ዕውቅና መስጠት ነው የሚሉት አቶ ዱቤ ከአስር አመታት በላይ ለኢትዮጵያ አትሌቲክስ እድገት አስተዋፅኦ ላደረግኩት የሚበረከት ነው። በወቅቱም ውጤታማ አፈፃፀሞች ላሳየሁባቸው እውቅና መስጠት ነው ብለዋል። በሽልማቱ መደሰታቸውን ገልፀው የበለጠ ለስራ እንደሚያነሳሳቸው ይናገራሉ። ከዚህም ቀደም ቬተራን የአንጋፋነት ፒን የሚባል ሽልማት የተሸለመ ኢትዮጵያዊ እንደሌለ የሚናገሩት አቶ ዱቤ ለአመታት የአትሌቶች ተወካይና ቴክኒካል ዳይሬክተር ሆነው ማገልገላቸው ለዚህ እንዳበቃቸው ገልፀዋል። ከአይኤኤፍ ፕሬዝዳንት ጆን ሪድጌዎን የተላከላቸው ደብዳቤም ለረዥም ጊዜ ለሽልማት የሚገባ ስራ በአትሌቲክሱ ስለሰሩ ሽልማቱ ተበርክቶላቸዋል የሚል ነው። አቶ ስለሺ ብስራት በበኩላቸው የተሸለሙት ፈጣን የሆነ ኮሚዩኒኬሽን ስላላቸው ነው ብለዋል። በጥሩ ዲፕሎማሲ ኢትዮጵያ የተመረጠች ሲሆን ይህንን ደግሞ የሚመሩት አቶ ዱቤ ጅሎ መሆናቸውን አቶ ስለሺ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ሁለቱም ኃላፊዎች ሽልማቱ ትልቅ እንደሆነ ይናገራሉ። አቶ ዱቤ በአሁኑ ወቅት በአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ውስጥ የአትሌቲክስ ጥናት ውድድርና የአትሌቲክስ ልማት ይመራሉ። አቶ ዱቤ ጅሎ ማናቸው የፌደራል ማረሚያ ቤት ለ አመታት ሯጭ ነበሩ በአስር ሺ ሜትር፣ አገር አቋራጭና ማራቶን ተወዳድረዋል በተለያዩ የማራቶን ውድድሮች ላይ ቢያሸንፉም በኦሎምፒክ ውድድር ላይ ተሳትፈው አያውቁም የአትሌቶች ተወካይ በመሆን ለረዥም ጊዜ አገልግለዋል በሳቸው ጊዜ ታዋቂ አትሌቶች እንደነ ደራርቱ ቱሉ፣ ኃይሌ ገብረሥላሴ፣ ወርቁ ቢቂላ፣ ሐብቴ ጂፋር ነበሩ በጎርጎሳውያኑ አቆጣጠር ዓ ም የፌዴሬሽኑ ቴክኒካል ዳይሬክተር ሆኑ በመካከል ለተወሰኑ ወራት አቋርጠው የነበረ ሲሆን ኃይሌ ገብረሥላሴ የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት ሲሆኑ ወደ ቀድሞው ቦታቸው መልሷቸዋል። ተያያዥ ርዕሶች
ኤኤንሲ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽኑን ውሳኔ ዘረኛ ነው አለ
ኤፕረል ማጋሪያ ምረጥ የዓለም አቀፍ አትሌቲክስ ስፖርት የበላይ አካል የሆነው ፌዴሬሽን አይኤኤኤፍ አዲስ ያወጣው ደንብ በደቡብ አፍሪካዊቷ የ ሜትር ርቀት የኦሊምፒክ አሸናፊ ካስተር ሴሜኒያ ላይ የተሰነዘረ ግልፅ ዘረኝነት ነው ሲል የደቡብ አፍሪካው ገዢ ፓርቲ ኤኤንሲ አወገዘ። ይህ አዲስ ደንብ ከሌሎች መካከል ባለፉት ዓመታት ተገቢ ባልሆነ ጫና ስር የቆየችውን ካስተር ሴሜኒያን ኢላማ ያደረገ ነው ሲል ኤኤንሲ ባወጣው መግለጫ ላይ አስፍሯል። አዲሱ ደንብ በመጪው ህዳር ወር ላይ ተግባራዊ እንደሚሆን ተነግሯል። በዚህም ከፍተኛ ተፈጥሯዊ የቴስቴስትሮን መጠን ያላቸው ሴቶች ከወንዶች ጋር እንዲወዳደሩ ወይም መድሃኒት የማይወስዱ ከሆነ የሚወዳደሩበትን የስፖርት አይነት እንዲቀይሩ ያዛል። ዓለም አቀፉ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን እንደሚያምነው የተወሰደው እርምጃ ከፍተኛ የቴስቴስትሮን መጠን ያላቸው ሴቶች በውድድሮች ላይ የሚይዙትን የበላይነት ለማስቀረት እንደሆነ ገልጿል። ይህንን ተከትሎም ኤኤንሲ የደቡብ አፍሪካ መንግሥት ፌዴሬሽኑ ያወጣውን አዲስ ሕግ ተቃውሞ ጣልቃ እንዲገባም ተማፅኗል። ይህ አዲስ ደንብ በአብዛኛው በምሥራቅ አውሮፓ፣ በእስያና በአፍሪካ አህጉሮች የሚገኙትን አትሌቶች ሰብአዊ መብት የሚፃረር ነው ሲል ፓርቲው በመግለጫው ጠቅሶ በውሳኔው የሚንፀባረቀው ዘረኝነት ግን ሊደበቅ አይችልም ብሏል። ሴሜኒያ እንደ አውሮፓዊያኑ በ በተካሄደው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ በ ሜትር የወርቅ ሜዳሊያ ካሸነፈች በኋላ ፆታዋንና አትሌትክስን በተመለከተ በዓለም ዙሪያ የክርክር ርዕስ ሆናለች። ሴሜኒያ ቀደም ሲል በአትሌቲክስ ስፖርት ባለስልጣናት የፆታ ምርመራ እንድታደርግ ተጠይቃ የነበረ ቢሆንም ውጤቱ ግን እስካሁን ለሕዝብ አልተገለፀም። ተያያዥ ርዕሶች
ይህንን ለማጋራት በ ዋትስአፕ
ለ ዓመታት የኤችአይቪ ተጠቂ የነበረ በሀገረ እንግሊዝ የሚኖር አንድ ግለሰብ ከረዥም የሙከራ ህክምና በኋላ ከቫይረሱ ነጻ መሆኑ ተሰምቷል። የካንሰር በሽታም ተጠቂ የሆነው የለንደን ከተማ ነዋሪ የሙከራ ህክምናውን ለ ወራት ሲከታተል የነበረ ሲሆን በሰውነቱ ውስጥ ያለው ደም ከቫይረሱ ነጻ ስለሆነ የኤችአይቪ መድሃኒቶቹን መውሰድ አቁሟል። ተመራማሪዎቹ እነደሚሉት ግን ሙሉ በሙሉ ከቫይረሱ ተፈውሷል ለማት ጊዜው ገና ነው ብለዋል። ኤች አይ ቪን የሚከላከለው መድሃኒት ተስፋ ሰጪ ነው ተባለ የዘርፉ ባለሙያዎች በህክምናው ውጤት መደመማቸውን ቢገልጹም ተመራማሪዎቹ ቫይረሱን ከደም ውስጥ ለማጥፋት የተጠቀሙት መንገድ ሁሉም ተጠቂዎች ላይ ተግባራዊ መሆን የሚችል ባለመሆኑ ተጨማሪ ስራ ይጠይቃል ብለዋል። ለወደፊቱም ለቫይረሱ ፈውስ ለማግኘት ትልቅ መነሻ ሊሆን እንደሚችልና ለብዙ ዓመታት ሲጨነቁ ለነበሩ ተጠቂዎች ተስፋ ሰጪ ነው ሲሉ ተደምጠዋል። በሙከራ ህክምናው ላይ የለንደን ኮሌጅ ዩኒቨርሲቲ፣ የለንደን ኢምፔሪያል ዩኒቨርሲቲ፣ የካምብሪጅ ዩኒቨርሲቲና የኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ ተመራማዎች ተሳትፎ ማድረጋቸው ታውቋል። በዚህ አይነት መንገድ ቫይረሱን ከደም ውስጥ የማጥፋት ስራ ሲከናወን ይህ ለሁለተኛ ጊዜ ነው። የዛሬ አስር ዓመት አንድ ጀርመናዊ የቫይረሱ ተጠቂ ተፈጥሮአዊ የመከላከል ብቃት ካለው በጎ ፈቃደኛ በተገኘ የመቅኔ ቦን ማሮው ንቅለ ተከላ ተደርጎለት ነጻ መሆን መቻሉ ይታወሳል። ምንም እንኳን ይሄኛው ግኝት አስደሳች ቢሆንም በሚሊዮን ለሚቆጠሩት የዓለማችን የኤች አይቪ ተጠቂዎች ተደራሽነቱ አጠራጣሪ ነው። የህክምና ሙከራው ከሌሎቹ ለየት ባለ መልኩ ለካንሰር ህክምና የሚደረጉ ስርአቶችን ይከተላል። ስለኤች አይ ቪ ኤድስ የሚነገሩ የተሳሳቱ አመለካከቶች አሁን ያሉት የኤችአይቪ ማዳከሚያ መድሃኒቶች ተጠቂዎቹ ጤናማና ረጅም እድሜ እንዲኖሩ የሚያስችሏቸው ስለሆኑ ይሄኛውን መንገድ እንደ ብቸና አማራጭ አድርጎ ለመወሰድ ከበድ ያደርገዋል። ሰውነታችን እራሱን ከበሽታ እንዴት እንደሚከላከል በእርግጠኝት ለመረዳትና ለወደፊት ፍቱን መድሃኒቶችን ለማግኘት ግን ይሄኛው ህክምና ፈር ቀዳጅ እንደሚሆን ጥርጥር የለውም። በለንደን ኢምፔሪያል ዩኒቨርሲቲ መምህር የሆኑትና በጥናቱ የተሳተፉት ፕሮፌሰር ኤድዋርዶ ኦሊቬራ እንደሚገልጹት በህክምናው ሂደት ሊምፎማ የተሰኘውን የካንሰር አይነት ለማከም የሚጠቀሙበትን መንገድ ተግባራዊ ስላደረጉ ሂደቱን አስቸጋሪ ያደርገዋል። የህክምና መንገዱ በራሱ መርዛማ የሆኑ ነገሮችን ስለሚያካትትና ለረዥም ጊዜ ስለሚካሄድ ተግባራዊነቱን ትያቄ ውስጥ ይከተዋል። ነገር ግን ወዴት መሄድ እንዳለብን ትክለኛ አቅጣጫ ጠቋሚ ነው። ቢቢሲ ማስተባበያ
አልማዝ አያና እና ሞ ፋራህ ለዓመቱ ምርጥ አትሌት የመጨረሻው ደረጃ ተፋላሚዎች መካከል ናቸው
ኖቬምበር ማጋሪያ ምረጥ የዓመቱ የዓለም ምርጥ አትሌት ምርጫ ቀናት ያህል ሲቀሩት በሴቶች ኢትዮጵያዊቷ አልማዝ አያና በወንዶች ደግሞ እንግሊዛዊው ሞ ፋራህ የመጨረሻው ደረጃ ላይ መድረሳቸው ታውቋል። ግሪካዊቷ ኤካትሪኒ ስቴፋኒዲ እና ቤልጄማዊቷ ናፊሳቶ ቲያም የአልማዝ ተፎካካሪ ሆነው ሲቀርቡ ሙታዝ ኢሳ ባርሺም ከኳታር እንዲሁም ዌይድ ቫን ኒከርክ ከደቡብ አፍሪካ ከሞ ፋራህ ጋር የሚፎካከሩ አትሌቶች መሆናቸውን የዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ማሕበር አስታውቋል። የ እና ሺህ ሜትሮች ሯጯ አልማዝ ዘንድሮ በተካሄደው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፕዮና በ ሺህ ሜትር አንደኛ ስትወጣ፤ በ ሺህ ሜትር ሁለተኛ በመውጣት ተሸላሚ መሆኗ ይታዋሳል። አልማዝ ያለፈው ዓመት የሴቶች የዓመቱ ምርጥ አትሌት ውድድር አሸናፊ ነበረች። በሌላ በኩል በወንዶቹ የለንደን የ ሺህ ሜትር አሸናፊ ትውለደ ሶማሊያ እና የእንግሊዝ ዜግነት ያለው ሞ ፋራህ ከኒከርክና ባርሺም ጋር ተናንቋል። የ ዓመቱ ፋራህ ከትራክ ውድድር ራሱን አግልሎ አሁን ላይ ወደ ማራቶን ማድላቱ ተነግሯል። አሸናፊዎቹ ኅዳር በሞናኮ በሚደረግ ዝግጅት ይፋ እንደሚደረጉ ታውቋል። ተያያዥ ርዕሶች
ሥልጣን ለደም ግፊት አጋልጦኛል ኃይሌ ገብረሥላሴ
ኖቬምበር የቢቢሲ ስፖርት አፍሪካ ባልደረባ ባለፈው ሳምንት ኃይሌ ገብረሥላሴን በአዲስ አበባ አግኝታው ነበር። ከመነሻውም ግሩም ጥያቄ ነበር ያነሳችለት። አንተ የዓለም ሪከርድ ስትሰብር፣ የኦሎምፒክ ወርቆችን ስታፍስ ነው የኖርከው። ዓለም የሚያውቅህም በጽናትህ ነው። ስናውቅህ በ ይቻላል መርህ ነው። ፍጹም ተስፋ የምትቆርጥ ሰው አልነበርክም። ለምን ሥልጣንህን ለቀቅክ እንዴትስ እጅ ሰጠህ እርግጥ ነው ኃይሌ ምላሽ ሰጥቷታል። ምላሹ ግን የሁልጊዜው አልነበረም። እንደሁልጊዜው አልተፍነከነከም። የሚናፈቀው ያ ሳቁ እምብዛምም ነበር። እንዲያውም ሥልጣን ለደም ግፊት አጋልጦኛል ሲል እግረ መንገዱን ያልተጠበቀ ምላሽን ሰጥቷታል፤ ለቢቢሲ ስፖርት አካፍሪካ ወኪል። ከሁለት ዓመት በፊት ወደዚህ ሥልጣን ስመጣ ብዙ ፈተና ነበረው። አትሌቶችን ማርካትና ጥያቄዎቻቸውን መመለስ ነበር ህልሜ። ያንን ለማሳካት ያለኝን ነገር ሁሉ ለዚሁ ሥራ መስጠት ነበረብኝ። ጊዜዬን፣ ገንዘቤን፣ ጉልበቴን፣ ዕውቀቴን ፤የሚገርምሽ በቤተሰባችን ደም ግፊት ያለበት ሰው የለም። አሁን እኔ ብቻ ነኝ ግፊት የያዘኝ ። በቃለ ምልልሱ መሐል እግረ መንገድ የተገለጸው ይህ የኃይሌ ገብረሥላሴ የጤና እክል በራሱ ለአድናቂዎቹ አስደንጋጭ ዜና መሆኑ እንደተጠበቀ ኾኖ ለመሆኑ ይህን ያህል ኃይሌን ሊያስመርር የቻለው ጉዳይ ምንድነው አትሌቶች ቅሬታ ነበራቸው። ጥቂት ቢሆኑም፣ የማይታወቁ ቢሆኑም፣ በኔ ደስተኛ ያልሆኑ አትሌቶች ሰልፍ አደረጉ። ዝነኛ ላይሆኑ ይችላሉ ኮ። ብዙ ላይሆኑ ይችላሉ። ግን ተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ። በቃ በኔ ደስተኞች አልነበሩም። እንዴ እነሱን ማስደሰት ካልቻልኩ ለምን ብዬ አመራር ላይ እቆያለሁ ለሌሎች ዕድል መስጠት ነበረብኝ። ኃይሌ የርሱን ከአትሌቲክስ ፌዴሬሽን በገዛ ፈቃድ መነሳት አስታኮ በአፍሪካ ሥልጣንንን ርስት ማድረግ ማብቃት እንዳለበትም እግረ መንገዱን ምክር ቢጤ ጣል አድርጎ ነበር። እኛ አፍሪካዊያን ለተቀረው ምሳሌ መሆን አለብን። ሥልጣን ላይ ሙጭጭ ማለት አያስፈልግም። የምንመራው ሕዝብ ካልፈለገን መልቀቅ ነው። ሕዝብ ካልወደደን ለምን ጎትቶ እስኪጥለን እንቆያለን። ሥልጣን እንደ አትሌቲክስ ነው። ካላሸነፍክ ለሚያሸንፈው አትሌት መልቀቅ ይኖርብሃል። በቃ የኃይሌ ወደ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን መምጣት ብዙዎች ይንሸራተት ይዟል ለሚሉት የአትሌቲክስ ውጤታችን እንደ ሁነኛ ማስፈንጠሪያ ቆጥረውት ነበር። አሁን ገና ሞያና ሞያተኛ ተገናኙ ያሉም ብዙ ነበሩ። ጉዞው በሁለት ዓመት ይገታል ያለ ግን አልነበረም። በኢትዮጵያ የሚገኙ ቤተ እስራኤላውያን ወደ ፅዮን ውሰዱን ተማፅኖ የቢቢሲ አፍሪካ የስፖርት ባልደረባ የመጨረሻ ጥያቄ ያነሳችለት የማበረታቻ መድኃኒቶች በአፍሪካ አትሌቶች ዘንድ የመዘውተሩን ጉዳይ ነበር። በአትሌቲክስ ሐቀኛ መሆን ቁልፍ ነገር ነው። ሲል ምላሽ መስጠት የጀመረው ኃይሌ በማበረታቻ ታግዞ ዘላቂ ውጤት ማምጣት እንደማይቻል አጽእኖት ሰጥቶ ተናግሯል። ዓለም አቀፍ አትሌት ለመሆን በቅድሚያ ሐቀኛና ታማኝ መሆን የግድ ነው። ሐቀኝነት ለድል ያበቃል። ሲል ከተናገረ በኋላ በተፈጥሮ መታደላችን ምን ያህል ለውጤችን አስተዋጽኦ እንደሚያደርግ ያብራራል። ኧረ ለመሆኑ ኢትዯጵያና ኬንያ ለምንድነው አበረታች መድኃኒት የሚፈልጉት ንገሪኝ እኛ እኮ ፈጣሪ የሰጠን ማበረታቻ አለ። እሱን አንጠቀምም ተመልከችው እስኪ ተራራውን። ተመልከቺው አየሩን። ይህ የኛ የተፈጥሮ ዶፒንግ ነው። ማበረታቻ የሚወስዱ አትሌቶች ለጊዜው ገንዘብ ማግኘት ቢችሉ እንኳ ያገኙት ገንዘብ በረከት እንደማይኖረውም ኃይሌ ጨምሮ ተናግሯል። ይዟቸው ነው የሚጠፋው። ይላል። የስኬታማነት ተምሳሌቱ ኃይሌ ለቢቢሲ አፍሪካ ስፖርት ባልደረባ የሕይወት ፍልስፍናውን በገደምዳሜ አጫውቷት ነበር፤ እግረ መንገዱን። ሕይወት አጭር ናት፤ ሀብትና ንብረት ይዘን አንቀበርም። ባዶ ኪሳችንን ነው የመጣነው፣ ባዶ ኪሳችንን ነው የምንሞትው። ስትቀበሪ ሳንቲም ሬሳ ሳጥንሽ ውስጥ የሚያጭቅልሽ አይኖርም። ባዶ ገላን ይዘን ነው የመጣነው፤ ባዶ ገላችንን እንለመሳለን። ይኸው ነው። ሲል አጠር ያለ አስተያየቱን ቋጭቷል። ተያያዥ ርዕሶች
በዓለም አቀፍ ውድድሮች በመሳተፍ የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ ነው ዓላማዬ
በዓለም አቀፍ ውድድሮች በመሳተፍ የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ ነው ዓላማዬ ህዳር
ፊቼ ጨምበላላ፦ የሲዳማ ሕዝብ አዲስ ዓመት
ግንቦት የፌቼ ጨምበላላ በዓል ገንዘብ ያበደረ እንዲመለስለት የማይጠይቅበት፣ ከብት የማይታረድበት፣ ዛፍ የማይቆረጥበት፣ ያጠፉ ይቅር የሚባሉበት ዕለት ነው ጨምበላላ። የሲዳማ ሕዝብ የጨረቃና ከዋክብትን አቀማመጥ በማጥናት አዲስ ዓመት ያከብራል። በዓሉም ፊቼ ጨምበላላ ይባላል። ይህ በዓል መከበር ከጀመረ ከ ዓመታት በላይ ማስቆጠሩን የአገር ሽማግሌዎች ይናገራሉ። የባህል አጥኚው አቶ ብርሃኑ ሃንካራ ደግሞ የፊቼ ጨምበላላ በዓል የሲዳማ ሕዝብ ማንነቱን ከተረዳበት ጊዜ አንስቶ ሲከበር የቆየ ነው ይላሉ። የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና ባህል ተቋም ዩኔስኮ በቅርስነት የመዘገበው ይህ በዓል ዛሬ መከበር ጀምሯል። ፊቼ ጨምበላላ በዓል የሚከበርበት ቋሚ ቀን የለውም። በአያንቱዎች ጥቆማ መሰረት በዓሉ የሚከበርበት ቀን ይቆረጣል። ከዚያም ለበዓሉ ሰፊ ዝግጅት ማድረግ ይጀመራል። ከዋዜማው አንስቶ በዓሉ መከበር ይጀምራል። ጎረቤት ተሰብስቦም ከእንሰት የሚዘጋጀውን ቦርሻሜ ተብሎ የሚጠራውን ምግብ በወተት ይመገባሉ። ያገቡ ሴቶች ልዩ የሆነ የጸጉር አሰራር አላቸው ለበዓሉ ከሚበሉ ባህላዊ ምግቦችና ከሚከናወኑ ጭፈራዎች በተጨማሪ የተለያዩ ባህላዊ ሁነቶችም ይካሄዳሉ። ቄጠላ፣ ኛፋሮና የመሳሰሉ ሙዚቃዎችም በበዓሉ ይከወናሉ። ቄጠላ በተባለው ባህላዊ ሙዚቃ፤ አገር፣ ዘመን፣ የአገር ሽማግሌዎችና ታዋቂ ግለሰቦች እየተወደሱ ይጨፈራል። ቄጠላ የተሰኘው ባህላዊ ጭፈራ በቡድን ሲያዜሙ የፊቼ ጨምበላላ ዋነኛ ትርጉም ሰላም ነው የሚሉት አቶ ብርሃኑ ሃንካራ፤ አንድነትና ፍቅር የበዓሉ መለያ መሆናቸውን ይናገራሉ። የተጣሉ ሰዎች በፊቼ ጨምበላላ በዓል ላይ ይታረቃሉ። ሃዘን ላይ የነበሩ ሰዎችም የሃዘን ልብሳቸውን ይቀይራሉ። ፊቼ ጨምበላላ ዘንድሮ ያገባች ሴት ሙሽርነቷን ጨርሳ ከሌሎች ሴቶች ጋር የምትቀላቀልበት በዓል ነው። በተለያዩ ምክንያቶች ከቀዬው ርቆ የነበረ ሰው ለፊቼ ጨምበላላ ወደቀዬው ይመለሳል። በበዓሉ ወቅት ለአካባቢ እና ለእንስሳት ትልቅ ትኩረት ይሰጣል ለዚህ በዓል ተብሎ እርድ አይፈጸምም፤ ስጋም አይበላም። ክብቶችን መምታትም ክልክል ነው። ላሞች ሳር የበዛበት መስክ ላይ ይሰማራሉ። በሲዳማ ሕዝብ ዘንድ በፊቼ ጨምበላላ በዓል ወቅት ማረስ ነውር ነው። ለዚህም ምክንያቱ ደግሞ የፊቼ ጨምበላላ በዓል የሲዳማ ሕዝብ ብቻ ሳይሆን የተፈጥሮም ነው ተብሎ ስለሚታመን ነው።ፊቼ የአዲስ ዓመት በዓል ዋዜማ ሲሆን፤ ጨምበላላ ደግሞ የአዲስ ዓመት መጀመሪያው ቀን ነው። የእድሜ ባለጸጎች ሁሉቃ ሲሠሩ ሲዳማ ከአንድ ዓመት ወደሌላው የሚሸጋገርበት ሂደት ሁሉቃ ይባላል። ሁሉቃ ማለት ከሸምበቆና ከአርጥብ ቅጠል ተሠርቶ የሚቆም ነገር ነው። ሁሉቃ በቤተሰብና በማኅበረሰብ ደረጃ የሚሠራ ሲሆን፤ አዲስ ዓመት ሲገባ ሰዎችና ከብቶች ይተላለፉበታል። የሲዳማ ሕዝብ አዲስ ዓመትን ሲቀበሉ፤ ዓመቱ የብልጽግና እንዲሆንላቸው ፊቼ ጄጂ ይላሉ። ቢቢሲ ማስተባበያ
ወንዶች አዞ ለመምሰል ቆዳቸውን የሚበሱባት ሃገር
ኦገስት ስለ ማጋራት ተጨማሪ ያጋሩ ማጋሪያ ምረጥ በአለማችን ሁለተኛዋ ትልቅ ደሴት በሆነችው ፓፓ ኒው ጊኒ፤ በመቶ የሚሆኑት ዜጎች መኖሪያቸው ገጠራማ በሆኑት አካባቢዎች ነው። አብዛኛዎቹ ለሰለጠነው አለም ብዙም ቅርበት የላቸውም። በዚህ ዘመን ይኖራሉ ተብለው የማይታሰቡ ባህላዊ ስነ ስርአቶች አሁንም ድረስ በዚህች ደሴት ላይ ይስተዋላሉ። በፓፓ ኒው ጊኒ የመንፈስ ቤቶች ተብለው የሚጠሩት የአምልኮ ቦታዎች በአብዛኛው ነዋሪ ትልቅ ቦታ የሚሰጣቸው ናቸው። በዚህ ቦታ የተለያዩ ሰዎች ነፍሳቸውን በተለያዩ የእንሰሳት መንፈስ የሚመሰሉላቸው ሲሆን፤ የአዞ መንፈስን የሚስተካከለው የለም። እነዚህ የአምልኮ ቦታዎች በብዙ የእንስሳት ቅሪቶች የተሞሉ ሲሆን፤ ከአሳማ እስከ ፈረስ፤ ከእባብ እስከ ንስር አሞራ ቅሪቶች በግድግዳዎቹ ላይ ይሰቀላሉ። ነገር ግን ለዚህ አካባቢ ሰዎች እንደ አዞ ሃይል እና ብልሃትን ያጣመረ እንስሳ የለም። ታዳጊ ወንዶች በእድሜ መብሰላቸውን ለማረጋገጥ ወደ እነዚህ የመንፈስ ቤቶች በመሄድ ጀርባቸው፣ ትከሻቸውና ደረታቸው ላይ ስለት ባላቸው ነገሮች ይበሳሉ። ምንም እንኳን ስነ ስርአቱ ከባድ ህመም ያለው ቢሆንም፤ ባህል ነውና ሁሉም የፓፓ ኒው ጊኒ ታዳጊዎች በጉጉትና በደስታ ያደርጉታል። ለእነሱ አዞን መምሰል የጥንካሬያቸውና በእድሜ የመብሰላቸው ማሳያ ነው። ታዳጊዎቹ ወደ መንፈስ ቤቶቹ የሚወሰዱት በአጎቶቻቸው ሲሆን፤ ቆዳቸውን የመብሳቱ ሂደት ከአንድ እስከ ሁለት ሰአት ሊፈጅ ይችላል። እንደውም ከዘመናዊ ፈጠራዎች መምጣት ጋር ተያይዞ የሚጠቀሟቸው ስለቶች እተሻሻሉ መጡ እንጂ፤ በድሮ ጊዜ የሚጠቀሙት ስል ቀርከሃ እንደነበር የአካባቢው ምክትል ተወካይ አሮን ማሊነጊ ይናገራሉ። ታዳጊዎች ከህመሙ ብዛት አንዳንድ ጊዜ ራሳቸውን ስተው እንደሚወቀድቁም ተወካዩ ይናገራሉ። ቁስሉ ቶሎ እንዲድንና ሌላ ችግር እንዳይፈጥር በአካባቢው በብዛት ካለ ዛፍ የሚገኝ ዘይት ይደረግበታል። ስነ ስርአቱ ያስፈለገው የታዳጊዎቹ እናቶች እነሱን ሲወልዱ ያፈሰሱትን ደም ለማስታወስና ከዚህ በኋላ የራሳቸውን ደም በማፍሰስ ትልቅ ሰው መሆናቸውን ለማሳየት ነው። ከዚህ በተጨማሪ ታዳጊዎች ስነ ስርአቱን ከጨረሱ በኋላ በመንፈስ ቤቶች ውስጥ ለወራት በመቀመጥ ከታላላቆቻቸው የህይወት መንገዶችንና እንደ አሳ ማጥመድ ያሉ ሌሎች አስፈላጊ እውቀቶችን ይማራሉ።
ሕንድ፡ ለሴቶች የተከለከለ ተራራን የወጣችው የመጀመሪያ ሴት
ጥር ዳንያ ሳናል ተራራውን የወጣች የመጀመሪያ ሕንዳዊት ናት ዳንያ ሳናል የተባለች ሕንዳዊት ለወንዶች ብቻ የተፈቀደ ተራራ በመውጣት ግንባር ቀደም ሆናለች። ተራራው አግስታይኮዳም ይባላል። ተራራው ጫማ ሜትር ርዝመት አለው። ይህን ተራራውን መውጣት እንደ ሀይማኖታዊ ጉዞ ይቆጠራል። የሕንድ ፍርድ ቤት በቅርቡ ሴቶች ተራራውን እንዲወጡ ከመፍቀዱ በፊት፤ ተራራው ጫፍ መድረስ የተፈቀደው ለወንዶች ብቻ ነበር። ዳንያ ተራራውን በመውጣት ታሪክ ብትሰራም፤ የሂንዱ እምነት ተከታይ የቀዬው ነዋሪዎች ሴቶች ተራራውን እንዲወጡ በመፈቀዱ ደስተኛ አይደሉም። የ ዓመቷ ዳንያ ለቢቢሲ እንደተናረችው፤ ተራራውን ስትወጣ ሊያስቆማት የሞከረ ሰው አልነበረም። የመብት ተሟጋቾች የዳንያ ጉዞ ለሴቶች መብት መከበር የሚያደርጉት ትግል መገለጫ መሆኑን ተናግረዋል። ሴቶች ተራራውን መውጣት እንዲፈቀድላቸው የድጋፍ ፊርማ አሰባስበው ወደ ሕንድ ፍርድ ቤት ያቀኑ ሴቶች ደስታቸውን ገልጸዋል። ከሴቶቹ አንዷ ዲቫያ ዲቫክራን የሴቶችን ጭቆና ለማስቆም አንድ ርቀት ወደፊት ተራምደናል ስትል ለቢቢሲ ተናግራለች። በሕንዷ ካርላ የሚገኘው አግስታይኮዳም ተራራ ከአካባቢው ተራሮች በርዝመት ሁለተኛው ነው። የአካባቢው ተወላጆች ሴቶች ተራራውን እንዲወጡ መፈቀዱ እምነታችንን ይጻረራል ቢሉም ፍርድ ቤቱ አቤቱታቸውን ውድቅ አድርጎታል። ዳንያ ተራራውን እየወጡ ከነበሩ ወንዶች ብቸኛዋ ሴት ነበረች። በቀጣይ ሳምንታት የእሷን ፈለግ በመከተል ወደ ሴቶች ተራራውን ለመውጣት ተመዝግበዋል። ቢቢሲ ማስተባበያ
ኢትዮጵያ፡ ሕንዳውያን የግንባታ ሠራተኞች ከታገቱ ቀናት ተቆጠሩ
ኖቬምበር ማጋሪያ ምረጥ የሃገረ ሕንድ የሆነው አይኤል እና ኤፍኤስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ በኢትዮጵያ ላለፉት ሶስት ዓመታት የተለያዩ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶችን ሲያካሄድ ቆይቷል። በቅርቡም ከነቀምት ጊዳ እና ከአጋምሳ ቡሬ ያሉ የመንገድ ግንባታዎችን ሲያካሂድ ነበር። ይሁን እንጂ ኩባንያው ባጋጠመው የፋይናንስ ቀውስ የመንገድ ግንባታ ስራውን ማከናወን ተስኖታል። ይህም ብቻ አይደለም፤ ለሰራተኞች ደሞዝ፣ ለተቋራጮችና ለአቅራቢዎች የሚከፍለው ገንዘብ አጥሮታል። ያነጋገርናቸው ተቋራጮች ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት ወስደው ክፍያው እንዲፈጸምላቸው ቢፈረድላቸውም ኩባንያው ግን ክፍያዎችን መፈጸም ተስኖታል። አቶ ሃብታሙ ካላዩ ከዚህ ኩባንያ ጋር ለሰራተኞች መኖሪያ የሚሆን ተገጣጣሚ ቤቶችን ለመገንባት ከሁለት ዓመታት በፊት ውል ወስዶ ነበር። በውሉ መሰረት መፈጸም የነበረበት ሺህ ብር ክፍያ ስላልተፈጸመላቸው ሥራውን ለማቋረጥ መገደዳቸውን ይናገራሉ። አቶ ሃብታሙ ክፍያው እንዲፈጸምላቸው ፍርድ ቤት ቢወስንላቸውም ኩባንያው ግን የተጠየቀውን ክፍያ መፈጸም አልቻለም ይላሉ። ኩባንያው ለሌሎች ተቋራጮች፣ የመኪና እና የተለያዩ ማሽነሪዎች አከራዮችም ያልተከፈለ ውዝፍ እዳ እንዳለበት አቶ ሃብታሙ ነግረውናል። ደሞዛቸው ከሶስት እስከ አምስት ወራት የዘገየባቸው የነቀምት፣ ወሊሶ እና ቡሬ ሳይት ሰራተኞች ግን ሕንዳዊ የሆኑ የኩባንያውን ሰራተኞች በማገት ክፍያ እንዲፈጸምላቸው ጠይቀዋል። በዚህም የተነሳ በቡሬ ሳይት ፣ ወሊሶ እንዲሁም ነቀምት ላይ በድምሩ ሕንዳውያን ላለፉት ስድስት ቀናት ታግተው ይገኛሉ። ለደህንነታቸው ሲባል ስማቸውንና የሚገኙበትን ሳይት የማንጠቅሰው አንድ ታጋች ኩባንያችን ባጋጠመው የፋይናንስ ችግር ምክንያት ለሰራተኞች ደሞዝ መክፈል አልቻለም፤ ላለፉት ስድስት ቀናት ከመጠለያ ጣቢያ እንዳንወጣ በአካባቢው ሰዎች ታግተናል፤ የኤሌትሪክ ኃይል አቅርቦት እና የመጠጥ ውሃ እጥረት ችግር አጋጥሞናል። ያለንበት ሁኔታ በጣም አስቸጋሪ ነው ሲሉ ያሉበትን ሁኔታ ያስረዳሉ። ይህ ታጋች እንደሚሉት ከሆነ ለሰራተኞች ለወራት ያክል ያልተከፈለ ደሞዝ፣ ለተቋራጮች እና አቅራቢዎች መፈጸም የነበረበት ክፍያ አለ። በአጠቃላይ ኩባንያው ወደ ሚሊዮን ብር የሚጠጋ ክፍያ መፈጸም አለበት ይላሉ።
የሕንድ ሚሊዮን ያለተፈለጉ ሴት ልጆች
ጃንዩወሪ ማጋሪያ ምረጥ ሕንድ ውስጥ ያሉ ወላጆች ከሴት ልጅ ይልቅ ወንድ ልጅ እንዲኖራቸው ባላቸው ፍላጎት የተነሳ ሚሊዮን የሚደርሱ ያለተፈለጉ ሴት ልጆች በሃገሪቱ እንዳሉ አንድ የመንግሥት ሪፖርት አመለከተ። የሕንድ የገንዘብ ሚኒስቴር ያወጣው ሪፖርት እንደሚለው በርካታ ጥንዶች ወንድ ልጅ ለማግኘት ሲሉ መውለዳቸውን ይቀጥላሉ። ሪፖርቱን ያዘጋጁት ባለሙያዎች እንዳሉት ይህ ሁኔታ በፆታ ምርጫ ምክንያት ከሚደረገው የፅንስ ማቋረጥ የተሻለው አማራጭ ቢሆንም ለሴት ልጆች ሊሰጥ የሚገባው ትኩረትን በከፍተኛ ደረጃ ሊቀንሰው እንደሚችል ያስጠነቅቃሉ። በወላጆች መካከል ያለው የወንድ ልጅ ምርጫን በተመለከተ የህንድ ዜጎች ሊነጋገሩበት የሚገባ ጉዳይ ነው ይላሉ ባለሙያዎቹ። የሪፖርቱ አዘጋጆች እንደደረሱበት ወንድ ልጅ እንዲኖራቸው የሚሹ ወላጆች ሴት ልጅ መፀነሷን ሲያውቁ በሚያደርጉት የፅንስ መቋረጥ ሳቢያ ከአጠቃላዩ የሃገሪቱ ህዝብ ሚሊዮን ሴቶች እንዲጎድሉ ምክንያት ሆኗል። በተጨማሪም የበለጠ እንክብካቤ ከሴት ልጅ ይልቅ ለወንድ ልጆች ይሰጣል። ምንም እንኳን የፅንስን ፆታ ለማወቅ ምርመራ ማድረግ ሕንድ ውስጥ ሕገ ወጥ ቢሆንም ምርመራው ስለሚከናወን በፆታ ምርጫ ሰበብ ለሚካሄድ የፅንስ ማቋረጥ እድልን ፈጥሯል። ወላጆች ወንድ ልጆችን እንዲመርጡ ከሚያደርጓቸው ነገሮች መካከል ንብረት ለሴት ልጆች ሳይሆን ለወንዶች ስለሚተላለፍ፣ ጋብቻ ሲታሰብም የሴቷ ቤተሰብ ጥሎሽ እንዲሰጥ ስለሚጠየቅ እና ሴቶች ካገቡ በኋላ ወደባሎቻቸው ቤት ስሚገቡ እንደሆነ ይነገራል። ይህን በህብረተሰቡ ዘንድ ያለው ጠንካራ ወንድ ልጆች የማግኘት ምርጫን መሰረት አድርጎ አንድ የሃገሪቱ ጋዜጣ በሳይንስ ድጋፍ የሌለውን ወንድ ልጅ የማግኛ ዘዴዎች ብሎ እስከማተም አድርሶታል። ጋዜጣው ካሰፈራቸው ዘዴዎች መካከል በመኝታ ጊዜ ወደ ምዕራብ ዞሮ መተኛት እና ከሳምንቱ ቀናት በተወሰኑት ውስጥ ግንኙነት መፈፀም ወንድ ልጅ ለማግኘት ይረዳል የሚል ይገኝበታል። የወንድ ልጆች ምርጫ ከሚታይባቸው የሕንድ ግዛቶች መካከል ፑንጃብና ሃሪያና ቀዳሚዎቹ ሲሆኑ በዝቅተኛ ደረጃ ላይ ያለችው ግዛት ሜጋላያ ናት። በፑንጃብና ሃሪያና ግዛቶች ከሰባት ዓመት በታች ላሉ ወንድ ልጆች አንፃር ሴት ልጆች ብቻ እንዳሉ በተደረገው ጥናት ተደርሶበታል። ተያያዥ ርዕሶች
ከድንበር ውዝግብ በኋላ ቻይናና ህንድ በውሃ ምክንያት ተፋጠዋል።
ሴፕቴምበር ማጋሪያ ምረጥ አጭር የምስል መግለጫ በየዓመቱ በዝናብ ወቅት ወንዙ በጣም ይሞላና በሰሜን ምስራቅ ሕንድ እና በባንግላዴሽ ትልቅ ኪሳራ ያስከትላል። ቻይናና ሕንድ አሁንም ሊከሰት የሚችል የድንበር ጦርነትን ቢያረግቡም ፍጥጫው ግን ወደ ሌላ አከራካሪ አለመግባባት አምርቷል፤ ውሃ። በዚህ የዝናብ ወቅት በስምምነታቸው መሠረት ዴልሂ ከቻይና ስለ ብራሕማፑትራ ወንዝ ማግኘት የነበረባትን የሃይድሮሎጂ ማለትም የውሃ ደረጃ እንቅስቃሴና ስርጭትን የተመለከተ የሳይንሳዊ ጥናት መረጃ እንዳልተረከበች ተናግራለች። የእስያ ትልቁ ወንዝ የሆነው ብራሕማፑትራ ከቲቤት ተነስቶ ወደ ሕንድ ፈሶ ከዚያም ወደ ባንግላዴሽ በማምራት ከጋንጂዝ ጋር ተቀላቅሎ በቤንጋል ሠርጥ ያበቃል። ቤይጂንግ የሃይድሮሎጂ ጣቢያዎቹ ማሻሻያ እየተደረገላቸው በመሆኑ ምንም አይነት መረጃ ማቅረብ እንደማይቻል ኣሳውቃለች። ቢቢሲ እንደሚለው ግን ባንግላዴሽ ከብራሕማፑትራ ተፋሰስ የታችኛው ክፍል ላይ ያለች አገር ብትሆንም ከቻይና እስካሁን ድረስ መረጃ እየተቀበለች እንደሆነ ነው። ይህ የወንዝ መረጃ ጠብ በቻይናና በሕንድ መካከል በሂማላያ ድንበር ተነስቶ ለሁለት ወራት የቆየውን ፍጥጫ ተከትሎ የተከሰተ ነው። አጭር የምስል መግለጫ በቻይናና በሕንድ መካከል የነበረው ግጭት አሁንም እንደቀጠለ ነው። አለመተማምን የባንግላዴሽ የዉሃ ሀብቶች ሚኒስቴር አኒሱል ኢስላም ሞሃማድ አገራቸው ውሃን የተመለከተ መረጃዎችን ከቻይና እየተቀበለች እንደሆነ ለቢቢሲ ኣሳውቀዋል። ለሕንድ ግን ቻይና መረጃ የማካፈሉን ተግባር ድጋሚ ትቀጥላለች የሚለው ሃሳብ አጠራጣሪ ሆኖባታል። የቻይና ቃልአቀባይ የሆኑት ጌንግ ሽዋንግ ይህን በተመለከተ ተገቢውን የሃይድሮሎጂ መረጃ መስጠት መቀጠል መቻል ወይም አለመቻላቸው ከዚህ በላይ በተጠቀሰው የማሻሻያ ሥራ ሂደት ላይ ተወሰነ ነው። ሕንድና ከቻይና ጋር ስለ ብራሕማፑትራ ወንዝ የፍሰት መረጃዎችን ለመቀበል ስምምነት ውስጥ ላይ የደረሰችው ከብዙ ዓመታት ጥረት በኋላ ነው። በድርቅ ወቅቶች ቻይና የብራሕማፑትራን ውሃ ወደ ደረቅ ክልሎችዋ ታዛውራለች ብለው ስለሚጠረጥሩ ዴልሂ የወንዙን ውሃ ፍሰት መረጃ ዝናብ በሌለበት ወቅትም እንዲሰጣት ጥያቄ አቅርባለች። አጭር የምስል መግለጫ ወንዙ ወደ ባንግላዴሽ ከመውረዱ በፊት ወደ ሕንድ ይፈሳል። ቤይጂንግ በወንዙ ላይ ብዛት ያላቸውን የኤሌክትሪክ ኃይል የሚያመነጩ ግድቦችን ገንብታለች። በመቀጠልም ውሃውን እንደማይገድቡ ወይም አቅጣጫ እንደማያስቀይሩና ከወንዙ በታች በኩል ያሉ አገራትን ፍላጎቶች እንደማይጻረሩ ተናግረዋል። በቅርብ ዓመታት በተለይም በሰሜን ምሥራቅ ሕንድ ውስጥ ቻይና በአንድ ጊዜ ከፍተኛ መጠን ያለው ውሃ ትለቃለች የሚል ፍራቻ አለ። ወንዙ ሰፊ ቦታን ለሚሸፍንባቸው አካባቢዎች አንዱ በኣሳም ሲሆን የዲበሩጋር ነዋሪዎችም የብራሕማፑትራ ውሃ መጠን በከፍተኛ ደረጃ ሲጨምርና ሲቀንስ እንዳዩ መስክረዋል። ይህንን ዜና ያጋሩ ስለማጋራት
ኬንያዊቷ ታዳጊ አንድን ግለሰብ ከጎርፍ ለማዳን ስትጥር ህይወቷ አለፈ
ዲሴምበር ማጋሪያ ምረጥ አንዲት ኬንያዊት ታዳጊ አንድን ግለሰብ ከጎርፍ ለማዳን ስትጥር ሰምጣ ህይወቷ አልፏል። ከመዲናዋ ናይሮቢ ወጣ ብሎ በሚገኘው ካንዲሲ የሚባል ወንዝ ገብታ ነው ህይወቷ ያለፈው፤ የአስራ ዘጠኝ ዓመቷ አን ዱኩ። አን እየተገነባ በነበረ ድልድይ ስር አድኑኝ እያለ በመማፀን ላይ የነበረ ግለሰብን ጩኸት ሰምታ ነው ለእርዳታው የመጣችው። ግለሰቡ ህይወቱ ቢተርፍም እሷ ግን ወንዝ ውስጥ በመውደቋ ህይወቷ አልፏል። እናቷ ኤልዛቤት ሙቱኩ ለቢቢሲ ጋዜጠኛ እንደተናገሩት ወንዝ ውስጥ ስትታገል አየሁዋት፤ ህይወቷንም ለማዳን ሞክሬያለሁ። አና አና ብዬ እየጠራሁዋት ነበር። እሷንም ለመጎተት እንዲያስችለኝ እንጨት መወርወር አስቤ ነበር። ነገር ግን የወንዙ ማዕበል በጣም ከፍተኛ ስለነበር፤ ልጄን ጥርግ አድርጎ ወሰዳት በማለት እንባ እየተናነቃቸው ተናግረዋል። በዚህ ሳምንት ከሰኞ ጀምሮ በምሥራቅ አፍሪካ በከፍተኛ ሁኔታ ሲጥል የነበረውን ዝናብ ተከትሎ ነው ወንዙ ከመጠን በላይ የሞላው። ነገር ግን ነዋሪዎች እንደሚሉት ባለፉት ሁለት ዓመታት ሰባት ሰዎች በወንዙ ተወስደው ለሞት ተዳርገዋል። በቴክኖሎጂ ኢ ፍትሐዊነትን የምትታገለው ኢትዮጵያዊት ወንዙን ለመሻገር ያገለግል የነበረው አሮጌ ድልድይ ከሁለት ዓመት በፊት የፈረሰ ሲሆን አዲሱ ድልድይ ባለመጠናቀቁ ነዋሪዎች ድንጋይ ከላይ በመደርድር እየተሻገሩ መሆኑ ተገልጿል። የሟቿ ታላቅ እህት ማርያም ዜኔት ለቢቢሲ እንደገለፀችው መንደራቸውን ከዋናው ገበያ ጋር የሚያገናኘው ድልድይን ማጠናቀቅ የአካባቢው ባለስልጣናት ኃላፊነት ቢሆንም፤ ይህንን ባለማድረጋቸውም ጥፋተኞች ናቸው ብላለች። ባለፉት ሁለት ዓመታት ብዙ ሰዎች ድልድዩን ሊያቋርጡ በሚሞክሩበት ወቅት ህይወታቸው አልፏል። ባለስልጣናቱ መጥተው ሃዘናቸውን ከመግለፅ ውጪ ምንም ያደረጉልን ነገር የለም። ዛሬ እህቴ ሞተች ነገስ ቀጣዩ ማነው ድልድዩ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት ሲሄዱም የሚመላለሱበት ነው። አዲስ መገንባት ካልቻሉ የድሮውን ለምን አፈረሱት በማለትም ትጠይቃለች። በልጃቸው ሞት ልባቸው የተሰበረው እናት በጣም አዝኛለሁ። የወደፊቱ መሪ፤ ወይም መምህር ትሆን ነበር። በዚህ ድልድይ ምክንያት የልጄን ሕይወት ማጣቴ ህመሜን አክብዶታል ብለዋል። ተያያዥ ርዕሶች
የበር መጥሪያ ደወል ኩባንያ ለፌስቡክና ለጉግል መረጃ አሳልፎ እየሰጠ ነው ተባለ
ጥር ይህንን ለማጋራት በ ዋትስአፕ የበር መጥሪያ ደወል ኩባንያ የደንበኞቹን መረጃ አሳልፎ ፌስቡክና ጉግልን ለመሳሰሉ ድርጅቶች አሳልፎ እየሰጠ እንደሆነ አንድ ምርመራ አጋልጧል። የራሱ አፕሊኬሽን መተግበሪያ ያለው ሪንግ አፕ የተሰኘው የበር መጥሪያ ደወል መከታተያ እንዲሁም የደንበኞችን ግላዊ መረጃዎችን መላክ እንዲያስችሉ አድርገው እንደተሰሩ ኤሌክትሮኒክ ፍሮንቲየር ፋውንዴሽን የተሰኘው ድርጅት በሪፖርቱ አመልክቷል። መረጃው እንደሚያሳየው አምስት ኩባንያዎች የተለያዩ መረጃዎችን ለምሳሌም ያህል የደንበኞችን ስም፣ ደንበኞች ስልካቸውን የሚጠቀሙበትን አድራሻና የሞባይል ኔትወርክን የመሳሰሉ አግኝተዋል ተብሏል። አደጋውን ስሰማ በረራው ጠዋት እንዳልሆነ ራሴን አሳመንኩኝ የረዳት አብራሪው ጓደኛ ኩባንያው ሪንግ በበኩሉ አሳልፎ የሰጠው መረጃ የተወሰነ እንደሆነ ነው። ኩባንያው ጊዝሞዶ ለተባለው የእንግሊዝ ሚዲያ እንደተናገረው እንደ ማንኛውም ኩባንያ ሪንግ የሞባይል መተግበሪያውን ለመፈተሽ በዚያውም ያሉትን አገልግሎቶች ለማሻሻል፣ እንዲሁም ደንበኞች በአገልግሎታችን ምን ያህል ረክተዋል የሚለውን ለማየት የሦስተኛ ወገን አገልግሎትን እንጠቀማለን። ኩባንያው ይህንን ይበል እንጂ ፋውንዴሽኑ በበኩሉ የደንበኞችን ግላዊ መረጃ መጠበቅ እንደተሳነውና በተለይም ከክትትል ጋር ተይይዞ ኩባንያው ለማንም የማያጋራው መረጃ እንደሆነ ቢገልፅም የተባለው ተግባራዊ አልሆነም ብሏል። ይህንን መረጃ በማጋራት ደንበኞች በማንኛውም ወቅት የጣት አሻራቸውን በመጠቀም ተንቀሳቃሽ ስልካቸውን በሚጠቀሙበት ወቅት የትኛውንም እንቅስቃሴያቸውን ለመሰለል አስችሏል ተብሏል። ኩባንያው የደንበኞችን መረጃን ያቀበለው ለፌስ ቡክ፣ ብራንች፣ አፕስ ፍላየር፣ ሚክስ ፖናልና ጉግል የመረጃ ኩባንያዎች ነው። የፋውንዴሽኑ ምርመራ እንደሚያሳየው ሪንግ ኩባንያ መረጃዎችን አሳልፎ የሰጠው አንድሮይድ ሶፍትዌሮችን ለሚቀብሉ ስልኮች ነው። ሪንግ የተባለው የበር መጥሪያ ደወልና ለቤት አገልግሎት የሚውሉ ካሜራዎችን እንዲሁም የደህንነት ቁሳቁሶችን የሚያቀርብ ሲሆን ባለቤትነቱም የአማዞን ነው። ኩባንያው ከዚህ ቀደምም ካሜራዎቹንና የደህንነት ቁሳቁሶቹን ለህግ አስከባሪ አካላት ለስለላ ተግባር አውሏል በሚል ተወንጅሏል። ከዚህ በተጨማሪ ጎረቤታሞች የስለላ ተግባር እንዲያከናውኑ በር ከፍቷል፤ እንዲሁም ካሜራዎቹም በተለያዩ አካላት እንደተጠለፉ መረጃዎችም በመውጣት ላይ ናቸው። ቢቢሲ ማስተባበያ
አምስቱ ተስፋ የተጣለባቸው አፍሪካውያን ሙዚቀኞች
ዲሴምበር ማጋሪያ ምረጥ አጭር የምስል መግለጫ ናይጀሪያዊው ዊዝ ኪድ ዴቪዶ፣ ዊዝኪድ፣ በርና ቦይ ከአፍሪካ ማህፀን የተገኙ ሙዚቀኞች ሲሆኑ፤ ድንበር፣ ቋንቋ ፣ ባህል ሳይገድባቸው በአለም አቀፉ የሙዚቃ መድረክም ስመ ጥር ሊሆኑ ችለዋል። ለዚያም ነው ምዕራባውያኖቹ መዚቀኞችም ሆነ ፕሮዲውሰሮች አይናቸውን ወደ አፍሪካ ሙዚቀኞች እያማተሩ ያሉት። በዚህ አመት በወጣው ላየን ኪንግ የካርቱን ፊልም ተነሳስታ ቢዮንሴ አልበሟን ስትሰራም ታዋቂ አፍሪካዊ ሙዚቀኞችን አካታለች። ሚስተር ኢዚና በርና ቦይም በሙዚቃው ዓለም ከፍተኛ ስፍራ በተቸረው በአመታዊው የኮቼላ ሙዚቃ ፌስቲቫል ተሳትፈዋል። ሊጠናቀቅ አንድ ወር በቀረው የአውሮፓውያኑ ዓመት የአድማጮችን ቀልብ መያዝ ከቻሉት ጥቂት አፍሪካውያን ሙዚቀኞች አምስቱ እነሆ፡ ሺባህ ካሩንጊ ኡጋንዳ አጭር የምስል መግለጫ ሺባህ በእናት ሃገሯ ኡጋንዳ በሙዚቃው ዘርፍ ተደማጭነት ያገኘችው ሺባህ በአሁኑ ወቅት ደግሞ ሃገሯን አልፎ ሙዚቃዋ ወደሌሎች ሃገራት ደርሷል። በሚስረቀረቅ ድምጿ የብዙዎችን ቀልብ መሳብ የቻለችው ሺባህ ከተለያዩ አርቲስቶችም ጋር በመጣመር ትስራለች። ሙዚቃውን ከዳንስና ከፋሽን ጋር በማጣመር ለራሷም ሆነ ለሃገሯ ስም ማትረፍ ችላለች። በመድረክም ላይ ባላት ድንቅ ችሎታ እንዲሁ ታዳሚውን ወደ ሙዚቃዋ ጠልቃ የምታስገባበበት መንገድ ብዙዎችን እንዲደመሙ አድርጓቸዋል። ጆቦይ ናይጀሪያ አጭር የምስል መግለጫ ጆቦይ ናይጀሪያዊው ጆቦይ ቤቢ በሚለው የፍቅር ዘፈኑ የብዙ አድማጮችን ጆሮ ማግኘት የቻለ ሲሆን፤ ይህ ሙዚቃውም በዩቲዩብ ላይ አስራ አምስት ሚሊዮን ተመልካቾችን ማግኘት ችሏል። በስሜት በተሞላ አዘፋፈኑና በሚንቆረቆረው ድምፁ የተለያዩ የሙዚቃ ስልቶችን ማጣመር የቻለ አርቲስት ነው። አፍሮ ቢትንና ፖፕን በማጣመር የሰራው ሌላኛው ዘፈኑ ቢጊኒንግ ከፍተኛ ተቀባይነትን ማትረፍ ችሏል። በነዚህ ነጠላ ዘፈኖቹ እውቅናን ማትረፍ የቻለው ጆቦይ በተለያዩ ሃገራትም በሚገኙ ፌስቲቫሎች ላይ ከሚጋበዙ ሙዚቀኞች አንዱ መሆን ችሏል። ብሪያን ናድራ ኬንያ ከሁለት ዓመታት በፊት ባወጣው ነጠላ ዘፈን ሊዮ የሙዚቃው ዓለም ላይ ስሙን የጣለው ብሪያን ሙዚቃውን ከሚሊኒየሙ ባህል የተገኘ፤ የተንቀሳቃሽ ስልክ ዘመንን ያማከለ፤ የከተማ ድምፅ በማለት ይገልፀዋል። ኬንያዊው ሙዚቀኛ፣ ገጣሚና የሙዚቃ ፀሐፊ የምስራቅ አፍሪካ የፖፕ ሙዚቃ ስልት አምባሳደር እየተባለ እየተጠራ ሲሆን፤ በዓለም አቀፉ ደረጃ ኬንያ የሙዚቃውን ገበያ ሰብሮ መግባት የቻለ ሙዚቀኛ የሌላት ሲሆን ብሪያን ይህንንም ሊቀይር ይችላል እየተባለ ነው። ለየት ያለ የአዘፋፈን ዘዬ ያለው ብሪያን ለስለስ ካሉ ዘፈኖቹ በተጨማሪ ራፕ ማድረግን እንዲሁም የተለያዩ የሙዚቃ ስልቶችን እንደ ሬጌና ሌሎችም ሙዚቃ ስልቶችን ማጣመር ችሏል። ኢኖስ ቢ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኦፍ ኮንጎ መነሻውን የኮንጎ ባህላዊ ሙዚቃ ያደረገው የ አመቱ ኢኖስ ሌሎች የሙዚቃ ስልቶችን በመጨመር ሙዚቃውን አንድ ደረጃ ወደፊት ሊያራምድ ይችላል እየተባለ ነው። ከታንዛንያው ሙዚቀኛ ዳይመንድ ጋር የተጣመረበት ዮፔ የተባለው ነጠላ ዘፈኑም ብዙዎችን አስደስቷል። የሙዚቃ ቪዲዮው በወጣበት በሶስት ወራትም አስራ አራት ሚሊዮን ተመልካቾች አይተውታል። ኢኖስ ቢ የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ መለያ የሆነውን ሩምባ የሙዚቃ ስልትንም ከሪትም ኤንድ ብሉዝና አፍሮ ቢትስ ጋር ማቀላቀል ችሏል። ሾ ማድጆዚ ደቡብ አፍሪካ አጭር የምስል መግለጫ ሾ ማድጆዚ በአለም የሙዚቃ መድረክ ዝናዋ እየናኘ ያለው ደቡብ አፍሪካዊቷ የሂፕ ሆፕ አርቲስት ሾ በዚህ ዓመት የቢኢቲ ብላክ ኢንተርቴይንመንት አዲስ ዓለም አቀፍ አርቲስት በሚል ዘርፍ ሽልማትን ማግኘት ችላለች። በታላቅ ስሜት የምትዘፍነው አርቲስቷ መድረክ ላይ ሲሆን ያ ስሜቷ በሰው ላይ ይሰርፃል ይሏታል። የደቡብ አፍሪካ ግኮም የሙዚቃ ስልት በመሳሪያ ብቻ የተቀነባበረ ቢሆንም ሾ ግን ራፕ ታደርግበታለች፤ በአንድ ሳይሆን በተለያዩ ቋንቋዎች። ምንም እንኳን ብዙዎቹ የደቡብ አፍሪካ አርቲስቶች የሙዚቃ ገበያ ትኩረት ሃገራቸው ላይ ቢሆንም ሾ ግን የአለም አቀፉን ገበያ እያማተረች ነው። ተያያዥ ርዕሶች
ታይላንዳዊው የ ዓመቱ ቦክሰኛ አኑቻ ኮቻና በቦክስ ውድድር ሳቢያ ሕይወቱ አለፈ
ኖቬምበር አጭር የምስል መግለጫ ታዳጊው የቦክስ ውድድር የጀመረው በ ዓመት ዕድሜው ነበር የ ዓመቱ ታዳጊ የቦክስ ውድድር ሳቢያ ሕይወቱ ማለፉን ተከትሎ ታይላንድ የህፃናት የቦክስ ውድድርን እንድታግድ የነበሩ ጥያቄዎች በርትተው ቀጥለዋል። አኑቻ ኮቻና በአንድ ግብረ ሰናይ ድርጅት ባዘጋጀው ውድድር ላይ ባጋጠመው የጭንቅላት ውስጣዊ ደም መፍሰስ ለሁለት ቀናት ህክምና ሲከታተል ቆይቶ ሕይወቱ አልፏል። የታቃራኒ ቡድን አባላት እንደገለፁት ታዳጊዎቹ ራሳቸውን ከአደጋ የሚከላከሉበት ትጥቅ አላጠለቁም ነበር። በዚህም ሳቢያ በውድድሩ ወቅት ታዳጊው ከመውደቁ በፊት ጭንቅላቱ ላይ መመታቱ ታውቋል። ታዳጊው ከ ዓመት ዕድሜው አንስቶ ቤተሰቦቹን ለመርዳት ግጥሚያዎችን አድርጓል። በታይላንድ ሟይ ተብሎ የሚጠራው የታዮች የቦክስ ውድድር በአገሪቱ በስፋት የሚታወቅ ነው። በሺዎች የሚቆጠሩ ተጋጣሚዎችና ቤተሰቦቻቸው ውድድሩን ገንዘብ የማግኛ መንገድ አድርገውታል። ይሁን እንጂ ይህንን ስፖርት ለማካሄድ ህጉ ክፍተት እንዳለበት ተደጋግሞ ይነሳል። በተቃራኒው አንዳንድ ሰዎች ህፃናቱን ከአደጋ ለመጠበቅ ሲባል ውድድሩን ለማገድ የሚደረገውን ጥረት አስፈላጊ አይደለም ሲሉ ይቃወማሉ፤ ምክንያታቸው ደግሞ በአገሪቱ ያለው ባህላዊ የቦክስ ውድድር አካል መሆን አለባቸው የሚል ነው። ይሁን እንጂ የጉዳዩን አደገኝነት ያሳሰበው የታይ ምክርቤትም ከ ዓመት በታች የቦክስ ውድድርን ለማገድ ህጉን እየመረመሩ ይገኛሉ። በታዳጊው አኑቻ ህልፈት በርካታ የታይ ነዋሪዎች አዝነዋል፤ በመካከለኛው ሳሙት ፕራካን ግዛት የተደረገው ውድድር ላይ የተነሳውን የቦክሰኛውን ምስል በመጋራት ሀዘናቸውን እየገለፁ ነው። በርካታ ቁጥር ያላቸው የቦክስ ከዋክብትም ሃዘናቸውን ገልፀዋል። ሃገሬን ሳላስብ የዋልኩበት፤ ያደርኩበት ቀን የለም ብርቱካን ሚደቅሳ የታይላንድ የብሔራዊ ስፖርት ባለስልጣን ባለፈው ዓመት ባወጣው መረጃ በአገሪቱ ዕድሜያቸው ከ ዓመት በታች የሆኑ ከ ሺህ በላይ ቦክሰኞች ተመዝግበዋል። ስፖርትን የተመለከተው የብሔራዊ ህግ አውጭ ጉባዔ ምክትል ኃላፊ ገን አዱሌኣድጂ ኢንታፖግ በበኩላቸው ዕድሜያቸው ከ ያሉ ህፃን ቦክሰኞች መመዝገብ፤ ከቤተሰቦቻቸው ፈቃድ ማግኘት እንዲሁም ራሳቸውን ከአደጋ የሚጠብቁበት ልብስ መልበስ አለባቸው ሲሉ ተናግረዋል። በዚህ ጉዳይ ላይ ዘመቻ የሚያካሄዱ ቡድኖች ለውድድሩ አነስተኛው ዕድሜ ዓመት መሆን አለበት ሲሉ ጠይቀዋል። ከአኑቻ ሞት ቀደም ብሎ ጣላኒያዊው ቦክሰኛ ክርስቲያን ዳጊኦ በውድድር ላይ ሕይወቱ ማለፉ የሚታወስ ነው። ተያያዥ ርዕሶች
በነጆው ጥቃት ከተገደሉት አንዱ የማዕድን ኩባንያው ባለቤት ነበር
ማርች ማጋሪያ ምረጥ ትናንት በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን ነጆ ወረዳ ሁምነ ዋቀዮ በተባለ ቀበሌ ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት የአምስት ሰዎች መገደላቸውን የኦሮሚያ ክልል የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ አስታውቆ ነበር። ማክሰኞ ዕለት በታጠቂዎቹ ጥቃት የተገደሉት አምስት ሰዎች ሰንራይዝ በሚባል በአካባቢው የማዕድን ማውጣት ሥራ ላይ ለተሰማራ ኩባንያ የሚሰሩ እንደነበር ታውቋል። በጥቃቱ የተገደሉት ሦስት ኢትዮጵያዊያን እና ሁለት የውጪ ሀገራት ዜጎች ሲሆኑ እነሱም የህንድና የጃፓን ዜግነት ያላቸው እንደሆ የአካባቢው ኮማንድ ፖስት አባል የሆኑት አቶ አደም ኢስማኤል ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። ከተገደሉት አራቱ ወንዶች ሲሆኑ አንዷ የውጪ ዜጋ ሴት ናት። ኢትዮጵያዊያን፣ ጃፓናዊትና ህንዳዊ በታጣቂዎች ተገደሉ እነዚህ የጥቃቱ ሰለባዎች ከማዕድን ኩባንያው ጋር ይሰሩ የነበሩ ሲሆን አንደኛው የኩባንያው ባለቤት እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል። አቶ አለማየሁ በቀለ ይህንን የማዕድን ማውጣት ሥራ ለመጀመር ሦስት ዓመታትን የፈጀ ጥናት ማከናወኑንና የምርት ሥራውን ለመጀመር በተቃረበበት ወቅት ከአራት ባልደረቦቹ ጋር በታጣቂዎቹ መገደሉን የቅርብ ጓደኛው አቶ አቦማ አምሳሉ ለቢቢሲ ተናግሯል። አቶ አለማየሁ ከአንድ ወር በፊትም በሥራው አካባቢ በድንጋይ በተፈጸመ ጥቃት በመኪናው ላይ የመሰባበር ጉዳት የደረሰበት ሲሆን፤ ከአካባቢው ወጣቶችና ህብረተሰብ ጋር ለመግባባትና ከሥራው ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማድረግ ለመወያየት ዕቅድ እንደነበረው ጓደኛው አቶ አቦማ ያስታውሳል። አቶ አለማየሁ በቀለ ተወልዶ ያደገው ጊምቢ ውስጥ ሲሆን ነዋሪነቱ አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ነበር። እንዲሁም ባለትዳርና የሦስት ልጆች አባት፤ የመጀመሪያ ልጁም ገና አምስት ዓመቱ እንደሆነ አብሮ አደግ ጓደኛው ጨምሮ ገልጿል። አምስት ነጥቦች ስለጌዲዮ ተፈናቃዮች ከአቶ አለማየሁ ጋር አብረው በጥቃቱ ከተገደሉት አንደኛው የመኪናው ሹፌር ሲሆን ሌሎቹ ግን በማዕድን ሥራው የሚረዱት ባለሙያዎች ነበሩ። ጃፓናዊቷና ሕንዳዊው ሥራውን ለማቀላጠፍ በዕውቀትና በልምዳቸው እንዲያግዙት የቀጠራቸው ባለሙያዎች እንደሆኑም ተገልጿል። ግድያው ከተፈጸመ በኋላ የወጡ መረጃዎች የድርጊቱ ፈጻሚዎች ማንነታቸው እንዳልታወቀ የያመለከቱ ቢሆንም አመሻሽ ላይ የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር በብሔራዊው ቴሌቪዥን ላይ ቀርበው ታጣቂዎቹ ኦነግ ሸኔ የተባለው ቡድን አባላት መሆናቸውን ገልጸዋል። ምክትል ኮሚሽነሩ ጀነራል ረታ በላቸው እንደተናገሩት፤ አምስቱን ሰዎች በመግደል መኪናቸውን ያቃጠሉት በአካባቢው እየተዳከመ የመጣው የሸኔ ቡድን አባላት ናቸው በማለት የጸጥታ ኃይሉም አስፈላጊውን እርምጃ ይወስዳል ብለዋል። ግድያውንና ምክትል ኮሚሽነሩ የተናገሩትን በተመለከተ ምላሽ እንዲሰጡ የኦነግ ቃል አቀባይ የሆኑትን አቶ ቶሌራ አደባን ቢቢሲ ጠይቆ የድርጅቱን ወታደሮች በተመለከተ የዕርቅ ኮሚቴው የያዘው ጉዳይ በመሆኑ ሃሳብ መስጠት አንችልም ብለዋል። ነገር ግን በተፈጸመው ግድያ እጅጉን ማዘናቸውንና አስፈላጊው ማጣራት መደረግ እንዳለበት አቶ ቶሌራ ጨምረው ተናገረዋል። ቀደም ባሉት ጊዜያት በምዕራብ ኦሮሚያ ከሚፈጸሙ ጥቃቶችና የጸጥታ ችግሮች ጋር በተያያዘ የኦነግ ስም በሚነሳበት ጊዜ ድርጅቱ በሚሰጠው ምላሽ ላይ መንግሥት ላይ ክስ ያቀርብ የነበረ ሲሆን አሁን ግን ከዚህ ተቆጥቧል። ተያያዥ ርዕሶች
በጦላይ የኦነግ ሠራዊት አባላት ላይ የተከሰተው ምንድን ነው
ኤፕረል ማጋሪያ ምረጥ ከባለፈው እሁድ ጀምሮ የጤና እክል ገጥሟቸው ሆስፒታል እየገቡ ያሉ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ኦነግ ወታደሮች ቁጥር እየጨመረ ነው። ወታደሮቹ ቁርስ ተመግበው ሲነሱ ብዙ እራሳቸውን እየሳቱ መውደቅ መጀመራቸው መነገሩ ይታወሳል። ወታደሮቹ ጨምረውም የቀረበላቸው ሻይ ውስጥ ነጭ ባዕድ ነገር መመልከታቸው እና የተለየ ጠረን እንዳለው ጨምረው ተናግረዋል። ሻይ በምንጠጣበት ብርጭቆ ስር ነጭ ዱቄት የሚመስል ነገር አግኝተናል፤ ይህንንም ለማሰልጠኛው አስተዳደሮች አሳይተናል ሲል አንድ ስሙ እንዲጠቀስ ያልፈለገ የኦነግ ሠራዊት አባል ለቢቢሲ ተናግሯል። ትጥቅ የፈቱ የኦነግ ወታደሮች የረሃብ አድማ ላይ ናቸው የጤና እክል በገጠማቸው የሠራዊቱ አባላት ላይ የሚታዩበት ምልክት ምን እንደሆነ ሲናገር የአፍ ድርቀት፣ የሆድ ቁርጠት፣ ሆድ የማቃጠል ስሜት፣ ከደም ጋር የተቀላቀለ ትውከትና የፊት መገርጣት ናቸው ብሏል። የኦሮሚያ ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር ረታ በላቸው፤ በጦላይ በሚገኙ የኦነግ ወታደሮች ላይ ያጋጠመው የጤና ችግር መንስዔ እየተጣራ ነው ያሉ ሲሆን የደረሰባቸው የጤና እክል ግን ለህይወት አስጊ አይደለም ብለዋል። እንደ ምክትል ኮሚሽነሩ ከሆነ የኦነግ ወታደሮች በወሊሶ ቅዱስ ሉቃስ ሆስፒታል የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው እንደነበር ተናግረዋል። ምክትል ኮሚሽነሩ የጦላይ ማሰልጠኛ አስተዳደሮች ጉዳት አስከተለ የተባለውን ሻይ ቀምሰው ምን የደረሰባቸው ነገር የለም ብለዋል። እኛ የቀረበላቸው ሻይ ውስጥ መርዝ ተጨምሯል ብለን አናምንም፤ ምርመራ እየተካሄደ ነው። እንደተባለው መርዝ ተጨምሮ ከተገኘ ግን ጠፋተኛው ላይ እርምጃ ይወሰዳል። በዚሁ ሆስፒታል እየታከመ የሚገኘው ሌላኛው የሠራዊቱ አባል ኢብሳ በበኩሉ የተሰጣቸውን ሁሉ ተመግበው ቢሆን ኖሮ ጉዳቱ ከፍ ያለ ሊሆን እንደሚችል ገልፆ ሁላችንም እናልቅ ነበር በማለት ተናግሯል። ኦነግ ሀገር ለመገንጠል ነው የምሠራው ብሎ አያውቅም ሽጉጥ ገለታ ዶ ር ይሄ ነገር የመርዝ ሽታ አለው ብዬ ስላስቆምኩዋቸው ሻዩን አልጨረሱትም ነበር። ገሚሱ ቀምሰው ብቻ ስለሆነ የተዉት በዚያ መንገድ ነው የተረፍነው ይላል። እከሌ ብለን ማንም ላይ ጣታችንን ባንቀስርም ህብረታችንን የማይወዱ ሰዎች እንዳሉ እንጠረጥራለን። ነገር ግን ግቢው ውስጥ ካሉ ሰዎች ጋር ምንም አይነት ግጭት የለንም ብሏል። የህክምና ባለሙያዎች ምን ይላሉ ወሊሶ በሚገኘው የቅዱስ ሉቃስ ሆስፒታል ሃኪም የሆኑት ዶ ር አብዱላቲፍ ይሲያቅ እስከ ዛሬ ማክሰኞ ከሰዓት ድረስ የኦነግ ሠራዊት አባላት ህክምና እየተደረጋለቸው መሆኑን ተናግረዋል። በእኛ ምርመራ መሰረት የምግብ መበከል መመረዝ ሳይሆን ራሱን የቻለ መርዝ ተጨምሮበት እንደሆነ ነው የሚያሳየው። የሠራዊቱ አባላትም መርዝ እንደሸተታቸው ተናግረዋል ብለዋል። ዶ ሩ ጨምረውም ታካሚዎች ራስ ምታት፣ የሆድ ቁርጠት፣ ሆድ የማቃጠል ስሜት፣ ከደም ጋር የተቀላቀለ ትዉከትና የፊት መገርጣት ምልክቶች እንደታየባቸው በመናገር እነዚህም የመርዝ ምልክቶች መሆናቸውን ተናግረዋል። ኢትዮጵያ አዲስ የጥላቻ ንግግር ህግ አያስፈልጋትም አቶ አብዱ አሊ ሂጂራ የክልሉ የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ አድማሱ ዳምጠው በበኩላቸው የኦነግ ሠራዊት አባላት በጤና እክል ምክንያት በወሊሶ ሉቃስ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው መሆኑንና የከፋ የጤና ችግርም እንደሌለ ለመንግሥት ሚዲያዎች በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል። በመግለጫቸው ጨምረው በሠራዊቱ አባላት ላይ የምግብ መመረዝ ደርሶባቸዋል፤ ሠራዊቱ ላይም ይህ ሆን ተብሎ የተደረገ ነው እየተባለ ማህበራዊ ሚዲያ ላይ የሚሰራጨው መረጃ ሀሰት ነው ብለዋል። ያጋጠመውን የጤና እክል መንስኤም ለማጣራት ፖሊስና የሚመለከታቸው አካላት ምርመራ እያደረጉ መሆናቸውን ገልፀው መንስኤውም ሲታወቅ ውጤቱ ለህዝብ ይፋ እንደሚሆን ነው። ተያያዥ ርዕሶች
በምዕራብ ኦሮሚያ ስድስት ሰዎች መገደላቸው ተሰማ
ሜይ ስለ ማጋራት ተጨማሪ ያጋሩ ማጋሪያ ምረጥ ሰኞ አመሻሽ ላይ በምዕራብ ኦሮሚያ ቄለም ዞን በመከላከያ ሠራዊት አባላት ላይ ተወረወረ በተባለ የእጅ ቦንብ ቢያንስ የስድስት ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተነገረ። በጉዳዩ ላይ ያነጋገርናቸው የአካባቢ ነዋሪዎችና ባለስልጣናት ቦንብ መወርወሩን ለቢቢሲ አረጋግጠው ፍንዳታውን ተከትሎ ያገጠመ ጉዳትን በተመለከተ የተለያየ ሃሳብ ሰጥተዋል። የቄለም ዞን፣ የዞን ጽሕፈት ቤት ፐብሊሲቲ ኃላፊ አቶ ሐምዛ አብዱልቃድር አደጋው የደረሰው በዞናቸው አንጪሌ ወረዳ ሙጊ ቀበሌ የሚባል ቦታ ላይ መሆኑን ተናግረዋል። ሰኞ አስር ሰዓት አካባቢ የኦነግ ሸኔ አባላት በመከላከያ ሠራዊት አባላት ላይ የደፈጣ ጥቃት መፈፀማቸውን የሚናገሩት ኃላፊው የወረወሩት ቦንቡ ፈንድቶ በአካባቢው የሚገኙ ስድስት ሰዎች መሞታቸውን አስረድተዋል።
ኢትዮጵያ፡ የኤች አይ ቪ ኤድስ ወረርሽኝ አዲስ ስጋት ፈጥሯል
ኦክተውበር ማጋሪያ ምረጥ ከአስር ዓመት በፊት የበርካታ ወጣቶችን ህይወት የቀጠፈው፣ ልጆችን ያለወላጅ የስቀረው እና ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ያስከተለው ኤች አይ ቪ ኤድስ አሁንም አንደ ወረርሽኝ ተከስቶ ስጋትን ፍጥሯል። የፌደራል ኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከያ እና መቆጣጠሪያ ጽ ቤት መረጃ እንደሚያሳየው በሃገር ደረጃ የቫይረሱ ስርጭት በመቶ ደርሷል። የዓለም ጤና ድርጅት እንደሚለው የኤች አይ ቪ ኤድስ ቫይረስ ስርጭት ከአንድ በመቶ በላይ ከሆነ በአንድ ሃገር ውስጥ የኤች አይ ቪ ኤድስ ወረርሸን ተከስቷል ይባላል። በ ዓ ም በሁለት ሰዎች ደም ውስጥ ብቻ ይገኝ የነበረው ቫይረስ ዛሬ ላይ ከ ሺ በላይ ዜጎች ደም ውስጥ ይገኛል ይላል፤ ከፌደራል ኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከያ እና መቆጣጠሪያ ጽ ቤት የተገኝው መረጃ። የኤች አይ ቪ ኤድስ ወረርሽኝ ቀንሷል የሚለው በህብረተሰቡ ውስጥ ያለው አመለካከት፤ በሽታው በድብቅ እንዲስፋፋ አስችሎታል። በ ዓ ም ብቻ አዲስ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ ሺ በላይ ነው፤ ይላል የፌደራል ኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከያ እና መቆጣጠሪያ ጸ ቤት። ከፍተኛ ተጋላጭነት የቫይረሱ ስርጭት በአማራ እና በኦሮሚያ ክልሎች እንዲሁም በአዲስ አበባ ከተማ ከፍተኛ ነው የተባለ ሲሆን፤ የስርጭት መጠኑም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ነው። ከዚህ በተጨማሪ ታላላቅ ፕሮጀክቶች በሚካሄዱባቸው ቦታቸው፣ አዲስ በሚመሰረቱ ከተሞች እና በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ የስርጭት መጠኑ ከፍተኛ ነው ተብሏል። በገጠር አካባቢ የሚኖሩና በአበባ እርሻ ሥራ ላይ ተቀጥረው ከሚሰሩ ሴቶች መካከል በመቶ የሚሆኑት ጥንቃቄ የጎደለው የግብረ ሥጋ ግኑኝነት በመፈፀማቸው ፅንስ ለማቋረጥ ተዳርገዋል፤ ይላል የፌደራል ኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከያ እና መቆጣጠሪያ ጽ ቤት። ለቫይረሱ ተጋላጭነት የፆታ፣ የሥራ አይነት እና የኑሮ ደረጃ አስተዋፅኦ አንደሚያደርጉ የጽ ቤቱ መረጃ ያሳያል። በሴቶች ላይ የለው የኢኮኖሚ እና ህብረተሰቡ የሚያደርስባቸው ጫና ለቫይረሱ ይበልጥ ተጋላጭ እንደሚያደርጋቸው መረጃው ያትታል። ከዚህም በተጨማሪ ሴተኛ አዳሪዎች ለቫይረሱ ተጋላጭነታቸው ጨምሯል። ጫት ቤቶች፣ ሺሻ ቤቶች እና ማሳጅ ቤቶች ለቫይረሱ ስርጭት መጨመር አስተዋፅኦ አበርክተዋል፤ ሲሉ አቶ ክፍሌ ምትኩ የፌደራል ኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከያ እና መቆጣጠሪያ ጽ ቤት የዘርፈ ብዙ ምላሸ ማስተባበሪያ ዳይሬክተር ተናግረዋል። ሃገሪቷ በ የኤች አይ ቪ ቫይረስን ስርጭት ለመግታት የያዘችው እቅድ በዚህ አካሄድ መሳካቱ አጠራጣሪ ሆኗል። ኢትዮጵያ የኤች አይ ቪ ስርጭትን መቀነስ ለምን ተሳናት ከጥቂት ዓመታት በፊት መንግሥት አና ምንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ባከናወኗቸው ተግባራት በቫይረሱ ምክንያት ይከሰት የነበረን ሞት በ በመቶ መቀነስ ተችሎ ነበር። በዚህ ስኬት ምክንያትም መንግሥትምና መንግሥታዊ የልሆኑ ድርጅቶች እንዲሁም ህበረተሰቡ በአጠቃላይ ለኤች አይ ቪ ኤድስ ይሰጡ የነበረው ትኩረት እንዲቀንስ ሆኗል። አቶ ክፍሌ እንደሚሉት በኢትዮጵያ የኤች አይ ቪ ቫይረስን ስርጭት ለመቀነስ ድጋፍ ሲያደርጉ የነበሩ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች፤ የተመዘገበውን ስኬት ከግምት ውስጥ አስገብተው ሃገሪቷ በሽታውን በራሷ አቅም መቆጣጠር ትችላለች በማለት የደርጉ የነበረውን ድጋፍ ሙሉ በሙሉ አቁመዋል። ጽ ቤታቸውም መንግሥት በመደበው በጀት የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት የሚያስችሉ ተግባራት አቅዶ እየተንቀሳቀሰ እንደሆነ ይናገራሉ። ተያያዥ ርዕሶች
ሥልጣን ለደም ግፊት አጋልጦኛል ኃይሌ ገብረሥላሴ
ኅዳር የቢቢሲ ስፖርት አፍሪካ ባልደረባ ባለፈው ሳምንት ኃይሌ ገብረሥላሴን በአዲስ አበባ አግኝታው ነበር። ከመነሻውም ግሩም ጥያቄ ነበር ያነሳችለት። አንተ የዓለም ሪከርድ ስትሰብር፣ የኦሎምፒክ ወርቆችን ስታፍስ ነው የኖርከው። ዓለም የሚያውቅህም በጽናትህ ነው። ስናውቅህ በ ይቻላል መርህ ነው። ፍጹም ተስፋ የምትቆርጥ ሰው አልነበርክም። ለምን ሥልጣንህን ለቀቅክ እንዴትስ እጅ ሰጠህ እርግጥ ነው ኃይሌ ምላሽ ሰጥቷታል። ምላሹ ግን የሁልጊዜው አልነበረም። እንደሁልጊዜው አልተፍነከነከም። የሚናፈቀው ያ ሳቁ እምብዛምም ነበር። እንዲያውም ሥልጣን ለደም ግፊት አጋልጦኛል ሲል እግረ መንገዱን ያልተጠበቀ ምላሽን ሰጥቷታል፤ ለቢቢሲ ስፖርት አካፍሪካ ወኪል። ከሁለት ዓመት በፊት ወደዚህ ሥልጣን ስመጣ ብዙ ፈተና ነበረው። አትሌቶችን ማርካትና ጥያ ቄ ዎቻቸውን መመለስ ነበር ህልሜ። ያንን ለማሳካት ያለኝን ነገር ሁሉ ለዚሁ ሥራ መስጠት ነበረብኝ። ጊዜዬን ፣ ገንዘቤን ፣ ጉልበቴን ፣ ዕውቀቴን ፤ የሚገርምሽ በቤተሰባችን ደም ግፊት ያለበት ሰው የለም። አሁን እኔ ብቻ ነኝ ግፊት የያዘኝ ። በቃለ ምልልሱ መሐል እግረ መንገድ የተገለጸው ይህ የኃይሌ ገብረሥላሴ የጤና እክል በራሱ ለአድናቂዎቹ አስደንጋጭ ዜና መሆኑ እንደተጠበቀ ኾኖ ለመሆኑ ይህን ያህል ኃይሌን ሊያስመርር የቻለው ጉዳይ ምንድነው አትሌቶች ቅሬታ ነበራቸው። ጥቂት ቢሆኑም ፣ የማይታወቁ ቢሆኑም ፣ በኔ ደስተኛ ያ ል ሆኑ አትሌቶች ሰልፍ አደረጉ። ዝነኛ ላይሆኑ ይችላሉ ኮ ። ብዙ ላይሆኑ ይችላሉ። ግን ተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ። በቃ በኔ ደስተኞች አልነበሩም። እንዴ እነሱን ማስደሰት ካልቻልኩ ለምን ብዬ አመራር ላይ እቆያለሁ ለሌሎች ዕ ድል መስጠት ነበረብኝ። ኃይሌ የርሱን ከአትሌቲክስ ፌዴሬሽን በገዛ ፈቃድ መነሳት አስታኮ በአፍሪካ ሥልጣንንን ርስት ማድረግ ማብቃት እንዳለበትም እግረ መንገዱን ምክር ቢጤ ጣል አድርጎ ነበር። እኛ አፍሪካዊያን ለተቀረው ምሳሌ መሆን አለብን። ሥ ልጣን ላይ ሙጭጭ ማለት አያስፈልግም። የምንመራው ሕዝብ ካልፈለገን መልቀቅ ነው። ሕዝብ ካልወደደን ለምን ጎትቶ እስኪጥለን እንቆያለን። ሥልጣን እንደ አትሌቲክስ ነው። ካላሸነፍክ ለሚያሸንፈው አትሌት መልቀቅ ይኖርብሃል። በቃ የኃይሌ ወደ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን መምጣት ብዙዎች ይንሸራተት ይዟል ለሚሉት የአትሌቲክስ ውጤታችን እንደ ሁነኛ ማስፈንጠሪያ ቆጥረውት ነበር። አሁን ገና ሞያና ሞያተኛ ተገናኙ ያሉም ብዙ ነበሩ። ጉዞው በሁለት ዓመት ይገታል ያለ ግን አልነበረም። በኢትዮጵያ የሚገኙ ቤተ እስራኤላውያን ወደ ፅዮን ውሰዱን ተማፅኖ የቢቢሲ አፍሪካ የስፖርት ባልደረባ የመጨረሻ ጥያቄ ያነሳችለት የማበረታቻ መድኃኒቶች በአፍሪካ አትሌቶች ዘንድ የመዘውተሩን ጉዳይ ነበር። በአትሌቲክስ ሐቀኛ መሆን ቁልፍ ነገር ነው። ሲል ምላሽ መስጠት የጀመረው ኃይሌ በማበረታቻ ታግዞ ዘላቂ ውጤት ማምጣት እንደማይቻል አጽእኖት ሰጥቶ ተናግሯል። ዓለም አቀፍ አትሌት ለመሆን በቅድሚያ ሐቀኛና ታማኝ መሆን የግድ ነው። ሐቀኝነት ለድል ያበቃል። ሲል ከተናገረ በኋላ በተፈጥሮ መታደላችን ምን ያህል ለውጤችን አስተዋጽኦ እንደሚያደርግ ያብራራል። ኧ ረ ለመሆኑ ኢትዯጵያና ኬንያ ለምንድነው አበረታች መድኃኒት የሚፈልጉት ንገሪኝ እኛ እኮ ፈጣሪ የሰጠን ማ በ ረታቻ አለ። እሱን አንጠቀምም ተመልከችው እስኪ ተ ራራውን። ተመልከቺው አየሩን። ይህ የኛ የተፈጥሮ ዶፒንግ ነው። ማበረታቻ የሚወስዱ አትሌቶች ለጊዜው ገንዘብ ማግኘት ቢችሉ እንኳ ያገኙት ገንዘብ በረከት እንደማይኖረውም ኃይሌ ጨምሮ ተናግሯል። ይዟቸው ነው የሚጠፋው። ይላል። የስኬታማነት ተምሳሌቱ ኃይሌ ለቢቢሲ አፍሪካ ስፖርት ባልደረባ የሕይወት ፍልስፍናውን በገደምዳሜ አጫውቷት ነበር፤ እግረ መንገዱን። ሕይወት አጭር ና ት፤ ሀብትና ንብረት ይዘን አንቀበርም። ባዶ ኪሳችንን ነው የመጣነው ፣ ባዶ ኪሳችንን ነው የምንሞትው። ስትቀበሪ ሳንቲም ሬሳ ሳጥንሽ ውስጥ የሚያጭቅልሽ አይኖርም። ባዶ ገላን ይዘን ነው የመጣነው ፤ ባዶ ገላችንን እንለመሳለን። ይኸው ነው። ሲል አጠር ያለ አስተያየቱን ቋጭቷል ። ቢቢሲ ማስተባበያ
የአንድ ቤተሰብ አባላት ግድያ በቤኒሻንጉል ክልሏ ያሶ ከተማ
ኖቬምበር ማጋሪያ ምረጥ ባለፈው ሳምንት በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ያሶ ከተማ በፈፀመ ጥቃት ስምንት የአንድ ቤተሰብ አባላት መገደላቸውን የሟች ቤተሰቦች ለቢቢሲ ተናገሩ። ህዳር ቀን ማታ ከሶስት ሰዓት በኋላ ታጣቂዎች የቤተሰብ አባላቱን በጥይት ገድለው ቤታቸውንም እንዳቃጠሉ በጥቃቱ ባለቤታቸውንና የባለቤታቸውን ወንድሞች ያጡት የስምንት ልጆች እናት ወ ሮ ልኪቱ ተፈራ ይናገራሉ። መጀመሪያ ተኩስ ከከፈቱብን በኋላ ቤት ውስጥ ጭድ ጨምረው እሳት ለኮሱብን። እኔና ልጆቼ በጓሮ በር በኩል አመለጥን። ሌሎቹ ግን እዚያው ተቃጠሉ በማለት ሁኔታውን ያስታውሳሉ። ልጃቸው አቶ ወጋሪ ፈይሳ በመኖሪያ ቤታቸው በወቅቱ ሃያ አንድ የቤተሰብ አባላት እንደነበሩና ቤታቸውም ፖሊስ ጣቢያ አቅራቢያ በመሆኑ ደህንነት ተሰምቷቸው እንደነበር ይናገራል። ነገር ግን ያልጠበቁት ነገር መከሰቱንና በተፈጠረው ነገርም ህፃናት ልጆች ከፍተኛ ድንጋጤ ውስጥ እንዳሉም ይገልፃሉ። የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የፀጥታና አስተዳደር ቢሮ ሃላፊ አቶ ሙሳ አህመድ ከተማው ውስጥ ግድያ ስለ መከሰቱ መረጃ እንዳላቸው ነገር ግን ዝርዝር ጉዳዮችን እንደማያውቁ ገልፀዋል። ከጥቃቱ የተረፉ የቤተሰቡ አባላት ሸሽተው የተጠለሉበት አዋሳኝ የምሥራቅ ወለጋ ሃሮ ሊሙ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ጋሮማ ቶሎሳ ግድያው ስለመፈፀሙ ማረጋገጫ እንዳላቸው ለቢቢሲ ተናግረዋል። አባቴ ፈይሳ ዲሳሳ፣ ወንድሙ ዲንሳ ዲሳሳን ጨምሮ ስምንት የአጎቶቼ ልጆችን አጥተናል። ግድያው በጣም አሰቃቂ ነበር ይላሉ አቶ ዋጋሪ። በተመሳሳይ እለት የቤተሰብ አባላቱን ግድያ ጨምሮ በያሶ ከተማ በተፈፀመ ጥቃት አርባ የሚሆኑ ሰዎች መገደላቸውን ኗሪዎችና የአዋሳኝ ወረዳ አስተዳዳሪው ቢናገሩም የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፀጥታና አስተዳደር ቢሮ ሃላፊው አቶ ሙሳ ግን አስር ሰው ብቻ ስለመገደሉ መረጃ እንዳላቸው ይገልፃሉ። ሆኖም ግን ጉዳዩን በሚመለከት ተጨማሪ መረጃ እንደሚያስፈልጋቸው መንገድ በመዘጋቱ ነገሮችን በቅርበት ማጣራት አልቻልንም በማለት ተናግረዋል። አቶ ሙሳ እንደሚሉት የረቡዕ ጥቃት ከመፈፀሙ ከጥቂት ቀናት በፊት ሁለት የመንግሥት ሰራተኞች ተገድለዋል። አርብ እለትም ደግሞ በካማሼ ሌሎች ሦስት ሰዎች መሞታቸውንም ገልፀዋል። በያሶ ጥቃቱን የፈፀሙት ታጣቂዎች ከመሆናቸው በዘለለ ስለታጣቂዎቹ እስካሁን ምንም የተረጋገጠ መረጃ እንደሌለ አቶ ሙሳ ይናገራሉ። ያፈነገጡ የኦነግ ታጣቂዎች ለአካባቢው ስጋት እየሆኑ እንደሆነ አቶ ሙሳ ቢናገሩም ያነጋገርናቸው ኗሪዎች እና የአዋሳኝ ወረዳ ሃላፊዎች ግን በአካባቢው የኦነግ ታጣቂ እንደሌለ ገልፀዋል። በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ አራት የካማሺ ዞን ሃላፊዎች አሶሳ ከተማ ስብሰባ ቆይተው ወደ ካማሺ በመመለስ ላይ ሳሉ በተከፈተባቸው ተኩስ ህይወታቸው ማለፉን ተከትሎ በተፈጠረ ግጭት ብዙዎች መገደላቸውንና ወደ በአስር ሺህዎች የሚቆጠሩ ከቀያቸው መፈናቀላቸው ይታወሳል። በአሁኑ ወቅት ግን ነገሮችን ለመቆጣጠር በያሶ ከተማ ፌደራል ፖሊስ፤ በካማሽ ደግሞ መከላከያ ሠራዊት እንደገባ አቶ ሙሳ ገልፀዋል። ተያያዥ ርዕሶች
ወንዶች አዞ ለመምሰል ቆዳቸውን የሚበሱባት ሃገር
ነሐሴ ይህንን ለማጋራት በ ትዊተር ይህንን ለማጋራት በ ዋትስአፕ በአለማችን ሁለተኛዋ ትልቅ ደሴት በሆነችው ፓፓ ኒው ጊኒ፤ በመቶ የሚሆኑት ዜጎች መኖሪያቸው ገጠራማ በሆኑት አካባቢዎች ነው። አብዛኛዎቹ ለሰለጠነው አለም ብዙም ቅርበት የላቸውም። በዚህ ዘመን ይኖራሉ ተብለው የማይታሰቡ ባህላዊ ስነ ስርአቶች አሁንም ድረስ በዚህች ደሴት ላይ ይስተዋላሉ። በፓፓ ኒው ጊኒ የመንፈስ ቤቶች ተብለው የሚጠሩት የአምልኮ ቦታዎች በአብዛኛው ነዋሪ ትልቅ ቦታ የሚሰጣቸው ናቸው። በዚህ ቦታ የተለያዩ ሰዎች ነፍሳቸውን በተለያዩ የእንሰሳት መንፈስ የሚመሰሉላቸው ሲሆን፤ የአዞ መንፈስን የሚስተካከለው የለም። እነዚህ የአምልኮ ቦታዎች በብዙ የእንስሳት ቅሪቶች የተሞሉ ሲሆን፤ ከአሳማ እስከ ፈረስ፤ ከእባብ እስከ ንስር አሞራ ቅሪቶች በግድግዳዎቹ ላይ ይሰቀላሉ። ነገር ግን ለዚህ አካባቢ ሰዎች እንደ አዞ ሃይል እና ብልሃትን ያጣመረ እንስሳ የለም። ታዳጊ ወንዶች በእድሜ መብሰላቸውን ለማረጋገጥ ወደ እነዚህ የመንፈስ ቤቶች በመሄድ ጀርባቸው፣ ትከሻቸውና ደረታቸው ላይ ስለት ባላቸው ነገሮች ይበሳሉ። ምንም እንኳን ስነ ስርአቱ ከባድ ህመም ያለው ቢሆንም፤ ባህል ነውና ሁሉም የፓፓ ኒው ጊኒ ታዳጊዎች በጉጉትና በደስታ ያደርጉታል። ለእነሱ አዞን መምሰል የጥንካሬያቸውና በእድሜ የመብሰላቸው ማሳያ ነው። ታዳጊዎቹ ወደ መንፈስ ቤቶቹ የሚወሰዱት በአጎቶቻቸው ሲሆን፤ ቆዳቸውን የመብሳቱ ሂደት ከአንድ እስከ ሁለት ሰአት ሊፈጅ ይችላል። እንደውም ከዘመናዊ ፈጠራዎች መምጣት ጋር ተያይዞ የሚጠቀሟቸው ስለቶች እተሻሻሉ መጡ እንጂ፤ በድሮ ጊዜ የሚጠቀሙት ስል ቀርከሃ እንደነበር የአካባቢው ምክትል ተወካይ አሮን ማሊነጊ ይናገራሉ። ታዳጊዎች ከህመሙ ብዛት አንዳንድ ጊዜ ራሳቸውን ስተው እንደሚወቀድቁም ተወካዩ ይናገራሉ። ቁስሉ ቶሎ እንዲድንና ሌላ ችግር እንዳይፈጥር በአካባቢው በብዛት ካለ ዛፍ የሚገኝ ዘይት ይደረግበታል። ስነ ስርአቱ ያስፈለገው የታዳጊዎቹ እናቶች እነሱን ሲወልዱ ያፈሰሱትን ደም ለማስታወስና ከዚህ በኋላ የራሳቸውን ደም በማፍሰስ ትልቅ ሰው መሆናቸውን ለማሳየት ነው። ከዚህ በተጨማሪ ታዳጊዎች ስነ ስርአቱን ከጨረሱ በኋላ በመንፈስ ቤቶች ውስጥ ለወራት በመቀመጥ ከታላላቆቻቸው የህይወት መንገዶችንና እንደ አሳ ማጥመድ ያሉ ሌሎች አስፈላጊ እውቀቶችን ይማራሉ።
ከድንበር ውዝግብ በኋላ ቻይናና ህንድ በውሃ ምክንያት ተፋጠዋል።
መስከረም ይህንን ለማጋራት በ ዋትስአፕ በየዓመቱ በዝናብ ወቅት ወንዙ በጣም ይሞላና በሰሜን ምስራቅ ሕንድ እና በባንግላዴሽ ትልቅ ኪሳራ ያስከትላል። ቻይናና ሕንድ አሁንም ሊከሰት የሚችል የድንበር ጦርነትን ቢያረግቡም ፍጥጫው ግን ወደ ሌላ አከራካሪ አለመግባባት አምርቷል፤ ውሃ። በዚህ የዝናብ ወቅት በስምምነታቸው መሠረት ዴልሂ ከቻይና ስለ ብራሕማፑትራ ወንዝ ማግኘት የነበረባትን የሃይድሮሎጂ ማለትም የውሃ ደረጃ እንቅስቃሴና ስርጭትን የተመለከተ የሳይንሳዊ ጥናት መረጃ እንዳልተረከበች ተናግራለች። የእስያ ትልቁ ወንዝ የሆነው ብራሕማፑትራ ከቲቤት ተነስቶ ወደ ሕንድ ፈሶ ከዚያም ወደ ባንግላዴሽ በማምራት ከጋንጂዝ ጋር ተቀላቅሎ በቤንጋል ሠርጥ ያበቃል። ቤይጂንግ የሃይድሮሎጂ ጣቢያዎቹ ማሻሻያ እየተደረገላቸው በመሆኑ ምንም አይነት መረጃ ማቅረብ እንደማይቻል ኣሳውቃለች። ቢቢሲ እንደሚለው ግን ባንግላዴሽ ከብራሕማፑትራ ተፋሰስ የታችኛው ክፍል ላይ ያለች አገር ብትሆንም ከቻይና እስካሁን ድረስ መረጃ እየተቀበለች እንደሆነ ነው። ይህ የወንዝ መረጃ ጠብ በቻይናና በሕንድ መካከል በሂማላያ ድንበር ተነስቶ ለሁለት ወራት የቆየውን ፍጥጫ ተከትሎ የተከሰተ ነው። በቻይናና በሕንድ መካከል የነበረው ግጭት አሁንም እንደቀጠለ ነው። አለመተማምን የባንግላዴሽ የዉሃ ሀብቶች ሚኒስቴር አኒሱል ኢስላም ሞሃማድ አገራቸው ውሃን የተመለከተ መረጃዎችን ከቻይና እየተቀበለች እንደሆነ ለቢቢሲ ኣሳውቀዋል። ለሕንድ ግን ቻይና መረጃ የማካፈሉን ተግባር ድጋሚ ትቀጥላለች የሚለው ሃሳብ አጠራጣሪ ሆኖባታል። የቻይና ቃልአቀባይ የሆኑት ጌንግ ሽዋንግ ይህን በተመለከተ ተገቢውን የሃይድሮሎጂ መረጃ መስጠት መቀጠል መቻል ወይም አለመቻላቸው ከዚህ በላይ በተጠቀሰው የማሻሻያ ሥራ ሂደት ላይ ተወሰነ ነው። ሕንድና ከቻይና ጋር ስለ ብራሕማፑትራ ወንዝ የፍሰት መረጃዎችን ለመቀበል ስምምነት ውስጥ ላይ የደረሰችው ከብዙ ዓመታት ጥረት በኋላ ነው። በድርቅ ወቅቶች ቻይና የብራሕማፑትራን ውሃ ወደ ደረቅ ክልሎችዋ ታዛውራለች ብለው ስለሚጠረጥሩ ዴልሂ የወንዙን ውሃ ፍሰት መረጃ ዝናብ በሌለበት ወቅትም እንዲሰጣት ጥያቄ አቅርባለች። ወንዙ ወደ ባንግላዴሽ ከመውረዱ በፊት ወደ ሕንድ ይፈሳል። ቤይጂንግ በወንዙ ላይ ብዛት ያላቸውን የኤሌክትሪክ ኃይል የሚያመነጩ ግድቦችን ገንብታለች። በመቀጠልም ውሃውን እንደማይገድቡ ወይም አቅጣጫ እንደማያስቀይሩና ከወንዙ በታች በኩል ያሉ አገራትን ፍላጎቶች እንደማይጻረሩ ተናግረዋል። በቅርብ ዓመታት በተለይም በሰሜን ምሥራቅ ሕንድ ውስጥ ቻይና በአንድ ጊዜ ከፍተኛ መጠን ያለው ውሃ ትለቃለች የሚል ፍራቻ አለ። ወንዙ ሰፊ ቦታን ለሚሸፍንባቸው አካባቢዎች አንዱ በኣሳም ሲሆን የዲበሩጋር ነዋሪዎችም የብራሕማፑትራ ውሃ መጠን በከፍተኛ ደረጃ ሲጨምርና ሲቀንስ እንዳዩ መስክረዋል። ቢቢሲ ማስተባበያ
አውታር በአገር ውስጥ ሆነው የኢንተርኔት አቅርቦት ላላቸው ጥሩ የመገበያያ አማራጭ ነው የሚለው ብርሃኑ፤ ባለፉት ዓመታት በኢትዮጵያ ሙዚቃ ውስጥ ትልቅ ችግር ለነበረው የኮፒራይት መብት ጥሰትና የባለቤትነት ጥያቄ መፍትሔ ይሰጣል ይላል።
አውታር የቀደምት ሥራዎችም ሆነ የአዳዲስ ሥራዎች መረጃ በሚገባ ተካቶበት፣ ሙያተኛውም ገቢ የሚያገኝበት እንደሆነ ያብራራል። ለዛ የተሰኘውን የሙዚቃ ሽልማት ከዘጠኝ ዓመት በፊት የጀመረው ብርሀኑ፤ ያኔ ሽልማቱ ሲጀመር የሙዚቃ ኢንደስትሪው የተቀዛቀዘ እንደነበር ያስታውሳል። ካለው የኮፒራይት መብት ጥሰትና የገቢ ማነስ አንፃር እንዲህ ዓይነት የማበረታቻ ሽልማቶች ቢበራከቱ፤ ሙያተኛው ይነቃቃል በማለት ሽልማቱ እንደተጀመረ ይናገራል። በዚህ ዓመት የወጡትን ሥራዎች አወዳድረው የሚሸልሙት የሚቀጥለው ዓመት በጥቅምት ወር በስድስተኛው ቀን ሲሆን፤ ሽልማቱ ከሐምሌ ዓ ም እስከ ግንቦት ፣ ዓ ም ድረስ የወጡትን ያካትታል። የዩቲዩብ ዓለም ከሆፕ ኢንተርቴይመንትና ከምነው ሸዋ ዩቲዩብ ላይ የሚጫኑ ሙዚቃዎች በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚገኙ የኢትዮጵያ ሙዚቃ አድናቂዎችን በመድረስ ረገድ ፈጣን መሆናቸውን ባለሙያዎች ይናገራሉ። አንድ ሙዚቃ በዩቲዩብ ሲጫን፤ ዩቲዩብ ለጫነው አካል ክፍያ ይፈፅማል። ይህን የሚያደርገው የዩቲዩብ ቻናል በእነዚህ ገጾች ላይ ማስታወቂያ ለመልቀቅ ስለሚፈልግ ሲሆን፤ ለዚህም በማለት የሥራው አጋር ያደርጋቸዋል። ዩቲዩብ እነዚህን ቻናሎች አጋር ሲያደርግ ያላቸውን ተከታይ ሰብስክራይበር እንደሚመለከት በሥራው ላይ የተሰማሩ ባለሙያዎች ያስረዳሉ። በየትኛውም የዓለም ክፍል ያሉ የሙዚቃ አፍቃርያን ወደ ቻናሎቹ መጥተው ሙዚቃ ባደመጡና ባዩ ቁጥር ዩቲዮብ ማስታወቂያ የሚለቅ ሲሆን፤ ለድርጅቶቹ ደግሞ በስምምነታቸው መሰረት ክፍያ ይፈፅማል። በኢትዮጵያ ስማቸው ገኖ ከሚሰማና የተለያዩ አዳዲስ የሙዚቃ ሥራዎች በየጊዜው ከሚጫንባቸው ቻናሎች መካከል ሆፕ ኢንተርቴይመንት፣ አድማስ እና ምነው ሸዋ ይገኙበታል። አጭር የምስል መግለጫ የምነው ሸዋ ኢንተርቴይመንት አርማ ብርሃኑ እንደሚለው፤ በዩቲዩብ ከተለቀቁና በርካታ አድማጮች ካገኙ ነጠላ ዜማዎች መካከል የትግርኛ ሙዚቃዎችን የሚያክል የለም። የሆፕ ኢንተርቴይመንት ሥራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ዮሴፍ ኃይሉ በበኩላቸው በዩቲዩብ ቻናላቸው በዚህ ዓመት ከተጫኑ የሙዚቃ ቪዲዮዎች መካከል ከፍተኛ ተመልካች ያገኘው ጆሲ ዮሴፍ ገብሬ እና ኤርትራዊቷ ድምጻዊት ሚለን ኃይሉ በጋራ ያቀነቀኑት ሙዚቃ መሆኑን ይናገራሉ። ይህ የሙዚቃ ቪዲዮ ከ ሚሊየን በላይ ተመልካች እንዳለው ያስታወሱት ዋና ሥራ አስኪያጁ፤ የጌትሽ ማሞ ተቀበል ፣ የሰላማዊት ዮሐንስ ሰናይ እና የወንዲ ማክ አባ ዳማ የተሰኙት ሥራዎች በቅድመ ተከተል መቀመጣቸውን ይጠቅሳሉ። ሆፕ ኢንተርቴይመንት በዚህ ዓመት ብቻ ከ በላይ የሙዚቃ ቪዲዮዎችን በቻናሉ ላይ መጫኑን የተናገሩት አቶ ዮሴፍ፤ ሥራዎቹ በተለያዩ የኢትዮጵያ ቋንቋዎ፣ የታዋቂና ጀማሪም ድምፃውያን መሆናቸውን ተናግረዋል። በቻናላቸው ላይ በእይታ ብዛት ቀዳሚ የሆነው የእነ ጆሲ ሙዚቃ በአንድ ቀን ስድስት መቶ ሺህ ተመልካች ያገኘ መሆኑንም አክለው ተናግረዋል። ከፍተኛ እይታ ያላቸው በየትኛውም ወቅት ከፍተኛ ተከፋይ ናቸው የሚሉት አቶ ዮሴፍ፤ ሙዚቃዎ በእነርሱ ስም ዩቲዩብ ቻናላቸው ላይ ከተጫኑ ባለ ሙሉ መብት ስለሆኑ የመብት ጉዳዮችንም ለማስከበር ድርጅታቸው ሙሉ ኃላፊነቱን ወስዶ እንደሚሠራ ተናግረዋል። አዝማሪዎቻችን የሙዚቃ ሳይንቲስቶች ናቸው የምነው ሸዋ ኢንተርቴይመንት ኮንቴንት ማናጀር የሆኑት አቶ ነብዩ ይርጋ፤ በቀን ሁለት ሙዚቃ በቻናላቸው ላይ እንደሚጭኑ ይናገራሉ። በቻናላቸው በዚህ ዓመት በብዛት የታየው የድምጻዊት ራሄል ጌቱ ጥሎብኝ የተሰኘው ሙዚቃ መሆኑን በመጥቀስ እስከ ሚሊየን ድረስ እንደታየ ይናገራሉ። ከራሔል ጌቱ ሥራ በተጨማሪ፤ የአሕመድ ተሾመ ሚሊየን ፣ የጃምቦ ጆቴ ሚሊየን ፣ የአብነት አጎናፍር ሚሊየን ፣ የሚካኤል መላኩ ሚሊየን ፣ የቤቲ ጂ ሚሊየን ተመልካች ማግኘታቸውን ጠቅሰዋል። በዚህ ዓመት በምነው ሸዋ ኢንተርቴይመንት ከ ሙዚቃዎች በላይ መጫናቸውን የተናገሩት አቶ ነብዩ፤ ለክፍያ ሦስት ዓይነት መስፈርት እንደሚጠቀሙ ተናግረዋል። እነዚህም የሙዚቃ ሥራውን ሙሉ በሙሉ መግዛት፣ ቅድመ ክፍያ ከፍሎ መግዛት ወይንም ዩቲዩብ ቻናሉ ላይ ከተጫነ በኋላ የሚገኘውን ክፍያ ሀምሳ ሀምሳ መካፈል መሆናቸውን ይናገራሉ። ይህ ዓይነቱን የክፍያ ሥርዓትን ሆፕ ኢንተርቴይመንትም የሚጠቀም ሲሆን፤ ቅድመ ክፍያ የተከፈላቸው ሥራዎች፤ የቅድመ ክፍያ ገንዘቡ ከዩቲዩብ ከሚገኘው ክፍያ ከተካካሰ በኋላ ቀሪው ከዩቲዩብ ገቢው ሀምሳ ሀምሳ የሚካፈል መሆኑን አቶ ነብዩ ጨምረው አስረድተዋል። አጭር የምስል መግለጫ የሆፕ ኢንተርቴይመንት የዩቲዩብ ገጽ ከምነው ሸዋ ጋር ውለታ የገቡ ድምፃውያን ውለታቸው ለሁለት ዓመት እንደሚቆይ የሚናገሩት አቶ ነብዩ፤ ሙሉ በሙሉ ግዢ ካልፈፀሙ የቅድመ ክፍያ ወይንም በታየ ቁጥር እንዲከፈል ለተስማሙ ድምፃውያን በየስድስት ወሩ ከዩቲዩብ ያገኙትን ክፍያ እንደሚያካፍሉ አክለዋል። የዚህ ዓመት የሙዚቃ ድግሶች ምን መልክ ነበራቸው አንድ ሙዚቀኛ አልበሙን ለገበያ ካቀረበ በኋላ ተስፋ ያደርግ የነበረው ይላል የለዛ መሰናዶ አዘጋጁ ብርሃኑ፤ ተስፋ ያደርግ የነበረው የሰንዱቁ ሽያጭ ገቢን አይደለም። የአልበም ሽያጭ በቂ አይደለም የሚለው ብርሃኑ፤ የሙዚቃ ድግሶች ከአድማጭ ጋር ለመገናኘትም ሆነ ገቢ ለማግኘት ሁነኛ መላ ተደርገው ይወሰዳሉ ይላል። ነገር ግን ባለፉት ሦስት ዓመታት በአገሪቱ የተለያዩ ክፍሎች የፀጥታው ሁኔታ አስተማማኝ ስላልነበር ተዘዋውሮ ኮንሰርቶች ለማቅረብ አዳጋች ሆኗል ይላል። ይህንን ዓመት ጨምሮ በአዲስ አበባም በጣት የሚቆጠሩ ኮንሰርቶች ብቻ መዘጋጀታቸውን ይናገራል። በዚህ ዓመት ከገጠመው ፈተና አንዱ የቢራ አምራቾች የሙዚቃ አልበሞችን ስፖንሰር ለማድረግ አለመቻላቸው መሆኑን የሚያስታውሰው ብርሃኑ፤ የሙዚቃ ባለሙያው ሥራዎቹ በአድማጮችና በአድናቂዎች ቢሰማለትም ጥሩ ገቢ ስለማያገኝበት የሙዚቃ ድግሶችን በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች በማዘጋጀት ገቢውን ለማካካስ ያስብ ነበር ይላል። የሙዚቃ ድግሶች ላይ በጣም በጣም መቀዛቀዝ አለ ሲል ሁኔታውን የሚገልፀው ብርሃኑ፤ በዚህ ዓመት ክፍለ ሀገር የተለያዩ ቦታዎች ተዘዋውሮ ሥራዎቹን ያቀረበ ሙዚቀኛ ሮፍናን ብቻ መሆኑን ይናገራል። ሮፍናን ባህርዳር፣ ጎንደር፣ መቀሌ፣ አዳማና አዲስ አበባ ኮንሰርት ማቅረቡን በመግለፅም፤ አዲስ አበባ ውስጥ ከቴዲ አፍሮና የጎሳዬ ተስፋዬ ኮንሰርት እንዲሁም በዓላትን በማስታከክ ከሚቀርቡ አውደ ርዕዮች ውጪ ሌሎች ትልልቅ የሙዚቃ ድግሶች እንዳልነበሩ ያስረዳል። የኤ ፕላስ ኤቨንትና ፕሮሞሽን ሥራ አስኪያጅ አቶ ኤርሚያስ ጌታቸው፤ የሙዚቃ ድግሶችን በማዘጋጀት ከ ዓመት በላይ ሠርተዋል። ከ በላይ ትልልቅ የሙዚቃ ድግሶች ላይ ተሳትፈዋል። በዚህ ዓመት መግቢያ ላይ የተካሄደው የቴዲ አፍሮ ኮንሰርት ላይ ከ ሺህ በላይ ትኬት መሸጡን የተናገሩት አቶ ኤርሚያስ፤ የሮፍናንና የጎሳዬ ኮንሰርቶች የተካሄዱት ጊዮን በመሆኑ እስከ አስር ሺህ ሰዎች ታድመዋል ሲሉ ቦታው የሚይዘውን የሰው ብዛት ከግምት በማስገባት ያስረዳሉ። ተፈራ ነጋሽ፡ በነገራችን ላይ ሙዚቃ አልተውኩም የጆርካ ኤቨንትስ ኤንድ ፕሮሞሽንስ ሥራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ አጋ አባተ፤ ከ ጀምሮ በርካታ ኮንሰርቶችን በመሥራት ስማቸውን የተከሉ ናቸው። ፌስቲቫሎችን፣ የስፖርታዊ ዝግጅቶችንና የአልበም ምርቃቶችን ጨምሮ ባለፉት አምስት ዓመታት ከ በላይ ኮንሰርቶችን ያዘጋጀው ጆርካ ኤቨንትስ ኢትዮጵያዊ ኮንሰርት፣ አዲስ ኮንሰርት ፣ ሄሎ መቀሌና ጊዜ ኮንሰርትንም አዘጋጅቷል። አቶ አጋ የድምፃውያንና ሌሎች የሙዚቃ ባለሙያዎች ክፍያ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየናረ መምጣቱን በማስረዳት፤ በዚህ ዓመት ከሥራው ላለመውጣት ብቻ ከሙዚቃ ድግሶች ይልቅ ባዛር ላይ ማተኮራቸውን ይናገራሉ። ባዛሮቹ ከ እስከ ቀን የሚቆዩ መሆናቸውን በመጥቀስም እስካሁን ድረስ ሦስት ባዛሮች ላይ መሳተፋቸውን ገልጸዋል። ለአንድ ድምፃዊ ከአንድ ሚሊየን ብር በላይ የሚከፈልበት ጊዜ ላይ ነው ያለነው የሚሉት የጆርካ ኤቨንትስ ሥራ አስኪያጅ ለመድረክ እስከ ሺህ ብር እንደሚከፈል፣ ለማስታወቂያም ከፍተኛ ወጪ እንደሚያወጡ ይናገራሉ። የኮንሰርት መግቢያ ዋጋ ዛሬም ድረስ ባለበት እንዳለ በማስረዳት፤ ከአምስት ዓመት በፊት አንድ ዶላር ብር እያለ በ ብር ይገባ የነበረ የሙዚቃ ድግስ ዛሬም በዛው ዋጋ እንደሚታይ በመጥቀስ የኮንሰርት ሥራ ፈተናን ያሳያሉ። በርካታ ሥራዎች ሠርተናል ነገር ግን ከትርፉ ኪሳራው ያመዝናል የሚሉት የጆርካ ኤቨንትስ ሥራ አስኪያጅ አቶ አጋ፤ በዚያ ምክንያት ከኮንሰርቶች ይልቅ ወደ ባዛሮችና ፌስቲቫሎች ላይ ማተኮራቸውን ተናግረዋል። አቶ አጋ አክለውም በዚህ ዓመት የሙዚቃ ሥራዎች ዋነኛ አጋር የነበሩት የቢራ አምራቾች የሙዚቃ ድግሶችን መደገፍ ላይ በመቀዛቀዛቸው ሥራው አብሮ መፋዘዙን ይጠቅሳሉ። ከቢራ አምራቾች ውጪ የድርጅቱን ስምና ምርት ለማስተዋወቅ ደፍሮ ወደ ኮንሰርት አዘጋጆች የሚመጣ እንደሌለ የሚናገሩት አቶ አጋ፤ እነርሱም ሲሄዱ ተቀባይነት እንደማያገኙ ያስረዳሉ። በዚህ ዓመት ከአገሪቱ ጠቅላላ ሁኔታ አንፃር የተቀዛቀዘ ቢሆንም የተወሰኑ የሙዚቃ ድግሶች መደረጋቸውን ይናገራሉ። የኤ ፕላሱ አቶ ኤርሚያስ፤ የቢራ ፋብሪካዎች ማስታወቂያቸውን በቴሌቪዥንና በሬዲዮ የሚያቀርቡበት ሰዓት ላይ ገደብ ቢደረግም የሙዚቃ ድግሶችን ከመደገፍ ወደኋላ ያሉ አይመስለኝም ይላሉ። ከዚያ ይልቅ በተደጋጋሚ የነበሩ መሰረዞች በዚህ ዓመት የሙዚቃ ድግሶች ለመቀዛቀዛቸው አንዱ ሰበብ ሊሆን እንደሚችል ይገምታሉ። የአዳዲስ አልበሞች አለመውጣት ለመቀዛቀዙ ሌላ ምክንያት መሆኑን ይናገራሉ። አንድ ኮንሰርት ለማዘጋጀት ከሚያስፈልገው የሥራ ፈቃድ ባሻገር ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለጸጥታና ደህንነት ሲባል መገኘት ያለበትን ፈቃድ ለማስጨረስ ያለው ውጣ ውረድ ራሱን የቻለ ራስ ምታት እንደሆነ የሚናገሩት የጆርካ ኤቨንትስ ሥራ አስኪያጅ፤ በዚህም የተነሳ በርካታ ሥራዎች ይሰረዛሉ ይላሉ። የከተማ አስተዳደሩ ለኮንሰርቶች ፈቃድ የሚሰጠው የሙዚቃ ድግሶች መተዋወቅ ከጀመሩ በኋላ ነው የሚሉት ኃላፊው፤ ቀኑ እየተቃረበ ሲመጣ የሚኖረው የፀጥታና የደህንነት ጉዳይ ተገምግሞ ስጋት ይኖራል ከተባለ እንደማይፈቀድ ያብራራሉ። ይህ ደግሞ ለተለያዩ ዝግጅቶች ቀድመው የወጡ ወጪዎች ላይ ኪሳራ እንደሚያስከትል አፅንኦት ይሰጡታል። ኮንሰርቶች ሲሰረዙ ለማስታወቂያ የወጡ ከፍተኛ ወጪዎች መና እንደሚቀሩ የሚያስረዱት አቶ ኤርሚያስ፤ ከተሰረዘ በኋላ ራሱ መሰረዙን ለታዳሚያን ለመንገር ወጪ እንደሚወጣም ያብራራሉ። የኮንሰርት አዘጋጆች በተደጋጋሚ ስለተሰረዘባቸው ዘንድሮ እጃቸውን ሰብሰብ እንዳደረጉ በማስረዳት፤ የቢራ አምራቾችም እንደ ከዚህ ቀደሙ የሚሰጡትን ገንዘብ እንደቀነሱ ይናገራሉ። ለዚህ ምክንያቱ ደግሞ ደጋፊ አካላት በመገናኛ ብዙኀን ስማቸው አለመጠራቱና ቢልቦርዶች እንደ ከዚህ ቀደሙ አለመሰቀላቸው ነው። የሙዚቃ እቃዎች ኪራይ፣ የቦታ ኪራይ እና የባለሙያዎች ዋጋ ውድ መሆን ከእነዚህ ጉዳዮች ጋር ሲደራረብ ኮንሰርቶች በመግቢያ ትኬት ሽያጭ ብቻ አትራፊ እንዳልሆኑ ያስረዳሉ። የኤ ፕላሱ አቶ ኤርሚያስ ዓ ም ተስፋ ይዞ ይመጣል ይላሉ። ሮፍናን ሌሎች ድምፃውያን ያልደፈሩትን የክፍለ አገር የሙዚቃ ድግስ ጉዞ ውጤታማ ሆኖ ማጠናቀቁ እንዲሁም አዳዲስ አልበሞች መውጣታቸው ዋና ዋና ከተሞች ላይ የሙዚቃ ድግስ ለማዘጋጀት ተስፋ እንደሚሰጡ ይጠቅሳሉ። በአዲስ አበባም ቢሆን የተለያዩ ድምፃውያን አድናቂዎች በጉጉት የሚጠብቋቸው ኮንሰርቶች ሊዘጋጁ እንደሚችሉ ያላቸውን ተስፋ ይናገራሉ። በዚህ ዓመት ከፍተኛ የአማራ ክልል ባለስልጣናት እና ወታደራዊ ሹማምንት ላይ በተፈፀመ ግድያ ምክንያት ታንዛኒያዊው ዳይመንድ ይገኝበታል ተብሎ ቀጠሮ የተያዘለት የሙዚቃ ድግስ ወደሌላ ጊዜ ተዛውሯል ሲሉ ሳይካሄድ ስለቀረው ኮንሰርት አቶ አጋም ሆኑ አቶ ኤርሚያስ ያስረዳሉ። ተያያዥ ርዕሶች
መሬት መንሸራተትና ጎርፍ በደቡብ ኢትዮጵያ ጥፋት አደረሰ
ሜይ ማጋሪያ ምረጥ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ ዞን መስቃን ወረዳና በአጎራባች ቀበሌዎች ባለፈው ሳምንት የጣለ ከባድ ዝናብን ተከትሎ ባጋጠመ የመሬት መንሸራተት ቢያንስ ሰዎች መሞታቸው ተዘገበ። መጀመሪያ ጎርፉን ሰበብ አድርጎ መሬቱ መሰንጠቅ ጀመረ፣ ጎርፉ እና ዝናቡ ካቆመ አንድ ሳምንት ቢሆነውም መሬቱ መሰንጠቁን አላቆመም። መሬቱም ወደታች እየሰመጠ ነው። አንድ ሁለት ቤቶችም ሰምጠዋል ይህን ምስክርነት የሰጡን ከአዲስ አበባ ኪሎ ሜትር ላይ በምትገኘው፣ መናጋሻዋን ቡታጂራ ባደረገችው የመስቃን ወረዳ ውስጥ የሚኖሩት አቶ ሙኸዲን መሃመድ ናቸው፡፡ በከባድ ዝናብ እና ጎርፍ የታጀበውን ያለፈውን ሳምንት ተፈጥሯዊ አደጋ የሚመስል ክስተት በዚህ አካባቢ መደጋገሙን ነዋሪዎች ይናገራሉ። ቦታው ዛቢዳር ተብሎ ከሚጠራው ተራራ አቅራቢያ፣ በኢትዮጵያ የስምጥ ሸለቆ ምዕራባዊ መንደርደሪ ላይ መገኘቱ በተደጋጋሚ ለደረሰው መሬት መንሸራተትና መሰንጠቅ ተጠቂ ሳያደርገው እንዳልቀረ የከርሰ ምድር አጥኚው አቶ ሚፍታ ሸምሱ ያምናሉ። ይህ ሰማይ ግም ባለ ቁጥር መሬቱ እየራደ የሚከተለው የመሬት መንሸራተት እና መሰንጠቅ የአሁኑ ለሦስተኛ ጊዜ መሆኑንም ያስታውሳሉ፡፡ ባሳለፍነው ሳምንት ላይ ይሄ ስፍራ የመሬት መሰንጠቅ ክስተትን አስተናግዷል። ክስተቱ የሰው ነፍስ ቀጥፏል፣ ንብረት አውድሟል። የመስቃን ወረዳ የኮሚኒኬሽን ቢሮ ጋዜጠኛ አቶ ሬድዋን ከድር፤ ከሰሞኑ የገጠመውን የጉዳቱን ዝርዝር ሲያስቀምጡ ቀበሌዎች ሰለባ እንደሆኑ ይናገራሉ። አጭር የምስል መግለጫ የተሰነጠቀው ዋና መንገድ በዘቢዳር ተራራ አካባቢ በተፈጠረ የመሬት መንሸራተት የአንድ ቤተሰብ አባላት የሆኑ ሰዎች የገቡበት ጠፍቷል። የተወሰኑት በቁፋሮ ተገኝተዋል። ቡታጂራ ከተማ በሚገኝ ወንዝ አካባቢ ህጻናትን ከደራሽ ውሃ ለማዳን የገባ አንድ ሰውም ህይወቱን አጥቷል ብለዋል በአጠቃላይ ከ ያላነሱ ሰዎች ህይወታቸው መጥፋቱንም ጠቁመዋል። ጎርፍና የመሬት መንሸራተት ያስከተሉት ጥፋት ይሄ ብቻ አይደለም። አቶ ሬድዋን ጨማረው እንደነገሩን በሰብል የተሸፈኑ መሬቶችና የመኖሪያ ቤቶች ወድመዋል እንዲሁም ነዋሪዎች ተፈናቅለዋል። ተፈጥሯዊው አደጋ ከአዲስ አበባ ተነስቶ አርባምንጭ የሚያደርሰውን አውራ መንገድ ለሁለት መሰንጠቁን፣ በዚህም ወረዳውን አልፈው የሚሄዱ ተጓዦች በሌላ ቅያሪ መንገድ እንዲያልፉ እየተደረገ መሆኑን ቢቢሲ ከነዋሪዎች ሰምቷል። የመስቃን ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሰለሞን አየለ ደግሞ ለቢቢሲእንደተናገሩት ሰወዎች በጎርፍ ምክንያት የተፈናቀሉ ሲሆን፤ በአሁኑ ሰዓት ወደ መኖሪያቸው እንዲመለሱ ጥረት እየተደረገ እንደሆነ ተናግረዋል። በተጨማሪም በመሬት መሰንጠቅ አደጋ የተፈናቀሉ ሰዎችአሁንም ስጋት ላይ ስለመሆናቸው ጠቁመው፤ በአጠቃላይ የደረሰው የንብረት ውድመት ግምት ሚሊዮን ብር ይደርሳል ብለዋል። የተወሰኑ በአደጋው የተፈናቀሉ አባወራዎችን እና ቤተሰቦቻቸውን የወረዳው አስተዳደር እና የቀይ መስቀል ማህበር ባዘጋጇቸው የድንኳን መጠለያ ውስጥ ለጊዜው እንዲርፉ እንደተደረገ የሚያነሱት አቶ ሬድዋን፤ የሚያዛልቀው መፍትሄ ግን በዚያ ስፍራ የሚኖሩ ሰዎችን ወደ ሌላ ቦታ ማስፈር እንደሆነ ያስረዳሉ። ከጎርፉ ጋር ተያይዞ ተጨማሪ የመሬት መንሸራተት ሊከሰት ይችላሉ የሚል ከፍተኛ ስጋት ያላቸው አቶ ሚፍታ ሸምሱ መወሰድ ባለበት የቅድመ ጥንቃቄ እርምጃም ይስማማሉ። በስፍራው የሚኖሩ ሰዎች ካለቅድመ ሁኔታ ከአከባቢው እንዲለቁ መደረግ አለበት። ነዋሪዎች በተሻለ ቦታ እንዲጠለሉ ተደርጎ ዘላቂ መላ ማበጀት ያስፈልጋል ሲሉ የሚመለከታቸው የክልልና የፌዴራል ተቋማት አደጋውን ለመቆጣጠር የበኩላቸውን እንዲያደርጉ ጠይቀዋል። ሆኖም ግን በአካባቢው የሚኖሩ አርሶ አደሮች ቦታቸውን ለቀው ወደ ሌላ ቦታ የመስፈር ፍላጎት እንሌላቸው ተጠቁሟል። ተያያዥ ርዕሶች
የቱሪስት ማግኔት የሆነችው ቬኒስ ከተማን ጎርፍ እያስጨነቃት ነው
ኖቬምበር ማጋሪያ ምረጥ በዓለም አቀፍ ደረጃ የቱሪስት ማግኔት አላት የምትባለው የጣልያኗ ቬኒስ ከተማ በጎርፍ እየተፈተነች ነው። ጎርፉ ቬኒስን በሚሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር አሳጥቷታል ተብሏል። በጎርፉ ምክንያት የውሃ መተላለፊያ የሆነው የከተማዋ ዋና አደባባይ ሴንት ማርክ ፣ትምህርት ቤቶችና ንግድ ቤቶች ተዘግተዋል። የጣልያን መንግስሥትም በዩኔስኮ ድረ ገፅ ላይ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጁን አስታውቋል። ጎርፍ ባጠቃቸው የምሥራቅ አፍሪካ አገራት ተጨማሪ ዝናብ ሊጥል ይችላል ተባለ ለውሃ እና ለስነ ህንፃዎቿ ጥበብ ቱሪስቶች የሚተሙላት ቬኒስን እያስጨነቀ ያለው ጎርፍ እርዝመት ማክሰኞ እለት ሴ ሜ ደርሶ ነበር ተብሏል። ቤታቸው በጎርፍ የተጎዳባቸው የቬኒስ ኗሪዎች እስከ አምስት ሺህ ዩሮ ሲያገኙ ንግድ ቤቶች ደግሞ ሺህ ዩሮ ድረስ ካሳ ይሰጣቸዋል ተብሏል። ከመቶ በላይ ከሚሆኑ ደሴቶች የተሰራችው ቬኒስ በየአመቱ በጎርፍ የምትጠቃ ሲሆን የአሁን እንደ አውሮፓውያኑ በ ተከስቶ ከነበረውና አስከፊ ከተባለው ጎርፍም የባሰ ነው ተብሏል። የጣልያን መንግሥት ለቬኒስ ሚሊዮን ዩሮ ድጋፍ እንደሚሰጥ ቃል ገብቷል።
ኬንያዊቷ ታዳጊ አንድን ግለሰብ ከጎርፍ ለማዳን ስትጥር ህይወቷ አለፈ
ታህሳስ ይህንን ለማጋራት በ ዋትስአፕ አንዲት ኬንያዊት ታዳጊ አንድን ግለሰብ ከጎርፍ ለማዳን ስትጥር ሰምጣ ህይወቷ አልፏል። ከመዲናዋ ናይሮቢ ወጣ ብሎ በሚገኘው ካንዲሲ የሚባል ወንዝ ገብታ ነው ህይወቷ ያለፈው፤ የአስራ ዘጠኝ ዓመቷ አን ዱኩ። አን እየተገነባ በነበረ ድልድይ ስር አድኑኝ እያለ በመማፀን ላይ የነበረ ግለሰብን ጩኸት ሰምታ ነው ለእርዳታው የመጣችው። ግለሰቡ ህይወቱ ቢተርፍም እሷ ግን ወንዝ ውስጥ በመውደቋ ህይወቷ አልፏል። እናቷ ኤልዛቤት ሙቱኩ ለቢቢሲ ጋዜጠኛ እንደተናገሩት ወንዝ ውስጥ ስትታገል አየሁዋት፤ ህይወቷንም ለማዳን ሞክሬያለሁ። አና አና ብዬ እየጠራሁዋት ነበር። እሷንም ለመጎተት እንዲያስችለኝ እንጨት መወርወር አስቤ ነበር። ነገር ግን የወንዙ ማዕበል በጣም ከፍተኛ ስለነበር፤ ልጄን ጥርግ አድርጎ ወሰዳት በማለት እንባ እየተናነቃቸው ተናግረዋል። በዚህ ሳምንት ከሰኞ ጀምሮ በምሥራቅ አፍሪካ በከፍተኛ ሁኔታ ሲጥል የነበረውን ዝናብ ተከትሎ ነው ወንዙ ከመጠን በላይ የሞላው። ነገር ግን ነዋሪዎች እንደሚሉት ባለፉት ሁለት ዓመታት ሰባት ሰዎች በወንዙ ተወስደው ለሞት ተዳርገዋል። በቴክኖሎጂ ኢ ፍትሐዊነትን የምትታገለው ኢትዮጵያዊት ወንዙን ለመሻገር ያገለግል የነበረው አሮጌ ድልድይ ከሁለት ዓመት በፊት የፈረሰ ሲሆን አዲሱ ድልድይ ባለመጠናቀቁ ነዋሪዎች ድንጋይ ከላይ በመደርድር እየተሻገሩ መሆኑ ተገልጿል። የሟቿ ታላቅ እህት ማርያም ዜኔት ለቢቢሲ እንደገለፀችው መንደራቸውን ከዋናው ገበያ ጋር የሚያገናኘው ድልድይን ማጠናቀቅ የአካባቢው ባለስልጣናት ኃላፊነት ቢሆንም፤ ይህንን ባለማድረጋቸውም ጥፋተኞች ናቸው ብላለች። ባለፉት ሁለት ዓመታት ብዙ ሰዎች ድልድዩን ሊያቋርጡ በሚሞክሩበት ወቅት ህይወታቸው አልፏል። ባለስልጣናቱ መጥተው ሃዘናቸውን ከመግለፅ ውጪ ምንም ያደረጉልን ነገር የለም። ዛሬ እህቴ ሞተች ነገስ ቀጣዩ ማነው ድልድዩ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት ሲሄዱም የሚመላለሱበት ነው። አዲስ መገንባት ካልቻሉ የድሮውን ለምን አፈረሱት በማለትም ትጠይቃለች። በልጃቸው ሞት ልባቸው የተሰበረው እናት በጣም አዝኛለሁ። የወደፊቱ መሪ፤ ወይም መምህር ትሆን ነበር። በዚህ ድልድይ ምክንያት የልጄን ሕይወት ማጣቴ ህመሜን አክብዶታል ብለዋል። ቢቢሲ ማስተባበያ
ታይላንዳዊው የ ዓመቱ ቦክሰኛ አኑቻ ኮቻና በቦክስ ውድድር ሳቢያ ሕይወቱ አለፈ
ኅዳር ታዳጊው የቦክስ ውድድር የጀመረው በ ዓመት ዕድሜው ነበር የ ዓመቱ ታዳጊ የቦክስ ውድድር ሳቢያ ሕይወቱ ማለፉን ተከትሎ ታይላንድ የህፃናት የቦክስ ውድድርን እንድታግድ የነበሩ ጥያቄዎች በርትተው ቀጥለዋል። አኑቻ ኮቻና በአንድ ግብረ ሰናይ ድርጅት ባዘጋጀው ውድድር ላይ ባጋጠመው የጭንቅላት ውስጣዊ ደም መፍሰስ ለሁለት ቀናት ህክምና ሲከታተል ቆይቶ ሕይወቱ አልፏል። የታቃራኒ ቡድን አባላት እንደገለፁት ታዳጊዎቹ ራሳቸውን ከአደጋ የሚከላከሉበት ትጥቅ አላጠለቁም ነበር። በዚህም ሳቢያ በውድድሩ ወቅት ታዳጊው ከመውደቁ በፊት ጭንቅላቱ ላይ መመታቱ ታውቋል። ታዳጊው ከ ዓመት ዕድሜው አንስቶ ቤተሰቦቹን ለመርዳት ግጥሚያዎችን አድርጓል። በታይላንድ ሟይ ተብሎ የሚጠራው የታዮች የቦክስ ውድድር በአገሪቱ በስፋት የሚታወቅ ነው። በሺዎች የሚቆጠሩ ተጋጣሚዎችና ቤተሰቦቻቸው ውድድሩን ገንዘብ የማግኛ መንገድ አድርገውታል። ይሁን እንጂ ይህንን ስፖርት ለማካሄድ ህጉ ክፍተት እንዳለበት ተደጋግሞ ይነሳል። በተቃራኒው አንዳንድ ሰዎች ህፃናቱን ከአደጋ ለመጠበቅ ሲባል ውድድሩን ለማገድ የሚደረገውን ጥረት አስፈላጊ አይደለም ሲሉ ይቃወማሉ፤ ምክንያታቸው ደግሞ በአገሪቱ ያለው ባህላዊ የቦክስ ውድድር አካል መሆን አለባቸው የሚል ነው። ይሁን እንጂ የጉዳዩን አደገኝነት ያሳሰበው የታይ ምክርቤትም ከ ዓመት በታች የቦክስ ውድድርን ለማገድ ህጉን እየመረመሩ ይገኛሉ። በታዳጊው አኑቻ ህልፈት በርካታ የታይ ነዋሪዎች አዝነዋል፤ በመካከለኛው ሳሙት ፕራካን ግዛት የተደረገው ውድድር ላይ የተነሳውን የቦክሰኛውን ምስል በመጋራት ሀዘናቸውን እየገለፁ ነው። በርካታ ቁጥር ያላቸው የቦክስ ከዋክብትም ሃዘናቸውን ገልፀዋል። ሃገሬን ሳላስብ የዋልኩበት፤ ያደርኩበት ቀን የለም ብርቱካን ሚደቅሳ የታይላንድ የብሔራዊ ስፖርት ባለስልጣን ባለፈው ዓመት ባወጣው መረጃ በአገሪቱ ዕድሜያቸው ከ ዓመት በታች የሆኑ ከ ሺህ በላይ ቦክሰኞች ተመዝግበዋል። ስፖርትን የተመለከተው የብሔራዊ ህግ አውጭ ጉባዔ ምክትል ኃላፊ ገን አዱሌኣድጂ ኢንታፖግ በበኩላቸው ዕድሜያቸው ከ ያሉ ህፃን ቦክሰኞች መመዝገብ፤ ከቤተሰቦቻቸው ፈቃድ ማግኘት እንዲሁም ራሳቸውን ከአደጋ የሚጠብቁበት ልብስ መልበስ አለባቸው ሲሉ ተናግረዋል። በዚህ ጉዳይ ላይ ዘመቻ የሚያካሄዱ ቡድኖች ለውድድሩ አነስተኛው ዕድሜ ዓመት መሆን አለበት ሲሉ ጠይቀዋል። ከአኑቻ ሞት ቀደም ብሎ ጣላኒያዊው ቦክሰኛ ክርስቲያን ዳጊኦ በውድድር ላይ ሕይወቱ ማለፉ የሚታወስ ነው። ከዚህ ዜና በተጨማሪ
መንፈስ ቅዱስ ከቅጣት የጋረደው አሽከርካሪ
ሜይ ማጋሪያ ምረጥ ጀርመን ውስጥ ነው። አንድ ሾፌር መንዳት ከሚገባው ፍጥነት በላይ እየከነፈ ሲጓዝ፤ በትራፊክ ፖሊስ ካሜራ እይታ ውስጥ ይገባል። ጀርመን ውስጥ ከፍጥነት ወሰን በላይ ማሽከርከር ዩሮ ብር ገደማ ያስቀጣል። ትራፊክ ፖሊሶችም ግለሰቡን ለመቅጣት የደህንነት ካሜራውን ሲመለከቱ ያልጠበቁት ገጠማቸው። የግለሰቡ መኪና ፊት ለፊት አንዲት ነጭ እርግብ ትበራለች። እርግቧ ትበር የነበረው በሾፌሩ መቀመጫ ትክክል ስለነበረ የግለሰቡን ማንነት መለየት አልተቻለም። ፖሊሶቹም እርግቧ የመንፈስ ቅዱስ አምሳያ ናት ብለው፤ ግለሰቡን ላለመቅጣት ወሰኑ። ፖሊሶቹ እርግብ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ መንፈስ ቅዱስን መወከሏን አጣቅሰው፤ ለግለሰቡ ከለላ ስለሰጠችው ከቅጣት ተርፏል ብለዋል።
የግንቦት ታሪካዊነት አጠያያቂ አይደለም ፕሮፌሰር ገብሩ ታረቀ
ሜይ ማጋሪያ ምረጥ ግንቦት እንደዘንድሮ አከራካሪ የሆነበት ጊዜ ያለ አይመስልም። በዓሉ አምባገነኑ የደርግ ሥርዓት የተወገደበትና ኢትዮጵያ ወደዲሞክራሲ ሥርዓት የተሸጋገረችበት ዕለት በመሆኑ በድምቀት መከበሩ መቀጠል አለበት የሚሉት እንዳሉ ሁሉ፤ ይህ ቀን ወንድም ወንድሙን ገድሎ ሥልጣን የያዘበት ዕለት ነው፤ ወደሥልጣን የመጣውም ሌላ አምባገነን ሆኖ እንዴት ክብረ በዓል ይሆናል የሚሉም አሉ። በሰሜን አሜሪካ የትግራይ ተወላጆች ማኅበር ፕሬዝዳንት አቶ አሉላ ሰለሞን በዓሉን ማክበር አለብን ከሚሉት ወገን ናቸው። ምክንያታቸውን ሲጠቅሱም የነበረው የእርስ በእርስ ጦርነት አብቅቶ የኢትዮጵያ ሕዝብ ወደ ሰላም የተሻጋገረበት ነው ይላሉ። አክለውም ኢትዮጵያ እንደ አገር ወደአዲስ ፖለቲካዊ ምዕራፍ የተሸጋገረችበት ነው የሚለውን አብዛኛው ሰው ይስማማበታል። ተከትሎ በመጣው ፖለቲካዊ ሥርዓት ስምምነት ባይኖርም መሠረታዊ በሆኑ እውነታዎች መለያየት የሚቻል አይመስለኝም በማለት ያለው የፖለቲካ ልዩነት እንደተጠበቀ ሆኖ፤ ቀኑ መከበር አለበት ይላሉ። አቶ አሉላ በዓሉ መከበር የለበትም የሚሉ ወገኖችንም ሀሳብ አከብራለሁ ያሉ ሲሆን፤ ሁሉም በግንቦት ድል ደስተኛ እንደማይሆን አንደሚረዱም ሳይጠቅሱ አላለፉም። በአገሪቱ የፕሬስ ነፃነት ባልነበረበት ወቅት በግንቦት የተገኘው ድል ለፕሬሱ ነፃነት የሰጠ ዕለት መሆኑንም ይጠቅሳሉ። በሂደት ፕሬሱም ሆነ ዲሞክራሲው ማደግ በነበረበት መጠን አላደገም የሚለው ሌላ መነጋገሪያ ርዕስ ሆኖ የሚቆይ ነው የሚሉት አቶ አሉላ፤ በታሪክ ግን ነፃ ፕሬስ በኢትዮጵያ ውስጥ የመጣበት መሆኑ እንደማይካድ ይጠቅሳሉ። ጋዜጠኛና በፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ የሚጽፉት አቶ ደጀኔ ተሰማ በበኩላቸው፤ ግንቦት አምባገነን መንግሥት ተገርስሶ ሌላ አምባገነን መንግሥት ወደሥልጣን የመጣበት ቀን ቢሆንም በዚህኛው መንግሥት ለውጦች እንደመጡ እረዳለሁ ይላሉ። ደርግ መስከረም ብሎ ሲያከብረው በነበረው በዓል እና ኢህአዴግ ግንቦት ብሎ በሚያከብረው በዓል መካከል ምንም አይነት ልዩነት አይታየኝም የሚሉት አቶ ደጀኔ፤ ደርግ መሬት ላረሹ የሚለው የሕዝብ ጥያቄ መመለስ መቻሉን አስታውሰው፤ የግንቦት ድልን ተከትሎ የመጣ ለውጥ ቢኖርም የለውጡ ተጠቃሚ የሆኑት ድሉ የኛ ነው የሚሉት ወገኖች ናቸው ይላሉ። የቀድሞው ግንቦት አርበኞች ግንባር አመራር የነበሩት አቶ ኤፍሬም ማዴቦ ደግሞ በዓል የሚከበረው ለሕዝብ ነው፤ ሕዝብ ካላከበረው አልተቀበለውም ማለት ነው ስለዚህ መከበር የለበትም ባይ ናቸው። ትንሽ ልጅ እያለሁ መስከረም ይከበር ነበር የሚሉት አቶ ኤፍሬም፤ ይህ የፊውዳሉ ሥርዓት የተገረሰሰበት በዓል በመሆኑ ትልቅ በዓል ነበር ይላሉ። ሕወሐት ሥልጣን ሲይዝ ይህንን በዓል ማክበር አቁመን እነሱ የገቡበትን ቀን ማክበር ጀመርን በማለት፤ ኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት ያለፈችበትን ሁኔታ ማሳያ በመሆኑ የሚፈጥርብኝ ስሜት ጥሩ አይደለም ይላሉ። አቶ ኤፍሬም ኢትዮጵያ አሁን ካለችበት የለውጥ ሂደት ራሳቸውን አግልለው አሁንም የሚያስቡት ኢትዮጵያን ወደኋላ መመለስ ነው ይላሉ። አክለውም እነሱ የቆሙለትን ዓላማና አሁንም የሚታገሉለትን ዓላማ ስመለከት መከበር የለበትም እላለሁ በማለትም ሀሳባቸውን ይቋጫሉ። ፕሮፌሰር ገብሩ ታረቀ በበኩላቸው የ ዓመቱ ጦርነት የአንድ እናት ልጆች የተጋደሉበት፤ የተዋደቁበት ጦርነት ነው ይላሉ። በዓሉ መድፍ እየተተኮሰ መከበሩ ከመጀመሪያውም ደስ አላለኝም በማለት፤ ወደፊትም መከበር ካለበት እስከዛሬ ይከበር እንደነበረው መሆን የለበትም ሲሉ ምክራቸውን ይሰጣሉ። ፕሮፌሰር ገብሩ ግንቦት እንደ በዓል ባይቆጠርም ታሪካዊነቱ አጠያያቂ አይደለም ይላሉ። አቶ ደጀኔ በበኩላቸው ግንቦት ልንጠየፈውም ሆነ ልናወድሰው የሚገባ ቀን አይደለም የሚል ሃሳብ ይሰነዝራሉ። ተያያዥ ርዕሶች
አምስቱ ተስፋ የተጣለባቸው አፍሪካውያን ሙዚቀኞች
ታህሳስ ይህንን ለማጋራት በ ዋትስአፕ ናይጀሪያዊው ዊዝ ኪድ ዴቪዶ፣ ዊዝኪድ፣ በርና ቦይ ከአፍሪካ ማህፀን የተገኙ ሙዚቀኞች ሲሆኑ፤ ድንበር፣ ቋንቋ ፣ ባህል ሳይገድባቸው በአለም አቀፉ የሙዚቃ መድረክም ስመ ጥር ሊሆኑ ችለዋል። ለዚያም ነው ምዕራባውያኖቹ መዚቀኞችም ሆነ ፕሮዲውሰሮች አይናቸውን ወደ አፍሪካ ሙዚቀኞች እያማተሩ ያሉት። በዚህ አመት በወጣው ላየን ኪንግ የካርቱን ፊልም ተነሳስታ ቢዮንሴ አልበሟን ስትሰራም ታዋቂ አፍሪካዊ ሙዚቀኞችን አካታለች። ሚስተር ኢዚና በርና ቦይም በሙዚቃው ዓለም ከፍተኛ ስፍራ በተቸረው በአመታዊው የኮቼላ ሙዚቃ ፌስቲቫል ተሳትፈዋል። ሊጠናቀቅ አንድ ወር በቀረው የአውሮፓውያኑ ዓመት የአድማጮችን ቀልብ መያዝ ከቻሉት ጥቂት አፍሪካውያን ሙዚቀኞች አምስቱ እነሆ፡ ሺ ባህ ካሩንጊ ኡጋንዳ ሺባህ በእናት ሃገሯ ኡጋንዳ በሙዚቃው ዘርፍ ተደማጭነት ያገኘችው ሺባህ በአሁኑ ወቅት ደግሞ ሃገሯን አልፎ ሙዚቃዋ ወደሌሎች ሃገራት ደርሷል። በሚስረቀረቅ ድምጿ የብዙዎችን ቀልብ መሳብ የቻለችው ሺባህ ከተለያዩ አርቲስቶችም ጋር በመጣመር ትስራለች። ሙዚቃውን ከዳንስና ከፋሽን ጋር በማጣመር ለራሷም ሆነ ለሃገሯ ስም ማትረፍ ችላለች። በመድረክም ላይ ባላት ድንቅ ችሎታ እንዲሁ ታዳሚውን ወደ ሙዚቃዋ ጠልቃ የምታስገባበበት መንገድ ብዙዎችን እንዲደመሙ አድርጓቸዋል። የሶስተኛ ወገን የማስታወቂያ ይዘት ማስጠንቀቂያ ጆቦይ ናይጀሪያ ጆቦይ ናይጀሪያዊው ጆቦይ ቤቢ በሚለው የፍቅር ዘፈኑ የብዙ አድማጮችን ጆሮ ማግኘት የቻለ ሲሆን፤ ይህ ሙዚቃውም በዩቲዩብ ላይ አስራ አምስት ሚሊዮን ተመልካቾችን ማግኘት ችሏል። በስሜት በተሞላ አዘፋፈኑና በሚንቆረቆረው ድምፁ የተለያዩ የሙዚቃ ስልቶችን ማጣመር የቻለ አርቲስት ነው። አፍሮ ቢትንና ፖፕን በማጣመር የሰራው ሌላኛው ዘፈኑ ቢጊኒንግ ከፍተኛ ተቀባይነትን ማትረፍ ችሏል። በነዚህ ነጠላ ዘፈኖቹ እውቅናን ማትረፍ የቻለው ጆቦይ በተለያዩ ሃገራትም በሚገኙ ፌስቲቫሎች ላይ ከሚጋበዙ ሙዚቀኞች አንዱ መሆን ችሏል። የሶስተኛ ወገን የማስታወቂያ ይዘት ማስጠንቀቂያ ብሪያን ናድራ ኬንያ ከሁለት ዓመታት በፊት ባወጣው ነጠላ ዘፈን ሊዮ የሙዚቃው ዓለም ላይ ስሙን የጣለው ብሪያን ሙዚቃውን ከሚሊኒየሙ ባህል የተገኘ፤ የተንቀሳቃሽ ስልክ ዘመንን ያማከለ፤ የከተማ ድምፅ በማለት ይገልፀዋል። ኬንያዊው ሙዚቀኛ፣ ገጣሚና የሙዚቃ ፀሐፊ የምስራቅ አፍሪካ የፖፕ ሙዚቃ ስልት አምባሳደር እየተባለ እየተጠራ ሲሆን፤ በዓለም አቀፉ ደረጃ ኬንያ የሙዚቃውን ገበያ ሰብሮ መግባት የቻለ ሙዚቀኛ የሌላት ሲሆን ብሪያን ይህንንም ሊቀይር ይችላል እየተባለ ነው። ለየት ያለ የአዘፋፈን ዘዬ ያለው ብሪያን ለስለስ ካሉ ዘፈኖቹ በተጨማሪ ራፕ ማድረግን እንዲሁም የተለያዩ የሙዚቃ ስልቶችን እንደ ሬጌና ሌሎችም ሙዚቃ ስልቶችን ማጣመር ችሏል። የሶስተኛ ወገን የማስታወቂያ ይዘት ማስጠንቀቂያ ኢኖስ ቢ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኦፍ ኮንጎ መነሻውን የኮንጎ ባህላዊ ሙዚቃ ያደረገው የ አመቱ ኢኖስ ሌሎች የሙዚቃ ስልቶችን በመጨመር ሙዚቃውን አንድ ደረጃ ወደፊት ሊያራምድ ይችላል እየተባለ ነው። ከታንዛንያው ሙዚቀኛ ዳይመንድ ጋር የተጣመረበት ዮፔ የተባለው ነጠላ ዘፈኑም ብዙዎችን አስደስቷል። የሙዚቃ ቪዲዮው በወጣበት በሶስት ወራትም አስራ አራት ሚሊዮን ተመልካቾች አይተውታል። ኢኖስ ቢ የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ መለያ የሆነውን ሩምባ የሙዚቃ ስልትንም ከሪትም ኤንድ ብሉዝና አፍሮ ቢትስ ጋር ማቀላቀል ችሏል። የሶስተኛ ወገን የማስታወቂያ ይዘት ማስጠንቀቂያ ሾ ማድጆዚ ደቡብ አፍሪካ ሾ ማድጆዚ በአለም የሙዚቃ መድረክ ዝናዋ እየናኘ ያለው ደቡብ አፍሪካዊቷ የሂፕ ሆፕ አርቲስት ሾ በዚህ ዓመት የቢኢቲ ብላክ ኢንተርቴይንመንት አዲስ ዓለም አቀፍ አርቲስት በሚል ዘርፍ ሽልማትን ማግኘት ችላለች። በታላቅ ስሜት የምትዘፍነው አርቲስቷ መድረክ ላይ ሲሆን ያ ስሜቷ በሰው ላይ ይሰርፃል ይሏታል። የደቡብ አፍሪካ ግኮም የሙዚቃ ስልት በመሳሪያ ብቻ የተቀነባበረ ቢሆንም ሾ ግን ራፕ ታደርግበታለች፤ በአንድ ሳይሆን በተለያዩ ቋንቋዎች። ምንም እንኳን ብዙዎቹ የደቡብ አፍሪካ አርቲስቶች የሙዚቃ ገበያ ትኩረት ሃገራቸው ላይ ቢሆንም ሾ ግን የአለም አቀፉን ገበያ እያማተረች ነው። ቢቢሲ ማስተባበያ
ትጥቅ የፈቱ የኦነግ ወታደሮች የረሃብ አድማ ላይ ናቸው
ማርች ማጋሪያ ምረጥ በአባ ገዳዎች ማግባባት ትጥቅ ፈትተው ወደተዘጋጀላቸው መጠለያ የገቡና አንድ ሺህ የሚሆኑ የቀድሞ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ኦነግ ወታደሮች የረሃብ አድማ ላይ መሆናቸውን ገለፁ። በጦላይ ወታደራዊ ካምፕ የሚገኙት እነዚህ የቀድሞ የኦነግ ወታደሮች በካምፑ ለአስቸጋሪ የኑሮ ሁኔታ መጋለጣቸውን ለቢቢሲ ተናግረዋል። አንድ የቀድሞ የኦነግ ወታደር የተያዝንበት ሁኔታ በጣም አስከፊ ነው። ብዙ ጓደኞቻችን በምግብ እጥረትና በንፅህና መጠበቂያ አገልግሎት ችግር ታመዋል ሲል ሁኔታውን ለቢቢሲ ገልጿል። ያልጠገገው የሀዋሳ ቁስል ከዚህም በተጨማሪ በቀጣይ ወደ መደበኛ ሕይወታቸው ይመለሱ ዘንድ ይሰጣችኋል የተባለው ስልጠናም ሆነ ሌሎች የተገቡላቸው ቃሎች አለመፈፀማቸውን ገልፀዋል። የኦነግ ወታደሮች ትጥቅ ፈትተው ወደ ካምፕ እንዲገቡ ኦነግን እና መንግስትን ሲያሸማግል የነበረው ኮሚቴ አባል የሆኑት የተቃዋሚ ፓርቲ መሪው አቶ በቀለ ገርባ ወታደሮቹ ችግሮች እንዳሉባቸው የሰሙ ቢሆንም በካምፑ ያሉበትን ሁኔታ ለመመልከት የክልሉን መንግሥት ፍቃድ እየጠበቁ እንደሆነ ተናግረዋል። በጉዳዩ ላይ የሚመለከታቸውን የክልሉ ሃላፊዎች ለማነጋገር ያደረግነው ጥረት አልተሳካም። ተያያዥ ርዕሶች
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የምዕራብ ዲስትሪክት ተጠባባቂ ሀላፊ አቶ ግርማ ጪብሳ፤ የባንክ ሠራተኞች በተለመደው ሁኔታ ደንበኞችን እያስተናገዱ ሳሉ ከረፋዱ አምስት ሰዓት አካባቢ ታጣቂዎች ወደ ባንኩ እንደገቡ ይናገራሉ።
በአጠቃላይ በምዕራብ ኦሮሚያ እና በቄለም ወለጋ በሚገኙ አሥር የንግድ ባንክ ቅርንጫፎች ላይ ጥቃት መሰንዘሩን አቶ ግርማ ይናገራሉ። ሀላፊው፤ አምስት ቅርንጫፎች መዘረፋቸውን እንዲሁም በተቀሩት አምስት ቅርንጫፎች ውስጥ የሚገኙ መገልገያ ቁሳ ቁሶች ሙሉ በሙሉ ከጥቅም ውጪ መደረጋቸውን ተናግረዋል። ኤቲኤም ገንዘብ መክፈያ ማሽኖች እና ኮምፒዩተሮች መሰባበራቸውንም ገልጸዋል። ገንዘብ ከተዘረፈባቸው አምስት ቅርንጫፎች መካከል በሁለቱ አራት ሠራተኞች ታግተው እንደነበረ እና ሁለቱ እንደተለቀቁ አቶ ግርማ ጨምረው ተናግረዋል። የተቀሩት ሁለት ሠራተኞች ስላሉበት ሁኔታ ግን ማወቅ አልቻልንም ብለዋል። በአካባቢው የደህንነት ስጋት ስላለ የደረሰውን ጉዳት ወደ ቅርንጫፎቹ ሄደን ለማጣራት አልቻልንም። መረጃም ተሟልቶ አልቀረበም የሚሉት አቶ ግርማ፤ እስካሁን በባንኩ እና በሠራተኞቹ ላይ የደረሰው የጉዳት መጠን አለመታወቁን ይናገራሉ። ጥቃቱን ያደረሱት የታጠቁ ቡድኖች መሆናቸውን ሰምተናል። ይሁን እንጂ ዘረፋውን የፈጸመው አካል ይሄ ነው ብዬ መናገር አልችልም በማለት አክለዋል። በተመሳሳይ በምዕራብ ወለጋ እና ቄለም ወለጋ የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ በርካታ ቅርንጫፎች እንዳሉት የሚያናገሩት የባንኩ የገበያ ጥናት እና የንግድ ኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ በለጠ ዋቅቤካ፤ በባንኮቹ ላይ ጥቃት እንደተሰነዘረ ጠቅሰው፤ እስካሁን ምን ያህል የባንኩ ቅርንጫፎች እንደተዘረፉና ጥቃት እንደደረሰባቸው የጠራ መረጃ እንደሌላቸው ገልጸዋል። አጭር የምስል መግለጫ የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መለያዎች የምዕራብ ወለጋ ዞን አስተዳዳሪ የሆኑት አቶ ገመቺስ ተመስገን፤ ቅዳሜ ዕለት በዞኑ በሚገኙ ስድስት ወረዳዎች ውስጥ በመንግሥት እና በግል ባንኮች ላይ በተመሳሳይ ሰዓት ዘረፋ እንደተፈጸመ ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ፣ ኅብረት ባንክ እና አዋሽ ባንክ እንደተዘረፉ ገልጸዋል። አቶ ገመቺስ እንደሚሉት፤ ዘረፋዎቹ የተፈጸሙት የሀገር መከላከያ ሠራዊት በሌለባቸው ስፍራዎች ነው። ከባንክ ዘረፋው ጋር ተያይዞ ታፍነው የተወሰዱ የባንክ ሠራተኞች እንዳሉ የሚናገሩት አቶ ገመቺስ፤ ከመካከላቸው የተለቀቁ እንዳሉና፤ እስካሁን የት እንደደረሱ የማይታወቁ ሠራተኞችን እያፈላለጉ መሆኑን አስረድተዋል። ይህን ጥቃት እየሰነዘረ ያለው የኦነግ ታጣቂ ነው የሚሉት አቶ ገመቺስ ከኦነግ ውጪ በእዚህ አካባቢ የታጠቀ ኃይል የለም ሲሉ ተናግረዋል። የሀገር መከላከያ ሚኒስቴር ምክትል ጠቅላይ ኤታማዦር ሹምና የኦፕሬሽን ኃላፊ ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ ባለፈነው አርብ በሰጡት መግለጫ፤ በምዕራብ ኦሮሚያ ላለው የጸጥታ መደፍረስ የኦሮሞ ነጻነት ግንባርን ኦነግ ተጠያቂ ያደርጋሉ። ምክትል ኤታማዦር ሹሙ፤ በአቶ ዳውድ ኢብሳ የሚመራው የኦነግ ጦር ላይ መከላከያ እርምጃ እየወሰደ እንደሆነ ተናግረው ነበር። ኦዲፒ፡ ኦነግ እንደ አዲስ ጦር መልምሎ እያሰለጠነ ነው ከዚህ ቀደም የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ፓርቲ ኦዲፒ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባልና የገጠር ፖለቲካ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ አዲሱ አረጋ፤ በአቶ ዳውድ ኢብሳ የሚመራው ኦነግ በኦሮሚያ በተለያዩ ስፍራዎች ይዘርፋል፣ አዲስ የኦነግ ጦር ይመለምላል፣ የክልል የመንግሥት ተቋሞችን ሥራ ያስቆማል፣ እንዲሁም የአካባቢውን አመራሮችን ይገድላል ሲሉ ተናግረዋል። በምዕራብ ኦሮሚያ የኦነግ ጦር አዛዥ ስለወቅታዊው ሁኔታ ምን ይላል የኦነግ ምላሽ አቶ ሚካኤል ቦረና የኦነግ ሸኔ የሥራ አሰፈጻሚ ኮሚቴ አባል ናቸው። አቶ ሚካኤል ኦነግ ለበርካታ ዓመታት የኦሮሞን ሕዝብ ነጻ ለማውጣት ሲታገል የቆየ ድርጅት ነው። ኦነግ በምንም አይነት ሁኔታ እንዲህ ያለ ተግባር አይፈጽምም ይላሉ። አቶ ሚካኤል የተፈጸመው ተግባር ሆነ ተብሎ የኦነግን ስም ለማጥፍት ነው ያሉ ሲሆን፤ መንግሥት ወደ ምዕራብ ኦሮሚያ በርካታ ጦሩን አሰማርቷል፤ በየአካባቢው እየተካሄደ ስላለው ነገር ሙሉ መረጃ ለማግኘት ቸግሮናል ይላሉ። ከጥቂት ሳምንታት በፊት የኦነግ የምዕራብ ዕዝ የጦር አዛዥ ኩምሳ ዲሪባ ወይም በቅጽል ስሙ መሮ፤ የክልሉ መንግሥት ኦነግ ላይ ያቀረበውን ወቀሳ በማስመልከት ለቢቢሲ ይህን ብሎ ነበር። የተኩስ አቁም ስምምነቱን ከደረስን በኋላ ኦነግ በራሱ ተነሳሽነት መንግሥት ላይ ተኩስ ከፍቶ አያውቅም፤ አጸፋዊ እርምጃ ካልወሰድን በቀር። ይህ ሁሉ ክስ ግን ሃሰተኛ ነው። መንግሥት ይህን ክስ የሚያቀርበው በዚህ አካባቢ ላይ ጦሩን በማዝመት ጦርነት ለመክፈት ቅድመ ዝግጅት ሲያከናውን ነው እንጂ ኦነግ ያፈረሰው የመንግሥት ሥርዓት የለም፤ የዘረፈውም የጦር መሳሪያ የለም። የአየር ጥቃት ዕሁድ ጠዋት የሀገር መከላከያ በምዕራብ ኦሮሚያ በሚገኙ የኦነግ ማሰልጠኛ ጣቢያዎች ላይ የአየር ጥቃት ሰንዝሯል የሚል መረጃ በስፋት ተሰራጭቶ ነበር። የምዕራብ ወለጋ ዞን አስተዳዳሪ የሆኑት አቶ ገመቺስ ተመስገን በጉዳዩ ላይ አስተያየታቸውን ጠይቀን፤ ይህ መረጃ እስካሁን አልደረሰኝም። በምዕራብ ኦሮሚያ የሀገር መከላከያ ሠራዊት ይንቀሳቀሳል። በተለያዩ አጋጣሚዎችም ከኦነግ ሠራዊት ጋር የተኩስ ልውውጥ አድርጓል። ዕሁድ ዕለት የአየር ጥቃት ተሰንዝሯል ወይም አልተሰነዘረም ማለት አልችልም ብለዋል። በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ የአየር ጥቃት የተፈጸመው በቤጊ እና ጊዳሚ ወረዳዎች አዋሳኝ ድንበር ላይ መሆኑ በስፋት ተነግሯል። ይሁን እንጂ ያነጋገርናቸው የአከባቢው ነዋሪዎች የአየር ጥቃት ተፈጽሟል ሲባል ሰማን እንጂ ያየነው ነገር የለም ይላሉ። ነዋሪዎቹ እንደሚሉት፤ የአየር ጥቃት ሲፈጸም ባይመለከቱም በአከባቢው የጦር ሄሊኮፕተሮች በብዛት ስለሚመላለሱ ከፍተኛ ስጋት ገብቷቸዋል። የኦነግ ሸኔ የሥራ አሰፈጻሚ ኮሚቴ አባል የሆኑት አቶ ሚካኤል ቦረና ግን መንግሥት በቤጊ እና ጊዳሚ ወረዳዎች ውስጥ የአየር ጥቃት እየሰነዘረ ነው ሕዝቡም እየተጎዳ ነው ብለዋል። አቶ ሚካኤል እንደሚናገሩት፤ የኦነግ ጦር የነበረበትን ስፍራ ሳይለቅ እራስን የመከላከል እርምጃ እየወሰደ ነው። ከፌደራል መንግሥት እንዲሁም ከመከላከያ ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም። ተያያዥ ርዕሶች
በምዕራብ ኦሮሚያ በታጠቁ ኃይሎች የተገደሉ ሰዎች ቁጥር ፖሊሶችን ጨምሮ መድረሱ ተገለፀ
ዲሴምበር ማጋሪያ ምረጥ አጭር የምስል መግለጫ የኦሮሚያ ኮሚሽነር አለማየሁ እጅጉ ኩምሳ በምዕራብ ኦሮሚያ አካባቢ ያለውን አለመረጋጋት ተከትሎ ፖሊሶችን ጨምሮ በአጠቃላይ ግለሰቦች መገደላቸውን የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር አለማየሁ እጅጉ ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቀዋል። በዚህም መግለጫ ላይ የፀጥታ ኃይሎችንና ግለሰቦችን በድብቅ ሲያስገድሉ የነበሩት አባ ቶርቤ ባለሳምንት የተሰኘው ቡድን አባላት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ተናግረዋል። በኦነግ እና በመከላከያ ሠራዊት መካከል በምዕራብ ኦሮሚያ ግጭት እንደነበር ተነገረ ኮሚሽነሩ በአካባቢው ግጭቶቹን በማነሳሳት ኦነግ ሸኔን የወነጀሉ ሲሆን፤ ቱ ፖሊሶችም የተገደሉት በኦነግ ሼኔ እንደሆነም ተናግረዋል። ከዚህም በተጨማሪ ኦነግ ሸኔን በገንዘብ የረዱ ሰዎችም ምርመራ እንደተጀመረም ኮሚሽነሩ አስረድተዋል። ኮሚሽነሩ ጨምረውም የኦነግ መሪ የሆኑትን አቶ ዳውድ ኢብሳ በስም ጠቅሰው ከመንግሥት ጋር አብረው ለመስራት የሰላም ስምምነት የፈረሙ ቢሆንም በአንፃሩ ለሰላም እየሰሩ እንዳልሆነ ገልፀዋል። በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች በመንቀሳቀስ የፀጥታ ኃይሎችንና ግለሰቦችን በድብቅ ሲያስገድሉ የነበሩት አባ ቶርቤ ባለሳምንት የተባለው ቡድን ተጠርጣሪዎቹ አባ ቶርቤ በሚል መጠሪያ በመደራጀት ሰላማዊ ዜጎችን፣ የመንግሥት ባለስልጣናት እና የፀጥታ ኃይሎችን ሲገድሉ እና ተጨማሪ ባለስልጣናትን ለመግደል ሲያሴሩ ተጠርጥረው እንደተያዙ ተገልጿል። ኮሚሽነሩ በቁጥር ሁለት ሺህ ሰባ ኤኬ የጦር መሳሪያዎች በቄለም ወለጋና ምዕራብ ወለጋ ዞን ከሚገኙ ፖሊስ ጣቢያዎችና ከባንክ ሦስት ሚሊዮን ብር እንደተዘረፈ ገልፀዋል። ተያያዥ ርዕሶች
ከምዕራብ ኦሮሚያ ከተሞች ጥቃት ጀርባ ያለው ማን ነው
ጁላይ ስለ ማጋራት ተጨማሪ ያጋሩ ማጋሪያ ምረጥ በነቀምቴ፣ በጊምቢ፣ ደምቢደሎና በሌሎችም የምዕራብ ኦሮምያ ከተሞች ባለፉት ሶስት ቀናት ግድያና የአካል ማጉደል ጥቃቶች ተፈፅሟል። ቤቶች ተቃጥለዋል መንገዶችም ተዘግተው ነበር። አቶ መንግስቱ መገርሳ የተባሉ ያነጋገርናቸው የጊምቢ ኗሪም ያረጋገጡልን ከተሞቹ በሰላም እጦት ታውከው መሰንበታቸውን ገልፀውልናል። ዛሬ ከሰዓት በኋላ ነገሮች በመረጋጋታቸው ተሽከርካሪዎች መንቀሳቀስ ቢችሉም ከትናንት ጀምሮ ቆመው እንደነበር የሚናገሩት አቶ ጋሪ፤ መንገዱ የተዘጋው ባልታወቁ ቡድኖች እንደሆነ ይናገራሉ። አቶ ጋሪ ጆግር የሚባል ቦታ ላይ መንገድ በመዘጋቱ አንድ ቀን አርጆ ላይ ከነተሽከርካሪያቸው መንገድ ላይ ማደራቸውን ገልፀውልናል። የኦሮምያ ክልል ፀጥታና አስተዳደር ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ባይሳ ኩማ በምዕራብ ኦሮምያ የተለያዩ አካባቢዎች ግድያ መፈፀሙን፣ በመንግሥት ሃይሎች ላይ ተኩስ የመክፈትና መሳሪያ የመንጠቅ እንዲሁም ቦምብ መወርወርና ሌሎችም ዓይነት ጥቃቶች መሰንዘራቸውን ለቢቢሲ ተናግረዋል። ያነጋገርናቸው ሌሎች ሰዎች ጥቃቱን የፈፀመው አካል ያልታወቀ ነው ቢሉም አዲስ ቡድን ሳይሆን ካለፉት ጥቂት ወራት ጀምሮ በኦሮሞ ህዝብ ነፃነት ስም አካባቢው ላይ ሲንቀሳቀስ የቆየ መሆኑን ጠቁመዋል። ጥቃቱን የፈፀመው የኦሮሞ ነፃ አውጪ ግንባር ኦነግ ነው የሚሉ መረጃዎች ማህበራዊ ሚዲያ ላይ በብዛት መንፀባረቃቸውን በመጥቀስ ጥያቄ ያቀረብንላቸው የኦነግ ቃል አቀባይ አቶ ቶሌራ አዳባ ከጥቃቱ ጀርባ ኦነግ እንደሌለበት ገልፀዋል። ከጥቃቱ ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር የዋሉ ግለሰቦች መኖራቸውን የገለፁት አቶ ባይሳ እስካሁን ከጥቃቱ ጀርባ ማን እንዳለ አለመረጋገጡንና በዚህ ረገድ አሁንም ምርመራ እየተደረገ እንዳለ ይጠቁማሉ። የቀድሞ የኦሮሚያ ክልል የኮሚኒኬሽን ቢሮ ሃላፊ አቶ አዲሱ አረጋ አርብ ማምሻው ላይ በፌስቡክ ገጻቸው ላይ የጠላትን ተልዕኮ ተቀብለው የህዝቡን ሰላም ለማወክ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ተጠርጣሪ ግለሰቦችን የጊምቢ ወጣቶች በቁጥጥር ስር በማዋል ለኦሮሚያ ክልል ፖሊስ አስተላልፈዋል ሲሉ አስፈረዋል። ይህንን ዜና ያጋሩ ስለማጋራት
ከ እኛ የተለየን ጦር በመቶ እንኳ አይሆንም መሮ የኦነግ ጦር አዛዥ
ፌብሩወሪ ማጋሪያ ምረጥ በመንግሥትና በኦነግ መካከል፣ በሽማግሌዎች አማካይነት የተደረሰውን ስምምነት ተከትሎ በርካታ የግንባሩ አባላት መሽገው ከነበሩባቸው ቦታዎች በሰላም እየተመለሱ ቢሆንም በምዕራብ ኦሮሚያ የሚንቀሳቀሰው የኦነግ ኃይል አዛዥ ግን ይህንን ለመፈፀም ዝግጁ እንዳልሆነ ገልጿል። በተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች ተሰማርተው የሚገኙ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ጦር አባላት የአባገዳዎችን ጥሪ ተከትለው ትጥቅ ፈትተው ወደ ጦር ካምፖች ከመግባታቸው በፊት ወደተዘጋጁላቸው ጊዜያዊ ማቆያ ስፍራዎች በዚህ ሳምንት እየገቡ እንደሆነ እየተዘገበ ነው። ኦነግ ሀገር ለመገንጠል ነው የምሠራው ብሎ አያውቅም ሽጉጥ ገለታ ዶ ር ሽምግልናውን የመሩትና ስምምነቱ ከፍጻሜ እንዲደርስ ጥረት እያደረጉ ያሉት አባገዳዎች እና የየአካባቢዎቹ ባለስልጣናት ለውሳኔው ተገዢ በመሆን ወደተዘጋጁላቸው ስፍራዎች ከነትጥቃቸው ሲመጡ አቀባበል እያደረጉላቸው ይገኛል። ይህ በእንዲህ እንዳለም የአባገዳዎችን ጥሪ ተከትሎ ሁሉም የኦነግ ጦር አባላት እየተመለሱ እንዳልሆነ ወደተዘጋጁላቸው ጊዜያዊ ማቆያ ስፍራዎች ከገቡ የኦነግ ጦር አባላት ተሰምቷል። ለዚህም እንደምክንያት የሚጠቀሰው የምዕራብ ኦሮሚያ የኦነግ ጦር አዛዥ የሆነው ኩምሳ ድሪባ ወይም በትግል ስሙ ጓድ መሮ የአባገዳዎችን ጥሪ አለመቀበሉ ነው። በኦነግ እና በመከላከያ ሠራዊት መካከል በምዕራብ ኦሮሚያ ግጭት እንደነበር ተነገረ በምዕራብ ኦሮሚያ የሚገኘው የኦነግ ጦር አዛዥ እንደሆነ በስፋት የሚነገርለት ኩምሳ ድሪባ መሮ ን ቢቢሲ ስለዚሁ ጉዳይ በስልክ አነጋግሮታል። እንደተባለውም መሮ ባለው ሁኔታ ስምምነቱን ተቀብሎ ለመግባት ዝግጁ እንዳልሆነ ገልጿል። የአባገዳዎችን ጥሪ ለመቀበል እና እርቅ ለማውረድ ዝግጁ ስለመሆኑ ሲጠየቅም የእርቅ የተባለው ኮሚቴ እኔን በአካል አግኝተው ለማነጋገር ፍላጎት የላቸውም። ትኩረት ያደረጉት ጦሩን አንድ በአንድ እጁን እንዲሰጥ ማድረግ ላይ ነው በማለት እሱም እነሱን ለማግኘት ያደረገው ጥረት አለመሳካቱን ይናገራል። እንዲያውም ጦሩን የመበታተን ዓላማ ይዘው ነው እየተንቀሳቀሱ ያሉት ሲል ይከሳል። የኦነግ ሊቀመንበር የሆኑት አቶ ዳውድ ኢብሳ የእርቅ ኮሚቴውን በመደገፍ የኦነግ ጦር ጥሪውን ተቀብሎ ወደተዘጋጀለት ስፍራ እንዲሄድ መልዕክት ማስተላለፋቸው ይታወሳል። የጦሩ መሪ መሮ የግንባሩ ሊቀመንበር ተገዢ መሆን አለመሆኑን ተጠይቆ ሲመልስ ሊቀመንበሩ የእርቅ ኮሚቴውን ያሉት፤ የኦነግ ጦር የእናንተው ነው። ሂዱና አወያይታችሁ የሚሉትን ስሟቸው ነው ብሏል። ጨምሮም እንደተናገረው እኔ በመሰረታዊ ጉዳዮች ላይ እንወያይ ነው ያልኩት እንጂ የፖለቲካ ፕሮፖጋንዳ ጥቅም የለውም፤ የኦሮሞ ህዝብ መሰቃየት የለበትም ነው የምለው። እነሱ ግን የጦሩ አባላት የእጅ ስልክ ላይ እየደወሉ አንድ በአንድ ጦሩን የማፍረስ ሥራ ነው እየሰሩ የሚገኙት ሲል ገልጿል። በምዕራብ ኦሮሚያ የፌደራል ፖሊስ አባላት ተገደሉ ያለው ችግር ከስር መሰረቱ መፍትሄ አላገኘም ብሎ የሚያምነው መሮ አሁን እየተደረገ ያለው በተለያዩ ስፍራዎች የሚገኙ ሰዎችን አንድ በአንድ የማስኮብለል ሥራ ነው። ከዚህ የተለየን ጦር በመቶ እንኳ አይሆንም። በመቶ አሁንም እንደታጠቀ ነው የሚገኘው በማለት ተናግሯል። ወደፊት መራራ ትግል ማድረጋችንን እንቀጥላለን ያለው መሮ ብቻዬን ብቀር እንኳ ትግል ማድረጌን እቀጥላለሁ እቅዴም ይሄው ነው በማለት በትጥቅ ትግሉ እንደሚቀጥል ጠንከር በማለት ተናግሯል። የቀረበውን የእርቅ ጥሪ ተቀብለው ከገቡት የኦነግ አባላት መካከል አንዱ የሆኑት የግንባሩ ጦር የሞራል እና ፖለቲካ መምህር የ ዓመቱ የዕድሜ ባለጸጋ አቶ ታፈሰ ኦላና በመሮ በኩል ያሉት ወታደሮች እየተመለሱ እንዳልሆነ አረጋግጠዋል። በምዕራብ ኦሮሚያ በታጠቁ ኃይሎች የተገደሉ ሰዎች ቁጥር መድረሱ ተገለፀ ጨምረውም መሮ መመለስ አይፈልግም፤ ስልክ እየደወለ ጸያፍ ቃል እየተናገረን ነው። እጃችሁን ለአባገዳዎች እየሰጣችሁ ሰዎች ከትግላችን ዓላማ ውጪ የሆነ ተግባር እየፈጸማችሁ ነው። ታሪክ ይፋረዳችኋል እያለ ያስጠነቅቀናል። አቶ ታፈሰ እንደሚሉት አሁንም በምዕራብ ኦሮሚያ ትዕዛዝ የሚሰጠው መሮ መሆኑንና የኦሮሞን ምድር የጦር አውድማ ማድረግ ነው የሚፈልገው። ህዝብ ሰላም እየፈለገ እሱ ግን አሁንም ደም ማፍሰስ የሚፈልግ ከሆነ ተሳስቷል ብለዋል። የኦነግ የምዕራብ ኦሮሚያ ጦር አዛዥ መሮ በአባ ገዳዎች የቀረበውን ጥሪ ተቀብለው ወደተዘጋጀላቸው ስፍራ የሄዱ የጦሩ አባላት ላይ ይሰነዝራል ስለተባለው ማስፈራሪያን በተመለከተ የምን ማስፈራራት ነው። መሳሪያ ይዘን እያየናቸው እኮ ነው እየሄዱ ያሉት። ምርጫቸው ነው። ማንም ማንንም አላስፈራራም ሲል ምላሽ ሰጥቷል። መሮ ችግሩን ለመፍታትም እንደቅድመ ሁኔታ የሚጠይቀው በደቡብ ኢትዮጵያ እና በተለያዩ ዞኖች ከሚገኙ አባላቶቻችን ጋር በቅድመ ሁኔታዎች ላይ ውይይት ማድረግ አለብን በማለት የሽምግልና ኮሚቴውም እንዲያወያያቸውና አንድ በአንድ የጦሩን አባላት ማስኮብለል ያለውን ድርጊት ማስቆም እንዳለባቸው ተናግሯል። የእርቅ ኮሚቴው ጸኃፊ የሆነውን ጀዋር መሐመድ በበኩሉ የኮሚቴው አባላት በተንቀሳቀሱባቸው ስፍራዎች ሁሉ የኦነግ የጦር አመራሮችን ለማግኘት ያደረጉት ጥረት የጦሩ አመራሮች ፍቃደኛ ሳይሆኑ በመቅረታቸው ሳይሳካ እንደቀረ ይናገራል። ወደ ምዕራብ ኦሮሚያ የተጓዙት አቶ በቀለ ገርባ እና አባ ገዳ በየነ ሰንበቶ ያደረጉት ሙከራ አልተሳካላቸውም። ወደ ደቡብ ኦሮሚያ የሄድኩት ደግሞ እኔ ነበርኩኝ። የኦነግ የምዕራብ ዞን የጦር ኃላፊ ሊያገኘን ፍቃደኛ አልነበረም። ሲል ተናግሯል። ተያያዥ ርዕሶች
የኖርዌይ ፓስፖርቴን መልሼ ኢትዮጵያዊ መሆን እችላለሁ አቶ ሌንጮ ለታ
ኖቬምበር ስለ ማጋራት ተጨማሪ ያጋሩ ማጋሪያ ምረጥ በኢትዮጵያ ፖለቲካ የለውጥ መንፈሱን ተከትሎ መንግሥት ባደረገላቸው ጥሪ ወደ አገር ውሰጥ ከተመለሱ የተቃዋሚ ፓርቲዎች መካከል የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር አንዱ ነው። በኢትዮጵያ የተቃውሞ ፖለቲካ አንጋፋ የሆኑት አቶ ሌንጮ ለታ ፖለቲካ በቃኝ እያሉ ነው የሚል መረጃ በማኅበራዊ ሚዲያ እየወጣ በመሆኑ አቶ ሌንጮ ለታን ስለ ጉዳዩ አነጋግረናል። የፖለቲካ ሩጫዎን ጨርሰዋል እየተባለ ነው። አቶ ሌንጮ፡ ፖለቲካ በቃኝ ብዬ አላውቅም፤ መረጃውን ከየት እንዳመጡት አላውቅም። ከፓርቲ ኃላፊነትዎ ለመልቀቅ ጥያቄ አቅርበዋል አቶ ሌንጮ ፡ ገና ፈረንጅ አገር እያለሁ ጀምሮ እየጠየቅኩ ነው።ይህን ለድርጅቴም አሳውቄያለሁ፤ በይፋም ተናግሪአለሁ። ግን ራሴ ፈልጌ ነው። ገና ድርጅቱ መወሰን አለበት። በይፋ በደብዳቤ ድርጅትዎን የጠየቁት መቼ ነው አቶ ሌንጮ፡ ጥያቄዬን በጽሑፍ አላቀረብኩም። ነገር ግን ለአባላት ስብሰባ ላይ በይፋ ከሚቀጥለው የማእከላዊ ኮሚቴ ምርጫ በኋላ ይሄን ኃላፊነት ተሸክሜ መቀጠል እንደማልፈልግ ተናግሪያለሁ። ፓርቲዎ ለጥያቄዎ ምን ምላሽ እየሰጠ ነው አቶ ሌንጮ፦ ገና ነው። ነገር ግን አሁን ስብሰባ ሊካሄድ ስለሆነ ውሳኔ ይሰጣል። ኃላፊነትዎን መልቀቅ የፈለጉት ለምንድን ነው አቶ ሌንጮ፡ እርጅና እርጅና ከኃላፊነት ብቻ ነው የሚያግድዎት ቀጣይ ተሳትፎዎት ምን ይሆናል አቶ ሌንጮ፡ እንደ አንዳንድ ኃላፊዎች እያነከስኩ ስብሰባ መሄድ አልፈልግም። ነገር ግን ሕይወቴ እስካለ ድረስ የፖለቲካ ሥራን መተው አልችልም። ረዥም ዓመታት በውጭ ሃገር ከቆዩ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች ጋር በተያያዘ የዜግነት ጉዳይ ይነሳል። ዜግነትዎ ምንድን ነው አቶ ሌንጮ፡ የኖርዌይ ፓስፖርት ነው ተሸክሜ የምዞረው። ግን የዜግነቴ ጉዳይ በውሳኔዬ ላይ ምንም ተፅእኖ አልነበረውም። ነገሩ ኃላፊነት መልቀቅ ከመፈለጌ ጋር አይገናኝም። ብፈልግ ድርጅቱ በኢትዮጵያ ለመመዝገብ ሲቃረብ የኖርዌይን ፓስፖርት ለኖርዌጅያኖቹ መልሼ ኢትዮጵያዊነቴን እንደገና ሥራ ላይ ማዋል እችላለሁ። ይህ ለውሳኔዬ ምክንያት የሆነ ነገር አይደለም። በውሳኔዎ እንደ እርሶ ለረዥም ዓመታት ተቃዋሚ ፓርቲዎችን እየመሩ ላሉ ማስተላለፍ የሚፈልጉት መልእክት አለ አቶ ሌንጮ፡ በተለይ ኦነግ ውስጥ ሃምሳ ዓመት ያገለገሉ ሁሉም ኃላፊነት ቢለቁ ጥሩ ነው ብዬ አምናለው። አሁን አዲስ ትውልድ ትግሉን ተረክቧል እና ለእነሱ መተው ነው የተሻለው መንገድ። በቀጣይ ተሳትፎዎት በምን መንገድ ይሆናል አቶ ሌንጮ፡ ፓርቲውን እያገለገልኩ እቆያለሁ። ከሌሎች ጋር በስፋት ለመሥራትም እቅድ አለኝ። ስለዚህ ቆይታዎ የሚሆነው በኢትዮጵያ ነው አቶ ሌንጮ፡ አዲስ አበባ
በኦነግ ሠራዊት ውስጥ የመሮ ምክትል የሰላም ጥሪውን ተቀብሎ ገባ
ፌብሩወሪ ማጋሪያ ምረጥ የ ጓድ መሮ ምክትል እና ዲነራስ በሚለው የትግል ስም የሚታወቀው ሁንዴ ዴሬሳ ከቀናት በፊት የአባ ገዳዎችን ጥሪ ተከትለው የጦር አባላቱን ይዞ ወደ ተዘጋጀለት ስፍራ ገብቷል። ሁንዴ ዴሬሳ የአባ ገዳዎችን የሰላም ጥሪ የተቀበለውና ወደ ተዘጋጀው ስፍራ የገባ የመጀመሪያው የኦነግ የጦር አዛዥ ነው ተብሏል። የኦሮሞ ነጻነት ግንባር የምዕራብ ኦሮሚያ ዞን ምክትል ጦር አዛዥ የሆነው ሁንዴ ዴሬሳ ወደፊትም ቢሆን በኦሮሞ እና የኦሮሚያ መብትን ለማስከበር መታገላችንን እንቀጥላለን ሲል ለቢቢሲ ተናግሯል። ኦነግ እና መንግሥትን ለማግባባት የሃገር ሽማግሌዎች እየጣሩ ነው ቅዳሜ ዕለት በአባ ገዳዎች አቀባበል ተደርጎለት የነበረው የጦር አዛዡ ተከታዮቹ በአምቦ ሰንቀሌ የፖሊስ ማሰልጠኛ ቆይታ ካደረጉ በኋላ ዛሬ ወደ ጦላይ የወታደር ማሰልጠኛ ማዕከል መሄዳቸውን ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። የምዕራብ ኦሮሚያ ዞን የጦር አዛዥ የሆነው መሮ ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ ላይ ወደፊት መራራ ትግል ማድረጋችንን እንቀጥላለን። ብቻዬን ብቀር እንኳ ትግል ማድረጌን እቀጥላለሁ እቅዴም ይሄው ነው ሲል መናገሩ ይታወሳል። ሁንዴ ዴሬሳ እንዴት የአባ ገዳዎችን ጥሪ ለመቀበል እንደቻለ ሲያብራራ ይህ የህዝብ ፍላጎት ነው። ህዝቡ የሚፈልገው ይህን ነው። በኦሮሞ ጉዳይ ላይ ኑ አብራን እንሥራ ብለው ጥሪ ስላቀረቡልን ከሠራዊቱ ጋር ከተወያየን በኋላ ጥያቄያቸውን ተቀብለናል ብሏል። የኦነግ የምዕራብ ኦሮሚያ ዞን በሁለት ተከፍሎ ነው የሚተዳደረው። ከጊምቢ በታች መሮ ነው ትዕዛዝ የሚሰጠው። ከጊምቢ በላይ እንደ ነቀምቴ፣ ሻምቡ እና ምዕራብ ሸዋ ደግሞ ትዕዛዝ የምሰጠው እኔ ነኝ የሚለው ሁንዴ የዕዝ ተዋረዱን ሲያስረዳ መሮ ከሊቀመንበሩ ዳውድ ኢብሳ ትዕዛዝ ይቀበልና ለእኛ ያስተላልፋል ብሏል። በምዕራብ ኦሮሚያ የኦነግ ጦር አዛዥ ስለወቅታዊው ሁኔታ ምን ይላል የሁንዴ የትግል አጋር እና አዛዥ የሆነው ኩምሳ ዲሪባ ወይም መሮ የእርቅ የተባለው ኮሚቴ እኔን በአካል አግኝተው ለማነጋገር ፍላጎት የላቸውም። ትኩረት ያደረጉት ጦሩን አንድ በአንድ እጁን እንዲሰጥ ማድረግ ላይ ነው በሚል እና በሌሎች ምክያቶች ጥሪውን እንደማይቀበል አርብ ዕለት ለቢቢሲ ተናግሮ ነበር። በዚህ ላይ ሁንዴ አስተያየቱን እንዲሰጡ ጠይቀን ይህን ትግል ህዝቡ የሚፈልግ ከሆነ አንድ መቶ ዓመት እንኳ በትግል ላይ እንቆያለን። የምንታገለው ለህዝቡ እስከሆነ ድረስ ህዝቡ የምፈልገው ሰላማዊ ትግል ነው እስካለ ድረስ የህዝቡን ስሜት ማዳመጥ ይኖርብናል። እሱ መሮ የግል አቋሙ ሊሆን ይችላል። ይሁን እንጂ ማዳመጥ ያለብን የግል ስሜታችንን ሳይሆን የህዝቡን ፍላጎት ነው በማለት የአባ ገዳዎችን ጥሪ ከሰማን በኋላ ከመሮ ጋር ተገናኝተን ተነጋግረን ነበር። የእርቅ ጥሪውን ከተቀበልን በኋላ ሃሳቡን ቀየረ ሲል የነበረውን ሁኔታ ገልጿል። አጭር የምስል መግለጫ የምዕራብ ኦሮሚያ ዞን የኦነግ ጦር አዛዥ ኩምሳ ድሪባ ወይም መሮ የመሮን ውሳኔ በተመለከተም ሽንፈት መሰለው፤ ሰው የሚለውን መቀበል ላይ ትንሽ ድክመት አለበት። ብቸኝነትም ያጠቃዋል፤ ከዚህ ውጪስ ሌላ ችግር የለበትም ብሏል። መሮ ከቀናት በፊት ለቢቢሲ እንደተናገረው ከዚህ የተለየን ጦር በመቶ እንኳ አይሆንም። በመቶ አሁንም እንደታጠቀ ነው የሚገኘው ብሎ ነበር። የመሮ ምክትል የሆነው ሁንዴ እንደሚለው ከሆነ ግን የእርቅ ጥሪውን ተቀብለው የወጡ የኦነግ ወታደሮች በጫካ ከሚገኙት ይበልጣሉ። ከ እኛ የተለየን ጦር በመቶ እንኳ አይሆንም መሮ የኦነግ ጦር አዛዥ በእኔ ስር የነበሩ የሠራዊት አባላት በሙሉ የእርቅ ጥሪውን በደስታ ተቀብለውታል፤ በጫካ የቀሩት አባላት የኦሮሞ ህዝብ ጥያቄ እስኪመለስ እንታገላለን የሚሉት ናቸው በማለት ተናግሯል። በኦነግ ጦር አባላት መካከል የእርቅ ጥሪውን እንቀበል፤ አንቀበል በሚል የሃሳብ ልዩነት ተፈጥሯል ወይ ብለን ለጠየቅነው ጥያቄ፤ ሁንዴ ሲመልስ ይህ በደንብ ያለ ነው። እኔ እንደማውቀው እንኳ ሦስት ቦታ ተከስቷል። ተያያዥ ርዕሶች
ኦዲፒ፡ ኦነግ በተለያዩ ዞኖች እንደ አዲስ ጦር መልምሎ እያሰለጠነ ነው
ዲሴምበር ማጋሪያ ምረጥ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ኦነግ ለሰላማዊ ትግል ወደ ሃገር ውስጥ ከገባ በኋላም በተለያዩ የክልሉ ዞኖች ውስጥ እንደ አዲስ ጦር መልምሎ እያሰለጠነ ነው ብለዋል የኦዲፒ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል እና የገጠር ፖለቲካ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊው አቶ አዲሱ አረጋ። አቶ አዲሱ ዛሬ ጋዜጠኞች ሰብሰበው በሰጡት መግለጫ፤ በኦነግ እና በኢትዮጵያ መንግሥት መካከል አሥመራ ላይ የተደረሰው ስምምነት ሆን ተብሎ ዝርዝሩ ከህዝብ ተደብቋል የተባለው ከእውነት የራቀ ነው ያሉ ሲሆን፤ የስምምነቱ ተፈጻሚነትም እንደፈለጉት በፍጥነት እየሄደ እንዳልሆነ አስረድተዋል። ከጥቂት ወራት በፊት በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶ ር ወርቅነህ ገበየሁ እና በኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ለማ መገርሳ የሚመራ ልዑክ ወደ ኤርትራ ተጉዞ ከኦነግ ጋር ስምምነት ማድረጉ ይታወሳል። በርካቶች መንግሥት ከኦነግ ጋር አሥመራ ላይ የደረሰውን ዝርዝር ስምምነት ለህዝብ ይፋ አለደረገም በማለት መንግሥትን ይወቅሳሉ። የኦነግ ሊቀመንበር የሆኑት አቶ ዳውድ ኢብሳም በቅርቡ ለሃገር ቤት መገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫ፤ በሁለቱ ወገን የተደረሰው ስምምነት ለህዝብ ግልጽ እንዳይሆን እያደረገ ያለው መንግሥት ነው ብለዋል። የኦነግ እና የመንግሥት እሰጣገባ በሃገር ውስጥ የሚንቀሳቀሱትን እና ከኤርትራ የገቡ የኦነግ ሰራዊቶችን በማሰልጠን እንደየ አስፈላጊነቱ የጸጥታ ኃይሉን እንዲቀላቀሉ ወይም በሌሎች መስኮች እንዲሰማሩ ለማድረግ ከኦነግ ጋር ከስምምነት መድረሳቸውን ያስታወሱት አቶ አዲሱ፤ በሃገር ውስጥ የሚገኙ የኦነግ ወታደሮችን ከኤርትራ ከተመለሱት ጋር በአንድ ላይ ሰልጠና ለማስጀመር ብንሞክርም በሃገር ውስጥ ያሉት ሳይገኙ ቀርተዋል ይላሉ። በሃገር ውስጥ የሚገኙ የኦነግ ወታደሮች ስልጠና እንዲጀምሩ ለ ቀናት ቢጠበቁም ሳይገኙ በመቅረታቸው ከኤርትራ ለመጡት ብቻ ሰልጠና መስጠት መጀመሩን አስታውቀዋል። በመንግሥት እና በኦነግ መካከል የተደረሰውን ስምምነት ለማስፈጻም ከሁለቱም ወገን ተወካዮች በተዋቀረው ኮሚቴ ስብሰባ ላይ በሚደረጉ ውይይቶች ከስምምነት ይደረሳል፤ ተፈጻሚ ግን አይሆኑም ይላሉ አቶ አዲሱ። በምዕራብ ኦሮሚያ በታጠቁ ኃይሎች የተገደሉ ሰዎች ቁጥር መድረሱ ተገለፀ የኦነግ አመራር በጠቅላለው ሰላማዊ ትግልን እንደ አማራጭ አድርጎ መቀበሉ አጠራጥሮናል የሚሉት አቶ አዲሱ፤ የኦነግ አመራር እና በምዕራብ ኦሮሚያ የሚገኙ የጦር አመራሮች የሚሰጡት መግለጫዎች የተለያዩ ናቸው ይላሉ። ኦነግ በጉጂ፣ ቄለም፣ ምዕራብ ወለጋ፣ ምስራቅ ወለጋ እና ኢሉ አባቦራ ዞኖች ውስጥ አዲስ ጦር መልምሎ እያሰለጠነ ነው ይህም እጅጉን ያሳስበናል ብለዋል አቶ አዲሱ። አቶ አዲሱ ጨምረውም ሕገ ወጥነት እየተስፋፋ ነው፤ አመራሮቻችንም እየተገደሉ ነው ብለዋል። ትናንት በነቀምቴ ከተማ ውስጥ የጉቶ ጊዳ ወረዳ ምክትል አስተዳደሪ የነበሩት ግለሰብ መገደላቸውን ያስታወቁ ሲሆን፤ የመንግሥት ባለስልጣናትን መግደል፣ የአስተዳደር ስርዓቱን ማፈራረስ፣ ዘረፋ እና ሚሊሻዎችን ጦር ማስፈታት የመሳሰሉ ወንጀሎች በኦነግ ሥራዊቶች እየተፈጸሙ ነው ብለዋል። ኦነግ ከመንግሥት ጋር ያደረኩት ስምምነት አልተከበረም አለ በሌላ በኩል ከቀናት በፊት የኦነግ ሊቀመንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ ድርጅታቸው ከመንግሥት ጋር ከስምምነት ላይ የደረሰባቸው ጉዳዮች በመንግሥት እየተጣሱ ነው ማለታቸው ይታወሳል። የተኩስ አቁም ስምምነቱ መከበር፣ የመንግሥት የጸጥታ ኃይል አስከባሪ እና ደህንነት አካል ገለልተኛ እንዲሆን ማድረግ፣ የኦነግ ሠራዊት ወደ መንግሥት ኃይል እንዲካተት ማድረግ ከኦነግ ሠራዊት አንፃር ከመንግሥት ጋር የተስማሙባቸው እንደሆኑ አመልክተው እነዚህ ስምምነቶች ግን በመንግሥት እየተጣሱ ነው ብለው ነበር። ተያያዥ ርዕሶች
በምዕራብ ኦሮሚያ የኦነግ ጦር አዛዥ ጃል መሮ ስለወቅታዊው ሁኔታ ምን ይላል
ዲሴምበር ማጋሪያ ምረጥ በኦሮሞ ነጻነት ግንባር እና በመንግሥት መካከል የተፈጠረው አለመግባባት በኦሮሚያ ክልል ውስጥ ከፍተኛ ውጥረትን አንግሷል። ይህን ብቻ አይደለም በቅርቡ በክልሉ ውስጥ ለሚፈጸሙ ግድያዎች እና ዘረፋዎች መንግሥት ኦነግን ተጠያቂ ሲያደርግ ቆይቷል። በቅርቡ የክልሉ ፖሊስ እና ባለስልጣናት በምዕራብ ኦሮሚያ ውስጥ ኦነግን የአከባቢው አስተዳደሮችን ይገድላል፣ ጦር መሳሪያ ይዘርፋል እንዲሁም ሚሊሻዎችን ትጥቅ ያስፈታል ሲሉ ከሰዋል። ኩምሳ ዲሪባ ወይም በትግል ስሙ ጃል መሮ ተብሎ የሚታወቀው በምዕራብ ኦሮሚያ የሚንቀሳቀሰው የኦነግ ጦር አዛዥ ነው። ጃል መሮ በምዕራብ ኦሮሚያ በሚንቀሳቀሳው የኦነግ ሠራዊት ዘንድ ከፍተኛ ተጽእኖ ፈጣሪ እንደሆነ ይታመናል። ይህ ብቻም ሳይሆን አንዳንዶች ከሊቀመንበሩ ዳውድ ኢብሳ እዝ ነጻ ሆኖ በራሱ የሚንቀሳቀስ ቡድንን የሚመራ እንደሆነ ይነገርለታል። ቢቢሲም በምዕራብ ኦሮሚያ ስላለው ሁኔታ እና ከኦነግ ከፍተኛ አመራሮች ጋር ስላለው ግነኙነት ከጃል መሮ ቃለምልልስ አድርጓል። ቢቢሲ፡ በምዕራብ ኦሮሚያ የሚገኘው የኦነግ ጦር ተልዕኮው ምንድነው ጃል መሮ፡ ኦነግ የራሱ የሆነ ፍላጎት ወይም ተልዕኮ የለውም። ኦነግ የኦሮሞ ህዝብ ፍላጎትን ነው የሚያስጠብቀው። ጦሩም የኦነግን ተልዕኮ ነው የሚወጣው። ይሄው ነው። ቢቢሲ፡ የኦነግን ጦር ወደ ካምፕ በማስገባቱ ጉዳይ ላይ የእርስዎ አቋም ምንድነው ጃል መሮ፡ በቀላል ቋንቋ ላስረዳህ። በአንድ ቤተሰብ አባለት ውስጥ አባት፣ እናት እና ልጆች ይኖራሉ። በዚህ ቤተሰብ ውስጥ ወላጆች ማለትም እናት እና አባት እስካሉ ድረስ ቤተሰባዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ውሳኔ መስጠት የሚኖርባቸው እነርሱ ናቸው፤ ልጆች አይደሉም። የኦነግ ጦር ወደ ካምፕ ይግባ ወይም አይግባ በሚለው ላይም የኦነግ አጠቃላይ አመራሮች የሚወስኑትን ነው እኛ የምናስፈጽመው። ወደ ካምፕ እንገባለን ወይም አንገባም የሚለውን እኔ ልመልስ አልችልም። ኦዲፒ፡ ኦነግ እንደ አዲስ ጦር መልምሎ እያሰለጠነ ነው ቢቢሲ፡ በምዕራብ ኦሮሚያ የሚንቀሳቀሰው የኦነግ ጦር ከሊቀመንበሩ አቶ ዳውድ ኢብሳ ትዕዛዝ ውጪ ነው ይባላል። ከአቶ ዳውድ ቁጥጥር ውጪ ናችሁ ጃል መሮ፡ በምዕራብ ዞን የሚገኘውም ይሁን በሌሎች ዞኖች ውስጥ የሚገኘው የኦነግ ሥራዊት በሙሉ ተጠሪነቱ፣ የሚመራውም፣ ትዕዛዝ የሚቀበለውም ከኦነግ ሊቀመንበር ከአቶ ዳውድ ኢብሳ ነው። አቶ ዳውድ ኢብሳ የኦነግ ሊቀመንበር ናቸው። የኦነግ ጦር ደግሞ ካሉት የኦነግ ዘርፎች አንዱ ነው። ስለዚህ ተጠሪነቱም ለሊቀመንበሩ ነው። በአጭሩ ይሄው ነው። ከዚህ የተለየ ነገር የለም። በኢትዮጵያ ፖለቲካ የኦነግ ስም ቅመም ነው የኦነግ የፖለቲካ ጉዳይ ኃላፊ ቢቢሲ፡ በቅርቡ ከአቶ ዳውድ ኢብሳ ጋር በምዕራብ ኦሮሚያ ተገናኝታችሁ እንደተወያያችሁ ተሰምቷል። የውይይታችሁ ርዕሰ ጉዳይ ምን ነበር ጃል መሮ፡ አቶ ዳውድ ኢብሳ የኦነግ ሊቀመንበር እና የጦር የበላይ አዛዥ ናቸው። ከእሳቸው ጋር ብዙ ጉዳዮች ያገናኙናል። ብዙ ጉዳዮች ላይ እንወያያለን። ውይይታችንም አንዴ ወይም ሁለት ጊዜ አይደለም። በቋሚነት በተለያዩ ጉዳዮች ላይ እንወያያለን። ይህ አዲስ ነገር አይደለም። የተወያየንበትን ርዕሰ ጉዳይ ማወቅ ካሻህ ግን እሳቸውን ደውለህ ጠይቅ። ቢቢሲ፡ ሰሞኑን እርሶ ለኦነግ ወታደሮች ያስተላለፉት መልዕክት እንደሆነ የተነገረ ደምጽ በርካቶች በማሕበራዊ ሚዲያ ላይ ሲቀባበሉት ነበረ። ድምፁ የእርስዎ ነው ጃል መሮ፡ ስለ ጉዳዩ የማውቀው ጉዳይ የለም። እስቲ ነገረኝ፤ ምንድነው እሱ ቢቢሲ፡ በማሕበራዊ ሚዲያ ላይ በስፋት ሰዎች ሲጋሩት የነበረው ወደ ደቂቃ ርዝማኔ ያለው የእርስዎ ነው በተባለ ደምጽ፤ ትጥቅ ያስታጠቀንም ሆነ የሚያስፈታን የለም የሚል ይዘት ያለው መልዕክት ነው የተላለፈበት። ጃል መሮ፡ እንዲህ ባለ ጉዳይ ላይ ድምጽ ቀርጸን አናሰራጭም። ይህ የምትለው ድምጽ የት እንደተቀረጸ፣ ማን እንደቀረጸው እና እኔ መሆኔ መረጋገጥ አለበት። ቢቢሲ፡ የቤንሻንጉል ጉሙዝ አስተዳዳሪዎችም እንዲሁም በቅርቡ አቶ ለማ መገርሳ ለካማሼ ዞን አስተዳደሪዎች ግድያ ተጠያቂው የኦነግ ጦር ነው ብለዋል። በዚህ ላይ የእርስዎ አስተያየት ምነድነው ጃል መሮ፡ በዚህ አካባቢ የታጠቀ ኃይል በርካታ ነው። የታጠቀ የመንግሥት አካል፣ የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ታጣቂዎች እንዲሁም የኦነግ ታጣቂዎች በስፍራው ይንቀሳቀሳለሁ። ይህ ሁሉ ታጣቂ ቡድን ባለበት ኦነግ ላይ ብቻ ጣት መቀሰር አይቻልም፤ ትክክልም አይደለም። ገለልተኛ የሆነ አጣሪ አካል ወንጀሉን የፈጸመውን ማጣራት አለበት። ቢቢሲ፡የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ኦነግ በምዕራብ ኦሮሚያ የመንግሥት ሥርዓትን ይንዳል፣ ጦር መሳሪያዎችን ይዘርፋል የሚሉ በርካታ ክሶችን ይሰነዝራል። እርስዎ ምን ይላሉ ጃል መሮ፡ ከዚህ ቀደም ጦርነት ላይ ነበርን። ስንዋጋ ነበረ። የሚወጋንን ጦር አስተዳደራዊ ሥርዓቱን፣ ፖሊስን፣ ሚሊሻውን መበጣጠስ ደግሞ ግድ ነው። የተኩስ አቁም ስምምነቱን ከደረስን በኋላ ኦነግ በራሱ ተነሳሽነት መንግሥት ላይ ተኩስ ከፍቶ አያውቅም፤ አጸፋዊ እርምጃ ካልወሰድን በቀር። የኦነግ እና የመንግሥት እሰጣገባ ይህ ሁሉ ክስ ግን ሃሰተኛ ነው። መንግሥት ይህን ክስ የሚያቀርበው በዚህ አካባቢ ላይ ጦሩን በማዝመት ጦርነት ለመክፈት ቅድመ ዝግጅት ሲያከናውን ነው እንጂ ኦነግ ያፈረሰው የመንግሥት ሥርዓት የለም፤ የዘረፈውም የጦር መሳሪያ የለም። እንደውም የኦነግ ጦር ሥነ ምግባር በተሞላበት መልኩ ተቆጣጥሮ ከያዘው ስፍራ አልተንቀሳቀሰም። ቢቢሲ፡ በምዕራብ ኦሮሚያ ኦነግ ተቆጣጥሬያለሁ የሚለው መሬት የትኛውን ነው ጃል መሮ፡ እሱን የምዕራብ ኦሮሚያ ህዝብን መጠየቅ ትችላለህ። ቢቢሲ፡ ወደ ምዕራብ ኦሮሚያ ከተሰማራው የሃገር መከላከያ ጦር ጋር የተፈጠረውን ግጭት ይንገሩኝ እስቲ ጃል መሮ፡ የመጣብንን ጠላት መመከት እና ወደ መጣበት የመመለስ ችሎታውም ሆነ አቅሙ አለን። መስዋዕትነት ለመክፈልም ዝግጁ ነን። አሁንም ቢሆን የመጣብንን ኃይል እየተከላከልን እንገኛለን። በዚህ መካከል ግን ችግር ውስጥ እየገባ ያለው እና እየተሰቃየ ያለው የኦሮሞ ህዝብ ነው። የመንግሥት ጦር ውስጥም ያሉት ወታደሮች ህጻናት እና የደሃ እናት ልጆች ናቸው። ይህ ግጭት ግን ለሁለቱም ኦነግ እና መንግሥት ወገን የሚያስገኘው ጥቅም የለም። በዚያም ሆነ በዚህ እየተጎደ ያለው ኦሮሞው ነው። ቢቢሲ፡ ለዚህ መፍትሄው ምንድነው ጃል መሮ፡ የግል የፖለቲካ ጥቅምን ለማስጠበቅ ከማሴር ይልቅ የኦሮሞን ህዝብ ጥቅም ብናስቀድም፤ ይህ ሁሉ ችግር በአንድ ለሊት መፍትሄ ያገኛል። የግል የፖለቲካ ጥቅም ከህዝብ ፍላጎት ካስቀደምን ግን ለዚህ ችግር መቼም ቢሆን መፍትሄ አይገኝም። ቢቢሲ፡ በኦሮሚያ የተለያዩ ዞኖች ውስጥ ኦነግ ሰላማዊ ትግል ለማካሄደ ወደ ሃገር ውስጥ ከገባ በኋላ ጦር እንደ አዲስ በመመልመል እያሰለጠነ ይገኛል ይባላል። ይህ ምን ያህል እውነት ነው ጃል መሮ፡ የተኩስ አቁም ስምምነቱ ከታወጀ በኋላ የተካሄደ ምንም አይነት ስልጠና የለም። ቢቢሲ፡ ስለ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ ምን ያስባሉ ጃል መሮ፡ በዚህ ጉዳይ ላይ አስተያየት መስጠት አልፈልግም። ቢቢሲ፡ ባለፉት ጥቂት ወራት በርካታ ለውጦች መጥተዋል። እርስዎ የኦሮሞ ህዝብ ነጻነቱን አግኝቷል ብለው ያምናሉ ወይም ኦሮሞ ነጻነቱን የሚጎናጸፈው መቼ ነው ጃል መሮ፡ እኔ እንደ አንድ ግለሰብ ነጻነቴን አላገኘሁም። ህዝቡም የእራሱን መልስ መስጠት ይችላል። ተያያዥ ርዕሶች
በምዕራብ ኦሮሚያ የእርቅ ኮሚቴ አባላት ታፍነው ተወሰዱ
ፌብሩወሪ ማጋሪያ ምረጥ አጭር የምስል መግለጫ በቄለም ወለጋ ታፍነው ተወስደዋል የተባሉት የእርቅ ኮሚቴ አባላት መካከል ከቀኝ ወደ ግራ የሚታዩት ሁለቱ ግለሰቦች ይገኙበታል የኦሮሞ ነጻነት ግንባር እና በመንግሥትን መካከል የተደረሰውን ስምምነት ተከትሎ የግንባሩን ወታደሮች ለመቀበል ወደ ቄለም ወለጋ አቅንተው የነበሩ ከሦስት ያላነሱ የአስታራቂ ኮሚቴ አባላት ታፍነው መወሰዳቸው ተሰምቷል። የእርቅ ኮሚቴው ሰብሳቢ የሆኑት አባ ገዳ በየነ ሰንበቶ ለቢቢሲ እንዳረጋገጡት የኮሚቴው አባላት የሆኑ ሁለት አባ ገዳዎች እና አንዲት ሴት በቄለም ወለጋ አንፊሎ ተብሎ ከሚጠራ ስፍራ ታፍነው እንደተወሰዱ ተናግረዋል። አባ ገዳ በየነ ሰንበቶ ለማግባባት ወጣ እንዳሉ ነው ታፍነው የተወሰዱት፤ ክፉ ነገር እንደማይገጥማቸው እርግጠኛ ነኝ። ይህንም ችግር በቅርቡ እንፈታዋለን ሲሉ ለቢቢሲ ገልጸዋል። ብዙ ፈተናዎች እንደሚኖሩን እየወቅን ነው እርቅ ወደማውረዱ የገባነው። እርቅ ለማምጣት ነው እየሰራን ያለነው። ሰላምም ይሰፍናል። የሚያጋጥሙን ችግሮች ወደ ኋላ አያሰቀሩንም ሲሉም ጥረታቸውን በዚህ ምክንያት እንደማያቋርጡም ተናግረዋል። ከዚሁ ጉዳይ ጋር በተያያዘ አነጋግረነው የነበረው የኮሚቴው ፀሃፊ ጀዋር መሃመድም የእርቅ ኮሚቴ አባላት ችግር እየገጠማቸው እንደሆነ ተናግሯል። የገጠመ ችግር አለ። በተለያዩ ስፍራዎች የሚገኙ ከኮሚቴው አባላት ጋር ውይይት ከተደረገ በኋላ ለህዝቡ መግለጫ እንሰጣለን ሲል ጀዋር ገልጿል። ጀዋር ሃሙስ ምሽት ላይ በፌስቡክ ገጹ ላይ ታፍነው ተወስደዋል ያላቸውን አራት ሰዎች ከስም ዝርዝራቸው ጋር አውጥቷል። ታፍነዋል ተወስደዋል የተባሉት ሰዎች የት እንዳሉ ምንም አይነት መረጃ እንደሌላቸው ተናግሯል። በተመሳሳይ መልኩ በምዕራብ ወለጋ መነ ሲቡ ወረዳ የቴክኒክ አባላቱ ድብደባ እንደተፈጸመባቸው ከነዋሪዎች ሰምተናል። ተፈጸሟል ስለተባለው ድብደባ ግን ከቴክኒክ ኮሚቴው አባላት ማረጋገጥ አልተቻለም። የእርቅ ኮሚቴ አባላቱን ማን አፈናቸው የቴክኒክ ኮሚቴ ሊቀመንበር የሆኑት አባ ገዳ በየነ ሰንበቶም ሆኑ የኮሚቴው ፀሃፊ ጀዋር መሃመድ የእርቅ ኮሚቴውን አባላት ያፈነው ኃይል ይህ ነው በማለት በስም ከመጥቀስ ተቆጥበዋል። ጀዋር የአባላቱን መታፈን ይፍ ባደረገበት ጽሁፍ እየደረሰብን ያለውን ስቃይ ሁሉ በሆዳችን ይዘን እየሄድን ነው። አሁን ግን የህይወት ጉዳይ ስለሆነ መናገር አለብን። አባ ገዳዎች፣ እናቶች እና የሃገር ሽማግሌዎች ለሃገር ሰላም እና እርቅ ለማውረድ ነው የሚደክሙት እንጂ ምንም በደል አልፈጸሙም። በአስቸኳይ እንዲለቀቁን እንጠይቃለን ሲል በፌድቡክ ገጹ ላይ አስፍሯል።
ያለታካሚዎች ፈቃድ ቀዶ ህክምና ያደረገው የማህጸን ሀኪም ተከሰሰ
ኖቬምበር አጭር የምስል መግለጫ ሀኪሙ ታካሚዎቹ የማያስፈልጋቸውን ቀዶ ህክምና ያለ ፈቃዳቸው አድርጓል ተብሏል ታካሚዎቹ የማያስፈልጋቸውን ቀዶ ህክምና ያለ ፈቃዳቸው አድርጓል የተባለ የማህጸን ሀኪም ቨርጂንያ ውስጥ ተከሰሰ። ዶ ር ጃቪድ ፐርዌዝ የተባለው ሀኪም፤ ህመም የሌለባቸው ሴቶችን ታማችኋል በማለት ከፍተኛ ጉዳት እንዳደረሰ የአሜሪካው የምርመራ ተቋም ኤፍቢአይ አሳውቋል። ሀኪሙ ባለፈው ጥቅምት በቁጥጥር ሥር ከዋለ በኋላ ከ በላይ ሴቶች ጉዳት አድርሶብናል ብለዋል። የ ዓመቱ ሀኪም ሀሰተኛ መረጃ በመስጠትና በማጭበርበር ክስ ተመስርቶበታል። የጡት ካንሰር የያዛት የጡት ካንሰር ሀኪም ኤፍቢአይ እንዳለው፤ ቨርጂንያ ውስጥ ሁለት ቢሮ ያለውና በሌሎች ሁለት ሆስፒታሎች የሚሠራው ሀኪሙ፤ ከታካሚዎች እውቅናና ፈቃድ ውጪ ቀዶ ህክምና ያደርግ ነበር። እንደ ጎርጎሮሳውያ አቆጣጠር ከ እስከ ድረስ፤ በመንግሥት ድጋፍ ህክምና ካደረጉ ሴቶች በ በመቶ ያህሉ ያለ ፈቃዳቸው ቀዶ ጥገና አድርጓል። ከ ታካሚዎቹ፣ በመቶው ቢያንስ ሁለት ጊዜ ቀዶ ህክምና ተደርጎባቸዋል። ኤፍቢአይ ስለ ሀኪሙ መረጃ ያገኘው ላይ ነበር። ከሀኪሙ ጋር በአንድ ሆስፒታል የሚሠራ ግለሰብ ጉዳዩን ከታካሚዎች ከሰማ በኋላ ለኤፍቢአይ ጠቁሟል። አንዲት ሴት ሀኪሙ በማህጸኗ ባደረገው ቀዶ ህክምና ሳቢያ መጸነስ እንደማትችል መግለጿን ኤፍቢአይ አስታውቋል። የኤፍቢአይ መርማሪ ዴዝሬ ማክስዌል እንዳሉት፤ ሀኪሙ ታካሚዎች ካንሰር እንደያዛቸው በማሳመን ቀዶ ህክምና ያደርግም ነበር። የሀኪሙ ጠበቃ ሊውረንስ ዉድዋርድ ከቢቢሲ ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ አልሰጡም። ዶ ር ጃቪድ ፐርዌዝ ፓኪስታን ውስጥ ህክምና አጥንቶ በአሜሪካ፣ ቨርጂንያ የሥራ ፈቃድ አግኝቷል። ከዚህ ቀደምም አላስፈላጊ ቀዶ ህክምናዎች በማድረግ ቨርጂንያ ውስጥ ምርመራ ሲደረግበት ነበር። ላይ ግብር በማጭበርበር ለሁለት ዓመት ከሥራ ታግዶም ነበር። ተያያዥ ርዕሶች
ከባድ ዝናብና የጎርፍ አደጋ በአንዳንድ አካባቢዎች ጉዳት አስከተለ
ኤፕረል ማጋሪያ ምረጥ ባለፉት ጥቂት ሳምንታት በደቡብ፣ በደቡብ ምሥራቅና በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ የጣለውን ከባድ ዝናብ ተከትሎ የጎርፍ አደጋ ተከስቷል። በዚህም በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት ከመድረሱ ባሻገር መንገዶች በመዘጋታቸው በአካባቢዎቹ የሚገኙ ነዋሪዎች ለችግር መጋለጣቸውን ይናገራሉ። አሁን እየጣለ ያለው ዝናብ ለእርሻና ለተለያዩ ተግባራት የሚጠቀምና የተጠበቀ ቢሆንም መጠኑ ከፍተኛ በመሆኑ ግን የተለያዩ ጉዳቶችን እያስከተለ መሆኑን የሚናገሩት የጉጂ ዞን የአደጋ ስጋት አመራር ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ አበበ አባቡልጋ ናቸው። ይህንን ዝናብ ተከትሎ በተለያዩ የኢትዮጵያ ደቡብና ደቡብ ምዕራብ አካባቢዎች መንገዶች የመቆረጥ፣ ፀረ ሰብል ተባዮች መከሰት፣ በንብረት ላይ ጥፋት መድረስና የመሳሰሉ ጉዳቶች ተከስተዋል ይላሉ አቶ አበበ። የሚጥለውን ከባድ ዝናብ ተከትሎ ጎርፍ ጉዳት ካደረሰባቸው አካባቢዎች መካከል አንዱ በሆነው በባሌ ዞን መደ ወላቡ ወረዳ ነዋሪ የሆኑት አቶ አህመድ ጁንዳ እንደሚሉት አደጋው የተከሰተው በዝናቡ ምክንያት ብቻ ሳይሆን በመሰረተ ልማት ጉድለት ጭምር እንደሆነ ይጠቅሳሉ። በፌደራል የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን የአቅርቦትና ሎጂስቲክስ ዳይሬክተር የሆኑት አቶ አይድሮስ ሃሰን እንደሚሉት መንግሥት ለአደጋ ተጋላጭ በሆኑ ቦታዎች ላይ አስፈላጊው ዝግጅት መደረጉን፤ ነገር ግን ከጎርፍ አደጋ ጋር በተያያዘ ከሶማሌ ክልል ውጪ ከሌሎች ቦታዎች ምንም ሪፖርት እንዳለቀረበ ይናገራሉ። የሚደርሱ አደጋዎችን ለመቋቋም በአንዳንድ አካባቢዎች ቀደም ተብሎ አስፈላጊ የሆኑ ድጋፎችን የማቅረብ ሥራ እንደተከናወነ የሚናገሩት አቶ አይድሮስ በዚህ መሰረትም በቅርበት ድጋፍ የሚሰጥ ሲሆን፤ ከዚያ በላይ ከሆነ ደግሞ በሚቀርብ ጥያቄ መሰረት ከፌደራል መንግሥቱ አስቸኳይ ምላሽ ይሰጣል። ጨምረውም ከኦሮሚያ ክልል ከጎርፍ አደጋ ጋር ተያይዞ የቀረበ ጥያቄ እንደሌለ ነገር ግን በሶማሌ ክልል አፍዴርና በሌሎች በተወሰኑ ወረዳዎች ላይ የጎርፍ አደጋ እንደነበርና መንግሥት አስፈላጊውን ምላሽ እየሰጠ መሆኑን ተናግረዋል። ከዚህ ጋር ተያይዞም የብሔራዊ ሜትሮሎጂ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ፈጠነ ተሾመ እንደሚናገሩት አሁን አደጋው በደረሰባቸው አካባቢዎች ከመደበኛው በላይ የሚሆን ዝናብ ሊጥል እንደሚችል ተተንብዮ ነበር ሲሉ አስታውሰዋል። ተያያዥ ርዕሶች
የግንቦት ታሪካዊነት አጠያያቂ አይደለም ፕሮፌሰር ገብሩ ታረቀ
ግንቦት ይህንን ለማጋራት በ ዋትስአፕ ግንቦት እንደዘንድሮ አከራካሪ የሆነበት ጊዜ ያለ አይመስልም። በዓሉ አምባገነኑ የደርግ ሥርዓት የተወገደበትና ኢትዮጵያ ወደዲሞክራሲ ሥርዓት የተሸጋገረችበት ዕለት በመሆኑ በድምቀት መከበሩ መቀጠል አለበት የሚሉት እንዳሉ ሁሉ፤ ይህ ቀን ወንድም ወንድሙን ገድሎ ሥልጣን የያዘበት ዕለት ነው፤ ወደሥልጣን የመጣውም ሌላ አምባገነን ሆኖ እንዴት ክብረ በዓል ይሆናል የሚሉም አሉ። በሰሜን አሜሪካ የትግራይ ተወላጆች ማኅበር ፕሬዝዳንት አቶ አሉላ ሰለሞን በዓሉን ማክበር አለብን ከሚሉት ወገን ናቸው። ምክንያታቸውን ሲጠቅሱም የነበረው የእርስ በእርስ ጦርነት አብቅቶ የኢትዮጵያ ሕዝብ ወደ ሰላም የተሻጋገረበት ነው ይላሉ። አክለውም ኢትዮጵያ እንደ አገር ወደአዲስ ፖለቲካዊ ምዕራፍ የተሸጋገረችበት ነው የሚለውን አብዛኛው ሰው ይስማማበታል። ተከትሎ በመጣው ፖለቲካዊ ሥርዓት ስምምነት ባይኖርም መሠረታዊ በሆኑ እውነታዎች መለያየት የሚቻል አይመስለኝም በማለት ያለው የፖለቲካ ልዩነት እንደተጠበቀ ሆኖ፤ ቀኑ መከበር አለበት ይላሉ። አቶ አሉላ በዓሉ መከበር የለበትም የሚሉ ወገኖችንም ሀሳብ አከብራለሁ ያሉ ሲሆን፤ ሁሉም በግንቦት ድል ደስተኛ እንደማይሆን አንደሚረዱም ሳይጠቅሱ አላለፉም። በአገሪቱ የፕሬስ ነፃነት ባልነበረበት ወቅት በግንቦት የተገኘው ድል ለፕሬሱ ነፃነት የሰጠ ዕለት መሆኑንም ይጠቅሳሉ። በሂደት ፕሬሱም ሆነ ዲሞክራሲው ማደግ በነበረበት መጠን አላደገም የሚለው ሌላ መነጋገሪያ ርዕስ ሆኖ የሚቆይ ነው የሚሉት አቶ አሉላ፤ በታሪክ ግን ነፃ ፕሬስ በኢትዮጵያ ውስጥ የመጣበት መሆኑ እንደማይካድ ይጠቅሳሉ። ጋዜጠኛና በፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ የሚጽፉት አቶ ደጀኔ ተሰማ በበኩላቸው፤ ግንቦት አምባገነን መንግሥት ተገርስሶ ሌላ አምባገነን መንግሥት ወደሥልጣን የመጣበት ቀን ቢሆንም በዚህኛው መንግሥት ለውጦች እንደመጡ እረዳለሁ ይላሉ። ደርግ መስከረም ብሎ ሲያከብረው በነበረው በዓል እና ኢህአዴግ ግንቦት ብሎ በሚያከብረው በዓል መካከል ምንም አይነት ልዩነት አይታየኝም የሚሉት አቶ ደጀኔ፤ ደርግ መሬት ላረሹ የሚለው የሕዝብ ጥያቄ መመለስ መቻሉን አስታውሰው፤ የግንቦት ድልን ተከትሎ የመጣ ለውጥ ቢኖርም የለውጡ ተጠቃሚ የሆኑት ድሉ የኛ ነው የሚሉት ወገኖች ናቸው ይላሉ። የቀድሞው ግንቦት አርበኞች ግንባር አመራር የነበሩት አቶ ኤፍሬም ማዴቦ ደግሞ በዓል የሚከበረው ለሕዝብ ነው፤ ሕዝብ ካላከበረው አልተቀበለውም ማለት ነው ስለዚህ መከበር የለበትም ባይ ናቸው። ትንሽ ልጅ እያለሁ መስከረም ይከበር ነበር የሚሉት አቶ ኤፍሬም፤ ይህ የፊውዳሉ ሥርዓት የተገረሰሰበት በዓል በመሆኑ ትልቅ በዓል ነበር ይላሉ። ሕወሐት ሥልጣን ሲይዝ ይህንን በዓል ማክበር አቁመን እነሱ የገቡበትን ቀን ማክበር ጀመርን በማለት፤ ኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት ያለፈችበትን ሁኔታ ማሳያ በመሆኑ የሚፈጥርብኝ ስሜት ጥሩ አይደለም ይላሉ። አቶ ኤፍሬም ኢትዮጵያ አሁን ካለችበት የለውጥ ሂደት ራሳቸውን አግልለው አሁንም የሚያስቡት ኢትዮጵያን ወደኋላ መመለስ ነው ይላሉ። አክለውም እነሱ የቆሙለትን ዓላማና አሁንም የሚታገሉለትን ዓላማ ስመለከት መከበር የለበትም እላለሁ በማለትም ሀሳባቸውን ይቋጫሉ። ፕሮፌሰር ገብሩ ታረቀ በበኩላቸው የ ዓመቱ ጦርነት የአንድ እናት ልጆች የተጋደሉበት፤ የተዋደቁበት ጦርነት ነው ይላሉ። በዓሉ መድፍ እየተተኮሰ መከበሩ ከመጀመሪያውም ደስ አላለኝም በማለት፤ ወደፊትም መከበር ካለበት እስከዛሬ ይከበር እንደነበረው መሆን የለበትም ሲሉ ምክራቸውን ይሰጣሉ። ፕሮፌሰር ገብሩ ግንቦት እንደ በዓል ባይቆጠርም ታሪካዊነቱ አጠያያቂ አይደለም ይላሉ። አቶ ደጀኔ በበኩላቸው ግንቦት ልንጠየፈውም ሆነ ልናወድሰው የሚገባ ቀን አይደለም የሚል ሃሳብ ይሰነዝራሉ። ቢቢሲ ማስተባበያ
የቱሪስት ማግኔት የሆነችው ቬኒስ ከተማን ጎርፍ እያስጨነቃት ነው
ኅዳር ይህንን ለማጋራት በ ዋትስአፕ በዓለም አቀፍ ደረጃ የቱሪስት ማግኔት አላት የምትባለው የጣልያኗ ቬኒስ ከተማ በጎርፍ እየተፈተነች ነው። ጎርፉ ቬኒስን በሚሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር አሳጥቷታል ተብሏል። በጎርፉ ምክንያት የውሃ መተላለፊያ የሆነው የከተማዋ ዋና አደባባይ ሴንት ማርክ ፣ትምህርት ቤቶችና ንግድ ቤቶች ተዘግተዋል። የጣልያን መንግስሥትም በዩኔስኮ ድረ ገፅ ላይ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጁን አስታውቋል። ጎርፍ ባጠቃቸው የምሥራቅ አፍሪካ አገራት ተጨማሪ ዝናብ ሊጥል ይችላል ተባለ ለውሃ እና ለስነ ህንፃዎቿ ጥበብ ቱሪስቶች የሚተሙላት ቬኒስን እያስጨነቀ ያለው ጎርፍ እርዝመት ማክሰኞ እለት ሴ ሜ ደርሶ ነበር ተብሏል። ቤታቸው በጎርፍ የተጎዳባቸው የቬኒስ ኗሪዎች እስከ አምስት ሺህ ዩሮ ሲያገኙ ንግድ ቤቶች ደግሞ ሺህ ዩሮ ድረስ ካሳ ይሰጣቸዋል ተብሏል። ከመቶ በላይ ከሚሆኑ ደሴቶች የተሰራችው ቬኒስ በየአመቱ በጎርፍ የምትጠቃ ሲሆን የአሁን እንደ አውሮፓውያኑ በ ተከስቶ ከነበረውና አስከፊ ከተባለው ጎርፍም የባሰ ነው ተብሏል። የጣልያን መንግሥት ለቬኒስ ሚሊዮን ዩሮ ድጋፍ እንደሚሰጥ ቃል ገብቷል።
የህፃናት አምባ ልጆች ማህበር የኮሎኔል መንግሥቱን ልደት ሊያከብር ነው
ሜይ ማጋሪያ ምረጥ የህፃናት አምባ ልጆች ማህበር የደርግ ሊቀመንበር ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለማሪያምን ልደትና የምስጋና ፕሮግራም በመጪው ሰኞ ሰኔ ቀን ዓ ም ሊያሰናዱ መሆናቸውን የማህበሩ ሰብሳቢ አቶ ጆኒ መርጊያ ለቢቢሲ ገለፀዋል። ከዚህ በፊት ልደታቸውን በይፋ አክብረን አናውቅም የሚሉት አቶ ጆኒ ዘንድሮ ለማክበር የማህበሩን አባላት ያነሳሳውን ጉዳይ ይገልፃሉ። ነገሩ ወዲህ ነው፤ ከወር በፊት አንድ በህፃናት አምባ ያደገና የማህበሩ አባል ኮሎኔሉን ለማግኘት እርሳቸው በስደት ወደ ሚኖሩበት ዚምባብዌ ለማቅናት ይነሳል። ግለሰቡ ስሙ እንዲጠቀስ ባይፈልግም አካሄዱ ግን እርሳቸውን ቃለ መጠይቅ ለማድረግ ነበር። የፍስሀ ተገኝ የቤተሰብ ፍለጋ ጉዞ ያሰበውም አልቀረ ታዲያ ወደ ዚምባብዌ ተሻገረ። ምንም እንኳን ኮሎኔሉን ለማግኘት ቁጥጥሩና ጥበቃው ጥብቅ ቢሆንም በወንድማቸውና እዚያው ዚምባብዌ በሚኖር አንድ የህፃናት አምባ ልጅ አማካኝነት ፈቃድ ማግኘት እንደቻሉ የማህበሩ ሰብሳቢ አቶ ጆኒ ይገልፃሉ። ታዲያ የማህበሩ አባላት ይህንን አጋጣሚ በመጠቀም ለእርሳቸው የሰላምታ ደብዳቤ ለመላክና በደብዳቤያቸው ላይም በትክክል የተወለዱበትን ቀን እንዲነግሯቸው ለመጠየቅ አሰበ። አቶ ጆኒ የልደት ቀናቸውን የጠየቁበትን ምክንያታቸውን ሲያስረዱም የኮሎኔሉ የልደት ቀንና ከአገር የወጡበት ቀን ተመሣሣይ ነው፤ እርሱም ግንቦት ቀን ነው የሚሉ መረጃዎች ይወጡ ስለነበር ትክክለኛ የልደት ቀናቸውን ለማወቅ ነው ብለዋል። ልደታቸውን ስናከብር እናስታውሳቸዋለን ብለን እንጂ ለምርምር ፈልገነው አይደለም ሲሉም ያክላሉ። የማህበሩ ኮሚቴ ለኮሎኔሉ የፃፉት ደብዳቤ ምንም ዓይነት ፖለቲካዊ ይዘት የለውም የሚሉት አቶ ጆኒ ደብዳቤው ልጅ ለአባቱ የሚፅፈው ዓይነት እንደሆነ አስረድተዋል። ጓድ መንግሥቱ እንባ የተናነቃቸው ለት በመሆኑም ደብዳቤው ስለ ደህንነታቸውና ስለ ልጆቻቸው ሁኔታ የጠየቁበት፣ ቤተሰባዊ ሰላምታ ያቀረቡበትና የልደት ቀናቸውን የጠየቁበት እንደሆነ ይናገራሉ። አቶ ጆኒ እንደገለፁልን ከደብዳቤው ጋር ባህላዊ የአልጋ ልብስ፣ ግድግዳ ላይ የሚሰቀል የመስቀል ቅርፅ ያለበት ጌጥ እና ለባለቤታቸው ውብአንች ቢሻውና ለእርሳቸው የሚሆን ባህላዊ ፎጣ ስጦታም ልከውላቸዋል። እርሳቸውም እንደ አባት ምላሻቸውን እንደላኩላቸው አቶ ጆኒ ነግረውናል። በምላሹ በላኩላቸው ደብዳቤ ላይም በጥሩ ጤንነት ላይ እንዳሉ፣ የተጋነነ የጤንነት ችግር እንደሌለባቸው፣ በልጆቻቸው እንደተባረኩ፣ አምስት የልጅ ልጆች እንዳዩ፣ ሁል ጊዜ ስለ ሃገራቸው እንደሚያስቡና ሃገራቸውን እንደሚናፍቁ የሚገልፅ አጭር ደብዳቤ ፅፈውላቸዋል። በደብዳቤው መጨረሻ ላይም የተወለድኩት፡ በአዲስ አበባ ፡ እንደኢትዮጵያ፡ አቆጣጠር፡ በ ዓ ም፡ ግንቦት አስራዘጠኝ ቀን፡ነው። ሲሉ በደብዳቤያቸው ላይ እንዳሰፈሩ አቶ ጆኒ ገልፀዋል። አጭር የምስል መግለጫ ከኮሎኔል መንግሥቱ የተላከላቸው ደብዳቤ ማህበሩ ቢሮ እንዳለውና እንደሌለው በመጠየቅም ቢሯቸው ላይ የሚያስቀምጡት የአፍሪካ ካርታ ያለበት ሰዓት ከደብዳቤያቸው ጋር ልከዋል። ይህ ብቻም ሳይሆን የእርሳቸው ፊርማ ያረፈበት፣ ለህፃናት አምባ ልጆች ፤ መልካም ንባብ የሚል ፅሁፍ ያለበት የመጀመሪያ መፅሃፋቸውን አክለዋል። በዋነኛነት እንደ ልጆች የሚሰሙን ነገሮች አሉ፤ በእርሳቸው ጊዜ በነበረው ሥርዓት ያልተገቡ ነገሮች ተከናውነዋል፤ ነገር ግን በዘመኑ በጣም ጥሩ ሥራዎችንም ሰርተዋል የሚሉት አቶ ጆኒ ባለፈው ሥርዓት በአጠቃላይ ደርግ በሚል መንፈስ የእርሳቸው ሥራ መጥፎነት ነው የተሳለው ይላሉ። በመሆኑም የህፃናት አምባ ልጆች ማህበር እርሳቸው በዘመኑ ከሰሯቸው በጎ ሥራዎች መካካል አንዱ የህፃናት አምባን ማቋቋም መሆኑን በመጥቀስንና መሰል ሥራዎችን በማንሳት የልደትና የምስጋና ፕሮግራም ለማዘጋጀት አስቧል። ከማደጎ ልጅነት ወደ እውቅ ገጣሚና የማንችስተር ዩኒቨርሲቲ ሃላፊነት ግንቦት ዓ ም የተወሰኑ የህፃናት አምባ ልጆች በግል በነበራቸው የመዝናኛ ፕሮግራም ላይ የኮሎኔሉን ልደት ያካበሩ ቢሆንም ዋናው ማህበር በመጭው ሰኞ ሰኔ ቀን ዓ ም ፕሮግራሙን ለማካሄድ እንዳቀደ አቶ ጆኒ መርጊያ ነግረውናል። በፕሮግራሙ ላይ እንደማንኛውም ልደት ኬክም ዳቦም ይኖራል፤ በዘመኑ የነበሩ ሰዎችንና ሌሎች እንግዶችን ጋብዘን ሞቅ አድርገን ለማክበር ነው ያሰብነው ብለዋል። ፕሮግራሙ የሚካሄድበትን ሰዓትና ቦታ ጊዜው ሲቃረብ እንደሚገልፁ ተናግረዋል። በአጠቃላይ በህፃናት አምባ ያደጉ ልጆች ቁጥራቸው ከ ሺህ በላይ ሲሆኑ አዲስ አበባ የሚገኙና የማህበሩ አባል የሆኑ ልጆች ቁጥር ስድስት መቶ እንደሚሆን የማህበሩ ሰብሳቢ አቶ ጆኒ ለቢቢሲ ገልፀዋል። የህፃናት አምባ በቀድሞ አጠራር በሸዋ ክፍለ ሃገር ሀይቆችና ቡታጂራ አውራጃ፤ አላጌ በሚባል አካባቢ የተቋቋመ ሲሆን ወላጆቻቸውን በጦርነትና በሌሎች ምክንያቶች ያጡ ህጻናትን ተቀብሎ የማሳደግ ዓላማ ነበረው። ህፃናት አምባው ሰብለ አብዮት ፣ መስከረም ሁለት፣ ኦጋዴን፣ ዘርዓይ ደረስ እና መንግሥቱ ኃይለማሪያም የተባሉ መንደሮችም ነበሩት። ተያያዥ ርዕሶች
ከሰላሳ በላይ የጴንጤ ቆስጣል አማኞች አሥመራ ውስጥ ታሰሩ
ሜይ ማጋሪያ ምረጥ ከሰላሳ የሚበልጡ የጴንጤ ቆስጣል እምነት ተከታዮች አሥመራ በደኅንነት ባለስልጣናት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ተቀማጭነቱን ለንደን ያደረገው ሪሊዝ ኤርትራ የተባለው የሃይማኖቶች መብት ተከራካሪ ቡድን ለቢቢሲ አስታወቀ። የእምነቱ ተከታዮች የተያዙት በሦስት የተለያዩ ቦታዎች በአምልኮ ላይ ሳሉ ተከብበው እንደሆነ የድርጅቱ ተወካይ ዶ ር ብርሃነ አስመላሽ ገልፀዋል። ኤርትራ የሃይማኖት እሥረኞችን ፈታች ከጥቂት ሳምንታት በፊትም የሚሆኑ ግለሰቦች በፀጥታ ኃይሎች ተይዘው የነበረ ሲሆን፤ ከመካከላቸው ሃምሳዎቹ እንደተለቀቁ ገልፀዋል። ቢቢሲ በጉዳዩ ላይ ከኤርትራ መንግሥት ምላሽ ለማግኘት ቢሞክርም አልተሳካም። የኤርትራ መንግሥት የጴንጤ ቆስጣል እምነትን ያገደው በፈረንጆቹ ከ ጀምሮ ነው። የሰብአዊ መብት ተሟጋች ቡድኖች እንደሚሉት የኤርትራ መንግሥትን እገዳ በተጣለባቸው የሃይማኖች መሪዎችንና የእምነቶቹ ተከታዮች ላይ ጭቆናና እስርን ጨምሮ መጠነ ሰፊ ተቋማዊ የመብት ጥሰቶችን እንደሚፈጽም ይከሳሉ። ወደ አሥመራ ለመጓዝ ማወቅ የሚገባዎ ነጥቦች ኤርትራ አብያተ ክርስቲያናትን መዝጋትና የእምነቶቹ ተከታዮችን ማሰር ከጀመረች አንስቶ በየዓመቱ ለንደን ከሚገኘው የኤርትራ ኤምባሲ ፊት ለፊት በመሆን በመንግሥት ላይ ተቃውሟቸውን እንደሚያሰሙ የሚናገሩት የሪሊዝ ኤርትራ ዳይሬክተር ዶክተር ብርሃነ ባለፈው ሳምንት ተመሳሳይ ነገር ማድረጋቸውን ለቢቢሲ ገልጸዋል። ጨምረውም ባለፈው ሳምንት የሪሊዝ ኤርትራ፣ የኤርትራ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን፣ የ ቸርች ኢን ቼይንስ እና ክርስትያን ሶሊዳሪቲ ዎርልድ ዋይድ አባላት በቦታው ተገኝተው የኤርትራ መንግሥት የሃይማኖት መብት እንዲያከብር የሚጠይቅ ደብዳቤ ለኤምባሲው እንዳስረከቡ ተናገረዋል። ተያያዥ ርዕሶች
ደቡብ ኮሪያዊው ፓስተር አማኞችን አስገድዶ በመድፈር ወንጀል ታሰሩ
ኖቬምበር አንድ ደቡብ ኮሪያዊ ፓስተር ስምንት የቤተክርስቲያኑ አማኞችን አስገድዶ በመድፈር ወንጀል ተከሰው ዓመት ተፈረደባቸው። ሊ ጃኢ ሮክ የተባሉት የ ዓመት ማሚን ሴንትራል ቸርች የተሰኘ ቤተክርስቲያን አገልጋይ ሺ ተከታዮች ያሏቸው ሲሆን፤ የቀረበባቸውን ክስ አልፈጸምኩም በማለት ሲከራከሩ ነበር። ተጎጂዎቹ ሴቶች ፓስተር ሊ ቅዱስ መንፈስ በእኔ ውስጥ አለ ስለሚሉን የታዘዝነውን ነገር ሁሉ እንፈጽም ነበር ብለዋል፤ አምላክ እኔ ነኝ ይሉም ነበር ብለዋል። አብዛኛዎቹ ደቡብ ኮሪያውያን በትልልቅና ብዙ ገንዘብ እንዲሁም ተጽዕኖ መፍጠር በሚችሉ ቤተክርስቲያኖች ውስጥ ይጠቃለላሉ። ነገር ግን እዚም እዚያም ከዋናዎቹ ቤተክርሰቲያኖች ተገንጥለው የራሳቸውን አገልግሎት የሚሰጡ ቤተክርስቲያኖችም አሉ። አብዛኛዎቹ ተገንጣይ ቤተክርስቲያኖች ደግሞ በማጭበርበርና ገንዘብ በመሰብሰብ ላይ ያተኮሩ ናቸው። የፓስተር ሊ ቤተክርስቲያንም ከእነዚህ መካከል አንዱ ነው ተብሏል። ቤተክርስቲያኑ እ አ አ በ ሲሆን የተቋቋመው፤ በመጀመሪያ አባላት ብቻ ነበሩት። በአሁኑ ሰአት ግን በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ተከታዮች ያሉት ሲሆን፤ የራሱ ዋና መስሪያ ቤትና ታዋቂ የበይነ መረብ ፈውስ አገልግሎት መስጫም አለው። አነጋጋሪው የአስገድዶ መድፈር ጉዳይ ለህዝብ ጆሮ መድረስ የጀመረው ባለፈው ዓመት አንዳንድ ሴቶች ፓስተሩ ወደ መኖሪያ ቤታቸው እንዲመጡ እየጠየቁ ግብረ ስጋ ግንኙነት ከእሳቸው ጋር ካልፈጸሙ እንደማይፈወሱ እንደተነገራቸው ይፋ ሲያደርጉ ነው። እሳቸውን እምቢ ማለት ከባድ ነው። እሳቸው ማለት ንጉስ ናቸው። እንደ አምላክም ናቸው። ከልጅነቴ ጀምሮ የቤተክርስያኑ ተከታይ ነበርኩ ብላለች አንዲት ሴት። ተመሳሳይ ጥቃት ደርሶብናል ያሉ ስምንት ሴቶች ጉዳዩን ለፍርድ ቤት አቀረቡ። ባለፈው ግንቦት ወር ላይም ፓስተሩ በቁጥጥር ስር ዋሉ። የፍርድ ውሳኔው በዋናው ዳኛ ሲነበብ ፓስተር ሊ አይናቸውን ጨፍነው ነበር ተብሏል። እስከ መጨረሻው ውሳኔ ድረስም ሴቶቹ ያልተገባ ባህሪ በማሳየታቸው ከቤተክርስቲያኑ የተወገዱ ናቸው በማለት ሲከራከሩ ነበር፤ ፓስተሩ። ተያያዥ ርዕሶች
ተዓምራዊቷ ቅድስት ማርያም ውቕሮ ገዳም
ኦክተውበር አጭር የምስል መግለጫ የቅድስት ማርያም ውቕሮ ገዳም፤ ትግራይ የትግራይ ምድር አቅፎ ከያዛችው ከ በላይ የሆኑት ከአለት ተፈልፍለው የታነፁት አብያተ ክርስትያን ለዛሬ አንዱን እናስተዋውቃችሁ። ቅድስት ማርያም ውቕሮ ትባላለች። ወደ አካባቢው ለመድረስ በጣም አስቸጋሪ የጠጠር መንገድና ወንዝ መሻገር የግድ ነው። መኪናችን ወንዙን መሻገር አቅቷት ስትንገዳገድ የተመለከቱት የአከባቢው አርሶ አደሮች ተጠራርተው መንገዱን አስተካክለው አሻግረውናል። ወደ ገዳሙ ቅጥር ግቢ ከተገባ በኋላ መጀመርያ ከአለት የተሰራው ሙዳዬ ምጽዋት ይገኛል። የገዳሙ አስተዳዳሪ ቄስ ዘሚካኤል ወልደጊዮርጊስ ሙዳዬ ምጽዋቱን ከማለፋችን በፊት ጫማችንን እንድናወልቅ ቀጭን ትዕዛዝ አስተላለፉ። በሰንሰለት ዙርያ ጥምጥም የተቆለፈው የገዳሙን በር ከፍተው አስገቡን። የበሩ መዝጊያ ከአንድ የዛፍ እንጨት ብቻ እንደተዘጋጀ ለመረዳት አይከብድም። ቄስ ዘሚካኤል፤ ገዳሟ መቼና እንዴት እንደተቆረቆረች ይናገራሉ። ይህች ገዳም ንግሥት ማርያም በ ጐንደር ላይ ሆነው በህልም ተገልፆላቸው ነበር የታነፀው። ደግሞ የሰው ልጅ በዶማ ቆፍሮ ነው ያነፀው በሉና እመኑ ሲሉ አፌዙብን። ብታምኑም ባታምኑም አብ ሃነጸ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ራሱ መንፈስ ቅዱስ ነው ያነፃት ብለን ነው የምናምነው ይላሉ። ገዳሟ ውስጥ የአንድ ትልቅ የጥድ ዛፍ ቁመት ያላቸው ዓምዶች ይገኛሉ። በሌሎች ገዳማትና አድባራት እንደሚደረገው ሁሉ በቅድስት ማርያምም ወንዶችና ሴቶች ተለያይተው ነው የሚቀመጡት። በጣሪያው ላይ ሦስት እምነ አድማስ ነበሩ። አንደኛው ወድቆ እንድያውም ጣልያን ለመውሰድ ሞክሮ አልተሳካለትም። ሁለቱ እስከ አሁን ድረስ አሉ። ድንጋዩ ላይ በእብራይስጥ ቋንቋ የተፃፈ ፅሑፍም ይታያል። እምነ አድማስ ድንጋይን ለመቁረጥና ለመጥረብ ኃይል የተሰጠው የድንጋይ ዘር ነው። ገዳሟ ውስጥ ከሚታወቅ ይልቅ የማይታወቀው ስለሚበዛ ቄስ ዘሚካኤል ያስታወሱትንና የነገሩንን ብቻ አሳጥሬ ልንገራችሁ። በአንድ የገዳሟ ጓዳ ውስጥ ልጅ መውለድ የዘገየባችው እንስቶች ተቀምጠው ፈጣርያቸውን የሚለምኑበት ከአለቱ ተፈልፍሎ የተዘጋጀ ወንበር ይታያል። ከፊት ለፊቱ ደግሞ መባ የሚያስቅምጡበት መደርደርያ አለ። በአንደኛው የገዳሟ ክፍል የቅድስት ማርያም መንበረ ታቦት አለ። መንበረ ታቦቱ ራሱ ሙሉ ለሙሉ ከአለት ተፈልፍሎ ነው የተሰራው። ከመንበረ ታቦቱ አናት ላይ ጉልላት ይታያል። ወደ መንበረ ታቦቱ ከካህንና ከዲያቆን ውጪ ምዕመን እንዲገባ አይፈቀድለትም። ገዳሟ ውስጥ የሚገኘው የጨለመው በር ፈለገ ኦር ይባላል። ሊቃውንቱ ጉድጓዱ ቀጥ አድርጐ እስራኤል ነው የሚያስገባው ብለው ያምናሉ። ድሮ ነው አሉ ካህናት ማሾና ጧፍ ይዘው ገብተው በዛው አልተመለሱም ብለውናል። መሪጌታ ቁጭ ብሎ ወደ ታቦቱ እያየ የሚጸልይበት ዙፋንም ተቀርጾ ይታያል። ዙፋኑ ከላይ ዘውድ አለበት፤ ይህም ከአለት ተፈልፍሎ ነው የተዘጋጀው። ገዳሟ ውስጥ የተለያየ ትርጉም ሊሰጣቸው የሚገቡ ጉልላት አሉ፤ የኮከቦች ተምሳሌት ብለው የሚጠሩዋቸው ቅርፆችም አሉ። የገዳሟ የበር መዝጊያዎች ከእየሩሳሌም በቀስተ ደመና ተጠፍረው እንደመጡ ይነገራል። ገዳሟ በር የሌላቸው መስኮቶችም አሉት። ልክ እንደ መንበረ ታቦቱ ከካህንና ዲያቆን ውጪ ሌላው ምዕመን የማይገባበት ቤተልሔምም አለ። በአንድ ትልቅ አለት ላይ ሆኖ ከቅድስት ማርያም በተጨማሪ የቅዱስ ጊዮርጊስ ገዳም አለ። ገዳሟ መወጣጫ አልነበራትም። በቅርቡ አንድ ምግባረ ሰናይ ግለሰብ ከብረት የተዘጋጀ መሰላል አሰርቶላታል። አጭር የምስል መግለጫ ወደ ቅዱስ ጊዮርጊስ ገዳም የሚያስወጣ መሰላል የቅዱስ ጊዮርጊስ ገዳም መስኮተ አብርሃምን ጨምሮ መስኮቶች አሉዋት። በመስኮተ አብርሃም በኩል አሻግሮ የቅድስት ማሪያም መንበረ ታቦትን ማየት ይቻላል። ሁለቱ ገዳማት ተአምራዊ የጥበብ ሥራ እንዳረፈባቸው ፍንትው ብሎ ይታያል። እነኝህን ታሪካዊ ገዳማት በእንግዶች እንዳይጐበኙ ወደ አከባቢው የሚወስደው የመኪና መንገድ አይመችም። ሌላው ቀርቶ ወንዙን በቀላሉ ለመሻገር እንኳን ድልድይ አልተሰራለትም። የወረዳው አስተዳደር ድልድዩን ለመስራት ሽርጉድ ሲል ተመልክተናል። ትግራይ ምድር ውስጥ የሚገኙት አብዛሃኛዎቹ ገዳማት በየተራራውና ሸንተረሩ ስለሚገኙ መሰረተ ልማት ካልተሟላላቸው በእንግዶች ሊጐበኙ አይችሉም። መንግሥት በዚህ ዙርያ ብዙ መስራት ይጠበቅበታል። ሌላው ቀርቶ ገዳማቱን ለማየት የሚሄዱት እንግዶች የሚያርፉበት መጠለያ እንኳን የላቸውም። ባለሃብቶችም መዋዕለ ንዋያቸውን በዚሁ ዙርያ እንድያውሉ ማበረታትና ሁኔታውን ማመቻቸት ይጠበቃል። ገደማቱም ጥገናና እንክብካቤ ይሻሉ። ከዚህ ውጭ የቅድስት ማሪያም ውቕሮ ተአምራዊ ናት ከማለት ባለፈ የተሰነደ ማስረጃ እንኳን የላትም። ተያያዥ ርዕሶች
የኖርዌይ ፓስፖርቴን መልሼ ኢትዮጵያዊ መሆን እችላለሁ አቶ ሌንጮ ለታ
ኅዳር ይህንን ለማጋራት በ ትዊተር ይህንን ለማጋራት በ ዋትስአፕ በኢትዮጵያ ፖለቲካ የለውጥ መንፈሱን ተከትሎ መንግሥት ባደረገላቸው ጥሪ ወደ አገር ውሰጥ ከተመለሱ የተቃዋሚ ፓርቲዎች መካከል የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር አንዱ ነው። በኢትዮጵያ የተቃውሞ ፖለቲካ አንጋፋ የሆኑት አቶ ሌንጮ ለታ ፖለቲካ በቃኝ እያሉ ነው የሚል መረጃ በማኅበራዊ ሚዲያ እየወጣ በመሆኑ አቶ ሌንጮ ለታን ስለ ጉዳዩ አነጋግረናል። የፖለቲካ ሩጫዎን ጨርሰዋል እየተባለ ነው። አቶ ሌንጮ ፡ ፖለቲካ በቃኝ ብዬ አላውቅም፤ መረጃውን ከየት እንዳመጡት አላውቅም። ከፓርቲ ኃላፊነትዎ ለመልቀቅ ጥያቄ አቅርበዋል አቶ ሌንጮ ፡ ገና ፈረንጅ አገር እያለሁ ጀምሮ እየጠየቅኩ ነው።ይህን ለድርጅቴም አሳውቄያለሁ፤ በይፋም ተናግሪአለሁ። ግን ራሴ ፈልጌ ነው። ገና ድርጅቱ መወሰን አለበት። በይፋ በደብዳቤ ድርጅትዎን የጠየቁት መቼ ነው አቶ ሌንጮ ፡ ጥያቄዬን በጽሑፍ አላቀረብኩም። ነገር ግን ለአባላት ስብሰባ ላይ በይፋ ከሚቀጥለው የማእከላዊ ኮሚቴ ምርጫ በኋላ ይሄን ኃላፊነት ተሸክሜ መቀጠል እንደማልፈልግ ተናግሪያለሁ። ፓርቲዎ ለጥያቄዎ ምን ምላሽ እየሰጠ ነው አ ቶ ሌንጮ ፦ ገና ነው። ነገር ግን አሁን ስብሰባ ሊካሄድ ስለሆነ ውሳኔ ይሰጣል። ኃላፊነትዎን መልቀቅ የፈለጉት ለምንድን ነው አቶ ሌንጮ ፡ እርጅና እርጅና ከኃላፊነት ብቻ ነው የሚያግድዎት ቀጣይ ተሳትፎዎት ምን ይሆናል አቶ ሌንጮ ፡ እንደ አንዳንድ ኃላፊዎች እያነከስኩ ስብሰባ መሄድ አልፈልግም። ነገር ግን ሕይወቴ እስካለ ድረስ የፖለቲካ ሥራን መተው አልችልም። ረዥም ዓመታት በውጭ ሃገር ከቆዩ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች ጋር በተያያዘ የዜግነት ጉዳይ ይነሳል። ዜግነትዎ ምንድን ነው አቶ ሌንጮ ፡ የኖርዌይ ፓስፖርት ነው ተሸክሜ የምዞረው። ግን የዜግነቴ ጉዳይ በውሳኔዬ ላይ ምንም ተፅእኖ አልነበረውም። ነገሩ ኃላፊነት መልቀቅ ከመፈለጌ ጋር አይገናኝም። ብፈልግ ድርጅቱ በኢትዮጵያ ለመመዝገብ ሲቃረብ የኖርዌይን ፓስፖርት ለኖርዌጅያኖቹ መልሼ ኢትዮጵያዊነቴን እንደገና ሥራ ላይ ማዋል እችላለሁ። ይህ ለውሳኔዬ ምክንያት የሆነ ነገር አይደለም። በውሳኔዎ እንደ እርሶ ለረዥም ዓመታት ተቃዋሚ ፓርቲዎችን እየመሩ ላሉ ማስተላለፍ የሚፈልጉት መልእክት አለ አቶ ሌንጮ ፡ በተለይ ኦነግ ውስጥ ሃምሳ ዓመት ያገለገሉ ሁሉም ኃላፊነት ቢለቁ ጥሩ ነው ብዬ አምናለው። አሁን አዲስ ትውልድ ትግሉን ተረክቧል እና ለእነሱ መተው ነው የተሻለው መንገድ። በቀጣይ ተሳትፎዎት በምን መንገድ ይሆናል አቶ ሌንጮ ፡ ፓርቲውን እያገለገልኩ እቆያለሁ። ከሌሎች ጋር በስፋት ለመሥራትም እቅድ አለኝ። ስለዚህ ቆይታዎ የሚሆነው በኢትዮጵያ ነው አቶ ሌንጮ ፡ አዲስ አበባ