id
stringlengths
4
5
url
stringlengths
39
537
title
stringlengths
2
65
text
stringlengths
2.53k
162k
38657
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%88%9B%E1%89%BB%E1%8A%A8%E1%88%8D
ማቻከል
ማቻከል በአማራ ክልል የሚገኝ ወረዳ ነው። የማቻከል ወረዳ የማቻከል ወረዳ በአማራ ክልል ምስራቅ ጐጃም ዞን ውስጥ ከሚገኙ 18 ወረዳዎች መካከል አንዱ ሲሆን በሰሜን ስናን ወረዳ በደቡብ ደ/ኤልያስ፣ በምዕራብ ደንበጫ ወረዳና በምስራቅ የጐዛምን ወረዳ ያዋስኗቷል፡፡ የወረዳው ርዕሰ ከተማ የሆነችው አማኑኤል ከአዲስ አበባ በተዘረጋው የአስፖልት መንገድ ላይ የምትገኝ ሲሆን ከሃገሪቱ ርዕሰ መዲና አዲስ አበባ 328 ኪ.ሜ ፣ በክልሉ ርዕሰ ከተማ ባህርዳር 234 ኪ.ሜ እንዲሁም የዞኑ ከተማ የሆነችው ደብረ ማርቆስ 30 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ትገኛለች፡፡ በወረዳው 24 ቀበሌዎች፣ 3 ንዑስ ከተማና በ1 የከተማ ቀበሌ የተከፋፈለ ሲሆን የወረዳው ዋና ከተማ አማኑኤልም በ1886 በደጃዝማች ጓሉ እንደተቆረቆረች ይነገራል፡፡ የማቻከል ወረዳ አጠቃላይ የቆዳ ስፋት 73558 ሄ/ር ሲሆን የአየር ፀባይ ሁኔታ 58.76 % ደጋ ፣39.1% ወይናደጋ 2.12% ውርጭና 0.02% ቆላ እንዲሁም ከባህር ወለል በላይ 1200-3200 ሜትር ከፍታ አለው፡፡ አማካኝ የሙቀት መጠኑ ከ22 የሚደርስ ሲሆን ከ1500-1800 ሚሊ ሜትር አመታዊ የዝናብ መጠን ይኖረዋል፡፡ በወረዳው ወ 6488 ሴት 66017 በድምሩ 130998 ህዝብ የሚኖር ሲሆን ከነዚህም መካከል ወንድ 59266 ሴት 60406 በድምሩ 119669 የሚሆነው ህዝብ በገጠር የሚኖር ነው፡፡ ሁሉም የወረዳው ህዝብ መቶ በመቶ የአማረኛ ቋንቋ ተናጋሪ ሲሆን 98.98 የኦርቶዶክስ ክርስትና 1.02 የሚሆነው ደግሞ የእስልምና ሃይማኖት ተከታይ ነው፡፡ የወረድዋ ህዝብ በአብዛኛው ኑሮው የተመሰረተው በግብርናው ክፍለ ኢኮኖው በተለይም በእርሻ ስራ ላይ ሲሆን ጥቂቶች ደግሞ በንግድ ስራ ላይ ተሰማርተው ይገኛሉ፡፡ ከወረዳው ጠቅላላ ስፋት ውስጥ 46372.19 ሄ/ር መሬት ለእርሻ ሰብል፣ 7648 ሄ/ር መሬት ለግጦሽ ፣ 4654 ሄ/ር መሬት በደን የተሸፈኑ ሲሆን ቀሪው ደግሞ በልዩ ልዩ ቆጥቋጦዎች፣ አትክልትና ወንዞች የተሸፈነ ነው፡፡ የአፈር አይነቱም 12.7% መሬት ጥቁር አፈር፣ 5.7% ግራጫ፣ 70.2% ቀይ አፈርና 11.35% ቡናማ አፈርን ያካተተ ነው፡፡ ይህም በወረዳው ውስጥ ለሚመረቱ የአገዳ ፣የብዕርና የቅባት ሰብሎች ምቹ ስብጥር እንዳለው ያመላክታል፡፡ በወረዳው ውስጥ 51 ቅድመ መደበኛ ፣ 72 የጐልማሶች ትምህርት ቤት ፣ 51 የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ፣ 2 ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ፣1 የመሰናዶ ት/ቤት ፣ 1 የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማት ይገኛሉ፡፡ በጤናው ዘርፍም 6 ጤና ጣቢያዎች እና በሁሉም ቀበሌዎች የጤና ኬላዎች ያሉ ሲሆን አንድም እናት በወሊድ ምክንያት አትሞትም የሚለውን መርህ ከግብ ለማድረስም 1 የቀይ መስቀልና 1 የጤና በድምሩ 2 አንቡላንሶች ለወረዳው ህዝብ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡ አጠቃላይ ሃገራዊና ወረዳዊ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎችን የተሳለጡ ለማድረግ እንደ ማንኛውም አካባቢ ህ/ሰቡ ግብር የመክፈል ልምዱ እየዳበረ የመጣ ሲሆን በገጠር 23715 ግብር ከፋይ አርሶ አደርና በከተማ የደረጃ “ሀ” ግብር ከፋይ 13 ፤ የደረጃ “ለ” 168 ፤ ደረጃ “ሐ” 1149 በድምሩ 1330 የሚሆኑ ነጋዴ ግብር ከፋዮች ሲኖሩ በተያዘው የበጀት አመትም ከ12 ሚሊዩን 56 ሸህ 40 ብር ግብር ለመሰብሰብ ታቅዶ እስካሁን 7 ሚሊዩን 759 ሽህ 627 ብር ከ18 ሳንቲም ለመሰብሰብ ተችሏል፡፡ ይህም የእቅዱን 64.36 በመቶ ማለት ነው፡፡ከመጠረተ ልማት ዝርጋታ አንፃር ስንመለከት የወረዳውን ከተማ ጨምሮ ቀበሌዎች የ24 ሰዓት የመብራት ተጠቃሚ ናቸው፡፡ በወረዳው ውስጥ በሁሉም ቀበሌዎች የኔትወርክ ዝርጋታ በመኖሩ የተንቀሳቃሽ ስልክ ተጠሟ መሆን ችሏል፡፡ ዋና ከተማውን ጨምሮ በድምሩ 8 ቀበሌዎች የ24 ሰዓት የመብራት አገልግሎት ተጠቃሚ ናቸው ካሉ ቀበሌዎች ከ18 በላይ የሚሆኑት በጋ ከክረምት አገልግሎት በሚሰጡ መንገዶች ከወረዳ ማቻከል ጋር የተገናኙ ናቸው፡፡ በወረዳው ውስጥ የተለያዩ ታሪካዊና ባህላዊ ቦታዎች የሚገኙ ሲሆን1880 ዓ.ም በንጉስ ተክለሃይማኖት ዘመን ቆሎቤና ሰሎሜ በተባሉ ጣልያዊያን እንደተሰሩ የሚነገርላትና 6 ሜትር ከፍታ 4 ሜትር ስፋትና 4 ሜትር ርዝመት ያለው የአድያ ድልድይ በዘመኑ በነበሩ ሰዎች በአበያ በረሃ ድንጋይ በማምጣት የተሰሩ በመሆኑ ቀልብን ይስባል፡፡ የኳሽባ ተክለሃይማኖት አንድነት ገዳም ከተፈጥሯዊ መስህብነት ባለፈ በአትክልትና ፍራፍሬ ተሸፍኖ በልማት ስራውም ሊጐበኝ የሚገባ ሌላው የቱሪስት መስህብ ሲሆን የጨኔ አንድነት ብሮግን እቅዱስ ላሊበላ አንድነት ገዳም ሌላው ተፈጥሯዊና ማራኪ ገዳም የወረዳው እንቁና ማራኪ የቱሪስት መስህብ ሃብቶች ናቸው፡፡ በአጠቃላይ የማቻከል ወረዳ ለነዋሪዎቹ ምቹ፣ ለጐብኝዎቹ እንግዳ ተቀባይና ማልማት ለሚፈልጉ የአየር ፀባዩ ተስማሚ የሆነ ተፈጥሯዊ ስነ ምህዳር በጋን ሰርቶ ለመለወጥ ተነሳስቶ ያለው ሰው አክባሪ ህዝብ ያለበት በመሆኑ ወደ ወረዳችን ደግመው ደጋግመው ይመጡና ያልመጡ ይጐብኙ ይዝናኑ፡፡ ህዝብ ቆጠራ አማራ ክልል የኢትዮጵያ ወረዳዎች
51566
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%89%A0%E1%8C%8C%E1%88%9D%E1%8B%B5%E1%88%AD
በጌምድር
የአማራ ብሔራዊ ክልል መንግስት ውስጥ የተለያዪ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ያሉበት ክልል ነው። የአማራ ክልል መንግስትም አማራን፣ የአገውአዊን፣ የኦሮሞን፣ የዋግእምራን፣ የአርጐባንና የቅማንትን ብሄር ብሔረሰቦች ወክሎ የተዋቀረ የክልል መንግስት ነው።በክልሉ የሚገኙት ሁሉም ብሔረሰቦች የራሳቸው ቋንቋ፣ባህልና ታሪክ እምነት ያላቸው ብሄረሰቦች ናቸው። በአብዛኛው ሁሉም በክልሉ የሚገኙ ብሄረሰቦች የአማርኛ ቋንቋን አቀላጥፈው ይናገራሉ፤የጋራ ማህበራዊ ህይወታቸውን ስንመለከት አጠቃላይ ማህበራዊ ክንዋኔዎችን የሚያደርጉ እና በአንድ አይነት ማህበራዊ ክንዋኔዎች የሚገለጹ ህዝቦች ናቸው፡፡በእምነት፣ በጥቃት ፣ በመልከ አምድራዊ አኗኗራቸው… ወዘተ ተከባብረውና ተደጋግፈው የሚኖሩ ሕዝቦች ናቸው። በጠቃላይ የክልሉ ህዝቦች በአብሮነት የክልሉን ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ በጋራ ና በአንድነት እኩል ተሳትፎ ያደርጋሉ። #የአማራ_ክልል_ብሔር_ብሄረሰቦችናሕዝቦችን አጠር አድርገን ዘርዝረን እንመልከት፦ "አማራ" የአማራ ክልል ብሄር አንድ አካል ነው፡፡ አብዛኛውን የክልሉን ህዝብ በመልከ ኣምድራዊ አቀማመጡ፣በቋንቋው ተናጋሪ ብዛት፣በሰፊው የሚሸፍን በመሆኑ የአጠቃላይ የክልሉ መጠሪያ ሆኗል፡፡"አማራዎች በአብዛኛው የክርስትና እምነት ተከታዮች ናቸው።በሸዋ፣በወሎ፣ በጐጃምና በጐንደር በስፋት ይገኛሉ። የራሳቸው ባህል ታሪክና ቋንቋ ያላቸው ብሔረሰቦች ናቸው። ከሁሉም ብሄረሰብ ጋር በአብሮነት ተቻችለው የሚኖሩ ህዝቦች ሲሆኑ የአማራ ብሔር እንደኔ እንደኔ ሁለት ተጨማሪ ተደራቢ ማንነቶች አሉት እነሱም፦ #ቤተ_እስራኤል_አማራ(#ፈላሻ)ቤተ እስራኤል የአማራ ብሄር አንዱ ክፍል ነው፡፡ሆኖም ወደእስራኤል አገር ከመሄዳቸው በፊት #ፈላሻ ወይም ቤተ እስራኤል የሚል መጠሪያ ነበራቸው፡፡ የድሮ ቋንቋቸው ግን አማርኛ ነበር፡፡ አሁን ወደእስራኤል ከሄዱ በኋላ ግን የኋላኛው ትውልድ "እብራይስጥኛን" እንደ በዋና ቋንቋነት ይናገራል፡፡ ታሪካቸው የተወሳሰበ ቢሆንም ከአማራ ብሄር የተለዩ አይደሉም። #ወይጦ_አማራ "ወይጦ አማራ" ከመባሉ ውጭ በማንኛውም መስፈርት በህይማኖትም በባህልም አማራ እንደሆኑ ይገልፃሉ የታሪክ ፃሀፊዎች፡፡ ስለሆነም የአማራ ብሄር ነገድ አካል ነው፡፡ ኦሮሞ በክልሉ መዋቅር ስር ከጥንት ጀምሮ በወሎ ምድር የሚኖሩ ማህበረሰቦች ናቸው።የራሳቸው ባህል ታሪክና ቋንቋ ያላቸው የእስልምና እምነት ተከታይ ማሕበረሰቦች ናቸው። የራስ አስተዳደራቸውን "የኦሮሚያ ልዩ ዞን" በሚል መስረተው ራሳቸውን በራሳቸው እያስተዳደሩ ይገኛሉ። "ዋግእምራ" በአማራ ክልል ከሚገኙት ብሄር ብሄረሰቦች አንዱ ነው።በሰሜን ምስራቅ አማራ የሚገኙ ብሄረሰቦች ሲሆኑ የራሳቸው ልዩ የሆነ ባሕል፣ ቋንቋ ና ታሪክ ያላቸው ብሔረሰቦች ናቸው።በአሁኑ ሰአት የራስ አስተዳደር ዋግእምራ ልዩ ዞን መስርቶ ራሳቸውን በራሳቸው እያስተዳደሩ ይገኛል። "አገውአዊ "የአማራ ብሄራዊ ክልል አንዱ ክፍል ነው፡፡ በምዕራብ አማራ የሚገኙ ብሔረሰቦች ሲሆኑ "የአገውኛ ቋንቋ" ን የሚናገሩ ና የራሳቸው ባህል ና ታሪክ ያላቸው ሕዝቦች ናቸው፡፡ የራሳቸው አስተዳደር "አዊ ልዩ ዞን" መስርተው ራሳቸውን በራሳቸው እያስተዳደሩ ይገኛሉ። "ቅማንት" የአማራ ብሄራዊ ክልል መንግስት አንዱ ክፍል ነው፡፡ የቅማንት ማሕበረሰቦች የራሳቸው ባሕል ታሪክና ቋንቋ ያላቸው የክርስትና እምነት ተከታይ ማሕበረሰቦች ናቸው። ከአማራ ሕዝብ ጋር በአብሮነትና በፍቅር ተሰሳስረው በመተሳሰብ የሚኖሩ ማሕበረሰቦች ናቸው።ራስን በራስ ለማስተዳደር ጥያቄ አቅርበው በ2007 ዓ.ም በሰሜን ጐንደር ዞን "የቅማንት ልዩ ወረዳን" መስርተው ራስን በራስ እያስተዳደሩ ይገኛሉ።የልዩ ወረዳዋ ህዝቦች ህገ መንግስታዊ መብታቸው ተከብሮ ቋንቋቸውን ለማሳደግ ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛሉ።ሙሉ በሙሉ መብታቸው ተከብሯል። ነገር ግን ከወረዳው ውጭ ባሉ አጐራባች ወረዳዎች የሚኖሩ የብሄረሰቡ አባላቶች የራስ አስተዳደር ጥያቄ አቅርበው ምላሽ እየጠበቁ ይገኛሉ። "የአርጎባ ማሕበረሰብ"ከጥንት ዘመን ጀምሮ በአማራ ውስጥ ከሚገኙት ብሄሮች አንዱ ነው፡፡ የራሳቸው ባህል፣ ቋንቋ ናታሪክ ያላቸው የእስልምና እምነት ተከታይ ማህበረሰቦች ናቸው። ቋንቋቸውም "አርጐብኛ" ይባላል። በተለያዩ የአፄ ገዢዎች ምክኒያት ቋንቋቸው ቢዳከምም ዛሬ ድርስ የአርጐብኛ ቋንቋን በጥቂት አካባቢዎቻቸው ላይ ይናገራሉ። ራስን በራስ ለማስተዳደር ለክልሉ ምክር ቤት ጥያቄ አቅርበው በ1998 ዓ.ም በደቡብ ወሎ ዞን የሚገኙት የብሄረሰቡ አባላቶች "የአርጐባ ልዩ ወረዳን" መስርተው ራሳቸውን በራሳቸው በከፊል እያስተዳደሩ ነው። የብሄረሰቡ ተወላጆች በወረዳው ብዙም ደስተኛ አይደሉም ምክኒያቱም የይምሰል ልዩ ወረዳ ነው……። በብሄረሰቡ ጥቂት ተወላጆች አማካኝነት ቋንቋቸውን ለማሳደግ የተለያዩ መፅሀፍትንና ብሮሸሮችን በማዘጋጀት ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛሉ። ከወረዳው ወጭ ያሉ በወረዳው አጎራባች ቀበሌ የሚገኙት የብሄሩ አባላት የራስ አስተዳደር ጥያቄ አቅርበው ምላሽ በመጠበቅ ላይ ይገኛሉ።በኦሮሚያ ልዩ ዞንና በሰሜን ሸዋ ዞን በ12 ወረዳዎች ከ92 ቀበሌዎች በላይ የሚገኙት የብሄረሰቡ አባላትም ከ1986 ዓ.ም ጀምሮ ራስን በራስ ለማስተዳደር ጥያቄ አቅርበው ምላሽ መጠበቅ ከጀመሩ ሰነባብተዋል። የአርጐባ ብሔረሰቦች ከማንኛውም ብሄር ብሄረሰብ ጋር በአብሮነት፣ በሰላምና በፍቅር ተቻችሎ በመኖር ከሚጠቀሱት የኢትዮዽያ ብሔር ብሔረሰቦችና ኅዝቦች ግንባር ቀደሞቹ ናቸው።ወሬ ላማሳመር ብዬ ሳይሆን በታሪክም ተግባርም የሚታወቅና የሚታይ ነገር ነው። በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች በአማራ፣ በኦሮሚያ፣ በሐረሪና በአፋር ክልል በብዛትና በስፋት በሚኖሩበት ሑሉ ከማንኛውም ብሄር ብሄረሰብ ጋራ ቋንቋውን፣ባህሉን ወረሰው የጋራ ማህበራዊ ትስስር ፈጥረው የሚኖሩ ብሔረሰቦች ናቸው። እነዚህ ከላይ ከ①/፩ኛ እስከ⑥/፮ኛ የተዘረዘሩት ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በአማራ ብሔረሰብ ስር በጋራ የሚኖሩ የአንድ ምድር ህዝቦች ናቸው።ሑሉም ባለፉት የአፄ መንግስታቶች ተፅዕኖ ቀንበር ውስጥ የነበሩ ብሔር ብሔረሰቦች ናቸው። ከሌሎች ብሔር ብሔረሶች ጋር በመሆን ባደረጉት ትግል በ1983 ዓ.ም አምባገነን መንግስት ድል አደረጉ። የፌደራሊዝም ስርዓት ተገንብቶ የሀገራችን ህገ መንግስት በህዝቦች ውሳኔ ከፀደቀ ቡሃላ ራስን በራስ የማስተዳደር የእኩልነት መብት ለሁሉም ለብሄር ብሄረሰቦች በሚል ፍትህ አገኙ። ይሁን እንጂ ይህን ስርኣት የሚጠሉት የአምባገነኑ ርዝራዦች ኢህአዴግን እንደጠላት አድርገው ይቆጥሩታል። ጭቁን የነበሩ ብሄር ብሄረሰቦች ግን ኢህአዴግን እያመሰገኑት እንደሆነ እርገጠኛ ነኝ። የአርጎባ ማህበረሰቦች ራስን በራስ ለማስተዳደር በድርጅታቸው አሕዴድ ኢህአዴግ አማካኝነት ከ1986ዓ.ም ጀምረው በኦሮሚያ ልዩ ዞን፣ በደቡብ ወሎና ሰሜን ሸዋ ዞኖች ራስን በራስ የማስተዳደር የመብት ጥያቄያቸውን አቅርበው «በደቡብ ወሎ ዞን ጥቂት ቀበሌዎችን ብቻ» እንዲያስተዳድር ወሰኖ የተቀሩት ደግሞ ከሌሎቹ ብሄረሰቦች በተለየ ሁኔታ ለህዝብ በማይታወቅና ግልፅ ባልሆነ ምክኒያት ምላሽ አላገኙም። ይሁን እንጂ የአርጐባ ብሔረሰቦች መብታቸውን በሰላማዊና በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ጥያቄያቸው አቅርበው አሁንም ምላሽ በመጠበቅ ላይ ናቸው! ግን ለምን? አባት ልጁን ድሮ ጎጆ እንደሚያወጣው ሁሉ…… ሑሉንም ብሔረሰቦች በእኩል አይኑ ሊመለከታቸው ይገባል። #ማስታወሻ፦ በፅሁፌ ላይ ስህተት ካለበት ይቅርታ እየጠየቅኩ አስተያዬታችሁን እሻለሁ ይገነባኛልና በተመቻችሁ ሁኔዎች ሁሉ ልትገልፁልኝ ትችላላችሁ እወዳችሗለሁ ደህና ሁኑ! 3,ከአማራ ክልል ኮሚኒኬሽን ቢሮ ብሮሸር "የጣና ሐይቅን እንታደግ! የ"እቦጭ" አርምን ተባብረን እናስወግድ!" "የብሔር ብሔረሰቦች መብት ተከብሮ በአንድነት፣በፍቅር፣ከሌሎች ሕዝቦች ጋር እኩል ተከባብረን የጋራ ኢትዮዽያችንን እንገንባ!" የጋራ ጠላታችን ድህነትን እንዋጋ! ©በሰዒድ አል ጀበርቲ ተፃፈ አዲስ አበባ-ኢትዮዽያ
52406
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%89%B5%E1%88%9D%E1%8A%90%E1%89%B5%20%E1%8C%88%E1%89%A5%E1%88%A9
ትምነት ገብሩ
ትምነት ገብሩ: የተወለደችው1983/1984- ትምነት ገብሩ ኢትዮ-እሪትሪያዊ ኮምፕዊተር ሳይንቲስትና (በአልጎሪዝም አድልዎ እና በመረጃ ማዕድን ) ላይ የምትሰራ አሜሪካዊ የኮምፒውተር ሳይንቲስት ነች. ትምነት ለቴክኖሎጂ ልዩነት ተሟጋች እና በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ () ውስጥ የሚሰሩ ጥቁር ተመራማሪዎች ማህበረሰብ የሆነው የ , ተባባሪ መስራች ስትሆን ቴክኖሎጂን የመጠቀም ውጤቶቹን ለመፈተሽ በአለም ዙሪያ ካሉ ተመራማሪዎች ጋር በአፍሪካ እና በአፍሪካ ኢሚግሬሽን ላይ በማተኮር የሚሰራው የተከፋፈለ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ምርምር ኢንስቲትዩት () መስራች ነች። እ.ኤ.አ. በ2021 ትምነት ገብሩ በፎርቹን ከአለም 50 ታላላቅ መሪዎች አንዱዋ በመሆን ተሸልማለች።< እ.ኤ.አ. በታህሳስ 2020 ገብሩ የስነምግባር አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቡድን ቴክኒካል መሪ በመሆን ከጎግል ድንገተኛ ስራ መልቀቅ የተነሳ የህዝብ ውዝግብ ማዕከል ነበረች። የትላልቅ የቋንቋ ሞዴሎች ብዙ ስጋቶችን እና አድሎአዊ ጉዳዮችን የሚዘረዝር ወይም ሁሉንም የጎግል ደራሲያን ስም የሚያስወግድ ገና ያልታተመ ወረቀት እንድታወጣ ጋዜጣው ጠይቃ፣ ይህም ወረቀት በእነዚያ ስርዓቶች ውስጥ ያለውን አድሏዊነት የሚቀንስባቸውን የቅርብ ጊዜ ጥናቶችን ችላ ብላለች። በውሳኔው ላይ ግንዛቤን ጠየቃ፣ እና አለመታዘዝ የስራ መልቀቂያዋን ለመደራደር እንደሚያደርጋት አስጠንቅቃለች። ጎግል የስራ መልቀቂያዋን እንደተቀበለ በመግለጽ ስራዋን ወዲያውኑ አቋረጠ። የመጀመሪያ ህይወት እና ትምህርት ትምነት ገብሩ ተወዳ ያደገችው አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ ነው። አባቷ በአምስት ዓመቷ ሞተ እና እናቷ አሳድጋለች። ሁለቱም ወላጆቿ ኤርትራ ናቸው። በመጨረሻ በዩናይትድ ስቴትስ የፖለቲካ ጥገኝነት አግኝታለች፣ ይህ ሁኔታ “አሳዛኝ ነው” ብላለች። ገብሩ በማሳቹሴትስ መኖር የጀመረችው የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቷን ለመከታተል ሲሆን ወዲያው በዘር ላይ የተመሰረተ መድልዎ መፈጸም እንደጀመረች ትናገራለች፣ አንዳንድ መምህራን ከፍተኛ ደረጃ ላይ የምትገኝ ብትሆንም የተወሰኑ የከፍተኛ ምደባ ኮርሶችን እንድትወስድ አልፈቀዱላትም። የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቷን ከጨረሰች በኋላ ገብሩ ከፖሊስ ጋር ያጋጠማት አጋጣሚ በቴክኖሎጂ ስነ-ምግባር ላይ እንድታተኩር አድርጓታል። አንዲት ጥቁር ሴት ጓደኛዋ በቡና ቤት ውስጥ ጥቃት ተፈጽሞባታል፣ ገብሩ ፖሊስ ደውሎ ሪፖርት አድርጓል። ጓደኛዋ የጥቃቱን ዘገባ ከማስገባት ይልቅ ተይዞ ወደ ክፍል እንዲገባ መደረጉን ትናገራለች። ገብሩ ወቅቱን ወሳኝ ወቅት እና "የስርዓት ዘረኝነት ግልፅ ምሳሌ" ብሎታል። በ2001 ገብሩ በስታንፎርድ ዩኒቨርሲቲ የሳይንስ የመጀመሪያ ዲግሪዋን እና የሳይንስ ማስተር ዲግሪዋን በኤሌክትሪካል ምህንድስና፣ በ2017 የዶክትሬት ዲግሪዋን አግኝታለች። ገብሩ የዶክትሬት ዲግሪያቸውን በ 2017 ውድድር ላይ ያቀረበች ሲሆን የኮምፒውተር ራዕይ ሳይንቲስቶች ስራቸውን ለኢንዱስትሪ እና ቬንቸር ካፒታሊስቶች አባላት ባቀረቡበት ወቅት ነው። ከሌሎች ስራ ፈጣሪዎችና ባለሀብቶች ጋር ተከታታይ ትብብር በማድረግ ውድድሩን አቶ ገብሩ አሸንፈዋል። በ2016 በፒኤችዲ ፕሮግራሟ እና በ2018 ገብሩ በጀላኒ ኔልሰን የፕሮግራም ዘመቻ ወደ ኢትዮጵያ ተመለሰች። ገብሩ የዶክትሬት ዲግሪዋን እየሰራች እያለች ስለ የወደፊት ስጋት አሳትሞ የማያውቅ ወረቀት አዘጋጅታለች። በሜዳው ውስጥ የልዩነት እጦት አደጋዎችን ስትጽፍ ከፖሊስ ጋር ባላት ልምድ፣ የስነ ሕዝብ አወቃቀር እና በፕሮፐብሊካ የትንበያ ፖሊስ ምርመራ ላይ በማተኮር በማሽን መማሪያ ውስጥ የሰዎች አድሎአዊነት ትንበያ አሳይቷል። በወረቀቱ ላይ የሰከሩ ወንድ ተሰብሳቢዎች ወሲባዊ ትንኮሳ በሚያደርሱባቸው የኮንፈረንስ ስብሰባዎች ላይ ያጋጠሟትን ልምዷን በማሰላሰል "የወንድ ክለብ ባህል" የሚለውን አጣጥላለች። ሙያ እና ምርምር ገብሩ አፕልን የተቀላቀለው በ2004 በሃርድዌር ዲቪዚዮን ለድምጽ ክፍሎች ሰርክሪት በመስራት ሲሆን በሚቀጥለው አመት የሙሉ ጊዜ የስራ እድል ተሰጠው። ኦዲዮ መሐንዲስ ሆና ከሰራችው ስራ ስራ አስኪያጇ ዋየርድ "አትፍራ" እና በባልደረቦቿ በጣም የተወደደች መሆኗን ተናግራለች። ገብሩ በአፕል ውስጥ በነበረችበት ጊዜ የሰውን ምስል መለየት የሚችል ሶፍትዌር ማለትም የኮምፒዩተር እይታን የመገንባት ፍላጎት አሳየች። ለመጀመሪያው አይፓድ የምልክት ማቀናበሪያ ስልተ ቀመሮችን ማዘጋጀቷን ቀጥላለች። በወቅቱ "በቴክኒካል አጓጊ ሆኖ አግኝቼዋለሁ" ስትል ለክትትል ያለውን ጥቅም ግምት ውስጥ እንደማትገባ ተናግራለች። ኩባንያውን ከለቀቀች ከረጅም ጊዜ በኋላ በ2021 የበጋው የ# እንቅስቃሴ በአፕል ሰራተኞች፣ ከገብሩ ጋር ያማከረችው ቼር ስካርሌትን ጨምሮ፣ ገብሩ “በጣም ብዙ አስጸያፊ ነገሮች” እንዳጋጠሟት እና “እንዴት እንደሚያስተዳድሩ ሁልጊዜ ትጠይቅ ነበር። [መ] ከትኩረት ብርሃን ለመውጣት" እሷ በአፕል ላይ ያለው ተጠያቂነት ረጅም ጊዜ ያለፈበት መሆኑን ገልጻ፣ በራዳር ስር መብረርን መቀጠል እንደማይችሉ አስጠንቅቃለች። አቶ ገብሩ ሚዲያው አፕልን እና ሌሎች የቴክኖሎጂ ኩባንያዎችን የሚዘግቡበትን መንገድ ተችተው፣ ፕሬስ ድርጅቶቹን ከህዝብ እይታ ለመጠበቅ ይረዳል ሲሉ ተችተዋል። እ.ኤ.አ. በ2013 ገብሩ በስታንፎርድ የሚገኘውን የፌይ-ፌይ ሊ ቤተ ሙከራን ተቀላቀለ። በይፋ የሚገኙ ምስሎችን መረጃ ማውጣት ተጠቀመች። ስለ ማህበረሰቦች መረጃ ለመሰብሰብ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የሚያወጡትን የገንዘብ መጠን ለማወቅ ፍላጎት ነበራት። አማራጮችን ለመመርመር፣ ገብሩ ጥልቅ ትምህርትን ከጎግል ጎዳና እይታ ጋር በማጣመር የዩናይትድ ስቴትስ ሰፈሮችን ስነ-ሕዝብ ለመገመት፣ ይህም የሚያሳየው ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ ባህሪያት እንደ የድምጽ አሰጣጥ ዘይቤ፣ ገቢ፣ ዘር እና ትምህርት ከመኪናዎች ምልከታ ሊወሰድ ይችላል። የፒክ አፕ መኪናዎች ቁጥር ከሴዳኖች ቁጥር ከበለጠ ህብረተሰቡ ለሪፐብሊካን ፓርቲ የመምረጥ ዕድሉ ሰፊ ነው። ከ15 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በብዛት ከሚኖሩባቸው 200 የአሜሪካ ከተሞች የተውጣጡ ምስሎችን ተንትነዋል። በቢቢሲ ኒውስ፣ ኒውስዊክ፣ ዘ ኢኮኖሚስት እና ዘ ኒው ዮርክ ታይምስ ተገኝተው ስራው በመገናኛ ብዙሃን በሰፊው ተዘግቧል። እ.ኤ.አ. በ 2015 ገብሩ በሞንትሪያል ፣ ካናዳ በሜዳው ከፍተኛ ኮንፈረንስ የነርቭ መረጃ ማቀነባበሪያ ሲስተምስ () ተካፍሏል። ከ3,700 ተሳታፊዎች መካከል ጥቂቶች ጥቁር ተመራማሪዎች መካከል አንዷ እንደነበረች ገልጻለች። በሚቀጥለው ዓመት እንደገና ስትገኝ፣ ቆጠራን ያዘች፣ እና ጥቁር ወንዶች አምስት ብቻ እንደነበሩ እና ከ8,500 ተወካዮች መካከል ብቸኛዋ ጥቁር ሴት እንደነበረች ገልጻለች። ገብሩ ከባልደረባዋ ዶ/ር ረዲኤት አበበ ጋር በመሆን በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ የሚሰሩ የጥቁር ተመራማሪዎች ማህበረሰብን ብላክ ኢን አይ ኤስን መስርተዋል። እ.ኤ.አ. በ2017 ክረምት ላይ ገብሩ ማይክሮሶፍትን በፍትሃዊነት ፣ ተጠያቂነት ፣ ግልፅነት እና ስነምግባር በ ) ቤተ ሙከራ የድህረ ዶክትሬት ተመራማሪ በመሆን ተቀላቀለ። እ.ኤ.አ. በ 2017 ገብሩ በፍትሃዊነት እና ግልፅነት ኮንፈረንስ ላይ ተናግሯል ፣ ቴክኖሎጂ ሪቪው በ ስርዓቶች ውስጥ ስላሉ አድልዎዎች እና በ ቡድኖች ውስጥ ልዩነቶችን መጨመር ችግሩን እንዴት እንደሚያስተካክለው ቃለ መጠይቅ አድርጎላቸዋል። ስኖው ከጃኪ ስኖው ጋር ባደረገችው ቃለ ምልልስ "የብዝሃነት እጦት አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ እና በተለይም የኮምፒዩተር እይታን የሚያዛባው እንዴት ነው?" እና አቶ ገብሩ በሶፍትዌር ገንቢዎች ውስጥ ያሉ አድልዎዎች እንዳሉ ጠቁመዋል። ገብሩ በማይክሮሶፍት በነበረበት ጊዜ የስርዓተ-ፆታ ሼዶች የተሰኘ ጥናታዊ ጽሁፍ አዘጋጅቷል፣ይህም በጋራ ደራሲ ዶ/ር ጆይ ቡኦላምዊኒ የሚመራውን ሰፊ ​​የማሳቹሴትስ የቴክኖሎጂ ተቋም ፕሮጀክት መጠሪያ ሆነ። ጥንዶቹ የፊት ለይቶ ማወቂያ ሶፍትዌርን መርምረዋል; ጥቁር ሴቶች ከነጭ ወንዶች በ 35% ያነሰ የመታወቅ እድላቸው ዝቅተኛ መሆኑን ማወቁ. ገብሩ ጎግልን የተቀላቀለችው እ.ኤ.አ. የቴክኖሎጂን ማህበራዊ ጠቀሜታ ለማሻሻል ያለውን አቅም ለማሻሻል በመፈለግ የሰው ሰራሽ የማሰብ ችሎታን አንድምታ አጥንታለች። እ.ኤ.አ. በ2019 ገብሩ እና ሌሎች የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ተመራማሪዎች አማዞን የፊት መለያ ቴክኖሎጅን ለህግ አስከባሪ ኤጀንሲዎች መሸጥ እንዲያቆም የሚጠይቅ ደብዳቤ ተፈራርመዋል ፣ምክንያቱም ለሴቶች እና ለቀለም ሰዎች ያደላ ነው ። የአማዞን የፊት ለይቶ ማወቂያ ስርዓት ከማንኛውም የቴክኖሎጂ ኩባንያ የፊት ለይቶ ማወቂያ ሶፍትዌር የበለጠ ጠቆር ያለ ቆዳ ያላቸው ሴቶችን በመለየት ላይ ችግር ነበረበት። በኒውዮርክ ታይምስ ቃለ ምልልስ ላይ ገብሩ ፊትን ለይቶ ማወቅ በአሁኑ ጊዜ ለህግ ማስፈጸሚያ እና ለደህንነት ሲባል ጥቅም ላይ መዋል የማይችል አደገኛ መሆኑን እንደምታምን ተናግራለች። ሽልማቶች እና እውቅና ገብሩ፣ ቡኦላምዊኒ እና ኢኒዮሉዋ ዲቦራ ራጂ የፊት ለይቶ ማወቂያ ላይ ያለውን የአልጎሪዝም አድልዎ ችግር በማጉላት በ ምድብ የ ፈጠራዎች ሽልማት አሸንፈዋል። እ.ኤ.አ. በ 2021 በፎርቹን ከአለም 50 ታላላቅ መሪዎች መካከል ገብሩ ተካቷል ። ገብሩ እ.ኤ.አ.
52795
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8D%8D%E1%88%AB%E1%8A%95%E1%8A%AD%20%E1%88%B2%E1%8A%93%E1%89%B5%E1%88%AB
ፍራንክ ሲናትራ
ፍራንሲስ አልበርት ሲናትራ (ዲሴምበር 12፣ 1915 - መይ 14፣ 1998 እ.ኤ.አ.) አሜሪካዊ ዘፋኝ እና ተዋናይ ነበሩ። "የቦርዱ ሊቀመንበር" የሚል ቅጽል ስም ተሰጥቷቸው በኋላም «አሮጌ ሰማያዊ አይኖች» ተብለው የሚጠሩት ሲናትራ በ1940ዎቹ፣ 1950ዎቹ እና 1960ዎቹ ውስጥ በጣም ታዋቂ ከሆኑ አዝናኝ አዘጋጆች አንዱ ነበሩ። ወደ 150 ሚሊዮን የሚገመት የሪከርድ ሽያጭ ካላቸው የአለም ከፍተኛ ሽያጭ ካላቸው አርቲስቶች አንዱ ናቸው። በሆቦከን፣ ኒው ጀርሲ ከኢጣሊያውያን ስደተኞች የተወለዱ ሲሆን፣ በልጅነት ሲናታራ ለማናዳመጡ ቅርብና ቀላል ከሆነላቸው ከሚስተር ቢንግ ክሮዝቢ የድምጽ ቄንጥ የተነሣ አንድ ከፍተኛ ተጽዕኖ አሳድረው ነበር። እና የሙዚቃ ስራውን በዥዋዥዌ ዘመን ከባንዲራዎች ሃሪ ጄምስ እና ቶሚ ዶርሴ ጋር ጀመረ። እ.ኤ.አ. በ 1943 ከኮሎምቢያ ሪከርድስ ጋር ከተፈራረመ በኋላ እንደ ብቸኛ አርቲስት ስኬት አገኘ ፣ “የቦቢ ሶክስሰሮች” ጣኦት ሆነ። ሲናትራ የመጀመሪያውን አልበሙን በ 1946 የፍራንክ ሲናራ ድምጽን አወጣ። በ1950ዎቹ መጀመሪያ ላይ የፊልም ስራው ሲቆም ሲናትራ ወደ ላስ ቬጋስ ዞረ፣ እዚያም በጣም ከሚታወቁት የመኖሪያ ፈፃሚዎች አንዱ እና የታዋቂው የአይጥ ጥቅል አካል ሆነ። የትወና ስራው በ 1953 ከሄ እስከ ዘለአለም በተባለው ፊልም ሲናትራ የአካዳሚ ሽልማት እና የጎልደን ግሎብ ሽልማትን በምርጥ ደጋፊ ተዋናይነት አግኝቷል። ከዚያም ሲናትራ ከካፒቶል ሪከርድስ ጋር ተፈራርሞ በርካታ በጣም የተወደሱ አልበሞችን አወጣ፣ አንዳንዶቹም በኋላ እንደ መጀመሪያዎቹ “የፅንሰ-ሃሳብ አልበሞች” ተደርገው ተቆጠሩ፣ በዊን ትንሽ ሰአት ፣ ለስዊንጊን አፍቃሪዎች ዘፈኖች! ፣ ኑ ከእኔ ጋር ፍላይ ፣ ብቸኛ ብቸኛ ፣ ማንም አያስብም ፣ እና ። ሲናትራ በ1960 ካፒቶልን ለቆ የራሱን ሪፕሪስ ሪከርድስ የተባለውን የሪከርድ መለያ ለመጀመር እና በርካታ የተሳካ አልበሞችን ለቋል። እ.ኤ.አ. በ 1965 ሴፕቴምበር ኦፍ የእኔ ዓመታት አልበም ቀረጸ እና በኤምሚ አሸናፊ የቴሌቪዥን ልዩ ፍራንክ ሲናትራ፡ ሰው እና ሙዚቃው ላይ ተጫውቷል። በ1966 መጀመሪያ ላይ ከተደጋጋሚ ተባባሪ ካውንት ባዚ ጋር በቬጋስ ውስጥ በሚገኘው ሳንድስ ሆቴል እና ካዚኖ ተመዝግቦ የሚገኘውን ሲናትራን በአሸዋ ላይ ከለቀቀ በኋላ በሚቀጥለው ዓመት ከቶም ጋር ካደረጋቸው በጣም ታዋቂ የትብብር ስራዎች አንዱ የሆነውን አልበም ፍራንሲስ አልበርት ሲናትራ እና አንቶኒዮ ካርሎስ ኢዮቢም መዝግቧል። በ 1968 ፍራንሲስ ኤ እና ኤድዋርድ ኬ ከዱክ ኤሊንግተን ጋር ተከተለ። ሲናትራ በ 1971 ለመጀመሪያ ጊዜ ጡረታ ወጣ ፣ ግን ከሁለት ዓመት በኋላ ከጡረታ ወጥቷል ። ብዙ አልበሞችን ቀርጾ በቄሳርስ ቤተመንግስት ዝግጅቱን ቀጠለ እና በ1980 "ኒውዮርክ፣ ኒውዮርክ"ን ለቋል። የላስ ቬጋስ ትርኢቱን እንደ መነሻ በመጠቀም በ1998 ከመሞቱ ጥቂት ቀደም ብሎ በዩናይትድ ስቴትስ እና በአለም አቀፍ ደረጃ ጎብኝቷል። ሲናትራ የፊልም ተዋናይ በመሆን ከፍተኛ ስኬታማ ሥራን ሠራ። ከዚህ እስከ ዘላለም በተሰኘው ምርጥ ደጋፊ ተዋናይ የአካዳሚ ሽልማትን ካሸነፈ በኋላ፣ በወርቃማው ክንድ ያለው ሰው እና የማንቹሪያን እጩ ውስጥ ተጫውቷል። ሲናትራ እንደ ኦን ዘ ታውን ፣ ጋይስ እና አሻንጉሊቶች ፣ ከፍተኛ ሶሳይቲ እና ፓል ጆይ ባሉ ሙዚቀኞች ውስጥ ታየ፣ ይህም ሌላ ወርቃማ ግሎብ አሸንፏል። በስራው መገባደጃ አካባቢ በቶኒ ሮም ውስጥ ያለውን የማዕረግ ባህሪ ጨምሮ መርማሪዎችን በተደጋጋሚ ይጫወት ነበር። ሲናትራ የጎልደን ግሎብ ሴሲል ቢ ደሚል ሽልማትን በ1971 ተቀበለ።በቴሌቪዥን ላይ የፍራንክ ሲናትራ ትርኢት በ1950 በሲቢኤስ የጀመረ ሲሆን በ1950ዎቹ እና 1960ዎቹ በሙሉ በቴሌቪዥን መታየት ቀጠለ። ሲናራ ከ1940ዎቹ አጋማሽ ጀምሮ በፖለቲካ ውስጥ በጥልቅ የተሳተፈች እና ለፕሬዝዳንቶች ፍራንክሊን ዲ. ከማፍያ ቡድን ጋር ስላለው ግንኙነት በኤፍቢአይ ተመርምሯል። ሲናራ ሙዚቃን እንዴት ማንበብ እንዳለበት ባይማርም በሁሉም የሙዚቃ ዘርፎች ችሎታውን ለማሻሻል ከልጅነቱ ጀምሮ ጠንክሮ ሰርቷል። ፍጽምና ጠበብት፣ በአጻጻፉ እና በመገኘቱ የሚታወቅ፣ ሁልጊዜ ከባንዱ ጋር በቀጥታ ለመቅዳት አጥብቆ ጠየቀ። በቀለማት ያሸበረቀ የግል ህይወቱን ይመራ ነበር እና ከአቫ ጋርድነር ጋር ሁለተኛውን ጋብቻውን ጨምሮ በተጨናነቀ ግንኙነቶች ውስጥ ተሳትፏል። በኋላም በ1966 ሚያ ፋሮውን እና በ1976 ባርባራ ማርክስን አገባ።ሲናትራ ብዙ ሀይለኛ ግጭቶች ነበሯት፤ ብዙ ጊዜ ከጋዜጠኞች ጋር ተገናኝተው ወይም ከስራ አለቆቹ ጋር አለመግባባት ፈጠሩ። ሲናራ በ1983 በኬኔዲ ሴንተር ክብር ተሸላሚ ነበር፣ በ1985 በሮናልድ ሬጋን የፕሬዚዳንትነት ሜዳሊያ ተሸልሟል፣ በ1997 የኮንግረሱ የወርቅ ሜዳሊያ ተሸልሟል። የግራሚ ባለአደራ ሽልማትን፣ የግራሚ አፈ ታሪክ ሽልማትን እና የግራሚ ሽልማትን ጨምሮ አስራ አንድ የግራሚ ሽልማቶችን አግኝቷል። የህይወት ዘመን ስኬት ሽልማት። በ20ኛው ክፍለ ዘመን 100 ከፍተኛ ተደማጭነት ያላቸውን ሰዎች በታይም መጽሄት ስብስብ ውስጥ ሲናትራ ተካትታለች። ሲናትራ ከሞተ በኋላ፣ አሜሪካዊው የሙዚቃ ሃያሲ ሮበርት ክሪስጋው “የ20ኛው ክፍለ ዘመን ታላቁ ዘፋኝ” ሲል ጠርቶታል እና እንደ ተምሳሌት ሰው መቆጠሩን ቀጥሏል። የአሜሪካ ዘፋኞች የአሜሪካ የፊልም ተዋናዮች
50210
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%88%B0%E1%8D%8D%E1%8A%90%E1%8C%8D
ሰፍነግ
ሰፍነጎች በእንስሳት የዘር ግንድ ላይ እጅግ ጥንታዊውንና የታችኛውን ቦታ ይዘው ይገኛሉ። ልብም ሆነ አንጎል የሌላቸው መሆኑ አይገዳቸውም ሰፍነጎች ከዕፅዋት ወገን የሚመደቡ ቢመስሉም አርስቶትልና ትልቁ ፕሊኒ በትክክል ከእንስሳት ክፍል መድበዋቸዋል። ሊቃውንት በመላው ዓለም በሚገኙ ውቅያኖሶችና ሐይቆች ቢያንስ 15,000 የሚያክሉ የሰፍነግ ዝርያዎች ይገኛሉ ብለው ይገምታሉ። እነዚህ ሁሉ ሰፍነጎች በቅርጽም ሆነ በቀለም እጅግ የተለያዩ ናቸው። ጥቂቶቹን ለመጥቀስ ያህል ቀጭን ጣት፣ ጉርድ በርሜል፣ የተዘረጋ ምንጣፍ፣ የሚያምር ማራገቢያና የጠራ ብርሌ የመሰለ መልክ ያላቸው ሰፍነጎች አሉ። አንዳንዶች ከስንዴ ቅንጣት ያነሱ ሲሆኑ ሌሎች ደግሞ ከሰው የሚበልጥ ቁመት አላቸው። አንዳንድ ሰፍነጎች በመቶ የሚቆጠር ዕድሜ ሊኖራቸው እንደሚችል የሳይንስ ሊቃውንት ያምናሉ። ኢንሳይክሎፒዲያ ብሪታኒካ “ሰፍነጎች በቅርጻቸው፣ በአሠራራቸውም ሆነ በእድገታቸው ከሌሎች እንስሳት የተለዩ ናቸው” ይላል። ይህ ሊሆን የቻለው እንዴት ነው? ሰፍነጎች እንደ ሌሎቹ እንስሳት የውስጥ አካል የላቸውም። ታዲያ ልብ፣ አንጎልም ሆነ የነርቭ አውታር ሳይኖራቸው እንዴት በሕይወት መኖር ይችላሉ? በሰፍነግ አካል ውስጥ፣ ለመኖር አስፈላጊ የሆኑ ተግባራትን የሚያከናውኑ ጥቃቅን ህዋሳት ይገኛሉ። የተለየ ተግባር ያላቸው ህዋሳት ምግብ ያጠምዳሉ፣ ምግቦቹን ወደ ሰፍነጉ የተለያዩ የአካል ክፍሎች ያጓጉዛሉ ወይም ቆሻሻ ያስወግዳሉ። ሌሎች ህዋሳት ደግሞ የአጥንት ወይም የውጭ ሽፋን ክፍሎችን በትጋት ይሠራሉ። እንዲያውም አንዳንድ ህዋሳት አስፈላጊ ሆኖ በሚገኝበት ጊዜ ወደ ሌላ ዓይነት ህዋስ መቀየር ይችላሉ። ሰፍነጎች ከሌሎች እንስሳት ልዩ የሚያደርጓቸው ተጨማሪ ባሕርያት አሏቸው። በሕይወት ያለን ሰፍነግ በወንፊት ላይ እየደፈጠጥክ ብትበጣጥሰው ሴሎቹ ዳግመኛ ተሰብስበው የመጀመሪያውን ሰፍነግ ማስገኘት ይችላሉ። ሁለት ሰፍነጎችን አንድ ላይ አድርገህ ብትፈጫቸው ከጊዜ በኋላ ሴሎቹ ተለያይተው የቀድሞዎቹን ሰፍነጎች ይሠራሉ። ናሽናል ጂኦግራፊክ ኒውስ “በዚህ መንገድ ራሱን ከሞት ሊያስነሳ የሚችል አንድም ተክል ወይም እንስሳ የለም” በማለት ተናግሯል። በተጨማሪም ሰፍነጎች እንደ ሁኔታው በመለዋወጥ መራባት ይችላሉ። አንዳንድ ሰፍነጎች እንደ ሕዋ መንኮራኩር ተስፈንጥረው በመጓዝ በሌሎች አካባቢዎች ሊራቡ የሚችሉ ሴሎችን ይወነጭፋሉ። እነዚህ ሴሎች የሕይወት ተግባሮቻቸውን በሙሉ ለጊዜው አቁመው ረዥም ጉዞ ከተጓዙ በኋላ እንደገና ይነቁና “ከተጫኑበት” ወርደው አዲስ ሰፍነግ ያስገኛሉ። ሌሎች ሰፍነጎች እንደ አስፈላጊነቱ ወንዴና ሴቴ በመሆን በጾታዊ ተራክቦ አማካኝነት አዲስ ሰፍነግ ይወልዳሉ። አንዳንዶቹ ደግሞ እንቁላል ይጥላሉ። የባሕር አጽጂዎች የሥነ እንስሳት ተመራማሪ የሆኑት አለን ኮሊንስ ሰፍነጎች “ከሌሎች እንስሳት የተለየ የአመጋገብ ሥርዓት አላቸው” በማለት ጽፈዋል። ሰፍነጎች በላይኛው ሽፋናቸው ላይ ከሚገኙ ጥቃቅን ቀዳዳዎች አንስቶ በመላው አካላቸው የተዘረጉ በርካታ ቱቦዎችና የተለያዩ ክፍሎች አሏቸው። በእነዚህ ቱቦዎችና ክፍሎች ግድግዳ ላይ ኮአኖሳይትስ የሚባሉ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ጥቃቅን ቀዛፊ ሴሎች አሉ። እያንዳንዱ ሴል ወደፊትና ወደኋላ እንዲቀዝፍ የሚያስችለው አለንጋ መሰል ጫፍ አለው። ቤን ሃርደር የተባሉ ጸሐፊ “[እነዚህ ሴሎች] ውኃ በሰፍነጉ ውስጥ ወደሚገኙ ሌሎች ሴሎች ያለማቋረጥ እንዲፈስ ሲያደርጉ ሌሎቹ ሴሎች ደግሞ በውኃው ውስጥ የሚገኙ የምግብ ቅንጣቶችን ይዘው እንዲዋሃድ ያደርጋሉ” በማለት ገልጸዋል። ሰፍነጎች የሰውነት መጠናቸውን አሥር እጥፍ የሚያህል ውኃ በየሰዓቱ በውስጣቸው እንዲያልፍ በማድረግ በውኃው ውስጥ የሚገኙ ምግቦችን፣ መርዛማ ኬሚካሎችንና እስከ 90 በመቶ የሚደርሱ ባክቴሪያዎችን ውጠው ያስቀራሉ። እንዲያውም የውኃው አፈሳሰስ በሚቀያየርበት ወይም በውስጣቸው የተጠራቀመውን ደለል ማስወገድ በሚፈልጉበት ጊዜ የውኃውን መጠን የመቆጣጠር አሊያም የፍሰቱን አቅጣጫ የመቀየር ችሎታ አላቸው። ዶክተር ጆን ሁፐር “የሰፍነጎችን ያህል . . . ጥሩ የባሕር አጽጂዎች አይገኙም” ብለዋል። በሰፍነጎች ውስጥ የማያቋርጥ የምግብና የውኃ ፍሰት መኖሩ እንደ ሽሪምፕና ክራብ ላሉት ትናንሽ ፍጥረታት አመቺ መኖሪያ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል። በአንድ ሰፍነግ ውስጥ 17,128 የሚያክሉ ነዋሪዎች ተገኝተዋል። በርካታ ባክቴሪያዎች፣ አልጌዎችና ፈንገሶች ከሰፍነጎች ጋር ተረዳድተውና ተደጋግፈው ይኖራሉ። አንድ ሰፍነግ በእርጥብነቱ ከሚኖረው ክብደት ውስጥ እስከ 50 በመቶ የሚሆነውን የሚይዙት ባክቴሪያዎች ናቸው። ሳይንቲስቶች፣ ሰፍነጎችና ተባባሪ ጥገኞቻቸው የአዳዲስ መድኃኒቶች ምንጭ ሆነው ሊያገለግሉ እንደሚችሉ ተስፋ ያደርጋሉ። እነዚህ መድኃኒቶች ኤድስን፣ ካንሰርን፣ ወባንና ሌሎች በሽታዎችን ለማጥፋት ጠቃሚ ሊሆኑ እንደሚችሉ ያምናሉ። ሸርሊ ፖምፖኒ የተባሉ ተመራማሪ ይህን በሚመለከት “ተፈጥሮ፣ ኮምፒውተሮቻችን እንኳን ሊያቀናጁ ከሚችሏቸው የበለጡ ውስብስብና ጠቃሚ ሞለኪውሎችን ያመነጫል” ብለዋል። መስተዋት ዓይነት ነገር የሚፈጥሩበት ሁኔታ ብዙ ሰፍነጎች ለገላ መታሻ እንደምንጠቀምባቸው ሰፍነጎች ለስላሳ ሳይሆኑ ሻካራ ወይም ጠንካራ ናቸው። እነዚህ ሰፍነጎች ስፔኪዩልስ የሚባሉ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ጥቃቅን የመስታወት ቅንጣቶች አሏቸው። ስፔኪዩሎች በአጉሊ መነጽር ሲታዩ ያላቸው ውበትና ዓይነታቸው የተለያየ መሆኑ በጣም የሚያስገርም ነው። እነዚህ ስፔኪዩሎች በተለያየ መንገድ እንደ ሰንሰለት ሲያያዙ በጣም ውስብስብ የሆነ አጽም፣ የመከላከያ መሣሪያ እንዲያውም ቁመቱ እስከ 3 ሜትር ውፍረቱ ደግሞ እስከ 1 ሴንቲ ሜትር የሚደርስ ገመድ ይፈጥራሉ። አንድ ሥጋ በል ሰፍነግ ፍጥረታትን አድኖ የሚይዝበት ባለ መንጠቆ መረብ አለው። ጥልቅ በሆነ ባሕር ውስጥ የሚገኘውና የቬነስ አበባ ቅርጫት እየተባለ የሚጠራው የሰፍነግ ዝርያ ስፔኪዩሎችን ተጠቅሞ በጣም ውብ የሆነ የአበባ ጥልፍ መሥራት ይችላል። እነዚህ እንደ ብርሌ የጠሩ የመስታወት ቃጫዎች ለስልክ ማስተላለፊያ የሚያገለግሉትን ዘመናዊ ፋይበር ኦፕቲክ ገመዶች ይመስላሉ። አንድ ሳይንቲስት “እነዚህ ሕያው ቃጫዎች በጣም ጠንካራ ናቸው” ብለዋል። አክለውም “በኃይል ብትቋጥራቸው እንኳ እንደ ሰው ሠራሾቹ ቃጫዎች አይበጠሱም” በማለት ተናግረዋል። እነዚህ ውስብስብ ቃጫዎች በባሕር ውስጥ እንዲሁም ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ባለበት አካባቢ እንዴት ሊፈጠሩ እንደሚችሉ ሳይንቲስቶች በውል ሊረዱት አልቻሉም። የቤል ቤተ ሙከራ ባልደረባ የሆኑት ቼሪ ሙሬይ “በዚህ መንገድ፣ ውስብስብነት የሌለው ይህ ፍጥረት ፋይበር ኦፕቲክ ገመዶችንና እንደ ሴራሚክ ያሉ ነገሮችን በመሥራት ረገድ የሚያጋጥሙ ችግሮችን ለመፍታት አገልግሏል” ብለዋል።
41766
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%89%B0%E1%8D%88%E1%88%AB%20%E1%8B%88%E1%88%8D%E1%8B%B0%E1%88%B0%E1%88%9B%E1%8B%95%E1%89%B5
ተፈራ ወልደሰማዕት
የክቡር አቶ ተፈራ ወልደሰማዕት የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣን ነበሩ። ከ1976 ዓ/ም አንስተው እስከ 1982 ድረስ በኢትዮጵያ ገንዘብ ሚኒስትር ሥልጣንና በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ በከፍተኛው የአመራር ቦታ ላይ ነበሩ። የህይወት ታሪካቸው ክቡር አቶ ተፈራ ወልደሰማዕት ከአባታቸው ከአቶ ወልደሰማዕት ማረሚ እና ከእናታቸው ከወይዘሮ ጀማነሽ በዳኔ በሰሜን ሸዋ ቅምቢብት ወረዳ እ. ኤ. አ. መስከረም 1 ቀን 1938 ዓ.ም ተወለዱ። አቶ ወልደሰማዕት እና ወይዘሮ ጀማነሽ ሶስት ወንድ ልጆችን ተገኝ፥ በቀለ ፥እና ተፈራን እና ሁለት ሴቶችን ጥሩነሽ ፥ እና ዘነበችን ያፈሩ ሲሆን ተፈራ የመጨረሻ ልጅ ናቸው። ክቡር አቶ ተፈራ የተወለዱበት ወቅት ግፈኛው ፋሺሽት ኢጣልያ ኢትዮጵያን የወረረበት እና ሕዝብዋን በመርዝ ጋዝ የፈጀበት ስለነበረ አቶ ወልደሰማዕት ዘምተው በጦር ሜዳ ግዳጃቸውን ከተወጡ በኋላ ወደ መኖሪያ አካባቢያቸው ተመልሰው ብዙም ሳይቆዩ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። እንዳካባቢው ህዝብ ሁሉ ወ/ሮ ጃማነሽም ልጆቻቸውን ይዘው ከመኖሪያ ስፍራቸው ተሰደዋል። ክቡር አቶ ተፈራም አዲስ አበባ ተወስደው የአገራቸውን የቤተክህነት ትምህርት በመከታተል ዳዊት እስከመድገም ድረስ ደርሰዋል። ከዚያም ቀዳማዊ ኃይለስላሴ ካክብ ፅባህ ትምህርት ቤት ገብተው ከአንደኛ አስከ አስራ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርትን አጠናቀዋል። ቀጥለውም ለአንድ ዓመት በመምህርነት ከአገለገሉ በኋላ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ኮሌጅ ገብተው በኢኮኖሚክስ የባችለር ዲግሪ በማዕረግ () በማግኘት እ.ኤ.አ. በ1964 ዓ.ም. ተመርቀዋል። ከኮሌጅ እንደተመረቁም በሕዝባዊ ኑሮ ዕድገት ሚኒስቴር ተቀጥረዋል። በዚህም መስሪያ ቤት ለተወሰነ ጊዜ ከሰሩ በኋላ ወደ ሔግ ኔዘርላንድ ለከፍተኛ ትምህርት ተልከው እ. ኤ. አ. በ 1967 ዓ.ም. በልማት ኢኮኖሚክስ የማስተርስ ዲግሪ አግኝተዋል። ከዚያም ወደ ሕዝባዊ ኑሮ ዕድገት ተመልሰው የፕላን ዩኒቲን በማቋቋምና የዩኒቲ ሃላፊ በመሆን የረጅም ጊዜ የልማት ፕላን እና ዓመታዊ የካፒታል ፕሮግራም እና በጀት በማዘጋጀት እ. ኤ. አ ከ1967 እስከ 1971 አገልግለዋል፡፡ ከዚያም ወደ ገንዘብ ሚኒስቴር በማዛወር በዋሺንግተን በኢትዮጵያ ኤምባሲ የኢኮኖሚ እና ፋይናንስ አማካሪ ሆነው እ. ኤ. አ. 1972-1974 ዓ.ም. ሰርተዋል በዚህም ሓላፊነታቸውን ከአለም ባንክ ከአይ. ኤም. ኤፍ ከአሜሪካ የኢንተርናሽናል የልማት ድርጅት ማለትም ከዩ. ኤስ. ኤይድ እና ከሌሎችም ድርጅቶች ጋር ለኢትዮጵያ የሚሰጠውን ዕርዳታ እያደገ አንዲሄድ ክትትል አድርገዋል። ከዚያም ወደ አዲስ አበባ ተመልሰው እ. ኤ. አ. ከ 1974-1975 ዓ.ም. በገንዘብ ሚኒስቴር የብድር አና ኢንቨስትመንት መምርያ ሃላፊ በመሆን የውጪ ብድር አና እርዳታን አንዲሁም በተለያዩ የፐብሊክ ኢንተርፕራይዞች የመንግስት ኢንቨስትመንተ ይዞታ ተከታትለዋል። ቀጥሎም እ. ኤ. አ ለ 1977-1982 በዚሁ መ/ቤት በምክትልነትና በተጠባባቂነት ከዚያም እ. ኤ. አ. ከ 1977-1982 ዓ.ም. በገንዘብ ሚንስቴር ከፍተኛ አገልግሎት አበርክተዋል። በዚህም ሓላፊነታቸው የሚኒስቴርነት ከፍተኛ አገልግሎት አበርክተዋል። በዚህም ሐላፊነታቸው የሚነስቴሩን ልዩ ልዩ የስራ ክፍሎች በአዲስ መልክ በማደራጀት ለአገሪቷ የልማትና ቋሚ ወጪዎች የሚውሉ ገቢዎችን በማሳደግ እና ሌሎች ሚኒስቴሮችም የቀለጠፈ የበጀት አሰጣጥ አገልግሎት እንዲያገኙ አንዲሁም በፋይናንስ ቁጥጥር እና በጥናት እና ምርምር ሚኒስቴሩ እንዲጠናከር እና የሚጠበቅበትን ወቅታዊ እና የተሟላ አገልግሎት እንዲያበረክት ከማንኛውም ጊዜ ይበልጥ ከኢንተርናሽናል እና ከአህጉራዊ ድርጅቶች በተለይም ከዓለም ባንክ አና ከአፍሪካ ልማት ባንክ ከተለያዩ አገሮች ለኢትዮጵያ ልማት ዕርዳታ እና ብድር ለማስገኘት ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል። እንደሚታወቀው ጊዜው አጅግ ፈታኝ የለውጥ እና የሽግግር ወቅት ስለነበር የአገሪትዋ የፋይናንስ ሁኔታ እንዳይናጋ በብልህነት በጥንቁቅነት በማስተዳደር የበጀት ዲሲፕሊን እንደተጠበቀ እንዲቆይ በለውጡም ምክንያት ለኢትዮጵያ ከምዕራብ አገሮች እና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች የሚሰጠው የወጪ ዕርዳታ እንዳይቀንስ ከፍተኛ ተጋኢደሎ አድርገዋል። በወቅቱ አዲስ የኢትዮጵያ ወዳጅ ከሆኑት አንፃር ለፖለቲካ ተቀጋይነት ሳይሆን የአገሪቱን ጥቅም ለማስጠበቅ የሚያስችል የኢኮኖሚ ግንኙነት እንዲጠበቅ ተዋግተዋል። በዚህም የተነሳ በአፍሪካም ሆነ በኢንተርናሽናል ደረጃ ብዙ አድናቆት እና አክብሮት አትርፈዋል። አብሮዋቸው የነበሩ የስራ ጓደኞቻቸውም ለዚሁ ሁሉ ምስክር ናቸው። ክቡር አቶ ተፈራ የገንዘብ ሚኒስትር በነበሩበት አመታት ሁሉ የብሔራው ባንክ የቦርድ ሊቀመንበር ስለነበሩ የአገሪቷን አጠቃላይ የሞንተሪ እና የፋይናንስ የበላይ ሓላፊ በመሆን የሚጠበቅባቸውን አመራር በብቃት ሰጥተዋል። ከላይ ከተዘረዘሩት ቋሚ የስራ ሓላፊነታቸው በተጨማሪ የብሔራዊ ፕላን ኮሚሽን ፥የካቢኔው የኢኮኖሚ አና ሕግ ኮሚቴዎች የቴሌኮሚኒኬሽን፥ የብሔራዊ ቡና ፥የከብት እርባታ እና የስጋ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦርዶች አባልም ሆነው አገልግለዋል። ክቡር አቶ ተፈራ በትዕግስት፥ በብልህነት እና በቅንነት እጅግ ከባድ የሆነውን ሓላፊነታቸውን በመወጣት ለብዙ ዓመታት ከአገለገሉ በኋላ የአገሪቷ ሁኔታ ከመሻሻል ይልቅ ወደባሰ አቅጣጫ እያመራ መሄዱን በመገንዘባቸው እ.ኤ.አ 1982 ዓ.ም. ቤተሰባቸውን ይዘው ወደ አሜሪካ በመምጣት ከስራቸው በገዛ ፈቃዳቸው ተሰናብተዋል። በረጅም ጊዜ የአገልግሎት ዘመን የቀሰሙትን ሰፊ የስራ ልምድ በተለይ በፋይናንስ አና ባንክኒግ በበጀት በጥናት እና ምርምር ከፍተኛ ፖሊስ ነክ የምክር አገልግሎት ለ 10 ዓመታት ያህል ለልዩ ልዩ አገሮች እና ድርጅቶች አበርክተዋል። ጥቂቶቹን ለመጥቀስ ያህል። በዋሽንግተን ለሚገኘው ኦቨር. ሲይስ. ዲቨሎፕመንት ካወንስል () እ.ኤ.አ. ከ1982-1983 ዓ.ም. በመመደብ ከሰሓራ በታች ያሉት የአፍሪካ አገሮች () የልማት ዕድገት በሚመለከት ጥናት አካሂደዋል። በአይ. ኤም. ኤፍ ተመድበው ለስወዚላንድ መንግስት ብሄራዊ ባንክ እ.ኤ.አ. ከ 1984-1987 ዓ.ም. የጥናት እና ምርምር አቅሙ የጥናት እና ምርምር አቅሙ ስለሚዳብርበት በማማከር ሰርተዋል። በዓለም ባንከ አማካሪ በመሆን ስለአፍሪካ ፐብሊክ ኢንተርፕራይዞች የስራ ክንውን እና የማሻሻያ ጥናት እ. ኤ. አ. በ1988 አካሂደዋል። በአይ. ኤም. ኤፍ ተመድበው ለሌሴቶ ማዕከላዊ ባንክ በፖሊሲ እና ኦፕሬሽን በጥናት እና ምርምር የባንኩ አቅም ስለሚጠናከርበት አማክረዋል። አይ. ኤም. ኤፍ እና የተባበሩት መንግስታት የልማት ድርጅት ለናሚቢያ መንግስተ የሚሰጡትን የቴክኒክ ዕርዳታ በማስተባበር እና ለናሚቢያ የገንዘብ ሚኒስቴር ከፍተኛ አማካሪ በመሆን አገልግለዋል። ክቡር አቶ ተፈራ ከአበረከትዋቸው ጽሁፎች መካከል በልማት ኋላቀር ከሆኑ አገሮች መካከል ስለጋምቢያ ሌሴቶ ማላዊ እና ሱዳን ኢኮኖሚ ጥናት (እ. ኤ. አ. 1981) ከሰሓራ በታች ስላሉት አፍሪካ አገሮች የልማት ፖሊሲ ( እ. ኤ. አ 1983) በኢትዮጵያ ልምድ ላይ የተመሰረተ ስለ አንዳንደ የአፍሪካ አገሮች አጀስትመንት () ፖሲሲ ከሌሎች ጋር በመተባበር የአፍሪካ ፐብሊክ ኢንተርፕራይዞች ስለሚሻሻሉበት ጥናት (እ. ኤ. አ. 1989) ስለ ሳዴግ አባል አገሮች የሞኒተር ውህደት/ ህብረት ስለ ናሚቢያ ፊዚካል ፖሊሲ (እ. ኤ. አ 1995)። ይህ ጥናት በናሚቢያ ካቢኔ ጸድቆ ተግባር ላይ ውሏል። ክቡር አቶ ተፈራ ከአፍሪካ አገልግሎታቸውን አጠናቀው ዋሺንግተን ወደ አይ.ኤም. ኤፍ ዋና መስሪያ ቤት በመመለስ በልዩ ልዩ ክፍላተ በመጨረሻም በጡረታ እስከተገለሉ ድረስ የፕላን እና የበጀተ ከፍተኛ በላሙያ በመሆን ሰርተዋል። ክቡር አቶ ተፈራ የ42 ዓመት የትዳር ጓደኛቸው ከሆኑት ከውድ ባላቤታቸው ከወ/ሮ ንግስተ ጌታቸው ሁለት ወንዶቸን ዶ/ር ሄኖክ ተፈራ፥ አቶ ዮሴፍ ተፈራንና እና አንድ ሴት ወይዘሪት ነፃነት ተፈራን አፍርተዋል። ሶስት የልጅ ልጆችንም ለማየት ታድለዋል። ክቡር አቶ ተፈራ ወልደሰማዕት በተመደቡባቸው የስራ ኃላፊነቶች ሁሉ ቅንነት ታማኝነት ጥንቁቅነት እና ለአገር እና ለወገን ተቆርቋሪነትን የሚያንጸባርቅ ጠባይ ነበራቸው። አቶ ተፈራ በዚህች ዓለም አኗኗራቸው እና አረማመዳቸው ሁሉ ኃላፊነት የሚሰማቸው እና ለቤተሰባቸው ፍጹም ፍቅርና እንክብካቤ የሚያደርጉ ለወዳጆቻቸውም በሚፈለጉበት ጊዜ ፈጥኖ ደራሽ ነበሩ። ህልፈት ህይወት ክቡር አቶ ተፈራ ወደሚወድዋት አገራቸው ኢትዮጵያ ዘመዶቻቸውን እና ወዳጆቻቸውን ለማየት ሄደው ባለፈው መጋቢት ወር ወደ ዋሺንግተን እንደተመሉ የጤና መታወክ ገጥሟቸው በምርመራ ላይ እንዳሉ በድንገት እ. ኤ. አ. 25 ቀን 2013 ከእኩለ ሌሊት በኋላ በተወለዱ በሰባ አራት ዓመታቸው በቦልቲሞር ከተማ ባለው በጆነስ ሆፕኪንስ ሆስፒታል ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። ሕመም ላይ በቆዩበት ጊዜ የውድ ባላቤታቸው እና የልጆቻቸው እንክብካቤ አንድም ቀን አልተለያቸውም፡፡ ዋቢ ምንጮች የኢትዮጵያ ካቢኔ አባላት