id
stringlengths
4
5
url
stringlengths
39
537
title
stringlengths
2
65
text
stringlengths
2.04k
162k
8724
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%88%98%E1%8A%AA%E1%8A%93
መኪና
መኪና የሚለው ቃል '' ከሚለው የጣሊያንኛ ቃል የተወረሰ ቃል ሲሆን፣ (ወይም አውቶሞቢል፣ ተሽከርካሪ) ከሥፍራ ወደ ሥፍራ በመንኮራኩር ላይ በሞቶር የሚነዳ ተንቀሳቃሽ አይነት ነው። ስዎችም ሆነ ዕቃ በመንገዶች ላይ ለማዛወር ይጠቀማል። በ1999 ዓ.ም.፣ በመላ ዓለም ውስጥ የመኪናዎች ቁጥር 800 ሚሊዮን ያህል ነበር። በተለምዶ «መኪና» የሚለው ስም የሚሰጠው ከዶቅዶቄ ትልቅ፣ ከካሚዎንም ወይም ከአውቶቡስ ትንሽ ለሆነ ባለሞቶር ተሽከርካሪ ነው፤ አንዳንዴ ግን ቀላል ካሚዎኖች ከመኪናዎች ጋር መመደብ ይቻላል። በአማካኝ ለመኪናዎች የተሳፋሪዎች ቁጥር ችሎታ 5 ሰዎች ቢሆን፣ በየአይነቱ ግን ከ1 እስከ 9 መቀመጫዎች ድረስ በመገኘት ይለያያል። በቤንዚን የሚሄድ ተግባራዊ መኪና መጀመርያ በጀርመን ሰዎች በ1877 ዓ.ም. ተፈጠረ። ከዚያ በፊት ግን በእንፋሎትም ሆነ በኤሌክትሪክ የሚነዱ መኪናዎች ይገኙ ነበር። መጀመርያ በእንፋሎት የሚነዳ ተሽከርካሪ የታቀደው በኢየሱሳዊው ሚሲዮን ቄስ በቻይና፣ የቤልጅግ ኗሪ ፈርዲናንድ ፈርቢስት በ1664 ዓ.ም. ነበር። እሱ በጻፈው መግለጫ መሠረት፣ ይህ ተሽከርካሪ ለቻይና ንጉሥ ካንግሺ ለጨዋታ እንዲሆን ጥቃቅን ምሳሌ ብቻ ነበር፤ እቅዱም በተግባር ከተሠራ ኖሮ አይታወቅም። ከዚያ በኋላ፣ በ1761 ዓ.ም. የፈረንሳይ ሠራዊት መድፎችን ለመሸክምና ለማዛወር የጠቀመ የንፋሎት ጋሪ በኒኮላ-ዦሴፍ ኩንዮ ተፈጠረ። በመጀመርያ የፈረንሳይ መንግሥት ትኩረት በዚህ ፍጥረት ተሳበና በ1763 ዓ.ም. ሁለተኛ እንፋሎት ጋሪ ተሠራ። ዳሩ ግን ለረጅም ጊዜ እንፋሎት ማስገኘት ስላልቻለ ተግባራዊው ዋጋ ጥቂት በመሆኑ፣ ወደ ማከመቻ ሥፍራ ተላከ። የመድፍ አለቃ ሙሴ ሮላንድ እንደገና በ1792 ዓ.ም. አገኘው፣ ነገር ግን ናፖሌዎን ለዚህ ጉድ ምንም ፍላጎት አልነበረውምና ሃሣቡ ለጊዜው ተረሳ። በዚሁም መካከል፤ በ1776 ዓ.ም. የስኮትላንድ ሰው ዊሊያም ሙርዶክ ባለ ሦስት መንኮራኩር የእንፋሎት ሠረገላ ሠራ። ጊዜውን ባለማግኘቱ ግን ሥራው መቋረጥ ነበረበት። ከዚያ በ1793 ዓ.ም. የሙርዶክ ጎረቤት የነበረ ሌላው የብሪታንያ ኗሪ ሪቻርድ ትሬቪሲክ የራሱን እንፋሎት ሠረገላ ሠራ። በ1795 ዓ.ም. ደግሞ «የለንደን እንፋሎት ሠረገላ» ፈጠረ፤ ይህም መኪና ለ10 ማይል በለንደን መንገዶች ላይ ስምንት ሰዎችን ወሰደ፤ ጉዞውም ከሰዓት በላይ ፈጀ። ሆኖም በኋላ ጊዜ በአጋጣሚ ግጭት ተጋጠመና ፈጠራው ለጊዜው ጠፋ። ብዙ ጊዜ ሳያልፍ ሌሎች ሰዎች አዳዲስ አይነቶች የእንፋሎት ተሽከርካሪዎች ሠሩ። በ1799 ዓ.ም. ደግሞ ውስጣዊ ፈነዳ ኤንጂን በስዊስ አገር ተፈጠረ፤ በመጀመርያው ይህን ፈጠራ ያካሄደው ጋዝ ሃይድሮጅን ብቻ ነበረ። በ1818 ዓ.ም. ሱሙኤል ብራውን በዚህ አይነት መሣርያ አንዱን ጋሪ በለንደን ኮረብታ ላይ እንዲወጣ አደረገ፤ የሙከራው ከፍተኛ ዋጋ ግን ተግባራዊ ፈጠራ እንዳይሆን ከለከለ። ከዚህ ትንሽ በኋላ፣ በ1820 ዓ.ም. የሀንጋሪ ሰው አንዮስ የድሊክ ለመጀመርያው ጊዜ በኤሌክትሪክ ሞቶር የሚሮጥ ትንሽ የተሽከርካሪ ምሳሌ ሠራ። እንዲሁም በአሜሪካ በ1826 ዓ.ም. እና በሆላንድ በ1827 ዓ.ም. ተመሳሳይ ባለ ኤሌክትሪክ ሞቶር ናሙናዎች ተሠሩ። በቅርብ ጊዜ ከዚያ ቀጥሎ፣ የስኮትላንድ ሰዎች መጀመርያው ሙሉ-መጠን ኤሌክትሪክ መኪና ለመሥራት ተከናወኑ። በሚከተሉት አሥርታት ላይ (1830ዎች-1840ዎች ዓ.ም.)፣ የእንፋሎት መኪና እና የኤሌክትሪክ መኪና ቀስ በቀስ በአውሮጳና በአሜሪካ መንገዶች ላይ ይታዩ ጀመር፤ እንደ ወትሮ ከቆየው ከባለ ፈረስ-ጋሪው ትራፊክ አጠገብ አነስተኛ ፈንታ ብቻ ወሰዱ እንጂ በዚያው ዘመን እኚህ አዳዲስ ፈጠራዎች እጅግ ብርቅ ዕይታ ሆነው ቀሩ። በተጨማሪ፣ በአገር ቤት መንገድ በሩቅ ጉዞ ለመሔድ ባለመቻላቸውና በጣም ውድ በመሆናቸው፣ ተግባራዊ ጥቅማቸው በከተማዎች ውስጥ ብቻ፣ በተለይም ለሀብታሞች ወይም እንደ ሕዝባዊ መጓጓዣ (እንደ ታክሲ) ነበር። ለፈረሶች አስደንጋጭ ሥራዎች እንደ ሆኑ መጠን፣ የእንግሊዝ መንግሥት መጀመርያ በ1853 ዓ.ም. የፍጥነት ወሰን በዚህ አይነት ትራፊክ ጣለ፤ ይህም ወሰን በከተማ 5 ማይል (8 ኪ/ሜ) በየሰአቱ ብቻ ነበረ። በ1857 ዓ.ም. የእንግሊዝ መንግሥት ባወጣ ሕግ ወሰኑን እንደገና ወደ 2 ማይል (3 ኪ/ሜ) በየሰአቱ ቀነሰው፤ ከዚህም በላይ ቀይ ባንዲራ የያዘ እግር መንገደኛ በጋሪው ፊት እንዲቀድመው ተገደደ። ስለዚህ «ፈረስ የለሽ ጋሪዎች» ከለንደን መንገዶች ለ30 ዓመታት ያህል ከማጥፋት ሁሉ ትንሽ ቀሩ። በመነጻጸር በፈረንሳይና በአሜሪካ አገራት በሕግ ቢታገሡም፣ ገና አልፎ አልፎ ብቻ የሚታዩ ድንቆች ይሆኑ ነበር። በዚሁም መካከል፣ በ1855 ዓ.ም. የቤልጅግ ሰው ኤቲየን ለኗር በሃይድሮጅን ጋዝ ውስጣዊ ፈነዳ ኤንጂን የሚነዳ መኪና ወይም «ሂፖሞቢል» ፈጠረ። በሙከራው ጉዞ 11 ማይል በፓሪስ መንገዶች በ3 ሰአቶች ጨረሰ። ለኗር 350 ያህል ሂፖሞቢሎችን ሸጠ። በ1862 ዓ.ም. የኦስትሪያ ሰው ሲግፍሪድ ማርኩስ ትንሽ ጋሪ በቤንዚን ውስጣዊ ፈነዳ ኤንጂን ሠራ። እንዲያውም ይህ ድርጊት የቤንዚን መኪና ፈጣሪ ያደርገዋል፤ ዳሩ ግን በ2ኛው ዓለማዊ ጦርነት ጊዜ ናዚ ባለሥልጣናት ይህን ዒላማ ከጀርመን መዝገቦች አስወገዱ፤ ይህም አቶ ማርኩስ ከአይሁዳዊ ዘር ስለነበር ነው። በማርኩስ ፈንታ በቤንዚን የሚሮጠውን ዘመናዊ መኪና የመፍጠር ክብር የሚሰጠው ለካርል ቤንዝ ሆነ። በ1877 ዓ.ም. በማንሃይም ጀርመን አገር መጀመርያ ቤንዝ ሞቶር-ጋሪ ሠራ። በ1880 ዓ.ም. ይህን ሞዴል በጀርመንና በፈረንሳይ በገበያው ላይ ይሸጥ ጀመር። በዚያም አመት የካርል ቤንዝ ሚስት ቤርጣ ቤንዝ ለመጀመርያው ጊዜ ለረጅም ጉዞ (106 ኪ/ሜ) በዚህ አይነት መኪና ሄደች። ከዚህ ትንሽ በኋላ በ1881 ዓ.ም. ሌላው ጀርመናዊ ጎትሊብ ዳይምለር የራሱን መጀመርያ ቤንዚን አውቶሞቢል ሠራ። በዚሁ ወቅት፣ በርካታ ሰዎች በኤውሮጳም ሆነ በአሜሪካ የቤንዚን መኪና መሥራት ንግድ ሞከሩ። በ1881 ዓ.ም. በፈረንሳይ አንድ የመኪና መሥሪያ ድርጅት (ፓንሃርድና ሌቫሦር) ቆሞ ነበር፤ እንዲሁም በ1885 ዓ.ም. በአሜሪካ ነበር (ዱርዬ ሞቶር-ጋሪ ድርጅት)። ከ1892 ዓ.ም. ጀምሮ፣ አሜሪካና ፈረንሳይ አገራት ሁለቱ በጅምላ በገፍ ምርት መኪናን ለመስራት ዝግጁ ነበሩ። ሄንሪ ፎርድ በዚያው ዓመት የዲትሮይት አውቶሞቢል ድርጅት መሠረተ። በቶሎ ግን በ1894 ዓ.ም. ፋብሪካው የቆመው ኦልድስ የሞቶር ተሽከርካሪ ድርጅት አንደኛውን ሥፍራ ወሰደ። በዓመቱም ውስጥ አያሌ ሌሎች ተወዳዳሪዎች ድርጅቶች ለአሜሪካ መንገዶች ብዙ ሺህ መኪናዎች ሠሩ፤ እነርሱም ዊንቶን ሞቶር ጋሪዎች፣ ፎርድ ሞቶሮች፣ ካዲላክና ቶማስ ቢ ጄፍሪ ድርጅት ነበሩ። በ1895 ዓ.ም. መጨረሻ፣ 9000 ያህል የቤንዚን መኪናዎች በአሜሪካ ነበሩ። በዚሁ ሰአት በአሜሪካ ከተገኙት መኪናዎች መካከል 40 ከመቶ የእንፋሎት አይነት ሲሆኑ፣ 38 ከመቶ የኤሌክትሪክ አይነትና 22 ከመቶ ብቻ የቤንዚን አይነት ነበሩ። ከ10 አመታት በኋላ ግን የቤንዚን መኪና ከሌሎቹ አይነቶች ይልቅ የተወደደው ዘዴ ሆነው ነበር። ይህም የሆነባቸው ሳቢያዎች ሁለት ናቸው፤ አንደኛው የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ በዚያን ጊዜ ቻርጅ ሳይደረግለት ከ1 ሳአት በላይ ሊጠቀም ስላልቻለ ነው፤ ለአጭር ጉዞዎች ብቻ ተስማሚ ነበሩ። ሁለተኛው፤ በቂ የፔትሮሌዩም ዘይት ምንጮጭ በመገኘታቸው ቤንዚን ርካሽ የነዳጅ አይነት ሆነ። ከዚህ በላይ ከ1904 ዓ.ም. ጀምሮ የቤንዚን መኪና አጀማመር ዘዴ እጅግ ከለለ። ስለዚህ ጥቂት አመታት ስያልፍ የእንፋሎት መኪናና የኤሌክትሪክ መኪና ጥቅም ለጊዜው ተረሳ።
8561
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%88%B5%E1%8A%95%E1%8B%B1%20%E1%8C%88%E1%89%A5%E1%88%A9
ስንዱ ገብሩ
ወይዘሮ ስንዱ ገብሩየመጀመሪያዋ ሴት የፓርላማ ተመራጭ፣ የጦር አርበኛ፣ ፀሐፊ- ተውኔት፣ ደራሲ፣ የመጀመሪያዋ ሴት ዲፕሎማት የነበሩት እና ሚያዝያ ፲፪ ቀን ፳፻፩ ዓ/ም በ፺፫ ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩን የክብርት ዶክቶር፣ ወይዘሮ ስንዱ ገብሩን ማንነት የሚዘክር “ዝክረ - ስንዱ ገበሬ”፣ በሚል ዝግጅት በእቴጌ መነን ትምህርት ቤት በኢትየጽያ የሴቶች ማኅበራት ቅንጅት (ኢሴማቅ)፣ ከኢትዮጵያ ሴት ደራሲያን ማኅበር፣ ከኢትዮጵያ ሴት መገናኛ ብዙኀን ማኅበር፣ ከኢትዮጵያ ሕግ ባለሙያ ሴቶች ማኅበረና፣ ከጾታዊ ጥቃት መከላከያ ማኅበር ጋር በትብብር የተዘጋጀ ዝክር ተከናውኗል። ልደትና የወጣትነት ዘመናት ወይዘሮ ስንዱ ገብሩ በሸዋ ክፍለ ሀገር በመናገሻ አውራጃ በአዲስ ዓለም ከተማ ጥር ፮ ቀን ፲፱፻፰ ዓ/ም ተወለዱ። አባታቸው ታዋቂው ዲፕሎማት፣ የመጀመሪያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል ፕሬዘደንት፤ ጣሊያኖች ከኢትዮጵያ ከወጡ በኋላ ደግሞ የምክር ቤቱ ፕሬዘደንት የነበሩት በዳግማዊ ምኒልክ ሹመትም የመጀመሪያው የጎንደር ከተማ አስተዳዳሪ የነበሩት ከንቲባ ገብሩ ደስታ ሲሆኑ ታናሽ እህታቸው ደግሞ የውብዳር ገብሩ (አሁን ታዋቂዋ ሙዚቀኛ እማሆይ ጽጌ ማርያም) ናቸው። ዕድሜያቸው ለትምህርት በደረሰበት ወቅት እቤታቸው አስተማሪ ተቀጥሮላቸው የአማርኛን ትምህረት ከፊደል መቁጠር እስከ ዳዊት መድገም በቤታቸው ተማሩ። ከዚያም ወደ አዲስ አበባ ሄደው በስዊድን ሚሲዮን ትምህርት ቤት በመግባት እስከ ስምንተኛ ክፍል ተምረዋል። ከንቲባ ገብሩ ወጣቷን ስንዱ ገብሩን እያስከተሉ ወደ ቤተ መንግሥትም ሆነ ሌላ ሥፍራዎች ይወስዷቸው እንደነበረና ከጊዜው አልጋ ወራሽ ተፈሪ መኮንንም ጋር እንዳስተዋዋቋቸው ተዘግቧል። አልጋ ወራሹም የወጣቷን ብልህነትና ትጋት በማድነቅ ወደ ፈረንጅ አገር ተልከው ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ ባዘዙት መሠረት ወይዘሮ ስንዱ በ፲፱፻፳፩ ዓ/ም (ፊታውራሪ አመዴ በ፲፱፻፲፱ ዓ/ም ይላሉ) ወደ ስዊስ ለትምህርት ቢሄዱም ኑሮው ስላልተመቻቸውና ትምህርት ይሰጥበት የነበረውን የጀርመንኛ ቋንቋ ስላልወደዱት ወደ ፈረንሳይ አቅንተው ትምህርታቸውን ቀጠሉ። በመጨረሻም በስዊስ እና በፈረንሳይ ሁለት ትምህርት ቤቶች በመዘዋወር በዲፕሎማ ተመረቁ። እዛው የሕግ ትምህርት ለመቀጠል ጀምረው የነበረ ቢሆንም፤ ፍላጎታቸው ወደ ሥነ-ጽሑፍ በማዘንበሉ በአጠቃላይ ለአምስት ዓመታት እዛው ተምረው ወደ ሀገራቸው ተመለሱ። ወደ ሀገራቸው እንደተመለሱም በአዲስ አበባ በቅዱስ ጊዮርጊስ ትምህርት ቤት ውስጥ የፈረንሳይኛ ቋንቋን፣ ሀይጅን፣ ቁጥርንና የአማርኛ ድርሰት አጻጻፍን ማስተማር ጀመሩ። በዚህ ሁኔታ አንድ ዓመት እንደቆዩ ለብላታ ሎሬንሶ ታዕዛዝ ተዳሩና ባለቤታቸው የሐረርጌ ክፍለሀገር አስተዳዳሪ ሆነው በመሾማቸው ወደዚያው ከባለቤታቸው ጋር አቀኑ። ከአንድ ዓመት ተኩል በኋላም ብላታ ሎሬንሶ የፍርድ ቤት ሹምና የዜና ስርጭት ኃላፊ ሆነው በመሾማቸው ወደ አዲስ አበባ ሲመለሱ አብረዋቸው ወደ አዲስ አበባ ተመለሱ። የፋሺስት ኢጣልያ ወረራ ዘመናት ፋሺስቶች ኢትዮጵያን በወረሩ ጊዜ ንጉሠ ነገሥቱ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ወደ እንግሊዝ ሀገር ሲሰደዱ ብላታ ሎሬንሶ ታዕዛዝም አብረው ከጃንሆይ ጋር ሄዱ። ወይዘሮ ስንዱ ግን ከቤተሰቦቻቸው ጋር እና ሆለታ ውስጥ ከሚገኙ ወደ መቶ የሚጠጉ የጦር መኮንኖች ጋር ተቀላቅለው ፋሺስቶችን ለመፋለም ወደ ቦሬ ሄዱ። እዚያም የመትረየስ አተኳኮስ ትምህርት ተማሩ። ወደ ነቀምት በመሄድም ሕዝብን እየሰበሰቡ ስለ ነፃነት ማስተማሩን ተያያዙት። በዚህ ወቅት በባንዳዎች ጠቋሚነት በፋሽስት እጅ ከመውደቅ ለጥቂት አምልጠው ጎሬ ላይ ከልዑል ራስ እምሩ ጦር ጋር ተቀላቀሉ። ከዚያም በጦርነቱ የሚጎዱ አርበኞችን ለማከም የሚሆን ቀይ መስቀል ለማቋቋም መፈለጋቸውን ለራስ እምሩ አማክረው በተሰጣቸው ፭ መቶ ብር አቋቁመው አርበኞችን መርዳት ጀመሩ። ወዲያው ግን እርሳቸው ተቀላቅለውት የነበረው የጥቁር አንበሳ ጦር ሲመታ በጣልያን ሠራዊት እጅ ተማርከው በእስር ወደ አዲስ አበባ አመጧቸውና የቁም እስረኛ ሆኑ። የካቲት ፲፪ ቀን ፲፱፻፳፱ ዓ/ም ግራዚያኒን ለመግደል በተደረገው ሙከራ ወንድማቸው መሸሻ ገብሩ አሉበት በመባል ይታሰሱ ስለነበር ወንድማቸውን ከአደጋ ለማዳን ሲሞክሩ በድጋሚ በፋሺስቶች እጅ ወደቁ። በወቅቱ ግራዚያኒ ይኖርበት የነበረው የገነተ ልዑል ቤተ መንግሥት ውስጥ ታሰሩ። ቀጥሎም ወደ አስመራ፣ ከዚያ ወደ ምጽዋ ተወሰዱ። ከምጽዋ ወደብ ሦስት መቶ ወንዶችና ስምንት ሴቶች (እማሆይ ጽጌ ማርያምን ጭምር) ሆነው በመርከብ “አዚናራ” ወደተባለች የኢጣሊያኖች እስር ቤት ተወስደው ዘጠኝ ወራት ታሰሩ። ከእስር በኋላም ወደ አዲስ አበባ ሲመለሱ በእንደዚህ ያለ ተግባር ላይ እንዳይሰማሩ ከፍተኛ ማስጠንቀቂያ ቢሰጣቸውም፤ ማስፈራሪያው ሳይበግራቸው አርበኞችን በግጥም፣ በወኔ ቀስቃሽ ጽሑፎች በማበረታታት፣ መረጃ በማቀበል፣ መሣሪያ በማዳረስ የጀግንነት ተግባር ፈጽመዋል። ከድል በኋላ ከድል በኋላ ወይዘሮ ስንዱ ለሁለት ዓመታት ደሴ ከተማ የሚገኘው የወይዘሮ ስኂን ትምህርት ቤት አስተዳዳሪ በመሆን፣ በኋላም ወደ አዲስ አበባ ተመልሰውም የእቴጌ መነን ትምህርት ቤት ምክትል ርዕሰ መምህርነት፣ ከዚያም የመጀመሪያዋ ሴት ርዕሰ መምህር ሆነው አገልግለዋል። በእቴጌ መነን ትምህርት ቤት በነበሩበት ወቅት፤ “ኮከብ ያለው ያበራል ገና”፣ “የየካቲት ቀኖች”፣ “የኑሮ ስህተት” የሚሉ ትያትሮችን ሠርተው አቅርበዋል። የመጀመሪያዋ ሴት የሕግ መምሪያ ምክር ቤት አባል ከ፲፱፻፵፰ ዓ/ም እስከ ፲፱፻፶፪ ዓ/ም ድረስ የመጀመሪያዋ የሴት የሕግ መምሪያ ምክር ቤት አባልና የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት ምክትል ሊቀ መንበር ሆነው አገልግለዋል። በዚህ ምክር ቤት አባል በነበሩበት ጊዜ ብቸኛዋ ሴት ከመሆናቸውም ባሻገር የሴቶች እኩልነት በማይከበርበት ጊዜ እና “የወንድ ዓለም” በገነነበት የታሪክ ምዕራፍ የሴቶችን ሰብዓዊ መብት ለማስከበርና እኩልነትን በሕግ ለማስተማመን ብዙ የታገሉ ሴት ነበሩ። ስለዚህ ጊዜ ሁኔታዎች ምስክርነት ከሰጡት በከፊሉ፦ “… የቤተሰብ ሕጉ በእርሳቸው ጊዜ ሲወጣ፣ የመኖሪያ ስፍራ የመምረጥን መብት በተመለከተ ለባል የተሰጠውን መብት ተከራክረው ተቀባይነት ቢያጡም የፍትሕ ብሔር ሕጉ ላይ ሴቶች ባገቡት ወንድ ስም ይጠሩ የሚለውን በመቃወም እንዳይፀድቅ ያደረጉና ያስቀየሩ ሴት ስለሆኑ ቀዳማይት ታጋይ እላቸዋለሁ። …” ወይዘሮ መዓዛ አሸናፊ፤ የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ ሴቶች ማኅበር የቦርድ ሰብሳቢ። “… የተፈጠሩበትን ዘመን፣ ሁኔታና አካባቢ አልፈው ዓላማቸውን ያሳኩ አንቱ ለተባለላቸው የአገልግሎቶችና የሥራ አይነቶች ከውጊያ እስከ ውሳኔ ሰጪነት በመቀመጥ ፈር ቀዳጅ ናቸው። በተቀመጡበት ሥልጣንም፣ ለተነሱበት ዓላማ ለሴቶች የእኩልነት ጥያቄ የከፈሉት አስተዋጽኦና ተግባራት በታሪክ የዘመኑ ታላቅ ሰው ያደርጋቸዋል …” ወይዘሮ ሳባ ገብረ መድኅን፣ የኢትዮጵያ ሴቶች ማኅበራት ቅንጅት ዳይሬክተር። እራሳቸውም በጊዜው የዚሁ ሸንጎ አባል የነበሩት ፊታውራሪ አመዴ ለማ ደግሞ ስለዚህ ጉዳይ ትዝታቸውን ሲያካፍሉን፦ “የፍተሐ ብሔሩ ሕግ ቀርቦ ስንከራከር፣ ምን ይላል ፍትሐ ብሔር ውስጥ ያን ጊዜ ሲወጣ፣ ‘የቤቱ ሹም ባል ይሆናል። ሚስት ለባሏ ታዛዥ መሆን አለባት። እንዲህ እንዲህ የሚል ሴቶችን የሚጫኑ አንቀጾች አሉ። ይሄንን ወይዘሮ ስንዱ የዚያን ጊዜ ቀደም ብለው የነቁ ስለነበረ “እንዴ! ለምን አንድ ጊዜ እኛን ንጉሠ ነገሥቱ እኩል ናችሁ ካሉን በኋላ በእራሳችን ስምምነት እንጂ በሕግ ሴቶችን የሚጨቁን ሕግ መግባት የለበትም” ብለው ተከራከሩ። እሺ ድምጽ ይሰጥበት ሲባል አንድ ሰው ብቻ ደገፋቸው። ተናደዱ። “እናንተ እዚህ ምክር ቤት የመጣችሁ ወንዶች፤ ስትመረጡ ሴትና ወንደ ነበር የመረጣችሁ፣ ግን ልትመክሩ የመጣችሁት ለወንዶች እንጂ ለሴቶች እንዳልሆነ ታዝቤአችኋለሁ። ይህ ዛሬ እናንተ የሰጣችሁት ውሳኔ፣ ከአንድ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ብዙ ሴቶች ገብተው ይገለብጡታል እና ዘለቄታ የለውም።” ብለው ተናደው ይሄን ተናግረው ወጡ። ይላሉ ሌላው የዚህ ሸንጎ አባልና ለብዙ ዘመናት የወይዘሮ ስንዱ ጓደና የነበሩት አቶ ጠንክር ተድላ፦ ሴቶችን በተመለከተ ጉዳይ ባል ከሚስቱ እውቀት ውጭ ከ አምሥት መቶ ብር በላይ እንዳይበደር የሚል ሃሣብ አቅርበው በጋለ ስሜት እንደተከራከሩና ውጤቱም ይህ ቁም ነገር ሕግ ለመሆን የበቃ መሆኑን ይመሰክራሉ። ሌላው ብዙ የተሟገቱበትና ውጤታማ የሆኑበት ጉዳይ በጊዜው ቀርቦ የነበረው ‘እንደ ፈረንጆች’ ተለምዶ የኢትዮጵያም ሴቶች ባል ሲያገቡ የባላቸውን አባት ስም እንዲጠቀሙበት የሚል ያልተሳካ የሕግ ረቂቅ ነበር። ሌላ አስተዋጽዖዎች የኢትዮጵያ ቀይ መስቀልና ቀይ ጨረቃ ማኅበር ፕሬዝዳንት፣ የሕዝባዊ ኑሮ እድገት ዋና ፀሐፊነትና አስተዳዳሪነት፣ በምዕራብ ጀርመን ለሦስት ዓመት የትምህርት አታሼ በመሆን አገልግለዋል። ወይዘሮ ስንዱ ከአሥር በላይ የግጥምና ልብ ወለድ መጻሕፍት የጻፉ ሲሆኑ ሠላሳ ሁለት ጽሑፎቻቸው በ[[አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ] ይገኛሉ። የድርሰት ሥራዎች ኮከብህ ያውና ያበራል ገና በግራዚያኒ ጊዜ የየካቲት ቀኖች (፲፱፻፵፯ ዓ/ም) የታደለች ህልም (፲፱፻፵፰ ዓ/ም) ርእስ የሌለው ትዳር (፲፱፻፵፰ ዓ/ም) የኔሮ ስህተት (፲፱፻፵፰ ዓ/ም) ከማይጨው መልስ (፲፱፻፵፱ ዓ/ም) ፊታውራሪ ረታ አዳሙ (፲፱፻፵፱ ዓ/ም) የመጀመሪያዋ የሴት ፓርላማ አባል፣ የሴት የሰብዓዊ መብት ተሟጋች፣ ጀግናና ፀረ-ፋሺስት አርበኛ፣ ፀሐፊ ተውኔት፣የመጽሐፍ ደራሲ፣ እና የመጀመሪያዋ የሴት ዲፕሎማት ስንዱ ገብሩ (የክቡር ዶክተር) ሰኞ ሚያዝያ ፲፪ ቀን ፳፻፩ ዓ/ም በተወለዱ በ ፺፫ ዓመታቸው ሕይወታቸው አልፎ በመንበረ ፀባዖት ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ተቀብረዋል። ወይዘሮ ስንዱ ገብሩ ላበረከቷቸው አስተዋጽዖዎች የወርቅ ሜዳሊያ፣ የንግሥት ሣባ የወርቅ ኒሻን፣ የቀይ መስቀል የወርቅ ሜዳሊያ እና በኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ዘመን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የክብር ዶክትሬት ተሰጥቷቸዋል። ዋቢ ምንጮች (ሰኞ ግንቦት 3 ቀን 2001 ዓ.ም. » በዮናስ ኃይለ መስቀል. ፌብሩዋሪ 20 ቀን 2007 ታይቷል። =15 (መስከረም ፳፭ ቀን ፳፻፫ ዓ/ም ታይቷል።) የኢትዮጵያ ጸሓፊዎች
52406
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%89%B5%E1%88%9D%E1%8A%90%E1%89%B5%20%E1%8C%88%E1%89%A5%E1%88%A9
ትምነት ገብሩ
ትምነት ገብሩ: የተወለደችው1983/1984- ትምነት ገብሩ ኢትዮ-እሪትሪያዊ ኮምፕዊተር ሳይንቲስትና (በአልጎሪዝም አድልዎ እና በመረጃ ማዕድን ) ላይ የምትሰራ አሜሪካዊ የኮምፒውተር ሳይንቲስት ነች. ትምነት ለቴክኖሎጂ ልዩነት ተሟጋች እና በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ () ውስጥ የሚሰሩ ጥቁር ተመራማሪዎች ማህበረሰብ የሆነው የ , ተባባሪ መስራች ስትሆን ቴክኖሎጂን የመጠቀም ውጤቶቹን ለመፈተሽ በአለም ዙሪያ ካሉ ተመራማሪዎች ጋር በአፍሪካ እና በአፍሪካ ኢሚግሬሽን ላይ በማተኮር የሚሰራው የተከፋፈለ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ምርምር ኢንስቲትዩት () መስራች ነች። እ.ኤ.አ. በ2021 ትምነት ገብሩ በፎርቹን ከአለም 50 ታላላቅ መሪዎች አንዱዋ በመሆን ተሸልማለች።< እ.ኤ.አ. በታህሳስ 2020 ገብሩ የስነምግባር አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቡድን ቴክኒካል መሪ በመሆን ከጎግል ድንገተኛ ስራ መልቀቅ የተነሳ የህዝብ ውዝግብ ማዕከል ነበረች። የትላልቅ የቋንቋ ሞዴሎች ብዙ ስጋቶችን እና አድሎአዊ ጉዳዮችን የሚዘረዝር ወይም ሁሉንም የጎግል ደራሲያን ስም የሚያስወግድ ገና ያልታተመ ወረቀት እንድታወጣ ጋዜጣው ጠይቃ፣ ይህም ወረቀት በእነዚያ ስርዓቶች ውስጥ ያለውን አድሏዊነት የሚቀንስባቸውን የቅርብ ጊዜ ጥናቶችን ችላ ብላለች። በውሳኔው ላይ ግንዛቤን ጠየቃ፣ እና አለመታዘዝ የስራ መልቀቂያዋን ለመደራደር እንደሚያደርጋት አስጠንቅቃለች። ጎግል የስራ መልቀቂያዋን እንደተቀበለ በመግለጽ ስራዋን ወዲያውኑ አቋረጠ። የመጀመሪያ ህይወት እና ትምህርት ትምነት ገብሩ ተወዳ ያደገችው አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ ነው። አባቷ በአምስት ዓመቷ ሞተ እና እናቷ አሳድጋለች። ሁለቱም ወላጆቿ ኤርትራ ናቸው። በመጨረሻ በዩናይትድ ስቴትስ የፖለቲካ ጥገኝነት አግኝታለች፣ ይህ ሁኔታ “አሳዛኝ ነው” ብላለች። ገብሩ በማሳቹሴትስ መኖር የጀመረችው የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቷን ለመከታተል ሲሆን ወዲያው በዘር ላይ የተመሰረተ መድልዎ መፈጸም እንደጀመረች ትናገራለች፣ አንዳንድ መምህራን ከፍተኛ ደረጃ ላይ የምትገኝ ብትሆንም የተወሰኑ የከፍተኛ ምደባ ኮርሶችን እንድትወስድ አልፈቀዱላትም። የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቷን ከጨረሰች በኋላ ገብሩ ከፖሊስ ጋር ያጋጠማት አጋጣሚ በቴክኖሎጂ ስነ-ምግባር ላይ እንድታተኩር አድርጓታል። አንዲት ጥቁር ሴት ጓደኛዋ በቡና ቤት ውስጥ ጥቃት ተፈጽሞባታል፣ ገብሩ ፖሊስ ደውሎ ሪፖርት አድርጓል። ጓደኛዋ የጥቃቱን ዘገባ ከማስገባት ይልቅ ተይዞ ወደ ክፍል እንዲገባ መደረጉን ትናገራለች። ገብሩ ወቅቱን ወሳኝ ወቅት እና "የስርዓት ዘረኝነት ግልፅ ምሳሌ" ብሎታል። በ2001 ገብሩ በስታንፎርድ ዩኒቨርሲቲ የሳይንስ የመጀመሪያ ዲግሪዋን እና የሳይንስ ማስተር ዲግሪዋን በኤሌክትሪካል ምህንድስና፣ በ2017 የዶክትሬት ዲግሪዋን አግኝታለች። ገብሩ የዶክትሬት ዲግሪያቸውን በ 2017 ውድድር ላይ ያቀረበች ሲሆን የኮምፒውተር ራዕይ ሳይንቲስቶች ስራቸውን ለኢንዱስትሪ እና ቬንቸር ካፒታሊስቶች አባላት ባቀረቡበት ወቅት ነው። ከሌሎች ስራ ፈጣሪዎችና ባለሀብቶች ጋር ተከታታይ ትብብር በማድረግ ውድድሩን አቶ ገብሩ አሸንፈዋል። በ2016 በፒኤችዲ ፕሮግራሟ እና በ2018 ገብሩ በጀላኒ ኔልሰን የፕሮግራም ዘመቻ ወደ ኢትዮጵያ ተመለሰች። ገብሩ የዶክትሬት ዲግሪዋን እየሰራች እያለች ስለ የወደፊት ስጋት አሳትሞ የማያውቅ ወረቀት አዘጋጅታለች። በሜዳው ውስጥ የልዩነት እጦት አደጋዎችን ስትጽፍ ከፖሊስ ጋር ባላት ልምድ፣ የስነ ሕዝብ አወቃቀር እና በፕሮፐብሊካ የትንበያ ፖሊስ ምርመራ ላይ በማተኮር በማሽን መማሪያ ውስጥ የሰዎች አድሎአዊነት ትንበያ አሳይቷል። በወረቀቱ ላይ የሰከሩ ወንድ ተሰብሳቢዎች ወሲባዊ ትንኮሳ በሚያደርሱባቸው የኮንፈረንስ ስብሰባዎች ላይ ያጋጠሟትን ልምዷን በማሰላሰል "የወንድ ክለብ ባህል" የሚለውን አጣጥላለች። ሙያ እና ምርምር ገብሩ አፕልን የተቀላቀለው በ2004 በሃርድዌር ዲቪዚዮን ለድምጽ ክፍሎች ሰርክሪት በመስራት ሲሆን በሚቀጥለው አመት የሙሉ ጊዜ የስራ እድል ተሰጠው። ኦዲዮ መሐንዲስ ሆና ከሰራችው ስራ ስራ አስኪያጇ ዋየርድ "አትፍራ" እና በባልደረቦቿ በጣም የተወደደች መሆኗን ተናግራለች። ገብሩ በአፕል ውስጥ በነበረችበት ጊዜ የሰውን ምስል መለየት የሚችል ሶፍትዌር ማለትም የኮምፒዩተር እይታን የመገንባት ፍላጎት አሳየች። ለመጀመሪያው አይፓድ የምልክት ማቀናበሪያ ስልተ ቀመሮችን ማዘጋጀቷን ቀጥላለች። በወቅቱ "በቴክኒካል አጓጊ ሆኖ አግኝቼዋለሁ" ስትል ለክትትል ያለውን ጥቅም ግምት ውስጥ እንደማትገባ ተናግራለች። ኩባንያውን ከለቀቀች ከረጅም ጊዜ በኋላ በ2021 የበጋው የ# እንቅስቃሴ በአፕል ሰራተኞች፣ ከገብሩ ጋር ያማከረችው ቼር ስካርሌትን ጨምሮ፣ ገብሩ “በጣም ብዙ አስጸያፊ ነገሮች” እንዳጋጠሟት እና “እንዴት እንደሚያስተዳድሩ ሁልጊዜ ትጠይቅ ነበር። [መ] ከትኩረት ብርሃን ለመውጣት" እሷ በአፕል ላይ ያለው ተጠያቂነት ረጅም ጊዜ ያለፈበት መሆኑን ገልጻ፣ በራዳር ስር መብረርን መቀጠል እንደማይችሉ አስጠንቅቃለች። አቶ ገብሩ ሚዲያው አፕልን እና ሌሎች የቴክኖሎጂ ኩባንያዎችን የሚዘግቡበትን መንገድ ተችተው፣ ፕሬስ ድርጅቶቹን ከህዝብ እይታ ለመጠበቅ ይረዳል ሲሉ ተችተዋል። እ.ኤ.አ. በ2013 ገብሩ በስታንፎርድ የሚገኘውን የፌይ-ፌይ ሊ ቤተ ሙከራን ተቀላቀለ። በይፋ የሚገኙ ምስሎችን መረጃ ማውጣት ተጠቀመች። ስለ ማህበረሰቦች መረጃ ለመሰብሰብ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የሚያወጡትን የገንዘብ መጠን ለማወቅ ፍላጎት ነበራት። አማራጮችን ለመመርመር፣ ገብሩ ጥልቅ ትምህርትን ከጎግል ጎዳና እይታ ጋር በማጣመር የዩናይትድ ስቴትስ ሰፈሮችን ስነ-ሕዝብ ለመገመት፣ ይህም የሚያሳየው ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ ባህሪያት እንደ የድምጽ አሰጣጥ ዘይቤ፣ ገቢ፣ ዘር እና ትምህርት ከመኪናዎች ምልከታ ሊወሰድ ይችላል። የፒክ አፕ መኪናዎች ቁጥር ከሴዳኖች ቁጥር ከበለጠ ህብረተሰቡ ለሪፐብሊካን ፓርቲ የመምረጥ ዕድሉ ሰፊ ነው። ከ15 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በብዛት ከሚኖሩባቸው 200 የአሜሪካ ከተሞች የተውጣጡ ምስሎችን ተንትነዋል። በቢቢሲ ኒውስ፣ ኒውስዊክ፣ ዘ ኢኮኖሚስት እና ዘ ኒው ዮርክ ታይምስ ተገኝተው ስራው በመገናኛ ብዙሃን በሰፊው ተዘግቧል። እ.ኤ.አ. በ 2015 ገብሩ በሞንትሪያል ፣ ካናዳ በሜዳው ከፍተኛ ኮንፈረንስ የነርቭ መረጃ ማቀነባበሪያ ሲስተምስ () ተካፍሏል። ከ3,700 ተሳታፊዎች መካከል ጥቂቶች ጥቁር ተመራማሪዎች መካከል አንዷ እንደነበረች ገልጻለች። በሚቀጥለው ዓመት እንደገና ስትገኝ፣ ቆጠራን ያዘች፣ እና ጥቁር ወንዶች አምስት ብቻ እንደነበሩ እና ከ8,500 ተወካዮች መካከል ብቸኛዋ ጥቁር ሴት እንደነበረች ገልጻለች። ገብሩ ከባልደረባዋ ዶ/ር ረዲኤት አበበ ጋር በመሆን በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ የሚሰሩ የጥቁር ተመራማሪዎች ማህበረሰብን ብላክ ኢን አይ ኤስን መስርተዋል። እ.ኤ.አ. በ2017 ክረምት ላይ ገብሩ ማይክሮሶፍትን በፍትሃዊነት ፣ ተጠያቂነት ፣ ግልፅነት እና ስነምግባር በ ) ቤተ ሙከራ የድህረ ዶክትሬት ተመራማሪ በመሆን ተቀላቀለ። እ.ኤ.አ. በ 2017 ገብሩ በፍትሃዊነት እና ግልፅነት ኮንፈረንስ ላይ ተናግሯል ፣ ቴክኖሎጂ ሪቪው በ ስርዓቶች ውስጥ ስላሉ አድልዎዎች እና በ ቡድኖች ውስጥ ልዩነቶችን መጨመር ችግሩን እንዴት እንደሚያስተካክለው ቃለ መጠይቅ አድርጎላቸዋል። ስኖው ከጃኪ ስኖው ጋር ባደረገችው ቃለ ምልልስ "የብዝሃነት እጦት አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ እና በተለይም የኮምፒዩተር እይታን የሚያዛባው እንዴት ነው?" እና አቶ ገብሩ በሶፍትዌር ገንቢዎች ውስጥ ያሉ አድልዎዎች እንዳሉ ጠቁመዋል። ገብሩ በማይክሮሶፍት በነበረበት ጊዜ የስርዓተ-ፆታ ሼዶች የተሰኘ ጥናታዊ ጽሁፍ አዘጋጅቷል፣ይህም በጋራ ደራሲ ዶ/ር ጆይ ቡኦላምዊኒ የሚመራውን ሰፊ ​​የማሳቹሴትስ የቴክኖሎጂ ተቋም ፕሮጀክት መጠሪያ ሆነ። ጥንዶቹ የፊት ለይቶ ማወቂያ ሶፍትዌርን መርምረዋል; ጥቁር ሴቶች ከነጭ ወንዶች በ 35% ያነሰ የመታወቅ እድላቸው ዝቅተኛ መሆኑን ማወቁ. ገብሩ ጎግልን የተቀላቀለችው እ.ኤ.አ. የቴክኖሎጂን ማህበራዊ ጠቀሜታ ለማሻሻል ያለውን አቅም ለማሻሻል በመፈለግ የሰው ሰራሽ የማሰብ ችሎታን አንድምታ አጥንታለች። እ.ኤ.አ. በ2019 ገብሩ እና ሌሎች የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ተመራማሪዎች አማዞን የፊት መለያ ቴክኖሎጅን ለህግ አስከባሪ ኤጀንሲዎች መሸጥ እንዲያቆም የሚጠይቅ ደብዳቤ ተፈራርመዋል ፣ምክንያቱም ለሴቶች እና ለቀለም ሰዎች ያደላ ነው ። የአማዞን የፊት ለይቶ ማወቂያ ስርዓት ከማንኛውም የቴክኖሎጂ ኩባንያ የፊት ለይቶ ማወቂያ ሶፍትዌር የበለጠ ጠቆር ያለ ቆዳ ያላቸው ሴቶችን በመለየት ላይ ችግር ነበረበት። በኒውዮርክ ታይምስ ቃለ ምልልስ ላይ ገብሩ ፊትን ለይቶ ማወቅ በአሁኑ ጊዜ ለህግ ማስፈጸሚያ እና ለደህንነት ሲባል ጥቅም ላይ መዋል የማይችል አደገኛ መሆኑን እንደምታምን ተናግራለች። ሽልማቶች እና እውቅና ገብሩ፣ ቡኦላምዊኒ እና ኢኒዮሉዋ ዲቦራ ራጂ የፊት ለይቶ ማወቂያ ላይ ያለውን የአልጎሪዝም አድልዎ ችግር በማጉላት በ ምድብ የ ፈጠራዎች ሽልማት አሸንፈዋል። እ.ኤ.አ. በ 2021 በፎርቹን ከአለም 50 ታላላቅ መሪዎች መካከል ገብሩ ተካቷል ። ገብሩ እ.ኤ.አ.
9680
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%88%8D%E1%8B%B5%E1%8B%AB
ልድያ
ልድያ (አሦርኛ፦ ሉዱ፤ ዕብራይስጥ፦ /ሉድ/፣ ግሪክ፦ /ሉዲያ/) በምዕራብ ትንሹ እስያ የተገኘ ታሪካዊ አውራጃና መንግሥት ነበር። በታወቀበት ዘመን ዋና ከተማው ሰርዴስ ሆነ። በአንድ ወቅት የትንሹ እስያ ምዕራብ ክፍል በሙሉ የሉድያ ግዛት ነበረ። በኋለ ዘመን ደግሞ ልድያ የሮማ መንግሥት ጠቅላይ ግዛት ነበረ። መሐለቅ መጀመርያ የተፈጠረው በልድያ ክ.በ. 660 አመት ያሕል እንደ ነበረ ይታመናል። የታሪካዊው ልድያ ጠረፎች በዘመናት ላይ ይለያዩ ነበር። በመጀመርያ በሚስያ፣ በካርያ፣ በፍርግያና በዮንያ ይወሰን ነበር። በኋላ፣ የንጉሦች አልያቴስና ቅሮይሶስ ሠልፎች ልድያን ሲያስፋፏት፣ ከሉቅያ በቀር ትንሹን እስያ ከሃሊስ ወንዝ ምዕራብ በሙሉ ገዙ። ከፋርስ ወረራ ቀጥሎ ማያንድሮስ ወንዝ በፋርስ መንግሥት የክፍላገሩ ደቡብ ጠረፍ ሆነ። በሮማ መንግሥት ውስጥ ደግሞ የልድያ ጠቅላይ ግዛት በአንድ በኩል ከሚስያና ከካርያ መካከል በሌላውም በኩል ከፍርግያና ከአይጋዮስ ባሕር መካከል ያለው አገር ሁሉ ነበረ። ቋንቋቸው ሉድኛ በሕንዳዊ-አውሮፓዊ ቋንቋዎች ቤተሠብ ሲሆን በዚሁም ቤተሠብ ውስጥ የአናቶላዊ ቅርንጫፍ አባል ነበር። ስለዚህ የሉዊኛና የኬጥኛ ቅርብ ዘመድ ነው።. ሉድኛም በመጨረሻ እስከ 1ኛ ክፍለ ዘመን ከክርስቶስ በፊት ድረስ እንደ መነጋገርያ ሆኖ ቆየ። ማዮንያ እና ልድያ የልድያ መንግሥት መጀመርያ የተነሣ የኬጥያውያን መንግሥት በ1180 ክ.በ. ገደማ ከወደቀበት ወቅት በኋላ ነበረ። ቀድሞ በኬጥያውያን መንግሥት ዘመን፣ የአገሩ ስም አርፃዋ ሲሆን ይህ ሉዊኛ የሚናገር አገር ነበር። ይሁንና ክሁሉ ጥንታዊ በሆኑት ኬጥያውያን ሰነዶች የአገሩ ስም «ሉዊያ» ይባላል። በግሪክ ምንጮች ዘንድ ግን፣ የልድያ መንግሥት መጀመርያ ስም ማዮንያ ተባለ፤ ሆሜርም (ዒልያድ . 431) የልድያን ነዋሪዎች ማዮናውያን () ይላቸዋል። ሆሜር ደግሞ ዋና ከተማቸውን 'ሰርዴስ' ሳይሆን 'ሁዴ' ይለዋል (ኢልያድ . 385)። ሆኖም 'ሁዴ' ምናልባት ሰርዴስ የቆመበት ሠፈር ስም ሊሆን ይቻላል.። ኋላም፣ ሄሮዶቶስ (ታሪኮች . 7) እንደሚነግረው፣ መዮናውያን ስለ ንጉሳቸው ስለ አቲስ ልጅ ሉዶስ () ስም አዲስ ስያሜያቸውን 'ልድያውያን' (ግሪክ፡ /ሉዶይ/) ተቀበሉ። ይህም የሆነ ከአፈታሪካዊው ሄራክሌስ ሥርወ መንግሥት በፊት እንደ ነበር ይላል። እንደዚህም ሕዝቡ በዕብራይስጥ ሉዲም () ሲባሉ፣ ምክንያቱም በጥንት ከሉድ ሴም (ዘፍ. 10) እንደ ተወለዱ መሆኑ ይታመናል። በመጽሐፈ ኩፋሌ ምዕ. 9 መሠረት እንደገና የሉድ ርስት ከ'አሦር ተራሮች' ወደ ምዕራብ እስከ 'ታላቁ ባህር' ድረስ ይሠጣል፤ ይህም ማለት የትንሹ እስያ ልሳነ ምድር በሙሉ ነው። ትልቁ ፕሊኒ (የተፈጥሮ ታሪክ 5:30) እና ሄሮክሌስ እንደ ጻፉት፣ ማዮንያ የተባለ መንደር ለረጅም ዘመን በዙሪያው ይገኝ ነበር። ሄሮዶቶስ ደግሞ የኤትሩስካውያን ሥልጣኔ (በዛሬው ጣልያን) በልድያውያን ሠፈረኞች እንደተመሠረተ በሉዶስም ወንድም በቲሬኖስ እንደ ተመሩ የሞለውን ትውፊት ይጠቅሳል። ነገር ግን የሃሊካርናሦስ ዲዮኒስዮስ ይህን ታሪክ አልተቀበለም፣ የኤትሩስካውያን ባሕልና ቋንቋ ከልዳውያን እጅግ ይለያይ ነበርና። በፓክቶሎስ ወንዝ የተገኘው የወርቅ ዝቃጅ የልድያ መጨረሻ ንጉስ ቅሮይሶስ ሀብት ምንጭ ሆነ። በአንድ ትውፊት ዘንድ መንስኤው የፍርግያ ንጉስ ሚዳስ 'የወርቅ ዕጆቹን' በውኆቹ ውስጥ ስለ ታጠቡ ነበር። መጀመርያ መሐለቆች የፈተና ደንጊያ የተባለው ፈጠራ ዕውቀት በልድያ ከተስፋፋ በኋላ፣ የልድያ ሰዎች ወዲያው ለብረታብረታቸው መደበኛ ጥረት ለማረጋገጥ ቻሉ። ይህ ቀላል መሣርያ ለግሪኮችም «የልድያ ደንጊያ» በመባል ታወቀ። ከዚያ በፊት ከጥንት ጀምሮ ወርቅና ብር በክብደት (ሰቀል) ለሸቀጥ ቢጠቅምም (ለምሳሌ በካሩም)፣ ብዙ ጊዜ ከሌሎች የብረት አይነቶች ጋር ተቀላቅሎ ነበር። አሁን የልድያ ንጉሥ ማሕተም የጥረቱ ማረጋገጫ ሆነ፤ በዚህም አዲስ የመሐለቅ ገበያ መጀመርያ መመሠረት ቻለ። በሄሮዶቶስ ታሪክ መሠረት፣ ልዳውያን ከሁሉ በፊት የወርቅና የብር መሐለቅ የተጠቀሙት ሰዎች ነበሩ፤ እንዲሁም ቋሚ ሱቆችን መጀመርያ የገነቡት ሕዝብ መሆናቸውን ይመሠክራል። እነኚህ መጀመርያ መሐለቆች በ660-600 ክ.በ. ገዳማ እንደ ተሰሩ ይታመናል። መጀመርያው መሐለቅ ከኤሌክትሩም (በተፈጥሮ የሚገኝ የወርቅና የብር ቅልቅል) ነው የተሠራ። በእስታቴር ሢሶ ድፍን ሆኖ ክብደቱ 4.76 ግራም ነበር፣ በንጉሡም ምልክት በአንበሣ ራስ ስዕል ይታተም ነበር። አንድ እስታቴር 14.1 ግራም ኤሌክትሩም ነበር። ይህም ለአንድ ወታደር የአንድ ወር ደመወዝ ነበረ። የልድያ ንጉሥ ቅሮይሶስ ስለ ሀብቱ ስመጥር ሆነዋል። ሆኖም በ558 ክ.በ. ቅሮይሶስ በፋርስ ንጉሥ በ2ኛ ቂሮስ እጅ ድል ስለ ሆኑ መንግሥቱ ወዲያው የፋርስ ክፍላገር ሆነ። ሥርወ መንግሥታት ልድያ በታሪክ 3 ስርወ መንግሥታት ነበሩዋት፦ አትያዶች (1300 ክ.በ) - አፈታሪካዊ ዘመን (ቅድመ ታሪክ) ሄራክሊዶች (እስከ 695 ክ.በ. ድረስ) - በሄሮዶቶስ ዘንድ ሄራክሊዶች ከጀግናው ሄራክሌስ ትወልደው ለ22 ትውልዶች ከ1197 ክ.በ ጀምሮ ለ505 አመታት ነገሡ። አልያቴስ በ784 ክ.በ. አካባቢ ነገሡ። የዚሁ ሥርወ መንግሥት መጨረሻ ንጉስ ሙርሲሎስ (ካንዳውሌስ) ነበረ። ከ17 አመታት ዘመን በኋላ በባልንጀራው በጉጌስ እጅ ተገደለ። ጉጌስ ወይም በአሦር ጽሕፈቶች 'የሉዱ ጉጉ' የተባለው በሙርሲሎስ ፈንታ ከ695 እስከ 660 ክ.በ. አካባቢ ነገሡ። በዚህ ዘመን ዘላኖች ኪሜራውያን ሕዝብ ብዙ ከተሞች በልድያ ዘረፏቸው። ጉጌስ ከግብጽ ጋር ስምምነት አድርገው ሠራዊቱን ወደ ግብጽ ልከው ከአሦራውያን ሃያላት ጋር ተጣሉ። 2ኛ አርዲስ (660-629 ክ.በ.) ሣድያቴስ (629-618 ክ.በ. ገዳማ) - ሄሮዶቱስ እንዳለው ይህ ንጉስ ከሜዶን ነገሥታት ጋር ታግለው ኪሜራውያንንም ከእስያ አባርረው ስምርንስንም ይዘው፣ ሚጢሊኒን ወረሩት። 2ኛ አልያቴስ (618-568 ክ.በ.) - የሜዶን ንጉስ ኩዋክሻጥራ ልድያን ባጠቃ ጊዜ፣ ከረጅም ጦርነትና በ593 ክ.በ. በአንድ ታላቅ ውግያ መካከል ግርዶሽ ድንገት መጥቶ ከዚያ ቀጥሎ በኪልቅያና በባቢሎን ነገሥታት አማካይነት ስምምነት ተደረገላቸውና ያንጊዜ ሃሊስ ወንዝ የሜዶንና የልድያ ጠረፍ ሆነ። ቅሮይሶስ (568-554 ክ.በ.) - ከዚህ ንጉስ የተነሣ 'እንደ ቅሮይሶስ ሃብታም' ዘይቤ ሆኗል። ቅሮይሶስ በፋርስ ንጉሥ በ2ኛ ቂሮስ ላይ ጦርነት አድርገው በ554 ክ.በ. ተሸንፈው ከዚያ የልድያ መንግሥት ጨረሰና የፋርስ መንግሥት ክፍላገር ሆነ። የፋርስ መንግሥት በ554 ክ.በ የፋርስ ንጉስ 2ኛ ቂሮስ ሰርዴስን ይዘውት ልድያ የፋርስ ክፍላገር ሆነ። የመቄዶንና የግሪኮች ዘመን የፋርስ መንግሥት ለመቄዶን ንጉሥ ለታላቁ እስክንድር በወደቀበት ወቅት ልድያ የክፍላገር ስም ሆኖ ቆየ። እስክንድርም ሲሞት መንግሥቱም በአለቆቹ በተከፋፈለው ጊዜ፣ ልድያ ወደ ሴሌውቅያ ተሰጠ። ከዚያ ወደ ጴርጋሞን መንግሥት ተጨመረ። የጴርጋሞን መጨረሻ ንጉሥ አገሩን ለሮማውያን በኑዛዜ ሰጠ። የሮማ መንግሥት ሮማውያን ሰርዴስን በገቡበት ጊዜ በ141 ክ.በ. ልድያ ወዲያው በሮማ መንግሥት ውስጥ የእስያ ጠቅላይ ግዛት ክፍል ሆነ። ይህ በጣም ሃብታም ጠቅላይ ግዛት ነበርና አገረ ገዡ ትልቅ ማዕረግ ነበረው። ዙሪያው ቶሎ የአይሁድ ሠፈረኞችንና የክርስትና ተከታዮችን አገኘ። በሐዋርያት ሥራ 16:14 መሠረት፣ አንዲት ቀይ ሐር ሻጭ ከትያጥሮን 'ልድያ' ተባለች፣ ትያጥሮንም ቀድሞ 'ልድያ' በተባለ አውራጃ ነበረ። በ3ኛ ክፍለ ዘመን ዓ.ም. ክርስትና ከኤፌሶን መቀመጫ በአገሩ ውስጥ ቶሎ ተስፋፋ። በሮማ ንጉስ ዲዮክሌቲያኖስ ትዕዛዝ 'ልድያ' በ288 ዓ.ም. እንደገና የትንሽ ጠቅላይ ግዛት ስም ሆነ። ዋና ከተማው እንደገና ሰርዴስ ሆነ። በቢዛንታይን ንጉሥ ሄራክሊዮስ ዘመን (602-633 ዓ.ም.) ልድያ በአናቶሊኮንና ትራቄሲዮን ክፍላገሮች ተከፋፈለ። ዙሪያው በመጨረሻው በ1382 ዓ.ም. የኦቶማን ቱርክ መንግሥት ክፍል ሆነ። እስከ ዛሬም ድረስ በቱርክ አገር ምዕራብ ይገኛል። ግርጌ ነጥቦች ዋቢ ድረ-ገጾች . የአለሙ መጀመርያ መሐለቅ (እንግሊዝኛ) ታሪካዊ አናቶሊያ
18217
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%88%8A%E1%8D%92%E1%89%B5-%E1%8A%A5%E1%88%BD%E1%89%B3%E1%88%AD
ሊፒት-እሽታር
ሊፒት-እሽታር በሱመር የኢሲን ሥርወ መንግሥት 5ኛው ንጉሥ ነበረ (1833-1823 ዓክልበ. የነገሠ)። በርሱ ዘመን መጀመርያ የኢሲን ተወዳዳሪ የላርሳ ንጉሥ ጉንጉኑም ኡርን ከኢሲን ያዘ። ሊፒት-እሽታር በተለይ የሚታወቀው በ1832 ዓክልበ. ባወጣው ሕገ መንግሥት ምክንያት ነው። ይህ ሕገ ፍትሕ ከላጋሽ ንጉስ ከኡሩካጊና ሕግጋት በኋላ፣ ከኡርም ንጉሥ ከኡር-ናሙ ሕግጋት በኋላ የወጣ ሲሆን ለሱመር ሦስተኛው የሚታወቀው ሕገ መንግሥት ነው። በሱመራዊ ነገሥታት ዝርዝር ላይ ፲፩ ዓመታት እንደ ነገሠ ሲለን ከዘመኑ ፲ የዓመት ስሞች ብቻ ይታወቃሉ። ከመጀመርያው ዓመቱ በቀር ግን የሌሎቹ ዓመታት () ቅድም-ተከተላቸው እርግጥኛ አይደለም። ከነዚህም መካከል ለምሳሌ፦ ፩ ፦ (1833 አክልበ. ግድም) ሊፒት-እሽታር ንጉሥ የሆነበት ዓመት ፦ (1832 አክልበ. ግድም) ኤኒንሱንዚ የዑር ጣኦት መቅደስ ሴት ካህን የመረጠበት ዓመት ፦ ሊፒት-እሽታር ፍትሕ በሱመርና አካድ ያደረገበት ዓመት ፦ በጣኦታቱ (ኤንሊልና ናና) ትዕዛዝ ኡር የታደሰበት ዓመት ፦ ማረሻ የተሠራበት ዓመት ፦ (1826 አክልበ. ግድም?) ሊፒት-እሽታር አሞራውያንን ያሸነፈበት ዓመት በተወዳዳሪው ጉንጉኑም ፲፫ኛው ዓመት (1832 ዓክልበ.)፣ የሊፒት-እሽታር ሴት ልጅ ኤኒንሱንዚ የዑር መቅደስ ጣኦት ሴት ካህን ሆና እንድትሾም አረጋገጠ። ስለዚህ የሊፒት-እሽታር ዓመት «» ከዚያ በኋላ ሊሆን አይችልም። በ1826 ዓክልበ.፣ ጉንጉኑም «የመንገድ ቤት» እንደ ያዘና ቦይ እንደ ከፈተ ይዘገባል። እነዚህ ድርጊቶች ደግሞ በሊፒት-እሽታር ሰነዶች ይጠቀሳሉ። የሊፒ- እሽታር ሻለቃ ናና-ኪአጝ በጻፉለት ደብዳቤ ዘንድ፣ ፮ መቶ የጉንጉኑም ወታደሮች «የመንገድ ቤት» ይዘው አዲስ ቦይ ሊከፈቱ ነው ሲል የሊፒት-እሽታርን እርዳታ ይለምናል። በሊፒት-እሽታር መልስ ፪ ሺህ ጦረኞች፣ ፪ ሺህ ቀስተኞች፣ እና ፪ ሺህ ባለ ዶማዎች መላኩን አመለከተ። ጉንጉኑምን ድል እንዳደረጉ አይመስልም፤ ጉንጉኑምም «የሱመርና አካድ ንጉሥ» የሚለውን ማዕረግ ይግባኝ ነበረው፤ ኢሲን ግን ለጊዜው ነጻነቱን ጠበቀው። የሊፒት-እሽታር ሕግጋት (1832 ዓክልበ.) ጽሑፉ በብዙ ፍርስራሽ ላይ ተገኝቷል። በሙሉ የተገኙት ሕግጋት የሚከተሉት ናቸው። §8 ሰው አትክልት እንዲትክልበት መሬቱን ለባልንጀራው ቢሰጥ፣ ባልንጀራውም መሬቱን በሙሉ ካልተከለበት፣ ያልተከለበትን መሬት ለባለቤቱ ሰው ከነድርሻው ይመልሰው። §9 ሰው ወደ ባለቤቱ አትክልት ቦታ ገብቶ በዚያ በስርቆት ቢያዝ፣ 10 ሰቀል ብር ይክፈል። §10 ሰው በባልንጀራው አትክልት ቦታ ዛፍ ቢቆርጥ፣ ግማሽ ሚና ብር ይክፈል። §11 በሰው ቤት አጠገብ የባልንጀራው ምድረ በዳ ካለ፣ ባለቤቱም ለባለ መሬቱ «መሬትህ ባዶ ስለ ሆነ ሌባ እቤቴ ሰርቆ ቢገባስ፤ ቤትህን አጥና» ብሎ ቢነግረው፣ ይህም ስምምነት ከተረጋገጠ፣ ባለ መሬቱ ለባለ ቤቱ ማንኛውን የጠፋውን ንብረት ያተካል። §12 የሰው ገረድ ወይም ባርያ ወደ ከተማው መሃል ቢሸሽ / ብትሸሽ፣ በሌላ ሰው ቤት ላንድ ወር እንደ ኖረ(ች) ከተረጋገጠ፣ በባርያው ፋንታ ባርያ ይስጠው። §13 ባርያ ከሌለው፣ 15 ሰቀል ብር ይክፈል። §14 የሰው ባርያ ባርነቱን ለጌታው ሁለት እጥፍ እንደ ረከበው ከተረጋገጠ፣ ያው ባርያ ነፃ ይወጣል። §15 ሚቅቱም (አገልጋይ) የንጉሥ ሥጦታ ከሆነ፣ አይወሰደም። §16 ሚቅቱም በነጻ ፈቃዱ ወደ ሰው ቤት ቢሄድ፣ ያ ሰው ከግድ ሊይዘው አይችልም፤ ወደ ወደደበትም ሊሄድ ይችላል። §17 ሰው ያለ ፈቃድ ባልንጀራውን የማያውቅበት ነገር ውስጥ ካሰረው፣ ባልንጀራው ግድ የለውም፣ ሰውዬውም ባሰረው ነገር ውስጥ ቅጣቱን ይሸክማል። §18 የርስት ባለቤት ወይም የርስት እመቤት የርስቱን ግብር መክፈል ካልቻለ(ች)፣ ሌላ ሰውም ከከፈለው፣ ባለቤቱ ለሦስት ዓመት ለቆ እንዲወጣ አይገደድም። ከዚያ በኋላ ግብሩን የከፈለው ሰው ርስቱን ይይዛል፣ የቀድሞውም ባለ ርስት ምንም ይግባኝ አያነሣም። §22 አባትዬዋ እየኖረ፣ ሴት ልጂቱ የቤተ መቀደስ አገልጋይም ሆነ ሠራተኛ ብትሆን፣ እቤተሠቡ እንደ አንዲት ወራሽ ትኖራለች። §24 ሰው ያገባት ሁለተኛው ሚሥት ልጆች ከወለደችለት፣ ከአባትዋ ቤት ያመጣችው ጥሎሽ ለልጆችዋ ይሁን፣ ዳሩ ግን የመጀመርያይቱ ሚስቱ ልጆችና የ2ኛይቱ ልጆች የአባታቸውን ርስት በእኩልነት ይካፈሉ። §25 ሰው ሚስቱን ገብቶ ልጆችን ወልዶ እነዚያም ልጆች በሕይወት ቢሆኑ፣ ከዚህም ሌላ ደግሞ ባርያይቱ ለጌታዋ ልጆች ከወለደችለት፣ አባቱም ደግሞ ለባርያይቱና ለልጆችዋ ነጻነትን ከሠጣቸው እንደ ሆነ፣ የባርያይቱ ልጆች ግን ርስቱን ከቀድሞው ጌታቸው ልጆች ጋር አይካፈሉም። §27 የሰው ሚስት ልጆችን ካልወለደችለት የአደባባይ ሸርሙጣ ግን ልጆች ከወለደችለት፣ እርሱ ለዚያች ሸርሙጣ እህልን፣ ዘይትንና ልብስን ያስገኛል። ሸርሙጣዋ የወለደችለት ልጆች ወራሾቹ ይሆናሉ፤ ሚስቱ እየኖረች ግን ሸርሙጣዋ እቤቱ ከሚስቱ ጋር ከቶ አትኖርም። §29 አማች ወደ ዐማቶቹ ቤት ገብቶ፣ ከዚያም ከቤቱ አስወጥተውት ሚስቱንም ለባልንጀራው ለመስጠት ቃል ከገቡ፣ አማቹ ያመጣውን ስጦታዎች በሙሉ ይመልሱለትና ሚስቱ ባልንጀራውን ልታገባ ሕጋዊ አይሆንም። §34 ሰው በሬን ተከራይቶ ሥጋውንም በአፍንጫው ቀለበት ከቀደደው፣ የዋጋውን ሲሶ ይክፈል። §35 ሰው በሬን ተከራይቶ ዓይኑንም ካጎዳ፣ የዋጋውን ግማሽ ይክፈል። §36 ሰው በሬን ተከራይቶ ቀንዱን ከሰበረው፣ የዋጋውን ሩብ ይክፈል። §37 ሰው በሬን ተከራይቶ ጅራቱን ካጎዳ፣ የዋጋውን ሩብ ይክፈል። ዋቢ ምንጮች የኢሲን ነገሥታት የመስጴጦምያ ታሪክ ሕገ መንግሥታት
46470
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8B%88%E1%88%8D%E1%89%83%E1%8B%AD%E1%89%B5
ወልቃይት
ወልቃይት ጠገዴ ማነው? “የወልቃይት ባህልና የማንነት ጥያቄ” የሚለው ፅሁፋ በገጽ 4, 2ኛው አንቀጽ ላይ “ስለዚህ የትግራይ ነጻ አውጭ ግንባር ወልቃይትን ከተቆጣጠረበት ጊዜ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ ያለውን ታሪክ በዜሮ ብናባዛው፤ የህዝበ-ውሳኔው ውጤት ከትግራይ ጋር መኖር የሚሹ ወልቃይቴዎች በሰፊ ልዩነት ሊያቸንፉ መቻላቸውን ያበስር ነበር” ይላል። ነገር ግን ይህ የአቶ ሃይሉ የሺወንድም ምኞትና ድምዳሜ ወይም ህወሃታዊ ተልዕኮ ከታሪክና ከተጨባጩ የወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ አቋምና ምርጫ ፍጹም እንደሚቃረንና እንደሚጋጭ በሁለት ቀደምት የህወሃት አባላት የቀረቡ ምስክርነቶች አጥጋቢ መልስ ስለሚሰጡ እነርሱን ኢትዮጵያውያን እንደ ዛሬው ህወሃት በለጠፈብን የብሔር ታርጋ ምክንያት የጎሪጥ መተያየት ሳንጀምርና ሃገራችን ጎጥ ጎጥ ከመሽተቷ 37 ዓመታት በፊት በትግራይ ነጻ አውጭ ቡድን በኩል ለወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ የቀረበው “ወልቃይት ጠገዴ ማነው?” ጥያቄ በወቅቱ የነበሩት ኩሩና በማንነታቸው ላይ ፍጹም ብዥታ ያልነበራቸው ወገኖቻችን የህወሃት ወኪል ለነበረውና ጥያቄውን ይዞ ለመጣው ለአቶ መኮንን ዘለለው በማያዳግም ሁኔታ መልሰውለት እንደነበር ታሪክ ህያው ምስክር ነው። በወቅቱ የነበረውን ሁኔታ የህወሃት ነባር አባልና የፋይናንስ ኋላፊ የነበሩት አቶ ገብረመድህን አርአያ በዲሴምበር 22, 2015 ኢትዮ- ሚዲያና ጎልጉል ድረ-ገፅ ላይ “በወልቃይት ጠገዴ፤ ጠለምት በአማራው ላይ ህወሃት የፈጸመው የዘር ማጽዳት ወንጀል” በሚል ባወጡት ጥልቅ ሰነድ በገጽ 2 ላይ፤ “በሪጅን 1 የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ የነበረው፣ በአባቱ ወልቃይት ፀገዴ፣ በእናቱ ሽሬ የሆነው መኮንን ዘለለው፣ የተወጠነውን ትልእኮ ይዞ ወልቃይት ፀገዴ ፀለምት እየተዘዋወረ ህዝቡን በመሰብሰብ ይህ መሬት የትግራይ መሬት ስለሆነ እናንተ ከእንግዲህ ወዲህ የሰሜን ጎንደር ዜጎች አይደላችሁም፣ የትግራይ መሬት ስለሆነ እንኖራለን ካላችሁ ትግሬዎች መሆናችሁን አምናችሁ ተቀበሉ፤ የትግራይ ዜጎች አይደለንም፣ ሰሜን በጌምድር የትግራይ አይደለም ካላችሁ ደግሞ የድርጅቱን የህወሓትን ውሳኔ ተጠባባቁ፤ የምታምኑበትን አሁን ተናገሩ በማለት ሲያስጠነቅቅ፣ ከህዝቡ በኩል ያገኘው መልስ ግን አንድ ነበር። የቀረበውን ሃሳብ ከህፃን እስከ አዋቂ፣ የወልቃይት ፀገዴና የፀለምት ህዝብ፣ እኛ የሰሜን በጌምድር (ጎንደር) አማሮች እንጂ ትግሬዎች አይደለንም፣ የታሪካችን ስር መሰረቱ የበጌምድር አማሮች ነን። ይህ ቆመህ የምትናገርበት መሬት ሰሜን በጌምድር ይባላል። ከጥንቱ ታሪካችን 3 ብትነሳም ይህ መሬት ታሪካዊ ነው። ያለፉት የኢትዮጵያ ነገሥታት ከጥንት ጀምሮ እስከ አሁኗ ሰአት በመንግሥት እውቅና ያገኘ የጎንደር፣«”የበጌምድር” ጠቅላይ ግዛት እየተባለ የሚጠራ ነው። ዋና ከተማችን ደግሞ ጎንደር ነው። የእናንተም ትግራይ ጠቅላይ ግዛት ይባላል፣ ዋና ከተማው ደግሞ መቀሌ ነው። ስለዚህ ኣናንተ የተሓህት ታግዮች ጉዳዩን ብታሱብበት ጥሩ ነው። ወደ እርስ በርስ ግጭ ያመራል።በተጨማሪም ታሪካዊ የወሰን ክልል አለን፣ እሱም ተከዜ ወንዝ ነው። የትግራይና በጌምድር የድንበር ክልሉ ተከዜ ወንዝ ነው። ከጥንት ጀምሮ የሁለቱ ኢትዮጵያውያን የድንበር ወሰን መሆኑን ልናረጋግጥ እንፈልጋለን በማለት በአንድነት ድምፅ ህዝቡ ራሱ አረጋገጠ።” በማለት ገልፀውታል። ይልቁንም በአቶ መኮንን ዘለለው በኩል ለቀረበላቸው የማንነት ጥያቄ “የበጌምድር አማሮች ነን” የሚለውን የማያወላዳ ምላሽ የሰጡ የማህበረሰቡ ታላላቅና የተከበሩ መሪዎች በአቶ ስዩም መስፍንና በአቶ ግደይ ዘራፅዮን መሪነት ታፍነው ወደ ትግራይ መወሰዳቸውንና በሳሞራ የኑስ ትእዛዝ እንደተረሸኑ እራሳቸው አቶ መኮንን ዘለለው ለኢሳት ቴሌቭዥን በሰጡት ቃለ-መጠይቅ ላይ በዝርዝር አጋልጠዋል። በዚህ “ወልቃይት ጠገዴ ማነው?” በሚለው የህወሃት ያልተቋረጠ ጥያቄ ዙሪያና ህዝባችን በሚሰጣቸው አንድ፤ ግልፅና ቀጥተኛ መልስ ምክንያት ወገናችን የጅምላ ግርፋቶች፤ መፈናቀሎች፤ እስራቶች፤ ግድያዎች፣ ስደቶች፣ ቅስም ሰባሪና፣ ፀያፍ በደሎች ተፈፅመውበታል። ታዲያ ይህ ሁሉ ሰቆቃ አሁንም ሳያባራ የትግራዩ ነጻ አውጭ ቡድን እነሆ ዛሬም እንደገና በእነ አቶ ሃይሉ የሺወንድም በኩል “ወልቃይት ጠገዴ ማነው?” ይለናል። አስቀድሞ በአቶ መኮንን ዘለለው በኩል ቀርቦ ህዝባችንን ለእልቂት የዳረገው ህወሃታዊ ጥያቄ ዳግም ለወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ መጠየቅ ማለት አንድም ወገኖቻችን በማንነታቸው ጸንተው በመቆማቸው ምክንያት የከፈሉትን መስዋእትነት እንደ “ውሻ ደም” በመቁጠር ለመሳለቅ ወይም በህዝባችን ላይ ለተደገሰው ቀጣይ ህወሃታዊ ፍጅት ሰበብ ለማዛጋጀትና የጥፋት መንገድ ለመጥረግ የታለመ የህወሃት ሆድ-አደሮች ምን እያሉን ነው? ወልቃይት ጠገዴ ማነው? ለሚለው የህወሃት መላዘን ወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ ምላሹ ከላይ በአይን እማኞችና በህያው ምስክሮች እንደተረጋገጠ አይተናል። ታዲያ ለምን የዛሬዎቹ ተላላኪዎች “ስለዚህ የትግራይ ነጻ አውጭ ግንባር ወልቃይትን ከተቆጣጠረበት ጊዜ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ ያለውን ታሪክ በዜሮ ብናባዛው፤ የህዝበ-ውሳኔው ውጤት ከትግራይ ጋር መኖር የሚሹ ወልቃይቴዎች በሰፊ ልዩነት ሊያቸንፉ መቻላቸውን ያበስር ነበር” እያሉ ሌላውን ህዝብ ለማደናገር ይሞክራሉ? ለምንስ በወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ በደል ላይ ይዘባበታሉ? የሚል ጥያቄ መነሳቱ አይቀርም። ከዚህ የሆድ አደሮች ዘመቻ የምንረዳው ነገር ቢኖር ተላላኪዎቹ ቀደም ሲል በተደጋጋሚ እንገልጸው እንደነበረው ሁሉ ከህወሃት የተሰጣቸውን “የወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብን በማዳከምና በመከፋፈል ትግሪያዊነትን አሜን ብሎ እንዲቀበል” የማስቻል ተልእኮ ለማሳካት በሚል በመላው ኢትዮጵያ በተለይም እንደ ጋምቤላ ባሉ አካባቢዎች በሚደረጉ የመሬት ዘረፋዎችና ቅርምቶች (ወልቃይት ጠገዴ ለትግራውያን ብቻ ነው) ቢንበሻበሹም ውጤቱ ግን “ጉም መዝገን” ሆኖባቸዋል። ይልቁንም በሃገር ውስጥ የሚገኘው የወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ ከምንግዜውም በላይ ተደራጅቶና ከመላው የአማራ ህዝብ ጋር አንድ ሆኖ ማንነቱ ለማስከበር ቆርጦና አምርሮ ሲነሳ ከህወሃት ይልቅ የተጨነቁት በወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ ስም ድርጎ ሲቀበሉ የከረሙት ናቸው። ከህወሃት በኩል ልምጭ የተቆረጠበት የሚመስለው ሆድ-አደሩ ቡድን መላውን የኢትዮጵያ ህዝብ ያንገሸገሸውንና ህወሃትን እስከ አንገቱ ያነቀውን፤ ይልቁንም በህወሃት/ኢህአዴግ መንደር እውቅና አግኝቶ ከጠ/ሚ እስከ ተራ ካድሬ እየተቀባበለ የሚዘምርለትን “የመልካም አስተዳደር እጦት” በምትባል “የጦስ ዶሮ” በመታከክ የወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ ያነሳውን ዘርንና ትውልድን ከጥፋት የመታደግና የአማራ ማንነቱን በትግሪያዊነት ከመተካት የማዳን ፈርጀ ብዙ ጥያቄ “የትግራይ ክልል ባለስልጣናት የአስተዳደር በደል ስለፈጸሙበት” ነው እያሉ ማፌዝ በወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ ቁስል በእሳት የጋለ ብረት እንደመስደድ ይልቅስ አቶ ሃይሉና የጥቅም ተጋሪዎቻቸው በወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ ላይ የደረሰው በደል የዘር ማፅዳትና በትግሪያዊነት የመተካት ዓለም-አቀፍ ወንጀል መሆኑን የምትስቱት አይመስለንም። ይህን በማንነታችን ላይ የተፈጸመና በዓለም-አቀፍ የፍርድ አደባባይ የሚያስጠይቅን ወንጀል በማኮሰስና “የትግራይ ክልል ባለስልጣናት የአስተዳደር በደል” አድርጎ በማቅረብ ከህወሃት ጋር የገጠማችሁን ኪሳራ ማወራረድ ወይም የሚቆረጥላችሁን ድርጎ ማሳደግ አትችሉም። ኪሳራችሁን ማወራረድም ሆነ ሌላም ማድረግ የምትችሉት ለጌቶቻችሁ እውነቱን በመናገር ብቻ ነው። ምክንያቱም የወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ ጎንደሬ-አማራ መሆኑን በአንድ ድምጽ ያረጋገጠውና በማንነቱም ምክንያት ለሚመጣ ማንኛውም ነገር ዋጋ ለመክፈል ዝግጁነቱንና ቁርጠኝነቱን በተግባር ያሳየው ገና “የትግራይ” የሚባሉ ገዥዎችና አስተዳደራቸው ከመፈጠሩ እጅግ አስቀድሞ እንደነበር ከወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ ባልተናነሰ እነ ስብሃት ነጋ ጠንቅቀው ያውቃሉና እራሳችሁን አታታልሉ። ትዝብት ላይም በሌላ በኩል ምንም እንኳ ዛሬ ህወሃት እስከ አፍንጫው ቢታጠቅና የሃገሪቱን መንግስታዊ ስልጣንና ሃብት እንዳሻው ቢያዝና ቢናዘዝበትም የወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ ዛሬም በማንነቱ ላይ ያለውን የቀደመ ጽኑ እምነትና የትውልዱን ምስክርነት ማስለወጥ አልተቻለውም። እንግዲህ ለህወሃትና ለእነ አቶ ሃይሉ የሺወንድም እውነታው እንደ እሬት መራራ ቢሆንባቸውም ታሪክ በደማቁ የመዘገበውና በእያንዳንዱ የወልቃይት ጠገዴ ተወላጅ ህሊና ተጽፎ የሚገኘውና ለትውልድ የምናስተላልፈው እውነታ ግን የወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ ህወሃት ዕርስታችንን ከመርገጡ በፊትም ሆነ በወረራ በተቆጣጠረ ጊዜ በጎንደሬ-አማራነቱ ጸንቶ በመቆም መራር መስዋእትነት እንደከፈለ ሁሉ ወደፊትም በማንኛውም የከፋ ፈተና ውስጥ ቢያልፍም ከጎንደሬ-አማራነቱ ሊያናውጸው የሚችል ምንም አይነት ምድራዊ ሃይል ያለመኖሩን ነው። ምክንያቱም ወልቃይት ጠገዴ አይደለም ለማንነቱና ለዕርስቱ፤ አምነው ለተጠጉትም አንገት እንደማያስደፋ ትግራውያን ያውቃሉ! ታዲያ ወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ ማነው? “በአፍ የመጣን በአፍ፣ በመጣፍ የመጣን በመጣፍ” መመለስ የቀደሙ አባቶቻችን ስርዓትና ብሂል በመሆኑና ታሪካዊ ጠላቶቻችንም እንደ አመጣጣቸው መመለስ ተገቢ በመሆኑ ህወሃት በተላላኪዎቹ በኩል በወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ መካከል ሊዘራ የሞከረውን እንክርዳድና በኢትዮጵያ ህዝብና በታሪካችን ላይ ሊፈጠር የታሰብውን ብዥታ ለማጥራት ሲባልና ለታሪክም ምስክር ይሆን ዘንድ “የወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ ማነው?” የሚለውን ጥያቄ በአጭሩ እንደሚከተለው ስንመልስ ጥልቁንና ተነግሮ የማይጠገበውን የወልቃይት ጠገዴና ጠለምት ታሪክ ለታሪክ ፀሃፊዎችና ለባለሙያዎች በመተው ነው። 1. የወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ እንደ ማንኛውም የሰሜኑ ኢትዮጵያ ማህበረሰብ ሁሉ የአካባቢውን ስያሜ በመውሰድ የእራሱ መጠሪያ አድርጎ ኖሯል። ለምሳሌ የጎንደሬ ዘሩ ምንድነው? የሚኖርበት አካባቢ ስያሜ ማን ይባላል? የጎጃሜውስ? የወሎዬው? የጋይንቴው? የምንጃሬው? የስሜንኛው? … ወዘተ ለመሆኑ እነዚህ ወገኖቻችን እራሳቸውን ሲጥሩ “እኛ ማነን” ይላሉ? እኛስ እነርሱን እነማን ናቸው እንላለን? ጎንደሬውን – ጎንደሬ ፤ ጎጃሜውን – ጎጃሜ ፤ ወሎዬውን – ወሎዬ፣ ደብረታቦሬውን – ደብረታቦሬ፤ ጋይንቴውን – ጋይንቴ፤ ስሜንኛውን – ስሜንኛ፤ በለሴውን – በለሴ፣ ወግሬውን – ወገሬ፣ ቋረኛውን – ቋሬ …. ወዘተ እያልን ወልቃይቴውን – ወልቃይቴ፣ ጠገድቼውን – ጠገድቼ፣ ጠለምቴውን – ጠለምቴ አላልንምን? እንላለን እንጂ! 2. ታዲያ የወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ አባቱ ማነው? የዘር ሐረጉስ ከየት ይመዘዛል ቢሉ? ወልቃይት የሚለው ስም ከስር መሰረቱ የአማራ መስራች አባት የሚባለው የተጠቀሰበት አገር ነው። አማራው ከወልቃይት ወደ ጠለምት ከዚያም ወደ ላኮ መልዛ (የዛሬው ወሎ) እያለ ሌላውን አካባቢ እያስፋፋ እስከ ሞቃዲሾ ተጉዞ ሃገር ያቀና ታላቅ ነገድ ያረፈበት መሆኑ ታሪክ ሁሌም ይመሰክራል። ወልቃይት ጠገዴ አማራ የሆነው ዛሬ ትግሬ ሊያደርጉት እንደሚታትሩት በተዘዋዋሪ ሳይሆን የአማራ አባትና ግንድ በመሆን ነው። ለዚህ ፅሁፍ በሚስማማ መልኩ ታሪካዊ ማስረጃዎችን እንመልከት። አለቃ ታዬ ወልደማርያም የተባሉ ሊቅና የተመሰከረላቸው ታሪክ ፀሃፊ “የኢትዮጵያ ህዝብ ታሪክ” በተባለው ዝነኛ መፅሃፋቸው በገፅ 16 ላይ እንዲህ ፅፈዋል። “ከለው ከሳባ ወደ ምዕራብ ወደ ደቡብ ያለ ያማራ የወልቃይት የጠገዴ አባት ነው። ከእነዚህም የኢትዮጵስ ልጆች የወንድማማቾቹ ነገድ ህዝብ ሁሉ በመልካቸውና በቁርበታቸው ይመሳሰላሉ። እኒህም ህዝብ የያዙት አገር በጥቅሉ ባባታቸው ስም ኢትዮጵያ ተብሎ ይጠራል።” በመቀጠልም የአማራው አባት አስገዴ ግንዱ ከወልቃይት ጠገዴ አርማጭሆ ከዚያም እያደገና እየሰፋ አማራ ሳይንት ድረስ የደረስ መሆኑን ገልጸው ጽፈዋል። አቶ አማረ አፈለ “ደም አይፍሰስ በቃ የህወሃት ማኒፌስቶ ያብቃ!” በሚለው መፅሐፋቸው በገጽ 27 ታሪካዊ ምስክርነታቸውን እንደሚከተለው አስፍረዋል። “ከተከዜ ጀምሮ ወደ ደቡብ እስከ ሸላሎ በተዘረጋው ምድር ላይ ያሉት ወረዳዎች ሕዝቡ አፍ መፍቻ ቋንቋው አማርኛ ነው። ከትግራይ ጋር በተከዜ ወንዝ ድልድይነት ጎረቤት ስለሆነ ወዲያና ወዲህ ማዶ ያለው የዐማራና የትግራይ ቋንቋ ቃላት ቢያንስ 80 በመቶ ተመሳሳይ በመሆናቸው መናገሩ አዳጋች አይሆንባቸውም። ይልቁንም የወልቃይት ጠገዴና ጠለምት መዘጋዎች ጥጥ ስለሚያመርት ብዙ የትግራይ ተወላጆች በጥጥ ለቀማ ወቅት በየዓመቱ ወደነዚህ መዘጋዎች ይመጣሉ። ዐማሮች ከእነርሱ ጋር ለመግባባት ሲሉ ትግርኛውን ይጠቀሙበታል። ከእንግዶች መካከል ሀገሬውን አግብተው የሚቀሩም አይጠፉም። ለዚህም ወደ ኋላ መለስ ብለን ታሪክ ስንመረምር ወልቃይት ጠገዴና ጠለምት በአክሱም፤ በላስታው በሽዋ ሆነ በጎንደር ዘመነ መንግሥት አንድም ግዜ የትግራይ ግዛት አካል ወይም ገባር የሆነበት የታሪክ ወቅት የለም። ይህን እውነት ለመረዳት ከጎንደር ዘመነ መንግሥት በፊት ጀምሮ 20ኛ ምዕተ ዓመት ሁለተኛ አጋማሽ ድረስ የታወቁ የውጭ ሀገር ጉብኝዎችና ታሪክ ፀሐፊዎች በተለያዩ ክፍለ ዘመናት ኢትዮጵያን እየተዘዋወሩ ካዩ በኋላ ስለ ብሔረስቦችና ስለ አስተዳደር ክፍሎች የተውልን ጹሑፎችና ካርታዎች ህያው የታሪክ ማስረጃዎች ናቸው።” “ለአብነት ያህል ፍራንሲስኮ አልቫሬዝ፤ ጅምስ ብሩስ፤ ዶክተር ሚካኤል ረሥል፤ ማንስፊልድ ፓርኪንስ፤ ስቨንረንሰን ወዘተ…….የተባሉ ታዋቂ ተመራማሪዎች ለትውልድ ያበረከቷቸውን መጻሕፍት መመልከት ይቻላል። ይልቁስ የኢጣሊያን መንግሥት ኢትዮጵያን በ1928 ዓ/ም ከመውረሩ በፊት በጐንደር ከተማና በሌሎች ከተሞች በከፈታቸው የቆንስል ቢሮዎች አማካይነት ባካሄደው ሰፊ የኢትዮጵያ ብሔረሰቦች ጥናት ባወጣው አስተዳደር መዋቅር ትግራይ ከኤርትራ ጋር ሲደርብ ጠገዴንና ጠለምትን የአማራ ክልል በማድረግ ትግሬ አለመሆናቸውን
50302
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8A%A0%E1%89%A3%20%E1%8C%8A%E1%8B%AE%E1%88%AD%E1%8C%8A%E1%88%B5%20%E1%8B%98%E1%8C%8B%E1%88%B5%E1%8C%AD
አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጭ
ኢትዮጵያዊው ሊቅና ጻድቅ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጭ የተወለዱት በ፲፫፻፶፯ ዓ.ም. በወሎ ክፍለ ሀገር በቦረና ወረዳ ሸግላ/ሰግላ በተሰኘች ቦታ ነው ። አባታቸው ሕዝበ ጽዮን ከተከበሩ መምህራን ወገን የሆኑ የቤተ መንግሥት ባለሟል ፤ መጽሐፍትን የሚያውቁ ጥበብ የተሞሉ ሲሆን የሰግላ አገረ ገዢም ነበሩ ። እናታቸው እምነጽዮንም ከወለቃ ሹማምንት ወገን የሆኑ ደግ ሰው ነበሩ ። ሲጀመር እናታቸው ፈሪሃ እግዚአብሔርን እያስተማሩ በጥበብና በዕውቀት አሳደጓቸው ። አባ ጊዮርጊስ የተመረጠ የሆነ ሰማዕቱን ቅዱስ ጊዮርጊስን በመማፀን የተወለዱ ልጃቸው ስለሆኑ እንደሰማዕቱ የእውነት ምስክር እንዲሆኑላቸው በመመኘት ስማቸውን ጊዮርጊስ ብለው ጠርተዋቸዋል ። ከተወለዱበትም ሀገር በመነሳት ጊዮርጊስ ሰግላዊ ተብለው ሲጠሩ በጊዮርጊስ ዘጋስጭና በጊዮርጊስ ሰግላዊ መካከል ምንም ልዩነት የለም ። የአባ ጊዮርጊስ አባት ሕዝበ ጽዮን በቤተ መንግሥት በንጉሡ ስዕል ቤት ከሚያገለግሉት ካህናት ጋር ይሠሩ ስለነበር ልጃቸው በመልካም አስተዳደግና የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት በማስተማር በዕውቀት አሳድገዋቸዋል ። በድቁናም አሹመዋቸዋል ። ከዚያም በኋላ በንጉሥ ዳዊት ዘመን በደብረ ሐይቅ ባሕር ወደምትገኘው የቅዱስ እስጢፋኖስ አባ እየሱስ ሞዐ ገዳምና ታዋቂ ትምህርት ቤት ወስደው ከታላቁ ዓቃቤ ሰዓት አባ ሠረቀ ብርሃን ጉባዔ ተቀላቅለው እንዲማሩ አድርገዋል ። ይሁን እንጂ አባ ጊዮርጊስ በትምህርት ቤቱ የሚሰጡትን የቀለም ትምህርቶች ቶሎ ለማጥናት አልቻሉም ። ወደ ኋላ የመቅረታቸው ዋናው ምክኒያትም አባ ጊዮርጊስ ከመማሩ ይልቅ የማረካቸው በሥራ እየደከሙ የገዳሙን አባቶች መርዳትና የብትህውናው ሕይወት መሆኑ ነው ። ጉዋደኞቻቸው በትምህርት ሲቀድሙአቸው ባዩ ጊዜ እጅግ አዘኑ ። በጾምና ጸሎትም ወደ እግዚአብሔር ጮሁ በፍፁም ልባቸውም አምነው ብርቱ ልመናን ከእመቤታችን ሥዕል ፊት ቁሞ በጠለቀ ተመስጦልቦና እንባን በማፍሰስ ወደ እግዚአብሔር " የአባቶቻችን አምላክ የምህረት ጌታ ሁሉን በቃልህ የፈጠርክ ሰውንም በረቂቅ ጥበብህ የፈጠርክ አቤቱ አንተ ከልዑል ጌትነትህ ጥበብን ስጠኝ በእውነትም አትናቀኝ እኔ ባሪያህ ነኝ የባሪያህም ልጅ ነኝና " በማለት ለመኑ ። ከዚህም በኋላ የዓለም ንግሥት የአምላክ እናት ተገለጸችላቸው ። በነሐሴ ፳፩ ቀንም ወደርሳቸው መጣች ፣ በዕውቀትና በትምህርት የሚተጉበትን ኃይል ሰጠቻቸው ። ከዚያም የዜማ የቅኔና የመጽሐፍትን ትርጉዋሜ ትምህርታቸውን በሚገባ አጠናቀቁ ብዙ መጽሐፍትንም ደረሱ ። በዚህም በቀሰሙት ዕውቀታቸው በዜማ በኩል ከቅዱስ ያሬድ ቀጥለው የሚጠሩ አባ ጊዮርጊስ ናቸው ። በቤተመቅደስም ዘማሪ ማኅሌታይ ተብለው ይጠራሉ ። በዚያም ዘመን ለነገሥት ፣ ለካህናት ፣ ለመኳንንት ፣ ለንቡራነእድ ፣ ለመሳፍንት ፣ ለሁሉም የቤተመንግሥት ሠራተኞች አስተማሪ ሆኑ ። በአንድ ወቅት ግብፃዊው ጳጳስ አቡነ በርተሎሜዎስ “ሥላሴን አንድ ገጽ” ብለው ያምናሉ ተብለው በተከሰሱ ጊዜነገሩን እንዲያጣሩ ከተመረጡት ከቄስ ሐፄ ተከሥተ ብርሃንና ከሐይቁ መምህር ከዐቃቤ ሰዓት ዮሴፍ ጋር አብሮ ተልኮ ነበር፡፡ እነዚህ ሦስት አበውጳጳሱን ካነጋገሩ በኋላ ክሱ ውሸት መሆኑን በማረጋገጥ ስለ ምሥጢረ ሥላሴ የሚገልጠውን የጳጳሱን እምነት በጽሑፍ ይዘው መጡ፡፡ ሊቅነታቸውን የተረዱት ዓፄ ዳዊት አባ ጊዮርጊስን ወደ ቤተመንግሥታቸው በማስገባት የስምንቱም ልጆቻቸው መምህር አድርገዋቸው ነበር ። ከእነርሱም ውስጥ ቅዱስ የተባለው ንጉሥ ቴዎድሮስ እንዲሁም በተለያዩ ጊዜ የነገሡት ንጉሥ እንድርያስ ፣ ዓፄ ይስሐቅ ፣ ንግሥት እሌኒ እና ዓፄ ዘርአ ያዕቆብ ይገኙበታል። ዐፄ ዳዊት በጋብቻ እንዲዛመዱዋቸው ጥረው ነበር ነገር ግን አባ ጊዮርጊስ ራሳቸውን የመንግሥተ ሰማያት ጃንደረባ ማድረግን ስለመረጡ በማስተማሩና በብሕትናው ጸንተው የአመክሮ ጊዜያቸውን ሲጨርሱ አቡነ በጸሎተ ሚካኤል ገዳም ገብተው መንኩሰዋል ። በዘመኑ ለተነሱ ለሁሉም የሃይማኖት ችግሮች አጥጋቢ መልስ በመስጠት የተዋህዶ ጠበቃ ፣ አይሁድን እና ሌሎች መናፍቃንን በጉባዔ ያሳፈሩት ሊቅ ክፉዎችና ምቀኞች በየጊዜው እየተነሱ መከራን ያደርሱባቸውና ይከሱዋቸው ነበር ። በአንድ ወቅት በሸዋ ይፋት ራሳቸውን ቤተ እስራኤል እያሉ የሚጠሩ አይሁድ ነበሩ ፡፡ ከአቡነ ዜና ማርቆስ ጀምሮ ብዙ መምህራን ወደነዚህ ሕዝቦች እየተሠማሩ ወንጌልን አስተምረዋል ፡፡ አቡነ ዜና ማርቆስ ወደ ክርስትና ለተመለሱት ቤተ እስራኤላውያን በእመቤታችን ፣ በቅዱስ ሚካኤል ፣ በአባኖብና በሰማዕቱ በጊጋር ስም አራት አብያተ ክርስቲያናትን አሠርተው ነበር ፡፡ ሁለቱ የመጀመሪያዎቹ አሁንም አሉ ፡፡ ይህ ሁሉ ቢሆንም ቤተ እስራኤላውያኑ ሙሉ በሙሉ ወደ ክርስትና አልተመለሱም ነበር ፡፡ ከእነዚህ አይሁድ መካከል አንዱ ከክርስቲያኖች ጋር በነገረ ሃይማኖት ለመከራከር ጥሪ አቀረበ ፡፡ “ክርስቲያኖች ከረቱኝ ወደነርሱ ሃይማኖት እገባለሁእኔ ከረታኋቸውም ወደኔ ሃይማኖት ይገባሉ” ሲል ነገሩን ጥብቅ አደረገው ፡፡ ዐፄ ዳዊት ይህን ጉዳይ ሲሰማ በጣም ስለ ተናደደ ሊቃነ ካህናቱን ፣ ንቡራነእዱንና የመጻሕፍት ዐዋቂዎችን ሁሉ ከየሀገሩ እንዲሰባሰቡ አዘዘ፡፡አይሁዳዊው በአንድ ወገን መምህራኑ በአንድ ወገን ሆነው ክርክሩን ጀመሩ፡፡የመጀመርያው እድል የተሰጠው ለአይሁዳዊው በመሆኑ ቀጥሎ ያለውንጥያቄ አቀረበ ፡ “እናንተ የእግዚአብሔር ልጅ ነው የምትሉት ይሄ ክርስቶስ እውነት የእግዚአብሔር ልጅ ከሆነ፣ ወደ ቢታንያ በመጣ ጊዜ አልዓዛር የተቀበረበትን ቦታ ሳያውቅ ቀርቶ "አልዓዛርን የት ቀበራችሁት?" ብሎ እንደጠየቀ በወንጌላችሁ ተጽፏል፡፡ ለዚህ መልስ ስጡኝ፣እኔንም ከመጽሐፈ ኦሪቴ ጠቅሳችሁ ጠይቁኝ?” ሲል የመከራከርያ ነጥቡን አቀረበ፡፡ በዚህ ጊዜ አባ ጊዮርጊስ ታሞ አልጋ ላይ ነበር ፡፡ ሊቃውንቱም “እንዲህያለው ነገር ያለ እርሱ አይሆንምና አባ ጊዮርጊስ ይምጣ” ሲሉ ለዐፄ ዳዊት ጥያቄ አቀረቡ ፡፡ አባ ጊዮርጊስም በአልጋ ላይ እያለ እንዲመጣ ተደረገ፡፡በአልጋ ላይ ሆኖም በጉባኤው ላይ ተገኘ፡፡ ጉባኤተኞቹ የቀረበውን ጥያቄ ነገሩት ፡፡ አባ ጊዮርጊስ የሰጠውን መልስ ገድሉ በሚከተለው መንገድ ይገልጥልናል “እኔ ግን በወንጌል ሳይሆን በኦሪት እከራከርሃለሁ፡፡ የምኩራብ መጻሕፍት ሁሉ ለቤተ ክርስቲያን የታወቁ ናቸውና ፡፡ ምኩራብ ዘራች ቤተክርስቲያንም አጨደችው፤ ምኩራብ ፈተለችው ቤተ ክርስቲያን ለበሰችው ፤ አዳምን በገነት ሳለ አዳም ሆይ ወዴት ነህ? ብሎ የጠየቀው ማነው? አብርሃምንስ ሚስትህ ሣራ ወዴት ናት? ብሎ የጠየቀው ማነው? እስቲ መልስልኝ? ሰይጣንንስ ከወዴት መጣህ? ብሎ የጠየቀው ማነው? እግዚአብሔር አብ አይደለምን?” በዚህ ጊዜ አይሁዳዊው መልስ አጥቶ ዝምአለ ፡፡ ንጉሡ ፣ ሊቃውንቱና መኳንንቱም እጅግ ተደሰቱ፡፡ ቅዱስ አባ ጊዮርጊስ እንደ ሰማዕት ግርፋትንና እሥራትን የተቀበሉ ፣ እንደ ሊቃውንት የመናፍቃንና የከሀድያንን ክርክር የረቱ ፣ እንደ መሐንዲስ ሐናጺ ፣ የሕግና የሥርዐት የሚስጥራትና የትርጉዋሜያት መምህር ፣ የጸሎትና የትምህርት መጻሐፍት ደራሲ ፣ የሥርዓተ ገዳምና ማኅበረ መነኰሳት አባት እንዲሁም ቢያንስ የአንድ ትምህርት መሥራች ሲሆኑ በግዞት በሄዱባቸውና በታሰሩባቸው ቦታዎችም ሆነ በተሾሙባቸው እንደ ደብረዳሞ ገዳም በመሰሉ ቦታዎች ሁሉ ሲያስተምሩና ሲገስጹ ኖረዋል ። በድርሰቱም እስካሁን በሃገራችን ተወዳዳሪ የላቸውም ። እጃቸው ከብዕር ተጨማሪ ከጠንካራ ሥራ ሳይቦዝኑ ዋሻ ሲፈለፍሉ የውሃ ጉድጉዋድ ሲቆፍሩ ድልድይ ሲሠሩ ኖረዋል ። አንደበታቸውና ሕሊናቸው ከምስጋና ሳያቁዋርጡ ለቤተክርስቲያን ጸሎትና ምስጋና ሥርዓት ሲተጉ ኖረው በፅድቅና በቅድስና ሕይወት እንዳጌጡ ለተዋህዶ ኮከብ ሆነው በተወለዱ በ፷ ዓመታቸው በ፲፬፻፲፯ ዓ.ም. ሐምሌ ፯ ቀን አርፈዋል ። ተማሪዎቻቸውም በመረረ ሐዘን ሆነው አፅማቸውን በጋስጫ ራሳቸው ፈልፍለው በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ስም በሠሩት ገዳም ውስጥ አስቀምጠውታል ። በትምህርታቸው የተመሰጡት ምዕመናን እና የቤተክርስቲያን ሊቃውንት በኛ ዘመን የተነሱት አዲሱ ዮሐንስ አፈወርቅ ሲሏቸው ዓፄ ይስሐቅ ደግሞ መናፍቃንን ሁሉ በማሳፈራቸውና በረቂቅ ድርሰቶቻቸው የኢትዮጵያ ቄርሎስ ብለዋቸዋል ። መጽሐፍ ቅዱስ
4280
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%89%80%E1%8C%AD%E1%8A%94
ቀጭኔ
= ቀጭኔ = ጉንደ እንስሳ ( = አምደስጌ ( = አጥቢ ( = ሙሉ ጣት ሸሆኔ = የቀጭኔ አስተኔ = ቀጭኔ ቀጭኔ በአፍሪካ የሚኖር ባለሙሉ ጣት ሸሆኔ ጡት አጥቢ አራዊት ሲሆን በምድር ከሚገኙ እንሰሳት በርዝማኔ የመጀመሪያውን ደረጃ ይዞ ይገኛል። ወንዱ ከ 4.4 እስከ 5.5 ሜትር ርዝማኔና 1,360 ኪሎግራም ክብደት ያስመዘግባል። እስካሁን በሪኮርድ የተያዘው የ 5.87ሜና የ2000ኪ.ግ ቀጭኔ ነው። ሴቶቹ በጥቁቱ አነስ ብለው ይታያሉ። ፈጣንና ባለ ግርማ እነዚህን ፍጥረታት በአራዊት ማቆያ ቦታዎች አንገታቸውን ከታጠሩበት አጥር በላይ ወጣ አድርገው የተመለከተ ሰው በአፍሪካ ቁጥቋጦዎች ነፃ ሆነው ሲሮጡ ያላቸውን ውበትና ግርማ መገመት ያስቸግራል። የቀጭኔ እንቅስቃሴ ትልቅ ግርማ ያለውና እንደ ውኃ ሙላት የሚፈስ ነው። በገላጣው የግጦሽ መስክ ላይ በሚጋልቡበት ጊዜ ቁመናቸው ትንሽ እንቅፋት ቢነካቸው ወድቀው የሚሰባበሩ ያስመስላቸዋል። ይሁን እንጂ እስከ 1, 300 ኪሎ ግራም የሚደርስ ክብደት ያላቸው ወንድ ቀጭኔዎች ቀልጣፋና ምንም የማያደናቅፋቸው ሯጭ ከመሆናቸውም በላይ በሰዓት እስከ 60 ኪሎ ሜትር ሊሮጡ ይችላሉ። ይህች አስደናቂ ፍጡር የምትገኘው በአፍሪካ ብቻ ነው። እርጋታዋና ሰላማዊ ተፈጥሮዋ ዓይን ይስባል። የቀጭኔ ፊት በዓይነቱ ልዩ የሆነና ቆንጆ ሊባል የሚችል ሲሆን ረዥምና ጠባብ ጆሮዎች፣ ሁለት ትናንሽ ቀንዶች እንዲሁም ጠቆር ያለ ለስላሳ ጠጉር አላት። ዓይኖቿ በጣም ትላልቅና ጥቁር ሲሆኑ ረዣዥም በሆኑ ቅንድቦች ይጠበቃሉ። ቀጭኔ ያን በመሰለ ከፍታ ላይ ሆና ሩቅ ስትመለከት ፊቷ ላይ የየዋህነት ገጽታ ይታይባታል። በጥንት ዘመናት ቀጭኔ ባላት አስደሳች ቁመና እንዲሁም ጨዋ፣ ዓይነ አፋርና ሰላማዊ ባሕርይ ያላት በመሆኑ በጣም ተወዳጅና ትልቅ ግምት የሚሰጣት ነበረች። በብሔራት መካከል ሰላምና በጎ ፈቃድ መኖሩን ለማመልከት የቀጭኔ ግልገሎች ለነገሥታትና ለገዥዎች በገጸ በረከትነት ይሰጡ ነበር። ጥንታዊ በሆኑት የአፍሪካ አለቶች ላይ ቀለማቸው የደበዘዘ የቀጭኔ ሥዕሎች እስከ ዛሬ ይታያል። ቁመተ ረዥም ከእንስሳት ሁሉ ቀጭኔን በቁመት የሚወዳደር የለም። ሙሉ ዕድሜ ላይ የደረሱ ወንድ ቀጭኔዎች ከእግራቸው ኮቴ አንስቶ እስከ ቀንዳቸው ድረስ ከ5.5 ሜትር የሚበልጥ ርዝመት አላቸው። በግብፃውያን ጥንታዊ ሥዕላዊ የአጻጻፍ ዘዴ ቀጭኔ በረዥም ቁመቷና አርቆ በመመልከት ችሎታዋ ምክንያት “መተንበይ” የሚለውን ግሥ ትወክል ነበር። ቀጭኔ በአፍሪካ መስኮች በሚሰማሩት የሜዳ አህዮች፣ ሰጎኖች፣ አጋዘኖችና ሌሎች እንስሳት መካከል ስትቆም እንደ ማማ ሆና ትታያለች። ቁመቷና አርቆ የማየት ችሎታዋ ማንኛውንም አደጋ ገና ከሩቅ ለማወቅ ያስችላታል። ስለዚህ የቀጭኔ መኖር ለሌሎች እንስሳት የመረጋጋት ስሜት እንደሚፈጥር ጥርጥር የለውም። አስደናቂ የሆነ አፈጣጠር ቀጭኔ ከዝሆን በስተቀር ማንኛውም ሌላ እንስሳ ሊደርስ በማይችልበት ከፍታ ላይ የሚገኙ ረዣዥም ቀንበጠቦችን ለመብላት የሚያስችል አስደናቂ አፈጣጠር አላት። ልዩ የሆነ የመቆንጠጥ ችሎታ ያለው የላይኛው ከንፈሯና እንደተፈገለው የሚተጣጠፍ ችሎታ ያለው ምላሷ ሹል በሆኑ እሾሆች የታጠሩ ቅጠሎችን ለመቀንጠብ ያስችሏታል። ቀጭኔዎች በቀን እስከ 34 ኪሎ ግራም የሚመዝን ዕፅዋት መመገብ ይችላሉ። የተለያዩ ዕፅዋትን የሚበሉ ቢሆኑም ይበልጥ የሚመርጡት በአፍሪካ ሜዳዎች የሚገኙትን እሾሃማ ግራሮች ነው። አንድ ወንድ ቀጭኔ ምግብ ለመፈለግ ምላሱን እስከ 42 ሳንቲ ሜትር መዘርጋት ይችላል። የቀጭኔ አንገት በጣም አስደናቂ የሆነ የመተጣጠፍ ችሎታ አለው። ይህም ላይኛዎቹን የዛፍ ቅርንጫፎች ለመቀንጠብ በምታደርገው እንቅስቃሴ ረዥሙን ራሷን እንደ ልቧ ለማዘንበልና ለማዟዟር ያስችላታል። ለቀጭኔ ወደ ላይ መንጠራራት በጣም ቀላል ነገር ሲሆን ተጎንብሶ ውኃ መጠጣት ግን ይከብዳታል። ወደ ውኃ ጉድጓድ በምትቀርብበት ጊዜ የፊት እግሮቿን ቀስ በቀስ ከፍታ ካራራቀቻቸው በኋላ ወደ ውኃው ለመድረስ እንድትችል ሁለት ጉልበቶቿን አጠፍ ታደርጋለች። ቀጭኔዋ እንዲህ ባለው አመቺ ባልሆነ ሁኔታ እያለች ረዥም አንገቷን እስከ መጨረሻ ትዘረጋለች። ደግነቱ ግን ከምትመገባቸው ቅጠላ ቅጠሎች በቂ እርጥበት ስለምታገኝ ቶሎ ቶሎ መጠጣት አያስፈልጋትም። የቀጭኔ አንገትና ትከሻ የቅጠል ቅርፅ ባላቸውና ቀጫጭን በሆኑ ነጭ መስመሮች ያጌጠ ነው። ቀለማቸው የተለያየ ሲሆን ከወርቃማ ዳለቻ አንስቶ እስከ ቡናማ እንዲያውም ጠቆር እስካለ ቀለም ይደርሳል። የቀጭኔ ዕድሜ እየገፋ በሄደ መጠን ቀለሟም እየጠቆረ ይሄዳል። የቤተሰብ ሕይወት ቀጭኔዎች ከ2 እስከ 50 የሚደርሱ አባላት ባሉት መንጋዎች ተደራጅተው አንድ ላይ የሚኖሩ ማኅበራዊ ፍጥረታት ናቸው። አንዲት ነፍሰ ጡር ቀጭኔ ልጅዋን ከ420 እስከ 468 ለሚደርሱ እርግዝና ቀናት ከተሸከመች በኋላ ሁለት ሜትር ቁመት ያለው ግልገል ትወልዳለች። ግልገሏ በምትወለድበት ጊዜ ራስዋን ታስቀድምና ከሁለት ሜትር ከፍታ ላይ ወደ መሬት ትወረወራለች። ይሁን እንጂ በ15 ደቂቃ ውስጥ ምንም ዓይነት ጉዳት ሳይደርስባት እየተውተረተረች ትነሳና ጡት ለመጥባት ዝግጁ ትሆናለች። ከሁለት ወይም ከሦስት ሳምንት በኋላ በደመ ነፍስ ተመርታ የግራር ቀንበጦችን መለቃቀም ስለምትጀምር ብዙም ሳትቆይ ረዥም እርምጃ ያላትን እናትዋን ተከትላ ለመሄድ የሚያስችል ጉልበት ታገኛለች። አንዲት የቀጭኔ ግልገል በጣም ውብ መልክ ሲኖራት የወላጆችዋ አነስተኛ ግልባጭ ነች። ቁመቷ ከቀጭኔ ርዝመት ጋር ሲወዳደር አጭር ብትሆንም ከብዙ ሰዎች ቁመት ግን ትበልጣለች። በእናቷ ጥንቃቄ የተሞላበት ጥበቃ ተማምና አላንዳች መሸበር አካባቢዋን የምትማትረው ግልገል ላያት ሁሉ ልዩ መስህብ አላት። ግልገል ቀጭኔዎች በተወለዱበት ወራት በግልገል መዋያ ተሰባስበው ሙሉውን ቀን ዕረፍት በማድረግ፣ በመጫወትና በአካባቢያቸው የሚሆነውን ነገር በመመልከት ጊዜያቸውን ያሳልፋሉ። የቀጭኔ ግልገል ለማመን በሚያዳግት ፍጥነት ያድ⁠ጋል። በስድስት ወር ጊዜ ውስጥ አንድ ሜትር የሚያክል ቁመት ሲጨምር በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ደግሞ በእጥፍ ያድጋል። በአንድ ሳምንት ብቻ 23 ሳንቲ ሜትር ያህል ሊያድግ ይችላል! እናትዬው ለልጅዋ ከፍተኛ ጥበቃ የምታደርግ ሲሆን ልጅዋ የተወሰነ ርቀት እንድትዘዋወር ብትፈቅድላትም ሩቅ የማየት ችሎታ ስላላት በዓይኗ ትከታተላታለች። ቀጭኔ ግዙፍ አካል፣ ከፍተኛ ፍጥነት፣ ቅልጥፍናና የማየት ችሎታ ስላላት ከአንበሳ በቀር የሚያጠቃት ጠላት የለም። ቢሆንም ይህችን የምታምር ፍጥረት የሰውን ያህል በብዛት አድኖ የገደለ የለም። ቀጭኔ በሚያምር ቆዳዋ፣ በሚጣፍጥ ሥጋዋና አንዳንዶች ምትሐታዊ ኃይል አለው በሚሉት ረዥምና ጥቁር ጭራዋ ምክንያት እጅግ ተፈላጊ ስለሆነች በአሁኑ ጊዜ የዚህች ሰላማዊ ፍጡር የወደፊት ሕልውና ስጋት ላይ ወድቋል። በአንድ ወቅት በብዙ የአፍሪካ አካባቢዎች እንደ ልብ ትታይ የነበረችው ቀጭኔ በአሁኑ ጊዜ የምትገኘው በቂ ጥበቃ በሚደረግላት ፓርኮች ብቻ ሆኗል። [የግርጌ ማስታወሻ] በአፍሪካ ገላጣ ምድር ላይ በሰፊው ተሰራጭተው የሚታዩት ትናንሽ ዓለታማ ኮረብቶች ኮፕጀስ'' ይባላሉ። እግረ ረዥሟ ተአምራዊ ፍጡር የቀጭኔ አካላዊ ቅርጽና ግዝፈት ችግሮች ማስከተሉ አይቀርም ብሎ የሚያስብ ይኖር ይሆናል። በጣም ትልቅ ቁመትና ረዥም አንገት ስላላት የተስተካከለ የደም ዝውውር እንዲኖራትና ወደ ሁሉም የአካሏ ክፍሎች ደም እንዲደርስ ማድረግ የማይቻል ነገር ሊመስል ይችላል። ለምሳሌ ያህል ቀጭኔ አንገቷን ወደ መሬት ስታጎነብስ በስበት ኃይል ምክንያት ብዙ ደም ወደ ጭንቅላቷ ፈስሶ አንጎሏን ማጥለቅለቅ ነበረበት። ራሷን ቀና በምታደርግበት ጊዜ ደግሞ ደሟ በከፍተኛ ፍጥነት ወደ ልቧ ተመልሶ ራሷን እስከ መሳት ሊያደርሳት ይገባ ነበር። ይሁን እንጂ ይህ ነገር አይደርስም። ለምን? የቀጭኔ የደም ዝውውር ሥርዓት በዓይነቱ ልዩ ለሆነው ለዚህች እንስሳ ቅርጽና መጠን እንዲያገለግል ሆኖ በታላቅ ጥበብ የተሠራ ነው። ልቧ ራሱ በጣም ትልቅ ሲሆን ደሙን ሦስት ሜትር ተኩል ገደማ ርቆ እስከሚገኘው እስከ አንጎላ ለመግፋት የሚያስችል አቅም አለው። በደቂቃ እስከ 170 ጊዜ የሚመታውና 7 ሳንቲ ሜትር ያህል ውፍረት ባለው ጡንቻ የተገነባው የቀጭኔ ልብ ከሰው የደም ግፊት በሦስት እጥፍ የሚበልጥ ግፊት ያመነጫል። ወደ አንጎል የሚሄደውን ደም የሚሸከመው ካሮቲድ የተባለው የደም ቧንቧና ከአንጎል ወደ ልብ የሚመለሰውን ደም የሚሸከመው ጀጉላር የተባለው የደም ቧንቧ እንዲህ ያለውን ከፍተኛ ግፊት መቋቋም የሚያስችል መጠን ሊኖራቸው ይገባል። በእርግጥም እነዚህ የደም ቧንቧዎች ከ2.5 ሳንቲ ሜትር በላይ ስፋት ያላቸው ከመሆኑም በላይ ጠንካራና የመለጠጥ ችሎታ ባላቸው ሕዋሳት የተገነቡ በመሆናቸው ከፍተኛ ጥንካሬና የመለመጥ ችሎታ አላቸው። ቀጭኔ ከጭንቅላቷ ጎንበስ በምትልበት ጊዜ ወደ አንጎሏ የሚሄደውን የደም ፍሰት የሚቆጣጠሩ ልዩ መቆጣጠሪያዎች አሏት። አንጎልና አንገት በሚገናኙበት ቦታ ላይ ትልቁ ካሮቲድ የደም ቧንቧ ሬቴ ሚራቢሌ ተብሎ ከሚጠራ አስደናቂ የሆነ መረብ መሰል አካል ይገናኛል። በከፍተኛ ኃይል ተገፍትሮ የመጣው ደም እዚህ ጋር ሲደርስ በጣም በርካታ ወደሆኑ ትናንሽ የደም ሥሮች እንዲገባ ስለሚደረግ የደሙ ግፊት ተስተካክሎ በአንጎል ላይ ጉዳት የማያስከትል ይሆናል። ቀጭኔዋ ራስዋን ጎንበስ በምታደርግበት ጊዜ ይህ በዓይነቱ ልዩ የሆነው መረብ ይለጠጣል፤ ራሷን ቀና በምታደርግበት ጊዜ ደግሞ ይኮማተራል። ይህም የስበት ኃይል የሚያሳድረው ተጽዕኖ ሚዛኑን የጠበቀ እንዲሆን ማድረግና የደም ግፊቷ በእጅጉ ቀንሶ ራሷን የምትስትበት ሁኔታ እንዳይፈጠር ለመከላከል ይረዳታል። የሳይንስ ሊቃውንት በጣም አስደናቂ ርዝመት ያለው የቀጭኔ አንገት ያሉት አከርካሪዎች ቁጥር ከአይጥ ወይም ከብዙዎቹ አጥቢ እንስሳ ጋር እኩል መሆኑን ሲያውቁ በጣም ተደንቀዋል! ይሁን እንጂ የቀጭኔ አከርካሪዎች በጣም ረዣዥሞችና እርስ በርሳቸው ልዩ በሆነ ሁኔታ የተሰካኩ በመሆናቸው እንደ ልብ ሊተጣጠፉ ይችላሉ። ቀጭኔ አንገቷን መጠምዘዝና ማጠፍ ስለምትችል ሁሉንም የአካሏን ክፍሎች ለመላስም ሆነ ረዣዥም የዛፍ ቅርንጫፎች ላይ ለመድረስ ትችላለች። የዱር አራዊት አጥቢ እንስሳት
16103
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8B%A8%E1%8B%9E%E1%88%AB%E1%88%B5%E1%89%B0%E1%88%AD%20%E1%8D%8D%E1%8A%AB%E1%88%AC%20%E1%8A%AD%E1%8D%8D%E1%88%8D%20%E1%8D%A9
የዞራስተር ፍካሬ ክፍል ፩
ክፍል ፩ በዚህ የመጽሃፉ ክፍል የዞራስተር ዋና ነጥቦች በስድስት ዋና ዋና ሃሳቦች ይጠቃላል። የመጀመሪያው የዞራስተር ነጥብ አጠቃላይ ሜታፊዝክን መካድ ነው። ሜታፊዚክ ማለት በተጨባጩ አለም ጀርባ የማናየው፣ የማንዳሰሰው፣ የማናሸተው እውነተኛ አለም አለ በማለት ይህን አለም ለማግኘት የሚጥር የፍልስፍና ዘርፍ ነው። በዞራስተር አስተያየት አንድ አለም ብቻ አለ፡ እርሱም ተጨባጩ አለም ነው። ሁለተኛው የዞራስተር ነጥብ የአይምሮና አካል ክፍፍልን መካድ ነበረ። በተለምዶ ሰው አካል አለው ብንልም በዞራስተር አስተያየት ሰው እራሱ አካል ነው። የሰው ልጅ ከማይጨበጥ ምናባዊ ነገር (አዕምሮ) እና ከተጨባጭ ነገር (አካል) የተሰራ ሳይሆን ሙሉ በሙሉ ከአካል የተሰራ ነው። በነደካርት የተነሳው ቀልበኛ ፍልስፍና የስውን ልጅ ከሁለት (አዕምሮና ሰወነት) ከከፈለ ወዲህ የስው ልጅ የስራ ውጤቶች ብዙ አመርቂ አልሆኑ፣ ይልቁኑ የጥንቶቹ ከያኒያን በ"ደማቸው የጻፉዋቸው መጽሃፎች" (በአይምሮ ከተጻፉ ዘመናዊ መጽሃፎች) በተለየ መልኩ ስሜት የሚነኩ እንደነበሩ አስተማረ። የሰው ልጅ "አዕምሮ" ከሆነ ወዲህ ስራው ሁሉ በቀመር የተወጠረና ምንም ስሜት የማይቀስቀስ ሆነ። ዞራስተር ሙሉ በሙሉ የግለሰብ ነጻነትን ይደግፋል። ግብረገብ፣ የጋራ ሰላምና፣ ይሉኝታ ለዞራስተር ደንታው አይደሉም። የህይወት ኃይሎች በምንም አይነት መታፈን የለባቸውም። የተመረጡ ነፍሶች የመንጋወችን ግብረ ገብና ስርዓቶች ወደጎን ትተው የራሳቸውን ዋጋ/ህግ አውጥተው የራሳቸውን አላማ ለማስፈጸም ይታገላሉ። ትክክለኛው የህይወት ጣዕም በህግጋትና ግብረገብ የተጋረደ ሳይሆን ከኃጢያትና ጽድቅ ወዲያ ርቆ የሚገኝ ነው። ሙሉው የግለሰብ ነጻነት "ሁሉ በሁሉ ላይ" ጦር እንዲያነሳ ሊያደርግ ይችላል። ይህ ግን በዞራስተር አይን ምንም አይደለም ምክንያቱም ሁሉም ህይወት ያለው ነገር "ኃይልን ይፈቅዳል"፡ ሁሉም ህይወት ያለው ነገር እራሱን ያረጋግጣል፣ ለመኖሩም ምልክት ትግል ያካሂዳል። ሄራክሊተስ እንደጻፈ "ጦርነት የሁሉ ነገር አባት ነው"፣ በዞራስቱራ አስተያየት ያለፍልሚያ ምንም ጥቅም ያለው ነገር አይመጣም። ዞራስተር ለጓደኞቹ የሚመክረውም "በአደጋ ኑር!" እያለ ነበር። ፍቅረኛሞች እንኳ ሳይቀሩ ችግር ሊገጥም እንዲችል መረዳት አለባቸው፣ በፍቅር መጎዳት የሚፈራ ወይም ቂም የሚያሲይዝ ሳይሆን እራስን ለማሳደግና አዳዲስ ነገሮችን ለመረዳት የሚያገልግል ዕድል ነው። ጦርነት ተቀባይነት ያለው መሳሪያ ብቻ ሳይሆን ተቀባይነት ያለው ግብም ነው። እራስን መወሰን ለዞራስተር ፍልስፍና ዋና ቁልፍ ነው። ይህ አለም ከላይም ሆነ ከታች ከጎንም ሳይቀር የተሰጠው ትርጉምም ሆነ ህግጋት የሉትም። ሁሉም ሰው የራሱን ትርጉምና ህግጋት በመፍጠር እራሱን ይወስናል። ሁሉም ሰው ልክ እንደሙሴ የራሱን ጽላት እንዲቀርጽ እንጂ ለሁሉም የሚሰራ ከላይ የተላለፈ ህግ የለም። ከዚህ አንጻር እራስን መወሰን ባንድ በተስተካከል የአለም ስርዓት ውስጥ ራስን መቻል ሳይሆን ከትርምስ ውስጥ የራስን አለምን እንደመፍጠር ነው። ህይወት ሂደት እንጂ ሁኔታ አይደለም። አንድ የሰው ልጅ በሂደት ላይ ያለ እንጂ፣ ቆሞ ያለ የሆነ ነገር አይደለም። እራስን እንደ አንድ ቋሚ ነገር ማሰብ በዞራስተር ስህተት ነው። በመጠበቅ፣ እውቀትንና ሃብትን ዝም ብሎ በማከማቸት ህይወት አይኖርም፣ ይልቁኑ እራስን በየጊዜው በማሸነፍና እራስን በመቀየር ህይወት ይኖራል። ሶስቱ ሽግግሮች ሌላው የዚህ ክፍል ዋና ሃሳብ ሶስቱ ሽግግሮች ናቸው፡፡የሰው መንፈስ እውነቱንና እራሱን ለማወቅ 3 ከባድ ለውጦች እንደሚያካሂድ ዞራስትራ በዚህ ክፍል ሲያስረዳ፦ " እነሆ ነፍሳችሁ ሶስት ጊዜ ይሻገራል፡ እንኪያስ ግመል ነበራችሁ፣ ግመሉ አምበሳ፣ በመጨረሻ አምበሳው ህጻን ልጅ!" ትርጉሙም የመጀመሪያው የመንፈስ ለውጥ ወደ ግመል ሲሆን ይህም "ትሁት መንፈስ"ን ያመላክታል፡ እራስን መካድ፣ በሃብት መቆጠብን፣ መታዘዝንና ችግርን መቋቋምን። ይህም ግመልን እራሷን ዝቅ አድርጋ የጭነት እንስሳ እንደሚያደርጋት ባህርይ ነው። " መጫን ያለበት መንፈስ እንዲህ ይጠይቃል "ከሁሉ ነገር ከባዱ ምንድን ነው?" መልሶም "በጫንቃየ ላይ ጭነቴን አዝየ በጥንካሬየ ሐሴት ማድረግ አይደለምን? እራሴን በማዋረድ ኩራቴን መግደል አይደለምን? የዋህነቴን በማጋነን ጥበቤን መፎተት አይደለምን?" ከዚህ የግመል አለም ወደ አንበሳነት የሰው መንፈስ ለሁለተኛ ጊዜ ይሻገራል። በዚህ ጊዜ ከጭነት ነጻ ይሆናል፣ ከላይ ወደታች በተዘርጋ የሃይል አሰላለፍ ቁንጮውን ለመያዝ ጥረት ያደርጋል፣ ራስ ገዝ ሆኖ ነጻነቱን በራስ ገዝነትና በሃያልነት ይደነግጋል። በታላቁ ዘንዶ ላይ ጦርነት ይክፈታል፣ የቀድሞውን ግብረገብ ጽንሰ ሃሳብ አውልቆ ይጥላል። "ለራሱ ነጻነትን ለመቀዳጀት፣ በህግጋት ላይ ሳይቀር "እምቢ" ለማለት፣ ወንድሞች፣ ለዚያ ለዚያ አንበሳ ያስፈልጋል። አዳዲስ ህግጋትን የመፍጠር መብት እንዳለ ለማወቅ ለተሸካሚና ለአክባሪ ነፍሳት እጅግ አስቸጋሪ ነው። ይህ ተግባር ለነዚህ እንደ ማደን እና የሚታደን እንስሳ ስራ ነው።" አንበሳ እንግዲህ የነበረውን እምቢ በማለት የሚያፈርስ እንጂ አዲስ የሚፈጥር አይደለም። ስለሆነም የሰው መንፈስ አዳዲስ ህግጋትን ለመፍጠር ለ3ኛ ጊዜ መሻገር ይኖርበታል። በዚህ የመጨረሻው ሽግግር መንፈሱ ከአንበሳ ወደ ህጻን ይቀራል። ህጻኑ አዲስ ጅማሬን፣ ንጹህ የዋህነትን የሚወክልና የድሮወቹን ህግጋት ድል ካደረገ በኋላ አዲስ ዋጋወችን ፈጣሪ ይሆናል። "ሕጻን የዋህነት ነው፣ ያለፈውን መርሳትም ነው፣ አዲስ ጅማሬ፣ ጨዋታ፣ እራሱን የሚያሽከረክር ጎማ፣ የመጀመሪያ እንቅስቃሴ፣ ቅዱስ የሆነ "አወ-ማለት"። አወ! ወንድሞች፣ የፈጠራ ጨዋታ ቅዱስ የሆነ "አወ" ማለትን ይጠይቃል፡ መንፈስ የራሱን ፈቃድ ይፈቅዳል፣ አለሙን ያጣ እንግዲህ የራሱን አለም ያገኛል።" ሁሉ ነገር በህጻን ልጅ ተጀምሮ እንደገና በህጻን ማብቃቱ የኒሺን የዘላለም ምልልስ ጽንሰ ሃሳብ የሚያንጸባርቅ ነው። በዚህ የዘላለም ድግግሞሽ የሰው ልጅ እራሱን በማሽነፍ ከነበሩበት ድክመቶች ሁሉ ነጻ በመውጣት አዲስ አይነት ሰው -- የራሱ ህግ/ዋጋ ያለው የበላይ ሰው ይፈጥራል። እኒህን ነጥቦች ለተመረጡ ተከታዮቹ ካስተማረ በኋላ ዞራስተር ወደተራራ ዋሻው እንደተመለሰ መጽሃፉ ያትታል። የዚህ ምክንያቱ ያለሱ ተጽዕኖ ተከታዮቹ በራሳቸው ውሳኔ የራሳቸውን ሃሳብ እንዲያዳብሩ ነው። አስተማሪነቱን ማቆሙም ይህን የፍልስፍናውን ግብ ላለማጣረስ ነበር። መደብ :የዞራስተር ፍካሬ
15768
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%88%9B%E1%8A%95%E1%8B%B4%E1%88%8D%E1%89%A5%E1%88%AE%E1%89%B5
ማንዴልብሮት
ቤንዋ ማንዴልብሮት (20 ህዳር 1924 – 14 ጥቅምት 2010 እ.ኤ.አ) ታዋቂ የ20 ና የ21ኛው ክፍለዘመን ሒሳብ ፈልሳፊና ተመራማሪ ነበር። የፍርክስክስ ጂዖሜትሪ አባት ተብሎ የሚታወቀው ይህ ሰው በዚህ በፈጠረው የሂሳብ ጥናት ዘርፍ ቅጥ የለሽና የተፈረካከሱ የጂዖሜትሪ ቅርጾችን ፣ በተለይ ባጎላናቸው (ቀረብ ብለን ባየናቸው ጊዜ ሁሉ) ከራሳቸው ጋር ተመሣሣይነት ያላቸውን ክስተቶችን በሂሳብ እኩልዮሽ ለመግለጽ ችሏል።ማንድልብሮት ፖላንድ አገር ተወልዶ በህጻንነቱ ፈራንሳይ አደገ ኋላም ቀሪ ዘመኑን በአሜሪካን አገር አሳለፈ። የአሜሪካና ፈረንሳይ ዜጋ ነበር። የፍርክስክስ ጂዖሜትሪ መፈጠር ከማንዴል ብሮት መነሳት በፊት የነበረው የሂሳብ ተማሪወች አስተሳሰብ እንዲህ ነበር፡ «በአለማችን ላይ የሚገኙ ቅርጾች እጅግ ውስብስብ፣ የጎረበጡ ፣ ፍርክስክስ ያሉና ቅጥ የሌላቸው ስለሆኑ በሂሳብ ቀመር ሙሉ ለሙሉ ለመግለጽ አይቻልም» ። በዚህ ምክንያት ሂሳብ ተማሪወች ትኩረት ሰጥተው ያጠኑት የነበረው በምናባቸው አስተካክለው ለፈጠሩዋቸው ቅርጾች፣ ለምሳሌ ለክብ፣ ሶስት ማዕዘን፣ አራት ማዕዘን፣ ፓራቦላ ወዘተ ነበር። እኒህ እንግዲህ በጣም የተስተካከሉ የምናባዊ አለም ፍጥረቶች እንጂ በርግጥም በተፈጥሮ የማይገኙ ናቸው። የማንዴልብሮት ትልቁ ግኝት እንግዲህ ከዚህ ከምናባዊ አለም ወጥተን ወደ ገሃዱ አለም ስንገባ የምናገኛቸውን የተወሳሰቡ ቅርጾችን፣ ለምሳሌ ደመናን፣ ተራሮችን፣ የባህር ወደብን፣ ዛፎችን በሂሳብ ቀመር ማስቀመጫ ዘዴን ማግኘቱና በሂደት ማስተካከሉ ነበር። ይህ ስራው ለዘመናዊው የኬዖስ ጥናት መሰረት ሆነ። የፍርክስክስ ጂዖሜትሪ ጥናት መሰረት ማንዴልብሮት በ1960ወቹ በተሰኘው የአሜሪካን የኮምፒውተር አምራች ኩባንያ ተቀጥሮ ይሰራ ናበር። በዚህ ወቅት ኮምፒውተሮች በሚያደርጉት የመረጃ ልውውጥ ወቅት የሚነሱ ኤሌክትሪክ ረብሻወች ምክንያት አንዱ ኮምፒዩተር ወደ ሌላው የላከው መልዕክት ስህተት ሆኖ ይገኝ ነበር። ምንም እንኳ የስህተቶቹ ተፈጥሮ በጊዜው በሳይንቲስቶች ባይታወቅም ስህተቶቹ ግን ሁልጊዜ የሚፈጠሩ ሳይሆኑ እየተጠራቀሙ በየተወሰኑ የጊዜ ክፍሎች የሚፈጠሩ መሆኑ ተደረሰበት፣ ማለት ለተወሰነ ጊዜ ስህተት የሌለበት ስራ ይሰራና ብዙ ስህተት ያለበት ስራ ደግሞ ለቀጣዩ ጊዜ ይፈጠራል። እኒህን ጥርቅም ስህተቶች በቅርበት ሲመረምር በርግጥም ቅጥ አልባ ከመሆን ይልቅ ንድፍ () እንዳላቸው ተገነዘበ። ንድፋቸውም እንዲህ ነበር፡ ሁለት ሰዓት የኮምፒውተሮቹን ልውውጥ ብናስተውል፣ አንዱ ስዓት ምንም ስህተት ሳይኖር ካለፈ መጪው አንድ ሰዓት ደግሞ ስህተት ይኖረዋል። በተጨማሪ ስህተት የተገኘበትን ሰዓት በ20 በ20 ደቂቃ ብንከፍለው እና ብንመለከት፣ አንዱ 20 ደቂቃ ያለ ስህተት ሲያልፍ ቀጣዩ 20 ደቂቃ ስህተት ይይዛል። እንግዲህ ሰዓቶቹን እየከፋፈለ ባጎላ ቁጥር በሁሉም የማጉሊያ ዘርፍ የስህተት አቃፊው ሰዓት መጠን ከስህተት አልባው ይጊዜ መጠን ጋር ያለው ውድር () ምንጊዜም ቋሚ እንደሆነ ተገነዘበ። በሌላ አነገጋር የኤሌክትሪኩ ረብሻ በፈለግነው መጠን ባጎላነው ቁጥር እራሱን ደጋሚ መሆኑን አሳየ፣ ማለት እያንዳንዷ ትንሽ ክፍል በጎላች ቁጥር ከሷ በላይ ያለውን የትልቁን ክፍል መልክ/ይዘት/ቅርጽ ትደግማለች። ማንዴልብሮት ይህ "እራስን የመድገም" ባህርይ በሌሎች የተፈጥሮ ክስተቶች እንደሚታይ ማስተዋል ጀመረ። ለምሳሌ የጥጥ ዋጋን በጥንቃቄ ሲመረመር፣ የየቀኑ፣ የየወሩና የየአመቱ የጥጥ ዋጋ ቅጥ አልባ ቢሆንም ነገር ግን የየቀኑ ዋጋ ለውጥ ከየየወሩ የዋጋ ለውጥ እንዲሁም ከየየአመቱ ለውጥ ጋር አንድ አይነት እንደሆነ ለማወቅ ቻለ። የዛፎች ቅጠሎችም ልክ እንዳንጠለጠላቸው ዛፍ ተመሳሳይ ቅርንጫፍ እንዳላቸው በሌላ ወገን ደግሞ የባህር ጠረፎች ላይ የሚስተዋሉት ገባ ብለው ያሉ ሰላጤወች (ወደ ዋናው ምድር ገባ ያሉ ወደቦች) ቀረብ ተብለው ሲታዩ በራሳቸው ላይ እንደገና ገባ ያለ አንስተኛ ሰላጤ ይኖራል ሆኖም እኒህ አንስተኛ ሰላጤወች ቀርበው ሲታዩ ሌሎች አንስተኛ ስላጤወች አሏቸው፣ ወዘተ...። በ1967 ባሳተመው "የብሪታንያ የባህር ጠረፍ ርዝመት ስንት ነው?" በሚለው መጽሃፉ በርግጥም የእንግሊዝ ጠረፍ ህልቁ መሳፍርት ሰላጤወች ያሉትና ርዝመቱ እንደ አትኩረታችን እንደሚለያይ አሳይቷል። የዚህ ምክንያቱ ከላይ ከላዩ እንይ ከተባል ጠረፉን መለካት ቀላል ቢሆንም ቀረብ እያልን ስንሄድ በወደቡ ውስጥ ሰላጤወች እናገኛለን ከዚያ ስንቀርብ በበሰላጤው ውስጥ ሰላጤ እና እያለ ሄዶ በድንጋይ ውስጥ ድንጋይ እናገኛለን በድንጋዩ ውስጥ አሸዋ እያለ ህልቁ መሳፍርት ይጠጋል። ርዝመቱ እንግዲህ በተለምዶ ቢታወቅም በትክክል ግን አይታወቅም። እነዚህን እራሳቸውን የሚደግሙ ክስተቶች እና ሌሎች ተመሳሳይ ንድፎች በነበረው ሂሳብ መግለጽ እንደማይቻል ስላወቀ በቀጣዮቹ አመታት የፍርክስክስ ጂዖሜትሪን () ለዚህ ተግባር ፈጠረ። ፍራክታል የሚለውንም የሂሳብ ቃል በ1975 ሰየመ። የዚህ ጥናቱ ውጤት በአንዲት የሂሳብ ቀመር ተጠናቀቀ፣ ። ይቺ ቀመር የ ማንዴልብሮት ስብስብ በመባል ትታወቃለች። መጽሃፉ ታተመ በ1982 ዓ.ም፣ ከሌሎች የከፍተኛ ሂሳብ ጥናት መጽሃፎች በላይ የተሸጠውን (የተፈጥሮ ፍርክስክስ ጂዖሜትሪ ) የተባለውን መጽሃፉን አሳተመ። በዚህ መጽሐፉ «ደመና የኳስ ቅርጽ አይደለም፣ ተራሮች የአሎ አሎ ቅርጽ የላቸውም፣ የባህር ጠረፎች ክብ አይደሉም፣ የዛፍ ቅርፊት ለስላሳ ሳይሆን ሸካራ ነው፣ መብረቅ በቀጥተኛ መንገድ አይጓዝም» በማለት በጊዜው የነበረውን የሂሳብና ሳይንስ አስተያየት ተቸ። የድሮው ጂዖሜትሪ ለተፈጥሮ ክስተቶች ምንም ተስማሚ እንዳልነበር ያሳመነው ማንዴልብሮት በመጽሃፉ እንዴት ከላይ የተገለጹት ክስተቶችና የስቶክ ገበያ ዋጋ ልውውጥ፣ የፈሳሾች ንቅንቅ፣ የመሬት እንቅስቃሴወች፣ ምህዋሮች፣ የእንስሣቶች የቡድን ባህርይና ሙዚቃ ሳይቀር በፍርክስክስ ጂዖሜትሪ ናሙናቸው እንዴት እንዲሰራ አስረዳ። ይህ እጅግ ሃይለኛ የሆነ ሂሳብ ፣ በአለንበት የኮምፒውተሮች ዘመን የበለጠ ሃይልን ሊጎናጸፍ ቻለ። በአሁኑ ዘመን ፍርክስክስ ጂዖሜትሪን በመጠቀም እውነተኛ ተራሮችን፣ የባህር ወደቦችን፣ ዛፎችን፣ ደመናወችንና የሴል እድግትን በማስመሰል በኮምፒውተር ስዕልና ተንቀሳቃሽ ምስል መስራት ይቻላል። ከዚህ ሌላ የዲጂታል ምስልን ለመጭመቅ፣ ለመኪና ጎማወች በጣም ጥሩ የሆኑ ንጥረ ነገሮችን ለመመራመር፣ ለአውሮፕላን ክንፍ አቅድ ለማውጣት፣ ሃኪም ቤት ሄዶ የሰውነትን ክፍል በራጅ ለማስነሳት ወዘተ... ከፍተኛ ግልጋሎት ይሰጣል። የፈረንሳይ ሰዎች ሒሳብ ተመራማሪዎች
1631
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%88%98%E1%88%88%E1%88%B5%20%E1%8B%9C%E1%8A%93%E1%8B%8A
መለስ ዜናዊ
መለሰ ዜናዊ (የትውልድ ስማቸው ለገሠ ዜናዊ አስረስ) (ሚያዝያ ፴ ቀን ፲፱፻፵፯ ዓ/ም - ነሐሴ ፲፬ ቀን ፳፻፬ ዓ/ም) የኢትዮጵያ የፖለቲካ ሰው ነበሩ። በአድዋ ትግራይ የተወለዱ ሲሆን ከ፲፱፻፹፯ ዓ/ም አንስተው እስከ ዕለተ ሞታቸው ድረስ በኢትዮጵያ የጠቅላይ ሚኒስትር ሥልጣን በከፍተኛው የአመራር ቦታ ላይ ነበሩ። የኢህአዴግና የሕውሓት ሊቀመንበር በመሆን ኢህአዴግ ስልጣን ላይ ከወጣ ጀምሮ ቆይተዋል። አቶ መለስ ዜናዊ አባታቸው (አቶ ዜናዊ አስረስ ከጎዣም አገው ቤተሰባዊ ትስስር እንዳላቸው ይታመናል) የትግራይ ተወላጅ ሲሆኑ፣ በእናታቸው በኩል ደግሞ ኤርትራዊ ናቸው። መለስ በታወቀው ጀነራል ዊንጌት 2ኛ ደረጃ ተምህርት ቤት የተማሩና ከአጼ አህለስላሴ የኮከብ ተማሪዎች ሽልማት የተሸለሙ፣ ከዛም ወደ በረሃ ወርደው በታጋይነት ከመሰለፍቸው በፊት፤ የአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ ሜዲካል ፋክልቲ ተማሪ ነበሩ። ትግርኛ፣አማርኛና፡ እንግሊዝኛ አቀላጥፈው መናገር ይችላሉ። መለስ ዜናዊ ስልጣን ላይ በነበሩባቸው ጊዜያት ለሀገራቸው ኢትዮጵያ ባደረጓቸው አስተዋፅኦዎች የኢትዮጵያ ባለውለታ ናቸው ይባላሉ፡፡ ኢትዮጵያም እንደ እርሳቸው ያለ መሪ አግኝታ እንደማታውቅ በሰፊው ይነገራል፡፡ ወደ ስልጣን አመጣጥ አቶ መለስ የሚመሩት ሕውሓት የኮሎኔል መንግስቱ ኅይለ ማርያምን አምባገነናዊ መንግስት በትጥቅ ትግል ሲታገሉ ከነበሩ ድርጅቶች አንዱ ነበር። አቶ መለስ የሕወሓት አመራር ኮሚቴ መሪ ሆነው በ1971 ተመረጡ፤ ቀጥሎም በ1975 የድርጅቱ ማእከላዊ ኮሚቴ ሊቀመንበር ሆኑ። የደርግ መንግሥት ከወደቀም ጀምሮ የሕወሓትና የኢህአዴግ ሊቀ-መንበርም ሆነው አገልግለዋል። ኢህአዴግ የአራቱ ፖለቲካ ፓርቲዎች ማለትም የኦሮሞ ህዝቦች ዲሞከራሲያዊ ድርጅት፣ የብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ፣ የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ፣ የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ውህደት ነው። ወደ ስልጣን ሲመጡ በጊዜው ላቋቋሙት ጊዜያዊ መንግስት ፕረዚዳንት ሆነው ካገለገሉ በሗላ 1985 ለመጀመሪያ ጊዜ ጠቅላይ ሚንስትር ሆነው ተመረጡ። በጊዜው የፕረዚደንትነቱን ቦታ የተረከቡት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ናችው። የሽግግር መንግስታቸው የአምባገነኑ የመንግስቱ ኃይለ ማርያም አስተዳደር እንደ ወደቀ አዲስ አበባን የተቆጣጠረው ኢአሓዴግ በሕዝብ ምርጫ ሳይሆን ብሔረሰቦችን መሰረት ባደረገ በጥቂት ግለሰቦች የሽግግር መንግሥቱ በመቋቋሙና በተለይም የአማራን ሕዝብ(የአማራን የፖለቲካ አስተሳሰብ) ያለው ፖርቲ ሳይወከል መቅረቱ አብዛኛውን ሕዝብና ምሁራንን በጣም አስቆጣ። የኢህአዴግ ደጋፊዎች በወቅቱ በአምባ ገነኑ ደርግ ስር ተጨቁኖ ለነበረው ድሃ ኢትዮጵያዊ የኢህአደግ ወደ ስልጣን መምጣት ሌላ አማራጭ ስላልነበር የኢሕአዴግን መንግስት ሕዝቡ ለመቀበል ስለ ተገደደ በጊዜው ኢህአዴግ ይህ ነው የተባለ ተቃውሞ አልገጠመውም። በአንጻሩ ከጅምሩ በትጥቅ ትግል ኢሕአዴግን ሲረዱ የነበሩ የአረብና የምዕራባውያን መንግስታት ከጎንህ አለን በማለት በሁለት እግሩ አንዲቆም አስችለውታል። ይሁን እንጂ እያደር ሲመጣ የአቶ መለሰ ዚናዊ መንግስት የታገለለትን ዓላማ ስቶ ዲሞክራሲን በማፈን የነጻ ፕሬስ አፈና በማካሄድና የብአዊ መብት ረገጣ ስላበዛ ብዙ የምዕራባዊያን ድጋፍና ከማጣቱም በላይ የብዙ ሺ ኢትዮጵያዊያን ለስደት ዳርጎአል። ሆኖም ዓለም አቀፉን ሽብርተኛ ለመታገል በሚል ሽንገላ ሱማሌን በመውረሩ ምክንያት በጆርጅ ቡሽ የምትመራ አሜሪካ ቀንደኛና ዋነኛ የኢህአዴግ ደጋፊ ሆና ቀርታለች። ቀጣዩ የአሜሪካ መሪ ባራክ ኦባማም የአገራቸውን ጥቅም ለማስጠበቅ ካላቸው ፍላጎት አልቃይዳንና አልሸባብ የተባሉ የአክራሪ እስላም ቡድኖችን እየታገልኩ ነው ላለው ኢሕአዴግን ድጋፋቸውን ቀጥለዋል። የኢህአዴግ ተቃዋሚዎች ምንም እንኳ በደርግ የግፍ አገዛዝ የተማረረው ኢትዮጵያዊ ሁሉ ኢህአዴግን ለመቀበልና አብሮ ለመስራት ወደ ኋላ ባይልም ውሎ ሲያድር ግን በኢህአዴግ የአገር ውስጥ ፖሊሲ መከፋቱ አልቀረም። የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ብሎ ራሱን የስየመው ቡድን ከኢህአዴግ ጋር በመቃቃሩ ራሱን ከፓርላማውና ከካቢኔው አግልሎ ወደ ትጥቅ ትግሉ ተመለሰ። ጠ.ሚ. መለስ የኤርትራን የመገንጠል ጥያቄ ያለምንም ማንገራገር መፍቀዳቸው ብቻ ሳይሆን ሁሉም ብሔረሰብ እንዲገነጠል የሚያስችለውን አንቀጽ በሕገ መንግስታቸው በማካተታቸው በተለይ በምሁራን ዘንድ የከረረ ተቃውሞ አስነስቶባቸዋል። ሁሉም በክልሉ በቋንቋው ይማር የተሰኘው ፖሊሲያቸውም በብዙዎች ዘንድ ጥርጣሬና መከፋፈልን በመፍጠሩ በሀገርና ከሀገር ውጭ በተደጋጋሚ የተቃውሞ ሰልፎች ተካሂዶባቸዋል። በ1997 ዓ.ም. አጋማሽ ጠቅላላ ምርጫ ሲደረግ ከተለያዩ የፖለቲካ ህቡዕ ፓርቲዎች የተውጣጣ ቅንጅት የተሰኘ ጥምር የፖለቲካ ፓርቲ እንደ አንድ የፖለቲካ ድርጅት ተወዳደረ። በውጤቱም የዓለም ታዛቢዎች በተገኙበት በአዲስ አበባ ከተማ ከመቶ 97 እጁ መራጭ የተቃዋሚውን ፓርቲ ቅንጅትን መረጠ። በውጤቱ የተደናገጠው የአቶ መለስ መንግስት ለመጀመሪያ ጊዜ የአዲስ አበባን ፖሊስ በፌዴራል ቁጥጥር ስር አዞረ። የአዲስ አበባ ምክር ቤትንም በኦሮሚያ መስተዳደር ስር እንዲተዳደር አዲስ ድንጋጌ አወጣ። ይሁን እንጂ ብዙም ገለልተኛ ታዛቢ በሌለበት ከአዲስ አበባ ውጪ ኢሕአዴግ 90 በመቶ ማሸነፉ ስለታወጀ ተቃዋሚዎች አድልዎ ተደርጎብናልና ምርጫው እንደገና ይጣራ ብለው ለከፍተኛ ፍርድ ቤት የክስ ማመልከቻ በማስገባታቸው ማጣሪያ ተካሄደ። ተቃዎሚዎች በጠቅላላው የምርጫ ውጤት ባለመስማማታቸው ያሸነፉበትን የፓርላማ ወንበር ባለመቀበል የገዢው ፓርቲ በበላይነት ከተቆጣጠረው ፓርላማ ራሳቸውን አገለሉ። ሚሥስ አና ጎሜዝ የተባሉ የአውሮፓ ታዛቢ ቡድን መሪ ምርጫው አድልዎና ጫና እንደነበረበት ለዓለም ሕዝብ ምስክርነታቸውን ተናገሩ። አብዛኛዎቹ ታዛቢዎች (አፍሪካ ሕብረት አና የጂሚ ካርተርማእከል) ምርጫው በኢትዮጲያ ከተካሄዱ ምርጫዎች በጣም የተሻለ መሆኑን መሰከሩ። በሺ የሚቆጠሩ የቅንጅት ደጋፊዎች በዋና ዋና ከተማዎች በመውጣት ሰላማዊ ሰልፍ በቁጣ በሚገልጹበት ጊዜ ቁጥሩ በርካታ የሆነ ሕዝብ በፖሊስ በቀጥታ በተተኮሰ ጥይት ሕይወቱን አጥቶአል። የአቶ መለስ መንግስት አብዛኛዎችን በህዝብ የተመረጡ የቅንጅት ፓርቲ አባላትንና በሺህ የሚቆጠሩ አባላትን ባገር ክህደት አና መንግስትን ለመገልበጥ በመሞከር ከሰሳቸው። ሁለት ዓመት በፈጀ የፍርድ ሂደትም ፍርድ ቤቱ የቅንጅት መሪዎችን አገርን በመክዳት ወንጀል ጥፋተኛ ሆነው አገኛቸው። ይሁን እንጂ ሁሉም የ ቅንጅት መሪዎችና አብዛኛው ደጋፊ አባላት ጥፋታቸውን አምነው ይቅርታ በመጠየቃቸው ከእስር ነጻ ወጡ።
49168
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8A%A5%E1%8C%8D%E1%88%AD%20%E1%8A%B3%E1%88%B5%20%E1%88%88%E1%8B%88%E1%8B%B3%E1%8C%85%E1%8A%90%E1%89%B5
እግር ኳስ ለወዳጅነት
እግር ኳስ ለወዳጅነት በ የሚተገበር ዓመታዊ የአለምአቀፍ የልጆች ማህበራዊ ፕሮግራም ነው። የፕሮግራሙ ግብ በወጣቱ ትውልድ ላይ በእግር ኳስ በኩል የጤናማ አኗኗር አስፈላጊ እሴቶችን እና ፍላጎትን ማስረጽ ነው። በፕሮግራሙ መዋቅር ውስጥ ከተለያዩ አገሮች የመጡ ዕድሜያቸው 12 ዓመት የሆኑ የእግር ኳስ ተጫዋቾች በዓመታዊ የአለምአቀፍ ልጆች መድረክ፣ የ«እግር ኳስ ለወዳጅነት» አለም ዋንጫ፣ አለምአቀፍ የእግር ኳስ ቀን እና የጓደኝነት ላይ ይሳተፋሉ ። የ ዓለምአቀፍ ፕሮግራሙ አስተባባሪ (ሩሲያ) እግር ኳስ ለወዳጅነት 2013 የመጀመሪያው የአለምአቀፍ የልጆች የእግር ኳስ ለወዳጅነት መድረክ እ.ኤ.አ. ሜይ 25፣ 2013 ለንደን ውስጥ ። ከ8 አገሮች የመጡ 670 ልጆች ተሳትፈውበታል፦ ከቡልጋሪያ፣ ታላቋ ብሪታኒያ፣ ሃንጋሪ፣ ጀርመን፣ ግሪክ፣ ሩሲያ፣ ሰርቢያ እና ስሎቬኒያ ። ሩሲያ በ2018 ዓ.ም. ላይ የፊፋ አለም ዋንጫ ግጥሚያዎችን ከሚያስተናግዱ 11 የሩሲያ ከተማዎች በተውጣጡ 11 የእግር ኳስ ቡድኖች ተወክላ ነበር። እንዲሁም የዜኒት፣ ቼልሲ፣ ሻልክ 04፣ ክርቨና ዝቨዝዳ ክለቦች የሕጻናት ቡድኖች፤ የ የልጆች ስፖርት ቀን አሸናፊዎች፤ እና አሸናፊዎች የእርሱ ፌስቲቫል አሸናፊዎችም በመድረኩ ላይ ተሳትፈዋል። በመድረኩ ጊዜ ልጆቹ ከሌሎች አገሮች ከመጡ አቻዎቻቸው እና ታዋቂ የእግር ኳስ ተጫዋቾች ጋር ተወያይተዋል፣ እና እንዲሁም በዌምብሌይ ስቴዲዮም 2012/2013 ላይ ሻምፒዮንሽ ሊግ ፍጻሜን ተከታትለዋል። የመድረኩ ውጤት ልጆቹ የሚከተሉት የፕሮግራሙ ስምንት እሴቶችን ቀምረው ያስቀመጡበት ክፍት ደብዳቤ ነው፦ ወዳጅነት፣ እኩልነት፣ ፍትሕ፣ ጤና፣ ሠላም፣ ታማኝነት፣ ድል እና ባህሎች። በኋላ ላይ ደብዳቤው ወደ የዩዌፋ፣ ፊፋ እና አይኦሲ መሪዎች ተልኳል]። ሴፕቴምበር 2013 ላይ ከቭላዲሚር ፑቲን እና በተደረገ ስብሰባ ላይ ሴፕ ብላተር ደብዳቤውን መቀበላቸውንና እግር ኳስ ለወዳጅነትን ለመደገፍ ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል። እግር ኳስ ለወዳጅነት 2014 የእግር ኳስ ለወዳጅነት ፕሮግራሙ ሁለተኛ ምዕራፍ እ.እ.አ. ሜይ 23-25፣ 2014 ዓ.ም. ላይ በሊዝበን ላይ የተካሄደ ሲሆን ከ16 አገሮች የመጡ 450 ታዳጊዎችን ያቀፈ ነበር፦ ቤላሩስ፣ ቡልጋሪያ፣ ታላቋ ብሪታኒያ፣ ሃንጋሪ፣ ጀርመን፣ ጣልያን፣ ኔዘርላንድስ፣ ፖላንድ፣ ፖርቱጋል፣ ሩሲያ፣ ሰርቢያ፣ ስሎቬኒያ፣ ቱርክ፣ ዩክሬን፣ ፈረንሳይ እና ክሮሽያ። ወጣቶቹ የእግር ኳስ ተጫዋቾች በአለምአቀፉ የእግር ኳስ ለወዳጅነት መድረክ ላይ ተሳትፈዋል፣ በጎዳና እግር ኳስ ላይ ተሳትፈዋል፣ እና 2013/2014 ላይ የዩዌፋ ሻምፒዮና ሊግ ፍጻሜን ተከታትለዋል ። የ2014 የአለምአቀፍ ጎዳና እግር ኳስ ውድድሩ አሸናፊ ቤንፊካ ታዳጊ ቡድን (ፖርቱጋል) ነው። የፕሮግራሙ ሁለተኛ ምዕራፍ ውጤት የእግር ኳስ ለወዳጅነት ንቅናቄ መሪ ምርጫ ነው። የተመረጠው የፖርቱጋሉ ፌሊፕ ሷሬዝ ነበር ። ጁን 2014 ላይ እንደ የንቅናቄው መሪ ዩሪ አንድሬየቪች ሞሮዞቭን ለመዘከር ዘጠነኛውን የአለምአቀፍ ወጣት እግር ኳስ ውድድርን ጎብኝቶ ነበር። እግር ኳስ ለወዳጅነት 2015 የአለምአቀፍ ማህበራዊ ፕሮግራሙ እግር ኳስ ለወዳጅነት ሶስተኛ ምዕራፍ ጁን 2015 በበርሊን ላይ ነው የተካሄደው። ከእስያ አህጉር የመጡ ወጣት ተሳታፊዎች – ከጃፓን፣ ቻይና እና ካዛክስታን የመጡ የልጆች እግር ኳስ ቡድኖች – ለመጀመሪያ ጊዜ በፕሮግራሙ ላይ ተሳትፈዋል። በጠቅላላ ከ24 አገሮች የመጡ የ24 እግር ኳስ ክለቦች ታዳጊ ቡድኖች በሶስተኛው ምዕራፍ ላይ ተሳትርፈዋል። ወጣት ተጫዋቾቹ ከሌሎች አገሮች ከመጡ አቻዎቻቸው እና የዓለም እግር ኳስ ኮከቦች፣ የፕሮግራሙ አለምአቀፍ አምባሳደር ፍራንዝ ቤከንባወር ጨምሮ፣ ጋር ተወያይተዋል፣ እንዲሁም የታዳጊ ቡድኖች አለምአቀፍ የጎዳና እግር ኳስ ውድድር ላይም ተሳትፈዋል። የ2015 አለምአቀፍ የጎዳና እግር ኳስ ውድድር አሸናፊ የራፒድ አነስተኛ ቡድን (ኦስትሪያ) ነው። የሶስተኛው የእግር ኳስ ለወዳጅነት ፕሮግራም ምዕራፍ ክስተቶች ከቀዳሚ የዓለም መገናኛ ብዙሃን በመጡ 200 አካባቢ ጋዜጠኛዎችና እንዲሁም ከአውሮፓ እና ከእስያ በመጡ የአለምአቀፍ የልጆች ፕሬስ ማዕከል አባል በሆኑ 24 ወጣት ሪፖርተሮች ተሸፍነዋል። የ2015 ዋናው ክስተት የዘጠኝ እሴቶች ዋንጫ ሽልማት ነበር፣ የተሸለመውም የባርሴሎና እግር ኳስ ክለብ (ስፔን) ነበር። አሸናፊው የተመረጠው በመድረኩ ዋዜማ ላይ በሁሉም 24 ተሳታፊ አገሮች ውስጥ በነበረው አለምአቀፍ ድምጽ አሰጣጥ ላይ በተሳተፉ ልጆች ነው። በመድረኩ መጨረሻ ላይ ሁሉም ተሳታፊዎች በወጉ መሠረት የ2014/2015 ሻምፒዮና ሊግ ፍጻሜውን በበርሊን ውስጥ ባለው የኦሊምፒክ ስታዲየም ላይ ተከታትለዋል ። እግር ኳስ ለወዳጅነት 2016 በ 2016 ለጓደኝነት የሚጀምሩ ዓለማቀፍ የልጆች ማህበራዊ መርሃ ግብር በኦንላይን አብሮ መሆን ተጫን ጉባኤ እንደ አንድ ክፍል ተሰጥቶ ነበር መጋቢት 24 ሙኒክ ውስጥ ተካሂዷል ተካሂዷል የአለምአቀፍ አምባሳደር የተሳተፈበት። በፕሮግራሙ አራተኛ ምዕራፍ ላይ ከአዘርባይጃን፣8 አዲሱ ወጣት ቡድን አልጄሪያ፣ አርሜኒያ፣ አርጀንቲና፣ ብራዚል፣ ቪዬትናም፣ ኪርጊዝታን እና ሶርያ ተቀላቅለውበታል፣ ስለዚህ ጠቅላላው የተሳታፊ አገሮች ብዛት 32 ላይ ደረሰ። እ.ኤ.አ. ኤፕሪል 5፣ 2016 ዓ.ም. ላይ ልዩ የሆነው የዘጠኝ እሴቶች ዋንጫ ምርጫ ተጀመረ ። በመላው ዓለም ያሉ አድናቂዎች አሸናፊውን መምረጥ ላይ ተሳትፈዋል፣ ነገር ግን የመጨረሻው ውሳኔ የተሰጠው የእግር ኳስ ለወዳጅነት ፕሮግራም ተሳታፊዎች ባካሄዱት ምርጫ ነው። ዋንጫው ያሸነፈው የባየርን እግር ኳስ ክለብ (ሙኒክ) ነው። የእግር ኳስ ለወዳጅነት ተሳታፊዎች ክለቡ ልዩ ፍላጎቶች ያላቸው ልጆችን ለመደገፍ ያደረጋቸው እንቅስቃሴዎችንና እንዲሁም በተለያዩ አገሮች ውስጥ ላሉ ልጆች ሕክምና ማቅረብና እርዳታ የሚያስፈልጋቸውን ልጆች ለመርዳት ያደረጋቸው ጅማሮዎችን አውስተዋል። አራተኛው የአለምአቀፍ ልጆች መድረክ እግር ኳስ ለወዳጅነት እና የልጆቹ አለምአቀፍ የጎዳና እግር ኳስ ውድድር የፍጻሜ ጨዋታ እ.ኤ.አ. ሜይ 27-28፣ 2016 ዓ.ም. በሚላን ውስጥ ተካሂዷል። የውድድሩ አሸናፊ የስሎቬኒያው የማሪቦር ቡድን ነው። በመድረኩ መጨረሻ ላይ ተሳታፊዎቹ በወጉ መሠረት የዩዌፋ ሻምፒዮና ሊግ ፍጻሜውን ተከታትለዋል ። የመድረኩ ክስተቶች ከቀደምት መገናኛ ብዙሃን በመጡ 200 ጋዜጠኛዎችና እንዲሁም ከተሳታፊ አገሮች በመጡ ወጣት ጋዜጠኛዎችን ባካተተው የልጆች አለምአቀፍ ፕሬስ ማዕከል ተሸፍኗል። ከሶርያ ክለብ አልዋህዳ የመጡ ወጣት የእግር ኳስ ተጫዋቾች በአራተኛው የእግር ኳስ ለወዳጅነት ምዕራፍ ላይ ተካፍለው ነበር፣ ይህም ከዚህ በፊት ያልተደረገ ነው። የሶርያው ቡድን ከፕሮግራሙ ተሳታፊዎች ውስጥ መካተቱ እና የሶርያ ልጆች በሚላን ውስጥ የነበሩ ክስተቶችን መጎብኘታቸው በአገሪቷ ውስጥ የነገሰውን ሰብዓዊ ቀውስ መወጫ አንድ አስፈላጊ እርምጃ ነበር። የአለምአቀፍ ቴሌቪዥን ጣቢያው ራሽያ ቱዴይ የአረብኛው የስፖርት እትም ቦርዱ በሶርያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ድጋፍ ልጆቹ በፕሮጀክቱ ላይ መሳተፋቸውን የሚያሳይ «ሶስት ቀናት ያለጦርነት» () የሚል ጥናታዊ ፊልም ሰርቷል። እ.ኤ.አ. በሴፕቴምበር 14፣ 2016 ዓ.ም. ላይ ከ7,000 በላይ ሰዎች ፊልሙን በደማስቆ ላይ ሲመረቅ ተመልክተውታል። እግር ኳስ ለወዳጅነት 2017 በ2017 የአለምአቀፍ ልጆች ማህበራዊ ፕሮጀክቱ እግር ኳስ ለወዳጅነት የተዘጋጀው በሴንት ፒተርስበርግ (ሩሲያ) ሲሆን የመጨረሻዎቹ ክስተቶች ከጁን 26 እስከ ጁላይ 3 ድረስ እዚሁ የተካሄዱ ናቸው። 2017 ላይ የተሳታፊ አገሮች ብዛት ከ32 ወደ 64 አድጓል። ለመጀመሪያ ጊዜ የእግር ኳስ ለወዳጅነት ፕሮግራሙ ከሜክሲኮ እና ከአሜሪካ የመጡ ልጆች ተከታትለውታል። በዚህም ፕሮጀክቱ የአራት አህጉራት — አፍሪካ፣ ዩሬዥያ፣ ሰሜን አሜሪካ እና ደቡብ አሜሪካ — ወጣት ተጫዋቾችን አገናኝቶ አንድ አድርጓቸዋል። በአምስተኛው ምዕራፍ ላይ ፕሮግራሙ በአዲስ ጽንሰ-ሐሳብ መሠረት ነው የተተገበረው፦ ከእያንዳንዱ አገር አንድ ወጣት ተጫዋች አገሩ/ሯን እንዲወክሉ ተመርጠዋል። አካል ጉዳት ያላቸው ጨምሮ ልጆቹ 12 ዓመት በሆናቸው ወንድ እና ሴት ልጆች በተመሠረቱ አለምአቀፍ የወዳጅነት ቡድኖች ላይ አንድነት አሳይተዋል። በተደረገ ግልጽ የዕጣ ስነ-ስርዓት የቡድኖቹ የአገር ጥንቅር እና የተሳታፊ አገሮች ተወካዮች የጨዋታ ቦታዎች ተወስኗል። ዕጣው በበይነመረብ ጉባዔ ሁነታ ላይ ነው የተካሄደው። ስምንቱ የወዳጅነት ቡድኖችን የመሩት ወጣት አሰልጣኞች ናቸው፦ (ስሎቬኒያ)፣ ስቴፋን ማክሲሞቪች (ሰርቢያ)፣ ብራንደን ሻባኒ (ታላቋ ብሪታኒያ)፣ ቻርሊ ሱዊ (ቻይና)፣ (ሩሲያ)፣ ቦግዳን ክሮለቨትስኪ (ሩሲያ)፣ አንቶን ኢቫኖቭ (ሩሲያ)፣ (ኔዘርላንድስ)። የእግር ኳስ ለወዳጅነት አለምአቀፍ ፕሬስ ማዕከል ተወካይየሆኑት ሊሊያ ማትሱሞቶ (ጃፓን) እንዲሁም በዕጣው ስነ-ስርዓቱ ላይም ተካፍለዋል። የእግር ኳስ ለወዳጅነት 2017 አለም ዋንጫ አሸናፊ «ብርቱካናማ» ቡድኑ ነበር፣ ይህም ከዘጠኝ አገሮች ወጣት አሰልጣኝ እና ወጣት እግር ኳስ ተጫዋቾችን ያካተተ ነበር፦ (ስሎቬኒያ)፣ ሆንግ ጁን ማርቪን ቱ (ሲንጋፖር)፣ ፖል ፑዊግ ኢ ሞንታና (ስፔን)፣ ጋብሪየል ሜንዶዛ (ቦሊቪያ)፣ ራቫን ካዚሞቭ (አዘርባይጃን)፣ ክሪሲሚር ስታኒሚሮቭ (ቡልጋሪያ)፣ ኢቫን አጉስቲን ካስኮ (አርጀንቲና)፣ ሮማን ሆራክ (ቼክ ሪፐብሊክ)፣ ሃምዛህ ዩሱፍ ኑሪ አልሃቫት (ሊብያ)። ቁልፍ የሰብዓዊ እሴቶች በወጣቱ ትውልድ ላይ እንዲሰርጽ ጥሪ ያቀረቡ ቪክቶር ዙብኮቭ (የ ዳይሬክተሮች ቦርድ ሊቀ-መንበር)፣ ፋትማ ሳሙራ (የፊፋ ዋና ሴክረተሪ)፣ ፊሊፕ ለ ፍሎክ (የፊፋ ዋና የንግድ ዳይሬክተር)፣ ጂዩሊዮ ባፕቲሳ (የብራዚል እግር ኳስ ተጫዋች)፣ ኢቫን ዛሞራኖ (የቺሊ አጥቂ)፣ አሌክሳንደር ከርዛኮቭ (የሩሲያ እግር ኳስ ተጫዋች) እና ሌሎች እንግዳዎች የአለምአቀፍ ልጆች መድረኩን እግር ኳስ ለወዳጅነት ተከታትለውታል። 2017 ላይ ፕሮጀክቱ ከ600,000 በላይ ሰዎችን አንድ ላይ ያሰባሰበ ሲሆን ከ64 አገሮች የተውጣጡ ከ1,000 በላይ ልጆችና አዋቂዎች የመጨረሻዎቹን ክስተቶች በሴንት ፒተርስበርግ ላይ ተከታትለዋል። እግር ኳስ ለወዳጅነት 2018 2018 ላይ ስድስተኛው የእግር ኳስ ለወዳጅነት ፕሮግራሙ በሩሲያ ውስጥ ከፌብሩዋሪ 15 እስከ ጁን 15 እንዲካሄድ ተወስኗል። የፕሮግራሙ ተሳታፊዎች 211 አገሮችን እና የዓለም ክፍሎችን የሚወክሉ ወጣት እግር ኳስ ተጫዋቾችን እና ጋዜጠኛዎችን ያካትታል። የ2018 ፕሮግራሙ ኦፊሴላዊ ጅምር በአየር ላይ በግልጽ የእግር ኳስ ለወዳጅነት ዕጣ የተሰጠ ሲሆን በውጤቶቹ መሠረት 32 የአለምአቀፍ እግር ኳስ ቡድኖች – የወዳጅነት ቡድኖች – ተመስርተዋል። አዲሱ የእግር ኳስ ለወዳጅነት ፕሮግራም ክፍል የአካባቢ ጥበቃ ተልዕኮ ነው – 2018 ላይ የአለምአቀፍ እግር ኳስ ወዳጅነት ቡድኖች በብርቅዬ እና አደጋ ላይ ያሉ የእንስሳት ዝርያዎች ነው የተሰየሙት፦ በ2018 ዓ.ም. የተፈጥሮ ጥበቃ ተልእኮ መሠረት የሚል መጠሪያ የተሰጠው የዓለም ማህበረሰብ በመጥፋት ላይ የሚገኙ እንሠሣትን ለማዳን የተጀመረውን እንቅስቃሴ እንዲደግፍ ጥሪ አቅርበዋል። የሩሲያ የዓሜሪካ የኔፓልና የታላቋ ብሪታኒያ የእንሠሣት ጥበቃ ክልሎች በእንቅስቃሴው ላይ ተካፋዮች ሆነዋል። ሞስኮ ውስጥ በተደረገው የእግር ኳስ ለወዳጅነት የመዝጊያ ሥነ ሥርዓት ላይ ወቅት ተካፋዮቹ በተፈጥሮ ጋዝ የሚንቀሳቀሱ በኤኮ ወዳጅ አውቶቡሶች ተጉዘዋል። በ2018 ውስጥ በእግር ኳስ ለወዳጅነት ፕሮግራም ውስጥ የሚሳተፉ አገሮች እና ክልሎች፦ 1. የአውስትራሊያ ኮመንዌልዝ 2. የኦስትሪያ ሪፐብሊክ 3. የአዘርባይጃን ሪፐብሊክ 4. የአልጄሪያ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ 5. ዩናይትድ ስቴትስ ቨርጂን ደሴቶች 6. የአሜሪካ ሳሞአ 7. አንጉላ 8. አንቲጓ እና ባርቡዳ 9. የግብጽ አረብ ሪፐብሊክ 10. አርጀንቲና ሪፐብሊክ 11. አሩባ 12. ባርቤዶስ 13. ቤሊዝ 14. የቤርሙዳ ደሴቶች 15. የቬነዝዌላ ቦሊቫሪያዊ ሪፐብሊክ 16. ቦስኒያ እና ሄርዘጎቪና 17. የብሪታኒያ ቨርጂን ደሴቶች 18. ቡርኪና ፋሶ 19. የሉክዘምበርግ ታላቅ ግዛት 20. ሃንጋሪ 21. የኡራጓይ ኦሪየንታል ሪፐብሊክ 22. ጋቦን ሪፐብሊክ 23. የጊኒ ሪፐብሊክ 24. ጂብራልታር 25. ብሩነይ ዳሩሳላም 26. እስራኤል 27. ኳታር 28. ኩዌት 29. ሊብያ 30. ፍልስጥኤም 31. ግረናዳ 32. ግሪክ 33. ጂዮርጂያ 34. የቲሞር-ሌስተ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ 35. የኮንጎ ዲምክራሲያዊ ሪፐብሊክ 36. የሳኦ ቶሜ እና ፕሪንሲፕ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ 37. የሽሪላንካ ዲሞክራሲያዊ ሶሻሊስት ሪፐብሊክ 38. የዶሚኒካ ሪፐብሊክ 39. ዮርዳኖስ 40. የአፍጋኒስታን እስላማዊ ሪፐብሊክ 41. የኢራን እስላማዊ ሪፐብሊክ 42. የማውሪታኒያ እስላማዊ ሪፐብሊክ 43. የጣልያን ሪፐብሊክ 44. የየመን ሪፐብሊክ 45. የካይማን ደሴቶች 46. ካናዳ 47. የቻይና ሕዝባዊ ሪፐብሊክ 48. የቻይና ታይፔይ (ታይዋን) 49. አንዶራ 50. ሊችተንስታይን 51. የጉያና ትብብራዊ ሪፐብሊክ 52. የኮሪያ ዲሞክራሲያዊ ሕዝባዊ ሪፐብሊክ 53. ባህሬን መንግሥት 54. ቤልጂየም መንግሥት 55. ቡታን መንግሥት 56. ዴንማርክ መንግሥት 57. ስፔንመንግሥት 58. ካምቦዲያመንግሥት 59. ሌሶቶ መንግሥት 60. ሞሮኮ መንግሥት 61. ኔዘርላንድስ መንግሥት 62. ኖርዌይ መንግሥት 63. ሳውዲ አረቢያመንግሥት 64. ስዋዚላንድመንግሥት 65. ታይላንድ መንግሥት 66. ቶንጋ መንግሥት 67. ስዊድንመንግሥት 68. ኪርጊዝ ሪፐብሊክ 70. የላዎ ሕዝብ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ 71. የላትቪያ ሪፐብሊክ 72. የሊባኖስ ሪፐብሊክ 73. የሊቱዌኒያ ሪፐብሊክ 74. ማሌይዥያ 75. የማልዲቭስ ሪፐብሊክ 76. ሜክሲኮ 77. ቦሊቪያ 78. ሞንጎሊያ 79. ሞንትሴራት 80. የባንግላዴሽ ሕዝብ ሪፐብሊክ 81. የፓፑዋ ኒው ጊኒ ነጻ ግዛት 82. የሳሞአ ነጻ ግዛት 83. ኒው ዚላንድ 84. ኒው ካሌዶኒያ 85. ታንዛኒያ 86. የተባበሩት አረብ ኢመሬቶች 87. የኩክ ደሴቶች 88. የቱርክ እና ካይኮስ ደሴቶች 89. የአልባኒያ ሪፐብሊክ 90. የአንጎላ ሪፐብሊክ 91. የአርሜኒያ ሪፐብሊክ 92. የቤላሩስ ሪፐብሊክ 93. የቤኒን ሪፐብሊክ 94. የቡልጋሪያ ሪፐብሊክ 95. የቦትስዋና ሪፐብሊክ 96. የቡሩንዲ ሪፐብሊክ 97. የቫኗቱ ሪፐብሊክ 98. የሃይቲ ሪፐብሊክ 99. የጋምቢያ ሪፐብሊክ 100. የጋና ሪፐብሊክ 101. የጓቴማላ ሪፐብሊክ 102. የጊኒ-ቢሳው ሪፐብሊክ 103. የሆንዱራስ ሪፐብሊክ 104. የጅቡቲ ሪፐብሊክ 105. የዛምቢያ ሪፐብሊክ 106. የዚምባብዌ ሪፐብሊክ 107. የህንድ ሪፐብሊክ 108. የኢንዶኔዥያ ሪፐብሊክ 109. የኢራቅ ሪፐብሊክ 110. የአየርላንድ ሪፐብሊክ 111. የአይስላንድ ሪፐብሊክ 112. የካዛክስታን ሪፐብሊክ 113. የኬንያ ሪፐብሊክ 114. የቆጵሮስ ሪፐብሊክ 115. የኮሎምቢያ ሪፐብሊክ 116. የኮንጎ ሪፐብሊክ 117. የኮሪያ ሪፐብሊክ 118. የኮሶቮ ሪፐብሊክ 119. የኮስታ ሪካ ሪፐብሊክ 120. የኮት ዲቯር ሪፐብሊክ 121. የኩባ ሪፐብሊክ 122. የላይቤሪያ ሪፐብሊክ 123. የማውሪሸስ ሪፐብሊክ 124. የማዳጋስካር ሪፐብሊክ 125. የመቄዶንያ ሪፐብሊክ 126. የማላዊ ሪፐብሊክ 127. የማሊ ሪፐብሊክ 128. የማልታ ሪፐብሊክ 129. የሞዛምቢክ ሪፐብሊክ 130. የሞልዶቫ ሪፐብሊክ 131. የናሚቢያ ሪፐብሊክ 132. የኒጀር ሪፐብሊክ 133. የኒካራጓ ሪፐብሊክ 134. የኬፕ ቨርዴ ሪፐብሊክ 135. የፓኪስታን እስላማዊ ሪፐብሊክ 136. የፓናማ ሪፐብሊክ 137. የፓራጓይ ሪፐብሊክ 138. የፔሩ ሪፐብሊክ 139. የፖላንድ ሪፐብሊክ 140. የፖርቱጋል ሪፐብሊክ 141. የርዋንዳ ሪፐብሊክ 142. የሳን ማሪኖ ሪፐብሊክ 143. የሲሸልስ ሪፐብሊክ 144. የሴነጋል ሪፐብሊክ 145. የሰርቢያ ሪፐብሊክ 146. የሲንጋፖር ሪፐብሊክ 147. የስሎቬኒያ ሪፐብሊክ 148. የሚያንማር ህብረት ሪፐብሊክ 149. የሱዳን ሪፐብሊክ 150. የሱሪናም ሪፐብሊክ 151. የሴራ ሊዮን ሪፐብሊክ 152. የታጂኪስታን ሪፐብሊክ 153. የትሪኒዳድ እና ቶቤጎ ሪፐብሊክ 154. የቱርክሜኒስታን ሪፐብሊክ 155. የኡጋንዳ ሪፐብሊክ 156. የኡዝቤኪስታን ሪፐብሊክ 157. የፊጂ ሪፐብሊክ 158. የፊሊፒንስ ሪፐብሊክ 159. የክሮሽያ ሪፐብሊክ 160. የቻድ ሪፐብሊክ 161. የሞንተኔግሮ ሪፐብሊክ 162. የቺሊ ሪፐብሊክ 163. የኢኳዶር ሪፐብሊክ 164. የኢኳቶሪያል ጊኒ ሪፐብሊክ 165. የኤል ሳልቫዶር ሪፐብሊክ 166. የደቡብ ሱዳን ሪፐብሊክ 167. የካሜሮን ሪፐብሊክ 168. የሩሲያ ፌደሬሽን 169. ሮማኒያ 170. የሕዝባዊ ሪፐብሊክ ቻይና የሆንግ ኮንግ ልዩ አስተዳደራዊ ክልል 171. የፖርቶ ሪኮ ነጻ ተጓዳኝ ግዛት 172. ሰሜናዊ አየርላንድ 173. ሴንት ቪንሰንት እና ግረናዲንስ 174. ሴንት ሉሲያ 175. የሶርያ አረብ ሪፐብሊክ 176. የስሎቫክ ሪፐብሊክ 177. የባሃማስ የጋራ ብልጽግና 178. የዶሚኒካ የጋራ ብልጽግና 179. የታላቋ ብሪታኒያ እና የሰሜናዊ አየርላንድ የተባበረ ንጉሳዊ ግዛት 180. አሜሪካ 181. የሰለሞን ደሴቶች 182. የቪዬትናም ሶሻሊስት ሪፐብሊክ 183. የኮሞሮስ ህብረት 184. የሕዝባዊ ሪፐብሊክ ቻይና የማካዎ ልዩ አስተዳደራዊ ክልል 185. የኦማን ሱልታኔት 186. ታሂቲ 187. የጓም ግዛት 188. የቶጎ ሪፐብሊክ 189. የቱኒዚያ ሪፐብሊክ 190. የቱርክ ሪፐብሊክ 191. ዩክሬን 192. ዌልስ 193. የፋሮዌ ደሴቶች 194. የኔፓል ፌዴራል ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ 195. የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ 196. የብራዚል ፌዴራላዊ ሪፐብሊክ 197. የጀርመን ፌዴራላዊ ሪፐብሊክ 198. የናይጄሪያ ፌዴራላዊ ሪፐብሊክ 199. የሶማልያ ፌዴራላዊ ሪፐብሊክ 200. የሴንት ኪትስ እና ኔቪስ ፌዴሬሽን 201. የፊንላንድ ሪፐብሊክ 202. የፈረንሳይ ሪፐብሊክ 203. የመካከለኛ አፍሪካ ሪፐብሊክ 204. የቼክ ሪፐብሊክ 205. የስዊስ ኮንፌዴሬሽን 206. ስኮትላንድ 207. ኤርትራ 208. የኤስቶኒያ ሪፐብሊክ 209. የደቡብ አፍሪካ ሪፐብሊክ 210. ጃማይካ 211. ጃፓን በ2018 ዓ.ም. በተደረገው የዓለም አቀፍ «የእግር ኳስ ለወዳጅነት» ሻምፒዮና ላይ 32 የዓለም አቀፍ ቡድኖች «የእግር ኳስ ለወዳጅነት» ቡድኖችተካፋይሆነዋል። የፍጻሜው ውድድር ዘጋቢም ሶሪያዊው ወጣት ዘጋቢ ያዝን ጣኃ ነበር። የፍጻሜው ውድድርም ዋና ዳኛም ወጣቱ ሩሲያዊው ቦግዳን ባታሊን ነበር። የ2018 «የእግር ኳስ ለወዳጅነት» ውድድር አሸናፊም «የሺምፓንዜ» ቡድን ሲኾን ተጫዋቾቹም ከዶሚኒካ ከሴንት ኪትስና ኔቪስ ማላዊ ኮሎምቢያ ቤኒንና ዴሞክራቲክ ሪፓብሊክ ኮንጎ የተውጣጡ ነበሩ። የቡድኑም አልጣኝ ከሣራንስክ (ሩሲያ የመጣው ተሣታፊ ቭላዲስላቭ ፐሊኮቭ ነበር። የስድስተኛው «የእግር ኳስ ለወዳጅነት» የመዝጊያ ሥነ ሥርዓት የህፃናት ጉባኤ ሰኔ 13 ቀን «በሞስ አኳረም» የውቂያኖስና የሥነ ተፈጥሮ ምርምር ማእከል ነበር። በሥነ ሥርዓቱም ላይ ቪክተር ዙብኮቭ (የጋዝፕሮም ሕዝባዊ አክሲዮን ማህበር የዲሬክተሮች ምክር ቤት ሊቀ መበር) ኦልጋ ገለዴትስ የሩሲያ ፌዴሬሽን መንግሥት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ኢከር ካሲሊ ስታዋቂው የእስፓኝ የእግር ኳስ ተጫዋችና የብሔራዊ ቡድን ካፒቴን አሌክሳንድር ከርዣኮቭ የሩሲያ የእግር ኳስ ተጫዋችና የወጣቶች ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝና የ54 ሀገሮች አምባሰደሮችና ሌሎች እንግዶች ተገኝተዋል። በመዝጊያ ሥነ ሥርአቱም ላይ የስድስተኛው ዙር ምርጥ ወጣት የእግር ኳስ ተጫዋቾች ሽልማት አግኝተዋል። ዴኦ ካሌንጋ ምቬንዜ ከዴሞክራቲክ ሪፓብሊክ ኮንጎ (ምርጥ አጥቂ) ያሚሩ ኦኡሩ ከቤኒን (ምርጥ በረኛ) ጉስታቮ ሰንትራ ሮቻ ከብራዚል (እጅግ ጠቃሚ ተጫዋች) በመኾን ልዩ ተሸላሚዎች ሆነዋል። የ2018 ዓ. ም. «የእግር ኳስ ለወዳጅነት» ምርጥ ወጣት ጋዜኛ አሩባዊቷ ሼይካሊ አሰንሲዮን በብሎጓ አማካይነት ወጣት የኦኪያኒያ ነዋሪዎች ለስነተፈጥሮ ልዩ ትኩረት እንዲሰጡ አሳስባለች። በሥነ ሥርአቱም ላይ የቀዳሚው «የእግር ኳስ ለወዳጅነት» ዙር ተካፋይ የነበረችው የህንዳዊቷ የአናኒ ካምቦጅ መጽሐፍ ተመርቋል። በ2017 ዓ. ም. አምስተኛው «የእግር ኳስ ለወዳጅነት» ውድድር ከተጠናቀ በኋላ አናኒ እንደ ወጣት ጋዜጠኛ በውድድሩ ወቅት ያገኘችውን ልምድ የሚዘግብ «ጉዞዬ ከሞሃይ እስከ ቅዱስ ፒተርቡርግ» የሚል መጽሐፍ ለአንባቢያን አቅርባለች። በመጽሐፉም ውስጥ ለዓለም መለወጥ እገዛ የሚያደርጉ ዘጠኝ እሴቶችን አስቀምጣለች። ሰኔ 14 ቀን «የእግር ኳስ ለወዳጅነት» ዓለም አቀፍ የልጆች ጉባኤ ከተጠናቀቀ በኋላ ወጣት የእግር ኳስ ተጫዋቾችና ጋዜጠኞች በዓለም አቀፍ የእግር ኳስ ማህበር (ፊፋ) በ 2018 ዓ. ም. በሞስኮ ከተማ በተዘጋጀው የዓለም የእግር ኳስ ሻምፒዮና መክፈቻ ሥነ ሥርት ላይ ተካፍዋል። ሰኔ 14 ቀን «የእግር ኳስ ለወዳጅነት» ዓለም አቀፍ የልጆች ጉባኤ ከተጠናቀቀ በኋላ ወጣት የእግር ኳስ ተጫዋቾችና ጋዜጠኞች በዓለም አቀፍ የእግር ኳስ ማህበር (ፊፋ) በ 2018 ዓ. ም. በሞስኮ ከተማ በተዘጋጀው የዓለም የእግር ኳስ ሻምፒዮና መክፈቻ ሥነ ሥርት ላይ ተካፍዋል። ልጆቹም በሉዥኒኪይ ስታዲየም በመክፈቻው ሥነ ሥርአት ላይ ተካፋይ የኾኑትን የ211 ሀገሮችን የሰንደቅ ዓላማዎች በታላቅ ክብር ሰቅለዋል። ከዚያም በሩሲያሲያና በሳኡዲ አረቢያ ብሔራዊ ቡድኖች መካከል የተደረገውን የመክፈቻ ጨዋታ ተመልክተዋል። በመክፈቻው ሥነ ሥርአት ላይ የተገኙት ፕሬዝደንት ቭላዲሚር ፑቲን የሩሲያሲያውን ወጣት «የእግር ኳስ ለወዳጅነት» አምባሳደር አልበርት ዚናቶቭን ወደ መንበራቸው በመጋበዝ የመክፈቻ ውድድሩን ተመልክተዋል። ወጣቱ አምባሳደርም ከብራዚላዊው የዓለም የእግር ኳስ ሻምፒዮን ሮቤርቶ ካርሎስና ከእስፓኙ የእግር ኳስ ተጫዋች ከኢከር ካሲሊያስ ጋር ሀሣብ ተለዋውጧል። በፍጻሜ ሥነ ሥርአቶች ላይም ከ211 ሀገሮች የተውጣጡ ከ1500 በላይ ልጆች ተካፍለዋል። በጠቅላላው በስድስተኛው ዓለም አቀፍ «የእግር ኳስ ለወዳጅነት» በተለያዩ የዓለም ክፍሎች በተደረጉት ከ180 በላይ ዝግጅቶች ላይ ከ240 ሺ በላይ ልጆች ተካፋይ ኾነዋል። የ2018 ዓ.ም ፕሮጀክቱም በከፍተኛ የሩሲያ ባለሥልጣናት በኩል ድጋፍ አግኝቷል። በዝግጅቱ መክፈቻ ሥነ ሥርአት ላይ የሩሲያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ኦልጋ ገለዴትስ የፕሬዝደንት ቭላዲሚር ፑቲንን የመልካም ምኞት መግለጪያ አንብበዋል። የሩሲያ ጠቅላይ ሚኒስትር ድሚትሪ ሜድቬደቭም በበኩላቸው ለስድስተኛው የዓለም አቀፍ «የእግር ኳስ ለወዳጅነት» ተሳታፊዎችና እንግዶች የመልካም ምኞት ቴሌግራም አስተላልፈዋል። የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አፈ ቀላጤ ማሪያ ዛኃሮቫ ግንቦት 23 ቀን ባደረገችው አጭር መግለጪያ የዓለም አቀፍ «የእግር ኳስ ለወዳጅነት» በዓለም ማህበረሰብዕ ዘንድ ዋነኛ ከኾኑት የሀገሪቷ ሰብአዊ ተኮር ፖሊሲዎች አንዱ እንደኾነ ገልጻለች። የዓለም አቀፍ የእግር ኳስ ማህበር (ፊፋ) የዓለም አቀፍ «የእግር ኳስ ለወዳጅነት» ን እንደሚደግፍ የገለጸ ሲኾን በሞስኮ የ2018 ዓ.ም. በተካሄደው ዝግጅት ላይ የተሣታፊዎችና የእንግዶች ቁጥር ወደ 5000 እንደሚጠጋ አስታውቋል። እግር ኳስ ለወዳጅነት 2019 እ.ኤ.አ. መጋቢት 18 ቀን 2019 ሰባተኛው ዙር የዓለም አቀፍ የህፃናት ማህበራዊ የእግር ኳስ ለወዳጅነት ፕሮግራም የተከናወነ ሲሆን የፍጻሜው ፕሮግራምም ከግንቦት 28 እስከ ሰኔ 2 ድረስ በማድሪድ ከተማ ተካሂደዋል ፡፡ ሚያዝያ 25 ቀን የዓለም አቀፍ የእግር ኳስ እና ወዳጅነት ቀን ከ 50 በላይ በሆኑ የአውሮፓ ፣ የእስያ ፣ የአፍሪካ ፣ የሰሜን እና ደቡብ አሜሪካ ሀገሮች የተከበረ ሲሆን የሩሲያ የእግር ኳስ ህብረትም () የበዓሉ ተካፋይ ሆኗል፡፡ /እ.ኤ.አ. ግንቦት 30 ቀን በማድሪድ ከተማ የተካሄደው የዓለም አቀፍ የህፃናት ማህበራዊ ጉባኤ መድረክላይ ከመላው ዓለም የተውጣጡ ባለሙያዎች - የእግር ኳስ አሰልጣኞች ፣ የህፃናት ቡድን ሐኪሞች ፣ ኮከቦች ፣ መሪ የዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ጋዜጠኞች ፣ የዓለም የእግር ኳስ አካዳሚዎች ተወካዮችና ፌዴሬሽኖች ተካፍለዋል። ግንቦት 31 ቀን ሁሉን አቀፍ የዓለም እግር ኳስ ሥልጠና በማድሪድ ተካሂዷል ፡፡ «የእግር ኳስ ለወዳጅኝነት የ ኦፊሴላዊ የምስክር ወረቀት ተቀብሏል ®. በሰባተኛው ዙር የእግር ኳስ ለወዳጅኝነት ውድድር ከአውሮፓ ፣ ከአፍሪካ ፣ ከእስያ ፣ ከሰሜን እና ከደቡብ አሜሪካ የተውጣጡ 32 ወጣት ጋዜጠኞች ዓለም አቀፍ የህፃናት ፕሬስ ማዕከልን በማዋቀር የዝግጅቱን ዜናዎች ከዓለም አቀፍ እና ከብሔራዊ መገናኛ ብዙሃን ጋር በመተባበር አቀናብረው አቅርበዋል። የሰባተኛው ዙር የእግር ኳስ ለወዳጅኝነት ተሳታፊዎች «የዘጠኝ እሴቶች ዋንጫ» (የዓለም አቀፍ የህፃናት ማህበራዊ ፕሮግራም እግር ኳስ ለወዳጅነት ሽልማት) ለሊቨርፑል እግር ኳስ ክለብ እጅግ ማህበራዊ ኃላፊነት ያለው ቡድን በማለት አበርክተዋል እ.ኤ.አ. ሰኔ 1 የሰባተኛው ዙር ፍፃሜ በማድሪድ የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበራት ህብረት () ፒች እግር ኳስ ሜዳ ተካሄዷል - በፍጻሜ ውድሩ ላይ የአንቲጉዋ እባብ ብሔራዊ ቡድንና የታስማኒያ ዲያብሎስ በመደበኛው ሰዓት 1: 1 ተለያይተው ነበር።የአንቲጉዋ እባብ በቅጣት ምት አሸናፊ በመሆን ዋናውን ሽልማት አግኝቷል ፡፡. እግር ኳስ ለወዳጅነት 2020 ስምንተኛው የእግር ኳስ ለወዳጅኝነት ውድድር እ.ኤ.አ. በ 2020 (እ.ኤ.አ.) ከህዳር 27 እስከ ታህሣስ 9 ቀን 2020 በዲጂታል መሥመር ላይ ተካሂዷል። ከ 100 በላይ ሀገሮች የተውጣጡ ከ 10,000 በላይ ተሳታፊዎች ቁልፍ በሆኑ ዝግጅቶች ላይ ተካፍለዋል ፡፡ . ለስምንተኛው ዙር ውድድር ሲባል አንድ ባለብዙ ተተጠቃሚዎችየእግር ኳስ ለወዳጅኝነት ተዘጋጅቷል ፣ በዚህ ፕሮግራምመሠረት የእግር ኳስ ለወዳጅኝነት 2020 ሻምፒዮና ተካሂዷል። ጨዋታውን ከታህሣስ 10 ቀን 2020 ጀምሮ- የዓለም እግር ኳስ ቀን መጫን ይቻላል ፡፡ ተጠቃሚዎች በዓለም አቀፍ ቡድኖች ውስጥ አንድ ላይ በመሆን በእግር ኳስ ለወዳጅኝነት ህጎች መሠረት በጨዋታዎች የመሳተፍ ዕድልን አግኝተዋል ፡፡ ይህ የባለብዙ አውታረ መረብ ተጠቃሚዎች ጨዋታ እንደ ወዳጅነት ፣ ሰላም እና እኩልነት ባሉ የፕሮግራሙ ዋና እሴቶች ላይ የተመሠረተ ነው። . እ.ኤ.አ. ኅዳር 27 የእግር ኳስ ለወዳጅኝነት የዓለም አቀፍ ሻምፒዮና 2020 የመስመር ላይ የእጣ አጣጣል ሥነሥርዓት ተካሂዷል ከኅዳር 28 እስከ ታህሳስ 6 ድረስ ለህፃናት የሰብአዊ እና የስፖርት ትምህርታዊ መርሃግብሮች ያለው ዓለም አቀፍ የመስመር ላይ የወዳጅነት ስብሰባ ተካሄደ ከኅዳር 30 እስከ ታህሳስ 4 ቀን ድረስ የልጆች ስፖርቶች ማሳደጊያ ፕሮጀክቶች የቀረቡበት “እግር ኳስ ለወዳጅኝነት” የተሰኘው ዓለም አቀፍ የመስመር ላይ መድረክ ስብሰባ ተካሄዷል ፡፡ ባለሙያዎች “እግር ኳስ ለጓደኝነት” ለዓለም አቀፍ ሽልማት የሚያበቁ ፕሮጀክቶች በማቅረባቸው አድናቆታቸውን ገልጸዋል » ከታህሳስ 7-8 (እ.ኤ.አ.) የእግር ኳስ ለወዳጅኝነት የመስመር ላይ የዓለም ሻምፒዮና ተካሄደ ፡፡ የዘንድሮው ሻምፒዮና በዲጂታል መድረክ በመስመር ላይ የተካሄደ ሲሆን የባለብዙ ተጫዋች እግር ኳስ አስመሳይ () እግር ኳስ ለጓደኝነት በልዩ ሁኔታ ተዘጋጅቷል . ታህሳስ 9 ቀን ታላቁ የእግር ኳስ ለወዳጅኝነት ፍፃሜ ተካሂዷል የተባበሩት መንግስታት 75 ኛ ዓመት የምስረታ በዓል በመደገፍ ከተለያዩ ሀገራት ለሕጻናት የተዘጋጁ ተከታታይ ድህረ-ገፆች በፕሮግራሙ ስምንተኛው ዙር ላይ ቀርበዋል በስምንተኛው ዙር ወቅት ሳምንታዊው “ስታዲየም እኔ የምገኝበት ሥፍራ” የሚል ትርኢት በዓለም ዙሪያ ካሉ ነጻ ወጥ የእግር ኳስ ባለሙያዎች() ጋር በመሆን ተጀምሯል ፡፡ በእያንዳንዱ ትዕይንት ውስጥ ነጻ ወጥ የእግር ኳስ ባለሙያዎች ወጣት አምባሳደሮችን የጨዋታን ብልሃት ያስተማሯቸው ሲሆን በእያንዳንዱ ክፍል መጨረሺያ ተካፋዮቹ የምርጥ ብልሃት ውድድር ላይ እንዲቀርቡ ይነገር ነበር ፡፡ ትርኢቱ በዓለምአቀፍ የመስመር ላይ ማስተር ክላስ ተጠናቅቋል ፣ በዚህም የእግር ኳስ ለወዳጅኝነት ፕሮግራም በተሳተፉት ተሳታፊዎች ቁጥር ለሁለተኛ ጊዜ የጊነስ ዓለም አቀፍ ክብረ ወሰን ባለቤት ሆነ (እ.ኤ.አ. ታህሳስ 6 ቀን 2020) . የመልካም ዜና አርታኢ - የእግር ኳስ ለወዳጅኝነት ፣ ልጆች ከዓለም ዙሪያ የተገኙ አዎንታዊ ዜናዎችን ለተመልካቾች ያካፈሉበት በወጣት ጋዜጠኞች የተጀመረው ሳምንታዊ ትርዒት . የእግር ኳስ ለወዳጅነት አለም ሻምፒዮና አለምአቀፍ የልጆች እግር ኳስ ውድድሩ በእግር ኳስ ለወዳጅነት ፕሮግራሙ መዋቅር ውስጥ ነው የሚካሄደው። በሻምፒዮናው ላይ የሚሳተፉ ቡድኖች – የወዳጅነት ቡድኖች – በግልጽ ዕጣው ስነ-ስርዓት ጊዜ ነው የሚመሠረቱት ። ቡድኖቹ በእግር ኳስ ለወዳጅነት መርሕ መሠረት የተደራጁ ናቸው፤ የተለያዩ አገራት፣ ጾታዎች እና አካላዊ ብቃት አትሌቶች ያላቸው በተመሳሳዩ ቡድን ውስጥ ነው የሚጫወቱት። የአለምአቀፍ ልጆች መድረክ እግር ኳስ ለወዳጅነት በዓመታዊው የአለምአቀፍ ልጆች መድረክ እግር ኳስ ለወዳጅነት ላይ የፕሮጀክቱ ወጣት ተሳታፊዎች ከአዋቂዎች ጋር በመሆን የፕሮግራሙ እሴቶችን በመላው ዓለም ላይ ማስተዋወቅና መገንባት ላይ ተወያይተዋል። በመድረኩ ጊዜ ልጆች ከሌሎች አገሮች ከመጡ አቻዎቻቸው፣ ታዋቂ እግር ኳስ ተጫዋቾች፣ ጋዜጠኛዎች እና ታዋቂ ግለሰቦች ጋር ተገናኝተው ይነጋገራሉ፣ እና በዚህም ለወደፊት ሁለገብ እሴቶችን አቻዎቻቸው ጋር ለማስተዋወቅ በራሳቸው የሚሰሩ አምባሳደሮች ይሆናሉ። አለምአቀፍ የልጆች ፕሬስ ማዕከል አንድ ልዩ የእግር ኳስ ለወዳጅነት ፕሮግራሙ አካል የራሱ የአለምአቀፍ ልጆች ፕሬስ ማዕከል ነው። መጀመሪያ በ2014 ላይ በተካሄደው የእግር ኳስ ለወዳጅነት ፕሮግራም ላይ ነበር የተደራጀው። በፕሬስ ማዕከሉ ውስጥ ያሉ ወጣት ጋዜጠኛዎች የፕሮግራሙን ክስተቶች በየአገሮቻቸው ይሸፍናሉ፦ ለብሔራዊ እና ለአለምአቀፍ የስፖርት ሚዲያ ዜና ያዘጋጃሉ፤ ለእግር ኳስ ለወዳጅነት ቴሌቪዥን ጣቢያ፣ ለአለምአቀፍ የልጆች እግር ኳስ ለወዳጅነት ጋዜጣ እና ለፕሮግራሙ ኦፊሴላዊ የሬዲዮ ጣቢያ ይዘት መፍጠር ላይ ይሳተፋሉ። የአለምአቀፍ ልጆች ፕሬስ ማዕከል የምርጥ ወጣት ጋዜጠኛ ብሔራዊ ውድድሮች አሸናፊዎችን፣ ወጣት ጦማሪያንን፣ ፎቶ አንሺዎችን እና ጸሐፊያንን ያገናኛል። ከፕሬስ ማዕከሉ የመጡ ወጣት ጋዜጠኛዎች ከፕሮግራሙ ውስጥ ሆነው እይታቸውን ያቀርባሉ፣ «ልጆች ስለልጆች» የሚለውን አሰራር በመተግበር። የእግር ኳስ እና የወዳጅነት አለምአቀፍ ቀን በእግር ኳስ ለወዳጅነት ፕሮግራሙ ስር የእግር ኳስ እና ወዳጅነት አለምአቀፍ ቀን ኤፕሪል 25 ላይ ይከበራል። ይህ በዓል 2014 ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ በ16 አገሮች ውስጥ ተከብሯል። በዚህ ቀን ላይ የወዳጅነት ግጥሚያዎች፣ ድንገተኛ ሕዝባዊ ትርዒቶች፣ ክፍት የስልጠና ክፍለ-ጊዜዎች፣ ወዘተ ተካሂደዋል። ከ50,000 በላይ ሰዎች በክብረ-በዓሉ ላይ ተካፍለውበታል። 2015 ላይ የእግር ኳስ እና ወዳጅነት ቀን በ24 አገሮች ውስጥ ተከብሯል። በፌስቲቫሉ ጊዜ የወዳጅነት ግጥሚያዎች እና ሌሎች ክስተቶች ነበሩ። ጀርመን ውስጥ የሻልክ 04 እግር ኳስ ተጫዋቾች ክፍት የስልጠና ክፍለ-ጊዜ አዘጋጅተው ነበር፣ ሰርቢያ የቴሌቪዥን ትርዒት አስተናግዳለች፣ ዩክሬን – በታዳጊ የቮሊን ኤፍሲ ቡድን እና በሉትስክ ከተማ የቤተሰቦች፣ ልጆች እና ወጣቶች ማዕከል የተመዘገቡ ልጆች መካከል ግጥሚያ ነበር። ሩሲያ ውስጥ የእግር ኳስ እና ወዳጅነት ቀን ኤፕሪል 25 ላይ በ11 ከተማዎች ላይ ተከብሯል። የፕሮግራሙን ቁልፍ እሴቶችን ለማስታወስ የወዳጅነት ግጥሚያዎች በቭላዲቮስቶክ፣ ኖቮሲቢርስክ፣ የካተሪንበርግ፣ ክራስኖያርስክ፣ ባርናውል፣ ሴንት ፒተርስበርግ እና ሳራንስክ ላይ ተካሂደው ነበር። በክራስኖያርስክ፣ ሶቺ እና ሮስቶቭ-ኦን-ዶን ውስጥ የወዳጅነት ቅብብል በኦሊምፒክ 2014 ችቦ ያዥዎች ተሳትፎ ተካሂዷል። በሞስኮ ውስጥ የእኩል ዕድል ውድድር በማየት የተሳናቸው ስፖርት ፌዴሬሽን ድጋፍ ተደራጅቷል። ሜይ 5 ላይ የእግር ኳስ እና የወዳጅነት ቀን በኒዝኒ ኖቭጎሮድ እና ካዛን ውስጥ ተከብሯል። 2015 ላይ የእግር ኳስ እና ወዳጅነት ቀን በ32 አገሮች ውስጥ ተከብሯል። ሩሲያ ውስጥ በዘጠኝ ከተማዎች ውስጥ ተከብሯል፦ ሞስኮ፣ ሴንት ፒተርስበርግ፣ ኖቮሲቢርክስ፣ ባርናውል፣ ቢሮቢድዛን፣ ኢርኩትስክ፣ ክራስኖዳር፣ ኖዝኒ ኖቭጎሮድ እና ሮስቶቭ-ኦን-ዶን። ኖዝኒ ኖቭጎሮድ ከቮልጋ ኤፍሲ ለመጡ ወጣት እግር ኳስ ተጫዋቾች የወዳጅነት ግጥሚያ አስተናግዳለች፣ እና የክለቡ አዋቂ ተጫዋቾች ለልጆቹ የማሟቂያ እና ስልጠና ስራዎችን አካሂዷል። በኖቮሲቢርስክ ውስጥ በተደረገ የወዳጅነት ግጥሚያ ላይ አካል ጉዳተኛ የሆኑ ልጆች ተሳትፈውበታል - የኖቮሲቢርስክ ክልል ቡድን የርማክ-ሲቢር። 2017 ላይ የእግር ኳስ እና ወዳጅነት ቀን በ64 አገሮች ውስጥ ተከብሯል። የሰርቢያው ተከላካይ ብራኒስላቭ ኢቫኖቪች እና የኔዘርላንድስ አጥቂው ዲርክ ኩይት ጨምሮ ታዋቂ እግር ኳስ ተጫዋቾች በመላው ዓለም ውስጥ በነበሩ ክስተቶች ላይ ተሳትፈዋል። ግሪክ ውስጥ ከአገሩ ብሔራዊ ቡድን ጋር በመሆን የአውሮፓ እግር ኳስ ሻምፒዮና 2004ን ያሸነፈው ቲዮዶራስ ዛጎራኪስ ክስተቱን ተከታትሏል። ሩሲያ ውስጥ ዜኒት ኤፍሲ የ2017 የእግር ኳስ ለወዳጅነት ፕሮግራም ወጣት አምባሳደር ለሆነው ዛካር ባዲዩክ ልዩ የስልጠና ክፍለ-ጊዜ አዘጋጅቷል። ስልጠና ላይ የዜኒት ኤፍሲ በረኛው ዩሪ ሎዲጊን የዛካር ችሎታን ከፍተኛ ግምት የሰጠው ሲሆን የበረኛ ሚስጥሮችን አጋርቶታል። «የእግር ኳስ ለወዳጅነት» ዘጠኝ እሴቶች ግንቦት 25 ቀን 2013 ዓ.ም. በተካሄደው የጀመሪያው ዓለም አቀፍ የልጆች ጉባኤ ላይ ከዩናይትድ ኪንግደም ከጀርመን ከስሎቬንያ ከሃንጋሪ ከሰርቢያ ከቡልጋሪያ ከግሪክ እና ከሩስያ የተውጣጡ ወጣት አምባሳደሮች የመጀመሪያዎቹን ስምንት እሴቶች አቀነባበሩ። እነሱም - ጓደኝነት፣ እኩልነት፣ ፍትህ፣ ጤና፣ ሰላም፣ ታማኝነት፣ ድል እና መልካም ልማዶች ናቸው። እሴቶቹም በግልጽ ደብዳቤ ይፋ ሆነዋል። ደብዳቤውም ለዓለም አቀፍ «የእግር ኳስ ማህበር (ፊፋ)፣ ለአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር () እና ለዓለም አቀፍ ኦሊምፒክ ኮሚቴ መሪዎች ተልኳል። በመስከረም ወር 2013 ዓ. ም. ዮሴፍ ብላተር ከቭላድሚር ፑቲንና ቪታሊሙትኮ ጋር በተገናኘ ጊዜ ደብዳቤውን እንዳገኘና «የእግር ኳስ ለወዳጅነት»ን ለመደገፍ ዝግጁ መሆኑን ገልጿል። እ.ኤ.አ በ 2015 ዓ.ም. ቻይና፣ ጃፓንና ካዛክስታን ከ «የእግር ኳስ ለወዳጅነት» መርሀ ግብር ጋር በመተባበር ዘጠነኛ እሴት ለመጨመር ወሰኑ። እሱም «ክብር» ነበር። የዘጠኝ እሴቶች ዋንጫ የዘጠኝ እሴቶች ዋንጫ የአለምአቀፍ ልጆች ማህበራዊ ፕሮግራም የእግር ኳስ ለወዳጅነት ሽልማት ነው። በየዓመቱ ዋንጫው ለፕሮጀክቱ እሴቶቹ ከፍተኛ ጽናት ላሳየ ይሸለማል፦ ውዳጅነት፣ እኩልነት፣ ፍትሕ፣ ጤና፣ ሠላም፣ ታማኝነት፣ ድል፣ ባህሎች እና ክብር። በመላው ዓለም ያሉ አድናቂዎች አሸናፊውን መምረጥ ላይ ይሳተፋሉ፣ ነገር ግን የመጨረሻው ውሳኔ የሚሰጠው የእግር ኳስ ለወዳጅነት ፕሮጀክት ተሳታፊዎች ባካሄዱት ምርጫ ነው። የዘጠኝ እሴቶች ዋንጫው የያዙ የእግር ኳስ ክለቦች፦ ባርሴሎና ፣ ባየርን ሙኒክ ፣ አል ዋህዳ (ልዩ ሽልማት)፣ ሪያል ማድሪድ ። የወዳጅነት አምባር ሁሉም የእግር ኳስ ለወዳጅነት ፕሮግራም እንቅስቃሴዎች የእኩልነት እና ጤናማ አኗኗር ምልክት የሆኑ የወዳጅነት አምባሮች በመለዋወጥ የሚጀመር ነው። አምባሩ ሁለት ሰማያዊ እና አረንጓዴ ክሮችን የያዘ ሲሆን የፕሮግራሙን እሴቶች በሚጋራ ማንኛውም ሰው መደረግ ይችላል። እንደ መሠረት ከሆነ «የእንቅስቃሴው ምልክት ባለሁለት ቀለም አምባር ነው፣ ልክ የእግር ኳስ ለወዳጅነት ፕሮግራሙ ውስጣዊ እሴቶች ያህል ቀላል እና መረዳት የሚቻል ነው። የፕሮግራሙ ወጣት ተሳታፊዎች የወዳጅነት አምባሮችን በታዋቂ ስፖርተኛዎች እና ግለሰቦች አንጓ ላይ አስረዋል፣ ከእነሱ ውስጥ እነዚህ ይገኙበታል፦ ዲክ አድቮካት፣ አናቶሊ ቲሞሹክ እና ሉዊስ ኔቱ፣ ፍራንዝ ቤከንባወር ፣ ሉዊስ ፌርናንዴቭ፣ ዲዲየር ድሮግባ፣ ማክስ ሜየር፣ ፋትማ ሳሙራ፣ ሊዮን ጎረካ፣ ዶመኒኮ ክሪሺቶ፣ ሚሸል ሳልጋዶ፣ አለክሳንደር ከርዛኮቭ፣ ዲማስ ፒሮስ፣ ሚዮድራግ ቦዞቪች፣ አደሊና ሶትኒኮቫ፣ ዩሪ ካመነትስ። በክፍለ-ጊዜዎች መካከል የነበረው የተሳታፊዎች እንቅስቃሴ የእግር ኳስ ለወዳጅነት ፕሮግራሙ ወጣት እግር ኳስ ተጫዋቾች ከኦፊሴላዊ ክፍለ-ጊዜው ውጭ በተለያዩ ክስተቶች ላይ ይሳተፋሉ። ሜይ 2013 ላይ የማሪቦር ታዳጊ እግር ኳስ ክለብ (ስሎቬኒያ) ተጫዋቾች ከካምቦዲያ ልጆች ጋር የበጎ-አድራጎት ወዳጅነት ግጥሚያ አድርገው ነበር ። እ.ኤ.አ. ሴፕቴምበር 14፣ 2014 ዓ.ም. ላይ በሶቺ፣ ሩሲያ ውስጥ የሩሲያ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ቭላዲሚር ፑቲን ከፊፋ ፕሬዚዳንት ሴፕ ብላተር ጋር ስብሰባ ባደረጉበት ጊዜ የፕሮግራሙ ሩሲያዊያን ተሳታፊዎች ከቭላዲሚር ፑቲን ጋር ተነጋግረዋል። ጁን 2014 ላይ የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ፍራንሷ ሆላንድ የእግር ኳስ ለወዳጅነት ፕሮግራሙ አባል የሆነውን የታቨርኒ ቡድን በፈረንሳይ እና ናይጄሪያ መካከል የተደረገውን የ2014 ፊፋ አለም ዋንጫ ግጥሚያ እንዲከታተሉ ወደ ኤሊሲ ቤተ-መንግስት ጋብዘዋል። ኤፕሪል 2016 ላይ የ2015 የእግር ኳስ ለወዳጅነት ፕሮግራም አምባሳደር በፕሮጀክቱ ላይ ስለነበራቸው የተሳትፎ ልምድ ለመጋራት ከጠንካራው የቤላሩስ ሰው ከኪሪል ሺምኮ እና ከቤት ኤፍሲ ወጣት እግር ኳስ ተጫዋቾች ጋር ተገናኝቶ ነበር። ዩሪ ቫሽቹክ ተምሳሌታዊው የወዳጅነት አምባር ለኪሪል ሺምኮ ሰጥቷል፣ በዚህም የፕሮጀክቱን ዓላማዎች የማስተዋወቅ ኃላፊነቱን አብሮ ሰጥቷል፦ ወዳጅነት፣ ፍትህ፣ ጤናማ አኗኗር። ሽልማቶችና እና ስጦታዎች የእግር ኳስ ለወዳጅነት ፕሮግራም የተለያዩ ውድድሮችን ያሸነፈ ሲሆን የተወሰኑ የሩሲያ እና አለምአቀፍ ሽልማቶችን የያዘ ነው። ከእነሱ ውስጥ እነዚህ ይገኙበታል፦ በ«የአለምአቀፍ ትብብር ግንባታ» ምድብ ውስጥ «ምርጥ የሩሲያ ማህበራዊ ፕሮጀክቶች»፣ በ«የኮርፖሬት ማህበራዊ ኃላፊነት» ምድብ ውስጥ የአለምአቀፍ የንግድ ተግባቢዎች ማህበር () የወርቅ መቃ ብዕር ሽልማቶች ፣ በ«ምርጥ የፕላኔቱ ማህበራዊ ፕሮጀክት» ምድብ ውስጥ የሳቤር ሽልማቶች ፣ በ«ምርጥ የአለምአቀፍ ስትራቴጂ» ምድብ ውስጥ የድራም ማህበራዊ ወቅታዊ ጉዳይ ሽልማቶች ፣ በ«ምርጥ የሚዲያ ስትራቴጂ» ምድብ ውስጥ የፈጠራ ዲጂታል ገበያ መፍትሔዎች አለምአቀፋዊ ሽልማቶች ፣ «በምርጥ የሩሲያ ማህበራዊ ፕሮጀክት» ምድብ ውስጥ «ብራማ ቀስተኛ» እና የግራንድ ፕሪክሽ «ብራማ ቀስተኛ» ። እግር ኳስ
17764
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8A%A0%E1%8B%99%E1%88%AA%E1%89%B5%20%E1%8C%89%E1%88%8D%E1%89%A0%E1%89%B5
አዙሪት ጉልበት
አዙሪት ጉልበት አንድ ቁስ ቀጥተኛ ሳይሆን የጎበጠ መንገድ ይዞ እንዲንቀሳቀስ የሚያደርግ የጉልበት አይነት ነው። አዙሪት ጉልበት ምንግዜም ለቁሱ ፍጥነት ቀጤነክ () ነው ፤ ማለት አቅጣጫው ወደ ሚጓዝበት መንገድ ቅጽበታዊ የጉብጠት ማዕከል የሚያመላክት ነው ኢሳቅ ኒውተን አማካሊ ጉልበትን ሲተረጉም «አዙሪት ጉልበት ማለት ቁሶች ወደ ማዕክላዊ ነጥብ እንዲያዘነብሉ የሚገደዱበት ወይም የሚሳቡበት ጉልበት ነው» ሲለው የዚህን ጉልበት ሂሳባዊ ቀመር ለመጀመሪያ ጊዜ ያሰላው የኔዘርላንዱ ሳይንስ አጥኝ ክርስቲያን ሃይጅን በ1651ዓ.ም. ነበር። አንድ ቁስ የግዝፈቱ መጠን ቢሆንና በ ጥድፈት፣ የ[ጉብጠት ሬዲየስ| [ጉብጠቱ ሬዲየስ ]] ቢሆን፣ የአዙሪት ጉልበቱ መጠን || እንዲህ ይሰላል፡ እዚህ ላይ አዙሪት ፍጥንጥነት ነው። የጉልበቱ አቅጣጫ ምንጊዜም ቁሱ ወደሚጓዝበት ክብ ማዕከል ነው። ቁሱ በእውነተኛ ክብ የማይጓዝ ከሆነ፣ ቁሱ ያለበተን ቅጽበታዊ ጎባጣ ከሁሉ በላይ የሚወክል ክብ ወይም ኦሱሌቲንግ ክብ ማዕከል፣ ወደዚያ ያመለክታል። ይህ ጉልበት አንድ አንድ ጊዜ ዜዋዊ ፍጥነትን በመጠቀም እንዲህ ይሰላል: የአዙሪት ጉልበት ምንጮች መሬትንና ሌሎች ፈለኮችን በሞላላ ምህዋራቸው እንዲጓዙ የአዙሪት ጉልበት የሚሰጣቸው የፀሐይ ግስበት ነው። አይሳቅ ኒውተን አጠቃላይ የፀሓይ ግስበትን የአዙሪት ጉልበት በማለት ይጠራው ነበር ሆኖም ግን እዚህ ላይ መረዳት ያለብን የአዙሪት ጉልበቱ ፈለኩ ለሚጓዝበት መንገድ ቀጤ ነክ የሆነው ክፍል ብቻ ነው። በገመድ ታስሮ በጠፍጣፋ ቦታ ላይ ለሚሽከረከር ቁስ የአዙሪት ጉልበት የሚሰጠው የገመዱ ውጥረት ነው። በወንጭፍ ድንጋይ ለመወርወር ድንጋዩን በምናሽከረከርበት ጊዜ የአዙሪቱን ጉልበት እጃችን ሲሰጥ፣ በገመዱ ተስተላልፎ ድንጋዩን በክብ ምህዋር ያሾራል። እስካሁን ያየናቸው የአዙሪት ምንጮች "የሚስቡ" ሲሆኑ የ"ሚገፉ" የአዙሪት ምንጮችም አሉ። ለምሳሌ መኪና በክብ መንገድ ሲጓዝ ክቡን ይዞ እንዲዞር የሚገፋው ከመሬትና ከመኪናው ጎማ የሚመነጭ ሰበቃ ፍሪክሽን ነው። የበቆሎ መጥበሻ ምሳሌ ፩. አንድ በቆሎ በበቆሎ መጥበሻ ለመጥበስ ፈለግን እንበል። በቆሎው 250 ግራም ቢመዝን፣ ከሰሉ 40 ግራም ቢመዝን፣ ቆርቆሮው 10 ግራም ቢመዝን። ለዚህ ተግባር ከልጥ የተሰራ ገመድ ቢኖር። ይህ ገመድ 0.5 ሜትር ረዥም ቢሆን እና፣ ገመዱ ላይ 2ኪሎ ወይም ከዚያ በላይ እቃ ሲቀመጥበት እሚበጠስ ቢሆን። የበቆሎው መጥበሻ በሰከንድ 1 ጊዜ ካልዞረ በቂ አየር ስለማይሰጥ በቆሎው በጥሩ ሁኔታ የማይበስል ቢሆን ያለን የልጥ ገመድ ሳይበጠስ በቆሎውን መጥበስ እንችላለን? (የመሬት ስበትን ለጊዜው ይርሱ) ፪ መፍትሄ መጀመሪያ ገመዱን የሚበጥሰውን ጉልበት መጠን እናስላ። 2ኪሎ ገመዱን ስለሚበጥስ፣ የሚያስፈልገው ጉልበት 2ኪሎ*9.8 ሜትር/ሰከንድ ስኩየርድ = 19.6 ኒውተን። ስለዚህ 19.6ና ከዚያ በላይ ኒውተን ገመዱን ይበጥሳል ቀጥሎ በቆሎውን በበቆሎ መጥበሻ አድርገን ስናዞረው የሚፈጠረውን የአዙሪት ጉልበት ማስላት ያስፈልጋል። ይህ ጉልበት ከ19.6 ኒውተን በላይ ከሆነ፣ በቆሎውን በገመዱ መጥበስ አንችልም ምክንያቱንም በጉልበቱ ብዛት ይበጠሳልና። ከላይ እንዳየነው የአዙሪቱ ጉልበት ከራዲየሱ ተገልባጭ ግንኙነት አለው፣ ስለዚህ ረጅሙን የገመድ ርዝመት ብንመርጥ ፦ ፤ በሰከንድ አንድ ጊዜ ለመዞር፣ 2*ፓይ* መጓዝ ግድ ይላል፣ ይህም 2*3.14*1 ማለት ነው = 6.28 ሜትር በሰከንድ። ከላይ የክርስቲያን ሃይጅንስን ቀመር በመጠቀም፣ በቆሎውን ለማብሰል አስፈላጊና አንስተኛ ጉልበት እንዲህ እናሰላለን ፡ : እዚህ ላይ አጠቃላይ ግዝፈት ይወክላል። (የገመዱን ኢምንት ግዝፈት ለጊዜው ችላ እንበልና)፦ =250 ግራም (በቆሎ) + 40ግራም (ከሰል) + 10ግራም (ቆርቆሮ) = 300 ግራም = .3 ኪሎ ግራም። ጥድፊያ = 6.28 ሜትር/ሰኮንድ ። ትልቁ ሬድየስ = 0.5ሜትር፤ ኒውተን። እዚህ ላይ ማስተዋል ያለብን ይህ ጉልበት በቆሎውን ለመጥበስ ከሚያስፈልጉን ጉልበቶች ሁሉ በጣም አነስተኛው ነው። ሆኖም 23.66ኒውተን ከ19.6 ኒውተን ስለሚበልጥ በቆሎውን ለመጥበስ ብንሞክር ገመዱ ስለሚበጠስ፣ በቆሎውን መጥበስ አንችልም። ገመዱን በማስረዘም በቆሎውን መጥበስ ይቻላል (ለምን? -- እራስዎት ይመልሱት) የተለያዩ ትንታኔወች ከዚህ በታች 3 አይነት የፍጥነት እና ፍጥንጥነት ቀመሮች አመጣጥን እናያለን። ቋሚ ክባዊ እንቅስቃሴ ቋሚ ክባዊ እንቅስቃሴ ስንል በአንድ ቋሚ መጠን መሽከርከርን ያመለክታል። ለዚህ አይነት እንቅስቃሴ የፍጥነት ቀመር በሁለት አይነት መንገድ ይሰላል፦ የጂዖሜትሪ ስሌት ከጎን የሚታየው ስዕል ላይ በግራ በኩል ያለው ክብ እንደሚያመላክተው፣ አንድ ቁስ በቋሚ ጥድፈት ሲጓዝ ሁለት ቦታ ላይ ይታአያል። አቀማመጡ በ ቬክተር ሲቀመጥ ፍጥነቱ ደግሞ በ ቬክተር ተወክሏል። የፍጥነቱ ቬክተር ለአቀማመጡ ቬክተር ምንጊዜም ቀጤነክ (ፐርፐንድኩላር) ነው። ለዚህ ምክንያቱ የፍጥነቱ ቬክተር ምንግዜም ለእንቅስቃሴው ክብ ታካኪ ስለሆነ ነው። ስለሆነም በክብ ስለሚጓዝ ም እንዲሁ በክብ ይጓዛል። የፍጥነቱ በክብ መጓዝ ከጎን በሚታየው ስዕል ላይ በቀኙ ክብ ይታያል። ፍጥንጥነቱ ም እንዲሁ በዚሁ ክብ ተቀምጧል። ፍጥነት የአቀማመጥ ቬክተር ለውጥ መጠን ሲሆን ፍጥንጥነት የፍጥነት ለውጥ መጠን ነው። የአቀማመጥና የፍጥነት ቬክተሮቹ አንድ ላይ ስለሚጓዙ፣ የየራሳቸውን ክብ በአንድ አይነት ጊዜ ይጓዛሉ። ይህ ጊዜ የተጓዙት ርቀት ለፍጥነታቸው ሲካፍል፣ እንዲህ ይሰላል በተመሳሳይ ሁኔታ, እኒህን እኩልዮሽ አንድ ላይ በማስቀመጥ ፍጥንጥነታቸውን ||, ስናሰላ እንዲህ እናገኛለን የዜዋዊ ሽክርክሪት መጠን በራዲይን በሰከን ሲሰላ እንዲህ ነው፡ ከጎን ያሉትን ሁለት ክቦች ስናወዳድር፣ ፍጥንጥነቱ ወደ ክብ መሃከል እንደሚያመላክት እናያለን። ለምሳሌ በግራው ክብ የአቀማመጥ ቬክተሩ ወደ 12 ሰዓት ሲያመልክት ፍጥነቱ ወደ 9 ሰዓት ያመለክታ፣ ይህ ማለት በቀኝ ካለው ክብ እንደምናየው ተመጣጣኙ ፍጥንጥነት , ወደ 6 ሰዓት ያመለክታል። ማለት የፍጥንጥነቱ ቬክተር ለአቀማመጡ ቬክተር ተቃራኒና ወደ ክቡ ማዕክል ያመላክታል። የቬክተር ስሌት ስዕል 3 ላይ እንደሚታየው የቁሱ መሽከርከር በቬክተር የሚወቀል ነው። ይህ ቬክተር ለመሽከርከሪያው ጠለል ጠለልነክ ሲሆን፣ ወደ የት እንደሚያመላክት በ ቀኝ-እጅ ቀመር ይሰላል። የዚህ የመሽከርከር ቬክተር መጠን እንዲህ ይሰላል , እዚህ ላይ በጊዜ ላይ ቁሱ ያለውን የ ዘዌያዊ አቀማመጥ ይወክላል። እዚህ ላይ ምን ጊዜም የማይለወጥ ቋሚ እንደሆነ ይታሰባል። በዚህ ወቅት የተጓዘው ርቀት በ ቅጽበት እንዲህ ይሰላል በቬክተር መስቀለኛ ብዜት፣ የዚህ ብዜት መጠን ሲሆን አቅጣጫው ለክቡ ምህዋር ታካኪ ነው። በሌላ አጻጻፍ፣ ይህን ውጤት የጊዜ ለውጡን ስናሰላ የላጋራንግ ቀመር እንዲህ ይላል: የላጋራንግን ቀመር ከላይ ላገኘነው ብዜት ስንጠቀም = 0 መሆኑን ባለመርሳት), በሌላ አባባል፣ ፍጥንጥነቱ ምንጊዜም ለራዲያል አቀመማመጡ ተቃራኒ ሲሆን፣ መጠኑም: እኒህ ቋሚ |...| መስመሮች መጠንን የሚያመላክቱ ሲሆኑ፣ ለ ) ስንጠቀም እዚህ ላይ የሚያመላክተው የክቡን ሬድየስ ነው። ማስተዋል እንደምንችለው ን በዜዋዊ ፍጥነቱ ከተካነው ከላይ በ ጂኦሜትሪ ካገኘውነው ውጤት ጋር ምንም ልዩነት የለውም : ሌሎች ተጨማሪ ንባቦች
README.md exists but content is empty.
Downloads last month
860